ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15...

40
ቁም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም 1

Transcript of ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15...

Page 1: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

1

Page 2: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

2

የሚቀጥለው ዕትምቁም ነገር መፅሔት ቁጥር 138 ጥቅምት

24 ቀን 2005 ዓ.ም ይጠብቋት!

ቴዲ አፍሮ የድሮ ት/ቤቱን ጎበኘ

የ1.3 ሚሊዮን ቤት የለንደን ኦሎምፒክ ተሸላሚ

ወንጀልና ወንጀለኞች

በልሃ ልበልሃ

ጥበብ ገበታ

18

22

24

28

40

16

8

‹‹ዓመት የማይጠበቅ ስራ ቢሰራስ?››ውድ የመፅሔቷ አዘጋጆች ሠላማችሁ የበዛ እንዲሆን በመመኘት

ደብዳቤ ፅፌላችኃለሁ፡፡ በህይወት ዘመኑ በበርካታ ጉዳዮች ላይ በመረዋና በማይሰለች ድምፁ አዚሞ አልፏል፡፡ ከዕልፈቱ በኋላም ስራዎቹ አይጠገቤና የማይሰለች ሆነው እያደመጥናቸው፤ እየተዝናናንባቸው፤ እየተማርንባቸው ነው፡፡ ለመሆኑ ይህ ድምፃዊ በጥበቡ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች ከማንም በበለጠ ሁኔታ በክብር ተሸኝቷል፡፡ ከሽኝቱ በኋላም ለመታሰቢያነቱ ሀውልት መቆሙን አብዛኞቻችን እናውቃለን፡፡ ነገርግን በመፅሔታችሁ ላይ የሀውልቱ ዙሪያ በቆሻሻ መከበቡን ሳነብ እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ የጥላሁን በርካታ አድናቂዎች እንዲሁም በስሙ የሚንቀሳቀሱ የአድናቂዎቹ ስብስብ እንደነበረ በወፍ በረር አውቃለሁ፡፡ ለምን እነዚህ ሰዎች የልደት በዓሉንና ህልፈት የሀውልት ቀኑን የማይጠብቅ ጠቃሚ ሥራ አይሰሩም፡፡ ለምሳሌ ሀውልቱን በፅዳት በመያዝና ተጨማሪ አስፈላጊ ነገሮች በዙሪያው መፈፀም የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ሰለሞን ጥበቡ (ከፈረንሳይ)

‹‹መልካም ራዕይ ይታያቸው››አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን በተመለከተ

ራዕያቸው ምንይሆን ብላችኋል፡፡ በእርግጥ በፅሁፍ ላይ የቀረበው ሀሳብ ጠንካራ፣የተዳሰሰውና የተጠቆመው ነገር ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በተሸሙበት ሥልጣን ህዝብና ሀገርን የሚጠቅሙ እንጂ የሚጠቀሙበት እንዳይሆኑ ፈጣሪ ይርዳቸው እላለሁ፡፡ ዘመኑ መልካም ራዕይ የሚያዩበት ፣መልካም ተግባር የሚፈፅሙበት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

ዘላለም አምተነህ (ከአ.አ)

‹‹ኮሎኔሉ ጥሩ ተናግረዋል›› የቀድሞው መንግስት ም/ፕሬዝዳንት ኮ/ል ደበላ ዲንሳ እንግዳችሁ

ነበሩ፡፡ ዘርዘርና ሰፋ ባለው ቃለ ምልልሳቸው ሰውየው ጥሩ ነገር ተናግዋል፡፡የእነሱ የስልጣን ዘመን ምን ይመስል እንደነበር የተናገሩት እንደራሴ ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ሌላው ደግሞ በእስር ዘመናቸው ምን አገባኝ ሳይሉ በበጎ ፈቃደኝነት ሥራ ተሰማርተው የፈፀሙት ተግባር ስማቸውን በመልካም እንዲነሳ የሚያደርግ ነው፡፡ ውድ የመፅሔቷ አዘጋጆች እንደዚሀ አይነት ሰዎችን እየፈለጋችሀሁ ማነጋገሩን ብትገፉበት ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም የትና ምን እየሰሩ እንደሆነ ማሳወቃችሁ የሙያ ግዴታችሁን እንደመወጣት ነውና፡፡

ሰላም አረፈአይኔ (ከሞጆ)

‹‹እንኳን ደስ ያላችሁ›› ቴዲ አፍሮ ተሞሸረ ተባለ፡፡ እናንተም በነበራችሁበት ቦታ ስለሆነው

መፃፋችሁ ነው፡፡ይህንን ደብዳቤ ለመፃፍ ያነሳሳኝ፡፡ የቴዲ ሠርግ እንደእኔ በርካታ ያልታሰቡ ገጠመኞች የሚታዩበት ይሆናል ብዬ ገምቼ ነበር፡፡ ግምቴ ትክክል ባይሆንም በደማቅ ሁኔታ የሠርጉ ዕለት በማለፉ በዚህ አጋጣሚ ከነባለቤቱ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ሀና አሰፋ (ከአ.አ)

Page 3: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

3

ለቁም ነገር እንሰራለን!በቁም ነገር ሚዲያና ኢንተርቴመንት

ኃ/የተ/የግ/ማ ሥር እየታተመ በየ15 ቀኑ የሚወጣ በኪነ ጥበብና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር

መፅሔት በ1994 ዓ.ም ተመሰረተ11ኛ ዓመት ቁጥር 137

ዋና አዘጋጅ፡- ታምራት ኃይሉ የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 13/14 የቤ.ቁ212/ 0911-232015ሪፖርተር፡- ብርክት ወንድሙአምደኞች፡- ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር ኃይለ ጊዮርጊስ ማሞ/ጴላጦስ ዘላለም ጌታቸው (ከሀዋሳ) ፀጋ ጊዮርጊስግራፊክስ ዲዛይነር፡- መሠረት ክበበውኮምፒውተር ፅሁፍ፡- ሰብለ ይታገሱ ሴልስ፡- ደረጀ ግርማ 0911-147100ሽያጭና ስርጭት፡- ሰለሞን ንጉሴ /0913-887175/ሕትመት ክትትል፡- በዛብህ ተክሉ /0911-416800/የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 17/18 የቤ.ቁ 401 ካሳንቺስ ከግብርና ሚኒስቴር ወረድ ብሎ ምናለ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ስልክ፡- 011-5-507410 ፋክስ፡- 011-5-507410 ፖስታ፡- 25099/1000 አ.አ ኢሜይል፡[email protected]አታሚ አፍሮ ማተሚያ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ቀበሌ 05 የቤ.ቁ......... ስልክ፡- 011-4-197447

ያለፈው ወር ዕትም ቁጥር 135 ቁጥር 134

‹‹መቼ ነው ዛሬ ነውነገ ነው ኢትዮጵያን የማየው››

ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ

በተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ተዘርፈው የተወሰዱ ቅርሶቻችንን ለማስመለስ እንደ ሀገርና እንደ ህዝብ ብዙ ጥረናል፡፡ አንዳንዶቹን በእጃችን ለማስገባት ስንችል ሌሎቹ አሁንም ድረስ የባዕዳን ሀገራት ሙዚየሞችን አድምቀው ለቱሪስቶች የገቢ ምንጭ መሆናቸው ያበሳጫሉና፡፡

ግን ውጪ ሀገር ስላሉ ቅርሶቻችን ስንጨነቅ በእጃችን ስላሉት ብዙ አናስብም፤ ለምን?

በልዩ ልዩ ምክንያት ከሀገር ተሰደው ‹‹ዲያስፖራ›› የሚል የማዕረግ ስም ይዘው ስለሚመጡ ወገኖቻችን እንደ ህዝብና እንደ መንግስት አብዝተን እየተጨነቅን ከሀገር የመውጣት ፍላጎት ሳይኖራቸው ሀገራቸውንና ወገኖቻቸውን በቅንነት ስለሚያገለግሉ ዜጎች ብዙም ማሰብ አንፈልግም፤ ለምን?

ከፍተኛ ብድርና እርዳታን ተንተርሰው የሚታቀዱ ትላልቅና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለማስጠናት በተቋም ደረጃ ለሀገር በቀል ድርጅቶች ዕድል ከመስጠት ይልቅ ከውጪ ሀገር አማካሪ ድርጅቶች ጋር መፈራረም ይቀለናል፤ ለምን?

በሀገራችን ደራሲያንና በሀገራችን ቋንቋ ከተዘጋጁ መፃህፍትና የጥበብ ውጤቶች ይልቅ ‹‹በአሜሪካ የታተመ›› ወይም ‹‹በአሜሪካዊ ደራሲ የተፃፈ›› የሚሉ ቅጥያዎች ያሏቸውን የኪነ ጥበብ ውጤቶች እንመርጣለን፤ ለምን?

ወደ ስፖርቱ ስንመጣም ከሀገራችን ስፖርተኞች ይልቅ በተለይ በእግር ኳሱ የአውሮፓ ተጫዋቾችን በይበልጥ እናውቃለን፣ ስለ እነርሱም እንጨነቃለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የስፖርቱ አመራር ለሀገር ውስጥ ሙያተኞች ክብር ከመስጠት ይልቅ አሰልጣኞችን ብቻ ሳይሆን የቴክኒክ ሙያተኞችን በብዙ ሺህ ዶላር ክፍያ በውጪ ሀገር በማስመጣት ለውጥ ለማስገኘት ሲጥር ይታያል፡፡

ሰሞኑን ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዚህ ድል ያበቁት ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች መሆናቸውን ማስታወስ ያስፈልጋል፤ ከዚህ በፊት ግን ለሀገር ውስጥ ሙያተኞች ዝቅ ያለ ግምት ከመስጠት ባለፈ በተጋነነ የደሞዝ ክፍያ የውጭ ሀገር አሰልጣኞችንና የአፍሪካ ተጫዋቾችን ማስመጣታችን ማፈራረቃችን ይታወሳል፤

በማንኛውም መስክ የውጭ ሰዎችን አለአግባብ ማምለክ ትተን ለዜጎቻችንና ለሙያተኞቻችን ተገቢውን ክብር መስጠት የምንጀመረው መቼ ይሆን?

Page 4: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

4

‹‹100 ደቂቃለአፍሪካ ዋንጫ

(ከታምራት ኃይሉ)

ጥቅምት 2 በዋቢ ሸበሌ ሆቴልመቅደላ ፕሮሞሽን ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ አፍሪካ ዋንጫ

ለማለፍ ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቀው ለነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አንድ ለየት ያለ የመዝናኛ ፕሮግራም በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ ወንድ ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ የሴት ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾችም ተገኝተዋል- ከአነ አሰልጣኞቻቸው፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ በድል እንዲወጣና ቡድናችን ጨዋታውን እንዲያሸንፍ በማሰብ ልዩ የኮሜዲያንና የአዝማሪ ጨዋታ ተዘጋጅቷል›› የሚለው የመቅደላ ፕሮሞሽን ዝግጅትን የሰሙ ሁሉ በዋናው መግቢያ በር ላይ ‹‹በትገባለህ አትገባም›› ትግል ላይ ነበሩ፡፡ አዳራሹ ከሚችለው በላይ በእግር ኳስ አፍቃሪያን በተጨናነቀበት ሰዓት ነው የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የገቡት፡፡ ተጫዋቾቹ ሲገቡም ‹ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ› የተሰኘው የዝነኛው ድምፃዊ ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ዘፈን ነበር አዳራሹን ያደመቀው፡፡

የመቅደላ ፕሮሞሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ልጅ ቴዎድሮስ ባጫ ስለ

ፕሮግራሙ አጠር ያለ የመግቢያ ንግግር ያደረገ ሲሆን 48 ሰዓታት ቀርቶት የነበረውን ወሳኝ ፍልሚያ ከአድዋ ጦርነት ጋር በማመሳሰል ነበር መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፉን እንዲሰጥ የጠየቀው፡፡

የምሽቱ ፕሮግራም ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም የ80 ሚሊዮን ህዝብን አደራ ተቀብለው ለተዋደቁት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች እጅግ አስፈላጊ እንደነበር መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ከጨዋታው በፊት በነበሩት ሳምንታትና ቀናት የሱዳኑ ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን ውድድሩ እግር ኳስ መሆኑን በመዘንጋት የሚሰጡ አስተያየቶች በየሚዲያው ላይ በርክተው ነበር፡፡ በእግር ኳስ ጨዋታ መሸነፍም ሆነ ማሸነፍ የማይቀሩ ክስተቶች መሆናቸውን ያልተረዱ ወይም ለመረዳት የማይፈልጉ ጋዜጠኞችና አስተያየት ሰጪዎች ማንም ልብ ባላለው መልኩ ከባድ ጫና ውስጥ ተጫዋቾቹን ከተዋቸው ነበር፡፡

ይህ ከእግር ኳስ ጨዋታ ህግ ውጪ ለተጫዋቾች የተሰጠው የተሳሳተ ግምት ‹‹ብንሸነፍ ምን ይውጠናል?›› እንዲሉ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ ለዚህም ነው ዋና አሰልጣኙ አቶ ሰውነት ቢሻው ባለፈው ማክሰኞ የኤድና ሞል ባለቤት አቶ ተክለብርሃን አምባዬ ለብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የ25

Page 5: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

5

‘‘

ሺህ ብር ሽልማት በሰጡበት መድረክ ላይ ወጥተው ስለ ድሉ ሲናገሩ ‹‹ማሸነፋችን በጣም ጥሩ ነው፤ ግን ተሸንፈን ቢሆንስ? ትልቅ ጭንቀትና ስጋት ነበረብን›› ያሉት፡፡ ደግነቱ መቅደላ ፕሮሞሽንና ቴዎድሮስ ባጫ በፌዴሬሽኑ አስቀድሞ ታስቦበት መዘጋጀት የነበረበትን ዝግጅት ተጫዋቾቹ ከልምምድ በኋላ እንደማንኛውም ስፖርተኛ ዘና ብለው መንፈሳቸውን የሚያድሱበት ዝግጅት አዘጋጅቶ ስለነበር በተለያዩ መድረኮች የምናውቃቸው ወጣት ኮሜዲያን የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆን በአዳራሹ የተገኙ ታዳሚያንን በሳቅ ሲያፈርሱ አምሽተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፉት በቀዳሚነት በተጫዋቾቹ ጥንካሬና በደጋፊው ሞራል ነው ካልን የአርብ ምሽቱ የመዝናኛ ፕሮግራም በቀጣይነት የሚጠቀስ ስንቅ እንደሆነ መመስከር እንፈልጋለን፡፡ የእግር ኳስ ባለሙያ ቀርቶ ኳስ አይቶ የማያውቅ ሁሉ በየኤፍ ኤሙ ሬዲዮ ጣቢያ እየደወለ ስለማሸነፍና ስለ ድል ብቻ በማውራት ውጥረት ውስጥ ገብተው የነበሩት ተጫዋቾች በምሽቱ በኮሜዲያን ቀልዶች፣ የአዝማሪ ሙዚቃ መንፈሳቸው ታድሶ ሲስቁ ታይተዋል፡፡

በነገራችን ላይ በዋቢ ሸበሌው መድረክ ላይ በቴዎድሮስ ባጫ ግጥም ተፅፎ በዘላለም ካሳዬ የተዜመውና በመኮንን ለማ የተቀናበረው የድል ዜማን አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ መርቆታል፡፡

የስታዲየም ውሎእሁድ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ለሚካሄደው ጨዋታ

ቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ነበር በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ግርግር መታየት የጀመረው፡፡ የጥቅምት ብርድ አጥንትን ሰርስሮ የሚገባ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የስፖርት አፍቃሪው ግን ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ ጋዜጣ በማንደድ የሌሊቱን ብርድ ለመቋቋም ሰልፍ ይዞ ታይቷል፡፡ ከንጋቱ 11 ሰዓትና 12 ሰዓት ላይ ማንም አይቀድመኝም ብለው ወደ ስታዲየም ለደረሱ ብዙ ሰዎች የወረፋው ርዝመት ከ500 ሜትር በላይ ነበር፡፡

ከረፋዱ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚተመው ህዝብ ብዛት የተነሳ የትራፊክ መጨናነቅ በመፈጠሩ ዋና ዋና መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኑ፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ማምሻውን ከክልል የመጡ የስፖርት አፍቃሪያንም በየበሮቹ ዙሪያ ሰልፍ ላይ ታይተዋል፡፡ በሁሉም የስፖርት ታዳሚያን ዘንድ ግን አንድ ተመሳሳይ ነገር ይስተዋላል፡፡ ሁሉም የማሸነፍ ጉጉት ይነበብባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ባንዲራ የያዙም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡

የጨዋታው መጀመሪያ ሰዓት ደርሶ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ከመግባታቸው በፊት የሰሞኑን ድል ያደመቁ ሁለት ዘፈኖች ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ በስታዲየሙ የሚደመጡት አንዱ የጃሉድ ‹‹የርግብ አሞራ›› የሚለው ሲሆን ሌላው የቴዎድሮስ ባጫ ድርሰት የሆነው ለወንዶቹና ለሴቶቹ ብሔራዊ ቡድኖች የተዜመው አዲስ ነጠላ ዜማ ነበር፡፡

የሀዋሳውን የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ያዘጋጀው ቤሌማ ኢንተርቴይመንት ዲጄ ዊሽንና ዲጄ መሳይን ይዞ የስታዲየሙን ተመልካች አስጨፍረዋል፡፡ እዛም እዚህም የብሔራዊ ቡድኑን አስጨፋሪዎች አቼኖንና አዳነን ተከትለው ልዩ ትርኢት የሚያሳዩት የስታዲየሙ ተመልካቾች በእርግጥም የብሔራዊ ቡድኑን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ተመልሶ የማየት ጉጉት የሚያሳዩ ነበሩ፡፡

ጨዋታው ለብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆን ለተመልካቹና ለስፖርት አመራሮችም ከባድ

ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ ክብደቱ ደግሞ የሚመዝነው በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ቡድናችንን ሱዳን ላይ ያሸነፈው በጨዋታ ብልጫ ብቻ አለመሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ይጀምራል፡፡ ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት በጎደለው በዚያ ጨዋታ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን 5ለ3 ያሸነፈው ተጨዋቾቻችን በተፅዕኖ ስር እንዲወድቁ ከተደረገ በኋላ ነው የሚለው ሁኔታ የሱዳኖችን የአዲስ አበባ ቆይታ ከባድ አድርጎታል፡፡

ውድድሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ አንዳችም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር አጥብቆ ሲጠይቅ የከረመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹ብሔራዊ ቡድናችን በሱዳን የተፈፀመውን አይነት ችግር ፈጥረን ብናሸንፍ እንኳን ካፍ ውጤቱን ሊሰርዘው ይችላል›› በማለት ተማፅኖ ሲያሰማ ቆይቷል፡፡ ተማፅኖው በእሁዱ ጨዋታ አልሰራም ለማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ተመልካቹን ወደ በቀል ከመሄዱ በፊት ውጤቱ በጨዋታ ብልጫ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጥቷል፡፡

ከእረፍት በፊት የነበረው ጨዋታ ብዙ አስጨናቂ ብቻ ሳይሆን የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች

ወደ ቡድናችን በሮች በተደጋጋሚ የተጠጉበት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድናች ተጨዋቾች ላይ የታየው ያልተለመደ የመናበብ ችግር አስቀድሞ ለተጫዋቾቹ የተሰጠው ግምት ተፅዕኖ ውስጥ እንደከተታቸው የሚያመላክት ነበር፡፡

በእረፍት ሰዓት ግን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውና ተጫዋቾቹ ለደቂቃዎች መመካከራቸውን የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ደጉ ደበበ ይናገራል ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ ማጥቃት ብቻ ነው፤ ጫና ፈጥረን መጫወት አለብን›› ተባባልን ይላል፤ እንደተባባሉትም ከእረፍት መልስ በ63ኛው ደቂቃ ጌታነህ ከበደ ከግራ መስመር ወደ መሀል ያሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ በጭንቅላቱ በመግጨት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጠረ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጎል ማሽን ሳላዲን ሰይድ ሁለተኛዋንና ኢትዮጵያን ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የሚመልሳትን ግብ አስቆጠረ፡፡

በሁለተኛው ግብ መላ የስታዲየሙ ታዳሚ በየቤቱ ጨዋታውን የሚከታተለው ተመልካች ደስታውን እያጣጣመ ባለበት ሰዓት አንድ አስጨናቂ ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኩል ተከሰተ፡

፡ ከቀኝ ክንፍ ወደ ኢትዮጵያ ቡድን የግብ ክልል የተሻገረው ኳስ ከሱዳን አጥቂ ለመከላከል አብሮ የሮጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው አንገቱ ተቀጭቶ ወደቀ፡፡ ሰዓቱ ወደ 86ኛው ደቂቃ እየተጠጋ ስለነበር ጀማል ደቂቃዎች በመግደል ድሉን አስጠብቆ ለመውጣት ያደረገው ስልት የመሰላቸው ብዙዎቹ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ጀማል ከወደቀበት ሊንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ ዳኛው ወጌሻ ገብቶ እርዳታ እንዲደረግለት ቢፈቅዱም ጀማል ራሱን ስቶ ስለነበር ሊነቃ አልቻለም፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኩል የተከሰተው የበረኛው መጎዳት ብቻ አይደለም፤ በረኛው እንዳይቀየር አስቀድሞ 3 ተጫዋቾች ተቀይረው ስለነበር ሌላ ተጫዋች ማስገባት አልተቻለም፡፡ በመሆኑም ከተጫዋቹ መሀከል አንዱ የበረኛውን ጓንት አድርጎ ወደ ግብጠባቂነት መቀየር

ከረፋዱ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚተመው

ህዝብ ብዛት የተነሳ የትራፊክ መጨናነቅ በመፍጠሩ ዋና ዋና መንገዶች ለተሽከርካሪ

ዝግ ሆኑ፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ማምሻውን ከክልል

የመጡ የስፖርት አፍቃሪያንም በየበሮቹ ዙሪያ ሰልፍ ላይ

ታይተዋል፡፡

Page 6: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

6ወደ ገፅ 32 ዞሯል

ነበረበት፡፡ አዲስ ህንፃ ይህንን ሀላፊነት ወስዶ ጨዋታው ተጀመረ፡፡ አዲስ ጓንት አድርጎ ጨዋታው ሲጀመር ሰዓቱ 90 ደቂቃ ላይ ያመለክት ነበር፡፡ የባከነ 10 ደቂቃ የጨመሩት ዳኛው እነዚያ የመጨረሻ 10 ደቂቃዎች ለሁሉም የስታዲየሙ ታዳሚያንና ለተጫዋቾቹ አስጨናቂ ሆነው ነው የተጠናቀቁት፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ

ኢትዮጵያ ከሶስቱ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን መስራቾች አንዷ ናት፡፡ ሌሎቹ ሀገሮች ግብፅና ሱዳን ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በ1949 ዓ.ም ሲሆን አዘጋጅዋ ሱዳን ነበረች፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ ለዋንጫ ያለፉ ቢሆንም በግብፅ ተረትታ ሁለተኛ ሆና ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው፡፡

በሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሶስተኛ ስትወጣ አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ይህም ድል ዘንድሮ 50 ዓመቱን ደፍኗል፡፡ ለአራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አራተኛ የወጣችው ሀገራችን በአምስተኛው በመጀመሪያ ዙር ላይ ተሰናብታለች፡፡ ድጋሚ በስድስተኛው አራተኛ ስትወጣ በሰባተኛው በመጀመሪያው ዙር ተሰናብታለች፡፡

በስምንተኛውና በዘጠነኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ ማጣሪያውን ለማለፍ ባለመቻሏ ሳትካፈል ቀርታለች፡፡ 10ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለሶስተኛ ጊዜ የማዘጋጀት ዕድል ያገኘችው ኢትዮጵያ በአዘጋጅነትዋ ተሳታፊ የመሆን ዕድል ቢገጥማትም በመጀመሪያው ዙር ተሰናብታ ሞሮኮ የዋንጫው ባለቤት ስትሆን የበይ ተመልካች ሆናለች፡፡ 11ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በጋና ሲዘጋጅና 12ኛው በናይጀሪያ ሲካሄድ ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ በነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ለመሳተፍ አልቻለችም፡፡ በነዚህ ውድድሮች አዘጋጆቹ ሀገሮች ጋናና ናይጀሪያ ናቸው ዋንጫውን የወሰዱት፡፡

ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተካፈለችበት በ1974 ዓ.ም በ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን አዘጋጅዋ ሊቢያ ነበረች፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ተካፋይ የነበሩት ሀገሮች አዘጋጅዋ ሊቢያ ጋና ካሜሩን ቱኒዚያ በምድብ አንድ ሲደለደሉ ኢትዮጵያ፣ ዛምቢያ፣ አልጀሪያና ያለፈው ዋንጫ ባለቤት ናይጀሪያ ነበሩ፤ ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር በሶስቱም ሀገራት ተሸንፋ የምድቡ መጨረሻ ሆና ነበር ያጠናቀቀችው፡፡

ይህ ከሆነ 31 ዓመት ሆነ፡፡ በዚህ መሀል ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምታደርጋቸውን የማጣሪያ ውድድሮችን በአሸናፊነት ለመወጣት ባለመቻሏ በመሰረተችው መድረክ ላይ መገኘት አልቻለችም፡፡ የሀገር ውስጥ ውድድሮችም እየተጠናከሩ ከመምጣት ይልቅ ተደጋጋሚ ውዝግቦች እየተበራከቱ በመምጣታቸው በአፍሪካ ሆነ በዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከማጣሪያ አልፎ ቅድመ ማጣሪያ ውስጥ ከሚመደቡ ደካማ ሀገራት መሀከል ተቆጥራለች፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ ላይ ማጣሪያውን አልፋ ለውድድር አትብቃ እንጂ በዞኗ በሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ላይ በተደጋጋሚ በመሳተፍ አራት ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች፡፡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ማለትም በ1996 እና 1997 ላይ የሴካፋ ዋንጫን ኢትዮጵያ እንድታነሳ ያስቻሏት የአሁኑ አስልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጣ ውረድ

ፀሀይና ዝናብ ብቻ ሳይሆን የሌሊት ብርድ ሳይቀር እየቻለ በስታዲየም እየተገኘ ድጋፍ የሚሰጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠር የስፖርት አፍቃሪ ያለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ በብዙ ውጣ ውረዶችና ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ያለ ስፖርት ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ መስራች በነበርንበት በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ ላይ ለ31 ዓመታት ያህል ዳግም ልንታይ ላለመቻላችን ብዙ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህ 31 ዓመታት ውስጥ ከፌዴሬሽን የአመራር አባላት ውዝግብና ክስ አንስቶ፣ እስከ ፊፋ የእገዳ እርምጃ ድረስ አስተናግዷል እግር ኳሳችን፡፡

ከአፍሪካ ዋንጫ ርቀን በተደጋጋሚ አሸናፊ ወደ ሆንንበት ወደ ምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ እንዳናተኩር የእሱም ውጤት እየከዳን ሄዷል፡፡ በ1997 ዓ.ም ለአራተኛ ጊዜ ዋንጫ ማንሳት የቻለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያሰለጥኑ የነበሩት የአሁኑ አስልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው ድሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ እየተሻሻለ ስለመሄዱ ማሳያ ተደርጎ ሊነገር የሚገባው እንዳልሆነ መስበክ በፈለጉ የስፖርቱ ሙያተኞችና ሚዲያዎች የማጥላላት ዘመቻ ተከፍቶባቸው ነበር፡፡ በያዙትና በሚያምኑት ነገር ላይ የመፅናት ባህሪ ያላቸው አቶ ሰውነት ‹‹ሴካፋ የደካማ ሀገሮች ውድድር ነው የሚሉ ራሳቸው ደካሞች ናቸው፡፡›› ብለው ለቁም ነገር መፅሄት መናገራቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ሰውነት ሰሞኑን ከአፍሪካ ዋንጫ ድል ጋር በተያያዘ ያንን ጊዜ ሲያስታውሱ ‹‹በሴካፋ ላይ ተወዳድሮ ዋንጫ መወሰድ ጥቅም የለውም ሲሉ የነበሩ ሰዎች ከጥቂት ዓመታት በኋላ በሴካፋ ላይ ተጫውተን ዙሩን እንኳን ማለፍ አቅቶን ስንባረር ነው ያንን ትችታቸውን ያቆሙት›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ በተደጋጋሚ የመሸነፍ ዕጣ ፈንታ የገጠመው ቢሆንም በመንግስት አልባዋ በሶማሌ ብሔራዊ ቡድን የዛሬ 9 ዓመት እንደተሸነፈበት ጊዜ ያህል የስፖርት አፍቃሪው መራራ ፅዋ የተጎነጨበት ጊዜ ነበር ለማለት ያስቸግራል፡፡ ይህ ነው የሚባል የስፖርት ፌዴሬሽን ቀርቶ ይህ ነው የሚባል መንግስት ከሌላት በሱማሌ የገጠር መንደሮች የጨርቅ ኳስ

ሲጫወቱ የሚውሉ ወጣቶች ጀለብያቸውን እያወለቁ መጥተው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ያሸነፉበት አጋጣሚ ጥቁር ነጥብ የጣለ ሆኖ አልፏል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጣ ውረድ በአሰልጣኞች መቀያየርም ብዙ ፈተናዎችን አልፏል፡፡ ከ30 በላይ አሰልጣኞችን የቀያየረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹የአሰለጣጠን ዘዴውን ነው እንጂ አሰልጣኝ ቢቀየር ዋጋ የለውም›› የሚሉ እንደ ገነነ መኩሪያ አይነት ተቆርቋሪ ወገኖችን ድምፅ እስከ ዛሬ ድረስ ቦታ እየሰጠው አይደለም በሚል ይተቻል፡፡ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግር የአሰልጣኝ ችግር ነው በሚልም ከአንድም አምስት ያህል የውጪ ሀገር አሰልጣኞች በወር እስከ 200 ሺህ ብር እየተከፈላቸው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ ግን ይህ ነው የተባለ መሠረታዊ ለውጥ አልታየም፡፡ አሁን እንደውም ኢትዮጵያ ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ ቀድሞ መድረኳ የመለሷት ሁለቱም አሰልጣኞች (ዋናውም ምክትሉም) ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የቀድሞው መላምትና የወጣው ወጪ ፍትሐዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡

የተጫዋቾች መጥፋት ሌላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈተና ነው፡፡ ለውድድር ወደ ውጪ ሀገር

የሚሄዱ ተጫዋቾች በየሄዱበት ሀገር በመጥፋት የሀገር ገፅታ ከማበላሸታቸውም በላይ እነሱም በስፖርቱ የመቀጠል ተስፋቸው ሲያጨልሙ ኖረዋል፡፡ በተለይም ካለፉት 20 ዓመታት በፊት የነበረው የውጪ ሀገር ጉዞ ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚደረግ ጉዞ ጋር ይነፃፀር ስለነበር ለውድድር የወጡ ተጫዋቾች በወጡበት ይቀሩ ነበር፡፡ በ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይም ተጫውተው ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት ተጫዋቾች ቁጥር ጥቂት እንደነበር የወቅቱን ሁኔታ የሚያውቁ ሰዎች ያስታውሳሉ፡፡

ሽልማትየኢትዮጵያ እግር ኳስ የስፖርት ተመልካች

ብቻ ሳይሆን የስፖርት ደጋፊም እንዳለው በተለያዩ ጊዜያት በተገኙ ድሎች ማግስት የሚደረገው ድጋፍ ያሳያል፡፡ ሀገራችን ከዚህ በፊት ያየችው የመጀመሪያው ህዝባዊ ድል በ1980 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተካሄደውን 15ኛው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ስታነሳ የነበረው የደስታ ስሜት ነበር፡

Page 7: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

7

ይልቅ ወሬ ልንገርህ

ለባለትዳሮች ብቻ

ስለ ቢላ ነጠላ ዜማ

ሰሞኑን መቼም ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ድል ነው እየተወራ ያለው አይደል? በእርግጥ ስለ ድሉ ብቻ ሳይሆን ከድሉ በኋላ ለተጫዋቾቹ እየተደረገ ስላለው ግብዣና ሽልማትም ሲወራ ሳትሰማ አልቀረህም፡፡

እናልህ ባለፈው ማክሰኞ የኤድናሞል ባለቤት አቶ ተክለብርሃን አምባዬ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ

ቡድን ተጫዋቾች አስቀድመው ቃል የገቡትን የ1 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ሽልማት ለመስጠት ተጫዋቾቹን ጠርተው ነበር፡፡ ታዲያ በደረቁ እንዳይመስልህ ድል ያለ የምሳ ግብዣ ነበር፡፡

በግብዣው ላይ በከተማ ውስጥ ያለ ታዋቂ ሰው ማን ቀረ መሰለህ? ማንም አልቀረም፡፡ እኔ ራሴ ነበርኩ፡፡ አንተን ግን አላየሁህም፡፡ እና ምን እንደሆነ ልንገርህ? መርሃባ! የምሳ ግብዣው እንደተጠናቀቀ ሁሉም ተጫዋቾችና እንግዶች 3ኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው ወደ ሲኒማ 3 አዳራሽ ነበር እንድንገባ የተደረገው፡፡ አዳራሹ ስንገባ የመድረኩ አጋፋሪ ማን ቢሆን ጥሩ ነው? ገምታ?

አትድከም አርቲስት ኪሮስ ሀይለስላሴ ነበር፡፡ ኪሮስ ያው እንደምታውቀው ጨዋታ አዋቂ አርቲስት አይደል? ለዚህ ነው መሰለኝ አልፎ አልፎ ነገር ያራዝማል፤ የዚያን ዕለትም ትንሽ ዝግጅቱን ቦርቀቅ አድርጎት ነበር፡፡ እናልህ ወደ አዳራሹ ስንገባ መድረክ ላይ ማን ቢኖር ጥሩ ነው? መሀሪ ብራዘርስ ባንድ ከተለያዩ ድምፃውያን ጋር ሆኖ የብሔራዊ ቡድናችንን ተጫዋቾች ለማዝናናት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ነበር፡፡

በዳዊት ፍሬው ሀይሉ ተወዳጅ የክላርኔት ጨዋታ የተጀመረው ዝግጅት የተለያዩ ድምፃውያንን ወደ መድረክ በመጋበዝ ፕሮግራሙን አድምቆታል፡፡ ግን የሚገርመው ነገር ምን መሰለህ? የብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች ዘፋኝ እየተቀያየረ ቢጫወትም ከወንበራቸው ንቅንቅ ሊሉ ነው? ለምን መሰለህ? ዳንስ ወይም ጭፈራ ስለማይችሉ እንዳይመስልህ ‹‹መጀመሪያ- የመጣንበትን ሽልማቱን እናግኝ›› ያሉ ነበር የሚመስለው፡፡

የሽልማት ሰዓቱ ደርሶ ሽልማት ከመሰጠቱ በፊት ምን ቢሆን ጥሩ ነው? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አስልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው፣ የሴት ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አቶ አብርሃም ተክለሀይማኖት የታዳጊ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ያሬድ ጠንቃቃው ከየቡድኖቹ አምበሎችና ከኢንጅነር ተክለብርሃን አምባዬ ጋር ሆነው መድረክ ላይ ወጡ፡፡ ለምን መሰለህ? ኬክ ሊቆርሱ፡፡

ምን የመሰለ ኬክ ቀርቦ ቆራሾቹም መድረክ ላይ ወጥተው፣ መሀሪ ብራዘርስ ባንድም፣ ‹‹ይህቺ ቀን ልዩ ናት›› የሚለውን ዜማ መጫወት ቢጀምርም ኬኩ ሊቆረስ አልቻለም፡፡ ‹ለምን?› አልክ? ቢለዋ ተረስቶ ነበር፡፡ የመድረኩ መሪ አንጋፋው ኪሮስ ሀይለ ስላሴ በተደጋጋሚ ኧረ ቢለዋ. . . ኧረ ቢለዋ . . . ቢለዋ እያለ ቢናገርም አያ ቢለዋ ከየት ይምጣ? ታዲያልህ ኪሮስ እየደጋገመ ቢለዋ. . . ቢለዋ. . ሲል ከመሀሪ ብራዘርስ ሙዚቃ ጋር ተዋህዶ የዕለቱ ነጠላ ዜማ ሆኖ ነበር. . .

በነገራችን ላይ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በዕለቱ ከኢንጅነር ተክለብርሃን አምባዬ የገንዘብ ሽልማት ሌላ የአይነት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፤ ማን መሰለህ የሰጣቸው? ሂቦንጎ በተሰኘው ነጠላ ዜማው የሚታወቀው ስንታየሁ ሂቦንጎ ነው፤ ምንድን? በቅርቡ ያወጣውን አዲስ አልበም ሲዲ በነፍስ ወከፍ ለሁሉም ተጫዋቾች አድሏል፡፡ አዲስ አልበም አወጣ ወይ? ነው ያልከው? በል ቻዎ . .

ውድ አማካሪ በአጋጣሚ እጄ በገባ በቁም ነገር መፅሔት ላይ የተሰጠው ምላሽ እኔም በውስጤ አምቄ የያዝኩት እውነት ነው፡፡ይህ እውነት ተዳፍኖ የሚቀር ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን የሚሆን አልመሰለኝም አንድ ወቅት በደረሰብኝ አደጋ የዘር ፍሬዬ ተጎድቷል ፤ሀኪሞች እንደነገሩኝ ከሆነ ዘር መተካት ፈፅሞ አልችልም ፡፡እኔ ግን ውስጤ አላመነምና ለማንም አልተነፈስኩም ፡፡የኋላ ኋላ አገባሁ፡፡ስድስት አመት በፍቅር ዘለቅን፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል ባለቤቴ ያለመፀነሷ ጉዳይ እየተሰማት መጣ ፡፡እንዲያውም በቅርቡ መመርመር አለብን እያለች ወጥራ ይዛኛለች፡፡እባክህን ምን አድርጌ ከዚህ ጉድ ራሴን ላውጣ?

A.T ነኝ ውድ ጠያቂዬ ጭንቀትህ ምን ያህል ሊሆን

እንደሚችል ይገባኛል፡፡ነገር ግን ምንም ያህል ብትጨነቅ በመጨነቅ ብቻ ለውጥ አታመጣም ፡፡ስለዚህ አማራጭ ያስቀመጥኩለትን ምላሽ መርጠህ በመጠቀም ራስህን ነፃ ለማውጣት ሞክር፡፡ መጀመሪያ ራስህን ጠይቅ ብመረመር ውጤቱ ምን ይሆናል?አቀባበሌስ እንዴት ይሆናል?እንዲሁም ባለቤቴስ ምን ትል ይሆን?ለእነዚህ ጥያቄዎች በቂና ትክክለኛ ምላሽ ባታገኝ መጥፎም ሆነ ጥሩ ነገር ቢገጥመኝ በሚል ራስህን በሁለቱም ቦታዎች ላይ አርገህ በመቁጠር ራስህን አለማምድ ፡፡ምክንያቱንም ሆነ ውጤቱን ለመቀበል ራስህን ማዘጋጃ መንገድ ይሆንሀልና ነው፡፡

ሌላውና ዋናው ደግሞ የባለቤትህ ሁኔታ ቀን በቀን አስተውል፡፡በጨዋታ መሀል ልጅ አለመውለዷ ያሳደረባትን ትክክለኛ ስሜት ለመረዳት ሞክር፡፡ በተለይ ሌሎች የእናንተን ቤት የመሰለ ታሪክ እያጫወትካት የምትሰጠው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ጠይቃት ፡፡ እግረ መንገድህን ባለቤትህ ውሳኔዋ ምን ሊሆን እንደሚችል መገምገሚያ መንገድ ይሆንሀል፡፡ብቻ በዛም አለ በዚህ ለባለቤትህ ጥያቄ ምላሽ መፈለግና መስጠት ይኖርብኻል፡፡ አብራችሁ መመርመራችሁ ጥሩ ነው፡፡ባታምንበትም የምትጠረጥረው አንድ ነገር አለ፡፡ ይሄ ደግሞ ውጤትህ ጥሩ ባይሆን እንኳን እንዳትደናገጥ ሊያደርግህ ይችላል፡፡ ሴት ልጅ አግብታ ካልወለደች በሰዎች ዘንድ አብዛኛውን ጊዜ ተወቃሽ የምትሆን እሷ ነች፡፡ ባለቤትህ የእንመርመር ጥያቄ ያነሳችው በራሷ ምክንያት ሳይሆን በአካባቢ ተፅዕኖ ሊሆን ይችላል፡፡ምርመራችሁ ምንም ሆነ ምን አለመውለዳችሁ ብቻውን የሚለያያችሁ ላይሆን ይችላል፡፡ አስጨናቂ ቢሆንም ውሳኔ ላይ ድረስና ተመርመሩ ፡፡ከምርመራ በኋላ ከባለቤትህ መልካም ምላሽ እንዲገጥምህ እመኛለሁ፡፡

Page 8: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

8

‘‘ዩኒቨርሲቲው

በወቅቱ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በበኩላቸው

የዩኒቨርሲቲው መሠረታዊ ችግር በማለት ያስቀመጧቸው አንዳንድ ነጥቦች ነበሩ፤

ከእነዚህም መካከል ዩኒቨርሲቲው ምን ግዜም ቢሆን በሦስቱም ሥርዓቶች (የዐፄውና የደርግን ጨምሮ) ነፃ ሆኖ እንደማያውቅና ለዚህም ማስረጃ ከዩኒቨርሲቲው አካዳሚ ኮሚሽን ጀምሮ ያሉት ቁልፍ›› ቦታዎች የገዢውን

መደብ አመለካከት በሚያራምዱ ሰዎች መያዙን አንድ ምሁር በምሬት መናገራቸው ነበር፡፡

መነሻበሀገራችን ትልቁ የትምህርት ተቋም መሆኑ

ስለሚታመንበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመፃፍ ቢያንስ በዚህ ተቋም ውስጥ እንደተማሪ ሳይሆን እንደመምህር ሆኖ ማለፉ የተሻለ ይመስለናል፡፡ ስለዚህ በፈርጀ ብዙ ችግሮች ተተብትቦ ስለሚገኘው የትምህርት ተቋም በርካታ ውይይቶች፣ ስብሰባዎች፣ ግምገማዎች እንዲሁም ዘንድሮ ደግሞ ‹‹ስልጠና›› በሚል ስያሜ መፍትሔ የማፈላለግ ሥራ ለመስራት ቢሞከርም ችግሩን እያነሱ ከመውቀጥ ባለፈ ጠብ የሚል ነገር የማግኘቱ ነገር ግን አሁንም ተስፋ አስቆራጭ መስሏል፡፡ በተለይ ደግሞ እንኳን ስለሚገኙበት ተቋም ቀርቶ ስለሀገርና አልፎም አህጉር ታላላቅ ሃሳቦችን ማመንጨት የሚችል አእምሮ ተሰብስቦ ይገኝበታል ተብሎ በሚታመነው ተቋም ምሁሩ ‹‹ይህ ሊደረግ ይገባል›› የሚል ነገር ቢያንስ ሚዲያውን ተጠቅሞ አለማስፈሩ ዛሬም የአድርባይነት መንፈስ ተቋሙን እንዳልተላቀቀው የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው ሰሞኑን እንደታየው አንዳንዶቹ መምህራን ጠንካራ ሊባል የሚችል ሀሳብ በአዳራሽ ውስጥ ሲናገሩ ቢደመጥም በበሰለና በሰከነ እንዲሁም ለውጥ ሊያመጣ በሚችል መንገድ የማቅረብ ድፍረቱ ቢታይ ደግሞ ለሀገር የሚበጅ ነበር እንላለን፡፡ በነገራችን ላይ ድፍረቱንም አግኝተው ቢሆን የተናገሩትን ከአዳራሹ ውጭ ‹‹እንዴት ደፈርክ›› የሚላቸው በዝቶ ስንመለከት የችግሩ መፍትሔ አስቀድሞ ከውስጥ መሰራት ያለበት መሆኑን አሳምኖናል፡፡

እንኳን ስለሚሰሩበት ተቋም ቀርቶ በሀገርም ጉዳይ ‹‹እኔ የለሁበትም›› የሚለው የአድርባይነት መንፈስ ካልተወገደ በቀር ‹‹ለውጥ›› የሚባለው ነገር በየዓመቱ ለውይይት የሚቀርብ አጀንዳ ከመሆን እንደማያልፍ በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ በተለይም ደግሞ የበርካታ ታላላቅ ሃሳቦች መፍለቂያ የነበረው ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ድምፁ የሚሰማው አዳራሽ ውስጥ ለ‹‹ስልጠና›› ሲሰበሰብ መሆኑ በራሱ በተቋሙ ስብስብ ላይ ጥያቄ የሚፈጥር ነው ባይ ነን፡፡ ይህ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደታላቅ የትምህርትና የምርምር ተቋም የሚጠበቅበትን ለሀገር ያበረክት ዘንድ ምሁሩ በግልፅና በድፍረት ሊቀረቡና ሊፈተሹ የሚገባቸውን ችግሮች በማውጣት ለውይይትና ለመፍትሔ ማቅረብ ይገባዋል፡፡ ምንም እንኳን የዚህ ፅሁፍ ዋነኛ ማጠንጠኛ በቅርቡ ‹‹ስልጠና›› በሚል ርዕስ የዩኒቨርሲቲው ምሁር ለሦስት ቀናት የታደመበትን የስብሰባ ድባብ ማስቃኘት ቢሆንም ወደፊት በተከታታይ ግን የተቋሙን መሰረታዊ ችግሮች በተለይም ዋነኛ ተልዕኮው የሆነው መማር ማስተማርንና ሌሎችንም የሚፈትሹ መጣጥፎችን ማቅረባችን አይቀሬ ይሆናል፡፡

እንግዲህ ሰሞኑን በዩኒቨርሲቲው ‹‹ስልጠና›› የሚል ርዕስ ተሰጥቶት የተካሄደውን ስብሰባ ከመቃኘታችን በፊት ለትዝታ ያህል መለስ ብለን ከ10 ዓመታት በፊት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በተገኙበት የተካሄደውንና የዩኒቨርስቲውን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሔ እንዲሰጥ ታምኖበት የነበረውን ስብሰባ ለአፍታ በአጭሩ እንቃኝ፡፡

Page 9: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

9

- ፈርስት ኤድ- አናቶሚ እና ፊዚዎሎጂ - - ፔዲኩር- ሳይኮሎጂ - ማኒኩር- ስውዲሽ ማሳጅ - ፌሻል ስክራፕ ማሳጅ - ታይ ማሳጅ - ቦዲ ስክራፕ ማሳጅ- ሪላክስ ማሳጅ - ታውል ማሳጅ- ስፖርት ቴራፒ ማሳጅ - ድራይ ማሳጅ- ሪፎክሶሎጂ ማሳጅ - እንግሊዝኛ ቋንቋ - ሾልደር ማሳጅ

አስመርቀ

ን ሥራ

እናስይዛ

ለን!

ሙሉ እውቅና ያለው ተቋም የምንሰጣቸው ኮርሶች

አድራሻ፡- ቦሌ አለም ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.502 ላይ ለበለጠ መረጃ፡- 0911-401637/0912-397692 011-6-611594

ዩኒቨርሲቲው ከመለስ ጋር

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከ10 ዓመታት በፊት የዩኒቨርሲውን መምህራን ለውይይት ጠርተው ‹‹ችግሩን እንፈትሽ›› ባሉበት ወቅት ዋነኛ አጀንዳው የነበረው በዩኒቨርሲቲው አካዳሚያዊ ነፃነት፣ በዲሞክራሲያዊና ኢዲሞክራሲያዊ ገፅታዎች፣ በመምህራንና ተማሪዎች ግንኙነት ላይ ወዘተ ያነጣጠረ እንደነበረ የሩቅ ጊዜ ትዝታችን ሆኗል፡፡ በተለይም ውይይቱ ‹‹ዩኒቨርሲቲው ከዲሞክራሲ ስርዓት አንፃር ምን ይጠበቅበታል? የሚለው ላይ ማተኮር እንዳለበት እንጂ በግለሰቦች ላይ ማነጣጠር አይገባውም›› የሚል ቅድመ ማስጠንቀቂያ አቶ መለስ ሲሰጡ መፅሐፍ ከማንበብ ይልቅ የግለሰቦችን ሕይወት እየተከታተለ በእነሱ ላይ ተንጠልጥሎ ለማለፍ የሚሞክረውን አድርባይ ሁሉ ኩም አድርገውት ነበር፡፡

በወቅቱ በዚያ ስብሰባ ላይ አቶ መለስ የብሔር ብሔረሰቦች መብት ካልተከበረ የግለሰቦች መብት እንደማይከበርና የግለሰቦች መብት ካልተከበረም የብሔረሰቦች መብት አይከበርም የሚለውን አጣምሮ የማያከብር፤ ለዲሞክራሲ አስተሳሰብ አንገቱን ለማቅናት የተቸገረ ዩኒቨርሲን ዲሞክራቲክ ነው ብሎ ለመቀበል እንደሚያስቸግራቸው አውስተው ተቋሙ ይህን አመለካከት የበላይ አድርጎ ሲያራምድ ብቻ ዲሞክራቲክ ነው ማለት እንደሚቻል ገልፀው ነበር፡፡ አቶ መለስ አክለውም ዩኒቨርሲቲው አሰራሩና አደረጃጀቱ ግልፅነት

የሌለው በሰዎች መልካም ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ መሆኑንም ነግረውት ነበር፡፡

አቶ መለስ የዩኒቨርሲቲውን በጀት አስመልክቶ ከፍተኛ የሚባል ገንዘብ፣ አንድ መቶ አስር ሚሊዮን ብር፣ (የአሁኑን በኋላ እንመጣበታለን) መመደቡን አስታውቀው ይህም በዩኒቨርሲቲው ከማይማረው አርሶ አደር የሚመጣ በመሆኑ አጠቃቀሙ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለው ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዩኒቨርሲቲው የፓርትነርሺፕ ግንኙነት መለመድ እንዳለበት፣ ተቋሙ የራሱ የትምህርት

ፍልስፍና እንደሚያስፈልገውና ይህ ይፋ መሆን እንዳለበት ለዚህም ለልማት ፕሮፌሽናል አመራር ሊሰጥ የሚችል ሰው፣ የሚጠይቅ፣ የሚመረመር፣ የሚያውቅ፣ ማወቅ ያላቋረጠ፣ በወሬ የማይነዳ፣ አመዛዝኖ አቋም የሚወስድ ሰው መፈጠር እንዳለበት በዚህ ዓላማም የጋራ መረዳት ከሌለ በጋራ መራመድ የማይቻል መሆኑን የዩኒቨርሲቲውን ተሰብሳቢ ምሁር አስረድተውት ነበር፡፡

በወቅቱ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው መሠረታዊ ችግር በማለት

ያስቀመጧቸው አንዳንድ ነጥቦች ነበሩ፤ ከእነዚህም መካከል ዩኒቨርሲቲው ምን ግዜም ቢሆን በሦስቱም ሥርዓቶች (የዐፄውና የደርግን ጨምሮ) ነፃ ሆኖ እንደማያውቅና ለዚህም ማስረጃ ከዩኒቨርሲቲው አካዳሚ ኮሚሽን ጀምሮ ያሉት ‹‹ቁልፍ›› ቦታዎች የገዢውን መደብ አመለካከት በሚያራምዱ ሰዎች መያዙን አንድ ምሁር በምሬት መናጋራቸው ነበር፡፡

ሌላውም ምሁር በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚታዩ ጉድለቶች በማለት ካስቀመጧው መካከል አንድ ሰው በበርካታ

Page 10: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

10

ኮሚቴዎች መመደብና ይህንንም ሁሉም አሜን ብለው መቀበላቸው፤ መምህራን (ምሁራን) አገር እየለቀቁ ለመኮብለላቸው የሚቀርበው ምክንያት የደመወዝ አነስተኛ መሆን ነው የሚባለው ነገር በቂ ምክንያት እንዳልሆነና መምህራን በነፃነት ለመስራት የጎደላቸው ነገር እንዳለ የሚያሳይ ነው፤ ምሁሩ የሚሰማውን እንዳይናገርም ስለሚፈራና ከስራው ተፈናቅሎም ልጆቹንና ቤተሰቡን የሚያስተዳደርበት እንዳያጣ ፈርቶ መሆኑም መታወቅ አለበት ብለው ነበር፡፡

በወቅቱ በዚያ ስብሰባ ላይ የነበሩት የመንግስት ባለስልጣን አቶ ተፈራ ዋልዋ የዩኒቨርሲቲውን ዲሞክራሲያዊ አሰራር ያቀጨጩ በማለት ያስቀመጧቸው ሦስት ነጥቦች ደግሞ ነበሩ፡፡ እነዚህም የመጀመሪያው ህጋዊው የአመራር አካል ደካማና ዩኒቨርሲቲውን ለመምራትና ለማስተዳደር አለመቻል ሲሆን ሁለተኛው በዩኒቨርሲቲው ህጋዊ ያልሆነ የአመራር አካል በስውር ዩኒቨርሲቲውን እንደፈለገ ሲያሽከረክረው መቆየቱንና ዲሞክራሲያዊ ኃይልም ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዳይመጣ ከፍተኛ መከላከል የሚያደርግ መሆኑን፤ እንዲሁም በሶስተኛ ደረጃ ከመምህራኑ አብላጫውና ምናልባትም ከ90 በመቶ በላይ የሚያቅፈው ደግሞ ለመብቱ መታገል የማይፈልገው ክፍል መሆኑ ነው ብለው ነበር፡፡

ከዚህ በተቃራኒ የቆሙ አንድ ምሁር ደግሞ መረር ብለው፡- ‹‹ዩኒቨርሲው የደርግ ኢሰፓ መፈንጫ ነበር፤ አሁን ደግሞ የኢህአዴግ መፈንጫ እንዳይሆን ስጋቱ አለኝ›› በማለት ፍርሃታቸውን ሲናገሩ አቶ መለስ በበኩላቸው የምሁሩ ስጋት እንደማያጣላቸው አውስተው ነበር፤ ግን ዩኒቨርሲቲው የኢህአዴግ መፈንጫ ከመሆኑ በፊት ደግሞ የመላ አማራ መፈንጫ መሆኑ መቋረጥ አለበት ማለታቸውን እናስታውሳለን፡፡

አንድ ምሁር ደግሞ የመማር ማስተማሩን ችግር አስመልክቶ፡- ‹‹ጠንካራ መምህራን አሉን፣ ችግራችን በጥራት ለማስተማር የሚያስችል አቅም አለመኖር ነው፡፡ በእዚህ ላይ ዲሞክራሲ አልዳበረም፡፡ ስም በማጥፋት፣ በማስፈራራት ሥራ እየተሰራ ነው›› በማለት የዚያን ጊዜውን ዩኒቨርሲቲ ገልፀውት ነበር፡፡

እንዲህ ዓይነቶቹን አስተያየቶች በስብሰባው ላይ ሲቀበሉ የቆዩት አቶ መለስ እንደማጠቃለያ ስለዩኒቨርሲቲው በሰጧቸው አስተያየቶች ትዝታችንን እንቋጭ፡፡ አቶ መለስ በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲው አመራር፡- ‹‹አመራር የመስጠት እንቅስቃሴ ውስጥ ያለ ግን አመራር የማይሰጥ አካል ይመስለኛል›› አሉት፡፡ በመቀጠልም በዩኒቨርሲቲው ቀርቦ የነበረውን ቻርተር ‹አውቀን ነው የተኛንበት›› ካሉ በኋላ ‹‹ግልፅነት ለሌለውና ተግባሩን በሚገባ ለማይወጣ አካል ቻርተሩን ማፅደቅ ተጨማሪ ምሽግ እንደመፍቀድ ይሆናል›› አሉ፡፡

በአቶ መለስ በሁለተኛ ደረጃነት ዩኒቨርስቲውን አስመልክቶ የተቀመጠው ችግር ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ሕገ መንግስታዊ መብት ውጭ ስውር ዓላማ ይዘው በስውር ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩ አካላት የሚገኙበት መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ባያሳድርም፤ በአብዛኛው የዩኒቨርሲቲው ምሁር ፖለቲካን በሩቁ በሚል አመለካከት መብቱን ለማስከበር እንኳን ሙከራ የማያደርግ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ያለውን ከፍተኛ እውቀት ለመጠቀም አለመፈለጉ በዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት መሆኑ አይቀርም ብለው ነበር፡፡ በመጨረሻም አቶ መለስ ዩኒቨርሲውን የምንለው፡

- ‹‹ብትጣፍጥ ተቃውሞ የለንም፤ እኛ ያልነው ግን ቢያንስ ለራስህ ብለህ ጣፍጥ እንጂ መምረር አለብህ የሚል አይደለም›› በማለት ነበር የተሰናበቱት፡፡

ለመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ከ10 ዓመታት ጉዞ በኋላ ማረርና መምረሩ የት ደርሶ ይሆን? ለወደፊቱ የምናደርገው ሰፊ ፍተሻ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዛሬ ከሰሞኑ ከነበረው ‹‹የስልጠና›› መድረክ የቃረምነውን በመበተን ተቋሙን ከአንድ አቅጣጫ ለማሳየት እንሞክር፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዛሬበመጀመሪያ ከስብሰባው የጥሪ ርዕስ እንጀምር፡

፡ በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ፋኩልቲዎች ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ የተለጠፈው ደብዳቤ ‹‹ስልጠና›› የሚል በመሆኑ መምህራን ወደ አዳራሽ የከተቱት በዚሁ መንፈስ ነበር፡፡ መምህራን ወደ አዳራሹ ከገቡ በኋላ የመድረኩ መሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መሆናቸውን ሲመለከት ደግሞ ‹‹ስልጠና›› የሚል ርዕስ በተሰጠው ስብሰባ ግራ መጋባት ጀመረ፡፡ ይሁንና ዶ/ር ደብረፅዮን ስብሰባው በዩኒቨርሲቲው ችግሮች ዙሪያ ለመወያየትና የመፍትሔ ሃሳቦችም ማፈላለግ ዋነኛ ዓላማው መሆኑን በመጠቆም የዩኒቨርሲቲው አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት በቅድሚያ ያለፈውን ሁለት ሺህ አራት የዩኒቨርሲቲውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጋበዙ፡፡

በወቅቱ የቀረበውን የ2004 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን ሪፖርት መንፈስ በአጭሩ እንቃኘው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከመንግስት የተመደበለት በጀት 1 ቢሊዮን 161 ሚሊዮን 653 ሺህ 800 ብር እንደነበር ም/ፕሬዚዳንቱ ሲጠቅሱ ይህ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ዓመታት በፊት የነበረውን 110 ሚሊዮን ብር አስታወስንና ታዲያ መንግሥት በዚህ ረገድ ለተቋሙ በቂ ድጋፍ አላደረገም እንዴት ሊባል ይችላል? የሚል ጥያቄ ተጫረብን፡፡ ከበጀቱ ውስጥ ደግሞ ከመደበኛ በጀት 95.96 በመቶ እንዲሁም ከካፒታል በጀት 77.8 በመቶ ተግባር ላይ መዋሉ በሪፖርቱ ሲጠቀስ የዩኒቨርሲቲው ስኬት እንግዲህ አብሮ መጠቀስ አለበት የሚለው የሁሉም ጉጉት ሆነ፡፡ ይሁንና ተቋሙ ባለፈው አንድ ዓመት አንድ የዩኒቨርሲቲ

ኢንዱስትሪ ቀን ከማክበሩ ባሻገርና ከአንዳንድ አቻ የውጭ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በምርምር ሥራዎች አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ከመድረሱ ባሻገር ዋነኛ ሥራው አድርጎ የከረመው የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን መፈፀም እንደነበር ሪፖርቱ ምሁራዊ ለዛ በሌለው የሪፖርት አቀራረብ ለማሳየት ተሞከረ፡፡

ከዚሁ ጋር ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኛ እንዲሁም ከአርብቶ አደር አካባቢ ለሚወጡ ተማሪዎች ትኩረት ሰጥቶ ባለፈው አንድ ዓመት መሰራቱን ሲስታውቅ በስፖርቱም ዘርፍ ጥሩ ውጤት ዩኒቨርሲቲው ማስመዝገቡንና በድራማም አንድ በሀገር አንድነት ላይ የሚያጠነጥን ድራማ ለብሔር ብሔረሰቦች ቀን መቀሌ ላይ በማቅረብ ሀገራዊ አድናቆት እንደተቸረው በሪፖርቱ ሰፍሯል፡፡ ከእነዚሁ ጋር በተጓዳኝ አንዳንድ በዓመቱ ውስጥ የታዩ ችግሮች በማለት በሪፖርቱ ከሰፈረው ውስጥ ግን የአዳራሹን ትኩረት የሳበው፡- ‹‹የተወሰኑ መምህራን ከተማሪዎች ጋር ዲሞክራሲዊ ግንኙነት አለመኖር. . .›› የሚለው ነበር፡፡

የ2004 ዓ.ም የሥራ ክንውን ሪፖርት ካበቃ በኋላ የመድረኩ መሪ ዶ/ር ደብረፅዮን የሻይ ዕረፍት ሆኖ የ2005 ዓ.ም ዕቅድን ሰምተን ውይይት በቡድን በቡድን ተከፋፍለን ይደረግና በየቡድኑ የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽ ይሰጥባቸዋል አሉ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የ2005 ዓ.ም ዕቅድ በጣም በአጭር በአጭሩ የቀረበና ትኩረቱን ከዩኒቨርሲቲው መሠረታዊ ችግሮች (የመምህራን ጥያቄዎች፣ የመማር ማስተማር የጥራት ችግር፣ በተማሪ አቀባበል ላይ የሚታዩ ችግሮች፣ በተቋሙ በሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮች . . . ወዘተ) ገሸሽ አድርጎ በተለመዱ፣ የተስፋ ቃላት የተሞላና የአንድ ታላቅ ምሁራዊ ተቋም ዕቅድ መስሎ የሚሸት ምንም ነገር የሌለው ነበር ማለት ይቻላል፡፡ እንግዲህ የክንውንና የዕቅድ ሪፖርት ከተደመጠ በኋላ የመድረኩ መሪ የአዳራሹን ግራ መጋባት በመጠኑ የተረዱት ይመስላል፤ ወይም ሪፖርቱ እሳቸውም ከጠበቁት በታች አነሰባቸው መሰል ተሰብሳቢውን ለውይይት ሲጋብዙ፡- ‹‹የማብራሪያ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ›› አሉ፡፡

በዚህ ጊዜ አንድ መምህር እጃቸውን አሳዩና ሲፈቀድላቸው፡- ‹‹የማብራሪያ ጥያቄ ምንድነው?

Page 11: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

11

YARED COMPUTERS ላፕቶፖችንና ዴስክቶፖችን ከሙሉ ዋስትና ጋር

እንደተለመደው አቅረበናል፡፡

አድራሻ፡- ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወረድ ብሎ ኢንተርናሽናል ፋሽን አጠገብ

ስልክ፡- 0911-973232/0910-992156

ላፕቶፕ ከ5300 ብር ጀምሮዴስክቶፕ ከ1800 ብር ጀምሮ

DELL, TOSHIBA, HP, PRINTERS

በራሱስ የማብራሪያ ጥያቄ የሚባል ነገር አለ እንዴ?›› በማለት ሲናገሩ አዳራሹ በሳቅ አጀባቸው፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮንም በሪፖርቱና በዕቅዱ ውስጥ ግልፅ ያልሆነ ወይም መብራራት አለበት፤ እንዲሁም የተዘነጉ መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ የምትሏቸውን እንድታነሱ መጋበዜ ነበር በማለት ሐሳባቸውን መስመር አስያዙ፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ እጆች በቅፅበት በአዳራሹ መታየት ሲጀምሩ ‹‹የተወሰኑትን አሁን የቀሩትን ደግሞ በቡድናችሁ እያነሳችሁ አንድ ላይ እንውያይበታለን›› በማለት ዶ/ር ደብረፅዮን ዕድሉን መስጠት ጀመሩ፡፡

የመጀመሪያው ተናጋሪ ያነሱት ጥያቄ በአዳራሹ ውስጥ የነበረውን መምህር ሲያብሰለስል የነበረ በመሆኑ ሌላው መምህር ተቀደምኩ ከማለት ባሻገር በጥያቄው አልተደነቀም፡፡ መምህሩ ጠየቁ፡- ‹‹በሪፖርቱ ላይ አንድ ችግር ሆኖ የቀረበው የተወሰኑ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት የላቸውም የሚል ነበር፡፡ ለመሆኑ ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት ማለት ምን ማለት ነው? የተወሰኑ መምህራን ተብሎስ ሲቀርብ በርካታዎች ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት አላቸው ማለት ነው?››

ከመድረኩ በዚህ ረገድ የተሰጠው ምላሽ ደግሞ፡- ‹‹አንዳንድ መምህራን ተማሪዎቻቸውን ያሽቆጠቁጣሉ፤ እንዲፈሯቸው ያፈልጋሉ፤ ይህ ደግሞ ተማሪው ያመነበትንና የማይሰማውን እንዳይናገር የማፈን አካሄድ ነው፡፡ ተማሪው መምህሩን ማክበር እንዳለበት ብናምንም ከልክ ሲያልፍ ግን የመማር

ማስተማሩን ሂደት የሚጎዳ ይሆናል፡፡ ተማሪውን የትምህርቱ እኩል አካል አድርጎ የማሰብ ችግር ታይቷል›› ተባለ፡፡

ሌላው መምህር ደግሞ የጠየቁት ጥያቄ አዳራሹን ያሳቀና መድረኩን ግራ ያጋባ ነበር፡- ‹‹ለመሆኑ ይህ ሪፖርት የተባለው ነገር ለእኛ አካዳሚሽያን መቅረቡ ፋይዳው ምንድነው? እኛ እኮ ይብዛም ይነስ ምሁራን ነን፡፡ አመራሩ የሰራውን ስራ ለቦርዱ ሪፖርት ያድርግ፡፡ ለእኛ ደግሞ በትምህርትና በምርምር ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን አመራሩ ለቅሞ በማውጣት እንድንወያይበትና መፍትሔ እንድናቀርብ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል›› ብለው ተቀመጡ፡፡

የመድረኩ መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ‹‹ጥያቄው ትክክል እንዳልሆነና መምህሩ የዩኒቨርሲቲው አካል እንደመሆኑ መጠን የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ፣ ስኬትና ችግር ማወቅ ያለበት ይመስለኛል፡፡ በምን አገባኝ ስሜት መሄድ መቆም አለበት›› በማለት ጠንከር ያሉ ቃላትን ሰነዘሩ፡፡

ሌላው መምህር ደግሞ፡- ‹‹የቀረበው ሪፖርትም ሆነ ዕቅድ ከአንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከመሰለ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅና በይዘቱም እጅግ የወረደ መሆኑን በቅድሚያ መተቸት እፈልጋለሁ›› አሉ፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘውም፡- ‹‹እኛን በዋነኛነት ሊያሳስበን የሚገባው በመማር ማስተማሩ ዙሪያ የሚታየው የጥራት ችግር ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በራሱ መስፈርት የመቀበል ስልጣኑ በትምህርት ሚኒስቴር መወሰዱ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ያልመረጠውን ተማሪ እየተቀበለ እንዴት ብቁ ዜጋ አድርጎ

ሊሰራው እንደሚችል ማሰቡ ግራ አጋቢ ነው›› በማለት ተቀመጡ፡፡

የመድረኩ አመራር ጥያቄው ትክክል መሆኑን ተቀብሎ ነገር ግን ለሽግግር ጊዜ ተብሎና በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በየክልሉ በመከፈታቸው የተማሪ ምልመላው በማዕከል (በትምህርት ሚኒስቴር) እንዲደረግ በመንግስት መወሰኑን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው እንደ አንድ የመንግስት የትምህርት ተቋም ራሱን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በመለየት ደሴት አድርጎ መሄድ አይቻለውም፡፡ የመንግስት አጠቃላይ ራዕይ ብዙና የሰከነ ዜጋን በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማፍራት እስከሆነ ድረስ ተቋሙ የራሱን የትምህርት አሰጣጥ እየፈተሸና እያሻሻለ መስራት ይጠበቅበታል የሚል ምላሽ ተሰጠ፡፡

ሌላው ምሁር ደግሞ፡- ‹‹ሪፖርቱ የዩኒቨርሲቲውን ዋነኛ አካል መምህሩን የረሳና በተለይም የመምህሩን ዘርፈ ብዙ ችግር ከግንዛቤ ሳያስገባ፣ መፍትሔም ለመስጠት ሳይሞክር መቅረቱ ያሳዝናል›› በማለት ተቹ፡፡ ምሁሩ አክለውም፡- ‹‹እኔ ተመራማሪ (researcher) ነኝ እያልኩ ስለምገዛው ድንችና ሽንኩርት ማሰብ አይገባኝም›› በማለት በተለይ በምርምር ሥራዎች ዙሪያ ዩኒቨርሲቲው ትኩረት አለመስጠት ብቻ ሳይሆን እንቅፋትም ሆኖ የሚቆምባቸው ጊዜያት በርካታ እንደሆኑ በመጥቀሱ ለዚህም ማሳያ የራሳቸውን ተሞክሮ እንደሚቀጥለው አስቀመጡ፡-

‹‹የዩኒቨርሲቲ መምህር ከመማር ማስተማሩ ተግባር ቀጥሎ ትልቁ ተልዕኮው ምርምርና ጥናት ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በዚህ ረገድ በቂ ድጋፍ እያደረገልን

አይደለም፡፡ አንድ ምርምር ለማድረግ የሚፈቀደው በጀት 20ሺህ ብር ነው፡፡ አሁን ይህ ብር እንኳን ምርምርና ጥናት ለማድረግ ቀርቶ ለፎቶ ኮፒስ ይበቃል? ይህም ይሁን ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም የተነሳ ነው በማለት ምርምር ለማድረግ ቆርጬ ተነሳሁና፤ ስጠይቅ የ20ሺህ ብር ፕሮፖዛል አቅርብ ተባልኩ፡፡ ፕሮፖዛሌን አቅርቤ ብጠብቅ፣ ብጠብቅ ግን ምላሽ አጣሁ፡፡ የጥናት ፕሮፖዛሉ ከዚህ በፊትም ለውይይት አቅርቤው ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ ችግሩ ከጥናቴ ርዕስ እንዳልሆነ በመገመት ከስድስት ወራት በኋላ ይህንኑ ወደሚመለከተው የዩኒቨርሲቲው ቢሮ በመሄድ ‹‹ጉዳዬ የት ደረሰ?›› በማለት ጠየቅሁ፡፡ የተሰጠኝ ምላሽ ግን የሚገርም ነበር፡፡ ‹‹የጥናት ርዕስህ ጥሩ ቢሆንም የተፈቀደልህ በጀት 20 ሺህ ብር ነበር፤ የአንተ ግን 20ሺህ 192 ብር ነው፤ 192 ብር ትርፍ በመምጣቱ ጥናቱ አልተፈቀደልህም›› አሉኝ፡፡ አክለው፡- ‹‹ከ20ሺህ ብር አምስት ሳንቲም ከጨመረ ወይም ካነሰ ጥናቱ ይወድቃል›› ተባልኩ፡፡ እኔን ያሳዘነኝ የምታደርገው ጥናት ለሀገር ምን ጥቅም አለው? የሚል አንድም ጠያቂ ማጣቴ ነው፡፡ ለመሆኑ ዩኒቨርሲቲው መምህራንን እንደተመራማሪ ድጋፍ የሚያደርግላቸው መቼ ይሆን?›› በማለት ወደ ወንበራቸው ተመለሱ፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመምህራንን ችግሮች የሚመለከቱ በርካታ ጥያቄዎች መዥጎድጎድ ጀመሩ፡፡ አንዳንዶቹን እናቅርብ፡-

አንዱ መምህር እንዲህ አሉ፡- ‹‹አንድ መምህር የተረጋጋ ትምህርት ለመስጠት የተረጋጋ ኑሮ ያስፈልገዋል፡፡ ስለሚበላው ምግብና ስለሚኖሩት የቤት አከራይ የሚጨነቅን መምህር እንዴት ነው ስለሚያስተምረው ትምህርት ጥራት እንነጋገር የሚባለው? ይህንኑ ተቋቁሞ ለማስተማር ሲመጣስ ቢያንስ ቢሮ ያስፈልገዋል፤ ለመሆኑ ከመምህሩ ስንት እጅ ነው ቢሮ ያለው? አንዲት ቢሮ ለአምስት እየተጋሩ ሁለቱ ተማሪ ሲያማክሩ ሌሎቹ መቀመጫ ጠረጴዛና ወንበር ስለማያገኙ ካፌ ሄደው መቀመጥ ግድ እንደሚሆንባቸው ይታወቃል? ለዚህ ነው የመምህሩ ችግር የተረሳ ይመስላል ለማለት የምንገደደው›› በማለት ተቀመጡ፡፡

ቀጣዩ አስተያየት ሰጪ መምህር ደግሞ እንዲህ አሉ፡- የዩኒቨርሲቲ መምህር ትርፍ ሥራ ሰርቶ 35 በመቶ የሚቆረጥበት ምክንያት ምን ይሆን? በጣም የሚገርመው ደግሞ ገንዘቡ ከደመወዙ ጋር እየተሰላ የሚቆረጥ በመሆኑ በዚህ እንኳን ኑሮውን እንዳይደጉም 1 ሺህ ብር ሰርቶ

ወደ ገፅ 30 ዞሯል

‘‘‹‹የዩኒቨርሲቲ መምህር ከመማር ማስተማሩ ተግባር ቀጥሎ ትልቁ ተልዕኮው ምርምርና ጥናት ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በዚህ ረገድ በቂ ድጋፍ እያደረገልን አይደለም፡፡ አንድ ምርምር ለማድረግ የሚፈቀደው በጀት 20ሺህ ብር ነው፡፡

Page 12: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

12

ፊ ል ም

በፀጋጊዮርጊስ ወርቅነህ[email protected]

የፊልም ፌስቲቫል ጽንሰ ሃሳብ በአለማችን ውስጥ ለብዙ ጊዜያት

አለም አቀፍ ፊልምፌስቲቫሎች

የቆየ ጉዳይ ነው፡፡ በሌሎች ሙያዎች የተለያዩ ነጋዴዎች ወይ ም የፈጠራ ሰዎች ምርቶቻቸውን ወይም ፈጠራዎቻቸውን ለብዙሀኑ ለማድረስ እንዲሁም ገዢዎችን ለማግኘት ወይም ለማስተዋወቅ አግዚቢሽኖችን ይጠቀማሉ በሲኒማው አለም ውስጥ ለተሰማሩ ባለሙያዎችም ይህ የፌስቲቫል መንገድ በሙያው ውስጥ የተሰማሩ ባለሙያዎች እርስ በርስ የሚገናኙበትና ልምዶቻቸውን የሚለዋወጡበት አዳዲስ በስራው መስክ ውስጥ ያሉ ጉዳዮችንና ዘመን አመጣሽ የሲኒማ ቴክኒኮችን

የሚቀስሙበት እንዲሁም ለዘርፈ አዲስ መጥ የሆኑ ፊልምሰሪዎች ስራዎቻቸውን ለተመልካቾችና በዘርፉ አንቱ ለተባሉ ጠበብት በማቅረብ ችሎታቸውን የሚያስገመግሙበት፤ በፊልም ሙያ ውስጥ የተሰማሩ ፕሮዲዩሰሮችና ሌሎች ባለሃብቶች ደግሞ ለሚያሰሩት ፊልም የሚመጥናቸውን ባለሙያ የሚያማርጡበትወርቃማ እድል ነው፡፡

በሃገራችን የፊልም ፌስቲቫሎችን የማዘጋጀት ዳርዳርታዎችን ከቅርብጊዜ ወዲህ መስማት የተለመደ ቢሆንም

እስካሁን ድረስ ከዝግጅት አልፎ በተግባር የተካሄደ ደረጃውን የጠበቀ ፌስቲቫል የለም፡፡ ስለዚህም በዝግጅት ደረጃ ላይ ያሉት እነዚህ ጅምር ፌስቲቫሎች በቅርጽ ደረጃ ምን አይነት አቀራረብን (format) በዘላቂነት እንደሚከተሉ፤ በአለምአቀፍ ደረጃ ያላቸው ተቀባይነት እስከምን ያህል እንደሚደርስ እንዲሁም ለምን ያህል እንደሚቆዩ ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ በመሆኑ ወደዚህ ጉዳይ ለዛሬ ጠለቅ ብለን አንገባም፡፡

በአለምአቀፍ ደረጃ እስካሁን ድረስ ህጋዊ የሆኑና የተለያዩ የሙያውን ንዑስ ዘርፎች ለማበረታት ተብለው የሚካሄዱ ወደ 400 የሚደርሱ ፌስቲቫሎች ሲኖሩ አህጉራችን አፍሪካ ከዚህ መሃል 10ያህሉን በማዘጋጅት የድርሻዋን እየተወጣች ትገኛለች፡፡ ነገር ግን ከነዚሁ መሃል በቀዳሚነታቸው፤ በባለሙያዎች ዘንድ በሚሰጣቸው ክብር እንዲሁም

በሌሎች ተመሳሳይ መስፈርቶች ነጥረው የወጡና በፊልም ታዳሚያዎች እንዲሁም ፊልምሰሪዎችና ሃያሲዎች በጥቅሉ የፊልም ፌስቲቫሎች ‹‹ሶስቱ ስላሴዎች›› (the trinity of film festivals) ተብለው ስለሚጠቀሱት ዝግጅቶች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሳምንታት ማየት እንጀምራለን፡፡

፩-ቬኒስ ፊልም ፌስቲቫልLa biennale di veneziaየቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል ለሌሎች

መሰል ዝግጅቶች መንገዱን የቀየሰና

አቅጣጫውን ያመላከተ ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡ ይህ ፌስቲቫል በሰሜን ምስራቅ ጣልያን የምትገኘውና118 ደሴቶችን በማካተቷና ከባህር ወለል እኩል በመገኘቷ ``«የውሃዋ ላይ ከተማ» እንዲሁም በትናንሽ ጀልባዎች በሻማ ብርሃን በሚደረጉ

የቱሪስት ሽርሽሮቿ «የፍቅር ከተማ » ተብላ የምትጠቀሰው ቬኒስ ለአለም ማህበረሰብ ያበረከተችውና በየአመቱ ከነሃሴ መጨረሻ እስከ መስከረም መጀመሪያ ድረስ የሚካሄድ ዝግጅት ነው፡፡

ወደ አመሰራረቱ ስንመጣ እ.ኤ.አ ከ14ኛው -17ኛው ክፍለዘመን የአውሮፓ ስነ ጥበብ ማእከል የነበረችው ጣልያን ዋና የገበያ ማእከል ሆና ስታገለግል የቆየችው ቬኒስ ከተማ ቀስበቀስ የኢኮኖሚ ብርታቷንና እንዲሁም የስነጥበብ መዲናነቷን በሃያኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ እያጣች መምጣቷ ያሳሰበው የከተማው ከንቲባ ጁሴፔ ቮልፒ በወቅቱ እያቆጠቆጠ የመጣውን የተንቀሳቃሽ ፊልም ስራ ተመርኩዞ ከተማዋን ወደድሮ የስነጥበብ ማእከልነቷ እንዲሁም ኢኮኒሚዋን ም ከዚሁ በሚገኝ ገቢ ተመርኩዛ ለመገንባት ያሰበው ቮልፒ ይህንን ፌስቲቫል አዘጋጀ፡፡ በወቅቱ ለአንድ ጀማሪ ዝግጅት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 25 ሺህ ተመልካቾችን በማሳተፍ የተጀመረው ቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል ከሲኒማ ማሳያነት ወደ ሌሎች ስነጥበብ ዘርፎችም ተሸጋግሮ በአሁኑ ጊዜ እንደ ስዕል፤ዳንስ፤ስነ ህንጻ(architecture)፤ሙዚቃና ቴያትር ያሉ ዘርፎችን አካትቶ በነዚሁ ዘርፎች አንቱ የተባሉ ባለሙያዎች በጥንቃቄ ተመርጠው በአዘጋጆች በሚላክላቸው ግብዣ መሰረት እየተገኙ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት ታላቅ የስነጥበብ ድግስ ለመሆን በቅቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል በዘመናዊ የሲኒማ አሰራር ውስጥ የፊልም አተራረክንና የዳይሬክተሮችን ሚና እንደ አዲስ በመቅረጽ በ50ዎቹና በ60ዎቹ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣውን

የፈረንሳውያኑ new-wave እንዲሁም ሲኒማ የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍና ለማመላከት ያለውን ከፍተኛ አቅም በ40ዎቹ ውስጥ ብቅ ብሎ ያሳየው የጣልያውያኖቹ neo-realism የፊልም ቴክኒኮች ከህዝቡ ጋር በደንብ የተዋወቁበትና ያበቡበት

Page 13: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

13

8 ከፍተኛ የሞባይል ጥገና ስልጠና8 ሀርድዌር ኤንድ ሶፍት ዌር8 የኮምፒውተር ጥገና ስልጠና8 የፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና ስልጠና8 የሣተላይት ዲሽ ጥገናና ተከላ8 የቲቪ፣ ዲቪዲ፣ ቪሲዲ እና ዴክ ጥገና8 አዶቤ ፎቶሾፕ8 ቪዲዮ ኤዲቲንግ

በጥራትና በብቃት ያስተምራል! ስልጠናው በማታና በቀን ይሰጣል!

6ቅዳሜና እሁድ ስልጠና እንሰጣለን6በግል መማር ለሚፈልጉ ሰዓት እናመቻቻለን

አድራሻ፡- ቁ.1 ሻሸመኔ ፀጋዬ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.305 ቁ.2 አዋሳ ፒያሳ አሜን ህንፃ 3ኛ ፎቅ 0916-485828/0911-488594

ፊ ል ም

ወደ ገፅ 31 ዞሯል

ቦታ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡

ሽልማቶችየቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል በሽልማት ደረጃ

በቋሚነት እንዲሁም አልፎ አልፎ የሚሰጡ ሜዳሎች እንዲሁም ትናንሽ ሃውልቶች ሲኖሩት እነዚህም እንደ ደረጃቸው በሃያሲያን፤የፕሮግራሙ አዘጋጆች ወይም ተመልካቾች ከፍተኛ ድምጽ ላገኙት ፊልሞች በ ፌስቲቫሉ መጨረሻ እንደሚከተለው ቅደም ተከተል ይበረከታሉ፡፡

የወርቃማው አንበሳ (golden lion, leoned’oro) ሽልማት ይህ ሽልማት ክንፋማ አንበሳ ቅርጽ ያለው

ትንሽ ሃውልት ሲሆን መነሻውም አንዳንድ የታሪክ እንዲሁም የሃይማኖት ምሁራን እንደሚናገሩት የወንጌላዊው ማርቆስ(st.mark) ምልክት ነው፡፡ ይህ በቬኒስ ባንዲራ እንዲሁም በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኝ ምልክት በአንድ ወቅት በቬኒስ ከተማ ውስጥ አርፎ የነበረውን ይህን ወንጌላዊና የከተማዋ ነዋሪዎች ከሱ ጋራ አለን ብለው የሚያስቡትን ቁርኝት ይወክላል፡፡

የዚህ ወርቃማ አንበሳ ሽልማት እ.ኤ.አ ከ1949 ጀምሮ በፌስቲቫሉ ምርጥ ለተባለው ፊልም ሲሰጥ

የቆየ ሲሆን በሲኒማው ማሕበረሰብ ዘንድ በምድረ አሜሪካ ከሚሰጠው የኦስካር ሽልማት የበለጠ የብቃት ማረጋገጫ እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

የብርማው አንበሳ(silver lion,

leoned’argento) ሽልማትይህ የብርማ አንበሳ (silver lion)በጣልያንኛ

አጠራሩ leoned’argentoተብሎ የሚታወቀው ትንሽ ሀውልት በቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል ውስጥ በየአመቱ የሚሰጥ ስያሜው አንድ ይሁን እንጂ በውስጡ ብዙ ዘርፎችን ያካተተ ሽልማት ነው፡፡

ይህ ሽልማት በብዙ ዘርፎች እና ሁኔታዎች

ላይ ለብዙ አመታት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን በሚከተሉት የሙያና የውድድር ዘርፎች ላይ ተወዳድረው ላሸነፉ ፊልሞችና ባለሙያዎች ይሰጣል፡፡ እነዚህ ዘርፎችም

- ምርጥ ዳይሬክተር (best director)- ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልም ዳይሬክት ባደረገ

ባለሙያ የተሰራ ምርጥ የፊልም ስራ(best film by a debut director)

- ምርጥ የፊልም ስነጽሁፍ (best screenplay)- ምርጥ አጭር ፊልም (best short film)-ምርጥ ሲኒማዊ ክስተት (cinematic

revelation)( ማለትም በሲኒማ አሰራር ውስጥ አዲስ መንገድን የፈጠረ አዲስ ስራን ያሳየ) ናቸው፡፡

የቮልፒ ሽልማት(volpi cup)ይህ የቬኒስ ፊልም ፌስቲቫልን በፈጠረው ካውንት

ጁሴፔ ቮልፒ ዲ ሚሱራታ ስም የተሰየመውና ቀደም ሲል ታላቁ የወርቅ ሜዳሊያ በመባል የሚታወቀው የዋንጫ ሽልማት በአመቱ ከፍተኛ የትወና ችሎታ ላሳዩ ወንድና ሴት ተዋንያን ይሰጣል፡፡

የዳኞች ልዩ ሽልማት (special jury prize)

ይህ የዳኞች ልዩ ሽልማት በአመቱ ውስጥ ከታዩ ፊልሞች ምርጡ ለተባለው ስራ የሚሰጥ ሲሆን ቀደም ብለን ካየነው ከወርቃማ አንበሳ(golden lion) ሽልማት የሚለየው ግን የወርቃማው አንበሳ ሽልማት የሚሰጠው በዳኞችና በተመልካቾች ድምር ድምጽ አሸናፊ ለሆነው ፊልም ሲሆን ይህ ሽልማት ግን ዳኞች በግላቸው ጥሩ የስነጥበባዊ ክህሎት ታይቶበታል ብለው የ ሚ ያ ም ኑ በ ት ን ስራ ከተመልካቾች ተጽእኖ ነጻ ሆነው የሚመርጡበት መድረክ

ነው፡፡ ይህ ሽልማት በአንዳንዶች ዘንድ በፌስቲቫሉ

ከሚሰጠው የወርቃማ አንበሳ ሽልማት ያነሰ ማእረግ እንዳለው ተደርጎ ቢቆጠርም እድሉን አግኝተው በእጃቸው የጨበጡት ፊልሞች ግን ከሌሎቹ የላቁ መሆናቸውን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡

The golden osella prize ይህ ሽልማት በቬኒስ ፊልም ውስጥ በየአመቱ

የሚሰጡ የሚከተሉትን ዘርፎች የሚያካትት ሲሆን በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያዊው ሃይሌ ገሪማ በ2008 ዐ.ም በጤዛ ፊልሙ ምርጥ የስክሪን ጽሁፍ ያሸነፈበት እንደመሆኑ ለሃገራችን የፊልም ተመልካቾች አዲስ አይደለም፡፡

በአቀራረብ ደረጃም እንደ ሌሎቹ ውድድሮች በተከታታይ ሳይሆን እንደአስፈላጊነቱ ይካሄዳል፡፡ በ(golden osella) ውስጥ የሚገኙት የውድድር ዘርፎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

• ምርጥ ዳይሬክቲንግ(Best directing)፡- በዚህ ዘርፍ የሚሰጠው ሽልማት ከብርማው አንበሳ ባነሰ ማእረግ እንደሆነ ልብ ይሏል

• ምርጥ የስክሪን ጽሁፍ(Best screen writing)

• ምርጥ ሲኒማቶግራፊ• ምርጥ ስነጥበባዊ አስተዋጽኦ(Best

technical contributions)• ምርጥ የቀረጻ ቦታ ዲዛይን(Best set

design)• ምርጥ ወጥ የሙዚቃ ማጀቢያ(Best

Page 14: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

14

አድራሻ፡- ፖፕላሬ ፀለረ ህንፃ ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ ስልክ፡- 011-6-555030/ 0911-252212/0911-196757

,የመኪና ወንበርና ምንጣፍ ሥራ,የዳሽ ቦርድና የኮርኒስ ሥራ,የቤትና የቢሮ ወንበሮች ሥራና ጥገና

ካሳሁን ለማ የመኪና ወንበሮች ሥራ

ትዕዛዝ ካለ24 ሰዓትእንሰራለን!

ፋስት ፉድ ፈጣን የሰውነት

ዕድገት ቢያስገኝም የአእምሮ ዕድገት ያበዛል ተባለ

በአሜሪካ ህፃናት ፋስት ፉድ አድናቂ ናቸው፡፡ ይህ በደቂቃ ተዘጋጅቶ በደቂቃ ለተመጋቢ ቀርቦ በደቂቃ ውስጥ የሚጠናቀቀው ፋስት ፉድ የህፃናትን ሰውነት በፍጥነት የሚያሳድግ ቢሆንም በአእምሮ ዕድገታቸው ላይ ያለው ተፅዕኖ ከባድ እንደሆነ ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡

በህፃናት የፋስት ፉድ የአመጋገብ ልምድ ላይ ጥናት ያደረጉት የአሜሪካ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎች በጥናታቸው የህፃናቱን የአመጋገብ ልምድና የማስተዋል ደረጃቸውን በዝርዝር ፈትሸዋል፡፡

በዚህም መሠረት ዕድሜያቸው ከ4-5 ዓመት በሆናቸው 4ሺህ በሚሆኑ የፋስት ፉድ አፍቃሪ ህፃናት ላይ የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ በየዕለቱ ፈጣን ምግብ የሚመገቡ ህፃናት ከማይመገቡት ህፃናት በሰውነት አቋማቸው ገዝፈው ሲገኙ በአእምሮ ዕድገታቸው ግን አንሰው ተገኝተዋል፡፡

በጎልድ ስሚዝ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው የተመራማሪዎቹ የጥናት ውጤት በመጨረሻ እንዳስገነዘበው ወላጆች ለልጆቻቸው ፋስት ፉድ እንዲመገቡ በብዛት ከመፍቀድ ይልቅ ኦርጋኒክ የሆኑ በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ምግቦችን ቢመግቧቸው የማስተዋል ችሎታቸው ይጨምራል፡፡

ሥነ ልቦና

ዜና ቴክኖ

በየዕለቱና በየሰዓቱ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች መረጃ የሚለዋወጡበትና የሚዝናኑበት ፌስ ቡክ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር እያሻቀበ ነው፡፡ ሰሞኑንም የፌስ ቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ ይፋ እንዳደረገው የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፁ ተጠቃሚዎች ቁጥር አንድ ቢሊዮን ደርሷል፡፡

ከኤንቢሲ ጋር ልዩ ቃለ ምልልስ ያደረገው ዙከርበርግ ገና ከተመሰረተ የ8 ዓመት ዕድሜ ያለው ፌስ ቡክ ባለፈው ዓመት ብቻ ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን በዓለም ዙሪያ አግኝቷል፡፡

‹‹ማንኛውም ሰው ከቤቱ ወደ ሥራ ቦታ ወይም ወደ ት/ቤት ሲሄድ ከሚያያቸውና ከሚያገኛቸው ሰዎች የበለጠ በኮምፒውተሩ

ማይክሮ ሶፍት የራሱን የሞባይል ስልክ ሊያመርት ነው

የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር 1 ቢሊዮን ደረሰ

የዓለማችን ግዙፉ የሶፍት ዌር አምራች የሆነው ማይክሮ ሶፍት በቅርቡ ለገበያ ያቀረበውን የWindows 8 ኦፕሬቲንግ ሲስተምን የያዘና የሚያስተዋውቅ አዲስ የሞባይል ስልክ እንደሚያመርት አስታወቀ፡፡

ፈጣን የኮምፒውተር ሥራ ለመስራት የሚያስችለውና የWindows 8 ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይጫኑለታል የተባለው አዲሱ የማይክሮ ሶፍት ሞባይል ሙሉ ለሙሉ የኮምፒውተርን አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ እንደሚመረት The telegraph ዘግቧል፡፡

ማይክሮሶፍት የሚያመርተውን የWindows 8 ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለማስጫን የኖኪያ የሳምሰንግ ስልክ አምራች ኩባንያዎች ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ስልክና ኮምፒውተርን በአንድነት የያዘው አዲሱ የማይክሮሶፍት ስልክ በመጪው የፈረንጆች አዲስ ዓመት ለገበያ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ብቃት ባላቸው ባለሙያዎቻችን

ላይ ይጠብቁታል‹‹ ያለው ዙከርበርግ ‹‹ይህም የፌስ ቡክን አስፈላጊነትን ያሳያል›› ብሏል፡፡

ፌስ ቡክ ለህዝብ አክሲዮን መሸጥ ከጀመረበት ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ወዲህ ከፍተኛ እመርታ እያሳየ ሲሆን ለዚሁም የፌስ ቡክ መላ ሠራተኞችንና ማኔጅመንቱን ዙከርበርግ አመስግኗል፡፡

ባለፈው ዓመት ፌስ ቡክን ከተቀላቀሉ 200 ሚሊዮን ሰዎች መሀከል 100 ሚሊዮን ፌስ ቡክን በሞባይል የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ ‹‹በዓለም ዙሪያ ከ5 ቢሊዮን በላይ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች አሉ›› ያለው ዙከርበርግ እነዚህን ሰዎች በሙሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ የማድረግ ዓላማ አለን ብሏል፡፡

Page 15: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

15

ማን ምን አለ? ከሰሞኑ

ZEWDITU FASHION DESIGN TRAINING CENTER

ዘውዲቱ የፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ ተቋም

የስልጠና መስኮች- የባህላዊና ዘመናዊ የስፖርት ልብስ ቅድና ስፌት- የዕረፍት ጊዜ ልብስ ቅድና ስፌት- የልጆች ልብስ ቅድና ስፌት- የሥራ ልብስ ቅድና ስፌት- የሀገር ባህል ልብስ ቅድና ስፌት- የውጪ ባህል ልብስ ቅድና ስፌት- የዩኒፎርም ልብስ ቅድና ስፌት- የጌጣ ጌጥ ጥልፍ ስራ- የዲዛይን ንድፈ ሀሳብና ተግባራዊ ትምህርት- የማሽን አያያዝ አጠቃቀም ትምህርት

አድራሻ፡- ለማንኛውም መረጃ በአድራሻችን ይደውሉ ቁ.1 ስድስት ኪሎ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ፊት ለፊት

ቁ.2 ፒያሳ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊትስልክ፡- 251-1-11232561/ 117452

ሞባይል፡- 0911-231515/0930-013394E-mail:- [email protected]

የሥራ ልምድ ባለው ማሰልጠኛችን ክህሎትዎን በትምህርት ያበልፅጉ

33ዓመት

TEN MONTHS CERTIFCATEThe First fashion Design center In Ethiopia Courses are- FAHION DESIGN - EMBROIDERY- INTERIOR DESIGN

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካም አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ነው፤ ወደ ግል አየር መንገድ ስንመጣ ግን እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ ነው ያለው፡፡ እዚህ ጎረቤታችን ካለችው ኬኒያ ጋር እንኳን መወዳደር አንችልም፡፡ በኬኒያ 56 የግል አየር መንገዶች ከ800 በላይ አውሮፕላን አላቸው፡፡ ቦይንግ አውሮፕላን ያላቸው የግል ተቋማት ሁሉ አሉ፡፡

ካፒቴን ሰለሞን ግዛው የአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት ባለቤት ለፋና ኤፍ ኤም

98.1 ኦቶሞቲቭ ጆርናል ፕሮግራም ላይ የተናገረው፡፡

‹‹ባለስልጣኑ በአንድ አይን ቢያይ ጥሩ ነው››

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግላቸውን የመገናኛ ብዙሃን ተቋሞች በአንድ አይንና በአንድ ሚዛን ቢመለከት ጥሩ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚዛን አለመስተካከል ይታይበታል፡፡

ጋዜጠኛ ተፈሪ አለሙ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የፕሮግራም ኃላፊ

መገናኛ ብዙሃን ለተሰኘው የብሮድካስት ባለስልጣን መፅሔት የገለፀው፡፡

‹‹የኢትዮጵያ የግል አየር መንገድ እድገት ያሳዝናል››

በአሜሪካ ኢትዮጵያዊው ታክሲ ሹፌር 21 ሺህ ዶላር ለባለቤቱ መለሰ

ኢትዮጵያዊው የታክሺ ሹፌር አዳም ወ/ማርያም በአሜሪካ ላስቬጋስ በታክሲ ማሽከርከር ስራ ነው የሚተዳደረው፡፡ ሰሞኑን በታክሲው ተሳፍሮ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ሊሄድ የፈለገ አሜሪካዊ ወደ ታክሲው ሲገባ 21 ሺህ 500. 10 ዶላር በቦርሳው ውስጥ ይዞ ነበር፡፡

አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ግን ግለሰቡ ቦርሳውን እረስቶ ነበር የወረደው፡፡ በወቅቱ አዳም የታክሲ ስራውን በፈረቃ ይሰራ ስለነበር ከሰዓት በኋላ ታክሲውን ሲረከብ በቦርሳው 21 ሺህ 500.10 ዶላር ነበር ያገኘው፡፡ በታክሲው

ውስጥ የተረሳው ብር የጓደኛው መስሎት ሲጠይቀው የእሱ አለመሆኑን ሲያውቅ ጉዳዩን ወዲያውኑ ያሳወቀው ለላስቬጋስ ፖሊስ ነበር፡፡

ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ምርመራ ሲያደርግ ጠዋት በታክሲ ተሳፍሮ የገንዘብ ቦርሳ እረስቶ የወረደውን ሰው ያገኘዋል፡፡ በዚህ መሰረት አዳም ቦርሳውን ይዞ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ሲያስረክብ የገንዘቡ ባለቤት ፖሊስ ጣቢያ ይጠብቀው ነበር፡፡ በሁኔታው የተደሰተው አሜሪካዊ ጠፍቶ ከነበረው ብር ላይ 2000 ዶላር ወረታውን ከፍሎታል ሲል ጆርናል ሪቪው ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

‹‹ሀገሬ እዚሁ ቁጭ ብዬ እንኳ ትናፍቀኛለች››ሀገሬን በጣም ነው የምወዳት

እዘሁ ተቀምጬ እንኳን በጣም ነው የምትናፍቀኝ፡፡ ከሀገሬ ብወጣ ለሁለት ሰዓታት እንኳን መቆየት የምችል አይመስለኝም፡፡

አርቲስት ትዕግስት ግርማ በአርሂቡ ፕሮግራም ላይ ቀርባ የተናገረችው

‹‹300 መቶ የሀበሻ ቀሚስ

አለኝ››የፈረንጅ ልብስ ቤቴ የለም፡፡ እስከ ዛሬ

ድረስ ሱሪ ለብሼ አላውቅም፡፡ ገንዘቤን የጨረሰው የሀበሻ ልብስ ነው፡፡ ቤቴ ውስጥ 300 የሀበሻ ቀሚስ አለ፡፡ አሁን እንደውም እየተጨመረ ነው፡፡

ድምፃዊ ማሪቱ ለገሰ ሁሌም ያለ ሀገር ልብስ መድረክ ላይ ወጥታ እንደማታውቅ

ተጠይቃ የተናገረችው

Page 16: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

16

ቁም ነገር፡- ከሰባት ዓመት በኋላ ነው በሙሉ አልበም የመጣኸው?

ሚካኤል፡- ልክ ነህ፡፡ቁም ነገር፡- 7 ዓመት እንዴት

አለፈ?ሚካኤል፡- በውጣ ውረድ /ሳቅ/

የመጀመሪያ ካሴቴን ያወጣሁት 97 ክረምት ላይ ነው፤ በደንብ የተሰማው ግን 98 ነው፡፡ ከዚያ በ2001 ሁለተኛ አልበሜን ለማውጣት ነበር እቅዴ አልሆነም፤ ከዚያ በኋላ እንደውም ከአንድ ዓመት በላይ በሀዘኑ ምክንያት ሙዚቃ አልሰራሁም፡፡፡

ሚካኤል በላይነህ ‹‹ማለባበስ ይቅር›› በተሰኘው ስለ ማግለል የሚሰብከው ህብረ ዝማሬ ላይ በዜማ ድርሰትና በድምፃዊነት በመሳተፍ ነው ከአድማጭ ጋር የተዋወቀው፡፡ በይበልጥ የሚታወቀው ግን ‹‹የፍቅር ምርጫዬ›› በተሰኘውና የፍቅረኞች ብሔራዊ መዝሙር ሊሆን በተቃረበው ለስላሳ ዜማው ነው፡፡ ‹‹አንተ ጎዳና›› ከተሰኘው ተወዳጅ አልበሙ በፊት ‹‹መለያ ቀለሜ›› የተሰኘ በፒያኖ የታጀበ የመጀመሪያ አልበም የሰራው ሚካኤል በቅርቡም ሶስተኛ አልበሙን እንካችሁ ብሎናል፡፡ ስለ አልበሙና ስለ ግል ህይወቱ ሚኪ እንዲህ ይላል. . .

ቁም ነገር፡- በዚያን ጊዜ አሜሪካ ነበርክ፤ እንዴት አለፈ?

ሚካኤል፡- ለማረፍ ነበር የሄድኩት፡፡ ከባድ ጊዜ ነበር፤ ለሶስት ወር ነበር የሄድኩት ግን ስሜቴን ሳየው ተጨማሪ ጊዜ መቆየት ነበረብኝ፡፡ ለመቆየት ከወሰንኩ በኋላ ደግሞ ቁጭ ከምል ብዬ በኢንተርኔት የሙዚቃ ትምህርት መማር ጀመርኩ፡፡

ቁም ነገር፡- የት?ሚካኤል፡- በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ

የሙዚቃ ቲዎሪ ትምህርት ነው ተምሬ የመጣሁት፡፡

ቁም ነገር፡- መድረክ አልሰራህም?

ሚካኤል፡- አልሰራሁም፡፡ ተጠይቄ ነበር፤ ግን ሙዚቃ ለመስራት በሚያስችል ሙድ ላይ አልነበርኩም፡፡ የኛንም የፈረንጆችንም አዲስ ዓመት ያሳለፍኩት እዚያ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- ከሀዘኑ በኋላ ቶሎ ወደ ሙዚቃው ለመመለስ አልተቸገርክም?

ሚካኤል፡- የራሱ የሆነ ተፅዕኖ አለው፤ ግን ከሙዚቃ አልተለየሁም፡፡ አሜሪካ ሀገር እንደሄድኩ እንደውም መጀመሪያ ያደረኩት ነገር ኪቦርድ መግዛት ነበር፡፡ ጥሩ ስሜት ላይ ስሆን

አንዳንድ ዜማዎችን እሰራ ነበር፡፡ቁም ነገር፡- በወቅቱ ለአዲሱ

አልበምህ የሰራሃቸው ስራዎች አሉ?ሚካኤል፡- ብዙዎች ዜማዎች

የሰራኋቸው በፊት ነው፡፡ አሜሪካ ሄጄ የሰራኋቸውም አሉ፡፡ የአልበም ስራውን ከጀመርኩ በኋላም የሰራኋቸው ዜማዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ትመጪ እንደሆን፣ ስንዋደድ፣ ቃል ነበረ፣ ቅርብ ጊዜ የተሰሩ ናቸው፡፡

ቁም ነገር፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራኸው ዜማ የቱ ነው?

ሚካኤል፡- ለመጀመሪያ ጊዜ

የሰራሁት ‹‹ሙሽራዬ›› የሚለውን ዜማ ነው፡፡

ቁም ነገር፡- እንዴት ሰራኸው፤ በአጋጣሚ ወይስ ሠርግ ነበረብህ?

ሚካኤል፡- ለአንድ ጓደኛዬ ሠርግ ነው የሰራሁት፡፡ ሂልተን ነበር ሠርጉ ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር በፒያኖ ነው ዘፈኑን የተጫወትኩት፡፡ ጥሩ ተቀባይነት ነበረው፡፡

ቁም ነገር፡- ዜማ መስራት እንደምትችል አመላክቶሃል ለማለት ቻላል?

ሚካኤል፡- ይቻላል፤ ግን የዚያን ጊዜ እኮ ተወሰኑ ዜማዎችን ሠርቼ ኤልያስ ጋር ነበሩኝ፡፡ ኤልያስ ሰምቶ ጥሩ አስተያየት ስለነበረው ዜማ መስራት እችላለሁ የሚለውን ነገር ውስጤ ነበር፡፡ የፍቅር ምርጫዬ የሚለው ዘፈን ሁሉ እኮ የዚያን ጊዜ ሳልሰራው እቀራለሁ ብለህ ነው?

ቁም ነገር፡- ብዙዎች አርቲስቶች ግጥምም ዜማም ይሰራሉ፤ አንተ ግን ዜማ ብቻ ነው የምትሰራው፤ ግጥም አትሞክርም?

ሚካኤል፡- ግጥም ከልጅነት ጀምሮ እየዳበረ የሚመጣ ነገር ይመስለኛል፡፡ ክህሎት ብቻ ሳይሆን የሥነ ፅሁፍ ልምድም የሚፈልግ ይመስለኛል፡

ሙዚ ቃ ና ሙ ዚ ቀ ኞ ች

‹‹ስሜቴን መግለፅ የምችለው በምሰራው

ዜማ ነው››

Page 17: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

17

የአቡልኸይርABBULHAIR’S

ሰውዲ ረዲSEWDA REDI

ወቅታዊና አዳዲስ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ ቦርሳዎችና የሌሊት ልብሶችን አስመጥተናል፡፡ መጥተው ይጎብኙን!!

አዳዲስ የሰርግ አልባሳትን አስገብተናል፡፡ እንዲሁም የክረምት ልብሶች አሉን፡፡

የተዘጋጁ ልብሶችና ጫማዎችReady Made Clothes & Shoes

አድራሻ፡- ፒያሳ ከአራዳ ህንፃ ፊት ለፊት ከዶን ዴንታል ክሊኒክ ከፍ ብሎAddress:- Piazza Infront of Arada Building, Near to Don Dental Clinik

Tel. 011-1-577273 Fax 251-1-566081/ P.O.box 22096 A.A

፡ የኔ ልምድ ወደ ዜማው ነው፡፡ ስሜቴን መግለፅ የምችለውም በምሰራው ዜማ ነው፤ ግን ግጥምንም እሰማለሁ አደንቃለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ዘፈንን ዘፈን የሚያደርገው ግጥሙ ነው ወይስ ዜማው ነው?

ሚካኤል፡- ዘፈንን ዘፈን የሚያደርገውማ ዜማው ነው፡፡ ዜማ የሌለው ግጥም እኮ መድብል ነው፡፡ ልክ በመፅሐፍ ታትሞ የሚቀርብ ማለት ነው፡፡ ለዘፈን ዜማ አስፈላጊ መሆኑን የምታውቀው የማታውቀውን ቋንቋ ዘፈን ስትሰማ ትወደዋለህ፤ ግጥሙን ሰምተህ አይደለም የምትወደው፡፡ የሚስብህ ዜማው ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ኦሮምኛ ቋንቋ አልችልም ግን የአሊቢራን ዘፈኖች በጣም ነው የምወዳቸው፡፡ የዘፈኑን መልዕክት አውቄው አይደለም፡፡ የወደድኩት ዜማው ነው የሚስበኝ፡፡ ስለዚህ አንድን ዘፈን ዘፈን የሚያደርገው ዜማው ነው፡፡ ግጥሙ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ግጥም ይዘህ ዜማ ትፈጥራህ ወይስ ዜማ ሰርተህ ነው ግጥም የምትፈልገው፤ ሙድህ እንዴት ነው?

ሚካኤል፡- ይሄ ነው የሚል ነገር የለኝም፡፡ ዜማ ሰርቼ ግጥም የምፈልግላቸው ስራዎች አሉ፤ ግጥሙን አይቼም ዜማ የምፈጥርላቸው ሥራዎች አሉ፡፡ እንደሁኔታው ነው፤ የሚገርምህ ግን በአሁኑ አልበሜ ላይ ግጥማቸውን የሰሩልኝ ልጆች በሙሉ ግጥማቸውን የፃፉት የኔን ዜማ ሰምተው አይደለም፡፡ ግጥሙን ሰጥተውኝ አይቼው ነው ዜማ የሰራሁላቸው፡፡

ቁም ነገር፡- ብዙ ሰዎች የመጀመሪያ አልበምህን መለያ ቀለሜ ሳይሆን፤ ‹‹አንተ ጎዳና››ን አድርገው ነው እንዲህ አይነት አስተያየት አላጋጠመህም?

ሚካኤል፡- አዎ የመጀመሪያ ሥራዬ ግን ‹‹መለያ ቀለሜ›› ነው፤ ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር በፒያኖ የተጫወትኩት አልበም ነው፡፡ አልበሙ የወጣው በ1995 ዓ.ም ነው፤ ትልቅ ፕሮጀክት ነበር ሰራው እንኳን አንድ ዓመት ወስዶብናል፡፡ ለማስመረቅ ደግሞ ወደ 6 ወር ወስዷል፡፡ በዚህ መሀል አንተ ጎዳና አልበም ሳይወጣ እነ ማለባበስ ይቅርን ነጠላ ዜማ ሰርቼ ከህዝብ ጋር በደንብ የተዋወቅሁት፡፡

ቁም ነገር፡- የዛሬ 8 እና 9 ዓመት ገደማ ትዝ ይልህ ከሆነ ጥሩ ጥሩ ግጥሞችን መርጠህ

የግጥም ንባብ መድረክ በቋሚነት ለማዘጋጀት ሀሳብ እንዳለህ አጫውተኸኝ ነበር፤ ያ ሀሳብ ምን ደረሰ?

ሚካኤል፡- ልክ ነህ፤ ያ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የቢዝነስ ሀሳቦች ነበሩኝ፡፡ በወቅቱ ከመለያ ቀለሜ አልበም በኋላ ሁኔታዎች አስቸጋሪ እንደሆኑ ነው ያየሁት ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ የማስባቸው የቢዝነስ ሀሳቦች አሉኝ፡፡ ግን የሙዚቃ ስራ አንድ ጊዜ ከገባህበት ሌላ ቢዝነስ ለመስራት ያስቸግራል፡፡ ሙሉ ጊዜ የሚፈልግ ሙያ ነው፡፡ በውጪው ዓለም ሀሳብ ካለህ አንተ የግድ ስራውን መስራት የለብህም ለሚሰሩ ልትሰጠው ትችላለህ፤ እኛ ሀገር ግን ሀሳብ ብቻውን የመሸጡ ጉዳይ አስተማማኝ ስላልሆነ ይዢያቸው የተቀመጥኩት ሀሳቦች አሁንም አሉኝ፡፡

ቁም ነገር፡- ከአዲስ አልበም በኋላ በየመድረኮች መጋበዝና መዝፈን የተለመደ ነው፤ አንተ ግን ብዙ መድረኮች ላይ አትታይም ለምንድነው?

ሚካኤል፡- በመጀመሪያ ደረጃ መድረኮችን እመርጣለሁ፤ እዛም እዛም በሚዘጋጁ መድረኮች ላይ ስጠራ መዝፈን አልፈልግም፡፡

ቁም ነገር፡- ለምን?ሚካኤል፡- ምክንያቱም ሙዚቃ በቂ ዝግጅት

ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ደውዬልህ ነገ ዝፈንልኝ ልልህ አይገባም፡፡ በዚያ ላይ ሁለት ዘፈን ብቻ እኮ ነው የምትዘፍነው ልትባል ትችላለህ፤ የሙዚቃ ስራ የአንድና የሁለት ዘፈን ጉዳይ መሆን የለበትም፡፡ በቂ ዝግጅት በቂ ልምምድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በላይ ደግሞ በቂ መሳሪያና ተጫዋቾች ሊኖሩ ይገባል፡፡ ቢያንስ 4 ሙዚቀኞች መኖር አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ ሊድ ጊታር፣ አንድ ቤዝጊታር ኪቦርድና ሳክስ ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ በሌሉበት በአንድ ኪቦርድ ብቻ ምን አይነት ሙዚቃ እንዲሰራ እንደሚፈለግ አላውቅም፡፡ በቅርቡ ኮንሰርቶች ይኖሩኛል እዚያ ላይ በሙሉ ባንድ ነው የምንሰራው፡፡

ቁም ነገር፡- ባንድ ነበረህ? ዘመን ባንድ የማነው?

ሚካኤል፡- ከጓደኞቼ ጋር በጋራ የመሰረትነው ባንድ ነበር፡፡ ባንዱ አሁንም አለ፡፡ የዛሬ 4 እና 5 ዓመት ኦሎምፒያ መውጫ ላይ የሚገኘው

ወደ ገፅ 33 ዞሯል

ሙ ዚ ቃ ና ሙ ዚ ቀ ኞ ች

Page 18: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

18

በቅድሚያ ስላደረጋችሁልኝ አቀባበል ከልብ አመሰግናለሁ እግዚአብሄር ይስጥልኝ፡፡ ዩኒፎርም ለብሼ ለአስር ዓመት በዚህ ትምህርት ቤት ተምሬያለሁ፤ ከኬጂ እስከ ስምንተኛ ክፍል ኬጂ A ፣ፕራይመሪም Aነበርኩ፡፡ በዚህ መሀል ብዙ ነገር ተምሬያለሁ፡፡ ትምህርት ቤታችን የጨዋ ተማሪዎች መገኛ ነበር ፡፡ ተማሪና አስተማሪ ይከባበራል፡፡ የቤተሰብ አይነት ግንኙነት እርስ በእርስ ነበረን፡፡ አሁንም እንደዛ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጎማ ሁላችንም ቀምሰናል፡፡ ቲቸር አንማው አማርኛ፣ ቲቸር ብርሀኑ ሂሳብና ህብረት፣ቲቸር ሳባ ጂኦግራፊ አስተምረውኛል ፡፡ ቲቸር ንጉሴ ደግሞ በእኛ ጊዜ ስፖርት አስተማሪ ነበሩ፡፡አሁንም ስፖርት መምህር ናቸው መሰለኝ ፡፡

- በተረፈ ለተማሪዎች የማስተላልፍላችሁ መልዕክት ቢኖር የምታስቡት ቦታ ለመድረስ ትምህርት ትልቁ መሰረት መሆኑን ነው፡፡በትምህርታችሁ መበርታት አለባችሁ፡፡ ትምህርት የምትፈልጉበት ቦታ የምትደርሱበት መንገድ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው አውቶቢስ ተሳፍሮ ከሆነ ወዳሰበበት ቦታ እንደሚደርስ እናንተም የተሳፈራችሁበት ትምህርት ቤት የሚያደርሳችሁ ወደ ፊት ወደምትደርሱበት

ቴዲ አፍሮ የድሮ ትምህርት ቤቱን ጎበኘስፍራ ነው፡፡

- ከዚህ ትምህርት ቤት ብዙ የህክምና ዶክተሮች ብዙ ተመራማሪዎች በውጭ ሀገር ያሉና የማውቃቸው አሉ፡፡ እናንተም ከእዚህ መሀል እንደምትሆኑ አስባለሁ፡፡ ስትማሩ ማወቅ ያለባችሁ ሁሉም ተማሪ ጎበዝ መሆን እንደማይችል ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ደካማ ሊሆን ይችላል፡ በትምህርታቸው ደካማ የሆኑትን መርዳትና ማሳየት ይጠበቅባችኋል፡፡በተረፈ የስፖርትም ሆነ የሙዚቃ ዝንባሌ ሲኖራችሁ እንዲደግፏችሁ አሳስባለሁ፡፡ምክንያቱም ዝንባሌ ከተፈጥሮ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይሄንን አጠንክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡

- እኔ በስራአስኪያጄ በኩል ወደፊት

ዓላማ አድርጌ እግዚአብሄር ረድቶኝ እንድፈፅመው እለምናለሁ፡፡ለትምህርት ቤታችሁ ጊታር፣ኪቦርድ ፣የሙዚቃ መሳሪያ አዘጋጅቼ ጊዜው ይሄ ነው ብዬ ባልናገርም አዘጋጅቼ ለመስጠት ቃል እገባለሁ፡፡ አሁን ካለንበት ህንጻ ስር አንድ ደረጃ ወርዶ አንድ ክፍል አለ፡፡ ድሮ ሰይጣን ቤት ነበር የምንለው ዴስክ ማስቀመጫ ነበር፡፡ ከበፊት ጀምሮ እመኝ የነበረው ክፍሉን አፅድቶ የሙዚቃ ዝንባሌ ላላቸው ተማሪዎች መለማመጃ ማድረግ ነው፡፡ ጥሩ ሙዚቀኛ ለመሆን ጥሩ ተማሪ መሆን ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን ደረጃ እግዚአብሄር በረዳኝ መጠን የደረስኩበት ደረጃ አለ፡፡ ሙዚቃው ላይ ደግሞ ትምህርት ብጨምር ኖሮ የበለጠ መሄድ እችል ነበር፡፡ እንደነ አበጋዝ ሙዚቃን ኮሌጅ ገብቶ መማር ኢትዮጵያ በሙዚቃ ትምህርት ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ ትምህርትን ከዝንባሌያችሁ ጋር አብሮ ለማስኬድ የሚረዳችሁ ለማድረግ ቃል እገባለሁ፡፡ በተለያየ ጊዜ ስራአስኪያጅ በረዳኝ መጠን መፅሀፍት ለመርዳት ወደ ኋላ አልልም፡፡ ከመምህራኖች ጋርም ያለኝን ግንኙነት ለማጠናከር እሞክራለሁ፡፡ አመሰግናለው እግዚአብሄር ይስጥልኝ፡፡

በልጅነቴ ከፍተኛ የሆነ የሙዚቃ ፍቅር ስሜት

ስለነበር በብዛት አድልቼ የነበረው በሙዚቃ ፍቅር ላይ ነበር፡፡ ነገርግን ከመካከላችሁ በትምህርቱ ደካማ ተማሪ ቢኖር የትም አይደርስም ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ እኔ ጎበዝ ተማሪ አልነበርኩም፡፡ ስለዚህ ማንም ልጅ ጎበዝ ሊሆን የሚችልበት እድል አለው፡፡

የምትወዳቸው መምህራን እነማን ነበሩ ለሚለው ጥያቄ የምወዳቸው ብዙ መምህራን ነበሩ፡፡ የበለጠ ግን የስነፅሁፍ የሙዚቃ ችሎታዬን ሊያበረታታልኝ የሚችሉትን አማርኛ መምህር የነበሩት አሁን ይኑሩ አይኑሩ ባላውቅም ቲቸር ስለሺ ፣ቲቸር ደምስ የሚባሉ በነገራችን ላይ ቲቸር ሀጎስ አሁን ሴንጆሴፍ ት/ቤት መሰለኝ ያሉት 5ኛ ክፍል እያለሁ የሳይንስ መምህር ነበሩ፡፡ የእሳቸውን ፈተና ሁል ጊዜ አስር ነበር የማመጣው የስነፅሁፍ የሙዚቃ ችሎታዬን ያበረታቱኝ ሰለነበር በእርሳቸው

ትምህርት በጣም ጎበዝ ነበርኩ፡፡ ቲቸር አንማውንም እንደዛው እወዳቸው ነበር፡፡ ሲፅፉ ልብ ብላችሁ ተመልክታችኋል? ሰሌዳ ላይ የእሳቸውን ፅሁፍ የሚያህል የለም አይደል? ቲቸር አንማው ጎበዝና ጥሩ የአማርኛ መምህር ነበሩ፡፡ ቲቸር ሳሚ ፣ቲቸር ንጉሴ ስፖርት ሰነፍ ተማሪ ካለ “ዱቄት” ነበር የሚሉት፡፡ ሌሎችም ብዙ አሉ፡፡

- የትምህርት ቤቱ ሁኔታ እንዴትነበር ለሚለው ጥያቄ እኔ በምማርበት ጊዜ ዩኒፎርም ነበረው ትምህርት ቤቱ፡፡ በዛን ጊዜ ውስን ትምህርት ቤቶች ነበሩ ዩኒፎርም ያላቸው፡፡አሁን የለበሳችሁት አይነት ዩኒፎም ያኔም ነበር፡ ሰኞ ሰኞ የሸሚዝ ንፅህና ይረጋገጥ ነበር፡፡ ፀጉሩ ፣ጆሮው ንፁህ ያልሆነ ፣ጥፍሩን ያልቆረጠ ልጅ ይቀጣል፡፡ እኔም ተመርጬ መርማሪ ሆኜ አውቃለሁ ፡፡ ብዙ ልጆችንም አስይዣለሁ፡፡ አስተማሪ በጣም እናከብር ነበር፡፡ የእጅ ኳስ ግጥሚያ ኖሮን ወደ ሌላ ትምህት ቤት ስንሄድ ወይም የሌላ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲመጡ በመካከላችን የሚታይ ሰፊ የስነ-ስርዓት ልዩነት ነበር፡፡ የትምህርት አሰጣጡና ጥራቱም ልዩ ነበር፡፡ ስፖርት በማንም ጊዜ 1ኛ Aነጭ ማልያ 1ኛB ቢጫ ፣1ኛC ቀይ ማልያ ነበረው፡፡ ስነ ስርአቱ እጅግ የተለየ ነበር፡፡ የምወደው ትምህርት አማርኛን ፣ሳይንስን እወድ ነበር፡፡ ከዚህ

ቴዲ አፍሮ አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘውንና እስከስምንተኛ ክፍል ድረስ የተማረበትን ቤተልሄም አንደኛና መለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰሞኑን ጎብኝቷል፡፡ የትምህርት ቤቱ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ከተማሪዎች ጋር ሆነው ደማቅ አቀባበል አድገውለታል፡፡ ቀድሞ በተማረበት ክፍል ከተማሪዎች ጋር የተወያየው ቴዲ ከተማሪዎች ለተነሱለት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቶ የመታሰቢያ ፎቶ ተነስቷል፡፡ ስለሙዚቃ ተሰጥኦ፣ ስለትምህርት አስፈላጊነት፣ስ ለመምህራን ዲሲፕሊን፣ ስለ ስፖርትና ስለልዩልዩ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ከዚህ በፊት 50 ኮምፒውተሮች ሰጠ ተብሎ ተነግሮ ሳይሰጥ ስለቆየበት ሁኔታም በአንዲት ተማሪ ተጠይቋል፤ ለድሮ ትምህርት ቤቱ 5 ኮምፒውተሮችንና የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡ ቴዲ በቤተልሄም ትምህርት ቤት ያደረገው ቆይታ ይህንን ይመስላል፡፡

Page 19: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

19

ሀሴት ህክምናዊ ስፖርት ማሳጅ ማዕከልበሀገራችን የመጀመሪያውና ብቸኛው ማዕከል በሰለጠኑ ባለሙያዎችና በዘመናዊ መሣሪያዎች በመታገዝ ሰውነትን በማሸትና በተመረጡ የአካል እንቅስቃሴዎች የሰውነትን ጤናና አቅም

በመመለስ ላይ ይገኛል፡፡

ለጡንቻና ለመገጣጠሚያ ህመም (ለአንገት፣ ለጀርባ፣ ለወገብ፣ ለዳሌ፣ ለጉልበት፣ ለቁርጭምጭሚት) ወዘተበእጅና በእግር ላይ ለሚያጋጥም የመደንዘዝና የመዛል ችግር በሥራ ጫና ለሚከሰቱ የሰውነት መወጣጠርና መዛል ለስፖርተኞች በልምምድና በውድድር ወቅት ለሚያጋጥሙ ጉዳቶችና ለመሳሰሉት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

አፋጣኝ መፍትሔ እንሰጣለንበተጨማሪም በህክምና ስፖርት ለታዘዘለቻው ታካሚዎች ተገቢውን የአካል

ብቃት እንቅስቃሴ እናሰራለን/ እናማክራለን

አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ ሰገን ሆቴል አጠገብ ረዊና ህንፃ ምድር ቤት ስልክ፡- 0911-429477/0920-018201

በተረፈ ለትምህርት ቤቱ ቃል በገባሁት መሰረት የሙዚቃ መሳሪያዎችን ዝንባሌው ላላቸው ልጆች ብርቱ ከሆኑ ማለትም መመዘኛው ትምህርት ላይ ጎበዝ መሆን መቻል አለበት፡፡ ይሄ ታይቶ ትምህርት ቤቱ ባወጣው ስርዓት መሰረት ዕድል ሰጥቶ የልጆቹን ዝንባሌ መጠበቅ አለበት፡፡

ከዚህ ቀደም እንደተባለው ጥያቄውን አስታውሳ ያነሳችው ተማሪ ጎበዝ አስተዋይ ነች፡፡ በተባለው ጊዜ ሊፈፀም ያልቻለበት ምክንያት አለ፡፡ ይኸውም ሃምሳ ኮምፒውተሮችን የገዛሁት ሳንሆዜ ነበር፡፡ ሳንሆዜ የሚገኘው ካሊፎርኒያ ውስጥ ነው፡፡ ወደዲሲ ከዲሲም ወደዚህ ለማምጣት አየር መንገድን ስፖንሰር ጠያቄ ነበር፡፡ ኮምፒውተሮቹ መጋዘን ውስጥ በየወሩ ለተቀመጡት እየከፈልኩ ብዙ ከቆየ በኋላ እስር ቤት ገብቼ ሳይመጣ ቀርቷል፡፡ ያንን ቃሉን ለመፈፀም ለትምህርት ቤታችን አሁን አምስት ኮምፒውተሮች በዛሬው ዕለት ለመስጠት ቃል እገባለሁ፡፡

- አንድ ሰው ከተሰጥኦ ጋር ነው የሚፈጠረው፡፡ እንዴት ነው ተሰጥኦውን ማሳደግ ያለበት ለሚለው ጥያቄ ማንም እናትና አባት ልጁ ትልቅ ቦታ እንዲደርስለት ይፈልጋል፡፡ እናትና አባት ልጄ የሚደርስበት መንገድ ይሄ ነው ብለው የወሰኑበት መንገድ አለ፡፡ ስለዚህ አባት በሚገፋና በሚቆጣችሁ ጊዜ ለእናንተ ስለሚያስብና የተሻለ ነገር አለ ብሎ የሚገምተው ነገር ስላለ ነው፡፡ አጋጣሚ ሆኖ የእኔ አባት ትምህርት ላይ ያለው አቋም ከፍተኛ ስለነበር በጣም ሀየለኛ ነበር፡፡ ትምህርቴ ላይ ከፍተኛ

ክትትልና ቁጥጥር ያደርግብኝ ነበር፡፡ ከእሱም መውደድና ለትምህርት ካለው ግምት አንጻር የመጣ ስሜት ነው፡፡ በዛው ነጠን እኔ ለሙዚቃ ያለኝ ስሜት ከፍተኛ ነበር፡፡ እንደምታውቁት አባቴ የሙዚቃ ባለሙያ ነበር፡፡ ዝግጅት በሚደረጉ ጊዜ ከመድረክ ጀርባ አብሬያቸው እሆናለው፡፡ ይሄንን መመልከቴ ተፅዕኖ አድሮብኛል፡፡ ከእዛ ጋር ተያይዞ በቀላሉ የምታስጠናኝ እየሩሳሌም መለሰ የምትባል ልጅ ነበረች፡፡ ሂሳብ ትምህርት ቶሎ አይገባኝም ነበር፡፡ እሷ ቀስ ብላ ስታስጠናኝ ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ ተረዳሁት ቶሎ፡፡” ትምህርት የመቀበል ተሰጥኦ አለህ ለምንድን ነው ጎበዝ ያልሆንከው” አለችኝ፡፡ አባቴም በነጋታው ወደትምህርት ቤት ይዞኝ እየመጣ እየሩሳሌም ስታስጠናኝ ቀስብላ ስለሆነ ቶሎ ገባኝ፡፡ ስለዚህ አባዬ ስታስጠናኝ ቀስ ብለህ አስጠናኝ አልኩት፡፡ አንድ ጊዜ ምን አደረገኝ መሰላችሁ? ወደ ትምህርት ቤት እያደረሰኝ ነበር፡፡ ቀኑ እሮብ ነበር፡፡ ማክሰኞ ማክሰኞ በቴሌቪዥን የሚታይ የህብረት ትርዒት ፕሮግራም አለ፡፡ እናም ይዞኝ እየተመለሰ ወደ ሙዚቃ እያደላሁ እንደነበር አውቋል፡፡ ሲያውጣጣኝ ጥላሁን ሲዘፍን እንዴት ነበር ይለኛል በስማም በጣም ቆንጆ ነበር አልኩት፡፡ አለማየሁ እሸቴስ ሲለኝ የእዛን ቀን አባቴን እንደወደድኩት መቼም ወድጄው አላውቅም፡፡ ከዛ ት/ቤት አድርሶኝ ሄደ፡፡

- አባቴ በልማድ የማውቀው ማታ 1ሰዓት ወይም ሁለት ሰዓት ወደ ቤት ሲመጣ ነው፡፡ የእዛን ቀን 12 ሰዓት መጥቶ ከጨዋታ ላይ ተጠራሁ፡፡ ስመጣ በጠዋት ሲያሳስቀኝ የነበረው ካሳሁን

ገርማሞ አንድ ትልቅ ሰሌዳና መግረፊያ ይዞ መጣ፡፡ “ዛሬ የተማርከው ምንድን?” ነው ሲለኝ ሳይንስ የተማርነው በስዕል ስለነበር ደስ ብሎኝ እሱን አቀረብኩ፡፡ እኔ የአርት ፍላጎት ስላለኝ ያስተዋልኩት ስዕሉን ነው፡፡”ይሄ በቀስት የተመለከተው ምን ይላል?”ፀጥ፡፡ “ይሄስ”?ፀጥ፡፡ “ጠዋት ግን ስለጥላሁን ገሠሠ ስጠይቅህ መልስህ ለጉድ ነበር” እያለ በጉማሬ ገረፈኝ፡፡ አባቴ በጣም ጨዋና ለትምህርት ከፍተኛ ጥንካሬና አቋም ያለው ሰው ነበር፡፡ አንድ ሰው ትልቅ ቦታ የሚደርሰው ዝንባሌውን ተከትሎ በሚደረገው የትምህር ት ድጋፍ ነው፡፡ በትምህርት ብደገፍ ኖሮ የበለጠ እሄድ ነበር፡፡ ከምንም በላይ የምመክራችሁ እናትና አባታችሁን መምህኖቻችሁን በደንብ ማክበር አለባችሁ፡፡ ትልቅ የምትሆኑበት መንገድ ይሄ ነው ከዛ በተረፈ ለትምህታችሁ ሰፊ ጊዜ ስጡ፡፡ ትምህርት የተማረ ሰው ትልቅ ሰው ይሆናል፡፡ ትምህርት ማለት ብርሀን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ መልዕክት ትምህርት ላይ ጎበዝ መሆን አለባችሁ፡፡

የቤተልሄም የቀድሞ ተማሪዎች በተለያየ አጋጣሚ አግኝቻለሁ፡፡ በሰርጌ ዕለትም እነዋለልኝ አደገ ፣እነፍፁም ብርሀኑና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡ አሜሪካ ሀገር ዲሲ ውስጥ ደረጄ ሙሉጌታ የሚባል እዚህ መምህርት እህት የነበረው ተማሪ አለ፡፡እሱና ፍስሀ አንድ ማህበር አቋቁመው ለመገናኘት ሞክረው ነበር ፡፡ ነገር ግን ከቦታ ቦታ ለስራ ስለምዘዋወር ከእነሱ ጋር ተገናኝቶ ለመስራት አልተመቻቸልኝም ነበር፡፡ ነገርግን ማህበሩ ተቋቁሞ ከእኔ የሚያስፈልግ ማንኛውም ድጋፍ ሲኖር በማንኛውም ሁኔታ ዝግጁ ነኝ፡፡

Page 20: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

20

አራምባና ቆቦ

ከመፅሐፍት

ትንግርትe በ17 54 ዓ.ም

ተወልደው በ1826 ዓ.ም የሞቱት ካፒቴን ጆን ዱግቲ በ1884 ዓ.ም የአሜሪካ የጦር ኃይል አዛዥ ነበሩ፤ በዚያን ዘመን የነበረው የአሜሪካ የጦር ኃይል ብዛት ሰማንያ ሰዎች ብቻ ያሉት ነበር፡፡

በጊንያ የሚገኝ ኬራስ የሚሉት አሳ ሌሊቱን የሚያሳልፈው በደረቅ መሬት ላይ በመተኛት ነው፡፡

በ950 ዓ.ም ተወልደው በ999 ዓ.ም የሞቱት በቱኒዚያ ውስጥ የካይሮዋን ሡልጣን የነበሩት አቤል ቃሲም ማንሱር አንድ ሌባ ወይም ዘራፊ በሚያዝበት ጊዜ እንዲገደልና ስጋውን ቤተሰቦቹ እንዲበሉት የሚል ደንብ አውጥተው ነበር፡፡

በመካከለኛው አፍሪካ ውስጥ የሚኖሩ የግራይ ጎሳ ሰዎች ሚስት ሲያገቡ ለሴቲቱ የጋብቻ ቀለበት የሚያስሩት የተጠመለለ ረጅም ሽቦ በክንዷ ላይ በማሰር ነው፡፡

ምንጭ፡- አስደናቂ ታሪኮች መፅሐፍ

አቤል ታሪኩ (ከአ.አ)

በጥቅምት - ዩኒቨርሲቲ ይከፈታል ምከረው ምከረው - እምቢ ካለ በአሸባሪነት ፈርጀው ምክር የደሃ ነበርሽ - ያለው ማነው ሌባ እናት - ልጇን ፖሊስ ጣቢያ አትልክም ከአፍ የወጣ - መተፋት አለበት

ሀገሬ ደምሰው /ከወላይታ/ከስራ ክፉ - መኪና ግፉአይን አይቶ - ልብ ደም ይረጫል የተናገሩት ከሚጠፋ - ማስታወሻ መያዝ ሞኝ ሲናገር - ብልጥ ያስተውላል ውሻ በቀደደው - ሾልኮ መውጣት

እዮብ ታምሩ (ከአዲስ አበባ)ላም ባልዋለበት - እረኛ የለምካፍ ከወጣ - ነገር ይመጣካልጠገቡ አይዘሉ - ካልሮጡ አያሸንፉቀን ያልፋል - ምሽት ይጨልማልሲሮጡ የታጠቁት - ጊዜ ቢያጡ ነው

ዘርጋው ይህ ዓለም (ካለሁበት)

የህሊና ፀሎት ተስፋ - መንግስተ እግዚአብሔር ነው፡፡ፈቃድ - የሀብት ድልብ ነው፡፡ፍቅር - ቅመም ነው፡፡ ሥራ - ኃይል ነው፡፡ መውደድ - ብርሃን ነው፡፡ ድፍረት - ዕድል ነው፡፡ ሀይማኖት - ፀጋ ነው፡፡ ፈገግታ - የሀዘን ማጠቃለያ ነው፡፡

ካርማኖ

- ሠጎን በሠዓት 70 ኪሎ ሜትር ትሮጣለች፡፡ ትንሽ አንጀቷ እስከ 46 ጫማ ይረዝማል፤ አንጎሏም ከአይኗ መጠን ያንሳል፡፡

- ግመል አጠገብዋ የሚቆጣ ሠው ካጋጠማት ትተፋለች፡፡- 75 ከመቶ የሚሆኑት የዱር እንስሳት ዕድሜያቸው ስድስት

ወራት ነው፡፡ - ፈጣኑ ዋናተኛ የሚል ስያሜ ያገኘው ሲል ፊሽ በሠዓት 109

ኪ.ሜ ይበራል፡፡ በተቃራኒው የባህር ፈረስ በሠዓት የሚጓዘው 0.016 ኪ.ሜ በመሆኑ ዘገምተኛው ዓሳ ይባላል፡፡

- የሠማያዊው አሳ ነባሪ የልብ መጠን አነስተኛ መኪናን ያህላል፡፡ የዚሁ እንስሳ የምላስ ርዝመት ከዝሆን ጋር እኩል ነው፡፡

- የአዞ ምላስ ከአፉ የላይኛው ጣሪያ ጋር የተያያዘ በመሆኑ መንቀሳቀስ አይችልም፡፡

- መልኳን የምትቀያይረው እስስት ብቻ አይደለችም፡፡ ዘላሊዋ እንቁራሪት በፀሐይ ብርሃን መልኳን አረንጓዴ ሠማያዊ ሲሆን በምሽት አረንጓዴ ይሆናል፡፡ በድቅድቅ ሌሊት ደግሞ ጥቁር ይሆናል፡፡

- ኪንግ ኮብራ የተባለው ትልቁ መርዛማ እባብ እስከ 5.5 ሜትር የሚያድግ ሲሆን የሚረጩት ጥቂት መጠን ያለው መርዝ እስከ 30 ሠዎችን ሊገድል ይችላል፡፡

- የሌሊት ወፍ ማንኛውም አይነት ምግቦችን ትመገባለች፡፡- የጉማሬ አይኖች፣ ጆሮ እና የአፍንጫ ቀዳዳዎች ከጭንቅላቱ

በላይ የሚገኙ ናቸው፡፡- አርማዲሊሶ የተባለ እንስሳ በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን

ሲወልድ ፆታቸው ተመሳሳይ ነው የሚሆነው፡፡ በቀን 18 ሠዓታት ሊተኛ ይችላል፡፡ በውሃ ውስጥ መራመድ የሚችል ብቸኛ እንስሳ ነው፡፡ በስጋ ደዌ በሽታ ሊጠቃ የሚችለው ብቸኛ እንስሳም አርማዳሊሶ ነው፡፡

ምንጭ፡- ዱር ለዱር አበበ መኮንን (ከመካኒሳ)

አስገራሚ የእንስሳት እውነታ

የምትወደው ለሁልጊዜ ሲለይህ የሚያስረሳህ እንጂ የሚያስታውስህን ነገር አትፈልግ አለበለዚያ ሕይትወትህ የሥቃይ ዘመን ይሆናል

/ፍቅር እስከ መቃብር/ሴቶች ትሁቶች ናቸው፡፡ ከወደዱ

ሁለመናቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ /ሰንሰለት/

ለመኖር መድፈር ያስፈልግሃል፡፡ /ላምሮት/

ቁንጅና እንደታማኝነት የልብ ወዳጅ የላትም፡፡

/ሀምሌት/ለዚህች ዓለም እብደት ተገቢ

በሽታዋ ነው፡፡ /የቃተተች ነፍስ/

ሶፍያ አብዶ (ከሳሪስ)

Page 21: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

21

ምስራቅ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ

ውበት/ፋሽንየኬኒያ ፓርላማ እንደራሴዎች ለራሳቸው የፈቀዱት የደሞዝ ጭማሪ ቀማኛ አስባላቸው

ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ የ1 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ ሆኑ

በሀገራችን ሴቶች ዘንድ ቀለምን ከፊት ገፅታ ጋራ ማስማማቱ የተለመደ አይደለም፡፡ ቀለም የሴቷን ውበት የማጉላት ብቃት እንዳለው ሁሉ ተስማሚ ያልሆነ ቀለም ውበትን የማደብዘዝ ባህርይ አለው፡፡ ይህም በመሆኑ አንዲት ሴት ቀለም ለመቀባት ስትፈልግ ተስማሚውን ልትመርጥ ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት የዳይመንድ የፊት ቅርፅ ያላት ቀይ ሴት ውበቷ ጎልቶ እንዲወጣ ጠቆር ያለ ቀለም መቀባት አለባት፡፡ ብዙውን ጊዜ ቀይ ሴቶች ቀይ ቀለም እንዲቀቡ አይመከሩም፡፡ ምክንያቱም የፀጉሯ መቅላት የፊቷን ውበት ይሸፍነዋልና ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ጥቁር ሴቶች ጥቁር ቀለም ሊቀቡ አይገባም፡፡ በምትኩ ፈካ ሊያደርጋቸው የሚችል ቀለም መምረጥ አለባቸው፡፡ የዳይመንድ የፊት ቅርፅ ያላቸው የቀይ ዳማ ሴቶች ደግሞ ከላይ ከተጠቀሰው ጥቁር ቀለም በመጠኑ ፈካ ያለ ቢቀቡ ከፊታቸው ገፅታ ጋር ይስማማል፡፡

ጠይምና ባለዳይመድን የፊት ቅርፅ ያላት ሴት ወደ ጥቁር ቡኒ የሚያደላ ቀለም ብትቀባ ይመረጣል፡፡ ከፊት ቅርፆች መካከል አንዱ የሆነው ባለ አራት መዓዘን ገፅታ ሲሆን ይህ ቅርፅ ያላት ጠይም ሴት የፊቷ ውበት የፈካ እንዲሆን ከቡኒ ጋር የተደባለቀ ሃይላይት ቀለሞችን ብትቀባ ያሳምራታል፡፡ በዚሁ የፊት ቅርፅ ስር የሚካተቱ ጠቆር ያሉ ሴቶች ደግሞ ወደ ወርቃማ የሚያዘነብል ቡናማ ከለር ምርጫቸው ነው፡፡

ቀለምና የፊት ቅርፅ

ሌላው የፊት ቅርፅ ባለ ሶስት ጎን ነው፡፡ ቀላ ያሉ ባለ ሶስት ጎን የፊት ገፅታ ያላቸው ሴቶች ደግሞ ውበታቸውን ያፈካዋል የሚባለው ቀለም ጠቆር ያለ ቡኒ ነው፡፡ ይህ ቀለም ብዙውን ጊዜ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሴቶች ለሽበት ማጥቆሪያነት የሚቀቡት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የቀይ ዳማ ከሆኑ የቀለም ምርጫዎ ቀይ ቡኒ ቢሆን በቀላሉ እይታን ያገኛሉ፡፡

የልብ ቅርፅና ጠይም የፊት ቀለም ያላት ሴት ፈዘዝ ያለ ቀይ ቡኒ የፀጉር ቀለም ውበቷ እንዲጎላ ያደርገዋል፡፡ በአንፃሩም ቀይዳማ ሆና ፊቷ ክብ ቅርፅ ያለው ከሆነ ቀላ ያለ ወርቃማ ከለር ያስውባታል፡፡

ተለምዷዊ የሆነውን የቀለም ምርጫሽን አስወግደሽ ከፊትሽ ገፅታና ከለር ጋር በማስማማት ውበትሽን ከመቼውም ይበልጥ የፈካ አድርጊው፡፡

እንደ ኬኒያ የፓርላማ አባላት አይን አውጣና ደፋር የለም›› ይላሉ የኬኒያ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ሰሞኑን የሕዝብ እንደራሴዎቹ ለራሳቸው የፈቀዱትን የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት አድርገው ለተቃውሞ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት፡፡

222 ወንበሮች ያሉት የኬኒያ ፓርላማ አባላት ‹‹ኑሮ ተወዷል›› በማለት ለራሳቸው የ110 ሺህ ዶላር ዓመታዊ የደሞዝ ጭማሪ አድርገዋል፡፡ የህዝብ እንደራሴዎቹ ለራሳቸው የፈቀዱት የደሞዝ ጭማሪ ለቀጣዮቹ 5 ዓመታት የሚታሰብ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እያንዳንዱ የፓርላማ አባል በዓመት የ120 ሺህ ዶላር ተከፋይ ነው፡፡

በኬኒያ የአንድ ዜጋ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ 1500 ዶላር ሲሆን የፓርላማ አባላቱን ድርጊት የተቃወሙ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ የኬኒያ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ለ ተ ቃ ው ሞ ወደ አደባባይ በመውጣት የህዝብ እንደራሴዎቻቸውን

በፀረ አፓርታይድ ትግል ዘመን ሥርዓቱን መቃወምና ህዝቡን በማነቃቃት የሚታወቁት ደቡብ አፍሪካዊው ሊቀጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ ስልጣን ላይ ያሉ መሪዎችን በድፍረት በመተቸት ለሚያደርጉት አስተዋፅኦ የ1 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አገኙ፡፡

በሀገራቸው መልካም አስተዳደር ላሰፈኑና በምርጫ ስልጣናቸውን ለህዝብ ለሚያስተላልፉ የሀገር መሪዎች ለ5 ዓመታት በየዓመቱ የ1 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በመስጠት የሚታወቀው የሞህ አብራሂሞ ፋውንዴሽን የዘንድሮውን የ1 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ለሊቀጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ ለመስጠት የወሰነው ስልጣኑን የለቀቀ አፍሪካዊ መሪ ባመኖሩ እንደሆነ ገልጿል፡፡

የሞህ አብራሂሞ ፋውንዴሽን ለረዥም ዓመታት በስልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ ለህዝብ የሚያስረክቡ የሀገር መሪዎች በሌሉበት ወቅት እንደ ዴዝሞን ቱቱ አይነት አህጉራዊ የለውጥ ሰው በመምረጥ ሽልማቱን ይሰጣል፡፡

ዴዝሞን ቱቱ ቀደም ሲልም የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ሆነው የተመረጡ ሲሆን በፀረ አፓርታይድ ትግልም ሆነ ከዚያ በኋላ ስለ ፍትህና፣ ስለ ነፃነት፣ ስለ ሰላምና ስለ ዲሞክራሲ የሚሰብኩ ሰው ናቸው፡፡ የሞህ አብራሂሞ ፋውንዴሽን ተቀማጭነቱ

በእንግሊዝ ሀገር የሆነ በሱዳናዊው ሞህ አብራሂሞ የበጎ አድራጎት ተቋም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

‹‹Thieves /ሌቦች/›› ሲሉ ገስፀዋቸዋል፡፡የመምህራንንና የጤና ባለሙያዎቹን ተቃውሞ

ተከትሎ የኬኒያ ፕሬዚዳንት ሙአሂ ኪባኪ የደሞዝ ጭማሪ ለሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ይደረጋል በማለት ለማረጋጋት ጥረት ቢያደርጉም በፓርላማው ውሳኔ ላይ የፕሬዚዳንቱ እጅ እንዳለበት በተቃዋሚዎቹ እየተነገረ ነው፡፡

ይህ የኬኒያ ፓርላማ አባላት የደሞዝ ጭማሪ እንደራሴዎቹን በዓለም ላይ ከፍተኛ ተከፋይ ያደርጋቸዋል፡፡ ዜናው የዴይሊ ኔሽን ነው፡፡

Page 22: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

22

ቁምነገር፡- ራስሽን ከማስተዋወቅ እንጀምር?ወ/ሮ አዜብ፡- ወ/ሮ አዜብ ሽፈራው እባላለሁ ባለትዳርና የአንድ ልጅ እናት

ነኝ፡፡ቁምነገር፡- በ8100 ምን ያህል ቴክስቶችን ልከሻል?ወ/ሮ አዜብ፡-እኔ የማስታውሰው ሶስት ጊዜ መላኬን ነበር ፡፡ዕጣው ከደረሰኝ

በኋላ እንደነገሩኝና ኮምፒውተር ላይ እንዳረጋገጡት ከእዛ በላይ ነው የላኩት ፡፡ይመስለኛል ሳላውቀው ልኬያለሁ ማለት ነው፡፡

ቁምነገር፡-ማስታወቂያውን ስትመለከቺ ምን ይሰማሽ ነበር?ወ/ሮ አዜብ፡-ማስታቂያውን ስመለከት በተለይ ቤቱ ያጓጓኝ ነበር፡፡ግን

ባየሁት ቁጥር እውነት ይሄ ቤት አጭር የፅሁፍ መልዕክት ለፃፈ ሰው ዕጣ ይወጣል?እያልኩ ተጠራጥሬያለሁ፡፡

ቁምነገር፡-ዕጣው እንደወጣልሽና የቤት ባለቤት መሆንሽን የተነገረሽ መቼ ነበር?

ወ/ሮ አዜብ፡-ነሀሴ 14ቀን2004ዓ.ም ነው የተነገረኝ፡፡ቁምነገር፡-በዕለቱ በምን ሁኔታ ላይ ነበርሽ?ወ/ሮ አዜብ፡-ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ስልክ ተደውሎ አሸናፊ መሆኔ

ተነገረኝ ፡፡በወቅቱ እቤት ነበርኩ፡፡አባቴ ልጄን እያጫወተ ነበር ፡፡በስልክ ደውለው የሚያሾፉ ሰዎች ስላሉ ነገሩን ያገናኘሁት ከእዚህ አይነት አጋጣሚ ጋር ነው እንጂ ቁምነገር አድጌ አልቆጠርኩትም፡፡አምኜም ስላልተቀበልኩት እሺ ብዬ ሰልኩን ዘጋሁት ፡፡መልሶ በዛው ስልክ ከ5 ደቂቃ በኋላ ተደወለልኝ፡፡ቤቱ የት እንደሆነ አውቀሻል ?አለኝ ፡፡በጣም እድለኛ ነሽ በማለት ስለራሴና ስለኑሮዬ ጠየቀኝ እኔም መልስ ሰጥቼው እሺ ብቻ ብዬ ስልኩ ተዘጋ ፡፡ ምነው ምላሽ ቀዘቀዘ እድለኛነትሽ ሲነገርሽ እንዲህ ነው የምተቀበይው? አለኝ ቤት ደርሶሻል መባል ቀላል ነገር አይደለም ስለዚህ አምኜ መቀበል አልፈለግኩም፡፡

ቁምነገር፡-ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አምነሽ የተቀበልሽው እንዴት ነው?

ወ/ሮ አዜብ፡-ሬድዮ ፋናዎች ደውለው እንኳን ደስ ያለሽ ሲሉኝ ነው እውነትነቱን አምኜ የተቀበልኩት፡፡ ቢሯቸው ሄጄ የበለጠ እውነትነቱን አረጋግጫለሁ፡፡

ቁምነገር፡- የግል መኖሪያ ቤት ነበረሽ?ወ/ሮ አዜብ፡-ባለትዳር ብሆንም የምኖረው ከቤተሰቦቼ ጋር ሰሜን ማዘጋጃ

አካባቢነው፡፡ቁምነገር፡-ባለዕድል የሆንሽበትን ቤት ያየሽው መቼ ነው?ወ/ሮ አዜብ፡-ቤቱን የተረከብኩ ዕለት መስከረም 9 ቀን2005 ነው፡፡ቁምነገር፡-ቤቱን ትገቢበታለሽ?ወ/ሮ አዜብ፡-ቤቱ የእኔ እንደሆነ ስላወኩ ነው መሰለኝ ተረጋግቼ ለመግባት

ነው ያሰብኩት ፡፡የቤት ዕቃ አሟልተን ለመግባት ከባለቤቴ ጋር ተነጋግረናል፡፡ቁምነገር፡-ቤቱ ስንት ክፍሎች አሉት?

‹‹የ1.3 ሚሊዮን ቤት የለንደን ኦሎምፒክ

ተሸላሚ››የለንደን ኦሎምፒክ የልዑካን ቡድን በገንዘብ ለመደገፍ በሚል 8100

የአጭር የፅሁፍ መልዕክት ላኩ የሚል ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሄድ ነበር፡፡ከሞባይል አንስቶ እስከ ዘመናዊ ቪላ ቤት ድረስ ለሽልማትነት ቀርበው የነበረ ሲሆን ባለዕደለኞች ተለይተዋል፡፡አሸናፊው ማን ይሆን? የሚለውን ጊዜ አልፎ የቤቱ ባለዕጣ ቤቷን ተረክባ የተሰማትን ስሜት እንደዚህ ገልፃለች፡፡

ወ/ሮ አዜብ፡- የዘነበው ፍሬው ሪል ስቴት ቤት ነው፡፡ በአጠቃላይ 200 ካሬ ስፋት ላይ ሲሆን ሶስት መኝታ ቤቶች ፤አንድ ኪችን ፤አንድ ሻወርና ሳሎንም አለው፡፡በተጨማሪ ሶስት ሰርቪስ ቤቶችና አንድ ሻወር ቤት ያለው ነው፡፡

ቁምነገር፡- ባለቤትሽ ስራው ምንድን ነው?ወ/ሮ አዜብ ፡- ባለቤቴ ስራው መርከበኛ ነው፡፡ይሄ ዕድል ከደረሰን በኋላ

የውጭ ኑሮውን ትቶ መጥቷል ፡፡ተለያይቶ መኖር ያየሰው ምን ያህል እንደሚከብድ ያውቀዋል፡፡የመርከበኛ የስራ ባህሪ ባህር ላይ እስከ አራት ወር ድረስ ያቆያል፡፡ለመገናኘት ረጅም ጊዜ ይወስድብናል ፡፡ሀሳቡና ጭንቀቱ አለ፡፡ይሄ ዕድል የሚያመለክተው እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም እኛን እንደጎበኘችን ነው፡፡

ቁምነገር፡- ባለቤትሽ ቤቱ ሲደርስሽ የት ነበር?ወ/ሮ አዜብ፡- ባህሬን ነበር፡፡ የነገርኩት በስልክ ነው እውነት ነው ብሎ

ለመቀበል ከበደው፡፡በኋላ ይሄ የእመቤቴ ስጦታ ነው አለ፡፡ቁምነገር፡-ትዳር ከመሰረታችሁ ስንት ጊዜ ሆናችኋል?ወ/ሮ አዜብ ፡-ግንቦት ሲመጣ ሶስተኛ ዓመታችን እንይዛለን፡፡ቁምነገር፡-ሎተሪ ቆርጠሸ ታውቂያለሽ ?ወ/ሮ አዜብ፡-ከአሁን በኋላ ለመቁረጥ አስባለው እንጂ ቆርጬ አላውቅም ፡፡ቁምነገር፡- ቤቱን ከተረከብሽ በኋላ ለሌሎች ሰዎች አሳየሽ?ወ/ሮ አዜብ፡-መስከረም 9 ረቡዕ ቀን ከተረከብኩ በኋላ እሁድ በ13

ጎረቤቶቼን፤ ጓደኞቼን እና ቤተሰቦቼን አሳይቻለሁ፡፡ ኦሎምፒክ ኮሚቴው ቃሉን ጠብቆ ይህ ቀረው የማይባል የፀዳ ቤት እንዳስረከቡኝ ለማሳወቅ ነው ፡፡በዚህ አጋጣሚ እጅግ በጣም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡

ቁምነገር፡-ከአትሌቶች ማንን ታደንቂያለሽ ?ወ/ሮ አዜብ፡-ጥሩነሽን ከነሁሉ ነገሯ በጣም ነው የምወዳት፡፡ቁምነገር ፡-ርክክብ ላይ ምንድን ነው የተሰጠሽ?ወ/ሮ አዜብ፡-የቤት ቁልፍና ካርታ ነው የተሰጠኝ የባለቤትነት ስም ማዞር ገና

ነው፡፡በቅርቡ እንደሚዛወርልኝ ተነግሮኛል፡፡ ቁምነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

Page 23: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

23

‹‹ዓለም አቀፍ ፓተንት ለማግኘት ጠይቄያለሁ››

ፓተንት

የስድስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጁ ይነተርከዋል፤ ‹‹ለምን እኛ ሀገር ኒዩክለር

አይመረትም?›› እያለ፡፡ አባት መማርህ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን ለመመለስ ነው፡፡ ‹‹ለምን እንዳልተሰራ መጠየቅህ አግባብ ቢሆንም እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ፤ ማንበብ፣ አንብቦ መሞከር ያንተ ፋንታ ነው›› እያለ ታዳጊ ልጁን በእውቀት ለማስታጠቅ መፃህፍት ያቀርባል፡፡ ንትርክ ደረጃ በሚደርስ ክርክር ይፋለማሉ፡፡ ይህ የፈጠራ ባለሙያ የአቶ ሰለሞን ሀይለማርያምና የታዳጊ ልጁ እሰጣገባ የኑሯቸው አካል ነው፡፡

ከአቶ ሰለሞን ጋር የተገናኘነው በስራ ቦታው ነበር፡፡ ሰንጋተራ በሚገኘው የሆቴል ቤት ደጆች አልፎ በሚገኝ የጓሮ ስፍራ፡፡ ቦታው ለስራምቹ አለመሆኑ ቢያሳብቅም የተለያዩ በብረትና ከእንጨት የተሰሩ የተለያዩ ፈጠራዎች ይታያሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ፀሀይ ያወየባቸው ዝናብ ያበላሻቸው ፈጠራዎቹን ተመለከትኩ ፡፡ኮምፒውተራይዝድ በሆነ መንገድ ይሰራል ሲል ከንድፍ አልፎ ተግባር ላይ ያዋለው ልጆችን በቀላል ዘዴ የማስተማሪያ ማቴርያል ይገኝበታል፡፡ ‹‹ከሁለት አመት አንስቶ ላሉ ህፃናት የሰራሁት ነው›› ይላል ሰለሞን፡፡ ህፃናቱ በእግራቸው ወለል ላይ ተደርጎላቸው ሲረግጡትም ሆነ ሲነኩት የረገጡት ፊደል ድምፅ እንዲያወጣ አድርጌዋለሁ፡፡ በአቅም ማጣት ስራ ላይ ባይውልም አለኝ ፡፡ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ፅ/ቤት በሰባት የፈጠራ ስራዎቹ የባለቤትነት ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡

ከእነዚህ ፈጠራዎቹ መካከል በአንዱ በአለም አቀፍ ደረጃ የፓተንት ጥያቄ አቅርቦበት ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡ ደረቅ ቆሻሻን መጠቀም ጭስ አልባ የማገዶ ከሰልና ቫርኒሽ ማምረት የተሻሻለ የጎዳና ላይ የቆሻሻ መሰብሰቢያ፤ የቆሻሻ መጣያ፤ አገልግሎት ላይ ከዋለ ወረቀት የማገዶ እንጨት እና ከቆሻሻ ሚቴን ጋዝ በማውጣት ፤የሎተሪ ማውጫ ማሽን፤ ኮምፒውተራይዝድ የህፃናት ማስተማሪያ በእጁ ከሚገኙት ሌሎች ተጨማሪ የፈጠራ ስራዎች በተለየ ፓተንት ያገኘባቸው እንደሆኑ የምስክር ወረቀቶቹን እያሳየ አጫውቶኛል፡፡

እድገትና ትምህርትበ1950 ዓ.ም ነው የተወለደው፡፡

በልጅነቱ መማርን ብቻ ሳይሆን ራሱን በስራ መደገፍ ያለፍኩበት መንገድ ነው ይላል፡፡ እንደ አሁኑ በእሱ

የትምህርት ዘመን 10ኛ ክፍል ሲደርስ 11 ና12 ክፍልን ቴክኒክ ትምህርት ቤት ገብቶ መማር ይቻል ነበር፡፡ እናም ተግባረዕድ ገብቶ በኤሌክትሪክሲቲ ሁለት ዓመት በመማር ሳያጠናቅቅ አቋረጠ፡፡ ሀገራችን በወቅቱ በሶማሌ ተወራ ሰለነበር ወታደርነት ተቀጥሮ ዘመተ፡፡ ከዘመቻ በ1968 ተመለሰ፡፡ ከውትድርና መልስ በቀላሉ ኑሮውን የሚደጉምበት ስራ አሰበ፡፡ የሴቶች ዘመናዊ አልባሳት ሞዴል ማውጣት ጀመረ፡፡ የቆዳ አልባሳትም እንዲሁ፡፡ቆዳው ላይ ህትመት ለመጨመር አስቦ ማተሚያ ማሽን ሰራ፡፡ ህይወቱን እንዲህ ቢገፋም ለፈጠራ ስራ የማይቦዝነው አይምሮው ችግር ፈቺ ያለውን ሙከራ ለመጀመር አነሳሳው፡፡

ቆሻሻን እንደጠላ ጥንሰሳውዳቂ አላስፈላጊ የተባለ ቆሻሻን

ሰለሞን ፈለገ፡፡አሰባሰበ፤ ሙከራውን በዚሁ ጀመረ ፡፡ቆሻሻን እንደጠላ ጠነሰሰ፤ ውጤቱም ተሳካና አሰቦ የተነሳውን የሚቴን ጋዝ አገኘ፡፡ በ1997 ዓ.ም የአዲስ አበባ ቆሻሻ ማከማቻ በነበረው በተለምዶ አጠራር “ቆሼ “ አካባቢ አርቴፊሻል ከሰልና እንጨት ማምረት ጀምሮ ነበር፡፡ከዚህ ጎን ለጎን ከቆሻሻ ሚቴይን ጋዝ ማውጣቱ ሌላ አስደሳች ፈጠራው ሆኖ አገኘው፡፡ ከብረት በተሰራች የአነስተኛ የማመቂያ ማኑዋል ማሽን እንደሚሰሩ እያሳየኝ ነበር ያጫወተኝ፡፡ አቶ ሰለሞን እንደሚለው ቆሻሻ አካባቢን በክሎ፣ መጥፎ ጠረን አውጥቶ የአይን ማረፊያ ማሳጣቱ ሊበቃ ይገባል ይላል፡፡በምርምር ሂደት ያገኘው የሚቴይን ጋዝ የማምረት ሄደት በቦታ

አለመመቸት ያሰበውን ያህል ውጤት አላገኘሁበትም ይላል ፡፡በወር ከ1 ሺህ ኩንታል በላይ ቆሻሻ ቢሰበሰብ ምርቱ ከፍ ሊል መቻሉን ያውቃል፡፡ ግን የት ተቀምጦ ቆሻሻው ይብላላል?እንዴትስ ለማብሰያነት የሀይል ምንጭ የሚሆነው ሚቴይን ጋዝ ይጣራል?ህልሙን ወደተጨበጠ እውነትነት በአነስተኛ ቦታ ማውጣት የቻለውን የሚቴን ጋዝ ምርት ጥቅም ላይ ውሎ ታየ፡፡

የሞዛንቢኩ ፕሬዝዳንት ጉብኝት

ሰንጋተራ በሚገኘው አነስተኛ የስራ ቦታው የሀገር መሪ ተቀበለበት፡፡ የሞዛንቢክ መሪ በአርማንዶ ጉብሪሰን የሚመጥን ባይሆንም አቅሙ በፈቀደው ከአካባቢውና ከቤተሰቡ ጋር በመሆን ድንኳን ጥሎ ተቀበላቸው ፡፡በወቅቱ የተሰማኝ ደስታ ላቅ ያለ ነበር ይላል፡፡ ፕሬዝዳንቱ እንዴት እንዳገኙት ሲናገር በአዲስ አበባ የሀገሪቱ አምባሳደር ከሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የተሰራውን አንብበው እንደሆነ ነው፡፡ በአንድ ኤግዚቢሽን ላይ ስራውን የተመለከተ ጋዜጠኛ ያናግረዋል፡፡አምባሳደሩ እጅ ጋዜጣው ከገባ በኋላ አድራሻውን አፈላልገው ያገኙታል፡፡እንዴትና በምን ሁኔታ እየሰራ እንዳለ በስራ ቦታው ይገኛሉ፡፡ ለአንድ ወር ያህል በወሰደ ክትትል በቦታው ተገኝተው ያረጋግጣሉ፡፡ ይሄንንም ለሀገራቸው ፕሬዝዳንት ያሳውቃሉ፡፡ ፕሬዝዳንት አርማንዶ ጉብሪስ ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በቦታው የተገኙት በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡ ወደ ማፑቶ እንዲመጣ ጋብዘውት ይሰነባበታሉ፡

፡ ይህ የሆነው በ2ሺህዓ.ም በመሆኑ በዛው ዓመት ወደዛ አምርቼ ነበር ይላል ሰለሞን፡፡ ለፈጠራ ስራው እውቅና ብቻ ሳይሆን ድጋፍ በመስጠት የስራ ቦታ በነፃ ተፈቅዶለት ተረከበ፡፡ ጥሬ ዕቃውን በቀላሉ እንደሚገኝ ያምናል፡፡ ወደተግባር መቀየሩም ፈታኝ አለመሆኑን ያውቃል፡፡ በሀገሪቱ ኢንቨስት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ እኔ ወደ ገንዘብ የሚመነዘር ሀሳብና እውቀት እንጂ ከአራት ቤተሰቦቼና ከማስተዳድራቸው አስር ሰራተኞቼ የሚተርፍ ሀብት በእጄ አለመኖሩ አደናቅፎኛል ይላል፡፡ ቢሆንም ግን አገልግሎት ላይ የዋሉ ምርቶችን በመለየት 180 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ፋብሪካ በማቅረብ ስራውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ሽልማቶች የሰለሞን የፈጠራ ስራዎች

አካባቢን ከብክለት የሚጠብቁ መሆናቸውን ያመኑ የተለያዩ ድርጅቶች በተለያየ ጊዜ ሸልመውታል፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ሽልማት ከክቡር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ እጅ በ1998 ዓ.ም ተቀብሏል፡፡ በመቀጠል ፎረም ፎር ኢትዮጵያ፤የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ፤ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ድጋፍና ሽልማት፤ ልደታ ክ/ከተማ እንቅስቃሴውን ማበረታታት የስራ ቦታ እስከመፍቀድ የደረሰ ብርታት ሰጥተውኛል በማለት ያስታውሳል፡፡

ምኞትየፈጠራ ባለሙያው ዘገባ

‹‹ለተማሪዎች ሞዴል እንፍጠርላቸው›› ይላል፡፡ ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን ተማሪዎች እኔም እንደሱ የመሆን ህልም አለኝ እንዲሁ በፈተና ውስጥ አልፈው ትልቅ ቦታ የደረሱ ሰዎችን ብናሳውቃቸው መልካም ዜጋን ማፍራት ያግዛል ይላል፡፡ ሌላው እኔን መሰል የፈጠራ ሰዎች ውስጣቸው ብዙ ነገር ያመቁ ይገኛሉ፡፡ እነሱ ሰርተው ያወጡትን ተግባር ላይ እንዲውል ድጋፍ የሚሰጥ አካል በመንግስትም ሆነ በግለሰቦች ቢቋቋም እንዲሁም፡፡ከምስክር ወረቀት ያለፈ ማበረታቻ ያስፈልጋል ባይ ነው፡፡

Page 24: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

24

ወ ን ጀ ል ና ወ ን ጀ ለ ኞ ች

‘‘አዳኝና ታዳኝ ተ ገ ና ኝ ተ ዋ ል ፡ ፡ የተዘረጋ ወጥመድ ታዳኙን ይሻል፡፡ ስለዚህ ይህ መረብ በሁለት

ወንድማማቾች ተጥሏል፡፡ መረቡ ያለመውን ይዞ እንዲገኝ ታላቅ ታናሽ ወንድሙ ላይ እምነት ጥሏል፡፡ እምነት የተጣለበት የሰላሳ ዓመት ወጣት ስራውን ጀምሯል፡፡ወንድማማቾቹ የወርቅ ቤት ባለቤቶች ወርቅ ለማደን ተነስተዋል፡፡ይህ የወንድማማቾቹ ሀሳብ እንዲተገበርሀብት ብቻ ሳይሆን በግራም የበረከተ ላቅ ያለዋጋ የሚተመንለት ወርቅ ያላቸው ሰዎች ይፈለጋሉ፡፡መንገዱ እንዲቀና ገንዘብ መድበው ታናሽ ሊሰማራ ተስማሙ፡፡ የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ነው ለእናቱ ምትክ የሌለው ብቸኛ ልጁ በባህሪው የተመሰገነ ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ከቤት ወደ ትምህርት ቤት ከመመላለስ ውጪ ሌላውን አለም የማያውቀው የተመሰገነ ነበር፡፡ ነበር የተባለለት ባህሪው የተቀየረው በእድሜው ከሚበልጠው በገንዘብ ሀይልም ከማይወዳደረው ሰው ጋር ከተቀራረበ በኋላ ነው፡፡ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም አቤልን(ስሙ የተቀየረ) ሰለቸው ፡፡በቦርሳው ቅያሪ ልብስ መያዝ ተማረ፡፡ ምክንያቱም ከቤት ወጥቶ ወደ ትምህርት ቤት መሄዱን ቤተሰብ ያውቃል፡፡እሱ ግን ከትምህርት ቤት ይልቅ የቀን

ባለ ወርቅ ቤቶቹየወርቅ ‹‹ሌቦች››

ፓርቲ መሄድ በልጦበታል፡፡ከእድሜ እኩዮቹ ጋር ያሻውን በነፃነት ያለተቆጣጣሪ ይፈፅማል ፤ያለከልካይ የፈለገውን ያደርግበታልና ይህ ቦታ ያስደስተው ጀምሯል ፡፡አቤል የትምህርት ቤት ፍቅሩን ለቀን ፓርቲ ሙሉ በሙሉም ባይሆንም በአብዛኛው አሳልፎ ሰጠ፡፡ እዚህ ቦታ ይዞት ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣው የባለወርቅ ቤቱ ወንድ ልጅ ጓደኛው ነው፡፡ ገንዘብ ከኪሱ የማያጣው ኪሮስ(ስሙ የተቀየረ) ለሚወጣው ገንዘብ ስስት አይታይበትም፡፡ ቀን በቀን መጋበዝ በእሱ፤የቀን ፓርቲ መግቢያ በእሱ፤ ተጨማሪ የመጠጥና የጫት ሌሎች ሱስ ለማያስይዙ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም በድጋሚ ለሚያስፈልጉ አዝናኝ ጉዳዮች ያወጣል፡፡ከትምህርት ቤት ደጃፍ እግሩ ራቀ ከቤት መቆየት እስር እየመሰለው ሄደ፡፡ለእሱ ደስታ ከጓደኛው ኪሮስ ጋረ መገናኘት እየሆነ ነው፡፡ፍቅራቸው ፀንቷል ፡፡ለጫትና ለመጠጥ ሩቅ የነበረው የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪው ወጣት መጠጥና ጫት ከሚገኙበት ቦታ አሳዶ መገኘት አዘወተረ፡፡ለሱስ እጁን ቀስ በቀስ ሰጠ፡፡የማያቋርጥ የገንዘብ ምንጭ የሆነው ኪሮስ በሂደት እጁን ወደ ኪሱ መስደድ ቀነሰ፡፡ ሱስ አቤል ላይ እየበረታበት ሲመጣ ጓደኛው ገንዘብ እያጠረው መምጣቱን አረዳው ፡፡በእጁ ገንዘብ የሌለው ሱሰኛው ተማሪ ግራ ተጋባ ፡፡ምን ማድረግ እንዳለበት የባለ ወርቅ ቤቱ ልጅ ጠቆመው መረቡ ተጣለ ታዳኝ ተዘጋጀ፤ታዳኝም ተመቻቸ ፡፡

አንድ ለቤቱ አንድ ለእናቱ የሆነው አቤል ወደ ቤት አማተረ ፡፡ሁሉ ባለው ምንም ያልጎደለው የሚባል ቤት እንዳለ ልቦናው ያውቃል፤ ሊጎድልበት አይገባም በሚል በቤተሰብ ተሟልቶለት እየተማረ ነው፡፡ተጨማሪ በሱስ ተጠምዷልና ኪሮስ ባመላከተው መሰረት ድርጊቱን ሀ ብሎ ሊጀምር በአግባቡ ወደ ማይቀመጠው የእናቱ የወርቅ ኮረጆ አመራ፡፡የመጀመሪያ ቀን የእናቱን ወርቅ ይዞ ሊወጣ ሲሰናዳ ልቡሌብነቱን ሲያውቅ ፈራ በማድረግና ባለማድረግ መሀል ቢሆንም በውሳኔው ፀንቷል፡፡ አቤል የጓደኛው ስራ ምን እንደሆነ ባያውቅም “የእናትህ ወርቅ አለ አይደል እንዴ” ያለውን ያስታውሳል፡፡ወርቁን ይዘህና ገዢ አናጣም ብሎታል ፡፡በቁጥር ለማያስታውሳቸው በርካታ ቀናት ገንዘቡን አልሰሰተበትም በደግነቱ ብቻ አዝናንቶት ከተዋወቁና ከተቀራረቡ ጊዜ አንስቶ ገንዘብ ስለሌለህ በሚል ፊት አልነሳውም፡፡ዛሬ ገንዘብ ከእጁ ሲያጣ ወርቅ ሸጦ ቢሸፍን ምን አለበት ?እያለ ተበረታቶ ሌብነትን ከእናቱ ወርቅ ጀመረ፡፡

ወርቅ በአርቴፊሻል የመጀመሪያው ቀን ሌብነት እጁ ሲለምድ አቤል

ወርቅ ያዘ ከቤት ወጣ፡፡ የተለያየ ዲዛይን ያላቸው የአንገት ፤የጆሮ ፤የእጅ አንባር በድፍረት ይዞ ሄደ ለጓደኛው ኪሮስ አስረከበው፡፡ ላመጣው ወርቅ ክፍያ አገኘ፡፡በእጁ ገብቶ የማያውቀው በርካታ የብር ኖት

እጁ ገባ ወርቁን የሚሸጥበት ቦታ የወሰደው ፤ ከገዢ ያገናኘው ተከራክሮ አትጉዳው ብሎ ያሻሻጠው ኪሮስ ነው፡፡ 43 ሺህ ብር በርግጥ ለገበያ የቀረበው የእናቱ ወርቅ 84 ሺህ ብር የሚያወጣ ቢሆንም እናቱ ወርቁን ከቦታው አጥታ እንዳትደናገጥ በምትኩ ከወርቁ በመጠንም ሆነ በዲዛይን ልዩነት የሌለው አርቴፊሻል አሰርቶ አስቀምጧል፡፡ በነፃነት ብሩን ከፈለገበት አላማ አዋለው፡፡የበዛ የመሰለው ብር ከአቤል እጅ አለቀ፡፡የተዘፈቀበት የሱስ መጠን ሰፍቷል ፡፡ወጪውም ተበራክቷል ፡፡ብዙ መሰል ጓደኞችን አፍርቷል፡፡ የቤተሰቦቻቸው የኑሮ ሁኔታ ተመሳሳይ ነው ፡፡በጋራ ለመዝናናት ሱሳቸውን ለማስታገስ ሲመሽጉ የባጥ የቋጡን ያወራሉ ፡፡ግን ሚስጥር አርገው የያዙትን የወርቅ ሌብነታቸውን አያነሱም ፡፡የቀን ፓርቲ ቤት ቤተኛ የጫት መቃሚያ ስውር ቦታ ደንበኛ ከሆኑ ብኋላ ብር አልበቃ ብሏቸዋል ፡፡ከእጃቸው ብር ሲጠፋ የእናቶቻቸውን ወርቅ ድራሹን ለማጥፋት አልሳሱም ፡፡ለማሻሻጥ ኪሮስ ስላለ አልተቸገሩም ፡፡

ዳግም እንደገና አቤል ሌብነት አጠንክሮ ይዟል ፡፡እናቱ

አልጠረጠረችውም፡፡ የት ቆየህ?ምን እያረክ ትውላለህ?አልተባለም፡፡ ነፃነትን በእጁ አደረገ ፡፡ኪሱ ባዶ እንዳይሆን የእናቱን ወርቅ በክፉ አይኑ ተመልክቶ አልቀረም ፡፡ለሁለተኛ ጊዜ ከማይቆለፈው የእናቱ የልብስ ማስቀመጫ ቁምሳጥን መሳቢያ ወርቅ አወጣ ፡፡ፒያሳ ወደ ሚገኘው ኪሮስ ወደ አስተዋወቀው

የመጀመሪያ ቀን የእናቱን ወርቅ

ይዞ ሊወጣ ሲሰናዳ ልቡሌብነቱን ሲያውቅ

ፈራ በማድረግና ባለማድረግ መሀል ቢሆንም በውሳኔው

ፀንቷል፡፡ አቤል የጓደኛው ስራ ምን እንደሆነ ባያውቅም “የእናትህ ወርቅ አለ

አይደል እንዴ” ያለውን ያስታውሳል፡፡ ወርቁን ይዘህና ገዢ አናጣም

ብሎታል፡፡

Page 25: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

25

ወ ን ጀ ል ና ወ ን ጀ ለ ኞ ች

የወርቅ ቤት ባለቤት ፈጥኖ ደረሰ ለሁለተኛ ጊዜ የመጣለትን ወርቅ ተረከበ፡፡በምትኩም ልዮነቱ በቀላሉ የማይታወቅ አርቴፊሻል አስረከበው፤ ወደ አቤል ኪስ 2.,700 ብር ገባ ፡፡በትክክለኛው የወርቅ ገበያ ቢቀርብ 15 ሺህ ብር የሚያወጣ ነበር እቃው፡፡ ይህ የአቤል ጭንቀት አልነበረውምና የሰጠውን ክፍያወደ ኪሱ አድርጎ አርቴፊሻሉን በወርቁ ቦታ ከተካ በኋላ ያመራው ደስታን አገኝበታለሁ ብሎ ወዳሰበው የቀን ጭፈራ ቤት ነበር፡፡

በቀን ፓርቲዎች ቦታ ጭፈራው ደርቷል ፡፡አንዱ ከሌላው በልጦ ለመታየት ይውረገረጋል ፡፡ዲጄው ሙዚቃውን በላይ በላይ እየቀያየረ ይጫወታል ፡፡መተፋፈር ከገደብ ያለፈበት ስፍራ እስኪሆን ከቤተኞቹ ወጣቶች አፍ እየተወረወረ በከንፈራቸው አልፎ የሚወጣውና የሚጨሰው ነገር ስፍራውን ጭስ መውጫ ያጣ ማድቤት አስመስሎታል፡፡

አቤል ከኪሱ የሚመነዝረው ገንዘብ ለዘለዓለሙ የማያልቅ ይመስላል ፡፡የትምህርትና የክፍል ጓደኛው ፍሰሀፅዮንም ረብጣ ብር እየመዘዘ ተዝናንቶ ዘና በሉ የሚል ነው ፡፡የድብቅ ቤቶች ደንበኞች በመሆናቸው ተቀራርበዋል ፡፡ገደብ ባበጁለት ቅርበታቸው ሚስጥራቸው ከራሳቸው ሳያልፍ ላይላዩን እየተጫወቱ ደስታ ያሉትን ያሳድዳሉ ፡፡ባያውቁትም በግልፅ ባይጫወቱትም የአንድ ሰው ብርቱ ቀኝ እጅ ሆነዋል፡፡ያውም እናቶቻቸውን ክደው ለአዲስ ወዳጃቸው እስከመታመን በደረሰ ቅርበት ፡፡አቤልና ፍስሀፅዮን መረብ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ አሳ ሆነዋል ፡፡ወጥመዱ ወደ ባህር ተጥሎ ባዶውን አልተመለሰም ወርቅ አልሞ በአዳኞቹ ተጥሏልና ፡፡የጓደኝነት መንፈስ የመሰለው ቅርበት ክፍተቱ መስፋቱ እየታየ ነው፡፡ባለወርቅ ቤቱ ወንድማማቾች ያለሙት ተሳክቷል፡፡ ኪሮስም በአቤል በፍስሀፅዮን ዙርያ ዘርግቶት የነበረውን መረብ ሰብስቧል ፡፡ወጣቶቹ ቀድሞ ለማያውቁት ሱስ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡ከሱስ ባህር ላለማውጣት ሌብነትን ከቤት ጀምረዋል፡፡ትምህርት ቤት ደህና ሰንብት ብለው ባይሰነባበቱም ወጣ ገባ እያሉ ሰፊ ጊዜያቸውን በጭፈራ ቤት ያሳልፋሉ ፡፡ህይወት እነሱ ጋር እንዲህ እየገፋች የነበረ ቢሆንም በዚህ ሊቀጥል ግን አልቻለም፡፡ወ/ሮ ዟፏ ተክሌ ለአመታት የገዟቸው ዲዛይናቸው ያማሩ የወርቅ ጌጣጌጦች ባሉበትናቸው፡፡የልብስ ቁምሳጥናቸው መሳቢያ በሳቡ ቁጥር ባያስተውሏቸውም ያመለከቷቸዋል፡፡በአግባቡ ባይቆለፍም ለጥርጣሬ የሚዳርጋቸው የቤተሰብ አባል የለም፡፡ አንድ ልጃቸው ደግሞ ለእሳቸው ትጉህና አመለ መልካም በመሆኑ በፍፁም አይጠራጠሩትም ፡፡ፍቅር ሰጥተው መልስ የሚሰጣቸው መለኪያ

ዜና ወቸ ጉድ

ሰዎቹ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ ይሁን እንጂ ነገሩን የፈፀሙት በዱባይ ነው፡፡ የ29 ዓመቱ ቤኪ እና የ28 ዓመቷ ኮርኖ ለጉብኝት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የቱሪስት መዲና ዱባይ ያመሩት ለእረፍት ነበር፡፡

ለአንድ ሳምንት ያህል በዱባይ ቆይታ ያደረጉት ሁለቱ ጥንዶች አንድ ቀን በታክሲ ሲሳፈሩ ለየት ያለና የዱባይ ቆይታቸውን የማይዘነጋ እንዲሆን በማሰብ ከታክሲው የኋላ ወንበር ላይ ሆነው መሳሳም ይጀምራሉ፡፡ መሳሳማቸው ብዙም ሳይቆይ መልኩን ይለውጥና መላ ልብሳቸውን አወላልቀው ላይና ታች መነባበር ይጀምራሉ፡፡

በየመንገዱ ላይ የደህንነት ካሜራ የሰቀሉ የዱባይ ፖሊሶች ታክሲው መብራት ይዞት ሲቆም በታክሲ ውስጥ ያለውን ትዕይንት በካሜራው አማካይነት ይመለከታሉ፡፡ ጉዳዩን በካሜራ ረዳትነት የተመለከቱ የዱባይ ትራፊክ ፖሊሶች ብዙም ጊዜ ሳያጠፉ ታክሲውን በትራፊክ ሞተረኛ አጅበው ወደ መንገድ ዳር እንዲቆሙ ያደርጋሉ፡፡

እንግሊዛውያኑ በፖሊስ ተይዘው ጣቢያ ሲወሰዱ ከመጠን በላይ መጠጥ ጠጥተው ስለነበር ‹‹ምነው?›› ሲባሉ ‹‹ምነው?›› ነበር መልሳቸው፡፡ ‹‹ዱባይ ደስ የምትል ከተማ ናት፤ ቆይታችንን አይረሴ ለማድረግ የፈፀምነው ነው›› ብላለች ኮርኖ ፈርጠም ብላ፡፡

በዱባይ አንዲት ሴት ባለትዳር ካልሆነች በስተቀር ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም እንደማትችል የሚደነግገው ህግ ለኮርኖ ሲነበብላት ምላሿ ‹‹አላውቅም›› የሚል ነበር፡፡ ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት ነፃ አያደርግምና ሁለቱ ጥንዶች በዱባይ ፍ/ቤት ቀርበው 3 ዓመት ከስድስት ወር በማረሚያ ቤት እንዲያሳልፉ የተፈረደባቸው ሲሆን በመጠጥ ሀይል ተደፋፍረው ድርጊቱን በመፈፀማቸው ከእስር በኋላ የ100 ሺህ ፓውንድ የሚያወጣ የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል፡፡ ዜናው የThe sun ነው፡፡

በታክሲ ውስጥ ወሲብ የፈፀሙ እንግሊዛውያን

ዘብጥያ ወረዱ

የሌለው ልጃችን ነው፡፡ምን አጉድለውበትስ ይሄንን ያስባል ብለው ያስቡ?ግን ያልጠበቁት ገጥሟቸዋል፡፡የረቀቀውን ዘርፍ ማን እንዴት ፈፀመው?

የአርቴፊሻሉ ውጤት ወ/ሮ ዟፏ ወርቆቹ ተሰርቀዋል ብለው

አላሰቡም ግን ግን የጌጣጌጦቹ ድምፅ ተቀይሯል ፡፡የወርቆቹ ዲዛይን አልተቀየረም፣ ማብረቅረቃቸውም አልተለወጠም ፡፡በእጃቸው መጠናቸውን ሲለኩ ክብደቱ የወረደባቸው ሆኖ ተሰምቷቸዋል፡፡ ይሄን ለማረጋገጥ ሲከንፉ ባለሙያ ጋር ሄደዋል፡፡ሁነኛ ባለሙያ አለበት ብለው ያመኑበት ቦታ ደርሰዋል፡፡ውስጣቸው የተፈጠረው ጥርጣሬ እንዲሆን እየተመኙ የመጡበትን ጉዳይ ተናገሩ ፡፡ወርቅ አንጣሪው የሰማውን ባያምንም ወርቅ ብለው ይዘው ከመጡት ውስጥ አንድም ወይዘሮዋ ያሉትን የከበረ ማጌጫ አለመኖሩን በሀዘኔታ አስረዳቸው ፡፡ከምርመራው ውጤት ወርቅ ሳይሆን ከወርቅ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ማጌጫ መሆኑን ሲረዱ እግራቸው ያመራው ወደ ቤት አልነበረም ወደ ፖሊስ ጣባያ እንጂ፡፡

የህግ ያለህ አንድ ልጇን አሳልፋ ለህግ የምትሰጥ ወላጅ

እናት ምን ያህል ትኖር ይሆን?ወይዘሮዋ ወርቃቸውን በአርቴፊሻል መለወጡን ለፖሊስ ተናገሩ፡፡ ማንን ይጠረጥራሉ? ከፖሊስ የቀረበ ጥያቄ ነበር፡፡ ልጄን ብለው ለመናገር አላንገራገሩም፡፡ በእናቱ የመጀመሪያ ተጠርጣሪ ሆኖ የተጠቆመው አቤል ተጠየቀ፡፡ያደረገውን ያለምን ማንገራገር የተናገረው በየዋህ አመላለስ ነበር፡፡”ኪሮስ ከሚባል ሰው ጋር ተዋወቅኩ ፡፡ለብዙ ቀናት ሲዝናናኝ ቆየ ፡፡በኋላ እሱ ብር ሲያጣ የእናትህ ወርቅ አለ አይደለም ወይ?ብሎ አምጣ አለኝ ፡፡ምንለማድረግ ስለው የሚገዛ አይጠፋም” በማለት አበረታታኝ ፡፡እናቴ ወርቁን ስታጣ ከእኔ በቀር ማንንም አትጠረጥርም ስለው በምትኩ አርቴፊሻል እንደ የቤቱ ባለቤት መሆኑን ለፖሊስ የደረሰበት ኪሮስ ወንድም ሀጎስ(ስሙ የተለወጠ) በአቤል ጠቋሚነት ተጠራ፡፡ወርቅ መግዛቱን ሳይክድ ተሰርቆ ስለመምጣቱ አለማወቁን ተናገረ ፡፡በኋላ ላይ የአቤል ጓደኛ ኪሮስ ካለበት ታድኖ ሲያዝ የታዳኝ አዳኝ ድራማ እንዴት እና በምን ሁኔታ እቅዱን መተግበሩን ተናገረ፡፡ የአቤል የትምህርት ቤት ጓደኛ የፍስሀፅዮን የድራማው አንድ አካልነትም የታወቀው የኋላ ኋላ ነበር፡፡ አንድ ቀን ያነሳው ወርቅ ይታወቅብኝ ይሆን በሚል ስጋት ቤት ውስጥ ባሳየው የባህሪ ለውጥ ጥርጣሬ ላይ የወደቀችው እናት ወርቁን ስትፈትሸው ከቦታው በማጣቷ እውነቱን እንዲያወጣ ሲጠየቅ የኪሮስ ስም ተነሳ፡፡እንደጓደኛው አቤል ተጠርጥሮ ፖሊስ ጣቢያ ሲገኝ ስለሆነው ሁሉ ተጨዋወቱ፡፡ ሚስጥራቸውን በመደባበቃቸው የሆነው መሆኑን ተረዱ ፡፡የአቃቤ ህግ ምስክር ለመሆን ተስማሙ ፡፡ባለወርቅቤቶቹ ወንድማማቾች ከሀምሌ 4ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ነበሩ ፡፡ታናሹን ለማጭበርበር ወንጀል አሰማርቶ ወርቅ ኖሮት ወርቅ ሲናፍቅ ወርቅ ሲያድን በፈፀመው የማጭበርበር ወንጀል ክስ ቢመሰረትበትም እስር ቤት እያለ በህመም አረፈ ፡፡ኪሮስ ግን ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የፌ/ከ/ፍርድ ቤት ሰኔ 22/2004 በዋለው ችሎት 3 ዓመት ከ4ወርእንዲሁም 4ሺህ ብር እንዲቀጣ ወስኖበት ወደ ማረሚያ ተላከ፡፡

ምስጋና ለአራዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሠራተኞችና ለአቃቢ ህግ ባለሙያዎች

አንድ ልጇን አሳልፋ ለህግ የምትሰጥ ወላጅ እናት ምን ያህል ትኖር ይሆን? ወይዘሮዋ ወርቃቸውን በአርቴፊሻል መለወጡን ለፖሊስ ተናገሩ፡፡ ማንን ይጠረጥራሉ? ከፖሊስ የቀረበ ጥያቄ ነበር፡፡ ልጄን ብለው ለመናገር አላንገራገሩም፡፡

Page 26: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

26

ህጉ ምን ይላል?

ባህል

ከእንስሳት ዓለምየአደገኛ ቦዘኔ መቆጣጠሪያ ህግ ምን

ይላል? 1. ማንኛውም ፖሊስ አደገኛ መሆኑን

በሚገባ የሚጠረጥረውን ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ ይችላል፡፡

2. ፖሊስ በጥርጣሬ የያዘውን ሰው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ 48 ሰዓት በማይበልጥ ግዜ ውስጥ ፍርድ ቤት ማቅረብ አለበት ፡፡ይህም ተጠርጣሪው ከተያዘበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለማምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠየቀውን አይጨምርም ፡፡

3. በዚህ አዋጅ አንቀፅ 6(1)መሰረት በአደገኛነቱ በሚገባ ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በዋስትና አይለቀቅም ፡፡

ስለ ጊዜ ቀጠሮ 1. አንድን በአደገኛነቱ የተጠረጠረን ሰው

የያዘ መርማሪ ምርመራውን በ28 ቀን ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅና የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ መላክ አለበት፡፡

2. መርማሪው ፖሊስ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ-ስርአት መሰረት አስፈላጊውን ምርመራ ያከናወናል ፡፡

3. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ2 የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ምርመራው በተለየ የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡

ሀ. የተጠርጣሪው ዕድሜ ለ. ስራ ለመስራ አቅም ያለው ስለመሆኑ ሐ. የተጠርጣሪውን መተዳደርያ ወይም የገቢ

ምንጭ መ. ተጠርጣሪው የትና ከማን ጋር እንደሚኖር ሠ.ተጠርጣሪው በአካባቢው ህዝብ

የሚታወቅበትን ባህርይ4. መርማሪው ፖሊስ በወንጀለኛ መቅጫ

ህግ ስነ-ስርዓት ቁጥር 38(ሐ)መሰረት ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ከታዘዘ ለዓቃቤ ህግ በደረሰው በ5 ቀናት ውስጥ ምርመራውን አጠናቅቆ ለዓቃቢ ህግ መመለስ አለበት ፡፡

(የአደገኛ ቦዘኔ መቆጣጠሪያ አዋጅ 1996 ዓ.ም)

የህፃናት አስተዳደግ በኢሳ ከኢሳ ጎሳ ህፃን እንደተወለደ የሚደረጉ የተለያዩ

ባህላዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ቀዳሚው ህፃኑ እንደተወለደ በባህላዊ ሁኔታ የተቀመመ ጢስ ይታጠናል፡፡

ጢስ የሚታጠነው ለሁለት ምክንያት ነው፡፡ አንደኛው ምክንያት ጨቅላው ብርድ እንዳያገኘው ሲሆን ሌላው ደግሞ መጥፎ ጠረን እንዳይከሰትበት በሚል እሳቤ ነው፡፡

በተጨማሪ ህፃኑ እንደተወለደ የተቆረጠው እትብቱ ደረቅ ሲወድቅ በከብት አልያም በግመል አንገት ላይ ይታሰራል፡፡ ይህ ማለት ከብቱ ወይም ግመሉ የህፃኑ ንብረት መሆኑ መገለጫ ይሆናል፡፡

ህፃኑ በተወለደ በአርባ ቀኑ ፀሀይ ለመሞቅ ይወጣል፡፡ የህፃኑ ፆታ ወንድ ከሆነ እናቱ በአንድ እጇ ዘምባባ በሌላው እጇ ጨቅላውን ትታቀፈዋለች፡፡ አባትየው በበኩሉ የጦር መሳሪያ ይዞ ይወጣል፡፡

እንዲሁም በመንደሩ በጉብዝናውና በሐብቱ ታዋቂና ዝነኛ የሆነው ሰው ይጠራል፡፡ ይህ ስሙ እንደመጣ ወደ ፀሀይ መውጫ ፊቱን አዙሮ ይቀመጣል፡፡ ህፃኑንም ጭኑ ላይ ያስቀምጣል፤ በመቀጠልም ትከሻው ላይ ሲያስቀምጠው አባት ሁለት ጊዜ ጥይት ይተኩሳል፡፡ የተወለደችው ሴት ከሆነች ጥይት አይተከሞስም፡፡

ሴት ልጅ ስትወለድ የሚደረገው ባህላዊ ስርዓት ይለያል፡፡ በአርባ ቀኗ ለፀሀይ ስትወጣ በትዳር ላይ ያለች በሙያዋ የታወቀች የመንደሩ ነዋሪ ትጠራለች፡፡ እሷም ወደ ምስራቅ ዞራ ትቀመጥና ጨቅላዋን ለማቀፍ ትሰናዳለች፡፡ እናቲቱ በአንድ እጇ ዘንባባና ህፃኗን ይዛ በመምጣት ታሳቅፋታለች፡፡ መጀመሪያ ጉልበቷ ላይ በኋላም ትከሻዋ ላይ ታስቀምጣታለች፡፡ ከዚህ በኋላ ህፃናቱ ወደቤት እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

ፓንዳዝርያችን በቁጥር ተመናምኗል፤ እንደውም

ለመጥፋት ጫፍ ደርሰናል ማለት ይቀለናል:: በቀደመው ጊዜ በብዛት እንገኝ የነበረው በእስያ አህጉር ነበር፡፡ አሁን ግን በቻይና በሶስት ስፍራዎች

ብቻ እንገኛለን:: የመኖሪያ ቦታችን የትና እንዴት እንደምንኖር ታውቁ ይሆን? ብታውቁም ባታውቁም ብንነግራችሁ አይከፋም:: በቀርከሃ ደን የተሸፈኑ ቦታ ላይ ነው መኖሪያችን:: የምንመገበውን ገምቱ ብንላችሁ ብዙም የሚከብድባችሁ ጥያቄ አይመስለንም:: የቀርቅሃ ደን ውስጥ ከኖርን ከደኑ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ግምት መገመት ትችላላችሁ? ገመታችሁ? አዎን የምንመገበው የቀርቀሃ ቅጠል ነው ለሰውነታችን ተፈላጊና በቂ የሆነ ጥቅም ከምንመገበው ቅጠል ለማግኘት ከ10-12 ሰዓቶች ቆይታ ያለው የገበታ ጊዜ አለን፡፡ ምግብ ለመብላት ይሄን ያህል ሰዓት መውሰዳችን ሳያስገርማችሁ አይቀርም፡፡ ሆኖም ግን ሁልጊዜ ይህን ያህል ሰዓት የምንመገበው የቀርቀሃ ቅጠል የማናገኝበት ጊዜ አለ፤ ይሄ የሚከሰተው ድርቅ ሊከሰት በመሆኑ ለእኛ ከቁጥራችን መመናመን ጎን ለጎን የሚያሰጋን ድርቅ ነው፡፡

ከሰሞኑበየጊዜው የሚወጡ ህትመቶች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ብሮድካስት ባለስልጣን

አስታወቀከየካቲት 2001 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2004 ዓ.ም

ድረስ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ወስደው የተመዘገቡ በየጊዜው የሚወጡ ህትመቶች ማለትም ጋዜጦችና መፅሄቶች ቁጥር እያሽቆለቆለ እንደሆነ መረጃዎች አመለከቱ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተቋቋመበትን 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ያሳተመው ‹‹መገናኛ ብዙሀን›› በተሰኘው ልዩ ዕትም መፅሄት ላይ እንደገለፀው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከባለስልጣኑ የምዝገባ ሠርተፍኬት ወስደው የነበሩት ጋዜጦች 89 የነበሩ ሲሆን በ2004 ዓ.ም መጨረሻ ቁጥሩ ወደ 25 ሲያሽቆለቁል የመፅሔቶች ቁጥር ከ137 ወደ 31 ወርዷል፡፡

ከነዚሁ በየጊዜው ከሚወጡ የህትመት

ውጤቶች መሀከል 22 ጋዜጦች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ህትመት ለማውጣት ባለመቻላቸው የምስክር ወረቀታቸው የተሰረዘ ሲሆን 57 መፅሔቶችም ተመሳሳይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

የምዝገባ ምስክር ወረቀት ወስደው ከአንድ ዓመት በታች ስርጭት ያልጀመሩት 10 ጋዜጦችና 15 መፅሄቶችም ሲሆኑ ስርጭት ጀምረው ያቋረጡት 33 ጋዜጦችና 33 መፅሄቶች እንደሆኑ የባለስልጣኑ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት 64 ጋዜጦችና 106 መጽሄቶች ከህትመት ውጪ መሆናቸው እንጂ ለምን ህትመት እንዳቋረጡ የባለስልጣኑ መረጃ አልጠቀሰም፡፡

Page 27: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

27

ከሰሞኑ

ዲያና የውበትና የፀጉር ሥራ ማሰልጠኛ ተቋም

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከቤተ መንግስት ጋራዥ ጀርባስልክ፡- 011-1-116003/ 0911-606133/ 0912-077670

የ3 ወር የ6 ወር እና ልዩ የ1 ወር ከ15 ቀን ሥልጠና እንሰጣለን፡፡

- በከተማችን ውስጥ የረጅም ጊዜ የማሰልጠን ልምድ ያለው- ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን የሚሸፍን - በቂ የመለማመጃ ጊዜና ቦታ ከብቁ መምህራን ጋር የሚያሰለጥን- በከተማችን በጥራት በማስተማር እጅግ ተደናቂነት ያተረፈ ተቋም

ተመዝግበው ብቁ የውበት ባለሙያ ይሁኑ!ሙሉ ዕውቅና

ያለው

ለ2005 ዓ.ም ምዝገባ ላይ ነን!

ማን፡- ዲጄ ሴንክና የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር

ምን፡- ምስለ ሠርግ ስነ-ስርዓት መቼ፡- መስከረም 27 ቀን 2005የት፡- በኮከብ አዳራሽ ፍቺ ለምኔ በሚል መሪ ቃል አንጋፋ ባለትዳሮችና

ትዳር ለመመስረት የተዘጋጁ ተጋቢዎች በአንድ አዳራሽ የተገኙበት የሠርግ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

በዲጄ ሴንክና በአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በጋራ በኮከብ አዳራሽ የተካሄደው ይህ ስነ-ስርዓት 50 ዓመትና ከዚያ በላይ የኖሩ የትዳር ጥንዶች ታድመው ታይተዋል፡፡ እንዲሁም በያዝነው አዲስ አመት ትዳር ለመመስረት የወሰኑ እጩ ሙሽሮች ተገኝተዋል፡፡

በአዳራሹ አንጋፋ ባለትዳሮችና አዲስ ተጋቢ

‹‹ፍቺ ለምኔ›› የሠርግ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ሙሽሮች አምረውና ደምቀው ታይተዋል፡፡ በሀገር ባህል አልባሳት፣ በቬሎና በሱፍ አልባሳት ከመታየትና ከመገኘት ባሻገር የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ በተለይ ከ50 ዓመትና ከዚያ በላይ በሶስት ጉልቻ ተጣምረው ከግማሽ እድሜያቸው የበለጠውን ሳይለያዩ እንዴት ሊያሳልፉ እንደቻሉ፤ የተናገሩት አንጋፋ ጥንዶች ነበሩ፡፡

አምስት አንጋፋ ባለትዳሮችና 50 አዲስ ተጋቢዎችን ያሳተፈው ይህ ዝግጅት እንዴት እንደተወጠነ አዘጋጁ ንግግር በዕለቱ አድርጎ ነበር፡፡ ዲጄ ሴንክ እንደተናገረው የትዳር መፍረስ በሀገራችን እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህ ስለምን ይሆናል በሚል የተቆርቋሪነት መንፈስ ሀሳቡን በተግባር ለመለወጥ መነሳቱን ገልጿል፡፡

በፍቺ ለምኔ ዝግጅት ላይ ክቡር ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በቪድዮ በአዳራሹ ለተገኙት አንጋፋ ባለትዳሮችና ሙሽሮች ንግግር አድርገዋል፡

፡ በዕለቱም በክብር አንግድነት የአርበኞች ማህበር ሊቀመንበር ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ዮሀንስ ጣሰው፣ የህፃናትና ወጣቶች አስተዳደር ቢሮ ተወካይ ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ አንጋፋዎቹና አዲስ ሙሽሮች በአንድነት ኬክ ቆርሰዋል፡፡ 10 ሜትር ይረዝማል የተባለውን ይህን ኬክ በተመሳሳይ ወቅት የቆረሱ ሲሆን በአዳራሹ ተገኝቶ የነበረው የሙዚቃ ቡድን በርካታ የሠርግ ዘፈኖች ተጫውተው ታዳሚውን ጭምር አስጨፍረዋል፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባ የወጣቶችን ማህበርን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራን፣ ውዳሴ ማህበርን፣ ኮከብ አዳራሽን፣ ዋቢሸበሌ ሆቴልን፣ሀበሻ የባህል ማዕከልን፣ ሀኒ ዲኮርንና ሀበሻ ቱር፣ አዲካ ቱርና መኪና ኪራይንና ሌሎችንም ላደረጉልን ቀና ትብብር ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲል ዲጄ ሴንክ ተናግሯል፡፡

Page 28: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

28

‘‘በ ላ - ል በ ል ሃ ! !

የደራሲያን ማህበር ቴምብር- ለባንዳ?የ

ኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በቅርቡ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመተባበር የአራት ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ደራሲያንን ምስል የያዘ ቴምብር ስለማሳተሙ

በመገናኛ ብዙሀን ተዘግቧል፡፡ በእርግጥ በዕለቱም በስፍራው ተገኝቼ የቴምብር ምርቃት ሥነ ሥርዓቱን ተከታትያለሁ፡፡ በወቅቱ ለዚሁ ዝግጅት ተብሎ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የተዘጋጀው የአራቱን ደራሲያን ታሪክ የያዘ በራሪ ወረቀት ተበትኖ ስለነበር አይኔ እንደገባ በቀዳሚነት የተመለከትኩት የነጋድራስ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስን ታሪክ ነበር፡፡

የደራሲያን ማህበር የደራሲያንን ምስል የያዘ ቴምብር ከፖስታ ቤት ጋር በመነጋገር ሲያሳትም ይህ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም፡፡ ከአሁኑ በፊት ለሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፣ ለከበደ ሚካኤል፣ ለስንዱ ገብሩና ለሀዲስ አለማየሁ ማሳተሙ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ለብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ስላሴ፣ ለተመስገን ገብሬ፣ ለቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ እና ኢትዮጵያዊ ካባ ለተደረበላቸው ለነጋድራስ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ነው ያሳተመው፡፡

ደራሲያን ማህበር አዘጋጅቶት በአዳራሹ ለምንገኘው ሰዎች የተበተነው የነጋድራስ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ታሪክ እኔ ከማውቀው ብቻ ሳይሆን ብዙዎቹ የስነ ፅሁፍ ሰዎች ከሚያውቁት የተለየ ታሪክ ነው፡፡ ማንም ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ሥነ ፅሁፍ ተምሮ የወጣ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው እኝህ ዛሬ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርና በመንግስታዊው ተቋም ፓስታ ቤት ትብብር ቴምብር የታተመላቸው ‹‹ደራሲ›› አፈወርቅ ገ/እየሱስ ኢትዮጵያን የወጉና በባንዳነታቸው ሀገር ያወቃቸው ፀሐይ የሞቃቸው ሰው ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ልቦለድ መፅሐፍ ‹‹ጦቢያ›› ደራሲ ተብለው የሚሞካሹት እኝህ

ሰው ክብሩን ያገኙት በድርሰታቸው ብቃት ወይስ ከማንም ቀድመው መፅሐፍ በማሳተም በመቻላቸው ነው? የሚለውን መከራከሪያ ወደጎን ትቼ ስለግለሰቡ ስብዕናና ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ለማፈራረስና ለማጥፋት ከተነሱ ሰዎች ጋር ያደረጉትን ትብብር እውነታውን ለማያውቁት ሁሉ ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

በዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ የተዘጋጀው ‹‹አጭር የኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ›› የተሰኘው ጥራዝ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ለትውልድ ቦታቸውና ቅድሚያ የሚሰጡ ጠባብ አመለካከት የነበራቸው ሰው ናቸው፤ ለዚህም ነው አንድ ፅሁፍ ፅፈው ሲጨርሱ ከስማቸው ቀጥለው ‹‹ዘብሔረ ዘጌ›› ይሉ የነበረው፡፡

አፈወርቅ ዝንባሌያቸው ስዕል መሳል እንጂ ፅሁፍ መፃፍ አልነበረም፡፡ እ.ኤ.አ. በ1889 ወደ ስዊዘርላንድ ከተማ ከሌሎች ሁለት ወጣቶች ጋር ተልከው የነበረ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያት ከስዊዘርላንድ ወደ ጣሊያን ገብተው ትምህርታቸውን የተከታተሉት

በቱሪን ከተማ ነበር፡፡ ጣሊያን ተምረው ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የሥዕል እንጂ የድርሰት ሙያ ይዘው ባለመምጣታቸው እቴጌ ጣይቱ አዲስ ያሰሩትን እንጦጦ የሚገኘውን የራጉኤል ቤተክርስቲያን በስዕል እንዲያስጌጡላቸው ነበር ያዘዟቸው፡፡ አፈወርቅ ግን የእቴጌይቱን ትዕዛዝ በአፋቸው ባይቀበሉም በልባቸው ውድቅ አድርገውት ነበርና ከሀይማኖት ደንባችንም ሆነ ከሞራል ሥርዓታችን ጋር በማይሄድ መልኩ ነበር ስዕል ለመሳል ወደ ቤተክርስቲያኑ ይገቡ የነበረው፤ ይኸውም ማንም ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው አንድ ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ ሲገባ ጫማውን ማውለቅ እንዳለበት የሀይማኖት ትምህርት ያዛል፡፡ አፈወርቅ ግን ጣሊያን ቱራን የተማሩ ‹‹ምሁር›› ስለነበሩ የቀሳውስቱን ማሳሰቢያ ወደጎን ትተው በጫማቸው ነበር ወደ ቤተመቅደሱ ይገቡ የነበረው፡፡

ይህ የድፍረት ስራቸው ታዲያ እቴጌይቱ ጋር ሲደርስ ‹‹ምነው›› ብለው ተቆጥተው ነው ያባረሯቸው፡፡ ታዲያ እኝህን ሀይማኖታዊ ሥርዓት የሚያፈርሱ ለመጪው ትውልድም መጥፎ አርአያ

የሚያወርሱን ሰው ነው በቴምብር ለማስታወስ እየተሞከረ ያለው?

አፈወርቅ ከእቴጌ ጣይቱ ጋር ተጣልተው ወደ ጣሊያን ተመልሰው ከሄዱ በኋላ በመምህርነት መስራታቸውን ነው ታሪካቸው የሚያስረዳው፡፡ ከ10 ዓመታት በኋላ ግን ወደ ኢትዮጵያ መመለሻቸው ሲደርስ የተመለሱት ወደ መሀል ሀገር ሳይሆን ወደ አስመራ ነበር፤ ለመሆኑ ነጋድራስ ወደ መሀል ሀገር ከመመለስ ይልቅ በወቅቱ በጣልያን አስተዳደር ስር ወደነበረችው ወደ ኤርትራ ለምን ለመሄድ እንደፈለጉ የቴምብር አሳታሚዎቹና ሀሳብ አቅራቢዎቹ ያውቁ ይሆን? መልሱ ቀላል ነው፤ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለጣሊያን መንግስት ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት መግለፃቸው ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ጥሩ ማስረጃ የሚሆነው በአስመራ ቆይታቸው ወቅት ይፅፏቸውና በየጋዜጦቹ ያሳትሟቸው የነበሩት ፅሑፎች ስለ አንድነት የሚገልፁ ሳይሆን መለያየትንና ቅኝ ተገዥነትን የሚሰብኩ መሆናቸው ነበር፡፡ በፅሑፋቸው ተቆጥተው በተደጋጋሚ ምላሽ ይሸጧው ከነበሩት ከብላቴ ገ/እግዚአብሔር ጋር ያደረጓቸው ክርክሮች ለኢጣሊያ መንግስት ያላቸውን ድብቅ ፍቅር ገሀድ ነጋድራስ አፈወርቅ ገ/የሱስ

ተመስገን ገብሬ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ስላሴ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ

በምግባሩ አፈወርቅ (ከ6 ኪሎ)

Page 29: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

29

በ ላ - ል በ ል ሃ ! !

ያወጣ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ታሪክ የፖስታ ቤትና የደራሲያን ማህበር ሰዎች አያውቁም ወይስ ለማወቅ አይፈልጉም?

ዛሬ ሀገራችን ከምትኮራባቸው ሌሎች ኢትዮጵያውያን ደራሲያን ጋር ታሪካቸውና ምስላቸው ታትሞ የክብር አክሊል የተደፋባቸው አፈወርቅ ኢትዮጵያን በመከፋፈል ረገድ ከተጠነሰሰው ሴራ ውስጥ እጃቸውን ያስገቡት በብዕራቸው ብቻ ሳይሆን የስልጣን ጥማቸውን መከታ አድርገው ጭምር ነበር፡፡ ከእቴጌ ይቱ ህልፈት በኋላ ወደ መሀል ሀገር ሲጠሩ የመጡት አፈወርቅ የስልጣን ክፍተት እንዳለና ሹመት ፈልገው ነበር፡፡ እንደፈለጉትም የድሬዳዋ ጉምሩክ ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙ ጊዜ ነጋድራስ የሚለውን የማዕረግ ስም በስማቸው ላይ የጨመሩትም ያን ጊዜ እንደሆነ መዛግብት ይገልፃሉ፡፡

የነጋድራስ አፈወርቅ ኢትዮጵያን መጥላትና የማፈራረስ ስትራቴጂ እቅዳቸው ጎልቶ የወጣው በ1928 ቱ የጣሊያን ዳግም ወረራ ወቅት ነበር፡፡ አፈወርቅ ጣሊያን ሀገራችንን በወረረበት ወቅት አርበኞች ሕዝቡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ የጠላትን ሴራ ለማክሸፍ ሲዋጋ አፈወርቅ ምን ያደርጉ እንደነበር የቴምብር አሳታሚዎቹ ያውቁ ይሆን? አፈወርቅ በዚያ ኢትዮጵያዊነት በሚፈተንበት ቀውጢ ሰዓት ከኢትዮጵያ አርበኞች ጋር በዱር በገደሉ አብረው ከመዋጋት ይልቅ አርበኞች እጃቸውን ለፋሽስቱ ጣሊያን መንግስት እንዲሰጡ ነበር ይቀሰቅሱ የነበረው፡፡ ታሪክ የአፈወርቅን ገድል እንዲህ መዝግቦት እናገኛለን፡፡

አፈወርቅ በወቅቱ ባላቸው የሥነ ፅሁፍ ችሎታ ተመርጠው ለኢጣሊያን መንግስት የፕሮፓጋንዳ አገልግሎት የሚሰጥ ጋዜጣ ያዘጋጁ ነበር፡፡ የጋዜጣው ስም ‹‹የቄሳር መንግስት መልዕክተኛ›› የሚሰኝ ሲሆን የጋዜጣው ዋጋ አዘጋጅ ሆነው የኢትዮጵያ አርበኞችን ትግል የሚያንኳስስና ሞራል የሚያዳክም ታሪኮችን ያፅፉ ነበር፡፡ በዚህም አገልግሎታቸው ለሀገር ተወላጆች ይሰጥ የነበረውን ትልቁን ሹመት ‹‹አፈ ቄሳር›› የሚለውን ከጣሊያን መንግስት አግኝተው ነበር፤ ታዲያ ከዚህ የበለጠ ባንዳነት ከወዴት አለ?

ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላየሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ›› ያለው ማን ነበር? እነ በላይ ዘለቀን የመሳሰሉ

ኢትዮጵያዊ አርበኞች ለውለታቸው መሰቀላቸው ሲገርመን ዓመታት ተቆጥሮ ባንዳ የሚሞገስበት ዘመን ላይ ደረስን?

በአምስቱ ዓመት የጠላት ወረራ ወቅት የአፈወርቅ ብዕር ኢትዮጵያውያን አርበኞች በጣሊያን ወታደሮች በብዛትና በግፍ እንዲፈጁ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ ለመሆኑ የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር የዚህ አይነት ሸፍጥ በቴምብር መታሰቢያ ሰበብ ሲፈፅም ምነው ዝም አለ? ነው ወይስ የአባትህ ቤት ሲዋረድ አብረህ ተሰለፍ ነው ነገሩ?

አፈወርቅ በዚሁ ጋዜጣቸው ላይ ከሚያሰፍሩት መራዥ አስተሳሰብ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያውያን አርበኞችን የአልገዛም ባይነት ስሜት ማኮሰስ ብቻ አልነበረም፡፡ ይልቁንም በሊግ ኦፍ ኔሽን ላይ ተገኝተው ታሪካዊ የተባለውን ንግግር ያደረጉትን ቀዳማዊ አፄ ሀይለ ስላሴን የሚያዋርድና ክብራቸውን የሚነካ ፅሁፎችን በመፃፍ የጣልያን መንግስትን አቋም በሚገባ አንፀባርቀዋል፡፡ ከዚህ ታሪካዊ የባንዳ ፅሁፍ ምሳሌ መጥቀስ ለእማኝነት ያግዛልና እነሆ፡-

‹‹የጥንት ጌታዬ ያጤ ኃይለ ስላሴ ነገር በጣም ያሳዝናል፤ በጣም ይገርማል፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ይላል ተረቱ ወይ መካሪ ማጣት? ያልታደ ሉት ንጉስ አጤ ኃይለስላሴ ተቀድሞ ጀምረው የታመነ ብልህ የወገኑ ተናጋሪ መካሪ ባጠገባቸው አጥተው የክፉዎችን የጉቦ ጉድጓድ የሆኑ ባለሟሎቻቸውንና ባለ ደሞዝ የወጪ አገር ሰዎች የሚመክሩትን አጉል ምክር ስለተከተሉ ይኸው ዛሬ ይህን መንግስታቸውን ጥለው ተሰደዱ፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለው አፋቸውን ጠቅመው አንደበታቸውን አለስልሰው ከተሰደዱበት እንዳይቀመጡ የማይረባ ትርፍ የማይገኝበት ክፉ ምክር እየሰጡ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ኒውስ በተባለ ጋዜጣቸው ላይ አለአቅማቸው በድፍረት የኢጣሊያን ነቀፌታ ደግመው ደጋግመው እንዲለቁ አድርገዋቸዋል፡፡ ጉሮሮ የሚውጠውን ይመጥነዋል ይባል ነበር፤ እነዚህ አማካሪዎቻቸው ግን ለጉሮሮና ለምላስ የማለሰልሰውን የጠርሙስ እንክትካችና ስብርባሪ እየፈተፈቱ እነሆ ይዋጡ ከማለት ደረሱ፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ይጠቅማቸው ይሆን? አይመስለኝም፤ ሌላውም አይመስለውም››

ምንጭ፡- የቄሳር መንግስት መልዕክተኛ ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቁጥር 3 ነሐሴ 6 ቀን 1929 ዓ.ም ገፅ 5

ዛሬ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርና ፖስታ ቤት ያከበሯቸው ሰው የህይወታቸው የመጨረሻ ሰዓታትም ለፈፀሙት ግፍ የእጃቸውን ያገኙበትና የእግዚብሔርን ፍርድ የተቀበሉበት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ በ1964 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረው ዝቅአርጋቸው ኃይለጊዮርጊስ የነጋድራስ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስን የህይወት ታሪክ ላይ ተመስርቶ ባዘጋጀው

የዲግሪ ማሟያ ፅሁፍ ላይ እንደገለፀው ‹‹ከጠላት ወረራ በኋላ ነፃነት ሲመለስ ነው አፈወርቅ የኢጣሊያ መንግስት ዋና የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆነው በማገልገላቸው ተይዘው መጀመሪያ ለፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ መስቀል መኖሪያ ቤት ከታሰሩ በኋላ የፈፀሙት ወንጀል ተዘርዝሮ ለዳኞች ሲቀርብ ያንን ሁሉ አርበኛ በብዕራቸው ማስፈጀታቸውን ረስተው ጥፋተኛ አይደለሁም ነበር ያሉት፤ ግን ከዳኞች የሞት ፍርድ አላመለጡም፡፡››

የኋላ ኋላ ደግሞ እንደዚያ ሲያብጠለጥሏቸው ወደ ነበሩት ወደ ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዙፋን ችሎት ቀርበው ይግባኝ በጠየቁበት ወቅት ንጉሱ ከሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ነበር የቀየሩላቸው፡፡ አፈወርቅ ግን በትዕቢት የተሞሉ ሰው ስለነበሩ የንጉሱን ምህረት ከምንም አልቆጠሩትም ነበር፡፡ ሌሎች በአካባቢው የነበሩ ሰዎች እልል ብለው ንጉሱን ሲያመሰግኑ አፈወርቅ ዝም ነበር ያሉት፡፡ ‹‹ምነው?›› ሲባሉም ‹‹አፈወርቅ ይታሰር ተባለ እንጂ ይፈታ አልተባለም›› በማለት በንጉሱ ላይ ሊያላግጡ የሞከሩ ሰው ናቸው፡፡

አፈወርቅ ከፍርድ በኋላም ወደ ጅማ ተወስደው ለረዥም ጊዜ ታስረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥም በህመም አይናቸው ጠፍቶ የእግዚአብሔር ፍርድ የተቀበሉ ሰው ናቸው፡፡ የጤናቸው ሁኔታ እየተባባሰ ሄዶም መስከረም 15 ቀን 1939 ዓ.ም በ79 ዓመታቸው ማረፋቸው ነው ታሪካቸው የሚገልፀው፡፡

ታዲያ ለእኝህ የኢትዮጵያ አርበኛ ጠላት ነው ደራሲያን ማህበርና ፖስታ ቤት መታሰቢያ የሚያሳትመው? ደራሲያን ማህበርስ እሺ ምርቱን ከግርዱ ሳይለይ አባል ማድረግና መሸለም ልምዱ ነው፡፡ በህዝብ ግብር የሚተዳደረው ፖስታ ቤት ግን የህዝቡን ሀብት ለህዝብ ጥቅም ላዋሉ ሰዎች ማዋል ሲገባው ለባንዳ መጠቀሚያ ማድረጉ ምን ይባላል፤ ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ. . . ዛሬም ድጋሚ እናዚም ይሆን?

አቢሲኒያ የሥነ ጥበብና ሞዴሊንግ ማሰልጠኛ ተቋም

አድራሻ፡- ራስ መኮንን ድልድይ ሰባ ደረጃ ከፍ ብሎ ናዝሬት ስኩል ፊት ለፊት011-1-577570/ 0911-683399

ሥዕል

ቅርፃ ቅርፅ

ቴአትር

ሙዚቃ

ሞዴሊንግ

የፋሽን ዲዛይን

አጫጭር ስልጠናዎችለሙሽሮችና ለሚዜዎች

እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ልዩ የሠርግ ውዝዋዜና የቯልስ

ስልጠና እንሰጣለን!!- በግል መሰልጠን ለሚፈልጉ ውዝዋዜ፤ ቯልስ እና ዳንስ

እናሰለጥናለን!

ንድፍና ቀለም ቅብ

ልብስ ስፌት

ለሴቶችና ለወንዶች

ዘመናዊ መሳሪያፒያኖ፣ኪቦርድ፣ጊታርባሕላዊ መሳሪያ

ክራር፣ ማሲንቆ

- ዘመናዊ ዳንስ- ባህላዊ ውዝዋሴ- ድምፅ አወጣጥ

በጀሶ እና በሲሚንቶ

- ትወና/ አክቲንግ- እስክሪፕት አፃፃፍ- ዳይሬክቲንግ

Page 30: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

30

ከገፅ 11 የዞረ

ዩኒቨርሲቲው. . .

600 ብር የማይሞላ ይዞ የሚገባበት ጊዜ ላይ ነው የሚገኘው›› አሉ፡፡

ሌላው መምህር ደግሞ በሪፖርቱ ላይ የቀረበውን የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በሌላ መነፅር ተመልክተውት መጡ፡- ‹‹ለእኔ እስከሚገባኝ ድረስ በሪፖርቱ ውስጥ እንደመልካም አስተዳደር የቀረቡት የተማሪ 70-30 መቀበል፣ የሴቶች ተሳታፊነትን ማበረታታት . . . ወዘተ የፖሊስ አተገባበር እንጂ የመልካም ሥራ ተግባራት አይደሉም፡፡ መልካም አስተዳደር ማለት ለዓመታት ሲነገሩ የነበሩትን የመምህሩን ችግሮች መፍታት ማለት ነው›› ብለው ተቀመጡ፡፡

እንዲሁ ሌላው መምህር ደግሞ ተነሱ፡- ‹‹ስለመማር ማስተማር ሲነሳ መምህሩ የሌለበት መማር ማስተማር አለ ወይ? ዩኒቨርሲቲው ኮምፒውተር ገዝቶ እንኳን ለመምህራን ይሰጥ ሲባል እኮ የተገዛው ለመማር ማስተማሩ ተግባር ነው የሚል ምላሽ የሚሰጥ ፋኩልቲ አለ፤ እንዴ! ዛሬ እኮ ቢያንስ ኢንተርኔት በርካታ መረጃ የሚገኝበት ዘመናዊ ላይብረሪ ነው፤ መምህሩ የሚፈልገውን መቅታዊ መረጃ የሚያገኝበት መንገድ ተነፍጎ በጥራት አስተምር ማለት ትንሽ አይከብድም?›› የሚል ጥያቄ ሰነዘሩ፡፡

ለእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች የተለያዩ ምላሾች ከመድረኩ የተሰጡ ቢሆንም በዶ/ር ደብረፅዮን የተሰጠው ምላሽ ግን አዲስ ወይም ያልተለመደ ምላሽ ሆኖ ማነጋገር ጀመረ፡፡ ዶ/ር ደብረፅዮን የመምህራንን የኑሮ ችግር የአብዛኛው ጥያቄ መሆኑ ተገቢ አይደለም በሚል ሀሳብ ጀመሩ፡-

‹‹የደመወዝ ጥያቄን አስመልክቶ የምታነሱት ጥያቄ ከእናንተ መምጣቱ አስገራሚ ነው›› አሉና ዶ/ር ደብረፅዮን ‹‹እናንተ እኮ ራሳችሁ ገንዘብ ናችሁ፡፡ እናንተ ሰው መቅጠር ሲገባችሁ መንግስትን ደመወዝ ጨምር ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ አሁን ተቀጥራችኋና ደመወዝ መጠየቃችሁ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ይህ ሥርዓትን ይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡ መንግስት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚፈቅደውን ለሁሉም ለማድረግ ፍቃደኛ ነው፡፡ ነገር ግን እናንተ ደግሞ ምሁራን ናችሁና ለምሳሌ ለምን የኮንሰልታንሲ ሥራ አትሰሩም? ደግሞ ይህን ስል 2ሺህ መምህር በዘመቻ መልክ ውጡና ሥራ ፈልጉ እያልኩ አይደለም፣ ተማሪውን ትምህርት ቤት አስገብታችሁ እናንተ ሥራ ፍለጋ ትዞራላችሁ ማለቴም አይደለም፡፡ ነገር ግን በርካታ ገቢን የሚደጉሙ ስራዎችን የመስራት አቅም አላችሁ እያልኩ ነው. . .

‹‹አንድ መምህር ደግሞ አፍሪካ ሀገር የሚገኝ ሌክቸረር የሚያገኘውን ከራሳቸው ጋር እያነፃፀሩ ሲያቀርቡ እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ከእናንተ ይመጣል ብዬ ተገርሜያለሁ፡፡ እኔ ሚኒስትር ሆኜ እዚህ ኬንያ ያለ ሚኒስትር ስንት እንደሚከፈለው እያወቅሁ ራሴን ከዚያ ጋር ማነፃፀር ልጀምር ማለት ይሆናል እኮ!. . . ›› በማለት ዶ/ር ደብረፅዮን ማራሪያቸውን ቋጩ፡፡

ለዚህ የሚኒስተሩ የዶ/ር ደብረፅዮን አስተያየት ሌላው መምህር አፀፋዊ ምላሽ የሰጡት ደግሞ በሚከተለው መንገድ ነበር፡- ‹‹ሚኒስትሩ ሲነግሩን ራሳችሁን ከአፍሪካ ሀገር ሌክቸረር ጋር አታወዳድሩ አሉን፡፡ ለመሆኑ የእኛ ሀገር ሚኒስትር የቤት ኪራይ፣ የመብራት፣ የውሃ ይከፍላል? ታፔላ አይቶስ ከታክሲ ጋር ሲሯሯጥ ይውላል? ቢሮ የሌለውስ ሚኒስትር እዚህ ሀገር አለ? እዚህ ላይ እንነጋገር ከተባለ ሚኒስትር እኮ የፖለቲካ ሥራ የሚሰራ እንጂ

አካዳሚሺያን አይደለም፡፡ የአካዳሚ ሥራ ማንበብ፣ መፈተሽ፣ ማጥናት፣ መመራመር ይፈልጋል፡፡ ይሄን ታዲያ በባዶ ሆድ እንዴት እንችለዋለን?››

በእንዲህ አይነት ሁኔታ የመጀመሪያው ክፍል ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላ ከሰዓት የሚቀጥለው አጀንዳ በምን ላይ አተኩሮ ቤቱ መወያየት እንደሚገባው ከመድረኩ ገና ተነግሮ ሳያበቃ መምህራኑ ከሻይ እረፍት መልስ አዳራሹ ውስጥ የታደለችውን የምሳ ኩፖን ይዞ በግፊያ መውጣት ጀመረ፡፡ የምሳው ሰልፍ ሳይረዝም በቶሎ ለማንሳት እንደሆነ ቢገባንም ማንም በድርጊቱ ያፈረ አይመስልም፡፡ ቢያንስ የሦስት ቀን ምሳውን የሚችለው አግኝቷልና፡፡

በቀጣዮቹ ፕሮግራሞች ሲሰነዘሩ የዋሉ ሐሳቦችም ከቀደመው የጠነከሩና አየሩን ያከበዱ እንጂ ውጥረቱን የሚያላሉ አልነበሩም፡፡ በተለይም በቀረበው የ2005 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ጥያቄና አስተያየት እንዲሰጥ የተጋበዘው የዩኒቨርሲተው መምህር አስተያየቱን የጀመረው የቀረበውን ዕቅድ በመተቸት ሳይሆን እንዲህ አይነት ዕቅድ አይተን አናውቅም በማለት ነበር፡፡

አንዱ መምህር እንዲህ አሉ፡- ‹‹በዕቅድ ላይ ተወያዩ ተብለናል፡፡ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ግን የቀረበ ዕቅድ አላየሁም፡፡ እንዲህ አይነት ዕቅድ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሲወጣም ያሳፍራል፡፡ በአጭሩ ይህ ዕቅድ ሳይሆን ምኞት ነው›› አሉና በማከልም፡- ‹‹ላለፉት ስድስት ዓመታት ‹የለውጥ ዕቅድ› ሲባል ሰምተናል፡፡ ይህ የ‹ለውጥ ዕቅድ› የሚባለው ነገር ለመሆኑ የሚቆመው መቼ ይሆን? Pretext አይደለምን?›› በማለት ተቀመጡ፡፡

ሌላው መምህር ደግሞ ዕቅዱን የተቹት፡- ‹‹ለመሆኑ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲንና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የሚለየው ምንድነው?›› በማለት ነበር ‹‹ዕቅድ በትምህርት ሚኒስቴር ወጥቶ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲ በኮፒ የሚታደል ከሆነ አንዱን ዩኒቨርሲቲ ከሌላው የሚለየውን ማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ለመሆኑ ዛሬ የቀረበልን የትምህርት ሚኒስቴር ዕቅድ ነው ወይስ የዩኒቨርስቲው?. . . በየዓመቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን የሚያህል ተቋም ዕቅድ የሚሰጠውስ ለምንድነው?››

‹‹አብዛኛው የቀረበው ዕቅድም ሆነ ውጤት ማኔጅመንት ላይ ያተኮረ እንጂ ከመማር ማስተማሩ ጋር የተገናኘ ወይም መምህራንን ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም፡፡›› ያሉት ሌላው መምህር ደግሞ፡- ‹‹የደመወዝ ጭማሪ፣ የመኖሪያ ቤት ችግር. . . አትጠይቁ እየተባልን ነው፡፡ ዩኒቨርስቲው በሚሰጠን የ300 ብር የቤት አበል ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ እንኳን የሰው የዶሮ መኖሪያስ ማግኘት ይቻላል?›› የሚል ጥያቄ አቀረቡ፡፡

የቀረበው ዕቅድ ከአዳራሽ ሰፊ ትችት እንደቀረበበት በግልፅ የታየ ነበር፡፡ ‹‹ዕቅድ ተብሎ የቀረበው ፅሁፍ በማንኛውም መመዘኛ ዕቅድ ተብሎ ሊጠቀስ አይገባውም›› ያሉ አንድ መምህር፡- ‹‹እስከሚገባኝ ድረስ ዕቅድ ማለት ጥናት ማለት መሰለኝ፤ በዚህ ዩኒቨርሲቲ ለረዥም ዓመታት እንደመኖሬ መጠን ዩኒቨርስቲው የፕላኒንግ እና ስትራቴጂ ቢሮ እንደነበረው አስታውሳለሁ፤ በዚህ ቢሮ ውስጥ ከቢዝነስና ኢኮኖሚ ክስ ፋኩልቲ ታዋቂ ዕቅድ አውጪዎች እየተፈለጉ ነበር ፕላኑን የሚያወጡት፡፡ ለመሆኑ ይህ ቢሮ ዛሬ በሌለበት ሁኔታ ይህን ዕቅድ ተብሎ የቀረበውን ነገር የሰራው ባለሙያ ማነው?›› የሚል ብዙዎችን ያስደነገጠ ጥያቄ

በቀጣዮቹ ፕሮግራሞች ሲሰነዘሩ የዋሉ ሐሳቦችም ከቀደመው የጠነከሩና አየሩን ያከበዱ እንጂ ውጥረቱን የሚያላሉ አልነበሩም፡፡ በተለይም በቀረበው የ2005 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ጥያቄና አስተያየት እንዲሰጥ የተጋበዘው የዩኒቨርሲተው መምህር አስተያየቱን የጀመረው የቀረበውን ዕቅድ በመተቸት ሳይሆን እንዲህ አይነት ዕቅድ አይተን አናውቅም በማለት ነበር፡፡

Page 31: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

31

ከገፅ 13 የዞረ

ፊልም . . .

original music)የማርሴሎ ማስትሮያኒ

ሽልማት(the marcello mastroianni award)

ይህ ሽልማት ጣልያውያኑ የምንጊዜውም ምርጥ ተዋንያናችን ብለው በሚያስቡት ማርሴሎ ማስትሮያኒ ስም የተሰየመነ ከ እ.ኤ.አ 1998

ጀምሮ በየአመቱ ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ጀማሪ ተዋንያን የሚሸለሙት ሽልማት ነው፡፡

የወጣቶች የፊልም ሽልማት(youth cinema

award)ይህ ሽልማት ወጣቶች በሲኒማው አለም

ውስጠ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት ሲባል አ.ኤ.አ 2004 ጀምሮ የተጀመረ ሽልማት ሲሆን በየአመቱ ከፈረንሳይ፤ካናዳ፤ፖላንድ፤ሃንጋሪናጣልያን ውስጥ ከ18-25 አመት የሆናቸው ወጣቶች የተሰበሰቡበት የዳኞች ኮሚቴ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ አሽናፊዎችን

ይመርጣል፡፡ ይህን ሽልማት ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርገው በየአመቱ ለውድድር የሚቀርኑት ዘርፎች ፍጹም የተለያዩና በአንድ አመት የነበረ ዘርፍ በሚቀጥለው አመት አለመደገሙ ነው፡፡

ለማጠቃለልም ያህል የቬኒስ ፌስቲቫል ወደ 80ዎቹ በሚጠጋ የእድሜ ቆይታው ከላይ ያየናቸውንና ሌሎችም ሽልማቶችን ይዞ በየአመቱ ታላላቅ ስራዎችን እያሞገሰና እያበረታታ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሽልማት ለአውሮፓውያን እንደሚያደላ በአንዳንዶች ዘንድ ቢታማም በሲኒማው ዘርፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ ግን የማይካድ ነው፡፡ የቬኒስ ፊልም ፌስቲቫልን ጉዳይ በዚሁ ባይቋጭም ለአንባቢያን በቂ መረጃን እንደሚሰጥ ተስፋ በማድረግ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ወደ ሌላ ታላቅ ፌስቲቫል ጉዞአችንን እንቀጥላለን፡፡

አስከተሉ፡፡‹‹ዕቅዱ ለክልልና ለአርብቶ አደሩ ትኩረት

እንሰጣለን ይላል›› በማለት ሐሳባቸውን መሰንዘር የጀመሩ ሌላ መምህርት ደግሞ፡- ‹‹ለመሆኑ ስንቱ የአዲስ አበባ ተማሪ ነው ብለቶ የሚያድር? እኔ በችግር ምክንያት ያቋረጡ ሁለት ተማሪዎች አሉኝ፡፡ የሳሙናና የሞዴስ እንኳን የሚያጡ በርካታ ሴት ተማሪዎች እንዳሉም አውቃለሁና ዕቅዱ በአንድ እጅ ማጨብጨብ እንዳይሆን›› አሉ፡፡

‹‹ዕቅዱ የመማር ማስተማሩን ችግር ቢያንስ መፍትሔ የሚጠቁም ቢሆን መልካም ነበር›› ያሉት ሌላው መምህር ደግሞ፡- ‹‹በትምህርቱ ዘርፍ ትልቁ ችግር ሆኖ የሚታየን የተማረው የመማር ፍላጎት ደካማ መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል›› አሉ፡፡ መምህሩ አክለውም፡- ‹‹ተማሪው ምን እሆናለሁ፣ ምን ይመጣብኛል የሚልና ሌላ የሚመካበት ሽፋን ያለው መስሎ መምህራን እንዲሰማን ይሞክራልና ቢያንስ የተማሪዎች Code of conduct የሚወጣበት ሥራ ቢታሰብ መልካም ነበር›› በማለት ወደወንበራቸው ተመለሱ፡፡

እንግዲህ ከብዙው በጥቂቱ በዩኒቨርሲቲው የ‹‹ስልጠና›› ስብሰባ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ይህን ሲመስሉ ከመድረክ የተሰጣቸው ምላሽ ደግሞ እንደተለመደው አጭርና ግልፅ ነበር፡፡ የመምህራን የኑሮና በተለይም የቤት ችግር የማይካድ እውነታ መሆኑን የተቀበሉት ዶ/ር ደብረፅዮንና የዩኒቨርስቲው አመራሮች መንግስት የደመወዝ እና የመኖሪያ ቤት ችግርን በተናጠል ለአንድ ዩኒቨርሲቲ መፍትሔ መስጠት ሳይሆን ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር በተገናዘበ መልክ ወደፊት የሚታይ እንደሆነ፤ የቤት ችግርም እንዲሁ የዩኒቨርሲቲው መምህራን በማህበር እየተደራጁና ዩኒቨርስቲውም የራሱን የቤት አቅም እየገነባ ለመፍታት የሚሞክር መሆኑን ሌሎቹም ጥያቄዎች እንዲሁ በሂደት መንግስት ለመፍታት የሚሰራባቸው ይሆናሉ አሉ፡፡ እቅዱንም አስመልክቶ በጥቅሉ የዩኒቨርሲቲውን የወደፊት ጉዞ ለመጠቆም ያህል እዚህ ቀረበ እንጂ በዝርዝር ተሰርቷል አሉ፡፡

ሀይማኖትና አክራሪነትበሁለተኛው ቀን ውይይት በሀይማኖት

አክራሪነት ዙሪያ አንድ ግለሰብ ፅሑፍ አቀረቡና ቤቱ እንዲነጋገርበት ተጋበዘ፡፡ ግለሰቡ በፅሑፋቸው ሀይማኖትና መንግስት የተለያዩ መሆናቸውንና ይህም በሕገ መንግስቱ መረጋገጡን አስታውሰው ይሁንና በአንዳንድ ሀይማኖቶች አክራሪነት እየታየ በመምጣቱ በዚህ ረገድ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የምሁሩ ክፍልም መውሰድ እንደሚገባው የሚያስጠነቅቅ ሀሳብ ያዘለ መልዕክት በፅሑፋቸው አስተላለፉ፡፡

እዚህ ላይ ሊጠቀስ የሚገባው ቁም ነገር ቢኖር አቅራቢው በጉዳዩ ላይ ያላቸው ዕውቀት ምን ያህል የጠለቀ ነበር? የሚለው ይሆናል፡፡ በተለይም በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ከእሳቸው ይልቅ የጠለቀ ምርምር ያደረጉና ያበረከቱ ብሎም ያነበቡ ምሁራን ለሚገኙበት አዳራሽ የዛሬ ዓመት ያቀረቡትን ወረቀት ትንሽ አሰማምረው ለማቅረብ ሲመጡ ቢያንስ ቤቱን የናቁት አስመስሎ ሳያሳይባቸው አልቀረም፡፡ ለማንኛውም በሃይማኖት አክራሪነት ዙሪያ በቀረበው ወረቀት ላይ ቤቱ አስተያየት ተጋብዞ የተሰጡ አስተያየቶችና ትችቶች በርካታ ቢሆኑም በዋናነት ሊጠቀሱ የሚገባቸውን ጨምቀን በማቅረብ እንሰናበት፡፡

- በመጀመሪያ የሀይማኖት አክራሪነት እንደ ችግር ተነስቶ ለውይይት መቅረቡ ጉዳት

ባይኖረውም ለችግሩ መባባስ የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ የሚገኘውን አካል መንግስት ለይቶ ማወቅ የቻለ አይመስልም፡፡ ለምሳሌ በሚዲያ የምንጠቀመው አክራሪ፣ ትምህተኛ፣ ጠባቦች. . . ወዘተ የሚለው ቋንቋ ችግሩን የሚያባብስ ነው ወይስ የሚያረግብ?

- ለመሆኑ አክራሪነት መገለጫው ሀይማኖት ብቻ ነው ወይስ ፖለቲካዊ አክራሪነትም አለ፡፡ መንግስት የሚሰራውን በዕውቀት ላይ ካልመሰረተ አደጋው ብዙ ነው፡፡ መንግስት የጠላውን የሚጠላ፣ የሚወደውን ደግሞ የሚወድ ካድሬ በዩኒቨርሲቲው እንዲፈለፈል አቅዶ ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በእርግጥ እንዲህ አይነት ካድሬዎች እየተመለመሉ በደብዳቤ ሌክቸረር እየተባሉ እንደተቀጠሩም እናውቃለን፡፡

- ሕገ መንግስቱን ላሉት ችግሮች ሁሉ እንደ መፍትሔ (Panacea) አድርገን የምንወስድ ከሆነም ትልቅ ችግር ነው፡፡ እንግሊዝ የተፃፈ ሕገ መንግስት የሌላት ሀገር ሆና ነገር ግን ማንኛውም ዲሞክራቲክ ሀገራት በሕገ- መንግስታቸው ያሰፈሯቸውን መብቶችና ነፃነቶች በሙላት የሚገኙባት ሀገር ናት፡፡ ስለዚህም ለችግሮች መፍትሔ መስጠት የሚቻለው በዕውቀት እንጂ በፕሮፓጋንዳ አይደለም፡፡

- መነጋገር ባለንባቸው ነገሮች ላይ በግልፅ እየተነጋገርን አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቀይ መስመር (Red lines) ስለሆነ እሱን አልፈን መሄድ አንችልም፡፡ ስለዚህ ተቀምጠን ሰምተን ምሳ በልተን እንሄዳለን፡፡ የችግሩ መንስኤ እኮ ያለው የፖለቲካው ሲስተም ላይ ነው፡፡ Access to resources and power እኮ በብሔር በመደራጀት ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያዊነት ብሎም በዕውቀት ሰዎች የሚገባቸውን ሥፍራ ለማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው?

- እናቴ አማራ አባቴ ኦሮሞ ቢሆን ምናልባት አማራ ሀገር ስሄድ አማራ፣ ኦሮሞ ሀገር ስሄድ ደግሞ ኦሮሞ ሆኜ ሊሳካልኝ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ወደ ሀይማኖት ስመጣ ሀይማኖት በጣም exclusivist ነው፡፡ ጠዋት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሄጄ ማታ መስጊድ መሄድ አልችልም እኮ! የሀይማኖት አክራሪነት የሚባለውን ነገር ከዚህ አቅጣጫ ቢፈተሽ፡፡

- ሰው ሁሉ ወደ ሀይማኖት የሚሄድ ሆኗል፡፡ ለምን ይመስላችኋል? ፖለቲካው ይሄን Stability የሚሰጥ አልሆነም፡፡ ሰው ውስጡ ሰላም ሲያጣ ይህንን ከአምላኩ ለመፈለግ ወደ ሀይማኖት ደጅ ይሄዳል፤ በዚያ ደግሞ ለብዙ ነገር ተጋላጭ ይሆናል፡፡

- በዚህች ሀገር በተለይም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በስፋት የሚታየው ችግር ምሁራዊ ቅንነት (Intellectual houesty) መጥፋት ነው፡፡ በሩቅ ሆኖ ለሚመለከትም ተቋሙ ዛሬ የፖለቲካ ትምህርት ቤት እንጂ የምሁር ተቋም አይመስልም፡፡ ለፓርቲ ስብሰባ ሲሮጥ የሚውል እንጂ ለምርምር ሲሄድ የሚታይም የለም፡፡

ወዘተ. . . . ወዘተ. . . . ወዘተ. . . .

በመጨረሻምየዚህ ‹‹አጭር›› መጣጥፍ መቅረብ ሦስት ዓለማ

ሰንቋል፡፡ የመጀመሪያው ዕድሜ ከሰጠን ከአስር ዓመት በኋላ ደግሞ ለትዝታ የምንጠቅሰው የዩኒቨርሲቲውን ታሪክ በአጭሩ ለማኖር ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ወደ ጥንቱ የምሁር ተቋምነቱ የሚመለስበትና በዩኒቨርሲቲው ሕግና ደንብ መሰረት ዕውቀቱ ተመዝኖ የተቀጠረው፣ ከመንግስት ሹመኛ በሚፃፍ ደብዳቤ ሌክቸረር እየተባለ ከሚቀጠረው ጋር ተቀላቅሎ ችግር ተፈጥሯልና የመለየት ሥራ እንዲሰራ ነው፤ ሦስተኛው መንግስት የዩኒቨርሲቲውን

Page 32: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

32

‘‘

ከገፅ 6 የዞረ

በ100 ደቂቃ. .

፡ በወቅቱ በሁለቱ ሙሉጌታዎች ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ መስመር ከዙምባብዌ ጋር አቻ ተለያይቶ በዳኙ ገላግሌ ፍፁም ቅጣት ምት ዋንጫውን ሲያነሳ የደርግ መንግስት በወቅቱ ለእያንዳንዱ ተጫዋች የሸለመው ከለር ቴሌቪዥን እንደነበር ሙሉጌታ ወ/የስ ለቁም ነገር መፅሄት ተናግሯል፡፡ ከዚያ በኋላ በተገኙ ተከታታይ የሴካፋ ድሎች ላይ ከመንግስት ሌላ ግለሰብ ባለሀብቶች ከፍተኛ የተባሉ ሽልማቶችን ሲያበረክቱ ተስተውሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት የ31 ዓመታትን ታሪክ ለቀየሩ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾችና አሰልጣኞችም የተለያዩ ባለሀብቶች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ ከሁሉም ከፍተኛ የተባለውን ሽልማት የሰጡት የሁልጊዜም የኢትዮጵያ እግር ኳስ አጋር ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲ ናቸው፡፡ ሼህ አላሙዲን ጨዋታወን በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው ባይከታተሉም ድሉን እንደሰሙ የ5 ሚሊዮን ብር ቼክ ለመፃፍ አልዘገዩም ተብሏል፡፡

የኤድና ሞል ማቲ ሲኒማ ባለቤት ኢንጂነር ተክለብርሃን አምባዬም ደግሞ በተደጋጋሚ ከጨዋታ በፊት የቡድኑን አባላት በየልምምዱ ሜዳ እየተገኙ ከሚያደርጉት ማበረታቻ በተጨማሪ ከውድድሩ በፊት ተጫዋቾቻችን የሚያሸንፉ ከሆነ እያንዳንዱ ተጫዋች 25 ሺህ ብር ሽልማት በመመደብ በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ባለፈው ማክሰኞ ምሳ ጋብዘው አስረክበዋል፡፡

በሽልማቱ ላይ የቱኒዚያ አቻውን 3ለ0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድንም ተካቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን የየራሳቸው ሽልማት እንደሚሰጡ የሚጠበቅ ሲሆን መንግስት ለተጫዋቾቹ የሚሰጠውን ሽልማት ከዚህ በፊት ከነበረውና ከተለመደው ለየት ባለ መልኩ ቢሰጥ የተሻለ እንደሆነ በዚህ አጋጣሚ እንጠቁማለን፡፡ ምክንያቱም አንዱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ችግር በስፖርቱ ላይ እርግጠኛ ሆነው ለመቆየት የመቻላቸው ጉዳይ አጠራጣሪ መሆኑ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ ገቢ ኖሯቸው ቤተሰባቸውን ማስተዳደር የማይችሉ ተጫዋቾች ሀሳባቸውን ሰብስበው ህዝቡ ማየት የሚፈልገውን ጨዋታ በማሳየት ሊያስደስቱት አይችሉም፡፡ በመሆኑም የብዙዎቹን ወጣቶች ህይወት ትርጉም ባለው መልኩ ለመለወጥ የሚችል ሽልማት ቢሰጣቸው ለወደፊቱ

ጨዋታ ብቻ ሳይሆን ከነሱ በኋላ ወደ ስፖርቱ ለሚመጡት ታዳጊ ወጣቶች መነቃቃት ሊፈጥር ይችላል፡፡

መንግስት ከፍ ከፍ ያሉ ሽልማቶችን ከራሱ ካዝና ለመሸለም ቢቸገር እንኳን ስፖንሰር በማፈላለግና ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን እንደተደረገው አይነት የ2 ብር የሞባይል የሎተሪ ዕጣ ለስፖርት ቤተሰቡ በማዘጋጀት እስከ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ተጫዋች መሸለም ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሽልማት ለወንዶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ብቻ ሳይሆን ብዙም ትኩረት ሳይሰጣቸው በግል ጥረታቸው ለተደጋጋሚ ለአፍሪካ ዋንጫ ላለፉት ሴት የብሔራዊ ቡድን አባላትን ይመለከታል፡፡ የታንዛኒያ አቻውን በድምር ውጤት 3ለ1 አሸንፈው፤ በያዝነው ወር በኢኳቶሪያል ጊኒ በምታዘጋጀው የአፍሪካ ሴቶች የእግር ኳስ ዋንጫ ያለፉት ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቻች ከዚህ በኋላ

የተለየ ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡በነገራችን ላይ ጠመኔያቸው

ትተው ወደ ስፖርቱ አሰልጣኝነት የገቡት አቶ ሰውነት ቢሻ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ታሪክ የሰሩ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ እኚህ አሰልጣኝ ዘወትር ከቤታቸው ወደ ስፖርት ሜዳ ለመምጣት ታክሲ ለማግኘት ሲጋፉ ማየት ወይም እሳቸው እንደሚሉት ‹‹ባለመኪናዎች እንዲያደርሷቸው መንገድ ዳር ሲቆሙ መመልከት ያማል፡፡ ይህንን የሚያነቡ ማናቸውም ወገኖች ለእኚህ ባለ ታሪክ አሰልጣኝ ከታክሲ ግፊያ ሊታደጋቸው ይገባል ሰዓቱም አሁንና አሁን ብቻ ነው እንላለን!

ዋሊያና ሉሲበኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የፀደቀ ስም መሆኑን እርግጠኛ ባልሆንም የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ‹‹ዋሊያ››፣ የሴቶቹ ደግሞ ሉሲ እየተባሉ ነው የሚጠሩት፤ የነዚህ ስያሜዎች ታሪካዊ ዳራና ተገቢነት በሚመለከታቸው ወገኖች ማብራሪያ ቢሰጥበት ደስ ይለናል፡፡ ምክንያቱም ስም ስነ ልቦናዊ አንድምታ

አለው፤ ዋሊያ በተራራ ላይ የሚኖር ገራምና በርጋጋ የዱር እንስሳ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ ግርማ ሞገስ አለው፡፡ ግን ግርማ ሞገስ ያለ ድፍረት ዋጋ የለውም፡፡ ብሔራዊ ቡድናችንም

የሴቶቹ ስያሜም ተመሳሳይ ችግር ይስተዋልበታል፡፡ ሉሲ በአፋር ሀዳር የተገኘች ከመጀመሪያዎቹ

የሰው ዘር ቅሪተ አካላት ጋር ግንኙነት ያላት ግኝት እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ሉሲ ኢትዮጵያዊ ስያሜ

አይደለም፤ ድንቅነሽ እንጂ፡፡ ቡድኑን በሊሲ ስም ለመጥራት ከሆነ የቡድኑ ስያሜ መባል ያለበት

ድንቅነሽ ነው፡፡

ለ31 ዓመት ከአፍሪካ ዋንጫ ላይ የጠፋው ብዙ ጊዜ ከግብፅ ጋር ስለምንመደብ ነው እየተባለ ሲነገረን ቆይቷል፡፡ ይህ አባባል የዋሊያ ባህሪን ከመላበስ የመጣ ስለመሆኑ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላልና ቢያንስ በስም ጉዳይ ብንወያይ እንላለን፡፡

የሴቶቹ ስያሜም ተመሳሳይ ችግር ይስተዋልበታል፡፡ ሉሲ በአፋር ሀዳር የተገኘች ከመጀመሪያዎቹ የሰው ዘር ቅሪተ አካላት ጋር ግንኙነት ያላት ግኝት እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ሉሲ ኢትዮጵያዊ ስያሜ አይደለም፤ ድንቅነሽ እንጂ፡፡ ቡድኑን በሊሲ ስም ለመጥራት ከሆነ የቡድኑ ስያሜ መባል ያለበት ድንቅነሽ ነው፡፡

ድንቅነሽም ብትሆን በሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘች አዲስ ግኝት ታሪኳ መነጠቁን መርሳት የለብንም፡፡ ከሉሲ 150 ሚሊዮን ዓመት በፊት ምድር ላይ እንደኖረች የታመነባትና የ3.21 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት ‹‹ሰላም›› የተሰኘችው የ14 ዓመት ሴት በኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ዶ/ር አለም ሰገድ ዘረሰናይ የዛሬ 4 ዓመት ተገኝታለች፡፡

ይህ በዓለም አቀፉ ኔቸር በተባለው ሳይንሳዊ መፅሄት ላይ የወጣው ግኝት ሰላምን ‹‹ሰው›› ሲላት ሉሲን ግን ‹‹በሰውና በዝንጀሮ መሀከል ባለ ዝግመተ ለውጥ መሀል የነበረች›› ሲል ነው የገለፃት፡፡ ታዲያ ለሴት ለብሔራዊ

ቡድናችን ተጫዋቾች ስያሜ ሰላም ነች ወይስ ሉሲ /ድንቅነሽ/ ተገቢ ሞዴል? እርግጠኛ ነኝ ሴት ተጫዋቾቻችን ይህንን ቢሰሙ ሉሲን /ድንቅነሽን/ አይመርጡም፤ ሰዎች ናቸዋ!. . . .

Page 33: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

33

‘‘ከገፅ 17 የዞረ

ዜማ. .

ቴምፕቴሽን ናይት ክለብን ሪትም ብዬው ማታ ማታ እሰራበት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን እኔ በተለያዩ ስራዎች የተነሳ አብሬ መስራት ስላልቻልኩ አቆምኩኝ፤ ልጆቹ አሁንም ይሰራሉ፡፡ አሁን የምናቀርበውን ኮንሰርትም ከዘመን ባንድ ጋር ነው የምሰራው፡፡

ቁም ነገር፡- መድረክ ላይ በሙሉ ባንድ ለመስራት የመውደድህን ያህል አልበምህን ግን በሙሉ ባንድ አይደለም የተሰራው፤ ለምድነው?

ሚካኤል፡- አልበም በሙሉ ባንድ መስራት እኛ ሀገር ቅንጦት ነው አይደለም በሙሉ ባንድ ከአንድ አቀናባሪ ጋር እንኳን እየተገናኘህ በምታስበው ጊዜ አልበምህን ሰርተህ ለመጨረስ አትችልም፡፡ ከጊዜው ሌላ የውጪ ጥያቄ አለ፤ ሙሉ ባንድ ስታሰራ ባንድ አግኝተህም ደግሞ የስቱዲዮ ችግር አለ፡፡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የምታስቀርፅበት ስቱዲዮ ያስፈልግሃል፡፡ እዚህ ሀገር ደግሞ ማን ጋር ነው የምትሄደው፡፡ ያሉት ከሁለትና ሶስት አይበልጡም፡፡ የነሱም ጊዜ አለ፤ ለምሳሌ እኔ በ2004 አልበሜን የግድ ማውጣት አለብኝ ብዬ ወስኜ ስለነበር የግድ መስራት ነበረብኝ፡፡ ስለዚህ ያለው ሌላው አማራጭም የስቱዲዮን ስራ ልክ እንደ ሙሉ ባንድ ሆኖ እንዲሰማ አድርገህ ማሰራት ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ግን ይቻላል?ሚካኤል፡- ይቻላል፤ ለምሳሌ የኔን

አልበም የሰሙ ሰዎች በሙሉ ባንድ እንዴት አሰራኸው ብለው የጠየቁኝ አሉ፡፡ ዋናው ነገር በጥሩ ባለሙያ መሰራቱ ነው፡፡

ቁም ነገር፡- የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበርክ፤ ፖለቲካ ተወዳለህ?

ሚካኤል፡- አልጠላም /ሳቅ/ ማንም ሰው እኮ ከፖለቲካ ውጪ መሆን አይችልም፡፡

ቁም ነገር፡- ፖለቲካል ሳይንስ የተማርከው መርጠህ ነው ወይስ በአጋጣሚ?

ሚካኤል፡- መርጨው ነው፤ ከሙዚቃ ውጪ አንድ ሌላ ሙያ እውቀት እንዲኖረኝ አሁንም እፈልጋሁ፤ ስለዚህ በወቅቱ መርጬ ፈልጌው ነው የገባሁት፡፡

ቁም ነገር፡- በአዲሱ አልበምህ ላይ የተጫወትካቸውን ዘፈኖች የፃፉልህ እነ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ናቸው፤ በዘፈን ግጥም ፀሐፊነት አይደለም የሚታወቁት፤ አንተ እንዴት ደፈርክ ከነሱ ለመውሰድ?

ሚካኤል፡- ምክንያቱ ግልፅ ነው፤ ጥሩ ግጥም ስለሚፅፉ ነው፡፡ ግጥሞቹን አይተሃቸው ከሆነ

ግልፅ ናቸው፡፡ በቀላል ቋንቋ የተፃፉ ናቸው፡፡ አገላለፃቸው ደስ ይላል፡፡ ሀሳቦቹም አዳዲስ ናቸው፡፡ ዘፈን ደግሞ በእኔ እምነት አንድ ጊዜ ሰምተህ የምታስቀምጠው ሳይሆን እየቆዬ ሲሄድ የበሰለ የሚደመጥ ነው፤ ለመደመጥ ደግሞ ግጥሙ ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል፡፡

ቁም ነገር፡- ግጥሞቹ ግን ጠንከር ያሉ አይመስልህም?

ሚካኤል፡- አይመስለኝም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ግጥም ወስጄ ከመዝፈኔ በፊት ሳነበው ገብቶኛል ወይ? የሚለውን ነው የምለካው፡፡ እኔ ካልገባኝ ለአድማጩ ልሰጠው አልችልም፡፡ ለዚህም ነው ግጥም ወስጄ ከመዝፈኔ በፊት ግር ያለኝ ነገር ካለ ከገጣሚዎቹ ጋር ቁጭ ብዬ የምነጋገረው፡፡ ትንሽ ወደ ፍልስፍናዊ ሀሳቦች የሚሄዱ ነገሮች ካሉ ምን ለማለት ፈልገህ ነው እንደዚህ ያልከው እላለሁ፡፡ ሲያስረዳኝ ካልተግባባን በል ቀይረው እኔ ለእያንዳዱ አድማጭ አሁን አንተ እንዳብራራኸው ለማብራራት አልችልም፡፡ የምንገናኘው በካሴት ወይም በሲዲ ነው ብዬ እንዲስተካከል አደርጋለሁ፡፡ ከዚህ አንፃር በአልበሙ ውስጥ ምን ለማለት ፈልጎ ነው እንደዚህ ያለው ብሎ የሚያመራምር ነገር የለም፡፡

ለምሳሌ ‹‹ልምጣ ያልሽ እንደሆን ቀና ነው ጎዳና

ልቤ ተመላልሶ ደልሎታልና›› የሚል ስንኝ አለ፡፡ ይህንን ስትሰማ አገላለፁ ይስብሃል እንጂ ምን ለማለት

ፈልጎ ነው አትልም፡፡ቁም ነገር፡- ግጥሞቹን

የዘፈንካቸው ከገጣሚዎቹ ጋር በደንብ ከተነጋገርካቸው በኋላ እንደሆነ ነግረኽኛል፤ ያንተ ዜማዎችስ ተተችተዋል?

ሚካኤል፡- ጥሩ ጥያቄ ነው /ሳቅ/ በሚገባ ተተችተዋልና ያው ቅንብሩን የሚሰሩት ልጆች ተችተዋቸው ነው የሰራኋቸው፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ ላይ እዚህ ጋር እንደዚህ ብትለው እያሉኝ በመግባባት ነው የሰራኋቸው፡፡ የሚገርምህ ያህንን አልበም የሰራሁት ከዚህ በፊት አብሬያቸው ካልሰራኋቸው የገጣሚያንና አቀናባሪዎች ጋር ነው፡፡ በዚህ ስራ ተግባብተን ሁላችንም በጥሩ ስሜት ነው የሰራነው፡፡ የጋራ ስራ የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

ቁም ነገር፡- የገብረክርስቶስ ደስታን ግጥም ዜማ ሰርተህለት ዘፍነኸዋል፤ የኮፒ ራይት ጉዳዩን ቤተሰቦቹን አግኝተህ ለመጨረስ ሞክረሃል?

ሚካኤል፡- ሞክሬያለሁ፡፡ በመጀመሪያ ስራውን ከሰራሁት በኋላ የሄድኩት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ኤልሳቤጥ ጋር ነበር፡፡ ከዚያ ከሰዓሊ በቀለ መኮንን ጋር አግኝቻቸው

ሙዚቃውን አሰማኋቸው፡፡ ከዚያ በቀለ ወደ ጌታ መኮንን ላከኝ፡፡ ጌታ መኮንን ሀጎስ የሚባል የገብረክርስቶስ ደስታ የቅርብ ዘመድ ጋር አገናኘኝ፤ እሱም ወ/ሮ ሙላቷ ከሚባሉ ሌላ ዘመድ ጋር አገናኘኝ፤ ሙዚቃውን አሰማኋቸው በጣም ደስ አላቸው፡፡ ግን የሱን ስራ በተመለከተ ሊፈቅድ የሚችል የቅርብ ቤተሰብ ወይም በስሙ የተቋቋሙ ፋውንዴሽን ስለሌለ ስራውን ለመፍቀድም ለመከልከልም አንችልም ነው ያሉኝ፡፡ ገብረክርስቶስ በስነ ጥበብ ቤተሰቡ ዘንድ ይታወቃል፡፡ በሌላው ህብረተሰብ ዘንድ ግን በዚህ አይነት ግጥሙ ስለማይታወቅ ብዘፍነው ዘመን የመሻገር አጋጣሚው ይጨምራል በሚል እምነት ወስኜ መጫወት ነበረብኝ፤ እንደውም በዚህ አጋጣሚ በስሙ ፋውንዴሽን ተቋቁሞ ከዚህ የተሻለ ስራ ሰርተን ብናጠናክረው ሁሉ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ የሚፈቅድ አካል ቢኖር እንኳን ለአንድ ግጥም የተወሰነ ክፍያ ከፍሎ መጫወቱ ብዙ አይጠቅመውም፡፡ ዘላቂ የሆነ ነገር ለመስራት ጥሩ መነሻ የሚሆን ነገር መስራት ነው የሚሻለው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡

ወደ ገፅ 38 ዞሯል

ገብረክርስቶስ በስነ ጥበብ ቤተሰቡ ዘንድ ይታወቃል፡፡ በሌላው ህብረተሰብ ዘንድ ግን በዚህ አይነት ግጥሙ ስለማይታወቅ ብዘፍነው ዘመን የመሻገር አጋጣሚው ይጨምራል በሚል እምነት ወስኜ መጫወት ነበረብኝ፤ እንደውም በዚህ አጋጣሚ በስሙ ፋውንዴሽን ተቋቁሞ ከዚህ የተሻለ ስራ ሰርተን ብናጠናክረው ሁሉ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

Page 34: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

34

ለወላጆች ባንክ

ከሰሞኑ

የባንኮች የብድር አገልግሎት እንደ ባንኮቹ ዓላማና የፋይናንስ አቅም መጠነኛ ልዩነቶች ቢኖሩትም በአብዛኛው የንግድ ባንኮች የሚሰጡት ብድሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

በተወሰነ ጊዜ ገደብ የሚከፈል ብድር (Term loan):- ይህ የብድር ዓይነት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በተቀመጠለት የመክፈያ ፕሮግራም መሰረት ከነወለዱ ተከፍሎ የሚያልቅ ለስራ ማስኬጃ ወይም ለኢንቨስትመንት ለልማት የሚውል ገንዘብ ነው፡፡

ኦቨርድራፍት (Overdraft):- በአበዳሪው ባንክ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች በሥራቸው ባህሪ የተነሳ የሚያጋጥማቸውን የአጭር ጊዜ የገንዘብ እጥረት ለማቃለል በባንኩ ካላቸው ተቀማጭ በላይ ገንዘብ እንዲጠቀሙ የሚሰጥ የብድር አይነት ነው፡፡

የግብርና ልማት ብድር (Agricultural input loan)፡- በግብርና ልማት ለተሰማሩ የህ/ሥ/ማህበራት፣ ለባለሀብቶችና ለክልል መንግስታት ለግብዓት ግዥ (ማዳበሪያ ምርጥ ዘር፤ ትራክተር ወዘተ. . ) የሚሰጥ ነው፡፡

ለአነስተኛ የብድር ተቋማት የሚሰጥ ብድር (MFI Looans)፡- ይህ ብድር ለአነስተኛ የብድር ተቋማት በተወሰነ የመክፈያ ጊዜና የወለድ መጠን እንዲከፍሉ የሚሰጥ ብድር ነው፡፡

ለማሽነሪዎችና መሳሪያዎች መግዣ የሚሰጥ ብድር (Machinery and Equipment loans)፡- ይህ ብድር የባንክ ደንበኞች ልዩ ልዩ የኮንስትራክሽን እና የፋብሪካ መሳሪያዎችን ለመግዛት እንዲችሉ የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው፡፡

የመኪና መግዣ ብድር (Motor vehicle loans)፡- ይህ ብድር በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ ተበዳሪዎች ለንግድ መኪና ግዥ የሚሰጥ ብድር ነው፡፡

በሸቀጥ መያዣነት የሚሰጥ ብድር (Merchandise Loans)፡- ይህ የብድር ዓይነት ለሽያጭ የተዘጋጁ ልዩ ሸቀጦችን በዋስትናነት በመያዝ የሚሰጥ የአጭር ጊዜ ብድር ነው፡፡ ይህ ብድር ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ ወይም በየጊዜው

የብድር አይነቶችን ያውቃሉ?የሚታደስ ሊሆን ይችላል፡፡

የፕሮጀክት ፋይናንስ ብድሮች (Project Loans)፡- ይህ የብድር አልገልግሎት ትርፋማነታቸው በጥናት የተረጋገጠ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር ወይም የተጀመሩትን ለማስፋፋት የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው፡፡

የሪል ስቴትና የግንባታ ብድር (Real Estate and Construction Loans)፡- እነዚህ የብድር አይነቶች ለሪል ስቴት አልሚዎች (ለግንባታ ሥራ እና ለሥራ ተቋራጮች (ለሥራ ማስኬጃ) የሚሰጡ የብድር ዓይነቶች ናቸው፡፡

የመተማመኛ ሰነድ ብድር (Letter of credit)፡- ይህ የብድር አገልግሎት በገቢ ንግድ የተሰማሩ ተበዳሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስመጧቸውን የዕቃ ሰነዶች በዋስትናነት በመያዝ ከሰነዱ ዋጋ የተወሰነ በፐርሰንት/በመቶኛ የሚሰጥ ብድር ሲሆን ብድሩም የሚከፈለው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡት ዕቃዎች ሰነዶች ለአበዳሪ ባንኩ ሲደርሱ ነው፡፡

የገቢ ወይም የወጪ ንግድ ሰነድ ብድሮች (Advance Against bills)፡- እነዚህ ብድሮች በገቢና በወጪ ንግድ ሰነዶች ዋስትናን አስመጪዎችና ላኪዎች ለሚያጋጥማቸው ጊዜያዊ ገንዘብ እጥረት መሸፈኛ የሚሰጡ የአጭር ጊዜ ብድሮች ናቸው፡፡

ቅድመ ጭነት የወጪ ንግድ ብድር (Pre-shipment Export credit)፡- ይህ የብድር አገልግሎት ላኪዎች የሚልኩትን ዕቃ ገዝተውና አዘጋጅተው ወይም አሰናድተው ለመላክ እንዲችሉ ለመደገፍ የሚሰጥ ብድር ነው፡፡

የዋስትና ሰነድ (Bank guarantees):- የንግድ ባንኮች ደንበኞቻቸው ከሶስተኛ ወገን ጋር ባላቸው የውል ግንኙነት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ግዴታቸውን መወጣት ባይችሉ በዋስትና ተቀባዩ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ኪሳራ ለመክፈል ባንኮቹ በፅሁፍ የሚሰጡት የዋስትና አገልግሎት ሲሆን ይህም ለምሳሌ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና፣ የጨረታ መሳተፊያ ዋስትና፣ የመሳሰሉትን ይጨምራል፡፡

ምንጭ፡- Ethiopian Banks & Insurances

ለልጅዎ ወደትምህርት ቤት ይዘው የሚሄዱትን ምግብ ምን እንደሆነ ማሰብ የእየለት ሀሳብዎ እንደሚሆን ርግጥ ነው፡፡ በተለይ እድሜያቸው በመዋእለ ህጻናት ደረጃ ከሆኑ በየቀኑ በምሳ እቃቸው የሚያኖሩት ምግብ ሁለት ጊዜ የሚመገቡ በመሆኑ ሀሳብ ይጨምራሉ፡፡ ምክንያቱም በሁለት የምሳ እቃ የተለያየ ነገር ለማኖር ከማሰብ አንጻር፡፡ ስለዚህ ለልጅዎ ምን አይነት ምግብ በምን ሁኔታ መቋጠር እንዳለብዎ ልብ ይበሉ፡፡

ህፃናቱ በቤት ውስጥ ቆይታቸው ምግብ ለመብላት ዝግጁ ወይም ፈቃደኛ ባለመሆን የሚያስቸግሩ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ አይነት ህፃናት ት/ቤት ሲሄዱ ከቤት በተሻለ ት/ቤት ሊበሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይሄንን ታሳቢ በማድረግ ከአቅማቸው በላይ ሊሆን የሚችል ምግብ አያስይዙ፡፡ ህጻናቱ የሚወዷቸውን ምግቦች ቅድሚያ ይስጡ፡፡ በተለይ ወደትምህርት ቤት የገቡት በቅርቡ ከሆነ ለዚህ ትኩረት መስጠት ይጠበቅብዎታል፡፡

ህጻናቱ ከቤት የወጡት ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ለመምህራኖቻቸው እንዲሁም ቦታው እንግዳና አዲስ ስለሚሆኑ ምግብ ለመመገብ ፈቃደኛ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ስለዚህ የሚወዷቸውን ምግብ ቢይዙ የተሻለ መሆኑ በባለሙያዎች የሚመከረው ለዚህ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የልጆቹን መጠን ያገናዘበ ምግብ ማስያዝ ያስፈልጋል፡፡ ሞግዚቶቻቸው ስለሚያበሏቸው በሚል የምሳ ዕቃቸውን በምግብ አያጨናንቁ፡፡ ልጆች ሊበሉት የሚገባውን መጠን ማስያዝ፡፡ እንዲሁም የሚይዙትንና መያዝ አይገባቸውም የሚሏቸውን የምግብ አይነቶች የህፃናቱ መምህራን ለወላጆች ይናገራሉ፡፡

ይሄንን ተግባራዊ ማድረጉ እንደ ወላጅ ለልጅዎ አሳቢ መሆንዎን ይጠቁማል፡፡ ስለዚህም ለህፃን ልጅዎ ወደ ትምህርት ቤት ቅባት የበዛበት ወጥ፣ በርበሬ ጠቃ ያለው ምግብ፣ ሾርባ፣ ክሬም ያላቸው ኬኮች፣ ጣፋጭነታቸው የበዛ ምግቦችን አያስይዙ፡፡ ከዚህ ይልቅ ፓስታ፣ መኮረኒ፣ ቅንጬ፣ ጨጨብሳ እንዲሁም በቁርስ ሰዓት ትምህርት ቤት የሚበሉት ብስኩት ፤ዳቦ ፤ዳቦውን በማር ፤ማርማላትን የመሳሰሉት ማብያዎችን ይቀቡላቸውና ያስይዙ፡፡

የአዲስ 1879 የመፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

ማን- በዳግማዊ ነቅዓጥበብ ምን- አዲስ 1879 መፅሀፍ የት- በተለያዩ የመፅሀፍት መሸጫ ቦታዎችመቼ- ከመስከረም 26 ወዲህ በጋዜጠኛው ዳግማዊ ነቅዓጥበብ የተዘጋጀው

መፅሀፍ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ አዲስ 18 1979 ቅፅ ፳ መፅሀፍ ታሪክን፣ ማህበራዊ ህይወትን፣ጠቃሚ ግኝትን ሰንቆ የያዘ ሲሆን ነውን ከነበር እያጣቀሰ፣ ታሪክን ወደኋላ መለስ ብሎ የሚያመላክት መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው ደብዳቤ ይገልፃል፡፡ መፅሀፏ 140 የገፅ ብዛት ያላት ሲሆን ፀሀፊው የኤፍ.ኤም 96.3 አዲስ 1879 በሚል የሬድዮ ፕሮግራም በማዘጋጀትና በማቅረብ ይታወቃል፡፡

Page 35: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

35

ሶዶኮ-15

ጥያቄ በመመለስ የ100 ብር የሞባይል ካርድ አሁኑኑ ይሸለሙ!!

- ሰዶኮ በዓለም ላይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚጫወቱትና አእምሯቸውን ጅምናስቲክ የሚያሰሩበት ጨዋታ ነው፡፡ እርስዎም ሶዶኮ በመጫወት የ100 ብር ካርድ ይሸለሙ፡፡የጨዋታው መመሪያ ወደ ጎን እና ወደ ታች ባሉ ባዶ ቦታዎች ላይ ከ1 እስከ 9 ያሉትን ቁጥሮች በመሙላት ይጫወቱ ቁጥሮቹ ግን አግድምም ሆነ ወደ ታች ሲገቡ መደጋገም የለባቸውም፡፡ በሰንጠረዥ ውስጥ ወደ ጎን ሁለት 9 ቁጥር ወይም ወደታች ሁለት 6 ቁጥር መኖር የለበትም፡፡ A,B.C,D እና E ባሉት ሳጥኖች ውስጥ የሚገቡ ቁጥሮችን ካገኙ ከዚህ ሰንጠረዥ ስር ባለው ባለ14 ዲጂት ቁጥር ውስጥ ባሉት A,B.C,D እና E ውስጥ በመክተት በሞባይልዎ ላይ ይሙሉ፡፡ እያንዳንዳቸው የ50/25 እና የ15 ብር የአየር ሰዓት አላቸው፤ መልካም እድል በ A,B.C,D እና E ውስጥ መግባት ያለባቸው ቁጥሮች 41A 43A 7368 4612 BB9 813 6928 6860 04C 813 9C22 81C0 587 485 74D2 0724 006 511 EE66 0448

የካምፓስ ህይወትዎን በመፃፍ ይሸለሙቁም ነገር መፅሄት በዚህ አምድ ላይ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ህይወታቸውን መሠረት ያደረጉ አዝናኝ፣ አስገራሚና አስደሳች ገጠመኞቻቸውን ለሚፅፉ ተማሪዎች የቁም ነገር መፅሄትን ይሸልማል፡፡ ገጠመኞቻችሁን በመፃፍ እንድትሸለሙ ተጋብዛችኋል፡፡

3 89

6 D

4

B 7 8

4

4

5

9

8

129

6

44

742

1

5

1

A6

1

C

E

ምረቃ በኪራይ ጋዋን

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ ባሳለፍኳቸው ሶስት ዓመታት ውስጥ የተለያዩ ገጠመኞች አሳልፌያለሁ፡፡ ለዛሬ በካምፓስ ህይወት ዓምዳችሁ ላይ ልፅፍላችሁ የፈለግሁት ሶስት ዓመት ሙሉ ሲማር ቆይቶ በመጨረሻ ሴሚስተር ፈተና ኤፍ በማምጣቱ ከምረቃ ስነ ሥርዓት ውጪ ስለሆነ ተማሪዎች ነው፡፡

ይህ ተማሪ የቅርብ ጓደኛዬ ስለነበር በምረቃ ወቅት ያደረጋቸቸውን ነገሮች ፈፅሞ አልረሳውም፡፡ ልጁ የዲላ ልጅ ነው፡፡ ለሶስት ዓመት ያህል ሲማር ክፍል የሚገባው እንደተመቸው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደውም በተከታታይ ክፍል ስለማይገባ ዊዝ ድሮው ያደረገ የሚመስላቸው ተማሪዎችም ነበሩ፡፡

ሳይኮሎጂ 101 የተባለውን ኮርስ በምንወስድበት ጊዜ ታዲያ መምህራችን በጣም ቀልደኛና ከተማሪዎች ጋር ተግባቢ ነበር፡፡ አንድ ሁለት ፔሬድ የተማሪዎችን ስም ከጠራ በኋላ ብዙዎቻችንን በአይን ይለየን ነበር፤ በመሆኑም ስማችንን ሳይጠራ ነበር ቀና ብሎ እየተመለከተ አቴዳንስ የሚይዘው፡፡ ታዲያ አንድ ቀን እየመጣ ሌላ ጊዜ የሚቀረው የዚህ የጓደኛችን ሁኔታ ግራ ያጋባው መምህራች ‹‹ታሪኩ የሚባል ተማሪ እዚህ ክፍል ነው ያለው ወይስ ሌላ ክፍል ነው?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ታሪኩ በአጋጣሚ ክፍል ውስጥ ስለነበር ‹‹እንዴ ቲቸር እዚህ ክፍል ነኝ›› ይላል፡፡

‹‹ታዲያ ለምንድነው ብዙ ጊዜ የማትመጣው?›› ሲለው ‹‹እንዴ ቲቸር ሁሌ እኮ እመጣለሁ እርስዎ ስለማያዩኝ ነው›› ይለዋል፡፡ ሁኔታውን የነቃው መምህር ‹‹ባለፈው ነበርክ?›› ሲለው፡፡ ‹‹አዎ!›› አለ ‹‹ምንድነው የተማርነው?›› ሲለው ‹‹ስለ በጀት አጠቃቀም›› ብሎ እርፍ አጅሬ ያለበትን ክፍል ብቻ ሳይሆም መምህሩ የምን አስተማሪ እንደሆነ አያውቅም ነበር፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለፈ ሲማር የነበረው ታሪኩ ውጤቱ ብዙም አስተማማኝ ስላልነበረ ገና ሰኔ ከመድረሱ በፊት ነበር እንደማይመረቅ አውቆ የመመረቂያ ልብስ ኪራይ ያፈላልግ የነበረው፡፡ ድክመቱ በትምህርቱ ላይ ነው እንጂ እንደዚህ አይነት ነገር ላይ ፈጣን በመሆኑ ውጤት ሲመጣ ከማይመረቁ ተማሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙን አገኘው፡፡

መቼም ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ታሪኩ ባለመመረቁ ፊቱ ላይ ምንም አይነት ቅሬታ አልነበረም፡፡ የሱ ስጋት ልጃችን ሊመረቅ ነው ብለው የሚመጡት ቤተሰቦቹ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ደግሞ የመመረቂያ ጋዋን ተከራይቶ ተዘጋጅቶበታል፡፡

ቤተሰቦቹ ደግሞ ልጃችን ተምሮ ጨርሰልን በማለት ሙሉ ልብሱን ገዝተውለት አሳምረውታል፡፡ የምረቃ ዕለት ታዲያ እኛ የሱን ያህል አላማረብንም፤ በወዳጅ ዘመዶችም አልታጀብንም፤ ግቢ ውስጥ ሁሉ ወዲያ ወዲህ እያለ ፎቶውን ሲነሳ ማን ቢያየው ጥሩ ነው? ሬጂስታራል፤ እናም እዚያው ቤተሰቦቹ ፊት ገዋኑን እንዲያወልቅ የተደረገው ጓደኛዬ ድጋሚ ወደ ካምፓስ እንዳይገባ ታግዷል፡፡

ኃይለ ልዑል ታዬ (ከሀዋሳ)

Page 36: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

36

የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በ1949 በካርቱም ሱዳን ኢትዮጵያ ፣ግብፅና ደቡብአፍሪካ ተካፋይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ግብፅ ከሱዳን እንዲጋጠሙ ዕጣ

ደረሰና ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካን በፎርፌ አሸንፋ ለፍፃሜ ብታልፍም ግብፅ ሱዳንንና ኢትዮጵያን በመርታት የዋንጫ ባለቤት ሆነች፡፡

2ኛው የአፍሪካ ዋንጫሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካይሮ በ1951

ተዘጋጅቶ አሁንም ተካፋይ ለመሆን ግብፅ ፣ኢትዮጵያና ሱዳን ተመዘገቡ፡፡በውድድር በነጥብ ብልጫ ስለነበር የኢትዮጵያ ቡድን በግብፅ 4ለ ዜሮ በሱዳን 1ለ ዜሮ ተሸንፎ ሲወድቅ ግብፅና ሱዳን ለፍጻሜ አልፈው ግብፅ 2ለ1 በመርታት የአፍሪካ ዋንጫ በ1953 ኢትዮጵያ አዘጋጀች ፡፡ከተመዘገቡት 9 ሀገሮች መካከል አዘጋጅዋ ኢትዮጵያ ግብፅ ደግሞ የዋንጫ ባለቤት በመሆን በቀጥታ ፣ቱኒዚያና ሞሮኮ

የአፍሪካ ዋንጫ ከ1ኛ-15ኛው፣ጋናና ናይጄሪያን በጨዋታ በማሸነፍ ፣ዩጋንዳ ሱዳንን በፎርፌ በመርታት ቱኒዚያ፣ኢትዮጵያ፣ግብፅ ና ዩጋንዳ ለግማሽ ፍፃሜው አለፉ፡፡ ከዚህም ኢትዮጵያ ቱኒዚያን 4ለ2፣ ግብፅ ዩጋንዳን 2ለ1 በማሸነፍ ኢትዮጵያና ግብፅ ለዋንጫ አልፈው ኢትዮጵያ 4ለ2 በማሸነፍ የ3ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ሆነች፡፡ ግብ አግቢዎች የቴሌው ተክሌ፣የጥጡ ጌታቸው ወልዴና ኢታሎ ጎሻሎ እንዲሁም የጊዮርጊሱ መንግስቱ ወርቁ ነበሩ፡፡

4ኛው የአፍሪካ ዋንጫአራተኛ አፍሪካ ዋንጫ በጋና በ1956 ተዘጋጅቶ

አዘጋጅዋ ጋና የዋንጫው ባለቤት ኢትዮጵያ በቀጥታ ሲያልፉ ቱኒዚያ ፣ግብፅና ሱዳን በማጣሪያ አለፉ፡፡

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በጋና 2ለዜሮ ፣በግብፅ 2ለዜሮ ተሸንፋ ቱኒዚያን 4ለ2 ረታት 4ኛ ስትሆን የዋንጫው ባለቤትጋና ሆናለች፡፡

5ኛው የአፍሪካ ዋንጫ5ኛው አፍሪካ ዋንጫ በ1958 በቱኒዚያ ሲዘጋጅ

ኢትዮጵያ በማጣሪያው ውድድር ከሱዳን ፣ከኬንያና ከዩጋንዳ ጋር ተመደበች፡፡ ሦስቱ አገሮች በደርሶ መልስ ተጋጥመው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ላይ ሱዳንን 1ለ ዜሮ ፣ኬንያን 2ለዜሮ፣ዩጋንዳን 2ለዜሮ ስትረታ በመልሱ ግጥሚያ በሱዳን 2ለ1፣በኬንያ 3ለ2 ስትሸነፍ ዩጋንዳን 2ለዜሮ በማሸነፍ 8 ነጥብ፣ ሱዳን 9 ነጥብ አግኝተው ነበር፡፡ሆኖም ኬንያ 2 የዩጋንዳ ተጫዋቾች አሰልፋ ስላጫወተች ኢትዮጵያ ክስ አቅርባ ኬንያን በፎርፌ 2ለዜሮ ስለረታች 10 ነጥብ አግኝታ ለ5ኛው አፍሪካ ዋንጫ አለፈች ፡፡ነገር ግን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ግጥሚያ ከአዘጋጅዋ አገር ጋር ስለደረሳት 4ለዜሮ ቀጥሎ በሴኔጋል 5ለ1ተሸነፈች፡፡በፍፃሜውም ጋና ቱኒዚያን 3ለ2 በማሸነፍ ጋና ለ2ኛ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ወሰደች፡፡

6ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 6ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በ1960 ኢትዮጵያ ውስጥ

ሲዘጋጅ ተካፋይ ሀገሮች ለመጀመሪያ ጊዜ 8 ሲሆኑ ፡፡እነርሱም ኢትዮጵያ፣ጋና፣አልጄርያ፣ዩጋንዳ፣ኮንጎ

ኪንሻሳ(ዛየር)፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ሴኔጋልና አይቮሪኮስት ነበሩ፡፡ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 2ለ1 ረታች፡፡ ጨዋታው 4 ደቂቃ እስኪቀር 1ለ1ነበሩ፡፡ ኢትዩጵያ የማሸነፊያውን ግብ ያገኘችው በፍፁም ቅጣት ምት ነበር፡፡

ኢትዮጵያ 2ኛውን ግጥሚያ ከአይቮሪኮስት ጋር አድርጋ 1ለዜሮ ስለረታች ከአዲስ አበባ ምድብ ኢትዮጵያ በአንደኝነት ፣አይቮሪኮስት በሁለተኝነት በአስመራው ምድብ ጋናና ኮንጎ ኪንሻሳ አለፉ፡፡

ከዚያም ኢትዮጵያ በኮንጎ ኪንሻሳ 3ለ2 ተሸንፋ ለፍጻሜ የማለፍ ዕድሏ ተጨናገፈ፡፡በዚህ ወቅት እስካሁን የማይረሳው በዕለቱ ተተኪ ያልተገኘለት ሸዋንግዛው ከአይቮሪኮስት ጋር ሲጫወቱ በጥፋት ከሜዳ ስለወጣ የቡድኑን አጥቂ መሥመር አናጋው፡፡የ6ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ዛየር ሆነች፡፡

7ኛው የአፍሪካ ዋንጫ1962 ዓ.ም 7ኛው አፍሪካ ዋንጫ በሱዳን

ሲዘጋጅ ኢትዮጵያ ታንዛንያን 7ለዜሮ እና 2ለ1 ረታት ለፍፃሜ አለፈች፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ ቡድን ካርቱም ላይ በአይቮሪኮስት 6ለ1፣በሱዳን 3ለዜሮ፣በካሜሮን 3ለ2 ተሸንፎ የመጨረሻውን ደረጃ የመያዝ ዕድል ገጥሞታል፡፡የ7ኛው አፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ሱዳን ነበረች ፡፡ተካፋዮቹ ኢትዮጵያ ፣አይቮሪኮስት፣ግብፅ፣ዛየር፣ጋና ፣ካሜሮንና ጊኒ ነበሩ፡፡

8ኛው የአፍሪካ ዋንጫየ8ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በ1964 በካሜሮን ሲዘጋጅ

ተካፋይ አገሮች አዘጋጅዋ ካሜሮን የዋንጫው ባለቤት ሱዳን፣ኬንያ፣ማሊ፣ቶጎ፣ኮንጎብራዛቪል፣ ሞሮኮና ዛየር ሲሆኑ የዋንጫው ባለቤት የሆነችው ኮንጎብራዛቪል ነበረች፡፡ ኮንጎ ዋንጫውን ያገኘችው በፍፃሜው ውድድር ማሊን 3ለ2 ረታት ነው፡፡

9ኛው የአፍሪካ ዋንጫ9ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በ1966 ግብፅ አዘጋጅ

ስትሆን ተካፋዮች አዘጋጅዋ ግብፅ፣ የዋንጫው

ባለቤት ኮንጎ ብራዛቪል፣ ዛየር፣ ዛምቢያ፣ ሞሪሺየስ፣ጊኒ፣ዩጋንዳና አይቮሪርኮስት ነበሩ፡፡ የ9ነኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ዛየር ስትሆን ዛየር የዋንጫው ባለቤት የሆነችው በፍፃሜ ውድድር ዛምቢያን 2ለዜሮ በመርታት ነው፡፡

10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት

በ1968 ተደረገ፡፡ ተካፋዮቹ አዘጋጅዋ ኢትዮጵያ የዋንጫ ባለቤት ዛየር፣ ግብፅ፣ ናይጄርያ፣ ሱዳን፣ ጊኒ፣ ዩጋንዳና ሞሮኮ ሲሆኑ የዋንጫው አሸናፊ ሞሮኮ ነበረች፡፡ ሞሮኮ ሻምፒዮን የሆነችው ፍፃሜው ግጥሚያ ከጊኒ ጋር 1ለ1 ተለያይተው ቀደም ብሎ ሞሮኮ በነበራት የአንድ ነጥብ ብልጫ ነው፡፡

11ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 11ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው ጋና ለ3ኛ ጊዜ

የዋንጫ ባለቤት ሆና ዋንጫውን የግሏ ያደረገችው፡፡ጋና የዋንጫው ባለቤት ለመሆን የቻለችው በፍፃሜው ውድድር ዩጋንዳን 2ለ1 ረታት ነው፡፡

12ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 1972 ናይጄርያ አዘጋጅ ሆና ዋንጫውንም አግኝታለች፡፡ተካፋይ አገሮች ግብፅ ፣ታንዛንያ ፣አይቪሪኮስት፣አልጄርያ፣ሞሮኮ፣ጊኒ አዘጋጅዋ ናይጄርያና የዋንጫው ባለቤት ጋና ሲሆኑ ናይጄርያ ሻምፒዮን የሆነችው በፍፃሜው አልጄርያን 3ለዜሮ ረታት ነው፡፡

13 ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ይህ ውድድር የተካሄደው በ1974 በሊቢያ

ዓረብ ጀማሂሪያ ነው፡፡ በዚህ ውድድር ተካፋይ የሆኑት ጋና ፣ካሜሮን ፣ቱኒዚያ በአንድ ምድብ ሲሆኑ ዛምቢያ፣አልጄርያና ናይጄርያ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን ከምድቡ በዛምቢያ በናይጄርያና በአልጄርያ ተሸንፎ የመጨረሻው ደረጃ ይዟል፡፡

በዚህ ውድድር ጋና ሊቢያን በፍፁም ቅጣት ምት 6ለ5 በሆነ ውጤት አሸንፎ ለ4ኛ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል፡፡

14ኛው የአፍሪካ ዋንጫየአይቮሪኮስት ዋና ከተማ የሆነችው በአቢጃንና

ለ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ድል ያበቁ ዋና አሰልጣኝ ጓድ ይድነቃቸው ተሰማ ከመሀል ረዳቶች ከግራ ፀሐዬ ባህረና አዳሙ አለሙ ናቸው

ታ ሪ ክ

Page 37: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

37

ከሰሞኑ

በቅርብ ቀን ቤሌማ የቴዲ አፍሮን የሀዋሳ ኮንሰርሰት ቅዳሜ ያካሂዳል

ኮካኮላ በአካባቢ ጥበቃ ላይ አየሰራ መሆኑን አስታወቀ

በኢትዮጵያ ሥራ ከጀመረ 50 ዓመት የሆነው የኮካኮላ ካምፓኒ በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ልዩልዩ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ባለፈው ሰኞ በራዲሰን ብሉ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣው መግለጫ ላይ እንደገለፀው ባለፉት 50 ዓመታት ህብረተሰቡን ሊጠቅሙ በሚችሉ ልዩ ልዩ ተግባራት ላይ መሳተፉን የገለፁት አቶ ጌታቸው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ በቀይ መስቀል አገልግሎትና በስፖርት ዘርፍ ውጤታማ ተግባራን አከናውኗል ብለዋል፡፡

ኮካ ኮላ ለፋብሪካው የሚጠቀምበትን ውሀ ተረፈ ምርት ወደ ወንዝ ወርዶ አካባቢን እንዳይበክል ድጋሚ ተጣርቶ ጥቅም ላይ ሊውል የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ ገንብቶ በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር የገለፁት አቶ ጌታቸው ይህም ህብረተሰቡ በተበከለ ውሀ ሳቢያ ጉዳት እንዳይደርስበት የሚያደርግ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ኮካኮላ ጤና ቀበና ግንፍሌን እናፅዳ ከተባለ ሀገር በቀል የወጣቶች ማህበር ጋር በመተባበርም በአዲስ አበባና በክልል ያሉ ወንዞች በአፈር መከላትና በውሀ ብክለት እየደረሰባቸው ያለውን ጉዳት በመግታት መልሶ የማልማት ስራ እየሰራ መሆኑን የማህበሩ ሊቀ መንበር ወጣት አበባየሁ አካሉ ተናግሯል፡፡ባለፈው ረቡዕ ዑራኤል አካባቢ የሚገኝ አጎዛ ገበያ ወንዝ ላይ የችግኝ ተከላ እንዳካሄደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሰሜን ዋልታ እስከ ደቡብ ዋልታ በእግሩ በመጓዝ የመጀመሪያው ሰው የሆነው እንግሊዛዊው ሚስተር ሮበርት ስዋን የተገኘ ሲሆን ስለጉዞው አላማና በጉዞው ወቅት ስለተመለከተው የአካባቢ ብክለት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ሚስተር ሮበርት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴ የሚያደርግ አንድ ሰው ከኢትዮጵያ መርጦ ወደ ደቡብ ዋልታ በረዷማ አህጉር አንታርቲክ የመውሰድ ሀሳብ እንዳለው የገለፀ ሲሆን ከዚህ በፊት 17 ያህል ሰዎችን ከአረቡ አለም መርጦ በመውሰድ ወጣቶችን ስለአካባቢያቸው እንዲያውቁ ማድረጉን ተናግሯል፡፡

ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰው አልበሙ ካወጣ ቡኋላ ከአዲስ አበባ ኮንሰርት ቀጥሎ የሚያቀርበውን ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በሀዋሳ እንደሚያቀርብ ቤሌማ ኢንተርቴመንት አሳወቀ፡፡

የቤሌማ ኢንተርቴመንት ባለቤትና ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ወሰን አበጀ ለቁምነገር መፅሄት እንደገለፀው በሀዋሳ እስታዲየም በሚቀርበው ኮንሰርት እስከ 15 ሺህ ህዝብ ይታደማል ተብሎ እንደሚጠበቅና ደረጃውን የጠበቀ መድረክና መብራት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሱዳን አቻውን 2 ለ 0 አሸንፎ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የተቀላቀለበትን ጨዋታ ከማድረጉ በፊት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፈቃድ በመውሰድ ቤሌማ ኢንተርቴመንት በዲጄ ዊሽና በዲጄ መሳይ ልዩ የመዝናኛ ሙዚቃ ማቅረቡን የገለፀው አቶ ወሰን ህዝቡ ብሄራዊ ቡድኑን እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ እንዲያበረታታ ድጋፍ ማድጉን ገልጿል፡፡

ለብሄራ ቡድኑ አስጨፋሪዎች አቼኖና አዳነ ያወጡትን ነጠላ ዜማ ቤሌማ ኢንተርቴመንት አባዝቶ ለስታዲየሙ ታዳሚ በነፃ ያሰራጨ ሲሆን ጥቅምት17 በሀዋሳ የሚካሄደውን የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የሚገልፁ ከ20 ሺህ በላይ ፍላየር ተበትኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ ቤሌማ ኢንተርቴመንትና የኮንሰርቱ ስፖንሰር ሜታ ቢራ ሙሉ የቡድኑን አባላት ሀዋሳ የቴዲ ኮንሰርት ላይ ተጋብዘው እንዲዝናኑ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

የሀዋሳው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የመግቢያ ዋጋው 120 ብርና ለቪኣይፒ 250 የተደረገ ሲሆን የሀዋሳ ፣የዲላ፣የሻሸመኔ ፣የዝዋይ የአርባምንጭና የሀዋሳ ዙሪያ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች በቀላሉ በኮንሰርቱ እንዲተደሙ ታስቦ የዋጋ ቅናሽ መደረጉን አቶ ወሰን ለቁምነገር መፅሄት ገልፀዋል፡፡

በበዋኬ ከተማ 14ኛውአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከየካቲት 25 እስከ መጋቢት 9 ቀን 1967 ድረስ ተካሄዷል፡፡

በዚህ ውድድር የተካፈሉት የ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው የጋና ቡድንና አዘጋጅዋ አይቮሪኮስት ያለማጣሪያ ያለፉ ሲሆን ቶጎ ፣ጋና ፣ናይጄርያና ግብፅ የማጣሪያውን ውድድር በማሸነፋቸው ተካፋይ ለመሆን ችለዋል፡፡

በአቢጃኑ የሁፌት ቧኘ ስታዲየም የተወዳደሩት አንደኛ ምድብ የተመደቡት አይቮሪኮስት ፣ቶጎ ፣ካሜሩንና ግብፅ ሲሆኑ በሁለተኛው ምድብ የተመደቡት ጋና፣ ናይጄርያ፣ አልጄርያና ማላዊ ደግሞ የቡዋኬ ስታዲየም ላይ ውድድራቸውን አከናውነዋል፡፡ ከመጀመሪያው ምድብ ግብፅና ካሜሮን ከሁለተኛው ምድብ አልጄርያና ናይጄርያ ለግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ስለበቁ ግብፅና ናይጄርያ አልጄርያና ካሜሮን እንዲጋጠሙ ተደርጓል፡፡

ናይጄርያ ግብፅ በመደበኛ ሰዓትና በተጨማሪው ሰላሳ ደቂቃ 2ለ2 ሲለያዩ ካሜሩንና አልጄርያ ደግሞ ባዶ ለባዶ ስለተለያዩ በፍፁም

ቅጣት ምት ተሰጥቶ ናይጄርያ ግብፅን 10ለ9 ካሜሩን አልጄርያን 5ለ4 በሆነ አጠቃላይ ውጤት በማሸነፋቸው ግብፅና አልጄርያ ለደረጃ ተጋጥመው አልጄርያ 3ለ1 በማሸነፍ 3ኛ ስትወጣ ግብፅ አራተኛ ሆናለች፡፡

ካሜሩንና ናይጄርያ ባደረጉት ግጥሚያ ካሜሩን ናይጄርያን 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡

15 ኛው የአፍሪካ ዋንጫ15ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

የተካሄደው በአሌክሳንድርያና በካይሮ ከተሞች ሲሆን የዋንጫ ባለቤት የሆነው የግብፅ ቡድን ካሜሩንን 2ለዜሮ አሸንፎ ነው፡፡ የግብፅ ቡድን ከመጀመሪያና ከሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጋር ለሦስተኛ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት መሆኑ ነው፡፡

በ15ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተካፋይ ዋንጫ ተካፋይ የሆኑት አገሮች አዘጋጅዋ ግብፅ የ14ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄርያ፣ ዛምቢያ፣ ሞሮኮ ፣አይቨሪኮስትና ቱኒዚያ ናቸው፡፡

ምንጭ፡- የስፖርት መፅሔታችን 1979 ዓ.ም

ለ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ ቡድን ተጨዋቾች

የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች በሙሉ ተጋብዘዋል

ታ ሪ ክ

Page 38: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

38

ከገፅ 33 የዞረ

ዜማ . . .

ቁም ነገር፡- ግን አሁን የሄድክበት ርቀት በአልበምህ ላይ አልገለፅክም ለምንድነው?

ሚካኤል፡- ልህ ነሀ፤ መግለፅ ነበረብኝ ግን ትንሽ ጥድፊያ ላይ ስለነበርኩ ሳይገባ ቀርቷል፡፡

ቁም ነገር፡- ክሊፕ ስንት ዘፈን ሰራህ?ሚካኤል፡- አንድ ነው እስካሁን የተሠራው ‹‹ትንታ›› ብቻ ነው፡፡ እሱም

ድሬ ቲዩብ ላይ የተለቀቀው ዛሬ /ቅዳሜ/ ነው ገና 24 ሰዓት ሳይሞላው 20ሺህ ሰዎች እንዳዩት ቁጥሩ ያመለክታል፡፡ ዳይሬክተሩ ያሬድ ሹመቴ ነው፤ ሌሎች ሶስት ወይም አራት ዘፈኖችን በቅርቡ እሰራለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- አዲካ ነው ያሳተመው፤ እንዴት ተገናኛችሁ?ሚካኤል፡- አዋድ የመጀመሪያ አልበሜን በጣም ይወደው ነበር፡

፡ የዚያን ጊዜ አዲካ ኮሙኒኬሽን ገና አልተቋቋመም ነበር፡፡ በኋላ ግን ድርጅቱ ከተቋቋመ በኋላ የሰራኋቸውን ዘፈኖች አሰማሁት፤ ወደዳቸው ከዚያ ሲያልቅ ወጣ ማለት ነው፡፡

ቁም ነገር፡- የሁለታችሁም ስም ነው አልበሙ ላይ ያለው ኮፒራይቱ የማነው?

ሚካኤል፡- ልክ ነው፤ የሁለታችንም ስም ነው ያለው፤ ግን ለተወሰነ አመት የነሱ ነው ኮፒራይቱ የሚሆነው፡፡

ቁም ነገር፡- በሼር ነው በሽያጭ ነው የታተመው?ሚካኤል፡- በሽያጭ ነው፡፡ቁም ነገር፡- በስንት የሚል ጥያቄ ይመችሃል?ሚካኤል፡- ዋጋውን መናገሩ ሰው ለስራው ያለውን ግምት ክፍያው

እንዲለካው ስለማልፈልግ ባልናገር ነው የሚሻለው፡፡ ነገር ግን ለስራዬ የሚገባኝንና ለቀጣይ ስራዬ የሚሆን ነገር አግኝቻለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራም ትልቅ ድጋፍ አድርጎልኛል፡፡ ለፕሮሞሽኑ እጅግ ከፍተኛ ወጪ ነው ያወታው፡፡ አዲካንም ቅዱስ ጊዮርጊስንም ከልብ ነው የማመሰግነው፡፡

ቁም ነገር፡- ጎጆ የወጣኸው በቅርቡ ነው፤ አዲሱ ትዳር እንዴት ነው?

ሚካኤል፡- በጣም ደስ ይላል?ቁም ነገር፡- ባለቤትህ ሆስተስ ነች ይባላል፤ ልክ ነው?ሚካኤል፡- ነበረች፡፡ አሁን በግል የማርኬቲንግ ስራ ላይ ነው ያለችው፡

፡ቁም ነገር፡- ሆስተስ ከነበረች አውሮፕላን ላይ ነው የተዋወቁት

የሚባለውስ?ሚካኤል፡- እሱም ልክ አይደለም /ሳቅ/ቁም ነገር፡- እሺ የት ተዋወቃችሁ?ሚካኤል፡- ሠርግ ላይ ነው የተዋወቅነው፡፡ አንድ የማውቃት ልጅ

ኤደን ገነት መናፈሻ ሠርግ ላይ ሙሽራዬ የሚለውን ዘፈን እየዘፈንኩ ድንገት አየት ሳደርጋት ፈገግታዋ የሚያዛልቅ መስሎ ተሰማኝ /ሳቅ/

ቁም ነገር፡- የዘፈኖችህ አድናቂ ነበረች?ሚካኤል፡- የኔ ብቻ ሳይሆን ሙዚቃ በጣም ትወዳለች፤ ታዳምጣለች፤

እንደውም ወደ አርቱ የመግባት ፍላጎቱ አላት፤ ትወና ትሞክራች፡፡ቁም ነገር፡- ከዘሪቱ ከበደ ጋር ችግኝ ተከላ ጀምራችሁ ቆመ፤

ምንድነው?ሚካኤል፡- የጀመርነው ግሪን ኢንቪቲሺ የሚል ድርጅት አቋቁመን

ነበር፡፡ ነገር ግን የማህበራት ምዝገባ ኤጀንሲ ኢንቪቲሺ ብላችሁ መንቀሳቀስ አትችሉም፡፡ የበጎ አድራጎት ማህበር ሆናችሁ ካልተመዘገባችሁ ሲሉን ለጊዜው ቆመ፤ እቅዳችን አዲስ አበባ ላይ አንድ ኮንሰርት ከሰራን በኋላ በየክልሉ እየሰራን ችግኝ ተከላውን ልንሰራ ነበር ግን አልሆነም፡፡ ከዚያ ወደ በጎ አድራጎት ማህበር ለመቀየር እንቅስቃሴ የሚያደርግልን መሀመድ የሚባል ልጅ ነው፤ እየተንቀሳቀስን ነው እንመለስበታለን፡፡

ቁም ነገር፡- ብዙ ሠርጎች ላይ ትጋበዛለህ፤ ራስህን እንደ ሠርግ ዘፋኝ ትቆጥራለህ?

ሚካኤል፡- እኔ ሠርግ ላይ የምጋበዘው የፍቅር ምርጫዬንና ሙሽራዬን ለመዝፈን ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ብዬ የማስበው ብዙዎቹ ሙሽሮች ከመጋባታቸው በፊት ፍቅረኛሞች ሆነው የፍቅር ምርጫዬ ዘፈን ተገባብዘዋል፡፡ እና ሲጋቡ ይህንን ዘፈን ቢዘፈንላቸው ደስ ይላቸዋል፡፡ ለዚህ ይመስለኛል የሚጋብዙኝ፡፡ በፊት በፊት አልዘፍንም እል ነበር፡፡ ነገር ግን የሰዎች ስሜት ሲጎዳ ሳይ ለምን ብዬ ያውም በዋጋ መደራደር ጀመርኩ ማለት ነው /ሳቅ/ አንድ ስራ አንድ ሰው ከሰራው በኋላ የእሱ ብቻ አይደለም የህዝቡም ነው፤ ስለዚህ እንደፍላጎታቸው እዘፍናለሁ፤ ያው የፍቅር ምርጫዬንና ሙሽራዬን ነው የምዘፍነው፡፡ ሙሽራዬን ግን ብዙ ጊዜ መዝፈን የምፈልገው ሙሽሮቹ ኬክ ሲቆርሱ ሳይሆን ከቆረሱ በኋላ ተያይዘው እንዲደንሱበት ነው፡፡ ምክንያቱም ግጥሙን ለእንደዚህ ተብሎ የተሰራ ነው፡፡ ይህንን ሀሳቤን ሳልነግራቸው ቀድመው ከገለፁልኝና ደስ ካለኝ ሠርግ አንዱ የሜድሮክ ኢትዮጵያ ክፍ ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰር የሆኑት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ልጃቸውን በቅርቡ ሸራተን ስታገባ እኔ ሳልነግራቸው ሙሽራዬ ከኬኩ በኋላ ብትጫወተው ጥሩ ነው ነበር ያሉኝና ደስ እያለኝ ነበር የተጫወትኩላቸው፡፡

ቁም ነገር፡- የፍቅር ምርጫዬን ያልዘፈንክበት ሠርግ አለ?ሚካኤል፡- የለም፡፡ ዋናው የምጠራው ለምን ሆነና፡፡ቁም ነገር፡- አንተ ሠርግ ላይስ?ሚካኤል፡- አልዘፈንኩም፡፡ የዘፈንኩት የሰይፉ ዮሐንስን በመልክሽ አይደለም

ውበትሽን የማውቀው የሚለውን ነው የተጫወትኩት፡፡ቁም ነገር፡- በመጨረሻስ?ሚካኤል፡- በመጀመሪያ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ አድናቂዎቼን የስራዬ

ነዳጅ ስለሆኑ አመሰግናቸዋለሁ፡፡ አልበሙን አብረውኝ ሰሩትን ሙያተኞች ሚኪ፣ ኪሩቤል፣ ቴዎድሮስ ፀጋዬ፣ዳዊት ተስፋዬ፣ መስፍን ትንሳኤ፣ አበጋዝ አዲካ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሉንም ባለበቴን ጭምር በጣም አመሰግናታለሁ፡፡

ዘወትር ቅዳሜ በሲኒማ አምፔር በ10 እና በ12 ሰዓትበልዩ ፕሮግራም ዘወትር እሁድ በሲኒማ አምፔር በ5፣በ8፣በ10 እና በ12 ሰዓት

‹‹የምር ፊልም ነው፤ እንዳያመልጥዎ››

Page 39: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

39

ከገፅ 40 የዞረ

የጥበብ . . . ‘‘?”በማለት ጠይቁት፡፡ኒናካዋም፡- ‹‹ብቻዬን መጥቻለሁ፤ ብቻዬንም

እሄዳለሁ፡፡ እርስዎ ምን ሊረዱኝ ይችላሉ?›› አለ፡፡ኢኪዩም፡-”ህይወትን ሰጥቶ በመሄድ ብቻ

ከተመለከትካት በእርግጥም ቅዠትህ እሱ ነው፤ እኔ ግን መምጣትና መሄድ የሌለበትን መንገድ እመራሀለሁ‹‹ አሉት፡፡ በዚህ በኢኪዪ ንግግር ኒናካም መንገዱ ተጠረገለት፤ በፈገግታ ሞትን ተቀበለ፡፡

በሞት ውስጥ ዘላለማዊነት እንጂ ጊዜ የለም የምንለውም ለዚሁ ነው፡፡ ህይወት በመጨረሻ ልትረግጠው የምትችለው ደረጃ ሞትን ብቻ ነው ሞት ከስጋህ ይለይሀል ፤አእምሮህን ይወስዳል..የምትመኘውና ተስፋ የምታደርገው ነገር ሁሉ መቆሚያው ሞት መሆኑን ማወቅህ ደግሞ ያስፈራሀል ፡፡ዕውቀት ሲበራልህና የመገለጥንም መሰላል ስትጨብጥ ግን ሞት የሚያስፈራ ክስተት ሳይሆን መለኮታዊ ሽግግር ሆኖ ይታይሀል፡፡ ኢኪዮን መልስ እናምጣ፡-

አንድ ምሽት በገዳም ውስጥ ተቀምጠው ሀይለኛ ቅዝቃዜ ይሰማቸዋል፤ በዚህ ጊዜ ከተቀመጡበት በመነሳት ከእንጨት ከተቀረፁት ሶሰት የቡድሀ ምስሎች አንዱን አንስተው በመፍለጥ እሳት አቀጣጥሉና መሞቅ ይጀምራሉ፡፡

ይህን የተመለከተ ደቀመዝሙር በድንጋጤ ‹‹መምህር! ምን እያደረጉ ነው? አብደዋል እንዴ? የቡድህ መነኩሴ ሲመስሉኝ እንዴት ቡድሀን አቃጥለው እሳት ይሞቃሉ?›› በማለት ጠየቃቸው፡፡

ኢኩዩ ግን በፈገግታ፡- ‹‹በውስጤ የሚገኘው ቡድሀ በጣም ሲበርደው ምን ላድርግ ብለህ ነው? ሕያው የሆነውን ቡድሀ ለእንጨት ቡድሀ መስዋዕት ማድረግ የተሻለ አይመስልህም?›› አሉት፡፡

በሞት ውስጥ የቡድሀን ሕያውነት የምናየው እንግዲህ በዚህ መልኩ ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙህን በሮች ሁሉን እየከፈትህ ስትሄድ ትቆይና አንድ እና የመጨረሻ በር ግን ከፊትህ ይጠብቅሃል፡፡ ይህን በር ከፍተህ ስትዘልቅ በዚያ በር ተመልሶ መውጣት የሚባል ነገር አይታሰብም፡፡ ይህ የመጨረሻ በር ነው፤ የመጨረሻውን በር ከማለፍህ በፊት ደግሞ የሞትን ፍርሃት የሚያሸንፈው የእውቀት መገለጥ ያስፈልግሃል፡፡ በዚያ የመገለጥ ደረጃ ላይ ስትገኝ የመጨረሻውን በር በፈገግታ ለማለፍ አይገድህም፡፡ ብቻህን አይደለህምና! ይህ ደግሞ በማንኛውም እምነት ውስጥ የሚገኝ ምስጢር መሆኑን ልብ እንበል፡፡ አስቀድመህ የፍርሃት ሁሉ ምንጭ የሆነውን እኔነትህን ተለየው፤ ‹‹እኔነት ከአንተ ከተለየ ለአንተ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ አይኖርህም፤ መወለድህን ዘወትር የምታስብ ከሆነ ግን መሞትህም እንዲሁ ያስጨንቅሃል፡፡ ቀጣዩን እንመልከት፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ዘመን ከሰዎች አንዱ ይቀርብለት የነበረ ጥያቄ፡- ‹‹አንተ መሲሁ ነህን? ወይስ አብርሃም ነህን. . .?›› የሚለው ነበር፡፡

ኢየሱስም፡- ‹‹አብርሃም ከመኖሩ በፊት እኔ አለሁ›› አላቸው፡፡ እዚህ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ምላሽ ስንመለከት ግራ አጋቢና ስህተትም ያለበት ሊመስለን ይችላል፡፡ የእምነት አባት የሚባለውና የመጀመሪያው ነቢይ አብርሃም የኖረበትን ጊዜ ወደኋላ ሄደን ካሰላን ደግሞ ኢየሱስ ዛሬ ላይ ቆሞ እንዲህ መናገሩ ስህተት ነው የሚሉ ይኖራሉ፡፡

ነገር ግን ኢየሱስ የሚነግረን ‹‹እኔ

አልተወለድኩም፤ አልሞትኩም›› ነው፡፡ ታላቁን የመገለጥ ደረጃ ስትጨብጥ ትናንትም ሆነ ዛሬ ወይም ነገ ፤አንተ አይኖርም፡፡ ጊዜን አልፈህ ትሄድና ዘላለማዊ ትሆናለህ፤ በዘላለማዊነት ውስጥ ደግሞ ጊዜ አይገኝም፡፡ በጊዜ ወሰን ከአንተ በፊት ከኖሩት እንኳን ትቀድማለህ፡፡ የኢየሱስ ምስጢር ተገለጠልህ ማለት እኮ በእሱ አለመወለድ ትወለዳለህ፤ በእሱ አለመሞትም ትሞታለህ፡፡

ዛሬ የሰው ልጅ የተያዘበት አንዱ ፍርሃት ከሞት በኋላ ወዴት እንደሚሄድ አለማወቁ ነው፡፡ ነገር ግን ወዴትም እንደማይሄድና መንገዱንም እየሄደበት መሆኑን ቢያውቅ ፍርሃቱ ከእሱ በተወገደ ነበር፡፡ ሞት ከአንተ የሚወስደው ሕይወትን ሳይሆን ጊዜን ነው፡፡ ጊዜ ደግሞ የአእምሮ ሀሳብና የሥጋ ምኞት የፈጠረው በነገ የሚገለፅ ክስተት ነው፡፡ ሞት ከአንተ ውስጥ ምኞትና ሃሳብን ሲወስድ ግን የሚቀረው አንተነትህ ከዘላለማዊነት ውስጥ የሚገለፅ ማንነት ይሆናል፡፡ የሕይወት ትርጉም ተንጠልጥሎ የሚገኘውም በእንደዚህ ዓይነቱ ‹‹ባዶነት›› (emptiness) ላይ እንጂ ከሞት በኋላ በምንጠብቀውና በሥጋ በተለማመድነው ዓለም ውስጥ በምናውቀው ምኞትና ሃሳብ ከሆነ ወዴት እንደምንሄድ ብቻ ሳይሆን ለምን እንደመጣንም ሳናውቅ የምናልፍ እንሆናለን፡፡

እዚህ ላይ በሞት ዙሪያ የጀመርነውን ቁፋሮ ስለሞት በሚደንቁ የዓለማችን እውነታዎችና ክስተቶች ማለዘብ የተሻለ ሆኖ አገኘሁት፡፡ እነዚህን እውነታዎች ማወቅ የሞትን ሀሳብ ቀለል ከማድረጉ ባሻገር የሞት መንገዱና አሟሟታችንም እንዲሁ የሚደንቅ ሆኖብኛል፡፡ የትኛው አሟሟታችን የተሻለ ይሆናል የሚለውን ለአንባቢዎቼ ፍርድ ልተውና ቀጣዮቹን የዓለማችን የሞት እውነታዎች እንመልከት፡፡ ለምሳሌ በዓለም ላይ በየዓመቱ በአውሮፕላን አደጋ ከሚሞተው የሰው ቁጥር በላይ በአህያ ምክንያት (ተገፍቶም ይሁን ተረግጦ) የሚሞተው ቁጥር ይበልጣል፤ ዝንብ የሰው ልጅን የገደለችውን ያህል የእስከዛሬ የምድራችን ጦርነቶች አልገደሉትም፡፡ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በዝንብ ምክንያት የተነሳውና የአውሮፓን አንድ አራተኛ ሕዝብ የጨረሰው ‹‹ጥቁር ሞት›› የተሰኘው በሽታ መንስኤ ዝንብ እንደነበር ያስታውሷል፤ ከምድር እንስሳት ሁሉ ደግሞ ለሰው ልጅ ሞት ዋነኛዋ መንስኤ የወባ ትንኝ ነች፡፡ ዛሬ በምድራችን ላይ አንድ መቶ አስራ ስድስት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መኖር የሚችል ሰው ከ2 ቢሊዮን አንዱ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው በምድር ሲኖር በሌላው ሰው የመገደል ዕድሉ ከ20 ሺህ አንድ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በጦር መሳሪያ ከሚሞተው የሰው ልጅ ይልቅ በሐኪሞች ስህተት የሚሞተው አምስት እጅ በልጦ መገኘቱንስ እናውቃለን፡፡

ከእነዚህ ዓይነቶቹ የሞት እውነታዎች ደግሞ ወደ ታዋቂ ሰዎች የሞት እውነታ ተሸጋግረን አንዳንዶቹን እንቆንጥር፡፡ ለምሳሌ ሮበርት ሄርቪ የተባለው ባለጸጋ በዓለም ላይ የሚታወቀው ሄርቪ ቸኮላት በተባለ ምርቱ ነው፡፡ ይህ ሰው የሞተው ደግሞ ቸኮላት የሚመረትበት ትልቅ ገንዳ ውስጥ በድንገት ወድቆና በቸኮላት ፈሳሽ ውስጥ ሰምጦ ነበር፡፡ ዶ/ር አሊስ ቼዝ በዓለም ድንቅ የተባለላትን ‹‹Nutrition for Health›› መፅሐፍ ያበረከተችና በጤነኛ አመጋገብ ዙሪያም በርካታ መፅሐፍትን የፃፈች ነች፡፡ ዶ/ር አሊስ በድንገት ከሞተች በኋላ ስለ አሟሟቱ የወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው ግን የሞቷ መንስኤ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የጀርመን ናዚ መንግስት

መሪና ለሚሊዮን አይሁዶች ሞት ምክንያት የሆነው አዶልፍ ሂትለር በእናቱ ማህፀን እያለ እናቱ መውለድ ባለመፈለጓ ሐኪሟ ፅንሱን ከሆዷ ውስጥ እንዲያወጣላት ብትለምነውም በሐኪሙ እምቢታ ምክንያት ልትወልደው በቅታለች፡፡ የዓለማችን የሠላም ተምሳሌትና ለገላው መሸፈኛ ከሚጠቀምበት እራፊ ጨርቅ በቀር ምንም እንደሌለው የታመነበት የሕንድ መሪ ማህተመ ጋንዲ ከሞት በኋላ አስከሬኑ ሲመረመር በቀጭን አንጀቱ ውስጥ አምስት የወርቅ እንክብሎች ተገኝተዋል፡፡ ታዋቂው የአሜሪካ የስነ ፅሁፍ ሰው ማርክ ትዌይን ሲወለድ ተወርዋሪ ኮከብ የታየችበት ቀን ነበር፡፡ ማርክ ትዌይን በአንድ ወቅት ይህ ተወርዋሪ ኮከብ ድጋሚ በምድር ላይ የሚታየው እሱ በሚሞትበት ቀን መሆኑን ተነበየ፡፡ በትክክልም ከ76 ዓመት በኋላ ኤፕሪል 12 ቀን 1910 ተወርዋሪ ኮከብ በምድር ላይ በድጋሚ ሲታይ ማርክ ትዌይንም ለዘላለም አንቀላፋ፡፡

እንግዲህ ይህን ያህል ከብዙው በጥቂቱ በሞት እውነታዎች ዘና ካልን በቂ ነው እላለሁና ወደጀመርነው ቁፋሮ እንመለስ፡፡ የሞት ትልቁ የመፈራት ምክንያት ወዴት እንደምንሄድ አለማወቃችን መሆኑን በቅድሚያ ብናስቀምጥም አሳባውያኑ ደግሞ ከየትም እንዳልመጣንና ወዴትም እንደማንሄድ የመገለጥ ደረጃ ላይ ብንደርስ ይህ ሁሉ ችግር አይኖርም ባይ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ከሕይወት እየቀነስን በሞት ፍርሃት የምንጨነቅበትን ጊዜ ሕይወትን በሙላት ለመኖር ማዋል የሚገባን፡፡ ሕይወትን በሙላት የኖረ ሲሞት በሞት ይስቃል እንጂ አያለቅስም፤ አያስለቅስም፡፡ ለምሳሌ ይህችን ዓለም ፈጣሪ ሰራት፤ ነገር ግን ሰይጣን አዳምና ሄዋንን ባያሳስትና የዕውቀት ዛፍ እንዳይበሉ ባያደርግ ዛሬ በምድር ላይ ‹‹ምንም›› ባልኖረ ነበር፡፡ ምክንያቱም በምድር ላይ የምናየው ነገር ሁሉ የተሰራው በዕውቀት ነውና! ይህ ዕውቀት ባይገኝ አዳምና ሄዋን ዛሬ እንደበሬ ሳርና ቅጠል እየበሉ በኤደን ጫካ ተቀምጠው ይቀሩ ነበር፡፡ ፈጣሪ በሰራው ምድር የአዳምና ሔዋን ዕጣ ፋንታ እኮ መኖር እንጂ መፍጠር አልነበረም፡፡ እንኳን ሌላውን የሰው ልጅ ዕውቀት የደረሰበትን ድንቅ ነገር ቀርቶ አምሳያቸውን ሰው የመፍጠር ብቃታቸው እንኳን ሰይጣን እስኪመጣ ድረስ ተሸፍኖ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ሰይጣን የምድራችን የመጀመሪያው አብዮተኛ ነው የሚባለው እሱ ባይኖር የዓለማችን ታላላቆች ቡድሀ፣ ኢየሱስ፣ መሀመድ፣ ሙሴ፣. . . ወዘተ ባላገኘናቸውም ነበር፡፡ እናም ስለሞት ስናስብ በእውቀት ጥበብ የተሸነፈ እንጂ ያሸነፈን አለመሆኑን እንረዳ፡፡ የሞት ማሸነፊያው ጥበብ ደግሞ ሕይወትን ክፉና በጎ በማለት ከፋፍሎ በመኖር ሳይሆን፤ ፍርድ ሳይሰጡ እንደአመጣጧ በሙላት ተቀብሎ መኖር ማለት ነው፡፡ በሞት መንገድ የጀመርነውን ፍተሻ በቀጣይዋ ወግ እንቋጫት፡-

አንድ ሕፃን እጅግ አድርጎ የሚወዳት ድመት መኪና ገጭቶ ይገድላታል፡፡ ሕፃኑ ግን የድመቱን መሞት አላየም ነበርና እናቱ ደብቃ ካቀፈቻት በኋላ እንዴት ብላ እንደምትነግረው ስትጨነቅ ትቆያለች፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ሕፃኑ ድመቷን መጠየቅ ይጀምራል፡፡ በዚህ ጊዜ እናት የድመቷን መሞት በዘዴ ልትነግረው በማሰብ እንዲህ አለችው፡-

‹‹አየህ ጆን. . .ድመቷን መኪና ገጭቶ ገድሏታል፤ ግን ምንም አይደለም፡፡ አሁን በገነት ከፈጣሪ ዘንድ ትገኛለች›› አለችው፡፡

በዚህ ጊዜ ሕፃኑ እናቱን በመደነቅ እየተመለከተ ጠየቃት፡- ‹‹ግን እማማ! የሞተ ድመት ፈጣሪ ምን ያደርግለታል?››

Page 40: ቁም ነገር በየ15 ቀኑ - Zehabesha – Latest Ethiopian News …‰ም ነገር በየ15 ቀኑ ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005 137ኛ ዕትም

ቁም ነገር

በየ1

5 ቀኑ

ቁም ነገር ቅፅ 11 ቁጥር 137 ጥቅምት 2005

137ኛዕትም

40

ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ጴላጦስ) ‹‹ጥበብ›› በተሰኙት ተከታታይ መፃሕፍቱ የሚታወቅ ደራሲ

ነው፡፡

ወደ ገፅ 39 ዞሯል

‹‹መወለድህን የምታስብ ከሆነመሞትህም ያስጨንቅሃል››

‘‘

ባለፉት ሁለት ተከታታይ የጥበብ ጉዞዎች ሞትን ከእምነት አንፃር ለመፈተሽ መሞከራችን አይዘነጋም፡፡ እነሆ ዛሬም በዚሁ ጉዞ ስንቀጥል ሞትን ከተለየ አቅጣጫ መፈተሽ ደግሞ የተገባ ሆኖ አገኘነው፤ ሙታን ከመቃብር የሚነሱበት ቀን እንደሚመጣ ይህም የፍርድ ቀን ተብሎ እንደሚታወቅ የተያዘውን እምነት ሳንዘነጋ ከሞት በኋላ ምን አይነት ህይወት ነው ሊኖረን የሚችለው የሚለውን የተቃራኒ አስተሳሰብ ደግሞ መፈተሽ እንጀምራለን፡፡ የጉዟችን መነሻ የሙላ ናስሩዲንን ገጠመኝ ብናደርግስ? (ሙላ ናስሩዲንን ከእንግዲህ ማስተዋወቅ የሚገባ መስሎ አይታየኝምና አዲስ አንባቢ የቀድሞውን የጥበብ መጣጥፎች አግኝቶ ቢመለከት በአንዱ ውስጥ አያጣውም)፡፡

አንድ ቀን ናስሩዲን አዘውትሮ ቡና ወደሚጠጣበት ስፍራ አንድ የህክምና ዶክተር እና ሌላው ደግሞ መምህር የሆኑ በመምጣት ተቀምጠው ወግ ይጀምራሉ፡፡ የወጋቸው ርዕስ ደግሞ ሞት ነበር፡፡

የህክምና ዶክተሩ እኔ ከሞት በኋላ በሳጥን ውስጥ ሆኜ አንድ ጊዜ የመስማት ዕድል ባገኝ ታላቅ

ዶክተርና ቤተሰቡን አፍቃሪ ነበር በማለት ሰዎች ሲናገሩ መስማት እሻለሁ አለ፡፡

መምህሩ በበኩሉ “እኔ ደግሞ ታላቅ መምህር እንደነበርኩና በትውልድ ውስጥ ታላላቅ ሰዎችን እንዳፈራሁ እንዲሁም ትዳሬን አክባሪና አፍቃሪ እንደነበርኩ ብሰማ ደስ ይለኛል”አለ፡፡

ናስሩዲን የሁለቱንም ካደመጠ በኋላ፡- ‹‹እኔ ግን ‹‹ተመልከቱ !ይንቀሳቀሳል!›› በማለት ሰዎች ወደ እኔ እየጠቆሙ ሲያወሩ ማዳመጥ ምኞቴ ነው›› አለ፡፡

ለአንዳንድ አሳብያን ሞት በህልም ይመሰላል፡፡ በህልምህ ስታደርግ የምታየውን ነገር አስታውስ ይሉናል እነዚህ አሳብያን፡፡ በእውኑ አለም ያለህ ያህል ታስባልህ፤ ትስቃለህ፤ ታወራለህ፤ ትሮጣለህ፤ ትወድቃለህ፤ ትነሳለህ፤…ወዘተ ስትነቃ ግን በአልጋህ ላይ እንደተኛህ ነው፡፡ በእውነታው አንተ የምትገኘው በዚህ አለም ላይ ነው፤ በመንፈስ

ግን ወደመለኮታዊው አለም ተሻግረህ እራስህን እየተመለከትክ ነው፡፡ በአጭሩ ከእውነታው አለም ባሻገር ሌላ በስጋህ የተለማመድከውን የምትፈፅምበት መንፈሳዊ አለም መኖሩን ማሳያ ነው ይላሉ፡፡

እዚህ ላይ ህልም መልካምና አስደሳች ነገር ብቻ የሚታይበት ሳይሆን መጥፎና አስፈሪ ቅዠቶችን የተሞላ መሆኑን ደግሞ ልብ በሉ የሚሉን አሉ፡፡ ከአስፈሪ ህልም ለመውጣት ትግል የምትገጥመውን ያህል አስደሳች ህልም ደግሞ ወደ እውነታው አለም መመለስ እንኳን እስኪያስፈራህ ድረስ የምታጣጥመው ትዕይንት ነው፡፡ ከእንደዚህ አይነቱ ህልም ስትመለስ እንኳን በእውነታው አለም አንዳች ትርጉም ሰጥተህ የወደፊቱን ተስፋ አድርገህ ትጠብቅበታለህ እንጂ የስጋዊ ምኞትና ሀሳብህ አንዱ ነፀብራቅ አድርገህ በቀላሉ የምትረሳው ነገር አይደለም፤ ለዚህ ነው ስለወደፊትህ ተስፋ የምታደርገውና የምትጠብቀው ነገር ባልኖረ ህልም ባይኖር የሚሉን አሳባውያኑ፡፡

በሞት ውስጥ ግን የወደፊት የሚባል ነገር የለም፡፡ ህልም፣ ቦታ፣ ጊዜና እንቅስቃሴ ሲፈልግ ሞት ግን ይህን የምታስብበት ዕድል አይሰጥህም፡፡ ስትሞት ነገ ምን እሆናለሁ፣ ምን ይደርስብኛል ከሚል ስጋት ነፃ ስለምትወጣ መሻትም ሆነ ፍላጎት አይኖርህም፡፡

በአጭር አገላለፅ ሞት የሚገድለው አንተን ሳይሆን ነገህን ነው፡፡ነገ ደግሞ የመኖርህ ወሳኝ ጉዳይ ነው ሁሉን የምታደርገው ለነገ መኖርህ ዋስትና እስከሆነ ብቻ እንደሆነ ልብ በል፡፡ ነገ ደግሞ የሚገኘው በጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ሞት ጊዜህን (ነገህን) ከገደለ ጊዜ ለአንተ የለም ማለት ይሆናል፤ ያለጊዜ ደግሞ ምን ማድረግ ትችላለህ? ያለ ጊዜ አእምሮስ ምን ያስባል፤ ምንስ ይመኛል፤ ምንስ ያመጣል? ሞት የጊዜን በር የሚዘጋ ሀይል ነው፤ ይህ ደግሞ ታላቅ ፍርሀት ይፈጥራል፡፡ ለመሆኑ ሞትን ይህን ያህል የምንፈራው ለምን ይሆን?

ለዚህ አጭሩና ቀላሉ መልስ ሆኖ የምናገኘው በሞት ውስጥ አሻግረህ የምትጠብቀውና ተስፋ የምታደርገው ነገር አለመኖሩ ነው፡፡ ህይወት በሙሉ በማሰብ የተሞላ ሆኖ ኖሯል ..ሞት ግን ማሰብን አይፈቅድልህም፡፡ በህይወትህ መገለጥ ደረጃ ላይ ስትደርስ ህይወት ማሰብ እንደማያስፈልጋት ታውቃለህ፤ ያን ጊዜ ሞትን መፍራት ሳይሆን ለመቀበል የተዘጋጀህ ትሆናለህ፡፡ ህይወት በመጨረሻ የምታስጨብጥህ መገለጥ ሞትን እንደሆነ ታያለህ፡፡ በቀጣዩ የዜን ቡድሂዝም ወግ ሀሳባችንን እናፍታታው፡-

የዜን ደቀመዝሙር የሆነው ኑናካዋ ለመሞት በሚያጣጥርበት የመጨረሻ ሰዓት የፍርሀት ስቃይ እያስጨነቀው ሲወራጭ የተመለከቱት የዜኑ መምህር ኢኪዮ “መንገድህን እመራህ ዘንድ ትወዳለህን

ፈጣሪ በሰራው ምድር የአዳምና

ሔዋን ዕጣ ፋንታ እኮ መኖር እንጂ መፍጠር

አልነበረም፡፡