AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ...

24
Dr. Sirak Hailu Chiropractic Physician በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ Saint Paul 1821 university Ave. w. Suit106 St. Paul, MN 55104 (651) 647 9100 Minneapolis 615 Cedar Ave. South Minneapolis, MN 55454 (612) 990-5314 18 18 18 ዓመት የጋራ የሥራ ልምድ አለን ዓመት የጋራ የሥራ ልምድ አለን ዓመት የጋራ የሥራ ልምድ አለን የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ታህሳስ 2005 ቅጽ IV ቁጥር. 46 ዘወትር ሰኞ የተማሪዎች ብፌ ሐሙስ እና እሁድ የተለመደው ብፌ ይጠብቃችኋል (651)-646 6900 or 1-877-302-3347 1821 university Ave. w. Suit 143 St. Paul, MN 55104 ዕውነትን እንጽፋለን፤ ዕውነት ያሸንፋል!! 2812 university Ave, Mpls, MN 55414 Tel: (612)770-3270 www.aklogasfawinsurancemn.com $10 Home sell- ing and buying is easy when you list with Demssie AMERICAN REALTY GROUP. Call the guy that knows how to make It happen! በመተባበር፣ በመመካከር አብረን እንክበር OFF. (763) 951 2931 Cell (612) 644 7665 Fax (763) 432 5069 [email protected] ቫይኪንድስን(Vikings) እና የአሜሪካን እግር ኳስ ዓለም 21 የቺካጎውን ኢትዮጵያዊ እውን መኪና ገጨውና ሞተ? 4 ዲሴምበር 12 ቀን 2012 ዓ.ም Minnesota Department of Health - Refugee Health Program ባስተካከለውና ለሕዝብ ይፋ ባደረገው መረጃ በ2011 ወደ ሚኒሶታ የመጡት የስደተኞች ቁጥር 1981 እንደሆነ ታወቀ። ዲፓርትመንቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ ከነዚህ ስደተኞች መካከል 100 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው። (ወደ ገጽ 16 የዞረ) ገጽ 6 የሚኒሶታ ዲፓርትመንት ኦፍ ኸልዝ (MDH) የዓለም አቀፉን የኤድስ ቀንን አስታኮ የአፍሪካውያን የኤድስ ቀንን በየዓመቱ ያከብራል። ዘንድሮም ይህ African World AIDS Day (AWAD) በዓል በሚኒያፖሊስ ሳፋሪ ሬስቶራንት (ኤድስ...ወደ ገጽ 7 ይዞራል) የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃውና ጉልበቱ በ20$ ብቻ። - Engine - Brakes - Suspension - Transmission - Electrical - Body - Interior More... ገ/መድህን የሙዚቃ ኮንሰርት የሚደረገው Dancers Studio Well- ness (415 Pascal St. N., Saint Paul, Minnesota 55104) መሆኑን ያስታወሰው ቡሽማን ኢንተርቴይመንት ወደፊትም ሌሎች ድምጻውያንን እንደሚያመጣ አስታውቋል። ቡሽማን ኢንተርቴይመንት መቀመጫውን በሚኒሶታ ያደረገና ለተለያዩ ዝግጅቶች የቪድዮ ፕሮዳክሽን ሥራዎችን ይሰራል። “ቺጌ” በሚለው ሲዲው ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ሃይሌ ሩትስ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እየተዘዋወረ ሥራዎቹን ሲያቀርብ ቆይቷል። አብርሃም ገ/መድህንም ከትግርኛ ዘፈኖቹ በተጨማሪ በትግርኛ የሙዚቃ ስልት “አንቺ ነሽ ሃገሬ” በሚለው ተወዳጅ የአማርኛ ዘፈኑ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፈዋል። (ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ የተለያዩ ዝግጅቶች ይደረጋሉ። በዋነኝነት ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ተወዳጆቹ ድምጻውያን ሃይሌ ሩትስና የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋቹ አብርሃም ገ/መድህን የሚያደርጉት የሙዚቃ ዝግጅት በጉጉት ይጠበቃል። ይህ የአዲሱ ዓመት የሙዚቃ ኮንሰርትን በሚኒሶታ ያዘጋጀው ቡሽማን ኢንተርቴይመንት ሲሆን ድርጅቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው ላይ “በዚህ የአዲሱ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ኮንሰርት ኢትዮጵያውያን ወጥተው በነዚህ ሁለት ተወዳጅ ድምጻውያን ዘፈኖች እየተዝናኑ በጋራ አዲሱን ዓመት እንቀበል” ሲል ጥሪውን አቅርቧል። ሰኞ ዲሴምበር 31 ቀን 2012 የሃይሌሩትስ እና የአብርሃም Ze-Habesha Newspaper Dec. 2012 Volume No.46 612-226-8326 KATAR RIVER RESTAURANT & BAKERY 2751 MINNEHAHA AVE, MPLS, MN 55406 በተቀበልነው ሽልማት በመበረታታት የተሻለ አገልግሎት እየሰጠን ነው ኬክ በትዕዛዝ ማቅረብ ጀምረናል 651-214-2584 ወይም 651-489-9220 አሁን ጊዜው የኢስት አፍሪካ የጤፍ እንጀራ ነው የሃገራችንና የውጭ ሃገር ቁርስ፣ ምሣና ራቶችን አድራሻችን የቀድሞው የሕንድ ሬስቶራንት የነበረው ራጃ መሐል ፍራንክሊን አቬንዩ ላይ ሚኒያፖሊስ 3025 E Franklin AveMpls, MN 55406 ( 612-344-5829) Lucy Ethiopian Restaurant ኬተሪንግ እንሠራለን ኬተሪንግ እንሠራለን ኬተሪንግ እንሠራለን

Transcript of AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ...

Page 1: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

Dr. Sirak Hailu

Chiropractic Physician

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

Saint Paul 1821 university Ave. w.

Suit106 St. Paul, MN 55104

(651) 647 –9100

Minneapolis 615 Cedar Ave. South

Minneapolis, MN 55454

(612) 990-5314

18 18 18 ዓመት የጋራ የሥራ ልምድ አለንዓመት የጋራ የሥራ ልምድ አለንዓመት የጋራ የሥራ ልምድ አለን

የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46

ዘወትር ሰኞ የተማሪዎች ብፌ ሐሙስ እና እሁድ የተለመደው ብፌ ይጠብቃችኋል

(651)-646 6900 or 1-877-302-3347 1821 university Ave. w. Suit 143

St. Paul, MN 55104

ዕውነትን እንጽፋለን፤ ዕውነት ያሸንፋል!!

2812 university Ave, Mpls, MN 55414

Tel: (612)770-3270

www.aklogasfawinsurancemn.com

$10

Home sell-

ing and buying is

easy when you list

with Demssie

AMERICAN REALTY GROUP.

Call the guy that

knows how to

make

It happen!

በመተባበር፣ በመመካከር አብረን እንክበር OFF. (763) 951 2931 Cell (612) 644 7665 Fax

(763) 432 5069 [email protected]

ቫይኪንድስን(Vikings) እና የአሜሪካን እግር ኳስ ዓለም 21

የቺካጎውን ኢትዮጵያዊ እውን መኪና

ገጨውና ሞተ? 4

ዲሴምበር 12 ቀን 2012 ዓ.ም Minnesota Department of Health - Refugee

Health Program ባስተካከለውና ለሕዝብ ይፋ ባደረገው መረጃ በ2011 ወደ ሚኒሶታ የመጡት የስደተኞች ቁጥር 1981 እንደሆነ ታወቀ። ዲፓርትመንቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ ከነዚህ ስደተኞች መካከል 100 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው። (ወደ ገጽ 16 የዞረ) ገጽ 6

የሚኒሶታ ዲፓርትመንት ኦፍ ኸልዝ (MDH) የዓለም አቀፉን የኤድስ ቀንን አስታኮ

የአፍሪካውያን የኤድስ ቀንን በየዓመቱ ያከብራል። ዘንድሮም ይህ African World AIDS

Day (AWAD) በዓል በሚኒያፖሊስ ሳፋሪ ሬስቶራንት (ኤድስ...ወደ ገጽ 7 ይዞራል)

የመኪናዎን ዘይት

ካለቀጠሮ እንቀይራለን

የዝናብ መጥረጊያዎን

ለማስቀየር እቃውና ጉልበቱ በ20$ ብቻ።

- Engine - Brakes - Suspension - Transmission

- Electrical - Body - Interior

More...

ገ/መድህን የሙዚቃ ኮንሰርት የሚደረገው Dancers Studio Well-

ness (415 Pascal St. N., Saint Paul, Minnesota

55104) መሆኑን ያስታወሰው ቡሽማን ኢንተርቴይመንት ወደፊትም ሌሎች ድምጻውያንን እንደሚያመጣ አስታውቋል። ቡሽማን ኢንተርቴይመንት መቀመጫውን በሚኒሶታ ያደረገና ለተለያዩ ዝግጅቶች የቪድዮ ፕሮዳክሽን ሥራዎችን ይሰራል። “ቺጌ” በሚለው ሲዲው ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ሃይሌ ሩትስ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እየተዘዋወረ ሥራዎቹን ሲያቀርብ ቆይቷል። አብርሃም ገ/መድህንም ከትግርኛ ዘፈኖቹ በተጨማሪ በትግርኛ የሙዚቃ ስልት “አንቺ ነሽ ሃገሬ” በሚለው ተወዳጅ የአማርኛ ዘፈኑ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፈዋል። (ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል)

የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ የተለያዩ ዝግጅቶች ይደረጋሉ። በዋነኝነት ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ተወዳጆቹ ድምጻውያን ሃይሌ ሩትስና የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋቹ አብርሃም ገ/መድህን የሚያደርጉት የሙዚቃ ዝግጅት በጉጉት ይጠበቃል። ይህ የአዲሱ ዓመት የሙዚቃ ኮንሰርትን በሚኒሶታ ያዘጋጀው ቡሽማን ኢንተርቴይመንት ሲሆን ድርጅቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው ላይ “በዚህ የአዲሱ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ኮንሰርት ኢትዮጵያውያን ወጥተው በነዚህ ሁለት ተወዳጅ ድምጻውያን ዘፈኖች እየተዝናኑ በጋራ አዲሱን ዓመት እንቀበል” ሲል ጥሪውን አቅርቧል። ሰኞ ዲሴምበር 31 ቀን 2012 የሃይሌሩትስ እና የአብርሃም

Ze-Habesha Newspaper Dec. 2012 ᴥ Volume No.46 612-226-8326

KATAR RIVER RESTAURANT & BAKERY 2751 MINNEHAHA AVE, MPLS, MN 55406

በተቀበልነው ሽልማት

በመበረታታት የተሻለ

አገልግሎት እየሰጠን ነው ኬክ

በትዕዛዝ ማቅረብ ጀምረናል

651-214-2584 ወይም 651-489-9220

አሁን ጊዜው የኢስት አፍሪካ

የጤፍ እንጀራ ነው

የሃገራችንና የውጭ ሃገር ቁርስ፣ ምሣና ራቶችን አድራሻችን የቀድሞው የሕንድ ሬስቶራንት የነበረው ራጃ መሐል ፍራንክሊን

አቬንዩ ላይ ሚኒያፖሊስ

3025 E Franklin Ave፣ Mpls, MN 55406

( 612-344-5829)

Lucy Ethiopian Restaurant ኬተሪንግ እንሠራለንኬተሪንግ እንሠራለንኬተሪንግ እንሠራለን

Page 2: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Page 3: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Ras Event Calendar

Saturday

Dec. 22 የምሽት ጨዋታ

——

Saturday

Dec. 29 ዳንኪራ ናይት

——

Every

Wednesdays ዲጄ ጆኒ ——

ኑ ተዝናኑ

ከራስ ምርጥ ምግቦች መካከል ልኳንዳ ጥብስ ከአዲስ አቀራረብ ጋር

ስፖርታዊ ጨዋታዎችን ለመከታተልራስ ምቹ

ነው

Page 4: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

ከዘላለም ገብሬ የቺካጎ የዘ-ሐበሻ ወኪል ባለፈው ሳምንት አርብ ምሽት እኩለ ለሊት ላይ ነበር

ለወላጅ እና ዘመድ አዝማዶቹ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ዜና ከአካባቢው የእለት ተረኛ ፖሊስ አባላት የልጃቸውን ህይወት ድንገተኛ አደጋ ላይ መውደቅ የሰሙት ።ይህንን ያልተጠበቀ ዜና መስማትም አይደለም ይሆናል ታስቦ አይታወቅም ፡ምናልባትከልጁ የአስተዳደግ እና የተፈጥሮ ባህርይ አንጻር እንዲህ አይነቱን ነገር መጠበቅም ሆነ መገመት ከባድ የሆነ የአይን ብዥታን ይፈጥራል ።በቺካጎ እና አካባቢዋ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አባላቶችም ሆኑ ሌሎች ዜጎች የዚህ ልጅ ወጣት በአጭር መቀጨት ያላስቆጫጨው ያሉ አይመስሉም ሁሉም እንደ እግር እሳት አንገብግቦአቸዋል አቃጥሎአቸዋል አዝነዋል ተክዘዋል አንብተዋል ሃዘናቸው አብሮአቸው እንደሚዘልቅ ትልቅ የፍቅር መተሳሰብ ያሳዩበት አጋጣሚ ….የሚኪያስ ህይወት በአጭር መቅረት ።

በደረቀው ለሊት የመጣው ይኸው አስከፊ ዜና የ እያንዳንዱን የኢትዮጵያዊ የልብ ስብራት ሆኖበታል በተለይም ወላጆቹን በቅርበት የሚያውቅ ሁሉ ሲያለቅሱ ያላለቀሰ ሲተክዙ ያልተከዘ ዝም ያለም አልነበረም ሁሉም በመንፈስ አብሮአቸው ተጉዞአል ።በእርግጥ ይህ ሎሆን የቻለበት ምክንያት በትምህርቱ ጎበዝ በባህርይው ቅን ሰውን አክባሪ እና ታዛዥ ሲሆን የወደፊት የኢትዮጵያ ባለ ራእይ የሆነ ወጣትን መነጠቅ አስመልክቶ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ይኸውም የአስራ ስምንት አመቱ ታዳጊ ወጣት ሚኪያስ ተፈራ በየነ ።

የሚኪያስ ተፈራ የህይወት ታሪኩ ከሚያሳየው አጭር መስመር ለአንባቢዎቻችን እንዲህ ብናስተዋወቃችሁ ወደድን እና ሚኪያስ ተፈራ ማን ነው ወደሚለው አጭር መዘርዝር ገባን …..ሚኪያስ ከአባቱ ከዶ/ር ተፈራ በዬ እና ከ እናቱ ወ/ሮ ንግስት አለሙ ገብረ ህይወት እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በኖቬምበር 12/1994 አመተ ምህረት በባህርዳር ከተማ ተወለደ ፣ከዚያም አባቱ በስራ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ በተዛወረበት ወቅት ወደ አዲስ አበባ ከቤተሰቦቹ ጋር በመዛወር ኑሮውን ለአጭር ጊዜ በመዲናይቱ አዲስ አበባ አደረገ ከዚያም በ1995 አመተ ምህረት እንደ ኤሮጳውያን አቆጣጠር ወደ አመሪካን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ አማክይነት መጥቶ ይህወቱን በሚድ ዌስት አካባቢ በሚገኘው ኢሊኖይ ስቴት ሸምበርግ ከተማ ውስጥ ኑሮአቸውን አደረጉ በተለያዩ ጊዜያትም በቺካጎ እና አካባቢዋ ማድረጋቸውም መረጃዎች ቢጠቁሙም ህይወቱን ግን በስኬት መምራት እና የትምህርቱን ቀዳሚነት ያሳየበት በሸምበርግ በሚገኘው ትምህርትቤቱ ውስጥ ባለ ብዙ ታሪክ መሆኑ ከተለያዩ መረጃዎች ለመረዳት ችለናል ሚኪያስ ከአጎቶቹ አክስቶቹ እናቱ እና አብቱ እንዲሁም እህስቶቹ እና ሌሎች የቅርብ ዘመዶቹ ጋር በመሆን ህይወቱ እስካለፈበት

ባለፈው ሳምንት አርብ ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር በደስታ ይኖረ የነበረ ፍልቅልቅ ወጣት ነበር ።ሚኪያስ በትምህርቱ በጣም ደስተኛ እና ጎበዝ ሲሆን በአጭር ረቀት ሩጫም ሃገራቸውን ካስጠሩት አትሌቶች ተርታ ይመደባል ተብሎ ትልቅ ስፍራ ከተሰጣቸው ታዳጊዎች መካከል አንዱ ነበር ።ህይወቱም ባለፈችበት እለትም የሩጫ ውድድር አከናውኖ የአሸናፊነትን ቦታ ተቀዳጅቶ ነበር ያሉት የቅርብ ዘመዶቹ ይህ ብቻም አይደለም በካሊፎርኒያ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ውስጥ የሙሉ ስኮላር ሽፕ አግኝቶ ሊሄድ የቀረው 4 ቀናት ነበር የቀሩት ዛሬስ ምን ነካብን እና ህልሙን ባጭር አደረገው በማለት ስሜታቸውን መ ቆ ጣ ጠ ር እስኪሳናቸው ድረስ እንባቸውን ያረግፋሉ ፤ሃዘናቸው እውነትን ፍለጋ ጎዞ ላይ እንደሆነች ያሳያሉ የዚያችን እውነትን ፍለጋ አቋራጭ ጎዳና ማን ያገኛት ይሆን ? እንዴት የሚኪያስ ህይወት በአጭር ልትቀጠፍ ቻለች የሚለውን አወዛጋቢ ሃሳብ እነሱ ግን አይጋሩትም ሁሉም ይህ ሊሆን አይችልም ይላል በአጠቃላይ በችካጎ የሚገኘውን ህብረተሰብ እንዴት ? መቼ ? ለምን ? በማን እና የት ? የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች አእምሮውን ወጥሮ ይዞታል ።

ለዚህም ምላሽ ለማግኘት ወላጆቹም ጥቂት ጊዜ ለምርመራ እንስጣቸው ይላሉ ወገኖቼ አሉ ዶ/ር ተፈራ በየነ በእኔ የደረሰ አይድረስባችሁ ነገር ግን የ እኔን ልጅ ጉዳት እንደ ልጃችሁ አይታችሁ ህብረታችሁን አሳዩኝ ውጤቱን ማየት ፍላጎት አለን ጉዳዩን በነጻ በሆነው ፍርድ ቤት እንዲታይልኝ በጋራ አብራችሁኝ እንጓዝ ዘንድ እጠይቃችኋለሁ ይላሉ ። የህግ ባለሙያው በሙያው ፣ወጣቱም በሃሳቡም ይሁን ባለው ሙያ ሌላውም ህብረተሰብ ቢሆን እንደ ቤተሰብ በቅርቡ በሚኪያስ ስም በምናወጣው አዲስ ዌብ ሳይት ሃሳባችሁን እንቀበላለን አንድነታችንን እናሳያለን ነገም ቢሆን በሌላው ወገናችን እንዳይደርስ ዛሬ ላይ ቆመን ምን ደረጃ ላይ እንዳለን ማሳየት አለብን ይላሉ ዶ/ር ተፈራ ። ወደ ሚኪያስ የህይወት ታሪክ እንመለስ እና ወጣቱ ጎበዝ ተማሪ ካገኛቸው አጠቃላይ

አዋርዶችን ጠቀስ እናድርግላችሁ እና የእውቀቱን አድማስ ስፋት እንገራችሁ ፤

፩ኛ በአጠቃላይ በትምህርት ውጤቱ ሁልጊዜም የማእረግ ተሸላሚ ነበር

2ኛ በ2007 የአሜሪካን ፕረዚዳንት ጆርጅ ቡሽ የከፍተኛ ትምህርት ከፍተኛ ተሸላሚ ነበር።

3ኛ በ2009 በአሜሪካ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የከፍተኛ ትምህርት ማእረግ ተሸላሚ ነበር

4ኛ በ2011 በትምህርት ቤቱ የስፓኒሽ ኦነር ሶሳይቲ ኢንዱኬትድ በመሆን ተመራጭ ሆኖአል 5ኛ በ2012 ከትምህርት ቤቱ የከፍተኛ የትምህርት ማእረግ ሜዳሊያ ተሸላሚ 6ኛ በ2012 የሚድ ሰበርብ ሊግ ሶስተኛ ደረጃ ተሸላሚ 7ኛ በ2012 በስቴት ኦፍ ኢሊኖይ የስቴት ስኮላር ሆኖ ተመረጠ 8ኛ በ2012 የናሽናል አዋርድ ዊነር ነበር 9ኛ በ2012 በካሊፎርኒያ የሚገኘው የፖሞና ኮሌጅ ምኡሉ ስኮላር ሺፕ የማጠቃለያ ተመራጭ በመሆን የመግቢያ ጥያቄና መልስ ዝግጅት ወይንም

ኢንተርቪው ለማድረግ በጉጉት ላይ ሳለ በአስከፊው አደጋ ህይወቱን የተነጠቀ ታላቅ ሰው መሆኑ የሚያሳዩ አጭር መዛግብቶቹ ያሳያሉ ።

በልጅነት እድሜው ከወላጆቹ ጋር የአሜሪካንን ህይወት አንድ ብሎ የጀመረው ይሄው ወጣት (ሚኪያ ተፈራ)ለቤተሰቦቹ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኑም መጠን ለእናት እና አባቱ ብርቅዬ ከመሆኑም በላይ ለህይወታቸው መስመር ልፍቅራቸው ደግሞ ማገር እንደነበር እና ውሮ ዎሸባ ተብለው ከተዳሩ በኋላ ያገኙት የመጀመሪያ ፍሬአቸውን ማጣታቸው ልባቸውን ብቻም ሳይሆን ቅስማቸውንም መሰበሩን ከዜና እረፍቱ በኋላ የስራተ ቅብሩ በተፈጸመበት ወቅት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ጓደኞቻቸው ቆመው ከገለጹት መካከል ነበር።በመቀጠልም እንዲህ አሉ “ዛሬ በመከራ ተገናኝተናል እንደ እኔ ወጣት እና ታዳጊ ልጅ ያላችሁ ወላጅ ቤተሰቦች ልጃችሁን አትነጠቁ መራራነቱ ይከፋባችኋል ሆኖም ላደረጋችሁት ትልቅ አስተዋጽኦ እግዚአብሄር ብድሩን

ይክፈላችሁ እኔ ምንም አቅም የለኝም ሆኖም ግን በዛሬው እለት ለዕኔ የመከራ ቀንም ቢሆንም በዚህች እለት እኔን እና የምወዳትን ባለቤቴን ንግስትን ለማጽናናት እዚህ ተገኝታችሁ ስላጽናናችሁን ከልብ እናመሰግናለን አሁንም ብድራችሁን በደስታ ይመልስልኝ በማለት አይናቸው እንደጎርፍ የሚያወርደውን እንባቸውን የጠራረጉ መናገር ቀጠሉ ግን አልቻሉም ሃሳባቸው ተቋረጠ አዳራሹም በእንባ እና ጩኸት እንደገና አስተጋባ ።አስራ ስምንተኛ አመቱን ከያዘ ብዙ ወራትን ያላስቆጠረው ታዳጊው ወጣት ሚኪያስ ተፈራ የተገደለው በመኪና አደጋ ተገጭቶ ገጭው አምልጦአል የሚል ምክንያት ከፖሊስ መኮንኖች እና መርማሪዎች ተደጋጋሚ የሆነ ምላሽ ይሰጥ እንጂ አሁንም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተለያዩ የተዛቡ ሃሳቦችን ማሰራጨታቸውን ቀጥለዋል ሆኖም የምርመራው ውጤት እስካሁም አልተገለጸም ከ3 ሳምንት በላይ የሚቆየው ይሄው ምርመራ ምን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ማንም የሚገምተው ነገር የለም ግን ሁሉም በጉጉት ምን ይሆን ገዳዩ እውነት ፖሊሶች እንደ ተናገሩት መኪና ይሆን ከሆነስ እንዴት ጉዳቱ ለምን አልከፋበትም የተፈነገተ ወይንም የግጭት ምልክት አያሳይም የሚለው ጥርጣሬ ሁሉንም እያነጋገረ ያለ ትልቅ የወቅቱ ጉዳይ ሆኖ ያለ ሃሳብ ነው ።በአንዳንድ ግለሰቦች አመለካከት ደግሞ እንዲህ ያለው የማጭበርበር ምልክት ነው ህብረተሰቡን ለማደናገር ያደረጉት እቅድ እንጂ ይህ የተቀነባበረ ወንጀል ነው የመኪናም ግጭት አይደለም በማለት ያሰምሩበታል ።በቺካጎ የሚገኙትንም ማህበረሰቦችም .. .. የልጃችን ህይወት እንዲህ ባለ ሁኔታ ሊቀጠፍ እንደማይችል ጠንቅቀን እናውቃለን እንደዚያም ከሆነ ገጨው የተባለውን መኪና ይዛችሁ አቅርቡልን እኛም ፍርዱን ለእግዜር እንተው ወይንም ጉዳዩ በፍርድ ቤት ይታይ ሲሉ ይናገራሉ ሙግታቸውንም ይሞግታሉ ።

ስለ ግጭቱም አስመልክቶ የተያዘ ከሌለ በወቅቱ ከጓደኞቹ ጋር እጓደኞቹ ቤት ፊልም በማየት እስከ ምሽቱ 11፡30 ድረስ በሰላም እንደነበር እና ወላጅ አባቱ መጥቼ ልውሰድህ ሲለው አይ ጓደኞቼ ያደርሱኛል ከ እነሱ ጋር መምጣት ስለምችል አትቸገር ብሎት የአንድ ሰአት ጊዜ እንዲሰጠው ፈቃዱን ጠይቆት በአንድ ሰአት ልዩነት ውስጥ ህይወቱ ጠፋ ተብሎ ከፖሊሶች ሲነገራቸው ምን ሊያስቡ ይችል ይሆን ?የጊዜያቶቹን ሁነቶች እና እንቅስቃሴዎች የተመለከተ ሁሉ ፍርዱን ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲያተኩሩ ያደርጋሉ ።በተለይም በምርመራ ወቅት ተይዘው ወደ ነበሩት ሶስት ጓደኛሞች ላይ ያተኩራል ግን ፖሊሶች እነሱን ሃያ አራት ሰአት ባልሞላ ጊዜያት ውስጥ ከእስር ቤት እንዲለቀቁ አድርጓል ለምን ይህም ምንም ፍንጭ ያልተገኘለት አጀንዳ ነው ። አክስቱ አበባ ገብረህይወት እንዳለችው ከሆነ ቀድሞ አብረውት እቤቱ ድረስ ያደርሱት የነበሩ ልጆች ከ2ኛ ክፍል (ሚኪያስ... ወደ ገጽ 9 የዞረ)

በፖስታ፤ ኢሜይል፤ በሶሻል ኔትወርኮች፣ በስልክ እና በአካል እናንተ አንባቢያን ያቀረባችሁት አስተያየት የሚስተናገድበት ነጻ አምድ ነው። ይጻፉልን፤ ይደውሉልን። (e-mail:- [email protected])

Ze-Habesha Newspaper is Legally

Registered in state of Minnesota -

USA

Founded in December 2008 Publisher :-

ZeHabesha LLC

ዋና አዘጋጅ:- ሔኖክ

ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in

Chief:-

Henok A.

Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:- ሊሊ ሞገስ፣

[email protected] ሮቤል ሔኖክ፣

[email protected] ቅድስት አባተ ዘላለም ገብሬ (ቺካጎ) [email protected]

አማካሪ፡- ዶር ዓብይ ዓይናለም

Ze-Habesha newspaper Address:-

6938 Portland Ave,

Richfield MN 55423

612-226-8326

www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabesha

www.twitter.com/zehabesha “Journalism can never be silent: that is its greatest virtue and its greatest fault. It must speak, and speak immediately, while the echoes of wonder, the claims of triumph and the signs of horror are still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ - አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው

ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ መልዕክት

ከታምራት ተስፋዬ ሰከንዶች ደቂቃን፣ ደቂቃ ሰዓትን፣ ሰዓት ቀናትን እየፈጠሩ

ይኸው ዛሬ ላይ ደረስን፡፡ ዛሬ ትላንት አይደለም፤ ትላንት የዓለምን ሁኔታ ለመተንበይ

የነቢይነትን ሚና መጫወት አይጠበቅብንም ነበር፡፡ ትላንት የዓለም ሁኔታ በአዝጋሚ ለውጥ ውስጥ ከመሆኑም በላይ ዓለም ለስር ነቀል ለውጥ የተጋለጠች አልነበረም፡፡ ዛሬ ሁሉ ነገር ከመለወጡ የተነሳ ነገን ለመተንበይ የማይቻልበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል፡፡ የማትጨበጠውን ዓለም ለመረዳት ሀገራችን ባለፉት ሦስት ወራት ያሳለፈውን ሁኔታ ማሰብ ብቻ በቂ ነው፡፡ ለዛሬም የሰሞኑ ዓቢይ ክስተት የሆነውን ፖለቲካዊ ለውጥ እስኪ ትንሽ አብረን እንየው፡፡

በነገራችን ላይ ገለአድ ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ የተራራ ስም ሲሆን ጌዴዮን ደፋር እና ፈሪ ወታደሩን የለየበት ቦታ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከሰሞኑ ኳታር ደሃ ላይ ሰንብተው ተመልሰዋል፡፡ ከዓመታቶች በፊት ኳታር ከኤርትራ ጋር ባላት ቅጥ ያጣ ግንኙነትና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ግንኙነቷን ከማቋረጧም በላይ የጐሪጥ መተያየት ደረጃ ላይ ደርሰው እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከሦስት ወር በፊት ራዕይ ስለማስቀጠል እና ራዕይ ስላለመበረዝ አበክረው ሲገልጹልን የነበረ ቢሆንም ቃላቸውን ጠብቀው ለመዝለቅ ሦስት ወር እንኳ ሳይሞላ መንታ መንገድ ላይ የቆሙ ይመስላል፡፡ የኳታሩ ጉዞ ምን ዓይነት ፖለቲካዉ ተግዳሮት አለው? እውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለአድን ተራራ መውጣት ጀምረው ይሆን? ከጉዞው በስተጀርባ ሀገራችን ምን ትጠ ብቃለች? እስኪ ትንሽ እንየው፡-

ራዕይ በማስቀጠልና በመበረዝ መሐል መበረዝና መደለዝ የሚሉ ቃላቶች እንደዛሬው የካድሬ

መዝገበ ቃላቶች ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ከጠጅና ከፈተና ወረቀት ያለፈ ጥቅም ላይ ለመዋል ዕድል አላገኙም ነበር፡፡ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትርን መለስ ተከትሎ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ‹የመለስን ራዕይ ሳይበረዝና ሳይደለዝ እናስፈጽማለን› ካሉ በኋላ እስከ ታችኛው የእዝ ሰንሰለት ድረስ ዓረፍተ ነገሩን በየቦታው መናገር ፋሸን ከመሆኑም የተነሳ እነዚህን ቃላቶች ሳያስገቡ አራት ነጥብ ላይ መድረስ እንዳልተቻለ በግልፅ እየታየ ይገኛል፡፡ መለስ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን በማደራጀት ሻእቢያን ለማጥፋት ሲሞክሩ እንጂ በኳታር ትከሻ ላይ ከሻእቢያ ጋር የመደራደር ራዕይ እንደነበራቸው ለመመስከር ምስክር ማስቆጠር አይጠበቅብኝም፡፡ እንግዲህ እዚያ ጋር አንደጥፋት ሊቆጠር ይችል የነበረው በነበረው ራእይ እቀጥላለሁ የሚል አስተሳሰብ ቢኖር ይመስለኛል፡፡ ዓለም በፈጣን የለውጥ ሂደት ውስጥ ሆና በትላንት ራዕይ ዛሬን አልፋለሁ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ በዚህ ወቅት እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ወ/ሮ አዜብም ከራእይ በራዦች መሐል አንዷ ቢሆኑ አይገርመኝም፡፡ ዓለምአቀፋዊ ፖለቲካ ለመተንበይ የማይቻለበት ሁኔታ ላይ ተደርሰዋል፡፡ ይመስለኛል የላይኛው አመራር በቀድሞ አመራር ዝግ የነበሩትን አንዳንድ ሁኔታዎች ለማስተካከል እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶሀ ጉዞ አንዱ ሊሆን ይችላል፤ የገባው መበረዝና መሰረዝ ያለበትን ሲሰርዝና ሲበርዝ በሽምደዳ ዕውቀት ላየ የታነፀው የወረዳና የቀበሌ ካድሬ ራዕይ ስላለመሰረዝና ስላለመደለዝ ይዶሰኩራል ምክንያቱም ይህ ፖለቲካ ነው፡፡

ዶሀ ምን ተገኘ? ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ኳታር የሁለትዮሽ ግንኙነቱን

በንግድ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዋ ዘርፎች ለመነጋገር ከኳታር

ባለሥልጣኖች ጋር ተገናኝተው ተወያዩ የምትለው ዜና ኢቲቪ ሳጥን ውስጥ ትቀመጥልንና አንኳር ጉዳይ የሆነው የኤርትራ ጉዳይ ላይ መወያየት ይሻላል፡፡ አሁን ባለንበት ጊዜ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሐል ማንኛውንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማድረግ ከኳታር የተሻለ አማራጭ ገበያው ላይ ማግኘት አይቻልም፡፡ እንደሚታወቀው ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት በኋላ ኢትዮጵያ የማሊያ ላውጥ በማድረግ በሯን ለድርድር የከፈተች ይመስላል፡፡ ይህን ሐሳቤን ከሚያጠናክሩልኝ

አንዱ በመለስ ጊዜ በኮብራ ሀዋሳና ባሕር ዳር ሲምነሽንሹ የነበሩት ኢትዮጵየ ውስጥ የሚገኙት የኤርትራ ተቃዋሚዎች በአሁን ወቅት ችላ ከመባላቸውም በላይ ባሕር ዳር ላይ ለተቃዋሚዎቹ ፕሮፓጋንዳ ይረዳ ዘንድ ሊቋቋም ታስቦ የነበረው የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ ለጊዜው ቆሟል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ በኳታር አማላጅነት ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማውረድ መፈለጓን ያሳብቅባታል፡፡

ኤርትራ ምን አለ? ከዐሥራ አምስት ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ጎትጓችነት

ለማድረግ የታሰበው ስምምነት ሦስት ነገሮችን ታስቦ የተገባበት ይመስለኛል፡፡

ሀ/ ዘላቂ ሰላም ኢትዮጵያና ኤርትራ ከሦስት ዓመት ደም አፍሳሽ ጦርነት

በኋላ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም በስተመጨረሻ ባደረጉት የገላጋይ ፍርድ ቤት ክርክር የጦርነቱ መንስኤ የሆኑት ውስጥ ዋነኛዋ የባድመ ቦታ ለኤርትራ በፍርድ ቤቱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ሆኖም መዘዙ ብዙ ዋጋ ስለሚያስከፍል እስከ ዛሬ ድረስ በቦታው

ላይ ሰላም ሳይወርድ ቆይቷል፤ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ግን ኢትዮጵያ የፍርድ ቤቱን ስምምነት ለመቀበል የተዘጋጀች የሚመስል መልእክት ከመንግስት ኮምኒኬሽን ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ በረከት ስምኦን ሰምተናል፡፡ አቶ በረከት ስምኦን ለኤርትራ ሬድዮ የፍርድ ቤቱን ፍርድ ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ከነገሩን አንድ ወር እንኳ አልሞላውም፡፡

መቼም ሰላም ማውረድ መልካም ሆኖ ሳለ ቁምነገሩ ግን የኤርትራን ጥያቄ አለማወቅ ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በእውነቱ

የኤርትራ ጥያቄ የመሬት ጥያቄ አይደለም፤ የኢኮኖሚና የበላይነት ጥያቄ እንጂ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባድሜን ለኤርትራ ሰጥቼ ሰላም አመጣለሁ ብሎ ካሰበ በእውነት ትክክለኛ ነጥቡን አላገኘውም ማለት ነው፡፡ አንድ እርግጠኛ የምሆነው ነገር ቢኖር ኤርትራ ወደዚህ ጨዋታ በምንም ዓይነት ሁኔታ እንደማትገባ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ጨዋታ ኢትዮጵያን እንደምታሸንፍ ታውቃለች፡፡ ኢሕአዴግ መሬት በመስጠት መጥፎ ታሪክ እንደሌለወ ገና ድሮ ገብቷታል፡፡ ሻእቢያ የኢትዮጵያን ጠላትነተ ለሁለት ከፍሎ ያየዋል፡፡ አንደኛውና ዋነኛው ጠላቴ የትግራይ ሹማምንት ብሎ ሲያስብ ቀሪውን የኢትዮጵያን ክፍል በሁለተኛነት ያስቀምጠዋል፡፡ ሻእቢያ ኤርትራን የአፍሪካ ሲንጋፖር አድርጋለሁ ብሎ ሲያስብ ግብአቶችንና (Input) የሰው ጉልበት (labor) በትግራይ እንደልቤ እያፈስኩኝ ያመረትኩትን እንደ ልቤ ትግራይ ላይና የተቀረው ኢትዮጵያ ላይ አየሸጥኩኝ ምናምን የሚል እቅድ ይዞ ወደ ሜደው የገባ ሲሆን ይህን ኢፍትሐዊ ንግድ ያስቀሩብኝ የትግራይ ሹማምንት ነው ብሎ ቂም ይዞ እንደነበርና የመጀመሪየውን የግፍ ፅዋ በትግራይ ውስጥ በሀይደር ትምህርት ቤት ላይ ያደረገው ግፍ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ፡፡ ሻእቢያ መቼም ቢሆን በተረጋጋችው ኢትዮጵያ ውስጥ የሲንጋፖር ሕልሙን ማሳካት አይቻለውም፡፡ ኤርትራ ሲንጋፖርን ለመሆን ኢትዮጵያ ሩዋንዳን በማድረግ ብቻ ነው ብሎ ገና ድሮ ደምድሟል፡፡ ስለዚህ በዚህ አመለካከት መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከዶሀ መልካም ነገርን ይዘው ተመልሰዋል ለማለት አይቻልም፡፡

ለ/ እሾህን በእሾህ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም የዶሀ ጉዞ ሁለተኛው

ምክንያት እንግዲህ ከኤርትራ ጋር በመስማማት የኢትዮጵያ ተቀዋሚዎችን ከጨዋታው በዜሮ ማስወጣት ይመሰለኛል፡፡ የእሾህን በእሾህ ጨዋታ በሀገራችን ከጥንት ጀምሮ ሲተገበር እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኢሕአፓን በመኢሶን፣ ሕወሓትን በኢዲዮ እንዲሉ…. ኢሳትን በኢቢኤስ… ተስፋዬ ገብረ አብን፣ በመስፍን ነጋሽ እንዲሉ… ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መጠናከራቸውና አስመራ ላይ መክተማቸውን የጠረጠረ ይመስላል፡፡ በእርግጥ ላለመስማማት ተማምለው የነበሩ ከሀገር ውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ከሌላ ጊዜ በተለየ ሁኔታ የመተባበር ሁኔታ እየታየባቸው ይገኛል፡፡ በኢትዮጰያ ውስጥ በትግል ታሪካችው አንጋፋ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሆነው ኦነግ አንኳነ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ከሴማውያን ጋር ለመስራት በሩን ክፍት ማድረጉ ለኢሕአዴግ ቁጣዩ ፈተና ምን እንደሚሆን ከወዲሁ ለመተንበይ አያስቸግርም፡፡ በዚህም ነጥብ ላይ ሻእቢያ ለድርድር በሩን አስካልከፈተ ድረስ የዶሀው ጉዞ ከወዲሁ በስኬት እንደማይጠናቀቅ (ኤርትራ... ወደ ገጽ 20 ዞሯል)

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Page 5: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ ታሪክ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጋር ከወገነ፤ አሜሪካስ

ለምን አትወግንም ? ፕሬዜዳንት ኦባማ አክራ፤ ጋናን በ2009 ሲጎበኙ ሁለት

አስቸኳይና አስፈላጊ መልዕክቶችን አስተላልፈው ነበር፡፡

‹‹ታሪክ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጋር ወግኗል›› ሲሉ: ለአፍሪካ መሪዎችና ገዢዎች ደግሞ ጠበቅ ያለ መልክት ኣስተላፈው ነበር፡፡

እንዳትሳሳቱ፡ ታሪክ ወገናዊነቱ ከጀግኖቹ አፍሪካውያን ጋር እንጂ በሥላጣን ላይ እራሳቸውን እንዳነገሱ ለማቆየት መፈንቅለ መንግሥት ከሚያካሂዱ ጋር አለያም ሕገ መንግሥታቸውን እንዳሻቸው ከሚለዋውጡት ጋር አይደለም፡፡ አፍሪካ የሚያስፈልጓት ጡንቻቸው የፈረጠሙ መሪዎች ሳይሆን የዳበሩ ተቋሞች እንጂ ... የሕዝቦቻቸውን ፈቃድ ከማያከብሩት እጅጉን በበለጠ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ መንግሥታት የከፍተኛ ሃብታም፤ በጣም የተረጋጉ እና የበለጠ የተዋጣላቸው ይሆናሉ… የልማት መሰረቱ መልካም አስተዳደር ነው፡፡ በበርካታ ቦታዎች እጅጉን ለረዘመ ብዙ ጊዜ ጎድሎ የነበረው ቅመም ይህ ነው፡፡ ይህ ነው የአፍሪካን እምቅ ችሎታ ሊያወጣው የሚችለው፡፡ ይህም ሃላፊነት በአፍሪካውያን ብቻ ነው ግቡን ሊመታ የሚችለው፡: ለአፍሪካውያን ህዝቦች የላኩት መልእክት አነሳሽ ተስፋ ሰጪ፤አደፋፋሪ ነበር፡፡

መሪዎቻችሁን በተጠያቂነት ለመያዝና ለሕዝቡ አስፈላጊውን ግልጋሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለመገንባት ስልጣኑ አላችሁ፡፡ በመንደራችሁ አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ፤ አቅማችሁንና እውቀታችሁን አዲስ ሃብት መፍጠሪያ፤ ከሌላው ዓለም ጋር መገናኛም ልታደርጉት ትችላላችሁ:: ከመሰረቱ አንስታችሁ የእርስ በርስ ግጭትን፤ በሽታን በማጥፋት ለውጥ ማምጣት ችላላችሁ፡፡ ያንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ አዎን ይቻላል! ምክንያቱም በዚህ ሰአት ታሪክ በመገስገስ ላይ ነውና፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ በተጨማሪም የተከበረና የረጋ ቃል ለአፍሪካ ህዝቦች ገቡ፡

አሜሪካ በማንም ሕዝብ ላይ ምንኛውንም አይነት የመንግስት ስርአት ለመጫን ፍላጎት የላትም፡፡… ማድረግ የምንፈልገው፤ ትኩረታችንን በመልካም አስተዳደር ላይ፤ የስልጣንጣን መባለግን በሚቆጣጠር እና ተቃዋሚ ሃይላት ድምጻቸው እንዲሰማ በሚያደርግ፤ የሕግ የበላይነት ለሚያስከብር፤ የፍትሕ ስርአቱን አስተዳደር በእኩል መብት በሚያካፍል፤ የሕዝባዊ ማሕበራት ተሳትፎን በሚያረጋግጥ ፓርላማ ላይ፤ ወጣቱ ትውልድ በስፋት የሚሳተፍበትን በሙስና ላይ ግልጽ አቋም የሚይዝ፤ ከሕጉ ጋር የተያያዘ ቁጥጥር፤ አግልግሎቶችን በማፋጠን፤ ሃላፊነት ለሚሰማቸው ግለሰቦችና ተቋማት፤ ተጠያቂነትንና ግልጽነትን ለሚያረጋግጡ ሁሉ ድጋፋችንን መጨመር ነው እቅዳችን፡፡

አሁን ግልጽ በሆነው የፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ላለፉት ጥቂት ዓመታት ያስተላለፍናቸውን አንዳንድ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ማንሳት ይኖርብናል፡፡ ከ2009 ይልቅ በ2012 በአፍሪካ የበዙ ባለ ጡንቻ መሪዎች አሉ? በየጎዳናውና በየወህኒ ቤቱ ጠንካራ የአፍሪካ ልጆች በ2009 ከነበረው በ2012 ያሉት ኣይበልጡም? አፍሪካ በ2009

ከነበሯት ደካማ ተቋማት አሁን ያሉት ይበዛሉ? በ2009 ከነበሩት የሕዝባቸውን ፍቃድና ፍላጎት የሚያሟላ የአፍሪካ መሪዎች የበለጡ አሁን አሉ? በአፍሪካ በ2009 ከነበረው የእርስ በርስ ግጭት አሁን ያለው ያንሳል? አሁን አፍሪካ መልካም አስተዳደር አላት? በርካታ የተቃዋሚዎች ድምጽ ይሰማል? ሕዝባዊ ተሳትፎስ በርክቷል? የወጣቱስ ተሳትፎ በ2009 ከነበረው አሁን ተሸሏል? የታሪክስ ሂደት ወደ ዴሞክራሲ፤ወደ ነጻነት፤ ሰብአዊ ምብት፤በመራመድ ላይ ነው? ወይስ አፍሪካ የኋሊት ፈላጭ ቆራጭነት ወደ ነገሰበት የጭለማው ዘመን፤ ወደ ማን አለብኝነትና የጭቆና አገዛዝ፤ አምባገነናዊ አስተዳደር እየተጓዘች ነው?

አሜሪካ ዛሬ ከጠንካራ አፍሪካውያን ጋር በጥንካሬ ቆማለች ወይስ ከነዚያ አምባገነን ገዢዎች ጋር ተቃቅፋ ኣልጋ ላይ ተጋድማለች?

ፕሬዜዳንት ኦባማ ሲያነሳሱዋቸው የነበሩት የአፍሪካ ጀግና ልጆችስ የት ገቡ?

እንደ አሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት የሰብአዊ መብት ትግበራ የ2011 (ሜይ 2012) ዘገባ እነዚያ ፕሬዜዳንት ኦባማ

ያሏቸው በርካታ ‹‹ጠንካራ አፍሪካውያን›› አሁን በወህኒ ቤት፤ በመከራ መቀበል፤ በስቃይ በመገረፍ፤ በመለጎም፤ በሽሽት ላይ፤ በሞት በመቀጠፍ፤ አለያም በስጋት ማቅ ተሸፍነው፤ ወከባውን በመሸሽ፤ በዘፈቀደ በየቦታው መያዝን፤ ከፍርድ በፊት በወህኒ መማቀቅን፤ስቃይን፤ ዱላን፤ ኢሰብአዊ መከራን፤ለሕይወት አስጊ የሆነውን እስራት፤ በንግግ ር ነጻነት መገደብን፤ የፕሬስ ነጻነትን ማጣት፤ ሕገ ወጥ ብርበራን፤ ይህና ሌሎችም መሰል ስቃዮች ናቸው የአፍሪካውያን የእለት ተእለት ሕይወት፡፡ የአፍሪካ ማሕበረሰብና ተቋማት በምግባረ ብልሹ ባለስልጣናት፤ በሙስና፤ ግልጽነት በመጥፋቱ፤በማያስፈልግና ወደኋላ ጎታች፤በሆነ ቢሮክራሲ ማነቆ ተይዘው፤ ማንኛውም ጉዳይ በገዢዎቹ መዋቅር ውስጥ ባሉትና ትዕዛዝ ተቀብለው

በሚተነፍሱ፤ በፖለቲካ ቁጥጥር ስር በሆኑ የፍትህ መዋቅሮች፤የተባሉትን ብቻ እሺ በሚሉና በራሳቸው ህሊና በማይገዙና በማይመሩ የፓርላማ አባላት ተከበው በጭለማ ውስጥ በመዳከር ላይ ናቸው፡፡ የአፍሪካውያን ማሕበረሰብ በሚያለያይ በሽታ ተከትበው፤በዘር፤ በነገድ፤ በጎሳ፤ በመንደር፤በጾታ፤ በቋንቋ፤በሃይማኖት፤በባህል፤በወረዳ ተለያይተው ነው ያሉት፡፡

የሰብአዊ መብትን ከሚደፍሩ ሃገራት ሁሉ ድፍረቱ በእጅጉ የበዛባት ሃገር ኢትዮጵያ ነች፡፡ በሜይ 2010 ገዢው ፓርቲ በፓርላማ ካሉት 547 ወንበሮች 545ቱን (99.6%)

መቀመጫዎችን ‹‹አሸነፈ››:: በዚያ የምርጫ ወቅት የሁዋይት

ሀውስ መግለጫ ያሳየው ጉዳዩ ‹‹አሳሳቢ›› የሚል ነበር:- ፍትሃዊና ነጻ ምርጫን ለማካሄድ ሁኔታው ከምርጫው ቀናት አስቀድሞም የተመቻቸና ትክክል አልነበረም፡፡ በቅርብ ዓመታት የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የፖለቲካወን ምህዳር በማጥበብ የተቃዋሚዎችን አካሄድም ለመስንከል በማስፈራራትና በማዋከብ፤የራሱን ሜዳ እያሰፋ በማመቻቸት የሲቪክ ማሕበረሰቡን በማግለል፤የነጻ መገናኛ ብዙሃንንም ተግባራቸውንና ክዋኔያቸውን በመቀነጣጠስና በማገድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ ሃሳብን በነጻ የመግለጽን ሂደት በእጅጉ የሚገድቡ ሲሆኑ ገዢው መንግስት እራሱ ከተቀበለውና ከፈረመው የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር ጨርሶ የሚጻረርና ተለዋዋጭ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ‹‹ያሳስባል›› ከሚል በጨዋነት ከተሰነዘረው የበለጠ ግንዛቤ የሚያስፈልገው ነው፡፡ድርጊቱ ቁጣን ሊያጭር ከድርገቱ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር የሚዛመድ እንዲሆን ግፊት ያስፈልገዋል፡፡ በቅርቡ በወጣው ኢትዮጵያን

የሚመለከተው የዩ ኤስ ስቴት ዲፓርትመንት የሰብአዊ መብት

ዘገባ (ሜይ 2012) ‹‹ ከ100 የሚበልጡ የፖለቲካ ሰዎች፤ጋዜጠኞች፤እና የድረገጽ ተሳታፊዎች (በዓለም አቀፍ በተወገዘው የጸረሽብርተኝነት ሕግ) መንግስት የፕሬስን ነጻነት ገደበ፤የመያዝና የመጠቃት ፍርሃት ጋዜጠኞች እራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ አስገድዷቸዋል፡፡ የእርዳታና የሰብአዊ ግልጋሎት

ሰጪዎች (CSO law) አሁንም የጠነከረ እገዳ በማድረግ የማሕበረሰቡና የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እንቅስቃሴዎች ከመዳከም ወደ መቆም እየተጓዙ ነው፡፡በጣም አሳሳቢ የሚባሉት የሰብአዊ መብት ችግሮች፤ ድብደባን በደህንነት ሰዎች መሰቃየትን፤ወህኒ ማጎርን፤በጣም የተበላሸ የወህኒ ሁኔታን፤ የሴቶችን ሕብረተሰባዊ ልዩነትን፤…… በጁንና ሴፕቴምበር (2011) የተካሄደው ሁለተኛው ዙር አፈናና እስር፤በርካታ ስመጥር ጋዜጠኞችን፤የፖለቲካ ተቃዋሚ አባላትን፤ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎችን፤አንዱዓለም አራጌን የአንድነትለፍትሕና ለዴሞክራሲና የመድረክን ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ጭምር፤ታዋቂውን የድረገጽ ጸሃፊና ተሟጋች እስክንድር ነጋ፤ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ አባልን ናትናኤል መኮንንን ያካተተ ነው።

ካረን ጄ ሃንራሃን የዴሞክራሲ ቢሮ፤ የሰብአዊ መብትና የሌበር ዲፒዩቲ ምክትል ጸሃፊ ለብሔራዊ አንዳውመንት በኦክቶበር 2012 ባደረጉት ንግግር

….በኢትዮጵያ ግብግብ ገጥሞናል፡፡ መሰረታዊው ጥየቄም ገዢው መንግስት በፖለቲካና ማሕበረሰቡ ተቋማት ላይ ጫናውን ሲያበዛና ገደቡ ልክ ሲያጣ፤ዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብትን በአግባቡ ማራመድ የሚቻለው እንዴት ተብሎ ነው፡፡ ይህም በሲቪል ማሕበረሱ ላይ የሚደረግ ጫና፤የሜዲያዎች ነጻነት ማጣት፤በጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ሰበብ ጋዜጠኞችን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አፈናና ማሳደድ፤ለአእስር መዳርግ የሚያካትት ነው፡፡ ወደፊት መራመዱ ለመንግስትም ቢሆን የተቃዋሚዎችንና የሲቪል ሕ በ ረ ሰ ቡ ን እ ድ ገ ት የ ሚ ያ ስ ከ ት ል ይሆናል፡፡ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መብቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ማስቻል ብቻ ሳይሆን የአሜሪካንና የኢትዮጵያ መንግስታት ሁለቱም የመረጋጋትና የልማት እድገትና ዋስትና ያገኛሉ፡፡

የአሜሪካን መሪዎች ምናልባትም ቀደም ሲሉ በቦታው ከነበሩትና ከፈላጭ ቆራጭና አምባገነኖች ተመሳሳይ ጥሪ የአሁኖቹ የአሜሪካ መሪዎች ሊማሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ አንድ

ወቅት ላይ ፕሬዜዳንት ትሩማን እንዳሉት፡‹‹ የተቃዋሚውን የመናገር ነጻነት ለማፈን የቆረጠ መንግስት የጉዞው አቅጣጫ አንድ ብቻ ነው፤ተደራራቢ ወደ ሆነና ለሁሉም ዜጎች የሽብርና ሁሉም በፍርሃት የሚኖርበት አካባቢ እንዲሆን በማድረግ

አምቆ የመግዛት ስርአት፤›› ይህ ነው በኢትዮጵያ ያለው

የማያከራክርና የማይካድ ሕይወትና ‹‹ጥሪ›› ‹‹አሳሳቢ›› የሚሉ ባዶ ቃላት አንዳችም ፋይዳ ሊናራቸው ሁኔታዎችን ሊቀይሩና የዜጎችን ሕይወት ሊለውጡ አይችሉም!

ዛሬ በአፍሪካ ያለው ያሜሪካ መምሪያ ብዙ ጉድለቶች ኣሉት

በዩ ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ጆኒ ካርሰን አባባል በአፍሪካ ውስጥ ሊያገለግሉ

የሚችሉ ‹‹አምስት የአሜሪካንን ፍላጎት የሚያሟሉ ምሶዎች

አሉ›› ይህም የሚያካትተው፤ (አሜሪካ... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

Page 6: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

(ክንፉ አሰፋ) ጃማይካዊውን የጥበብ ሰው ጋሪሰን ሃውክን በመንተራስ አርቲስት ጂጂ እና ቴዲ

አፍሮ ሰሞኑን የለቀቁት 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'´ ነጠላ ዜማ በብዙዎች አድናቆትን እየተቻረ ይገኛል። ብዙዎችንም አነቀቅቷል። ሙዚቃው የተለየ ነ ው ፣ የ ሚ ያ በ ረ ታ ታ እ ና የሚያነቃቃም ነው።

'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!

ብዙውን ግዜ በጦር ጀብዱ የፈጸመን ወይንም ድል ያደረገን ሰው ጅግና ብለን እንጠራዋለን። ጀግንነትን በዚህ መስፈርት ብቻ ከለካነው - ይህ ቀላሉ ጀግንነት ሊሆን ይችላል። ከባዱ እና እውነተኛው ጀግንነት ግን ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን ማሸነፍ መቻል ነው።

ምንም አይነት ጅብዱ ቢፈጽም ራእይ ግን የሌለው ሰው ጀግና ሊሆን አይችልም። ህይወት ካለ ተስፋ አለ። ተስፋ ካለ ህልም አለ። ህልም ካለ ራዕይ አለ። ራእይ ያለው ሰው ነው ጀግና። 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!

የኢትዮጵያ አርቲስቶች በተለያዩ ወቅቶች ከፍቅር ወጣ ያሉ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ሲጫወቱ አስተውለናል። በአብዮት ዘመን፣ በጦርነት ዘመን፣ በድል ዘመን፣ ወዘተ ... አብዛኞቹ ዘፈኖችም ሆኑ ቀረርቶዎች ታዲያ ፈረንጆቹ ኢንስፓሬሽናል እንደሚሉት መንፈስን የሚያነቃቁና የጀግነነት ሞራልን ከፍ የሚያደርጉ አልነበሩም።

አንቱ የሚባሉ የሃገራችን አርቲስቶች ካቀነቀኗቸው የፍቅር ዜማዎች አንዳንዶቹ የሚደንቁ ናቸው።

ቆዳዬ ተገፎ ይሁንልሽ ጫማ፣ ስጋየም ይደገም ላንቺ ከተስማማ.. ፍየል ቅጠል እንጂ አትበላም እንጉዳይ፣ በጥርሷ ሰላሳ ባይኗ መቶ ገዳይ... አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ እስቲ ቁጥር ጥሩ፣ እኔ ልጣራ ነው እናንተ ሞክሩ የሚሉ ስንኞችን እናያለን:: አርቲስቶቹ ከፍቅር ወጣ ሲሉ ደግሞ፣ ይለያል ዘንደሮ...ይለያል! አባረህ በለው... ፍለጠው ቁረጠው.. አያ ሆሆ ማታነው ድሌ .. ደም በደም ይሁን መረማመጃው! ወዘተ የመሳሰሉትን ስራዎቻቸውን መጥቀስ

ይቻላል። በርግጥ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገሮች የድምጽ ተሰጥኦ ብቻውን የአንድ ጥበብ

ሰው መመዘኛ ተደርጎ ስለሚወሰድ መልዕክቶቹ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚያዳምጥና የሚተች እምብዛም አይኖርም። ችግሩ ያለው የአርቲስቶቹ የአካዳሚ እውቀት እና የግጥም ስራ ችሎታ ማነስ ላይ ነው።

በአርቲስቶቹ ላይ በሚደረጉ ተጽእኖዎች እና አንባገነን መሪዎች አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩባቸው አሊያም የአርቲስቶቹ መሃል ሰፋሪነት ባህርይ ለችግሮቹ ምክንያቶች ሆነው ሊጠቀሱ ይታያል።

እንደነዚህ አይነት ዘፈኖችና ቅኝቶች የሰውን ስሜት በጊዜው እና ለጊዜው ሊቀሰቅሱ ቢችሉም ዘለቄታ አልነበራቸውም። ግዚያዊ ሆነው አልፈዋል።

የሬጌ ሙዚቃ ዘውግ ብዙውን ጊዜ የሚያጠነጥነው ተስፋን በሚሰጥ፣ መንፈስን በሚያበረታታና የጀግንነት ሞራልን በሚጭር የዜማ መልእክቶች ላይ ነው:: የሬጌ እና የአር. አንድ ቢ. ዘውግ በማቀላቀል የሚያቀነቅነው አርቲስቶቹ ጋሪሰን ሃውክም ሰለ ተስፋ ብዙ አዚሟል። አርቲስት ጂጂ እና ቴዲ ተንተርሰው ያዜሙትም 'ሰርቫይቭ'’ በተሰኘው የጋሪሰን አልበም ነው - የመኖርን እና የመቆየትን ተስፋ የሚያጭር የጋሪሰን የሙዚቃ ስራ።

ጂጂ እና ቴዲ ውብ የአማርኛ ግጥም ጨምረውበት ለሙዚቃው ሌላ ኢትዮጵያዊ ነብስ ዘሩለት። (ቴዲና ጂጂ... ወደ ገጽ 18 የዞረ)

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

(ኤፍሬም እሸቴ ከሜሪላንድ - adebabay.com)

የተረጋጋ ባሕር። ማዕበል የሌለበት። እንዋኝህ ቢሉበት፣ በጀልባ ቢንሸራሸሩበት፣ አሣ ቢያሰግሩበት፣ ቢዝናኑበት … የሚመች …። እንደ ስምጥ ሸለቆ ኃይቆቻችን ያለ … የሰፋ፣ የሰከነ፣ የተረጋጋ፣ የተንጣለለ ውኃ። የረጋ ሕይወት፣ የተረጋጋ ማኅበረሰብ እንደዚያ ነው። …

በጥንታውያን ገዳማውያን አበው ታሪክ ከተጻፉ ታዋቂ ምሳሌዎች አንዱ በረጋ ውኃ ተመስሎ ይነገራል። ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ አንዱ ወጣኒ ገዳማዊ (ጀማሪና ተማሪ የገዳም ሰው) ምክር ፍለጋ ወደ አንዱ አረጋዊ አባት ዘንድ ሄደ። የተማሪው ጥያቄ “ውስጤ ተረጋግቶ በገዳም መኖር የምችለው፣ በጎውንና ክፉውን መለየት የምችለው እንዴት ነው?” የሚል ነበር። አረጋዊው መምህር መልሱን በተግባር ሊያሳዩት ፈለጉ። እናም ውኃ የተቀመጠበት ሰፊ ሳፋ መሳይ ነገር አቅርበው ራሱን ውኃው ውስጥ እንዲመለከት አዘዙት። ነገር ግን ሳፋውን በእጃቸው እየናጡ ውኃውን ያነቃንቁት ነበር። ጀማሪው ገዳማዊ በጠራው ውኃ ውስጥ የተሰባበረ የራሱን ፊት ተመለከተ።

ቀጥሎም የሳፋውን ውኃ እንዲረጋ ካደረጉ በኋላ ራሱን እንዲመለከት አደረጉት። አሁን ግን ኩልል ባለው ውኃ ውስጥ የጠራ የራሱን ፊትና ገጽ ተመለከተ። ጥያቄውንም በዚሁ መልስ ሰጡት። ጥርት ያለ ሐሳብ እንዲኖርህ ብትሻ ውስጥህን መጀመሪያ አረጋጋ፤ ከሁካታ፣ ከቱማታው ተለይተህ ለራስህ ጸጥታን አስለምድ። ከዚያ የራስህን ማንነትና ስህተትህንም አጥርተህ መመልከት ይቻልኻል። ንውጽውጽታ በበዛበት ኅሊና የጠራ ሐሳብ ማግኘት አይቻልም። እንዴት ተደርጎ?

አንድ ግለሰብ በውሳጣዊ ማንነቱ በሚነሣ ሐሳብ ምክንያት አጥርቶ ማየት፣ አስተውሎ መጓዝ፣ ሰክኖ መኖር እንደሚሣነው ሁሉ አንድ ማኅበረሰብም በውሳጣዊ ሁኔታው ምክንያት አጥርቶ ማየት፣ አስተውሎ መጓዝ፣ ሰክኖ መኖር ሊሳነው ይችላል። ከራሱ ያልታረቀ ሰው ራሱን ጎድቶ ለሌላው እንደማይረባው ሁሉ ማኅበረሰብም ጤናማነቱ ካልተጠበቀ “ከመ እንስሳ” ከመኖር ያለፈ ፋይዳ ላይኖረው ይችላል።

ባደጉትና ባላደግነው አገሮች መካከል ያለው አንደኛው ልዩነት ይህ ይመስለኛል። የተረጋጋ ማኅበረሰብ “ለነገ”፣ ለመጪው ትውልድ ብሎ ማሰብ ይችላል። ከአንድ ወር በኋላ የምትደርሰውን ጎመን ብቻ ሳይሆን ከዓመታት በኋላ የሚያፈራውንም ተክል ይተክላል። ዛሬ እንብላ እንጠጣ፣ ነገ ለምታልፍ ዓለም፣ ነገ ለምንሞተው (“ንብላዕ ወንስተይ ጌሰመ ንመውት”) ብቻ ሳይሆን ለነገ፣ ለከነገ ወዲያ፣ ለጡረታ ዘመኔ፣ ለልጅ ልጆቼ ቅርስ የሚል ውሎ የሚያድር ሐሳብ ያመነጫል።

ለሀብት-ለሀብት ከሆነ ወርቅ ተንተርሰው፣ አልማዝ ላይ ተቀምጠው፣ ድፍድፍ ነዳጅ ከጓሯቸው ተቀብሮ የሚኖሩ ብዙ አገሮች አሉ። ከኮንጎ እስከ ሴራሊዮን፣ ከሶማሊያ እስከ ካሜሩን ችግሩ የተፈጥሮ ሀብት አይደለም። በየዕለቱ ቦንብ እንደ እንጉዳይ የሚፈላባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ቢያንስ በነዳጅ ሀብት አይታሙም። በከርሰ ምድር ሀብት ይህ ቀረሽ የማትባለው ሩሲያ፣ የአፍሪካ ትልቋ ናይጄሪያ ወይም ደቡብ ሱዳን ገንዘብ ሊቸግራቸው የሚችሉ አገሮች አይደሉም። ነገር ግን የተነዋወጹ ባሕሮች፣ ያልተረጋጉ ሕዝቦች፣ ባለህበት እርግጥ ከማለት ያለፈ ሊዘልቁ የማይችሉ አገሮች መሆናቸው ነው። የማዕበሉ ንውጽውጽታ በምን ይርጋ?

በየትኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ ለዚያ አገር ሕዝብ ሰላማዊ አንድነት በጎ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ብዙ አካላት አሉ። ከነዚህም መካከል ሃይማኖታዊ እና ማኅበረሰባዊ ተቋማት (ሲቪክ ተቋማት) ዋነኞቹ ናቸው። መንግሥታት በፖሊስና በወታደር ኃይሎቻቸው ከሚያመጡት ሰላምና መረጋጋት ይልቅ ሃይማኖታዊና ሲቪክ ተቋማት የሚያሰፍኑት ሰላም የተሻለ፣ ተዓማኒና ዘላቂ ነው። ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ጥንታዊ አገሮች ከመንግሥት መዋቅሮች ይልቅ እነዚህ ሃይማኖታዊና ማኅበረሰባዊ ተቋማት የተሻለ ተደራሽነትና ታማኝነት ነበራቸው። ይህ ተደራሽነት በበጎ ጎኑ ብዙ አዎንታዊ ፋይዳዎችን ሊያበረክት የሚችል የጤናማ ማኅበረሰብ ጥሩ ሀብት ነው። በዚህ መሠረት ላይ ማነጽ ከተቻለ በዳበረ ባህላዊ ሀብቱ የሚኮራና ራሱን የቻለ ኅብረሰተብ መፍጠር ይቻላል። የሕዝብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ማንነቱ መነካት የሌለበት አንድም ለዚህ ነው። መብቱም ነው። የማንነቱ መገለጫ።

“ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ” እንደሚባለው “በአገርህ ያለውን የሃይማኖታዊና ሲቪክ ተቋሞች አያያዝ ንገረኝና የአገርህን ሁኔታ ልንገርህ” ማለት ይቻላል። እነዚህ ተቋማት በነጻነት፣ በስፋት እና ሁሉን ባገናዘበ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ማኅበረሰቡ ከመንግሥት ሊያገኛቸው የማይችላቸውን ዘርፈ ብዙ ጥቆሞች ሊሰጡት ይችላሉ። ኅብረተሰቡም የሰከነ ኑሮ ይኖራል። ተቋማቱ ነጻነት ከሌላቸውና ማነቆ የሚበዛባቸው ከሆኑ ደግሞ የዚያ ሕዝብ የአንድነቱ አያያዥ ባህላዊ ገመድ ዕለት ወደ ዕለት እየሳሳና እየተበጠሰ ይሄዳል። ውሎ አድሮ በብዙ ገንዘብ ሊገኝ የማይችል አገራዊ ሀብት ይከስማል። በተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል፣ በድንበርተኞች መካከል፣ የሚታየው አለመግባባትና ጦር መማዘዝ እየሰፋ ከመሔዱም በላይ የአገር አንድነት የሚባለው ትልቅ ቁም ነገር ጥያቄ ላይ ይወድቃል።

በዚህ ረገድ ካየነው ኢትዮጵያውያን የእምነት ተቋማትና ሲቪክ ተቋማት በዘመናችን እንደሚገባቸውና እንደሚጠበቅባቸው የተረጋጉ እንዳልሆኑ እንመለከታለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት አሥርት የዘለቀ አስተዳደራዊ ቀውስ ውስጥ ስትዳክር ቆይታለች። በእስልምና እምነት ውስጥም እንዲሁ የዘለቀ ችግር ቢኖርም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተነሣው ነውጥ ብዙዎችን ለእስር ዳርጓል፣ የእምነቱ ተከታዮችም በየአርቡ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። በሲቪክ ተቋማት በኩል ይህ ነው የሚባል በነጻነት የሚንቀሳቀስ አገራዊ ተቋም አለ ማለት ያስቸግራል። ነጻ ሚዲያው ከዓመት ዓመት እየተዳከመና እየመነመነ ብልጭ ድርግም ማለት ይዟል። ጋዜጠኞችን በእስር በማጎር ትልቅ “ዝና” ካላቸው የዓለም አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ወዘተ ወዘተ

በሃይማኖቱ በኩል የጠቀስነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በአብነት ስንመለከት በውስጥ ያለው መከፋፈል ሥር ከመስደዱ የተነሣ ሁለት “ሲኖዶስ” እስከማቋቋም መደረሱ ይታወቃል። ይኸው ችግር ይፈታ ዘንድ

ለረዥም ጊዜ የተደረጉ ሙከራዎች ፍሬ ሳያፈሩ ቆይተው አሁን ግን የተሰነጠቀውን ለመጠገን ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ታይቷል። ከኅዳር 26-30/2005 ዓ.ም ድረስ በዳላስ ቴክሳስ በተደረገ የዕርቅና የሰላም ጉባዔ ለ20 ዓመታት ላለመተያየት ሲገዘቱና ሲገዛዘቱ የነበሩ አባቶች ፊት ለፊት ተገናኝተው ተወያይተዋል። አብረውም ጸልየዋል። በዳላስ በጉባኤው የተገኘው ሕዝብም ደስታውን በይፋ ሲገልጽ ሰንብቷል። በዚህ ጉባዔ ላይ ተወያዮቹ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ቢነጋገሩም ዋነኛ የሆነው ጉዳይ ግን በስደት የሚገኙት የአራተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ነበር። የጋራ መግለጫቸው ላይ እንደተጠቀሰው የቀድሞው ፓትርያርክ ወደ አገራቸው ስለሚመለሱበት

ሁኔታ የሚያስማማ ሐሳብ ላይ መድረስ አልቻሉም። ከአገር ቤት የመጡት ልዑካን “ሙሉ ክብራቸውና ጥቅማጥቅማቸው እንደተሟላላቸው በሚፈልጉት ቦታ ይቀመጡ” ሲሉ በውጪ አገር የሚገኙት አባቶች ደግሞ “ወደ መንበረ ፕትርክናቸው ተመልሰው እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው በፓትርያርክነት ይምሩ” የሚል ሐሳብ አቅርበዋል።

ነገሩ በዚሁ ሳይቋጭና ሳይወሰንበት ቢቆይም የሐሳብ ልዩነቱ እንደከዚህ በፊቱ ተጣልተው እንዲለያዩ አላደረጋቸውም። “ፈግጠው - ፈግጪው” አለመባባላቸው ብቻ ሳይሆን ለየምልዓተ ጉባዔዎቻቸው አቅርበው ውሳኔ ለመጠየቅና በድጋሚ ከአንድ ወር በኋላ በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ለመገናኘት ወስነዋል። በብዙዎች አንድምታም “ተስፋ ሰጪ” ጉባዔ እንደነበር ተወስቷል። በሁለቱም በኩል ያሉት “ምልዓተ ጉባዔዎች” ውይይቱ በቀና መልኩ እንዲቀጥል ማድረግ ከቻሉ የዘመናችንን አንድ ወሳኝ የልዩነት በር ይዘጋሉ ማለት ነው።

ይህንን የሰላም ውይይት በድጋሚ ማንሣት ያስፈለገው ጉዳዩ ከሃይማኖታዊ አጀንዳነትም የዘለቀ ብዙ አገራዊ አንድምታ ስላለው ነው። ከፍ ብለን እንደጠቀስነው ቤተ ክርስቲያኒቱ የአገሪቱን አንድነት ከሚጠብቁ ዋልታዎች አንዷ ናት። መዳከሟና ማኅበረሰባዊ ፋይዳዋ መቀነሱ የሚጎዳው የእምነቱን ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንና በጎ ኅሊና ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ነው። ከዚህ አንጻር የእምነቱ ተከታይም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ጉዳይ ከቁምነገር ሊጥፈውና ሊከታተለው ይገባል። የእምነቱ ተከታይ ምእመንም ነገሩን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለተቀመጡ ጥቂት የእምነቱ መሪዎች ብቻ መተው አይገባም። እንደ መሪነታቸው የሚሉትን መስማትና መከተል ቢገባም አንድነትን የሚያክል ቁምነገር መፈጸም ሲያቅታቸው ግን ምእመኑ መጠየቅ ይኖርበታል።

“እንትንን በእንትን ላይ ማነሣሣት” ካልተባለብኝ በስተቀር በሰሜን አሜሪካ ባሉ ካህናትና ምእመናን በኩል ያለው “አንድ የመሆን” ፍላጎት በአገር ቤት ባሉት አባቶችና ምእመናን ዘንድም እንዲንጸባረቅ ይጠበቃል። (ብፁዓን... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

It's a Great Time to BUY a

Home in Minnesota!

"There hasn't been a better

time to BUY in Years..."

Mortgage rates are at an all

time low! Sellers are motivated = Affordble Prices!

Mulugeta Mikael Big Real Estate 1561 Selby Ave

St.Paul, MN

www.bigrealtymn.com

[email protected]

Cell (612) 600-4823

Fax( 651) 967-0484

Real Estate Is Still One of the Best Investments You Can Make

If you are buying or selling a home in the in the Twin city Metro and need agent to help you make the experi-

ence less stressful and more exciting then, Mulugeta Mikael is the right agent for you.

Owning a home is a great investment in your fu-

ture and can lead to many, many years of

happiness.

So why wait? It's a Great Time to BUY!

Call Mulugeta today! @

612-600-4823

ነገሩ በዚሁ ሳይቋጭና ሳይወሰንበት ቢቆይም የሐሳብ ልዩነቱ እንደከዚህ በፊቱ ተጣልተው እንዲለያዩ አላደረጋቸውም። “ፈግጠው - ፈግጪው” አለመባባላቸው ብቻ ሳይሆን ለየምልዓተ ጉባዔዎቻቸው አቅርበው ውሳኔ ለመጠየቅና በድጋሚ

ከአንድ ወር በኋላ በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ለመገናኘት ወስነዋል።

በብዙዎች አንድምታም “ተስፋ ሰጪ” ጉባዔ እንደነበር ተወስቷል።

በዚህ በአዲሱ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በተለያዩ አገሮች የተበተንን ከተለያዩ ነገድና ቋንቋ የሆንን ሁላችን በያለንበት ሥፍራ እጆቻችንን ወደ ፈጣሪአችን እግዚአብሄር እንድንዘረጋ

አበረታታችኋለሁ።

እግዚአብሄር ከአገራችን ያወጣን ምድራችንን በመወከል ለፍጥረት ሁሉ ፈጣሪአችንን እንድንለምን አቅዶ ከሆነ በምን እናውቃለን??

“ደግሞስ ወደ መንግስት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደሆነ ማን ያውቃል?? መጽሐፈ አስቴር 4:10

መዝሙረ ዳዊት 68:31

አዲሱ ዘመን (2013/2005) ይቅር የምንባባልበት የምንቻቻልበት፤ አንዱ አንዱን የሚደግፍበትና የሚያበረታታበት ዘመን ይሁንልን

Team Serve & Every Tribe & Tongue Church

Pastor Jim Destaye Crawford P.O. Box 18482

Minneapolis MN 55418

[email protected]

ዘወትር አርብ ከምሽቱ 6 ሰዓት ጀምሮ፤ እንዲሁም ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 4:30 ጀምሮ መካፈል ትችላላችሁ

Page 7: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

ከዳንኤል ክብረት Danielkibret.com

ሁለት ተማሪዎች አንድ የቤት ሥራ ተሰጣቸው፡፡ የቤት ሥራው የተማሪዎችን ችሎታ ለመፈተን

በከተማ ደረጃ የተዘጋጀ የዕውቀት መለኪያ ፈተና ነበር፡፡ ይህ ፈተና በሁለት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ አንደኛው ተማሪ አባቱ የናጠጡ ነጋዴ ሲሆኑ እናቱም አሜሪካ ተወልደው አድገው በአንድ የውጭ ድርጅት ለመሥራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው፡፡ እርሱም የሚማረው ‹‹አበባ የቀጠፈና አማርኛ የተናገረ ይቀጣል›› የሚል ማስታወቂያ በተለጠፈበት አንድ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሁለተኛው ተማሪ አባቱ የቀን ሥራ በመሥራት የሚተዳደሩ እናቱም ዶሮ የሚያረቡ ናቸው፡፡ ልጁም የሚማረው ከተቋቋመ ከሦስት ዓመቱ ጀምሮ መስኮቱ ተዘግቶ በማያውቅ አንድ የመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡

የቤት ሥራው እንዲህ ይላል ‹‹ዶሮን በተመለከተ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናንተ ከምታውቁትና ከወላጆቻችሁ ጠይቃችሁ መልሱ››

ሁለቱም ተማሪዎች ወደቤታቸው ከገቡ በኋላ የቤት ሥራውን መሥራት ጀመሩ፡፡

የነጋዴው ልጅ ‹‹ዶሮ›› የሚለው ነገር ግልጽ አልሆነለትምና እናቱ ከሥራ ስትገባ ጠብቆ ጠየቃት፡፡ ‹‹ዶሮ፣ ምን መሰለህ፣ ኦ ማይ ጋድ፣ ቺክን ማለት ነው›› አለችው፡፡ ልጁም ፈገግ አለና ‹‹ኦኬ፤ ታደያ ለምን ቺክን አላሉትም›› አለና ጠየቃት፡፡ ‹‹ቺክን እዚህ ሀገር ውድ ስለሆነ ብዙ ሰው ቺክን አይበላም፡፡ ለዚያ ነው ዶሮ ያሉት›› ስትል አስረዳችው፡፡

የመጀመርያው ጥያቄ እንዲህ ይላል ‹‹አንዳንድ እንስሳት አካላቸው በፀጉር የተሸፈነ ነው፤ ሌሎቹም በላባ ይሸፈናል፡፡ የዶሮ አካል በምን የተሸፈነ ነው?›› የዶሮ አርቢዋ ልጅ ከት ብሎ በመሳቅ በጥያቄው ተገረመና‹‹ ዶሮ በላባ የተሸፈነች ናት›› ሲል መልሱን ጻፈ፡፡ የነጋዴው ልጅ ደግሞ ‹‹ዶሮ በሁለት ነገር ትሸፈናለች፡፡ ከላይ በላስቲክ የምትሸፈን ሲሆን ከሥር ደግሞ በነጭ ካርቶን ትሸፈናለች›› ሲል ሱፐር ማርኬቱን እያስታወሰ መልሱን በኩራት ጻፈው፡፡

ከዚያም ሁለቱም በየቤታቸው ሆነው ወደ ሁለተኛው ጥያቄ ተዘዋወሩ፡፡ ‹‹ዶሮ የሚገኘው ከየት ነው?›› ይላል ጥያቄው፡፡ የዶሮ አርቢዋ ልጅ ፈጠን ብሎ ‹‹ዶሮ የሚገኘው ከዕንቁላል ተፈልፍሎ ነው›› ሲል በደብተሩ ላይ አሠፈረ፡፡ የነጋዴውም ልጅ ሳቅ አለና ‹‹ዶሮ የሚገኘው ከኒውዮርክ ሱፐር ማርኬት፣ ከፍሎሪዳ ሱፐር ማርኬት፣ ከሆላንድ ሱፐር ማርኬት፣ ከኤክስ ዋይ ሱፐር ማርኬት ፍሪጅ ውስጥ ነው›› ሲል በኩራት መልሱን ጻፈ፡፡

ጥያቄው እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ‹‹ውሻ ሲጮኽ ‹ዋው፣ ዋው› ይላል፡፡ ላም ‹እምቧ› ብላ

ትጮኻለች፤ ጅብ ‹አውውውው›ብሎ ይጮኻል፡፡ ለመሆኑ ዶሮ ሲጮኽ ምን ይላል?››

የነጋዴው ልጅ አንገቱን ነቀነቀና ‹‹ዶሮ ድምጽ የላትም፤ ኢት ኢዝ ኦልሬዲ ዴድ››ሲል ሞላ፡፡ የዶሮ አርቢዋም ልጅ ‹‹ዶሮ ሲጮኽ ኩኩሉ ይላል›› ብሎ ጻፈ፡፡

‹‹በባህላችን ዶሮ አሥራ ሁለት ብልቶች አሏት ይባላል፡፡ ከወላጆቻችሁ ጠይቃችሁ ስማቸውን ዘርዝሯቸው፡፡›› ይላል ቀጣዩ ጥያቄ፡፡

የዶሮ አርቢዋ ልጅ ወደ እናቱ ጠጋ ብሎ ጠየቃት፡፡ ‹‹አይ የኔ ልጅ ዶሮኮ ድሮ ነበር እንጂ ዛሬ ከአሥራ ሁለት የሚበልጥ ብልት ሊኖራት ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምን ያልጨመረ ነገር አለ፡፡ ወይም ደግሞ እንደ ድኻ ኑሮ ቀንሳ ከሆነም ቁጥሩ ቀንሶ ሊሆን ይችላል፡፡ ማን አይቷት ብለህ ነው፡፡ እኔ እንደተሸፈነች ነው የምሸጣት፡፡ ዛሬ

ዛሬኮ ዶሮ የሚሸጥ፣ ዶሮ የሚያይና ዶሮ የሚበላ ተለያይተዋል፡፡ ዶሮ የሚሸጥ ዶሮ ያረባል እንጂ አይበላም፡፡ ቢበዛ ዕንቁላሏ ይበቃዋል፡፡ ዶሮ የሚያይ ደግሞ ገበያ ሲወጣ ዶሮ ከማየት ውጭ ዶሮም ዕንቁላልም በልቶ አያውቅም፡፡ ዶሮ የሚበላ ግን ዶሮ ከየት እንደምትመጣ ባያውቅም ዶሮ ይበላል፡፡ እኛ ዶሮዋ ተሸፍና ስለምንሸጣት ብልቷን ረስተነዋል፡፡ እነርሱ ደግሞ ስለ ብልቷ ስለማይጨነቁ አያውቁትም፡፡ አሁን ይህንን ጥያቄ ብለው የሰጧችሁ እንድትጓጉ ካልሆነ በቀር ምን ይጠቅማችኋል? በል ሂድና እመይቴ የዝናሽን ጠይቃቸው፡፡ እርሳቸው የደጃች ዘመዱ ወጥ ቤት ነበሩ፡፡

ልጁ ወደ እመይቴ የዝናሽ ዘንድ ሄደ፡፡ ‹‹አዬ ልጄ አሁንማ ረስቼ፡፡ ዶሮ በሁለት መቶ ብር እየተሸጠ ማን ብልት ያስታውሳል ብለህ ነው፡፡ አታጓጓኝ እባክህ፡፡ እኔኮ ዶሮ ሲያምረኝ ድሮ የበላሁትን እያስታወስኩ ነው የምጽናናው፡፡ ‹ድኻ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ› ሲባል አልሰማህም፡፡ በል እስኪ ጣፍ ትዝ ካለኝ፡፡ አጭሬ ሁለት፣ መላላጫ ሁለት፣ ፈረሰኛ አንድ፣ መቋደሻ አንድ፣ ክንፍ ሁለት፣ እግር ሁለት፣ አቃፊ አንድ፣ ጉሮሮ አንድ፣ አሥራ ሁለት አልሆነም፡፡ ወደፊትኮ የዶሮ ቅርጫ ካልተጀመረ ዶሮ እንዳማረን መቅረቱ ነው፡፡ ዱሮማ የዶሮ ዳቦም እንሠራ ነበር፡፡ ወዳጄ ዛሬ እንኳን ዶሮ ያለበት ዳቦ ባዶውም ዳቦ

አልተገኘ› አሉና ሸኙት፡፡ የነጋዴው ልጅ ሁለት ነገር አልገባውም ‹‹ብልት›› ምንድን ነው? አለ ለራሱ፡፡ አሥራ ሁለት ብልት የሚባል ነገር ሰምቶ አያውቅም፡፡ ወደ እናቱ ሄደና ‹‹ማማ የቺክን አሥራ ሁለት ብልት ምንድን ነው?›› አለና ጠየቃት፡፡ ‹‹አይዶኖ፡፡ እስኪ ጉግል ላድርግ›› ብላ ወደ ኮምፒውተሯ ሄደች፡፡ ‹‹ቆይ ብልት በእንግሊዝኛ ምንድን ነው? ሌት ሚ ሰይ ፓርትስ››

‹‹ትዌልቭ ፓርትስ ኦፍ ቺክን›› ብላ ጉግል ላይ ጻፈችና ሰርች አደረገችው፡፡

‹‹እንደዚህ የሚባል ነገር የለም›› አላት ጉግል፡፡ ‹‹የሌለ ነገር ነው እንዴ የሚሰጧችሁ፡፡ ትዌልቭ

ፓርት የሚባል የዶሮ ነገር የለም››ትንሽ አሰበችና ‹‹እስኪ ቆይ ዲክሽነሪ ሪፈር ላድርግ›› ብላ ወደ ሳሎን ሄደች፤ አንድ የአማርኛ እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላትም አወጣች፡፡

‹‹ቆይ ‹በ› ከማን ቀጥሎ ነው፡፡›› ከ‹ሀ› ጀምራ ወደ ‹በ› ለመድረስ አልቻለችም፡፡‹‹ሚኪ ‹በ› ከማን አጠገብ ነው ያለው?››

ብላ ልጇን ጠየቀችው፡፡ ‹‹ከ‹ቡ› ጎን›› አለና መለሰላት፡፡

ከመጀመርያው ገጽ ጀምራ እያገላበጠች በመዝገበ ቃላቱ ላይ መፈለግ ጀመረች፡፡‹‹አማርኛ መሻሻል አለበት፡፡ ከ‹ኤ› ቀጥሎ ‹ቢ› እንዲመጣ ማድረግ አለባቸው፡፡›› ብላ አማረረች፡፡ ከዚያም በስንት ፍለጋ እንደምንም ብላ ‹ብ›ን አገኘችው፡፡ ‹‹ብልት›› ለሚለው ቃል መጀመርያ የተሰጠውን ትርጉም አየችና፡፡ ‹‹ማነው ግን ይህን ሆም ወርክ የሰጣችሁ›› አለችው ልጇን፡፡ ‹‹ሆም ሩም ቲቸር ነው›› ‹‹ባለጌ ነው፡፡ ብልት የሚል ቃል አሁን ለልጅ ይሰጣል፡፡ በቃ ዶሮ እንኳን አሥራ ሁለት አንድም ብልት የላትም ብለህ ጻፍለት›› አለችው ተናድዳ፡፡

ልጁም እንደ እናቱ ተገርሞ ወደ ቀጣዩ ጥያቄ አመራ፡፡ ‹‹የዶሮን ልዩ ልዩ ጥቅሞች ግለጡ›› ይላል፡፡ የዶሮ አርቢዋ ልጅ እናቱን ጠየቃትና እንዲህ መለሰችለት

‹‹ዶሮ ለሦስት ነገር ትጠቅማለች፡፡ አንደኛ ጠዋት ጠዋት ለመቀስቀስ ይጠቅማል፡፡ ሁለተኛ ተሽጦ ገንዘብ ይገኝበታል፡፡ ሦስተኛ ደግሞ ዕንቁላል ያስገኛል፡፡›› ልጁም ጻፈ፡፡

የነጋዴውም ልጅ እንዲህ ሲል መልሱን ሰጠ ‹‹ዶሮ ለወጥ፣ ለአሮስቶ፣ ለግሪል፣ ከሩዝ ጋር ለመብላት፣ ለሰላጣ ትጠቅማለች፡፡ አንዳንድ ሬስቶራንት ደግሞ እግሯን ለብቻ፣ ክንፏን ለብቻ ግሪል አድርገው ይሸጧታል፡፡ ዕንቁላሏ ደግሞ ለሳንዱች፣ ለዕንቁላል ፍርፍር፣ ለጥብስ፣ ለፓን ኬክ ይጠቅማል››

ጥያቄዎቹ ቀጠሉ፡፡ ‹‹ዶሮ ተመግባችሁ የምታውቁ ከሆነ ስለ ጣዕሙ ግለጡ››

ይላል፡፡ የዶሮ አርቢዋ ልጅ ወደ እናቱ ተጠጋና ነገራት፡፡ ‹‹ወይ ጣጣ፤

እኔኮ አንተን የላክሁህ እንድትማር እንጂ እንድትራቀቅ አይደለም፡፡ አሁን ይሄ ልጅን ማጓጓትና ማሳቀቅ ትምህርት ይባላል፡፡ ለመሆኑ ራሳቸው መምህራኑስ የዶሮ መግዣ ዐቅም አላቸው? እኔኮ ስንት እንደምሸጠው ዐውቃለሁ፡፡ በሁለት መቶ ብር ለሦስት ወር የሚበቃ ሽሮ መግዛት ስችል የአንድ ቀን ዶሮ በልቼ የት ልደርስ ነው? በል ልጄ ‹ዶሮ ትሸጣለች እንጂ አትበላም በላቸው፡፡›› አለችው፡፡

ወዲያው ልጁ ቀበል አደረገና ‹‹እንዴ እማዬ መምህራችንኮ ዶሮ ይበላል ብሎናል››አላት፡፡

‹‹እኛ ዶሮ አንበላም፡፡ ፈረስ የሚበሉ አሉ፡፡ እኛ ግን አንበላም፡፡ እንትኖች ውሻ ይበላሉ ሲባል እሰማለሁ፡፡ እኛ ግን አንበላም፡፡ አይጥ የሚበሉ አሉ፤ ዝንጀሮ የሚበሉ አሉ፤ ዕባብም የሚበሉ አሉ፡፡ ታድያ እኛ እነዚህን እንበላል?›› አለችና ጠየቀችው፡፤

የጠራችው ዝርዝር እያቅለሸለው ‹‹ኧረ አንበላም›› አላት፡፡ ‹‹አየህ ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ ዶሮም የሚበሉ ይኖራሉ፡፡ እኛ

ግን አንበላም››አለችው፡፡ ‹‹ለምንድን ነው ግን እኛ ውሻ፣ አይጥ፣ ዝንጀሮ ያልበላነው?›› ‹‹ሃይማኖታችን አይፈቅድማ›› ‹‹ዶሮስ የማንበላው?›› ‹‹እንደዚያው ነው ልጄ›› ‹‹ታድያ እነ አካሉኮ ይበላሉ›› ‹‹አየህ የሀብታሞችና የድኾች ሃይማኖት እዚህ ሀገር

ይለያያል፡፡ ሀብታሞች መብልን እኛ ደግሞ ጦምን እናበዛለን፡፡ እነርሱ በደም ብዛት እኛ በደም ማነስ እንታመማለን፣ እነርሱ በስኳር ብዛት እኛ በስኳር እጥረት እንቸገራለን፣ እነርሱን ውፍረት እኛን ክሳት ያስቸግረናል፡፡ የነርሱ ልጆች አልበላም ብለው የኛ ልጆች እንብላ ብለው ይገረፋሉ፡፡ እነርሱ ገብርኤልን እኛ ሚካኤልን እንዘክራለን፡፡ በዚህ ምክንያት ሃይማኖታችን ተለያይቷል፡፡››

17.7243 18.0788

27.6871 28.2408

1843.4000 1880.2680

250.5100 255.5202

294.3200 300.2064

297.9100 303.8682

98.5000 100.4700

31.0028 31.6229

21.0500 21.4710

22.2555 22.7006

17.2920 17.6378

17.8696 18.2270

4.7260 4.8205

4.8254 4.9219

22.1447 22.5876

2.1151 2.1574 ዋጋ እናወዳድራለን፤ ሌላ ቦታ ውሰዱ በተባሉበት ዋጋ እንሸጥልዎታለን

617 Cedar Ave S Minneapolis, MN 55454

612-332-7020

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ከሰሞኑ ግብይት የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ

24ቱ የሃገር ቤት

ኦርጋኒክ ቢራ በማይታመን

ዋጋ

አክሱሚት እና ጉደር ሁለቱ 15$ ብቻ የሃገር ቤት ጠጦችን ይዘዙን በተመጣጣኝ ዋጋ እናደርሳለን።

ምንዛሪ ግዢ ሽያጭ

የአሜሪካን ዶላር 18.1527 18.5158

ፓውንድ 29.4146 30.0029

ስዊዝ ፍራንክ (100) 1977.6300 2017.1826

የስዊድን ክሮነር(100) 273.1100 278.5722

የኖርዌይ ክሮነር(100) 323.6700 330.1434

የዳኒሽ ክሮነር (100) 320.1500 326.5530

የጅቡቲፍራንክ(1000) 100.8000 102.8160

የህንድ ሩፒ (100) 33.0891 33.7509

የኬንያ ሽልንግ (100) 21.0700 21.4914

የጃፓን የን (100) 21.6826 22.1163

የካናዳ ዶላር 18.3750 18.7425

የአውስትራሊያ ዶላር 19.1184 19.5008

የሳዑዲ ሪያል 4.8403 4.9371

የኤመሬትስ ድርሃም 4.9421 5.0409

ዩሮ 23.8871 24.3648

የደቡብ አፍሪካ ራንድ 2.1148 2.1571

0

811 University Avenue West, St Paul, MN 55104

African

Country of Origin

New HIV Infections Reported In The Last 8 Years

2004 – 2011

(NOTE: There were 366 African-born cases reported from 1985 – 2003)

Total Living with HIV/

AIDS in 2011

2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011

Ethiopia 10 9 9 6 3 6 1 5 212

Kenya 10 5 4 12 9 6 1 11 140

Liberia 6 5 7 10 6 5 4 10 129

Somalia 4 3 2 6 1 2 10 7 89

Cameroon 6 9 2 2 5 6 1 1 72

Other* 17 14 11 13 11 16 16 10 302

All African Born Cases

53 45 35 49 35 41 33 44 944**

HIV/AIDS among African-born Minnesotans

የሚኒሶታ ዲፓርትመንት ኦፍ ኸልዝ (MDH) የዓለም አቀፉን የኤድስ ቀንን አስታኮ የአፍሪካውያን የኤድስ ቀንን

በየዓመቱ ያከብራል። ዘንድሮም ይህ African World AIDS Day (AWAD) በዓል በሚኒያፖሊስ ሳፋሪ ሬስቶራንት ወደ 80 የሚጠጉ አፍሪካውያን በተገኙበት ተከብሯል። ከዚህ ክብረ በዓል በኋላ ዘ-ሐበሻ በሚኒሶታ የጤና ዲፓርትመንት ውስጥ የሚሰሩትን የሚዲያ ስፔሻሊስቱን ሮይ ኔልሰንን በሚኒሶታ የሚገኙ ከኤች አይቪ ጋር አብረው የሚኖሩትን ሰዎች ቁጥር በሃገራት ደረጃ እንዲሰጡን ጠይቀናቸው ነበር። በዚህም መሠረት እስከ 2011 ድረስ ያለውን አሃዝ ያደረሱን ሲሆን የ2012 መረጃ ይህ ዓመት ከተጠናቀቀ በኋላ ሲወጣ ይልኩልናል።

በሚኒሶታ በ2011 ዓ.ም ከኤች አይቪ ጋር እየኖሩ ያሉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከአፍሪካውያን አንደኛ እንደሆንን ይህ መረጃ ያሳያል። 212 ኢትዮጵያውያን ከኤች አይቪ ጋር የሚኖሩ ሲሆን፤ ሁለተኛ ኬንያውያን ናቸው። በ140 ሰዎች። ላይቤሪያውያን 129፣ ከሶማሊያ 89፣ ከካሜሩን 72 ሰዎች ከኤች አይቪ ጋር ይኖራሉ። ሌሎች 302 ሰዎች ከ26 የአፍሪካ ሃገራት የመጡ አብረው ከቫይረሱ ጋር እየኖሩ መሆኑን የዲፓርትመንቱ መረጃ ያመለክታል።

*The “Other” category includes those from at least 26 other African countries **This total includes those living with HIV who have moved to Minnesota from other states and countries where they were initially diagnosed

Page 8: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Two Location

5103 University Ave, NE,

5104Columbia Heights, MN 55421 2929 university Ave. SE

Minneapolis, MN 55414

የዶክተር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፦ ጥያቄህ ሚዛን ደፍቶ አገኘነውና መልስ ልንሰጥበት ወሰንን፡፡ ባለፈው የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ እትማችን ላይ በስፋት ስለጨው ጽፈን ነበር። አሁንም እስኪ ስለዚህ በአጠቃላይ በደምብዛትና በጨው ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ይዘን ቀርበናል ተከታተለን፡፡

በአንድ ወቅት በስራ ላይ በነበርኩበት ወቅት አንድ የደም ግፊት ታማሚ የሆኑ ተጫዋች አዛውንት አጋጥመውኝ ነበር፡፡ አንዴ ስለህመማቸው እያዋየኋቸው እያለሁ ‹‹ሰማህ ልጄ?›› አሉኝና ት/ቤት ያላገኘሁትን ‹‹ሌክቸር›› ሰጡኝ፡፡ ‹‹አየህ? ደም ግፊት ማለትኮ የሚጥም ምግብ ማለት ነው›› አሉኝ፡፡ ግራ ገባኝና ‹‹እንዴት አባቴ?›› አልኳቸው፡፡ ‹‹እንዴት ማለት ጥሩ! የሚጥም፣ ጣት የሚያስቀረጥም ምግብ ስበላ ከከረምኩ ደም ግፊትህ ተነስቷል ትሉኛላችሁ፡፡ የናንተን ምክር ሰምቼ ጨውም፣ ቅባትም፣ ምኑም ምኑም ያልገባበትን እህል ውሃ የማይል ምግብ የበላሁ ሰሞን ደግሞ ደም ግፊት የለብህም ትሉኛላችሁ፡፡ ታዲያ ደም ግፊት ማለት የሚጥም ምግብ ማለት አይደል›› ሲሉ ሃሳባቸውን አብራሩልኝ፡፡

ጨዋታ አዋቂው አዛውንት በየዋህ አገላለፅ ያስተላለፉት ታላቅ ቁም ነገርን ነው፡፡ ሁል ጊዜ ግራና ቀኝ ሲነገር የምናዳምጠው ነው- የደም ግፊት ህሙማን ጨው፣ ቡናና ሌሎችንም ነገሮች ከምግባቸው እንዲያስወግዱ የመከሩን ነገር፡፡ አሁን አሁን ይህ ህመም በአገራችን በሚገርም ፍጥነት ተስፋፍቶ ‹‹የተለመዱ›› ከሚባሉት ህመሞች ጎራ ተመድቧልና ጥያቄው ተገቢ ነው፡፡

ውድ ጠያቂያችን የደም ግፊት ህመም (hypertension) በደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም በግድግዳዎቻቸው እንደልብ መለጠጥ አለመቻል የሚመጣ ህመም ነው፡፡ የደም ቧንቧዎች ይህን አይነቱ ገፅታ ሲኖራቸው ደም በውስጣቸው የሚጓዝበት ኃይል ይጨምርና አይነትና ከፍታቸው ለተለያዩ የጤና አደጋዎች ይዳረጋሉ፡፡ የደም በአንጎል ውስጥ መፍሰስ፣ የልብ የደም ቧንቧዎች መዘጋትና መጥበብ፣ ስር የሰደደ የኩላሊት መዳከም በጣም የተለመዱትና ለህልፈት ሊያበቁ የሚችሉት

የደም ግፊት መጨመር መዘዞች ናቸው፡፡ መጀመሪያ ነገር የደም ግፊት እንዲመጣ የሚያደርገው

ምክንያት እስካሁን በውል አይታወቅም፡፡ ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ነገሮች ግን ተለይተዋል፡፡ እንደ ስኳር ህመም ሁሉ ደም ግፊትም በከፊል በዘር፣ በከፊል ደግሞ በአኗኗር ዘይቤ የተነሳ ይመጣል፡፡ የዘር ስሪቱ ሲታይ በደም ግፊት ህመም የመያዝ ዕድሉ ከፍ ያለ ሰው (ለምሳሌ ወላጆቹ የደም ግፊት ህሙማን የሆኑ) የአኗኗር ዘይቤው ለዚህ ህመም የተመቻቸ ከሆነ በደም ግፊት ህመም ይያዛል እንደማለት ነው- በግርድፉ ሲቀመጥ፡፡ የዘር ስሪትን ማስተካከል የማይታሰብ ነው፡፡ ነገር ግን የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል በበሽታው አለመያዝም፣ ከተያዙ በኋላ ማስተካከልም ይቻላል፡፡

ለደም ግፊት የተመቻቸ የአኗኗር ዘይቤ ስንል ምን ማለታችን ነው? ከልክ ያለፈ ውፋሬ፣ በጣፋጭነት ቅባታማ

ምግቦች ተሞልቶ በፍራፍሬና አትክልት ያልተደገፈ አመጋገብ፣ የማያንቀሳቅስ የስራና የኑሮ ገፅታ፣ በዕድሜ መግፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የእነዚህ ነገሮች መኖር በደም ግፊት የመያዝ ዕድልን ይጨምራል፡፡ አንዴ በህመሙ ከተያዙ በኋላ ደግሞ ከእነዚህ በተጨማሪ ጨው በብዛት መመገብ፣ ሲጋራ ማጤስ፣ የስኳር ህመም፣... ወይ የደም ግፊቱን ከፍ ማለት ያባብሱታል፣ ወይ ደግሞ በሱ የተነሳ የሚመጡትን መዘዞች ይበልጥ ያከፏቸዋል፡፡ እንግዲህ በደም ግፊት የተያዘ ሰውም ከሌሎቹ እርምጃዎች በተጓዳኝ ምግቡ ውስጥ የሚኖረውን የጨው መጠን እንዲቀንስ የሚመከረውም ለዚህ ነው፡፡ ጨው መመገብ የደም ግፊቱ ከፍታ እንዲባባስ ከማድረግ በተጨማሪ ለደም ግፊት የሚወሰዱት መድኃኒቶችም በቅጡ እንዳይሰሩ ያደርጋል፡፡

ህመሙ ያለበት ሰው ላይ ጨውን በጥቂቱ ብቻ መመገብ የሚኖረው ጠቀሜታ አያጠያይቅም፡፡ ገና ባልተያዘው ሰው ላይስ? በጨው ይዘቱ ያየለ ምግብ መመገብ በደም ግፊት ሊያስይዘው ይችላል? ጥናቶች ለዚህ ያላቸው ምላሽ በከፊል አዎንታዊ ነው፡፡ እላይ የዘረዘርናቸው የአኗኗር ገፅታዎችና በዘር የመጠቃት እድል እያሉበት ጨው አብዝቶ የሚመገብ ሰው

መጠነኛ ወይም ጥቂት ጨው ከሚወስደው ጋር ሲነፃፀር ቀድሞ በደም ግፊት የመጠቃት ዕድሉ ከፍ ይላል፡፡ ተመራማሪዎቹ ለዚህ እንደማስረጃ የሚያቀርቡት ምዕራባውያኑ በምግባቸው ውስጥ የሚጨምሩት ጨው ከፍ ያለ መሆኑን፣ የታዳጊ አገር ነዋሪዎች ግን የሚወስዱት የጨው መጠን መጠነኛ ከመሆኑ ባሻገር አብዛኛው በቀጥታ ከምግቡ ከራሱ የሚገኝ እንጂ ምግብ ላይ የሚጨመር አለመሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ሌሎቹ የዘርና የአኗኗር ገፅታዎችን ልዩነት አውጥተንም ከጨው ጋር በተያያዘ ብቻ ስናወዳድር ምዕራባውያኑ ይበልጥ በደም ግፊት እንደሚጠቁ እናስተውላለን፡፡

መልዕክቱስ? የጨው መብዛት ከምላስ ያለፈ ፋይዳ የለውም፣ ማነሱ ግን ሊጠቅመን ይችላልና የጨዋችንን ነገር ልብ እንበለው፡፡ ያለበለዚያ እንደአዛውንቱ ‹‹ደም ግፊት ማለት የሚጥም ምግብ ነው›› ለማለት እንበቃለን፡፡

ውድ ጠያቂያችን ከቀረበው ፅሑፍ በቂ ማብራሪያ እንዳገኘህ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ ያለፈው አንዴ አልፏል፡፡ ተገቢው ጥንቃቄ አይለይህ፡፡

ማንኛውንም ነገር በመጠኑም ቢሆን አይጎዳምና የጨው መጠናችንንም በአግባቡ ብንወስድ ይመረጣል፡፡

ለምን እንደሆነ አላውቅም ጨው የበዛበት ነገር እወዳለሁ፡፡ በቅርቡ ታምሜ አንድ የግል ሆስፒታል ስመረመር ጨው ስላበዛሁ ደም ብዛት ይዞሃል ተባልኩ፡፡ ከመቼ ወዲህ ነው ጨው ደግሞ የደም ብዛት የሚያስይዘው? እባካችሁ እውነት መሆን አለመሆኑን

አስረዱኝ፡፡ የዘ-ሐበሻ የዘወትር አንባቢ ሳምጆ

ውድ አዘጋጆች፡- በጣም የምወዳትና የምሳሳላት ቆንጆ ፍቅረኛ አለችኝ፡፡ ከተዋወቅን 6 ወር ሆኖናል፡፡ ለመጋባትና አብሮ ለመኖር እናስባለን፡፡ በቅርቡ ግን አንድ ግራ የሚያጋባ ነገር ገጥሞናል፡፡ ይኸውም ፍቅረኛዬ የምትሰራበት የኮምፒውተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ አንድ አለቃዋ እንደሚወዳትና እንደሚያፈቅራት በተደጋጋሚ እንደሚገልፅላት ትነግረኛለች፡፡ ብዙ ጊዜም የተለያዩ ስጦታዎችን ይሰጣታል፡፡ መጀመሪያ ላይ ስጦታዎቹን ማን እንደሚሰጣት አትነግረኝም ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን አጥብቄ ስጠይቃት አለቃዋ እንደሆነ ነግራኛለች፡፡

አለቃዋን ቢሮ ድረስ ሄጄ ላነጋግረው ሞክሬያለሁ፡፡ ነገር ግን የተለወጠ ነገር የለም፡፡ እንደውም አለቃዋ እኔን ካየኝ በኋላ ከኔ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣ ከእሱ ጋር እንድትሆን እንደሚጨቀጭቃት ትነግረኛለች፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዴት ልንጋባ እንችላለን? ብዬ እየተጨነቅሁ ነው፡፡ ከዚያ መ/ቤት እንድትወጣ አለበለዚያ ግንኙነቷን እንድታቆም በተደጋጋሚ ብነግራትም ልታስቀይመው እንደማትፈልግ በመግለፅ ተግባራዊ ልታደርግ አልቻለችም ምን ይሻለኛል?

ደበበ ውድ ደበበ፡- ምን ማድረግ እንዳለብህ የምነግርህ ከዚህ

በታች ያለውን ጥያቄ ስትመልስ ነው፡፡ ለመሆኑ ፍቅረኛህ በእርግጥ ትወደኛለች ብለህ ታስባለህ? ለምን ስላንተ ሳይሆን ስለ አለቃዋ ስሜት መጎዳት የምትጨነቅ ይመስልሃል? በመ/ቤቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታስ በየጊዜው እየመጣች ላንተ የምትነግርህ ለምንድን ነው? ለማስቀናት ነው? እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በጥሞና አስበህባቸው ለመመለስ ሞክር፡፡

በመጀመሪያ ማድረግ ያለብህ ፍቅረኛህ ለምን ስለ ራሷ ተፈላጊነት ብቻ ስታወራ ላንተ ስሜት እንደማትጨነቅ ጠይቃት፡፡ በእርግጥ ብዙ ሴቶች በፍቅረኞቻቸው ወይም በባሎቻቸው የመረሳት ወይም የመተው ስሜት እንዳይሰማቸው በሌሎች ወንዶች እንደተፈለጉ አድርገው ማውራት ይቀናቸዋል፡፡ የምትወድህና አንተ እንዳልከው ወደ ፊት አብራህ በትዳር ለመኖር ሀሳቡ ካላት ግን አንተን ለማስቀናት አትሞክርም፡፡ በዚሁ ድርጊት መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ ግን ከአለቃዋ ጋር ከማስቸገር የዘለለ ግንኙነት አላት ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምክንያቱም አለቃዋ አንተን ከተዋወቀ በኋላ እንኳን ሀሳቡን ለመቀየር ፍላጎት እንደሌለው ነው የሚታየው፡፡ እሷም አንተን ወስዳ ካስተዋወቀች በኋላ ከአለቃዋ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቆም ነበረባት፡፡ ግን ጭራሽ ፍቅረኛሽን ተይውና አብረን እንሁን እዳላት ነው የነገረችህ፡፡ ይህ ታዲያ ምን ማለት ነው? ግንኙነታቸው በመ/ቤት ደረጃ ብቻ የተወሰነ ላለመሆኑ የራስህን ማጣራት መስራት አለብህ ባይ ነኝ፡፡ ይህንን ካረጋገጥክ በኋላ የራስህን ውሳኔ ለመወሰን ትችላለህ፡፡ መልካም ዕድል፡፡

Zehabesha.com

የሁለት ዓመት የትዳር ግንኙነት አለኝ፡፡ በሁለት ዓመት የትዳር ህይወቴ ባለቤቴ የፍቅር ቴክስት ሜሴጅ ልካልኝ አታውቅም፡፡ ቴክስት ሜሴጅ የምታደርገው አንድ የሆነ ጉዳይ ሲኖራትና መልዕክት ልትነግረኝ ስትፈልግ ብቻ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ምንም እንኳን ስራ እንደሚበዛባት ባውቅም ‹‹I love you›› የሚል መልዕክቷን ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ‹‹ለምንድነው የፍቅር መልዕክት የማትልኪልኝ›› ብዬ ስጠይቃት ‹‹በአካል አገኝህ የለም እንዴ?›› ትለኛለች፡፡ ነገር ግን በአካል እኔ እወድሻለሁ እስከምላት ጊዜ ድረስ አስባ እወድሃለሁ አትለኝም፡፡ ችግሬን እንዴት ማስወገድ እችል ይሆን? ማስተዋል ማንኛውም ነገር በተፈጥሮ የሚገኝ ነው ብለህ ማሰብ

የለብህም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ፍቅራቸውን በግልፅና በተደጋጋሚ የመግለፅ ልምድ ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በድርጊታቸው ነው ፍቅራቸውን መግለፅ የሚፈልጉት፡፡ ያንተ ባለቤት ምናልባት ፍቅሯን በተግባር ማሳየት የምትፈልግ ትሆናለች፡፡ ዋናው ነገር ግን ሰዎችን በልምምድ ወደ ሚፈልጉት የፍቅር ግንኙነት ማምጣት እንደሚቻል ማመን ያስፈልጋል፡፡ ባለቤትህ ‹‹I love you›› እንድትል ትፈልጋለህ፡፡ ፍላጎትህን ለማሳካት መንገዱን መክፈት ያለብህ አንተ ነህ፡፡ ይህንን ለማድረግ ቀላል ሙከራ አድርግ፡፡ ‹‹ I love you›› የሚለውን መልዕክት በቀን ቢያንስ ለሁለት ጊዜ ለባለቤትህ ላክላት፡፡ የመጀመሪያ ቀን ምንም ምላሽ ላታገኝ ትችላለህ፡፡ በሁለተኛው ቀን ግን እመነኝ ምላሽ

ትሰጥሀለች፡፡ ምላሿ ምናልባት ያንኑ መልዕክት መልሳ መላክ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን በቀጣይ ቀናቶች የተለያዩ አጫጭር የፅሑፍ መልዕክቶችን ትልክልሀለች፡፡ የፅሑፍን መልዕክት ተወዳጅና ጣፋጭ ለማድረግ ደግሞ አንተ የምትልከውን ፅሑፍ መልዕክት ጠያቂ እንዲሆን ብታደርገው ይመረጣል፡፡ ለምሳሌ ‹‹እኔ እወዳጅሻለሁ አንቺስ?›› ብትላት የራሷን ሀሳብ ጨምራ ትልክልሀለች፡፡ ‹‹ለመጀመሪያ ቀን ያየሁሽ ዕለት የተሰማኝ ደስታ ልዩ ነበር፤ አንቺስ የኔ አይነት ስሜት ነበረሽ?›› ብትላት መልሷን ትሰጥሀለች፡፡ ፍቅርህን በልምምድ ልታሻሽለው ትችላለህ፡፡ መልካም ዕድል፡፡

የ25 ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ነኝ፡፡ ከፍቅረኛዬ ጋር የፍቅር ግንኙነት ስንፈፅም እርካታ ላይ መድረስ አልቻልንም፡፡ በዚህ ደግሞ ፍቅረኛዬ ሁል ጊዜ እንደተከፋ ነው፡፡ ነፃ ሆኜ ወሲባዊ ግንኙነት ለመፈፀም ሁል ጊዜ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን አልጋ ላይ ከወጣሁ በኋላ ስሜቴ አልታዘዝ ይለኛል፡፡ እንደውም ብዙ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት ለመፈፀም ስዘጋጅ ወደ አዕምሮዬ ቶሎ የሚመጣው የእናቴ ንግግር ነው፡፡ አስታውሳለሁ ገና የ16 ዓመት ልጅ ሆኜ ከጎረቤታችን ልጅ ጋር ወሲብ ስንፈፅም እናቴ በድንገት ያልተቆለፈውን በር ከፍታ ገብታ ተናገረችኝ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ ስሜቴ ትክክል አይደለም፡፡ እባካችሁ ውድ የዘ- ሃበሻ አዘጋጆች ፍቅረኛዬን እንዴት ማስደሰትና ራሴንም ማርካት እንደምችል ምክር ለግሱኝ? መልሳችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ ኤስ

ውድ ኤስ፡- ችግርሽን በሚገባ ተረድቻለሁ፡፡ በመጀመሪያ ከችግርሽ ለመውጣት ቀዳሚው ነገር ‹‹አልችልም›› የሚለው ቃል በተደጋጋሚ በህሊናችን ውስጥ የሚያቃጭል ከሆነ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡ ስለዚህ አንቺም ለፍቅረኛሽ ደስታ መስጠት የማትችይ እና ለራስሽም እርካታ ላይ መድረስ የማትችዪ አድርገሽ አታስቢ፡፡ ‹‹እችላለሁ፤ አደርገዋለሁ›› በይና በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት የማትችዪ እንኳን ቢሆን እችላለሁ ማለትሽ ለፍቅረኛሽ ደስታ ይሰጠዋል፡፡ ቋንቋ በስሜታችን ላይ የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በልጅነትሽ እናትሽ ወሲብ መፈፀም ላይ እያለች በድንገት መጥተው ማስደንገጣቸው ወይም እንድትሸማቀቂ ማድረጋቸው

ተገቢ አይደለም፡፡ ተገቢ አይደለም ያልኩሽ ድርጊቱን ሊያስቆሙ የሞከሩበትን መንገድ ነው እንጂ ወሲብ በዚያ ዕድሜሽ ስትፈፅሚ ዝም ማለት ነበረባቸው ማለቴ አይደለም፡፡ ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው በልጅነታቸው ወሲብ መፈፀም እንዳይጀምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ይህንን ፍላጎታቸውን ለልጆቻቸው የሚገልፁት ግን በአግባቡ አይደለም፡፡ እናትሽም ከነዚህ ወላጆች መሀከል የሚመደቡ እንደሆኑ የወሰዱት እርምጃ ያሳያል፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ያለ ዕድሜያቸው ወሲብ እንዳይፈፅሙ መምከር እንጂ ወሲብን መጥፎ ነገር አድርገው መሳል የለባቸውም፡፡ በዚያን ወቅት የአንቺ እናትም የወሲብን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ካብራሩልሽ በኋላ በዚያ ዕድሜሽ

መፈፀምሽ ግን የሚያስከትለውን ጉዳት ቢነግሩሽ ኖሮ ዛሬ ስለ ወሲብ ያለሽ ግንዛቤ የተለወጠ ይሆን ነበር፡፡ አሁን ካለሽበት ችግር ለመውጣት ሁለት ነገሮችን ማድረግ ብቻ ይበቃሻል፡፡ የመጀመሪያው የእናትሽን ንግግር ለመርሳት ሞክሪ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ፍቅረኛሽን ለማስደሰት ብቃት ያለሽ ልጅ እንደሆንሽ ለራስሽ ደጋግመሽ ንገሪው፡፡ ይህን ጊዜ በሚገባ ወሲብ ለመፈፀምና ፍቅረኛሽን ለማስደሰት ትችያለሽ፡፡ ሰዎች ወሲብ ሲፈፅሙ የሚረኩት ትክክል ስለሆኑ አይደለም፡፡ ትክክል ነን ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ ስለዚህ አንቺም በዚሁ ጎዳና ተጓዥ፡፡ መልካም ዕድል፤ ህይወትሽ እንደሚለወጥ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሀብታም መሆን ሁሉም ይፈልጋል፡፡ ግን የፍላጎታችንን ያህል ተሳክቶልን ሀብታም የሆንን አይደለንም፡፡ ዘ ስትሪት የተባለው በፋይናንስ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ጋዜጣ የተለያዩ ሰዎችን ሀሳብ እና ልምዶች አሰባስቦ የፋይናንስ ባለሞያዎችንና ሚሊየነሮችን ትንታኔ በተቀበለበት ወቅት ተለይተው የታወቁ ከሀብት መስመር የሚያርቁ የዕለት ተዕለት ልምዶችና አስተሳሰቦች ታትመው ወጥተው ነበር፡፡ ‹‹የምታገኘው የገንዘብ መጠን ሀበታም በመሆንህ ላይ ያለው አስተዋፅኦ ትንሽ ነው፡፡ ዋነኛው ጉዳይ ያገኘኸውን ገንዘብ የምትቀበልበትና የምታስተናግድበት መንገድ ነው ይላሉ›› ሀሳባቸውን የሰጡት ሚሊየነሮች፡፡ ይህን መነሻ አድርገው ትንታኔ የተሰጠባቸውን አስር ከሀብት ያራቁንና ሀብታም እንዳንሆን ያደረጉንን ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡ 1. ጎረቤቶች ስላንተ ስለሚያስቡት ትጨነቃለህ ከጎረቤቶችህና ውድድር ውስጥ ከገባሃቸው ሰዎች የተሻለ የቁስ

ባለቤት መሆንህን ለማሳየት በየጊዜው አዳዲስ ግን ዘለቄታ የሌላቸውን እቃዎች በመግዛት ለፍተህ የመጣኸውን ገንዘብ ታባክናለህ፡፡ በዚህም ብልፅግህናህን ከማፋጠን ይልቅ ሰዎችን ስታስደንቅ ዕድሜህን እና ሀብትህን ስታባክን ትኖራለህ፡፡ 2. ትዕግስት የለህም ለህይወትህና ኑሮህ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን መግዛት

ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ገንዘቡ በእጅህ ላይኖር ይችላል፡፡ ገንዘቡ እስኪመጣ ከመጠበቅ ይልቅ በወለድም ቢሆን ተበድረህ ትገዛለህ፡፡ የራስህ ገንዘብ ሲመጣ እዳውን ብቻ ሳይሆን በወለዱ ምክንያት ሌላውንም ሊጠራቀም የሚችል ገንዘብ ይዞብህ ይሄዳል፡፡ 3. በአቋራጭና በፍጥነት ለመክበር ትፈልጋለህ አብዛኞቹ የምናውቃቸው ሀብታሞችና ሚሊየነሮች ጥረው

ግረው ሰርተው በረጅም ጊዜ ሀብታቸውን እንዳፈሩ የሚታወቅ ቢሆንም አንዳንዶቻችን በአንድ ሌሊት መበልፀግ እንፈልግና ያለንን ገንዘበ ሁሉ በፍጥነት ያበለፅገናል ባልነው ጉዳይ

እናጠፋለን፡፡ አብዛኞቹ በአቋራጭ እና በፍጥነት መክበሪያ መንገዶች ደግሞ በአጭበርባሪዎች የተያዙ በመሆኑ ያለህን ጥሪት በዚህ ሂደት ስለምታጣ ሀብት ማፍራት እንዳማረህ ይቀራል፡፡ 4. በማይገባህ ስራ ውስጥ ገንዘብህን ታፈሳለህ ጓደኛህ አቶ እከሌ የሆነ ስራ ጀምሮ በፍጥነት ገንዘብ አፍሶበት

ይሆናል፡፡ ግን የእርሱ ስራና መንገድ የአንተ ሊሆን ይችላል? የስነ ጥበብ ሰው ሆነህ ሳለ በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ገብቼ በአጭር ጊዜ እከብራለሁ ብለህ ከሆነ ይህ ጥርጣሬ ላይ ይጥላል፡፡ ይህን መሰል ከራሳችን ትምህርት፣ ችሎታ፣ ተሰጥኦና ብቃት ጋር ባልተያያዘ ስራ ውስጥ ገንዘብን ማፍሰስ ከሀብት የመድረሻ መንገዱን በእጅጉ ያርቅብናል፡፡ 5. የምትወደውን ስራ አትሰራም ሁሉም ሰው የሚያልመውን እና የሚደሰትበትን ስራ ብቻ

እንዲሰራ መጠበቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ቢያንስ ውጥረት እና ጭንቀት ውስጥ ወደማይከትህ ስራ መሰማራት ይመከራል፡፡ ብዙ ገንዘብ አለው ብለህ የምትሰራው እና የማትፈልገው ስራ የማያስከትልብህን ድብርት እና ውጥረት ለማስታገስ ብርህን ስትረጭ እና ‹‹ስትዝናና›› ጥሪትህ ያልቃል፡፡ ገንዘብ ማጠራቀም ከዝርዝርህ መጨረሻ ይሆናል፡፡ 6. የገንዘብ ነገር ላይ ፈሪ ነህ ያለህን ገንዘብ በባንክ አካውንት ማስቀመጥ ለብክነት

እንዳትጋለጥ ቢረዳህም ኪሳራን ፍራቻ ብሩን የማታንቀሳቅሰውና የማትሰራበት ከሆነ ካለህ ነገር መቼም ፈቀቅ አትልም፡፡ እንዲያውም የዋጋ ግሽበት በየወቅቱ በሚያምሳት በዚህች ዓለም ያስቀመጥከው ገንዘብ ዋጋው እየረከሰ የሚሄድበትም ዕድል ይኖራል፡፡ 7. የማትጠቀምበትን ዕቃ ትገዛለህ እስቲ እቤትህ ግባና ያሉህን እቃዎች ተመልከት፡፡ ወሳኝ

ጥቅም ያላቸው እና በእርግጥ የምትፈልጋቸው ምን ያህል ዕቃዎች ናቸው? ላለፉት በርካታ ወራት ያልተጠቀምክባቸው

ዕቃዎች ቁምሳጥንህ ውስጥ፣ መኝታ ቤትህ አለዚያም ኩሽና ውስጥ ምን ያህሉ አሉ? ተመልከታቸውና ልምድህን አስተካክል፡፡ 8. ገንዘብህን አትከታተልም ምን ያህል ገንዘብ እንደነበረህ፣ ምን ያህል እንዳጠፋህ ያለብህ

ዕዳ ይኖር እንደሆነ እና መሰል የገንዘብ ጉዳዮች ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ቁጭ ብለህ ማስላትና መስራት ይኖርብሃል፡፡ በባንክ አካውንትህ ስላለው ወጪና ገቢህ ክትትል አድርገህ አስፈላጊውን ማስተካከያ ማድረግን ካልለመድህ የገንዘብ ጉዳይ ቸልተኝነትህ ብዙ ሊያስከፍልህ ይችላል፡፡ 9. መጥፎ ልምዶች አሉህ የገንዘብ ፀር የሆኑ ክፉ ልማዶች ከሚባሉት መካከል ሲጋራ፣

አልኮል፣ ጫት እና ቁማር ሱሰኛ ከሆንክ ገንዘብ የማስተዳደር እና ተጨማሪም የማፍራት አቅምህ በእጅጉ ይፈተናል፡፡ በእቅድ የመስራት፣ የመዝናናትና የመስራት ልምድህን በማዛባት የሚበልጠውን ጊዜህን ከዚሁ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች እንድታጠፋ ትገደዳለህ፡፡ 10. በህይወት ግብ የለህም ወደ ፊት ማሳካት የምትፈልጋቸውና አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት

ብለህ የምትቆጥራቸው ግቦች ከሌለህ ሀብትና ብልፅግናን ማሰብ ይከብዳል፡፡ የምትቆምለት፣ የምትሰራለት ህልም እና ግብ የበለጠ ለስኬት ይገፋፋሃል፡፡ ይህ ደግሞ ገንዘብን ይዞ ይመጣል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ወደሃብት የሚደረግ ጉዞን የሚገቱ

መሰናክሎች መካከል አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት አለዚያም ከዚያ በላይ የሆኑት በአንተ ህይወት ውስጥ የሚንፀባረቁ ጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እስቲ ቁጭ በል እና በጥሞና አሰላስላቸው፡፡ መወገድ የሚችሉትን በቶሎ አስወግድ፣ ጭንቅላትህንም ለእነዚህ እንቅፋቶች የነቃ እንዲሆን አድርገውና በህይወትህ እንዳይደገሙ ተከላከላቸው፣ መልካም ውጤት ቀና የሀብት ጉዞ፡፡

Page 9: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 45 ላይ በ18 ጥይት በባለቤቷ ተደብደባ ስለተገደለችው ወጣት ከአዲስ አበባው ቁምነገር መጽሔት የተላከልንን ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል። ከብዙ አንባቢያን በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረው ‹‹የግድያው ምክንያት›› ምንነት የማወቅ ስለነበር በወቅቱ ከፍሬህይወት ጋር አብረው በመኪና ውስጥ የነበሩትና በሶስት ጥይት የቆሰሉት እናቷ ወ/ሮ ተናኘ ሀ/ማርያም መጽሔቱ አነጋግሯቸዋል። የባለፈውን ዘገባ ያጠናቅረዋልና ያንብቡት። በዚህ አጋጣሚ የቁምነገር መጽሔት አዘጋጅ ታምራት ኃይሉን እናመሰግናለን ስለ ዘገባው።

ቁምነገር፡- ፍሬህይወት በትዳር የነበራት ህይወት ምን ይመስል ነበር?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ፍሬህይወት በትዳር በሰላም የኖረችው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው፡፡ ቀሪው 4 ዓመት በመከራ ውስጥ ነበር የኖረችው ለማለት እችላለሁ፡፡ ነፍሷ አልወጣም እንጂ በጭንቅ ውስጥ ነበረች ያለችው፡፡

ቁምነገር፡- እንዴት? ወ/ሮ ተናኜ፡- እየደበደባት፣ ፀጉሯን እየነጨ፣ በረኪና

ጠጪ እያለ ነበር የኖረችው፡፡ ለምሳሌ አንድ ጊዜ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ የፍሬህይወት ታናሽ ወንድም ማታ ቤታቸው ውስጥ ነበር፡፡ ታላቅ ወንድሜ የሚለው ሰውም ሊጠይቀኝ መጥቷል ይል ነበር፡፡ ከዛ ሌሊት ተነስቶ ሲደበድባት ወንድሟ እኛ ጋር ደውሎ ድረሱላት ይለናል፡፡ የለበስነውን ነገር አናውቅም፡፡ በለሊት ከአባቷ ጋር ተያይዘን ኮንትራት ታክሲ ይዘን እንሄዳለን፡፡ ግን እንዴት ብለን በር አስከፍተን እንግባ፡፡ በር ላይ ቆመን ሳለን ወንድም የተባለው ሰው መጣ፡፡ ከዚያ ‹‹ ወንድሜ ምን ድን ነው ችግሩ ጥፋቱስ የማን ነው?›› ብዬ ስጠይቀው ‹‹ልጅዎ ጋር ምንም ችግር የለም፤ ጥፋቱ ሁሉ የሱ ነው፡፡ የሚችሉ ከሆነ ልጅዎን ያድኑ›› ነበር ያለኝ፡፡ ከዛ ተያይዘን ወደ

ቤት ውስጥ ስንገባ የሷ ፊት ቀልቶ ተቀምጣለች፡፡ እሱ ውስኪ በጠርሙስ ይዞ ተቀምጧል፤ ምንድን ነው ልጄ? ስለው‹‹ ምን ልትሰሩ መጣችሁ›› ነበር ያለን፡፡ ለምንድን ነው እንደዚህ የምትለው ስለው ወደ ሌላ ክፍል ገባ ትንሽ ቆይቶ ተመልሶ መጣ፡፡ ከዛ መዛት ጀመረ፡፡ ሁኔታው አላምር ሲለኝ ይዘናት እንሂድ አልኩት፡፡ ግን በሌሊት መጥተው ሚስቴን ይዘውብኝ ሄዱ ብሎ ለወሬ እንዲመቸው ሊያደርግ ይችላል ብዬ የለም ጠዋት ሲነጋ ችግሩን እንነጋገራለን ብዬ እዚሁ ነው እኔ የማድረው ብዬ መኝታ ቤት አስገብቻት በሩን ቆልፈን ተኛን፡፡ እሱ እዛው ውስኪውን ይዞ ሳሎን ተኝቶ 11 ሰዓት ሲሆን ተነስቶ ወጣ፡፡ እንደዚህ እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን እየፈፀመባት ነበር ዓመታት ያለፉት፡፡

ቁምነገር፡- ችግሮች ሲፈጠሩ በሽማግሌዎች በኩል

ለመፍታት አልተሞከረም? ወ/ሮ ተናኜ፡- የቀረ ነገር እኮ የለም፤ የቅርብ ሚዜዎች

ሳይቀሩ የተከበሩ ትላልቅ የቤተክርስቲያን ሰዎች ሳይቀሩ ጉዳዩን ያላዩ ሰዎች የሉም፡፡ ሰውየው ምላሱ አይቻልም፤ የማይለው ነገር የለም፡፡ ዛሬ ተፈታ የተባለ ችግር ነገ እንደገና ይመጣል፤ ሰው ከቁብ የሚቆጥር ሰው አይደለም፤ በየጊዜው ይጠጣል፣ ያ ጨሳል፤ ሌላው ቀርቶ ያድራል ያልቻለችው ነገር አልነበረም ፡፡

ቁምነገር፡- የቅርብ በሚባል በሱ ዘመዶች በኩልስ ችግሩን ለመፍታት አልሞከራችሁም?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ምን ዘመድ አለው፤ እኛ የትስ እናውቃቸዋለን? ከሠርጉ በኋላ ለመልስም ሆነ ለቅልቅል ጊዜ ይዟቸው የሚመጣው ጓደኞቹንና ሚዜዎቹን ነው፡፡ መሰረቱንም ቤተሰቡንም አስተዋውቆን አያውቀም፡፡ ያው የሴት ልጅ ነገር ትውውቃቸው በውጪ ነው፡፡ ዘመዶችህ ቤተሰቦችህ እነማን ናቸው የሚል ጥያቄ አላቀረበችለትም፡፡ በውጪ ተዋውቀው ሽማግሌ ተላከ አባቷ አልቀበልም አለ ፡፡

ቁምነገር፡-ለምን? ወ/ሮ ተናኜ ፡- የመጡት ሰዎች የራሱ ስራ አለው፣ ትልቅ

ሰው ነው፣ ቤቱም እዚህ ራስ አምባ ሆቴል አጠገብ ነው ምናምን አሉ፡፡ አባቷ ግን ልጄን አልሰጥም አለ፡፡ ምክንያቱም ፍሬህይወት ገና ልጅ ነች ለትዳር ሳይሆን ለትምህርቷ ነው ቅድሚያ መስጠት ያለባት፤ ካገባች ትወልዳለች፣ ከወለደች ደግሞ ትምህርቷን ለመማር አትችልም፤ ትምህርቷን ትጨርስና ይደርሳል ነው ያለው፡፡ ሽማግሌዎች ለ12 ጊዜ ያህል ቀጠሮ ስጡን እያሉ ተመላልሰዋል፡፡ ፍሬህይወት ያን ጊዜ ገና 22 ዓመቷ ነው፡፡ እሱ ግን የሚተኛ ሰው ስላልነበር የሚያሸንፉንን ሽማግሌ የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማህበርተኛችን ትልቅ ካህን ይዞ መጥቶ እንዲገስፁንና እንዲቆጡን አስደርጎ በስተመጨረሻ ተሸነፍንለት፡፡ አባቷ እንኳ የዛን ጊዜሁሉ እንቢ ብሎ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ምናልባት ይህን ያህል ጊዜ ሽማግሌዎች የተመላለሱት ልጄ ፀንሳ ይሆን እንዴ ብዬ በማሰብ ማታ ስትመጣ ጠብቄ አጥብቄ ጠየቅኳት፡፡ እሷ ግን ፈፅሞ እንደዚህ አይነት ነገር ነበር የለም ያለችው፡፡ ከዛ አባትየው ባይስማማም ቀን ተቆርጦ ያሁሉ እናንተ ባለፈው ጊዜ የዘረዘራችሁት ሠርግ ተደገሰ፡፡ በመጨረሻም ሁኔታው አላምር ሲላት ወደ ፍርድ ቤት ሄደች ፡፡

ቁምነገር፡- ፍቺ? ወ/ሮ ተናኜ፡- አዎ የሱ ሽማግሌዎች ሳይቀሩ እኛ በዚህ

ጉዳይ ውስጥ ከዚህ በኋላ አንገባም ብለው እስከማለት ደርሰዋል፡፡ በትዳሩ ላይ እንዴት እንደሚወሰልት ፣የት ሆቴል ከማን ጋር መቼ እንዳደረ ሁሉ ጠይቃ መረጃ ይዛበታለች፤ ድምፁን ሁሉ በስልክ ቀድታዋለች፤ እሱ እራሱ ድርጊቱን ከማፈር ይልቅ በግልፅ ተናግሮታል፡፡

ቁምነገር፡-ምን ብሎ? ወ/ሮ ተናኜ፡- ያው አንደሚታወቀው የብሎኬት ማምረቻ

አለው፡፡ በተያያዘ የመንግስት ቤቶች አጀንሲ ጨረታ አሸንፌ ግን ብሩን ሊለቁልኝ አልቻሉም፡፡ እዚህ ያሉት ሰዎች ጉቦ ካልሰጠኸን ብለው እንቢ ስላልኳቸው ገንዘቤን ሊያስቀሩብኝ ሲሉ ገንዘቤን ለማግኘት ስል እዛ የምትሰራና ልታስለቅቅልኝየምትችል ልጅ ይዤ በተደጋጋሚ በማደር ላስለቅቅ ቻልኩ ብሎ የተናገረ ሰው ነው ፡፡ ይሄ እኮ የሚገርም አይደለም፡፡ ኮንዶም፣ የሴቶች ልብሶች ምን የቀረ ነገር አለ መኪናው ውስጥ አግኝታበታለች፡፡ ለሽማግሌዎች እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከተናገረች በኋላ ከዚህ በኋላ ልጆቼን በሰላም ላሳድግ ብላ ነው ወደ ፍርድ ቤት የሄደችው፡፡

ቁምነገር፡- የእሱ ምላሽ ምን ነበር? ወ/ሮ ተናኜ፡- በተጋቡ በሁለተኛው አመት ሌሊት

የደበደባት ጊዜ ቤቱ ሄደን እያለ ‹‹ውሰዷት ልጃችሁን አልፈልጋትም›› ነበር ያለው፡፡ የዛን ጊዜ እንደውም አንድ ልጅ ወልዳ ሁለተኛውን ቅሪት ነበረች፡፡ ግን ውሰዷት እያለ ነበር ሲደነፋ የነበረው፡፡ ፍርድ ቤት ለፍቺ ተከሶ ሲቀርብ ግን ፍቺውን ለማክሸፍ ያላደረገው ጥረት የለም፤ አልሆን ሲለው ደግሞ እገላለሁ እያለ ሲዝት ነው የቆየው፡፡ ቁምነገር፡- ፍቺው በፍርድ ቤት ከፀደቀ በኋላ የንብረት ክፍፍሉስ?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ምንም የተከፋፈለችው ንብረት የለም፡፡ አልፈልግም በጤናዬ ብቻ መውጣት ነው የምፈልገው ነው ያለችው፡፡

ቁምነገር፡-ለልጆቹ ማሳደጊያስ? ወ/ሮ ተናኜ፡- የፍርድ ቤቱን ወረቀት ላሳይህ እችላለሁ፡፡

እኔ ይቅርብኝ ለልጆች ማሳደጊያ ግን ይስጠኝ በወር 50 ሺህ ብር ያገኛል ብላ በፍርድ ቤት ስታመለክት የምችለው በአንድ ልጅ 500 ብር ነው በየወሩ አንድ ሺህ ብር እሰጣለሁ ብሎ ነው የፀደቀለት፡፡ ለዚያውም ያንን አንድ ሺህ ብር በየወሩ አይሰጣትም ነበር፡፡

ቁምነገር፡- ራስ አምባ ሆቴል ጋር ያለው ቤት የእርሱ አለመሆኑ ለፀባቸው ምክንያት እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ፤ ፍሬህይወት የምታውቀው ነገር ነበር?

ወ/ሮ ተናኜ፡- እኔ ይሄንን አላቅውም፡፡ ቤቱ የሱ ይሁን የሌላ ሰው ይሁን እኛ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲያወራ ብቻ ነው የምናውቀው፡፡ ሰውየው ለነገሩ የማይቀጥፈው ነገር የለም፡፡ ከዚህ በፊትም ወደዚህ ወደ ሲኤምሲ አካባቢ የሚያሰራ ህንፃ አጠገብ መኪናውን አቁሞ ፎቶ በማስነሳት እዚህ እኛ ጋር አምጥቶ በማሳየት ይህ ህንፃ የኔ ነው በቅርቡ ጨርሼው ወደ እዛ ቤት እንገባለን እያለ ይነግረን ነበር፡፡ በኋላ ግን ህንፃው የእሱ አለመሆኑንደርሰንበታል፡፡ የተባለውም ቤት የሱ ይሁን አይሁን የምታውቀው ነገር የለም፡፡ ህዝብና መንግስት ረድተውን ካላጣሩልን በስተቀር አናውቅም፡፡

ቁምነገር፡- ከፍቺ በኋላ ፍሬህይወት ምን ትሰራ ነበር? ወ/ሮ ተናኜ፡- አንድ ትንሽ የጉዞ ወኪል ድርጅት ገና

በማቋቋም ላይ ነበረች፡፡ ንግድ ፈቃድ አውጥታቢሮ ገና እያደረጀች ነበር፡፡ ልጆቿ ከሌሎች ልጆች እንዳያንሱ በትምህርታቸውም በልብሳቸውን ለመቻል እሷ ቀን ሙሉ ፆሟን እየዋለች ነበር እራሷን ለመቻል ደፋ ቀና የምትለው፡፡ ቁምነገር፡- ቅዳሜ ቅዳሜ ልጆቹን የሚወስደው ከየት ነው? ወ/ሮ ተናኜ፡- ከዚህ ከኛ ቤት ነው የሚወስዳቸው፡፡ ቀኑን ሙሉ አጫውቶ የሚመልሰው እዚህ ነው፡፡ እሷ ተከራይታ ነው የምትኖረው፡፡ ከተፋቱ በኋላ ልታገኘው ስለማትፈልግ ከሁለት ሰዓት በፊት በጠዋት አምጥታቸው ቶሎ ነው የምትሄደው፡፡ ማታም መጀመሪያ መምጣቱን በስልክ አረጋግጣ ነበር መጥታ የምትወስዳቸው፡፡

ቁምነገር፡- በስልክ አይገናኙም ነበር? ወ/ሮ ተናኜ፡- ፈፅሞ አይገናኙም፤ ከፍቺ በኋላ አንድ

አመት ከስድስት ወር ስልኩንም አንስታ አታውቅም፤ አታናግረውም፡፡ ልጆቿን ግን ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት ወስዷቸው ይመልስ ነበር፡፡

ቁምነገር፡- ከግድያው ቀን በፊት የግድያ ዛቻ በደብዳቤ ፅፎ ልኮ እንደነበር ሰምቻለሁ፤ ምንድን ነው?

ወ/ሮ ተናኜ፡- በቃሉ በተደጋጋሚ ሲዝት ነበር፡፡ እንደውም የእሷን ታናሽ ወንድም እዚህ አፍሪካ ዳቦ ቤት ጋር ደውሎ ጠርቶት አንድ ጥይት ይበቃታል ንገራት ብሎት ነበር፡፡ ይህንን ስንሰማ ምስክሮች ይዘን በመሄድ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተን ነበር፡፡ ያው ምን እንደተባለ አናውቅም ተለቀቀ፡፡ ከግድያው አንድ ሳምንት በፊት ደግሞ ልጆቹን ወስዶ አጫውቶ ሲመልሳቸው የአንድ ዓመት ወንዱ ልጅ ኪስ ውስጥ ደብዳቤ ፅፎ አስቀምጦ ነበር፡፡ ያንን ወረቀት ያገኘነው ከቀብር በኋላ ቤት ውስጥ ያሉትን ልብሶች ለማጠብ ስናገላብጥ ነው፡፡ እሷም የዛን ዕለት የልጆቿን ልብስ ኪስ በደንብ ስላልፈተሸች ነው እንጂ ዛቻውን ልኮላት ነበር፡፡

ቁምነገር፡-ደብዳቤው ምንድን ነበር የሚለው? ወ/ሮ ተናኜ፡- በቀደም ዕለት ‹‹ልጆቹን ከትምህርት ቤት

ልትወስጂ የሄድሽ ጊዜ ግንባርሽን ብዬ ልደፋሽ ነበር ግን፤ ከዛ የተሻለ ሌላ መንገድ ስላለ ጠብቂ ነው›› የሚለው፡፡ (ለቅሶ) የገደላት ዕለትም ለጓደኛው ፃፈ የተባለ ደብዳቤው ከኪሱ ውስጥ መገኘቱን ፖሊስ ተናግሯል፡፡ እዚህ ላይ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብየምጠይቀው ነገር በእግዚአብሔር ስም ይህቺን የ29 ዓመት የልጆች እናት በክላሽንኮፍ ጠመንጃ በአደባባይ በጠራራ ፀሐይ መንግስትና ህዝብ ባለበት ሀገር በግፍ በገደላት ሰው ላይ ፍትህ እንዲሰጥ ነው፡፡ ሴት ልጅ እናት ነች፣ እህት ነች ፣ ሀገር ነች፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ለመንግስት ጩሀቴን እንዲያሰማልኝ በየሀይማኖቱ ስም ነው የምማፀነው፡፡(ለቅሶ)

ቁምነገር፡- አሉ የተባሉ ንብረቶችም ለማሳገድ ምን እያደረጋችሁ ነው?

ወ/ሮ ተናኜ ፡- እውነት ለመናገር በዚህ በኩል ምን ማድረግ እንዳለብንና የት መሄድ እነዳለብን ገና አላውቅንም፤ ሀዘን ላይ ነው የከረምነው፤ ብሎኬት ማምረቻ የተባለውንም ወደ 20 ክፍሎች ያሉት ቤት፤ መኪናዎችም አሉ የተባሉት ለልጆቿ ማሳደጊያ ሊሆን ስለሚችል በህግ አግባብ በኩል ምን

ማድረግ እንዳለብን ሙያው ያላቸው ወገኖች ቢረዱንን እንዲተባበሩን በሴት ል ጆ ቻ ቸ ው አ ም ላ ክ በእህቶቻቸውና በእናቶቻቸው ስም እለምናለው፡፡ ማንም የሚወዳት ሴት ልጅ ያለው ሁሉ ይተባበረን ነው የምለው ፡ ፡ ቁምነገር፡- በእርሶ በኩል ግን ለእንደዚህ አይነት ግድያ የሚያበቃ የከረረ ፀብ ወይም ምክንያት ብለው የሚገምቱት ነገር ምንድን ነው?

ወ/ሮ ተናኜ፡- ምቀኝነት ነው፤ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ከሱ ከተለያየች በኋላ የሱ ሀሳብ ከነልጆቿ ሲርባት ተመልሳ ከእግሬ ላይ ወድቃ ቤት ትገባለች ነበር፡፡ ቢያይ አልሆነም፤ አሁን ራሷን ለመቻል ትንሽ ሱቅ ብጤ የትኬት ቢሮ ለመክፈት ደፋ ቀና ስትል ለምን እራሷን ለመቻል ትሮጣለች ነው፤ የትኬት ቢሮዋ እኮ ደግሞ ብታያት ገና ምንም ነገር ስራ ያልተጀመረበት ነው፤ የአየር መንገድ ትኬት የሚሸጥ ሰው በደንብ ስራን ያውቀዋል፤ ከተገኘም ከአንድ ትኬት ስለሚገኘው ብር ለዚያውም ትኬት የሚገዛ ሰው ከመጣ ነው፤ ለምን ይሄንን ከፈተች ነው የሱ ሃሳብ፤ ከዚህ ውጪ ይሄ ነው የሚለው ምክንያት አይታየኝም ፡፡ ምክንያቱም ከተፋታች በኋላ እንኳን አምስት ሳንቲም አልጠየቀችውም፡፡ ለልጆቿ በየወሩ ተቆራጭ መስጠት ያለበትን ብር ሲያስቀር እንኳን ለምን አትለውም፡፡ አሁን ልጆቿን ለማሳደግ ቀና ደፋ ስትል ቅናት አላስቀምጥ አለው፡፡ የሱ ሃሳብማ ድሃ ሆና እንድትኖር ነው፡፡

ቁምነገር፡- እርስዎስ ጤናዎት እንዴት ነው? ወ/ሮ ተናኜ፡- ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ተርፌያለሁ ልጄን ግን ገደላት፡፡

ቁምነገር፡- ከእርሶ ሌላ የተጎዳ ሰው ነበር? ወ/ሮ ተናኜ፡- አዎ ሁለት መንገደኞች በጥይት

ተመትተዋል፡፡ እንደውም አንዱ ሰውዬ በጣም ተጎድተዋል ተብሏል፡፡ መንገድ ላይ የነበረ የ10 ዓመት ልጅም ተመትቷል፡፡

ቁምነገር፡- በመጨረሻ የሚገልፁት ነገር ካለ? ወ/ሮ ተናኜ፡- በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ላይ ቅሬታ

አለን፡፡ እኛ በልጃችን ሞት ሳቢያ ሀዘኑ የእግር እሳት ሆኖብን ሳለ ሃሰተኛ መረጃ ለህብረሰቡ ያሰራጩብን ጋዜጦችና መፅሔቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቆንጆ መፅሔት ንብረት ተካፍላለች ከሱ በኋላ ልጅ ወልዳለች እያሉ ያቀረቡት ዘገባ መላ ቤተሰቡን አሳዝኗል፡፡ መረጃውን መጥተው ጠይቀው አረጋግጠው መዘገብ ሲገባቸው ያልሆነ አሉባልታ ይዘው በመውጣት ህብረተሰቡን ማደናገራችን ትክክል አይደለም፡፡ እኛ ልጃችንን አንድ ጊዜ በግፍ ተነጥቀናል፤ ዳግመኛ ታሪኳ መበላሸት የለበትም፤ ብለን እንዲያርሙ ስንጠይቃቸው የሚያርሙበት መንገድ የሚያሳዝን ነው፡፡ ሴት ልጅ እንደ ወንድ ልጅ አይደለችም፡፡ ወንድ በድብቅ ወልዶ ልጅ ሊያመጣ ይችላል፤ ሴት ልጅ ግን ሰው ሳያያት ልታረግዝነና ልትወልድ አትችልም፡፡ ከሆነም ወለደች የሚሉትን አምጥተው ቢያሳዩን ጥሩ ነው ፡ ፡አልሆነም እንጂ ከዚያ ውጪ ከተፋታች በኋላ ብትወልድስ ችግሩ ምንድንነው፡፡ ስለዚህ ሚዲያዎችን እባካችሁ ስለ ሴት ልጅ ብላችሁ እውነታን አታዛቡ ጠይቃችሁ ፃፉ ነው የምለው፡፡ በማንኛውም መልኩ የልጃችንን ሀዘን ሊካፈሉንና በህግም በኩል ሊረዱን የሚፈልጉ ሁሉ በ0911693061 ሊያገኙኝ ይችላሉ፡፡

ቁምነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

ሚኪያስ.... ከገጽ 4 የዞረ

ጀምረው ጓደኛሞች ሆነው ፍቅርን ያሳለፉ የነበሩ ጓደኛሞች ዛሬ ችግር ሲደርስበት የት ነበሩ መንገድ ላይ ሲገጭስ የተገጨበትን መኪና ለምን አልገለጹም ወይንም ከገደሉት ምክንያቱን አላሳወቁም የሆነ ያደረጉት ነገር እንዳለ እና በ እነርሱ ውስጥ ብቻ የተቀበረ ሚስጥር አለ ሲወድቅ ካዩት 911 ወይንም ለወላጅ አባቱ እንዲህ ሆነ ብለው ለምን አልገለጹለትም ሌሎች ሰዎች የመጀመሪያ እርዳታ እንደሰጡት እና ከዚያም ፖሊስ መጥቶ ወደ ሆስፒታል መውሰዱን ነው የሰማሁት ይህ ከበስተጀርባው ነገር አለ ! በማለት የውስጣዊ ጥርጣሬዋን አጋርታናለች ።

የሳምንቱ የልብ ስብራታችን አሁንም ከ እርሱው ጋር አብሮ ይጓዛል ዝም የሚል አንደበት አይኖረንም ፣አዎ ሚኪያስ የሃገር የህዝብ የቤተሰብ እንዲሁም የራሱ መኩሪያ እና ተስፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ታላቅ ተማሪ እንደነበር አጠቃላይ የቺካጎም ህዝብ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ መምህራን ተማሪዎች እና ስተዳደር ሰራተኞች በቀብሩ ስነስርአት ወቅት ገልጸውልኛል የመጨረሻው ስኬት ግን የጨለማው ጉዞ የህይወቱ ፍጻሜ መሆኑ ቅጭታችንን ይብስ ወደ ማንነት ጥያቄ ወስዶብናል ስለሆነም ይህንን ምላሽ እንሻለን እንላለን !የዘሃበሻ እና የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ዝግጅት ክፍል በቦታው ተገኝተው ያደረጉትን ጥንቅር ወደፊትም ለማቅረብ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ .. .. .. በዚህ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይቀርባል ተብሎ የታሰበውን ታክስኮሎጂ ወይንም የአሻራ ምርመራ ውጤት በጥንቃቄ መጠበቅ እና የመጨረሻውን ውጤት ማየት የሁላችንም ጉጉት ነው በእርግጥም ይህንን ጉዳይ የያዘው የሸምበርግ የወንጀል ምርመራ ክፍል ለመገናኛ ብዙሃን ምንም ነገር ለመግለጽ እንደማይፈልግ በቺካጎ ሰን ታይምስ ላይ የቀረበው ሪፖርት ሲያሳይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ልጁ አስፓልት ላይ ተኝቶ ነው የተገጨው ብለው የሰጡትም መረጃ መገናኛ ብዙሃኖችን ሊያሳምን አለመቻሉ ይባሱኑ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲከታቸው አድርጓል ስለዚህ ወላጅ አባቱ ዶ/ር ተፈራ እንደገለጹት እኛም ህብረታችንን ወደ አንድ አቅጣጫ መልሰን ጉዳዩን ትኩረት እንዲሰጥበት አብረን እጅ ለ እጅ ተያይዘን እንጓዝ እላለሁ “ፍርድ ነጻ ፍትህ እያልን ጩኸታችንን እናሰማ ዘንድ “ለዚህም ደግሞ ከዚህ ቀደም በሚኒያፖሊስ በአንዲት ወጣት ላይ የደረሰውን የመኪና አደጋ አስመልክቶ ወላጅ አባቷ ያቀረቡትን ሪፖርት እንዳስታውስ እና የተደረገውን ካምፒየን ምን ይመስል እንደነበር ረድቶኛል ያም በአካባቢው የነበሩትን ህብረተብ አንድነት እና ህብረት አጉልቶ ያሳየ ኢትዮጵያዊነታችን የተንጸባረቀበት ስለሆነ ዛሬም በመላው ሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን ኢትዮጵያኖች ለዚህ ጥሪ ሁላችሁም ምላሻችሁን ትሰጠ ዘንድ ከመተማመን ጋር ነው ። ለዚህም የመጨረሻውን የምርመራ ውጤት ማወቅ አስፈላጊ ነውና ሁላችንም መጠበቅ መልካም ነው ።

Page 10: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

መብት የተሰኘው አምዳችን በአሜሪካን ሃገር እየኖርን ሕግን ሳናውቅ ብዙ ነገሮችን ለምናጣ ወገኖቻችን ትልቅ ትምህርት ሰጪ አምድ ነው። በአምዱ ላይ በአሜሪካ ሕጎች ዙሪያ ጥያቄዎቻችሁን ተቀብለን እዚሁ ከሚገኙ

የሕግ ባለሙያዎች መልስ እናሰጣችኋለን። ጥያቄዎቻችሁን ላኩልን።

ይህ አምድ በአሜሪካ የኢትዮጵያውያንን ኑሮ በትዝብት መልክ አቅርቦ እንደንማማርበት ታስቦ የተከፈተ ነው። ሁሉም የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አንባቢ በዚህ አምድ ላይ ትዝብቱን ማስፈር ይችላል። ታዲያ ትዝብቱ መስተማርን አንግቦ ቢቀርብ ለኮምዩኒቲያችን ትልቅ ትምህርትን ይሰጣል ብለን እናምናለን። ተሳተፉበት።

ከናዖድ ቤተ-ሥላሴ (naodlive.com)

ልጄ ሰሞኑን ያልተለመደ ጠባይ ማሳየት ጀመረ፡፡ ብቻውን አይተኛም፤ ብቻውን አያነብም፤ ብቻውን አይቀመጥም፤ እራት ለመብላት ሲቀመጥ እንኳን እግሩን ወንበሩ ላይ ሰቅሎ ነው (እግሩ ስር አውሬ ያለ ይመስል)፡፡ በጣም ለየት ያው ጠባይ ደግሞ፤ወደ መኝታ ክፍሉ የሚሄድበት ሩጫ ው፡፡ ወደ መኝታ ክፍሉ ሲሄድ ዌይም ከመጭታቤቱ ወደ ሳሎን ሲመጣ በፈጣን ሩጫ ነው፡፡ በሩጫው ወቅትም፤ አልፎት የሚሄደውን የእኛን መኝታቤት ዞር ብሎም አያይም፡፡…ነገሩ ከእኛ መኝታ ቤት ጋር የተያያዘ አንደሆነም የጠረጠርኩት ያኔ ነው፡፡

‹‹are you OK?›› አልኩትና ወደ ነገሩ ገባሁ፡፡ እርሱም ያለ ብዙ ማንገራገር፤ ሰሞኑን ማይክል ጃክሰን ፈርቶ ሊሞት እንደሆነ ነገረኝ፡፡ የማይክል ጃክሰንን ስም ሲጠራ፤

ልክ ማይክል ጃክሰን የሚሰማው ይመስል እየተገላመጠ፤ በሹክሹክታ ነው፡፡ ነገሩን ምን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ ቢሆንም ተናግሮ ይቅለለው ብዬ ማይክል ምንያስፈራል፤ እንደውም Moon walk ዳንስ የሚደንሰው እርሱ ነው ብዬ፤ የማይክልን ‹‹ቢል ጂን›› ዘፈን፤ ከYoutube ላይ አውጥቼ በቴሌቭዢን አዘፈንኩላቸው፡፡ ትልቁ ልጄ የማይክልን Moon walk ዳንስ እያደነቀ ሲመራመር፤ ትንሹ ግን አሁንም መረበሹን አላቆመም፡፡

Dad! Did he eat you leg? ትንሹ ልጄ ‹‹ማይክል ጃከሰን እኮ Werewolf /ዌር ዎልፍ/ ነው››

አለኝ፡፡ ዌር ዎልፍ ማለት በሀበሻኛ ጭራቅ ማለት ነው፡፡ ልጄ፤ ቀን ይውልባት የነበረችው ሞግዚቱ ቤት፤የማይክልን ጃክሰንን Thriller ዘፈን አይቶ ኖሮ፤ ትዕይንቱ በአዕምሮው እየመጣ ነው የሚያስጨንቀው፡፡

‹‹ማይክል ሞቷል እኮ›› አልኩት፡፡ ‹‹No! እናንተ መኝታ ቤት አለ›› አለኝ ‹‹የት ቦታ›› አልኩት ‹‹አልጋችሁ ስር›› አለኝ፡፡ እስኪ እንየው ብዬ ይዤው ሄድኩኝ፡፡ እየተንቀጠቀጠ ተከተለኝ፡፡ እኔም ድፍረት የሚሰጠው መስሎኝ፡፡ ‹‹ተመልከት!

አልጋ ስር ምንም የለም›› ብዬ እግሬን ወደ አልጋው ስር ሰደድኩ፡፡ እግሬ ከአልጋው ደጋፊ እንጨት ጋር ተላተመ፤ ልጄ የኳኳታ ድምጹን ሲሰማ፤ ዓይኑ በእንባ ተሞላ፡፡

‹‹Dad! Did he eat you leg›› አለኝ፡፡ ‹‹አይ አልበላኝም›› አልኩት፡፡ ሙከራዬ፤ ነገሩ የበለጠ እንዳስጨነቀው ስለገባኝ፤ ትልቁን ልጄን ጠራሁና በአጽናኝነት ከጎኑ እንዲሆን አደረኩት፡፡ ከዚያ የአልጋውን ፍራሽ አንስቼ፤ የአልጋው ስር ባዶ እንደሆነ አሳየሁት፡፡ ትንሹ ልጄ ተደንቆ ሊሞት ደረሰ፡፡ ‹‹እንዴ ማይክል የለም!›› አለ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን ፍርሀቱ ተመለሰ፡፡ ‹‹አሁንስ ምን አስፈራህ?›› አልኩት፡፡ ‹‹ማይክል creepy ክሪፒ /ሾላካ/አስፈሪ/ ነው፡፡ የልብስ መሳቢያዎች ውስጥ ሁሉ ሊደበቅ ይችላል›› አለኝ፡፡ በዚህ ዓይነት ቤቱን ማፈራረስ መጀመሬ እንደሆነ ስለገባኝ፤ ሌላ ዘዴ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እናም…ከዘመናት ጀምሮ፤ ጭራቅን፤ ሰይጣንን፤ ወዘተ ከህልማችንም ከሀሳባችንም ሲያባርሩልን ወደኖሩት ሌላ ስውራን መላዎቻችን ዞርኩ፡፡ ወደ መላዕክት፡፡

ማይክል ጃክሰንን በቅዱስ ሚካኤል ልጆቼ፤ ከእመቤታችንን ጋር ለየት ያለ ዝምድና እና ትውውቅ እንዳላቸው ስለማውቅ፤ ወደ ስዕሏ ወሰድኩና ከእመቤታችን ስዕል ጋር ወዳሉት የመላዕክት ስዕል አሳየኋቸው፡፡ እናም እንዲህ አልኳቸው፡፡ በአጭሩ፡፡ ‹‹እመቤታችን፤ ልጅ አቅፋ አይደለም የምታዩዋት፤ ልጅ በጣም

ስለምትወድ ነው፡፡ እና ልጆችን ዌር ዎልፍ ሲያስፈራቸው፤ አጠገቧ ያሉትን መላዕክቶች፤ ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርዔልን ትልካቸውና ዌር ዎልፍን ይገድሉታል›› አልኳቸው፡፡

ልጄ ታዲያ ‹‹ዌር ዎልፍ እኮ አደገኛ ነው፤ ሁለት መላዕክትማ አይችሉትም›› አለኝ፡፡ እኔም መላእክት የሚያሸንፉበትን መላ ማስረዳት ቀጠልኩ፡፡ ‹‹ሁለቱ መላዕክት እኮ አለቆች ናቸው፡፡ ስንተ ወታደሮች

እንዳላቸው ታውቃለህ! አንድ ሚሊዬን›› አልኩት፡፡ ‹‹wow!›› አለ፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ፊቱ በፈገግታ ሲፈነዳ አየሁት፡፡ ማጠናከሪያዬን ታሪክ ቀጠልኩ፡፡ ‹‹ልጆች እንቅልፍ ሲተኙ፤ እመቤታችን አንድ ሚሊዬን መላዕክት ትልካለች፡፡ ልጆች

ሲፈሩ ደግሞ ሁለት ሚሊዬን መላዕክት ትልካለች፡፡ ልጆች በጣም ሲፈሩ ደግሞ 100 ሚሊዬን መላዕክት ልካ፤ ዌር ዎልፍን ድምጥማጡን ታጠፋለች›› አልኩት፡፡ (ማይክል ጃክሰን.... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

አዎ!! ሰሞኑን ይፋ የሆነው የዲቪ ዜና አስደንጋጭ የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ዲቪ አከተመለት፣ በሩ ተዘጋ ከሚሉት ጀምሮ በሂደት ጉዳያቸውን እያንቀሳቀሱ ያሉት እድለኞች ስጋት ገብቷቸዋል። ጉዳያቸው የተጨናገፈ ያህል ተስፋ የቆረጡም አሉ። በተለይም ዜናውን ተከትሎ በተለያዩ ድረገጾች ዜናውን ለመቀባበልና ላልሰማ ለማሰማት የነበረው ውክቢያ ፈጣን ነበር። የ“ዲቪ ቀረ” ወሬ ያዲስ ዓመት ርችት መስሎ ሞገዱን አጣቦ ከርሟል። ደግነቱ እንዲጸድቅ የተጠየቀው ህግ ዲቪ የደረሳቸውንና አሜሪካ የገቡትን ከነቤተሰቦቻቸው የሚመለከት አለመሆኑ እንጂ ከዚህም በላይ በሆነ ነበር። ይህን ሁሉ እንድናነሳ ያደረገን ሰሞኑን ከአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት ዲቪን አስመልክቶ የተላለፈውን የውሳኔ ሃሳብ ተከትሎ በበርካታ ኢትዮጵያውያን አዋጅ በአዋጅ ሳይሻር፣ ነባር ህግ በአዲስ ህግ መተካቱ ይፋ ሳይሆን “ዲቪ

ቀርቷል” የሚያሰኝ ድምዳሜ ላይ የመደረሱ ጉዳይ ነው። ሁለት ዓስርተ ዓመታትን ሊያስቆጥር ጥቂት የቀረው

የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራም በመጀመሪያ ሕግ ሆኖ ሲወጣ የነበረው ዓላማ በአሜሪካ ውስጥ የስደተኛ ቁጥራቸው ጥቂት ለሆኑ አገሮች የቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ በመስጠት የተመጣጠነ የኢሚግሬሽን ሥርዓት ለመከተል ነበር፡፡ ገና ከጅምሩ እጅግ በርካታ መላምቶችና ነቀፋዎች የተሰጡበት ይኸው ፕሮግራም እስካሁን ቀጥሎ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ አሜሪካ በፈቃዳቸው አንዳንዶችም እጅግ ውድ ዋጋ ከፍለው እየተጋዙበት ይገኛሉ፡፡ ለተሻለ ኑሮ!!

የዲቪ ሎተሪ እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1995 ሲጀመር ለ55ሺህ ሰዎች ከዓለም ዙሪያ የመኖሪያ ፈቃድ በመስጠት ሲሆን ከ1999 ዓም ጀምሮ 5ሺህው ቪዛ ናካራ

(NACARA) ተብሎ በሚጠራው ህግ መሠረት ኒካራጓውያን፣ ኩባውያን፣ ጓቴማላውያን እና ከቀድሞ የሶቪየት አገራት ለሚመጡ ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዲውል በመደረጉ የዲቪ አጠቃላይ ቁጥር ወደ 50ሺህ ዝቅ ብሏል፡፡

ይህም ሆኖ በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ የዲቪ ፕሮግራም ኢትዮጵያው በብዛት እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ከአፍሪካ ውስጥ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የቪዛ ቁጥር የሚበልጠው የናይጄሪያውያኑ ብቻ ነው፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት መረጃ እንደሚጠቁመው ከ1995 እስከ 2012 ድረስ ከኢትዮጵያ ብቻ ወደ 61ሺህ ሰባት መቶ ለሚጠጉ እድለኞች የዲቪ ሎተሪው የወጣላቸው ሲሆን፣

63ሺህ ስድስት መቶ ደግሞ ለናይጄሪያውያን ተሰጥቷል፡፡ ከናይጄሪያና ኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ጋና በእነዚሁ ዓመታት 41ሺህ ስድስት መቶ አካባቢ ቪዛ አግኝታለች፡፡ ዝቅተኛ ከሚባሉት መካከል የኢኳቶሪያል ጊኒ ሲሆ በእነዚህ 17ዓመታት ውስጥ 30ቪዛ አግኝታለች፡፡

በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ህግ ተሃድሶ እንደሚያሻው በየምርጫውና የምክርቤት ስብሰባ ላይ ከፍተኛ ክርክር የሚያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ህጉ እድሳት እንዲደረግለት የሚፈልጉት ፖለቲከኞች ከበስተጀርባው የፓርቲያቸውን የፖለቲካ ዓላማ የማስፈጸም ተግባር ስለሚያስቀድሙ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ተጠቃሚ ከመርዳት አኳያ እስካሁን ይህን ነው የሚባል ለውጥ አልመጣም፡፡

ባራክ ኦባማ የዛሬ አራት ዓመት ሥልጣን በያዙበት ወቅት በምርጫ ዘመቻቸው የኢሚግሬሽንን ህግ እንደሚያሻሽሉ

ቃል ቢገቡም እስካሁን ግን ምንም የመጣ ለውጥ የለም፡፡ በዚሁ የኢሚግሬሽን ህግ ላይ ተሃድሶ በማምጣት የአብዛኛውን ላቲን አሜሪካ ተወላጅ ልብ ለመሳብ የሚፈልጉት ሪፓብሊካውያኑም በዚህ ጉዳይ ላይ አልተኙም፡፡ ባለፈው ዓመት የመስከረም ወር በቴክሳሱ የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወካይ ላማር ስሚዝ ወደ መድረክ የመጣው ይህ ረቂቅ ህግ ብዙም ሳይገፋ ወዲያው ነበር ወደ መቃብር የወረደው፡፡ ተወካዩ ያቀረቡት

ረቂቅ ሕግ H.R. 6429: STEM Jobs

Act of 2012 የሚባል ሲሆን ዋንኛ ዓላማውም በየዓመቱ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና

እና ሒሳብ የትምህርት ዘርፎች ለሚመረቁ ስደተኞች በየዓመቱ 55ሺህ የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ) በመስጠት አሜሪካ እንዲቀሩ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ሲሆን በየዓመቱ በዲቪ ፕሮግራም የሚሰጠው ቪዛ እንዲቀር በረቂቅ ሕጉ ላይ አብሮ ጥያቄው ቀርቧል፡፡ ረቂቅ ሕጉ በባችለር ዲግሪ ስለሚመረቁም ሌሎች መዘርዝሮችን አካትቷል፡፡

በአሜሪካ የፕሬዚዳንታዊ፣ የተወካዮችና የሕግ መወሰኛ ምክርቤት ምርጫ በተጠናቀቀ ወቅት የፕሬዚዳንትነትንና የሕግ መወሰኛ ም/ቤትን መቆጣጠር ያቃታቸው ሪፓብሊካኑ የተወካዮች ም/ቤትን በአብላጫው የሚቆጣጠሩ በመሆኑ ባለፈው ሳምንት ረቂቅ ሕጉ እንደገና ተነስቶ በ245 ድጋፍ 139 ተቃውሞና 48 ድምጸተዓቅቦ በተወካዮች ም/ቤት እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡

ለረቂቅ ሕጉ ድጋፍ ከሰጡት ከ245 መካከል 27ቱ ብቻ ናቸው የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካዮች፤ ከተቃወሙት መካከል ደግሞ 5ቱ ብቻ የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወካዮች ናቸው፡፡ በአሜሪካ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መሠረት ረቂቅ ሕጉ በሥራ ላይ ለመዋል ዴሞክራቶች በአብላጫው በሚቆጣጠሩት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት (ሴኔት) ቀርቦ መጽደቅ አለበት፡፡ ከዚያም ፕሬዚዳንቱ ፊርማቸውን ሲያኖሩበት በተግባር መዋል ይጀምራል፡፡ እነዚህን ሁለት ከፍተኛ መስናክሎች የማለፍ ግዴታ የሚጠብቀው ይህ ረቂቅ ሕግ ዴሞክራቶች በሚቆጣ ጠሩት የህግ መወሰኛ ም/ቤት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚገጥ መው ይጠበቃል፡፡ (ዲቪ.... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

የDNA ምርምር ሲሳሳት፤ የሰው ጆሮ አይጥ ላይ ያበቅላል

የዲቪ ሎተሪ እድለኛ ነው። ባገኘው እድል መሰረት አሜሪካ ለመግባት ማሟላት የሚገባውን ሁሉ እያከናወነ ይገኛል። በአካል አዲስ አበባ፣ በሃሳብ አሜሪካ ያለው ወጣት ስራውን በገዛ ፈቃዱ ተሰናብቷል። እቃውን ለሚወዳቸው ማከፋፈል ጀምሯል። አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍሮ የብስና ውቂያኖስ አልሰነጠቀም እንጂ በምኞት በየቀኑ በረራ ያደርጋል። አሜሪካ!!

“ማርና ወተት የምታፈሰው አሜሪካ እንደገባሁ” እያለ ቃል የሚገባላቸው ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ ስንቅ እያዘጋጁለት ነው። ስጦታ ያበረከቱለትና ድንገት ካልተገናኘን በማለት የተሰናበቱት አሉ። እንዳኮበኮበ ያለው ወጣት ላሊበላ ሬስቶራንት ጫማ እያስጠረገ የአጭር የስልክ መልዕክት ይደርሰዋል። መልዕክቱ “ዲቪ ቀረ” የሚል ነበር። ወዲያው “ማን ነው ቀረ ያለው” ሲል መልሶ ጠየቀ። ደነገጠ። ብርክ ያዘው። ህልሙ፣ ውጥኑ ሁሉ ሲተን፣ ከእጁ ሲያመልጠው ታየው፡፡ ለተወሰነ ጊዜ መረጋጋት አቅቶት ነበር። ሌላም ሌላም … ይህንን ገጠመኝ ያገኘነው ከአንድ ወዳጃችን ነው።

Page 11: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ውለታ... ከገጽ 15 የዞረ

ጠባሳ (Trauma) ምንም አልተጨነቀም ነበር፡፡ በአንፃሩ ሌሎች አገራት ታዋቂ ሰዎቻቸውን የአርዓያነት ሚና

በኅብረተሰብ ውስጥ ስለሚያጫውቷቸው ለታዋቂ ሰዎቻቸው እንክብካቤያቸው የላቀ ነው፡፡ ከእነዚህ ታዋቂ ሰዎች ጀርባ ባሕላቸው፣ ቋንቋቸው፣ እሴታቸው እና ባንዲራቸው መኖሩን ለደቂቃ አይዘነጉትም፡፡ እንግሊዛውያን ከሼክስፒርም፣ ከቻርልስ

ዲከንስ-ም ሆነ ከእግር ኳስ ተጫዋቾቹ ቤካም እና ሩኒ ጀርባ ታላቋ እንግሊዝ መኖሯን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በተለይ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፡፡ እናም ለታዋቂ ሰዎቻቸው ይጠነቀቃሉ፡፡ የሰዎቻቸውን አያያዝ ያውቃሉ፡፡

በእንግሊዝ አገር ውስጥ ለጥበብ ሰዎቻቸው፣ ለጸሐፊዎቻቸው፣ ለጋዜጠኞቻቸው እና ለኅብረተሰቡ ምርምር ለሚያደርጉ ሰዎች በኑሮ ውጣ ውረድ ውስጥ ሰጥመው ለኅብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት እንዳይገቱ “አርት ሬዝደንስ” የተባለ ተቋማዊ አገልግሎት አላቸው፡፡ ቢታመሙ ያሳክሟቸዋል፣ ቢቸገሩ መፍትሄ ያመላክቷቸዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ የአገልግሎት ተቋም በለጋሽ ግለሰብ፣ ድርጅቶችና በመንግሥታዊ ድጎማ የሚንቀሳቀስ ሲሆን የሥራውን እቅድ አቅርቦ ተቀባይነት የሚያገኝ ጥበበኛ እንደ ተፈቀደለት ጊዜያት ለሁለት ሣምንት፣ ለወራት፣ ለአንድ ዓመት እና ለሁለት ዓመት ለኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ በተቋሙ ቀርቦለት የጥበብ ሱባዔ ይገባል ማለት ነው፡፡ እቅዱን ተግባራዊ እንዲያደርገው፡፡

አየህ ወዳጄ አርት ሬዝደንስ የተባሉት ተቋማት ጥበብን

የማዋለድ ሥራ ይሰራሉ፡፡ የዚህ ጸሐፊ ጓደኛም የሦስት ወር አገልግሎት ተሰጥቶት ተግባራዊ ማድረግ ተስኖት የነበረውን ጥበባዊ ክህሎቱን ባህር ተሻግሮ ተወጥቷል፡፡ ወደ እንግሊዝ የመብረሪያውን የአየር ትኬት፣ የምግብና የመኝታ አገልግሎቱን እና የቀን ተቀን የኪስ ገንዘቡን ሁሉ ሰጥተው ነበር በውስጡ የታመቀውን ኪነት ያዋለዱት፡፡

አስተውለህ ከተመለከትክ በአፍሪካ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቡርኪናፋሶ በመሳሰሉ አገራት ትልልቅ ፋውንዴሽን አሉ ለኅብረተሰባቸው አገልግሎት የሰጡ ሰዎች የህይወት ዕክል ሲገጥማቸው ሊያቃኗቸው የሚተጉበት፡፡ እዚህ የእኛ ሀገር ኢትዮጵያ ግን ምንም እንኳ የሦስት ሺህ ዓመት እንደ ሀገር የመቆም ታሪክ ቢኖረንም፣ ምንም እንኳ የቀደምት ሥልጣኔና ጥበብ ባለቤቶች ብንሆንም እንደ አንድ ኅብረተሰብ ገና በቅጡ አላደግንም፤ ገና ህፃን፡፡

በየዘርፉ ያገለገሉ አርዓያ ሰዎቻችንን የህይወት ውጣ ውረድ ሲገጥማቸው ቀና ልናደርጋቸው ከመጣር ይልቅ ቁልቁል ገደል ልንከታቸው እንረባረባለን፡፡ ታመው ከማሳከም ይልቅ ሞተው እናለቅስላቸዋለን፡፡ እንደ ልመንህ ታደሠ ያሉትን ወደ ሆስፒታል ወስደን ወደ ጤናቸው እና የመረጋጋት ህይወት ከመመለስ እና ብሄራዊ ክብራችንን ከመጠበቅ ይልቅ በጎዳና ከንፈር እንመጥላቸዋለን፡፡

አየህ ወዳጄ መፍትሄው እዚሁ ጉያችን ሥር አለ፤ የአእምሮ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች አሉ፣ በዘርፉ ስፔሻሊስት ሐኪሞቹ አሉ፣ መድሃኒቶች አሉ ነገር ግን ይህን አቀናጅቶ ለእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ አገልግሎት የሚሰጥ የተደራጀ ተቋም የለንም፡፡ እናም ያላደገ ኅብረተሰብ ነን ያልኩት ለዚህ

ነው፡፡ ያላደገ ኅብረተሰብ ያደጉ ግለሰቦቹን እንደ ድመት ካለማወቅ ወልዶ ይበላቸዋል፡፡

ስለዚህ ውጤቱ አንቺም- ዜሮ- ዜሮ፣ አንተም ዜሮ- ዜሮ፣ እርሱም ዜሮ ዜሮ፣ ሁላችንም ዜሮ ሆነ፡፡ ወዳጄ ታዋቂው ኢትዮጵያዊው ኮሜዲያን ልመንህ ታደሠ በአደባባይ ብቻውን ሲጋልብ በርቀት ይታየኛል፡፡ ለእርሱ የሰጠነውን ኅብረተሰባዊ ምላሽ የተመለከተ ዕጩ ጠቢብ በአገልግሎት መንፈስ ጥበብን ያጋራን ይመስልሃል? ይልቅ ጥበብን ይነግድብሃል!!

አሜሪካ... ከገጽ 13 የዞረ

በ2009 በአክራ ‹‹አሜሪካ ራዕዩን (መልካም አስተዳደርና ሰብአዊ መብት መከበርን) በቃላት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን አቅም ሊያጠናክር በሚገባ መልኩ የማሻሻልና ቅድሚያ የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡ በሞስኮ የዓለምአቀፋዊ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ሊከበሩ የሚገባበት ማስገደጃዎች ሊኖሩ እንደሚገባና እነዚህ ድንጋጌዎች መፋለስም እንደሌለባቸው በማሳሰብ ንግግር

አድረጌያለሁ፡፡›› ብለው ነበር፡፡ ታሪክ በሂደት ላይ ነው! ‹‹የኢትዮጵየዊያን ማግኒቲስኪ ሕግ›› ሊኖረን ተገቢ ነው፡፡ይህም ከወዳጆቻችንና አጋሮችቻን በምናገኘው ትንሽ ድጋፍ እውን ይሆናል! በትክክለኛው የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ጎን መቆም ማለት በትክክለኛው የታሪክ ጎን መቆም ማለት ነው፡፡

* ፕሮፌስር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሳን በርናርዲኆ የፖሊቲካ ሳይንስ መምሀርና የህግ ጠበቃ ናችው።

ቴዲ እና ጂጂ.... ከገጽ 18 የዞረ

ብዙ አቀንቅኗል። በተለይ ‘ዎር’ ፣ ‘ ጌት አፕ ስታንድ አፕ’ ፣ እና ‘ ዋን ላቭ’ በሚሉት ስራዎቹ ሚሊዮኖችን ከማነቃቃት አልፎ በአለም ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። በቦብ ማርሊ ስራዎች የተነሳሱ የሬጌ አቀንቃኞች ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሆነዋል።

ሙዚቃ በህብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ተጽእኖ እንዳለው በተለይ አንባገነን መሪዎች ጠንቅቀው ያውቁታል። በ1800ዎቹ ናፖሊዮን ንግስናውን ሲያውጅ በወቅቱ አንቱ የተባለው ሲንፎኒስት ቤትሆቨንን ሰስተኛ ስራ በቦናፓርት ስም እንዲወጣ አዞት ነበር። ቢቶቨን ግን ከህይወቱ ይልቅ ጥበቡን መርጦ አሻፈረኝ አለ:: አቶ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከትማ ከንቲባ በነበሩ ግዜም ከታፊ አርቲስቶችን ሰብስበው አርከበ የሚል አልበም እንዲለቁላቸው ጠይቀው ነበር። አርቲስቶቹ ግን እንቢም እሺም ሳይሉ እንዳመለጡ አጫውተውኛል። አርቲስቶቹ የተጠየቁትን ቢያደርጉ ኖሮ ህዝብ ዋጋ ያስከፍላቸው እንደነበር ማጤናቸውም ትልቅ ነገር ነው።

እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ ተለቆ የነበረው We shall overcome (እንወጣዋለን) የሚለው የአፍሪካ አሜሪካን የነጻነት መዝሙር በህዝብ አእምሮ ሰርጾ በመግባት ለጥቁሮች የነጻነት ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው።

ዛሬ እነ ጂጂ እነ ቴዲ ተስፋን ስለመሰነቅ አቀነቀኑ። ተስፋ ባለመቁረጥ ውስጥ ስለሚገኝ ጀግንነት። ተስፋ ያለው ሰው አይፈራም። የሚገድል ሳይሆን የማይፈራ ሁሉ ጀግና ነው።

'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!

Hours: 6:00am - 10:00pm Monday-Sunday Play Ground Nutritious Breakfast, Lunches, for kids Languages Spoken: English, Amharic, Oromo,

Somali & Arabic Excellence in Education &

Child Development

በተለያዩ ስታይሎች ተኩስና ሹሩባ እንሰራለን

የስፓ አገልግሎታችን ልዩ ነው ሙሽራ እንሞሽራለን

የፀጉር ቀለም፣ ቁርጥ፣ ጸጉር መቀጠልና ሌሎችም አገልግሎቶች አሉን

ፀጉር የውበት አክሊል ነውና

ወደ ግሎባል ሳሎን በመምጣት ተውበው ይሂዱ

Global Braids Salon፡ 1821 University Ave, Suit 130 St. Paul, MN 551004 651-646-5854

Page 12: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ትልቁን የMoroccan Oil ሻምፖና

ኮንዲሽነር ከገዙ

Moroccan Oil ለሚገዙ

Bouncy

Cream Large

Nairobi Products

አሜሪካ... ከገጽ 5 የዞረ

(1) ዴሞክራሲውን የሚያግዙ እና የዴሞክራሲ መዋቅሮችን፤ ነጻ፤ ፍትሃዊና ግልጽ ምርጫዎችን የሚያጠናክሩ፤ (2) የአፍሪካን እድገት ልማት የሚያግዝ፤ (3) ግጭቶችን መከላከል፤ ማቅለል እና ውሳኔዎችን ማስፈጸም (4)ፕሬዜዳንታዊ ጅማሮዎችን እንደ ዓለም አቀፍ የጤና ጅማሮዎችን መደገፍ፤የወደፊቱን መመገብ፤ዓለም አቀፍ የዓየር ንብረትን ጅማሮዎችን መደገፍ (5) ከአፍሪካ ሃገርና ሕዝብ ጋር በሽግግር ሂደቶች ላይ እንደ አደንዛዥ እጽ ቁጥጥርን፤ ሕግ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን፤ የሰዎች ሽያጭን›› ያካትታል:: እንደ ካርሰን አባባል ‹‹በአሁኑ ወቅት›› የዩ ኤስ ፖሊሲ በአፍሪካ በኮት ዲ ቩዋር በጊኒ፤በናይጄር፤መንግስታዊ ሰላማዊ ሽግግሮችን ረድቷል፡፡በናይጄርያ የተሳካ ምርጫ እንዲካሄድ አድርጓል፤የደቡብ ሱዳንን ነጻነት አረጋግጧል፡፡ በዴሞክራቲክ ኮንጎም የጾታንና የወሲባዊን ሁከቶችን ለማቆም በንቃት በመንቀሳቀስ ላይና በመካከለኛው አፍሪካ በመላው በመንቀሳቀስ ላይ ያለውን የሎርድ ሬዚስታነስ ሠራዊት ለማክሸፍም በጽናት በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ የወደፊቱን መመገብ የሚለው የዩ ኤስ ዓለም አቀፋዊ የምግብ ዋስትና ጅማሮ 12 የአፍሪካ ሃገራትን ያካትታል፡፡

የዩ ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት የሰብአዊ መብት ዘገባ (ሜይ 2012) የሂላሪ ክሊንተን ገለጻ፡ “እንደሃገር አስተዳደሪነቴ በዓለም ዙርያ ባደረግሁት ጉዞ የሰብአዊ መብትን ለማስከበርና የፍትሕና ስርአት ለማስከበር ሲሉ የራሳቸውን ሕይወት ለአደጋ

ያጋለጡ በርካታ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ በትልቁም ይሁን መጠኑ ባነሰ መልክ መንግስቶቻቸውን ተጠያቂ እንዲሆንና ለዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ድንጋጌ ተገዢነት ይሞግታሉ፤ ቆራጥነታቸውና ድፍረታቸው ለሰላማዊ መሻሻል አነሳሥ ነው፡፡ይህ ዘገባ ድፍረትና ጥንካሬያቸውን በሚገባ ዕውቅና በመስጠት እንደማሳሰቢያነትም ያገለግላል፡ ዩናይትድ ስቴትስ ሰብአዊ ክብርን ለማራመድ ከሚጥሩ ጋር አብሮ በመቆም በጥረታቸውም ላይ የዓለም ትኩረትና ድጋፍ ብርሃን እንዲያበራ ከማድረግ አንቆጠብም፡፡”

እነዚህ መጠነኛ ክንዋኔዎች ፕሬዜዳንት ኦባማ ከሰነዘሩዋቸው እነዚያ ግዙፍ፤ ተስፋ ሰጪ ቃላቶች ጋርና አስተዳደራቸው መልካም አስተዳደርንና ሰብአዊ መብትን በማስከበሩ ረገድ በአፍሪካ የተደረገው ሲመዘን እጅጉን ተራርቀውና በማይመጣጠን ደረጃ ኣንሰው ይገኛሉ፡፡ አሁን ጊዜው ያለፈውን በማንሳት መወነጃጀያ፤ ጥርስ ማፋጪያ፤ ሆድ ማከኪያ፤ እና ጣት መቀሳሰርያ ግዜ አይደለም፡፡ ወደ ፕሬዜዳንታችን የትግል ጥሪ በመመልከትና ትኩረታችንን በማገናኘት ‹‹ወደፊት እንቀጥል›› በማለት የሞረሽ ጥሪ ማድረግ ነው የሚገባን፡፡

አሜሪካኖች በአብዛኛው የሚታወቁበት በቀጥታ አነጋገራቸው አካፋን አካፋ በማለታቸው ነው፡፡ እኔ ዘወትር በተራ አሜሪካውያንና በጥቂት ታላላቅ መሪዎቻቸው የማደንቅላቸው ባሕሪያቸው ነው፡፡የሚሉትን ያደርጋሉ የሚያደርጉትን ይላሉ፡፡ ‹‹ቀጥተኛ ተናጋሪው›› የሚባሉት ፕሬዜዳንት ሃሪ ኤስ ትሩማን ‹‹ለማንም መከራና ስቃይ

አልመኝም፡፡ እውነቱን በምናገርበት ጊዜ እነሱ ግን መከራ ነው ይላሉ::›› ስለዚህም እኔም ትንሽ ቀጥተኛ ንግግር አደርገ ለሁ፡፡ ስለ ሰብአዊ መብት ጉራና እወጃ በቂ ያህል ሰምተናል፡፡ የአፍሪካን የሰብአዊ መብት ችግር ስለ መቅረፍ፤ በአፍሪካ መልካም አስተዳደርን ስለመገንባት ‹‹ስለ ግጥሚያው ጥሪ ወይም ስለፍላጎት ቅስቀሳው›› ‹‹ችግሮች‹› ‹‹አከራካሪ ጉዳይነት›› ስለሁሉም ርዕሶች በሚገባ እናውቃለን፡፡ በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊያንም አሜሪካ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብትን ለማረጋገጥ ስላደረገውና ሳያደርገው በቸልታ ስለታለፈው፤ በቂ ጉርምርምታም፤ መነጫነጭ፤እንዲሁም ምሬት በበቂ አድምጠናል፡፡ ከእንግዲ ምንም የጎንዮሽ ንግግር አያስፈልግም ግልጡን በቀጥታ እና ቀጥተኛ የሆነ ድርጊት ማሳየት ብቻ ነው፡፡ በፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን፤በአፍሪካ መልካም አስተዳደርንና ሰብአዊ መብትን በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ ሁለት ምርጫዎች ብቻ ናቸው ያሉት፤ በቃን ብሎ በቁርጥ ‹‹ብድግ‹‹ : አለያም እጅን ኣጣጥፎ ኣፍን ለጉሞ ጭጭ በማለት ነው:: በሌላ አነጋገር: አሜሪካ ቆርጦ ከጠንካራዎቹ አፍሪካውያን ጋር በመቆም ትልቅነቱን ያስመሰክራል:: ካልሆነ ደግሞ ተሸመድምዶ በመድከም በ ምጽዋት፤በዓለም ባንክ፤ በአይ ኤም ኤፍ ገንዘብና ብድር በአፈሙዝ ሃይል ሥላጣን ይዘው ከሚገዙት ከጨካኞቹ ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ መሪዎች ጋር ተቃቅፎ በውርደት መጋደም ነው፡፡

ጀግኖች ኢትዮጵያውያን መርጃው መንገድ፡ የት ይጀመር?

በርካታ ልምድ ያካበቱት ኢትዮጵያዊያን ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ኤች አር 2003ን (“Ethiopia Democracy and Accountability Act of 2007”) በሚገባ ያስታውሱታል፡፡ያ የሕግ ረቂቅ በኣመሪካን ምክር ቤት ቀርቦ ነበር፡፡ (H.R. 4423 “Ethiopia Consolidation Act of 2005”) በቅድሚያ በኮንግሬስማን በኒው ጀርሲው ክሪስ ስሚዝ የአፍሪካን የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ በሚመሩበት ጊዜ የቀረበ ነው፡፡(ረቂቁ ቆየት ብሎ በውጭ ጉዳይ ኮሚቴ H.R. 4423 and H.R. 5680 ብሎ ተሰይሞ ነበር፡፡) በ2007 የኒው ጀርሲው ኮንግሬስማን ዶናልድ ፔይን የኮሚቴው ሰብሳቢ ሲሆኑ ጉዳዩን ተረክበው የ85 የኮንግሬስ አባላትን ድጋፍ ለማግኘት ችለዋል፡፡ ረቂቁ በ2007 የቤቱን ድጋፍ ቢያገኝም ወደ ሴኔት ቀርቦ ድምጽ ሊያገኝ አድል ኣልነበረዉም፡፡ በረቂቁ ሕግ ውስጥ በርካታ ለመልካም አስተዳደር፤ ለተጠያቂነት፤ ስለሰብአዊ መብት መከበረና መረጋገጥ፤ ስለዴሞክራሲ፤ ስለፍትህ መከበርና ስለ ሕግ የበላይነት ስለነጣ የፍትህ ስርአት፤ ስለፍትህ ባለሙያዎች ስልጠና፤ስለምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ መሆንና ሌሎችንም አስፈላጊ የሆኑ ሕዝባዊና ሃገራዊ ጉዳዮችን ያቀፈ ነበር፡፡

የኢትጵያን ‹‹ማግኒቲስኪ ሕግ” ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2009 በአክራ ባደረጉት ንግግር

አፍሪካውያን ‹‹በሽታንና አለመግባባትን ሊያሸንፉ፤ከመሰረቱ ጀምሮ ወደ ላይ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ፡፡ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰአት ታሪክ እየገሰገሰ ነው›› አዎን ትችላላችሁ (አሜሪካ.... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ DRIVERS/DETAILERS NEEDED

Positions need to be filled at MSP AIRPORT

Work with car rental at MSP Airport

DRIVER JOB: Driving rental cars inside and outside of the airport

(ሹፌሮች)፡ የሚከራዩ መኪናዎችን ኤርፖርት ውስጥና ከኤርፖርት ውጭ መንዳት

DETAILERS/ CAR WASHER: Clean rental cars so they may be rented again

(Washing, vacuuming, filling, etc.)

(መኪና ማጠብ፡) የሚከራዩ መኪናዎች ተመልሰው እንዲከራዩ ማጽዳት (ማጠብ፣ ቫኪውም ማድረግ፣ መሙላት)

Both Jobs require: - VALID DRIVER’S LICENSES (ሕጋዊ መንጃፈቃድ)

- DRIVING RECORD ( Bring printed version) (የመንጃ ፈቃድ ሪከርድ)

- CRIMINAL BACKGROUND CHECK ( Bring printed version) (ከወንጀል

ነጻ የሆነ/የሆነች)

- MUST BE AUTHORIZED TO WORK IN THE U.S (በአሜሪካ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት)

- SOCIAL SECURITY CARD (የሶሻል ሴክዩሪቲ ካርድ)

Full time and part time positions AVAILABLE (በሙሉ ሰዓትም ሆነ በፓርታይም ለመሥራት ይችላሉ።

CONTACT INFORMATION:

Carolina Chicosqui (952) 374-8442 - Morning (ጠዋት ለካሮሊና ይደውሉ)

Alazar Berhanu (612) 715-3080 - Afternoon (ከሰዓት ለአላዛር ብርሃኑ ይደውሉ)

Page 13: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Phone:- 651-641-0931 2147 university avenue west suite 117 . St. Paul, MN 55114

www.gobena-law.com

Law Practice with Passion!

GOBENA & ASSOCIATES Attorney At Law

አሜሪካ... ከገጽ 12 የዞረ

ብለው ለኣፍሪካኖች ተናግረው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሕግ በአሜሪካ ኮንግሬስ ማለፍ የሚገባው አሁን ነው፡፡በሁለቱም ወገኖች የፓርቲ አሰላለፍ በኩል ስምምነቱ አለና፡፡ በዴሞክራቶችም ሆነ በሪፓብሊካንስ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ቅድሚያ የአየተሰተጠው ነዉ፡፡ የማግኒቲስኪ ሕግ ተብሎ ኣዲስ የዎጣው አመላከችና ፈር ቀዳጅ የሆነ የሰብአዊ መብትን መደፈር የሚያስከብር ድንጋጌ ነው፡፡ይህን ሕግ በቅድሚያ ያነሱትና ያቀረቡት እንዲሁም በተዘዋዋሪ መልክ ድጋፋቸውንና በመጨረሻም ድምጻቸውን በመስጠት ያሳለፉት ሊመሰገኑ የሚገባቸው ናቸው፡፡ (* የለነገሩ ኦባማ አስተዳደር የንግዱን ሕግና የሰብአዊ መብቱን ድንጋጌ ማቀላቀል አያስፈልግም የሚል አቋም ቢይዝም በመጨረሻው ላይ ግን ተስማምቷል::)

“የማግኒቲስኪ ሕግ” በጣም ከፍተኛ የሆነ የሪፓብሊካኖች ድጋፍ ነበረው፡፡ የሪፓብሊካኑ አሪዞና ሴኔተር ጆን ማኬይን ‹‹ ስለማግኔቲስኪ ግፍና በደል ለመናገር፤ እንዲሁም ሌሎችም አሁን በሕይወት ያሉና በሩስያ ወህኒ ቤቶች አለ አግባብ በመሰቃየት ላይ ስላሉት መታገልና ለነጻነታቸው መቆም አሜሪካ የሞራል ግዴታ አለበት›› በማለት አሳስበዋል፡፡

‹‹ለቭላድሚር ፑቲንና ለሩስያ የሰርቆት መንግስት እንዲህ አይነቱ ኢሰብአዊ ድርጊትና የዜጎች በተለያየ መልኩ መብቶች መገፈፍና ለእስር መዳረግ፤ በወህኒ ስቃይ ማየትን እኛ አሜሪካውያን ልንቀበለው የሚገባን አለመሆኑን የምናሳውቅበት ነው፡፡ ይህ ሕግ ደግሞ ጸረ ሩስያ አይደለም፡፡ይልቅስ ሩስያን ደጋፊ ሕግ ነው:: እኔ ስለነሱ ግፍ ስተፈጸመባቸው እጨነቃለሁ፤በጸሎቴም አስባቸዋለሁ፡፡›› የአሪዞናው ሴኔተር ጆን ማኬን፤ ይህ ሕግ በሁሉም ሃገራት ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል፡፡ የዴሞክራቲኩ ኒው ሃምፕሻየር ሴኔተር ጂያን ሻሂን አሜሪካ በሁሉም ቦታዎች ስለሰብአዊ መብት ትኩረት ያደርጋል፤ ‹‹ስለ ሃገራቸው የሙስና ዝቅጠት ደፍረው ከሚናገሩት ጋር አብረን እንቆማለን፤ ይህ ሕግ በዓለም ላይ ላሉት ማግኒቲሰኪዎች ሁሉ ነው፡፡›› ሕጉ በዓለም አቀፍ ሁሉ እንደ ምሳሌ የሚወሰድ ነውና በየትም ቦታ እንደሚከበር እምነት አለኝ፡፡ ሁዋይት ሀውስም በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቶ ፕሬዜዳንቱ እንደሚፈርሙት ጠቁሟል፡፡ ‹‹አስተዳደሩ በሩስያ የዴሞክራሲ እውነታና የህግን የበላይነት ለማረጋገጥ ከሚሹና በዓለም አቀፍ ደረጃም እውን እንዲሆን ከሚጥሩ ከኮንግሬስና ከአጋሮቻችን ጋር መስራቱን ይቀጥላል›› ብለዋል ኦባማ::

ማግኒትኪ የሩስያ መሪዎች ሙስና ያጋለጠ ወጣት ጠበቃ

ነበር፥ በዚህ ምክኒያት ባለስጣኖችጭ ኣስረው ኣሰቃይተው በስር ገደሉት:: የየሩስያ ፕሬዜዳንቱ ነጻ ካውንስል ለሲቪል ማሕበረሰብ ልማትና ሰብአዊ መብት ዋስትና በደረሰበት ማጣራት መሰረት፤ የማግኒቲስኪ ተይዞ መታሰር ከሕግ ውጪ የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የፍርድ ቤቱ ሂደትም ማግኒቲስኪ በሩስያ ፌዴሬሽን ፍትህ በፍርድ ቤቱ፤ በአቃቤ ሕጉ፤ እንደተነፈገውና ምርመራ የተካሄደበትም በስርቆት በወነጀላቸውና ማንነታቸውን ይፋ ባወጣባቸው ግለሰቦች ነበር፡፡ በእስር ላይ በነበረበት ጊዜም አስፈላጊ የሆነውን የህክምና እርዳታ እንዳያገኝ ሆኖ በ8 የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች በመጨረሻው የሕይወቱ ሰአት በግፍ እንደተደበደበ ተገሎኣል፡፡ ድርጊቱንም ባለስላጣናቱ ከመካዳቸውም ባሻገር አንዳቸውም በድርጊታቸው የተነሳ ለጥያቄ እንኳን ወደ ፍርድ ቤት አልቀረቡም፡፡

ፍትሕን ተነፍገው በወህኒ በመሰቃየት ላይ ያሉ በርካታ ‹‹ኢትዮጵያዊያን ማግቲሰኪዎች›› አሉ፡፡ በ2005 በተካሄደው ምርጫ ወቅት ባዶ እጃቸውን ዴሞክራሲንና ሰብአዊ መብትን ለማስከበር ገዢው መንግስት እራሱ ያጸደቀውን ሕገ መንግስት እንዲከበር ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉትን ንጹሃን 200 ዜጎች በፖሊስና በደህንነት አባላት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በተሰጠ ቀጥታ ትዕዛዝ በጥይት ተደብድበው

መሞታቸውና ከ800 የማያንሱት በጠና መቁሰላቸው ተረጋግጦ እያለ፤ ይ ህንንም በቀጥታና በተዘዋዋሪ የፈጸሙት ይከበርልኝ የዜግነት ክብሬ አይደፈር በማለቱ የተፈጸመበት የሰብአዊ መብት መገርሰስ ዓልም ሊፋረደው የሚገባ እንጂ በሕግ ማውጣትና በማስፈራራት ብቻ ሊታለፍ የሚገባው ሊሆን አይገባም፡፡ የነዚህና የሌሎችም በግፍ የተገደሉና ለመከራ የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ ከያሉበት ከፍ ብሎ ይጣራልና ሰሚ ሊያጣ አይገባውም፡፡

በዩ ኤስ ኮንግሬስ ለውጥ ማየት ታላቅ ደስታ ነው፡፡ በሰብአዊ መብትና በመልካም አስተዳደር አዲስ አስተሳሰብና አመለካከት ያለ ይመስላል:: እነዚህ ሁነቶችም የዓለም አቀፉ ድንጋጌዎችና የሰለጠነ ሕብረተሰብ አንድ አካል ናቸው፡፡ ለምንግስት ብቻ ሊተው የሚገባም አይደለም››:: ሰብአዊ መብት የሁሉም ሰብአዊ ፍጡር የጋራ ጉዳይ ነው፡፡ለሩስያው ጀግና ሰርጂ ማግኒቲስኪ ጥሩ የሆነው ህግ ለኢትዮጵያዊያኖቹ ጀግኖች ለ 16 ዓመቱ መለስካቸው አላምነውም ፤ ለ22 ዓመቱ ሃድራ ኦስማንም፤፤ለ50 ዓመቷ እቴነሽ ይማምም፤ለ23 ዓመቱም ቴዎድሮስ ግደይ፤ ለ24 ዓመቱም ጋሻው ሙሉጌታ፤ለ21 ዓመቱም ሌቺሳ ፋታሳም….. በግፍ የተገደሉ ሰማታት ተገቢ ነው፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ (አሜሪካ.....ወደ ገጽ 11 የዞረ)

“let our family fight for your fam-

ily”

የኮዲ ቤተሰብ ጠበቃዎች ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር አብረው በመሥራትና ጥብቅና በመቆም የረዥም ልምድ አላቸው!!

የኮዲ ሕግ ጠበቃዎች ቡድን በሥራ ቦታ አደጋ፣ በመኪና አደጋ፣ በራስ ላይ

በሚደርስ ማንኛውም አደጋ የሰዎችን መብት በማስከበር ማግኘት የሚገባቸውን

ጥቅም በማስገኘት የታወቀ ነው። እርስዎም ምርጫችሁ እኛ እንሁን።

Phone: 651.294.0994 Fax: 651.292.4955 Email: [email protected] Our Location: 359

Commerce Court Vadnais Heights, MN 55127 www.codylawgroup.com

Page 14: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

520 Snelling Avenue North Saint Paul, MN 55104

(651) 644-3500 ወይም (952) 688 3099 ከፋሲካ ምግብ ቤት ጎን

Page 15: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

አግልግሎትዎን

መዲናመዲናመዲና ጋዜጣ ላይ ለማስተዋወቅ 612-226-8326

ከጌታቸው ወርቁ ከአዘጋጁ፦ ይህን አሳዛኝ ጽሁፍ ጸሐፊው ኢትዮጵያ ውስጥ

በሚታተመው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ላይ አውጥተውት ነበር። እዚህ ውጭ ሃገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን አንድ ነገር ብናደርግ በሚል ስሜት ተነሳስተን በዘ-ሐበሻ ላይ ልናትመው መወሰናችንን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። መልካም ንባብ።

ይኸውልህ ወዳጄ የተመለከትኩትን፣ የታዘብኩትን እና ያስተዋልኩትን እንደወረደ ላጫውትህ፡፡ ያ ጉምቱ የጥበብ

ሰው፣ ያ የኮሜዲ-የጭውውት አውራ፣ ያ ጥበብን የተቀባው

ባለትልቅ ተሰጥዖው ሰው፣ ያ ከሥነ-ሠብዕ ጥበብ ተሻግሮ

የአዕዋፋትን ዝማሬ ምስጢር፣ የንፋስን ሿሿታ፣ የበር-መስኮት ሲጥሲጥታ ሳይቀር በጥበብ ሥራው ላይ አክሎ የሚከውንልህ ተዋናይ ልመንህ ታደሠ፣ ከፒያሳ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ቢስ መብራት አደባባይ ላይ፣ እንደ ማንም ቆሼ ሲለቅም ተመለከትኩት፡፡

ልመንህን ያየ፣ እኔን-አንተን አየ፤ እኔን-አንተን ያየ ኅብረተሰቡን አየ፤ ኅብረተሰቡን

ያየ-ተቋማቱን አየ ነው እያልኩህ ያለሁት ወዳጄ፡፡

ያ የጥበብ አውራ ልመንህ ታደሰ ሰውነቱ ገርጥቶ፣ የማይቀይራትን ጥቁር ሰማያዊ ወይም ጥቁር ሱፍ በውሃ ሰማያዊ ሸሚዝ አጥልቆ፣ የተጨራመተች ልሙጥ ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቶ፣ እንደ ባይንደር መሳይ ነገር ላይ የተጨረማመቱ ቡጭቅጫቂ ወረቀቶችን ይዞ የሥነ ሥዕል ንድፍ እንደሚሰራ ጀማሪ ሰዓሊ ከአደባባይ ሆኖ

ድምም-ፍዝዝ ይላል፤ በጀርባው ባነገተው ጥቁር ቦርሳ /ኮሮጆ/ አንዳች ነገሮችን ሸክፏል፡፡ ልመንህ ታደሠ ተርቦም ሊሆን

ይችላል-ማን ያውቃል? ለጠቅ አድርጎ ደግሞ ከቢስ መብራት

ሳይርቅ አቀርቅሮ ራመድ-ራመድ ይልና

ወዲያው ቆሼ-ነገር ይለቅማል ከመሬት፤

ከዚያም ቀረብ ብሎ ከ ድ ማ ሜ ው ከሚያናጥበው ሰው ጋር ከራሱ ጋር ብቻ በሚያወራ ሰው ድምጸት አንዳች ውል የሌለው ነገር ያወራል፡፡ ብዙዎች የእድሜ አቻዎቹና የእድሜ ትንሾቹ እያፌዙበት ያልፋሉ፡፡ “ልመንህ

በአደባባይ ‹ላይቭ› እየተወንክ ነው፣ ልመንህ አለባቸው ተካ

ይጠራሃል- አትሄድም ቶሎ፣ ልመንህ ኑሮ ጠረረብህ፣ ልመንህ ከዋሺንግተን ተንደርድረህ ፒያሳ ጎዳና…” እና ሌላም ሌላ በጆሮዬ ያደመጥኩት ከኅብረተሰቡ የተበረከተለት አቀባበል ነው፡፡ የጎዳና ተዳዳሪዎች ብቻ በፍቅር ሲቀርቡት አስተውያለሁ፡፡ ሊንከባከቡት ይሞክራሉ ግን ደግሞ እርሱ አይመቻቸውም፡፡

“እብዱ” ልመንህ ፊቱን ወደ ፒያሳ አዙሮ ተንቀሳቀሰ፡፡ እንደ ብዙ ወጪ ወራጅ ኢትዮጵያዊያን እና

ኢትዮጵያዊያት እኔም በለበጣ ከንፈሬን እየመጠጥኩ ተዘባበትኩበት፤ እንደ ብዙ አሽከርካሪዎች እኔም ገልመጥ አድርጌው የስላቅ ፈገግታ አሳይቼ የእርምጃዬን ማርሽ ጨምሬ ወደ መርካቶ እብስ ለማለት ፈልጌ ነበር፤ ግን አልቻልኩም፡፡ (በመጽሐፍ ቅዱስ ያለው የሣምራዊው ታሪክ ትውስ አለኝ) አንዳች የጥፋተኝነት ስሜት ጭምድድ አድርጎ ያዘኝ፡፡

አይምሰልህ ወዳጄ! ልመንህን እኔ በግል አልበደልኩትም፤ በአካልም አላውቀውም፡፡ በተናጥል ያስቀየመኩትም አንዳች ነገር የለም! በቅርቡ “አበደ” ብለው ከአሜሪካ አገር አውጥተው (ዲፖርት አደረጉት ነው የሚባለው) በተወለደበት ኅብረተሰብ ውስጥ አምጥተው ህዝቡ ውስጥ እስኪደፉት (እስኪጥሉት) ጊዜ ድረስ እንደዚህ ገፅ ለገፅ በአካል አይቼውም አግኝቼውም አላውቅ፡፡

በቲቪ ስክሪን እና በሲዲዎች ብቻ የምመለከተውና

የማደንቀው ብርቅዬ አርቲስት ነበር፡፡ ነበር ልበል እንግዲህ-ጎዳና ላይ ጣልነው አይደል፡፡ እኔ እና እሱ በትውልድም፣ በደረጃም ዱባ እና ቅል የምንባል ነን፡፡ የትና የት ይልቀኛል መሰለህ ኢህአዴግ ከበረሃ ወደ አዲስ አበባ በትጥቅ ትግል

አሸንፎ በገባ እና ሥልጣነ-መንበሩን በተቆናጠጠበት ጊዜ የነበረውን አስፈሪ የሽግግር ወቅት፣ የበቅሎ ቤቱን ፍንዳታ፣ በልጅ ዓይናችን ያየነውን የሸጎሌውን ፍንዳታና እልቂት፣ በየቤታችን ጣራ በስቶ የሚመጣውን ተባራሪ ጥይትና የመትረየስ እሩምታ የፈጠረብንን ዘግናኝ የፍርሃት አባዜ በጥበብ ሥራቸው ያረሳሱን ከነበሩ ኮሜዲያን አንዱ እና ዋናው ልመንህ ታደሠ ነበር፤ ከአለባቸው ተካ ጋር ተጣምሮ፡፡

እንደማስታውሰው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የመቶ ሃያ ፕሮግራምን አሁን (እሁድ መዝናኛ) ሲጀምር የዝግጅቱ አስኳል ተደርገው ከሚጠበቁት አርቲስቶች ልመንህ ታደሠ እና አለባቸው ተካ ዋናው ነበሩ፡፡ ዛሬ አለባቸው ተካ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ካለፈ ሰነባበተ፤ ልመንህ ታደሠ ደግሞ አብዷል ተብሎ የወለደ (ያፈራ) ኅብረተሰብ ጥሎ አይጥልም ተብሎ

ከአሜሪካን አገር ወደ አዲስ አበባ ፒያሳ-አራት ኪሎ ጎዳና

ከደጅ ተደፍቷል፣ ተጥሏል ነው እያልኩህ ያለሁት፡፡ ግን እኮ የወለደ (ያፈራ) ኅብረተሰብ ጥሎ አይጥልም

የሚለው አባባል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ አይመስለኝም፡፡ ምናልባትም ወላጅ እናትህ ጥላ አትጥልህ ይሆናል፡፡ እንደ ኅብረተሰብ ግን ጥሎ እንዳይጥልህ ወይ በሥጋ የምትወለደው ቤተሰብ ከአጠገብህ ሊኖር ይገባል፤ አልያም በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በኑሮ መደብ ወይም በፖለቲካ ርዮት የምትቧደነው ቡድን

ሊኖርህና ያም ቡድን በማህበረ-ፖለቲካው ጥሩ ሥፍራ ሊኖረው ግድ ነው፡፡

አለበለዚያ ከዚያ ውጭ ከሆንክ እንደ ልመንህ ታደሠ ልቀህ የጎላህበት፣ ሌት ተቀን የሰራህለት፣ ቋንቋውን የተቀኘህለት፣ ባህሉን ያዳበርክለት፣ ኪነቱን ያጎላህለት እና የኅብረተሰብ አገልግሎት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል የሰጠኸው

ህዝብ (የግለሰብ እና የማህበራዊ ተቋማት ስብስብ) “ውይ!” ብሎ ከንፈሩን እንደ ጡጦ መጥጦ “ዋ እንደርሱ እንዳትሆን” እያለ ለራሱና ለቤተሰቡ መማሪያው ያደርግሃል እንጂ ለአንተ ምንም አይፈይድልህ፡፡ ምክንያቱም እንደ ኅብረተሰብ ገና ህፃን ልጅ ነው አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ ስብስብ፡፡

ይህን የምልህ አንድ ልመንህ ታደሠን ዋቢ አድርጌ ብቻ እንዳይመስልህ፡፡ በርካታ ለኅብረተሰቡ አገልግሎት የሰጡ ሰዎችን ከሠፈሬ፣ ከአካባቢዬ ልጠራልህ እችላለሁ፣ ዳሩ ግን

አንተ እነርሱን በጉልህ አታውቃቸውም፣ እኔ ጸሐፊውና የአካባቢዬ ሰዎች ብቻ ነን የምናውቃቸው፡፡ አንተ እና በዙሪያህ ያሉ ሰዎች የምታውቋቸው እኔ የማላውቃቸው ለኅብረተሰቡ ብዙ የሰሩ ሰዎች እንደሚኖሩም እገምታለሁ፡፡

ስለዚህ በጋራ በምናውቃቸው ሰዎች ብቻ ለመጨዋወት እንሞክር ካልከኝ ደግሞ አንሙትን ታውቀው የለ? ምነው አንሙት ያ አጭሩ:-

ባለዋሽንት የጊሽ አባይ ኪነት ቡድን ጥበበኛ፣ አዎን

እንዴት እርሱን ታጣዋለህ- ውለታ መብላት ነው የሚሆንብህ፤ ከድምፃዊያን ይሁኔ በላይ እና ሰማኸኝ በለው ጋር “አንቱየዋ እነርሱ እኮ ልጆች ናቸው፣ ይጫወቱ በጊዜያቸው” ሲል በሙዚቃዊ ድራማው ላይ የሚያቀነቅነው ባለዋሽንቱ እረኛ! ይኸውልህ ከጥቂት ዓመታት በፊት እርሱም በኑሮ ደህይቶና ተደብቶ ሸራተን ፊት ለፊት ላስቲክና ማዳበሪያ ዘርግቶ ተቀምቶ ነበር፡፡ ለነፍሴ ያሉ አበውና እመው ዳቦ እና ጣሳ ውሃ ሲሰጡት በእርሱ የጥበብ በረከት ሲዝናና እና ሲጨፍር የነበረው ኅብረተሰብ እና የማህበረ ፖለቲካው ሊቃውንት በማርሴዲስ መኪና ፍስስ እያሉ ወደ ሸራተን ሆቴል ሲገቡ የለበጣ ፈገግታቸውን እያሳዩት በበላይነት መንፈስ እየተኮፈሱበት ያልፉ ነበር፡፡

አብረውት ከልጅነት እስከ እውቀት የተጠበቡት ጥበበኞች ዝና እና ገንዘብ እንደ አሸን ባፈሱበት በዚያ ወቅት እንኳ ለእርሱ ጠብ ያደረጉለት ነገር አልነበረም፡፡ በመጨረሻ እራሱን እየገዛ እየተነቃቃ ሲመጣ ግን እንዲህ አድርጌለት ነበር፣ እምቢ አለኝ እንጂ እንዲህ ላደርግለት አስቤ ነበር፣ ቅብርጥሶ እያሉ ሞራል በሚያንሳቸው አንዳንድ መጽሔቶች ሞራላቸውን ሊያነቃቁ ሞከሩ፡፡

እሺ ወዳጄ ደግሞ በሌላ ሰው ታሪክ ልሰልስህ፤ ደራሲና ተርጓሚ ህሩይ ምናሴን (አውግቸው ተረፈ) ታውቀዋለህን? እርሱም እንዲሁ አበደ ተብሎ ከአደባባይ ወድቆ የእርሱን ማበድ ሳይሆን የእኛን የማኅበረሰቡን ማበድ እና ሞራል ማጣት

ገሃድ አውጥቶብን ነበር፡፡ አንድን ሰው በማህበረ-አገልግሎት ዘመኑ እንደ ሸንኮራ ምጥጥ አድርገን ተጠቅመን እንደማናችንም አንዳች የህይወት ውጣ ውረድ ሲገጥመው ግን ምጣጩን ገለባ ብለን አደባባይ እንጥለዋለን፡፡ ምንም ውለታ እና

ባለዕዳነት እንኳ አይሰማንም-እኔ፣ አንተ እና ኅብረተሰቡ ወዳጄ፡፡

ጸሐፊ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሙሉ ታፈሰንም እንዲሁ ከትውስታህ ትስተዋለህ

ብዬ አልጠረጥርም-ወዳጄ፡፡ ይኸው ያን የመሰለ ጸሐፊ የኑሮ ውጣ ውረዱ ላይ የእኛን የወደቀ ላይ ምሣር ማብዛት ጨምረንበት አደባባይ

ከወረወርነው ዓመታት አለፉ፡፡ እዚህ ጊዮርጊስ አደባባይ ላይ ተቀምጦ ዘወትር ይታዘበናል፡፡

ትላንት ቤቱ እየተመላለሱ ተልካሻ የጥበብ ሥራቸውን እንዲያቃናላቸው አድርገው ስማቸውን የገነቡ የጥበብ ነጋዴዎች

ሁሉ ዛሬ በመኪና “ሰላም ነሽ ሰሌ” እያሉ ያልፉታል-እነርሱ ጥበብን ስለነገዱ አተረፉ፤ እርሱ ነጋዴ ባለመሆኑ አበደ ተባለ፣ አለቀ በቃ!

የሰለሞንን ብዕር ያልተጋራ እና ትሩፋቱን ያልተጠቀመበት የያን ጊዜው የኪነት ሰዎችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች የሉም ለማለት እደፍራለሁ – ካለኝ መረጃ፡፡ ግን ዛሬ እነርሱም የእርሱ የገንዘብ ተጠቃሚዎቹም ሆኑ እኛ የጥበብ በረከቱን ያጣጣምን

የኅብረተሰቡ አባላት በእርሱ የጎዳና ሕይወት የኛን የበላይነት እያሳየን ምንም ሳንፈይድ ባለዕዳነታችን ሳይሰማን እንደ ከብት በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን የጦጣ ኑሮ እንኖራለን፡፡ ወዳጄ ከቀድሞዎቹ ሰለባዎች ዋቢ

ከፈለክ ደግሞ ድምፃዊቷ ባለ-ክራር ሜሪ አርምዴን ታማ ቤቷን ዘግታ ስትቀመጥ የገጠማትን ወደ ኋላ ሄደህ

አስታውስ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ በመረዋ-ተርገብጋቢ ድምጽዋ “እንቁጣጣሽ … እንቁጣጣሽ …” እና “ትዝታን በፖስታ

ልኬልሃለው፣ መልሱን በቶሎ እጠብቃለሁ” እያለች የምታዜመው ዘሪቱ ጌታሁን ታማ ሐኪም ወደ ውጭ አገር ሄደሽ ካልታከምሽ በሕይወት የምትቆዪው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው ብሏት ቤቷን ዘግታ ተቀምጣለች፡፡

በቃ ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለው ዓይነት ማለት ነው የእርሷ ቆይታ፡፡ ወዳጄ አንተን ማስደበር እንዳይሆንብኝ እንጂ ሌሎች በርካታ የታዋቂ ሰዎችን ዋቢ ታሪክ እያነሳሁ ባወጋህ በወደድኩ፤ ግን ስንቱን አንስተን በማውራት ስንቱን የኅብረተሰብ አባላት አስቀይመን

እንችለዋልን፡፡ ያ የጥበብ አውራ ልመንህ ታደሰ እመር-እመር እያለ በመራመድ የሚለክፉትን “ፍንዳታዎች” እና

የሚያሽሟጥጡትን ሽማግሌ-“ግንባታዎች” የመልስ ምት እየሰጠ፤ በአንድ ብር ምጽዋት ሊያልፉት የሚፈልጉትን ቁንን ሰዎች ሁለት ብር የመልስ ምት እየሰጠ፣ ገንዘቡን እየበተነ ያልፋል፡፡

እኔም ጸሐፊው ከኋላው እከተላለሁ-ጅል ታዛቢ ሆኜ፡፡ ሲኒማ አምፔር ጋር አንድ ትልቅ ሰው አስቆሙትና እጁን ይዘው “ልመንህ ምነው እንዲህ ራስህን ጣልክ አሉት?” ሀዘኔታ በሚታይበት የፊት ገፅታ፡፡ እርሱ በባይንደር መሳይ ነገሩ የያዛቸውን ወረቀቶች እንዳይነጥቁት በመስጋት ይመስላል በአንድ እጁ ደረቱ ላይ ለጥፎ ለምን አትተወኝም እኔ ማናችሁንም አልፈልግም፣ ተጣልቻችኋለሁ አላቸው፡፡ ሰውየው ሳቃቸው መጣ፡፡ ሌሎች ብዙ ሰዎች ከበዋቸው ቆሙ፡፡ ልመንህ ተቆጣ፡፡ እጁን አስለቅቆ የአራት ኪሎን መንገድ ያዘ፡፡ አስፋልት ዳር ለነበሩ የጎዳና ተዳዳሪዎች

የያዘውን አንድ-አንድ ብር ሣንቲም እንዳለ ለገሳቸው እናም እየሳቀ ከራሱ ጋር እያወራ ነጎደ፡፡

ይህ እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ክንፎች ያላቸው ወፎች በጋራ ይበራሉ በሚል ብሂል ለመረዳዳት የተሰባሰቡ የሙያ ማህበራት ባሉበት ሀገር ነው፡፡ የደራሲያን ማህበር፣ የሴት ደራሲያን ማህበር፣ የኮሜዲያን ማህበር፣ የሙዚቃ ማህበር፣ የተውኔት ባለሙያዎች ማህበር፣ የፊልም ባለሙያዎች ማህበር፣ የፕሮዲሰሮች ማህበር፣ የ … ማህበር ባሉበት ሀገር ነው፡፡ አየህ ወዳጄ ሀበሻ አበሻ ነው፡፡ ግለሰብ ሆነ ኅብረተሰብ፣ ተቋም ሆነ ዳያስፖራ (በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ) በዚህ ረገድ የሚፈይደው በጎ ነገር የለም፡፡

በቅርቡ ከአሜሪካ አገር ለእረፍት የመጣ ጓደኛዬ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሠን በአንድ ቅዝቅዝ ባለ ሀበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ሲዘፍን እንደተመለከተው በኩራት ነግሮኝ እዚህ እንደ ታምር የምናያቸውን ድምፃዊያን እዚያ በአንድ ቢራ በቅርብ እንመለከታቸዋለን አለኝ፤ ልመንህ ታደሠን ጨምሮ፡፡ አሜሪካ ሁላችንንም እኩል አድርጋናለች፤ ይህንንም ለእከሌ ድምፃዊ ድሮ እኮ ሀገር ቤት እንደ ብርቅ ነበር የማይህ፣ እዚህ ግን

እንደዋዛ አገኘሁህ ብዬ ነግሬዋለሁ በማለት ሥለ-

ብርቅዬዎቻችን ምንምነት ሲነግረኝ በእነርሱ ሥነ-ልቦና ላይ ስላሳረፈው አሉታዊ (ውለታ...ወደ ገጽ 10 የዞረ)

• ያ የኮሜዲ አውራ “እብድ” ተብሎ ጎዳና ላይ “ቆሼ” ይለቅማል!

• እርሱን ያፈራው ኅብረተሰብ የወደቀን ቀና ከማድረግ እንዳይቃና ይተጋል

• ስለዚህ ኅብረተሰቡ እንደ ድመት የራሱን ልጆች ይበላል!

አርቲስት ዘሪቱ ጌታሁን

በሚኒሶታ የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካውያን ቢዝነስ አዋርድ

አሸናፊ

እንኳን አብሮ

ደስ ያለን

Page 16: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

ስኳር ... ከገጽ 17 የዞረ

ዘ- ሃበሻ፡- በፋብሪካ የተመረተው ስኳርም ሆነ ከተለያዩ ምግቦች ቀጥታ ባልሆነ መንገድ የምናገኘው ስኳር ተመሳሳይ የጤና ችግሮችን ነው የሚያመጡት?

ዶ/ር፡- የጉዳት መጠናቸው አንድ ቢሆንም ጊዜው ግን በእጅጉ ይለያል፡፡ ትክክለኛው ስኳር እንደተጠቀምንበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ደም ውስጥ ይገባል፡፡ ምንም አይነት ጊዜ ሳይሰጥ ለጤና መቃወስ ሊያጋልጠን ይችላል፡፡ በአንፃሩ ግን ከተለያዩ የምግብ አይነቶች የምናገኘው ስኳር በስታርች ቅርፅ ነው፡፡ ስታርች በስርዓተ ልመት ውስጥ ለመፈጨትም ሆነ በደም ውስጥ ለመሰራጨት የሚወስደው ጊዜ ረዘም ያለ ነው፡፡ ሰውነታችን ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ቶሎ ብሎ ለችግር አያጋልጥም፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ከመጠን የዘለሉ ከሆነ ከላይ በዝርዝር ላየናቸው የጤና ችግሮች ያጋልጣሉ፡፡ ልዩነቱ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

ዘ- ሃበሻ፡- ሌላ አንባቢያችን ደግሞ ‹‹ስኳር ድንችን ጨምሮ ጣፋጭ ነገሮችን መመገብ አዘወትራለሁ፡፡›› ካሉ በኋላ የኩላሊት ጤና ችግር እንዳለባቸውም በደብዳቤያቸው ገልፀዋል፡፡ ለመሆኑ የአመጋገብ ስርዓት ለኩላሊት በሽታ ያጋልጣል?

ዶ/ር፡- ጠያቂዋ ወ/ሮ እንዳሉት ስኳርም ሆነ ጣፋጭ ምግቦችን አዘውትሮ ተመጋቢ መሆን በቀጥታ ከኩላሊት በሽታ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ የሚገናኘው ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ነው፡፡ ስኳርና ደም ግፊት በሽታ ካለ አልያም ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንና የሰውነት ክብደት መጨመር ሁኔታ የሚታይባቸው ሰዎች የደም ስር ጤና ችግሮች የሚያጋጥማቸው መሆኑ አይቀርም፡፡ በዚህም ሳቢያ የኩላሊት ጤና ይታወካል፡፡

ዘ- ሃበሻ፡- ጣፋጭ (ስኳር) መራሾቹ የጤና ችግሮች የበለጠ የሚያጠቁት ማንን ነው?

ዶ/ር፡- ከጾታ አንፃር ካየነው ችግሮቹ በሁለቱም ጾታዎች ላይ በእኩል ደረጃ ይስተዋላሉ፡፡ ይህም ማለት የማንኛውም ሰው የስኳር (የካሎሪ) ምግቦች አጠቃቀም ከልክ በላይ ከሆነ ቀደም ሲል ለጠቀስናቸው የጤና ቀውሶች መጋለጡ አይቀርም፡፡ ከዕድሜ አንፃር መጠነኛ ልዩነቶች አሉ፡፡ በቀላሉ ከደም ጋር የሚዋሀደው የገበታ ስኳሮችን ከ40 ዓመት ዕድሜ በኋላ አዘውትሮ መመገብ (መጠቀም) ከላይ ለገለፅናቸው የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድል ከእጥፍ በላይ ይጨምረዋል፡፡

ዘ- ሃበሻ፡- ለጤና ተስማሚ የሚባለው የስኳር መጠን ምን ያህል ነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- የገበታ ስኳርን መጠቀም የምንችለው መጠን እንደ ዕድሜያችንና የስራ ባህሪያችን የሚለያይ ነው፡፡ ለምሳሌ በቀን አንድ የሻይ ማንኪያ ብጠቀም ወደ 4 ግራም ስኳር ተጠቀምኩ ማለት ነው፡፡ ከ4 ግራም ስኳር ውስጥ ወደ 16 ካሎሪ አገኛለሁ፡፡ ይህ እንግዲህ ከሌሎች የምግብ አይነቶች ቀጥታ ባልሆነ መንገድ የምናገኘውን የካሎሪ መጠን ሳይጨምር ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በተለይም የስራ ባህሪው ብዙም በእንቅስቃሴ ላይ ያልተመሰረተ አልያም ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ ከሆነ በቀን በአማካኝ ከ2 ማንኪያ ስኳር በላይ ባይጠቀሙ ተመራጭ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ብዙ ኃይል በሚያስወጣ የስራ

መስክ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ግን የካሎሪ መጠናቸውን መጨመር ግድ ነው የሚላቸው፡፡ ሁሉም ሰው መገንዘብ ያለበት የሚጠቀሙት የካሊሪ ይዘት በተቻለ አቅም ከገበታ ስኳር የሚገኘው ከ10 በመቶ በላይ ባይሆን ተመራጭ መሆኑን ነው፡፡

ዘ- ሃበሻ፡- ለስኳር ህሙማንና በተለያዩ የጤና ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ‹‹በሐኪም አርቴፊሻል ስኳር ተጠቀሙ ተብለናል፤ አርቴፊሻል ስኳር በአገራችን አለ ወይ? በራሱስ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት አይኖርም ወይ?›› የሚሉትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ይደመጣል፡፡ በዚህ ረገድ የተወሰነ ማብራሪያ ቢሰጡበት ጠቃሚ ይመስለኛል?

ዶ/ር፡- አርቴፊሻል የስኳር አይነቶች በእንክብል መልክ ተዘጋጅተው በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለያዩ ሱፐር ማርኬቶች ይሸጣሉ፡፡ አርቴፊሻል ስኳሮች እንደ መደበኛው ስኳር ጣፋጭነት ቢኖራቸውም በካሎሪ ይዘታቸው ግን ዜሮ በሚባል ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ትንሿ አርቴፊሻል ስኳር ተገቢውን ጣዕም የመስጠት አቅም ስላላት ብዙ አያስፈልግም፡፡ የካሎሪ ይዘት ስለሌላቸውም ጤና ነክ ጥቅማቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን አያዛቡም፣ ለጥርስ መበስበስ አያጋልጡም፣ የሰውነት ክብደትን አይጨምሩም፡፡ የጎንዮሽ ጉዳትን በተመለከተ አንዳንድ በአይጥና በድመት ላይ የተሞከሩ የምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የወጡ መረጃዎች አርቴፊሻል ስኳሮች በተመጠነ መልኩ መጠቀም ካልተቻለ ለካንሰር በሽታዎች ያጋልጣል ይላሉ፡፡ በሌሎች ጥናቶች ደግሞ አርቴፊሻል ስኳሮች ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌላቸው ያስረዳሉ፡፡ ለማንኛውም በበቂ ጥናት ምላሹ እስኪገኝ ድረስ አርቴፊሻል ስኳሮችን በተመጠነ መልኩ መጠቀሙ ተገቢ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡

ቫይታሚን A ቫይታሚን ኤ Retinol ተብሎም ይጠራል፡፡ በዋነኛነት

ከእንስሳት ተዋፅኦ ከሚገኙ ምግቦች ይገኛል፡፡ ቬጂቴሪያን የሆናችሁ ሰውነታችሁ ቫይታሚን ከጥራጥሬና ከአትክልት ስለሚያገኘው ብዙም ፍርሃት አይግባችሁ፡፡ ይሁንና በተክሎችና በጥራጥሬዎች ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን አይነት Carotene የሚባለው ነው፡፡ ሰውነታችን ካሮቲኑን በመሰባበር የቫይታሚን ኤ ሟሟያ ያደርገዋል፡፡

ለሰውነትዎ የሚሰጠው ጠቀሜታ ለጥሩ የዓይን ብርሃን ወሳኝ ነው፡፡ የተፀነሰ ሽል ጤንነቱ

ተጠብቆ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድግ ይረዳል፡፡ ጤናማ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ስፐርም ፍሬያማ እንዲሆን ያግዛል፡፡ ሰውነታችን ኢንፌክሽኖችን እንዲዋጋ ያደርጋል፡፡ የሴሎችን አወቃቀር የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

የቫይታሚኑ እጥረት ምልክቶች የተወላገዱ ጥርሶች፣ የአጥንት ግንባታ መዘግየት፣

በጨለማ ማየት አለመቻል (Night Blindness)፣ የተጉረበረበ ቆዳ፣ ለብርድና ለጉንፋን በቀላሉ መጋለጥ፣ ሳይነስ፣ የሽንት ትቦ ኢንፌክሽኖች፣ በፍጥነት የሰውነት ክብደት ማሽቆልቆል፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት ዋነኞቹ ምልክቶች ናቸው፡፡

ቫይታሚኑን የያዙ ምግቦች አይብ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ ካሮት፣ ጉበት፣ አፕሪኮት፣

ስኳርድንች፡፡

ቫይታሚን B ይህ ቫይታሚን ሰፊ ቤተሰብ አለው፡፡ ቲያሚን፣

ራይቦቭላቪን፣ ፎሊክ አሲድ፣ ባዮቲንና ፓይሪዶክሲን የቫይታሚኑ ቤተሰቦች ለሆኑት ቫይታሚን B1, B2, B3, B5, B6, B7, B9 የተሰጡ ስሞች ናቸው፡፡

ለሰውነትዎ የሚሰጠው ጠቀሜታ ቫይታሚን B1 (ቲያሚን) የኬሚካሎችን ውህደት

ያግዛል፡፡ በተለይ ሰውነት ግሉኮስን ለሃይል ምንጭነት እንዲጠቀም ያደርጋል፡፡

ቫይታሚን B2 (ራይቦቭላቪን) ካርቦ ሃይድሬትስን ይሰባብራል፡፡

ቫይታሚን B3 (ናያሲን) የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ቫይታሚን B5 (ፓንቶቴኒክ አሲድ) በካርቦሃይድሬትስ መሰባበሩ ላይ ከመሳተፉም በላይ

ሰውነት ፕሮቲኖችንና ስቦችን እንዲጠቀም በማድረግ ከብጉንጅ፣ አልሰር እራሱን እንዲከላከል ያግዛል፣ የደም የሊፒድ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የመራቢያ ስርዓት ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ቫይታሚን B6 (ፓይሪዶክሲን) አሚኖ አሲዶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡

ቫይታሚን B7 (ባዮቲን) ስቦች፣ ፕሮቲኖች፣ ካርቦሃድሬትስ በስራ ላይ እንዲውሉ

ያግዛል፡፡ ቫይታሚን B9 (ፎሊክ አሲድ) ይህ ቫይታሚን በጣም አስፈላጊና ለሰውነትም በርካታ

ጠቀሜታዎችን የያዘ ነው፡፡ የምግብ መዋሀድን ያግዛል፡፡ የማህፀን አፍ ካንሰርን ይከላከላል ለሽል በጥሩ ሁኔታ ማደግ ወሳኝ ነው፡፡

Neural Tube በተለመደው ሁኔታ እንዲፈጠር ያግዛል፡፡ በተጨማሪም ቫይታሚን B9 DNA እና ሌሎች Nucleic አሲዶች እንዲፈጠሩ ከሚረዱ ግብአቶች አንዱ ነው፡፡ ለጥሩ እንቅልፍ፣ ለሙድና የምግብ ፍላጎት ተጠያቂ የሆኑት ሲሮቶኒን የተባሉ ኒውሮ ትራንስሚተሮች ዕድገት ወሳኝ ሚና ያለው ቫይታሚን ነው፡፡

የቫይታሚኑ እጥረት ምልክቶች ድካም፣ የሰውነት መዛል፣ ፈጣን የልብ ምትና

አተነፋፈስ፣ የወየበ ቆዳ፣ ፈጣን የክብደት መቀነስ፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ድርቀት

ቫይታሚኑን የያዙ ምግቦች ስንዴ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ ጥራጥሬ፣ ማሽላ፣ ድንች፣ እንቁላል፣

ወተት፣ የበሬ ስጋ እና የአሳማ ስጋ B1- ከጥራጥሬ B2 እንቁላል፣ ወተት፣ ጥራጥሬ፣ የበሬ ጉበት B3 ባቄላ፣ የበሬ ጉበት፣ አሳ፣ ድንች፣ ኦቾሎኒና ስጋ B5 በርካታ ምግቦች ይህን ቫይታሚን ይዘዋል፡፡

ቫይታሚኑን ባክቴሪያዎች አንጀት ውስጥ ነው የሚፈጥሩት B6 ስፒናች፣ ሙዝ፣ ስጋ፣ ቲማቲም፣ አሳ እና በቆሎ

B 7 የዕንቁላል አስኳል፣ ጉበት፣ ባቄላና ኦቾሎኒ B9 አረንጓዴ አትክልቶች፣ ጉበት፣ ኩላሊት፣ እንቁላል፡፡

ቫይታሚን C ከቫይታሚኖች ሁሉ ብዙ የተወራለት ቫይታሚን ሲ

ሳይሆን አይቀርም፡፡ የሰው ልጅ፣ ዝንጀሮ፣ ጎሬላና አይጦች ሰውነታቸው ቫይታሚን ሲ ማምረት የማይችል ብቸኛ ፍጡሮች ናቸው፡፡

ለሰውነት የሚሰጠው ጠቀሜታ ቫይታሚን ሲ ለድድ ጠቃሚ ነው፡፡ ኢንፌክሽን

እንዳይከሰት በመከላከል ቁስል በቶሎ እንዲድን የበኩሉን ይወጣል፡፡ ጉንፋንን በማዳን በኩልም ዝነኛ ስም አለው፡፡

የቫይታሚኑ እጥረት ምልክቶች ቁስሎች ለመዳን ረዘም ያለ ጊዜ ይወስድባቸዋል፣ የድድ

ማበጥና መድማት፣ በቀላሉ የቆዳ መቧጨር፣ ደረቅ ፀጉር፣ ደካማ የበሽታ መከላከል አቅም፣ የአፍንጫ መድማት፣ ድካም

ቫይታሚን የያዙ ምግቦች ሎሚ፣ ብርቱካን፣ መንደሪን፣ ቲማቲም፣ ብሮኮሊ፣

ጎመን፣ እንጆሪ፣ ቃሪያ፣ የፈረንጅ ቃሪያ፣ ባለ አረንጓዴ ቅጠል ተክሎች፣ አበባ ጎመን፣ ፓፓዬ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ቫይታሚን D ‹‹የፀሐይ ብርሃን ቫይታሚን›› ተብሎ የሚጠራው

ቫይታሚን ዲ በአብዛኛው ከፀሐይ ብርሃን የሚገኝ ነው፡፡ ይሁንና ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መጠን እንደ ቆዳቸው ቀለምና እንደ መኖሪያ ስፍራቸው የተለያየ ነው፡፡

ለሰውነት የሚሰጠው ጠቀሜታ Scleroderma እና psoriases የተባሉ የቆዳ በሽታዎች

ይፈውሳል፡፡ የበሽታ መከላከል አቅምን በማሳደግ ካንሰርና መሰል በሽታዎችን ይከላከላል፡፡ የልብና የደም ቧንቧዎችን ጤንነት ይጠብቃል፡፡ ይህም ሰውነታችን የደም ግፊትንና

ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቆጣጠር ያስችለዋል፡፡ ቫይታሚን ዲ የደም የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር

ስለሚያስችል ለስኳር በሽታ ህሙማን ጠቃሚ ነው፡፡ ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን በማድረግ አጥንትን የሚያሳሱ በሽታዎችን ይከላከላል፡፡

የቫይታሚን እጥረት ምልክቶች የዚህ ቫይታሚን እጥረት ስስ አጥንቶች እንዲኖሩና

አጠቃላይ የአጥንት አወቃቀር እንዲዛባ የሚያደርገው ሪኬትስ ይከሰታል፡፡ የአጥንት ህመምና የጡንቻ መድከም ይከሰታል፡፡

ቫይታሚኑን የያዙ ምግቦች መሽሩም፣ ሳልመን፣ ሰርዲን፣ ቱና፣ የአሳ ዘይት፣ እንቁላል ቫይታሚን K ብዙም ያልተነገረለት ጠቀሜታውም ያልተገለፀለት

ቫይታሚን ነው፡፡ በአንጀት ውስጥ የሚመረት ሲሆን በጥቂት መጠን የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ሁሉም ሰው የዚህ ቫይታሚን እጥረት አለበት፡፡

ለሰውነት የሚሰጠው ጠቀሜታ ቫይታሚኑ የደም መርጋትን ይከላከላል፡፡ በጉበት ህመም

የተነሳ የሚከሰት የደም መፍሰስን ያስወግዳል፡፡ አጥንትን በሚያሳሳው Osteoporosis ለተጠቁ ህሙማን በጣም ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ለአጥንት ጤንነት ወሳኝ የሆነውን ካልሲየምን ሰውነታችን እንዲጠቀም ይረዳል፡፡

የቫይታሚኑ እጥረት ምልክቶች መድማት፣ በሴቶች ከባድ የወር አበባ መኖር፣ የድድ

መድማት፣ በምግብ መፍጫ ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የአፍንጫ መድማት፣ በቀላሉ መቧጨር፣ የአጥንት ችግሮች

ቫይታሚኑን የያዙ ምግቦች ስፒናች፣ አተር፣ ብሮኮሊ፣ የሽምብራ ጠርጥር፣ ካሮት

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

በቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል? በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር

አለ፤ አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን

2400 Minnehaha Avenue #204 Minneapolis, MN 55404 (612) 275-0970

በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት የትርጉም ሥራ

ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

ሌላ ያልተስተካከለ እንቅልፍ የታየበት ሌሊት፡፡ እናት ከንቅልፏ ተነስታ የልጇን ሳል በማዳመጥና ለማባበል በመሞኮር ላይ ነች፡፡ በጣም ስለሚያሳስባት ዛሬ ማታ መተኛት ኣትችልም፡፡ ላለፉት ኣራት ቀናቶች፣ ልጇ በአስቸጋሪው ሳል ሰበብ መብላት፣ መጠጣት፣ እንዲሁም መተኛት አስቸጋሪ ሆኖበታል፡፡ ነገ፣ ልጇን ለመንከባከብ ለተጨማሪ ኣንድ ቀን ከስራ ትቀራለች፡፡ መቼ ነው የሚያልቀው በማለት ትገረማለች፡፡ እሷ በጣም ደክሟታል አንዲሁም ልጇም በመጥፎ ሁኔታ ላይ ነው፡፡ መጥፎ ኣጋጣሚ ሆኖ፣ መጨረሻው ቅርብ ኣይደለም ምክንያቱም ይህ ሳል ትክትክ/ደረቅ ሳል ስለሆነ፣ እንዲሁም ለረጂም ግዜ የሚዘልቅ በመሆኑ "የ100-ቀን ሳል" በመባል ይታወቃል፡፡

ትክትክ/ደረቅ ሳል (ፐርቱሲስ)– ከባድና በጣም ተዛማች የማስተንፈሻ ኣካል በሽታ ሆኖ፣ ምልክቱም ተከታታይና ከባድ የሳል ጥቃት ሲሆም ልዩ መግለጫው በሽተኛው አየር ወደ ውስጥ ሲያስገባ የሚሰማው “የመጮህ አይነት” ድምጽ ማስከተሉ ነው፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት ያደርሳል፣ ሆኖም ግን በልጆች ላይ ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ፣ በሚነሶታ ከ3,500 ሰው በላይ በትክትክ በሽታ መለከፋቸውን በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

ደግነቱ ግን፣ የትክትክ በሽታን መከላከል የሚችሉ ክትባቶች አሉ፡ የሚነሶታ የጤና ቢሮ (MDH) ጨቅላዎችና ልጆች ከትክትክ/ደረቅ ስል፣ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ፣ አንዲሁም መንጋጋ ቆልፍ (DTaP) በሽታዎችን በማካተት የሚከላከል በ2 ወር፣ 4 ወር፣ 6 ወር፣ አንዲሁም ከ15 አስከ 18 ወር የልጅነት ዕድሜ የሚሰጥ ክትባት መውሰድን ይመክራሉ፡። የDTaP ማጠናከርያ ክታበት ከ4 አስከ 6 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ይሰጣል፡፡ከ DTaP የሚገኘው መከላከል ከጊዜ በኋላ ስለሚዳከም፣ የሚነሶታ ጤና ቢሮ(MDH) ሌላ Tdap የሚባል

የትክትክ/ደረቅ ሳል ክትባት ለወጣቶች( ከ10-12 ዕድሜ ክልል ውስጥ) አና ለታዳጊዎች እንዲሰጥ ይመክራል፡፡ በቅድመ-ወጣትነት ዕድሜያቸው የTdap ክትባት ያልወሰዱ አዋቂዎች አሁን ኣንድ ክትባት መውሰድ ኣለባቸው፡፡ በዕድሜ ከፍ ያሉ ልጆችና ኣዋቂዎች እራሳቸውን በመከላከል፣ ዕድሜያቸው በጣም ትንሽ በመሆኑ በDTaP ክትባት ሙሉ መከላከያ ማግኘት ለማይችሉ በዙሪያቸው ለሚኖሩ ህጻናቶች የመከላከያ ክበብን መፍጠር ይችላሉ።።

የትክትክ/ደረቅ ሳል ክትባቶች በጣም ውጤታማ ናቸው፣ ሆኖም ግን አንደ ሁሉም ዓይነት ክትባቶች፣ 100% ውጤታማ ኣይደሉም፡፡ ምንም እንኳ ቢከተቡም፣ በበሽታው ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ የትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ ኣብዛኛውን ጊዜ ተመርምሮ ሳይታወቅ ያልፋል ምክንያቱም ኣብዛኛውን ግዜ ጉንፋን በሚመስል ምልክት ስለሚጀምር፤ ሆኖም ግን ለሳምንታት ወይም ወራት የሚዘልቅ ተከታታይ

የሆነ የሳል ጥቃቶች ሊለወጥ ይችላል፡። መጥፎ ኣጋጣሚ ሆኖ፣ ኣንዳንዶቹ በትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ መያዛቸውን ላያውቁ ስለሚችሉ ባለማወቅ ወደ ሌሎች፣ህፃናቶች ጭምር፣ ሊያስተላልፉት ይችላሉ፡፡

አንድ ሀኪም የትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታን ከጠረጠረ፣ በሽታውን በምርመራ ለማረጋገጥ ምርመራ ሊደረግ ይችላል፡፡ በምርመራ የማወቅ ሂደቱ ኣስቀድሞ ከተደረገ፣ የበሽታው ምልክቶች ከባድነት ለመቀነስና አንዳይተላለፍ ለማድረግ የፀረ-ነፍሳት(አንቲባዮቲክስ) መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ የርስዎ ወይም የልጅዎ ሳል ትክትክ/ደረቅ ሳል ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ከህፃን ኣጠገብ ስለመሆን ጉዳይ ሀኪሙን ማናገር ኣስፈላጊ ነው፡፡ ልጅዎ በትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ ተለክፏል ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ወድያውኑ ሀኪም ዘንድ ይሂዱ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንድ ህፃን አመላካች የሆነውን ሳል ወይም ትክትክ የሚል ድምፅ ኣይኖረውም፣ ስለዚህ ከባድ የማስተንፈስ ችግር አንዳይኖር በንቃት ያስተውሉ፡፡

በበለጠ ለመረዳት፣ የሚነሶታ ጤና ቢሮ(MDH) የትክትክ በሽታ(ፐርቱሲስ) ድረገፅ

በwww.health.state.mn.us/pertussis ይጎብኙ፡፡ በተጨማሪ ከአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠርያና መከላከያ

ማእከሎች (CDC) www.cdc.gov/pertussis ድረገፅ

በመጎብኘት ወይም 1-800-CDC-INFO በመደወል መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

ስደተኞች... ከገጽ 1 የዞረ

‘ይህ የስደተኞች አሃዝ በሪፊውጂ የመጡትንም፣ እዚህ ሃገር መጥተው ጥገኝነት የጠየቁትንም እንደሚያጠቃልል ያስታወቀው ዲፓርትመንቱ ብዛት ያላቸውን ስደተኞች የተቀበሉትም ራምዜና ሄኒፐን ካውንቲዎች እንደሆኑ በሪፖርቱ ላይ አስቀምጧል። በ2011 ከኤርትራ 20 ስደተኞች፣ ከሶማሊያ 327፣ ከሱዳን 12፣ ከታንዛኒያ 2፣ ከዩጋንዳ 2፣ ጋምቢያ 1፣ ከጊኒ 1፣ ከኬንያ 11፣ ከላይቤሪያ 21 ስደተኞች ሚኒሶታ ገብተዋል።

ለነዚህ ስደተኞች መካከልም የጤና ምርመራና ህክምና እንደተደረላቸው አስታውቆ የቲቢ፣ የሄፒታይተስ ቢ ኢንፌክሽን፣ በግብረ

ሥጋ ግንኙነት ወቅት ለሚተላለፉ በሽታዎች፣ የወባ ክትባቶች እና ህክምናዎችን እንዳገኙ አብራርቷል።

Page 17: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

አዘጋጅ፦

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

‹‹እየጣፈጠኝ ያዘወተርኩት ስኳር፤ ለስኳር ህመምስ ያበቃኝ ይሆን?››

እንዴት እንደለመድኩት ባላውቅም ስኳር በብዛት የገባባቸውን ምግቦች መመገብ በጣም ነው የምወደው፡፡ ሌላው ቢቀር እንጀራ እንኳ በሽሮ ከምመገብ እላዩ ላይ ስኳር እየነሰነስኩ ስበላው ነው ደስታ የሚሰጠኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ግን ይሄን ድርጊቴን ከልጅነቴ ጀምረው አይወዱልኝም፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ለስኳር በሽታ ትጋለጫለሽ የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ ጣፋጩ ስኳር የስኳር በሽታን ያመጣል? እየጣፈጠኝ ያዘወተርኩት ስኳር ለኮሌስትሮል በሽታ እንዳጋለጠኝ ተነገረኝ፤ ምን ይሻለኛል?

“”ሳምራዊት በቀለ

‹‹ለኮሌስትሮል ችግር ያጋለጠኝ የስኳር ፍቅር ይሆን?››

ሻይም ይሁን ቡናና ሙቅ ስኳር ካልበዛባቸው በስተቀር አልጠጣም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ስኳር ድንች መመገብ የዘወትር ምርጫዬ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ልማድ የዛሬ ሳይሆን ላለፉት 26 ዓመታት አብሮ የኖረ ነው፡፡ የሰውነት ክብደቴም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ከ50 እና ከ100 ሜትር በላይ ፈጠን ፈጠን ብዬ መራመድ የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጤንነት አልሰማኝ ሲል ወደ አንድ ጤና ተቋም ሄጄ ተመረመርኩ፡፡ በደሜ ውስጥ የቅባት መጠን መጨመር (የኮሌስትሮል) ችግር እንዳጋጠመኝ ተነገረኝ፡፡ ለመሆኑ ለኮሌስትሮል ችግር ያጋለጠኝ ስኳርነት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አዘውትሬ መመገቤ ነው ወይስ የሰውነት ክብደቴ ከመጠን በላይ መሆኑ ነው?

ወ/ሮ አለምፀሐይ

‹‹አርቴፊሻል ስኳር ብጠቀም ለሌላ የጤና ችግር

ያጋልጠኝ ይሆን?›› ከስኳር በሽታ ጋር ላለፉት ዓመታት

አብረን ኖረናል፡፡ 45 ዓመቴ ነው፡፡ ስኳሬን ለመለካት ወደ ህክምና ተቋም በሄድሁ ቁጥር ከምግብ ስርዓቴ ውስጥ ስኳርንም ሆነ ሌሎች ጣፋጭ መጠጦችን እንዳስወግድ ደጋግመው ነግረውኛል፡፡ እኔ ግን ሻይና ቡና ከመጠን በላይ ስለምወድ ስኳር መተው አልቻልኩም፡፡ ይሄን ችግሬን የተረዱት ሐኪሞች አርቴፊሻል ስኳር ብጠቀም ለጤናዬ መልካም መሆኑን መክረውኛል፡፡ አርቴፊሻል ስኳርን ብጠቀም ለሌላ የጤና ችግር አያጋልጠኝ ይሆን? ከእውነተኛው ስኳርስ ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

አቶ ታረቀኝ ጡኡመልሳን ስኳር ሁላችንም በየዕለቱ ደጋግመን ከምንጠቀምባቸው

ምግቦች በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው፡፡ በብዙዎቻችን ማለት ይቻላል በምንጠጣውም ሆነ በምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ ስኳር መኖሩ ቀዳሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ከደም ግፊት፣ ከስኳርና ከኮሌስትሮል ህመሞች በተጨማሪም ከመጠን በላይ ከሆነ አካላዊ ውፍረት ጋር በተደጋጋሚ ስሙ አብሮ ይነሳል፡፡ ስኳር ተመጋቢ መሆን የሚያስከትለው የጤና ችግር አለ? ምን ያህል የስኳር መጠን መመገብ ነው ለጤና ጠንቅ የሚሆነው? የሚሉና ከስኳር ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች በስልክና በደብዳቤ ደርሰውን ተመልክተናቸዋል፡፡ በላካችኋቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን አንድ የህክምና ባለሙያን አነጋግረናል፡፡ ዶክተሩ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ናቸው፡፡

ዘ- ሃበሻ፡- ጣፋጩ ስኳር ከጣዕም ፈጣሪነቱ ባሻገር በምግብነት የሚያስገኘው ጠቀሜታ ምንድን ነው?

ዶ/ር ፡- ስኳርን ጠቅለል ባለ መልኩ ትርጓሜውን ስናየው የመጣፈጥ ጣዕምን የሚሰጠን ምግብ እንደማለት ነው፡፡ በምግብ ይዘትነቱ የሚመደበው ከካርቦሐይድሬት ነው፡፡ በውስጡ ሐይድሮጅንና ኦክስጅን የሚባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ ስኳር ቀላልና ቅይጥ ተብሎ በሁለት መሰረታዊ አይነቶች ይከፈላል፡፡ ቀላል የሚባለው በነጠላ የምናገኘው ሲሆን ለምሳሌ ግልኮስን፣ ፍርኩቶስና ጋላክቶስ የሚባሉትን የስኳር አይነቶች የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡ ቅይጥ የምንለው ደግሞ በጥንድ በጥንድ የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ማልቶስ፣ ሰክሮቶውስ፣ እና ላክቶስ በመባል የሚታወቁ ቅይጥ የስኳር አይነቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም በተለምዶ የምንጠቀምበት ስኳር ስኩቶስ በመባል የሚታወቀውን ነው፡፡ ይሄን ቅመም በብዛት የምናገኘው ከሸንኮራ አይነቶች ደግሞ ከተለያዩ ምግቦች ቀጥታ ባልሆነ መንገድ እናገኛቸዋለን፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የሰዎች የስኳር ተመጋቢነት ልምድ የመጨመር እንጂ የመቀነስ ሁኔታን እያሳየ አይደለም፡፡ አገራችንን ጨምሮ በዓለም ላይ እ.ኤ.አ በ2011 ይፋ የተደረገ መረጃ

እንደሚያመለክተው 168 ሚሊዮን ቶን ተመርቶ ለተጠቃሚዎች ተከፋፍሏል፡፡ ይሄ ማለት አንድ ሰው በአማካኝ በዓመት 24 ኪሎ ስኳር ይጠቀማል፡፡ ስኳር ተመጋቢ መሆን ለተለያዩ ጤና ነክ ችግሮች የሚያጋልጥ ቢሆንም ዛሬም ድረስ የሰዎች አጠቃቀም ላይ ግን ምንም አይነት ለውጥ አይታይም፡፡

ስኳርን ከሸንኮራ አገዳና ከስኳር ድንች በተጨማሪ ከአትክልት፣ ከፍራፍሬ፣ ከወተት፣ ማርና ከመሳሰሉ የምግብ አይነቶች ልናገኝ እንችላለን፡፡ በቀጥታም ይሆን ቀጥታ ባልሆነ መልኩ የምንመገበው ስኳር ሰውነታችን በመሰባበር ወደ ጉሉኮስ ይቀይረዋል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ሴሎች የተመረተውን ጉሉኮሱን በማቃጠል ለመኖር፣ ለመንቀሳቀስና ለመስራት የምንጠቀምበትን ኃይል ያስገኝልናል፡፡ በሌላ አገላለፅ ከ1 ግራም ጉሉኮስ 4 ካሎሪ (ኃይል ወይም ጉልበት) እናገኛለን፡፡

ዘ- ሃበሻ፡- አንዲት አንባቢያችን በላኩት ደብዳቤ ‹‹ከምግብ ገበታዬ አይለየኝ ያልኩት ስኳር ምላሴን አጣፍጦ ጤናዬን አመረረው፡፡ ሰውነቴ መሆን ከሚገባው በላይ ጨምሯል፡፡ የሰውነቴ ውፍረት ‹‹ሮቶ›› የሚል ቅፅል ስም እስኪወጣልኝ አድርሶኛል፡፡ ከሰውነት ክብደቴ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ባላውቅም የደም ግፊት በሽታም አለብሽ ተብያለሁ፡፡ እኔን ያጋጠመኝ ችግር ከስኳር ተመጋቢነት ጋር ይያያዛል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ስኳር ተመጋቢነት ማዘውተር ከጤና ችግሮች ጋር የሚያያዝበት ሳይንሳዊ ምክንያት ይኖር ይሆን?

ዶ/ር ፡- ጠያቂዋ እንዳሉት በምግብ ስርዓታቸው ውስጥ ስኳርን ያዘወትራሉ፡፡ ከፍ ያለ የሰውነት ክብደት አላቸው፡፡ በእርግጥ የሰውነት ክብደት መጨመር ሌላ ነገር ሳይጨመርበት ለተለያዩ የጤና ችግሮች የሚያጋልጥ መሆኑ በግልፅ ይታወቃል፡፡

ከምንጠቀመው ስኳር የሚመረተው ጉሉኮስ የሚሰጠን ኢነርጂ ከሚፈለገው በላይ ሲሆን ሰውነታችን የሚያስወጣበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ ከምንጠቀምበት መጠን በላይ የሆነው ኃይል በሰውነታችን ውስጥ ይከማቻል፡፡ የተከማቸውን ካርቦ ኃይድሬት (ስኳር) ሰውነታችን ወደ ፋትነት ይለውጠዋል፡፡ ሳንጠቀምበት ቀርተን ወደ ፋትነት የተለወጠው ኢነርጂ የሰውነታችንን ክብደት መጨመሩ አየቀርም፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ውሎ አድሮ ከቀላል እስከ ከባድ የጤና ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም፡፡

ዋና ዋና የሚባሉትን ስኳር አማጭ የጤና ቀውሶችን በተወሰነ መልኩ ለማየት እንሞክር፡፡

- የደም ውስጥ ስኳር መጨመርን (ስኳር በሽታን) ያስከትላል፡- ሰውነታችን ከሚፈልገው መጠን በላይ ስኳር ስንመገብ ምንም

አይነት ጊዜ ሳይሰጥ በፍጥነት ተሰባብሮ በደማችን ውስጥ ይገባል፡፡ በዚህ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ስኳር በደም ውስጥ ይፈጠራል፡፡ በዚህ ጊዜ የቆሽት ስራ ይስተጓጎላል፡፡ በዚህም ሳቢያ ቆሽት የሰውነትን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ኢንሱሊንን በብዛት በማምረት ይረጫል፡፡ ይህ ሁኔታ ከቀጠለ ቆሽት ኢንሱሊን የማምረት አቅሙ እየተዳከመ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡ - ከመጠን በላይ የሰውነት ክብደት መጨመር ያመጣል፡፡ በየዕለቱ ከምንመገበው ስኳር የሚመረተውን ግሉኮስ በአግባቡ ማቃጠል ካልተቻለ ወደ ፋት እየተለወጠ ይከማቻል፡፡ ይህ ሁኔታ የሰውነት ክብደት ከሚፈለገው መጠን በላይ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡ የሰውነት ክብደት አላግባብ ሲጨምር ቆሽት ኢንሱሊን ማምረት ብትችልም የተመረተው ኢንሱሊን የሚፈለግበት ቦታ ሄዶ መስራት አይችልም፡፡ ካልሰራ ደግሞ ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላችን ሰፊ ይሆናል፡፡ ከስኳር በሽታ በተጨማሪ የሰውነት ክብደት በመጨመሩ ምክንያት ደም ግፊት፣ የኮሌስትሮልና የኩላሊት ጤና ችግሮችን ያስከትላል፡፡ - የልብና የደም ስር ጤና ችግሮችን ያመጣል፡- ስኳርን አዘውትሮ መመገብ በሚያስከትለው የፋት ክምችት ሳቢያ የልብ ጡንቻዎች ድክመትንና የደም ስሮች መጥበብን በማምጣት አጠቃላይ የጤና ሁኔታችንን ያናጋዋል፡፡

- ለኮሌስትሮል መጠን መዛባት ያጋልጣል፡- ኮሌስትሮል ጠቃሚና ጎጂ በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ መጠኑ ከፍ ያለ ስኳር ተመጋቢ መሆን ጠቃሚውን የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ ሲያደርገው በአንፃሩ ደግሞ ጎጂው የኮሌስትሮል አይነት መጠን እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡ ይህም አጠቃላይ የጤና ሁኔታችን ችግር ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡

- የመርሳት (አልዛይመርስ) በሽታን ያስከትላል፡- ቀይ ስጋን፣ ቅባታማና ሙሉ በሙሉ ተፈትገው ገለባቸውን ያጡ ምግቦችን መመገብ ለመርሳት (ለአልዛይመር) በሽታ ያጋልጣል፡፡ ከተገለፁት ምግቦች በተጨማሪ ስኳርና ሌሎች በተለይም ጣፋጭነት ያላቸውን ምግቦች አዘውትሮ ከመጠን በላይ መመገብ ዕድሜ እየጨመረ በሚሄድበት ጊዜ ለትክክለኛው የመርሳት በሽታ ያጋልጣል፡፡

- የማየት አቅምን ያዳክማል፡፡ በአይናችን ውስጥ ሬቲና የሚባል ምስል ማረፊያ አካል አለ፡፡ ሬቲናው ውስጥ ደግሞ ማኩላ የምትባል ቦታ አለች፡፡ ማኩላ ማለት በብርሃን ጊዜ አይናችን የምናየውን ምስል ጥርት አድርጎ እንድናይ የሚያደርገን ነው፡፡ ነገር ግን ስኳር ተመጋቢነትን ስናዘወትር ማኩላ ከጊዜው ቀድማ እንድታረጅ ትገደዳለች፡፡ በዚህም ሳቢያ ለአይነ ስውርነት የመዳረግ እድልን በከፍተኛ ፍጥነት ያባብሰዋል፡፡

- የጥርስ መበስበስን ያመጣል፡- አዘውትረን የምንመገበው ስኳር ጥርስ ላይ ሲከማች ባክቴሪያዎች በማራባት ጥርስ እንዲበሰብስ ያደርጋሉ፡፡ (ስኳር... ወደ ገጽ 16 የዞረ፟)

ደርሶ የሚያድነን ተመልካች ባየው

11/27/2012 ሚኔያፖሊስ

ዘመናይ ባይ ሰውነት ቆሞ እያየሁት በዓውደምሕረት ለብሷል ቆብም ደፍቷል የተካነ መስሎት ቦታውማ የተቀደሰበት የተፀለየበት ያራገፈውን ከርሱም አንደበት ምዕመኑ ሰምቶት ገርሞት የሚያዳምጠው ክቡሩ የግዜር ፍጥረት መስሎት ነበር ያገኘ ትምህርት በዛብኝ አለ ተደናቆርኩ በጩኸት አከታተለ የስድብ ናዳ መዓት እያስመሰለ ፀሎት ሽሙጥና አሽሙር ተካብተውበት ገባ ከመቅደስ ሊተኛበት ሰኦቴን ብሎ ጓጓ ለኪሱ ወይ አልመነኮሱ አንቱታ ፈልገው ባይቀድሱ ባንደበታቸው ቤቱን ባያረክሱ ከጩኸት ጋር እየደነሱ ታሪክ መስሏቸው የማይኖር በመደገፍ የዱሮውን መንበር አስበው ኖሮ የማይወጣ ምስጢር ሕዝብ ሳያውቀው ሳይመክር ለጳውሎስ ሊሸጡ የኛን ደብር አርፎ መቀመጥ ይሻል ነበር ባልነበሩበት ቤቱ ሲቆረቆር የኔ ብለው በባዶ ከመፎከር ምን አለ መቅጠፉ ቢቀር? ሰይጣኑ መጣ ሰው ተመስሎ? ወጣት ነኝ ብሎ? አዛውንት ብሎ? ብሶበትም ቄስ ነኝ ብሎ !! ተስገበገበ ጌታ ልሁን ብሎ ቀዳሽ ወዳሽ መስሎ እንዳህያው ባመድ ላይ ተንከባሎ አዲሱን ጉድህ ታየብህ ብሎ ስንቱን አሣየን ብሎ ብሎ ተለዋዋጭ እንደገበሎ ዓይን ያወጣ ዕብድ ዘሎ ዘሎ ስብዕነቱ ተመሰቃቅሎ ወዲያ መጣል ነው ከስር ፈንቅሎ ሁሉን ታዝበው ምዕመናን ዛሬማ እያሉ በቃን ይብቃን ቤቱ የቀራጭ አይሁንብን አሉ ጮሁ ጭፈራው ይቅርብን እንድንፀልይ በሰላም እየመጣን መቼ ተሣነህ የውስጣችን በላ በላ ጌታችን አድነን እንዳንጓዘው በድጋሜ ተሰደን አንተው ጠብቀን ጌታችን !!

ሾሌ ያ ነጭ ጠላ ክንፈ ሚካኤል ([email protected]) ሾሌ ያ ነጭ ጠላ ለሙዚቃው አድባር ለታላቁ ጥላ ጥላሁን ያ ጥላ ሁን ከየት እናግኝህ አሁን ማን ያጥላልን በዚህ ዘመን እንዲያው ሃምሳ ዓመት መዝፈን እስር ጨለማ ብርሃን ሲፈራረቁብህ አልፈህ ሁሉን። ምን ያረጋል ሞት አይቀር ቀድመህ ብለሃል ደጋጉን ቢያስቀር አንተም አንዱ ነበርክ ከሚቀሩት ለኢትዮጵያ ብለው ከኖሩት። ቢለወጥ ሞት-ተራ ለሚወዱት ለጥላሁን ነበር የኔ ሕይወት ግን አይቀርም ዕልፈት ተለየን ከጥላሁን ድንገት።

ሾሌ ያ ነጭ ጠላ ለታላቁ አድባር ለታላቁ ጥላ ከእችክ እችክ እስከ ኡኡታ አያስከፋም ከእይዋት ስትናፈቀኝ እስከ መለያየት ሞት ነው ከምክሬን ስምኝ እስከ እንጉዳዬ ነሽ ከልጅቷ እስከ ኩሉን ማን ኳለሽ።

ካንዱ ቀን እስከ እያሳቀችኝ ካራዊቱ እስከ የሕይወቴ ሕይወት ካሳለፍነው እስከ የጥንቱ ትዝ አለኝ ከምኞቴ ተሳካ እስከ አባት ደስ ይለዋል ይህን ሁሉ ፀጋ ማን ያገኘዋል። ካመልካች ጣት እስከ ሩቅ ምስራቅ እንዲህ እንደ አሁኑ ሳንራራቅ ከሰፊው ህዝብ እስከ ነገሥታት ሾሌ ያ ነጭ ጠላ ዝንት ዓመታት ከሌሊት ጨረቃ እስከ ዓይኔ ሁልጊዜ

ከዘምባባ ዛፍ ነሽ እስከ ሞናሊዛ ዘፈን እንደ አሁኑ ሳይንዛዛ ሙዚቃው ጣዕም ያለው ለዛ አሳለፍነው በዋዛ ፈዛዛ። ከዋይ ዋይ ሲሉ እስከ ግፋ በለው ካገር የጋራ ነው እስከ ሀገር አለኝ ሾሌ ያ ነጭ ጠላ ለጥላሁን የማይሰለች እስከ አሁን።

ከምግብ አይነቶች እስከ እንቁጣጣሽ ከዘንድሮ እስከ ምን ታደርጊዋለሽ የታሰረበት ሦስት አልማዞች። እማይሰለች እማይጠገብ መድረክ አይበቄ ስግብግብ በላንቃ ድምፅ በቲያትር ባይን ጥቅሻ ሁለ ገብ። ካገር ፍቅር ብሔራዊ ኦልኬስትራ ኢትዮጵያ ከሁሉ ሠርቶ ከባለ ሙያ ካድናቆት በላይ ለሁሉ መለኪያ። ከስግብግብ ጆሮዬ ለዕውነት እሞታለሁ ከባለ ጠላ እስከ ሁሉን አይቼዋለሁ። ትቶልን ካለፈው ይሁነኝ ማልቀሻ ዘላለም እንዲሆን ለኛ ማስታወሻ። ተጠልቆ ያልቃል ወይ ዓባይን በጭልፋ የጥላሁን ሥራ ኦሜጋና አልፋ ልሰናበተው እንግዲህ በይፋ ለዘላለሙ እሱም ያንቀላፋ በአርካን ፉኔ በሾሌ ያ ነጭ ጠላ ለሙዚቃው አድባር ለታላቁ ጥላ።

ግጥሞችን ላኩልን፤ እናስተናግዳለን።

በፒያሳ ገበያ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል አንዳንዶቹን እናስታውሳችሁ

ታዋቂው የኢንሹራንስ ባለሙያ ኤፍሬም በጥሩ ዋጋ ጥሩ የኢንሹራንስ ከለላ ለመኪናዎ፣ ለቤትዎና ከፈለጉም ለጤናዎ ያስገኝልዎታል

በቦሌ ሃዋላ እና በመኒ ግራም በመጠቀም ወደ ሃገር ቤት

ገንዘብዎን በፍጥነት እናደርሳለን

የበግ፣ የበሬና የዶሮ ሥጋ አለን፤ ለቁርጥ የሚሆነውን ጊርጊሮ ሥጋችንንም

ይጠይቁን

በፒያሳ ገበያ፡ ቅመማ ቅመማ ቅመሞች፣ ጤፍ፣ ጀበና፣ ሲኒ፣ የሃገር ባህል

አልባሳት፣ ወርቅ፣ ሻንጣዎች፣ የስልክ ካርዶች፣ አዳዲስ ሙዚቃዎችና ቪዲዮዎች

ሁሉም አሉን።

ኬተሪንግ ጀምረናል

Page 18: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

በ 55 ዓመቱ ቅዳሜ ሕዳር ስምንት ቀን 2005 ከጠዋቱ 5am ላይ ያረፈው ዶ/ር መሠረት ቸኮል የቀብር ሥነ- ሥርዓት በሚኒሶታ ተፈጽሟል። ኢትዮጵያውያን የዶ/

ር መሰረት ሃዘብ የሚወጣላቸው አይደለም። በመቶዎች የሚቆጠሩ ወዳጆቹና ቤተሰቦቹ በተገኙበት በተከናወነው የቀብር ሥነ- ሥርዓት በሕይወት ዘመኑ ያከናወናቸው ሥራዎች ሁሉ ተዘክረዋል።

በሚኒያፖሊስ ሌክውድድ መቃብር የዶ/ር መሠረት ቀብር የተፈጸመ ሲሆን፤ በቤተልሄም ሉተራን ቸርች በተደረገው የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ በሚኒሶታ የሚገኙ ታላላቅ ጸሐፊያን ለዶ/ሩ ያላቸውን ክብር በግጥም ገልጸዋል። በተለይ አንድ ልጁ ኤደን መሠረት ከልጅነቷ ለአባቷ የተለየ ፍቅር እንደነበራትና ለአባቷ ከነበራት ፍቅር የተነሳ ምክሮቹንና እርሱነቱን ትከተል እንደነበር ገልጻለች። “መሰረት መሠረት ነው፣ መሠረት ማድረግ የሚችለውን ያደርጋል፣ መስጠት የሚችለውን ይሰጣል ራሱን ከሌላ ሰው ጋር አያወዳድርም” የሚለውን አባባሉን አረአያ በማድረክ በዚህ አባባሉ ራሷን ፈልጋ እንዳገኘችና ይህንን በሕይወቷ ላይ ተግባራዊ ማድረጓን በመናገር በአባቷ መታሰቢያ ላይ የታዳሚውን መንፈስ ቆንጠጥ አድርጎ የያዘ ዝማሬ አሰምታለች። ሕዝቡም ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በእንባ ተራጭቷል።

የዶ/ር መሠረት ቸኮልን የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ከአባቱ ከአቶ ቸኮል ረታ እና ከ እናቱ ወ/ሮ የእናት ፋንታ አስረስ በ1950 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለደ። በአምስተኛው ዓመቱ በፈንጣጣ በሽታ ተጠቂ በመሆኑ በተደረገለት ህክምና ሕይወቱን ለማትረፍ ቢቻልም የዓይን ብርሃኑን የማጣት አደጋ በስምንት ዓመት ዕድሜው ደረሰበት። በሰበታ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል። በተማሪነት ዘመኑ ለመዝሙርና ለሙዚቃ እንዲሁም ለመጽሐፍ የነበረው ፍቅር ከፍተኛ ነበር። በዕድገት በህብረት ዘመቻ በባህር ዳር ከተማ በመምህርነት ተመድቦ ግዴታውን ለመውጣት ችሏል። በ1971 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲቱት በ እንግሊሽ ዲፓርትመንት ገብቶ በ1974 ዓ.ም ከጠቅላላው ተማሪ በላቀ ውጤት የዓመቱ ኮከብ ተማሪ ሆኖ ከወቅቱ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት እጅ የወርቅ ተሸላሚ በሆን የመጀመሪያውን ዲግሪ አገኘ።

ከዚያም Ethiopian Extrnal Service ተብሎ በሚታወቀው መስሪያ ቤት በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ በሪድዮ ጣቢያው በየሳምንቱ የሚደረገውን የባህልና የሙዚቃ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች የሚጋበዙበት የውይይት ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያገለገለ ሲሆን ማዘር ትሬዛን በፕሮግራሙ ላይ ለማቅረብ የቻለ፤ በአነባበቡ፣ በፕሮግራሙ ጥልቀት፣ ታማናዊ በሆነ አቀራቡ የብዙ አድማጮችን ቀልብ የሳበ ነበር። በተለያዩ ሃጉሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን ያገኘ ሲሆን ከቀይ ጨረቃ አፍሪካ አቀፍ

የሬድዮ ፕሮግራም አምስት ጊዜ እውቅና አግኝቷል። በ1982 ዓ.ም ከባለቤቱ ወ/ሮ በልዩ በላይ ጋር ህጋዊ

ጋብቻ በመፈጸም በ1983 ዓ.ም የትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ ሜኔሶታ በማቅናት የማስትሬት ዲግሪውን ጀምሮ በ1986ና በ1989 ዓ.ም የኮምዩኒከሽንና በፖለቲካል ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን፣ በ1991 እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን (PHD) በመገናኛ ብዙሃን ትምህርት ከዩኒቨሪሲቲ ሚኒሶታ አግኝቷል።

ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በከፍተኛ ተምህርት ተቋሞች በማስተማር ሥራ ተሰማርቶ በዩኒቨርሲቲ ሚኒሶታ፣ በዊስካንሰን ሪቨል ፎል ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሃዮ በሚገኘው አሽላንድ ዩኒቨርስቲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን ከመምህርነት እስከ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት አገልግሏል።

ከማስተማሩና ከምርምሩ ተጨማሪ የተለያየ ኮሚቴዎች አባልና ስብሳቢ በመሆን ሙያዊ ግልጋሎት ሰጥቷል። በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፊችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አቅርቧል። እንዲሁም

ከአካዳሚ ጋር ያልተያያዙ ሁለት መፅፎችን ለአንባብያን አበርክቷል። The quest for press freedom በኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ሜዲያ ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ሰጥቷል። ይህ መጽሐፉ በቅርብ ጊዜ በገበያ ላይ እንደሚውል ሕይወቱ ከማለፉ በፉት ለጓደኞቹና ለዘመድ አዝማድ አብስሯል። እንዲሁም ሁለት ለመጨረስ ያልታደላቸው ያሬድ ገብረሚካኤልና የዛሪኤይቱ ኢትዮጵያ ጽሁፎችን ለ Encyclopedia Aethiopica Vol.5 አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወቃል። ዶክተር መሠረት ከመምህርነትና ከምርምር ሥራዎቹ ባልተናነሰ መልኩ የሚታወቀው በሰብአዊ መብት ተሟጋችነቱ፤ ለሃገሩ ባለው ቅናቂ አስተሳሰብና በተለይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በሚሰጠው ትንታኔ ነበር። በዚህ በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ የ እንግሊዘኛ ዜና በማዘጋጀት፤ በአሜሪካ ሬድዮ ጣቢአ የዘወትር ተባባሪ በመሆን፤ በ1995 ምርጫ ዘመን ድምጽ ላጡ ድምጽ በመሆን ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ዕውቀቱን በመለገስ፣በተለይዩ ከተሞች በተናጋሪነት በመጋበዝ አስተዋጽሆ አድርጓል።

በ2007 በሜሪላንድ ተቀማጭ የሆነ የታዋቂ ግልሰቦችን ታሪክ የሚያጠናቅር ድርጅት በማቁቋምና የድርጅቱም ሊቀመንበር በመሆን አገልግሏል። በሕይወት ዘመኑ ብዙ ልጆችን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ አድርጓል።

መሠረት በሥራው ላይ የማይኩራራ፣ ይህን አደረኩ ብሎ የማይናገር፣ እራሱን ዝቅ አድርጎ ከማንኛውም ሰው ጋር ተግባብቶ የሚኖር፣ ለ እውነት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ጓደኞቹ ይናገራሉ።

ባለፉት ሁለት ወራት የጉበት ካንሰር በሽተኛ መሆኑን ካወቀ በኋላ ከእራሱ ይቅል ለወገኖቹ በማሰብ ሌሎች ተገቢውን ምርመራ እንዲያከናውኑ ያሳስብ ነበር። ዶ/ር መሠረት ቸኮል በተወለደ 55 ዓመቱ ቅዳሜ ሕዳር ስምንት ቀን 2005 ከጠዋቱ 5am ላይ ህክምና ሲደረግለት በነበረው በፓርክ ኒክለት ሜተዲስት ሆስፒታል ባለቤቱን ወ/ሮ በልዩ በላይን፣ ልጁን ኤደን መሠረትን፣ ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን

በመለየት ከዚህ ዓለም አልፏል።

ቴዲ እና ጂጂ.... ከገጽ 6 የዞረ

እነዚህ ሁለት አርቲስቶች የሚጋሯቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ሁለቱም ወደ ሬጌው ዘውግ የሙዚቃ ያዘነብላሉ። ሁለቱም ልዩ የጥበብ ተሰጥዖ ያላቸው፣ በስራቸው የሌላ ጥገኛ ያልሆኑ፣ ሁለቱም የሚሰሩትን የሚያውቁ የሚያውቁትንም የሚሰሩ አርቲስቶች ናቸው። ሁለቱም ለጥበብ ስራቸው መስዋእትነትን የከፈሉ ናቸው። የህዝብን ቀልብ ሊስቡ ፤ የህዝብን ልብ ሊገዙ ያስቻላቸው ምስጢርም ይኸው ነው። የኢትዮጵያው የሙዚቃ አባት አቶ አለማየሁ ፈንቴ በኢቲቭ ቀርበው የሚያደንቁትን የሙዚቃ ሰው ሲጠየቁ ሳይግደረደሩ ነበር "ጂጂ" ፤ እጅጋየሁ ሽባባው ፤ ሲሉ የመለሱት። የኦሮምኛ ሙዚቃ ባህሉን ሳይቀይር አገርኛና አለም አቀፍኛ ቃናና እውቅናን የሰጠው ታዋቂው ድምጻዊ አሊ ቢራ ደግሞ ከዘፋኞች ቴዲ አፍሮን እንደሚያደንቅ በዚሁ ቴሌቭዥን ተሰምቷል።

በአለማችን የጥበብ ሰዎች ሚና ጎልቶ የሚታየው ተፈጥሮ ባደላቸው የጥበብ ስራ ብቻ ሳይሆን፤ እነዚህ ሰዎች በጥበብ ስራቸው ውስጥ ለህዝብ በሚያስተላልፉት መልእክትም ጭምር ነው። ጥበብ አንድን ህብረተሰብ ይቀርጻል :: የሙዚቃ አርቲስቶች ስለ ስጋዊ ፍቀር ብቻ ሳይሆን ስለ ህዝብ፣ ስለ ሃገር፣ ሰለ መብት ወዘት የሚቀኙዋቸው ቅኝቶች ህብረተሰብን የመለወጥ ሃይል አላቸው። የናይጄሪያው ፌላ ኩቲ እና ጃማይካዊው የሬጌ አባት ቦብ ማርሊይ በዚህ ረድፍ ያበረከቱት ሚና ቀላል አይደለም።

እናቱ በጸረ- ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ታጋይ ፤ አባቱ ደግሞ የቤተ ክርስትያን አገልጋይ ቄስ ነበሩ - ፌላ ኩቲ። እ.ኤ.አ. በ1958 ህክምና እንዲያጠና ቤተሰቦቹ ወደ ለንደን ቢልኩትም፣ የህክምና ዶክትሬቱን ወደ ጎን በመተው ሙዚቃ ማጥናትን መረጠ። ሁለቱ ወንድሞቹ በህክምና ተመርቀው ዶክተር ሲባሉ ፌላ ኩቲ ግን ዶክተር ሆኖ አንቱ መባልን አልመረጠም።

የሙዚቃውን ትምህርት አጠናቅቆ ልዩ የጃዝ ባንድ መሰረተ። ፌላ ኩቲ ሃኪም ሆኖ ስጋዊ በሽታን ከማከም የላቅ ህክምና እንዳለ የተረዳው ገና በለጋ እድሜው ነበር። የጥቁር ዘር መረገጥ እና የበታችነት ስሜት ያመጣው በሽታም ህክምና እንደሚያስፈልገው ጠንቅቆ የተረዳ ባለ ራእይ መሆኑን የኋላ ኋላ ስራዎቹ መስክረዋል። የሰው ልጅ ጭቆና እንዲወገድ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ በሙያው አበርክቷል። ከነጮች የበላይነት እና ከአንባገነኖች ግፍ ህዝብ ነጻ እንዲሆን በሙዚቃው የታገለ ጀግና ነው። ለዚህም መስዋእትነትን መክፈል ነበረበት።

ፌላ ኩቲ በሙያው ያመነበትን በማድረጉ ምክንያት ታስሯል፣ ተደብድቧል፣ ከሃገርም እንዲወጣ ተደርጓል። ፌላ ጥቁሮችን በመንፈስ ነጻ የማውጣት ህልም ነበረውና አሜሪካ በመጓዝ ‘ ብላክ ፓወር’ የተሰኘ ንቅናቄን መድስርቶ ነበር። የኋላ ኋላ የአሜሪካ ባለስልጣናት ከሃገር እንዲወጣ አደረጉት እንጂ። አንባገነን መሪዎች በአካሉ ላይ ያደርሱት የነበረው ስቃይ ለሱ ኩራቱ ብቻ አልነበረም። የባሰ መንፈሰ ጠንካራ አደረገው። በአለም ዘንድ ዝናንና ከበሬታንም አተረፈለት።

ወደ ሬጌው ዘውግ ስንገባ ደግሞ የቦብ ማርሊ ስራዎች እናገኛለን። የቦብ ስራዎች በእጅጉ የሚያንጸባርቁት በማህበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ነው። ቦብ ለጥቁሮች በተለይ ለአፍሪካ ነጻነትና ሰላም ብዙ አቀንቅኗል። በተለይ ዋር፣ ጌት አፕ ስታንድ አፕ እና ኦነ ላቭ በሚሉት ስራዎቹ ሚሊዮኖችን ከማነቃቃት አልፎ በአለም ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።

ወደ ሬጌው ዘውግ ስንገባ ደግሞ የቦብ ማርሊ ስራዎች እናገኛለን:። የቦብ ስራዎች በእጅጉ የሚያንጸባርቁት በማህበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ነው። ቦብ ለጥቁሮች በተለይ ለአፍሪካ ነጻነትና ሰላም (ቴዲና ጂጂ ... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

HOW BEAUTY CAN LEAD TO GENOCIDE

This

Can Lead to

This.

Believe it.

The picture I have posted above is of an East African

woman and the second, young boys dead in the Rwandan

Genocide.

The Rwandan Genocide. Where did it stem from? A Geno-

cide that took the lives of 800,000 people, how did its be-

gin? Who planted the ideas of a superior race into the

minds of the Rwandan people? And why does it continue in

Congo today? Here is how Beauty leads to Genocide.

Author and Journalist Philip Gourevitch in the the book We

Wish to inform you that tomorrow we will be Killed with

our families Stories From Rwanda tells us the beginning of

the Rwandan Genocide . Gourevitch explains to the reader

how one of the root causes of Genocide was the

“difference” in the appearance of Hutus and Tutsis. This is

called Racial Science. I am quoting this book throughout

this post.

The Hamtic hypothesis founded by Englishman John Han-

ning Speke in 1863 says that “all culture and civilization in

central Africa had been introduced by the taller, sharper-

featured people, whom he considered to be Caucasoid tribe

of Ethiopian origin, descended from the biblical King

David, and therefore a superior race to the native Ne-

groids.” ( 51) Basically, white looking Africans will in-

troduce civilization to black looking Africans.

Speke kept a journal, Journal of the Discovery of the

Source of the Nile, this journal was devoted to and used

biblical references to explain why dark Africans are inferior

to the white human being. In a journal called Fauna he

says, “…take man–the true curly-head, flab-nosed,

pouch-mouthed negro…How the negro has lived so many

ages without advancing seems marvelous, when all the

countries surrounding Africa are so forward in capari-

son...the African must soon either step out from his

darkness, or be superseded by a being superior to him-

self.” (52)

So while in Africa, Speke discovered a “superior” set of

people. these people had “Fine oval faces, large eyes, and

high noses, denoting the best of blood of Abyssinia( Ethio-

pia).” During this time, it is important to note that The

tutsis were a tribe in Ethiopia. Speke liked these peoples bridged noses- he labeled them lost christians and suggested

with training they can be superior like the English people.

“Few Rwandans would deny that the Hamatic myth is one of the essential ideas by which they understand who they are in

this world.” (53)

So this is how the story goes. After Speke, there was justifi-cation among Europeans to enslave, colonize and rule over

the dark man. After European powers held a conference in

1885 to divide the African states which they would colonize, ethnic groups were designated a state to which they did not

have a say in belonging to. Rwanda was awarded to East Germany and soon after WWI, Belgium colonized Rwanda.

Colonization takes strategy, Europeans did not simply

come into Africa with guns and try to enslave the people. No, they came in calm, smiling, “worked” with the current

leaders to attain what they want. In Rwanda, Belgium used

the Speke analysis of the dark man to name Hutus and Tutsis different ethnic groups, differentiate the two by having scien-

tists measure their noses, and administered Tutsis to be their

chiefs. They encouraged Tutsis to exploit and degrade Hutus and placed one group above another. Rwanda wasn’t

Rwanda anymore, it was a country where the law of the

land declared Tutsis better than Hutus.

Long Story short, in 1957, a group of the” inferior” race,

Hutus, published the Hutu Manifesto which argued for a

majoritarian democracy- embraced the Hamatic myth-

argued the Hutu people were the original the rightful lead-

ers of the nation since bridge nosed Tutsis were from

Ethiopia. They wanted their country back. decades later,

800,000 Rawandas would be killed so Hutus can Rule

Rwanda again.

all of this because one white man liked one persons nose

better than another persons nose.

I write this post not to only share the history of the Rwan-

dan Genocide, but to show you, how labeling something

more attractive than another can lead to preference, which

as seen above leads to tragic events such as genocides. East

Africans from countries such as Ethiopia, Eritrea, and

Somalia are often praised for their Eurocentric beauty.

But should we proud that we were labeled beautiful by a

white scientist that caused ethnic conflict and deaths of

thousands of people? Should we proud that this very no-

tion is what justified slavery, and rape of women, in

North America 300 years ago? Is it fair to leave out our

sisters in these countries that were not praised by Mr.

Speke? You tell me, are East African women now colo-

nized through prostitution in placed like Dubai? Is it

colonization that leads dark women to bleach their skin

in hopes of making it lighter? Do we perpetuate and use

Spekes lies in our personal lives? We need to ask and

answer these questions for beauty leads to Genocide and it has the power to lead to

Genocide again.

By Lulete Mola (Minnesota)

eastafricangirl.wordpress.com

በወንድማችን ምስጋናው የተከፈተው አዲሱ አልፋ ጋራዥ መኪናዎ በማንኛውም ሰዓት

ብትጋጭ ወይም ቀለም ሲፈልጉ ቀጠሮ አክብሮ በፍጥነት ያድሳል፤ ለማንኛውም ጥገናም ወደ ጋራዣችን ይምጡ፤ በቂ የሰው ኃይል አለን!

213 West 29th Street, Minneapolis, MN 55408 651-239-6540

We Guarantee Customer SatisfactionWe Guarantee Customer Satisfaction

የኛ ትርፍ የደንበኞቻችን ደስታ

Interest Interest Free Free

FinancingFinancing

Alpha Auto SalesAlpha Auto Sales Lowest Price Guaranteed!

Page 19: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

ጥረት እያዩ የሚያበረታቷት አካላት አሉ። የክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ እና የሴቶች የሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ተጠቃሽ ናቸው። የተለያዩ አውደ ርዕዮች ሲኖሩ ይጋብዟታል። በእዚህ መልኩ ባገኘችው አጋጣሚ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ባዘጋጀው ውድድር ተካፍላ ሦስት ሺ ብር፤ ደሴ በተዘጋጀው ውድድርም ሁለት ሺ ብር በሽልማት አግኝታለች።

በየጊዜው የምታገኛቸው ማበረታቻዎችና የሰዎች በጎ ምላሽ ያነሳሳት ወይዘሮ ሙሉነሽ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የሥራ ፈጠራ ተሰጥኦ ውድድር ተካፋይ ሆናለች። ለውድድሩ የቀረቡት ተወዳዳሪዎች እንዴት አድርገው የሥራ ዕቅድ እንደሚያቀርቡ ሠልጥነዋል፡፡ በወቅቱ ነፍሰጡር የነበረችው ወይዘሮ ሙሉነሽ በሠለጠነችው መሠረት ዕቅዷን ያዘጋጀችው የሚያብጠውን እግሯን እያስታመመች ነበር። ውስጧ ከፍተኛ ተነሳሽነት ስለነበር በአግባቡ ያዘጋጀችው የሥራ ዕቅድ ከዳኞችም ሆነ ከተመልካቾች ጥሩ ምላሽ አስገኝቶላታል።

ገጽ page December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ይህ አምድ እያዝናኑ የሚያስተምሩ፤ ቁምነገሮች የሚስተናገዱበት ነው። በአምዱ ላይ የአንባቢያን ተሳትፎ ይበረታታል። ምንጭ ጠቅሰው ያስገረመዎትን እውነታ ያካፍሉን

ውስኪ ለጉራ ነው ደም ያጠራል ቢራ

የሃሳቤ ተካፋይ እንደምን ነሽ ጠላ ከዳንኤል በቀለ

በሀገራችን በዓላትንና የተለያዩ ድግሶችን ለማድመቅ ጠላ ማዘጋጀት በብዙዎች ዘንድ የተለመደና የኖረ ባህል ነው፡፡ በተለይ ከሃይማኖት ጋር የተያያዙት ዋና ዋና በዓላት፣ ሠርግ ፣ክርስትና እንዲሁም የሟቾችን መታሰቢያ ለመዘከር የሚታሰቡ ቀናት ላይ ጠላ አይጠፋም። በገጠሩ የሀገራችን ክፍሎችም አርሶ አደሩ ምርቱን ለመሰብሰብ በሚጠራው ደቦ ላይ ሥራው የሚካሄደው « የዶሮ ዓይን» የመሰለ ጠላን ጐንጨት እየተባለ ነው።

የጠላ አዘገጃጀት የራሱ የሆነ ሂደት አለው። በቅድሚያ ብቅልና ጌሾ ከተፈጨ በኋላ ውሃ ተቀላቅሎ ይጠነሰሳል። በመቀጠል በሦስተኛው ወይም በአራተኛው ቀን ከገብስ፣ ከስንዴ ወይም ከዳጉሳ የተዘጋጀ የጠላ ቂጣ ከጥንስሱ ጋር ይቀላቀላል፡፡ ይሄ ከተብላላ በኋላ አሻሮ ይጨመርበታል። አሻሮ ከተለያዩ የእህል ዓይነቶች ሊዘጋጅ ይችላል። በቆሎ፣ ገብስ እና ዳጉሳ በብዛት የተለመዱ ናቸው። የእነዚህ እህሎች ውህድ ጠላን ይፈጥራል።

ይህ ባህላዊ የጠላ አጠማመቅ ዘዴ ለዘመናት ሲሠራበት ኖሯል። ከጥንስሱ ጀምሮ ጠላው ለመጠጣት ዝግጁ እስኪሆን ከ15 እስከ 20 ቀን ይፈጃል። ጥሬ ዕቃዎቹን ከገበያ ገዝቶ ማዘጋጀትና ጠላ ለመጥመቅ የሚደረገው ሂደት ጊዜ ከመፈለጉም ባሻገር ሥራው አድካሚ ነው። ከዘመናዊ የአኗኗር ሥርዓት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ይህን ባህላዊ መጠጥ ለማዘጋጀት ያለው ፍላጎት እየቀነሰ ሊመጣ ይችላል። በተለይ በከተሞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች መስፋፋት ለጠላ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ አመቺ ባለመሆናቸው ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ግድ ይላል።

ወይዘሮ ሙሉነሽ አለነህ ለእዚህ መፍትሔ አማራጭ ይዛ ብቅ ብላለች። በ1998 ዓ.ም ከባህርዳር ኪያሜድ የጤና ኮሌጅ በነርስነት የተመረቀችው ወጣት በሙያዋ ሥራ ፈልጋ መቀጠርን እንደ አንደኛ አማራጭ አልወሰ ደችውም። ይልቁንስ ዘወትር በውስጧ የሚመላለሰውን ጠላን ዘመናዊ በመሆነ መልኩ ለ ማ ዘ ጋ ጀ ት የሚያስችለውን ዘዴ ለመሞከር ጥረት ማድረግ ጀመረች።

ለሃሳቡ መነሻ የሆኗት የተለያዩ ጉዳዮች አሉ። የመጀመሪያው አብዛኛው ሰው በበዓላትና በድግስ ቀናት ጠላ ለማዘጋጀት ፍላጎት ቢኖረውም በጊዜ እጥረት የተነሳ ያሰበውን ማድረግ አለመቻሉ ነው። ባህላዊውን መጠጥ ከቤት የማግኘት ፍላጎቱ ከፍተኛ ቢሆንም ካለው የአዘገጃጀት ውጣውረድ የተነሳ ጠላ ከየቤቱ እየጠፋ መሄዱን ታስታ ውሳለች።

ሌላኛው ምክንያት የጋራ መኖሪያ ቤት መስፋፋት ነው። ባለችበት አካባቢ ይህ ሁኔታ ጎልቶ ይታያል። የጋራ መኖሪያ ቤቶችና ዘመናዊ ግንባታዎች እየተስፋፉ መጥተዋል። በእነዚህ ቤቶች ጠላ ለማዘጋጀት የሚደረገውን ባህላዊ ቅደም ተከተል መተግበር ያስቸግራል። ጌሾ ይወቀጣል፣ አሻሮ ይቆላል፣ የጠላ ቂጣ ይጋገራል። እነዚህን ለማከናወን ዘመናዊ ቤቶቹ አመቺ አይደሉም።

በዓላትን ባህላዊውን ሥርዓት አከናውኖ

ማሳለፍ የለመዱ ሰዎች የጠላ ከቤት መጥፋት ቅር ያሰኛቸዋል። ባህል የማንነት መገለጫ ነውና ተጠብቆ ሊዘልቅ ይገባል እንጂ ሊጠፋ አይገባም የምትለው ወይዘሮ ሙሉ በአንድ ወቅት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አስመ ልክቶ በተደረገ ስብሰባ አንድ እናት የሰነዘሩት አስተያየት ሃሳቧን እንድ ትገፋበት እንዳደረጋት ትናገራለች። በዕለቱ ከተለያየ አካባቢ የመጡ ሰዎች ተሰብስበው ስለጋራ መኖሪያ ቤቶች ጠቀሜታ ውይይት ይደረግ ነበር። በቤቶቹ ላይ የተለያየ ጥያቄና አስተያየት ይሰነዘ ራል። አንድ እናት በሰ ጡት አስተያየት «ቤቶቹ ጠላ ለማዘጋጀት አይመ ቹም፡፡ ቡና መውቀጥም አይቻልም። ታዲያ

እን ዴት ነው ጠላና ቡና ሳናዘጋጅ የምንኖረው?» የሚል ነበር።

ወይዘሮ ሙሉነሽ ይህን ሃሳብ እያውጠነጠ ነች ጠላ በቀላሉ የሚዘ ጋጅበት ዘዴ ትፈልግ ጀመር፡፡ ከረጅም ጥረት በኋላ ለጠላ የሚያስፈ ልጉትን ግብዓቶች በሙሉ በመቀላቀል በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ጠላ ለማዘጋጀት ችላለች። ውህዱ ጌሾ፣ ብቅል፣ የጠላ ቂጣ እና አሻሮ የያዘ ነው። ሁሉም ግብዓቶች ተመጣጥነው ይገኛሉ። ይህን ዱቄት በመመሪያው መሠረት የሚያስፈልገውን ውሃ ጨምሮ ከተቀመጠው ቀነ ገደብ በኋላ የሚፈ ለገውን ጠላ ማግኘት ይቻላል።

የወይዘሮ ሙሉነሽ የፈጠራ ሥራ አዲስ አቅጣጫ የሚያመለክት ነው። ጠላን ለማዘጋጀት የሚታለፉትን ሂደቶች ያሳጥራል።

ለ ዚ ህ ም

ሥራዋ የኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት በ2002 ዓ.ም የፈጠራ ባለቤትነት መብት ሰጥቷታል።

ወይዘሮ ሙሉነሽ ጠላን በእዚህ መልኩ አዘምኖ ለማዘጋጀት መነሻ የነበራት ካፒታል 500 ብር ብቻ ነበር። የምትረዳት አንድ ሠራተኛም ነበረች። የጠላውን ዱቄት እያዘጋጀች ለሰዎች በመስጠት አስተያየታቸውን ሰበሰበች። የምታገኘው ምላሽ አበረታች ነበር። ያገኘችው በጎ ምላሽ ስንቅ ሆኗት አነስተኛ ሱቅ በመክፈት ሽያጭ ጀመረች።

መጀመሪያ ላይ ተጠቃሚው አነስተኛ ነበር። አዲስ ነገር እንደመሆኑ አልተላመደም። ቀስ በቀስ አንዱ ለአንዱ እየነገረ ተጠቃሚው እየጨመረ መጣ። ብዙዎች ጥረቷን ያደንቁና ያበረታቷት ጀመር። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከደንበኞቿ የሚሰጣትን አስተያየት እየተቀበለችም ሥራዋን አሻሻለች።

ጠላን በእዚህ መልኩ ማዘጋጀቱ በርካታ ጠቀሜታ እንዳለው ወይዘሮ ሙሉነሽ ታምናለች። በበዓላት ወቅት ጠላ ለመጥመቅ የሚባክነውን ጊዜ ይቀንሳል። ባህል እንዳይረሳ ያደርጋል። የአልኮል መጠኑን መመጠን ይቻላል። አንድ ጊዜ ጥሩ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያልተዋጣለት ጠላ ከመጥመቅ ያድናል።

ወይዘሮ ሙሉነሽ ጠላን በዘመናዊ መልክ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ነው። የአልኮል መጠኑን ለማስለካት ሞክራለች። በአንድ ወቅት ባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ በተዘጋጀ ዓውደርዕይ በባለሙያ ታይቶ አምስት በመቶ የአልኮል ይዘት እንዳለው ተረጋግጧል። አውስትራሊያ፣ አሜሪካ እና ግሪክ የመሳሰሉ አገራት የተላከው የጠላ ዱቄት ከተጠቃሚዎች ጥሩ ምላሽ አስገኝቶላታል።

የጠላ ዱቄቱ ከአንድ ኪሎ ጀምሮ በላስቲክ ታሽጎ የተዘጋጀ ሲሆን፤ አብሮትም የአጠቃቀም መመሪያ ሰፍሯል፡፡ በቀጣይ ወደ ውጭ ለመላክ ሊሟሉ የሚገባቸውን መስፈርቶች በማጥናትና ዝግጅት በማድረግ የውጭውን

ገበያ ለመያዝ ታስባለች። ወይዘሮ ሙሉነሽ ያደረገችውን

ዘወትር ሐሙስ የክትፎ

በቆጮ ቀን

ጥቂት አደሴ ቁኒ - Suiridae

አደሴ ቁኒ ምድቧ በአይጥ አስተኔ ክፍለ መደብ ውስጥ በሚገኘው ‹‹Suiridae›› በሚባለው የአደሴ-ቁኒ አስተኔ ዘመድ ውስጥ ነው:: ይህ ዘመድ 273 ብቸኛ ዝርያዎች አሉት:: በመላው ዓለም በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛል:: በአፍሪቃ ውስጥ 36 የአደሴ ቁኒ ብቸኛ ዝርያዎች ይገኛሉ:: በኢትዮጵያ ውስጥ ስንቶቹ እንደሚገኙ የተደረገ ጥናት አላገኘሁም:: ሆኖም ግን መስመር የሌለው የመሬት አደሴ ቁኒና የጂኦፍሮይ ባለመስመር የመሬት አደሴ ቁኒ በርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል:: የመሬት አደሴ ቁኒዎች በሙሉ፣ ‹‹Xerus›› በሚባለው ዝርያ ውስጥ

ይመደባሉ:: አደሴ ቁኒዎች በጠቅላላ ጎፈሬያምና ረጅም ጅራት አላቸው:: ጅራታቸው ለብቻው የቀረውን አካላቸውን ያህል ርዝመት አለው:: የመሬት አደሴ ቁኒዎች የቀን እንስሳት ናቸውና ተግባሮቻቸው ሁሉ የሚከናወኑት የፀሐይ ብርሃን ባለበት ወቅት ነው::

ማንኛውንም ጠጣር ሽፋን ያለውን ፍሬ የመስበር ችሎታ አላቸው:: እናም የተለያየ የዓየር ጠባይ ባላቸው ስፍራዎች ሁሉ መኖር ይችላሉ:: በአገራችን ያሉት አደሴ ቁኒዎች እስከ 1 ኪ.ግ ይመዝናሉ:: ማህበራዊ አደረጃጀታቸው፣ ማህበራዊና ኩይሳዊ ነው:: መኖሪያቸው በሚቆፍሩት ጉድጓድ ውስጥ ነው::

ጉድጓዳቸው የተገናኙ ቱቦዎችን የመሰለና ባለብዙ መውጫ ነው:: ‹‹Xerus erythropus›› የሚባለው ባለመስመሩ የመሬት አደሴ ቁኑ፣ ቡናማ ሆኖ በጎንና በጎኑ፣ ከትከሻው ጀምሮ እስከ ዳሌው የሚዘልቅ ነጭ መስመር አለው::

ከሞሮኮና ከሴኔጋል ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ አልፎም እስከ ታንዛንያ ይኖራሉ:: ከደረቅ ሣራማ ስፍራዎች እስከ መለስተኛ በረሃዎች ድረስ መኖር ይችላሉ:: እስከ 2000 ሜከፍታ ድረስም ይገኛሉ:: ባለ መስመሩ አደሴ ቁኒ፣ ከሁሉም አደሴ ቁኒዎች በበለጠ ሰፊ ስርጭት ያለው ነው:: ጎፈሬአማ ጅራታቸውን፣ ረጃጅም ነጭና ጥቁር ፀጉሮች እየተፈራረቁ ቀለበቶች ይሠሩበታል::

የሚወልዱት በማንኛቸውም ወራት ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ በአማካይ ከ1-3 ግልገሎች ይወልዳሉ:: የሚያረግዙት ለ6፣ ለ7 ሳምንታት ነው:: የመሬት አደሴ ቁኒዎች ሙሉ ለሙሉ የሚኖሩት መሬት ላይ ነው:: የሚጨነቁና የሚፈሩ ቢሆኑም፣ ራሳቸውን ለመደበቅ ጥረት አያደርጉም:: ሲንቀሳቀሱ ጭራቸው ሽቅብ እንደ ደጋን ሠርቶ ቆሞ፣ ጡብ ጡብ እያሉ ነው:: ምግባቸው ዕፀዋት ሲሆኑ፣ በተለይ ሥራ ሥሮችና አኩራች እንዲሁም የወደቁ ፍራፍሬዎችን ይበላሉ::

እንዳቅማቸው ብዙ ምግብ ባገኙ ጊዜ እጥረት ለሚሆንበት ጊዜ የሚሆናቸው ምግብ ያጠራቅማሉ:: የተተከሉ ዕፀዋትን ሊያጠቁ ይችላሉ:: ለውዝ፣ ስኳር ድንች፣ በቆሎ የመሰሉትን ይበላሉ:: በአንዳንድ ስፍራዎች አደሴ ቁኒዎች ሲናከሱ ገዳይ መርዝ አላቸው ብለው ሰዎች ያምናሉ:: አንዳንድ በሽታዎች ሊያጋቡ የሚችሉ ናቸው::

ምንጭ፡ ሰሎሞን ይርጋ (ዶ/ር) ‹‹አጥቢዎች›› (2000)

በእኩል ሰዓት በሁለት እጆች ሁለት ዓይነት ቋንቋን መፃፍ የሰውነት ክፍሎቻችን የየራሳቸው ተግባርና ኃላፊነት አላቸው፤ እጆች የሚሰሩትን ሌላው የሰውነት ክፍል ለመሥራት ይቸገራል። እግር የሚያገለግለውን ያህልም እግርን ተክቶ ሊሠራ የሚችል የሰውነት ክፍል አለ ብዬ አለምንም። በተጨማሪም ለብዙዎቻችን ግራ እጅ የሚሰራው ሥራና ቀኝ እጅ የሚፈጽመው ተግባር እንኳን እጅግ የተራራቁ ናቸው አንዱ አንዱን ሊተካ አይችልም። ቻይናዊት ናት፤ ዕድሜዋ ደግሞ 24 ዓመት። ቺን ሲይዋን ትሰኛለች፤ ታዲያ ይህች ወጣት ለብዙዎቻችን ፈታኝ ብሎም ለመሞከር እንኳን አስበነው የማናውቀውን ክስተት ትሞክራለች፤ ኸረ የምን ትሞክራለች ተግባራዊ በማድረግም ብዙዎችን አስገርማለች፤ ሲይዋን በእኩል ሰዓት ግራና ቀኝ እጇ በመጠቀም የተለያዩ ሁለት ቋንቋዎችን መፃፍ መቻሏ ነው ልዩ ያደረጋት ተሰጥኦ ይላል የቢቢሲ ዘገባ። እንደ ዘገባው ሲይዋን በአንድ ጠረጴዛ ላይ ሆና በአንድ እጇ እንግሊዝኛ በሌላው ደግሞ ቻይንኛ በመፃፍ ዓለምን ጉድ አስብላለች ። «የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ነው ይህንን የጀመርኩት፤ እንዴት እንደጀመርኩት አላስታውስም። ሆኖም ሁለቱንም እጆቼን በመጠቀም ለመፃፍ ከፍተኛ ጥረትን አደርግ ነበር። የቤት ሥራም ሲሰጠን በሁለት እጄ ሁለት የቤት ሥራ ስለምሠራ በፍጥነትም እጨርስ ነበር። ይህንን የተመለከቱ የክፍል ጓደኞቼ ደግሞ በጣም በመደነቅ እኔን ለማስመሰል ጥረት ያደርጋሉ፤ የተሳካላቸው ባይኖሩም» ትላለች ሲይዋን። ሲይዋን በአሁኑ ወቅት የመጀመሪያ ዲግሪዋን በእንግሊዘኛ ያገኘች ሲሆን ፤ የራሷን የግጥም መጽሐፍም በማዘጋጀት ላይ እንደምትገኝ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። እዚህ ቀደም 20ኛው የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ጀምስ ጋርፊልድ በዕኩል ሰዓት በሁለት እጆቻቸው ጽሑፎችን በመፃፍ ይታወቁ ነበር። ፕሬዚዳንቱ በአንዱ እጃቸው እንግሊዝኛ ከፃፉ ሌላውን ደግሞ የጥንት ግሪካውያንን ቋንቋ ለመጻፍ ይጠቀሙበት ነበር። በእዚህም ብቸኛ ተብለው ቆይተዋል።

ትልቁ መሶብ ሰሞኑን በባህርዳር የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር

ይህን የሚያህል ግዙፍ መሶብ ተሰርቶ ነበር። በኢትዮጵያ ትልቂ መሶብ ተብሎም በታሪክ

ተመዝግቧል።

Page 20: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

ገጽ page December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ኤርትራ... ከገጽ 4 የዞረ

ግልፅ ያደርገዋል፡፡ ይልቅስ የእሾህን በእሾህ ጨዋታን ወደ ጐን አድርጐ መንግሥት የሀገራችንን ችግር በሀገራችን እንፍታው በማለት መቀነቱን ጠበቅ አድርጐ ብሔራዊ እርቅ ቢያደርግ ይመረጣል፡፡ እሾህን በእሾህ መርሕ ይዞ የገለአድን ተሪራ መውጣት ከባድ ከመሆኑም በላይ የጌዲዮን ወታደር ለመሆን ትንሽ ያስቸግራል፡፡

ሐ/ የግብፅ ጉዳይ ሦስተኛው የዶሀ ጉዞ ከዓባይ ግድብ ጋር ተያየዞ ከግብፅ ጋር

የሚገናኝ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ግብፅ የዓባይ ግድብ እውን እንዳይሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትንኮሳ ታደርጋለች ብሎ መንግስታችን የተጨነቀ ይመስለኛል፡፡ ግብፅ የውክልና ጦርነት (Proxy war) ኤርትራን ተጠቅማ ታደርጋለች የሚለው መላምት አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ግብፅ ግዙፉን አየር ኃይሏን ተጠቅማ የኤርትራ አየር ላይ እንደልቧ እየተንሳፈፈች ታጠቃናለች የሚለው ሌላው እሳቤ ይመስለኛል፡፡ ይህንንም ለመከላከል ኢትዮጵያ በኳታር አማካኝነት ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማውረድ አስባለች ማለት ነው፡፡ ይህ መቼም መልካም እሳቤ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ቅድመ ዝግጅት በመከላከያ በኩል ማድረግና የቀጥታ ውይይት ከግብፅ ጋር ማድረግ እንደአማራጭ ቢያዝ አይከፋም ባይ ነኝ፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ወቅት የዓባይን ግድብ አስመልክቶ ከግብፅ ስለሚሰነዘረው ሁኔታ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ ‹ግብፅ እኛን አትደፍረንም፣ ታውቀናለች› የሚል መልስ መስጠታቸው ትዝ ይለኛል፡፡ በወቅቱ ይህ መልስ ብዙም አልተመቸኝም ነበር፡፡ ከወቅቱ ጋር የተያያዘ መልስ ነው የሚል ግምትም የለኝም፡፡ ድሮ ጦርነት በወኔ ማሸነፍ ይቻል ነበር፡፡ ዛሬ ነገሮች ተለውጠዋል፤ ጦርነት ቴክኖሎጂ ሆኗል፡፡ የላቁ ቴክኖሎጂዎችና ብዙ ገንዘብ ለጦርነት ያፈሰሰ አካል ነው፡፡ የድል ፅዋ ሊጨብጥ የሚችለው፡፡ የቹን ዙ መጽሐፍ ለዛሬ ጦርነት ዋጋ አይኖረውም፡፡ ግብፅ በየዓመቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለመከላከያዋ አሜሪካ እንደምተደጉማት መረሳት የለበትም፡፡ ቴዲ አፍሮ ‹ጋሻው፣ ጐራዴው ቀላ› ሲል በግብፅኛ ‹አሞራ በሰማይ ሲያይሽ ዋለ› የሚል ትርጉም እንዳለው መረሳት የለበትም፡፡ በእርግጥም የግብፅ አየር ኃይል ግዙፍ ነው፡፡ ስለዚህም ጠቅላይ ሚኒስተራችን አብዝተው ወደካይሮ መጓዝና ዳፕሎማሲውን ከግብፅ ጋር ማጠንከር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያኔ ነው ገለአድን መውጣት የሚቻለው፡፡

የአፍ ወለምታ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በዶሀ ካደረጉት ውስጥ አንዱ

ከቀድሞው ደርቢያችን አልጄዚራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ይጠቀሳል፡፡ በቃለ ምልልሱ ላይ ወደ አስመራ ለመሄድና ኢሳያስን በአካል ማግኘት እንደሚፈልጉ ተናግረው ሐሳባቸውን ማጠናከሪያ መለስ 50 ጊዜ ኢሳያስን ለማናገር እንደሞከሩ ነግረውናል፡፡ የሳቸውን ፍላጐት በመልካም ባየውም የመለስ ግን የአፍ ወለምታ ትመስለኛለች፡፡ የሀገሬ ሰዎች 10፣ 50 ወይም 100 የሚሉ ቁጥሮችን አብዝቶ ይወዷቸዋል፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አንድም ቀን ትንታኔዎች 49 ወይም 51 ላይ ሆነው አያውቁም፡፡ ኦ!... ለካ ኢኮኖሚያችን 11% ነው፡፡… በ1992ዓ.ም. የጦርነቱ ማብቂያ አካባቢ ዳሬ ሰላም ላይ መለስና ኢሳያስ ተገናኝተው ነበር፡፡ ኢሳያስም መለስን ለብቻቸው ካላነገርኩዋቸው ሀገር ይያዝልኝ ቢሉም መለስ ግን ፈቀደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን በዚያ ወቅት የመንግስት ልሳን ከሆነችው እፎይታ መጽሔት ላይ ማንበቤ ትዝ ይለኛል፡፡ ያኔ መለስ ኢሳያስን ቢያናግሩ ኖሮ አዲስ አበባ ላይ ማርክሲስቱ ተወልደ እና ስዬ አብርሃ በወቅቱ በሕወሓት ውስጥ ተከስቶ ለነበረው ክፍፍል ይጠቀሙበታል ብለው መለስ አስበውት ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በተለያየ ወቅት መለስ ኢሳያስን ከመንበረ ስልጣኑ እንደሚያስወግዱ ሲዝቱ እንጂ ለድርድር ሲጠይቁ ተሰምተው አይታወቅም፡፡ ስለዚህም የአቶ ኃይለማርየምን ንግግር ለማመን ያስቸግረኛል፡፡

እንደ ማጠናናቀቂያ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዶሀ ጉዞ ለሀገራችን መልካም ነገር

ይዞ እንዲመጣ ሙሉ ምኞቴ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጅማሮ መልካም ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን ዲፕሎሲያዊ ጥረቱ ሀገር ውስጥም መቀጠል አለበት ብዬ አስባሁ፡፡ በተለያዩ ወቅቶች ከመንግስት ጋር ተጣልተው ትጥቅ ያነሱትንም ሆነ በስደት ያሉትን የሀገሪቱ ልጆችን ማወያየትና ወደ ሰላማዊ ፖለቲካዉ ውድድር እንዲገቡ ማሳመን ቀጣይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕቅድ እንዲሆን እመኛለሁ፤ መንግሥት ሲተችበት

የነበረበትን ቢያስተካክል እና የኢትዮጵያ ልጆች በአንድ የሚቆሙበትን መንገድ መንግሥታችን ቢያመቻች እመኛለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር! -----

ጸሐፊውን ለማግኘት በዚህ ኢሜይል አድራሻ ይጻፉላቸው:- [email protected]

ብፁዓን... ከገጽ 6 የዞረ

ነገሩ በዚሁ ሳይቋጭና ሳይወሰንበት ቢቆይም የሐሳብ ልዩነቱ እንደከዚህ በፊቱ ተጣልተው እንዲለያዩ አላደረጋቸውም። “ፈግጠው - ፈግጪው” አለመባባላቸው ብቻ ሳይሆን ለየምልዓተ ጉባዔዎቻቸው አቅርበው ውሳኔ ለመጠየቅና በድጋሚ ከአንድ ወር በኋላ በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ለመገናኘት ወስነዋል። በብዙዎች አንድምታም “ተስፋ ሰጪ” ጉባዔ እንደነበር ተወስቷል። በሁለቱም በኩል ያሉት “ምልዓተ ጉባዔዎች” ውይይቱ በቀና መልኩ እንዲቀጥል ማድረግ ከቻሉ የዘመናችንን አንድ ወሳኝ የልዩነት በር ይዘጋሉ ማለት ነው።

ማይክል ጃክሰን... ከገጽ 10 የዞረ

ልጄ፤ በደስታ ፈነጠዘ፤ እመቤታችንን ስዕል ጋ ሄዶ የራሱን ጸሎት አደረሰ፡፡ እናም……በሰላም ተኛ፡፡

መጽናኛ የሌለው ክሪፒ እውነት ጠዋት እንደነቃ ሮጦ ወደ እኔ መጣ፡፡ ዳድ…ልክ ነህ…

እመቤታችን መላዕክትን ልካ ነበር፡፡ እንዴት እንዳወቅኩ ታውቃለሁ…ቴዲ ቤሬን/ አቅፌው ተኝቼ ነበር፡፡ ጠዋት ስነቃ ግን ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ አየሁት›› አለኝ፡፡ እንኳን ተሸለህ ብዬ ‹‹አላልኩህም›› አልኩት፡፡

‹‹ዳድ›› አለኝ፡፡ ‹‹ግን አሁንም ትንሽ ትንሽ እየፈራሁ ነው›› አለኝ፡፡

‹‹አትፍራ፤ ዌር ዎልፍ እኮ Imaginary ነገር ነው›› አልኩት፡፡

‹‹እ…..ላይሆንም ይችላል›› አለኝ፡፡ ቀጠለና ‹‹ሳይንቲስቶች፤ ላቦራቶር ውስጥ፤ በDNA ቴክኖሎጂ የተለያየ ፍጥረት ሊፈጥሩ እኮ ይችላሉ›› አለኝ፡፡

በሆዴ ‹‹እዚህ ላይ ልክ ነህ›› አልኩ፡፡ ለዌር ዎልፍ እንጂ ለዲ.ኤን.ኤ መልስ የለኝምና፡፡ ስለዚህ፤ ነገሩን ለጊዜው በሌላ ወሬ አረሳሳሁት፡፡ ከዌር ዎልፍ ይልቅ፤ የዲ.ኤን.ኤው ነጥብ ትክክል ነውና፡፡ የሰው ጠላቱ፤ ጭንቅላቱ እንጂ ጭራቅ አይደለምና፡፡ ጭንቅላታችንን በዲ.ኤን.ኤ የሚሰራው ነገር ዘይገርም ነገር ብቻ ሳይሆን ዘ ይዘገንንም ጭምር ሆኗልና፡፡

ዲቪ... ከገጽ 10 የዞረ

ይህንንም ቢያልፍ እንኳን ፕሬዚዳንቱ ካልተስማሙበት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ሕጉን “አልፈርምም” በማለት ውድቅ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ፕሬዚዳንቱና አብላጫው የህግ መወሰኛ አባላት ከተመሳሳይ ፓርቲ በመሆናቸው ህጉን ያለመፈረማቸው ዕድል ዝቅተኛ ነው፡፡

በቅርቡ በተጠናቀቀው ምርጫ ከፍተኛ ሽንፈት የተጎነጩት ሪፓብሊካውያኑ በብዛት የስደተኞች ድጋፍ ያለውን የዴሞክራቲክ ፓርቲን በቀጣይ ምርጫዎች ለመርታት አስቀድመው ያቀዱት ነው የሚባልለት ይህ ሕግ በተለይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ከእስያ ለሚመጡት ስደተኞች እንደዚህ ያለውን ዕድል በመስጠት የምርጫ ድጋፍ ካሁኑ ለማግኘት የወጠኑት ነው እየተባለ በሰፊው ይነገርለታል፡፡ ስለሆነም ጉዳዩ የኢሚግሬሽንን ሕግ ለማደስ ሳይሆን የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት ነው በማለት የኢሚግሬሽን ተሟጋቾች ይነቅፋሉ፡፡ ዕድሉ ከአንዱ ጭብጦ ነጥቆ ለሌላው በመስጠት ዓይነት (የዜሮ ድምር ጨዋታ) ከሚካሄድ ይልቅ የዲቪን ፕሮግራም ሳያስቀር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምሩቃንንም ዕድል የሚያሰጥ መሆን አለበት በማለት ዴሞክራቶች ይከራከራሉ፡፡ በሕግ መወሰኛው ላይ ሲቀርብም ረቂቅ ሕጉ ውድቅ ካልተደረገ ምናልባት ይህንን ዓይነት ማሻሻያ ይደረግበታል የሚል ግምትም አለ፡፡

የዚህ ረቂቅ ሕግ ደጋፊና አቀንቃኞች ግን በዲቪ ፕሮግራም እየተካሄደ ያለውን ማጭበርበርና ውስልትና በመጥቀስ የዲቪ ፕሮግራም ለአሜሪካ የሚሰጠው ጥቅም እምብዛም እንዳልሆነ ይተቻሉ፡፡ በተለይ ይህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ የመጣውን ማጭበርበር ለመከላከል የሚደረገው አሠራር በአጠቃላይ በኢሚግሬሽን ሕጉ ላይ እያስከተለ ያለውን ተጽዕኖ ይጠቅሳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዲቪ ፕሮግራም የሚመጡት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁና የሁለት

ዓመት የሙያ ሥራ ልምድ ያላቸው በመሆኑ 21ኛው ክፍለዘመን ለሚጠይቀው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ብቃት የሌላቸውና ለአሜሪካ ዕድገት የሚያበረክቱት ከቁጥር የማይገባ ነው በማለት የዲቪ ፕሮግራምን ያጥላላሉ፡፡

የዲቪ ፕሮግራም መቅረት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት ወደ ውጪ ከሚልኳቸው ስደተኞች የሚያገኙትን የውጪ ምንዛሪ የሚያስቀር ቢሆንም አዲሱ ህግ ሥራ ላይ ከዋለ የሚያደርሰው ጉዳት ከዲቪ የላቀ እንደሚሆን ግምት ይሰጣል፡፡ በተለይ በምዕራባውያን እየተደገፉ ሥልጣን ላይ ለዘመናት የቆዩ አምባገነን መንግሥታትን የተማረው የሰው ኃይላቸው በጭቆና ከመኖር ወደ ውጪ ለመውጣት በሚያደርገው ፍላጎት ቀጥተኛ ድጋፍ በመስጠት አምባገነንነትን በተዘዋዋሪ መንገድ ከመደገፍ አልፎ በአገራት ዕድገት ላይ የራሱ ተጽዕኖ ያስከትላል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

የሆነው ሆኖ የዲቪ ፕሮግራም እስካሁን አልቀረም፡፡ ይህ አዲስ የተወሰነው ውሳኔም በፕሮግራሙ ላይ የራሱ የሆነ ጥላ ቢጥልም ወደፊት የሚቀሩትን የሕግ አወጣጥ ሥርዓቶችን ተከትሎ በተግባር እስኪተረጎም ድረስ የዲቪ ፕሮግራም ይቀጥላል፡፡ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ባለሥልጣን ለሪፖርተር እንደገለጹት አዲሱ ሕግ ገና ጸድቆ በተግባር ላይ ያልዋለ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት የቪዛ ተራቸውን በሚጠበወቁና የጉዞ ዝግጅት በጀመሩ ላይ ምንም ተጽዕኖ እንደሌላው አስታውቀዋል፡፡

ስለዚህ ጫማ አስጠራጊው ወጣት ከድንጋጤው በረድ ይበል፡፡ የ“አሜሪካ ስገባ” ምኞቱንና ሕልሙንም ይቀጥል – ይንሳፈፍበት፡፡ አሜሪካ ማርና ወተት የምታፈስ አገር ስለመሆኗ ቃል የሚገባለት ባይኖርም፤ ዲቪ ግን እንዳልቀረ እናረጋግጥለታለን፡፡ በአገሩ እየኖረ ስደተኛ ከመሆን ህጋዊ ስደተኛ ሆኖ መኖር ይሻል ይሆን? ወይስ ነገሩ ከዝንጀሮ ቆንጆ … ይሆን? መልሱን ባውቀው እኔስ ስደተኛ ሆኜ እቀር ነበር?

ሩኒ... ከገጽ 22 የዞረ

እንድታደርግ እገፋፋህ ነበር›› ሲል መገረሙን አብራርቷል፡፡ ዝውውሩ ይፋ ከተደረገ ከሶስት ሳምንት በኋላ ዩናይትድ ዊጋንን 4-0 ሲያሸንፍ የመጀመሪያ የመጫወት እድል የተሰጠው በትነር አጀማመሩ ድንቅ ነበር፡፡ እንዲያውም ሶስት የዊጋን ተከላካዮችን አልፎ ጎል አስቆጥሯል፡፡ በዕለቱ ሲያጠቃ ብቻ ሳይሆን ሲከላከልም ከወቅታዊ የኤቭራ አቋም በብዙ መሻሉን አስመስክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የሆነው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው፡፡

በትነር ከዊጋኑ ምርጥ ትዝታው በኋላ ለዩናይትድ ሶስት ጨዋታዎች አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ በእነዚህ ግጥሚያዎች ልጁ ልክ እንደ ኤቨራ ሲያጠቃ የሚያስፈራ ሆኖ ታየ፡፡ አንዳንድ አሀዛዊ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ እንዲያውም በትነር ሸርተቴ ሲወርድ፣ ኳስ ቆርጦ ሲያስቀር እና ሲያቀብል ስኬቱ ከኤቭራ በጣም ያነሰ ነው፡፡ እንዲያውም ባልተገባ ጨዋታ ከፈረንሳዊው በሶስት እጅ የሚበልጡ ቅጣት ምቶችን ለባላጋራው ያስገኛል፡፡ እነዚህ ሁሉ በትነር በዩናይትድ ኤቭራን ለመተካት ገና ብዙ መሻሻል እንደሚኖርበት ይጠቁማሉ፡፡ ሆላንዳዊው ባለፉት ዓመታት በዓለም ከምርጦቹ የግራ ፉልባኮች ጎራ ይመደብ የነበረውን ኤቭራ ቦታ ለመውሰድ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ ለአሁኑ ግን ቁጥሮች ፍርዳቸውን ሰጥተዋል፡፡ በትነር በአሁኑ አቋሙ ከዩናይትዱ ምክትል አምበልም የባሰ ጣጠኛ ተከላካይ ነው፡፡

ሁኔታውን ልብ ብሎ የተከታተለው የዴይሊ ሜይሉ ፀሐፊ ሀሳቡን ሲገልፅ ‹‹ፓትሪክ ኤቭራ እየወረደ መሆኑ ጥያቄ የለውም›› ይላል፡፡ ‹‹ቦታው ፈርጉሰንን የሚያሳስብ ነው፡፡ ቀዳዳውን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚደፍን የረዥም ጊዜ መፍትሄ ያስፈልጋል፡፡ ዩናትድ በትነርን እንደመፍትሄ ተስፋ እያደረገ ነው፡፡ ክለቡ የተሻለ ትልቅ ስም ያለው እና ማንነቱን ያስመሰከረ ተጨዋች ማምጣት አለበት፡፡ የኤቨርተኑ ቤይንስን የመሰሉ ተጨዋቾች ኃላፊነቱን በሚገባ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ዩናይትድ ትልቅ ክለብ ነው፡፡ አነስተኛ ዋጋን መሰረት አድርጎ ተጫዋቾችን ማምጣት ከክለቡ ደረጃ ጋር አይሄድም››

ፈርጉሰን ኤቭራን ለመተካት ወደ ውስጥ ማየት ካለባቸው ሌላኛው ተስፋቸው ፋቢዮ ዳ ሲልቫ ነው፡፡ ብራዚላዊው እስካሁን በፕሪሚየር ሊግ ማንነቱን በወጥ ብቃት አላሳየም፡፡ አሁን በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ በሚገኘው ኪውፒአር የውሰት ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ተጫዋች ኦልድ ትራፎርድን ከወንድሙ ጋር ከረገጠ አራት ዓመታት ቢቆጠሩም ከ58 ጨዋታዎች በላይ ለክለቡ አላደረገም፡፡ የፋቢዮ እድገት በታሰበው መጠን አለመሆን እና የመጫወት እድል የማጣቱ

ሰበብ ተደጋጋሚ ጉዳቱ እና የእንግሊዝ እግርኳስን መቋቋም የሚያስችለው የጠንካራ ተክለ ሰውነት ባለቤት አለመሆኑ ነው፡፡ ፋቢዮ አሁንም በውሰት በሄደበት ኪውፒአር መልካም ነገር አልገጠመውም፡፡ የደረሰበት ጉዳት ለተጨማሪ ጊዜያት ከሜዳ ርቆ ህክምናውን እንዲከታተል አስገድዶታል፡፡

የፋቢዮ ባለተሰጥኦ መሆን ጥያቄ አያስነሳም፡፡ ደህና ሆኖ ሜዳ ላይ በተገኘባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የተለየ ብቃቱን ብልጭታ አሳይቷል፡፡ እስካለፈው ውድድር ዘመንም ፋቢዮ የግራ ፉልባክ ሚናን ቀጣይ ተረካቢ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ በ2010/11 እንዲያውም ከወንድሙ ራፋኤል ጋር የቀኝ ፉልባክ ቦታን እየቀየረ ወጥ ብቃት በማሳቱ በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ባርሴሎናን ሲገጥሙ በቋሚነት እንዲሰለፍ ሆኗል፡፡

ይሁን እንጂ ፋቢዮ በፉልባክ ቦታ እንከን አልጠፋውም፡፡ የ22 ዓመቱ ብራዚላዊ እንደ ኤቭራ እና በትነር ባልተገቡ አጨዋወቶቹ የቅጣት ምቶች መገኛ ሰበብ ይሆናል፡፡ በመልሶ ማጥቃት የሚጠቀሙ ቡድኖች ዩናይትድን ሲገጥሙት ፋቢዮ ባላጋራውን መቆጣጠር ይቸገራል፡፡ ፋቢዮ አሁን በ22 ዓመቱ እንደቀድሞው እንደ ታዳጊ ሊታይ አይችልም፡፡

የኤቭራን ቦታ ለከርሞ መውረስ ካለበት ዘንድሮ ሳይዘገይ ወጥ እና አስደናቂ ብቃት ማሳት ይጠበቅበታል፡፡ ካልሆነ ከኤቨራ ሌላ ቦታውን ቀድሞው የሚያገኙ ተጫዋቾች አይጠፉም፡፡ የፈርጉሰን ሌላ ተስፋ ቲለር ብላኬት ይመስላል፡፡ ምርጡ ዘኪ ፋራየርስ ወደ ቤልጅየሙ ስታንዳርድ ለዬዥ መጓዙ ያሳረራቸው የዩናይትድ ደጋፊዎች በተመሳሳይ ሚና የሚጫወተውን እና ተስፋ ሰጪውን ብላኬት ወደውታል፡፡ ብላኬት የተወለደው እና ያደገው በማንቸስተር መሆኑም እውነተኛ ዩናይትዳዊ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ላይ በተለያዩ የዕድሜ ክልሎች እንግሊዝን የወከለ ሲሆን ወደ ፊት ትልቅ ይሆናሉ ተብለው ተስፋ ከተጣለባቸው ከዋክብት አንዱ ነው፡፡

በእንግሊዝ ከሚገኙ የእግር ኳስ አስተያየት መስጫ ድረገፆች አንደኛው ስለ 18 ዓመቱ ብላኬት እንዲህ አስፍሮ ነበር፡፡ ‹‹በቁመቱ 1.85ሜትር የሚደርሰው ወጣት ሜዳ ላይ ትልቅ ሆኖ ይታያል፡፡ በመሀል መጫወት የሚችል ሲሆን ጠንካራ ሸርተቴዎችን ይወርዳል፡፡ ኳሷን ሲጫወት ጎበዝ ነው፡፡ በዚህ ላይ ቅጣት ምት ሲጠቀም አደገኛ ነው፡፡ ሮቤርቶ ካርሎስ በሉት፡፡ ማንቸስተራዊው ልጅ ትልቅ ተጫዋች ሊሆን የሚያስችሉት ብቃቶች ሁሉ አሉት››

ብላኬት በቅደም ተከተል ሲታይ የዩናይትድን ግራ ፉልባክነት ሚና ለመውሰድ ኤቭራ እና በትነር ይቅደሙት እንጂ ለወደፊቱ በትዕግስት ከጠበቀ በቡድኑ ቦታ ማግኘቱ የሚቀር አይመስልም፡፡ ይህንን የተረዱ የሚመስሉት ፈርጉሰንም ወጣቱን ባለፈው ክረምት ከዋናው ቡድን ጋር የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን እንዲቀላቀል አድርገውታል፡፡ ሆኖም ብላኬት በተለይ በብስለቱ በኩል ገና ብዙ ይቀረዋል፡፡

ብላኬት በተለይ ባላጋራ ተጫዋችን እንዲጠብቅ ሲደረግ መጠነኛ ችግር ተስተውሎበታል፡፡ በተጨማሪም ኳሷ እግሩ ስትገባ በራስ መተማመኑ ሲከዳው ታይቷል፡፡ ባለፈው ወር የሳውዛምፕተን ከ21 ዓመት በታች ቡድን ሌላኛው ምርጥ ወጣት ሉክ ሻው ቦታውን እንዳይነጥቀው ይሰጋል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫዋቹን በቅርብ የተከታተሉት ተንታኞች ብላኬት የኤቨራን ቦታ ከሌሎቹ ቀድሞ ሊረከብ እንደሚችል ያብራራሉ፡፡

ባርሴሎና... ከገጽ 22 የዞረ

ሙከራ ተደረገ፡፡ በፌብርዋሪ 23 ቀን 1981 200 ወታደሮች በሌትናንት ኮሎኔል አንቶኒዮ ቴሄሮ እየተመሩ ወደ ስፔን ፓርላማ ገቡ፡፡ ንጉሱ ሁዋን ካርሎስ ጣልቃ በመግባት በቴሌቪዥን ቀርበው መፈንቅለ መንግስቱን አወገዙ፡፡ ከሳምንት በኋላ የባርሴሎናው አጥቂ ኤንሪኬ ካስትሮ ጎንዛሌዝ (ኩዊኒ) ክለቡ ሄርኩለስን 6-0 እንዲረታ ከረዳው በኋላ ታገተ፡፡ እገታው ገንዘብ በሚፈልጉ ተራ ወንጀለኞች የተደረገ ቢሆንም በወቅቱ የወጡ ሪፖርቶች የስፔን አንድነትን በማይሰብክ ቡድን እንደታገተ ገልፀው ነበር፡፡ ቡድኑ ባርሴሎናን የመሰለ ‹‹ተገንጣይን›› ክለብ ሻምፒዮን እንዲሆን አይፈልግም ነበር፡፡

እንደ ሁልጊዜው በስፔን እግርኳስና ፖለቲካ የሚሰማው ግን ሁልጊዜም የተቆራኙ ሆነዋል፡፡ የካታላን ነፃነት ህዝበ ውሳኔ ፖለቲካዊ ጨዋታም ወይም ካታሎኒያ በፋይናንሱ የበለጠ ነፃነት እንዲኖራት የቀረበ ማስፈራሪያ ወይም በቅርቡ የሚፈታ ትክክለኛ ህልም መሆን አለመሆኑ ወደ ፊት የሚታይ ቢሆንም የአንድ አገር እና በትውልዱ ታላቅ የሆኑት ክለቦች ብሔራዊ ቡድን እጣ ፈንታ ሊወሰን የቀሩት ግን ጥቂት ቀናት ብቻ

ይመስላሉ፡፡

Nuru Dedefo, ESQNuru Dedefo, ESQNuru Dedefo, ESQ... Attorney at Law & CounselorAttorney at Law & CounselorAttorney at Law & Counselor

If you have legal issues, If you have legal issues, If you have legal issues,

you need a lawyer who you need a lawyer who you need a lawyer who

fights for your rights. fights for your rights. fights for your rights.

Nuru Dedefo fights for Nuru Dedefo fights for Nuru Dedefo fights for

your rights.your rights.your rights.

--- Car AccidentsCar AccidentsCar Accidents

--- Work place injuriesWork place injuriesWork place injuries

--- ImmigrationsImmigrationsImmigrations

--- Family LawFamily LawFamily Law

--- Criminal LawCriminal LawCriminal Law

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:

3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 554213989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 554213989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421

(763)(763)(763)---781781781---5254 (office), (6125254 (office), (6125254 (office), (612---559559559---0489) Cell0489) Cell0489) Cell

(763)(763)(763)---781781781---5279 Fax5279 Fax5279 Fax

ነጻ ፓርኪንግ ከሬስቶራንታችን ፊት

ለፊት ዩኤስ ባንክ ፓርኪንግ

Page 21: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

አዘጋጅ ዳኒ ከሚኒያፖሊስ የአሜሪካን እግር ኳስን ለምትወዱ እና ለምትናፍቁም

ሆነ ሌላ ስፖርትን ለምታደንቁ አንባብያን በሙሉ ይህንን ጽሁፍ ሳቀርብላችሁ በደስታ ነው።

12ኛው ሳምንት - ቺቻጎ(Chicago bears) በጥንካሬ ቫይኪንድስን(Vikings) አሸንፉል

የአሜሪካን እግር ክዋስ ስፖርት ከተጀመረ 3ወራትን ብያስቆጥርም ከአሁን ጀምሬ እስከ መቸረሻው ድረስ አብሪያችሁ እቆያለሁ።

የቺቻጎ አከፋፋይ ጄይ ከትለር(Jay Cutler) 188 ያርድ በመወርወር ቺቻጎ 28-10 እንዲያሸንፍ ረድቶታል። ቺቻጎ ከ ግሪን ቤይ ፓከርስ(Packers) ጋር አቻ ላይ ይገኛል እንዲህም በእንዲህ እንዳለ ሚኒሶታ ከቺቻጎ በአንድ ነጥብ ወደሁዋላ ይቀራል። የቺቻጎ ተከላካዮች ታዋቂዉን የ ሚኒሶታ ሩውጭ የሆነውን ኤድሪያን ፒተርሰን ብዙም ሳያሳልፉ ዘግተው 108 ያርድ ብቻ እንዲሮጥ አድርገዋል። ለ ቫይኪንድስ(Vikings) መሸነፍ ትልቁ ምክንያት የሚሆነው የቺቻጎ ተከላካዮች 3 ጌዜ የ ቫይኪንድስን ኩዋስ በመንጠቅ ነጥቦችን አስቆጥረዋል። በ 12ኛው ሳምንት ሚኒሶታ የተደናገጡ ይመስላሉ

13ኛው ሳምንት - ቫይኪንድስን(vikings) ድጋሚ ሽንፈት

በ 13ኛው ሳምንት የ ሚኒሶታ ምድብ ከነበረው አንዱ በ ግሪን ቤይ ፓከርስ(Packers) ከተማ ከ ቫይኪንድስን(Vikings) ጋር ተጋጥመዋል። ምድብን ማሸነፍ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ የቫይኪንድስን ተጨዋቾቺ ካለፈው ስተታቸው ተምረው ዝግጅት ያደረጉም ይመስል ነበር። ጨዋታው በሚኒሶታ አስፈራሪነት ቢጀመርም በተለይም ለታዋቂዉ ሯጭ ኤድሪያን ፒተርሰን (Adrian Peterson) 210 ያርድ በመሮጥ የሚያስመሰግን ውጤትን በያመጣም ነገር ግን የ ቫይኪንድስ ወርዋሪ ክርስቲያን ፖንደር(Christian Ponder) ብቃት ማነስ የተነሳ ሁለት ጌዜ ኩዋሱን ለተቃራኒ ተከላካዮች አሳልፎ በመስጠት ሽህንፈትን እንድንቀዳጅ ምክንያት ሆኑዋል. ሚኒሶታ በብዛት ማተኮር የነበረበት ክዋስን በጥንቃቄ ይዞ መሮጥ(Run) ላይ መሆን ሲገባው ሳለ ነገር ግን ክዋስ ማሳለፍ(Pass) ላይ አተኩሮ በመገኘቱ 13ኛውን ሳምንት ለያሸንፉ የሚችሉትን ጨዋጣ ሊሸነፉ ችለዋል

14ኛው ሳምንት - ማሸነፍ ደስ ይላል

ባለፉት 12ኛ እና 13ኛ ሳምንት በተከታታይ ቫይኪንድስ(Vikings) ሽንፈትን አጎናፅፈውን ቢሆንም የ ሃገሬ ሰው "ሳይደግስ አይጣላም" እንደሚለው በ14ኛው ሳምንታቸው ወሳኘ የሆነውን ግጥሚያ በሚኒያፖሊስ አድርገው የቺቻጎን ቡድን ሊያሸንፉ ቸለዋል። የዚህ ሳምንት ተሸላሚ ሊሆኑ የሚገባቸው የሚታወቀዉ ሯጭ ኤድሪያን ፒተርሰን (Adrian Peterson) እና ተከላካዮቹ ናቸው ብዬ አስባለሁ። ኤድሪያን ፒተርሰን 154ያርድ በመሮጥ 2 ግብን ሲያስቆጥር ስሚዝ(Smith) የ ቺቻጎን ክዋስን በመንጠቅ ስስተኛውን ግብ አስቆጥሩዋል። በ 12ኛ እና በ 13ኛው ሳምንት ቫይኪንድስ(Vikings) ሲጠቀሙ የነበረው የ ቸዋታ ስልት የማያዋጣ

መሆኑን ተገንዝበው በመቀየር ክዋስ ማሳለፉን ቀንስው ወደ ክዋስ ይዞ መሮጥ ላይ አተኩረው በመገኘታቸው ይህን ጨዋታ ሊያሸንፉ ችለዋል። በሌላ በኩል የተቃራኒው ቡድን አከፋፋይ ጄይ ከትለር(Jay Cutler) 260 ያርድ በመወርወር 6 ነጥብን ቢያስቆጥርም 2 ጌዜ ለቫይኪንድስ(Vikings) ክዋስን በመለገስ ቺቻጎን ከ ጨዋታ ውቺ አድርጉዋቸዋል።

15ኛው ሳምንት - ድል ለቫይኪንድስ(Vikings) እድሜ ለ ኤድሪያን ፒተርሰን

(Adrian Peterson) ባለፍው እሁድ ማለትም 15ኛ ሳምንት ላይ የሚኒሶታ

ቫይኪንድስ(Vikings) ወደ ሴንት ሉዊስ ሚዙሪ(St. Louis Missouri) በመሄድ ራምስ (Rasms) የሚባለውን ቡድን ገጥመዋል። ቫይኪንድስ(Vikings) አከፋፋይ እንደ ተፈራው ሳይሆን የመጀመሪያውን ነጥብ በማስቆጠር ቫይኪንድስ

(Vikings) 7 ለ ባዶ እንዲመሩ አድርግዋል። ባለፉት 3ት ሳምንት ስለ ታዋቂው ኤድሪያን ፒተርሰን (Adrian Peterson) በመናገር ባሰለቻችሁም በዚህ ሳምንት 212 ያርድ ሮጦ 14ኛውን ነጥብ በመጀመሪያው ዙሪያ በማስቆጠር Vikings የሞራል ብርታትን እንደሰጠ አይተናል። በዚህ በ2012 የጨዋታ ሲዝን ፒተርሰን 1812 ያርድ እንደሮጠ ቢታወቅም የአሜሪካን እግር ክዋስን በአንድ የጨዋታ ወቅት በከፍተኛ አርቀት በመሮጥ ልከርድ ለመስበር 294 ብቻ የሚቀረው መሆኑን ብዙ የስፖርት ቃል አቀባዮች ተናግረውለታል። የባለፈው እሁድ ማሸነፍ ወደ ጥሎማለፍ በቀጥታ ባያሳልፈንም ቸዋታውን በማሸነፋችን እና የኛ ምድብ የሆነው ቺቻጎ በ ግሪን ቤይ ፓከርስ(Packers) በመሸነፉ ከምድባችን ሁለተኛ በመሆን ለጥሎማለፍ ምድብ ውስጥ ለመግባት ያለንን እድል አስፍቶልናል።

ሁሉም ቡድኖች ከጥሎማለፍ በፊት የሚቻወጡት ባጠቃላይ 16 ቸዋታ ሲሆን ከአሁን በሁዋላ የሚቀራቸው 2ጨዋታ ብቻ ነው። ስለዚህ የሚቀጥለው የ Vikings ዕጣ ምን ይሆን ብለን ሁላችን እንጠይቅ ይሆናል። ካለፉት 4 ጨዋታ 2ቱን ማሸነፋችን 8-6 እንድንሆን መርዳት ብቻም ሳይሆን ከሚቀሉት 2 ቸዋታዎች አንዱን ካሸነፍን(ምንም እንኩዋን አስቸጋሪ ቡድኖች ቢገጥሙንም) እናም ሌላ ምድብ ያሉ ቡድኖች ካሸነፉ Vikings ወደ ጥሎማለፍ ለመግባት ይችላሉ ብለን መተንበይ እንችላለን። ለሚቀጥሉት 4ሳምንታየስፖርቱን ሂደት እስከመጨረሻው አብረን እንከታተላለን። ካሁን በሁዋላ ለ Vikings ይረባቸዋል ብዬ የማስበው የጨዋታ ስልት ክዋሱን ለ ኮከብ ተጨዋች በመስጠት የሚቀጥሉትን 2 ጨዋታዎች ለማሸነፍ መታገል ይሆናል።

በዚህ አጋጣሚ ይህንን ስፖርት የምትወዱም ሆነ የማትወዱ አንባቢዎች ጊዜያቺሁን ሰውታችሁ ስላነበባችሁ በጣም አመሰግናለሁ። ስለ ስፖርቱ ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት እንቀበላለን። በሚቀጥለው ወር በስፖርቱ ዙሪያም ሆነ ከ እንናንተ ያኘሁትን መልእክት አካፍላችሁዋለሁ ።

ለወሩ ያድርሰን። አሜን! ኤድሪያን ፒተርሰን (Adrian Peterson) ለኮከብነት

እንዲመረጥ ምኞቴ ነው ሀሳብም ሆነ አስተያየት ካላችሁ ላኩልን

Danny - Minneapolis [email protected] አራዳ.org

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

መላዋ ካታሎኒያ ምርጫ ስታካሂድ ለውድድር የሚቀርቡት ከስፔን 17 ክልሎች የአንዷ የክልል የፓርላማ መቀመጫዎች ብቻ አይደሉም፡፡ የስፔን እና ካታሎኒያ የወደፊት እጣ ፈንታ ጭምር እንጂ፡፡ ካታሎኒያ በተቃርኖ የተሞላች ክልል ናት፡፡ በስፔን እጅግ ብዙ እዳ ያለባት ስትሆን ለማዕከላዊው መንግስት ከፍተኛ ግብር የምትገብረውም ክልል ናት፡፡ የግብር እና የወጪዎች ጉዳይ ላይ የቀጥታ የበላይነት ካታሎኒያ ይሰጣት ዘንድ የሚጠይቁት የግዛቷ መሪ አርቱር ማስ ከስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራሆይ ጋር የከረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ባለፈው በተደረገው ምርጫም ዋነኛ የክርክር ርዕስ ነበር፡፡ ጥያቄው የበጀት ነፃነት ቢሆንም ምርጫው የካታላን ነፃነትንም ይወክላል፡፡

ይህን የሚደግፉ ሰልፎች ደግሞ በካታላን የተለያዩ ከተሞች እና የካታላን ብሔርተኝነት መግለጫ በሆነው የባርሴሎናው ስታዲየም ካምፕኑ ተደርገዋል፡፡ በኦክቶበር በተደረገው የኤልክላስኮ ግጥሚያ ሙሉው ስታዲየም በካታላን ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ የነበረ ሲሆን ተመልካቾችም ‹‹ነፃነት ነፃነት›› በማለት በከፍተኛ ድምፅ ስለካታላዊነት ዘምሯል፡፡ ባርሴሎና በቅርቡ በቻምፒየንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ የስኮትላንዱን ሴልቲክ ለመግጠም ወደ ፓብከሄድ ስታዲየም አቅንቶ ነበር፡፡ የሴልቲክ ስታፍ የባርሴሎና አጫዎቻቸውን ‹‹እንኳን ደህና መጣችሁ›› ያሉት የስፔንን ሳይሆን የካታላንን ሰንደቅ አለማዎች በስታዲየሙ ዙሪያ በማውለብለብ ነበር፡፡ በ2014 ከታላቋ ብሪታኒያ ለመገንጠል የራሳቸውን ህዝበ ውሳኔ የሚያደርጉት ስኮትላንዶች ለካታላዊያን ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል፡፡

ምንም እንኳን የባርሴሎና መስራቾች ዓለም አቀፋዊ ይዘት ቢኖራቸውም ክለቡ የካታላን ብሔርተኝነት ማቀንቀኛ ዋና ማዕከል ሆኗል፡፡ በአምባገነኑ ጄኔራል ፍራንኮ ዘመን ካምፕኑ በመላው ካታሎኒያ የካታላን ቋንቋ እና ፖለቲካዊ ተቃውሞ የሚገለፅበት ስፍራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ የክለቡ ፕሬዝዳንቶች የባርሴሎና መሪነት እና የሜዳ ላይ ስኬት ዋነኛ የፖለቲካ መሳሪዎች እንደሆኑ ይቆጥሯቸዋል፡፡ ከካታላን የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ ጋርም የጠበቀ ቁርኝት አላቸው፡፡ የቀድሞው የክለቡ ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፓርታ ዴሞክራሲ ካታላን የተባለ ፓርቲ አባል ናቸው፡፡ ፓርቲውን ወክለውም በክልሉ ፓርላማ መቀመጫ ነበራቸው፡፡ የአሁኑ የባርሳ ፕሬዝዳንት ሳንድሮ ሮሴል አባት ሁዋን ሮሴል በ1970ዎቹ የጄኔራል ፍራንኮ ዘመን ማብቂያ አካባቢ የክለቡ ቺቭ ኤግዜኪዩቲቭ ነበሩ፡፡ አባት ሮሴል እና ጓደኛቸው የአምባገነኑ መሞት በሰሙ ወቅት በፕላስቲክ የተሰራ የጄኔራሉን ምስል በመያዝ ወዲህ እና ወዲያ ተወራውረውታል፡፡ በመጨረሻም ሮሴል መሬት ላይ ጥለውት ምስሉ ተቦጫጨቀ፡፡ ይህ የባርሳ ታሪክ ነው፡፡

ነገር ግን የነፃነት ትግሉ ስኬታማ ከሆነ የባርሴሎና ብቻ ሳይሆን የስፔን እና የካታላን እግር ኳስ እንዴት ይሆናል? ብሎ ማሰብም ተገቢ ነው፡፡ በምርጫው የካታላንን ነፃነት የሚያራምዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች የክልሉን ፓርላማ አብዛኞቹን መቀመጫዎች እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በፍጥነት የነፃነት ህዝበ ውሳኔ እንዲሰጥ መገፋፋታቸው አይቀርም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ራሆይ እና የስፔን መንግስት ጉዳዩን በዝምታ አላለፉትም፡፡ የነፃነት ጥሪውን ‹‹ህገ-ወጥ››፣ ከክልሉ ፓርላማ ስልጣን በላይ የሆነ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ አዲስ የካታላን ሪፐብሊክ ከተቋቋመ የአውሮፓ ህብረትን እንዳይቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ይህን ደግሞ የካታላን ፕሬዝዳንት ካርተር ማስ በቤልጅየም ብራሰልስ በህብረተሱ ስብሰባ ላይ ተቃውመውታል፡፡

በዚህ ከቀጠለ ካታሎኒያ በምዕራብ አውሮፓ የምትገኝ ከሌሎች ሀገራት የተነጠለች ትሆናለች፡፡ ጥቂቶ እንደ ሀገር የተቀበሏት ሌሎች ደግሞ ያልተቀበሏት ሆና ትቀጥላለች፡፡ ምናልባትም በሀገራቸው በሚያራምዱት የፖለቲካ አቋም ምክንያት እየተዳኙ እንዳሉት ኮሶቮ እና ደቡብ ኦሴቲያ ካታሎኒያ ልትመዘን ትችላለች፡፡ ካታሎኒያ በመላው ዓለም ተቀባይነት ብታገን እንኳን በአግሮ ኳሱ በኩል አባል እንድትሆን ለፊፋ እና ለአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጥያቄ ማቅረብ አለባት፡፡ ክሮኤሺያን የመሳሰሉ ሀገራት ከዩጎዝላቪያ ከተገነጠሉ በኋላ እንዳደረጉት የራሷን የተለየ የሊግ ስርዓትም መዘርጋት ይኖርባታል፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ተለየ የእግርኳስ ማህበር ቢኖራትም (የካታላን ብሔራዊ ቡድን ከ200 በላይ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን አድርጓል) የፊፋ

አባል አይደለም፡፡ ያከናወኗቸው ግጥሚያዎችም በላሊጋው የገና እረፍት ወቅት የሚደረጉ የወዳጅነት ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ካታላን ነፃነቷን ካወጀች የባርሴሎና ሀያልነት ይቀንሳል ማለት ነው፡፡ ክለቡ ደረጃው በወረደ ሊግ ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ ይሆናል፡፡ ቫሌንሲያመ፣ ኤስፓኞል እና ሌቫንቴን የመሳሰሉ ስመትር ክለቦች በሊጉ ሊወዳደሩ ቢችሉም አጠቃላይ ጥራቱ ይወርዳል፡፡ ባርሴሎና በትንሽ ሀይቅ ውስጥ ትልቅ አሳ

ይሆናል፡፡ ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርገው ታላቅ ግጥሚያም የኋላ ታሪክ ብቻ ይሆናል፡፡ ያለተቀናቃኙ፣ ያለትልቅ ፉክክር እና ከማእከላዊ ስፔን ከነጩ ቤት ከሚመጣው ክለብ የበላይ ለመሆን ያለው ፍላጎት በሌለበት ባርሳ የአሁኑን ቡድን መሆን ይችላል? የካታላን ሊግ ባርሴሎናን በገንዘብ እጅጉን ይጎዳዋል፡፡ የሪያል ማድሪድ ኪስም መጉደሉ አይቀርም፡፡ ጊርና የተባለ ዝቅተኛ ክለብ እንደ ሪያል፣ አትሌቲኮ ቢልባኦ እናሲቪያ ማራኪ አይሆንም፡፡ የስታዲየም ተመልካችንም ሆነ የቴሌቪዥን የማርኬቲንግ ኤግዚኪዩቲቮችን የሚስብ አይሆንም፡፡ የሊግ ፉክክሩ መውረድ የባርሴሎና ደረጃ ማሽቆልቆል ማለት ነው፡፡ ተጫዋቾቹ ከላ ማሲያ የተገኙትም ሆነ የተገዙት ‹‹ትልልቅ›› ሊጎችን መዳረሻቸው ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ ባርሳ በዓመታት ውስጥ ከዓለም ምርጥነቱ ወደ ተራ ክለብነት ሊወርድ ይችላል? ሌላው አማራጭ ባርሴሎና (እንዲሁም ቫሌንሲያ እና ሌሎች ክለቦች) በስፔን ሊግ ለመቆየት መጠየቅ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ የሚያስችል ክፍተትም አለ፡፡ የአጎራባች ሀገሯ አንዶራ ክለቦች በስፔን በታችኛው ዲቪዚዮን እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ እዚህ

ላይ ግን ሌላ ጥያቄ ይነሳል፡፡ የላ ሊጋው አባል በመሆን የሚገኘው የፋይናንስ እና የፉክክር ጥቅም ከክለቡ ጋር ከተቆራኘው የካታላን ብሔርተኝነት ስሜት ይልቃል? የሚል፡፡ ‹‹ባርሳ ከክለብ በላይ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የቆመ ክለብ ነው፡፡ ባርሳ ሁሉንም የፖለቲካ አመለካከቶች ያጠቃልላል፡፡ ምክንያቱም መላውን የካታላን ህዝብ (ባርሴሎና... ወደ ገጽ 22 የዞረ)

BISRAT ALEMAYEHU & ASSOCIATES

Meet your Friendly and Experienced professionals

At the Center for Multi-Services Tax (year-round), In-

surance, Real Estate/

Mortgage, and Many

Others

ታክስ (ዓመቱን በሙሉ)፣ ኢንሹራንስ፣ ሪል እስቴትና በርካታ ተዛማጅ

አገልግሎቶች

BUDGET INSURANCE (A Member of Wiser Insurance Group)

More Insurance Companies, More Price Choices!

[Auto. Home. Life. Health. Business] Address: 1821 University Ave. W. Suite S-301 Saint Paul, MN 55104

Tel: 651 649 0644 / 651 209 6077 Fax: 651 649 0620

የቫን ፔርሲ እና የዌይን ሩኒ አዲስ ጥምረት

ክለቦችን አስደንግጧል የኤቭራ ብቃት እያሽቆለቆለ ነው

የዘንድሮው ማንቸስተር ዩናይትድ ሲያጠቃ ያስፈራል፡፡ ወደ ፊት መስመር የሚመጡትን ኳሶች ሁሉ ወደጎልነት የመቀየር አቅም ያላቸው የሚመስሉ አጥቂዎች ይዟል፡፡ ሮቢን ቫን ፔርሲ እና ዌይን ሩኒ በአንድነት የተሰለፉበትን ቡድን ለ90 ደቂቃዎች መከላከል እንዲህ ቀላል አይደለም፡፡ ሆኖም የሰር አሌክስ ፈርጉሰኑ ቡድን የፊት መስመሩን ይበልጥ አጠናክሮ ሲቀርብ እንከን አልጠፋውም፡፡ የተከላካይ መስመሩ እንደቀድሞው አልሆነም፡፡

የቀኝ ፉልባኩ ራፋኤል ዳ ሲልቫ ዘንድሮ ምርጥ ብቃቱን ማውጣት ቢጀምርም የመሀል ተከላካዮቹ ሪዮ ፈርዲናንድ እና ጆኒ ኢቫንስ ወጥ አቋም ማሳየት አልቻሉም፡፡ አልፎ አልፎ ቢሆንም ጥምረታቸውን እና ግላዊ ብቃታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ስህተት መስራት ቀጥለዋል፡፡ ከሁሉም የከፋው ግን የፓትሪስ ኤቭራ ብቃት ይበልጥ ማሽቆልቆል ነው፡፡ የዩናይትድ ደጋፊዎች እንደቀድሞው በፈረንሳዊው መተማመን አቅቷቸዋል፡፡

ቀደም ሲል ሲበዛ አስተማማኝ የነበረው የግራ ፉልባክ በብዙዎቹ የዩናትድ ጨዋታዎች መቸገሩን ገፍቶበታል፡፡ በተለይ በቴክኒክ የበለፀጉ የክንፍ ተጫዋቾች ሲያገኙት የኤቭራ ድክመት እየጎላ መጥቷል፡፡ በመልሶ ማጥቃት የሚያመልጡትን የባላጋራ መጠበቅ ሲያቅተው እና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ያልተገቡ አጨዋወቶች ሲፈፅም እንዲሁም ዋጋ የሚያስከፍሉ ቅጣት ምቶች ሲያስገኝ እየታየ ነው፡፡ በጣም በቅርቡ ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ ጋር ሲጫወት ኤቭራ ያሳየው ደካማ ብቃት የዘንድሮ አቋሙ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡

በእርግጥ ኤቨራ ጥሩ የተጫወተባቸው ግጥሚያዎች አሉ፡፡ በተለይ ከኒውካስል እና ፉልሃም ጋር በነበሯቸው ጨዋታዎች ፉልባኩ ምርጥ ነበር፡፡ የኦልድ ትራፎርድ ታዳሚዎችም በብቃቱ ተደስተው እና ኤቭራ ደግሞ መታደሱን ማመን ጀምረው ነበር፡፡ በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ግን ይህ አልቀጠለም፡፡ አሁን ብዙዎች የኤቭራ ነገር እያበቃ መሆኑን ለመቀበል ተገደዋል፡፡ በእርግጥም የ33 ዓመቱ ኮከብ ከዚህ ውድድር ዘመን በኋላ በዩናይትድ ቢቆይ እንኳን የቦታው ቀዳሚ ተመራጭ የሚሆን አይመስልም፡፡

የኤቭራ አቋም መውረድ ዘንድሮ የጀመረ አይደለም፡፡ አምናም ተጫዋቹ የወትሮው ጥንካሬው እየከዳው መሆኑ በግልፅ ይታይ ነበር፡፡ ይህንን ያስተዋሉት ፈርጉሰን በክረምቱ ወደ ዝውውር ገበያው ቢገቡም የገዙት ብዙዎች ስሙን እንኳን ሰምተውት የማያውቁትን ወጣት ነበር፡፡

ዩናይትድ በሊጉ ምርጥነቱን ያስመሰከረውን ሌይተን ቤይንስ እንደሚያስፈርም ሲጠበቅ አሌክሳንደር በትነርን መምረጡ ለደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን ለ23 ዓመቱ ልጅ ሀገር ሰዎችም አስደንጋጭ ነበር፡፡ ዩናይትድ እስኪገዛው ድረስ የተጫዋቹ ፈላጊ የነበሩት ክለቦች ቬርደር ብሬመን እና ሳውዛምፕተን ብቻ መሆናቸው በራሱ ልጁ ለቀያይ ሰይጠናቱ ይመጥናል? የሚል ጥያቄ ያጭራል፡፡ በትነር ራሱ ዝውውሩ በፍፁም ያላሰበው እንደነበር ገና ለህክምና ምርመራ ሆላንድን ከመልቀቁ በፊት ለሀገሩ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡

‹‹ከአንድ ሳምንት በፊት እኔ እና ቫን ፔርሲ ዘንድሮ ለማንቸስተር ዩናይትድ እንደምንጫወት ብትነግረኝ በቀጥታ የአዕምሮ ጤንነት ምርመራ (ሩኒ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

Page 22: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

(እውነተኛ የወንጀል ታሪክ) ሻጭና ገዥ

ወ/ሮ መሰረት ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ዘመናዊ ቪላ ቤት ገዝታ መኖር ከጀመረች አምስት ዓመት ሆኗታል፡፡ ይህንን ቤቷን ደግሞ መሸጥ ፈልጋለች፡፡ ገዢ እንዲፈልግላትም እህቷ ቤት ተከራይቶ ለሚኖር አንድ ደላላ ነግራለች፡፡ ወ/ሮ እመቤት ደግሞ ወደዚህ ደላላ ጋ የመጣችው የሚሸጥ ቤት ፍለጋ ነው፡፡ ደላላው ከወ/ሮ እመቤት ፍላጎት ጋር የሚስማማው የወ/ሮ መሰረት ቤት እንደሆነ ያለ አንዳች ጥርጥር ገምቷል፡፡ እናም በቀጥታ ወ/ሮ መሰረት ቤት አመራ፡፡

...ወ/ሮ መሰረትን ሳትወጣ አገኛት፡፡ ቤት የምትገዛ ሴት እንዳገኘና ገዢዋ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቤት መግዛት እንደምትፈልግም ጨምሮ ነገራት፡፡ እርሷ ቤቱን የገዛችው 800,000 ብር እንደሆነ ታውቃለች፡፡ ነገር ግን ሁለት ሚሊዮንም የምትገዛት ከሆነ ያለማመንታት ለመሸጥ ወሰነች፡፡ ይህንንም ለደላላው ነገረችው፡፡ በዚህ ተስማምተው ገዢዋን አገናኝቶ አስተዋወቃት፡፡ ወ/ሮ መሰረት የምትሸጠውን ቤት ለገዢዋ አሳየች፡፡ እንደወደደችው ተናገረች፡፡ ጥሩ ግቢ እንደሆነና በማግስቱ ተመልሳ መጥታ በደንብ እንደምታየው ተናግራ በዚህ ተለያዩ፡፡

ይህን የተመለከተው ደላላ ‹‹ሴትየዋ ቦታውን ስለወደደችው ከአራት ሚሊዮን በታች አይሸጥም በያት፤ እኔም ከፍ ያለ ኮሚሽን አገኛለሁ›› ሲል ለወ/ሮ መሰረት ሹክ አለ፡፡ አልተቃወመችውም፡፡ በማግስቱ ቤት ገዢዋ መጥታ ቦታውን በድጋሚ ተዘዋውራ ካየች በኋላ ‹‹ልጆቼ ውጪ ናቸው፤ እኔ የምፈልገው ቤቱን ሳይሆን ቦታውን ነው፤ ትክክለኛ መሸጫ ዋጋሽ ስንት ነው?›› የሚል ጥያቄ አቀረበች፡፡ ሻጭም የመጨረሻ ዋጋው 3 ሚሊዮን ተኩል እንደሆነ ቁርጥ ዋጋ ጠራች፡፡ በዋጋው ተስማሙ፡፡

ገዢ ‹‹ገንዘቡን ልጆቼ ስለሚልኩ ስልክ ቁጥርሽን ለነርሱ እሰጣቸዋለሁ፤ ይደውሉልሻል›› ብላት ስምምነታቸውን ጨርሰው ተለያዩ፡፡ በቀጣዩ ቀን ‹‹unknown number›› የሚል ስልክ ወ/ሮ መሰረት ስልክ ላይ ተደወለ፡፡ የወ/ሮ እመቤት ልጆች መሆናቸውና ከውጪ ሀገር እንደደወሉ ገለፁላት፡፡ አያይዘውም ስለቤቱ ጉዳይ አንዳንድ ሁኔታዎችን ጠይቀው መረጃ አገኙ፡፡ በስልክ በተለዋወጡት መልዕክትም ደዋዮቹ ‹‹እናታችን ቤቱን ወዳዋለች፤ ገንዘቡን የምንልከው እኛ ነን፤ ያን ያህል ገንዘብ አሁን በባንክ ብንልክ ለመላኪያ የሚቆረጠው ገንዘብ ብዙ ይሆናል፤ ስለዚህ ታማኝ ሰው ፈልገን እንልካለን፤ ስለዚህም ትንሽ ጊዜ ጠብቂን›› አሏት፡፡ እርሷም በዚህ ተስማምታ ስልኩ ተዘጋ፡፡ ከዚህ ቀን ጀምሮ ገዢ በየጊዜው ወደዚህ ቤት እየተመላለሰች ሻጯን ትጠይቃታለች፤ ቅርርባቸውም አደገ፤ እንዲያውም እቤት መዋልና ማደር ጀምራ ወዳጅነታቸው ተጠናከረ፡፡

ምስጢሩ ወ/ሮ እመቤት ለወ/ሮ መሰረት አንድ ምስጢር ማወያየት

ፈልጋለች፡፡ ይህን ምስጢር የምትነግራት እርዳታዋን ፈልጋ እንደሆነ አስቀድማ ገለፀችላት፡፡ ወ/ሮ መሰረትም አቅሟ የሚፈቅድ ከሆነ ልትረዳት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃታለች፡፡

ወ/ሮ እመቤት ባሏ ኮሎኔል እንደሆነ፤ ስራውም የመንግስት ባለስልጣን አጃቢ እንደነበር፣ አንድ ውድ ዕቃ እንዳለውና ከዚህ በፊት ከውጪ የመጡ ሰዎች ሊገዙት ሲሉ አይሆንም ብላ እንዳስቀመጠችው፣ አሁን ግን መሸጥ እንደፈለገች፣ በፊት ዕቃውን ሊገዙ የጠየቋቸው ሰዎች ውጪ ሀገር እንደሚኖሩና ስልክ ቁጥራቸውን እንደሰጧት፣ እርሷ መሃይም በመሆኗና የቋንቋ ችግር ስላለባት ደውላ ዕቃውን ስለመሸጥ ጉዳይ እንድታነጋግርላት ለወ/ሮ መሰረት ምስጢሯን አካፈለቻት፤ ወ/ሮ መሰረት ስልክ ስትደውል ግን ስልኩ አልሰራ አለ፡፡ ሌላ አማራጭ ለመጠቀም ወሰኑ፤ በኢ-ሜይል የዕቃውን ገዢዎች ማግኘት፡፡ አገኘቻቸው፡፡

ውዱን ዕቃ ገዢ ናቸው የተባሉት ከአሁን ቀደም ከወ/ሮ እመቤት ጋር እንደተገናኙ ለወ/ሮ መሰረት አረጋግጠው ከውሱን ቀናት በኋላ አዲስ አበባ ስለሚመጡ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ሊገናኙ ቀጠሮ ያዙ፡፡ እርሷም ይህንኑ ለወ/ሮ እመቤት ነገረቻት፡፡ ወ/ሮ እመቤትም የሚሸጠው ዕቃ አልማዝ

(ዳይመንድ) መሆኑን፤ ሰዎቹ በእርግጠኝነት እንደሚገዟት ገልፃ የሽያጩን ጉዳይ ነገሬ ብላ እንድትከታተል ሙጥኝ ብላ ለመነቻት፡፡

...የተጠበቀው የቀጠሮ ቀን ደረሰ፤ ወ/ሮ መሰረትም በወ/ሮ እመቤት የቀረበላትን ልመና ቸል ሳትል በአንድነት ተያይዘው ወደ ቀጠሮ ስፍራ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አመሩ፡፡ እርሷ አስተርጓሚ ወ/ሮ እመቤት ደግሞ ባለጉዳይ ሆና ሆቴሉ እንደደረሱ ከአንድ ጥቁር ሰው ጋር ተያዩ፤ ገዢውም ጥቁር ሰው መሆኑን ወ/ሮ እመቤት ነግራት ሰውየውን አነጋገሩት፡፡ በመጨረሻም ሰውየው ‹‹ዕቃውን ይዛችሁት እንድትመጡ›› በማለት ለቀጣዩ ቀን ቀጥሯቸው፤ ይህንን ያደረገውም በዕለቱ ሌሎቹ ጓደኞቹ እረፍት ላይ በመሆናቸው መሆኑን አስረዳቸው፡፡

በቀጠሮው መሰረት ለመገናኘት ተስማምተው ሲለያዩ ወ/ሮ እመቤት ለወ/ሮ መሰረት ሌላ ምስጢር ሹክ አለቻት፡፡ አልማዙ (ዳይመንዱ) የሚገኘው የእንጀራ ልጇ ጋር መሆኑን፡፡ ስለሆነም ዳይመንዱ እንዲሸጥ የእንጀራ ልጇን እንድታግባባላት ተማፀነቻት፡፡ ይህንንም ተልዕኮ ለማሳካት የእንጀራ ልጇን አስተዋወቀቻት፡፡ የእንጀራ ልጇም ለወ/ሮ መሰረት ስለ ዳይመንዱ ሲነግራት ‹‹አባቴ... እኔና እህቴን ወልዶ ስላላሳደገን ‹ይህንን ዳይመንድ ሸጣችሁ አምስት ሚሊዮን ብር አንተ ውሰድ፤ ቀሪውን ደግሞ ለእነሱ አከፋፍል› ብሎኘል፡፡ እኔ ደግሞ ብሩ ቅድሚያ ካልተሰጠኝ ዳይመንዱን ፈፅሞ አልሰጥም›› ይላል፡፡ ወ/ሮ እመቤት ግን የእንጀራ ልጇን እንድታሳምንላት ወ/ሮ መሰረት ቤት መመላለሱን አዘወተረች፡፡

ወ/ሮ መሰረት በተራዋ ለወ/ሮ እመቤት የግል ምስጢሯን አካፈለቻት፡፡ ‹‹የእናንተን ዳይመንድ ከሸጣችሁ በኋላ እኔም ከውጪ ሀገር የቀድሞ ባሌ በስጦታ የሰጠኝ ዳይመንድ ስላለኝ መሸጥ እፈልጋለሁ›› ስትል ለወ/ሮ እመቤት አማከረቻት፡፡ ወ/ሮ እመቤት ግን የእንጀራ ልጄ አሻፈረኝ አለ በማለት በድጋሚ እንድትለምንላት ልጁን ወ/ሮ መሰረት ቤት ይዛው መጣች፡፡ በወ/ሮ መሰረት ምክር መለስ ያለ የመሰለው ልጅ ‹‹እኔ የማለውቃቸው፣ እናንተ የምታውቋቸው ገዢዎች ዳይመንዱን ከተቀበሉኝ በኋላ ሊነጥቁኝ አሊያም ሊክዱኝ ይችላሉ፤ እና አንቺ ኃላፊነት ከወሰድሽ ላሳያቸው እችላለሁ›› በማለቱ ወ/ሮ መሰረትም በዚህ ተስማሙ፡፡ በተያዘው ቀጠሮ መሰረት ዳይመንዱን ይዞ መጥቶ ይገዛሉ ከተባሉት ሰዎች ጋር ተገናኙ፡፡ ገዢዎቹም ‹‹ትክክለኛ ዳይመንድ መሆኑን ካረጋገጥን አርባ ሚሊዮን ብር እንገዛለን›› ሲሉ ጆሮ የሚያቆም ዋጋ ጠሩ፡፡ ቀጠሉና እንዲህ አሉ፡- ‹‹ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ይሄን ያህል ገንዘብ ይዘን አልመጣንም፤ ስለዚህ ሴትየዋን ዱባይ ይዘናት እንሂድና ገንዘቡን ትራንስፈር እናደርጋለን››

ዋና ተደራዳሪዋ ወ/ሮ መሰረትም ‹‹በቅድሚያ የልጁን ድርሻ አምስት ሚሊዮን ብር ስጡትና ቀሪውን ከሴትየዋ ጋር ተነጋገሩ›› አለቻቸው፡፡ እነርሱም ‹‹የልጇን ድርሻ አንቺ ስጪልኝና እኛ ለእሷ እንተካለን›› አሏት፡፡ እርሷ ግን ‹‹እኔ ገንዘብ የለኝምና መስጠት አልችም፤ የልጁን ገንዘብ ካልሰጣችሁት ደግሞ ዳይመንዱን አይሰጣችሁም›› አለቻቸው፤ ለጊዜው ስምምነታቸው በዚህ ተፋርሶ ተለያዩ፡፡

09/06/2002 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00፣ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ

አለሚቱ በወ/ሮ መሰረት ቤት በሰራተኝነት ተቀጥራ መስራት ከጀመረች በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በቤት ውስጥ የምትታየው እንደ ቤተሰብ አባል እንጂ እንደ ሰራተኛ አይደለም፡፡ ሰራተኛዋ ወ/ሮ እመቤት የወ/ሮ መሰረትን ቤት ለመግዛት ከጠየቀችበት ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ መካከል መቀራረብ ተፈጥሮ ወደዚህ ቤት ስትመላለስ ታውቃታለች፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ሰራተኛዋ ከወ/ሮ መሰረት ሁለት ህፃናት ልጆች እንዲሁም ከወ/ሮ መሰረት እህት ልጅ ጋር ቤት ውስጥ ተቀምጠው እየተጫወቱ ነው፡፡ የቤቱ ባለቤት ወ/ሮ መሰረት ቤት ውስጥ የለችም፡፡ ከወ/ሮ እመቤት ጋር እዚህ ቤት ቀደም ሲል ይመጣ የነበረ ወጣት ወ/ሮ እመቤት በምታሽከረከርው መኪና ጋቢና ተቀምጧል፤ በር ላይ ሲደርሱ ወ/ሮ እመቤት የመኪናዋን ጥሩንባ ተጫነችው፤ ሰራተኛዋ አለሚቱ ባለመኪናዋ ሴትዮ ከቤቱ ባለቤት ጋር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፈጠረችውን ወዳጅነት ታውቃለችና የግቢውን በር

ከፍታ አስገባቻቸው፡፡ ሴትየዋ ከመኪና ወርዳ ወደ ቤት ስትገባ አብሯት የመጣው ሰው መኪናው ውስጥ ቁጭ ብሎ ይጠብቃታል፡፡

ወ/ሮ እመቤት የወ/ሮ መሰረትን ስም ጠርታ ‹‹የለችም እንዴ?›› ስትል ሰራተኛዋን ትጠይቃታለች፡፡ ሰራተኛዋም ቤት ውስጥ አለመኖሯን ትነግራታለች፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹...በቃ መሲ አሁን ትመጣለች፤ እስከዚያ ቡና አቀራርቢና ይፈላ›› ትላለች፡፡ ትዕዛዙን ካስተላለፈች በኋላ በቀጥታ ያመራችው ወደ ወ/ሮ መሰረት መኝታ ቤት ነው፡፡ መኝታ ቤት እንደገባች አልጋ ላይ ተቀምጣ ኮመዲኖውን በተመሳሳይ ቁልፍ መክፈት ትጀምራለች፡፡ ድንገት ሰራተኛዋ ተመለከተቻት፤ ሰራተኛዋም የወ/ሮ መሰረትን የእህት ልጅ ጠርታ አሳየቻት፡፡ ምን እየሰራች እንደሆነም ጠየቀቻት፡፡ በዚህ ጊዜ ወ/ሮ እመቤት ‹‹ከዚህ ዞር በሉ እንጂ፤ ልጅ ወሬ ማየት የለበትም›› ካለች በኋላ ከጉርድ ቀሚሷ ጎን የሻጠችውን ሽጉጥ በመምዘዝ ‹‹ሁላችሁም ዝም በሉ›› ብላ ደቀነችባቸው፡፡

ህፃናቱ በድንጋጤ ሲጯጯሁ እነርሱንም ዝም በሉ ብላ በሽጉጥ አስፈራራቻቸው፡፡ ህፃናቱ ለቅሷቸውን ባያቆሙም ሽጉጧን እንደያዘች ኮመዲኖውን በቁልፍ ከፍታ በጥቁር ፌስታል የተቀመጠ ዕቃ አውጥታ የጌጣጌጥ ማስቀመጫውንም ጥቁሩ ፌስታል ውስጥ ጨምራ ከቤቱ ወጣች፡፡ የያዘችውን ሽጉጥ አብሯት ለመጣው ሰው በማቀበል ፌስታሉን መኪናው ውስጥ አድርጋ መኪናዋን አስነስታ ወጣች፡፡ እርሱም ሽጉጡን ይዞ ከመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ በመቆም ፀጥ እንዲሉ አስፈራራቸው፡፡ እርሷ ከግቢው ከወጣች ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሞባይል ስልኩ የጥሪ ድምፅ አሰማ፡፡ ስልኩን አንስቶ እሺ የሚል ቃል ብቻ ተናግሮ ዘጋው፡፡ ቤቱ ውስጥ ያሉትንም ልጆች ‹‹አንድ ሰው እንዳይንቀሳቀስ፤ እኔ እዚሁ ግቢ ውስጥ ነው የምቆየው፤ አንድም ልጅ እንዳይጮህ›› ካለ በኋላ የቤቱን በር ከውጪ ቆልፎባቸው ወጥቶ ሄደ፡፡ ቤት ውስጥ የቀሩት ሰዎች ወደ ወ/ሮ መሰረት ስልክ ደወሉ፤ ስልኩ አይሰራም፡፡ ወ/ሮ መሰረት ወደ ቤቷ የተመለሰችው ከመሸ ነው፡፡ ያኔ ነበር የሆነውን ሁሉ የነገሯት፡፡ ለምን አልደወላችሁልኝም ብትል ስልኩ እንዳስቸገራቸው ነገሯት፤ ስልኩን ስታየው ከመስመሩ ተነቅሏል፡፡

ወ/ሮ እመቤት ወ/ሮ መሰረትን ቤትሽን እገዛሻለሁ በማለት ቤተኛ ከሆነች በኋላ፣ የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አለመኖራቸውን በማረጋገጥ ከአባሪዋ ጋር በመሆን፣ የወ/ሮ መሰረት መኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባት ቤት ውስጥ የነበሩትን ሰዎች አስፈራርታ ዝም በማሰኘት፣ የግል ተበዳይን ኮመዲኖ በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍታ በጥቁር ፌስታል የተቀመጠ ጥሬ ገንዘብ 200,000 ብር፣ ባለ 21 ካራት 200 ግራም የአንገት፣ የጆሮና የጣት የወርቅ ጌጣጌጦች ግምታቸው 120,000 ብር፣ ግራሙ ያልታወቀ የእጅ ብራስሌት፣ የአንገት ጌጥና የጣት ቀለበት፣ ግራሙ ያልታወቀ በግምት 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ዳይመንድ ካልተያዘው ጓደኛዋ ጋር በመሆን ይዛ መጥፋቷ ታውቆ ክስ ተመሰረተባት፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለችው ወ/ሮ እመቤት ‹‹የተዘረዘረውን የወንጀል ድርጊት አልፈፀምኩም፤ አባሪ የተባለውን ተጠርጣሪም አላውቅም፤ እኔ ምንም አይነት መሳሪያ የለኝም፤ ስለቀረበብኝ የክስ ጉዳይ ምንም የማውቀው ጉዳይ የለም፤ የቀረበብኝ ክስ ጉዳይም ጥፋተኛ አይደለሁም›› ስትል የተከሳሽነት ቃሏን ሰጠች፡፡ ሆኖም ወ/ሮ እመቤት በተከሰሰችበት በጦር መሳሪያ ዘረፋ ወንጀል በወቅቱ ወንጀሉ ሲፈፀም በቦታው የነበሩ አራት የሰው ምስክሮች ቀርበው መሰከሩባት፡፡ የቀረቡትም ምስክሮች እንደ ከሳሽ የክስ አቀራረብ በትክክል ወንጀሉ ለመፈፀሙ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

በተጨማሪም ተከሳሽ ወ/ሮ እመቤት ወንጀሉን ከፈፀመች በኋላ ሆን ብላ በሌላ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በሌላ ሰው እንድትከሰስ አድርጋ ታስራ ለመደበቅ መሞከሯ ታወቀ፡፡ ይኸው ጉዳይ ተጣርቶ የሀሰት ክስ የመሰረቱባት በፍርድ ቤት ቅጣት ያገኙ መሆኑም ማስረጃ ቀረበ፡፡ ወ/ሮ እመቤት በተከሰሰችበት የከባድ ውንብድና ወንጀል የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ19/05/03 በዋለው ችሎት ክስና ማስረጃውን ከህግ ጋር አገናዝቦ በሰጠው ውሳኔ በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና በ100,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ ወሰነባት፡፡

ባርሴሎና... ከገጽ 21 የዞረ

ይወክላል›› ያሉት አባት ሮሴል መሆናቸውን መዘንጋት የለበትም፡፡ ክለቡ ማንን እንደሚወክል እናት እንደሚወከል መመለስ ያለበት የባርሳ ቦርድ ነው፡፡ የቦርዱ ምላሽ ግን በሁሉም ደጋፊዎች ተቀባይነት ይኖረዋል ማለት ይከብዳል፡፡

የስፔን እና ካታላን ብሔራዊ ቡድኖችን ምን ይውጣቸዋል? በየዓመቱ ዲሴምበር ወር ላይ የሚካሄዱ የካታላን ኢንተርናሽናል የወዳጅነት ግጥሚያዎች አሉ፡፡ የ2011 ስኳድ ቪክቶራ ቫልዴዝ፣ ጄራርድ ፒኬ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ፣ ሰርጂዮ ቡስኬትስ እና ሴስክ ፋብሪጋዝን አካትቷል፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ደግሞ ከስፔን ጋር የአውሮፓ እና የዓለም ሻምፒዮኖች ናቸው፡፡ በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሁሉም የሚመኛቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ለካታላን ብሔራዊ ቡድን ለመጫወት አዋጅ የሚያስነግሩ ምን ያህሉ ናቸው የሚለው አነጋጋሪ ነው፡፡ አቋም መፈተሻ ጨዋታን ለካታላን ብሔራዊ ቡድን አድርጎ ወደ ዓለም ሻምፒዮኖቹ መመለስ አንድ ነገር ሲሆን በዘመናዊው እግርኳስ እጅግ ስኬታማ ለሆነው ብሔራዊ ቡድን እስከ መጨረሻው ድረስ ጀርባን መስጠት ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን በሪያል እና ባርሳ መካከል ከፍተኛ ተቀናቃኝነት ቢኖርም የስፔን ብሔራዊ ቡድን የካታላኖች፣ ካስቲያኖች እና ባስኮች ውህደት ውጤት ነው፡፡ ተጫዋቾችም ክልላዊ ክፍፍሎች እና ማንነት ጥቂት ትርጉም እንዳላቸው አፅንኦት የሰጡ ሲሆን ይህ አመለካከታቸውም ስኬትን አምጥቶላቸዋል፡፡ በአየርላንድ ተጫዋቾች ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል፡፡ በሰሜን አየርላንድ የተወለዱ ተጫዋቾች ለአየርላንድና ለተወለዱባት አገር የመጫወት ዕድል አላቸው፡፡ አርበኝነት፣ ማንነት፣ የአንድ ማህበረሰብ አካልነት እና የእግርኳስ ህይወትን ማሻሻል በተጫዋቹ ለየትኛው ቡድን ልጫወት የሚል ውሳኔ ላይ ተፅዕኗቸውን ያሳርፋሉ፡፡ እነዚህ የተወሳሰቡ ምርጫዎች ደግሞ የካታሎኒያ እና ስፔንን ተጫዋቾች ያጋጥሟቸዋል፡፡

ይህ አጣብቂኝ ወደ ካታላን ብሔርተኝነት ይመልሰናል፡፡ ምንም እንኳን ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ካታላናዊያን ‹‹ነፃነታቸውን›› ፍለጋ ሰልፍ ቢወጡም አብዛኛዎች በክልሉ የሚኖሩ ሰዎች ስደተኞች ወይም የስደተኛ ልጆች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ከድሃዋ አልሜሪያ የመጡ ናቸው፡፡ ከሰሜን አፍሪካ የመጡ ስደተኞች በሀብታሞቹ እና ትልቆቹ የካታላኒያ ከተሞች ኑሮን ለማሸነፍ ከትመዋል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች የካታላን ብሔርተኝነት ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም፡፡ በቃ የተለየ ቋንቋ ወደሚናገር ግዛት የመጡ ባዕዳን ናቸው፡፡ አካባቢያቸውንም መላመድ አለባቸው፡፡ ይህን ለማድረግ ከተጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ እግርኳስ ነው፡፡ ባርሴሎና የካታላን ብሔርተኝነት ምልክት እና ተሸካሚ ቢሆንም የባዕዳን ክለብ ነው፡፡ ከመስራቾቹ መካከል ስዊዘርላንዳዊ እና እንግሊዛዊ ይገኙበታል፡፡ በክለቡ ጀግኖች ዝርዝር ውስጥ ኩበላ፣ ዮሀን ክሯይፍ እና ሪስቶ ስቶችኮቭ የሚባሉ ካታላናዊ ያልሆኑ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ስፔን ከዓለም ጦርነት በኋላ ራሷን ከዓለም ስትነጥል ባርሳ ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የካምፕ ኑን በሮች ከፍቶ ነበር፡፡ ባርሳ ባለተሰጥኦዎችን በቤቱ በማሳደጉ ቢወደስም ታዳጊ ማዕከሉ የአርጀንቲናዊ፣ ብራዚላዊ እና ሆላንዳዊ ውህደት ውጤት ነው፡፡ ስደተኞቹ እና ልጆቻቸው ደረቱን ለካታላን ብሔርተኝነት እንደሚሰጥ ካላታናዊ ሁሉ ባርሴሎናዊ ናቸው፡፡ ክለባቸውን ማሳነስንና የብሔራዊ ቡድኑን መድከም ይቀበላሉ?

ስፔን ባለፉት ዓመታት በተመሳሳይ መንገድ አልፋለች፡፡ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሀገሪቷ ገና ዴሞክራሲ እየፈነጠቀ ነበር፡፡ ከጄኔራል ፍራንኮ ሞት በኋላ የ1982ቱን የዓለም ዋንጫ ለመደገስ ሽርጉድ እያለች ነበር፡፡ በዚያ ወቅት ስፔን ከአምባገነኑ ስርዓት መውደቅ በኋላ ራሷን ከምዕራቡ ዓለም ጋር የምታቆራኝበት ነበር፡፡ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አባል ለመሆንም ተቃርባ ነበር፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ከአሁኗ ስፔን ሁኔታ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ልክ እንዳሁኑ በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ነበረች፡፡ የስራ አጥ ቁጥሩ ጨምሮ የክልላዊ ውህደት ነግሰው ነበር፡፡ የባስክ ተገንጣይ ቡድን ኢቴኤ በተደጋጋሚ ጥቃቶችን ይሰነዝር ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ በቀኝ ክንፍ አክራሪዎች እና የጦር ኃይሎች የመፈንቅለ መንግስት (ባርሴሎና... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

‘ፍቅር እና ወንጀል” በሚለው አምዳችን በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ እዚህ አሜሪካ ውስጥ የሚፈጸሙ እውነተኛ የፍቅርና የወንጀል ታሪኮችን እንዲሁም ሌሎችን ዘገባዎችን እናቀርብበታለን።

ኬክ ጀምረናል

651-214-2584 ወይም 651-489-9220 ደውሉ

የጤፍ እንጀራችን ለምን ተወዳጅ

እንደሆነ ለማረጋገጥ ዛሬውኑ

የትንሣኤን በዓል በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

የተጸነሰባትን፤ የተወለደባትን፤ ልዩ ልዩ ገብረ ተአምራት የፈጸመባትን፤ ሥራዓተ ጥምቀት ያካሄደባትን፤ ሞትና ድል አድርጎ በክብር የተነሳባትን፤ ያረገባትን፤ ብርሃነ መለኮቱን

የገለጸባትን ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን ይጎበኙ ዘንድ ታላቅ ታሪካዊና መንፈሳዊ ጥሪ

ቀርቦልዎታል።

መጪውን የትንሣኤ በዓል በሀገር ቅድስት ኢየሩሳሌም ለማክበር ለሚፈልጉ ምዕመናን ልዩ የጉዞ፣ የሆቴልና የጉብኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ዝግጅቱ ሆቴልን፣ ምግብንና ጉብኝትን ያጠቃልላል።

ይህ ለረጅም ጊዜ ሲመኙት የነበረው ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን መጎብኘት ታሪክ ዕድል አያምልጥዎ፤ እያለ የሰላም ጉዞ ወኪል ጥሪውን ያቀርባል።

ምዕመናን ጋር አብረው በመጓዝ ታሪካዊዋን ቅድስት ከተማ፣ ቅዱሳት ገዳማትና አካባቢዋን መጎብኘት እንዲችሉ በስልክ ቁጥር 310-649-

5030 ደውለው ሰላምን ያነጋግሩ።

ሰላም የጉዞ ወኪል 5250 West Century Blvd. Suite #205

Los Angeles, CA 90045

Page 23: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

One-Stop

Shopping

Center

Page 24: AMERICAN REALTY GROUP. - Zehabesha – Latest ...ስለሙዚቃ ኮንሰርቱ ተጨማሪ መረጃ በገጽ 5 ይገኛል) የ2012 አዲስ ዓመትን ለመቀበል በሚኒሶታ

December 2012 ᴥ volume IV ᴥ No. 46 ታህሳስ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 46 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

At Furniture CFW we understand your goal of having a warm and inviting home – not just a house. We offer the highest quality furniture, a vast array of styles, and excellent value so that your goal can easily become a reality.

2941 Chicago Ave Minneapolis, MN 55407 612-998-5300

ከ8 ወደ 10 እንጀራ አደገ