Wof Washa Field Study Final Draft

53
በአብክመ ባህል፡ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ የዱር እንሰሳት ጥናት፤ልማት፤ጥበቃና አጠቃቀም የስራ ሂደት በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የወፍ ዋሻ ጥብቅ የመንግስት ደን ጥብቅ ቦታ የመሆን አቅም ለመለየት የተካሄደ የመስክ ጥናት አበጀ ዘዉዴ አብርሃም ማርየ መጋቢት 2002, ባህር ዳር

description

Field study

Transcript of Wof Washa Field Study Final Draft

Page 1: Wof Washa Field Study Final Draft

በአብክመ ባህል፡ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮየዱር እንሰሳት ጥናት፤ልማት፤ጥበቃና አጠቃቀም የስራ ሂደት

በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የወፍዋሻጥብቅ የመንግስት ደንጥብቅ ቦታ የመሆን አቅም ለመለየት የተካሄደ የመስክጥናት

አበጀ ዘዉዴ

አብርሃም ማርየ

መጋቢት 2002, ባህር ዳር

Page 2: Wof Washa Field Study Final Draft

ማሳሰቢያ

የወፍ ዋሻ የተጥሮ ጥብቅ ደን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜንሸዋ አስተዳደር ዞን በባሶና ወራና፤በአንኮበርና በጣርማበር ወረዳዎችይገኛል፡፡ ይህ ሪፖርት የወፍ ዋሻን ጥብቅ ደን ተፈጥሮአዊ ገጽታ፤ እየደረሰበት ያለዉን ጫናና የባለድርሻ አካላትን ሚና ጥናት ዉጤት ይዟል፡፡ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን በተፈጥሮዉ ማራኪ የመሬት አቀማመጥና በመጥፋት ላይ ያሉ እፅዋትና የዱር እንሰሳት መኖሪያ ከመሆኑም ባሻገር የስነምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ፤ ከባቢያዊ ሙቀት መጨመርን በመከላከልና በቱሪዝምመስህብነት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ነገር ግን በቂ ጥበቃ የማይደረግለት በመሆኑ ባልተገባ አጠቃቀም ሊሰጥ የሚችለዉን ጥቅም አለመስጠት ብቻ ሣይሆን ባለዉ ተፈጥሮአዊ ገጽታም የመኖር አቅሙ ፈተና ላይ ወድቋል፡፡ስለዚህ ደኑን ከዉድመት መታደግ የሚቻለዉ አሁን ካለዉ የጥበቃ ስልት የተሻለና ዘለቄታ ያለዉ ጥበቃ፡ አያያዝና አጠቃቀም ሊወጣለት ነዉ፡፡ለመፍትሔዉ የሁሉንም አጋር አካላት ትኩረት ይሻል፡፡ የግድም ይላል ምክንቱም ቅርስን ለትዉልድ የማስተላላፍ ግዴታ ስላለብን፡፡

Page 3: Wof Washa Field Study Final Draft

ማዉጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የወፍዋሻጥብቅ የመንግስት ደንጥብቅ ቦታ የመሆን አቅም ለመለየት የተካሄደየመስክጥናት............................................................................................................................................. 1

ማዉጫ 1. መግቢያ ................................................................................................................................... 3

1. መግቢያ.................................................................................................................................................. 5

2. በመስክ ስራው የተከናወኑዋና ዋና ተግባራት.......................................................................................... 6

3 የጥናቱመነሻ ......................................................................................................................................... 6

4. የጥናቱ አስፈላጊነት............................................................................................................................... 7

5 .የጥናቱ ዓላማ ......................................................................................................................................... 8

6. የጥናቱ ስልትና ሂደት............................................................................................................................. 8

7.ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ጉሳቁሶች............................................................................................................... 9

8.የዋፍ ዋሻጥብቅ የተፈጥሮ ደን አጠቃላይሁኔታ ..................................................................................... 9

8.1 የመስክጥናት ለማካሄድ የተመረጡ ቦታዎች .................................................................................... 9

8.2 መገኛ /Location/ና ስፋት ................................................................................................................ 11

8.3 የአየር ንብረት ................................................................................................................................. 12

8.4 የመሬት አቀማመጥ ........................................................................................................................ 13

9. የጥናቱዉጤቶችናትንተና .................................................................................................................. 14

9.1 የደን ጥበቃ ስልትናታሪክ................................................................................................................ 14

9.2 የወፍ ዋሻ ዝርዝር የተፈጥሮሀብትናመስህቦች ............................................................................... 16

9.2.1 የስነምህዳርውክልና ................................................................................................................. 16

9.2.2 የእጽዋት ሽፋንና አይነት………………………………………………………………………...17

9.2.3 ዱር እንሰሳት …………………………..…………………………………………………...............19

9.2.4 የመሬት ለምነትና የዉሃሃብት ................................................................................................. 20

9.2.5 በወፍዋሻና በአካባቢዉ የሚገኙ የተፈጥሮና ባህላዊመስህቦች ................................................... 22

10. የኢኮኖሚናማህበራዊሁኔታ ............................................................................................................. 26

Page 4: Wof Washa Field Study Final Draft

10.1 አዋሳኝ ቀበሌዎች .......................................................................................................................... 26

10.2 የሚበቅሉ ሰብሎች ........................................................................................................................ 29

10.3 የህብረተሰቡዋናዋና የገቢምንጮች............................................................................................... 30

11. በወፍዋሻ የተፈጥሮ ደን ላይ እየደረሱ ያሉችግሮች............................................................................. 30

12. የወፍ ዋሻጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም................................................................................................ 35

12.1 ታሳቢጥብቅ ስፍራውየሚኖረውጠቀሜታ................................................................................... 35

12.2. ጥብቅ ቦታ የመሆን አቅምማረጋገጫመስፈርቶች........................................................................ 36

12.3 የታሳቢፓርኩጠቀሜታናጥብቅ ቦታ የመሆን አቅምማረጋገጫመስፈርቶች ጥምረትዝምድና... 38

14. የባለ ድርሻ አካላትጥንተና ................................................................................................................. 39

15. የወፍ ዋሻታሳቢጥብቅ ስፍራ የመሆን ዓላማ...................................................................................... 42

16. በጥናቱወቅት ያጋጠሙችግሮች........................................................................................................ 43

17. ለወደፊትመከናወን ያለባቸው ስራዎች............................................................................................... 43

16. ማጠቃለያ .......................................................................................................................................... 45

ዋቢመጽሃፍት ........................................................................................................................................ 47

ዕዝል 1. ዋና ዋና የእፅዋትዝርያዎች ........................................................................................................ 48

ዕዝል 2 የእንሰሳት ዋና ዋናዝርያዎች ....................................................................................................... 51

ዕዝል 3 ዋና ዋና የአዕዋፍዝርያዎች ......................................................................................................... 52

ዕዝል 4. በወፍዋሻጥብቅ የተፈጥሮ ደንና በአካባቢዉ የሚገኙ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችናመገለጫዎቻቸዉ፡፡................................................................................................................................... 53

Page 5: Wof Washa Field Study Final Draft

1. መግቢያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ መስሕብ ቦታዎች ተጠንተው፣ ተለይተውና በሚያመች የጥብቅ ስፍራ ተመድበው እንዲለሙ ለማድረግ እንዲቻል የሚመለከታቸውን የሴክተር መስሪያቤቶች በማቋቋምና በማደራጀት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም በእጅጉ የተፈጥሮ ሀብቱና የፓርኩ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ተዳክሞ የነበረውን የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ዛሬ ወደሚገኝበት የተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገር ከመደረጉም በላይ አዳዲስ ጥብቅ ስፍራዎችን በማቋቋም ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በቆላማውና በምዕራባዊ የክልሉ ክፍል በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የሚገኘውን ሰፊ የደን ሽፋን በማካለል በተፈጥሮ ገጽታው የሚታወቀውን የአላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ ፣ በደቡብ ወሎ በቦረና ፣ በመሐል ሣይንትና በሳይንት ወረጃዎች የሚገኘውን የቦረና ሣይንት ብሔራዊ ፓርክ ፣ የመንዝ ጓሳ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ እንዲጠኑ ፣ እንዲቋቋሙና አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት አንስቶ በፌዴራል ደረጃ ሊተዳደሩ የሚችሉበትን አመች ሁኔታ በመፍጠሩ በአሁኑ ሰዓት የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክና የአላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ በፌዴራል የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት እንዲተዳደሩ አስችሏል፡፡

የክልሉ መንግስት ከላይ የተቀጠሱት ተግባራትና ሌሎች ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም ያላቸውንና የተፈጥሮ ይዞታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ጥናት ፣ ልማትና ጥበቃ እንዲሁም የአጠቃቀም ደረጃቸውን አቅም ለመወሰንና ለማስተዳደር ቀደም ሲል የፓርክ ልማትና ጥበቃ ባለስልጣንን አሁን ደግሞ በባህል ቱሪዝምና ፓርከች ልማት ቢሮ የዱር እንስሳት ጥናት ፣ ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀምን የሰራ ሂደት በማደራጀት ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

የዱር እንስሳት ጥናት ፣ ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም የስራ ሂደትም በስሩ የተዋቀሩትን የጥናት ፣ የልማትና ጥበቃ እንዲሁም የአጠቃቀም የስራ ቡድኖችን በማስተባበርና አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ የስራ ሂደቱን አላማ በማሣካት ላይ ይገኛል፡፡ የስራ ሂደቱ ከሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት አንዱ ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም ያለቸውን የተፈጥሮ ቦታዎች በIUCN በአለም የተፈጥሮ ጥበቃ ሕብረት መስፈርት መሠረት በማጥናት የጥብቅ ስፍራነት ደረጃቸውን መወሠን ነው፡፡

በዚህም በክልሉ በስሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን በባሶና ወራና ፣ በአንኮበርና ጣርማበር ወረዳዎች የሚገኘውን የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅሙን ለማወቅ የሚያስችል ጥናት ከጥር 12 እስከ የካቲት 2/2ዐዐ2 ዓ.ም በቦታው በመገኘት ጥናት ተካሂዷል፡፡ በጥናቱ የተገኙትን ዝርዝር የተፈጥሮ ኃብት ፣ ካባቢያዊ ፣ ማህበራዊና ኢከኖሚያዊ ሁኔታዎችን በማካተት ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅሙን የሚለኩ መረጃዎችን በዚህ ሪፖርት ተካተዋል፡፡ ጥናቱ የዋፍ ዋሻን የጥበቃ ታሪክ ፣ የደኑን ሽፋን ፣ በውስጡ የሚኖሩ የዱር እንስሳትን የጥበቃና የአጠቃቀም ሁኔታዎችን በማካተት የተካሄደ ሲሆን በተገኙ መረጃዎች መሠረት የIUCN ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም መገምገሚያ መስፈርቶችን በማካተት በምን የጥበቃ ስልትና ምድብ የተፈጥሮ ሃብቱ በዘላቂነት ሊኖር እንዲሁም ተገቢውን ጥቅም ሊሰጥ የሚችልባቸውን መንገዶች በማመላከት ውሰኔ ለመስጠት በሚያሰችል መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡

ስለዚህ የባህል ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ ፣ የዱር እንስሳት ጥናት ፣ ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም የስራ ሂደት ፣ የሰሜን ሸዋ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ የሶስቱ ወረዳዎች /የባሶና ወራና ፣ የአንኮሪርና የጣርማበር/ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ባለቤትና ዋነኛ አጋር አካላት በመሆናቸው በቀጣይ ደኑ ያሉበትን ችግሮች በመቅረፍ የተሻለ የጥበቃ ይዘት እንዲኖረው ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች አጋር አካላትም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በደኑ ላይ የሚታዩ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን በመቀነስ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የሚያስችሉ ስልቶችን ይጠቁማል፡፡

Page 6: Wof Washa Field Study Final Draft

በመጨረሻም የተፈጥሮ ደኑ በተሻለ የጥበቃ ስልትና ዘላቂ ልማት የሚጠበቀውን ጥቅም እንዲሰጥና በዋነኛ የገቢ ምንጭነትም ሊየገለግል የሚችልበት የቱሪዝም አቅም ተዳሷል፡፡

2. በመስክ ስራው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ወፍዋሻ የመንግስት ደንታሪክ የአጠባበቅ ስልት በማካተት ትንተና ተሰጥቷል፡፡ የወፍዋሻ የመንግስት ደን የተፈጥሮ አቀማመጥ፣ ስነምህዳርና የብዝሃሕይወት ክምችትተለይቷል፣ የወፍ ዋሻ የመንግስት ደን በአለም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ህብረት (IUCN) መስፈርት መሠረት

የሚገባው የጥበቃ ስልትተዳሷል፡፡ ከወፍ ዋሻ የመንገግስት ደንውስጥና ወጭ (የተወሰኑ) ለቱሪዝምምቹ የሆኑ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች

ተለይተዋል፤፤ በወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና እንስሳትና እጽዋት ዝርዝርና ሳይንሣዊ መጠሪያ

ተለይቷል፣ በወፍ ዋሻ የመንግስት ደን አጠባበቅ ላይ ያሉችግሮችና የመፍትሄ ሃሣቦችተተንትነዋል፣ በወፍ ዋሻ የመንግስት ደን የሚያስተዳድሩትመንግስታዊመስሪያ ቤቶችና ሌሎችአካላት የነበራቸውንና

የሚኖራቸውሚናተለይቷል፡፡ በወፍ ዋሻ የመንግስት ደን የአካባቢው ማህበረሰብ ያለው የአጠቃቀም ሁኔታና የሚያስከትለው አሉታዊ

ተፅዕኖ ከሚጠበቀውመፍትሄሃሣብጋርተዘርዝሯል፡፡

3 የጥናቱ መነሻ

የወቅቱ ትኩረት የአካባቢ ጥበቃ ለአለውና ለመጭው ትውልድ ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት በርካታ የተፈጥሮ አካባቢዎችና የተራቆቱ ስፍራዎች ተጠብቀውና ለምተው እየደረሠ ያለውን የአካባቢያዊ ለውጥና የአየር መዛባት ሊታደጉ ይችላሉ የሚል ነው፡፡ ለዚህም በርካታ የአካባቢ ጥበቃና የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ከመቸውም ጊዜ በተሻለ እንዲሠራ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው፡፡ ስለዚህ በእጅጉ እየተመናመነ የመጣውን የዱር እንስሳት ሃብትና የተፈጥሮ ገጽታዎች በተገቢው ጥበቃና ስልት ዘላቂ የሆነ ሕብረተሰቡን የሚያግዝ አጠቃቀምና ይዘታቸው ሳይዛባ የስነ-ምህዳርና የቱሪዝም አቅማቸውን በማጐልበት ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ ሁለንተናዊ ጥቅም እንዳለው በመገንዘብ ተግባራዊ ምላሽ የሚሰጥበት በመሆኑ ነው፡፡

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደንም ከ15ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ የጥበቃ ትኩረት አግኝቶ በንጉስ ደንነት እየተጠበቀ ቆይቶ በ2ዐኛው ክፍለ ዘመን መባቻ የመንግስት ደን በመጣል እየተጠበቀ ቢሆንም አሁን ደግሞ የተሻለ የአጠባበቅ ስልት መቀየስ ፡፡ ይህ ተግባራዊ ለማድረግ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድና ያለበትን ደረጃ ለመገምገምየ ሚያስችሉና ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም እንዳለው አመላካች የዳሰሳ ጥናቶች ማካሄድ በማስፈለጉ ጥናቱን ለማካሄድ ተችሏል፡፡

በቅድሚያ ትኩረት የተሰጠውና የጥናቱ መነሻ የሆነው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልሉን በስድስት የልማት ቀጠናዎች በመክፈል በወጣው የአምስት አመት (2002-2007) ስትራቴጅክ እቅድ በምስራቅ አማራ የልማት ቀጠናና (አንኮበርና ጣርማበር) በመካከለኛዉ የልማት ቀጠና (ባሶና ወራና) የሚገዉኘዉን የወፍ ዋሻ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ወደፓርክ ሊያድግ የሚችል መሆኑ የተገለጸ በመሆኑ ይህንም በጥናት ማረጋገጥ በማስፈለጉ ነው፡፡ በተጨማሪም የወፍ ዋሻ ደን ከፍተኛ የሆነ የደን ሽፋን ያለውና በየጊዜው እየቀነሰ የመጣ በመሆኑ የተለየ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚደርስበትን አሉታዊ ተጽዕኖ መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን በዎፍ ዋሻ አካባቢ የተቋቋመው የሱናርማ አገርበቀል ግብረሰናይ ድርጅት በጥናቱ በገለፃቸው አብይት ችግሮች የጥበቃና የልማት ደረጃው እንዲሻሻል ማስፈለጉን ይገልጻሉ፡፡

Page 7: Wof Washa Field Study Final Draft

በሌላ በኩል በክልሉ መንግስት በደን ሃብታቸው የተሻሉ ከሚባሉት የተፈጥሮ አካባቢዎች አንዱ መሆኑና በኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት እንዲስቲቲዩት 2ዐዐ5 ትስራቴጅክ ፕላን የተካተተ በመ ሆኑ ደኑን አጥንቶ የጥበቃ ስልቶችንና ለወደፊት በዘላቂ ጥበቃና አጠቃቀም ስልት መጠበቅ ከሚገባቸዉ ቦታዎች አንዱ በመሆኑ ነዉ፡፡

ጥናቱን ለማካሄድ አስፈላጊው በጀት የሰው ኃይልና ተሽከርካሪ መገኘቱ ለመስክ ስራው የተሰጠውን ትኩረት በማጉላት አስቸጋሪና ወጣ ገባ የሆነው የመሬት አቀማመጥ እንዲሁም ቀዝቃዛና ነፋሣማ የአየር ንብረት በመቋቋም ተከናውኗል፡፡

4. የጥናቱ አስፈላጊነት

የወፍ ዋሻ ደን ቀደም ሲል የንጉስ ደን ኋላም በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት የመንግስት ደን በመባል በመጠበቅ ላይ ሲሆን ከያዘው ብዝሃ ሕይወትና ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ አኳያ ጥብቅ ስፍራ ሆኖ የጥበቃና የአጠቃቀም ስልቱ እንዲሻሻል በተለያዩ መረጃዎችና ጥናቶች መገለጹ፣

የደኑና በውስጡ የሚገኙ የዱር እንስሳት አሁን ባለው የአጠባበቅ ስልት ለዘላቂ ልማት በሚያስችል መልኩ አለመሆንና የደኑ ስፋት ከጊኬ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመምጣቱና በውስጡ የሚገኙ የዱር እንስሳት ቁጥር መመናመናቸው፣

የወፍ ዋሻን ደን አሁን ካለበት የአጠባበቅ ስልት ወደ ተሻለ አጠባበቅና ዘለቄታ ባለው መንገድ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ቀደም ሲል የተካሄዱ ጥናቶች በቂ አለመሆናቸው አብዛኛው የተፈጥሮ ሃብት ይዘትና የችግሮቹ መንጮች በዝርዝር አለመታወቃቸው ጥናቱን ማካሄድ ወሳኝ ሆኖ በመገኘቱ፡፡

የወፍ ዋሻን የጥበቃና የጐብኝዎችን ፍላጐት ለማርካት በአካባቢው የሚገኙ መስህብነት የላቸው ተፈጥሮአዊና ባሕላዊ በዝርዝር በመካተት የላቸውን ትስስር በማጉላት በቱሪስት መስህብነቱ የበለጠ ጠቀሜታ እንዲኖረው ማድረግ አሁን ያሉትን የአጠቃቀም ችግሮች ለመቀነስ የጐላ አስተዋጾ ይኖራቸዋል፣

የወፍ ዋሻን ደን በመንከባከብና በማልማት ኃላፊነት ያለባቸውና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውንና ደኑን ተጠብቆ እንዲቆይ ያከናወኑትንና ለወደፊትም የሚኖራቸውን ሚና ለይቶ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፣

ደኑን ለመጠበቅና ለመንከባከብ የሚያስችሉ የመሠረተ ልማቶች ፣ የማቴሪያልና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን አይነትና የሚፈለጉበትን ደረጃዎች ለይቶ ማስቀመጥና በሂደት ተግባር ላይ የሚውሉበትን ስልት ለመቀየስ፣

የወፍ ዋሻ ደን በተለያዩ ሶስት ወረጃዎች ክልል ውስጥ ስለሚገኝ በእያንዳንዱ ወረዳ የሚመለከታቸው አካላት በምን ያህል መጠን በመተባበርና በመተጋገዝ በጋራም ሆነ በተናጠል እያደረጉት ያለውን አስተዋጾ መለየት ስለሚያስፈልግና በዚህም የአካባቢው ማህበረሰብ ለጥበቃ የተሰጠውን ትምህረትና እያደረገ ያለውን አስተዋጾ በመለየት መልካም አሠራሮችን ለማጐልበት ችግሮችን ደግሞ ከወዲሁ ማስተካከል እንዲቻል ጥናቱ ከፍተኛ አስተዋጾ ስላለው፡፡

Page 8: Wof Washa Field Study Final Draft

5 .የጥናቱ ዓላማ

የወፍ ዋሻን የመንግስት ደን የብዝሃ ሕይወት ክምችት፣የተፈጥሮ ገዕታ› አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለማጥናት፡፡

የወፍ ዋሻ የመንግስት ደን ባለው የብዝሃ ሕይወት ክምችና ተፈጥሮአዊ ገጽታ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ባህላዊ ቅርሶች ይዘት የIUCN ጥብቅ ስፍራ የመሆን መስፈርቶችን በማካተት የጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅሙን ማወቅ፣

የወፍ ዋሻን ጥብቅ የመንግስት ደን አጠባበቅ ለማጐልበትና ሊሰጥ የሚችለውን ጥቅም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ አጋር አካላትን ሚና መለየት፡፡

6. የጥናቱ ስልትና ሂደት

የወፍ ዋሻን ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም ለማጥናት የIUCN የጥናት ሂደቶችን በመከተል የተከናወነ ሲሆን ሒደቱም በሚከተሉት ደረጃዎች ተካሂዷል፡፡ የወፍ ዋሻ ደን ሊጠና የሚገባዉ ታሳቢ ጥብቅ ስፍራ መሆኑን በመለየት የወፍ ዋሻ ደን በዉስጡ የያዛቸዉን ፊዚካልና ስነሕይወታዊ ሀብቶች መኖራቸዉን ማረጋገጥ እነዚህ ሃብቶች የወፍ ዋሻ ደን ጥብቅ ስፍራ እነዲሆን ያስችላሉ ወይስ አያስችሉም የሚለዉን

ምላሽ ለመስጠት መጠናት አለበት በሚል የሚከተሉት የደኑ ሃብት በማተኮር ጥናቱ ተካሂዷል፡፡1. የተፈጥሮ ሀብቶቹ አይነት፤ጥበቃና ጥቅም መለየት 2. የተፈትሮ ሀብቶቹ ያሉበትን ደረጃዎችና ዕየሰጡት ያሉን ጥቅም መመዘን 3. ከባቢዊ ችግሮችና ስጋቶች መለየትና ተጽእኖአቸዉን ማወቅ

ከላይ የተጠቀሱትን ሂደቶች ለማሟላት የሚከተሉት የጥናት ስልቶች ተግባራዊ ሁነዋል፡፡

የወፍ ዋሻ ጥብቅ የመንግስት ደን ላይ ቀደም ሲል የተሰሩ ጥናቶችንና ሌሎች ተግባራትን ከተለያዩ ምንጮች መፈለግና ማጠናቀር፣

በሶስቱም ወረዳዎች የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብት ባለሙያዎችና የጥበቃ ሠራተኞች ጋር በመሆን በደኑ ውስጥ የሚገኙ የእጽዋትና የእንስሳት ዝርያዎችን እንዲሁም የመሬት አቀማመጥ ፣ ወንዞችንና የተለየ ገጽታ ያላቸውን የተፈጥሮ አቀማመጥ በመለየት ፣ ያላቸውን ተፈጥሮአዊና ባህላዊ ገጽታዎች መመዝገብ፣

የዱር እንስሳትና እጽዋትን ለመለየት የሚያስችሉ ጋይድ ቡከ በመጠቀም የጥናት ብሎኮችን መጠቀምና የተገኙትን በመመዝገብ፡፡

በIUCN መስፈርት መሠረት የተቀመጡትን መለኪያዎች በመጠቀም ጥብቅ ደኑን መግለጽና መረጃዎችን መተንተን፡፡

በላይ በተጠቀሱት ጥናትና ሂደት ጥብቅ ስፍራ የመሆን ዕድሉን የሚያገዙ እዉነታዎችና መከናዎን ያለባቸዉን ጉዳዮች በመለየት የወፍ ዋሻ ደን ጥብቅ ስፍራ እነዲሆን የሚያስችሉትን ሁኔታዎች ተለይተዋል፡፡ በዚህም ያሉትን የብዝሃ ህይወትና የተለየ ገፅታ ወይም ሊጠበቅ ያስቻሉተን ነጥቦች ለመለየት ተችሏል፡፡

Page 9: Wof Washa Field Study Final Draft

ከዚህ በኋላ የሚሰጡ ዉሳኔወችና ስራዎች ከጥናቱ ግኝትና በሚያሟላዉ የጥበቃ ስልት ይወሰናል፡፡ እነርሱም ጥብቅ ስፍራ ለማድረግ የቦታ ዲዣይንና የዳር ደንበር ወሰን በመለየት የስፋት መጠኑንና ቅርፅ ለጥበቃ ያለዉን አመችነተ፤ ተጓዳኝ ችግሮችንና መፍትሄዎች በአጥኝዎች ከቀረበዉ ትንተና በመነሳት በጋራ ጥናቱ ላይ በሚሠጥ ግምገማ ይወሰናል፡፡ በከዚህ በኋላ ጥብቅ ስፍራ የሚሆንበትንምድብ በጋራ ዝርዝሩ ከቀረበ በኋላ መሰየምና የማቋቋሚያ ሰነድ ማዘጋጀት ይሆናል፡፡

7.ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ጉሳቁሶች

ከላይ የተዘረዘሩትና ስልቶች በመከተልና የሚከተሉትን ቁሣቁሶች በመጠቀም ጥናቱ ተካሂዷል፡፡ እነዚህም፡-

ጂ.ፒ.ኤስ የመገኛ ኮኦርድኔት/ነጥብ/ና ከባህር ወለል በላይ የቦታዎችን ከፍታ ለማወቅ፣ ባናኩላር አቅርቦና አጉልቶ የሚያሳይ፣ የፎቶ ካሜራ የተገኙትን የተፈጥሮ ሃብቶች ፣ የአካባቢ ገጽታና የባህላዊ ቅርሶች በፎቶ የተደገፉ

መረጃ በመያዝ፡፡ የዱር እጽዋትንና እንስሳትን ለመለየት የሚያስችል መመሪያ መጽሃፍ /Guide Book/

8.የዋፍ ዋሻጥብቅ የተፈጥሮ ደን አጠቃላይሁኔታ

8.1 የመስክጥናት ለማካሄድ የተመረጡቦታዎች

የወፍ ዋሻን የተፈጥሮ ደን ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም ለማጥናት ሁለተኛ ደረጃ መረጃዎችን ከድህረ ገጽና ህትመቶች በማሰባሰብ፤ በ2002 እና በ2005 በሰሜን ሸዋ ዞን ግብርናና ገጠር ልማትና በሱናርማ በተባለ አገር በቀል ድርጅት የጥናት መረጃዎችንና በኢትዮጲያ የተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በደኑና በአካባቢዉ ስላሉ አእዋፋት የተደረጉ ጥናቶችን በመለየት ጠቃሚ መረጃዎቸን በመሰብሰብ በተለይ ቀደም ሲል ስለነበረዉ የደን ሽፋንና ብዝሃ ህይወት ከሞላ ጎደል ለማወቅ ተሞክሯል፡፡ አሁን ያለበትን ደረጃ በዞንና በሶስትም ወረዳዎች ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት በመገኘት መረጃዎችን ለመሰብሰብ ቃለመጠይቅ ተካሄዷል፡፡

ፎቶ 1. በባሶና ወራና ወፍ ዋሻ ደበሌ ፤ጎሹ አገርና ጎሽ ሜዳ በኩል በከፊል ሲታይ

Page 10: Wof Washa Field Study Final Draft

እነዲሁም በዞንና በወረዳ ደረጃ የተሠጡ ትንተናዎችን በመለየትና ከየወረዳዎቹ ከተወከሉ ባለሙያዎችና ከደኑ ዘበኞች ጋር በመሆን በተለያዩ ወካይ ቦታዎች የጥናት መረጃ መሰብሰቢያ መስመር (Transect line) በመንቀሳቀስ አንደኛ ደራጃ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ ለዚህም በባሶና ወራና በኩል የዳገታማዉን ገደል አፋፍ ተከተሎ ከደበሌ እሰከ ቀይት (ጎሽ ሜዳ)፤ አባሞቴ፡ በጉዶበረትና ባሶ ደንጎራ ከዋናዉ ከደብርሲና ደብረብርሃን መንገድ እስከ ወፍ ዋሻ ደን መዳረሻ በአራትየጥናት መስመሮች በመንቀሳቀስ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡

ፎቶ 2. በባሶና ወራና ወረዳ በኩል በአባሞቴና ጉዶ በረት አካባቢ የጥናት መስመሮችና የተፈጥሮ ገጽታዎች

በአንኮበር ወረዳ በኩል ከአንኮበር (ጎረቤላ) ቤተመንግስት፤ በታሪዊዋ አልዩ አንባ ከተማ ከዚያም በሃር አምባ በኩል በዘንቦና በመስጫ ቀበሌችዎ ከደኑ ክልል ዉጭ ደቡብና ምስራቃዊ አዋሳኝ በሚገኙ ቀበሌዎች መረጃወችን ለመሰብሰብ፡- በመስጫ ቀበሌ ከመስጫ ዉቲ፤ከዉቲ ሸለቆ በረት፡ ከሸለቆ በረት መስጫ፤ ከመስጫ ፍቅሬ ግንብ፡ ከፍቅሬ ግንብ መሃል ወንዝ፡ ከመሃል ወንዝ ቁንዲ ላይ ጎረቤላ ድርስ ጥናት የተካሄደባቸዉ የጉዞ መስመሮች ናቸዉ፡፡ በዚህ የጥናት መስመር በዘጎ፤ በመስጫ፡ በመሃል ወንዝ፤ በዘንቦና በላይ ገጎረቤላ የሚገኙ መስህቦችና የተፈጥሮ ገጽታዎች ተቃኝተዋል፡፡

ፎቶ 3 ከአልዩ አንባ እስከ ዘንቦ የሚገኙ የተፈጥሮ ገጽታዎችና የቆላማዉ የአንኮበር ወረዳና የአፋር አዋሳኝቀበሌዎች በከፊል

Page 11: Wof Washa Field Study Final Draft

በጣርማ በር ወረዳ በኩል ደኑን የሚያዋስኑት ሶስት ቀበሌዎች ብቻ ቢሆኑም ስያሜዉን ያገኘበትና የጥበቃ ጽ/ቤት የሚገኘዉም በዚህ ወረዳ በኩል ሲሆን በደብረ ማዕዛ ቀበሌ በኩል ወደ ወፍ ዋሻ ቀበሌ በመሄድ ከጉዶ በረት አዋሳኝ እስከ ዋንዛ በረት የአዋዲን ወንዝ የግራ ገጽታ በመከተል የመስክ ቅኝት ስራዉ ተካሂዷል፡፡

ፎቶ 4፡ በጣርማ በር ወረዳ በኩል ያለዉ የወፍ ዋሻ ደን፡ ከዠኖ በረት ግርጌ አስከ አዋዲ ወንዝ ያለዉ የተፈጥሮ ገጽታ

8.2 መገኛ /Location/ና ስፋት

የወፍ ዋሻ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን በአብክመ በሰሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን በባሶና ወራና ፣ በአንኮበርና በጣርማ በር ወረዳዎች ይገኛል፡፡ የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ከደብረ ብርሃን ከተማ 24ኪ.ሜ ርቀትላይ ከደብረብርሃን አንኮበር መንገድ የሚገኝ ሲሆን 39042’00’’ እስከ 39040’00" ምስራቅ ሎንግቲውድና ከ9034’00" እስከ 10020’00” ሰሜን ላቲቲዩድ ላይ ይገኛል፡፡

የወፍ ዋሻ ደን በምስራባዊዉ ክፍል ገደላማ በምስራቃዊዩ ደግሞ ወጣገባና ሸለቆ የበዛበት ከስምጥ ሸለቆ ይዋሰናል፡፡ ከደቡብ ምስራቅ ወደ ሰሜን ምእራብ የተዘረጋዉ የተራራማ ሰንሰለቱ ተፋሰስ ደግሞ የአዋሽን ወደ ምስራቅና የአባይን ደግሞ ወደ ምእራብ ባለዉ ክፍል የያዘ ነዉ፡፡

የተፈጥሮ ደኑ ስፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ1994 92200ሄክታር ይሸፍን የነበረዉ እ.ኤ.አ በ2002 ዓ.ም ወደ 8290ሄክታር በ2005 ራግሞ ወደ 8222ሄክታር ዝቅ ማለቱን የሱናርማ ጥናት ያመላክታል በአለፉት ሶስት አመታት ደግሞ ከዚህም ሊቀነስ እንደሚችል አሁን እየታዩ ያሉት ችግሮች አመላካች ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም በዘንቦ፡ በእመምረትና በመስጫ ቀበለዎች በመንደርና በእርሻ ማሳ የተቆራረጡ ደኖችን የሚጨምር ሲሆን ተከታታይ የደን ሽፋን ያለዉ ከ600ሺ ሄክታር አይበልጥም፡፡ ሆኖም የተቆራረጡት ደኖች ዋነኛ የዝግባና የወይራ ዛፎች የሚገኝባቸዉ ናቸዉ፡፡

የወፍ ዋሻ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን በአብዛኛው በአንኮበር ወረዳ የሚገኝ ሲሆን የደኑ ክልል የሚገኝባቸውና ከደኑ ድርሻ ያላቸው ቀበሌዎች በባሶና ወራናና በአንኮበር ስድስት ስድስት ቀበሌዎችበጣርማበር በኩል ደግሞ ሶስት ቀበሌዎች ናቸው፡፡ በባሶና ወራና ወረዳ በሣብ አፍሮ አልፓይን ስርዓተ ምህዳር የጓሣ ፣ ጅብራ ፣ የዋሊያ ሾህ /ጋርዳ/ና ጦስኝ የሚበቅልባቸውን የገደሉን አፋፍ ተከትሎ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ደበሌ ፣ ጐሽ አገር ፣ ቀይት ፣ አባሞቴ ፤ጉዶ በረትና ባሶ ደንጐራ ቀበሌዎች የሚገኙ የወፍ ዋሻ አዋሳኝ ጐጦችን ያካትታል፡፡

በአንኮበር ወረዳ በኩል ዋናው የደኑ ሽፋን የሚገኝበት ቢሆንም በበርካታ ጐጦችና የእርሻ ቦታዎች በደኑ አካባቢ በመኖራቸው የደኑ ሽፋን በተቆራረጠ መልኩ በመኖሪያ አካባቢዎችም ይታያል፡፡ የወፍ

Page 12: Wof Washa Field Study Final Draft

ዋሻ ደን በአንኮበር ወረዳ የሚገኝባቸው ቀበሌዎች ከደቡብ ወደ ሰሜን ላይ ጐረቤላ፤ መሃል ወንዝ፤እመምረት ፣ ዘጐ፣ መስጫና ዘንቦ ቀበሌዎች ሲሆኑ ፍቅሬ ግንብ እርቦማርና ውቲ የሚባሉ ጐጦች ቀደም ሲል የነበረውን የደን ሽፋን በመቁረጥ በተፈጥሮ ደን ተከበው የሚገኙ የእርሻና የመንደር ጐጦች ናቸው፡፡

በጣርማበር ወረዳ በኩል ጥብቅ የተፈጥሮ ደኑ ስያሜውን ያገኘበት የወፍ ዋሻ ቀበሌና ደብረማዕዛ የተባሉ ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን ዋንዛ በረት በምስራቅና ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የዋዱ ወንዝን ተከትሎ የሚገኘውን የደኑን አካል ያካልላል፡፡ ቀደም ሲል ለደኑ በተሰጠው ትኩረት በ1959 የተሠራውና ከ1954 ህ.ም ጀምሮ ቋሚ የመንግስት ሠራተኞች የሚገለገሉት ጽ/ቤትም የሚገኘው በዚሁ ወረዳ በወፍ ዋሻ ቀበሌ ነው፡፡

በአጠቃላይ የወፍ ዋሻ የመንግስት ደን የ15 ቀበሌዎች አካል የሆነና በሶስት ወረዳዎች ተከፍሎ የሚገኝ ነው፡፡ በዚህም ባሶና ወራና በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ እስከ ሰሜን ምዕራብ ሲያካልል ፣ አንኮበር ደግሞ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ምስራቅና ሰሜን ምስራቅን አቅጣጫ ያካልላል፡፡ የጣርማበር ወረዳ በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ደኑን ያዋስናል፡፡ ስለዚህ የወፍ ዋሻ የመንግስት ጥብቅ ደን ከላይ በተጠቀሰው የጂኦግራፊ ኮኦርድኔት ከ2ዐዐዐ እስከ 37ዐዐ ሜትር ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ሳብ አፍሮ አልፓይንና ደረቅ ምንታኔ ስርዓተ ምህዳር የሚገኝ ነው፡፡

8.3 የአየር ንብረት

የወፍ ዋሻ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን የአየር ንብረት ከባህር ወለል በላይ በሚገኝበት ከፍታ የሚወሰን ሲሆን የአዋዲ ወንዝን ተከትሎ ዝቅተኛውን ከባህር ወለል በላይ እስከ 16ዐዐ ሜትር ድረስ ዝቅ እስከሚለው ከዋንዛ በርት ግርጌ አንስቶ እስከ 37ዐዐ ሜትር ጐሽሜዳ ኮረብታዎች የሚደርስ በመሆኑ ከወይና ደጋ እስከ ደጋ ያለውን የአየር ንብረት ያጠቃልላል፡፡ የላይኛውና ጓሣው አካባቢ በገደላገደልከደን ክልል የሚዋሰንና ነፋሣማ ሲሆን ከገዳላማው ግርጌ ዋናው የወፍ ዋሻ አካል በአስታ ፣ በጽድና ፣ በምሳር ገንፎ ትላልቅ ዛፎች የተሸፈነና ዙሪያው በዳገታማ ኮረብታ የታጠረ በመሆኑ የአየሩ እንቅስቃሴ ጸጥ ያለ ነው፡፡ በሌለ በኩል ገላጣና ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉት የመንደር አካባቢ ውቲ ፣ ዘንቦና መስጫ አልፎ አልፎ ነፋሣማና ቅዝቃሴአቸው የመለዋወጥ ባህሪ የሚታይባቸው ናቸው፡፡

የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደንና አካባቢው በሁለት እርጥብ ወቅቶች /Bimodal Rain fall/ የተከፈለ ነዉ፡፡ከሰኔ እስከ መስከረም ዋናውና የመኸር እርጥብ ወቅት ሲሆን ሌላው ከታሳስ እስከ የካቲት ያለው የበልግ ዝናብ ወቅት ነው፡፡ በዚህም የዝናብ ወቅት መነሻና መቆሚያ መራዘም በመኖሩ በርካታዎቹ ወራት ርጥበታማ አዘል ናቸው፡፡ ይህ የአየር ንብረት አካባቢው በአመት ለበርካታ ወራት ዝናብ እንዳያጣ ከማድረጉም በላይ ከፍተኛ የደን ሽፋንና ትላልቅ ዛፎች እንዲኖሩ አስተዋጾ የሚያደርግ ነው፡፡ አማካይ የዝናብ መጠን፤የሙቀትና እርጥበት ለማወቅ በአካባቢው የአየር መረጃ ጣቢያባለመኖሩ መያዝ አልተቻለም፡፡ ሆኖም ባለዉ የዝናብ ስርጭትና ዕርጥበታማ ወራት መብዛትከተለመደዉ የድራይ ሞንታኔ የደን ሽፋና ቁመት መጨመር ዝርዝር ጥናት ቢካሄድ የአርጥብመንታኔ ደን ሽፋን እንደሚሆን ብዙ አመላካች ሁኔታወች አሉ፡፡

Page 13: Wof Washa Field Study Final Draft

8.4 የመሬት አቀማመጥ

የወፍ ዋሻ ደን የመሬት አቀማመጥ ደኑ በቀላሉ ተመንጥሮ እንዳይጠፋ ይከላከላል ማለት ይቻላል፡፡ ጆኦግራፊያዊ አቀማመጥ ሲኖረው አካባቢው በጣም ወጣ ገባ ሲሆን 55% ዳገታማ 35% ወጣ ገባ እና 5% ሜዳማና 5% አምባ ነው (SUNARMA,2002) የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን በባሶና ወራና ወረዳ በኩል ከደበሌ እስከ ባሶ ደንጎራ ምዕራባዊዩ ክልል ከፍተኛውን አካባቢ የያዘና ሜዳማ ሲሆን ወደ ወፍ ዋሻ ዋናው ደን የሚዋሰነው በገደላማና ማራኪ የዕፅዋት ስብጥር ባለበት ገደላገደል ነው፡፡ ሆኖም ደኑን ቁልቁል ለማየትና ማራኪውን ገጽታ ለመቃኘት የሚያመቹ የገደል አፋፍ መመልከቻ ከፍታ ቦታዎች ሲኖሩ አልፎ አልፎ ወደ ዋናው ደን

ፎቶ 5. የወፍ ወሻ ደን የመሬት አቀማመጥ ከተለያየ አቅጣጫ

በእግር መግባት የሚያስችሉ መንገዶች ቁንዲ ፣ ጐሽ ሜዳ ፣ ጥቁርት ባዶ ፣ ዥኖበር የሚባሉ የመግቢያ በሮች አሉ፡፡

የወፍ ዋሻ የመሬት አቀማመጥ ተፋሰሱ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ከፍታው እየቀነሰ የሚመጣ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ጅረቶች ከደቡባዊና ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ እንዲሁም ከምዕራባዊዩ ገደላገደል በመነሳት ከዋናዉ ደን ወደ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በመጓዝ በመጨረሻ በደኑ መሃል ወደ አፋር ክልል ከሚጓዘው አዋዲ ወንዝ ይቀላቀላሉ፡፡ ስለዚህ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን በምዕራብ በኩል በገደላገደልና በምስራቅ ደግሞ አልፎ አልፎ ከሚታዩት ኮረብታዎችና ዳገታማ አካባቢዎች መሃሉ ረባዳማ በርካታ የተከፋፈሉ ሸለቆዎች ያሉበት ነው፡፡ ይህ ሸለቋማ አካባቢ በትላልቅ የድድ ፣ የምሳር ገንፎ ፣ ወሣራ ፣ወይል፣ ቀጨሞና ዝግባ ዛፎች የተሸፈነና በተፈጥሮ ገላጣ የሆነ ሜዳ የሌለበት ነው፡፡

በአጠቃላይ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ገንዳ መሰል በሸለቆዎች የተከፋፈለና በምዕራብ ገደላማ በምስራክቅ በኮረብታዎች በደቡብ ድልድይ በመሠለ ዳገታማ የደን ሽፋን ያለመ ሲሆን ሰሜናዊዩ ክፍል ደግሞ ዝቅተኛ በመንደርና በእርሻ ቦታዎች የተከበበ ነው፡፡ ሆኖም ደኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ ከመስጫ ቀበሌ እስከ ወፍ ዋሻ ጽህፈት ቤት መሃል ያለው አሁን ዋናው የደኑ አካል ሆኖ ገንዳ በመሠለ ቅርጽ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ከቀንዲ ዳገት ወደ ደቡብ የገደላማውን ግርግርጌ ተከትሎ እስከ አንኮበር እንደሚደርስና በስሜን ደግሞ ባሶ ደንጎራን ተከትሎ ከደብረሲኖ ከተማ አናት ድረስ በስፋት እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

Page 14: Wof Washa Field Study Final Draft

9. የጥናቱዉጤቶችና ትንተና

9.1 የደንጥበቃ ስልትናታሪክ

የወፍ ዋሻ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን አጠባበቅ ትሩፋት በኢትዮተያ ታሪክ በደንና ዱር እንሰሳት ጥበቃ ፋና ወጊ የሆኑት አፄ ዘርዓያቆብ ወደ 15ኛው ክፍለ ዘመን ይወስደናል፡፡ በኢትዮጵያ ነገስታት ታሪክ እንደዛሬው የደን መመናመን በአለም አቀፍና በሃገር ደረጃ ያመጣው ጉዳት ሳይታወቅ እንዲሁም ደግሞ አገሪቱ ከ4ዐ% በላይ በደን በተሸፈነችበት፤ጥቅሙም በወቅቱ እምብዛም ጐልቶ በማይታዎቅበትና ዘመናዊ ትምህርት በማይሰጥበት ወቅት ነዉ፡፡ ለመናገሻ ሱባ ፣ ለወፍ ዋሻ ፣ ለደንቆሮ ጫካና ለሰሜን ተራራዎች የሰጡት የጥበቃ ትኩረት በአገር ብቻ ሳይሆን በአፍሪቃም የደን ተቆርቋሪ እንደሆኑና ዛሬ ለሚደረገዉ የጥበቃ ሂደት መሰረት ጥለዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት የወፍዋሻ ደን ከአፄ ዘርዓያቆብ ጀምሮ ሲጠበቅና በኋላም በ18ኛው ክፍል ዘመን መሪ ደጃዝማች አምሃ እየሱስ /1744-1775/ የአንኮበርን ለሸዋ መናገሻነት በመመስረትና ለደኑ ጥበቃ በሰጡት ትኩረት በስፋት የደኑን ማዕከላዊ ክፍል ሸፍኖ የሚገኘው የአበሻ ጽድ የአምሃ እየሱስ ጽድ በመባል እስካሁንም እሳቸው እንደተከሉት ተደርጐ ይነገራል፡፡ የደኑ ጥበቃ የንጉስ ደን በመባል እየተጠበቀ ከቆየ በኋላ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት የመንግስት ደን የሚል ስያሜ አንደተሰጠውና ከፍተኛ ጥበቃ እንደተደረገለት ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩተ ጊዜዉን በትክክል ባያዉቁትም ቀደም ሲል በወፍ ዋሻ ዉስጥ ያሉ አንዳነድ ደልዳላ አካባቢወች ይታረሱ አንደነበርና መንደርም እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ሆኖም የደኑን ጥቅም የተረዱት ነገስታት በደን ሃብትነቱ እንዲቆይ ጠንካራ የጥበቃ ሰረሰተኞችንና ቁሳቁስ በማሟላት አንዲቆይ አድርገዋል፡፡

በአጼ ሚኒሊክ ዘመነመንግስት ጀምሮ የወፍ ዋሻ የንጉስ ደን ከመባል ወደ መንግስት ደን ሲሸጋገር ለጥበቃ ዘበኞ አበል/ደመወዝ መክፈል የግድ ይላል፡፡ ለዚህም በጥበቃ ለተሠማሩት ዘበኞች በሪም (በደኑ አቅራቢያ ካሉ የእርሻ መሬት ተለይቶ ሕዝብ እንዲያርስላቸውና በምርቱ) እንዲተዳደሩ ተፈቀደ፡፡

በጣርማ በር ወረዳ በወረዳ የፍ ዋሻ ቀበሌ የሚገኘዉና በ1850ቹ የተቐቐመዉ የወፍ ዋሻና ሙገሬዛላ ደን ጽ/ቤት በተገኘው መረጃ መሰረት አቶ ቸርነት ወልደ አማኑኤል በ1890 ዓ.ም የተወለዱትናአስከ 1954 ዓ.ም ድረስ በሪም ይጠብቁ እንደነበር የቐሚ ቅጥር ማስራጃቸዉ ይገልፃል፡፤ አሁንምየልጅ ልጃቸዉ በቐሚነት ተቀጥሮ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

በአጾፄ ሐይለስላሴ ዘመነ መንግስት በ1950ዎቹ መጀሪያ ላይ ሌላው ለጥብቅ የመንግስት ደኑ የተሰጠው ትኩረት ደግሞ የራሱ ጽ/ቤት ኖሮት ሠራተኞቹ ከመሬት ምርት /በሪም/ ቀርቶ በደመወዝ እንዲተዳደሩ በቋሚነት መቅጠርና የወፍ ዋሻና ሙጌራ ዛላ የደን ጥበቃ ጽ/ቤት መከፈት ነበር፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በ1950ቹ ዓ.ም ዘጠኝ ቋሚ ዘበኞች እንዲቀጠሩ ሲደረግ መጀመሪያ በመሬት አበል (ሪም) ይከፈላቸዉ የነበሩትን ጭምር ያካተተ እንደነበር በጽ/ቤት የሚገኘው ማደራቸው ያስረዳል፡፡ በዚህም ወቅት የዘመናዊ ጥበቃ ፋና ወጊ ቐሚ የጥበቃ ሰራተኞች ሁነው የበ1954 ተቀጠሩት በፎቶግረፉ ላይ የሚታዩት ከግር ወደቀኝ፡- አቶ በጋሻው፣ አቶ በየነ ወልደጌዎርጊስ፣ አቶ ቸርነት ወልደአማኑኤል ፤አቶ ኃይለመስቀል አፍሩ፤አቶ አደገ ገብሬ፤አቶ ሀብተወልድ ተፈራ፤አቶ ጌታቸው ቤተማርያም፤ስማቸው ያልታወቀና አቶ ሳህለ ዘለቀ ነበሩ፡፡

Page 15: Wof Washa Field Study Final Draft

የቋሚ ዘበኞች ቅጥር ከተካሄደ በኋላ የተካሄደው የጽ/ቤት ግንባታና ስራ ማስጀመር ነበር፡፡ ይንንም ተግባራዊ ለማድረግ በ1956 ዓ.ም የጽ/ቤት ስራ መጀመሩን በጽ/ቤቱ የሚገኘው የወጭና ገቢየደብዳቤዎች መዝገብ ያስረዳል፡፡ ጽ/ቤቱ በዘመናዊ የግንባታ ሕንፃ እንዲሠራ ከአዲስ አበባው የእርሻ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ተሠጥቶ በ1958 ዓ.ም የግንባታ ውል ተይዞ ጽ/ቤቱ በጣርማበር ወረዳ በወፍ ዋሻ ቀበሌ ከወፍዋሻ ደን ሰሜናዊ ድንበር ላይ እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደርሶ በ1959 ዓ.ም ተሠራ፡፡ የወፍ ዋሻ ደን ጽ/ቤት ያስተዳድር የነበረው የወፍ ዋሻን ሰፊ ደንና ከደብረብርሃንና አዲስ አበባ መሃል የሚገኘውን የሙገሬ ዛላን ደን ጭምር ስለነበር ጽ/ቤት የወፍ ዋሻ ሙጌራ ዛላ ደን ጽ/ቤት ይባል ነበር፡፡

ፎቶ 6. የመጀመሪያወቹ ቋሚ የጥበቃ ሰራተኞች

የወፍ ዋሻ ደን በውስን የሰው ኃይል እየተጠበቀ የነበረ ቢሆንም የጥበቃ ስልቱ ጠበቅ ያሉ የማስተማርና የቅጣት እርምጃዎችን ያካተተ ስለነበር ከአንኮበር እስከ ጣርማበር ድረስ በሚገባ ተጠብቆ እንደነበር አሁን ያሉት የጥበቃ ሠራተኞችም ሆኑ ነዋሪዎች በዋቢነት የሚጠቅሱት ነው፡፡ በሌላ በኩል በወቅቱ የነበረው ስልት አንድ የጥበቃ ሠራተኛ በተመደበበት አካባቢ በሚገባ ባይጠብቅና ደኑና የዱር እንስሳቱ ላይ ጉዳት ቢደርስ በፍጥነት ወደ ሕግ የሚቀርብበትና ጀግንነቱንና ሃላፊነቱን እነዳልተወጣና በደካማነት ይፈረጅ ስለነበር የጽ/ቤቱ ኃላፊም ሆኑ የጥበቃ ሠራተኞች ነጥተው ይጠብቁ እንደነበር በማህደራቸው የተገኙ የጽሁፍ ማስረጃዎችና የደብዳቤ ልውውጦች ያስረዳሉ፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብ በሕግ የሚደርስበትን ቅጣት በመገንዘብና ጥብቅ ደን መሆኑን በማወቅ በየትኛውም ጊዜ መሬቱን ለሌላ ስራ እንዲውል የጠየቀበት ጊዜ የለምባይኖርም ነገር ግን የጥበቃ ስልቱ በላላባቸው ስርዓቶች (በደርግና በአሁኑ ስርአቶች) ደኑን ለተለያየ አገልግሎት በመጠቀምና የግጦሽ ቦታ በማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡ የሚከለከሉተ የዉም አይን አይቶ እግር ካጋጠመ የጣዉላ እንጨት ብቻ ይከለከላል፡፡

ፎቶ.7 በ1959 ዓ.ም የተሰራዉ የወፍ ዋሻና ሙገሬ ዛላ የደን ጥበቃ ጽ/ቤትና አሁን በጥበቃ ላይ ያሉ ሰራተኞችና አጥኝዎች፡

በደርግ ዘመን ትኩረቱ ወደ ሰው ሰራሽ ደን በመሆኑ ብርካታ ደኖች ተተክለዉ በስፋት የሚታዩ ሲሆን በጽ/ቤቱ አጠገብ አንድ የችግኝ ጣቢያ በማቋቋም ችግኝ አፍልቶ ከመስጠት ያለፈ ስራ ባለመሠራቱ የተፈጥሮ ደኑን በስፋት የመጠቀም ባህል የተጀመረው ያኔ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም በደኑ ዉስጥ የነበለዉ የጎሽሜዳ ችግኝ ጣቢያ ድሮዉንም በደኑ መሃል ስለሆነ አመች ነዉ ባይባልም

Page 16: Wof Washa Field Study Final Draft

እየተሰራበት አይደለም፡፡ አሁን ያሉት ጊዜያዊም ሆኑ ቋሚ የጥበቃ ሠራተኞች እንደነግሩን የሙገሬ ዛላ ደን እንደጠፋና የወፍ ዋሻ ደንም እጅጉን የተመናመነ እንደሆነ በጥናቱም ወቅት ተረጋግጧል፡፡

አብዛኛዎቹ ቋሚ ዘበኞች ወደ ችግኝ ጣቢያ ስራ በስፋት ሲሰማሩ ደኑን እንዲጠበቅ የተደረጉት የኩንትራት ዘበኞችና ቋሚ ዘበኛ በተቆጣጣሪነት በመመደብ ነው፡፡ ይህ አሰራር እሁንም የቀጠለና እየተሠራበት ያለ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጠባቂዎች ነገር ግን የጣውላ እንጨት በገሃድ ሲወጣ ከመቆጣጠር ያለፋ ጥበቃ እየተደረገለት አይደለም፡፡ በዚህም ለበርካታ አመታት ከደን ጨፍጫፋዎች የተሰበሰቡ የደን መጨፍጨፊያ መሳሪያዎች ጣውላ ውሳኔ ሳያገኙ ተከማችተው ይገኛሉ፡፡ የደኑ ዳር ድንበር መጥፋትና ወደ እርሻና የግጦሽ መሬት መለወጥ ከጥበቃ በመላላቱ ለበርካታ አመታት ሕገወጥ ሰዎች የያዟቸው መሬቶች ከጊዜ ብዛት በባለቤትነት የሚሟገቱባቸው ናቸው፡፡

ባሁኑ ወቅት የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ጽ/ቤት የማይሰራ ሲሆን ደኑ የሚተዳደረዉ በሶስቱ ወረዳዎቸየየድርሻቸዉን ለመጠበቅ በጠቀጠሩ ቋሚና ኮንትራት ዘበኞች ነዉ፡፡ በዚህም በባሶና ወራና ወረዳ 36፣በአንኮበር 41 እና በታርማ በር ወረዳ 32 በድምሩ 109 የጥበቃ ሰራተኛዎች ተመድበው በመጠበቅላይ ይገኛሉ፡፡ የሚከፈላቸዉም በክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በሚላክ በጀት ነዉ፡፡ ወረዳዎቹካላቸዉ የደን ቆዳ ስፋትና ጠባቂዎች ብዛት አጣጥመዉ ለኮንትራት ዘበኞች ይከፍላሉ የስራእንቅስቃሴአቸዉን ይቆጣጠራሉ ሆኖም ጥበቃዉ የላላና ችንደሰዎቹ ጥንካሬ የሚወሰን ክፍያዉምአናሳ እነደሆነ ዘበኞችም ሆኑ ዬወረደዎቹ ሃላፊዎች ይናገራሉ፡፡

9.2 የወፍ ዋሻ ዝርዝር የተፈጥሮሀብትናመስህቦች

9.2.1 የስነምህዳርውክልና

የወፍ ዋሻ ደን በተለያዩ ምክንያቶች እየተመናመነ ቢመጣም በጣም ማራኪ የሆኑ የስነ ምህዳር አምባ ነው፡፡ በአቀማመጡ የደጋማውን ከፍተኛ አካባቢ ከደበሌ እስከ ባሶ ደንጎራ የአፍሮ አልፓይን ገጽታና እጽዋት እንደ ጅብራ አስታ፣ ጓሣ ፣ የዋሊያ ሾህ (ጋርዳ) የሚበቅሉበት በዋነኛነት ሜዳማና ከዋናው ደን ቀጥ ባሉ ገደል የተከፈለ ነው፡፡ አልፎ አልፎ በሚገኙት ወደ ዋና ደን የመግቢያ ገደሎች ወደ ደኑ ወረድ ሲባል የገደሉን አፋፍና ግርጌ ተጠንተው የበቀሉት ከቁጥቋጦ እስከ ትልቅ ዛፍ በመሆን የሚሸፍነው የአስታ ዛፍ ነው፡፡ ቁልቁል በማቋረጥ የአስታው ደን እያነሰ የአበሻ ጽድ እየተተካና በጣም ረዣዥም፤ ያረጁና ትላልቅ 15ዐ ሴ.ሜትር ዲ.ቢ.ኤች በላይ ባላቸው ግዙፍ ዛፎች የተሸፈነ ነዉ፡፡

ፎቶ 8. የሳብ አፍሮ አልፓይን ስርአተ ምህዳር ወካይ ቦታዎች የዠኖ በር ጓሳና የደበሌ ጋርዳ (ዋሊያ ሾህ)

Page 17: Wof Washa Field Study Final Draft

የአበሻ ጽድ ዋናውን የደን ሽፋንና ከጅረቶች መነሻ ጀምሮ እስከ ዋዲወንዝ ድረስ አብዛኛውን ቦታ የሸፈነ ቢሆንም ቀጨሞ ፣ ወይራ ፣ ምሣር ገንፎ ፣ ወይል ፣አምጃ ኮሶ ፣ አዛምር ፣እምብስ ፣ ቀለዋና ወይናግፍት የሚባሉ እጽዋቶች አጅበውት ይገኛሉ፡፡ በአጣቃላይ የወፍ ዋሻ ደን በደረቅ ሞንታኔ ስነምህዳር ቢዎከልም ማእከላዊ ክፍሉ ግን የእርጥብ ሞንታኔ ክፍል የያዘ ነው፡፡ ስለዚህ የዋፍ ዋሻ ከላይ የተገለጸውን የመሬት አቀማመጥና የእጽዋት ስብጥር ከከፍተኛው የባህር ወለል በላይ አስከ 37ዐዐ ሜትር ጅባራ፤ አስታና ጓሳ፣ ከ25ዐዐ-3000 የአበሻ ጽድና የምሳር ገንፍ ዛፎች እንዲሁም 2500 ሜትር በታች አብዛኛወቹ ከደኑ ውጭ ይሁኑ እንጅ በርካታ የደን ስብጥር ያለበት የምንታኔ የደን ሽፋን ያለው ነው፡፡

ፎቶ 9. የድራይ ሞንታኔ ደን በረቱ (ጎሽ ሜዳ) ከመስጫና ዉቲ መሃል

ስለዚህ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን የሳብአፍሮ አልፓይንና የደረቅ ምንታኔ ስነ-ምህዳር ውክልና ያለውና በአረጁና በትላልቅ አበሻ ጽድ ፣ የዝግባ ፣ የምሳር ገንፎና ወይራ ዛፎች የሚገኙበት ከፍተኛ ጥበቃ የሚያስፈልገውን የስነ ምህዳር ቀጠና ከማራኪ የመሬት አቀማመጥና አመች የጐብኝዎች መነሃሪያ ሊሆን የሚችል ነው፡፡

ፎቶ 10. የእርጥብ ሞንታኔ ስርአተ ምህዳር የሚያሟሉ በረዣዥም የዝግባ፡የምሳር ገንፎና ያበሻ ፅድ ዛፎችየተሸፈ፡፡

9.2.2 የእጽዋት ሽፋንና አይነት

የወፍ ዋሻ ጥበቅ የተፈጥሮ ደን በብዛኛው በአረጁና ግዙፍ በሆኑ በአበሻ ጽድ ፣ በዝግባና በወይራ ዛፎች የተሸፈነ ቢሆንም ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው የአበሻ ጽድ ነው፡፡ ደኑ ከተለየየ አቅጣጫው ሲመለከቱት ጠቅጥቅ ያለ ይምሰል እንጂ ውስጡ በእጅኑ የተጐዳና ተተኪ ዛፎች የሌሉበት ነው፡፡ ትላልቅ የዝግባ ዛፎች የሚገኙት በማር አርቦ ፣ በውቲ ፣ በአዋዲ ወንዝና ጣርማበር ደንበር አካባቢ በመሆኑ ጉዳቱ እጅግ የበዛና በተቆራረጡ አካባቢዎች ቢሆንም የዝግባ ዛፍ በቀላሉ ተተኪ ሊኖረው የሚችልና አልፎ አልፎም ቢሆን ችግኞች ይታያሉ፡፡ የአበሻ ጽድ ግን ምንም አይነት ችግኝም ሆነ አዲስ የበቀሉ ዛፎች አይታዩም፡፡ ይህም ደኑ በውስጡ ሊይዝ የሚገባውን የደን ስብጥር ለመጠበቅ ያልያዘና ተመሣሣይ ችግኞችን መትከል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል”፡፡ የደኑ ዛፎች ዝርዝር በዕዝል አንድ የተመለከተ ቢሆንም ስነ-ምዳሩን ተከትሎ ከላይ ወደታች ጅባራ ፣ ጓሣ፣ ጋርዳ፤ አስታ ፣

Page 18: Wof Washa Field Study Final Draft

የአበሻ ጽድ ፣ ኮሶ ፣ አምጃ፤ ምሳርር ገንፎ ፣ ቀጨሞ፣ ዝግባ፡ ወይራ፤እምብስ፡ ብሳና፤ ዋነዛ፤ አጣጥ፡ የተፈጥሮ ስብጥሩን በመጠበቅ የሚበቅሉ በርካታ የቁጥቋጦና የሳር ዝርያዎች ዋና ዋና እጽዋቶች ናቸው፡፡ በተለይ በአገራችን ቁጥራቸው እየተመናመኑና ጥበቃ የሚያስፈልጋቸዉ የአበሻ ጽድ፤ ዝግባ፡ ኮሾ፡ ወይራና ምሳር ገንፎ ሊጠበቁበት የሚችል ዋነኛ ተፈጥሮአዊ የሆነ ቦታቸዉናበሚፈለገው ቁመትና መጠን ሊጠበቁበት የሚችል የእነዚህ ቅርስ አንባ ነዉ፡፡

ጋርዳ ጓሳ ምሳር ገንፎ

ዝግባ ኮሶ

የአበሻ ጽድ

ፎቶ 11 ዋና ዋና የእጽዋት ዝርያዎች

የደኑ ሽፋንም የስርዓተ ምህዳሩን የዕጽዋት ስብጥር በመያዝ በሳብ አፍሮ አልፓይን / ጅብራ፣ ጓሳ፤አስታ ፣ ዋሊያ ሾና / ጋርዳ/ በሞንታኒ ደን የላይኛው ክፍል / አስታ፤አምጃ ኮሶና አበሻ ጽድ/ በሞንታኔ የደን በታችኛው ክፍል / ምሣር ገንፎ ቀጨሞ፣ ዝግባና ወይራ በመሆን የደን ሽፋን ስብጥሩ ተይዞ ይገኛል፡፡ ሆኖም ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉት የአበሻ ጽድ፣ ኮሶና ዝግባ አሁን የሚታት በጣም ያረጁና እድሜ ጠገብ ሲሆኑ በተለይም ከ10-50 ሴ.ሜትር ዲቢኤች ያላቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸዉ ነው፡፡

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን በእጽዋት ስብጥርና ቁመት በጣም ከፍተኛውን ደረጃ የያዘና በአገሪቱ ዋነኛ የደን ሽፋን መገለጫ ነው የሚባለውን የሃረና ደን እንዲሁም እረጃጅምና ግዙፍ ዛፎች የሚገኙበትን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሚወክል ነው፡፡ በተለይም በአማራ ክልል በተመሣሣይ ስርዓተ ምዓዳር እነዚህ የእጽዋት አይነቶችና የደን ስብጥር በዚህ ሁኔታ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡

Page 19: Wof Washa Field Study Final Draft

በSUNARM /ሱናርማ/ የሚባለዉ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የልማት ማህበር 2ዐዐ5 በወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ባደረገው ጥናት የወፍ ዋሻ ደን ኮንፈረስ በሚባሉት የዛፍ ዝርያዎች በብዛት የተሸፈነና ከተመዘገቡት 26 የዛፍ አይነቶች 30.3% የኮንፈረስ ዛፎች ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ 18.60% የአበሻ ጽድ 11.43% ደግሞ የዝግባ ዛፎች ናቸው፡፡ በመቀጠልም የምሳር ገንፎ ዛፎ 13.14% ይሸፍናል፡፡ ይህም የዝግባ ዛፎች በተሸለ የደን ስርጭትም ሆነ ብዛት አለው፡፡ ሆኖም የኮንፈረስ ዛፎች

በሽፋንም ሆነ በስብጥር ከፍተኛውን ቦታ ይዘው ይገኛሉ፡፡

የSUNARM ሱናርማ 2ዐዐ5

እንደሚያመለክተው የወፍ ዋሻ የደን ሽፋን ስብጥር በአራት ምድብ በተከፈሉ የዛፍ አይነቶች ተመደባል፡፡ እነርሱም፡-

ፎቶ 12. የጭላዳ ዝንጀሮ መንጋ ጎሸ ሜዳ (ቀይት)

1. የኮንፈርስ ዛፎች /የአበሻ ጽድና ዝግባ/2. ሜርቻንቴብል ሃርድ ውድ / ብሳና ሰንቦ፣ ኮሶ፣ወይራ፣ ጥቁር እንጨት ፣የዝንጀሮ ወንበር/3. ፓቴንሻሊ ዩዜብል ሐርድ ውድ /የቁልቀል፣ እምብስ፣ ምሳር ገንፎ፣ ውልከፋ/4. ሌሎችየዛፍ ዝርያዎች /አስኳር ፣ አስታ፣ የፊግ ዛፎች / አምጃ/ ሲሆኑ የደኑ ሽፋን ከዛፎቹ ውፍረት ጋር ሲነፃፀር በጣም በዝቅተኛ የውፍረት መጠን ያላቸው ዛፎች በመብዛታቸው የደኑ መጐዳት የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም የሆነው እንደጥናቱ ማጠቃለያ እየመረጡ መመንጠር፤ ለግንባታና ለእንጨት ኢንዱስትሪ መጠቀም ነው፡፡ በዚህም 4ዐ እስከ 1ዐዐ ሴንቲ ሜትር ዲያሜትር ውፍረት ያላቸውን ዛፎች ለመረጣ ምንጠራው ሰለባዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአረጁ ዛፎች ብቻ መቅረትና በሕይወት ያሉት በመዉደቅ ወይም በመድረቅ በመጥፋት ላይ እንዲሆኑ ጥናቱ ያስረዳል፡፡

በዚህም ጥናት ተረጋገጠው ከዚህ የተለየ አይደለም በማገገም አቅም አስታ ፣ ዝግባና የዋሊያ ሾህ/ጋርዳ/ የተሻሉ ቢሆንም የሚደርስባቸው ጫና ግን በተፈጥሮ ካላቸው የማገገም አቅም በላይ ነው፡፡ የአበሻ ጽድ ፣ ኮሶ፤ ወይራና ምሳር ገንፎ ደግሞ በተፈጥሮም ቢሆን ምቹ ሁኔታ ካልተፈጠረ ለማገገም የሚቸገሩ በመሆናቸው አሁን ያሉት በትላልቅና ያረጁ ዛፎች ናቸዉ፡፡ ስለዚህ እነዚህ በአይነትም ሆነ በብዛት እንዲሁም ደግሞ በቁመት ሽፋን በክልሉ ካሉ ደኖች ለየት ባለ ሁኔታ ያሉትን ዛፎች ትኩረት ሰጥቶ መጠበቅ የትውልድ ማስተላለፍና ለዘላቂ የስነ-ምህዳር ለመጠበቅም ሆነ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ጠቀሜታ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡

9.2.3 ዱር እንሰሳት

በወፍ ዋሻ ደን የሚኖሩ የዱር እንስሳትን ለመለየት የደኑ ሽፋንና የተፈጥሮ ገጽታው ወሳኝ ነው፡፡ በደኑ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ልማትና ጥበቃ ለዱር እንስሳትም በተመሳሳይ ሆኔታ ይገለፃል፡፡ ሆኖም ደኑ ያፈራቸዉን ያላግባብ መጠቀም መዉሥጡ ያሉትን ለጉዳት በመዳረግ ደኑ ዉጤታማ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ቀደም ሲል የስነ-ምህዳሩን ቀጠናና የደኑን ሽፋን በመከተል ይኖሩ የነበሩና

Page 20: Wof Washa Field Study Final Draft

አሁንም ያሉ የዱር እንስሳት በርካታ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ በአሁኑ ሰዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚታወቁት ተራ ቀበሮ፣ ቀይ ቀበሮ ፣ የደልጋ አንበሳ፣ ጦጣ ጥርኝ ጉሬዛ ፣ ነጠብጣም ጅም ፣ ባለመስመር ጅብ ፣ ጃርት ፣ የስታርክ ጥንቸል ፣ ሰሳ ፣ ጭላዳ ዝንጅሮ ፣ ሽክኮ፣ ተራና የሚኒሊክ ድኩላ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ቀይ ቀበሮ በአሁኑ ሰዓት ከአካባቢው ጠፍቷል፡፡ ተራ ቀበሮም ቢሆን በቀላሉ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በጓሣውና የገደሉን አፋፍ መጠጊያ አድርጐ ከደበሌ እስከ ጉዶ በረት ድረስ ጭላዳ ዝንጀሮ ፣ ሽክክና ፣ በርካታ የአእዋፍ ዝርያዎች /ጋጋኖ ፣ ቄሱ ፣ ቁራና ገዴ/ በብዛት ይገኛሉ፡፡

ፎቶ 12. የጭላዳ ዝንጀሮ መንጋ ጎሸ ሜዳ (ቀይት)

በርካታ የአእዋፍ ዝርያዎች በተለይም ከኤርትራ ጋር የምንጋሪቸውና በአገራችን ብቻ የሚገኙ ዋትልድ አይቤስ፤ ኋይት፤ ኮላር ፒጐን ፣ ከላከ ውይንግድ ላቨበርድ፣ ቲክ ቢድል ሪቨን ፣ ኋይት ቢልድ ስታርሊንግ ፣ብሉ ወይንግድ ጉዝ እና ክሊፍ ቻት ሲሆኑ በአገራችን ብቻ የሚገኙ ደግሞ አንኮበር ሶሪን እና አብሲኒያን ሎንግ ክላው ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ሽኮኮና ጉሬዛ በብዛት የሚገኙና ዋነኛ መኖሪያቸው እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ ተራ ድኩላም ሆነ የሚኒሊክ ድኩላ በተለይም ወንዱ በከፍተኛ ደረጃ ስለሚታደን እንደልብ ባይታይም በተወሰኑ አካባቢዎች ወፍ ዋሻ ቀበሌ በዥኖ በር ግርጌ በብዛት የሴት/ጐማ/ ድኩላወች ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ በዱር እንስሳት በኩል የበርካታ አእዋፍ ፣ የጉሬዛና ሽክኮ አካባቢ በመሆኑና በአገራችን ብቻ የሚገኙት የጭላዳ ዝንጀሮ ፣ የሚኒሊክ ድኩላና ስታርክ ጥንቸል መኖሪያ በመሆኑ ለደኑ ጥበቃና አደን ቁጥጥር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ጥበቃ እንዲደረግ ከወዲሁ የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ የደኑም ሆነ የእንስሳቱ መጠበቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቱሪዝም ጠቀሜታውን በማጉላት በቀላሉ ገቢ ልናገኝበት የሚያስችለን ነው፡፡

9.2.4 የመሬት ለምነትና የዉሃ ሃብት

የወፍ ዋሻን ጥብቅ ደን በአፋር አይነትና ለምነት ተንትኖ ለማስቀመጥ የተለየ ሳይንሣዊ የመረጃ አሰባሰብና የትንተና ዘዴዎችን የሚጠይቅ በመሆኑ በዚህ ጥናት ተካቷል ለማለት የስቸግራል፡፡

ፎቶ 13. በሳሳዉ የደኑ አካል ለክለት የተጋለጠ አፈርና ደን አልባዉ የዉቲ ተራራ ምስራቃዊ ጎን

ነገር ግን ከደን ሽፋን አኳያና በአካባቢው ከሚደረገው የአፈርና የውሃ ጥበቃ አንፃር ያለውን የአፈር ሁኔታ መግለጹ አስፈላጊ ነው፡፡ በአፍሮ አልፓይን ስርዓተ ምህዳር ከመሬቱ ከፍተኛ ደጋማ በሆኑ አካባቢዎች ከመኖሩና የእርሻና መንደር እንዲሁም የግጦሽ መሬቶች በብዛት ጥቅም ላይ በመሆናቸው የሚበቅሉት ጥቂት እጽዋትም ተመናምነዋል፡፡ የእርሻ መሬቶችም በተደጋጋሚ በመታረሳቸው ለምነታቸው ስለተሟጠጠ ጓይ (አፈር ማቃጠል)፤የተፈጥሮ ማዳበሪያ ፍግና ኮምፓስት መጠቀምም

Page 21: Wof Washa Field Study Final Draft

ሆነ የመጠቀም ፍላጐቱ ሰፊ ነው፡፡ ለዚህም የተጠራቀመዉን ፍግ ለመበተን በደቦ ይሰራሉ ድግስም ይዘጋጃል፡፡

ስለዚህ እነዚህ አካባቢዎች ከደበሌ እስከ ባሶ ደንጐራ ያሉና በብዛት ገብስ በማብቀል የሚታወቁ ሲሆን ባቄላና ስንዴም ይዘራል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች መሃል ወንዝ ፣ መስጫና ዘንቦ እስከ ጣርማ በር ወረዳ ባሉ በታችኛው የወፍ ዋሻ አካል የሚገኙትም ቢሆን ያን ያህል በዘመናዊ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ታግዘዋል ብሎ መናገር ባያስችልም በየማሣው የሚታዩት ርከኖች ሕብረተሰቡ በአፈርና ዉሀ ጥበቃ ስራ የተሻለ አመለካከትም ሆነ የአሠራር ብቃት እንዳለው አመለካች ናቸው፡፡ እንዲሁም በአንኮበር ፤በፍቅሬ ግንብና መሃል ወንዝ አካባቢ ያሉት የአስተራረስ የእርከን አሠራርና የተፋሰስ ባሀልና ልማዳዊ ክንውኖች አካባቢው በዚህ ረገድ ቀደም ያለ ስልጣኔ እንዳለው ገላጭ ምስክሮች ናቸው፡፡

ፎቶ 14 የመሬት ለምነትን ለመጠበቅ አፈርን ማቃጠ(ጓይ) እና ፍግን ከደኑ በረት ወደ ማሳ ማጓጓዝ

በወፍ ዋሻ አካባቢ ከሌላ ቦታ መጥቶ ወደ ደኑ የሚገቡ ወንዞች ባይኖርም የላይኛውን ጓሣና ገደላገደል የመሬት አቀማመጥ በመንተራስ በርካታ ምንጨች ይፈልቃሉ፡፡ ኃይል ባይኖራቸው ከየመነሻቸው ተነስተው ትናንሽ ጅረቶችን በመፍጠር በመጨረሻ ትልቁንና ሁሉንም ሰብስቦ ወደሚይዘው አዊዲወንዝ ይወርዳሉ፡፡ አብዛኛወቹ በደኑ ውስጥ ባሉ ሸለቆወች እየሾለኩ የሚሄዱ በመሆናቸው ስያሜያቸው ከሸለቆ ያለፈ አይደለም፡፡ እነሱም አይራሬ፤ ሸለቆ በረት ፣ ጥቁር ወንዝ ፣ ጨመቆት ወንዝ፣ ዥኖ በር ቨለቆ በመባል የሚታወቁና አመቱን በሙሉ ውሃ የማይጠፋባቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቨለቆዎች የሚወርደውን ውኃ ሰባስቦ ወደ አዋሽ የሚወርደው የአዋዲ ወንዝም በበጋ ወቅት ውኃው

በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የመቆራረጥ ባሕሪ ቢታይበትም ለቆላማው ቀበሌዎችና አልፍም ለአፋር ክልል ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥቅም እየሰጠ ቀሪው አዋሽ ወንዝ ይጨምራል፡፡

የደኑ ሸለቆዎች አመቱን በሙሉ ውኃ አለማጣት ሁለት ምክንያቶችን ልንሰጥ እንችላለን አንደኛው የአካባቢው የአየር ንብረት በሁለት የእርጥብ ወቅቶች /ከታህሳስ-የካቲትና ከግንቦት-መስከረም/ የተከፈለ በመሆኑ በአመቱ 9 ወር ያህል ዝናብና የእርጥበት ወራት መኖራቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የወፍ

ፎቶ 15 የወይዘሮ አየለች የተቀናጀ ባህላዊ የተራራ ላይ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ አንኮበር

Page 22: Wof Washa Field Study Final Draft

ዋሻ ደን ደጋማውን ክፍል ተንተርሶ በጣም ትላልቅና ረጃድም ዛፎች የተሸፈነ በመሆኑ በደረቅ ወቅት ሸለቆዎችም ሆኑ የደኑ ውስጥ ለድርቀት የተጋለጠ አለመሆንና ደኖች የአካባቢውን የተፈጥሮ ሚዛን የአየር ንብረት በመጠበቅ ካላቸው አስተዋጾ የተነሳ ነው፡፡ በደኑ ውስጥ የሚኖሩ ሸለቆወች በዙሪያው ያሉ ምንጮች ለነዋሪው ሕዝብ ሆነ ለእንሰሳት በዋነኛነት የውሃ ምንጭ በመሆን በስፋት ያሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ፎቶ 16. ባህላዊ እርከን ፍቅሬ ግንብ

9.2.5 በወፍ ዋሻና በአካባቢዉ የሚገኙ የተፈጥሮና ባህላዊመስህቦች

የሰሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን የብዙ መስህብ ሃብቶች ባለቤት ስትሆን ለዚህ ጥናት ወቅት በወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደንና አጎራባች ወረዳዎች የታዩ የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ መስህቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደንበትክክል የተመዘገበ መረጃ ባይኖርም ቦታውን የአለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች እየጎበኙትመሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህም የመስክ ጥናት ወቅት ገማሳ ገደል /የሚኒልክ መስኮት/ ላይአምስት የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ጭላዳ ዝንጀሮንና የአካባቢውን መሬት አቀማመጥ ሲጎበኙተመልክተናል፡፡ በተጨማሪም በተለይ በርካታ የዱር እንሰሳትና እጽዋት አጥኝወች ጥናት አንዳካሄዱየደኑ የጥበቃ ሰራተኞች ይገልጻሉ፡፡

Page 23: Wof Washa Field Study Final Draft

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን በውስጡ የተለያዩ ታላላቅ አጥቢ የዱር እንስሳትን እንደ የሚኒሊክ ድኩላ፣ጨላዳ ዝንጀሮና ጉሬዛ የመሳሰሉትን አቅፎ የያዘ በመሆኑ በተለይም ጉሬዛን በቅርብ ርቀትና በፈለጉትቁጥር ለመመልከት ትክክለኛ ቦታው እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በዚህም የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደንየጉሬዛ ዋነኛ ቦታዉ መሆኑና ለጎብኝዎች በቀላሉ ሊታ የሚችል መሆኑ ነዉ፡፡

ፎቶ 17 የወፍ ዋሻ ደን ማራኪ የተፈጥሮ ገፅታና ብዝሃ ህይወት በከፊል

የተፈጥሮ ደኑ የታላላቅ አጥቢዎች ብቻ መነሃሪያ ሳይሆን በሃገሪቱ ውስጥ ካሉት 69 የአዕዋፍ ብዝሃማዕከላት፤ መጠበቂያና መመልከቻ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙትን አንኮበር ሴሪን (Ankober Serin) እና አብሲኒያን ሎንግ ክለዉ (Abyssinian Longclaw) ሲሆኑበኢተዮጵያ ብቻ ይገኙ የነበረና አሁን ኤርትራ ጋር የተጋራቻቸው የአዕዋፍ ዝርያዎች ዋትልድአይቢስ (Wattled Ibis)፣ ኋይት ኮላርድ ፒጎን (White-collared Pigeon)፣ ብላክ ዉይንግድ (Black-winged Lovebird)፣ ቲክ ቢልድ ራቨን (Thick-billed Raven)፤ኋይት ቢልድ ስታርሊግ (White-billed Starling)፤ ሩጊት (Rouget's Rail)፤ ብሉ ዊይንግድ ጉዝ (Blue-winged Goose) ና ሩፒሊስ ቻት (Rueppell's Chat ናቸዉ)፡፡ እንዲሁም በብዙ ቦታ የማይገውን የቅልጥም ሰባሪ /Lammergeyer/ መገኛ በመሆኑ፡፡

የዱር እፅዋትን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረቡትን እንደ የሃበሻ ፅድ፣ኮሶና ዝግባ የመሳሰሉትን አቅፎ የያዘ ከመሆኑም ባሻገር እድሜ ጠገብና ከ40 ሜ በላይ ቁመት ያላቸውን ዛፎች መመልከት ከፈለጉ ጉዞወትን ወደ ወፍ ዋሻ ያድርጉ፡፡ የወፍ ዋሻ የብዝሃ ህይወት ሃበት መገኛ ብቻ ሳይሆን ማራኪ ገጽታዎችን መመልከት የሚችሉበት እንደ ዜኖ በር፣ ገማሳ ገደል፣ጥቁሪት ባዶ፣ጎሽ ሜዳ፣ቁንዲና ውቲን የመሳሰሉ መመለከቻ ቦታወችን የያዘ ሲሆን ከከፍታ ቦታዎች በመሆን የደኑን የተለያየ ክፍልና ወደ አፋር በመመልከት የተፈጥሮን ድንቅ ስጦታዎች መመልከት ይቻላል፡፡

Page 24: Wof Washa Field Study Final Draft

በሌላ በኩል በደጋማዉና በማህበረሰቡ የአጠቃቀም ስልት ጥበቃ እየተደረገላቸዉ ማራኪና ዘለቄታ ባለዉ መልኩ የሚጠበቁና ጥቅም ላይ እዋሉ ያሉት የጎሽ ሜዳና የዥኖ በር አካባቢ የማህበረሰብ ጓሳና ጅባራ ማራኪና ቀልብን የሚስቡ ናቸዉ፡፡

ገማሳ ገደልገማሳ ገደል /የሚኒሊክ መስኮት/ አጼ ሚኒሊከ ወደ ሰላ ድንጋይና ጣርማ በር ሲሄዱ በባሶና ወራና ወረዳ በባሶ ደንጎራ ቀበሌ በዎፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን በስተሰሜን ጫፍ የሚገኝ ሲሆን አጼ ሚኒሊክ ከትወልድ ሰፈራቸው አንጎለላ አያቶቻቸው ወደ አሉበት ሰላ ድንጋይ ሲያልፉ እንደሚያርፉበትና ወደ ቆላው የሚመለከቱበት እንደነበር የአካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ አካባቢ አሁንም ቢሆን በቱሪስቶች የሚጎበኝ ሲሆን የጭላዳ ዝንጀሮን ለመመልከት የሚፈልጉ ቦታው ላይ መገኘት ብቻ በቂ

ነው፡፡ የወፍ ዋሻንና ቀላማውን አከባቢ

ለመመልከት በመመልከቻ ቦታነትም ያገለግላል፡፡ ይህን ቦታ የአካባቢ ነዋሪወች በቆብ

መሻጫነት የሚጠቀሙት ሲሆን በዚህ ቦታ ቦታ ላይ ለቱሪስት ማረፊያ ቢሰራበት ሃብቱን በአግባቡ መጠቀም ያስችላል፡፡

ፎቶ 18 በባሶ ደንጎራ ከዋናዉ መንገድ ዳር የሚገኘዉ ገማሳ ገደል (የሚኒልክ መስኮት)

አንኮበር

አንኮበር ከሸዋ ነገስታት ከተማዎች አንዷ ስትሆን በመሪ ደጃዝማች አመሃ እሱስ(እ.ኤ.አ1744 -.1775) የሸዋን መናገሻ ከዶቃቂት ወደ አንኮበር እንዳሸጋገሩት መረጃዎች ይጠቁማሉ 36 ነገስታት እንደነገሱባት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መሪ ደጃዝማች አመሃ እየሱስ የወፍ ዋሻን የተፈጥሮ ደን ይንከባከቡ እንደነበረና የሃበሻ ጽድም በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ የአመሃ እየሱስ ዛፍ ደኑንም እንዲሁ የአመሃ እየሱስ ደን በማለት ይጠሩታል፡፡ የአንኮበር ከተማ አከባቢ መስህቦችን አቅፎ የያዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚኒሊክ ቤተመንግስት የቤተመንግስቱ ፍርስራሽ፣ማድቤት ፍርስራሽ፣የሚኒሊክ ስልክ ቤትና ሰገነት ሊጎበኙ የሚችሉ ሲሆን በንጉስ ሳህለስላሴ የተሰራው የአንኮበር ሚካኤል ቤተክርስቲያንም በዚሁ አካባቢ ይገኛል፡፡ እቴጌ ጣይቱና አጼ ሚንልክ የተጋቡባት የአንኮበር መዳህኒያለም ቤተክርስቲያንም ከዚሁ ስፍራ ነው የሚገኘው፡፡ በአንኮበር ቤተመንግስት አከባቢ ሊጎበኑ ከሚችሉት ሰው ሰራሽ ቅርሶች በተጨማሪ ማራኪ የሆነ የተፈጥ የመሬት ገጽታና ድንቅዬና ብርቅየ የዱር እፅዋት ይገኙበታል፡፡ መንም እንኳን የተገነባበት ቦታ ቅርሱን ለመጠበቅ ምቹ ቦታ ላይ ባይሆንም አከባቢውን ሲጎበኙ ቆይታወትን አንኮበር ቤተመንግስት ሎጂ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ፎቶ 19 የአንኮበር ሎጂ

Page 25: Wof Washa Field Study Final Draft

አንጎለላ

አንጎለላ ከሸዋ ነገስታታ ቀደምት ከተማዎች አንዷ ስትሆን በባሶና ወራና ወረዳ በአንጎለላ ቀበሌ ትገኛለች፡፡ የአንጎለላ አካባቢ የሸዋ ነገስታትን አሻራ አቅፋ የያዘች ስትሆን ንጉስ ሚኒሊክም የተወለዱት በዚሁ አካባቢ ሲሆን ለመታሰቢያቸውም ከተወለዱበት ቦታ ላይ የአንጎላላ ክሊኒክ የተገነባ ሲሆን በዚሁ ግቢም ውስጥ የአጼ ሚኒሊክ እትብት የተቀበረበትም ቦታ ተለይቶ ምልክት ተደርጎበታል ፡፡ የክሊኒክ ግንባታው አንዱ አካል የሆነው የአጼ ሚኒሊክ ሀውልትም በዚሁ ግቢ ውስጥ ይገኛል ፡፡ ሆኖም ግን ይህ የመታሰቢያ ክሊኒክ አገልግሎት መስጠቱን ያቆመ በመሆኑ የሰሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን በጀት መድቦ ስራ ሊያስጀምረው ይገባል፡፡

ፎቶ 20 አንጎለላ የአፄ ሚኒሊክ ትዉልድ ቦታ (እንቁላል ኮሶ)ና መታሰቢያ ክሊኒክ

ከሚኒልክ የትውልድ ሰፈር በቅርብ ርቀት የአንጎላላ ኪዳንምህረት ቤተክርስቲያን ትገኛለች ይህች ቤተክርስቲያን አጼ ሚኒልክ ክርስትና የተነሱባት ስትሆን የአጼሚንልክ የጦር ጀኔራል የነበሩት ፊታውራሪ ገበየሁ አጽም ያረፈው በዚች ቤተክርስቲያን ነው፡፡

የንጉስ ሳህለስላሴ ቤተመንግስት በዚህ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን

የበተመንግስቱ ፍርስራሽ፣ሰገነት፣ንጉሱ

ችሎት የሚሰጡበት ኩምበል ዛፍና ሌሎች ብርቅየና ድንቅዬ የዱር እጽዋትና አዕዋፍ በዚሁ አካባቢ ስለሚገኙ አካባቢውን ቢጎበኙ የሸዋን ነገስታት ታሪክ በአግባቡ ሊረዱ

ይችላሉ፡፡ ፎቶ 21 የንጉስ ሳህለስላሴ የፍርድ መስጫ አደባባይ ሰገነትና ኮነበል ዛፍ

Page 26: Wof Washa Field Study Final Draft

አልዩ አንባአልዩ አንባ ከጎረቤላ (የአንኮበር ወረዳ ዋና ከተማ) ከተማ 14 ኪ.ሜ ላይ በስተ ምስራቅ የምትገኝ ስትሆን በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመረያ የቆላውንና የደጋውን አካባቢ አካባቢ የምታገናኝ የንግድ ማዕከል በመሆን አገልግላለች፡፡ሲራራ ነጋዴዎችም ከቀይ ባህርና ከሃረር እስከ ዘይላ ድረስ ይመጡ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ፎቶ 22. አልዩ አምባ የአበዱል ረሱድ የቀብር ቦታና ባህላዊ ግብይት

የአልዩ አንባ ከተማ በፊት ብቻ ሳይሆን አሁንም ቢሆን በብዝሃ ባሕል የግብይት ማዐከል በመሆን በገበያ ቀን የአርጎባ፣ የአፋርና አማራ ብሄረሰቦችን ባህል መመልከት ይቻላል፡፡ አልዩ አምባ የመጀመሪያዋ የቀረጥ ከተማ እንደነበረች ከአንኮበር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከአልዩ አንባ የገበያ ስፍራ በተጨማሪ የአበዱል ረሱድ የቀብር ቦታ በዚህ አካባቢ የሚገኝ አንዱ የመስህብ ስፍራ ነው፡፡

10. የኢኮኖሚናማህበራዊሁኔታ

10.1 አዋሳኝ ቀበሌዎች

የወፍ ወሻ የተፈጥሮ ደን በበርካታ ቀበሌወች የተካተተና በመንደር፤ በእርሻ ቦታና በግጦሽ መሬቶችየተከበበ ነዉ፡፡ ከደኑ ድርሻ ካላቸዉ በሶስቱም ወረዳ ያሉ የ15 ቀበሌ ነዋሪዎች ደኑን ይጠቀማሉ፡፡ሆኖም ሡናርማ በ2005 እንዳጠናዉ ከደኑ ድርሻ ካላቸዉ ቀበሌዎች 67250 ሰዎች ይኖራሉ፤፡ ከነዚህ ዉስጥ 27865 ሰወች በአንኮበር 6 ቀበሌዎች ፤29886 ሰዎች ባባሶና ወራናና 6 ቀበሌዎች 9499ሰወች ደግሞ በ2 ቀበሌዎች በጣርማ በር ወረዳዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ (67250 ሰዎች) ዉስጥ በፕሮጅክቱ 40150 ሰወች በቀጥታ ተጠቃሚ ሲሆኑ 27100 ሰዎች ደግሞ ቀጥታ ተጠቃሚ ያልሆኑ ናቸዉ፡፡

ምንጭ ሡናርማ 2005

ሠንጠረዥ1 የወፍ ዋሻ የሚገኝባቸዉ ቀበሌዎች የህዝብ ብዛት መረጃ (2005)ተ.ቁ

ወረዳ አባወራየህዝብ ቁጥር

ወንድ ሴት ድምር ቀጥታ ተጠቃሚ ቀጥታ ተጠቃሚ ያልሆነ1 አንኮበር 4258 13695 14170 27865 19510 83552 ባሶና ወራና 7115 15116 14770 29886 12370 175163 ጣርማ በር 2077 4739 4760 9499 8270 1229

ድምር 13450 33550 33700 67250 40150 27100

Page 27: Wof Washa Field Study Final Draft

ባሶና ወራና ወረዳ በኩል የስድስት ቀበሌዎች ድርሻ ሲኖረዉ እነርሱም፡- ደበሌ፤ ጎሹአገር፤ ቀይት፤አባሞቴ፤ ጉዶበረትና ባሶ ደንጎራ ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም በደን የተሸፈነና ለእርሻ ካ

ልሆነ በስተቀር የደጀን መሬት የለዉም፡፡ በባሶና ወራና ወረዳ በኩል የተፈጥሮ ደን ክልል ተብሎየሚታወቀዉ ከደበሌ እስከ ባሶ ደንጎራ ያለዉ ገደላገደልና ከሱ ገርጌ ያለዉ ዳገታማና በከፊልበቁጥቋጦ የተሸፈነዉ ተፈጥሮ ደን ያለባቸው አከባቢወች ብቻ ነዉ፡፡

ከገደላማዉ አፋፍ በላይ የሚገኘዉ ጓሳ፤ ጅባራና ጋርዳ የሚበቅልባቸዉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉለግጦሽ አለያም በህብረተሰቡ የሚጠበቁ የጓሳ�ገር ክልክል መሬቶች ናቸዉ፡፡

ጎሽ ሜዳ (ቀይት) ጎሹ አገር (ደበሌ)

ጥቁሪት ባዶ /አባ ሞቴ/ ዠኖ በር

ፎቶ 23 በባሶና ወራና ከደበሌ እስከ ቀይት (ጎሽ ሜዳ)፣ አባ ሞቴና ዠኖ በር

በተለይ በቀይት ቀበሌ በጎሽ ሜዳ ጎጥና በጉዶበረት በዠኖ በር ጎጥ በከፍተኛ ደረጃ በህብረተሰቡእተጠበቀ ያለና በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኝ ጠፈጥሯዊ ይዞታቸዉን የጠበቁ ቦታዎችበምሳሌነት ከሚጠቀሱት በስተቀር ከአፋፍ በላይ በጥብቅ ስፍራነት ሊጠበቅ የሚችል ቦታ የለም፡፡ነገር ግን ገደላገደሉን ተጠግቶና በሜዳማዉ ጓሳ አካባቢ የበርካታ ጭላዳ

ዝንጀሮ፤ አሽኮኮና አእዋፋት መኖሪያ አንዲሁም ደግሞ ለጎብኝዎች አመች የመመልከቻ ቦታዎችየሚገኙበት ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ከደኑ የሚወጣዉ የጣዉላ ምርት የሚጓጓዘዉ በአብዛኛዉ በእነዚህአካባቢዎች ነዉ፡፡ በተፈጥሮ ደንና የአፈር ለምነት መመናመን ምክንያት የመጣዉን የምርት መቀነስለማካካስ ህብረተሰቡ ጓሳ በመሸጥና ወጣቶቸ ደግሞ ጦስኝ በመልቀም ይተዳደራሉ፡፡ በአነዚህ አካባቢየሚኖሩ ህዝቦች በተፈጥሮ ደኑ ላይ በተለያየ መልኩ የሚደርሱት ጫና የከፋ በመሆኑ ትኩረትየሚጠይቅ ነዉ፡፡ የተፈጥሮ ደኑን ለማገዶና ለተለያዩ አገልግሎቶች በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀሙየአስታ የደን ሽፋን እየተመናመነ ቢመጣም በአካባቢዉ በርካታ ሰዉ ሰራሽ ደኖች ስላሉ የአጠቃቀምስልት በመንደፍ በተፈጥሮ ደኑ ላይ ያለዉን ጫና መቀነስ ይቻላል፡፡ በመኖሪ መንደሮች አቀማመጥበቀይት ቀበሌ ጎሽ ሜዳ በእጅጉ ወደ ተፈጥሮ ደኑ የተጠጋ ሲሆን ሌሎች አካባቢዎች ግን ጓሳዉንናየተፈጥሮ ደኑን ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር ከ2 እስከ 3 ኪሎ ሜትር ከገደላማዉ አፋፍ የራቁናቸዉ፡፡

Page 28: Wof Washa Field Study Final Draft

በአንኮበር ወረዳ በኩልም በበርካታ ቀበሌወች ያካተተ ሲሆን እነርሱም፡- ላይ ጎረቤላ፤ መሃልወንዝ፤ዘጎ፤ እመምህረት፤ መስጫና ዘንቦ ቀበሌዎች ድርሻ ነዉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በመንደር፤በእርሻ ቦታና በግጦሽ መሬቶች የተከበበ ብቻ ሳይሆን ደኑ በፈቅሬ ግንብ፤ ዉቲ፡ አስታከል፤መስጫ፤ አርቦማር በሚባሉ መንደሮችና በእርሻመሬቶች የተቆራረጡ ቦታዎች በርካታ ናቸዉ፡፡

መስጫ

ፍቅሬግንብ መሃል ወንዝ

ከዘጎ እስከ ሃር አምባ ዘጎ መስጫ እርቦ ማር

ፎቶ 24 በአንኮብር ወረዳ የወፍ ወሻ ደን የሚገኝባቸዉ ቀበሌዎች

በተጨማሪም መንደሮችና የእርሻ መሬቶች ከደኑ በጣም የተጠጉ በመሆናቸዉ በደኑ ወስጥ በረትበመስራት ወተት ከሚሰጡ ላሞች በስተቀር ሌሎች ከብቶቸ በደኑ ያኖራሉ፤ በደኑም ዉስጥምይሰማራሉ፡፡ በደኑ ዉስጥ በርካታ እንሰሳት ቢኖሩም በሚደረገዉ አደን የተነሳ ከጉሬዛና አእዋፋትበስተቀር ሌሎችን የዱር አንሰሳት እንደልብ ማየት አስቸጋሪ ነዉ፡፡ በእነዚህ ቀበሌዎች የሚኖሩህዝቦች የደኑን ሃብት በዘፈቀደ የመጠቀምና ለህገወጦች መጠለያ በመስጠት ችግሩን ለማባባስ የከፋመሆኑ እንጅ የሚታየዉ የቤት አንሰሳት ቁጥር ከሌላ አካባቢ ከሚታየዉ የበዛ ነዉ ለማለትአያስደፍርም፡፡ ከተፈጥሮ ደኑ በተላም ዝግባና ፅድን በስፋትና ከግንባታ አልፎ ለማገዶ የሚጠቀሙሲሆን ለመከላካል የማስተማርም ሆነ የጥበቃ ስራዉ የተዳከመ ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህ በርካታምክንያቶች አየተሰጡ ያሉ ቢሆንም ዝግባ፤ የአበሻ ጽድና ኮሶ በመጥፋት ላይ ያሉ መሆናቸዉንየተረዱ አይመስልም፡- ምክንያቱ ከሌሎች ዛፎች እምብዛም ጥቅም ላይ ሲዉሉ አይታዩም፡፡በአንኮኮበር ወረዳ በኩል ያሉ ቀበሌዎች በተላይም ልዩ ትኩረት የሚሻቸዉ ዝግባ፤ የአበሻ ጽድ፤ወይራና ኮሶ ዛፎች በብዛት በመኖሪና በእርሻ መሬት በተጠጋዉ በደኑ ክፍልና በጎጦች በተቆራረጡትደኖች በብዛት መገኘታቸዉ እደረሰ ያለዉ ጉዳት የላቀና ለመፍተሄዉም የጋራ ርብርብ የሚጠይቅነዉ፡፡ በተላይ በፍቅሬ ግን 110 በላይ አባዉራዎች በዉቲ ደግሞ 180 በላይ አባዉራዎች በእርሻናበከብት እርባታ የመተዳደደሩና ደኑን በዘፈቀደ የሚጠቀሙ በመሆናቸዉ የሚያደርሱት ጉዳት የላቀነዉ፡፡ አነዚህ ጎጦች ደኑን በመቆራረጥ በመሃል የሚገኙ በመሆናቸዉ ለመደፊት ለሚደረገዉጥበቃም ልዩ ትኩረት ያሻቸዋል፡፡

በጣርማ በር ወረዳ ሶስት ቀበሌዎች ብቻ የደኑ አካል ቢሆኑም በርካታ የደኑ ሽፋንና እንሰሳሣትየሚገኙት በዚህ ወረዳ በኩል ነዉ፡፡ ምክንያቱም ለደኑ የተደረገዉ ጥበቃ ጥረት የተመሰረተዉ በዚህ

Page 29: Wof Washa Field Study Final Draft

አካባቢ በመሆኑ ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ደኑ በመጎዳትም ሆነ በማገገም የተደረገ ጥረቶችየሚታዩት የነበረዉ በዚሁ ወረዳ በኩል ነዉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ከፍተኛ ጉዳትና ኡታዊ ተጽእኖበእርሻ መሬት መስፋፋት፤ በግጦሽ፤ በአደንና በደን ምንጠራ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ይገኛል፡፡አሁን ያሉት የጥበቃ ሰራተኞችም ሆኑ የአካባቢዉ ነዋሪዎች የደኑ ጥበቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየላላመምጣቱን ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል በሌሎች ወረዳዎች እየደረሱ ያሉ አሉታዊ ተጽእኖዎችለመግታት የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር አለመኖሩን አመላካችና ህገወጦች ካነዱ ወደ ሌላወበመንቀሳቀስ በተፈጥሮ ደኑ ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ አልፎም በወቅቱ እርምጃእንደማይወሰድባቸዉ የጥበቃ ሰራተኞቹ በምሬት የሚናገሩት ነዉ፡፡

ወፍ ወሻ ከዠኖበር ግርጌ የወፍ ወሻ ጽ/ቤት

ዋንዛ በረት በጣርማ በር ዉቲና አስታከል (ዘንቦ) በአንኮበርፎቶ 25. የወፍ ዋሻ ደን በጣርማ በር ወረዳ በኩል እየደረሱ ያሉ ተጽዕኖዎች በከፊልሲታይ

10.2 የሚበቅሉ ሰብሎች

በወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን አካባቢ ሚበቅሉ ሰብሎች የደጋና የቆላ በሚል በሁለት ይከፈላሉ፡፡ በባሶናወራና በኩል የደጋ ሰብሎች ገብስ፤ ስንዴ፤ ባቄላና ተልባ በስፋት ይበቅላሉ፡፡ በተለይ ወደ ደኑመዳረሻ ከደበሌ እስከ ባሶ ደንጎራ ገብስና በቄላ በስፋት የሚዘራ ሲሆን አልፎ አልፎ ስንዴምይዘራል፡፡ ሆኖም ምርታማነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እቀነሰ መምጣቱንና የመሬቱም ለምነት መቀነሱንነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ በአንኮበር ወረዳ ከቁንዲ እስከ በጎረቤላና አካባቢዉ እነዲሁም በዉቲ፤ በመሃልወንዝና መስጫ ገብስ፤ ባቄላና ስንዴ በብዛት ይበቅላሉ፡፡ በወረዳዉ ምስራቃዊ ክፍል በአልዩአንባ፤ዘጎ፤ሃር አምባ፤ ዘንቦና አስታከል አካባቢ ማሽላና ጤፍ በብዛት ይበቅላሉ፡፡ በጣርማ በር ወረዳበኩል ከደብረ ማእዛ እሰከ ዋንዛ በረት ገብስ፤ ስንዴ፤ ባቄላና አተር በብዛት የሚበቅሉ ሲሆን ቋሚሰብሎችና አትክልትም ይበቅላሉ፡፡ በየጊዜዉ እየቀነሰ የመጣዉን ምርት ለማሻሻል ጓይ (አፈርማቃጠል)፤ ፍግ፤ አፈራርቆ በመዝራትና እርከንን፤ በእጽዋትና አግሮፎረስትሪ በማገዝ በስፋትናዉጤታማ በሆነ መልኩ ሰብሎች በበረካታ አካበባቢዎች ይመረታሉ፡፡ ሆኖም አካባቢዉ ወጣገባበመሆኑና በተደጋጋሚ በመታረሱ በአመት ሁለት ጊዜ ባይመረትና ከደኑ ባይጠቀሙ የግብርና ምርቱበቂ ነዉ ለማለት አያስደፍርም፡፡

Page 30: Wof Washa Field Study Final Draft

10.3 የህብረተሰቡዋናዋና የገቢምንጮች

በወፍ ዋሻ አካባቢ የሚኖሩና ከደኑ ድርሻ ባላቸዉ 15 ቀበሌዎች ደኑን ለግጦሻ፤ለግንባታና ለማገዶእንጨት እነዲሁም በህገወጥ መንገድ ለእርሻና ለመኖሪያ ቦታነት ደንበር ገፍተዉ በመዝለቅይጠቀሙበታል፡፡ በሁሉም ቀበሌዎች የሚኖሩ ዋነኛ መተዳደሪያቸዉ ግብርና ሲሆን በንግድ ስራየሚታገዙ በርካታ ናቸዉ፡፡ አንዳንድ ነዋሪዎች ከደኑ በህገወጥ መንገድ የጣዉላ ምርት በማምረትለተሰማሩት የጉልበት እገዛ በማድረግ ዉስን ገቢ ያገኛሉ፡፡ በዚህም የረባ ገቢ ሳይኖራቸዉ በርካታየአበሻ ጽድ፡ ዝግባና የኮሶ ዛፎች በየጊዜዉ ይመነጥራሉ፡፡ ሆኖም ህገወጦች አንድ የዝግባ ዛፍ እስከሃያ ሺ ብር እንደሚሸጡ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ህገወጥ ተግባር በርካታ ሰዎች ዋና የገቢምንጭ አድረገዉ እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ ሌላዉ ከብቶችን ወደ ደኑ በማሰማራት ከሚደረገዉእርባታ ባሻገር በደኑ ዉስጥ በረት ሰርተዉ እንሰሳትን ያረባሉ፡፡ በደጋማዉና በባሶ ወራና ወረዳ የደኑአካል በሆኑት ቀበሌዎች የሚኖሩት ደግሞ የጓሳ ሳር ክልክል በማጨድና ጦስኝ በመልቀም ከእርሻምርት ባሻገር በዋና የገቢ ምንጭት ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህም በጎሽ ሜዳ፡ በአባሞቴና በጉዶ በረትቀበሌዎቸ በርካታና ሰፋፊ የጓሳ ክልክል ቦታዎች በህብረተሰቡ እየተጠበቁ ለነዋሪዎች ተከፋፍለዉይታጨዱና ይሸጣሉ፡ና፡ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከሚሸጠዉ ጓሳና ጦስኝ ኑሮአቸዉን የሚደጉም ገቢከማግኘታቸዉም በላይ ጓሳዉ በሚገባ እየተጠበቀ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በዚህ ጥናትም በተለይ በጎሽሜዳ፤ጥቁሪት በርና በዠኖ በር ስፋት ያላቸዉ አካባቢዎች በጓሳ ሳርና በጅብራ እፅዋት ተሸፍነዉማየት ተችሏል፡፡ ሆኖም ለአስታና ለሌሎች ዛፎች የተሰጠዉ ትኩረት አናሳ ነዉ፡፡ እንዳዉም አስታናሌሎች ዛፎች የጓሳዉን እድገት ይገታሉ በሚል አየተመነጠሩ ነዉ፡፡

11. በወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ላይ እየደረሱ ያሉችግሮች

በአጠቃላይ የጥበቃ ስልቱ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በንጉስ ደንነት ተከብሮ ፣ በመንግስት ደንነት ደግሞ በከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል በአፄ ሚኒሊክና አፄ ኃይለስላሴ ዘመን መንግስት የቆየ ሲሆን በደርግና በኢህአዲግ መንግስት ደግሞ ጣውላን በመቆጣጠርና ወደ ችግኝ ጣቢያ ስራዎች ማድላት የታየበትና አሁን ያሉትን የአደን፡ ልቅ ግጦሽ ፣ ለግንባታና ለማገዶ የሚደረገዉን የደን ጭፍጨፋ ያልታሰገ ነዉ፡፡ ለዚህም በደበሌና በመስጫ ቀበሌዎች በጣውላ ስራ፣በአናጼነትና እንዲሁም እንጨት በመሠንጠቅና በማስተካከል ሕገወጥ ስራ የተሠማሩ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡ የአካባቢዉ ነዋሪዎችም ለግንባታና ለጣዉላ ብቻ ሳይሆን ለማገዶና ላጥር ሳይቀር የአበሻ ጽድ ፍልጥ በስፋት ይጠቀማሉ፡፡

በደጋማዉ አዋሳኝ ያሉት ጐጦች የገደሉ አፈፍ ገደባቸው እንጂ ዋናው የደንና የዱር እንስሳ መጠለያና መመገቢያ የሆነው ጓሣውና ጅብራው የሚበቅልበት ለእርሻ ፣ ለመንደርና ለልቅ ግጦቭ እየዋለ ነው፡፡ በዚህ ወረዳ ያለው የተፈጥሮ ደንና ጓሣ በማህበረሰቡ የተጠበቁት ጐሽ ሜዳና ዥኖበረት አካባቢ ካለው የማህበረሰብ ጥብቅ ቦታ ካልሆነ አብዛኛው ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ውጭ ለሆነ አልግሎት የዋለ ነው፡፡ በጣርማ በር ከዠኖ በር ግርጌ አስከ ዋነዛ በረት ድርት የአዋዲ ወንዝ ተከትሎ በወፍ ዋሻ ቀበሌ ደኑን ለእርሻና ለመንደር አገልግሎት በማዋል ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ በሁሉም አካባቢዎች ያለ ሲሆን ልቅ ግጦሽ፤ ለጣዉላና ፤ ለግንባታ የሚደረገዉ ቆረጣ እጅጉን አስከፊ ነዉ፡፡ ስለዚህ በወፍ ዋሻ ደን እየደረሱ ያሉ ጉዳቶችና የወደፊት ስጋቶች በሚቀጥዉሁኔታ ተገልጠዋል፡፡

Page 31: Wof Washa Field Study Final Draft

የተቀናጀና ሁሉን አቀፍ የሆነ ጥበቃ አለመኖር፡ የወፍ ወሻ ደን በርካታ ጠባቂዎች ቢኖሩትም የጥበቃስልቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የላላና ለሚከሰቱ ችግሮች በወቅቱ ምላሽ በሚሰጥ መልኩ የተደራጀ አይደለም፡፡በደኑ ዉስጥ የሚከለከል ቢኖር ጣዉላ ብቻ ነዉ፡፡ ደኑ ግን እደረሰበት ያሉተ ጫናዎች በርካታናቸዉ፡፡ የጥበቃ ትኩረት የተሠጠዉ የጣዉላ ምርትን መቆጣጠር ቢሆንም ለተለያዩ ሰራዎች ሰዎችወደ ደኑ እንደፈለጉ ሲለሚገቡ ህገወጥ ስራዎችን ለመስራት አመች ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ለምሳሌየማገዶ እንጨት ለመልቀም ትላለቅ መጥረቢያ ይዞ በመግባት ደረቅ እንጨት ከመሰብሰብ ይልቅእርጥብ ግንድ መፍለጥ፤ እንደልብ የጦር መሳሪያ ይዞ መዘዋወርና ማደን እንዲሁም ለህገወጦችከለላ መስጠት፡፡

ፎቶ 26 ከደኑ የተፈለጠ እርጥብ የአበሻ ጽድ የማገዶ እንጨትና እየደረቀ የሚወድቀዉ በደኑ ዉስጥ በረት በመስራትና በዚያዉ ሰበብ ጣዉላ ማምረትና አደን ማደን ጥበቃዉም ሆነየጥበቃዉ ስልት የተቀናጀ ባለመሆኑ ለመከላለከል አስቸጋሪ ነው፡፡

ምክንቱም የሚመለከታቸዉ መስሪቤቶችም ሆኑ የባለሙያ ክትትል አናሳ ነው፡፡ በጥበቃዉ የፖሊስየቀበሌ ስራ አስፈጻሚ፡ ፍርድ ቤቶችና መስተዳድር አካላት የተቀናጀ የጥበቃና የቁጥጥር ስራ ሲሰሩአይታይም፡፡ በዚህም ለበርካታ አመታት ዉሳኔ ያላገኙ ከህገወጦች የተያዙ የጣዉላ ምርትና የደንመጨፈጨፊያ መሳሪያዎች ተሠብስበዉ ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሶስቱም ወረዳዎች ያሉ ባለሙዎችምሆኑ የሚመለከታቸዉ አላላት በተፈለገዉ ጊዜ ተገናኝቶ ለችግሮች እልባት አለመስጠት፡፡ ችግሮችንተወያቶ የጋራ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ አንዱ በሌላዉ ማመካኘት፡፡ ስለዚህ እነዚህን ችግሮችለመፍታት በጋራ በደኑ ቁጥጥር ላይ የሚካሄዱ ስራዎችን ለይቶ ማዉጣትና መፍትሄወችበተመሳሳይ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግና የሚመለከታቸዉን የህግ አከላት ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡማድረግ ይገባል፡፡

ለግንባታና ለጣውላ ስራ የደን ጭፍጨፋ: የወፍ ዋሻ ታሳቢ ጥብቅ ስፍራ ለብዙ ዓመታት ትኩረትከተሰጣችው የመንግስት ደኖች ውስጥ የተመዘገበ በመሆኑ ከመንግስት በጀት እየተመደበለትበመጠበቅ ላይ ላይ ሲሆን አሁንም በሶስቱ ወረዳዎች በድምሩ 109 የጥበቃ

ፎቶ 27. በህገወጥ መንገድ የተመረተ ጣዉላና የእርሻ መሳሪያዎች

Page 32: Wof Washa Field Study Final Draft

ሰራተኛዎች ተመድበው በመጠበቅ ላይ ቢሆኑም በደኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ የዝግባና የፅድ ዛፍ ምንጠራይካሄዳል፡፡ በተለይም በአንኮበር ወረዳ በመስጫ ቀበሌ መስጫና ውቲ ጎጦች አካባቢ የጎላ ነው ፡፡ከጣውላና ለቤት ግንባታ ከሚደረገው ጭፍጨፋ በተጨማሪ የኮሶ ዛፍ ለእርሻ መሳሪያና ለአልጋእግር በሰፊው ይጨፈጨፋል፡፡ ይህንም ጭፍጨፋ ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ስራ ከደኑ ሲወጣ

መቆጣጠር እንጂ ውሥጥ የሚደረገው ቁጥጥርውስን ነው፡፡

የእርሻ መስፋፋት: በባሶና ወራና ወረዳ ጓሳውንተከትለው አርሶ አደሮች ያልተሰጣቸውን መሬትበማረስ የቀይ ቀበሮን መናኸሪያ በማጥፋትከእብድ ውሻ በሽታ በተጨማሪ ለቀይ ቀበሮመጥፋት በምክንያትነት የሚጠቀስ ሲሆንበአንኮበር ወረዳ ተዳፋቱን በመከተል የአስታንቁጥቋጦ በመመንጠርና በመቆፈር ወደእርሻመሬትነት እየቀየሩት ሲሆን ይህም ችግርበጣርማ በር ወረዳም ውስጥ የሚታይ ሲሆንለችገሩ መባባስም መንደሮች በደኑ ውስጥናአከባቢ መኖራችው አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡

ፎቶ 28. ልቅ ግጦሽና (ዠኖ በር) እርሻ መሽፋፋት (ዋነዛ በረትና ዉቲ)

ልቅ የግጦሽ ስርዓት መኖር፡ በዎፍ ዋሻ ውስጥ ከብት የማይገባበት በጓሳውና በደኑ መካከል ባለውገደል ብቻ ሲሆን በደኑና በጉሳው ውስጥ ከብት የሚሰማራ ሲሆን ከብቶች በእግራቸው መረጋገጥናበግጦሽ ምክንያት የአፈር ክለት እንዲከሰትና ተክሎች እንደገና ራሳቸውን እንዳይተኩ ምክንያትሁነዋል፡፡የቤት እንስሳትን የሚያሰማሩና የሚጠብቁ ሰወች ምሳር በመያዝ ለደኑ መጨፍጨፍምክንያት ሁነዋል በዚህ ጥናት ወቅትም ምሳር ይዞ የሚገባ ሰው እንደማይከለከል መመልከትችለናል፡፡ ከከብት አሰማሪዎች ጋር አብረው የሚንቀሳቀሱ ውሻዎች የእብድ ውሻን በሽታ በማስተላለፍለቀይ ቀበሮወች መጥፋትና ለተራ ቀበሮወች ቁጥር መመናመን በምክንያትነት የሚወሰድ ሲሆንየቤት እንስሳትን እንቅስቃሴ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመወያየት መግታት ለዱር እንስሳትህልውና ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ የሚገባው ተግባር ነው፡፡

ህገ-ወጥ አደን፡ በጫካው ውስጥ ውስጥ የተለያዩ የዱር እንስሳትና አዕዋፍ የሚገኙ ሲሆን የመኖሪያአካባቢያቸውን በመመንጠርና የመመገቢያና የመራቢያ አካባቢያቸውን ከመረበሹ በተጨማሪ ህገ-ወጥአደን በተለይም የሚኒሊክ ድኩላ፣ድኩላና ሰሳን ቁጥር በማመናመንና ወደ አንድ አካባቢ እንዲሰባሰቡአድርጓል ፡፡ በዚህ ጥናት ወቅት የአብይ ጾም መግቢያ ላይ ሶስት ጥይት ደኑ ውስጥ ሲተኮስሰምተናል፡፡ ይህን የዱር እንስሳትን ማሳደድ ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶት የተጠናከረ ጥበቃ ሊካሄድይገባል፡፡

የደን ቃጠሎ በወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ውስጥ በዋናነት በጣሊያን ወረራ ወቅት የደን ቃጠሎየተከሰተ ሲሆን አልፎ አልፎ በተወሰነመልኩም ቢሆን እየተከሰተ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ለዚህየየደን ቃጠሎ በምክንያትነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት ውስጥo ከሰል ማክሰልo ማር ቆረጣo መብረቅo የእረሻ መሬት ለማስፋት የሚደረግ ቃጠሎo ከከብቶች ማደሪያ አካባቢ ለምግብ ዝግጀትና ቅዝቃዜን ለመከላከል ሳት ማንደድ

Page 33: Wof Washa Field Study Final Draft

o በተፈጥሮ ደኑ ውስጥ ያለው የደረቅ እንጨት ክምችትo የእንጨት ምርት የኮንተሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴo ለአደን የሚለቀቅ ሰደድ እሳት

ለደን ቃጠሎ ከላይ የተዘረዘሩት በምክንያትነት ቢዘረዘሩም በወፍ ዋሻ ውስጥ ከሰል አክሳዮች በተውትእሳት በ2000 ዓ.ም ቃጠሎ የተከሰተ መሆኑን የአካባቢ ነዋሪዎች ያስረዳሉ፡፡ በዋናነት በወፍ ዋሻውስጥ ለደን ቃጠሎ ስጋት ሊሆን የሚችለው በውስጡ የተከማቸው የደረቅ እንጨት ክምችት ሲሆንይህም የሚቀነስበትን መንገድ መቀየስ ያስፈልጋል፡፡

በደኑ ውስጥ መንደርና የእርሻ ቦታ መኖር፡ በደኑ ውስጥ በእረቦ ማር እንዲሁም በደን የተከበቡየውቲ፣የአስታከልና የፍቅሬ ግንብ መንደሮች የእርሻ መሬት በመኖሩ የዱር እንስሳቱን እንቅስቃሴከመግታቱም ባሻገር የተፈጠሮ ሃብቱን በማራቆት ለአፈር ክለት እያጋለጠው ይገኛል፡፡

ፎቶ 29 ማር እርቦ በደን መሃል የሚገኝ መንደርና የዉቲ ተራራ መእራባዊ ጎን የተፈጥሮ ደንናምስራቃዊ ጎን የእርሻ ቦታ

ለዚህም በተጠቀሱትና ሌሎች አጎራባች መንደሮች ያለው የእርሻ ስራ እንቅስቃሴ በተፈጥሮ ሃብቱላይ እያደረሰ ያለውን ተጽኖ ለመቀነስ በህገወጥ የሚስፋፉ የእርሻ መሬቶችን መቆጣጠር ይጠይቃል፡፡በተጨማሪም መሃል ወንዝ፡ ወፍ ወሻና ዋንዛ በረት ቀበሌዎች በከፍተኛ ሁኔታ መንደሮች ወደ ደኑየቀረቡ በመሆናቸዉ በደኑ ላይ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ለቀፎ ልብስ ዛፍ መላጥ

የጽድ ዛፍ በአብዛኛው ለቀፎ ልብስእየተላጠ በመሆኑና እንዲሁም ዛፉንለመጣል እየተከረከረ ስለሚተው የዘፉእድሜ የገፋና ከስር የሚተካ ችግኝካለመኖሩ ጋር ተያይዞ የዛፉ ህልውናበአደጋ ላይ በመሆኑ በሶስቱ ወረዳዎችየሚገኑኙ ግብርናና ገጠር ልማትጽ/ቤቶች ለደን ጥበቃው ልዩ ትኩረትሰጥተው የሚንቀሳቀሱበት መንገድቢፈጠር፡፡

ፎቶ 30. ለቀፎ መሸፈኛና ለማድረቅ የተላጠና የተከረከረ የአበሻ ዕድ

Page 34: Wof Washa Field Study Final Draft

የእንስሳት በሽታ

በባሶና ወራና ወረዳ ከጎሽ ሜዳ አስከዜኖበር ድረስ የለውን ጓሳ ተከትሎ የቀይ ቀበሮ እስከ አለፉትአምስት አመታት በአካባቢው እንደነበር ከአካባቢው ነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል፡፤ ሆኖም ግንበአካባቢው በተደጋጋሚ በሚከሰተው የዕብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ቀይ ቀበሮ ከአካባቢው የጠፋሲሆን ተራ ቀበሮም ለመጥፋት በመቃረብ ለይ ነው፡፡ ይህን በሽታ ለመቆጣጠር ለውሻዎች ክትባትመስጠት አስፈላጊ ሲሆን ውሻዎች ወደ ቦታው አንዳይሰማሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ የአብድ ውሻበሽታን ለመቆጣጠር የስሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ለውሻወች ክትባትሊያዘጋጂ ይገባል፡፡

የታሳቢ ጥብቅ ስፍራው ደጀን የሌለው መሆን

የወፍ ዋሻ ታሳቢ ጥብቅ ስፍራ ዙሪያውን በመንደር የተከበበና ወደጥብቅ ስፍራው የሚኖረውን ጫናለመቀነስ የሚያስችል ደጀን መከለል አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን ጫና ለመቀነስ የሚያስችልሊከለል የሚችል የደጀን ክልል ስለሌለው ለጥበቃው አስቸጋሪ ነው፡፡

የታሳቢ ጥብቅ ስፍራው ቅርጽ ለጥበቃ ምቹ አለመሆን

የታሳሚ ጥብቅ ስፍራዎች ክብና ሰፊ ቢሆን ለጥበቃ ምቹና የብዝሃ ህይወት ሃብቱን በቀላሉለመጠበቅ ያስችላል ፡፡ ሆኖም ግን የወፍ ዋሻን ቅርፅ ስንመለከት እንደ ደጋን የተጥመዘመዘና ቀጭንሲሆን ከአንዱ ዳር በመነሳት ሌላው አካባቢ ያለዉን ደንና የዱር እንስሳት ሃብቱን ለመጠበቅየሚደረገውን ጥረት ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ በተላይ በአስታከል (ዘንቦ)፤ በማር እርቦና በዉቲ(መስጫ)፤ፈቅሬ ግንብ (እመምረት)፤ዘጎ ና መሃል ወንዝ የሚባሉ አካባቢዎች ከዋናዉ የወፍዋሻ የተፈጥሮ ደን በእርሻና በመንደር የተቆረጡ ወይም በቀጭን የተፈጥሮ ድንና የግጦሽ ቦታየተያያዙ በመሆናቸዉ ለጥበቃ አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም እነዚህ የተቆራረጡ ደኖች የበርካታእጽዋት መገኛ መሆን እንክብካቤና የተሻለ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፤

የጓሳ አጨዳ

በባሶና ወራና ወረዳ ከቁንዲ እስከ ዠኖ በር ድረስ ባለው ከፍተኛ ቦታወች የጓሳው መሬት በህገወጥአራሾች ከመታረሱ ባሻገር የጓሳና የጦስኝ አጨዳ ስለሚካሄድና የኣስታ ቁጥቋጦዎች ጓሳውን ሸፈነብንበሚል ከቁጥቋጦው ይልቅ ለጓሳው ትኩረት ስለሚሰጡ አስታው እየተመነጠረ ይገኛል ፡፡ በተለይምዠኖ በር አካባቢ ያለውን የአስታ ቁጥቋጦ ትኩረት ተሰጥቶ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

የአገር በቀል ዛፎችን ከባቢያዊ ጥቅም አለመረዳት

ለተለያየ አገልግሎት በርካታ አገር በቀል ዛፎች በዘፈቀደ ተቆርጠዉና ተመንጥረዉ ይታያሉ፡፡ ለዚህምየግንባታና የማገዶ እጥረት በምክንያትነት እነዳይወሰድ በአቅራቢያ የሚገኙት ከፍተኛ የደን ሽፋንናብዛት ባላቸዉ የባህር ዛፍ ደኖች የተቆረጠ ማየት አስቸጋሪ መሆኑ ለአባባላችን ዋስትና ነዉ፡፡ ስለዚህአገር በቀል ዛፎች ከላቸዉ ከባቢያዊ ጥቅም ባሻገር በቶሎ የማደርሱና እንክብካቤ የሚጠይቁናበጎብኝዎችም ተፈላጊ መሆናቸዉን ነዋሪዎቹ የተረዱ አይመስልም፡፡ ለማገዶ እንጨት እንኳን የወደቀደረቅ እንጨት ከመልቀም እርጥብ ወይም ግንድን መፍለጥ የተለመደ ነዉ፡፡

የበጀት እጥረትና የደን አጠቃቀም ችግሮች

የተፈጥሮና ሰዉ ስራሽ ደኑን ለመጠበቅም ሆነ በአገባቡ ለመጠቀም የሚታይ ጥረት አናሳ ነዉ፡፡ በዚህምክንያት በርካታ ሰዉ ሰራሽ ደኖች አረጅተዉና ጥቅም ከሚሰጡበት ደረጃ አልፈዉ ይታያሉ፡፡የመንግስት በመሆናቸዉና የተተከሉ መሆን ደግሞ በህገወጥ መንገድ ተመንጥረዉም ሆነ ተሰርቀዉአይታዩም፡፡ ይህ የሚያሳየዉ የጥበቃ ስልቱ ህብረተሰቡ በአገር በቀል ዛፎች ጠቀሜታ ግንዛቤ

Page 35: Wof Washa Field Study Final Draft

እንዲኖራቸዉ ጥረት ያደረገ ሳይሆን የጣዉላ ምርት እነዳይኖር ብቻ በመሆኑ የአገር በቀል ዛፎችለተጨማሪ አሉታዊ ጫና እነዲጋለጡ ያደረገ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ለጥበቃ ሰራተኞች የሚከፈለዉደመወዝም አንስተኛ በመሆኑ ሕገወጦችን ለመከላከል አቅም የሚፈጥር ሳይሆን አበዛኛዎች ተባባሪእንዲሆኑ የሚያበረታታ ነዉ፡፡ ደመወዝ ብቻ ሳይሆን አብዛናወቹም የጥበቃ መሳሪያ የሌላቸዉበመሆኑ ሕገወጦችን ለመከላከል አቅም የላቸዉም፡፡ በሌላ በኩል በገሃድ ከሚታየዉ የደን ምንጠራዉጭ ለሚታዩት ችግሮች ቁጥጥር ለማድረግ አቅም አላቸዉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በአንፃሩ የደንጥበቃዉም ሆነ ቁጥጥሩ በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ሁኔታ አለመሆን አንዱ በሌላዉ ማመካኘትየተለመደ ነዉ፡፡ የጥበቃ ሰራተኞች ደመወዝ ማነስ ብቻ ሳይሆን የስራ ማስካሄጃም የሌላቸዉበመሆኑ ወጭ የሚጠይቁ ስራዎች ለማከናወን የማይችሉ መሆኑ ችግሮችን የሚያባብስ ነዉ፡፡

12. የወፍ ዋሻ ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም

12.1 ታሳቢጥብቅ ስፍራው የሚኖረውጠቀሜታ

ሀ/ ሥነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታ

ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር ያላቸዉ ግብግበ ዘለቄታዊ የተፈጥሮ ገጽታ መኖርን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እነዲሆን ማድረግ ያስችላል፡፡ በዚህም ዘለቄታዊ ጥቅም

በደኑ ውስጥና በአካባቢው ያለው ስርዓተ ምህዳር እንዳይዛባ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋል ፡፡ ለመጥፋት የተቃረቡትን የሃበሻ ጽድ ፣ኮሶ፤ዝግባና የወይራ ዛፍን ለመጠበቅ ያስችላል፡፡

እፅዋቱም በተፈለገዉ ቁመትና እድገት ደረጃ እንዲገኙ ያስችላል፡፡ በታሳቢ ጥብቅ ስፍራው ውስጥ ያለው ብዝሃ ህይወት ሳይጠፋ እንዲኖር፡፡ የአካባቢውን የአየር ሚዛን እንዲጠበቅ ያስችላል፣ በአካባቢው የሚገኙ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በአይነትም ሆነ በብዛት ይጠበቃሉ፣ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በቦታቸው እንዲጠበቁና እንዳይጠፉ ይረዳል፣ የተስተካከለ የውሃ ሃብት እንዲኖር ያስችላል (ከታሳቢጥብቅ ስፍራው የሚነሱ ምንጮችና

ጂረቶች አመቱን በሙሉ እንዲፈሱ አስችለዋል)፡፡

ለ/ ኢኮኖሚያው ጠቀሜታ በታሳቢ ጥብቅ ስፍራው ከጐብኝዎች ጋር ተያይዞ ከቱሪዝም አማራጭ ገቢዎች ለህብረተሰቡና

ለመንግስት ገቢ ያስገኛል፣ በታሳቢ ጥብቅ ስፍራው ጥበቃ ሠራተኝነትና በተፈቀደ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ በመሣተፍ

የአካባቢው ህብረተሰብ ቀጥተኛ ተጠቃሚ ይሆናል፣ ከምርምርና ሣይንሳዊ ጥናት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን ገቢና አቅም ያጐለብታል፣ የ›=¢-~]´U እንቅስቃሴ ስለሚስፋፋ ለአካባቢው ህብረተሰብ አንድ ¾Ñu= U”ß ÃJ“M፡፡ የአካባቢው የአየር ሚዛን ስለሚጠበቅ ከእርሻ ስራ የሚገኘው ገቢ ዘላቂና አስተማማኝ ይሆናል፡፡ በሆቴልና አገልግሎት በመስጠት በረካታ ነዋሪዎች ኑሮአቸዉን ማሻሻል ይችላሉ ተጨማሪ

እዉቀትም ይኖራቸዋል፡፡

ሐ/ ማህበራዊ ጠቀሜታ ዓለማቀፋዊና ማህበረሰባዊ የሆኑ ጠቃሚ የባህልና ልምድ ልውውጥ ይኖራል፣ ከታሳቢ ጥብቅ ቦታው መቋቋም ጋር የመሠረተ ልማቶች መስፋፋት ት/ቤት፣ የኢኮ ቱሪዝም

ማህበራት መደራጀት የሰውና የእንስሳት ጤና ኬላዎች ይገነባሉ፣ በሶስቱም ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ደኑን ለመጠበቅም ሆነ በአገባቡ ለመጠቀም የሚያስችል

ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ በአካባበዉ የሚኖሩ የአማራ፤ የአረጎባና አፋር ማህበረሰቦች በደኑ አጠቃቀምና ጥበቃ ያላቸዉ አሰተረዋጾ ይጎላል፡፡

Page 36: Wof Washa Field Study Final Draft

መ/ሳይንሳዊ ጠቀሜታ የዱር እንሰሳትና ዕፅዋትን ባሉበት ሁኔታና በተፈተሮአዊ አኗኗቻዉ ለሚደረግ ምርምር

በማእከልነት ያገለግላል የባህላዊ መድሃኒቶችን ደህንነት በመጠበቅና በመንከባከብ ጥቅም ላይ በማዋል ሣይንሳዊ

ጥናትንም ለማካሄድ ይረዳል፡፡ በመጥፋት ላሉ የዱር እንስሳትና እጽዋት ሳይንሳዊ ምርምር ሊድረግ ያስችላል፡፡ የተፈጥሮ ደኑና ገጽታዉ ለከባቢያዊ ደህንነት፤ ለብዝሃ ህይወትና ለስርአተ ምህዳር መስተካከል

ያላቸዉ አስተዋጾ ይታወቃል በዚህ ረገድ ለሚደረጉ ምርምሮች የመስክ ላቦራቶር ሊሆን ይችላል፡፡

መ/ የተፈጥሯዊነት ጠቀሜታ ምንም እንኳን አካባቢው ከሰው ልጆች ተጽዕኖ ነጻ ባይሆንም በአንጻራዊነት ከአካባቢው የተሻለ

በመሆኑ ተፈጥሯዊነትን ጠብቆ ለመቆየት ያስችላል፡፡ በዉስጡ ያሉትን ብዝሃ ህይወትና ሌሎች(አፈር፤ዉሃና የመሬት አቀማማጥ) በተፈጥሮአዊ ገጽታቸዉ ቆይተዉ ዘለቄታ ባለዉ መልክጥቅም እነዲሰጡና ተፈጥሮአዊ ይዘታቸዉ እነዳይጓደል ይረዳል፡፡

ሠ/ የበስህብነት ጠቀሜታ አካባቢው የሰው ልጅን ቀልብ ሊገዙ የሚችሉ መመልከቻ ቦታወችና ማራኪ ገጽዋች የያዘ ሲሆን

ከነዚህም ቦታዎች ውስጥ እንደ ቁንዲ፣ገማሳ ገደል ፣ጎሽ ሜዳ ፣ጥቁሪት ባዶና ዠኖ በር፤ ዉቲየመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ አካባቢዎች እራሳቸዉ ማራኪ ከመሆናቸዉ ባሻገር የደኑንስብጥርና ሽፋን እነዲሁም የብዝሃ ህይወት ክምችት ለመቃኘት የሚያሰችሉ ናቸዉ፡፡ ሲለዚህበተፈትሮዐዉ ይዘቱ ለጎብኝዎች ማራኪ የሆነ መዝናኛና እርካታ ሊሰጡ የሚችሉ የተፈጥሮመስህብ ቦታዎች ያሉበት ነዉ ማለት ይቻላል፡፡

12.2. ጥብቅ ቦታ የመሆን አቅምማረጋገጫመስፈርቶች

ሀ/ ወካይነት /representativeness/ የተፈጥሮ ደኑ በተለያዩ አካባቢዎች በልቅ ግጦሽ፤ በደን ጭፍጨፋና በእርሻ የተጎዳ ቢሆንም

አካባቢው የሰብ አፍሮ አልፓይን ስረዓተምህዳር እንዲሁም በታችኛው የደኑ አካል የሞንታኔስረዓተምህዳር ደንን የሚወክል ስለሆነ በጥብቅ ስፍራነት ቢከለል በልማት ቀጠናው ወካይ የሆነየጥበቃ ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡ የዚህ ስርዓተ ምህዳር በአገሪቱ ካሉ ፓርኮች በከፊል በስሜንተራራዎች፤ በቦረና ሳይንትና በባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርኮች ብቻ ይወከላል፡፡

ከስርዓተምህዳር ውክልና በተጨማሪ የሚኒሊክ ድኩላና የአንኮበር አመዴ ወፍን ለመጠበቅ ወካይአካባቢ ነው፡፡ በስረዓተ ምህዳር ደረጃ ይመሳሰል እንጂ የዎፍ ዋሻ ደን በጣም ረዣዥምና ከፍተኛዉፍረት ባላቸዉ ዛፎች የተሸፈነ ነዉ፡፡ስለዚህ በዚህ ስርዓተ ምህዳር ባሉ ሌሎች ደኖች ከ20 ሜትር በላይ ቁመትና ከ8ሜትር በላይ መጠነ ዙሪያ ያላቸዉ ዛፎች ማግኘት አስቸጋሪ ነዉ::

ለ/ የብዛ-ህይወት ክምችት / Diversity/ የአካባቢውን የብዝሃ-ህይወት ሃብት ስንመለከት የሃበሻ ጽድ፣ኮሶና ዝግባ ዛፎች በብዛት

የሚገኝበት መሆኑና ሌሎች ዕጽዋትም በከፍተኛ ቁጥርና እድገት የገኙበታል፡፡ የጉረዛና ጭላዳ ዝንጅሮ ቁጥር በበቂ ሁኔታና ለጎብኝወች በቀላሉ ለማስጎብኘት በሚያስችል

ቁጥርና ስርጭት ይገኛል፡፡

Page 37: Wof Washa Field Study Final Draft

ለጊዘዉ ደኑ በአገባቡ ባለመጠበቁ እነደልብ ለማየት አስቸጋሪ ቢሆንም የሚኒሊክ ድኩላና ተራደኩላ ጥበቃዉ ከተጠናከረ በአጭር ጊዜ በከፍተና ቁጥር ሊታዩ የሚችሉበት ነዉ፡፡

ከፍተኛ ቦታዎች እንደ ደሴት ሆነው የብዝሃ-ህይወትንና ስርዓተ-ምህዳርን ስለሚይዙ ወፍ ዋሻደንም የድንቅየና ብርቅየ የዱር እንስሳት መናኸሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡

የአዕዋፍ መናኸረያ መሆኑ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙትን Ankober Serin Abyssinian Longclaw የያዘ በመሆኑ፡፡

በኢተዮጵያ ብቻ ይገኙ የነበረና አሁን ኤርትራ የተጋራቻቸው የአዕዋፍ ዝርያዎች Wattled Ibis White-collared Pigeon Black-winged Lovebird Thick-billed Raven White-billed Starling Rouget's Rail Blue-winged Goose Rueppell's Chat የሚገኙበት በመሆኑ፡፡

ሐ/ ልዩ መገለጫ / Distinctiveness/ ከፍታን መሰረት ያደረገ የተያያዘ የዕፅዋት ስብጥርን ከሳብ አፍሮ አልፓይን አስከ ዝቅተና

ሞንታኔ ስርዓተምህዳር አካቶ የያዘ መሆኑ /Distinctive layers from the higher sub afro alpin to lower montane forest /

ዕፅዋት ዕድገታቸዉን እስከ ባላቸዉን አቅም በማድረስ ያለዉን ምቹ ሁኔታ ዉክልና የገለጸነዉ፡፡ ስለሆነም በጣም ረዣዥምና ከፍተኛ ዉፍረት ባላቸዉ ዛፎች የተሸፈነ ነዉ

ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች (አነኮበር የ36 የሸዋ ነገስታት መናገሻ)፣ የአጼ ሚኒሊከ የትዉልድቦታ (አንጎለላ)ና አልዩ አምባ (ጥኝታዊ የንግደ ከተማ)ና ሰዉ ሰራሽ የጣርማ በር የዋሻ መንገድበቅርብ ርቀት መኖራቸው የወፍ ወሻን የተፈጥሮ ደን ልዩ ያደርጉታል፡፡

መ/ ኢኮሎጂያዊ ጠቀሚታ /Ecological importance/ በታሳቢ ጥብቅ ስፍራው ውስጥና በአካባቢው ያለው ስርዓተ ምህዳር እንዳይዛባ ከፍተኛ

አስተዋፅኦ ያደርጋል ማለትም ከአካባቢው በተለየ የተሸለ የደን ሽፋን ስላለው ዝናብ ስርጭት የተስተካከለ እንዲሆን አስችሏል፣

ይህ አካባቢ በክልሉ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረቡትን የሃበሻ ጽድ ፣ኮሶ፤ዝግባና የወይራ ዛፍን ለመጠበቅ ያስችላል፣

በአካባቢው የሚገኙ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በአይነትም ሆነ በብዛት በተፈጥሮአዊ ገፅታቸዉ ይጠበቃሉ፣

ብርቅየ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በቦታቸው እንዲጠበቁና እንዳይጠፉ ይረዳል፣ የተስተካከለ የውሃ ሃብት እንዲኖር ያስችላል

ሠ/ በአካባቢው ላይ ያለ ጫና መጠን /Degree of interference/ ከፍተኛ ተዳፋትነት ያላቸው ቦታዎች ተመንጥረው ለእርሻ ስራ መዋላቸው የሚንልክ ድኩላና ሰሳ አደን መኖር የልቅ ግጦሽ መኖር ለጣውላና ለግንባታ አገልግሎት የነባር ዛፎች መመንጠር የተቀናጀ ጥበቃና የደን እንክብካቤ አለመኖር

ረ/ የአካባቢው ሳይንሳዊ ጠቀሜታ /Scientific and monitoring uses/

Page 38: Wof Washa Field Study Final Draft

የዕጽዋትንና የዱር እንሰሳትን የተፈጥሮ አካባቢቸዉን ለማጥናት በሞዴልነት ያገለግላል የዱር እንስሳት በሽታ ክስተትን በተለይም የእብድ ውሻ በሽታን ለአካባቢ ክትትል በሚኖረው ጠቀሜታ የተፈትሮ ሚዛን ለዉጥን መለካት ያስችላል የዱር እፅዋት ናሙናና ተፈጥሮአዊ እድገትንና በሰዎች ጣልቃ ገብነት የሚመጣዉን ለዉጥ

ለማየት

ሰ/ የቦታ ስፋት/area size/ታሳቢ ጥብቅ ቦታው በጥብቅ ስፍራነት ተመዝግቦ በውስጡ ያሉትን የተፈጥሮ ሃብቶች ለመያዝ ቢያንስ አንድ ሽህ ሄክታር መጠበቅ ይኖርበታል የሚለውን የ IUCN መስፈርት የሚያሟላና ከ8000ሄ/ር በላይ የሚሸፍን ታሳቢ ጥብቅ ስፍራ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙትን የሚኒልክ ድኩላ፤ጭላዳ ዝንጀሮና የአንኮበር አመዴ ወፍ መኖሪያ ነው ፡፡

ሸ/ ቅርፅ /መጠነ ዙሪያ/shape/ጥብቅ ስፍራዎች በሚቋቋሙበት ወቅት በተቻለ መጠን ዝቅተኛ መጠነ ዙሪያ እንዲኖራቸውይጠበቃል ፡፡ ሆኖም ግን የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ዙሪያውን መንደርና የእርሻ መሬትየበዛበት በመሆኑና ደጀን ስለሌለው የደር ድንበር ወጣ ገባነት ስለሚበዛበትና ቅርጹም ሾጣጣበመሆኑ ከስፋቱ አንጻር ሲታይ ረጂም መጠነ ዙሪ ነው ያለው፡፡ ሆኖም ዋናዉ ደን ለቁጥጥርአመችና በገደልና በኮረብታዎች የተከበበ ነዉ፡፡

ቀ/ በውስጡ የሚገኙ ብርቅየና ድንቅየ ዝርያዎች/Endemicity/ከታለላቅ አጥቢዎች ውስጥ የጭላዳ ዝንጀሮና የሚኒልክ ድኩላ የሚገኙ ሲሆንከአዕዋፍ ዝርያዎች

Ankober Serin Abyssinian Longclaw ይገኙበታል

12.3 የታሳቢፓርኩጠቀሜታናጥብቅ ቦታ የመሆን አቅምማረጋገጫመስፈርቶች ጥምረት ዝምድና

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን በርካታ ጠቀሜታ ያለዉና ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ ከተጠበቀ የሚሰጣቸዉ ጠቀሜታዎች አካባቢያዊ፤ አገራዊና አለማቀፈዊ አሰተዋፆ ይኖራቸዋል፤፤ በተለይም ያለዉ የደን ሽፋንና መልካምድራዊ አቀማመጥ የብዝሃ ህይዎትና ተፈጥሮአዊ ገፅታ ከመጠበቅ አልፎ የአለምሙቀትንና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የጎላ አስተዋጾ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ የተፈጥሮ ደኑ የሚሰጠዉጠቀሜታ ከIUCN ጥብቅ ስፍራ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸዉ ክራይተሪያ ሲነፃፀር ጥብቅ ስፍራየመሆን አቅሙን ማየት ይቻላል፡፡ ከዚህ በታች የተቀመጠዉ ሰንጠረዥ ያለዉ የተፈትሮ ሀብትናየሚሰጠዉን ጠቀሜታ ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅሙን በማነፃፃር ሊጠበቅ የሚገባዉን ደረጃ ለመወሰንያስችላል፡፡ ይህም የመመዘኛ መስፈርቶች በታሳቢ ፓርኩ ጠቀሜታ ላቸዉን ተፅእኖ ያመላክታል፡፡

Page 39: Wof Washa Field Study Final Draft

ሰንጠረዥ የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ጠቀሜታና ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም መመዘኛ መስፈርቶች ንፅፅርአቅም

ጠቀሜታ

ወካይነት ብዝሃ ህይወት

ልዩመገለጫ

ኢኮሎጂያዊጠቀሚታ

በአካባቢውላይ ያለጫናመጠን

የአካባቢውሳይንሳዊጠቀሜታ

የቦታስፋት/

ቅርፅ /መጠነ ዙሪያ/

ብርቅየናድንቅየዝርያዎች

ደረጃከፍተና%

ሥነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታ

ከ ከ ዝ ከ ከ ከ ዝ ዝ ከ 66%

የተፈጥሯዊነት ጠቀሜታ

ከ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ዝ ከ 89%

ኢኮኖሚያው ጠቀሜታ

ከ ከ ዝ ከ ከ ከ ከ ከ ከ 89%

ማህበራዊ ጠቀሜታ

ከ ከ ዝ ከ ከ ከ ከ ከ ዝ 78%

ሳይንሳዊ ጠቀሜታ

ከ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ከ ከ 100%

የመስህብነትጠቀሜታ

ከ ከ ከ ዝ ከ ከ ከ ዝ ከ 78%

ደረጃ ከፍተኛበ%

100% 100% 40% 86% 100% 100% 86% 43% 86% 83.3%

መፍቻ ከ፡- ከፍትኛ 1-2 ችግሮችና የማያሟላቸዉ ነጥቦች ካሉ ዝ፡- ዝቅተኛ ከሁለት በላይ ችግሮችና የማያ14ሟላቸዉ ነጥቦች ካሉ

14. የባለ ድርሻ አካላት ጥንተና

የአማራ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ፡፡ የወፍ ዋሻ የተፈጥሮና በአካባቢዉ የሚገኙ ሠዉሰራሽ ሰፋፊ ደኖች የሚጠበቁት በየአመቱ ከአማራ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በሚመደብ በጀት ነዉ፡፡ ነገር ግን የጥበቃዉን ሂደትና በአጠቃላይ ያሉ ችግሮችን በመፍታት የጥበቃ ስልቱን ለማሻሻልና የአካባቢዉ ህዝብ ከደኑ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የተደረገ ጥረት አይታይም፡፡ አንዲያዉም ከዞኑና ከወረዳዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች በክልሉ የደን ኤጀንሲ የተቋቋመ ስለሆነ በቅረብ ጊዜ መፍትሄ ያገኛል የሚል እነደሆነና በዞንና በወረዳ ያሉ የሚመለከታቸዉ አካላትም ይህን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም አሁን አየደረሱ ያሉ ችግሮችን ለማቃለልና የጥበቃ ስልቱን ለማጠናከር ከጣዉላ ቁጥጥር ዉጭ በደኑ ላይ የሚደረገዉ ጥበቃ እንዲጠናከር የሚደረገዉ ክትትል አናሳ ነዉ፡፡

የሰሜን ሸዋ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ፡ የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ጥብቅ ደን በሶስት ወረዳዎች የሚገኝና የክትትልና የቁጥጥር ስራዉ በተቀናጀ መልኩ እነዲካሄድና በዉስጡ የሚገኘዉ ብዝሃ ህይወት እንዲጠበቅ የማስተባባርና የመከታታል ሃላፊነት ያለበት ሲሆን በባለሙያና በበጀት እነዲሁም ያለዉን የጥበቃ ሃል ማስተባባርና ወቅታዊ ክትትል ባለማድረግ በርካታ ስራዎች ተጓተዉና ፍጻሜ ሳያገኙ በመየቆየታቸዉ ደኑ ትኩረት ያነሰዉ እነደሆነ ነዋሪዎችም ሆኑ የትበቃ ሰራተኞች ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ በህገወጦች ላይ የሚደረገዉ ክትትልና ለህብረተሰቡ የሚሰጠዉ ትምህርት መቀነስ አብይ ምክንያቱ በዞን ደረጃ ያለዉ ክትተል አናሳ መሆን እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ የደኑ የጥበቃ ሁኔታና በዉስጡ ያለዉ ብዝሃ ህይወት ላይ እየደረሱ ያሉ አሉታዊ ጫናዎችና ህብረተሰቡ ደኑን በምን ደረጃ እየተጠቀመበትና ከጥበቃ ሰራተኞች ጋር ያለዉ ግንኙነት በመረጃ ተደግፎ የተቀመጠ ሰነድ የለም፡፡ ስለዚህ በየትኛዉም ጊዜ ለሚመጣ አጥኝና ደኑን ለሚጎበኝ ድጋፍ ከመስጠት ያለፈ የተደራጀ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሕገወጥ ተግባራትንና የጥበቃ ስራዉን በወቅቱ የመቆጣጠርና እንክብካቤ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ማለት አይቻልም፡፡

Page 40: Wof Washa Field Study Final Draft

የሰሜን ሸዋ የአካባቢ ጥበቃ፤መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያና የየወረዳዎቹ ጽ/ቤቶች፤የበወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን በትብቅ ደንነት ከተከለለ በርካታ አመታት የተቆጠሩ ስለሆነና የትበቃ ሰረሰተኞች ስላሉት በባለቤትነት ይገባኛል ክርክር ባይኖርም መምሪያዉም ሆነ ጽ/ቤቶች ጠንካራ ቁጥጥር መታረስ የሌለባቸዉና ባለቤተነት በሌላቸዉ በጣም ዳገታማና መታረስ የማይገባቸዉ መሬቶች በህገዎጥነት ታርሰዋል፡፡ ለሚቀርበዉ ጥያቄ ይዦታ መሬታቸዉ እነደሆነ ከመናገር ዉጭ የሚቀርብ ማስረጃ የለም፡፡ እነዚህ ድርጊቶች መነሻቸዉ በመሬት አስተዳዳርና አካባቢ ጥበቃ የሚደረገዉን የባላቤትነትና የቁጥጥር ስራ አናሳ መሆን ነዉ፡፡በዚህም በተለይ በዋኘዛበረት፡ በወፍ ዋሻ፤በዉቲ፤ በአስታከል፤ በርቦማር፤ በዘንቦ፤ በእምመረት፤ ፍቅሬ ግንብ፤ በመሀል ወንዝ፤በቀይት፤በአባሞቴና ጉዶ በረት በደኑ አዋሳኝ ባሉ ጎጦች በህገወጥ መንገድ የታረሱ ዳገታማ የደን መሬቶች በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ የአካባቢዉን ብዝሃ ህይወትም ሆነ ስነምህዳር ለመጠበቅ ህገዎጥ የመሬት ይዞታ ከመለየትና ከመቆጣጠር ጀምሮ ደን ለአካባቢ ጥበቃ ያለዉን አስተዋጾ በማጉላት አሰፈላጊዉን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡

የሰሜን ሸዋ አስተዳዳር፡ የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ጥብቅ ደን በዞኑ አስተዳዳር ክልል ዉስጥ በመሆኑ ማንኛዉንም አስተዳዳራዊ ሂደትና የደኑ ጥበቃና ቁጥጥሩ በምን ሁኔታና ደረጃ እንዳለ በሶስቱም ወረዳዎች ያለዉን እንቅስቃሴ መከታታልና ሥራዎች በተፈቀደዉ ሁኔታ መከናወናቸዉን በመከታተተል አስፈላጊዉን ድጋፍ ማድረግ ለችግሮች ከሚመለከታቸዉ የበላይና ከፈጻሚ አካላት ጋር በመሆን በወቅቱ እንዲፈቱ መደረግ አለበት፡፡ በዚህ እረገድ በአስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉት ስራዎች በተፈለገዉ ደረጃ አለመሆኑን በመስክ ጥናቱ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የሶስቱም ወረዳዎች ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤቶችና የደኑ ጥበቃ ሰራተኞች ያላቸዉ ቅንጅትና ቁጥጥር የላላ መሆን መስተዳዳሩ የሰጠዉ ትኩረት አናሳ መሆኑን አመላካች ነዉ፡፡ በደኑ ጥበቃና ቁጥጥር ድርሻ ያላቸዉ የፖሊስ፡ ፍርድ ቤቶችና የቀበሌ መስተዳዳር የተፈጥሮ ሃብቱ ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ ለጥበቃ ሰራተኞች ብቻ የተተወ ይመስላል፡፡ በዚህ ረገድ የጥበቃ ሰራተኞችም ሁለንተናዊ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር ሰለማይደረግባቸዉና ተመጣጣኝ ደመወዝ ስለማይከፈላቸዉ በተለያዩ የግል ስራዎች በመጠመድ በስራቸዉ ላይ ያደረሱት ተጽእኖ ተገምግሞ ዉሳኔ የተሰጠበት ሁኔታ አይታይም፡፡ ከደኑ ጽ/ቤት በተገኘዉ መረጃ ቀደም ሲል በነበረዉ አጠባባቅ ከፍተኛ የሆነ ክትትልና እያንዳነዱ የጥበቃ ሰራተኛ ክትትልና አስፈላጊዉ ደጋፍ ይደረግለት አንደነበርና የህግ አፈጻጸሙም የተሻለ እንደነበርያመላክታል፡፡

ባሶና ወራና፤ የአንኮበርና የጣርማ በር ወረዳዎች ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤቶች፡- በቀጥታ የደኑንሁኔታና የጥበቃ ሰራተኞችን የእለት ከእለት እነቅስቃሴ የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ ናቸዉ፡፡ በዚህምደኑ በምን ሁኔታ መጠበቅ እንዳለበትና እየደረሱ ያሉ አሉታዊ ተጽእኖዎችን በመከታተልናበመቆጣጠር ዉሳኔ እነዲያገኝ ያደርጋሉ፡፡ አንዱ ወረዳ ከሌላዉ ጋር በመቀናጀትና በመመካካርችግሮችን ለመቅረፍ የተደረገዉ ጥረት አናሳ ነዉ፡፡ የጥበቃ ሰራተኞች ደመወዝ አንስተኛ ከመሆኑባሻገር ትጥቅና አልባሳት በጣም ጥቂት ለሆኑና ለቋሚ ዘበኞች ብቻ የሚሠጥ ሆኖ አፈጻጸሙ ከወረዳወረዳ ይለያያል፡፡ በወረዳ ደረጃ ልምድ ያላቸዉ ባላሙያዎች አለመኖርና በመስክ ከሚገኘዉ መረጃዉጭ በቢሮ የተጠናከረ አለመሆን፡፡ በጠጨማሪም በደኑ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች የብዝሃ ህይዎትጠቀሜታ ሳይሆን ከደኑ በልማዳዊ መንገድ ሊያገኙት የሚገባቸዉን እንደፈለጉ ሲተቀሙ ይታያል፡፡ዘለቄታዊና የደኑን ደህንነት የሚያስጠብቅ ሥልት መጠቀም የሚችሉበት የምክክርና ዉይይትመድረክ አለመኖሩን ነዋሪዎች ስለደኑ ካላቸዉ አመለካከት ለመረዳት ተችሏል፡፡

ሱናርማ /SUNARMA/ዘላቂ የተፈጥሮ ሃበት አያያዝ ማህበር፡- ሱናርማ በወፍ ዋሻ አካባቢከማህበረሰቡ ጋር የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራት ደኑ በህብረተሰቡ የሚደርስበትን ጫናለመቀነስ የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ነዉ፡፡ ማህበሩ በተለያዩ የተፈጥሮ ሃብት

Page 41: Wof Washa Field Study Final Draft

እንክብካቤዎች በማተኮር ለሶስቱም ወረዳዎች የተፈጥሮ ሃብት ዘርፎችና በቀጥታ ለህብረተሰቡ ድጋፍበማድረግ የደኑን ደህንነት ዘላቂ ለማድረግ ይሰራል፡፡ በ2002 እና በ2005 የደኑን ሃብትና ያሉትንችግሮች በማጥናት ስራዉን የጀመረ ሲሆን በተገቢዉ ሁኔታ ድጋፍ ለመስጠት ካለዉ አላማ አኳያለማሳካት ባለበት የሰዉ ሀይልና ከአቀረበዉ በጀት አኳያ ለግብ ሊደረስ ይችላል ብሎ ለመገመትያስቸግራል፡፡ አብዛኛዎቹ ስራዎች በማህበሩ የሚሩ በመሆናቸዉ ዘለቄታ ባለዉ መልኩ በጋራም ሆነተረክቦ አየሰራባቸዉ ያሉ ችግኝ ጣቢያዎች የተፈለገዉን ያህል አገልግሎት ይሠጣሉ ብሎ መገመትያዳግታል፡፡ አብዛናዎቹን ስራዎች ከተደራጁና በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበሩ ችግኝ ጣቢያዎችንተረክቦ እየሰራ በመሆኑ በዘላቂነት ሊቆየ ይችላል ብሎመገመት ያስቸግራል፡፡ በዚህ ረገድ ማህበሩየችግኝ ጣቢያዎቹንም ሆነ ሌሎች የተፈጥሮ ሃብት ስራዎች ክፍተት እያየ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስድጋፍ ቢያደርግ የተሸለ እንደሚሆን የመስኩ ጥናት ያመላክታል፡፡ በአጠቃላይ ለደኑ ልማትናለማህበረሰቡ ጥቅም አስቦ የድርሻን ለመወጣት ማህበሩን ብቸኛና ተቀባይነት ያለዉ አካሄድ እንደሆነበአረእያነቱ የሚጠቀስ ነዉ፡፡

የ15 ቱም ቀበሌ አስተዳደር ፤- የዎፍ ዋሻ ደን በተፈጥሮ ጥብቅ ደንነት ተከልሎ ለበርካታ አመታት እንዳለ ቢያዉቁም በሁሉም ቀበሌዎች የደኑን ደንበር ገፍቶ ቤት መስራት፤ማረስ (በገደልና በወንዝ ካልተከለለ በሰተቀር) አደን፤ ለጣዉላና ለግነባታ ደኑ ሲመነጠር አስፈላጊዉን ክተትልና ቁጥጥር አለማድረግ ይታያል፡፡ አልፎ አልፎ የጥበቃ ስራቸዉን ባልተወጡ ዘበኞችና ህገዎጦች ያለዉ ቁጥጥርና ክትትል አናሳ ነዉ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ሊታረሱ የማይገባቸዉ ቦታዎች ታርሰዉ ሲገኙ እንኳን ለመከላከል የታየዉ ጥረት ይህ ነዉ ማለት አይቻልም፡፡ በተጨማሪም በአመራር ላይ ሁነዉ እንኳን በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተዉ ሀለፊነታቸዉን ያልተወጡ እንዳሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

የአካባቢዉ ማህበረሰብ፡- በወፍ ዋሻ አካባቢ 3 ማህበረሰቦች (አማራ፤ አፋርና አርጎባ) የሚኞሩ ሲሆን በቆላማዉ አካባቢ የሚኖሩ ደኑ ላይ ያላቸዉ ጫና አንስተኛ ቢሆንም ወደ ደኑ ዘልቆ በመግባት እነደሚያድኑ የጥበቃ ሰራተኞች በምሬት ይናገራሉ፡፡

ነገር ግን በጥናቱ ወቅት በደኑ ዉስጥ ለአደን ጥይት የተተኮሰ ቢሆንም ከየተኛዉ አካባቢ የመጡ እንደሆነ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ማህበረሰቡ ደኑ ለብዙ ዘመናት በደንነት ተጠብቆ የቆየ መሆኑን ሰለሚያዉቁ በባለቤትንትም ሆነ የደኑን ልማት በመጥላት ለማጥፋት የተደረገ የጅምላ ደን ጭፍጨፋ ባይኖርም ካለዉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አኳያ ጣዉላ ለሚያመርቱ በምንጠራና ለግንባታ እነዲሁም ለማገዶ ሊጠፉ የተቃረቡትን ዝግባ፤ የአበሻ ጽድና ኮሶ ዛፎችን በመመንጠር የሚተባበሩ በርካታ ናቸዉ፡፡ በተለይ ከሰዉ ሰራሽ ደኑ ይልቅ ለአገር በቀል ዛፎች ጥኩረት ስለማይሰጡ በረካታ ዛፎችያላገባብ ተቆርጠዉና ተመንጥረዉ ይታያሉ፡፡ በሌላ በኩል የደኑን ስብጥር አለመጠበቃቸዉናበተቆራረጠ መሬት መሆናቸዉ እንጂ በባሶና ወራና በኩል በጎሽ ሜዳ፤ ጥቁሪት ባዶና ዠኖበረትአካባቢ የተፈጥሮ ገጽታቸዉን የተጠበቁ የጓሳና ጅብራ ዛፎች ያሉባቸዉ ሰፋፊ ቦታዎች ይገናሉ፡፡በአንፃሩ የአስታና ሌሎች ዛፎች ለጓሳዉ ማደግ ሲባል መመንጠራቸዉ የብዝሃ ህይዎትባለቤትነታቸዉን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ አሰራሩ ፍትሃዊና ህጋዊ አለመሆኑና በደኑ ላይ ጫናመፍጠሩ እንጂ ከዋናዉ ደን ለጣዉላ ንግድ፤በደጋዉ በጓሳ ሳርና በሁሉም አካባቢዎች በልቅ ግጦሽምክንት የደኑን የተፈጥሮ ይዘት እየተዛባ ያለዉ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ በዚህም ለደኑም ሆነለህብረተሰቡ ፍትሃዊ ባልሆነ መልኩ እየሰጠ ያለዉ ጠቀሜታ የተፈጥሮ ገጽታዉን እድሜ በእጅጉይቀንሰዋል፡፡

Page 42: Wof Washa Field Study Final Draft

ፎቶ 31 በዠኖ በር አካባቢ አስታዉ የጓሳዉን እድገት ያስቀራል በሚል በከፍተኛ ደረጃ ይመነጠራል

15. የወፍ ዋሻታሳቢጥብቅ ስፍራ የመሆን ዓላማ

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ጥብቅ ስፍራ የመሆን አቅም ባለዉ የተፈጥሮ አቀማማጥ፤ ብዝሃህይዎትና የሚሠጠዉ ጠቀሜታ የተገለጸ ቢሆንም በጥናቱ እንደተረጋገጠዉ ወሳኙ ያሉትን ችግሮችበመቅረፍና የተፈጥሮ ሃብቱ ወደ ነበረበት የመመለስ ጥረት ላይ የወደቀ ነዉ፡፡ ለዚህም ሑሉምአጋር አካላት የየድርሻቸዉን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ከሆነ የዎፍ ዋሻ ጥብቅ ስፍራ በመሆንየሚከተሉትን አላማዎች የሚያሳካ ይሆናል፤፡

የወፍ ዋሻ በጥብቅ ስፍራነት መቋቋም ዋና አላማ ለብዝሃ ህይወት ጥበቃ፡ ባለው ስርዓተ-ምህዳር ውስጥ የብዝሃ ህይወት ሃብትን የዘቦታ

ልማትና ጥበቃ ለማካሄድ የሚያስችል የዕጽዋትና እንሰሳት ስብጥርን በማጥናት፤በማልማትናበመጠበቅ ለተተኪ ትዉልደ ለማሰተላላፍ፡፡

ማራኪ የመሬት አቀማመጥንና ተፈጥሮአዊ ገፅታን ለመጠቀምና ለማቆየት፡-ተፈጥሮአዊናማረኪ የሆነዉን የመሬት አቀማመጥ ለሰዉ ልጆች አእምሮ ማደሻ በማድረግ የመዝናኛእድሎችን መፍጠርና በተፈጠሮአዊ ገፅታዉ በማቆየት በዚህ ሁኔታ በዉስጡ ያሉትንተፈጥሮአዊ ሃብቶች በዘለቄታ ቱሪዝምና በጠመጣጣኝ አጠቃቀም ጥቅም ላይ ለማዋል፡፡

ለትምህርትና ምርምር፡- ብዝሃ ሕይወትንና ተፈጥሮአዊ አካባቢዎችን የትምህርትና የምርምርማእከል በማድረግ በዘርፉ የሚጠበቀዉን ሳይነሳዊ እድገት ለማመጣትና አግባብ ባለዉመንገድ ለማልማትና ለመጠቀም፡፡

Page 43: Wof Washa Field Study Final Draft

በዘላቂ ቱሪዝም ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማስፋፋት፡ የተፈጥሮ መዝናናዎችን በማስፋፋትነበኢኮቱሪዘም በመደራጀት ለጎብኝዎች በሚሠጥ አገልግሎት የንዋሪዉን ህዝብ ኑሮ ማሻሻልናመሰረተ ልመቶችን ለማሳደግ፤፤ በዚህም ዋነኛ የገቢ ምንጭ በመሆን በኢኮኖሚዉ እድገትሚና እነዲሩ ለማድረግ

16. በጥናቱ ወቅት ያጋጠሙችግሮች

በመሬቱ አቀማመጥና ቅርፅ የተነሳ ለበርካታ ጊዜአት በደኑ ወጭና ዉስጥ በእግር መጓዝ በቂ የመስክ ልብስ፤ ጫማ ፣ድንኳን ፣ ምግብና መጓጓዣ አለመኖር የዝናብ ወቅት በመሆኑ በጭጋግና ጉም አካባቢዉን በሚገባ ለመመልከት አስቸጋሪ መሆን በሚደርስባቸዉ ጫና ምክንያት የዱር እንሰሳት በቀላሉ አለመታየት ወይም በተወሰነ አካባቢ

መሰባሰብ ሊኖር የሚችለዉን ብዛት ለመወሰን መቸገር፡፡

17. ለወደፊትመከናወን ያለባቸው ስራዎች

የወፍ ዋሻን ደን በተፈጥሮ ይዞታዉ ለማቆየትና አግባብ ባለዉ መልኩ ለመጠቀም ባለድርሻ አካላትየሚጠበቅባቸዉን በተፈለገዉ ጊዜና ሁኔታ ማከናዎን ይኖረባቸዋል፡፡ ስለዚህ በጥናቱ ወሳኝ ናቸዉተብለዉ የተመረጡትን ባለድረሻ አካላት ሃለፊነት ለማስቀመጥ ተሞክሯል፤፡

በክልሉ ባህል፤ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ፡- በቢሮ ለስራዉ ቀጥተና ተጠሪነጥ ያለዉ የዱር እንሰሳት ጥናት፤ ልማት፤ ጥበቃና አጠቃቀም የስራ ሂደት የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን አለበት ፡፡ የዚህን ጥናት ዉጤት ለቢሮዉ በማቅረብ ዝርዝር ዉቱን በማሳዎቅ በማጠቃለያ ሃሳቦቹ

መግባባት ላይ መድረስና ጥናቱን ለሚመለከታቸዉ አካላት መላክና አስተያየት መቀበል፡፡ ዝርዝር የዱር እጽዋትና እንስሳት ስርጭት፤ በዱር ሀብቶቹና በአካባቢው ማህበረሰብ ያለውን

ትስስር መለየትና ሊጠበቁ የሚችሉትነ ሃብቶችና ተያያዥ ችግሮችን በመለየት ሊጠበቅ የሚችልበትን ስልት ማሳወቅ፡፡

የጥናቱን ዉጤት መሰረት በማድረግ አካባቢው ለተፈጥሮ ጥብቅ ስፍራነት ባለውን ጠቀሜታ ተስማሚዉን የጥብቅ ስፍራ ደረጃ መስጠትና ቀጣይ ስራዎችን በፍጥነት ማከናወን፡፡

በጥናቱ የተገኙትን ማጠቃለያዎች መነሻ በማድረግ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጠቀሜታዎችናለቱሪዝም ያለውን አስተዋጾ በማረጋገጥ መከለልና ደንበሩ በህግ እነዲወሰን ጥረት ማድረግ፡፡

በሚስማማዉ ጥብቅ ስፍራነት የሚከለል ከሆነ የመሠረተ ልማትና ግንባታ ቦታዎች መለየትና በጥብቅ ስፍራነት ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ የዳሰሳ ጥናቱን መረጃዎች ለሚመለከተው ለውሣኔ ማቅረብና ሕጋዊ ሰውነት ማሰጠት፡፡

ለጥናት ፣ ለክለላና ሕጋዊ እውቅና ለማሠጠት ለሚደረጉ ጥረቶች አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት የገንዘብ ድጋፍ ማፈላለግ፡፡

በተለያዩ የጥናት፣ የክለላና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች የሚመለከታቸው አጋር አካላት ማሣተፍና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማድረግ ዘላቂ አጋርነታቸውን ለማረጋገጥ ወቅታዊ ግንኙነትና ተግባረዊ እንቅስቄሴ በማድረግ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

በክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ፡ ሠፋፊ የመንግስት ደኖችን የመቆጣጠርና የመከታተል ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በስሩ በተቋቋመዉ የደን ኤጀንሲ ዘላቂ በሆነ ጥበቃና ጥቅም በሚሰጥበት የጥበቃስልት እነዲጠበቅ አስፈላጊዉን ጥረት ማድረገ ይገባዋል፡፡ በዚህም በየደረጃዉ የሚገኙ አስፈጻሚናፈጻሚ አካላት አስፍላጊዉን ትብብር እንዲያደርጉ ዉሳኔ ላይ መድረስና ለተፈጻሚነቱ ክትትል

Page 44: Wof Washa Field Study Final Draft

ማድረግ ይገባዋል፡፡ አሁን ያለዉን የጥበቃ ሁኔታ መሻሻልና የጥበቃ ሰራተኞች ሁሉንም አይነትደንን የሚያጠፋ ድርጊትን ሊቆጣጠሩ የሚችሉበትን አቅም መፍጠርና ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም ምላሽመሰጠት አለበት፡፡ በሌላ በኩል በአካባቢዉ በርካታ ሰዉ ሰራሽ ደኖች ያሉ ሲሆን እነዚህን አግባብያለዉ የአጠቃቀም ስልት በመንደፍና የተጎዱትን በማልማት ህብረተሰቡ ከጠፈጥሮ ደኑ ሲያገኝየነበረዉን ጥቅም በመተካት በአገባብ ባለዉና ፍትሃዊ በሆነ አማራጭ መንገድ በማቅረብ በተፈጥሮደኑ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና መቀነስ ያስችላል፡፡

የዞንና የወረዳ አካባቢ ጥበቃ፤ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፡- አብዛናዎቹ በደኑ ጥግ ያሉ የእርሻመሬቶች ሕገወጥ እንደሆኑ ነዋሪዎችም ሆነ የጥበቃ ሰራተኞች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ በደኑ ዙሪያምሆነ በዉስጥ የተያዙ ህገወጥም ሆነ ሕጋዊ የሆኑ መሬቶችን ለይቶ መመዝገብና የማይታረስ ወይም ያልተሠጠ መሬትን እንዳያርሱ መከልከል ይገባል፡፡ ለዚህም የቀበሌ አመራር ከፍተኛዉን ሚናየሚጫወቱ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የደኑን ስፋትና ሽፋን መለየትና ካርታ ማንሳት ስራዎችንሊያፋጥንና የደንበር ዉዝግቦችን ማቃለል ከመቻሉም በላይ አዲስ ደንበር ገፍቶ የሚያርስ እነዳይኖርጥረት መደረግ አለበት፡፡ በሌላ በኩል የወል መሬቶቹን የእጽዋት ሽፋን በማሻሻል የአጠቃቀም ስርአትእነዲሆን ማድረግና ዘላቂነቱን ማረጋገጥ፡፡ የሚወሰነዉ ዘላቂ የጥበቃ ስልት ተግባራዊ እነዲሆንናየህግ ማቀፍ እነዲኖረዉ አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ፡፡

በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በግ/ገ/ል/ጽ/ቤቶች ባለሙያዎችና በአስተዳድር አካላት መከናወን ያለባቸውለ-፡-የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳት መኖሪያ ከሶስት ወረዳዎች የሚገኝና የ15 የገጠር ቀበሌዎች አካል ነዉ፡፡ የእነዚህ ቀበሌዎች የአካባቢው ነዋሪዎች የግብርና ባለሙያዎችና የመስተዳድር አካላትን ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ የአካባቢው እየተካሄደ ያለውን አደን ፣ የሕገወጥ እርሻ መስፋፋት ፣ የደን ምንጠራ ፣ ከሰል ማምረትና ፍትሃዊ ያልሆነ የመሬት አጠቃቀምን ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ህብረተሰቡ የተፈጥሮ ደኑና የዱር እንስሳቱ ባለቤት በመሆኑ ለትዉልድ የማስተላላፍ ግዴታም አለ፡፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ ወረዳ የሚገኙቀበሌዎችና የወረዳ አስተዳድር አካላት የሚመለከታቸውን አጋር አካላት በማስተባበር በበላይ አካል ውሳኔ አግኝቶ ለሚፈለገው አገልግሎት እስኪውል ድረስ አስፈላጊውን ጥበቃና እንክብካቤ የማድረግ ኃላፊነነት አለባቸው፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ወረዳ መከናወን ያለባቸው ቀዳሚ ተግባራት የሚከተሉት ናቸዉ፡- ከፍተኛ የሆነ የዱር እንስሳት አደንን ለመከላከል የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተማር መከለል

የሚቻልባቸውን በጋራ በመወሰን ነዋሪው ሕዝብ ለዱር እንስሳት ጥበቃ አስተዋጾ እንዲያበረክት ማበረታታት፡፡

በአካባቢው እየተስፋፋ የመጣውን ሕገወጥ እርሻ መከለልና ሕጋዊ ሊሆኑ የሚችሉትን ከተፈጥሮ ደኑና የዱር እንስሳት አኗኗር ጋር በማይቃረን መልኩ ሕጋዊ እውቅና በመስጠት ኃላፊነት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

በባሶና ወረባ ወረዳ በተለይም በደጋው አካባቢው የሚደረግ የዱር እጽዋትና እንስሳት መኖሪያየሚሆን ክልክል መጠበቅና የጓሳ እንክብካቤ አበረታችና በአካባቢው ነዋሪዎችም የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ ይህንኑ አሠራር በሌሎች ቀበሌዎች ማሠራጨትና ክትትል በማድረግ እንዲለመድ ቢደረግ፡፡

በየወረዳው የሚገኙ የተፈጥሮ ደኖችና በውስጣቸው የሚኖሩ የዱር እንስሳት ሁኔታና ያሉበት ደረጃ በየጊዜው በተጠናከረ የደን ግብረኃይል እየተገመገመ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ፡፡

Page 45: Wof Washa Field Study Final Draft

በደኑ ውስጥና በገደላገደሉ ስር በርካታ ሕገወጥ ቁርጥራጭ የእርሻ መሬቶች በመከታተልና በመቆጣጠር ህገወት እርሻ እነዳይካሄድ ጥረት ማድረግ፡፡ የአካባቢውን ደህንነት በመጠበቅና ጥቅም ላይ የሚውልበት ስልት በበላይ አካል እስኪወሰን በየቦታዉ የተቆራረጡ በተፈጥሮ ደን ገጽታቸው እንዳለ መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡

በደኑ ውስጥ አደን፡ ሕገወጥ የእርሻ ስራ፣ ጣዉላ በማምረት፣ ደን ቃጠሎና ምንጠራ የሚያካሂዱትን ግለሰቦች በመከታተልና ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ፡፡

የወፍ ዋሻ ሰፊ የዱር እጽዋትና እንስሳት ሽፋን የላቸው ቀበሌዎችና በርካታ ንዑስ ቀበሌዎች የሚያዋስኑት በመሆኑ የቀበሌ አስተዳደሮች ለተፈጥሮ ሃብቱ ጥበቃ ያላቸው ኃለፊነት ሰፋ ያለ መሆኑን ተገንዝበው አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የቀበሌ አስተዳዳርና የደን ዘበኞች ቅንጅተ በመፍጠር በአካባበው አደን ፣ ህገወጥ የእርሻ ስራና የደን ደንበር ገፍቶ ማረስ የመከላከል ቅንጅታዊ የሆነ አሠራር በመፍጠር ደኑንና የዱር እንስሳቱን መጠበቅና መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

16. ማጠቃለያ

የወፍ ዋሻ በዚህ ፈጣን የስነምህዳር ዳሰሳ ጥናት ከማራኪ መልካ ምድረዊ አቀማመጥ (ጎሽ ሜዳ፤ቁንዲ፤ አባሞቴ፤ጥቁሪት ባዶ፤ዠኖ በር፤ገማሳ ገደል፤ፍቅሬ ግንብ፤ መሃል ወንዝ፤ ዉቲና እመምረት) ባሻገር የዱር እንሰሳት (ጉሬዛ፤ ጭላዳ ዝንጀሮ፤ ሚኒሊክ ድኩላና ሰሳ እንዲሁም የተለያዩ አዕዋፍ ያሉት ሲሆን በርካታ የዛፍ (የአበሻ ጽድ፣ዝግባ፤ ኮሶ፤ ምሳር ገንፎና ወይራ)በብዛት መኖራቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የወፍ ዋሻ የተለያየ ስነምህዳር ያለውና በመጥፋት ላይ ያሉ፣ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውና በቂ መረጃ የሌላቸው የዱር እንስሳትና እጽዋት የያዘ ነው፡፡ ካለው የተፈጥሮ ገጽታው ጋር ተዳምሮ ከ6ሺ እስከ 8ሺ ሄክታር ጥብቅ ስፍራ ሊሆን የሚችል ለብዝሃ ህይወት ጥበቃ፤ ለሳይንሣዊምርምር ፣ ለመንፈሳዊ፤ ለትምህርታዊና ለመዝናኛ ሊሆን የሚችል አቅም ያለው የቱሪዝም መስሕብ ቦታ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታው የወፍ ዋሻ ከተጠበቀና አሉታዊ ጫና ከተቀነሰ የብሄራዊ ፓርክነት መስፈርትን ያሟላል፡፡ አለያም በመጥፋት ላይ ላሉ የዱር አጽዋትና እንሰሳት መጠበቂያ ሳንክቿሪ ሊሆን ይችላል፡፡ የወፍ ዋሻ ደን በአሁኑ ሰአት በመረጣ ምንጠራ የተጎዳ ቢሆንም ከ89% በላይ በተፈጥሮ ገፅታው በመሆኑ በቀጣይ ዝርዝር ጥናትና የደንበር ክለላ ተካሂዶ ሕጋዊ እውቅና ለማሰጠት የሚያስችሉ ስራዎች በአጭር ጊዜ ሊከናወኑ ይገባል፡፡

የወፍ ዋሻ ማረኪና ወጣገባ የተፈጥሮ ገጽታና አገር በቀል የሆኑ አፅዋትና የዱር እንሰሳት አለዉ፡፡ በዉስጡ መንደርም ሆነ ሰብል የማይመረትበት የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በተፈጥሮ አካባቢያቸው የሚገኙበት ቦታ ነው፡፡ ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች የተቆራረጡና በደን የተሸፈኑ ቦታዎች ከመኖራቸዉ ባሻገር በዋናዉ ደን ዉስጥ ሳይቀር ጣዉላ አምራቾች፤ አዳኞች፤ ደን መንጣሪዎችና ደንበር ገፍተዉ በሚያርሱ በውስጡ የሚገኘዉ የተፈጥሮ ሃብት እየተጎዳ ይገኛል፡፡

የወፍ ዋሻ የተፈጥሮ ደን ለቱሪዝምና ለሌሎች መሠረተ ልማቶች አይነትና ግንባታ በመለየትና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ለተገቢው ጥብቅ ስፍራ እንዲውል ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጥናት የወፍ ዋሻ ጥብቅ ስፍራነት በቱሪዝምና በተጓዳኝ አገልግሎቶች ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር በሌላ የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ያለው ጠቀሜታ ከመሬቱ ወጣገባነት ፣ ድንጋያማና ገደላገደል ከመሆኑ አንጻር ሲታይ የጐላ ጠቀሜታ የለውም፡፡ ሆኖም ብርቅና በተፈጥሮ

Page 46: Wof Washa Field Study Final Draft

አድገታቸዉ የሚሰገረሙና ከስነምህደሩ በተለየ ሁነታ ያደጉ ዣፎችና ተወዳጅ የሆኑ የዱር እንሰሳት በከፍተኛ ጉዳት ላይ ቢሆኑም ከተጠበቁ በአጭር ጊዜ በበቂ እድገትና ቁጥር ልናገኛቸዉ እንችላለን፡፡ በተጨማሪም በዱር እንስሳቱ አያዝ፤ አጠባበቅና በመኖሪያ አካባቢያቸው ስርጭትና አኗኗር ዝርዝር ጥናት ያስፈልጋል፡፡

የጥበቃ ሰራተኞችንና ለደኑ ጥበቃ አስተዋጾ ይኖራቸዋል የሚባሉ አጋር አካላትን በማስተባበርና ሃላፊነት በመስጠት በተፈጥሮ ደኑና በዱር እንስሳቱ ላይ የሚደርሰውን ለጣዉላ ምርት ጭፍጨፋ፤ የአደን፣ ልቅ ግጦሽና በሰዎች ዝውውር የመረበሽ አሉታዊ ጽዕኖዎችን መቀነስ ወይም ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ይቻላል፡፡ ለዚህም በሶስቱም ወረዳ የተፈጥሮ ሃበት ባለሙያዎችና የጥበቃ ሰራተኞች በተቀናጀ መልኩ ሊሰሩ ይገባል፡፡ ከወረዳዎችና ከቀበሌ እንዲሁም ከፍርድቤቶችና ከፖሊስ ጋር ተባብሮ መስራትንና የአካባቢዉን ህብረተሰብ በጉዳዩ ባለቤት እንዲሆንና አላማዉን እንዲረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የአካባበዉ ማህበረሰብ ማደን፤ ልቅ ግጦሽንና እርጥብ ዛፎችነ በመቁረጥ፤ በመላትና በመከርከር ደኑን መጨፍጨፍ የለበትም፡፡ በጥናቱ እንደተረጋገተዉ ከደኑ ህብረተሰቡ በብዛት የሚጠቀመዉ በልቅ ግጦሽ፤ ለማገዶና ለግነባታ እንጨት በመቁረጥ ነዉ፡፡ በልቅ ግጦሽ በኩል የቤት እንሰሳቱ ሊሰማሩባቸዉ የሚችሉ ከደኑ ዉጭ ያሉ የወል መሬቶችን በአግባቡ ፍትሃዊ በሆነ መልኩመጠበቅና መጠቀም፡፡ በደኑ ዉስጥ ማሰማራት የሚያስገድደዱ ሁኔታዎች የሚፈጠሩ ከሆነየዱር እንሰሳት መራቢያና ማደሪያ የሆኑ ቦታዎችን በጥናት በመለየት በሌሎች አካባቢዎችቢሰማሩ ደኑ በአብዛኛዉ በትላላቅ ዛፎች የተሸፈነ በመሆኑ በግጦሽ ምክንያት የሚደርሰዉ ጫናየከፋ ጉዳት ላያደርስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በደኑ ዉስጥ በረት መበረት፤ በጥበቃ ስም የደንምንጠራ ማካሄድና የዱር እንሰሳትን ማባረርና ለህገወጥ ጣዉላ አምራቾች መጠለያ መስጠትአያስፈልግም፡፡ ለማገዶና ለግንባታ የሚሆን ደረቅና የራሳቸዉ እድገት በመጨረስ የወደቁትንዛፎች በመልቀም በተወሰኑ አካባቢዎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ነገር ግን ለጣዉላ ምርትና ለግንባታአገር በቀል ዛፎችን መጠቀም በራሳቸዉ ማሳ ያሉና ያሳደጓቸዉ ከሆነ ነዉ፡፡ ቀደም ሲል ያደጉናሥነምህደር ጠብቀዉ ያሉትን መመጠርና መጠቀም ቅርስን ለትዉልድ አናስተላልፍም በሚልሓላፊነትን መርሳት ነዉ፡፡ ስለዚህ ለማገዶና ለግንባታ በአካባቢዉ በርካታ የሠዉ ሰራሽ ደኖችስላሉ እነሱን በበለጠ በማልማትና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም የግባታና የማገዶ ፍጆታንመደጎም የሚቻልበት ሁኔታ ማመቻቸትና ህብረተሰቡም ደንን በማሰፋፋት የተጎዱ መሬቶችንመንከባከብና በደን መሸፈን ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ፍትሃዊ በሆነና ሃላፊነት ባለዉ መልኩከተከናወኑ ደኑ በተፈለገዉ ጥብቅ ስፍራነት ሊዉል የሚችልበትን ሁኔታ የሚያረጋግጡ ናቸዉ፡፡

በመጨረሻም የሠሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር፤ ግብርናና ገጠር ልማት፤ ባህልና ቱሪዘም የየወረዳዎችን መስሪቤቶችና የቀበሌ አስተዳደር በማሰተባባር ቅድመሁኔታዎችን ሊያመቻቹና ጥብቅ ስፍራ እንዲሆን አስፈላጊዉን ጥረት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ የክልሉ መንግስትም ሆነ ባህል፤ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ አስፈላጊውን የበጀት ፣ የባለሙያና የማቴሪያል ዝግጅት በማድረግ ቀጣይ ስራዎች ተከናውነው በተፈለገው የጥበቃ ደረጃ ተመድቦ አካባቢያዊ ፣ አገራዊና አለማቀፋዊ አስተዋጾ እንዲኖረው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የየወረዳዎቹ የሚመለከታቸው አካላትም የሚጠበቅባቸውን በወቅቱ ማከናዎን መከታተልና መቆጣጠር የሚችሉባቸው አማረጮች ሊቀመጡ ይገባል፡፡

Page 47: Wof Washa Field Study Final Draft

ዋቢመጽሃፍት

የአብክመ ዝክረ ሕግ 96/1996 /2003/ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፓርኮች ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ማቋሟሚያ አዋጅ፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ባህርዳር ኢትዮጵያ፤የአብክመ ፓርኮች ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን /2005/ የአላጥሽ ፓርክን ሕጋዊ እውቅና ለማሰጠት ለአብክመ ክልል ምክር ቤት የቀረበ ደጋፊ ሰነድ ባህርዳር ኢትዮጵያ፡፡

Azene Bekele Tesema . 2007. Useful Trees and Shrubs for Ethiopia: Identification, Propagation and Manage-ment for 17 agroclimatic zones. World Agroforestry Center, RELMA, ICRAF Eastern Africa Region, Nairobi, Kenya.Azene Bekele Tesema . 1993. Useful Trees and Shrubs For Ethiopia: Identification, Propagation and World Agroforestry Center, RELMA, ICRAF Eastern Africa Region, Nairobi, Kenya.Beinhard F. and Admassu Adi, 1994. Honeybee flora of Ethiopia. DED Weikersheim: Margraf Verlage, min-istry of Agriculture Germany and Ethiopia.EXNHS/1996/ Important Bird Area of Ethiopia! A first Inventory, Addis Ababa Ethiopia. FAO of UN/1984/ Vegetation and Natural region and their significance for land use planning: report paper for the government of Ethiopia, United Nations development program, technical report 4. AG: DP/ETH178/0031 Rome Italy.IUCN /1994/ The IUCN Guideline for protected area management categories.Kumera Wkjira and Zelalem Tefera (eds) /2005/ Wildlife Management. Parks Development and protection Authority: Compendium of notes on wildlife conservation and Management A training manual for park management and project experts, Bahirdar, Ethiopia.SUNARMA. 2005. Forest and lanad use management project ( Am(hara national Regional State, North Shewa) Forest Inventory Report (0 Deraft).

Page 48: Wof Washa Field Study Final Draft

ዕዝል 1. ዋና ዋና የእፅዋት ዝርያዎች

No Varnacular name Scientific Name 1 Gerar Acacia abyssinica2 Merenz Acokanthera schimperi3 Embes Allophylus abyssinicus4 Ret Aloe vera5 Dong Apodytes dimidiata6 Shembeko Arundo donax7 Yeset kest Asparagus africanus8 Zinkila Berberis hostii9 Yenebir tifir Bridelia micranath

10 Anfar Buddleja polystachya11 Zigta Calpurnia aurea12 Gumero Capparis tomentosa13 Agam carissa edulis14 Kahot Celtis africana15 Azo Hareg /Abeta/ Clematis simensis16 Misrch Clerodendrom myricoides17 Fiyelefegi Clutia abyssinica18 Avalo Combretum molle19 Wanza Cordia africana20 Bisana Croton macrostachyus21 Yehanj Tid Cupressus lusitanica22 Yemidr koso Deliphinium dasycaulon23 Ameraro Discopodium penninervum24 Keteketa Dodonaea viscosa25 wulkifa Dombeya torrida26 Koshim Dovyalis abyssinica27 Moata Dracaena steudneri28 Dendero Echinops giganteus29 Sembo/Lol Ekebergia capensis30 Enkoko Embelia schimperi31 Asta Erica arborea32 Korch Erythrina brucei33 Key Bahir Zaf Eucalyptus camaldulensis34 Nech Bahir Zaf Eucalyptus globulus35 Dedeho Euclea schimperi36 Guassa Festuca spp37 Shola Ficus sur38 Ashekit Gaium asparinides39 Yetota Kula Galiniera saxifraga40 Somaya Grewia bicolor

Page 49: Wof Washa Field Study Final Draft

41 Kosso Hagenia abyssinica42 Garda/Yewaliya Eshoh Helichrysum spp43 Amja Hypericum revolutum 44 Misar genfo Ilex mitis45 Tembele Jasminum abyssinicum46 Yehabesha Tid Juniperus procera47 Sensel Justicia schimperiana48 Andahula Kalanchoe petitiana49 Ashenda /Abelbila/ Kniphofia foliosa50 Kese Laggara tomentosa51 Jibera Lobelia rhynchopetalum 52 Tosign (yedur) Lotus discolor53 Kelewa Maesa lanceolata54 Shenet Myrica salicifolia55 Kechemo Myrsine africana56 Kumbel Mytenus arbutifolia57 Atat Mytenus ovatus58 Asquar Nuxia congesta59 Woyira Olea europaea60 Sigid weira Olea welwitschii61 Tefie Olinia rochetiana62 Keret Osyris quadripartita63 Woynagft Pentas schimperana64 Indod Phytolacca dodecandra65 Pinus Pinus patula66 Weyel Pittosporum abyssinicum67 Zegeba Podocarpus falcatus68 Yezinjero woniber Polyscias fulva69 Chocho Premna schimperi70 Tikure Inchet Prunus africanus71 Seged Psydrax schimperiana72 Gesho Rhamnus prinoides73 Wodel asfes Rhoicssus tridentata74 Tilem Rhus retinorrhoea75 Qammo Rhus vulgaris76 Kega Rosa abyssinica77 Enjory Rubus apetalus78 Tult Rumex nepalensis79 Embuaco Rumex nervusus80 Chifreg Sedum spp81 Nechilo Senra incana82 Yeshikoko gomen Solanecio gigas83 Embuay Solanum marginatum

Page 50: Wof Washa Field Study Final Draft

84 Tosign Thymus schimperi85 Lankuso Urera hypselodendron86 Sama Urtica simensis87 Inkoy Ximenia americaca

Page 51: Wof Washa Field Study Final Draft

ዕዝል 2 የእንሰሳት ዋና ዋና ዝርያዎች

No Vernacular name Common name Scientific name

1 Tera Kebero Common Jakal Canis aureus

2 Key Kebero Ethiopian wolf Canis simensis3 Dalega anbesa Caracal Caracal caracal4 Tota Vervet Monkey Cercopithecus aethiops5 Teregne African civet cat Civettictis civetta

6 Gureza Abyssinian black and white colobus Colombus abyssinicus7 Netebetab jib Spotted hyaena Crocuta crocuta

8 Faro Gent Genetta genetta

9 Jib Balmesmre Striped Hyaena Hyaena hyaena

10 Jart Porcupine Hystrix cristata

11 Aner Serval Cat Leptailurus serval

12 Yestark Tenchel Starck's Hare Lepus starckii13 Sesa klipspringer Oreotragus oreotragus

14 Neber Leopard Panthera pardus

15 Nech Zenjero Hamadryas baboon Papio hamadryas

16 Ydure asama Bush pig Potamochoerus porcus

17 Megoza/Kefodefi/ Retal (Honeybudger ) Procavia capensis

18 Shekoko Rock Hyiraxs Procavia capensis

19 Midaqua Grey duiker Sylvicapra grimmia

20 Chilada Zenjero Gelada baboon Theropithecus gelada

21 Dekula Common bushbuck Tragelaphus scriptus

22 Yeminilik Dekula Menelik’s bushbuck Tragelaphus scriptus meneliki

23 Filfel Common mole rat Cryptomys hottentotus

24 Ayit Rat Arvicanthis Spp

Page 52: Wof Washa Field Study Final Draft

ዕዝል 3 ዋና ዋና የአዕዋፍ ዝርያዎች

No Common name Scientific name 1 Moorland Francolin Francolinus psilolaemus2 Erckel's Francolin (Francolinus erckelii3 Blue-winged Goose Cyanochen cyanoptera

4 Wattled Ibis Bostrychia carunculata

5 White-collared Pigeon Columba albitorques

6 Dusky Turtle-dove Streptopelia lugens

7 Black-winged Lovebird Agapornis taranta

8 Scarce Swift Schoutedenapus myoptilus

9 Nyanza Swift Apus niansae

10 Thick-billed Raven Corvus crassirostris

11 Slender-billed Starling Onychognathus tenuirostris

12 White-billed Starling Onychognathus albirostris

13 Rueppell's Robin-chat Cossypha semirufa

14 Moorland Chat Cercomela sordida

15 Rueppell's Chat Myrmecocichla melaena

16 White-winged Cliff-chat Myrmecocichla semirufa

17 Swainson's Sparrow Passer swainsonii

18 Baglafecht Weaver Ploceus baglafecht

19 Abyssinian Longclaw Macronyx flavicollis

20 Ethiopian Siskin Serinus nigriceps

21 Abyssinian Citril Serinus citrinelloides

22 Brown-rumped Seedeater Serinus tristriatus

23 Ankober Serin Serinus ankoberensis

24 Streaky Seedeater Serinus striolatus

25 Hooded Volture Necrosyrtes monachus26 Lammergeyer Gypaetus barbatus27 Tawny Eagle Aquila rapax28 Augur Buzzard Buteo rufofuscus29 Black Kite Milvus migrans30 Speckled Pigon Columba guinea31 Red-eyed Dove Streptopelia semitorquata32 Carmine Bee-eater Merops nubicus33 Crowned Hornbill Tockus erythchynchus34 Striped Swallow Hirundo abyssinica36 Red-cheeked Cordon-blue Uraeginthus bengalus37 Cape Rook Corvus capensis38 Fan-tailed Raven Corvus rhipidurus39 Pid Crow Corvus albus40 Rouget's Rail Rougetius rougetii

Page 53: Wof Washa Field Study Final Draft

ዕዝል 4. በወፍ ዋሻጥብቅ የተፈጥሮ ደንና በአካባቢዉ የሚገኙ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡቦታዎችናመገለጫዎቻቸዉ፡፡

ተ.ቁ.

ወረዳ

የቦታ ስም (ቀበሌ)መገኛ/coordinate/

ከፍታየሚሰጠውአገልግሎት ያለው ኃብትና የተፈጥሮ ገፅታ X Y

1ባሶና ወራና ወፍ ቃሪያ/ደበሌ/ 580506 1070820 3667 መመልከቻ

አሸንዳ፣ጋርዳ፣ጦሽኝ፤ አስታናባህር ዛፍና ወደ መስጫና

2 ጐሽ በር/ጐሹ አገር/ 581281 1072098 3524 መመልከቻ አስታ፣ ጋርዳ፤ገደላማ አፋፍ

3ቁራ ማርያም /ጐሹአገር/ 580724 1072047 3518 የግጦሽ ቦታ ጓሣ ፣ ጋርዳ ፣ የግጦሽ ሣር

4 ቅንጭሊት /ጅብጐራ/ 580430 1072729 3680 መመልከቻ ድንጋያማ ፣ ጋርድ ፣ ጅብራ5 አዲስ አገር/ጐሹ አገር/ 580348 1072834 3689 መመልከቻ ድንጋያማ ፣ ጋርጃ ፣ ጅብራ ፣ ጓሣ

6 አዲስ አገር/ጐሱ አገር/ 580267 1073088 3647 መመልከቻጭራዳ ፤ሽኮኮ ፤ጋጋኖ ወፍ፤ጋርጃ ፣ ጅብራ ፣ጓሣ

7 ጐሽ ሜዳ/ቀይት/ 580030 1073599 3583 ሜዳማ ጭራዳ ፣ ጓሣ ፣ ካፋፍ በታች ጋርዳ ፣ ቆቅ

8 ጐሽሜዳ/ቀይት/ 580344 1074538 3530መመልከቻ/ተራራ

ወደዉቲ ፣ መሃል ወፍ ዋሻ ፣ ደብረሲናመመልከቻና ጭላዳ ፣ ጋርዳ ጅብራ

9 ኪዳን አገር/ጐሽ አገር/ 579171 1071112 3430ግጦሽናእርሻ ጓሣ ፣ ጋጋኖ ፣ ሠውሰራሽ ደን

10የጉዝጓዝ ወንዝ/ጐሹአገር/ 578885 1070264 3386 ወንዝ ጓሣ ፣ ሠውሰራሽ ደን

11 ጥቁረት ባዶ/አባሞቴ/ 579750 1077303 3453 መመልከቻ አስታ ፣ ጋርዳ ፣ ግጦሽ ወደወፍ ዋሻ መውረጃ

12የመውቂያአገር/ጉዶበረት 578594 1080714 3372

ዥኖበርመግቢያ ጓሣ ፣ ጅብራ ፣ ጦስኝ /ደንበርመግቢያ/

13 ዥኖ በር/ጉዶበረት/ 580627 1079859 3426 መመልከቻየአዋድ ጅረት ፣ ወፍዋሻ ፣ ወቲን ፣ መስጫ፣ሸለቆ በረት

14 ዥኖ በር/ጉዶበረት/ 5808051 1074806 3441 መመልከቻየአዋድ ጅረት ፣ ወፍዋሻ ፣ ወቲን ፣ መስጫ፣ሸለቖ ትበረት አስታ ፣ ጋርዳ አሸንዳ

15አንጐለላ ኪዳነ ምህረት 547331 1064823 2832 ቤ/ክርስቲያን

አፄ ሚኒሊክ ክርስትና የተነሱበትና የችሎትቦታ የነበረ

16አንኮበር

አልይ አምባ/አንኮበር/ 587201 1057482 1723 ከተማየጥንት ንግድ መስመር አማራ አርጐባና አፋርየሚገባያዩበት

17 ዘንቦ /ዘንቦ/ 588682 1.1E+08 2040የቀበሌጽ/ቤት መንደርና እርሻ

18 ውቲ ሰሜን ጫፍ 583985 1076469 3250 መመልከቻ የአስታና ድድደን

19ሸለቆ በረት መሃል ወፍዋሻ 582041 1076752 2861 ሸለቆ ትላልቅ የድድ ዛፍና አልፍ አልፍ ወይራና ኮሶ

20 ጐሽሜዳ ዉቲ 583432 1077242 3234 ደን መሃል የከብት በረት ውቲ

21ደብረ ብከላይ/እመምራረት/ 585201 1068280 2817 መንገድ

ከመስጫ ወደ ፍቅሬ ግንብ መንደር የርሻ ቦጻ

22 ፍቅሬግንብ/እመምረት/ 587220 1067991 2989 መመልከቻ

ወደ ዘንቦ፣ወቲ፣መስጫ ጉጉፍቱ፣አስታኮልሐርአምባ ፣ ቆቦ ማሪየምና አርቦማርን ለመመልከት

23ጣርማ በር

ወፍዋሻ ላይገይገነት/ቀርከሃው/ 582273 1082320 2870

በጣርማ በር ደን ደንበር መቆጣጠሪያ የትላልቅ ደን

24 ከዜኖ በርግርጌ ወፍ ዋሻ 582140 1080366 3064 ደን መግቢያ የተመነጠረ አስታ ደን25 ፊላማዶ አንቧይ/አየር/ 581499 1078806 3111 ደን የግጦሽ ደን 26 ወይራ በረት 582380 1078325 2823 የድኩለ ቦታ ደን ቀጨሞድድ