ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት...

22
በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ በፕሮጀክቶች መዘግየት መንግሥት ለ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል አስተዳደሩን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረጉ 25 ተቋማት በህግ ሊጠየቁ ነው ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት ከፖለቲካ በላይ ስለሆነ ለፖለቲካ አያጎነብስም >> 6 ገጽ ውሳኔ ያገኙ የወንጀል ታሪኮች ዶሴ ተናጋሪው ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 ክፍለዮሐንስ አንበርብር አዲስ አበባ፡- ባለፉት 10 ዓመታት በሜጋ ፕሮጀክቶች መዘግየት መንግስት ለ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ መዳረጉ ተገለፀ። በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በኮንስትራክሽን ሥፍራዎች ጥንቃቄ ጉድለት በሦስት ዓመታት ውስጥ ከ3ሺ200 ሰዎች በላይ ሞተዋል። የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር አርጋው አይሻ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ መንግስት በሚያስተዳድራቸው አንድ ሺ ፕሮጀክቶች መዘግ የት የተነሳ 43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ አውጥቷል። ለአብነትም በቅርቡ በተጠናቀቁ ሦስት የስኳር ፕሮጀክቶች የ9ነጥብ6 ቢሊዮን ብር፤ እንዲሁም በመነሻው 700 ሚሊዮን ብር ተበጅቶለት የነበረው መገጭ ግድብ አምስት ቢሊዮን ብር ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን አስታውሰዋል። እንደ ዶክተር አርጋው ገለፃ፤ የግዥ ሥርዓት አለመዘመን፤ የዲዛይን መቀያየር፣ የፕሮጀክት ክትትልና ሪፖርት አያያዝ ደካማ መሆን፣ ሌብነት፣ አዋጭነት ጥናት በተገቢው መንገድ አለመካሄዱ፣ የአማካሪዎች፣ ተቋራጮች፣ ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶችና አሰሪ ደርጅቶች የተቀናጀ አሠራር አለመከተል መንግስትን ለወጪ መዳረጉን - በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ጥንቃቄ ጉድለት 3ሺ200 ሰዎች ሞተዋል ክፍለዮሐንስ አንበርብር አዲስ አበባ፡- አዲስ አበባ ለመቃብር ሥፍራዎች የሚውል ሁለት ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት በላይ ብትከልልም ዘመናዊ አሠራር ባለመከተሏ በቂ አለመሆኑን የአዲስ አበባ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ገለፀ። በአግባቡ የለሙ የመካነ አዲስ አበባ ከሁለት ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት ለመቃብር ሥፍራ ብትከልልም አይበቃኝም አለች በ2010 ዓ.ም ቤተሰቦቻቸው ያልታወቁ 3ሺ890 ሰዎችን ቀብራለች አዲስ አበባ... በ4ኛው ገጽ ዞሯል በፕሮጀክቶች... በ4ኛው ገጽ ዞሯል የርብ የመስኖ ግድብ ስራ ፕሮጀክት የተጀመረው በ2000ዓ.ም ሲሆን፤ ይጠናቀቃል ተብሎ ውል የተገባለት በአራት ዓመት ነበር፡፡ ሆኖም ፕሮጀክቱ የተጠናቀቀው በ2011ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በጀት ቢያዝለትም 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ፈጅቷል፡፡ ከ40 ዓመታት በኋላ ቤተሰባቸውን ያገኙት ተረት ተናጋሪ 2 ገጽ መንትዮቹ የዘመን ሐኪሞች 14 ገጽ ቅዳሜ መፅሔት 3 ገጽ >>

Transcript of ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት...

Page 1: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር!

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

በፕሮጀክቶች መዘግየት መንግሥት ለ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል

አስተዳደሩን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረጉ 25 ተቋማት በህግ ሊጠየቁ ነው

ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት ከፖለቲካ በላይ ስለሆነ ለፖለቲካ አያጎነብስም >>

6ገጽ

ውሳኔ ያገኙ የወንጀል ታሪኮች

ዶሴተናጋሪው

ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75

ክፍለዮሐንስ አንበርብር

አዲስ አበባ፡- ባለፉት 10 ዓመታት በሜጋ ፕሮጀክቶች መዘግየት መንግስት ለ43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ መዳረጉ ተገለፀ። በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በኮንስትራክሽን ሥፍራዎች ጥንቃቄ ጉድለት በሦስት ዓመታት ውስጥ ከ3ሺ200 ሰዎች በላይ ሞተዋል።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር አርጋው አይሻ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ መንግስት በሚያስተዳድራቸው አንድ ሺ ፕሮጀክቶች መዘግ የት የተነሳ 43 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ አውጥቷል። ለአብነትም በቅርቡ በተጠናቀቁ ሦስት የስኳር ፕሮጀክቶች የ9ነጥብ6 ቢሊዮን ብር፤ እንዲሁም በመነሻው 700 ሚሊዮን ብር ተበጅቶለት የነበረው መገጭ ግድብ አምስት ቢሊዮን ብር ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን አስታውሰዋል።

እንደ ዶክተር አርጋው ገለፃ፤ የግዥ ሥርዓት አለመዘመን፤ የዲዛይን መቀያየር፣ የፕሮጀክት ክትትልና ሪፖርት አያያዝ ደካማ መሆን፣ ሌብነት፣ አዋጭነት ጥናት በተገቢው መንገድ አለመካሄዱ፣ የአማካሪዎች፣ ተቋራጮች፣ ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶችና አሰሪ ደርጅቶች የተቀናጀ አሠራር አለመከተል መንግስትን ለወጪ መዳረጉን

- በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ጥንቃቄ ጉድለት 3ሺ200 ሰዎች ሞተዋል

ክፍለዮሐንስ አንበርብር

አዲስ አበባ፡- አዲስ አበባ ለመቃብር ሥፍራዎች የሚውል ሁለት ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት በላይ ብትከልልም ዘመናዊ አሠራር ባለመከተሏ በቂ አለመሆኑን የአዲስ አበባ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ገለፀ። በአግባቡ የለሙ የመካነ

አዲስ አበባ ከሁለት ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት

ለመቃብር ሥፍራ ብትከልልም አይበቃኝም አለች በ2010 ዓ.ም

ቤተሰቦቻቸው ያልታወቁ 3ሺ890 ሰዎችን ቀብራለች

አዲስ አበባ... በ4ኛው ገጽ ዞሯልበፕሮጀክቶች... በ4ኛው ገጽ ዞሯል

የርብ የመስኖ ግድብ ስራ ፕሮጀክት የተጀመረው በ2000ዓ.ም ሲሆን፤ ይጠናቀቃል ተብሎ ውል የተገባለት በአራት ዓመት ነበር፡፡ ሆኖም ፕሮጀክቱ የተጠናቀቀው በ2011ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር

በጀት ቢያዝለትም 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ፈጅቷል፡፡

ከ40 ዓመታት በኋላ ቤተሰባቸውን ያገኙት ተረት ተናጋሪ 2ገጽ

መንትዮቹ የዘመን ሐኪሞች

14ገጽ

የቅዳሜ መፅሔት

3ገጽ

>>

Page 2: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

2 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ ዜና>>

ከፍለዮሐንስ አንበርብር

ሐዋሳ፡- ላለፉት አርባ ዓመታት ከቤተሰባቸው ጋር ሳይገናኙ የቆዩት የተረት አባት በ2011 ዓ.ም ፈጣሪ ረድቶኝ ቤተሰቤን አግኝቼ ተደሰትኩ፤ ደስታዬ ወደር አጣ አሉ።

ላለፉት አርባ ዓመታት በዓሳ አጥማጅነት፣ በጥበቃ፣ ጫማ አሳማሪነት፣ ሱቅ በደረቴና በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተሰማርተው ሕይወታቸውን ሲመሩ የነበሩት የ58 ዓመቱ አባት በ2011 ዓ.ም በልጅነት ከተለዩዋቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር በአጋጣሚ ለመጀመሪያ ጊዜ መገናኘታቸውን ተናግረዋል።

ሀድያ ምስራቅ ባደዋቾ 1953 ዓ.ም የተወለዱት አቶ ታደሰ አሰፋ ሎንቺን በምትባል መኪና ሐምሌ በ1969 ዓ.ም በአንድ ብር ከ90 ሳንቲም ከፍለው ወደ ሐዋሳ ከተማ በመሄድ ሕይወት ጀምረው በዚያው መቅረታቸውን ገልፀዋል።

አቶ ታደሰ እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ የተማሩ ሲሆን፤ በ1966 ዓ.ም የአብዮት ፍንዳታ ወቅት ትምህርታቸውን አቋርጠዋል። አሁንም በ58 ዓመታቸው መማር ያስባሉ።

አቶ ታደሰ በአሁኑ ወቅት፤ በሃዋሳ ከተማ ሌዊ ሪዞርት ለአገር ውስጥና የዳያስፖራ ልጆች ተረት በመናገር የሚተዳደሩ ሲሆን፤ የጥበቃ ሥራም ይከውናሉ። ከዘንዶ፣ ጅብና ሌሎች እንስሳት ጋር የጠነከረ ቁርኝት እንዳላቸውና መግባባት እንደሚችሉም ከልዩ ተሞክሯቸው አካፍለውናል።

አቶ ታደሰ አመጋገባቸው፣ የሕይወት ፍልስፍ ናቸውና ቀጣይ እቅዳቸው የተለየ ሲሆን ድል ባለ ድግስም የውሃ አጣጫቸው ጋር ቢጣመሩ ደስታቸው ወደር እንደማይኖረው ይናገራሉ። የተረት ተናጋሪው የአቶ ታደሠ ሙሉ ታሪክ በቅርቡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅዳሜ ዕትም ‹‹እንዲህም ይኖራል›› ዓምድ እናቀርባለን።

ከ40 ዓመታት በኋላ ቤተሰባቸውን ያገኙት ተረት ተናጋሪ

አብርሃም ተወልደ

አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ ተከታታይ የሆነ የህክምና ሥልጠና ባለመኖሩ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ገለጸ።

ማህበሩ 55ኛ ዓመታዊ የሕክምና ጉባዔውንና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ትናንት ባካሄደበት ወቅት የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ገመቺስ ማሞ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ ለውጥ ያላመጣው የሕክምና ጥራት ጉዳይ መቅረፍ ያልተቻለው በዘርፉ ላሉ ሙያተኞች ተከታታይ ሥልጠና ባለመሰጠቱ ነው።

እንደ ዶክተር ገመቺስ ገለፃ፤ ችግሩን ለመቅረፍ በሕክምና ትምህርት ቤቶች የሚከወነውን የመማር ማስተማር ሂደትን አጠናክሮ መሥራት ወሳኝ ነው። በሥራ ላይ ባሉት ሙያተኞችም ላይ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በመስጠት የጥራት ጉድለቱን ማስተካከል ይገባል። ማንኛውም የሕክምና ባለሙያም ሕክምና ትልቅ ትኩረትን የሚሻ ከመሆኑም በላይ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ለማዳን የሚደረግ ሥራ መሆኑን በመገንዘብ አስተሳሰቡንና አካሄዱን ማስተካከል ይኖርበታል። ጤና ለሁሉም የሚለው አጀንዳ ዓመታትን ያስቆጠረና ቀን ቢቆረጥለትም መሳካት ያልቻለ ነው።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በበኩላቸው፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከማህበሩ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ በመጥቀስ፤ ተደራሽነትን በተመለከተ የተሠራ ሥራ መኖሩንና ጥራቱ ላይ ደግሞ ትኩረት በመስጠት ለመሥራት በሂደት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ጥራት ያለው ሕክምና

እየተሰጠ እንዳልሆነ ተገለጸ

ጨፌ ኦሮሚያ የመሬት ወረራን የመከላከል ስራውን አጠናክሮ

እንደሚቀጥል አስታወቀጉባኤውን ከየካቲት 19 ቀን ጀምሮ ያካሂዳል

ዘላለም ግዛው

አዲስ አበባ፤ የመሬት ወረራን ለመከላከልና ህጋዊ መስመር የማስያዙ ስራ የሚቀጥል እንጂ ወደ ኋላ የሚመለስ ጉዳይ አለመሆኑን ጨፌ ኦሮሚያ አስታወቀ።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ከየካቲት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን አምስተኛው የጨፌ ስራ ዘመን አራተኛ ዓመት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የመሬት ወረራን እየተከላከሉ ወደ ህጋዊ መስመር የማስገባት ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነው።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ስድስቱ የኦሮሚያ ከተሞች በቅርበት የሚገኙ በመሆናቸው የሁሉም ሰው ፍላጎት አርፎባቸዋል ያሉት አፈጉባኤዋ፣ በመቶ ሺዎች የሚገመት ሄክታር በህገ ወጥ መንገድ ተይዟል ብለዋል።

የሽግግር ወቅት እንደመሆኑ የመሬት ወረራና ሌሎች ሰፋፊ ችግሮች እንደሚከሰቱ ጠቅሰው፣ ‹‹በህገ ወጥ መንገድ አንዴ ተይዟልና የራሱ ጉዳይ ተብሎ አይተውም ህጋዊ መስመሩን እንዲይዝ ይሰራል›› ብለዋል።

20 እና 30 ዓመታት፣ የተወሰነ ጊዜ የኖረም ህጋዊ የሚያደርገው ነገር ካለ በህግ የሚታይበት አግባብ እንዳለም ጠቁመዋል። ጉልበት፣ ገንዘብ ስላለውና ከተወሰነ ሰው ጋር በጥቅም በመገናኘት በህገ ወጥ መንገድ የተያዘን መሬት ህጋዊ ማድረግ እንደማይቻል ተናግረዋል። በሽግግር ወቅት አብዛኛው ህዝብና አመራር ሰላም ለማስጠበቅ በሚሯሯጥበት ወቅት የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና ኪሳቸውን ለመሙላት የሚሯሯጡ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

በክልሉ ዋነኛ የግጭት መንስኤ የነበረው የመሬት ጉዳይ መሆኑን ያስታወሱት አፈ ጉባኤዋ፤ መንግሥት ችግሩን ለማስተካከል የተለያዩ ማሻሻያዎች ማድረጉን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ተጠናክሮ የታገለ ባለመኖሩ ችግሩ መስፋቱን አመልክተዋል።

ሰፋፊ መሬት በተለያየ ሰው ስም ተይዟል፣በሌላ በኩል ደግሞ ማደሪያ አጥተው የሚቸገሩ ዜጎች አሉ፣በመሆኑም ይህንን ስርዓት የማስያዝ ስራ ይሰራል ብለዋል። ቀደም ሲል በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃ እንደተወሰደባቸውም አስታውሰዋል።

የመሬት ወረራን ለመከላከልና ህጋዊ መስመር በማስያዙ ሂደት የሚፈናቀሉ ዜጎችን ሰላማዊ የመኖሪያ አካባቢ እንዲያገኙ ለማድረግ ጨፌው እንደሚመክርበትም አንስተዋል።

የኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ እና ኦሮሚኛ ቋንቋ ሁለተኛ የፌዴራል የስራ ቋንቋ የማድረግ ጉዳይ በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ በመጠቆም፤ የሌሎች አገሮች ተሞክሮ እየታየ እንደሚገኝ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚመለስ መሆኑን ጨፌ ኦሮሚያም እንደሚያምንበት ወይዘሮ ሎሚ ተናግረዋል።

በክልሉ መስተካከል ያለባቸው የሰላምና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ ምዕራብ ኦሮሚያ የተወሰኑ ዞኖችና ሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን የሚስተካከሉበት ሁኔታ ትኩረት ተደርጎ ውይይት ይደረግበታል። የሴቶችን ተሳትፎ የበለጠ ለማጠናከር ጨፌው ትኩረት ሰጥቶ ይመክራል።

ጨፌው የዳኞች ሹመት፣ የህብረት ስራ ኤጀንሲ አስመልክቶ አዋጅ እንደሚያጸድቅ እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ከወከሉት ህብረተሰብ ጋር ተገናኝተው የሚመካከሩበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያይም ጠቁመዋል።ወይዘሮ ሎሚ በዶ

ፎቶ

በገባ

ቦ ገብ

አቶ ታደሰ አሠፋ

Page 3: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

3የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ዜና >>

አስተዳደሩን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረጉ 25 ተቋማት በህግ ሊጠየቁ ነው- በሦስት ተቋማት ብቻ ከ672 ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት ተገኝቶባቸዋል

-ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ከደንብና መመሪያ ውጭ ግዢ ተፈጽሟል

ማህሌት አብዱል

አዲስ አበባ፡- ጥሬ ገንዘብ በማጉደል፣ የተሰበሰበ ገንዘብ በወቅቱ ፈሰስ ባለማድረግ፣ ባለማወራረድ፣ በአግባቡ ወጪ ባለማድረግና በብክነት ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረጉ 25 ተቋማት በህግ ሊጠየቁ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር አስታወቁ።

የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር ወይዘሮ ፅጌወይን ካሳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ መስሪያ ቤታቸው በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በ27 ተቋማት ላይ የፋይናንስ ህጋዊነት ኦዲት ለማድረግ አቅዶ በ25 ተቋማት ላይ ባከናወነው የኦዲት ስራ ተቋማቱ አስተዳደሩን ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረጉ መሆናቸው አረጋግጧል። በመሆኑም ተቋማቱ እስከ የካቲት 2011ዓ.ም መጨረሻ ሂሳባቸውን ማስተካከል ካልቻሉ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል።

እንደ ዋና ኦዲተሯ ማብራሪያ፤ ኦዲት ከተደረጉ ተቋማት መካከል ከንቲባ ጽህፈት ቤት፣ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ 672 ሚሊዮን 689ሺ ብር የጥሬ ገንዘብ ጉድለት የታየባቸው ሲሆን፣ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ኦዲት ከተደረገ በኋላ ጉድለቱን ተመላሽ በማድረግ ማስተካከል ችሏል። ሁለቱ ተቋማት ግን እስካሁን የጎደለውን ሂሳብ አላስተካከሉም። በተለይም የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 534ሺ ብር ከተማሪዎች የሰበሰበውን የወጪ መጋራት ሂሳብ ለፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ፈስስ ባለማድረግ ክፍተት ታይቶበታል።

በተመሳሳይ የጉለሌ እጽዋት ማዕከል ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው በተቋሙ ከተቀጠሩት ሰራተኞች ከወርሃዊ ደመወዛቸው ላይ የወጪ መጋራት 10

በመቶ ተቀናሽ ሳያደርግ 17ሺ347 ብር ከፍሎ ተገኝቷል።በተጨማሪም ዘጠኝ ተቋማት 32ሚሊዮን 562 ሺ328

ብር በወቅቱ ሳይሰበስቡ መቅረታቸውን በምርመራው መረጋገጡን ወይዘሮ ፅጌወይን ጠቁመው፤ ከእነዚህም መካከል የትራንስፖርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት፣ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታልና ትምህርት ቢሮ በዋነኝነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አመልክተዋል። ውበትና መናፈሻ ዘላቂ ማረፊያ ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ጉለሌ እፅዋት ማዕከል፣ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታልና ትምህርት ቢሮ 26 ሚሊዮን 558ሺ 141ብር በውሉ መሰረት ቅድሚያ ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ ተመላሽ ሳያደርጉ መቅረታቸውን አስገንዝበዋል።

«በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ግንባታውን ከሚያከናውን ህንፃ ተቋራጭ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 232ሺ 906 ብር መሰብሰብ ሲገባው መሰብሰብ የቻለው 1ሚሊዮን 944ሺ 266 ብር ብቻ መሆኑን አረጋግጠናል» ብለዋል። ይህም የቅድሚያ ክፍያ ተመላሽ ሲደረግ ሂሳቡ በትክክል ባለመሰላቱ መሆኑን አስረድተዋል። በተመሳሳይ ትምህርት ቢሮ 3 ሚሊዮን 104 ሺ 125 ብር ከማን እንደሚሰበሰብ የማይታወቅ ሂሳብ መገኘቱን አመልከተዋል። ይህም የሆነው ሂሳብ በዝርዝር መመዝገብ ባለመቻሉና ማስረጃዎች በተገቢው ሁኔታ ተደራጅተው በወቅቱ እንዲሰበሰብ ባለመደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ዋና ኦዲተሯ ማብራሪያ፤ ኦዲት በተደረጉ ተቋማት የግዢ አዋጅ ደንብና መመሪያ ተጠብቆ መከናወኑንና ክፍያውንም ህጋዊነቱን ተከትሎ መፈፀሙን ለማረጋገጥ ሲጣራ 18 ተቋማት 26 ሚሊዮን 586ሺ 626 ብር ከደንብና መመሪያ ውጭ ግዢ ፈፅመው ተገኝተዋል። ከእነዚህ ተቋማት ውስጥ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል 6 ሚሊዮን ብር፣ የአስተዳደሩ

አደረጃጀትና መዋቅር ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት 3 ሚሊዮን 943 ሺ ብር እንዲሁም ውበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ 3ሚሊዮን 883ሺ477 ብር ያለአግባብ ግዢ በመፈፀም ተጠቃሽ ናቸው።

ከደንብና መመሪያ ውጪ አበልና ደመወዝ በመክፈል ረገድም 11 ተቋማት ከመመሪያ ውጭ 3ሚሊዮን 397ሺ 668 ብር አበል መክፈላቸውን እንዲሁም ስድስት ተቋማት 2ሚሊዮን 300ሺ833 ብር ደመወዝ ያለአግባብ ከፍለው መገኘታቸውን በምርመራ መረጋገጡን አስረድተዋል። በተመሳሳይ ከንቲባ ጽህፈት ቤትና እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በድምሩ 57ሺ 316ብር ከመመሪያ ውጪ የትርፍ ሰዓት ክፍያ መፈፀማቸውን አመልክተዋል።

ዋና ኦዲተሯ «ባደረግነው ማጣራት የአስተዳደሩ አደረጃጀትና መዋቅር ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት በሌላ የመንግስት ተቋም የሚሰራና ደመወዝ በየወሩ የሚቀበል ሰራተኛን በ2008 እና በ2009በጀት ዓመት ያለአግባብ 279ሺ106 ብር ከፍሎ ተገኝቷል» ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ተቋሙ አንድ ሰራተኛ ሲቀጠር ከዚህ ቀደም ይሰራ ከነበረበት ተቋም መልቀቂያ ማምጣቱን የሚያረጋግጥበት አሰራር ባለመፍጠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በእነዚህና በሌሎች ተቋማቱ ላይ ያሉ ብልሹ አሰራሮች የከተማ አስተዳደሩን ብሎም የአገርን ኢኮኖሚ ለኪሳራ እየዳረገ በመሆኑ መስሪያ ቤታቸው ከከተማዋ ምክትል ከንቲባ ከኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር በመነጋገር ተቋማቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ያጎደሉትን ሂሳብ እንዲያስተካክሉ አለበለዚያ በህግ ተጠያቂ መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ላይ መደረሱን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት ለሁሉም ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው አስታውቀዋል።

ጌትነት ምህረቴ

አዲስ አበባ፡- በ2003ዓ.ም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪነት የተሸጋገሩ በኤሌክትሪክ አቅርቦች ችግር ምክንያት ስራችንን አቁመናል ሲሉ አማረሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ችግሩ መኖሩን አምኖ ጥያቄያቸውን ለማስተናገድ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

የንብ ብረታብረትና እንጨት ስራ ማህበር መስራች ወጣት ወንድያፍራው የዋግሹም ድርጅታቸው ከስምንት ዓመት በፊት ከጥቃቅንና አነስተኛ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ሲሸጋገር በተደራጀ ሁኔታ የተለያዩ የኮንስትራክሽንና የግብርና ማሽኖች ለመስራት ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡ይሁን እንጅ የኤሌክትሪክ መስመር ባለመዘረጋቱ ስራቸው በእጥልጥል ላይ መቅረቱን ይናገራሉ፡፡ይኸው ችግር የሊዝ ማሽን እንዳይወስዱ አድርጓቸዋል፡፡

ድርጅታቸው የብሎኬት ማሽኖች፣ ሚክሰሮች፣ ውሃ ከጉድጓድ ማውጫ ማሽኖችን፣ የሩዝና የቡና መፈልፈያ ማሽኖችን ለመስራት የንግድ ፈቃድ አውጥቷል፡፡ በዚህም ከውጭ የሚገቡ ማሽኖችን በመተካት የውጭ ምንዛሬ

መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በኤሌክትሪክ እጦት

ስራችንን አቁመናል አሉወጪን ማዳን እንደሚቻል አስታወሰው፤ ድርጅታው እነዚህን ማሽኖች የሚተክልበት 2500 ካሬ ሜትር ላይ ህንጻ ቃሊቲ አካባቢ የገነባና ከሶስት ዓመት በፊትም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማግኝት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ የፈጸመ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለም፡፡ የሊዝ ፋይናንስ ማሽን ውሰዱ ተብለው ያልወሰዱት ያለ ስራ ከሚቀመጥና ወለድ እንዳይጨምርባቸው በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ድርጅታቸው አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በማስመዝገብ በ2003ዓ.ም ወደ መካከለኛ

ኢንዱስትሪ የተሸጋገረ ቢሆንም ከዚህ በኋላ በርካታ ችግሮች አሳልፈናል የሚሉት አቶ ያረጋል ገሰሰ በበኩላቸው፤12 ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ክፍያ ቢፈጸምም ፖል ብቻ ቆሞ፣ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለማግኘታቸው ስራ ፈት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኤሌክትሪክ ከሌለ ተጨማሪ ዕዳ ስለሚሆንባቸው የሊዝ ፋይናንስ ማሽን አለመውሰዳቸው አስታወሰዋል፡፡

ወጣት ጌታነህ ዝናቡ በበኩሉ በቃሊቲ አካባቢ የመስሪያ ህንጻውን ቢያጠናቅቅም

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሊያገኝ ባለመቻሉ ስራ አቁሟል፡፡ የተለያዩ የብረታ ብረትና እንጨት ምርቶችን ለማምረት ቢያቅድም ኤሌክትሪክ መስመር ሊዘረጋለት ባለመቻሉ ስራ ፈት ሆኗል፡፡ ችግሩን በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢያመለክቱም ‹‹ከዛሬ ነገ ይገባላችዋል›› ከሚል ምላሽ ውጭ በተግባር ጠብ ያለ ነገር እንዳላገኙ አስታወሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ከ60 ሺ በላይ ድርጅቶችና ግለሰቦች የኤሌክትሪክ

አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ክፍያ የከፈሉ ቢሆንም አገልግሎቱን ማግኘት አለመቻላቸውን አምነዋል፡፡ የስርጭትና የማከፋፈያ መስመሮችን በወቅቱ የማሻሻል ስራዎች ባለመሰራታቸው የአገልግሎቱ ፈላጊዎችን ጥያቄ ማስተናገድ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ክፍያ ፈጸመው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥያቄ መመለስ ያልተቻለው በግብዓት ችግር ምክንያት ነው፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ60ሺ በላይ ዜጎች ለአገልግሎቱ ክፍያ ፈጸመው ኤሌክትሪክ ሀይል እንዲገባላቸው እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትም ሰባት የአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ግብዓት አምራቾችን በጨረታ አወዳድረው ግዥ በመፈጸም ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የትራንስፎርመሮች፣ የኤሌክትሪክ ገመድና ቆጣሪዎች በመረከብ ክፍያ ለፈጸሙ ደንበኞች ኤሌክትሪክ የማስገባት ስራ ተጀምሯል፡፡ የመካከለኛ ኢንዱስትሪዎችም በዚህ ሂደት ችግራቸው እየተፈታ ይሄዳል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም አንድ ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት አቅደው እየሰሩ መሆኑን አስታወሰዋል፡፡

ፎቶ

- በፀ

ሐይ

ንጉሤ

ወይዘሮ ፅጌወይን ካሳ

Page 4: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

4 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ ዜና>>

በፕሮጀክቶች...

በምክንያትነት ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ግንባታዎች

ሲከናወኑ 80 በመቶ መስክ ላይ ከፍተኛ ድካም የሚሰራ ሲሆን፤ 20 ከመቶ ብቻ በፋብሪካ ተጠናቆ የሚቀርብ በመሆኑ በፍጥነትና በጥራት ለመስራት ከፍተኛ ጊዜ፣ መዋዕለ ንዋይና ጉልበት ይጠይቃል። ይህም ለብክነቱ አንዱ መንስኤ ነው። በውጭው ዓለም ደግሞ 90 ከመቶ የኮንስትራክሽን ሥራ በፋብሪካ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ 10 ከመቶ በመስክ የሚሠራ ነው። በእኛ ሃገር ግን ይህ ባለመሆኑ ዘርፉ ከበርካታ ችግሮች የፀዳ እንዳይሆን አስችሎታል።

ዶክተር አርጋው እንዳሉት፤ ከፕሮጀክቶች መዘግየት በተጨማሪም በኮንስትራክሽን ስፍራዎች

ጥንቃቄ ጉድለት ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ ከሆስፒታሎችና ሌሎች ተቋማት በተገኘ መረጃ፤ 3ሺ200 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በአፈር መደርመስ፣ ከጥንቃቄ ጉድለትና ከግንባታ ላይ መውደቅ ዋንኞቹ የአደጋው መንስኤዎች ሲሆኑ፤ መረጃዎች በአግባቡ ቢያዙና አገራዊ አሃዙ በሥርዓት ቢጠናቀር ጉዳቱ ከዚህ በእጅጉ የገዘፈ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

በኮንስትራክሽ ዘርፍ ያለውን ችግር ለማቃለልም ኢንስቲትዩቱ ከአዲግራት፣ አዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ሐዋሳ ዩኒቨርሲዎች እና ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በ38 ርዕሰ ጉዳች ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ላይ መሆኑን

አብራርተዋል። የባለሙያዎችን ክህሎት ለማሳደግም ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ 8ሺ500 በላይ ባለሙያዎችን ማሰልጠን ተችሏል። የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በአዋጅ 2289/2005 ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ችግር ፈቺ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁመው፤ በቀጣይም ችግሮች እንደሚቃለሉም ዶክተር አራጋው አረጋግጠዋል።

የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በግንባታ ሥፍራዎች ከሚከሰት የጥንቃቄ ጉድለት በየቀኑ ስድስት ሺህ ሰዎች ሲሞቱ፤ ከፍተኛ የሆነ የሃብት ብክነትም ይስተዋላል።

መቃብር ስፍራዎች ሠርግ እና ልደት እየተደገሰባቸው መጠነኛ ገቢም እያስገቡ መሆኑንም ተገልጿል።

የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አደባባይ ሰንደቅ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ መንግስት በሚያስተዳድራቸው 15 ስፍራዎች ሁለት ሚሊዮን 40ሺ623 ካሬ ሜትር መሬት ለመቃብር የተከለለ ሲሆን፤ በተጨማሪ በቤተ እምነቶች የተያዙ ከ80 በላይ ሰፋፊ የመቃብር ሥፍራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ከሚሰጠው አገልግሎት አኳያ በቂ አለመሆኑን አብራርተው ይህን ለማስተካከል ኤጀንሲው፣ ቤተ እምነቶች እና ማህበረሰቡ በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አቶ አደባባይ እንዳሉት፤ ቀጨኔ መድሃኒያለም፣ ጳውሎስ ወጴጥሮስ፣ ሳሎጎራ፣ ጉራራ፣ መካኒሳ፣ ዮሴፍ፣ ባለወልድ፣ ጀሞ፣ ፍሊጶስ፣ ሸጎሌ፣ ኮተቤ ገብርኤል፣ የኮልፌ ሙስሊም መቃብር፣ አዲስ አንድ እና አዲስ ሁለት የተሰኙ 15 የመካነ መቃብር ስፍራዎች በመንግስት የሚተዳደሩ ሲሆን፤ ከአገልግሎትና ከህብረተሰቡ ፍላጎት አኳያ በቂ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ 80 የመካነ መቃብር ሥፍራዎች በቤተ እምነቶች የሚተዳደሩ ቢሆንም፤ በከተማዋ ያሉት ዘላቂ ማረፊያዎች አያያዝና አጠቃቀም ዘመናዊ አለመሆኑን አብራርተዋል።

ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት ከመካነ መቃብር ስፍራዎቹ አጠቃቀምና አያያዝ በቂ ባይሆንም፤ የተወሰኑት በመልካም ይዞታ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ጥቂት የመካነ መቃብር ሥፍራዎች በጥሩ ሁኔታ ስለተያዙ ሠርግና ልደት ይደገስባቸዋል ብለዋል።

መቃብር ስፍራዎችን ከአስፈሪነት ድባብ ወጥቶ ማራኪ መዝናኛ እንዲሆኑ በሰፊው እየተሰራ ነው። ሆኖም ነዋሪዎች በዚህ አካባቢ ሄዶ የመዝናናት ባህል ያልዳበረ በመሆኑ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በቀጣይ የዘላቂ ማረፊያ ሥፍራዎች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዘወተሩበት፣ ለማንበቢያ ምቹ የሆኑ ቤተመጽሀፍት የሚገነቡበትና የጎብኚዎች ፍሰት የሚበዛበት ሥፍራ ለማድረግም እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በኤጀንሲው የካፒታል ፕሮጀክ ቶች ክትትል ባለሙያ አቶ ዮሐንስ ንጉሴ በበኩላቸው፤ መንግስት በሚያስተዳድ ራቸው የዘላቂ ማረፊያዎች ብቻ በ2010 በጀት ዓመት 8ሺ374 ሰዎች የተቀበሩ ሲሆን፤ 3ሺ890 ሰዎች አሊያም ቤተሰቦ ቻቸው ያልታወቁ ናቸው። በ2011 ግማሽ በጀት ዓመት ውስጥ ደግሞ 4ሺ792 ሰዎች ተቀብረዋል። ከነዚህ ውስጥ 2ሺ091 ሰዎች ቤተሰብ ያልተገኘላቸው ናቸው። ይህ አሀዝ የ80 ቤተ እምነቶች መረጃን የማይጨምር ሲሆን፤ ቁጥሩ ከዚህ በእጅጉ የላቀ እንደሚሆን ገልፀዋል።

አቶ ዮሐንስ እንዳሉት፤ የመካነ መቃብር ሥፍራዎች በተቻለ መጠን ገቢ እያስገኙ ቢሆንም በቂ አይደለም፡፡ ለአብነትም በ2010 በጀት ዓመት ከእነዚህ ሥፍራዎች 195ሺ ብር መገኘቱን ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 62/2010 የውበት፣ መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በሚል የሥም፣ ተግባርና ኃላፊነት ማሻሻል ማድረጉ ይታወሳል።

አዲስ አበባ ከሁለት ሚሊዮን...

ወንድወሰን ሽመልስ

ጅግጅጋ፡- በክልሉ በተለይም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚስተዋለውን የመምህራን እጥረትን ለማቃለል እንዲቻል ለመምህራን የማበረታቻ ፓኬጅ ለመተግበር የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑን የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዲላሂ መሐመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ባለው የመምህራን ፍላጎትና አቅርቦቱ መካከል ሰፊ ክፍተት አለ። በተለይ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ችግሩ ሰፊ ነው። ይህ ደግሞ በመማር ማስተማሩና በትምህርት ጥራት ላይ የራሱ ተጽዕኖ ስላለው፤ ክልሉ የሚያስፈልጉትን መምህራን ለማግኘት እንዲችል በጥናት ላይ የተመሰረተ የመምህራን ማበረታች ፓኬጅ ለመተግበር እየሰራ ይገኛል። በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

እንደ አቶ አብዲላሂ ገለጻ፤ በክልሉ አሁንም

ድረስ 90 በመቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ፍላጎቱን የሚሸፍነው ከሌሎች ክልሎች በመጡ መምህራን ነው። ሆኖም በቋንቋ ምክንያት ይህ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አለመኖሩ ፈተና ሆኗል። የክልሉ ተወላጆች ደግሞ በቂ ደመወዝና ማበረታቻ ስለማያገኙ እምብዛም አስተማሪ መሆን አይፈልጉም።

በክልሉ ያሉ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችም ጥቂት በመሆናቸው፤ በክልሉ ወደ አራት ሺ ለሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአንድ ዓመት ለአንድ ትምህርት ቤት አንድ ሰው እንኳን እመድባለሁ ቢባል 4000 ሰው ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው፣ ሦስት የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ደግሞ በጥቅሉ በዓመት 700 መምህራን ነው ለገበያው የሚያቀርቡት ብለዋል። ይህ ደግሞ በፍላጎቱና አቅርቦቱ መካከል ሰፊ ክፍተት መኖሩን ያሳያል። በዚህም አስር አስተማሪ ሊኖረው የሚገባ ትምህርት ቤት በሁለትና አምስት አስተማሪ እንዲሰራ መገደዱን አስታውቀዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ መምህራንን ለመቅጠር ክልሉ ተወዳዳሪ ሆኖ ሰው እንደሚያገኝ የጠቆሙት አቶ አብዲላሂ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ግን ከፍተኛ ችግር ላይ ስላለ ይሄን ለማሻሻል እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም መምህርነትን የተሻለ ሙያ መሆኑን ለማሳየት እንደሚፈልጉና ጥሩ አቅም፣ ሙያና ስነምግባር ያላቸውን ሰዎች ወደ ማስተማር በማምጣት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የደመወዝ ችግሩን የመፍታት ጉዳይ በፌዴራል መንግስት የሚወሰን መሆን ለዚህ እርምጃቸው ምክንያት እንደሆናቸው በመጥቀስም፤ ጥናቱን መሰረት በማድረግ የሚከናወነው የመምህራን ማበረታቻ ፓኬጅ ለመምህራን በተለይም በመጀመሪያ ደረጃ ላሉት የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ አብራርተዋል። ለዚህም የተለያዩ የማበረታቻ አማራጮችን እያዩ መሆኑንና ምናልባትም በዚህ ዓመት ከሐምሌ ወር አንስቶ ማበረታቸውን ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

በሶማሌ ክልል ለመምህራን የማበረታቻ ፓኬጅ

ለመተግበር ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

ራስወርቅ ሙሉጌታ

አዲስ አበባ፡- በለገጣፎ ከተማ ከመሬት ወረራና ሕገወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ማንነትን መሰረት ያላደረገና ሕገ ወጥነትን የመከላከል ስራ ብቻ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገለጸ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ባንቴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱ መረጃዎች እውነት ካለመሆናቸው ባሻገር ሆን ተብሎ የክልሉን ገጽታ ለማጠልሸት የሚደረጉ ናቸው።

የሚወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአሰራር የተፈጠረ ችግር ካለም ቅሬታ የሚቀርብበትና የማጣራት ስራ የሚሰራ ኮሚቴ የክልሉ መንግስት ያቋቋመው መሆኑን ጠቁመዋል።

በለገጣፎ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞችም ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ያሉት ኃላፊው፣ያለውን ውስን ሀብት በህጋዊነት እኩል ለመጠቀም የተጀመረው በሕጋዊ መንገድ ህግን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።ከማንነት ጋር የማይያያዝ ህግ የማስከበር ስራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ኃላፊው እንዳብራሩት ከመሬት ወረራና ሕገ ወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘ ሕግን መሰረት ባደረገ መልኩ ህግ የማስከበር ስራ እየተሰራ ያለው ከ2006 ጀምሮ መሆኑን አስታውሰው፣ በለገጣፎ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊትም በቡራዮ ከ700 በላይ እንዲሁም በመቱ ከ611 በላይ ሕገወጥ ግንባታዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ።

ይህም እየተደረገ ያለው ./በመጀመሪያ ሕገወጥነትን በመከላከል የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሲሆን፣ ሁለተኛም ከመሬት

ወረራና ሕገ ወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘ ሕብረተሰቡ ‹‹ሕገወጥ ግንባታ ተስፋፋ፡ አርሶ አደሩ እየተፈናቀለ ነው›› በማለት በተደጋጋሚ ሲያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግና ጥናት በማካሔድ፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥና የከተሞችን እድገት በፕላን መሰረት በማድረግ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ለማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል።

በለገጣፎ የፈረሱት ቤቶች አንዳንዶቹ ቦታዎች እንደ ጤናና ትምህርት ቤት ለመሳሰሉ ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲውሉ መንግሥት ካሳ የከፈለባቸው ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ናቸው። ይሄም ሆኖ ወደ ማፍረስ ከመገባቱ በፊት የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል የሚሉት ኃላፊው። ጉዳዩ በ2005 በወጣው የሊዝ አዋጅ ከሰባት እስከ አስራ አምስት ዓመት እስራትና መቀጮ

የሚያስከትል ቢሆንም ወደዚህ ከመገባቱ በፊት የማወያየት፡ ማስጠንቀቂያ የመስጠትና ህገወጥ ግንባታ አከናውነው ለሚፈረስባቸው መፍትሄ ለመስጠት 140 ካሬ ሜትር ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጣቸውም አቅጣጫ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በወቅቱ መረጃዎቹን የሚያቀርብና ፈቃደኛ ሆኖ የሚያፈርስ ባለመኖሩ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ህግን መሰረት ያደረገ ሕገወጥነትን የመከላከል እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

‹‹በህጋዊ መንገድ ከአርሶ አደሩ ገዝተን ነው የሰራነው። ሕጋዊ ካልሆነ በወቅቱ ስንሰራ መንግስት ለምን አላስቆመንም›› የሚል ቅሬታ ከተነሺዎች ይቀርባል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ኃላፊው በሰጡት ምላሽ፣ መሬት የመንግስትና የህዝብ ነው። ሕገወጥ ስራ ሰርቶ በህጋዊ መንገድ መጠየቅ አይቻልም። መሬት ሊተላለፍ የሚችለው አንደኛ በሊዝ በጨረታ

ሲሆን ሁለተኛው ለመኖሪያም ሆነ ለአርሶ

አደሩ በምደባ ነው። በመሆኑም ከዚህ ውጪ

የሚከናወኑ የመሬት ግዠና ሽያጭ ሕገ ወጥ

መሆናቸው አመልክተዋል።

በወቅቱ እርምጃ ላለመወሰዱም

በተመለከተም፣ የክልሉ መንግሥት እንደዚህ

አይነት ህገወጥ ድርጊቶች እንዲፈፀም

ያደረጉና መከላከል እያለባቸው ያልተከላከሉ

አመራሮችንና አባላቱን ከተሀድሶ ወዲህ ከ7 ሺ

በላይ በመለየት ግማሹ እንዲባረሩ ቀሪዎቹም

በህግ እንዲጠየቁ ማደረጉን በማስታወስ፣

አሁንም በየከተሞቹ ባለሙያዎች መሀንዲሶች

በቁጥጥር ስር እየዋሉ በህግ የሚጠየቁት

በህግ እየተጠየቁ አስተዳደራዊ እርምጃ

የሚወሰድባቸውም እየተወሰደባቸው እንደሆነ

ገልፀዋል።

በለገጣፎ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ማንነትን

መሰረት ያደረገ እንዳልሆነ ቢሮው ገለጸ

140 ካሬ ሜትር ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጣቸውም አቅጣጫ ተቀምጦ እንዳልተጠቀሙበት ተጠቆመ

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

Page 5: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

አገል

ግል

«ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት ከፖለቲካ በላይ ስለሆነ ለፖለቲካ አያጎነብስም» 6ገጽ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

«ምግቡ ኦልካ፤ ዘፈኑ ዋካ!ዋካ!››

‹‹ቁራኛዬ›› በአዲስ መንገድ

‹‹እንዲህም ይኖራል››የግራሞት ጥግ ነው። ሕይወትን በየፈርጁ ያነቡበታል። አይተው ያላስተዋሉትን፣ ቀርበው ያላወቁትን የሕይወት ገጽ ያገኙበታል። ለእዲህ ያለው በቅርባችን እያለ ያላስተዋልነው ሀሳብና ታሪክ ያዋጡ። በአድራሻችን ይጠቁሙንና በጋራ እንዘግበው።

16ገጽ

12ገጽ

ተናጋሪው ዶሴመጋቤ አዕምሮ

ማረፊያኪነጥበብ

ሲራራየዘመን ሃኪም

ነጻ ሃሳብ

ገጽ9101112131417

በውስጥ ገጾች

እንዲህም ይኖራል

የቅዳሜ መፅሔት

Page 6: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

6 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

የዘመን

እንግዳ >>

ማህሌት አብዱል

አዲስ ዘመን፡- አንዳንዶች ‹‹የፍቅር አባት›› ሌሎችም ‹‹የታሪክ አባት›› ይሉዎታል። የትኛው ይስማማዎታል?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡-እኔ ራሴን የማየው እንደ ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት አድርጌ ነው። ነገር ግን ተማሪ ሆኜ ታሪክ እወድ ስለነበር በታሪክ በጣም ጥሩ ውጤት አመጣ ነበር። እናም ጸሐፊ ተውኔትና ገጣሚ ባልሆን የታሪክ ጸሐፊ እሆን ነበር ብዬ አስባለሁ። ደግሞም ታሪኩን ብቻ ሳይሆን የምወደው አጻጻፋቸውንም ጭምር ስለነበር ለቋንቋም ልዩ ፍቅር አድሮብኛል። አንቺ እንዳልሺው የአማራና የኦሮሞው እውነተኛው የዘር ምንጭ የሚለውን መጽሐፍ ከጻፍኩ በኋላ የታሪክ አባትና የፍቅር አባት የሚሉ ቅጽሎች ሰጥተውኛል። እንግዲህ ይህ የህዝብ አስተያየት ነው።

አዲስ ዘመን፡- በሌላ በኩል ደግሞ አነጋገሪና አከራካሪ ግለሰብ ናቸው ይባላል። እርስዎ አከራካሪ ሰው ነኝ ብለው ያምናሉ? ከሆነስ ለምን?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፦ እኔ የማቀርባቸው ሃሳቦች ለክርክር ወይም ራሴን አነጋጋሪ ሰው ለማድረግ አይደለም። አንድ የሚታየኝና የመሰለኝን ነገር ለሌሎች እናገራለሁ፤ እጽፋለሁ። ከዚያ በኋላ ሰዎች ያከራክራል፤ አያከራክርም ብለው ይፈርጁታል። ይሁን እንጂ እኔ እስቲ የሚያከራክር ነገር ልጻፍ ብዬ ተነስቼ አላውቅም።

አዲስ ዘመን፡- ለእርስዎ የአገር አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት ነው? በተለያዩ አካባቢዎችና መድረኮች ስለአገር አንድነትና ሕብረት

የሚያስተምሩትስ ከምን መነሻ ነው?ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- እንግዲህ በእኔ እምነት

በእኩልነት ላይ እስከተገነባና በፍትህ ርትዕ ላይ እስከተቀመጠ ድረስ የአገር አንድነትን ማስጠበቅ ለማንኛውም አገር ጠቃሚ ነው። ሁሉም አገር ተበታትኖ ሳለ አንድ ያደረጉት ሰዎች አሉ። ለምሣሌ ከአውሮፓ ጣሊያን ተበታትና ሳለች «ጋሪ ባልዲ» የተባለ ሰው በግድም በውድም አገሪቱን አንድ አድርጎ ዛሬ ትልቅ አገር ለመሆን በቅታለች። ጀርመንም እንዲሁ ተበትኖ እያለ «ቢስማርከ» የሚባል ሰው «ዘ አይረን ቻንስለር» እያሉ የሚጠሩት ግለሰብ አስተባብሮ አገሩን አንድ በማድረጉ ዛሬ ጀርመን ከዓለም ሀብታም ከሆኑት አገራት መካከል በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች። ግን ይህ ሲሆን በቀላሉ ተሳክቶለታል ማለት አይደለም። አንዳንድ ትንንሾቹ አገሮች ጀርመን አንድ ከሆነች እነርሱ ስለሚዋጡ ቢስማርክን በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውት እንደነበር ይታወሳል። አሜሪካም እንከፈል ብለው ደቡቦቹ ብዙ ጦርነት አድርገው ከ20 ሚሊዮን ሰው አልቆ እነአብረሃም ሊንከን አሸንፈው አሜሪካ በጣም ትልቅና ገናና አገር ለመሆን በቃች። ለሁለት ተከፍላ ቢሆን የዛሬ ትልቅነቷ አይኖርም ነበር። ስለዚህ ከዓለም አገራት ታሪክ እንደምንረዳው አንድነት በሠላም ቢሆን ጥሩ ነው፤ ካልሆነ ደግሞ በኃይል ይገነባል። ይህም ለኢኮኖሚም ሆነ ለፖለቲካው ጠቀሜታ አለው። ይህን ያህል የምደክመውና ከፍተኛ ዋጋ ከፍዬ ስለኢትዮጵያ የማስተምረው አገሬን ስለምወድ ነው። አሁንም ድረስ በራሴ ወጪ ነው የምንቀሳቀሰው። በድርጅት አይደለም።

አዲስ ዘመን፡- ይህ ጥረትዎ ምን ያህል ውጤታማ እየሆነ ነው ?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- እኔ እንደሚመስለኝ እየዞርኩ በማስተምረውም ሆነ በምጽፋቸው ጽሑፎች የበርካቶችን አመለካከት መቀየር ችያለሁ። ለምሣሌ እኔ በልዩ ምክንያት የጻፍኩት «የአማራና የኦሮሞ እውነተኛው የዘር ምንጭ» የሚለው መጽሐፍ ከወጣ በኋላ እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎችም እንደሚመስክሩት መጽሐፉ ልዩ ተፅዕኖ ፈጥሯል። በተለይም የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲያንሰራራ ረድቷል ብዬ አምናለሁ። ደግሞም አዳዲሶቹ መሪዎች ‹‹ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው›› እስከማለት የደረሱት ከዚህ የተነሳ ይመስለኛል። እንደውም ዶክተር አብይ አህመድ ጀርመን በቅርቡ በሄዱበት ጊዜ የእኔን መጽሐፍ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ስለዚህ መጽሐፌ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሯል ለማለት እደፍራለሁ።

በአካልም እየዞርኩ ስለአማራና ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ስለኢትዮጵያዊነት እየሰበኩ ነው። በዚህም ለአርባ ዓመታት ተጣልተው የነበሩ ወገኖችን ማስታረቅ ችያለሁ። እነዚህ ሰዎች ለአርባ ዓመታት በፖለቲካ ምክንያት የማይናገሩ ሰዎች አውሮፓ ውስጥ ተቃቅፈው ተላቅሰዋል። እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሄጂያለሁ። እዛም «ተፋቀሩ ኢትዮጵያ ናችሁ» ብዬ ሁለተኛ ጎሰኝነትን እንዳያራምዱና በኢትዮጵያዊነት ብቻ ለማንፀባረቅ ቃል ገብተዋል። ስለዚህ እዚህ አገር እስካለሁ ድረስ ስለአገር አንድነት ማስተማሬን፤ መስበኬን እቀጥላለሁ።

አዲስ ዘመን፡- አንዳንዶች ስለሀገር አንድነት የሚሰብኩት የፖለቲካ ተልዕኮ ይዘው እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ ምን ያህል እውነት ነው?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- ፖለቲከኛ አይደለሁም። የፖለቲካ አጀንዳም የለኝም። ነገር ግን ፖለቲካ

አላውቅም ማለት አይደለም። ከፖለቲካ በላይ ነኝ ብዬ አስባለሁ። ገጣሚ፣ ጸሐፊ ተውኔት ከፖለቲካ በላይ ስለሆነ ለፖለቲካ አያጎነብስም። ስለዚህ ስለምንቀውና ስለማልፈልገው ነው ፖለቲካ ውስጥ የሌለሁበት። ይሰለቸኛልም እንጂ! አዲስ ነገር የለበትም። እኔ ደግሞ አዲስ ነገር መስማትና ማንበብ ነው የምፈልገው። ይሁንና የፖለቲካ ንቃተ ህሊናዬ «ፖለቲከኛ ነኝ» ከሚሉት የሚያንስ ሆኖ አይደለም። በልጅነቴም የንጉሡን ሥርዓት በመቃወም ዴሞክራሲ እንዲመጣ ብዙ ታግያለሁ። አውሮፓም ሄጂ በስነ ፅሁፍ አማካኝነት ደርግን ስታገል ነው የኖርኩት ። ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ፍልስፍና ተምሪያለሁ። ስለዚህ ንቃትና እውቀቱ አለኝ፣ ግን አልፈልገውም።

አዲስ ዘመን፡- የአማራና ኦሮሞን እውነተኛ የዘር ምንጭ የሚለውን መጻፍ የጻፉት በልዩ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል። ልዩ ምክንያትዎ ምን ነበር?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- ይህንን መጽሐፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ዋነኛው ጉዳይ እንደሚታወቀው ከአገራችን ህዝብ 70 በመቶውን ቁጥር የሚይዙት የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ባለመግባባት እስከ መጋደልና ደም መፋሰስ የደረሱበት ወቅት ነበር። እኔ ደግሞ ባደረጉት የታሪክ ምርምር ሁለቱ ህዝቦች የአንድ አባትና እናት ልጆች መሆናቸው ስላየሁ ይህንን ባለማወቃቸው ለምን ይጋደላሉ? ብዬ እውነተኛ ታሪካቸውን እንዲያውቁና ሠላም ይፈጠራል ከሚል ተስፋ ነው መፅሐፉን የጻፍኩት። እንዳሰብኩትም ጥቅም እየሰጠ ነው ያለው። በሌላ በኩል ደግሞ «ሁለት ዝሆኖች ሲራገጡ የሚጎዳው ሣሩ ነው» እንደሚባለው ሁሉ በእነርሱ ጠብና ጦስ ደግሞ ሌላውም ህዝብ ስለሚጎዳ ሁለቱ እየተጣሉ

ሌላው ህዝብ በሠላም ይኖራል ማለት ከንቱ እሳቤ ስለሆነ በእነርሱ ዳፋ አገር እንዳይጎዳ በማለት ሁለቱ መታረቅ እንዳለባቸው አምኜ ነው የጻፍኩት።

ሁሌም የምሰጠውን ምሣሌ ላክልልሽ። ጀርመን ሄጄ ጀርመንኛ የሚናገር ልጅ ብወልድ፤ ፈረንሳይ ሄጄ ፈረንሳይኛ የሚናገር ልጅ ብወልድ፤ ጣሊያን ሄጄ ጣሊያንኛ የሚናገር ልጅ ብወልድ፤ እነዚህ ልጆቼ በቋንቋ ባይግባቡም ወንድማማችነታቸው ሊፋቅ አይችልም። እኔም አማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ስለተናገርኩ አባት መሆኔ አይሰረዝም። እኔና ልጆቼን ያዛመደን በመኃላችን ያለው የእኔ ደም እንጂ ቋንቋ አይደለም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ትበቃናለች። በሰላም በፍቅር ወንድማማችና እህታማማች ሆነን እንኑር የምለው።

አዲስ ዘመን፡-ይህንን መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ በርካታ ተከታዮችን ያገኙትን ያህል የሚቃወሙዎትም አሉ። በተለይም ቀድሞ ከተጻፉ የኢትዮጵያ ታሪኮች አንፃር መጽሐፉ ተዓማኒነት እንደሌለው የሚያነሱ የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ። እርስዎ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለዎት?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- ብዙዎቹ ሳይሆኑ ጥቂቶች ናቸው የማይቀበሉኝ በሚለው ይስተካከል። እነርሱ ጉዳዩን ስላልተረዱትና የኢትዮጵያ ታሪክ አስደናቂና ተረት የሚመስል ስለሆነ እንደተረት አይተውት ሊሆን ይችል። ሌላው ደግሞ ይህንን ሃሳብ ህዝብ ውስጥ እንዲሰራጭ ያደረጉ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ። አንደኛው ጉዳይ ለእነርሱ አቋም ስለማይመቻቸውና የማይጠቅም ስለሆነ፤ ሁለቱ ትላልቅ ህዝቦች ቢካፈሉ የሚጠቀሙ በመሆኑ፤ በነዚህ ምክንያቶች ጥቅማችንን ነካ ከማለት ተነሳስተው ነው የሚቃወሙኝ።

«ገጣሚ ጸሐፊ ተውኔት ከፖለቲካ በላይ ስለሆነ ለፖለቲካ አያጎነብስም»

- ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

ተወልደው ያደጉት በድሬዳዋ ከተማ ነው። በሙያቸው ፀሐፊ-ተውኔትና የሥነ ጽሁፍ ምሁር ናቸው። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ይታወቃሉ። በአሁኑ ወቅት የ70 ዓመት እድሜ ባለፀጋ ናቸው። «ጓደኛሞቹ»፣ «ፍቅር በአሜሪካ» እና ሌሎችንም ቴአትሮችን ለመድረክ አብቅተዋል። በርካታ ግጥሞችንና

መጽሐፎችን ለህትመት አብቅተዋል። «የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ» በተሰኘው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው ስማቸው ጎልቶ ይነሳል።

በአሁኑ ወቅት ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ታዋቂው የሥነ ጽሑፍ ምሁር ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፤ በሊንከን ዩኒቨርሲቲ በሂዩማኒቲስ የትምህርት ዘርፍ በማስተማር ላይ ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም «Heaven to Eden» እና «The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians» የሚሉ መጽሐፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ አሳትመዋል። ሁለቱም (አማዞን) በተባለ የመጽሐፍ መሸጫ ድረ ገፅ ላይ ከተፈላጊ መጻሕፍት ተርታ ተሰልፎላቸዋል። በቅርቡም «ላሟ» የተሰኘ ባለ ሁለት ገቢር ቴአትር ጽፈው አጠናቀዋል። የዛሬው የዘመን እንግዳችን ናቸው።ከእርሳቸው ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንደሚከተለው ይቀርባል።

በገጽ 7 ዞሯል

Page 7: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

7የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

እውነተኛ ታሪካቸውን እንዲያውቁ ሰላም ይፈጠራል ከሚል ተስፋ ነው መፅሃፉን

የጻፍኩት። እንዳሰብኩትም ጥቅም እየሰጠ ነው ያለው። በሌላ በኩል ደግሞ «ሁለት

ዝሆኖች ሲራገጡ የሚጎዳው ሳሩ ነው» እንደሚባለው ሁሉ በእነርሱ ጠብና ጦስ

ደግሞ ሌላውም ህዝብ ስለሚጎዳ ሁለቱ እየተጣሉ ሌላው ህዝብ በሰላም ይኖራል

ማለት ከንቱ እሳቤ ስለሆነ በእነርሱ ዳፋ አገር እንዳይጎዳ በማለት ሁለቱ መታረቅ

እንዳለባቸው አምኜ ነው የጻፍኩት።

ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ «ለምን እኛ እዚህ ታሪክ ውስጥ የለንበትም» በሚል ነው የሚቃወሙት። ይህንን የሚሉት ደግሞ አንዳንድ ምሁራን ናቸው። ይህንን ታሪክ ለምን እኛ መጀመሪያ አልጻፍነውም ወይም ታሪክ ውስጥ የለንበት ወይም እኛን እንዴት አላማከረንም በሚል በምሁርነት ሳይሆን በግል ፍላጎት ተነሳስተው የሚያቀርቡት ነው። የሚገርመው እስከዛሬ ድረስ አንድም ምሁራዊ ትንተና ወስዶ በዚህ በዚህ ምክንያት እንደዚህ ያለኝ ምሁር አላገኘሁም። እንዲሁ በጅምላ ‹‹ይሄ ተረት ነው››፤ ‹‹ይሄ የማይመስል ነው› የሚሉት። የተከራከርኳቸውም ግለሰቦች አሉ። ተረት ነው ካሉ ተረት ስለመሆኑ አብነት አድርገው እንዲጠቅሱ ጠይቂያቸው ነበር። ነገር ግን እስካሁን ማስረጃ ያቀረበ የለም።

በነገራችን ላይ ተረት ወይም አፈ-ታሪክም ቢሆን ክፉ ነገር ነው ብዬ አልወስደውም። ምክንያቱም ብዙ አገሮች በአፈ-ታሪክ ላይ ነው የተገነቡት። የጋራ አፈ- ታሪክ አላቸው። ለምሳሌ ብንጠቅስ የጣሊያን መስራቾች በስፋት በአፈ ታሪካቸው ነው አንድነታቸውን ማጠናከር የቻሉት። የእኛ አገር አፈ ታሪክ በእውነት ላይ የተመሰረተ ነው። አስደናቂ ስለሆነም ነው ተረት የሚመስለው። የ4000ውን ዓመት ብቻ ብናወራ ኢትዮጵ የሚባልና እንቂዮፓ ጊዮን የምትባል እናት አስር ልጆች ወልዳ እነዚያ ተባዝተው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሊፈጠሩ ችለዋል።

አፈ-ታሪክ በወረቀት ስላልተጻፈ ታሪክ አይደለም ማለት አይቻልም። እንደሚታወቀው በርከት ያለው ታሪካችን በንግሥት ዮዲት እንደጠፋ ይነገራል። ግን እውነት አይመስለኝም። ንግሥት አስቴር ብላት ይሻላል። ዮዲት ጉዲት እያሉ ሲሰድቧት ኖሯል። በእኔ እምነት መሰደብ የሌለባት ሰው ናት።

ለኢትዮጵያ ውለታ የዋለች ሰው ነች፤ እስከ ዛሬ ስሟን ሲያጠለሹ የኖሩት አረቦች ናቸው። አረቦችን ወይም ከአረብ ጋር ግኑኝነት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ግዕዝን አጥፍተው አረብኛ አምጥተው አገሪቱን ሙሉ አረብ ሊያረጉ ሲሞክሩ ነው አሳድዳ የወጋችው። የአረብ ጳጳሳት ኢትዮጵያኖችንና የዮዲትን ወገኖችን ቤተ-እሥራኤሎች እየሱስን የገደሉ ናቸው ምን ትጠብቃላችሁ ግደሏቸው እያሉ ተቻችለው አብረው የሚኖሩትን ሰዎች እየገደሉ ሲያስቸግሩ በዚህ ተናዳ ነው ይህንን የፈፀመችው። እንዳውም ኢትዮጵያን ከአረብ ወረራ ታድጋለች። ለዚህም ነው ስሟን

ያጠፉት።እናም በዛ ወቅት ንግሥት አስቴር (ዮዲት)

የአክሱምን መንግሥት ስታባርር ታሪካችን ተበትኖ ነበር። አክሱም ላይ የታሪክ ዘጋቢ የሆነ የጅናድ የመጨረሻ የአክሱም ልጅ አክሱማዊ ሲራክ የሚባል ትልቅ አዋቂና ጠቢብ ሰው የቤተ መጽሐፍት ቤቱም ኃላፊ ስለነበር የተቻለውን ያህል የተለያዩ መጽሐፍ አትርፎልናል። በዚያ ጊዜ ውስጥ የሱ መጽሐፍ ወደ ላሊበላ ተወስዶ ከ300 ዓመት በኋላ እስከሚባዛ ድርስ ዓፄ ላሊበላ ግብፅ ሄዶ ያንን መጽሐፍ ሰጡት እሱ አስተረጎመው። ከዚያ እንደገና ጠፋና

በአምደፂዮን ጊዜ ማለትም ከሁለት ሺ ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዳግም እስከሚያጽፉ ድረስ በመሃል ያለው ጊዜ በአፈ ታሪክ ነበር የሚታወቀው። ስለዚህ አፈ ታሪክም የሚናቅ አይደለም። ስለዚህ የጻፍኩትን አፈ ታሪክ ነው ቢሉትም ችግር የለብኝም።

አዲስ ዘመን፡- እርስዎ ይህንን ቢሉም ሌሎች ታሪክ አዋቂዎች ግን አፈታሪክ የሆነን ነገር ወደ ጽሑፍ በማምጣት የአገሪቱ የታሪክ አካል ማድረግ ተዓማኒነት ያሳጠዋል ሲሉ ይሞግታሉ። በተለይ ደግሞ አፈታሪክ ሲጻፍ ሰዎች ከነበሩበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ስለሚጽፉት

ታሪክን ያዛባሉ ብለው ያምናሉ። ለዚህ ምን ምላሽ ይኖርዎታል?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- አሁን እኮ ራስሽ መልሰሽዋል። በጽሑፍ ላይ ስለቀረበ ብቻ አንድ ታሪክ አስተማማኝና ትክክለኛ ነው ማለት አይደለም። እንደ ጸሀፊው አያያዝ እንደ አላማው ይወሰናል። ስለዚህ ለእውነተኝነቱ በጽሑፍ ላይ መስፈሩ ብቻ ዋስትና አይደለም። በቃል ስለተደረገ እውነተኛ አይደለም ማለት አይደለም። ስለዚህ ከአፍ ወደ አፍ ሲተላለፍ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እኮ የቃል ማህበረሰብ ነው። ኢ-ሜል ወይም ደብዳቤ

የዘመን

እንግዳ >> ፯

በገጽ 8 ዞሯል

ፎቶ

- በገባ

ቦ ገብ

Page 8: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

8 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

«ኦሮሞዎች በግዕዝ ...የቃል ማህበረሰብ ነው። ኢ-ሜል ወይም ደብዳቤ ከሚጽፍልሽ ስልክ አንስቶ ማውራት ይቀለዋል። ይህም ተረት የለመደና በተረት ያደገ ህዝብ መሆኑን ነው የሚያሳየው። ስለዚህ ከሁለቱም በኩል ያለውን አመዛዝኖ መፍረድ ዘመናዊ ባለ ታሪክ ወይም የአንባቢው ፈንታ ነው። ግን ሁለቱም ወሳኝ መሆናቸውን አምናለሁ።

አዲስ ዘመን፡- አሁንም ቢሆን ጥቂት የማይባሉ ምሑራን እርስዎ አለ የሚሉትን ታሪክ እውነተኛ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። እርስዎ ምን ይላሉ?

ፕሬፌሰር ፍቅሬ፡- ለምሣሌ አንዱን ጥቀሺልኝ።አዲስ ዘመን፡- ለምሣሌ ፕሮፌሰር ጌታቸው

ኃይሌ አንዱ ናቸው።ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- ከእርሳቸው ጋር ብዙ

ተከራክረናል። ላነሷቸው መልስ 34 ገፅ አጥጋቢ መልስ ሰጥቼ ዓለም በሙሉ ያየው ነገር ነው። ይሄ ጉዳይ ወደ ኋላ ነው የሚወሰደን። እኔና እርሳቸው ያንን ደረጃ አልፈን ከዚህ በኋላ አንነጋገርም ተባብለን አልፈነው የተደመደመ ጉዳይ ነው።

አዲስ ዘመን፡- ተማመናችሁ ማለት ነው?ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- እኔም የራሴን አቋም ይዤ፤

እርሳቸውም የራሳቸውን ይዘው ነው የተለያየነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ላነሷቸው ጥያቄዎች ሰፊ ማሳመኛ ትንታኔ ነው ያቀረብኩት። እንደሱም ብዙ መልስ የተሰጠበት ህዝብን ያሳተፈ ነገር ጉዳይ የለም። ግን በአጠቃላይ ሁኔታውን ሳየው እርሳቸው ሌላ ምክንያት ስላላቸው እንጂ ከተዓማኒነት ጋር የሚያያዝው ነገር የለም። የእሳቸውን ጽሑፍ ካነበብሽ መጀመሪያ ላይ ሲጽፉም የመጽሐፍ ግምገማ (ቡክ ሪቪውም) አይደለም፤ ሂስም አይደለም ብለው ጠቅሰዋል። እንዳውም አርዕስቱ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን ለማሞገስ ነው የሚለው። ከዚያ በኋላ ግን የኔ መጽሐፍ ዋነኛ ምንጭ የሆኑትን መሪራስ አማን በላይ ጋር ቅራኔ ስለነበራቸው ብቻ መጽሐፉን ወደ ማጥላላት ሄዱ። ከእኔ ጋር ግን ወዳጆች ነበርን።

አዲስ ዘመን፡- የኢትዮጵያን ታሪክ ማን ነው መጻፍ ያለበት ብለው ያምናሉ?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- ማንኛውም ታሪክ የሚያፈቅር፣ እውነታውን ተረድቶት በትክክል ተገንዝቦ እውነተኛ ፍርድ ሳያዳላ የሚጽፍ፣ ህዝብ እንዲያውቅ የሚሻ፣ መጻፍ፣ ማንበብ መመራመር የሚችል ሰው መጻፍ ይችላል።

አዲስ ዘመን፡- ሌላው በመጽሐፍዎ ላይ የኦሮሞ ብሔረሰብ አመጣጥን በሚመለከት ከዚህ ቀደም በታሪክ ከምናውቀው በተለየ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከሌሎች አገራት መምጣቱን እንደማይቀበሉት ገልፀዋል። ለዚህ መነሻዎ ምንድን ነው?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- የኦሮሞ ብሔረሰብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን መጣ የሚለው ነገር ፈጽሞ አልቀበለውም።ለአብነት መጥቀስ ካስፈለገ ዓፄ ይኩኑ አምላክ በ13ኛው ክፍለ ዘመን እናታቸው ሃዊ ጊፍቲ መንዲያ ይባላሉ፤ የሸዋ ኦሮሞ ነበሩ። ኦሮሞ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከሆነ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እንዴት ሊሆን ቻለ? የእርሷስ አባት አዛዥ ጫላ በሸዋ ላይ ሥልጣን ያላቸው ኦሮሞ እንዴት ሆኑ? ዓፄ ልብነድንግል ራሳቸው ሚስታቸውና እናታቸው እንዴት ኦሮሞ ሆኑ? ስለዚህ ኦሮሞች በ16ኛው ክፍለ ዘመን መጡ የሚለው ታሪክ እውነት አይደለም ማለት ነው። ግን በተጠቀሰው ወቅት የመጡ ሰዎች አሉ። አረንጓዴ መሬት የያዙ። እነርሱም ቀደም ብለው ከብቶቻቸውን ሣር እያጋጡ በገዳ መስፋፋት ሥርዓት መሰረት ሆነ በጀብደኝነት ወደ ሱማሌ አካባቢ ኬኒያ ድንበር፤ ማዳጋስካር ድረስ የሄዱ ነበሩ። እናም በ16ኛው ክፍለ ዘመን ቦረንና ቤረቱማ የሚባሉ ወንድማማቾች ከነጎሳዎቻቸው የግራኝን ኮቴ እየተከተሉ ከዓፄ ልብነድንግል ጋር ሲዋጋ የሚከላከል መሬት የሚጠብቅ ስላልነበር ዘላለም ከኢትዮጵያ ያልወጣውን ኦሮሞ ጭምር ያደረጉትን እንቅሳቅሴ ነው የኦሮሞ ወረራ የሚሉት።

አማራውንም ከደቡብ አረቢያ ከኦሮሞ በፊት የመጣነው ብለው ተክለፃድቅ መኩሪያ የጻፉት ስህተት ነው። እዚሁ ጎጃም ላይ ‹‹ደሸት›› ወይም ደሴት የሚባለው ንጉሥ የኢትዮጵ ዘር የሆነው 3ሺ600 ዓመት አካባቢ እሱ አራት ወንድ ልጆችን

አዲስ ዘመን፡- ባለፉት 27ዓመታት በስፋት ተሰራጭቶ የነበረና የአማራና የኦሮሞን ህዝብ ሲያጋጭ የቆየው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዋነኛው የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ጉዳይ ነው። በተለይም ንጉሡ «የሴቶችን ጡት ቆርጠዋል፤ አልቆረጡም» የሚለው ጉዳይ ሲነሳ እርስዎ አልቆረጡም ከሚሉት ወገን ነዎት። ለዚህ አባባልዎ ምን ማስረጃ አለዎት?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፌ ላይ በደንብ አብራርቼዋለው። ግን ለአንቺ ለመመለስ ያህል ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ጡት ስለመቁረጣቸው በጽሑፍ የቀረበ ወይም የዓይን ምስክር የተናገረ ተመዝግቦ ካለ እኔ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። እኔ የዓፄ ምኒልክን ባህሪ ሳስበው እንደዚህ የሚያደርጉ

አይመስለኝም። በተባለው ወቅት ንጉሡ ያንን ጦር አላዘዙም። ራስ ዳርጌ ነበሩ የበላይ። ራስ ዳርጌም ቢሆን ይህንን የሚያደርጉ ሰው አይደሉም፤ ትልቅ ጀግና ነበሩ። ደግሞም እኮ ጡት መቁረጥ የኢትዮጵያን ባህሪ አይደለም። አረብ ሊያደርግ ይችላል። ኢትጵያውያን ጀግኖች የእህቶቻቸውን ጡት አይቆርጡም። ባይሆን ወስደው ሚስት ያደርጋሉ እንጂ። ምንአልባትም ጀግንነታቸውን ለማሳየት የወንድ ብልት ሊቆርጡ ይችላሉ። ከወንድ ጋር ተዋግተው ሳለ ምን ስላደረጉ ነው የሴቶቹ ጡት የሚቆረጠው? ስለዚህ ዓፄ ምኒልክ ጡት ቆርጠዋል የሚባለው ጉዳይ በመላ ምትም አያስኬድም።

በእኔ እምነት ይህንን የሀሰት ታሪክ የሚነዙት ከኦሮሞዎች ይልቅ ሌሎች ዓፄ ምኒልክን የሚጠሉ አክራሪ ሰዎች ናቸው ብዬ ነው የማምነው። ዘላለም ኦሮሞና አማራ እንዲቃቃሩ የሚደረግ የተንኮል ሸፍጥ ነው። ሐውልት ከሚተከል ይልቅ በዚያ ቦታ ፋብሪካ ቢተከል ለዚያ ህዝብ ይጠቅመው ነበር። ስለዚህ ይህ ጉዳይ የምኒልክን ስም ለማጥፋት ታስቦ የተደረገ ነው የሚል እምነት አለኝ። እንደውም ዛሬ የምንጠቀምብትን ከባቡሩ ጀምሮ መሰረተ ልማት በዘረጉት ለአገራችው ብዙ ቁም ነገር የሠሩ ንጉሥ ናቸው። በዚያም የጣሊያን ባሪያ እንዳንሆን ነፃነታችንን ያረጋገጡልን የመላው ጥቁር መሪ የሆኑ ትልቅ ሰው ናቸው። ደግሞም በአገራችን ከነበሩት መሪዎች በላይ ሰብአዊ ርህራሄ ባህሪያቸው ይታወቃሉ። ስለዚህ ስለእርሳቸው የሚባለው ነገር

ከእውነት የራቀ ነው የሚል እምነት አለኝ።

አዲስ ዘመን፡- የሀገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይመለከቱታል?

ፕሮፌስር ፍቅሬ፡- ጥሩ ነው የሚል አመለካከት አለኝ። ባለፉት 40 ዓመታት ሀገር ተንቃ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለችም፤ ኢትዮጵያዊስ ማነው? ኢትዮጵያዊነት አይረባም እየተባለ ሲጣጣል ከርሞ አሁን «ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን» የሚሉ

መሪዎች ተፈጥረዋል። እነዚህ መሪዎች ደግሞ በፍትህ፣ በዴሞክራሲ፣ በሀገር እድገትና ብልፅግና ያምናሉ። ከሙስና ነፃ የሆኑ ናቸው። የታሰሩ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ አድርገዋል። ከውጭ ያሉትንም ጭምር ጠርተው ‹‹ውጭ ከምትሞቱ መጥታችሁ ተሳተፉ›› ብለው ዕድል ሰጥተዋቸዋል። በሃሳብ ልዕልና ካሸነፉ ስልጣን የሚይዙበት ምቹ ሁኔታ ፈጥረውላቸዋል። ወታደሩም

ከሚለው መጽሃፌ ውጭ የተሰወረውና ያልተነገረው «የአይሁዳውያንን የኢትዮጵያውያን ታሪክ» የሚል መጽሃፍ ጽፌ በይብራይስጥኛ ተተርጉሟል በእንግሊዘኛም ጽፌዋለሁ።

«የአማራና ኦሮሞ እውነተኛ የዘር ምንጭ»

‹‹ደሸት››

ወይም ደሴት የሚባለው ንጉስ የኢትዮጵ ዘር የሆነው 3ሺ600 ዓመት አካበቢ እሱ አራት ወንድ ልጆችን ወለደ። እነሱም መንዲ፣ መደባይ፣ ጂማ ፣ ማጂ የሚባሉ ሲሆኑ ማጂ አማራን ወለደ ። እነዚህ ስሞች አሁንም አሉ። መንዲ ወለጋ ውስጥ የቦታ ስም ነው።

ወለደ። እነሱም መንዲ፣ መደባይ፣ ጂማ፣ ማጂ የሚባሉ ሲሆኑ ማጂ አማራን ወለደ ። እነዚህ ስሞች አሁንም አሉ። መንዲ ወለጋ ውስጥ የቦታ ስም ነው። መደባይ ከትግራይ ወረዳ ውስጥ መደባይ ዛና መደባይ ወለል ይባላሉ። መደባዮች ራሳቸው የደሸት ዘር እንደሆኑ አያውቁም ትግሬ ነን ነው ብለው የሚያስቡት የሚናገሩት ትግርኛ በመሆኑ ነው። ጅማና ማጂም የቦታ ስም ናቸው። ሁሉም የደሸት ልጆች ናቸው። ጎጃም ላይ ሳሉ ሱባ የሚባል ቋንቋ ነበር የሚናገሩት። በመጸሐፌ ሽፋንና ውስጥ ፊደሎቹ አሉ። ከ3200 ዓመት በፊት ቀድሞ ካሉ ህዝቦች ከነጋፋት ጋር ሲቸግራቸው መጋፋትና መዋጋት ወደ ሸዋ መጡ የአማራ ልጆች ኦሮሞዎች ወገኖዎቻቸውን ተከትለው። ጅማ የወለዳቸው ኦሮምኛ ሲናገሩ ኦሮሞ ተባሉ። ሌሎቹ ደግሞ ሱባን ትተው አማርኛ ሲናገሩ አማራ ናቸው ተባሉ። ሁለቱም ግን ዘራቸው የደሸት ልጆች ናቸው። ጀማ የሚባለው ልጅ ደግሞ አሁንም ጀማ የሚባል ወንዝ አለ። ስለዚህ በአጠቃላይ ያኔ የነበሩ ሰዎች ናቸው። ከውጭ የመጣ የለም። አሁን እኔ አሜሪካን አገር እኖራለሁ አርባ ዓመት ቆይቼ ስመጣ ኢትዮጵያዊነቴን ልክድ አልችልም። ቋንቋችን 84ቢሆንም ይበታትነናል እንጂ አንድ አያደርገንም። ከልዩነቶቻችን ይልቅ አንደነታችን ላይ ማተኮር ይገባናል።

አዲስ ዘመን፡-በመጽሐፍዎ ላይ ኦሮምኛ ቋንቋ የግዕዝ ፊደላትን ቢጠቀም አምስት የተለየዩ ጥቅሞች እንደሚኖሩት ዘርዝረዋል። ከእነዚህ ውስጥም ከላቲን ይልቅ ግዕዝን መጠቀሙ ኦሮሞዎችን እንደ ባዕድ ከመታየት እንደሚያድናቸው ጠቅሰዋል። ይህን ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- ምን ማለቴ እንደሆነ ገብቶሻል። ግን ከእኔ አፍ ከሆነ መስማት የፈለግሽው ልነግርሽ እችላለሁ። እንደምታውቂው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በግዕዝ ፊደል ነው የሚጽፈው። በሌላ በኩል ኦሮሞዎች፣ ሱማሌዎችና አፋሮች በላቲን ነው የሚጽፉት። ይህ መሆኑ ከሌሎች ወገኖች ዘንድ እንደ ባዕድ እንዲታዩ ያደርጋቸዋል። ስለዚህ ይሄ ደግሞ ጥሩ አይደለም። ከሰው ይለያቸዋል፣ ያርቃቸዋል፣ ያገላቸዋል። ሌሎችም ተጨባጭ ምክንያቶች አሉኝ። ለምሣሌ በላቲን ከመጻፍ ይልቅ በግዕዝ ቋንቋ ቢጻፍ በጥቂት ቃላት ሃሳብን መግለጽ የሚቻል በመሆኑ ጊዜን፣ ገንዘብንና ጉልበትን ይቀንስልናል። አንዳንዱ ቃላት እንዳውም «ጨ» የለውም። በፊት የሚሰጠው ምክንያት የአማርኛ ፊደል እንደማይበቃ ተደርጎ ነው። ግን በቀላሉ ድምፆችን መጨመር የሚቻልበት መንገድ አለ።

ግን ቀደም ያሉት ፖለቲከኞች እንደ ኃይሌ ፊዳ ያሉ ሰዎች የግዕዝን ፊደል የአማራና የትግሬ ሀብት ብቻ አድረገው ያምኑ ስለነበር «በእነሱ ፊደል አንጽፍም የእነሱንም ቋንቋ አንናገርም» ብለው ያደረጉት ነገር ነው።በጣም የሚገርመው ኤርትራ ስትገነጠል ቋንቋዋንም ይዛ ነው የተገነጠለችው እስካሁንም የእኛን ፊደል ነው የምትጠቀመው። ቢገባን የግዕዝ ፊደል የኦሮሞም ነው። ስለዚህ ኦሮሞ እህትና ወንድሞቼን የምመክረው በተለያየ ምክንያት ከሌሎች ኢትዮጵያን ጋር እንድንቀራረብ በአገራችን ፊደል መጻፍ ይገባናል የሚል ነው።በተጨማሪም መታወቅ ያለበት ጉዳይ ኦሮሞዎች የራሳችን ፊደል በሆነ በግዕዝ መጻፋችን በኢትዮጵያዊነታችን ክብርና ኩራት ያስገኝልናል። ምክንያቱም ከአፍሪካ የራሳችን ፊደል ያለን እኛ በመሆናችን። በተለይም ኦሮሞ የኢትዮጵያ ልጅ ሆኖ መገለል የለበትም። ወደ ቀድሞው መመለስ አለበት። እንደ ችግር የሚነሱት ድምፆችም ቢሆኑ ሁሉ ዶክተር አበራ ሞላ በሚባል ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ተቀርፀዋል። ስለዚህ ቀና መንፈስ ካለ መመለስ ይቻላል ማለት ነው። ይሁንና በአሁኑ ወቅት ምንአልባት ይህንን ከቁምነገር የቆጠረው ሰው ላይኖር ይችላል። ወደፊት ግን አገር ስትረጋጋ የማይቀር ነገር ነው ብዬ አምናለሁ።

ወደፊት እመጣና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየዞርኩ

የተለየዩ የትምህርት አይነቶችን ለማስተማር ሃሳብ አለኝ። ደግሞም ቴአትር ቤት በሌለበት አካበቢ ቴአትር ቤቶችንና የባህል ማዕከል ለመክፈት እቅድ አለኝ።

የዘመን

እንግዳ >>፰

ቢሆን ከሁሉም የተውጣጣ እንጂ ከአንድ ብሔር ብቻ እንዳይሆን ያንንም ከልሰው በፀጥታውም ያለውን ሁሉ ግፍ የሚሰሩና የሚያሰቃዩ መርማሪዎችን በሕግ እንዲጠየቁ አድርገዋል። ወደፊት ለመራመድ በሰላም በፍቅር በአገር ግንባታ በነፃነት እንድንራመድ እያደረጉ ናቸው። ከእነርሱ ጋር ተባብሮ ኢትዮጵያ ወደ ፊት እንድትራመድ ማድረግ ይገባናል።

አዲስ ዘመን፡- ባለፉት 27 ዓመታት የብሔርተኝነት አስተሳሰብ ስር ሰዶ ቆይቷል። አሁን እርስዎ የሚያቀነቅኑትን ኢትጵያዊነት መመለስ እንዴት ይቻላል? ምንስ መሥራት ይገባል?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- እኔ የምመክረው ኢትዮጵያዊነትን ማስፋፋት ነው። ምክንያቱም በጎሳ ላይ የተመሰረተው ክልል አልበጀም። ስለዚህ የጥፋት ሁኔታን ስለፈጠረ አሁን ኢትዮጵያዊነት ላይ አተኩረን መሥራት ይገባናል። የአንድ እናት አባት ልጆች መሆናችንን ተገንዝብን ያለፈውን ትተን ወደፊት መራመድ ይገባናል። ደግሞም በሰላም በፍቅር መኖራችን ለሁላችንም ነው የሚበጀው። ከጥፋት ያድነናል። ለዚህ ኢትዮጵያዊነት በደንብ መሰበክ አለበት። በትምህርት ቤት ውስጥ ማስተማር አለብን። ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጽባርቁ መጽሐፍት በደንብ መነበብ አለባቸው። መገናኛ ብዙኃንም ማስተማር አለባቸው።

አዲስ ዘመን፡- በኪነጥበብ ዘርፉ ምን ያህል ሥራዎች አበርክተዋል? በቀጣይስ ምን ለመሥራት አቅደዋል?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- በርካታ ናቸው። በልጅነቴ አገር ውስጥ ሳለሁ አዲስ ዘመንን ጨምሮ በበርካታ ጋዜጦችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ግጥሞቼ ይወጡ ይነበቡ ነበር። «ወላለ» የሚባል አጭር ልቦለድም ጽፊያለሁ። መታወቅ ስጀምር በቴሌቪዥን ድራማ እሰራ ነበር። በቴአትር በእንግሊዘኛና በአማርኛ ያሉት ሲደመሩ ወደ 30 የሚደርሱ ተውኔቶችን ጽፊያለሁ። ግጥም ከልጅነቴ ጀምሮ የጻፍኳቸው ወደ አስር ቅጽ ሊሆኑ ይችላሉ። የእንግሊዝኛ ደግሞ ፍልስፍና ላይ የሚያጠነጥን ድራማ ጽፌያለሁ። ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል። ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የኪነጥበብ ማህበራት ድርጅቶች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቻለሁ። በታሪክ በኩልም «የአማራና ኦሮሞ እውነተኛ የዘር ምንጭ» ከሚለው መጽሐፌ ውጭ የተሰወረውና ያልተነገረው «የአይሁዳውያንን የኢትዮጵያውያን ታሪክ» የሚል መጽሐፍ ጽፌ በይብራይስጥኛ ተተርጉሟል፣ በእንግሊዘኛም ጽፌዋለሁ። ከፍተኛ አድናቆት አስገኝቶልኛል። ሦስተኛ «ይህች ናት የኔ ምድር» የምትል የግጥም መድብል በሲዲም ጭምር አስቀርጬዋለሁ።

አዲስ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር አባል ነበሩ? የውጭ አገር የትምህርት ዕድልስ ያገኙበት አጋጣሚ ምን ነበር?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- አይ እኔ ውጭ አገር ስለምኖር ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም። የጀርመን ደራሲያም ማህበር አባል ነበርኩ። ግን ሰዎች ማህበር ውስጥ ከተውሃል ብለውኛል። የአባልነት መዋጮም አልከፍልም። በስብሰባቸውም ላይ ተገኝቼ አላውቅም። ምንአልባት ወደፊት ልገባ እችላለሁ። የውጭ ዕድሉንም ያገኘሁት 12ኛ ክፍል እንደጨረስኩ በግጥም ተወዳድሬ ነው። ሁለተኛው ደግሞ «ወለለ» የተባለው ግጥም ተተርጎሞ ሩሲያ የትምህርት ዕድል አግኝቼአለሁ። በነገራችን ላይ እኔ የመጣሁት ከሀብታም ቤተሰብ አይደለም፤ ግን በእግዚአብሔር ቸርነትና በእኔ ትጋት እዚህ ልደርስ ችያለሁ።

አዲስ ዘመን፡- ወደ አገርዎ ተመልሰው የማገልገል ዕቅድ የለዎትም?

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- አለኝ። ወደፊት እመጣና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየዞርኩ የተለየዩ የትምህርት አይነቶችን ለማስተማር ሃሳብ አለኝ። ደግሞም ቴአትር ቤት በሌለበት አካባቢ ቴአትር ቤቶችንና የባህል ማዕከል ለመክፈት ዕቅድ አለኝ።

አዲስ ዘመን፡- መሥሪያቤታችን ድረስ በመምጣት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግዎ በዝግጅት ክፍሉና በአንባቢዎቼ ስም ከልብ አመስግናለሁ።

ፕሮፌሰር ፍቅሬ፡- እኔም አመሰግናለሁ።

Page 9: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

9የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ዶሴ

ተናጋሪው አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም 9>>

መልካምስራ አፈወርቅ

እንደ መነሻ

ህንዳዊቷ ወይዘሪት ሚኒክሲ ጄቴላን ኢትዮጵያን እንደ ሀገሯ ተቀብላ መኖር ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህ እውነት ደግሞ የእሷ ብቻ አይደለም። አብረዋት የሚኖሩ ቤተሰቦችዋ ጭምር እንጂ። እነርሱ ኢትዮጵያን «ውድ ሀገራችን» ሲሉ ይጠሯታል።ኢትዮጵያና ሀገራቸው ህንድ በርካታ ዓመታትን የተሻገረ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ያውቃሉ። ይህ በጎነት የወለደው ትስስርም ዛሬ ለእነርሱ ተርፎ በሀገረ ኢትዮጵያ እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗል።

ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍና ዝቅ ያሉ ስፍራዎች ለህንዳውያኑ ሩቅ አይደሉም። መሀል ፒያሳን ይዞ ዙሪያ ገባ ያለው አካባቢም የእነዚህ ዜጎች መገኛ ነው። በቀደምቶቹ የፒያሳ ቤቶችና ዕድሜ ጠገብ ህንጻዎች ህንዶች ቤተሰብ መስርተው፣ ልጆች አፍርተው ኖረዋል።

ሁለቱን ሀገራት ለዓመታት ያስተሳሰራቸው የዕውቀት ዕትብት ህንዳዊ ምሁራን በበርካታ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ለኢትዮጵያውያን ዕውቀትን እንዲዘሩ ምክንያት ሆኗል። ዛሬም እነዚህ ዜጎች ከአዲስ አበባ መሀል እምብርት አልራቁም። ልክ እንደ ቀድሞው ሁሉ በነበረው ልምድና ህይወታቸው ከከተማዋ ነዋሪ ጋር ተቀላቅለው ሰላማዊ ኑሯቸውን ቀጥለዋል።

የጄቴላን ቤተሰቦችም ቢሆኑ ከዚህ የዘለለ ታሪክ የላቸውም። እንደ አብዛኞቹ ወገኖቻቸው ኢትዮጵያን «ሀገራችን» ሲሉ ይኖሩባታል። እስካሁን የዚህች ሀገር ቆይታቸው መልካም የሚባል ነው። የራሳቸውን ንብረት አፍርተው በሰላም ኖረዋል። ልጆች ወልደው አሳድገዋል፣ አስተምረዋል። መተዳደሪያ የሆናቸው የንግድ መደብርም በርካታ ጎብኚዎች አሉት። እስከዛሬ በንግድ ውሏቸው የገጠማቸው ችግር የለም።

እነርሱ ኢትዮጵያውያን ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባዮች መሆናቸውን ያውቃሉ። የአንዳንዶቹ ልጆችም በትምህርት ቤቶቻቸው ባልንጀሮች ሆነው አብረው ይውላሉ። እነርሱም ከአዋቂዎቹ ጋር በጉርብትና ይገናኛሉ። የሁለቱ ሀገራት ባህልና ልምድ እምብዛም ያለመራራቅ ደግሞ ባዕድነቱን አሳስቶታል። ይህ መሆኑም በመደብራቸውና በመኖሪያቤታቸው ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ዓመታትን ከነሱ ጋር እንዲዘልቁ አስችሏል።

ቴዎድሮስ አደባባይ የሚገኘው መኖሪያቤታቸው ከንግድ መደብራቸው ብዙ አይርቅም። ይህ መሆኑም ስራውን በአግባቡ እንዲወጡ አግዟቸዋል። ሁሌም ከስራ መልስ ቤተሰቡ ወጣ ብሎ ይዝናናል። በዚህ ሰአት የሚጠየቁ ዘመዶች፣ የሚጎበኙ ህሙማንና ሌሎችም ካሉ በቂ ጊዜ ይሰጣቸዋል። እንዲህ በሚሆን ጊዜም የቤቱን አባወራና እማወራ ጨምሮ ሁለቱ ልጆቻቸው አይለያዩም። ወንዱ ልጃቸው መኪናውን እያሽከረከረ፣ ሴቷ ልጃቸው ጄቴላንም ከጎናቸው እያወጋች ያሻቸው ደርሰው ይመለሳሉ።

እስከዛሬ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ከነሰላማቸው ጠብቀዋቸዋል። ካሰቡት ቦታ በቸር ደርሰው የሚመለሱት ያለስጋት ነው። በሰፈርም ቢሆን ከሌሎች ነዋሪዎች አይለዩም። በሰፊው የመኖሪያ ግቢያቸው ዓመታትን ቢያሳልፉም ባዕድነትና ባይተዋርነት ተሰምቷቸው አያውቅም። አዎ! ኢትዮጵያ ማለት ለእነርሱ ሁለተኛዋ ሀገራቸው ናት። ልክ እንደ እናት ምድራቸው ህንድ ሰርተው የሚያድሩባት፣ ውለው የሚሰባሰቡባት እልፍኛቸው ሆናለች።

የመኖሪያ ግቢያቸው ሁሌም በዘበኞች ይጠበቃል። የጥበቃ ሰራተኞቹ በፈረቃ እየተለዋወጡ ያድራሉ። የስራ ባህርይው ወጣቶችን ከዕድሜ ጠገቦች የሚለዋውጥ ስለመሆኑ የቤተሰቡ አባላት አይጠፋቸውም። ይህ ደግሞ ይበልጥ ደህንነት እንዲሰማቸው አድርጓል። በሰፊው ግቢያቸው ጥሩ እንቅልፍን ጠግበው የሚያድሩት የእነሱን ጥበቃ አምነው ነው።

የስልሳ ስድስት ዓመቱ አዛውንት አቶ ደምሴ ገዳ ተረኛ በሚሆኑበት ጊዜ ዙሪያ ገባውን ይቃኛሉ። ይህ ዓይነቱ ጥንቃቄ በስራ ቆይታቸው ያዳበሩት ልምድ ነው። ለተቀጠሩበት ሙያና እንጀራን ለሚያገኙበት ውሎ አይቀልዱም። ከሌሎች ወጣቶች ይልቅ በእርሳቸው ላይ የሚኖረውን እመኔታ ያውቁታልና ሁሌም በስራቸው እንደተጠነቀቁ ነው።

ሂደትብርዳማው የጥቅምት ወር ተጠናቆ የህዳር

ወር ገብቷል። ይህ ወቅት ከውርጭና ቅዝቃዜ አይርቅም። በማለዳ ወጥተው በምሽት ለሚመለሱ ሁሉ ቅጣቱ የከፋ ነው። እያንቀጠቀጠ፣ እያንዘፈዘፈ ጉልበቱን ያሳያል።

የረፋዷ ጸሀይ ደርሳ ሙቀቷን በስሱ እስክትለግስም ከሰው አንጀት ፈጥኖ አይወጣም። ይህ አይነቱ ጊዜ በጥበቃ ስራ ለሚሰማሩትን በእጅጉ ይፈትናል። አዳራቸውን በደጅ፣ ትኩረታቸውን በበራፍ ለሚያደርጉ ብርቱዎችም ውርጩ የየዕለት ጓደኛቸው ይሆናል።

ህዳር 12ን አብዛኞች በተለየ ቀን ያስቡታል። ዕለቱን አስታውሰውና የሚሆውን አድርገው አካባቢውን በጭስ የሚያጥኑ ጥቂቶች አይደሉም። በዚህ ቀን ከተማው ሁሉ በጥቁር ጭስ ዳመና ይታፈናል። የመንደሩ ቆሻሻ ሁሉ ተጠራርጎ በእሳት እየጋየም ዶጋ አመድ ይሆናል። ህዳር 12 ቀን 2002 ዓ.ም የሆነውም እንዲሁ ነው። በዕለተ ህዳር ሚካኤል ፒያሳና አካባቢውን ይዞ መላው አዲስ አበባ ቆሻሻውን ሲያቃጥልና ጭሱን ሲያቀረና ውሏል።

በአንድ ጥግ ተቀምጠው በትኩረት የሚያወጉ ቡድኖች ግን ይህ ሁሉ አላሳሰባቸውም፤ አላስጨነቃቸውም። ለእነሱ እንዲህ አይነቱ ወግና ልማድ ምናቸውም ሆኖ አያውቅም። አሁን በዋዛ የማይተውት ታላቅ ጉዳይ ላይ ይገኛሉ። ይህን ለማሳካት ደግሞ ዛሬን ጨምሮ በርካታ ጉባኤዎችን ተቀምጠዋል። ላሰቡት ዓላማ የሚውሉትን ዕቃዎች ለማዘጋጀት ጊዜ ወስዶባቸዋል። በሀሳብ ለመዛመድና ስምምነት ለመድረስም እንዲሁ። አሁን ባሉት ቁሶች ላይ አዲስ ለማከል፣ በጎደሉትም የተሻሉትን ለመተካት ምክክር ይዘዋል።

አምስቱ የቡድን አባላት ለምሽቱ ተግባራቸው የሚያስፈልጉትን ሁሉ በአይነት ለይተው ስራ ተከፋፍለዋል። ሀላፊነቱን ሲረከቡም ምን ማድረግ

መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተመርቷል። ዶሴው የሚናገረው ታሪክ ግን ዛሬም ድረስ አለ። የተወሳሰቡ ወንጀሎች ከተራቀቁ የምርመራ ሂደቶች ጋር ዶሴው ውስጥ ናቸው። በዚህ ዓምድ ታሪካቸውን ልንሰማ የፈቀድናቸውን ዶሴዎች እንዲናገሩ ገልጠናቸዋል። የእውነተኛ ባለታሪኮችን ስም ማህበራዊ ሓላፊነት ወስደን ለደህንነታቸው ሲባል ቀይረናቸዋል።

እንደሚኖርባቸው ምክር ተለዋውጠዋል። ለዚህ ደግሞ ከእስከዛሬው ተሞክሯቸው ልምድን በትዝታ እየጨለፉ እቅዳቸውን በጥንቃቄ ነድፈዋል። በያዙት አጀንዳ ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች፣ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ችግሮችና ስለሚወሰዱ ፈጣን ርምጃዎች ሁሉ አስቀድሞ ታስቦባቸዋል።

ለዕቅዳቸው ስኬት ደግሞ ተባባሪ ባለውለታዎቻቸውን አልረሱም። እነርሱን በቅርበት መያዙ መውጫ መግቢያውን ለማወቅ ያግዛል። ለእንዲህ አይነቱ ታላቅ ጉዳይም ሁነኛ የመረጃ ስንቆች ይሆናሉ።ያለነርሱ ዓላማቸው የሳሳ፣ ውጥናቸው የኮሰሰ እንደሚሆን ተረድተዋል። እስከዛሬ በመረጃ አቀባዮቻቸው እየታገዙ ብዙ እቅዶቻቸውን አሳክተዋል። ከጥቅማቸው እያጋሩ፣ ከቀመሱት እያላሱ በርካቶቹን ድልድይ አድርገው ተሻግረዋል።

አሁንም ስራቸውን ያለኮሽታ ለማጠናቀቅ ያሰቡትን ውስጥ አዋቂ በእጃቸው ይዘዋል። በእርሱ እየተመሩ መንገዱን ያለስጋት ይጀምሩታል። በሚያልፍበት እያለፉም ካሰቡበት ይደርሳሉ። ይህን ታላቅ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ልበ ደንዳና መሆን ያስፈልጋል። ይህ ስሜት ደግሞ ሁሌም ከእነሱ ጋር የኖረ ነው። የሁልግዜው ጭካኔና ድፍረታቸው ደብዝዞ አያውቅም።

ጄቴላንና ቤተሰቦቿ ስራቸውን አጠናቀው በጊዜ በቤታቸው ታድመዋል። ከትንሽ የዕረፍት ቆይታ በኋላ ደግሞ ከቤት የሚወጡበት ጉዳይ አላቸው። ጊዜው ከምሽቱ አንድ ሰአት ከሰላሳ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ ሰዓት ከቤት ርቆ ጉዳይን ለመከወን ይከብዳል። ቤተሰቡ ግን ይህ አላስጨነቀውም። ያሻው ስፍራ ደርሶ ለመመለስ የቤት መኪናውን ይጠቀማል።

አዛውንቱ የጥበቃ ሰራተኛ አባ ደምሴ ቤተሰቡ ከወጣ በኋላ እንደወትሯቸው ዙሪያ ገባውን ጎብኝተው ተመልሰዋል። የዋና በሩንም ከዕለቱ ወጣት ተረኛ ዘብ ደነቀ ጋር ተባብረው ዘግተዋል። ትንሹ የእግረኞች በር ቁልፍ ስለሌውና ጠባብ ስለሆነ እንደነገሩ መለስ አድርገውታል። ከመግቢያው ትይዩ ተቀምጠው ደጁን እየተቆጣጠሩ ነው። ብርዱ አንጀታቸው ሲገባ ይታወቃቸዋል።

አባ ደምሴ በድንገት ከበስተኋላቸው አንድ ድምጽ የሰሙ መሰላቸው። እሱን ተከትለው ዞር ከማለታቸው ግን ከአስደንጋጩ እውነታ ጋር ተጋፈጡ። አምስት ሰዎች ወደ እርሳቸው እየመጡ

አንደኛው ባለጭንብል ሾፌሩን ከጋቢናው እየጎተተ አወረደው። ይህኔ እናት አባቱ በድንጋጤ እየጮሁ ሊያስቆሙት ሞከሩ። ነገሬ አላላቸውም። የልጁን አንገት እንቆ እንደያዘ ከመሬት ላይ አንጋለለው። ወዲያው ፕላስተር ይዘው የቆሙት ባልንጀሮቹ በአፉ ላይ ለጥፈውበት ወደቀሪዎቹ ቤተሰቦች አመሩ። ጄቴላንንና አዛውንት እናትና አባቷን በተመሳሳይ ዝም ለማሰኘት ጊዜ አልወሰደባቸውም።

የምሽቱ እንግዶች መላውን ቤተሰብ በገዛ ቤታቸው ተቆጣጥረው ያሻቸውን ማድረግ ይዘዋል። ሁሉንም በሲባጎ ገመድ ከወንበር ጋር ጠፍረውም በስል ጩቤዎቻቸውና በያዙት ሽጉጥ እያስፈራሯቸው ነው። ከዚህ በኋላ ቀጣዩን ስራ ለመከወን መንገዱ ቀና ነው። የሚጠበቁት ተይዘው ግቢው ጭር ብሏል። ትልቁ ቤት ዘልቀው ወደ መኝታ ቤት ሲያመሩ ከዘመናዊ ቁምሳጥኖች ጋር ተፋጠጡ።ጊዜ አልፈጁም። የወርቅና የአልማዝ፣ ጌጣጌጦች የሚገኝበትን ፈልቅቀው ባዘጋጁት ሻንጣ መክተት ጀመሩ።

በርካታ የወርቅ ካቴናዎች፣ ጉትቻዎች፣ ውድ ዋጋ ያላቸው አርቴፊሻል ጌጦች፣ የእጅ ሰዓቶችና ሌሎችም ከእጆቻቸው ገቡ። ወርቅ ቅብ ዕቃዎችና የጸሎት መጽህፍቶቹንም አልማሯቸውም። ሰላሳ አምስት ሺህ የኢትዮጵያ ብርና ሌሎች የውጭ ሀገራት ገንዘቦችንም ሰበሰቡ። ሌሎች ቁምሳጥኖችን ከፍተው የሚፈልጉትን በአይነት እየለዩ አከማቹ። ሁሉን ጨርሰው የልባቸው ሲሞላም በውስጥ አዋቂያቸው ዘብ እየተመሩ በገቡበት ወጥተው ከአካባቢው ተሰወሩ።

የፖሊስ ምርመራ ሲነጋ ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ ከስፍራው

ደረሰ። የሆነውን ተመልክተውና የተደረገውን አረጋግጠው መረጃዎችን ሰበሰቡ። የአሻራ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ሁሉ በጥንቃቄ እየመዘገቡ ከመዝገባቸው ከተቱ። ተበዳዮችን ጨምሮ በአካባቢው ለምስክርነት የሚበጁ ማስረጃዎች ሁሉ አንድ በአንድ ተፈልገው ሰፈሩ።

መዝገቡን የያዘው የምርመራ ቡድን በቴዎድሮስ አደባባይና አካባቢው የሚጠረጠሩ ደጋጋሚ ወንጀለኞችን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። እነርሱን መነሻ አድርጎም በርካታ እውነታዎችን መለየት እንደሚቻል ያምናል። ይህ ሁሉ ከምርመራው ክፍል አንዱ ነው። ይህ ብቻ ግን በቂ አይሆንም። በቡድን የተደራጀ የፖሊስ ሀይል ጉዳዩን በጥንቃቄ ይዞታል። ድርጊቱ ሁሌም ሰላማዊነቷን ለሚመሰክሩላት ኢትዮጵያና አምነዋት ለሚኖሩባት የውጭ ዜጎች ሁሉ በጎ ገጽታን የሚያበላሽ ነው። እናም ስለ ሀገሪቱ መልካም ስም ሲባል ተጠርጣሪዎቹ በፍጥነት ሊያዙ ግድ ይላል።

የምርመራ ቡድኑ ሳይሰለች መረጃ ማሰባሰቡን ተያይዞታል። አሁን የቀን ከሌቱ ድካም ፍሬ ይዟል። በጥርጣሬ የተያዙት፣ ከተያዙትም እውነቱን ያመኑት፣ድርጊቱን ሁሉ ለፖሊስ ተናዘዋል። በምርመራው ሂደት ወጣቱ ጥበቃ ደነቀ ሀብቱ አስራ አምስት ሺህ ብርና የተለያዩ ጌጣጌጦችን ከቀበረበት ጉድጓድ አውጥቶ አስረክቧል። ፖሊስ ሌሎችንም መረጃዎች አጠናክሮ መዝገቡን ለክስ አቅርቧል። ተከሳሾች በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጧል።

ውሳኔ መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም ማለዳ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ተሰይመዋል። ክስ ከቀረበባቸው አምስት ተከሳሾች መሀልም የሶስቱን ለማየት ተዘጋጅተዋል። ደበበ ዘሩ፣ ጌታነህ ብርሀኑና ደጉ በላቸው እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንድ እስከሶስተኛ ተከሳሾች ሆነው ቀርበዋል።

የመሀል ዳኛው ዛሬ ከመጨረሻ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የክሱን ዝርዝር እያነበቡ ነው። ሶስቱ ግለሰቦች በውጭ ሀገር ዜጎቹ ላይ በፈጸሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል አንደኛ ተከሳሽ በአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት፤ ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በአስራ አንድ ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።

ባጐረስኩ ተነከስኩ

ነው። ሁሉም በአለባበሳቸው ይለያሉ። ሳንጃና ጩቤ ታጥቀው ፊታቸውን በጭንብል ሸፍነዋል። አባ ደምሴ ልክ እዳይዋቸው ለመጮህ ሞከሩ። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን በፈርጣማ እጆች ታንቀው የኋሊት ወደቁ።

ባለጭንብሎቹ ሽማግሌውን መሬት ለመሬት እየጎተቱና ተቀባብለው እያንገላቱ ወደ ጓሮ ወሰዷቸው። በጀርባቸው አስተኝተውም በወፍራም

ፕላስተር አፋቸውን አሸጉት። ሁለቱን እጆቻቸውን ወደ ኋላ የፊጥኝ አስረው ወደ ዕቃ ማስቀመጫው ኮንቴነር አስገቧቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን ለአፍታ እንኳን እረፍት እልሰጧቸውም። በእርግጫ እያሽቀነጠሩ፣ በጥፊ እያቃጣሉ አሰቃይ ዋቸው።

ጥበቃው የእነርሱን ድርጊት መቃወማቸው አናዷቸዋል። ለመጮህ ማሰባቸውንም ከድፍረት ቆጥረውታል። እናም «ይገባቸዋል» ያሉትን ማስፈራራትና ከባድ ምት እያሳረፉባቸው ነው። ከመንገላታቱና ከድብደ

ባው በኋላ አዛውንቱ ጥበቃ ስቃያቸውን ውጠው በዓይናቸው መታዘብ ይዘዋል። ከሰዎቹ መካከል አንደኛውን በድምጽ የሚያውቁት መስሏቸው ደነገጡ።

በእርግጥም አልተሳሳቱም። ፊቱን ሸፍኖ ድርጊቱን የሚያስተባብረው ወጣት አብሯቸው ያመሸው ተረኛ ዘብ ነበር። አዎ! ጥበቃው ደነቀ ለምሽቱ እንግዶች ውስጥ አዋቂያቸው ነው። እስካሁንም በእርሱ ምሪት ታግዘው ያሰቡትን አድርገዋል።

ጊዜው እየገፋ ጨለማው እየበረታ ነው። ከሶስት ሰዓት በኋላ የፒያሳ ጎዳናና አካባቢው ከእግረኞች ግርግር ይታቀባል። ከወዲያ ወዲህ የሚሮጡ የጎዳና ልጆችና ከየመዝናኛ ቤቱ ጎልቶ የሚወጣ ሙዚቃም ስፍራውን ተቆጣጥሮት ያመሻል። ከፒያሳ አፋፍ ቆልቆል ብለው ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ሲሻገሩ ደግሞ ይበልጥ መቀዛቀዙ ይታያል። አብዛኞቹ ህንጻዎች የቀን ንግድ ቤቶችና የመኖሪያቤቶች በመሆናቸው ተዘግተው ያመሻሉ።

ከምሽቱ አራት ሰዓት እያለፈ ነው። የስፍራው ጭርታ ጨምሯል፤ የተለመደው ቅዝቃዜ ጀምሯል። በድንገት ግን የጨለማውን ግዝፈት ያሸነፈ ረጅም ብርሀን ታየ። እሱን ተከትሎም ጭርታውን የሚሰብር የመኪና ጡሩንባ ተሰማ። ይሄኔ ፊቱን በፎጣ የጠመጠመ አንድ ሰው እየተጣደፈ በሩን ወለል አድርጎ ከፈተው። ወዲያው ከደጅ የቆመው መኪና ወደግቢው ዘለቀ። ቦታ ለመያዝም አቅጣጫውን ቀይሮ ወደማደሪያው ተጠመዘዘ።

አሁን አምስቱ ሰዎች ከተደበቁበት ጥግ ወጥተዋል። ሁሉም ፊታቸውን በጭምብል ሸፍነው በመከላከያ ሰራዊት ልብስ ይታያሉ። በእጃቸው የያዙት የፖሊስ ዱላ እህል ውሃ አያሰኝም። ያገኘውን ሁሉ ለመጨርገድ የተዘጋጀ ይመስላል። ከነርሱ መሀል ሁለቱ ድንገት መዘው ያወጡትን ቢላዋ እያብለጨለጩ ነው። ከመካከላቸው አንዱ ማጭድ መሳይ ባለጥርስ ቢላዋውን እያወዛወዘ ወደፊት ቀርቧል።

በድንገቴው ከበባ ብርክ የያዛቸው አራት ቤተሰቦች ባሉበት ሆነው እየተንቀጠቀጡ ነው። ጄቴላን የመኪናውን በር የከፈተላትን ወጣት ጥበቃ ለይታዋለች። ሁሌም ፊቱን የሚሸፍነው ወጣት ደነቀ ነው። ሌሎቹም ቢሆኑ ከእሷ የተለየ ግምት የላቸውም። ፊት ለፊት የተጋፈጧቸው ቡድኖች ወደእነሱ ቀርበዋል። አመጣጣቸው በፍጥነት፣ ንግግራቸውም በታላቅ ቁጣ ሆኗል።

የመኪናውን የፊት በር በርግዶ የከፈተው

ትልቁ ቤት ዘልቀው ወደ መኝታ ቤት ሲያመሩ ከዘመናዊ ቁምሳጥኖች ጋር ተፋጠጡ።ጊዜ አልፈጁም። የወርቅና የአልማዝ፣ ጌጣጌጦች የሚገኝበትን ፈልቅቀው ባዘጋጁት ሻንጣ መክተት ጀመሩ።

የካቲት ፲፮/፳፻፲፩

Page 10: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

10 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ በአንደበተ ርቱዕነታቸው ይታወቃሉ። ስማቸውን በተመለከተ በስህተት ይሁን በልማድ ‹‹መጋቤ ሐዲስ›› በሚለው ብቻ የሚጠሯቸው ብዙ ናቸው። ምናልባት እንደ እርሳቸው የታወቀ ሌላ መጋቤ ሐዲስ ስለሌለ ሁላችንንም ያግባባናል እንጂ መጋቤ ሐዲስ የእርሳቸው መጠሪያ ስም ሳይሆን ማዕረጋቸው ነው። ትርጓሜውም ሐዲስን የሚመግቡ ማለት ነው። የእርሳቸው ሙሉ ስም እሸቱ አለማየሁ ነው። ማዕረጋቸውን አስቀድመን መጋቤ ሐዲስ እሸቱ እያልን መጠቀም እንችላለን።

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ይኖራሉ የተባለበት መድረክ መቆሚያ መቀመጫ ይጠፋል። ለዚህም ነው መድረኮች ሲዘጋጁ የሚያስተዋውቁት ‹‹መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ይገኛሉ›› እያሉ ነው። የሚገኙበትን መድረክ ልብ ብላችሁ ከሆነ ለታዳሚ መያዣ የእርሳቸው ንግግር መጨረሻ ላይ ነው የሚደረገው። ገና ወደ መድረክ ሲጠሩም በጭብጨባና ፉጨት አዳራሾቹ ይደምቃሉ።

ብዙ ጊዜ የሚገኙት ለአንድ ጉዳይ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ እንጂ፤ እርሳቸው እንዲናገሩ ተብሎ ለብቻው መድረክ ሲዘጋጅ ብዙም አይስተዋልም። የእርሳቸው ንግግር ግን ራሱን ችሎ መድረክ የሚያዘጋጅ ነው፤ ይሄ ማለት በቃ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ እንዲናገሩ መድረክ ማዘጋጀትና እርሳቸው ብቻ የሚናገሩበት መድረክ ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በለውጥ ላይ ነው። ለውጡን ለማስቀጠል የሚያስችል አስተሳሰብ መፍጠር ተቀዳሚ አላማው አድርጓል። ይህን ተከትሎም ለሰራተኞቹ አነቃቂ ሀሳቦችን ሊመግብ ፈለገና መጋቢ ሃዲስ እሸቱን በእንግድነት ጋበዛቸው። እኛም ከዛሬ ጀምረን ለምናሳትማት አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጋዜጣ «መጋቤ አዕምሮ» በተሰኘው አምዳችን እንደሚከተለው አሰናዳነው።

ለድርጅቱ ሰራተኞች ይህኛው መድረክ ለየት ያለ ነበር። እንደወትሮው መድረክ ‹‹ተጀምሯል ሂዱ!›› ወደ አዳራሽ ሂዱ የሚል ቅስቀሳ አልተደረገበትም። በዚያ ላይ ቀኑ ብዙ ሰራተኛ የማይገኝበት ቅዳሜ ነበር፤ የዚያን ዕለት ግን ይህ አልሆነም። ሰራተኛው የተባለውን ሰዓት ጠብቆ በአዳራሹ ተገኘ።

ከወትሮው የሚለይበት ሌላው ድባብ ደግሞ መግባትና መውጣት አለመኖሩ ነው፤ የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ንግግር ይህን ያህል ቀልብን የገዛ እንደነበር ምስክር አይሻም። ራሱን ችሎ እንዲህ አይነት መድረክ ቢዘጋጅላቸው ምን ያህል ታዳሚ እንደሚገኝ አሳይቷል።

እውቅና ስለመስጠትከፊት ያሉ ሰዎችን ማበረታታት ከኋላ

ለሚሮጠው ሰው በረከት ነው። እነ ሃይሌ እና እነ ደራርቱ ሮጠው ሲጨርሱ የሚገረፉ ቢሆን ኖሮ ማንም ሩጫ የሚሞክር አይኖርም ነበር። ሮጠው ከጨረሱ በኋላ ወርቅና ብር ስለመጣ እኛም ብንሮጥ እናገኛለን ብለው ሰዎች ይሮጣሉ። አይተናል ከፖለቲካ ብዙ የሸሹ ሰዎች፤ ጫፉ እስራት ነው ሲባሉ ይሸሻሉ። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ ያለ ነው። ስለዚህ የፊተኛውን ማበረታታት የኋለኛውን ማበረታታት ነው።

አሁን የመጣው ትውልድ ብልጥ ነው። ኪሱንና ነፍሱን ያስታረቀ ነው። አሳቢ ነው፤ ትምህርት ሲማር በምን ብመረቅ ስንት ብር አገኛለሁ ብሎ ነው። ድሮ እንደዚህ አልነበረም፤ በመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ስንማር መቼ እንደምንጨርስ አናውቀውም ነበር፤ ከጨረስን በኋላም ምን እንደምናገኝ አናውቀውም። ለማወቅ ብቻ ነበር ትምህርቱ። የአሁን ትውልድ ግን 12ኛ ክፍል ሲጨርስ ምን ቢማር ምን እንደሚያገኝ አስልቶ ነው።

ጭብጨባ እና መድረክ እኔ መድረክ ላይ ጭብጨባ ለምጃለሁ፡፡ ጭብጨባ ለሁለት ነገር ያገለግላል። አንድ ለራሱ ለታዳሚው ነው፤ ያነቃቃዋል። እዚህ ሆኖ ቤቱ ቡና የሚያፈላ አለ፤ ስብሰባ ውስጥ ቁጭ ብለው ብዙ ሴቶች ቤታቸው አልጋ የሚያነጥፉ አሉ፤ ቤት ይጠርጋሉ። እነዚህ ሰዎች በጭብጨባ ካልተቀሰቀሱ ይጠፋሉ። አንዳንድ ሰዎች ጆሯቸው አለ፤ ግን ጥሪ አይቀበልም። አንዳንዱ ሰው እኮ መንገድ ላይ እየሄደ እንኳን ስታናግሩት አይሰማም። ሁለተኛው የጭብጨባ ጥቅም ለተናጋሪው ነው። ተናጋሪውን አለን እየሰማንህ ነው ለማለት ያግዘዋል።

መለወጥእንጨት የወየበ (የጠወለገ) ቅጠሉን ማርገፍ

አለበት፤ አበባ አበባውን አርግፎ ፍሬ ማፍራት አለበት። ብዙ ጊዜ ሰዎች ውበትን ለማድነቅ ‹‹አይኑ ወይም አይኗ የባቄላ አበባ ይመስላል›› ይላሉ። ለገበሬ የባቄላው አበባ ውበት ሳይሆን ተስፋ ነው። አበባ በከተማ ማጌጫ ነው፤ ለገበሬ ግን ተስፋ ነው፤ ሕይወት ነው። በአበባው በኩል ወደፊት የሚያየው ተስፋ አለው። ምክንያቱም ባቄላው አበባውን ካረገፈ በኋላ ፍሬ ያፈራል። ገበሬው ሲመነጥር፣ ሲያርስ፣ ሲያርም የሚከርመው አበባ ለማግኘት ሳይሆን ፍሬ ለማግኘት ነው። መሬቱን አለሳልሶ ማዳበሪያውን አድርጎ የሚዘራው ፍሬ ለማግኘት ነው። ዛሬ ጊዜ መሬቱ ራሱ ሙስና ለምዶ ያለማዳበሪያ ምርት አልሰጥም እያለ ነው።

አንድ ዛፍ የወየበ ቅጠሉን ካላረገፈ አዲስ

ስንቀይር ደርግ ይመጣል ብሎ ያሰበ አልነበረም፤ ግን እንደዚያ ሆነ፤ ከዚያ በኋላም እንደዚያ ሆነ፤ ከዚያም እንደዚያ ሆነ።

በአሮጌ ሱሪ ዕቃ ስንለውጥበት አዲስ ሱሪ መገኘቱን ማረጋገጥ አለብን፤ ምክንያቱም የሚመጣው ለውጥ ምንድነው ተብሎ መታወቅ አለበት። አዲስ ሱሪ ሳይገዛ አሮጌውን ቢጥሉት ራቁት መሄድ ይመጣል። አሮጌን ሲጥሉም አዲስ አዘጋጅቶ ነው። ስለዚህ ስንለወጥ የሚጠቅመንን ነገር ማወቅ አለብን።

ኢትዮጵያውያን ለለውጥ እንግዶች ናቸው ሲባል እንሰማለን፤ ለውጥ አንወድም። ጥንታውያን አባቶቻችን ለለውጥ እንግዶች አልነበሩም። ከውጭው ዓለም ያለውን እውቀት ለማስገባት የተጻፈውን ጽሑፍ ስትመለከቱ ለውጥ ፈላጊ ነበሩ። የግሪክን ፍልስፍና እስከነትርጓሜው ያስገቡ ሊቃውንት አሉ። የነሶቅራጠስንና የነፕሌቶን ፍልስፍና ትርጓሜ ውስጥ አስገብተው መማሪያ አድርገውታል። ከዚህም የተነሳ ትርጉም ሁሉ አይመስሉም፤ እዚሁ አገር በቅለው ያደጉ ነው የሚመስሉት።

ትልቁ ችግራችን መወያየት አንችልም፤ በፖለቲካችን የመወያየት ባህል የለንም። በትዳር እንኳን የመወያየት ባህል የለንም። ባልየው መጥቶ መመሪያ ነው የሚሰጥ። የባልና የሚስት ጉዳይ አብሮ የማደርና ያለማደር ጉዳይ ሆኖ ነው የሚታየው፤ እንዲያውም አሁን አሁን እርሱም እየተደበላለቀ ነው፤ አሁን አሁን በሚስትና በቤት ሰራተኛ መካከል መቀላቀል እየታየ ነው።

ሀሳባችንን ሰው ላይ መጫን ነው የምንወድ። በንጉሡም ጊዜ፣ በዚያኛውም ጊዜ፣ በዚያም ጊዜ በዚያም ጊዜ…. አንዱ የሌላውን እስኪ አስረዳኝ የመባባል ነገር የለም። ሙስሊሙ ኦርቶዶክሱን፣ ኦርቶዶክሱ ሙስሊሙን፣ ፕሮቴስታንቱ ሙስሊሙን… አንዱ ሌላውን እስኪ ይሄን አስረዳኝ አንባባልም። እስኪ ቁርዓን ምንድነው የሚል፣ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው አንባባልም።

በፖለቲካ አንዴ የደገፍነውን አካል እዚያው ላይ ሙጭጭ ነው፤ እገሌ የእንትና ደጋፊ ነው ከተባለ ዶግማ አርጎት ቁጭ ነው። የተቃወምነውንም አካል ተቃውሞው ላይ ሙጭጭ ነው። እንደነ አሜሪካ ባሉ አገራት ግን

እንዲህ አይደረግም። ሪፐብሊካንን ይደግፍ የነበረ ሰው የፖለቲካውን ርዕዮተዓለም አይቶ ዲሞክራት ሊሆን ይችላል፤ ዲሞክራት የነበረውም እንዲሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ባለበት አክርሮ ዝም ነው፤ አያነብም። ከብዙ ዓመታት በፊት የተከናወነ ሁነት ላይ ነው ያለው ። አገሪቱ ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ የማይሰማ ሁሉ አለ። አጼ ኃይለሥላሴ በ1967 ዓ.ም ሞተው በ1975 ዓ.ም አንድ የዋድላ ገበሬ ‹‹በኃይለሥላሴ አምላክ›› ይል ነበር። አጼ ኃይለሥላሴ መሞታቸውን

የሚነግረው አልነበረም። ያኔ ደግሞ እንደዛሬው ፌስቡክ እንኳን የለም።

የፖለቲካ ፓርቲ የሚመሩ ሰዎች የሕዝቡን ችግር አያውቁም፤ እነርሱ ጥሩ ቢሮ ካገኙ ህዝቡ ጥሩ ኑሮ እየኖረ ይመስላቸዋል።

በቅርቡ ኳታር ነበርኩኝ። 300 ሺህ ዜጋ ነው ያላቸው፤ ሀብት የተትረፈረፈ ነው። በአገሪቱ ውስጥ ግን ከሦስት ሚሊዮን በላይ ስደተኛ ይኖርበታል። እነርሱ ግን በጣም የሰለጠኑ ስለሆኑ ‹‹ለምን መጣህ! ከየት መጣህ! ምንድነህ! ቋንቋህ ምንድነው›› አይሉም። በአገሪቱ እስልምና መንግስታዊ ሃይማኖት ነው፤ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው። እኛ ግን ቦታ ተዘጋጅቶልን ስንሰብክ ስንዘምር አንድ እንኳን የገላመጠን የለም፤ ልባሞች ናቸው ማለት ነው። ስለዚህ እኛም ከሚለወጡ ነገሮች ግን አብረን ካልተለወጥን፤ አስተሳሰባችንን ካላሻሻልን አስቸጋሪ ነው።

በአሮጌ ሱሪ ዕቃ ስንለውጥበት አዲስ ሱሪ መገኘቱን ማረጋገጥ አለብን፤ ምክንያቱም የሚመጣው ለውጥ ምንድነው ተብሎ

መታወቅ አለበት። አዲስ ሱሪ ሳይገዛ አሮጌውን ቢጥሉት ራቁት መሄድ ይመጣል። አሮጌን ሲጥሉም አዲስ አዘጋጅቶ ነው። ስለዚህ ስንለወጥ የሚጠቅመንን ነገር ማወቅ አለብን።

ቅጠል አያወጣም፤ አንድ ተክል አበባውን ካላረገፈ ፍሬ አያፈራም። የሰው ልጅም ያረጀ፣ ያፈጀ፣ የቆሸሸ እና የተበላሸ አስተሳሰቡን ካላራገፈ አይለወጥም። አዲስ ሀሳብ ለሌለው አዲስ ሰው መሆን አይችልም።

በዓለም ላይ ብዙ አይነት ለውጥ ይታያል። ለውጥ ተፈጥሯዊም ነው። ቀን አልፎ ጨለማ ይመጣል፤ ክረምት አልፎ በጋ ይመጣል፣ ሰኞ አልፎ ማክሰኞ ይመጣል። ይሄ ሁሉ ለውጥ አስፈላጊ ነው። በለውጥ ውስጥ ደግሞ የሰው ሁኔታም ይለወጣል። ለምሳሌ ሰኞ የተበሳጬ ሰው ማክሰኞ ሊደሰት ይችላል። ስለዚህ በሁሉም ነገር ለውጥ ያስፈልጋል።

ለውጥ ሲባል ሁለት ነገሮች አሉ። አንደኛው ለውጥ ያስፈልጋል አያስፈልግም የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ያስፈልጋል ከተባለስ ምን አይነት ለውጥ የሚለው ነው። በፖለቲካችን ውስጥ ብዙ ለውጥ አለ፤ ለምሳሌ አጼ ኃይለሥላሴን

መጋቤ አዕምሮ ስንል የከፈትነው ይህ አምዳችን ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ፣ ለአስተሳሰብ ቀረጻ የጎላ ሚና ባላቸው የተለያዩ እሴቶቻችን ዙሪያ የተመረጡ ንግግር አዋቂዎች የሚያቀርቧቸው ነጻ ሃሳቦች የሚድስተናገድበት ይሆናል።

ትልቁ ችግራችን መወያየት አንችልም፤ በፖለቲካችን የመወያየት ባህል የለንም። በትዳር እንኳን የመወያየት ባህል የለንም። ባልየው መጥቶ መመሪያ ነው የሚሰጥ።

መጋቤ አዕምሮ>>

አዲስ ሀሳብ የሌለው አዲስ ሰው መሆን አይችልም

Page 11: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

11የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ማረፊያ >>

ወግ

‹‹ድልድዩን ከመስበርህ በፊት ዋና እንደምትችል እርግጠኛ ሁን›› (ኬኒያውያን)

‹‹አዲሱ ባልዲህ ውሃ የሚይዝ መሆኑን ሳታረጋግጥ አሮጌውን አትጣል›› (ስዊድናውያን)

‹‹አንድን ሰው ልብስ ከመጠየቅህ በፊት መጀመሪያ ለራሱ ምን ዓይነት ልብስ እንደለበሰ ልብ ብለህ ተመልከተው››

( ቤኒናውያን)

‹‹ውሸት መላውን ዓለም ትዞራለች ፤ እውነት ደግሞ እቤቷ ቁጭ ብላ የሚሆነውን ትጠባበቃለች››

(ፈረንሳያውያን)

‹‹ጠማማ ዕድል ያለው ሰው ወደ ወንዝ አትላከው›› (ይዲሻውያን)

‹‹በጓደኛህ ግንባር ላይ ያረፈውን ዝምብ ለማባረር ብለህ መጥረቢያ አትጠቀም›› (ቻይናዊያን)

‹‹አይጥ በድመት ላይ ከሳቀች አቅራቢያዋ ጉድጓድ አለ ማለትነው›› (ናይጄሪያውያን)

‹‹ውሃ ውስጥ ሰምጠህ የመሞት ፍላጎት ካለህ በጎደለው ኩሬ ውስጥ እየተንቦራጨክ ራስህን አታሳቃይ››

(ቡልጋሪያውያን)

‹‹ተኩላዎች ዳኞች ሆነው በተሰየሙበት ችሎት ላይ የበጎችቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም››

(ይዲሻውያን)

‹‹እንቁላል የሞላ ቅርጫት ተሸክመህ አትጨፍር››(ጊኒያውያን)

የሳምንቱ ጥቅሶች

ለምን ተባለ

ሳይነስ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አየር የሚንሸራሸርባቸውን ክፍሎች የሚያጠቃ የህመም ዓይነት ነው። ህመሙ ሦስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፣ አኪዩት፣ ሰብ አኪዩት እና ክሮኒክ ሳይነስ (ሲኖሳይተስ) በመባል ይታወቃሉ።

የህመሙ መነሻዎች የቫይረስና ባክቴርያ ኢንፌክሽን ሲሆን፣ አልፎ አልፎ የሰዎች አፈጣጠር ወይም አናቶሚ ለህመሙ መከሰት ሰበብ ይሆናል። ከሁሉም በላይ ግን ለበሽታው መከሰት ምክንያት እየሆነ ያለው አለርጂ ነው። ይህም “አለርጂክ ሳይኖሳይተስ” በመባል ይታወቃል።

ይህንን ህመም ለመከላከል የሚጠቅሙ 5 ቀለላልና ተፈጥሮአዊ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡-

ቀይ ጥሬ ሚጥሚጣቃጠሎን መቋቋም እስከቻሉ ድረስ ሳይኖሳይተስን ለማከም ወደር የማይገኝለት ተፈጥሯዊ

መድሃኒት ነው። አፍንጫን በፍጥነት በማጽዳት ውስጡ ላይ ያለን እብጠት በማጥፋት እፎይታን ይሰጣል። በሚመችዎት መንገድ አዘጋጅተው መጠቀም ይችላሉ።

ዕርድዕርድ በውስጡ ከርከሚን የሚባል እብጠትና የመለብለብ ስሜትን የሚከላከል ንጥረነገር

አለው። ይህ ንጥረነገር ሳይኖሳይተስን ከመከላከሉም በተጨማሪ የሰውነትን የበሽታ የመከላከል አቅም ከፍ ያደርጋል። 500 ሚ.ግ የእርድ ዱቄትን በውሀ በማዋሀድ ወይም በእንክብል መልክ በቀን ሁለት ጊዜ መውሰድ ጠቃሚ ነው።

ነጭ ሽንኩርትነጭ ሽንኩርትን በብዛት መመገብ እጅግ በርካታ የጤና ትሩፋቶችን ያስገኛል። በውስጡ አሊሲን

የተሰኘ ንጥረነገር የያዘ ሲሆን፣ ይህ ንጥረነገር ቫይረስ፣ ባክቴርያና ፈንገስን የሚከላከል በመሆኑ ለሳይኖሳይተስ ኢንፌክሽን ፍቱን መድሃኒት ነው። በቀን ውስጥ ከሁለት እስከ ሦስት ራስ ፍሬሽ ነጭ ሽንኩርትን በማንኛውም ዓይነት መመገብ ከፍተኛ ውጤት ያስገኛል።

ቀረፋበውስጡ ጎጂ የሆኑ ሳይኖሳይተስን የሚያስከትሉ ባክቴርያዎችን የሚገድል ኬሚካል አለው።

ከግማሽ የሻይ ማንኪያ እስከ አንድ የሻይ ማንኪያ ድረስ ከወለላ ማር ጋር በመቀላቀል በአንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሀ መጠጣት ፍቱን መድሃኒት ነው።

ዝንጅብልዝንጅብል በውስጡ ፀረ- የአፍንጫ ፈሳሽ እና ፀረ- መለብለብና እብጠት ኬሚካሎችን በውስጡ

ይዟል። እንዲሁም የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ስለሚጨምር ሳይኖሳይተስን ለመከላከል ይረዳል። የዝንጅብል ሻይን ከሎሚ ጭማቂ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ለሳይኖሳይተስ ፍቱን መድሃኒት ነው።

(ምንጭ:- የኛ ቲዩብ)

ይህ ረድፍ የአንድ አካባቢ ወይም ቦታ ለምን እንደተባለ የሚገለጽበት ንዑስ ዓምድ ነው። በአገራችን ውስጥ ያለ የትኛውንም ቦታ እናስተዋውቃለን።“ለውጥ‘ማ አለ”

ዋለልኝ አየለ

ሰው ግን ‹‹ለውጥ›› የሚለው ቃል ትርጉም አልገባውም ልበል? ለነገሩ የአንድ ቃል ትርጉም የሚታወቀው በገባበት ዓረፍተ ነገር ዓውድ ነው። ይልቅ ይሄንን ለቋንቋ ተመራማሪዎች እንተወውና ወደ

ለውጣችን እንመለስማ።ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን መምጣት

ወዲህ ‹‹ለውጥ›› የሚለው ቃል የብዙ ንግግሮች ማስጀመሪያ ሆኗል። ገና ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ‹‹መደመር›› የሚለው ቃል ነበር ፋሽን የሆነው። ምንም እንኳን አብሮ የመጣ ቢሆንም ‹‹ለውጥ›› የሚለው ቃል በኋላ እየሰፋ መጣ። ይሄ የሆነበት ምክንያት አለው። ለውጥ የሚታወቀው እየቆየ ሲሄድ በመሆኑ ነው።

ከግለሰቦች ጀምሮ መገናኛ ብዙኃን ሁሉ ‹‹ከለውጡ በፊት›› እና ‹‹ከለውጡ በኋላ›› የሚል ድንበር ተበጅቷል። ወደው አይደለም! ብዙ ለውጥ ስላለ ነው። ባለሥልጣን ተለውጧል፣ የመገናኛ ብዙኃን ባህሪ ተለውጧል፣ ራሱ ሕዝቡም ተለውጧል (አንባቢ ሆይ አስተሳሰቡን ማለቴ እንደሆነ ይረዱልኝ)። አገሪቱስ? እሷም ተለውጣለች!

እንግዲህ ለውጥ በመኖሩ ተስማማን አይደል? አሁን ዋናው ጥያቄ ‹‹ለውጡ ምንድነው?›› የሚለው ነው።

በአንድ የመጽሐፍ ውይይት መድረክ ላይ ነው። ከአስተያየት ሰጪዎች አንደኛው ‹‹ከለውጡ ወዲህ›› ሲል አወያዩ አቋረጠውና ‹‹ለውጥ ግን አለ ብለህ ታምናለህ?›› ብሎ ጠየቀው። ይሄው የለውጥ ‹‹አለ›› ‹‹የለም›› ጉዳይም ትንሽ መወያያ ሆኖ ቆየ። ይሄን ነገር ያነሳሁት እዚያ የነበረውን ውይይት ለመግለጽ ሳይሆን ምሳሌ እንዲሆነኝ ነው። አወያዩ ለውጥ መኖሩ እንዴት እንዳልታየው ገርሞኝም ጭምር ነው። ይልቅ የለውጡን አይነት ነው መወያየት ያለብን እላለሁ።

ለውጥ አለ፤ ድብን አድርጎ ለውጥ አለ! ይሄንን ጉዳይ በስፋት የሚያስተጋቡት መገናኛ ብዙኃን ስለሆኑ ከመገናኛ ብዙኃን ነው የምጀምር። መገናኛ ብዙኃን ላይ ለውጥ አለ። ታዲያ ይሄን ነገሬን ያጠናክርልኝ ዘንድ አቶ ጃዋር መሐመድ በፋና ኤፍ ኤም 120 ደቂቃ ፕሮግራም ላይ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት የተናገረውን ነገር መግለጽ ፈለግሁ።

‹‹የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ለውጥ እንዴት አየኸው?›› ስትል ጠየቀች ጋዜጠኛዋ። ጃዋርም መለሰ። ‹‹መለስ መለስ መለስ ይል የነበረ ቴሌቭዥን አብይ አብይ አብይ ነው ያለው፤ ይሄ ለእኔ ለውጥ አይደለም›› ነበር ያለው።

የለውጡ ነገር ጃዋር እንዳለው ነው። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙኃን (በተለይም የመንግሥት) ከነበሩበት ነው የተገለበጡት። ይሄ ለውጥ ሊሆን ይችላል። ይሄንኑ የአዲስ ዘመን ጋዜጣን ምሳሌም ላንሳማ!

አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩበት ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ ነሐሴ 14 የአዲስ ዘመን ጋዜጣ እትም ልዩ ዕትም ነበር የሚሆነው። መጣ ከተባለው ለውጥ ወዲህ ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም የወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንኳን ልዩ ዕትም ሊሆን ስለአቶ መለስ ዜናዊ አንዲት መጣጥፍ እንኳን አልተጻፈም! ታዲያ ይሄ ነገር እንዴት ነው ጎበዝ? (ይሄንኑ ጋዜጣ እዚሁ ራሱ አምድ ላይ መተቸት ቻልኩ ማለት ነው? ለውጥማ አለ!)

ሁለት ነገር መጠርጠር ነው እንግዲህ! አንድ፤ የዝግጅት ክፍሉ ኃላፊዎች ከመንግሥት በሚመጣ ትዕዛዝ

ብቻ ነው የሚንቀሳቀሱት ማለት ነው፤ አድርጉ የተባሉትን ያደርጋሉ፤

እንዳታደርጉ የተባሉትን ደግሞ ይተዋሉ። ሁለት፤ የአቶ መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት ማክበር አግባብ አለመሆኑን

አምኗል ማለት ነው። በቃ እስከዛሬ ተሳስተናል፤ ከዚህ በኋላ መስተካከል አለብን፤ የአቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት ሽፋን የሚያስፈልገው አይደለም ብሎ አምኗል ማለት ነው።

ሁለቱን መገናኛ ብዙኃን ምሳሌ የጠቀስኩት አንጋፋ ስለሆኑ ነው፤ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሲባል ወደሰው አዕምሮ የሚመጡትም ሁለቱ ናቸው (በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የህትመት መገናኛ ብዙኃን ልብ አይባሉም)።

ሌላው የተለወጠው ደግሞ ሕዝቡ ነው(ኧረ እንዲያውም ዋናው ለውጥ)፤ በዚህ አጋጣሚ መገናኛ ብዙኃኑንም የለወጣቸው ሕዝቡ ነው። ‹‹መገናኛ ብዙኃን የሕዝብ ዓይንና ጆሮ ነው›› ይባላል አይደል? ግን የአገራችንን መገናኛ ብዙኃን አይንና ጆሮ የደፈነው ራሱ ህዝቡ ነው! (መገናኛ ብዙኃን የሕዝብን አመለካከት መቀየር አለበት እንደሚባል አውቃለሁ)

እስኪ የሕዝቡን ለውጥ እናስተውል!የመገናኛ ብዙኃን አሁን እያደረጉ ካሉት ውጭ መዘገብ አይችሉም፤

ምክንያቱም ሕዝቡ ይቆጣል። ጎበዝ አንዳንዴ እኮ ሕዝብም ትክክል ላይሆን ይችላል። አንድ ነገር ሲደጋገም እውነት ይሆናል የሚባለው ነገር ትክክል ነው። የሕዝብ ቁጣ የተነሳበት ነገር ሁሉ ሕዝብ ትክክል ነው ስለሚባል እንደ ስህተት አይታይም፤ በዚህም ብዙ ውድመት ደርሷል። ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይን የሚተች ዘገባ ቢሰራ ከመንግሥት ይልቅ ሕዝቡ ይቆጣል። ሚዛናዊ የሆነ ዘገባ ቢሰራ ‹‹ለውጡን ያልተቀበለ›› ተብሎ ዘመቻ ይደረግበታል፤ ለአብዛኛው ሕዝብ ለውጥ ማለት በአንድ ወገን ብቻ ያለው ሆኖበታል። ይሄን የሕዝብ ቁጣ በመፍራትም መገናኛ ብዙኃን ሕዝቡ የሚፈልገውን ብቻ ይሰራሉ ማለት ነው።

እንደግለሰብ እንኳን ነፃ ሀሳብ ማራመድ ላይቻል እኮ ነው! ከለውጡ በፊት መንግሥት ነበር የሚያስቸግረው፤ አሁን ደግሞ ሕዝቡ ነው እያስቸገረ ያለው። ከለውጡ በፊት የነበረው የሕዝቡ ወቀሳ ‹‹የሀሳብ ነፃነት ይከበር›› ነበር። አሁን ግን ህዝቡ የሀሳብ ነፃነት እያከበረ አይደለም። አንድ ሰው የተለየ ሀሳብ ሲናገር ‹‹ለውጡን ያልተቀበለ›› ተብሎ በደቦ ይዘመትበታል።

ለማንኛውም ለውጥ አለ!አብሮ የመንጋጋቱ ነገር እንዳለ ሆኖ ግን የማይካድ ለውጥ አለ።

በቀደመው ኢህአዴግና በዳግማዊው ኢህአዴግ የነበረው ሁኔታ የተለያየ ነው። ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃንም ብዙ ብለውለታል። ከኤርትራ ጋር የተጀመረው ሰላማዊ ወዳጅነት ቀላል ጉዳይ አይደለም። የአገራቸው አፈር የናፈቃቸው ወገኖች አገራቸው መግባት ቀላል ነገር አይደለም፤ ወጣቱ የሚያነበው ጋዜጣና መጽሔት መኖሩ ቀላል ነገር አይደለም። እንኳን ለአሳታሚውና ለመገናኛ ብዙኃኑ ባለቤቶች ለአንባቢም የሚያሳቅቅ ጊዜ ነበር።

ግና ይሄ ሁሉ ሲሆን አገሪቱ ውስጥ ያለው መፈናቀል ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አልታየም። ‹‹ከለውጡ ወዲህ!›› በተባለው ጊዜ ውስጥ በሰው ልጅ ላይ የማይደረጉ ዘግናኝ ድርጊቶችን አይተናል(የለውጡ አካል ይሆኑ?) ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገር አንድነትን እየሰበኩ የዘውግ ፖለቲካ ሊያሸነፍ እየተገዳደረ ነው።

የለውጧን ነገር በሁለቱም እንየው። ጥሩ ለውጥ አለ፤ የደረሰ ጥፋትም አለ። መገናኛ ብዙኃን ተለውጠዋል፤ ግን የተለወጡት ወደገዥው ነው። ዞሮ ዞሮ ግን ባለሥልጣንም ስለተለዋወጠ ‹‹ለውጥ›› አለ!

አባባ

መረጃ ለጤናችን

ሳይነስን ለማከም ቀላል መንገዶች

?እነዚህ ቦታዎች ለምን እንደተባሉ ከታሪክ ሰነድ አጣቅሰን ምላሽ እንሰጣለን?ለዛሬ መነሻችንን ከአገራችን ርዕስ መዲና አዲስ አበባ እናደርጋለን። አዲስ አበባ አገርኛ

መጠሪያ ያላቸው በርካታ ሰፈሮች አሏት። የአዲስ አበባ ሰፈሮች ስያሜ ከገጠሩ አካባቢ በተሻለ ግልጽ ናቸው። ችግሩ ግን ለምን ተባለ? የሚለውን ጠይቀን አለማወቃችን ነው።

አንዳንድ ሰፈሮች ለምን እንደተባሉ ከታሪካቸውና ከአሰያየማቸው ግልጽ ናቸው። የአንዳንዶቹ ግን ለምን እንደተባሉ ሰው ካልነገረን በቀር ትክክለኛውን ምላሽ አናገኝም። ለምሳሌ በጀግኖች ስም የተሰየሙ አደባባዮች ወይም ጎዳናዎች ለምን እንደተባሉ ለብዙ ሰው ግልጽ ይሆናል። አንዳንድ ሰፈሮች ግን በተለያየ አጋጣሚዎች ይሰየማሉና ለዛሬ ሦስቱን ሰፈሮች ለምን እንደተባሉ እንንገራችሁ።ሰባራ ባቡር

ይህ ሰፈር ከፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ በስተጀርባ፤ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በኩል ወደ አስኮ ስንሄድ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይን አለፍ ብለን የምናገኘው ነው። ሰባራ ባቡር ስያሜውን ያገኘው ‹‹ሙሴ ሰርኪስ ተርዚያን›› በተባሉ አርመናዊ ነጋዴ አማካኝነት ከውጭ አገር መጥቶ እዚህ ቦታ ላይ በተበላሸ የመንገድ መስሪያ ተሽከርካሪ (ሮለር) ምክንያት ነው። እዚህ ቦታ ላይ ተሽከርካሪው ሲበላሽ ሰባራ ባቡር ተባለ። ባቡር የሚለውን ስያሜ የተሰጠው በወቅቱ በሞተር የሚሰሩ ማሽኖች ሁሉ ባቡር የሚል ስያሜ ይሰጣቸው ስለነበር እንደሆነ ይነገራል።‹‹ የባቡር ወፍጮ›› እንደሚባለው ሁሉ የመንገድ መስሪያው ሮለርም ባቡር ተሰኝቷል።በቅሎ ቤት

በቅሎ ቤት ከስቴዲየም ወደ ቃሊቲ ስንሄድ ‹‹ላንቻ›› አካባቢ የሚገኝ ሰፈር ነው። በቅሎ ቤት ስያሜውን ያገኘው በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት መድፈኛ ጦር መቀመጫው ላንቻ አካባቢ የነበረ ሲሆን በወቅቱ መድፎችን ወደ ሌላ ቦታ መውሰድ ሲፈለግ ተፈታተው በበቅሎ ይጫኑ ነበር። በዚህ ምክንያት በመድፈኛ ጦር ሰፈር ውስጥ ለማጓጓዣነት የሚያገለግሉ ከመቶ ያላነሱ በቅሎዎች ነበሩ። በአካባቢው በርካታ በቅሎዎች ስለነበሩ ሰፈሩ «በቅሎ ሰፈር»ተባለ። እየቆየ ሲሄድ ደሞ «በቅሎ ቤት» እየተባለ መጠራት ጀመረ።ጠመንጃ ያዥ

ጠመንጃ ያዥ ተብሎ የሚጠራው ሰፈርም ከስቴዲየም ወደ ቃሊቲ ሲኬድ የሚገኝ ነው። ጠመንጃ ያዥ የተባለበት ምክንያት ከጣልያን ወረራ በፊት የቤተ መንግሥት ጠባቂዎች በብዛት ይኖሩበት ስለነበርና ጠመንጃ ይዘው በብዛት ስለሚታዩ የተሰጠው ስያሜ ነው።

መጋቤ አዕምሮ፲፩

Page 12: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

12 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

‹‹ቁራኛዬ››ኪነጥበብ>>

ዋለልኝ አየለ

ጸሐፊና አዘጋጅ፡- ሞገስ ታፈሰ(ፒ.ኤች.ዲ) የፊልሙ ርዝማኔ፡- 1፡40የፊልሙ ዘውግ፡- ትውፊታዊ ፊልምተዋንያን፡- ዘሪሁን ሙላቱ (እንደ ጎበዜ)፣

የምሥራች ግርማ (እንደ አለሜ)፣ ተስፋዬ ይማም (እንደ ጎንጤ)፣ ፍሬሕይወት ከልክሌ (እንደ ንግስት ዘውዲቱ) እና ሌሎች

‹‹ፊልም ለምን ታያላችሁ?›› ብለን ወጣቶችን ብንጠይቅ ‹‹ለመዝናናት›› የሚሉን ይበዛሉ። ለዚህም ይመስላል ብዙ ጊዜ ፊልም የሚያዩት ቅዳሜና እሁድ ወይም በሌሎች የዕረፍት ቀናት የሚሆነው። ምናልባት በሥራ ቀን ስለማይመች ይሆናል። ለመዝናኛ መሆኑን የምናውቀው ግን ብዙ ወጣቶች ‹‹ምን ያዝናናሃል?›› ተብለው ሲጠየቁ ‹‹ፊልም›› ስለሚሉ ነው።

ለመከራከር እነዳታስቡ! ፊልምን ለመዝናኛነት ብቻ ሳይሆን ለመማሪያም የሚያዩት እንዳሉ አሳምሬ አውቃለሁ። ለዚህም ምሳሌ ይኖረኛል። ወጣቶች ተሰባስበው በሚያወሩበት አጋጣሚ ሀሳብ ከተነሳ የፊልም ታሪክ ማንፀሪያ ይሆናል። እንደፊልሙ ይዘት ፍቅር፣ ታሪክም ይሁን ፖለቲካ ለሀሳብ ማጠናከሪያነት ይጠቀሙበታል። የፊልሙ ገጸ ባህሪያትም በቀልድም ይሁን በቁም ነገር በገሃዱ ዓለም ላይም ተፅዕኖ ይፈጥራሉ።

እነዚህ ወጣቶች ለምን በፊልም ተፅዕኖ ሥር ወደቁ? ይሄ የኪነጥበብ ጉልበት ነው። ለዚህም ነው የፊልሞች ይዘት ላይ ተደጋጋሚ ወቀሳ የሚነሳው። ወጣቶችን የመቀልበስ ሃይል ስላላቸው።

ለዛሬው ከፊልም ወቀሳ ልወጣ ነው (እሰየው ነው!)። በቅርቡ ‹‹ቁራኛዬ›› የተሰኘ ፊልም ሲኒማ ቤቶችን ተቀላቅሏል። ፊልሙ እስካሁን ከተደጋገሙት ፊልሞች ለየት ያለ ነው። ስካርን፣ ዝሙትን፣ ሴተኛ አዳሪነትን ከሚያሳዩና መቼታቸው ከጭፈራ ቤት ከማይወጣ ፊልሞች የተለየ መሆኑ አንድ አዲስ ነገር ነው። ከይዘቱ በፊት ግን የፊልም ባህሪ ነውና አንድ ነገር ልበል።

ቁራኛዬ ፊልም አዝናኝ ነው። መዝናናት የሚለው ቃል ከጫጫታና ሆይ ሆይታ ጋር ብቻ የሚገለጽ አይደለም። መዝናናት አዕምሯችን ያለመደውን ነገር ሲያይ ነው። ቁራኛዬ ደግሞ እንደዚያ ነው።

ፊልም የምንወድበት አንዱ ምክንያት እኛ የማንኖረውን ሕይወት ስለሚያሳየን ነው። በልቦለድ ሥራዎች ውስጥ ምናባዊ ፈጠራዎች ቀልባችንን ይይዙታል። ያንን ኑሮ መኖር እንፈልጋለን፤ ወይም ደግሞ በተቃራኒው ‹‹ሰው እንዲህ ይኖራል!›› ብለን እንደነቃለን።

ቁራኛዬ ፊልም እኛ ወጣቶች ያልኖርንበትን ሕይወት ነው ሚያሳየን። ፊልሙ ለወጣቶች ፊልም ይሁን እንጂ ያን ዘመን ለኖሩ ግን ዘጋቢ ፊልም ነው። ቁራኛዬ ፊልም ምናባዊ ሳይሆን እውናዊ የአገርቤት ሕይወት ነው። ከመቶ ዓመት በፊት የነበረው የአገር ቤት ሕይወት ማለት ነው። ከመቶ ዓመት በፊት የነበረን ታሪክ የምናውቀው መጽሐፍ በማንበብ ነው። ቁራኛዬ ፊልም ላይ ደግሞ ሕይወቱን በመኖር ነው። ፊልሙን ማየት ምንኛ በሀሳብ እንደሚያሰምጥ!

የፊልሙ ይዘት ታሪክ፣ ባህልና ፖለቲካ ነው። ከመቶ ዓመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ። የፊልሙን ይዘት መተንተን የታሪክ ባለሙያ ይጠይቃል። በውስጡ ብዙ የሚተነተኑ ነገሮች ሲኖሩ፤ የፊልሙ ዋና ታሪክ ግን ጎበዜ የተባለ የቆሎ ተማሪ ፍቅረኛውን አለሜን ከእብሪተኛው ጭቃሹም ጎንጤ ለማስመለስ ጥረት ያደርጋል። የሚያስመልሳትም የወቅቱን የፍትሕ ሥርዓት ጠብቆ ነው። ባላንጣውን ተቆራኝቶ ፍትህ ፍለጋ ወደ ንግስት ዘውዴቱ ችሎት የአጼ ስርዓቱን ተከትሎ በሙግት መርታት ነበረበት። ሥርዓቱን ተከትሎም ፍትሕ አግኝቷል።

በቁራኛዬ ፊልም ውስጥ የምንማረው ነገር ዋናውን ታሪክ ብቻ አይደለም። በውስጡ ያሉ ብዙ ነገር አለ። እንደሚታወቀው የተለያዩ አገራት በፊልም አገራቸውን ያስተዋውቃሉ። በዚህ በኩል ቁራኛዬ ፊልም የተሳካለት ነው።

መልክዓ ምድርፊልሙ አንኮበር ላይ ያተኩር እንጂ ብዙ የኢትዮጵያ

ገጠራማ አካባቢዎችን የሚወክል ነው። የውጭ ፊልሞችን ስናይ በረሃማ አካባቢዎች፣ ጫካው፣ ገደሉ…ሁሉ ይታያል። አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ፊልሞች ግን ከሆቴልና ጭፈራ ቤት አይወጡም። የሚያተኩሩትም የከተማ ሕይወት ላይ ነው። ቁራኛዬ ፊልም ላይ የገጠሩን መልከዓ ምድር እናያለን። መልክዓ ምድር ቀላል ነገር አይደለም።

የገጠር ቤቶች ምን እንደሚመስሉ፣ እንዴት እንደሚኖሩ፣ ምን አይነት የመገልገያ ዕቃዎችን እንደሚጠቀሙ ያሳየናል። ይሄ

እንግዲህ ለዚህ ዘመን ነዋሪ (በተለይም ለከተሜው) መዝነኛም ነው ማለት ነው። መቼም ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ቪላ ቤት ማየት አያዝናናውም፤ አዲስ ነገርም አያሳየውም። አዕምሮ ደግሞ የሚዝናናው ከለመደው ነገር ወጣ ያለ ሲያይ ነው።

ቁራኛዬ ፊልም ለዚያ ዘመን ነዋሪዎች ዘጋቢ ፊልም ነው የሚመስለው። እንኳን ለዚያ ዘመን ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን የገጠሩ ሕይወት እንደዚሁ ነው። ፊልሙ የተቀረጸው ልክ እንደዘጋቢ ፊልም ነው። የመገልገያ ዕቃዎች፣ መልክዓምድሩ በገሃድ ያለው ነው። የታሪኩን ሁነት ተከትሎ ሜዳውን፣ ገደሉን፣ ወንዙንና ተራራውን ያሳየናል።

ቋንቋና ባህልበፊልሙ ውስጥ አንድ ነገር በጣም ገርሞኛል። የፊልሙ

ገጸ ባህሪያት የሚናገሩት ቋንቋ ንጥር ያለ የአገርቤት አነጋገር። እዚህ ላይ ግን ደራሲው ሞገስ ሲናገር የሰማሁትን ላካፍላችሁ። አነጋገራቸውን በተመለከተ 11 ጊዜ ደግሞ ደጋግሞ አርሞታል። በተለይ የመጀመሪያው አስቂኝ እንደነበረም ያስታወሳል። ያንን ታሪክ ድንቅ ባህልና ወግ ይዞ የአራዳ ቃላት ሁሉ ነበሩበት። ለዕይታ የቀረበውን ፊልም ግን በቀጥታ የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት ነው የሚመስለው።

ከተዋናዮች አንዱ (ጎበዜን ሆኖ የተወነው) በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ሲናገር ሰምቼው ነበር። ያንን ሲናገር የሰማሁትን ቋንቋና ባህል ስለማውቀው የፊልሙ እውናዊነት የበለጠ አስገረመኝ።

በገጠር አከባባቢ(በተለይም በሰሜን ሸዋ) በከተማ ውስጥ የማይታወቁ እንደ «ኮቼ» እና «ዝግን» የሚባሉ የምግብ አይነቶች አሉ። «ኮቼ» የሚባለው ከጥብስ ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ሥጋው ለብቻው ነው እንጀራ ላይ የሚደረገው። «ዝግን» የሚባለውና ፊልሙ ላይ ያለው ግን ከወጥ ጋር ነው። ስሙ እንደሚያመለክተው ዝግን ማለት ከወጡ ውስጥ ያለው ሥጋ በእጅ መዝገን(ማፈስ) የሚቻል ነው። ይህን ወጥ እናቶች በእጃቸው (በሁለት እጆቻቸው መዳፍ) እያፈሱ እንጀራ ላይ ያደርጋሉ። ተዋናዩ አዲስ የሆነበትና የገረመው ይሄ ነበር። ፊልሙ ምን ያህል የአካባቢን ባህል እንዳጠና በግልጽ ያሳየናል።

‹‹በሕግ ከሄደች በቅሎዬ ያለሕግ የሄደች ጭብጦዬ››ባህርዳር የሚሰራ አንድ የህግ ባለሙያ በአማራ ቴሌቭዥን

እንግዳ ሆኖ ሲናገር በሰማሁት አንድ ገጠመኝ አስታወሰኝ። የፍርድ ቤት ዳኛ እያለ ያጋጠመው ነው። ሁለት ሰዎች ተካሰው መጡ። የተካሰሱት በሃምሳ ብር ነው። ሃምሳ ብር ተበድሮ ስላልመለሰለት ማለት ነው። ዳኛው ነገሩ ስላስገረመው በሽማግሌ (ወይም ጓደኝነት ነገር) አወራቸው። ማንም ያሸንፍ ማን የፍርድ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ የሚያባክኑት የጊዜና የገንዘብ

መጠን ከሃምሳ ብር ጋር አይነጻጸርም፤ በብዙ እጥፍ ይበልጣል። ‹‹እሱን አልሳትኩትም›› ነበር ያለው ከሳሹ። ሃምሳ ብር ያለአግባብ ከሚወሰድበት ተጨማሪ ወጭ አውጥቶ እውነቱን ማሳወቅ ነው የፈለገው።

ወደፊልሙ ስንመለስ ‹‹በህግ ከሄደች በቅሎዬ ያለህግ የሄደች ጭብጦዬ›› የሚለው የአበው አባባል የፊልሙ ማስተዋወቂያ(ፖስተር) ላይ እናገኘዋለን። አባባሉ ደግሞ ፊልሙ ውስጥ ተተግብሮ እናገኘዋለን።

ሚስቱን በጭቃ ሹሙ ጎንጤ የተቀማው ጎበዜ ፍትሕን ፍለጋ የወቅቱን ሥርዓት ተከትሎ ወደ ንግስቷ ይሄዳል። ፍርዱ የሚሰጠው ከሳሽና ተከሳሽ (በወቅቱ የሚጠቀሙት ቃል ይሄ ባይሆንም) የነጠላቸው ጫፍና ጫፍ አንድ ላይ ታስሮ ነው። እስከፍርዱ ፍጻሜ የየዕለት እንቅስቃሴያቸው ሁሉ እንደተቆራኙ ነው። ሲጸዳዱ እንኳን እንደተቆራኙ ነው። እንደዚያ ተሳስረው ሜዳና ገደሉን፣ ወንዙን አቋርጠው ይሄዳሉ።

‹‹በህግ ከሄደች በቅሎዬ ያለህግ የሄደች ጭብጦዬ››

የሚለውን አባባል እዚህ ጋ በግልጽ እናገኘዋለን። ጎበዜ እና ጎንጤ ተቆራኝተው ፍትሕን እየፈለጉ ሳለ ጎበዜ

ታመመ፤ ጎንጤ በጣም ጨነቀው። ፍትሕን ሳናገኝ ይሞትብኛል ብሎ ነው የተጨነቀው። ሁለቱም ፍትሕን ማግኘት የፈለጉት በሚሰጣቸው ፍርድ ብቻ ነው። ለህሊናቸው ታማኝና ተገዢ ነበሩ ማለት ነው። ባላንጣውን እዚያ ጫካ ውስጥ መግደል ይችል ነበር። ዳሩ ግን እርሱን ቢገድለው በህግ ተከራክሮ አሸናፊነቱ አይታወቅለትም። መግደል ማንም ሊያደርገው የሚችለው ነው፤ ተከራክሮ ማሸነፍ ግን የብልሆች ነው። ሥርዓተ ሙግቱም በበልሃ ልበልሃ ነው።

በዚህ ፊልም ውስጥ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ምን ያህል ለህሊናቸውና ለህግ ተገዥ እንደነበሩ ያሳያል። ሰለጠኑ በሚባሉት አገሮች ሳይቀር በዚህ ዘመን አደገኛ አጥር ሁሉ ወንጀልን ማዳን አልቻለም። በዚያን ጊዜ ግን ለአንዲት የነጠላ ጫፍ ቁርኝት ተገዢ ነበሩ። 15 ቀን ሙሉ በነጠላ ጫፍ ታስረው ሲቆዩ ያንን መፍታት ተስኗቸው አይደለም። ሌላው ይቅርና በዚያ ወጣ ገባ በበዛበት አካባቢ ውስጥ ብቻቸውን ሲሄዱ የነጠላውን ጫፍ ፈተው ሰው ያለበት ሲደርሱ ማሰር ይችሉ ነበር። ግን የህግ ተገዥነታቸው ለህሊናቸው ነበርና ይህን የሚያስብ ተንኮል ልቦናቸው አይፈቅድማ!

አተዋወንእንደአንድ የፊልም ተመልካች (ባለሙያ አይደለሁም

ለማለት ነው) ስለአተዋወኑ አንድ ነገር ልበል። በፊልም ውስጥ የሚደረግ የአተዋወን ድርጊት ‹‹አርቲፊሻልነት›› ይበዛዋል። ያ ማለት ብስጭትን ወይም ደስታን ወይም ሌላ የሆነ ስሜትን ለመግለጽ በገሃዱ ዓለም የሌለ ይሆናል። ድንገት ተቆርጦ ብናገኘው ፊልም እንደሆነ ይታወቃል ማለት ነው። በቁራኛዬ ውስጥ ግን እንደዚያ አይደለም። አተዋወኑ በቀጥታ የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩትና የሚያደርጉት ነው የሚመስል።

ፊልሙ እንዴት ተሰራ?ይሄን ፊልም ለመሥራት በጠቅላላው የአምስት ዓመት ጊዜ

ወስዷል፤ አምስት ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል። ጸሐፊና አዘጋጁ ሞገስ ታፈሰ(ፒ.ኤች.ዲ) በማህበረሰብ ጥናትና ልማት (Social Work and Social Development) ምሩቅ ነው። በማህበረሰብ ላይ የሚያተኩሩ በርካታ ጥናትና ምርምሮችን እና ዘጋቢ ፊልሞችን ሰርቷል።

ቁራኛዬ ፊልምን ለመሥራት የተጠቀመው ጥናት መረጃ በማሰባሰብ ጥናት ብቻ ሳይሆን አብሮ በመኖር ነው። የሚበሉትን እየበላ፣ የሚጠጡትን እየጠጣ እና የሚኖሩትን

ሁሉ እየኖረ ነው። ፊልሙን የሰራው በቀጥታ የሚኖሩትን ኑሮ ነው። ከመቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው አዛውንትንም አግኝቶ መረጃ ያሰባሰበበት አጋጣሚ ነበር። ከእነዚህ የዕድሜ ባለጸጎች ያገኘው ነገር ደግሞ ከአንዳንድ ሰዎች ለተነሳ አንድ ጥያቄ መልስ ሆኖታል።

የፊልሙ ታሪክ በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግስት ላይ የሚያተኩር ነው። እንደ «ቁራኛዬ» እና «ሌባሻይ» ያሉ ሥርዓቶች ደግሞ ከንግስት ዘውዲቱ በፊት በነበሩት በልጅ ኢያሱ ጊዜ በአዋጅ የቀረ ነው፤ ታዲያ ለምን ያ ሥርዓት በንግስት ዘውዲቱ ጊዜ ሆነ? የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ።

ሞገስ እንደሚለው ልጅ ኢያሱ በአዋጅ ያስቀሩት እንጂ ማህበረሰቡ ሥርዓቱን ይጠቀምበት ነበር። እንዲያውም እስከ ቀዳማዊ ኃይልሥላሴ ድረስ ይከናወን ነበር።

አስተያየትቁራኛዬ ፊልም እውነተኛውን የአገርቤት አኗኗር በማሳየቱ

ወደዘጋቢ ፊልምነት የተጠጋ ነው። ይህ የሆነው ደግሞ ፊልሙን የሰራው ሰው፤ አንድም የማህበረሰብ አጥኚ ስለሆነ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጥናቱን የሰራው ዝም ብሎ በመጠየቅና መረጃ በማሰባሰብ ብቻ ሳይሆን በመኖር መሆኑ ነው።

ሁለት ማሳረጊያአንድ፡- ኪነ ጥብብ የማንም ሰው ሕይወት ነውና ፊልም

በስነ ጽሑፍ ሰዎች ብቻ ሳይሆን በየትኛም ሙያ ውስጥ ያሉ ሰዎች ቢሰሩት እንደዚህ ገላጭ ይሆናልና ሌሎችም ቢነሳሱ፤

ሁለት፡- ራሳቸው የፊልም ሰዎች ይስሩት ከተባለም በመጠየቅና በአንድ ሰሞን ጥናት ብቻ ሳይሆን እንዲህ በጥልቀት በማጥናትና ኖሮ በማየት ቢሆን! ለፊልም ሰሪዎች ልቦና ይስጥልን!

የፊልሙ ታሪክ በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግስት ላይ የሚያተኩር ነው። እንደ «ቁራኛዬ» እና «ሌባሻይ» ያሉ ሥርዓቶች ደግሞ ከንግስት

ዘውዲቱ በፊት በነበሩት በልጅ ኢያሱ ጊዜ በአዋጅ የቀረ ነው፤ ታዲያ ለምን ያ ሥርዓት በንግስት ዘውዲቱ ጊዜ ሆነ? የሚሉ ጥያቆዎች ነበሩ።

በአዲስ መንገድ

፲፪

Page 13: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

13የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

ቁጥሮች ይናገራሉ

ሲራራ >>

ገበያው በሳምንቱ

ጌትነት ምህረቴ

በአክሱም ዘመነ መንግሥት ጥንታዊው የንግድ መስመር በምጽዋ ተጀመረ። በመካከለኛው ዘመን የንግድ መስመሩ ወደ አራት አድጓል። ኢትዮጵያ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በቀይ ባህር መስመር ህንዶችና ግሪኮች የንግድ ግንኙነት ያደርጉ እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል። በሌላ በኩል ደግሞ ግብጾች የዓባይን ወንዝ ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር።

በኢትዮጵያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም በአንሰራራው የረዥም ርቀት ንግድ የሲራራ ነጋዴዎች መጠሪያ ስያሜ ጀበርቲ (Jabarti) እና አፍካላ (Afkala) ይባሉ ነበር። ጀበርቲ ተብለው የሚጠሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ ሙስሊም ሲራራ ነጋዴዎችን ሲሆኑ አፍካላ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የነበሩ የኦሮሞ ሲራራ ነጋዴዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

ረዥም ርቀት ንግድ ይካሄድ የነበረው ግትልትል ግመሎች (Caravan) በሚጠቀሙ ነጋዴዎች ነበር። እነዚህ ነጋዴዎች ደግሞ ሲራራ ይባላሉ። በዘመኑ ዘራፊዎችና የየድንበሩ የተለያዩ አስተዳዳሪዎችና ገዥዎች ከፍተኛ የሆነ ቀረጥ በማስከፈል ሲራራ ነጋዴዎችን ያማርሯቸው ነበር። እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም ነጋዴዎቹ በቡድን ሆነው በመጓዝ ረጅም ርቀት ይነግዱ ነበር። በቡድን ሆነው የሚሄዱትን ነጋዴዎች የሚያስተባብርና የሚመራ አንድ ሰው ይሾማሉ፤ መጠሪያ ስያሜውም «ነጋድራስ» ይባላል። በወቅቱም ዘመናዊ መገናኛና መጓጓዣ ስላልነበረ ብዙ ፈተናዎች የሚያጋጥማቸው ቢሆንም ያንን ተቋቁመው ነበር የሚነግዱት።

ሲራራ ነጋዴዎቹ ወደ ውጭ ከሚልኩት ሸቀጦች መካከልም ወርቅ ፣ዝባድ ፣ ቆዳ ፣ሌጦ ፣እጣንና ቡና ይገኙባቸዋል። ወደ ሀገር የሚያስመጡት ደግሞ መዳብ ፣ቅመም ፣ልብስ፣ ዶቃዎች፣ ሃርና ሌሎች ሸቀጦች ይገኙባቸዋል።

ዋነኛ የገበያዎቹ ማዕከል ደግሞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተዘረጉ የንግድ መስመሮች ናቸው። ለአብነት ያህል እናርያ፣ ቦንጋ በከፋ ፣ ሂርማታ በጅማ ፣አሰንዳቦ በወለጋ ፣ባሶ በጎጃም ፣ በጎንደር መተማ፣ ሱዳን ተሻግሮ ወደ ግብጽ ሲያቀና ሌላው መስመር ደግሞ በጎንደር፣ ዓድዋ ፣አዶሊስ /ምጽዋ ዋነኛ የንግድ መስመር ነበሩ። ምጽዋ የሀገሪቱ የሰሜኑ ክፍል መዳረሻ፣ የንግድ ኬላና ወደብ ሆና ለረጅም ጊዜ አገልግላለች።

በምስራቅ ምዕራብ የንግድ መስመር ደግሞ ሶዶ በጉራጌ ፣አንኮበር እና አልዩ አምባ በሰሜን ሸዋ፤ድሬዳዋና ሐረር በሐረርጌ ይገኙበታል። በዚህ መስመር የዜይላና በርበራ መዳረሻ ወደቦች ሆነው አገልግለዋል። ይህ ረዥም ርቀት የንግድ መስመር የሀገራችንን ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ይጠቁመናል።

አጼ ምንሊክ ዛሬ ያለችውን ኢትዮጵያ አንድ አድርገው ከማስተዳደራቸው በፊት ይብዛም ይነስም የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በጌምድር፣ ጎጃም፣ ትግራይና የሸዋ አካባቢዎች የራሳቸው ነጻ ግዛት ነበሩ። ሌላው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ ከፋ፣ ጅማና ወለጋ ራሳቸውን የቻሉ ግዛቶች እንደነበሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶክተር ብርሀኑ ደኖ ያወሳሉ። ይህንን መሰረት አድርጎ

ይህ አምድ በዋናነት በማይክሮ ደረጃ ያሉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ይሆናል፤ ትልልቅና አነጋጋሪ ሰበር ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ ንግድና አጠቀላይ የቢዝነስ ዘገባዎች ይስተናገዱበታል። ከትንንሽ ስራዎች ተነስተው በትክክለኛው መንገድ ሰርተው ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች ተሞክሯቸው ያካፍሉበታል። የሳምንቱ ልዩ ልዩ ሸቀጦችና የግንባታ ግብአቶች የገበያ ሁኔታ ይዳሰስበታል።

ጀበርቲ ተብለው የሚጠሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ ሙስሊም ሲራራ ነጋዴዎች ሲሆኑ አፍካላ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የነበሩ የኦሮሞ ሲራራ ነጋዴዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

ከአልዩ አምባ እስከ ዘይላ፤ ከአሰንዳቦ እስከ ምጽዋ

• በ2010 ዓ.ም 135 ነጥብ 53 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል።

• በዘንድሮ በጀት ዓመት 199ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ባለፉት ሰባት ወራት 113 ነጥብ 86 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል።

• የዘንድሮ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

ከሾላና መገናኛ ገበያዎች የተገኘ የዋጋ መረጃ

አይነት መጠን ዋጋባቄላ በኩንታል ከ3500

እስከ 4000 ብር

ሽንብራ በኩንታል ከ3000 እስከ 3500 ብር

ምስር በኪሎ ከ60 እስከ 65 ብር

ማኛ ጤፍ በኩንታል ከ2800 እስከ 3000ብር

በቆሎ በኩንታል ከ1100 እስከ 1200ብር

ቲማቲም በኪሎ ከ14 እስከ 16ብር

ሽንኩርት በኪሎ ከ14 እስከ 16 ብር

ሲሚንቶ በኩንታል ከ250 እስከ 260

ፌሮ ብረትበ32 ሚሊሜትር

በኪሎ 42 ብር

፲፫

በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ይቆረጥ የነበረው ደረሠኝ

አንደኛ ከቦንጋ ጀምሮ በሶዶ አድርጎ አልዩ አምባ ደርሶ በሐረር አቋርጦ በዘይላና በበርበራ ወደብ ወደ መካካለኛ ምስራቅ አገሮች መዳረሻውን ያደረገ የንግድ መስመር ነበር።

ሁለተኛው የንግድ መስመር ደግሞ ጅማ ፣ሲቃ-አሰንዳቦ-ሆሮ ጉድሩ(ምዕራብ ወለጋ) ባሶ በሚባለው አካባቢ አቋርጦ በጎንደር- በመተማ አድርጎ ወደ ሱዳን የሚሄድ የንግድ መስመር ነው። ሦስተኛው ደግሞ ጅማ ፣ሲቃ-አሰንዳቦ-ሆሮ ጉድሩ (ምዕራብ ወለጋ) ባሶ በሚባለው አካባቢ አቋርጦ በጎንደር አልፎ በዓድዋ አድርጎ ወደ ምጽዋ ይሄድና ወደ ውጭ ይወጣል። የሰሜንና የደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አንድ አይነት የፖለቲካ አስተዳደር ስርም ባይሆኑም ያን ጊዜም ቢሆን ለረጅም ጊዜ በንግድ የተሳሰሩና የሚተዋወቁ ነበሩ።

እነዚህ የንግድ መስመሮችም ለዘመናዊው ንግድ መሰረትና አመላካች ናቸው። ለረጅም ጊዜና ከ23 ዓመት በፊትም በምጽዋ ነበር የወጪና የገቢ ንግድ የሚካሄደው። (አሁንም ግንኙነቱ ተሻሽሎ መጠቀም ልንጀምር ነው) ።ሌላው መስመር ቀደም ሲል የነበሩት የንግድና የወደብ መስመሮች ታጁራ፣ በርበራና ዘይላም አሁን እየተጠቀምንበት ካለው በጅቡቲ ወደብ መልካም ስነ ምድራዊ አቀማመጣቸው ቅርበት ያላቸው ናቸው።

ቀደም ሲል በመተማ በኩል ወደ ሱዳን የሚሄደው የንግድ መስመርም አሁንም ነዳጅና አንዳንድ ዕቃዎች የሚገቡበት ነው። በጥቅሉ የአየር ትራንስፖርትን ሳይጨምር አሁንም ብዙ የገቢና የወጪ ንግዶች የሚካሄዱት ቀደም ሲል በነበሩት መስመሮች አቅራቢያ ነው።

ከዋና ዋና የንግድ ሸቀጦች መካካልም የከብት ቆዳ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ የአውራሪስ ቀንድ፣ ዕጣን፣ ዝባድና አቡጀዴ ልብስ ይገኙበታል። በመካከለኛው ዘመን ዕቃ በዕቃ ከመለዋወጥ ጎን ለጎንም በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ አሞሌ ጨው ዋነኛው የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ አገልግሏል።

በአጼ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት ደግሞ ንጉሱ ከኦስትሪያ መንግሥት ጋር በፈጠሩት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በንግሥት ማሪያቴሬዛ ስም የታተመው የማሪያ ቴሬዛ ብር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወረቀት መገበያያ ገንዘብ ሆኖ ማገልግል ጀመረ። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው አቢሲንያ ባንክም የውጭ

ገንዘብ ነበር የሚጠቀመው። ቀስ በቀስ የባንክ ሥራ እየተስፋፋ ሲመጣ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንገሥት ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ አሳትማ ሥራ ላይ አውላለች።

«ንግዱ በሚፈለገው መልኩ ተስፋፍቷልና አድጓል ማለት አይቻልም» የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶክተር ብርሀኑ፤ በእጅ ሙያተኞች ለምሳሌ ሸማኔው፣ ሸክላ ሰሪውና ነጋዴው የተለያዩ አሉታዊ ስያሜ የሰጣቸው ስለነበር በሚፈለገው መልኩ ንግዱ አድጓል ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። በመሆኑም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችም በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች እንዳይስፋፉ ጫና አሳድሯል።

የትምህርት አለመስፋፋት፣ ባህላችንና የፖለቲካ ስርዓቱ የአገር ውስጥ ምርቶችን የሚያጥላላ ስለሆነ ንግዱ ረጅም ዘመን እንደማስቆጠሩ የተስፋፋ እንዲሆን አላስቻለም። ይህም የመፍጠር ችሎታንም እንዲቀጭጭ አድርጎታል። በትንሽ የእጅ ሥራ ሙያ የተጀመረው የአገር ውስጥ ንግድ ሥራ ተስፋፍቶ ለማደግ ዕድል ስላላገኘ ከውጭ የመጣው ሸቀጥ ነው ዘመናዊ የሚባለው። በዓለም ላይ ዘመናዊ ንግድ ተጀመረ የሚባለው ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ነው። የእንጨት፣ የመጠጥ፣ ልብስ፣ የቆዳ ውጤቶች ድንበር አቋርጠው ይሸጡ ነበር።

ጥንት መካከለኛው ምስራቅ የነበረው የንግድ መዳረሻ ዛሬ ከመካከለኛው እስያ አገራት ወደ አውሮፓና አሜሪካ አቅጣጫውን ቀይሯል። ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ፊታቸውን ወደ አሜሪካ፣አውሮፓና ሩቅ ምስራቅ እስያ ማድረጋቸውን ምሁሩ ይተነትናሉ። የኢትዮጵያ ምርቶች የግብርና ምርቶች ስለሆኑ ንግዱ ወደ እነዚህ አገራት እያዘነበለ ነው። በአሁኑ ጊዜ መካከለኛ ምስራቅ አገራት ብዙ የኢንዱስትሪ መስፋፋት አይታይም። ሰላምና መረጋጋትም የለም።

የኢትዮጵያን እሴት ያልተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች በብዛት የሚፈልጉት ቻይና፣ ምዕራብ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ናቸው። በዚህ ምክንያት ብዙ አገራት ፊታቸውን ወደእነዚህ አገራት አዙረዋል። ኢትዮጵያም የዚሁ አካል ናት። ምክንያቱም የዓለም አቀፍ የንግድ መዳረሻዎች የሚወሰኑት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ፍላጎት ነው። አሁንም በዘመናዊ ዓለም የንግድ መዳረሻንና የሚላኩ ምርቶችን አይነት ማስፋፋት ያስፈልጋል።

አልዩ አምባ እስከ ዘይላ ወደብ ድረስ ተዘርግቶ ለነበረው የሲራራ ንግድ ማዕከል ነበረች። በ1834 እና 1835 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የቀረጥ ውል የተፈረመው በአልዩ አምባ ገበያ መሠረት ነው። በአጼ ምንሊክ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረጥ መሥሪያ ቤት ሲከፈት በአልዩ አምባ የጉሙሩክ ጽሕፈት ቤት ሥራውን እንዲጀምር ተደርጎ ነበር።

በዚህም መሠረት በዘይላ ወደብ የንግድ መስመር በኩል ወደ ሀገራችን በሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ላይ የቀረጥ ክፍያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረባትና የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የጉሙሩክ ከተማ አልዩ አምባ ሆነች። ከአንድ ሺህ 500 እስከ አንድ ሺህ 700 የሚጠጉ ግመሎች የአገር ውስጥ ሸቀጦችን ወደ ውጭ ያጓጉዙባት እንደነበርም ይነገራል።

በተጨማሪ አልዩ አምባ ከተማ በ19ኛው ከፍለ ዘመን የሲራራ ንግድ ማዕከል ነበረች ። በከተማዋ ከፐርሽያ፣ ከህንድና ከዓረብ አገሮች የሚመጡ በርካታ የውጭ ዜጎች ይኖሩባት እንደነበርም ጎብኝዎች ጽፈውላታል። በአጼ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት የታክስ ስርዓት ቢኖርም በገቢና በምርት ላይ የተጣሉት ዘመናዊ የታክስ ስርዓት ተግባራዊ የሆነው ግን በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት ነው። ይህ የታክስ ስርዓት እየተሻሻለ ሄዶ ዛሬ ላይ ደርሷል።

• የበጀት አመቱን ዕቅድ ለማሳካት በቀሪዎቹ አምስት ወራት 65 ነጥብ 54 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ይጠበቃል

Page 14: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

14 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ >>

መንትዮቹ የዘመን ሃኪሞቻችን ናቸው። ዶክተር ኢየሩሳሌም ጌታሁን እና ዶክተር ቃልኪዳን ጌታሁን ይባላሉ። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሜዲካል ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሀያት ሜዲካል ኮሌጅ በህክምና በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በ«ትዊንስ ክሊኒክ» በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከአንባቢዎች ለሚቀርቡላቸው የጤና ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ።

ዳንኤል ወልደኪዳን

መንትዮቹ ሃኪሞች ዶክተር ኢየሩሳሌም ጌታሁን እና ዶክተር ቃልኪዳን ጌታሁን ሻሸመኔ ከተማ ነው ተወልደው ያደጉት። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ሻሸመኔ ካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት ተምረዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በኩየራ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሜዲካል ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሀያት ሜዲካል ኮሌጅ በህክምና በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል። በአሁኑ ወቅት በግላቸው «ትዊንስ ክሊኒክ»ን በመክፈት በሙያቸው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

መንትዮቹ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ በየክፍሉ ደረጃ በአንድ ወንበር ላይ ተቀምጠው ተምረዋል። ፍላጎታቸውና የልጅነት ህልማቸው አንድ አይነት በመሆኑ ሀኪም መሆንን ይመኙ ነበር። ምርጫቸውም አንድ አይነት ነበር። የሚፎካከሩት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ሳይሆን እርስ በርሳቸው ነበር። አንድም ጊዜ በመካከላቸው ሌላ ተማሪ ሳያስገቡ እየተፈራረቁ ነበር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የሚይዙት። ልዩነት ቢመጣም እጅግ በጣም ጥቂት ነጥቦች ይሆናል።

ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ዩኒቨርሲቲ እሥከሚጨርሱ ድረስ የመምህሮቻቸው ድጋፍ አልተለያቸውም። የፈተና ውጤታቸው አንድ አይነት እየሆነ ያስቸገራቸው መምህራን ቦታ በመቀያየር ቢፈትኗቸውም ውጤቱ ያው ነበር የሚሆነው። ሲሳሳቱም ተመሳሳይ፤ ሲሰርዙም እንዲሁ ተመሳሳይ ነበር።

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገቡ ከመጀመሪያ ደረጃው ብዙም የተለየ አልነበረም። ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥባቸው ከፍተኛ ቢሆንም በአጋጣሚ ወደ ህክምና ትምህርት የሚያስገባቸው አልነበረም። ሁለቱም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ነበር ምርጫቸው ያደረጉት። ላቦራቶሪን ለመማር ፈለጉ ተሳካላቸው። በምርጫቸው መሰረትም አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ አንዳይነት የትምህርት ክፍል፤ ብሎም አንድ ዶርም በአንድ ተደራራቢ አልጋ ላይ ተኝተው ተማሩ። ተጋግዘው ስለሚያጠኑም በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቁ።

በዚህ ወቅት ነበር በህይወታቸው አስቸጋሪ የሚባለው ጊዜ የተከሰተው። ዶክተር ኢየሩሳሌም በጥቂት ነጥብ በልጣ ስለነበር ትምህርት ሚኒስቴር ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ይመድባታል። ለመጀመሪያ ጊዜ መለያየታቸው እርግጥ የሆነው ያኔ ነበር።

ዶክተር ኢየሩሳሌም ለስልጠና ወደ አዳማ ዩኒቨርሲቲ ስታመራ ለዶክተር ቃልኪዳን ውስጧ እየሩሳሌም ካላንቺ መኖር አይሆንላትም ይላት ነበር። እርሷ ሀያት ሜዲካል ኮሌጅ ለህክምና ትምህርት ስትመዘገብ እህቷንም አስመዘገበቻት። እንዳሰበችውም ሆነና ዶክተር ኢየሩሳሌም የጅማ ዩኒቨርሲቲን መምህርነትን ትታ ወደ አዲስ አበባ መጣች።

አስቸጋሪ የሆነባቸውን የመለያየት አጋጣሚ አስወግደው ዳግም ዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሀያት ሜዲካል ኮሌጅ ተማሩ። መንትዮቹ ዶክተሮች እስካሁን ባለው የህይወት ጉዟቸው ለአንድ ወር ብቻ ተለያይተዋል። ያንንም እንደ አስቸጋሪ ጊዜ ያስታወሱታል። 15 ቀን ለስልጠና አዳማ ዩኒቨርሲቲ እያለች፤ ቀጣዩን 15 ቀናትም በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስራ ስትጀምር። እንደዛም ሆኖ ቢያንስ በሳምንት ሁለትና ሶስት ጊዜ ይገናኙ ነበር። ከዚህ ውጭ አስካሁን በመንፈስም ሆነ በአካል የለያቸው አጋጣሚ አልተፈጠረም።

የተግባር ትምህርታቸውን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተማሩ። የአንድ ዓመት ልምምዳቸውንም እዛው አገልግለዋል። በማዕረግ ተመርቀው ከወጡ በኋላም ወደ ትውልድ ሀገራቸው ሻሸመኔ በመልካ ኦዳ ሆስፒታል ተመድበው ለተወሰነ ጊዜ አገልግለዋል። ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ክሊኒክ በመክፈት በግላቸው መስራት ጀመሩ።

መንትዮቹ ዶክተሮች ክሊኒክ ለመክፈት ሲያስቡ የመጀመሪያ ስራቸውን ያደረጉት ብዙ ህዝብ የሚኖርበትንና ክሊኒክ የማይበዛባቸውን አካባቢዎችን በማጥናት ነበር። በጥናታቸው መሰረት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ገና በመልማት ላይ ያለ፤ የህክምና ተቋማትም ያልተስፋፉበት በመሆኑ ምርጫቸው አደረጉት። ስያሜውንም «ትዊንስ ክሊኒክ» አሉት።

የትዊንስ ክሊኒክ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅነቱን ኃላፊነት በአምስት ደቂቃ ቀድማ የወጣችው ዶክተር ኢየሩሳሌም

መንትዮቹ የዘመን ሀኪሞች

ተረከበች። ክሊኒኩ በህክምና መሳሪያዎች የተሟላ ነው። የ24 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል። በላቦራቶሪ፣ በአልትራሳውንድ በመታገዝ የእናቶች እርግዝና ክትትል፣ መለስተኛ የቀዶ ህክምና ከጳውሎስ ሆስፒታል በሚመጡ ስፔሻሊስት ሀኪሞች በመታገዝ ሙሉ ህክምና ይሰጣሉ። በታካሚዎች ፈቃድ ሁለቱም ዶክተሮች በአንድ ላይ የሚመረምሩበት አጋጣሚም ብዙ ነው። በቋሚነት ለ10 ባለሙያዎች፤ በትርፍ ሰዓት ለ6 ሰራተኞች የስራ እድል በመፍጠር እራሳቸውን አግዘው የአካባቢውን ማህበረሰብ በማገልገል ላይ ናቸው።አሁን ያሉበትን ደረጃ መነሻቸው መሆኑን በማመናቸው የማህበረሰቡን ፍላጎትና ያለውን ክፍተት በመለየት በተለያዩ ሙያዎች ስፔሻላይዝ ለማድረግ ይፈልጋሉ።

መንትዮቹ ዶክተሮች የሚዝናኑት እርስ በርሳቸው ነው። ዶክተር ቃልኪዳንን የምታዝናናት ኢየሩሳሌም ስትሆን፤ ዶክተር ኢየሩሳሌምን የምታዝናናት ደግሞ ቃልኪዳን ብቻ ናት። የሁለቱም ደስታ ያለው በሁለቱ ውስጥ ነው። ሁለቱም እናታቸው ጋር ወይም ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ጋር በማሳለፍ ይዝናናሉ። ሻይ ቡና የማለት ሀሳብ ካላቸው ይቀዳደሙ ይሆናል እንጂ ምርጫቸው አንድ ቦታ ይሆናል። የቴሌቪዥን ፕሮግራም ምርጫቸው፣ የመጽሀፍ ምርጫቸው፣ ስፖርት የመስራት ፍላጎታቸው አንድም ቀን ተጋጭቶባቸው አያውቅም። በቀለም፣ በምግብ፣ በቦታ ምርጫ ሳይቀር አንዷ ያሰበችውን የአንዷም ምርጫ ይሆናል።

አሁን አንድ ላይ ስለሚኖሩ ስለሚመካከሩም የአለባበስ ምርጫቸው አንድ አይነት ነው። ወደፊት ህይወት በትዳር ልትለያያቸው ግድ ይላልላና ምን አስበው ይሆን? የሚል ጥያቄ አነሳሁላቸው። «የግል ኑሮ መኖሩ አይቀርም ግን በእርግጠኝነት

አንድ ዓይነት አለባበስና አንድ ዓይነት የጸጉር ስታይል ይኖረናል። ምክንያቱም እኔ ልለብስ ያሰብኩትን ልብስ እሷ አውጥታ ትጠብቀኛለች። አሁንም አንዳችን ነን የሁለታችንንም ልብስ የምንመርጠው። ስለዚህ ተለያይተን ብንኖርም እኔ የምፈልገውን ልብስ ለብሳ እንደምትወጣ እርግጠኛ ነኝ» በማለት የመለሰችልኝ ዶክተር ቃልኪዳን ነበረች።

ሌላ ጥያቄ ለዶክተር ቃልኪዳን አስከተልኩላት በጣም የወደድሽው ልብስ አንድ ብቻ ቢሆን ምን ታደርጊያለሽ? መልሷ ፈጣን ነበር። «በርግጠኝነት አልገዛውም! አሁን ትልቅ ሆንን ያን ያህል የምርጫ ችግር ላያጋጥመን ይችላል፤ ነገር ግን ልጅ እያለን እናታችን ስትገዛልን አንዳይነት ልብስ ሆኖ መጠነኛ የአበባ ልዩነት ቢኖረው እንኳን አንለብሰውም። ታስቀይረዋለች እንጂ አንለብሰውም»

መንትዮቹ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የጊዜ እጥረት እንደሚኖርባቸው ይታመናል። ነገር ግን እውቀታቸውን ለማህበረሰቡ ለማካፈል መሻታቸው ብዙ በመሆኑ ካላቸው ጊዜ ቀንሰው ሳይሆን ማህበራዊ ኃላፊነታቸው የሚወጡበት እንደሆነ አምነው በቂ ጊዜ መድበዋል። ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የዘመን ሀኪም ሆነዋል።

የዘመን ሀኪም ለመሆን አዲስ ዘመን ጋዜጣን እንዴት መረጣችሁት?

‹‹አዲስ ዘመን ጋዜጣን የመረጥንበት ምክንያት 78ኛ ዓመቱን የያዘ ሀገራዊ ጋዜጣ ነው። እዚህ አንጋፋ ጋዜጣ ላይ መስራት እንደ እድል ነው የቆጠርነው። ብዙ አንባቢ እንዳለው ስለምናምን

በቀላሉ ማህበረሰቡን ለማገልገል የተሻለ አማራጭ ይሆንልናልና ቀዳሚ ምርጫችን አድርገነዋል»

ከአንባቢ ምን ትጠብቃላችሁ? «ከአንባቢያን ጥሩ ምላሽ እንደሚኖር እንጠብቃለን።

ለሚመጡ ማናቸውንም ጥያቄዎች በምንችለው አቅም ለመመለስ ዝግጁ ነን። የሚሰጡንን ማንኛውንም አስተያየት በመቀበል ፍላጎታቸውን ለማርካት ጥረት እናደርጋለን»

አንባቢዎች ጥያቄዎቻቸውን በምን መልኩ ቢልኩ ይመቻችኋል?

«አንባቢዎቻችን ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን እንዲያገኙ ጥያቄዎቻቸውን በተቀመጡት የጥያቄ ማቅረቢያ አማራጮች ቢልኩ ይመቸናል። ጥያቄዎቹን በማደራጀትና መረጃዎችን በማሰባሰብ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን››

መልዕክት‹‹ እኛ የዘመን ሀኪም በመሆናችን እጅግ በጣም

ደስተኞች ነን። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አክብሮ ይሄን እድል ስለፈጠረልንም ከልብ እናመሰግናለን። አንባቢዎችም ማወቅ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ጥያቄ ተከታትለን ምላሽ እናቀርባለን። አንባቢዎቻችንም ጥሩ የጤና ግንዛቤ እንደሚያገኙ እናምናለን። እንደምትማሩበትና እንደምትጠቀሙበት እርግጠኞች ነን»

ውድ አንባቢዎቻችን አንጋፋው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአዲስ ዘመን ቅዳሜ ከሚስተናገዱት አሳታፊ አምዶች መካከል ይህ «የዘመን ሀኪም» የተሰኘው አምዳችን ከእናንተ ለሚቀርቡ ጤናና ጤና ነክ ጥያቄዎች ምላሽ የሚቀርቡበት ነው።በየትኛውም የጤና ችግርዎ ለሚያነሷቸውጥያቄዎች በመንትዮቹ ዶክተሮች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጥበታል።

አድራሻችን በፌስቡክ-Ethiopian Press Agencyበስልክ-0111264326 0111264240በኢሜይል- [email protected] [email protected]

እኛ የዘመን ሀኪም በመሆናችን እጅግ በጣም ደስተኞች ነን። ጋዜጣው አክብሮ ይሄን እድል ስለፈጠረልንም አዲስ ዘመን ጋዜጣን ከልብ እናመሰግናለን። አንባቢዎችም ማወቅ የሚፈልጉትን ማን ኛውንም ጥያቄ ተከታትለን እናቀርባለን። አንባቢዎቻችንም ጥሩ የጤና መረጃዎችን በማግኘት ጥሩ ግንዛቤ እንደሚያገኙ እናምናለን።»'’

ዶክተር ኢየሩሳሌም ጌታሁን ዶክተር ቃልኪዳን ጌታሁን

፲፬

Page 15: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

15የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

ስድስቱ የኢህአዴግ ቀናትከእናንተም ከእኛም

Website - www.press.et Email - [email protected] Facebook - Ethiopian Press Agency

ዋና አዘጋጅ

ፍቃዱ ሞላአድራሻ ኢሜይል - [email protected]

ወረዳ - 13

የቤት ቁጥር - B402 H11

ስልክ ቁጥር - 011-126-42-40

ምክትል ዋና አዘጋጅ ዳንኤል ወልደኪዳንስልክ ቁጥር - 011-1-26-43-26ኢሜል - [email protected]

አዘጋጆች

ጌትነት ምህረቴቦጋለ አበበ ክፍለዮሃንስ አንበርብርማህሌት አብዱልመልካምስራ አፈወርቅዋለልኝ አየለ

አምደኞች

ጌታቸው በለጠ/ዳግላስ ጴጥሮስአሸናፊ ዘደቡብፍሬው አበበ

የኢትዮያ ፕሬስ ድርጅት ዋና

ስራ አስኪያጅ

ስልክ - 011-126-42-22

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍ

ኢሜይል - [email protected]

ስልክ - 011-156-98-73ፋክስ - 011-156-98-62

የማስታወቂያ መቀበያ ክፍል

ስልክ - 011-156-98-62

የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያ

ስልክ - 011-1-26-43-39

ማከፋፈያ

ስልክ - 011-157-02-70

ርዕሰ አንቀጽ

ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም ተቋቋመ

አዲስ ዘመን

አስተያየት

የዝግጅት ክፍል ፋክስ - 251-011-1-56-98-62

ለውጥ ላይ ነን። የዛሬው ለውጥ ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ አርግዟል። ነፍሰጡሯን አገር በሚፈለገው መንገድ ማዋለድ ከተፈለገ፤ አንድ አካል ብቻውን ተጉዞና አግዞ ይጨርሰዋል ማለት ዘበት ነው። የትላንቱ መጥፎ ወደ ነገ እንዳይሻገር ጥሩውን ይዞ ሀገርን ወደፊት ለማራመድ ለውጡን የጋራ ማድረግ የግድ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ሚዲያው ደግሞ ህዝቡ ለሚጠብቀው ለውጥ ማሻገሪያ ድልድይ ነው። በአገራችን የታሪክ ምዕራፎች ሁሉ የታዩ ለውጦችን ሚዲያው እርሾ ሆኖ ለውጡን ማስቀጠል ቢገባውም በተቃራኒው የቆመበት ታሪኩ የበረከተ ነበር።

በየዘመኑ የነበሩ ሚዲያዎችም ለህዝብ አገልጋይ ከመሆን ይልቅ በየዘመናቸው የነበረውን መንግሥት ሲያገለግሉ ኖረዋል። የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በ2009 ይፋ ባደረገው አንድ ጥናት የአገራችን ሚዲያ አድርግ የተባለውን ብቻ የሚያደርግ “ባሬስታ” ሆኗል ሲል ገልጾታል። ከዚህ ቀደም ተብሎም በተለያዩ መድረኮች ሚዲያው “አዝማሪ” ሆኗል የሚል ስያሜ ተሰጥቶት እንደነበር አይዘነጋም።ይሄ ከማንም በላይ ለሙያው ባለቤቶች ትልቅ ዱላ ነው።

የአገራችን ሚዲያ ሳንካው ብዙ ነው። ይህ ሳንካ በአንድ መድረክ፣ በአንድ አካል ጥረት፣ በአንድ ሰሞን ሥራ ብቻ አይቀረፍም። ነገር ግን በየሚዲያ ተቋሙና በየዘመኑ በሚሰሩ ስራዎች ሌሎች ከደረሱበት ደረጃ መድረስ ይቻላል ብለን እናምናለን። ከዚህ አንጻር ሁሉም አካል የድርሻ የድርሻውን መውሰድ አለበት።

የመጀመሪያው ድርሻ ወሳጅ መንግሥት ነው። መንግሥት ሚዲያው ይለወጥ ዘንድ የሚፈልገው ከአንገት ነው ከአንጀት? የሚለውን በተግባር ማሳየት አለበት። ስለሆነም በአዋጅና በመመሪያ መመለስ የሚገባቸውን ጉዳዮች ሳይውል ሳያድር መመለስ አለበት። ለአብነት ያህልም የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 590/2000ን ያወጣ መንግሥት ማስፈጸሚያ መመሪያውን ሳያወጣ ከ10 ዓመት በላይ አስቆጥሯል። ስለሆነም “እንዳያማህ ጥራው…” ያስመሰለውንና መረጃ ለማግኘት ትልቅ ሳንካ የሆነውን የአዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ በፍጥነት ማውጣት አለበት።

በሚዲያ ግብዓቶች ላይ የተጣለው ታክስ፣ በቅንጦት እቃዎች ላይ የሚጣለው የሱር ታክስ ነው። ይሄ ስህተት እንደሆነ መንግሥት ካመነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ሚዲያውን በተለይም የህትመት ሚዲያውን በህትመት ዋጋ ውድነት የተነሳ ቁልቁል የሰደደውን ይህንን የታክስ አይነት መንግሥት በፍጥነት ለአገርና ለህዝብ በሚበጅ መልኩ ማስተካከል አለበት።

የሲቪክ ማህበራት፣ ዜጎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ባለሀብቶች፣ ምሁራንና መሰል አካላት ሚዲያውን አብዝተው ይፈልጉታል። በተቃራኒው ሚዲያው አብዝቶ ሲፈልጋቸው ግን አብሮ ላለመስራት ሰበባቸው ብዙ ነው። ለውጥ እንፈልጋለን ከተባለ ሁሉም ለሚዲያዎች ተባባሪና አጋዥ መሆን አለባቸው።

ሚዲያዎች በተለይም የህዝብ የሆኑት ነጻ ሃሳብን ማስተናገድ ላይ ውስኑነት እንደነበረባቸው የአደባባይ ሀቅ ነው። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርም ሚዲያዎች እንደ አራተኛ የመንግሥት ኣካል ናቸውና በዚያ ልክ ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ከአንዴም ሁለት ሦስት ጊዜ ተናግረዋል፤ ለዘርፉ መለወጥ መንግሥታቸው ያለውን ቁርጠኝነት ግልጽ አድርገዋል። “ሜዳውም ያው ፈረሱም ያው” ሲሉም ጭምር መቀየር ያለበትን አመራርና አሰራር ቀያይረው የሚጠበቅባቸውን አድርገዋል። ከዚህ በኋላ ፋንታው የባለፋንታው ነው ብለን እናምናለን።

ከዚህ አንጻር የለውጡ ተቋዳሽ የሆነው ድርጅታችን በሚያሳትማቸው የህትመት ውጤቶቹ ላይ ስር ነቀል የይዘት ለውጥ ለማምጣት ላለፉት ስድስት ወራት ሲወጣና ሲወርድ ቆይቷል። የዚህ ድካሙ ፍሬ የሆነችው “አዲስ ዘመን ቅዳሜን” ለአንባቢዎቹ እነሆ ሲል አንድም መርቁልን አንድም ጉድለታችንን አቀበሉን አብራችሁንም ስሩ በማለት ጭምር ነው።

አሁን ሁሉም ነገር ተለውጧል ብለን እናምናለን። ከዚህ አንጻር ጋዜጣችንም በርካታ ነጻና የተለያዩ ሃሳብ የሚስተናገዱባቸው፣ በእርግጥም የህዝብ አገልጋይ መሆን የሚያስችሉ አሰራሮችንና አምዶችን ይዛ መጥታላች። ስለሆነም ሃሳብ አለኝ የምትሉ ሁሉ ወደ ጋዜጣችን ጋዜጣችሁ ፈጥናችሁ ኑ! አብረን እንስራ የምንለውም የአገርዎ ጉዳይ ያገባዎታል ብለን ስለምናምን ጭምር ነው።

አዲስ ዘመን ቅዳሜ የመለወጥ የለውጥም መጀመሪያችን ናት። ድርጅታችን እድሜውን የሚመጥን አይነት ሚዲያ መሆን እንዳለበት ያምናል። ስለሆነም ጉድለታችንን ትሞሉ ዘንድ፣ ጎባጣችንን እያቀናችሁ መልካሙንም እያወደሳችሁ ታነቡ ዘንድ የለውጥ ጅማሬያችንን እነሆ ብለናል።

ዮአማአ ከአዲስ አበባ

አንድ አባባል አለ፤ “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው” የሚል። እናም አንባቢ ሆይ የአገራችን አስተዳዳሪ ኢህአዴግ ነውና የእሱ ውደቀትና ድል የእኛም ውድቀትና ድል ነው ብዬ አምናለሁ። ስለሆነም ለአፍታም ቢሆን ወደኋላ ልመልስዎትና የኢህአዴግን የአምስት ቀናት ፈተናም ይበሉት ገድል ላስታውስዎና ነጻውን ሀሳቤን በነጻው አምድ ላይ አቀብዬዎ ልውጣ ።

እንዲህ ይጀምራል…. ከዓመት በፊት አገራችን ከዳር ዳር በተለያዩ

የነውጥ ማዕበል ተመትታ ክፉኛ ተናጠች። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከአንዴም ሁለት ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ቢታወጅም ነውጡ የሚከስም አልሆነም።ይልቁንም እየተባባሰና መልኩን እየቀያየረ ወርሀ ታህሳስ ላይ አደረሰን። ታህሳስም ባተ፤ አምሰቱ የኢህአዴግ ቀናት ስል የከተብኩት ታሪክም እንዲህ ተመዘገበ።

ታህሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም የአገሪቷ ሁኔታ ያላማረው የኢህአዴግ ሥራ

አስፈጸሚ አገሪቷ የገባችበትን ቀውስ ለመፍታት ስብሰባ መቀመጡን ይፋ አደረገ። ግንባሩ ለ17 ቀናት ድምጹን አጥፍቶ ግምገማ አካሄደ። አልፎ አልፎ ይወጡ ከነበሩ መግለጫዎች በስተቀር የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ በምን ዙሪያ እንደሚመክር በእርግጠኝነት መናገር ቀላል አልነበረም። ስለሆነም አይኖች ሁሉ አራት ኪሎ ላይ ሆነው ሰነበቱ።

ታህሳስ 20 ቀን 2010 ዓ.ም በ17 አመታት የትጥቅ ትግል የመንግስትነት

እርካቡን የጨበጠው የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ

ጥልቅ ተሀድሶውን 17ኛው ቀን ላይ ማብቃቱን አስታወቀ። ግንባሩ በውስጣዊና ውጪያዊ ችግሮች እንደተተበተበ ማረጋገጡንና ችግሮቹን ለመፍታትም የ17 ቀናት ስብሰባውን በድል ማጠናቀቁን በመግለጫው አበሰረ። ድፍን ያለ መግለጫ ስለነበረም ጭምር ብዙ ብዙ እያስባለን ለአምስት ቀናት ቆየን። በእነዚህ ቀናትም በመግለጫው የተነሳ ኢህአዴግ “አበጀህም”፤ “መስሎሃልም” ተባለ። (እኔ ምንድን ነበር ያልኩት..?)

ታህሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ምየተመረጡ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን

በተገኙበት የአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች ሊቃነመናብርት በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጡ። በዚህ መግለጫም “እውነትም ኢህአዴግ ታድሷል” የሚያስብሉ ውሳኔዎች መተላለፋቸው ይፋ ተደረጉ። የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት፣ ማዕከላዊ የተባለውን የወንጀል ምርመራ ዘግቶ ሙዚየም ለማድረግ እንደተወሰነ የሚገልጹና ሌላም ሌላም ውሳኔዎች ለህዝብ ይፋ ተደረጉ። ሁሉም ተደመመ።

ከዚህ በኋላ በአገሪቷ አራቱም አቅጣጫዎች ተነስቶ የቆየውና ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አስገብቶን የነበረው ሰላም ማጣት ይሰክናል የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አደረ። ይህ ግን አልሆነም። ኢህአዴግ ወሰንኩ ካለውም በላይ የህዝብ ጥያቄ አይሎ አገሪቷን ከዳር ዳር ናጣት፤ ሰላሟም በብዙ ራቃት።

የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና የኢፌዲሪ

ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ

መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ። ሁሉም ደነገጠ። ኢህአዴግ አበቃለትም ተባለ። ለመሆኑ የአቶ ሀይለማርያም በቃኝ ማለት “ከአንገት ነው ከአንጀት” ብዙ አከራከረ። ግራ ቀኙ በገባው ልክ እየተከራከረ ቀናት ተቆጠሩ።

መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓም የአቶ ሀይለማርያምን በቃኝ ማለት ተከትሎ

ኢህአዴግ እንደተለመደው በምክር ቤት ደረጃ ስብሰባ ተቀመጠ። የምክር ቤቱ ስብሰባ በቀላሉ የሚታይም የሚጠበቅም አልሆነም። ምክንያቱም በስብሰባው መቋጫ አዲሱን ሊቀመንበሩን መምረጡ አይቀርምና የግንባሩ ሊቀመንበር ማን ይሆን? የሚለው ብቻ ሳይሆን ከየትኛው ብሄራዊ ድርጅት ይመረጣል? የሚለውም ፈታኝና አጓጊ ሆነ። ቀጣዩን የኢህአዴግ ሊቀመንበር መምረጥ የአገሪቷን ጠቅላይ ሚኒስትር መምረጥም ጭምር ስለሆነ ምርጫው በቀላሉ የሚታይ አልሆነም።

የሆነው ሁሉ ሆነና ዶክተር አብይ አህመድ የግንባሩ ሊቀመንበር ሆነው ወጡ። አዲስ ፊት በኢህአዴግ ቤት ታየ። አዲስ ተስፋም በአገር ላይ ፈነጠቀ።

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓም አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ

አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብለው እርካቡን ሊጨብጡ በምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጸሙ። ኢትዮጵያም አዲስ ታሪክ አጻፈች ። አዲስ መሪ አገኘች። እነሆ ይህ ከሆነ አስር ወራት ተቆጠሩ።

ኢህአዴግ በእነዚህ ስድስት ታሪካዊ ቀናት አልፎ ሌላ ሰባተኛ ቀን ሰባተኛ ታሪክ ሊያስመዘግብ ወደ ምርጫ እየተንደረደረ ነው። ቀጣዩ ምርጫ

አሁን ያለው ኢህአዴግ ትክክለኛ መፈተኛው ነው። ቀጣዩን ምርጫ በትክክልም ምርጫ ማድረግ ከቻለ ለአገራችንም ለራሱ ለኢህአዴግም ትልቅ ኩራት ይሆናል። ማድረግ ካልቻለም ታሪክ መመዝገቡ የግድ ነውና ሌላ የማንከስ ታሪክ ሆኖ መመዝገቡ አይቀሬ ነው። ኳሷ ያለችው በኢህአዴግ ሜዳ ነው። ወደየት ይለጋታል አብረን የምናየው ይሆናል።

እስከ ሰባተኛው ታሪካዊ ቀን ድረስ ማለት የምንችለው ማለት የሚገባንን ብቻ ይሆናል። እናም አንባቢ ሆይ በእኔ እምነት ኢህአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲ ወይንም በመንግስትነት እጁ ወደ ምርጫ እያደረገው ያለው ጉዞ ይበል የሚያሳኝ ነው። ምርጫ ቦርድ የሁሉንም ወገን ይሁንታ ባገኙና ስለብቃታቸውና ገለልተኛነተታቸው ጥያቄ ባልተነሳባቸው ሰው ተዋቅሯል። ይሄ ሊመጣ ላለው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሩ መንደርደሪያ ነው። ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳም የሚፈተኑበት አገራዊ ሃላፊነት ላይ ናቸው።

ፍርድ ቤቱም በጣም ብቃትና ባላቸውና ገለልተኛ ሰው እየተመራ ይገኛል። በምርጫ ውጤት የሚከፋ አካል ካለ ነጻ ፍትህ የሚያገኝበት እድልም ተመቻችቷል ማለት ነው። እና ምን ቀረ? ተፎካካሪ ፓርቲ ነዋ!

አዎን ፓርቲዎች ሆይ ከወዲሁ ወገባችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ ተዘጋጁማ። የዘራችሁትን እንደምታጭዱ ከወዲሁ አውቃችሁ በርትታችሁ መልካም መልካሙን ብቻ ዝሩ። ባለ ሁለት አገር የሆናችሁም በግራ እና በቀኝ ያላችሁም አንዷን አገራችንን አብዝተን እንደምንፈልጋት ተረድታችሁልን እኔ ብቻ ትክክል ነኝ ከሚል እሳቤና አጀንዳ ውጡ።

የለውጥ ጅማሬያችንን እነሆ!

፲፭

Page 16: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

16 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ እንዲህም ይኖራል>>

ክፍለዮሐንስ አንበርብር

አንዲት በጭስ የታፈነች ቤት ውስጥ ዘልቄያለሁ። እዚህ ሰነፈጠኝ፣ አቃጠለኝ ብሎ መነጫነጭ የለም። ቤቷን ለተላመዷት ሰዎች የምድር ዓለም ናት። ሠላምታ ሰጥቼ ለማዕድ ቤት ቀረብ ብዬ ከመደቡ ላይ ተቀመጥኩ። ግራ ቀኝ የተደረደሩ ሰዎች ቁልጭ ቁልጭ እያሉ የሚጠብቁት እንዳለ ሁኔታቸው ያሳብቅባቸዋል። የልባቸውን ያሳኩት ደግሞ እንደየአቅማቸው፣ ሻይ፣ አረቄ፣ ቢራና ውሃ እየተጎነጩ ይጨዋወታሉ። በዚያች ጭስ ባፈናት እልፍኝ በጥዋቱ ጨዋታው ደርቷል። ሁኔታውን ላልተላመደ እንግዳ ሰው ግን ጭሱ ስለሚያፍነው፤ በደቂቃዎች ውስጥ ሊወጣ ይችላል።

ወደ ቤቱ የመጣሁበትን ጉዳይ አስረድቼ፤ በጭስ በታፈነችው ማብሰያ ክፍል ውስጥ እየተጨናበስኩ ዘለቅሁ። በሐዋሳ ሙቀት ላይ ተጨማሪ በዚች ጠባብ ክፍል ውስጥ በሚንቀለቀለው እሳትና ጭስ ታፍኜ ቆይታ አደረግሁ። ከብረት ምጣዱ ላይ የተጣደው ነገር በኃለኛው ይንቸከቸካል።ሽታው ሆድ ያላውሳል፤ ጭሱ ያፍናል፣ ሙቀቱ ጉልበት ያዝላል።

በዚህች ቤት የተገኘሁት በሐዋሳ ‹‹ኦልካ›› እየተባለ የሚጠራውን ምግብ ከጅምሩ እስከ አሠራሩ ላስተዋውቃችሁ ነው። የዚህን ምግብ ስያሜ ማን፣ መቼ እና ለምን እንደሰጠው በትክክል ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ተጠቃሚዎቹ ‹‹ኦልካ›› በሚለው ስያሜው ይግባባሉ።

ወይዘሮ ብርቱካን ብርሃኑ ‹‹ኦልካ›› ለደንበኞቿ ማቅረብ ከጀመረች አምስት ዓመታትን አስቆጥራለች። እርሷ ለኦልካ፤ ኦልካም ለእርሷ ባለውለታ ሆነዋል። ‹‹ኦልካ›› ማለት በዋናነት የከብቶች አንጀት ከተለያዩ ቅመማቅመሞች ጋር ተከሽኖ የሚዘጋጅ ምግብ ነው። አሰራሩም አድካሚና ፍዳ የሚያበላ ነው።

ወይዘሮ ብርቱካን የኦልካን አሰራር አንዲህ ትተርከዋለች። በመጀመሪያ የከብት አንጀት በሚገባ ይታለባል፤ ከዚያም ይከተፋል። በዚህ ሁሉ ሂደት ግን አንዳችም የውሃ ጠብታ አይነካውም። ‹‹ኦልካ›› በተፈጥሮ ቅባት ስላለው ተጨማሪ ቅባትና ፈሳሽ አያስፈልገውም። ከዚያ በመጥበሻ ላይ በእሳት ብስል ተደርጎ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ አዝሙድ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ኮረሪማ እና መከለሻ ቅመም በአንድነት ተፈጭቶ በስሱ ብን ይደረግበታል። ሊወጣ ሲልም የስጋ መጥበሻ (ሮዝመሪ) ጣል ይደረግበታል። በመጨረሻም ለተጠቃሚው ሲቀርብ ነጭ ሽንኩርት ከዝንጅብል ጋር ስልቅ ተደርጎ ይፈጭና ለማባያ እና ማጣፈጫ ከላይ ይጨመራል። ‹‹ኦልካ›› በበቆሎ ቂጣ ዛቅ ተደርጎ፤ አሊያም ደግሞ በእንጀራ ጠቅለል አድርገው ሲመገቡት አንጀት ያርሳል።

ኦልካ ሰውነትን ሰፋ፣ ደረትን ገፋ የሚያደርግ ሲሆን፤ ከጠቀሜታው የተነሳ ስፖርተኞችም በሚገባ እንደሚያጣጥሙት ነው ወይዘሮ የምትናገረው። ሽሮ እና ኦልካን የሚበለ ሰው ልዩነቱ የትዬሌሌ ነው የምትለው ብርቱካን የምትናገረው። ኦልካ አንዴ ልክክ አድርጎ የበላ ሰው ሙሉ ቀን የርሃብ ስሜት አይሰማውም። በጨዋታችን መሃል የኦልካው መረቅ እንጀራው ላይ እንዳያርፍም ወንፊት በመሰለ መካከለኛ ጭልፋ ዛቅ እያደረገች ታወጣለች።

‹‹ኦልካ›› በአብዛኛው በጥዋት የሚመገቡት ምግብ ነው የምትለው ወይዘሮ ብርቱካን፤ ከፍተኛ ስብ ስላለውና ከፀሐይ ሙቀት ጋር ስለማይስማማ ተመራጩ ጊዝ ማለዳ ላይ ነው። ረፈድ ሲል ብዙ ተጠቃሚ የለውም።

«ምግቡ ኦልካ፤ ዘፈኑ ዋካ! ዋካ!››

ብዙም አይታወቅም። ሐዋሳ ኦልካን በሰፊው እየተጠቀመችበት ቢሆንም፤ ስሙ ይለያይ እንጂ በሌሎች አካባቢዎች ጥቅም ላይ እንደሚውል ይነገራል። በአንዳንድ ስፍራዎች ‹‹ቲሽ፣ ሞርቶ›› እና የመሳሰሉ ስሞች አሉት።

ከአምስት ዓመት በፊት ቄራ ከሚሠራው አጎቷ የምግቡን አሰራር የቀሰመችው ወይዘሮ ብርቱካን ዛሬም ድረስ ከኦልካ ጋር ወዳጅነታቸው እንደቀጠለ ነው። ሐዋሳ ሠላም ሆና ሳለ እስከ 100 ኦልካ በቀን ትሸጣለች። በአሁኑ ወቅት ግን የሐዋሳ የሠላም አየር አልፎአልፎም ቢሆን ስለተረበሸ ከ40 ኦልካ በላይ አትሸጥም።

ወይዘሮ ብርቱካን ከኦልካ ጋር ፍቅሯን ማዝለቅ ትፈልጋለች። ‹‹ኦልካ›› ከጨረጨሰችው ማዕድ ቤት ወጥቶ ባለኮኮብ ሆቴሎች ዝናን ያተረፈ ምግብ እንዲሆ ትፈልጋለች። አልፎ አልፎ አዲስ አበቤዎችም ወደ ብርቱካን ቤት ሲያቀኑ ‹‹ኦልካ ምንድን ነው?›› ብለው ሲጠይቋት በአጭሩ ‹‹የተከሸነ ስጋ ጥብስ ነው›› በማለት ታላምዳቸዋለች። አንዴ የቀመሱት ሳያመነቱ ደምበኞቿ ይሆናሉ።

አቶ በኃይሉ ማቲዮስ ከባለቤቱ ብርቱካን ጋር ነው ለደንበኞቹ ኦልካ እየከሸነ የሚያቀርበው። ኦልካ ሲሰራ ቢላዋውም በጣም መሳል እንዳለበት ይናገራል። ሽንፍላ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ በሚገባ መለያየት አለበት። የበሬውን አንጀት የሚከትፈው ሰውም ፈርጠም ያለ ጡንቻ ሊኖረው ይገባል። ከውሃ ንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ በሚገባ መፅዳት አለበት። ሞራውንም ገለል፤ ገለል አድሮ መለየት ያስፈልጋል።ኦልካ ሲዘጋጅ ከባዱ ሥራ አንጀት መክተፉና ንጹህ አድርጎ ከውስጡ ያለውን ፈሳሽ ማለብ እንደሆነ ይነገራል።

‹‹በሐዋሳ የበሬ አንጀቱ ብቻ ሳይሆን ከንፈሩም ጥቅም ላይ ይውላል›› የሚለው በኃይሉ፤ በተለምዶ በአካባቢው አጠራር ‹‹ቡርቡርቻ›› ተብሎ የሚጠራው የከብቶች ከንፈርም ለጥርስ ጥንካሬ ሲባል ለምግብነት ይውላል። «ከበሬው አካል እጢዎች፣ ከዓይንና ጆሮው በስተቀር አንዳችም የሚጣል የለም። ሁሉም ተፈላጊ፤ ሁሉም አስፈላጊ በመሆኑ እንክት ተደርጎ ይበላል። በሬ ሲታረድ ከድምፁ በስተቀር አንዳችም ነገሩ መሬት አይወድቅም» የሚለው አቶ በኃይሉ እርሱም ኦልካ

እያጣጣመ ደንበኞቹንም እያስደመመ ኑሮውን ይገፋል።

አቶ በኃይሉ ኦልካ በማን እና መቼ እንደተጀመረ በትክክል ማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ ይናገራል። በአሁኑ ወቅት እርሱ በሚሠራበት አካባቢ ቄራ በመኖሩ ‹‹ኦልካ›› በዚያው ሰፈር ስለመጀመሩ ግን በወሬ ወሬ ሰምቷል።

የኦልካን ውለታ በሚገባ ጠንቅቀው ከሚመሰክሩት ወጣቶች መካከል የገበያ ሰፈር ነዋሪው ምስጋናው ጳውሎስ አንዱ ነው። ምስጋናው ሰውነቱ በእጅጉ ደንዳና ነው። የእጁ ውፍረት፣ የደረቱ ስፋት እና ሁለመናው የኦልካን ውለታ በቅጡ ካስመሰከሩ ሰዎች አንዱ ይመስላል። ኦልካ የሚበላ ሰው ሰውነቱ ደንዳና፤ ተክለ ቁመናው ማራኪ እንደሆነና ለችግሮች የማይገበር ሰውነት እንዳለው የሚገልፀው ምስጋናው፤ የእርሱ ሰውነት በኦልካ የተገነባ መሆኑን ይናገራል።

ኦልካ አንዴ በልተውት ሙሉ ቀን ሌላ ምግብ የሚያስረሳ፤ የድሆች አለኝታ ነው። አሁን ግዙፍ ሆኖ ለሚታየው ተክለ ሰውነቱ የኦልካ ውለታ የበዛ እንደሆነ አጫውቶኛል። ቢያንስ በሳምንት ሦስት ቀን ኦልካን ይመገባል። አሁንም ከኦልካ ጋር ወደጅነታቸው እንደቀጠለ ነው። ኦልካ ለምስጋናው የምግብ ልክ፤ ምስጋናው ለኦልካ የአስመስጋኝ ልክ ናቸው። እንዲያው በደፈናው ላይለያዩ ተዋደዋል!

ጉዶ ደላላው ሐዋሳ ውስጥ አረብ ሰፈር ነዋሪ ሲሆን፤ ጌታቸው ከሚባል ወዳጁ ጋር ኦልካን ሲያጣጥም ነው ያገኘሁት። ከኦልካ ጋር ነው ያደገው። ‹‹ምግባችን ኦልካ፣ ዘፈናችን ዋካ! ዋካ!›› ነው ይላል። 20 ለሚጠጉ ዓመታት ኦልካን በፍቅር ቅርጥፍ አድርጎ አጣጥሟል። ምንም እንኳን ጉዶ ደላላው የኦልካ አፍቃሪ ቢሆንም ሰውነቱ እንደ ሌሎች ተመጋቢዎች ደንዳና አይደለም። ያም ሆኖ አብሮ አደጉ በመሆኑ ‹‹ኦልካ›› ባለውለታው ነው።

«በሬ ሁሉ ነገሩ ጥቅም ላይ ውሎ እያመለጠ ያለው ድምፁ ብቻ ነው» የሚለው ጉዶ ደላላው፤ ‹‹ኦልካ›› ከበላ በኋላ ቅባቱ ከፍተኛ ስለሆነ በፍጥነት እንዲለቅ እጁን በአጃክስ ሳሙና እጥብ፤ ጉሮሮውን ደግሞ ሻይ ተጎንጭቶ ፅድት ያደርገዋል። በዋጋ ደረጃም ቢሆን፤ ኦልካ ከምግብ ሁሉ ርካሽ ነው። ‹‹ዛሬ ኦልካን ልክክ አድርጎ ያጣጣመ ሰው፤ ከምግብ

ጋር የሚገናኘው በሁለተኛው ቀን ነው፤ እንዲሁም ኦልካን የበላ ሰው አሲድ ቢጠጣም አይጎዳውም›› ሲል ኦልካን ያንቆለጳጵሰዋል።

ጉዶ ደላላው፤ በፆም ወቅት ‹‹ኦልካ›› አቅራቢዎች በእጅጉ ስለሚቀንሱ፤ ወደ ሐዋሳ ፍቅር ኃይቅ ጎራ ብሎ ዓሳ ያጣጥማል። ፆም እስኪፈታ ድረስ ከኦልካ ጋር ይነፋፈቃሉ።

«አፍህ ወተት እንደጠጣ ህፃን፤ እጅህ ደግሞ ሊጥ እንዳቦካች ሴት ነጭ ከሆነ አንተ ኦልካን ስለመመገብህ ማንም ያውቃል» የሚለው ጉዶ ደላላው፤ ኦልካ መብላት ብቻ ሳይሆን ከአሠራሩ እስከ አበላሉ መላ አለው ይላል።

«ኦልካ አጣጥመህ በሰከንዶች ልዩነት እጅህን በሳሙና እና አመድ እሽት አድርገህ ካልታጠብከው ቀኑን ሙሉ የበላኸው ምግብ አጠገብህ ያለውን ሰው አፍንጫ ቢረብሸው፤ ሊያስደንቅ አይገባም። አፍህ ወዝ በወዝ ሆኖ ደጋግመህ ብትጠርገው አንዳችም አያስገርምም» የሚለው ጉዶ ደላላው፤ ከፍተኛ የቅባት መጠን ስላለው፤ ሲበላ ከሆድ እስከ እጅ ልክክ ይላል። የስጋ ተዋፅኦዎችን በ25 ብር መጠቀም ቀርቶ ማሰቡ ነውር በሆነበት ጊዜ፤ ኦልካን በ25 ብር ስለምናጣጥም የስጋ አምሮታቸውን እንደሚቆርጡ ይናገራል።

‹‹ኦልካ›› በሐዋሳ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በርካታ ሰዎች የሕይወት ወዳጅነቷ የጠነከረ በመሆኑ እያመሰገኑ የሚቋደሱት ብዙናቸው። በአንጻሩ ደግሞ ስለምግቡ ስምና አሠራር ሲሰሙ ‹‹ዓጃኢብ›› የሚሉ ከተሜዎች በሐዋሳ ይገኛሉ። ኦልካ ለሰሚው ግራ፤ ለተጠቃሚው ምቾት ነው።

ኦልካ የሚያዘወትር ሰው ከሌላ ምግብ ለመላመድ ብዙ አያስቸግረውም፤ ወዲያውኑ ሊወዳጅ ይችላል። አሁን በሬው ሁሉ ነገሩ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ቆዳው ጫማ፣ ቀንዱ ዋንጫ፣ ስጋው በውድ የሚሸጥ ነው። አንጀቱም ቢሆን ዕድሜ ‹‹ኦልካ››ን ለሚከሽኑ ሁሉም ነገር ሥፍራ ሥፍራውን ይዟል። በሐዋሳ የኦልካ አፍቃሪዎች ‹‹ምግባችን ኦልካ፤ ዘፈናችን ዋካ ዋካ!›› እያሉ በፍቅር ይሰለቅጡታል። ግን የሚያሳስባቸው ነገር ቢኖር የበሬን ድምፅ እንዴት ወደ ጥቅም እንቀይረው? የሚለው ሆኗል!

የከብት አንጀት በሚገባ ይታለባል፤ ከዚያም ይከተፋል። በዚህ ሁሉ ሂደት ግን አንዳችም የውሃ ጠብታ አይነካውም። ‹‹ኦልካ›› በተፈጥሮ ቅባት ስላለው ተጨማሪ ቅባትና ፈሳሽ አያስፍልገውም። ከዚያ በመጥበሻ ላይ በእሳት ብስል ተደርጎ፣ ቀይሽኩርት፣ ነጭ አዝሙድ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ኮረሪማ እና መከለሻ ቅመም በአንድነት ተፈጭቶ በስሱ ብን ይደረግበታል። ሊወጣ ሲልም የስጋ መጥበሻ (ሮዝመሪ) ጣል ይደረግበታል።

‹‹የበሬ አንጀቱ ብቻ ሳይሆን ከንፈሩም ጥቅም

ላይ ይውላል››

ሕይወት ፈርጀ ብዙ ገጽታዎች አሏት። መውጣት እንዳለ ሁሉ መውረድም ይኖራል። ከመውረድ ውስጥም በትጋት መውጣት ይቻላል። አግኝቶ ማጣት እንዳለ ሁሉ አጥቶም ይገኛል።ይህ የህይወት እውነታ ነው። በጥቂቶች የህይወት መውጣትና መውረዶች ውስጥ ብዙዎች ይማራሉ። የህይወትን ፈተናዎችም ያውቃሉ። በከፍታ ውስጥ የሚገኙት ‹‹ እንዲህም ይኖራል እንዴ?›› ብለው ራሳቸውን ይጠይቃሉ። ለተቸገሩት ያዝናሉ። ካላቸው ቀነሰው የሌሎችን ችግር ይካፈላሉ። በተጨማሪም

ችግር ብልሃትን ያስተምራል እንዲሉ ከችግር ጋር ተላምዶ ከመኖር ይልቅ ለመፍትሄ የሚታትሩትንም ያበረታታሉ። በመሆኑም ‹‹እንዲህም ይኖራል›› ብለን በከፈትነው አምዳችን ህይወትን በየፈርጁ ታስተውሉበት፤ ¸አስተውላችሁም ትማሩበት ዘንድ ጋበዝናችሁ። ለአስተያየቶቻችሁ፤ ለመሰል ታሪኮች ጥቆማችሁ እንዲሁም ለድጋፋችሁ የዝግጅት ክፍላችን አድራሻ ትጠቀሙ ዘንድ ጋበዝናችሁ።

ወይዘሮ ብርቱካን የአንድ ከብት አንጀት ከ150 እስከ 200 ብር ከቄራ ተቀብላ፤ የትራንስፖርት፣ ከታፊ እና ሌሎች ሂሳብ አውጥታ አንድ ኦልካ በአንድ ጭልፋ ሙሉ እና ግማሽ በ25 ብር ትሸጣለች።

‹‹አንጀት ዱሮ መሬት ተቆፍሮ የሚቀበር እንጂ ለምግብነት አይውልም ነበር›› የምትለው ወይዘሮ ብርቱካን፤ እንደምግብ የሚጠቀሙት ቢኖሩ እንኳን በገጠሪቱ አካባቢ ያሉ ሰዎች እንጂ ከተሜው አያውቀውም ነበር። አሁን ግን ሐዋሳ ውስጥ ኦልካ፤ አንጀት የሚያረካ፣ ዝናው እየናኘ ያለ ምግብ መሆኑን ትናገራለች።

በእርግጥ ከሩቅ የሚመጡት ብቻ ሳይሆኑ ሐዋሳ ውስጥ ሆነውም ‹‹ኦልካ››ን የማያውቁ አያሌ ሰዎች አሉ። በተለይም በሐዋሳ ውስጥ ፒያሳ፣ አቶቴ፣ ሎጊታ በሚባሉ አካባቢዎች ኦልካ

፲፮

Page 17: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

17የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ነጻ ሃሳብ >>

የሥነ ጽሑፍና የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ ናቸው። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበርን ለዘጠኝ ዓመታት ያህል በፕሬዚዳንትነት መርተዋል። ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዘመንና የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ታትመው በሚሠራጩ የተለያዩ የኅትመት ውጤቶች ላይ (ዳግላስ ጴጥሮስ) በሚል የብዕር ስሙ በርካታ ጽሑፎቹን አስነብበውናል። በግላቸው 12፣ ከሌሎች ጸሐፍት ጋር በርካታ መጻሕፍትን ለአንባብያን አቅርበዋል።

ጌታቸው በለጠ

ጌታቸው በለጠ - (ዳግላስ ጴጥሮስ)

ታሪክ ታሪክን ይድገም ወይንም ታሪክ የራሱን አምሳያ ይፍጠር በእውነቱ እርግጠኛ አይደለሁም። የሆነው ሆኖ ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬንም ከነገ ጋር የሚያጣቅሱ ክስተቶች ደጋግመው የመከሰታቸው ነገር ግን እርግጥ ነው። ወደ ሀገራችን ቀደምት ታሪክ መለስ ብዬ ከዛሬ እውነታ ጋር የመንትያ ያህል ባይሆንም ተቀራራቢና መመሳሰሎች የተስተዋሉባቸውን አንዳንድ አጋጣሚዎች በማስታወስ ከዛሬ እውነታችን ጋር እያነጻጸርን ለመመልከት እንሞክራለን።

የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊት ከሀገራችን ተሸንፎ ጦርነቱ በድል ከተጠናቀቀ በኋላ ሀገርን ሀገር የሚያሰኙ መሠረታዊ መዋቅሮች በሙሉ ፈራርሰው ነበር ማለት ይቻላል። ሀገሪቱ ከደቀቀችበት ፍርስራሽ አገግማ በሁለት እግሯ ለመቆም በምትውተረተርበት ፈታኝ ወቅት አንድ ያልተጠበቀ አደጋ አጋጥሞ ነበር። በርካታ ዜጎች በቡድን እየተደራጁ ችኮላና ግልፍተኝነት እንደተጠናወታቸው «የፋሽስት ወራሪ ሠራዊት ተዋርዶ እንዲሸነፍና የሉዓላዊነታችን ክብር ተመልሶ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን በድል አንዲውለበለብ በማድረጉ ፍልሚያ ውስጥ ተቀዳሚው ባለውለታ ማነው? ሀገርን ማን ታደጋት ማንስ በደላት? ዋነኛ ተዋናዩስ ከእኛ በስተቀር ማን ሊሆን ይችላል?» በማለት በየአደባባይ ዲስኩር እያሰሙ «ዘራፍ!» ማለት በመጀመራቸው ጉዳዩ ያልተጠበቀ ሀገራዊ ተግዳሮት ሆኖ ገዝፎ ወጣ። ንትርኩም ከዳር ዳር ተቀጣጠለ።

መንግሥት ገና ሳይጠናከር የተነሳው ይህ ጠንካራ ወጀብ በነፃነት ማግሥት በቀዳሚ ፈተናነት የተመዘገበ ተግዳሮት ብቻ ሳይሆን ሰይፍ አማዞ የሚያጨራርስ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። በቀላል አገላለጽ በፋሽስት ወራሪዎች ላይ ያረፈው ሰይፍ ወደ እርስ በእርስ ደረጃ ሊመዘዝ ተቃርቦ ነበር ማለቱ ይቀላል።

ንጉሠ ነገሥቱ ጥያቄውን ችላ ብለው ወደ ጎን አልገፉትም። የሚያስከትለውን አደጋ ጠርጥረው በነፃነት ትግሉ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማድረግ ለድሉ መገኘት እውቅና ይገባቸዋል ያሏቸውን ሦስት ቡድኖች በኮሚቴ አስጠንተው በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ለሜዳይና ለሽልማት ዕጩ አድርገው ይፋ አደረጉ።

በድልድሉ መሠረትም በተቀዳሚነት የታጨው የድሉ ባለቤት «ስደተኛ አርበኛ» የሚባለውና ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ከሀገር ተሰዶ የወጣው ቡድን ሲሆን፤ በሁለተኛ ደረጃነት የተቀመጠው ደግሞ በዱር በገደሉ እየተንከራተተ “እምቢኝ ለነፃነቴ!” ብሎ አምርሮ በመፋለም ሲጥልና ሲወድቅ የነበረው “ዱር ቤቴ” ባዩ ጀግናው አርበኛ ነበር። በሦስተኛነት ለእውቅናና ለሽልማት የታጨው ደግሞ ከጠላት ጋር እየበላና እየጠጣ በስውር ሀገራዊ ግዳጁን ይወጣ የነበረው “የውስጥ አርበኛ” ነበር።

ንጉሠ ይህንን የዕውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ይፋ አድርገው የተግባር እንቅስቃሴ ከመጀመሩ አስቀድሞ ያልተገመተ የአመፅና የእምቢተኝነት እንቅስቃሴ በተፋላሚ አርበኞች አማካይነት ውስጥ ለውስጥ መቀጣጠል ጀመረ።

የአመፅ እንቅስቃሴው መንስዔ የቅደም ተከተሉ ጉዳይ ነበር። “አጥንታቸውንና ደማቸውን በጦርነቱ ዐውደ ግንባር የገበሩ አርበኞች ቀዳሚ መሆን ሲገባቸው እንደምን ከሀገር ሸሽቶ የወጣው ከሀዲና ፈርጣጭ ስደተኛ ንጉሡን አስቀድሞ በተቀዳሚ ረድፍ ላይ ለሽልማትና ለዕውቅና ይታጫል” የሚል። በቤንዚን ላይ እሳት ለማቀጣጠል ጊዜ ይጠብቁ የነበሩ እንግሊዞችም ውስጥ ውስጡን “እንኳንስ ተቀዳሚ የሜዳይ ተሸላሚነት ቀርቶ ሀገሪቱን መምራት ያለባችሁ እናንተ አርበኞች ናችሁ” በማለት መርዛማ ምክራቸውን መርጨታቸውን ተያያዙት።

ብልሁ ንጉሥ እልህ ከመጋባት ይልቅ ተፋላሚ አርበኞች ያነሱትን ጥያቄ በመቀበል ቅደም ተከተሉን አስተካክለው የአንደኛ ደረጃ ሽልማትና ኒሻን በተጋድሎው ግንባር ላይ የነበሩ አርበኞች፤ በሁለተኛ ደረጃ ራሳቸው የተካተቱበት ስደተኛ አርበኞች፤ በሦስተኛ ደረጃ የውስጥ አርበኞች እንዲሸለሙ የምደባው ቅደም ተከተል ተስተካክሎ አመጹ ተገታ።

ተንጓለው የቀሩትና በሕዝቡ ዘንድ ጥርስ የተነከሰባቸው ሀገር ከዳተኛ ባንዶች ውሳኔውን እንደሰሙ የአርበኞችን መከፋፈልና ኩርፊያ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለንጉሠ ነገሥቱ ወሬ በማወሻከት፣ አርበኞችን ከስደተኞች፣ የውስጥ አርበኞችን ከጀግኖቹ ጋር በማናከስ ከፍ ያለ ውስብስብ ችግር ፈጠሩ። አልፎም ተርፎ “በጀግና ወግ” በሽለላና በፉከራ እያቅራሩ ዋነኞቹ የሜዳልያና የኒሻን ተሸላሚ ለመሆን አንገታቸውንና ደረታቸውን ሲያቀብሉ ያስተዋለ አንድ የሀገራችን ጎምቱ የጥበብ ሰው እንዲህ ሲል ተቀኘ፤

«ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፣የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።አንበሳና ዝሆን እንዴት ባንድ ዋሉ፣ወራቱ ነው እንጂ ጓድም አልነበሩ።»በዘመነ ደርግም ቢሆን መሰል ታሪክ መደገሙን አንዘነጋም።

በ1966 ዓ.ም ለዘመናት የተዳፈነው የለውጥ ረመጥ ፈንድቶ ንጉሡን ከዙፋናቸው ባስወገደ ማግሥት ውስጥ ለውስጥም ሆነ በይፋ በርካታ ቡድኖች “የለውጡ ዋነኛ ተዋናይ ማን ነው?” የሚል ጥያቄ በማንሳት ከአተካሮም አልፎ ደም እስከማቃባት ደርሶ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

የለውጡ ተቀዳሚ አቀጣጣይ እኔ ነኝ ብሎ ተሜ እጁን ከፍ አድርጎ ቢጠይቅ የሰማው አልነበረም። መምህሩ፣ ወዛደሩ፣ የታክሲና የአውቶቡስ ሾፌሮችም የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የተንበረከከው በእኛ ወሳኝ አድማና የሥራ ማቆም ጥሪና ሰበብ ነው ቢሉም ጆሮ የሰጣቸው አልነበረም። የቡድኖቹን ዝርዝር እዚህ ላይ እንግታና በዚህን መሰሉ ግርግር መካከል ጠብመንጃ ያነገተው ወቴ “እኔን ማን ሊቀድመኝ” በማለት አፈሙዙን ወድሮ የተቀናቃኞቹን አፍ በሙሉ በማዘጋቱ በአስራ ሰባት ዓመታት ውስጥ የደረሰው ሀገራዊ መከራ፣ የትውልድ ዕልቂትና ግፍ የሚዘነጋ አይደለም።

ዛሬስ? በሀገሪቱ ብልጭ ላለው ተስፋማ የለውጥ ብርሃን የቀዳሚ ባለድርሻ ባለቤትነትን ቀድሞ ለመውሰድ ድምፁን ከፍ አድርጎ “እንዲያው ዘራፌዋን የማያንጎራጉር ማን አለ?” ራሱን በራሱ የጎበዝ እልቅና ሾሞ ደሜን ለገበርኩለት ለውጥ፤ “ነጭ ከሰል፣ ጥቁር ወተት አቅርቡልኝ” እያለ የስልጣን ዛር የሚያስገዝፋቸው ቡድኖች ቁጥራቸው ቀላል ነው?

በኦሮሞ ቄሮ፣ በአማራ ፋኖ፣ በጉራጌ ዘርማ፣ ነብሮ፣ በሲዳማ ኤጄቶ፣ በጋምቤላ ዳልዲም፣ በሱማሌ ባርባራታ፣ በአፋር ዱኮሂና፣ በራያ ጉማ ወዘተ በሚሉ ስያሜዎች የሚጠሩት ወጣቶቻችን

በቀዳሚነት የለውጡን ክብሪት የለኮስነው እኛ ነን፤ ሕይወትና ደማችንንም ገብረናልና የተቀዳሚነቱ ክብርና ጥቅም የእኛ ነው በማለት በአደባባይ ሲናገሩ ይደመጣሉ። እርግጥ ነው የእነዚህ ወጣቶቻችን የትግል አስተዋፅዎና መስዋዕትነት በቀላሉ የሚገመት ያለመሆኑ ይገባኛል። ተገቢውን እውቅና ቢያገኙም ችግር የለበትም።

ስደተኛ ፖለቲከኞች፣ ባህር ማዶ ተጠልለው የኖሩ አክቲቪስቶች፣ የማኅበራዊና የአንዳንድ መደበኛ የሚዲያ አካላትም አንዲሁ ፊት ለፊት ለመቆም ሲጋፉ እየታዘብን ነው። አንዳንድ ቡድኖችም ሀገሪቱ የጀመረችው የለውጥ ነፋስ አንዲነፍስ ከቂሊንጦ እስከ ዲሲ፣ ከኤርትራ በረሃ እስከ ፍራንክፈርትና ሚኒያፖሊስ እየተንከራተትን ቀዳሚ ተዋንያን በመሆን ለነፃነት ቀድመን የጮኽነው ቀዳሚዎቹ እኛ ነን እያሉ ነው።

“የፈርዖን የልጅ ልጅ መባልን እንደ ጉድፍ የተጠየፉ” የገዥው የፖለቲካ ቡድን አንቀባሮ ያሳደጋቸው “የቤት ልጆች” ሙሴዎችም “ቲም

እከሌ” በሚለው ቡድናቸው አማካይነት እንደምን በነፍሳቸው እየተወራረዱ እንደታገሉ በግላጭ ነግረውናል። ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥም በሕዝባቸው ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ዘንድ ሳይቀር እየተወደሱና ላስመዘገቡት ውጤት እየተመረቁና እየተጨበጨበላቸው ይገኛል።

ከሁሉ የሚገርመውና “አበስኩ ገበርኩ” አሰኝቶ እንድናማትብ የሚያስገድደን፣ እንድንቆጣም የሚገፋፋን ሌላው ጉዳይ እዚያ ማዶ ድብብቆሽ እየተጫወቱ ያሉ ቀደምት ጡንቸኞችም ሳይቀሩ ደረታቸውን ነፍተው፣ ለዛሬው የለውጥ ብርሃን ችቦው እንዲቀጣጠል ፍኖተ ካርታውን የነደፍነው እኛ ነበርን ማለታቸውን ከአንደበታቸው አድምጠናል። ለጊዜው ዝርዝሩን እዚህ ላይ ልግታ።

ታሪክ እንኳ ጥርስ ቢታደል ተንከትክቶ ለመሳቅ የማያንገራግርበትን አንዳንዱን ጉዳይ ጫን ብለን አንመልከተው። አንዳንድ በረሃ ሰንባች ቡድኖች፣ ሰሞንኛ ሀገር ገቦችና ሩቅ ነዋሪ “ባለ ሁለትና ሦስት ፓስፓርት ባለቤት” መጻተኞች የለውጡ “ተቀዳሚ ፋና ወጊዎች እኛ ነን። የእኛን ቀዳሚነት የሚጋፋ ካለ ጡንቻችን ያርፍበታል” እያሉ ያስፈራሩናል። “ተቀዳሚነታቸውን” እንድናምንላቸውም የሚጎተጉቱን በረሃ ውስጥ በነበሩበት የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ ጠብመንጃቸውን ታቅፈው ያንጎራጉሩ የነበረውን “እንዲያው ዘራፌዋን” በአዝማችነት እያቀነቀኑ፤ “ገዳይ እወዳለሁ፤ ተኳሽም አልጠላም” የሚለውን ስንኝ በተግባርና በቀረርቶ ጭምር በማጀብ ነው።

ለውጥ በሀገራችን መጥቷል? ምን ያጠራጥራል። የለውጥና የነውጥ አየሩ ተቀላቅሎ ምድሪቱን እየሰነፈጣት መሆኑ ምስክር መች ያሻዋል? ጎን ለጎንም ከለውጡ ጋር በመንትያነት የተዳበለ“የጎበዝ አለቆች” ነውጥም ሀገሬን እያመሳት፣ ሰላማዊውን ሕዝብ እያፈናቀለና የሕይወት፣ የአካልና የኢኮኖሚ ዋጋ ከማስከፈል አልፎም ምድሪቱን ለመከራ መዳረጉንም ነጋ ጠባ እያስተዋልንም እየሰማንም ነው። እናስ ለለውጡ መቀጣጠል ተቀዳሚ ባለድርሻ አካላት እነማን ናቸው?

በእኔ ትሁት አስተያየት ጣቴን ወደ አንድ ቡድን ወይንም አካል ለመቀሰር እቸገራለሁ። ምክንያቴም ግልፅ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ ይነስም ይብዛ ሁሉም ዜጋ፣ በተለያየ አደረጃጀት የተሰባሰበ የፖለቲካ ቡድንም ሆነ ማንኛውም አካል ደረጃው ይለያይ እንጂ የጠጠር ያህል ቢሆንም ድርሻ ይኖረዋል የሚል እምነት አለኝ።

ቄሮ በነፍሱ ተወራርዶ አደባባይ ወጥቶ ሥርዓቱን ሲሞግት፣ ፋኖ ዘራፍ እያለ ደረቱን ለጥይት ሲሰጥ፣ ዘርማ እምቢኝ በማለት ተቃውሞውን ሲያፋፍም ብቻውን አልነበረም። አይደለምም። “እኔ ብቻ!” ብሎ የሚኩራራም ከሆነ ስህተት ነው። ከሕዝብም መቀያየም ይመስለኛል። ምክንያቱም የትኛውም ቡድን እምቢተኛነቱን ለመግለጽ አደባባይ ሲወጣ ዘርና ሃይማኖት፣ ዕድሜና ፆታ ግድ

ያላለው ዥንጉርጉር የሕዝብ ሠራዊት በነቂስ ወጥቶ አደባባዩን በመሙላት ብሶቱንና ቁጣውን አብሮ ገልጧል። ይህ መሠረታዊ እውነታ እየተዘነጋ ራስን ብቻ ከፍ አድርጎ የለውጥ ሞተሩ የተገጠመው እኔ ጭንቅላት ላይ ነው ብሎ ማለት ጥፋት ብቻ ሳይሆን ኃጢአትም ነው። አረጋዊያን፣ ጎልማሶች፣ ወጣቶችና ነፍስ ያላወቁ ሕፃናት ሳይቀሩ ለውጡ እንዲመጣ አብረው ተደብድበዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ ታስረዋል፣ በግፍ ውሳኔም ተገድለዋል።

የትኛውም የወጣት ቡድን ለውጡ የእኔ መስዋዕትነት ፍሬ ብቻ ነው ብሎ ቢሟገት ያስገምታል እንጂ አያስመሰግንም። ፖለቲከኛውም እኔ ብቻ ብሎ ደረት ቢነፋ አይሆንም። አክቲቪስቶችም ሥርዓቱን እንደ ኢያሪኮ ግንብ የናደው የእኛ የጩኸት ብርታት ነው ብለው ኡኡታ ቢያሰሙ፣ ሚዲያውም የሞገድ ድሉን ቢተርክ፣ ምሁሩም የእኔ የትርክት ተፅእኖ ላቅ ያለ ነው ብሎ ቢያውጅና ቢናገር አግባብ አይደለም። ለምን ቢሉ ሁሉም ቡድን የራሱን የለውጥ ጠጠር ወረወረ አንጂ ከጀርባውና ከጎኑ የሕዝብ ደጀን፣ የሕዝብ ኃያል ድምፅ እንደነበረ ሊዘነጋው አይገባም።

የዛሬው የለውጥ ብርሃን እንዲፈነጥቅ የፀረ ዴሞክራሲና ኢሰብዓዊ ድርጊት ፈጻሚ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ግፍና መከራ ተቋቁመው የሕይወትና የአካል፣ የንብረትና የሥነ ልቦና ቀውስ የደረሰባቸው በርካታ ዜጎቻችንም የዚህ ለውጥ ዋና ሰበብ እንደሆኑ እውቅና ሊሰጥ ይገባል። በማይተካው አንድ ሕይወታቸው ተወራርደው፣ በማይድን የኅሊና ጠባሳና አካላዊ ጉዳት ተሰብረው የተያያዝነው የለውጥ ብርሃን እንዲፈካ ማሾውን ከፍ አድርገው በመያዝ ታሪክ የሰሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጀግኖች ዜጎቻችን ከተዘነጉማ ሀሰት ብቻ ብለን የምናልፈው ሳይሆን የታሪክ ወቀሳና ፍርድም ያስከትላል።

ለውጥን ከነውጥ ለይቶ ማየት እንደማይቻል ቢገባኝም፤ ለውጡ መስመሩን እንዳይለቅ፣ ነውጡም በለውጡ ላይ እንዳይሰለጥን ተቀዳሚው ተመስጋኝና ለሽልማት ሊታጭ የሚገባው ትልቁ ባለድርሻ ፊት አውራሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆን ይኖርበታል።

«የለውጡን ክብሪት ለኩሼ ያቀጣጠልኩትና ያጋጋምኩት ተቀዳሚው ባለውለታ እኔ ነኝ። የአንደኛ ደረጃ ሽልማትና ኒሻን አንገቴ ላይ ሊንጠለጠል የሚገባውም ለእኔ ብቻ ነው» ባይ ቡድንም ሆነ ግለሰብ ካለ መልሱ “ሕዝብ ይቅደም፤ ሕዝብ ይወስን” መባል አለበት።

በለውጥ አዋላጅ ቀዳሚነት ጉዳይ ላይ ከመሻኮትና “ከእንዲያው ዘራፌዋ” ቀረርቶ ይልቅ በጋራ የሚያቀራርበንን የራሮት እንጉርጉሮ ብናዜም ሺህ ጊዜ የሚሻል ይመስለኛል። በዘመናት መካከል መልዕክቱ የማይደበዝዝ አንድ ሕዝባዊ ግጥም ላስታውስ፤

«አባት የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል፣እናት የሞተች ዕለት በሀገር ይለቀሳል፣ወንድም እህት ቢሞት በሀገር ይለቀሳል፣ሀገር የሞተ እንደሁ ወዴት ይደረሳል።» የትግሉን ፍሬ ቀድሜ ልግመጥ ብሎ ከመጋፋት በፊት ለውጡ

እየተወሳሰበና እየተጋመደ አቅጣጫ ወደ መሳት ደረጃ እንዳይሸጋገር ልንከባከበው ይገባል። በሀገር ህልውና ጉዳይ “ያበጠው ይፈንዳ!” ፉከራ አዋጭም፤ አትራፊም አይሆንም።

በተለይም ለሥልጣን የሚራኮቱ የፖለቲካ ልሂቃን በአደባባይ የሚፎክሩባቸውን የቀረርቶ ይዘቶች አጥብቀው ቢመረምሩ መልካም ይመስለኛል።

“ገዳይ እወዳለሁ፤ ተኳሽም አልጠላ፣ሲደክመኝ አርፋለሁ በእነ እነቶኔ ጥላ።”እያሉ በማንጎራጎር በሀገር ህልውና ላይ እሣት አቀጣጥለው

በወገን ደም ከጨቀዩ በኋላ እንደ ቀድሞ በባሌም ይሁን በቦሌ በኩል ሾልኬ መውጣት አያቅተኝም ብሎ መፎከር ፋሽኑ አርጅቶ በእነ ዘመነ ቼ ጉቬራ ማብቃቱን ሊገነዘቡ ይገባል። የአሸናፊነት ክብር የሚሰጠው ጠብመንጃ አንግቶ ላቅራራ ሳይሆን በሃሳብ ልዕልና ደምቆ ለወጣ ጀግና ብቻ ነው። ሰላም ይሁን!

ሞንኛው «እንዲያው ዘራፌዋ!»

ቄሮ በነፍሱ ተወራርዶ አደባባይ ወጥቶ ሥርዓቱን ሲሞግት፣ ፋኖ ዘራፍ እያለ ደረቱን ለጥይት ሲሰጥ፣ ዘርማ እምቢኝ በማለት

ተቃውሞውን ሲያፋፍም ብቻውን አልነበረም። አይደለምም። “እኔ ብቻ!” ብሎ የሚኩራራም ከሆነ ስህተት ነው። ከሕዝብም መቀያየም ይመስለኛል።

፲፯

Page 18: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

18 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ ነጻ ሃሳብ >>

በሕትመት ጋዜጠኝነት ከ18 ዓመት በላይ ልምድ ያለው ጋዜጠኛ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከመደበኛ ሙያው በተጨማሪ ለተለያዩ ድርጅቶች በሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ በአማካሪነት በመሥራት ይታወቃል። ከጵሑፉ ጋር በተያያዘ ጸሐፊውን ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን አድራሻ ይጠቀሙ።

[email protected]

ፍሬው አበበ

(ፍሬው አበበ)

እነሆ የፊንፊኔ/አዲስአበባ አጀንዳ ወደ ጠረጴዛው ተመልሷል። ኦሮሚያ በአዲስአበባ ላይ ያላት ልዩ ጥቅም መከበርን አስመልክቶ ከ23 ዓመታት በፊት በሕገመንግሥቱ ምላሽ ያገኘ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌውን መተግበር ባለመቻሉ ዛሬም ወደግጭት ለሚያንደረድሩ ውዝግቦች መነሻ ምክንያት ሆኗል።

እርግጥ ነው፤ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ አጽድቆ ወደሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት መርቷል። ግን አዋጁ ከአንድ ዓመት በላይ በምክር ቤቱ መጽደቅ አልቻለም። ለምን?

ፓርላማው ረቂቅ አዋጁን ተቀብሎ ምን አደረገ

ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር ዕይታ የተመራላቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የቤቶች ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ላይ የሕዝብ አስተያየት ማሰባሰቢያ መድረክ ታህሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም በጋራ አዘጋጁ። ልብ በሉ!... ይህ የሆነው የኢህአዴግ አዲስ አመራር ወደፊት ከመምጣቱ ከወራት በፊት ነው። የዚህ አጀንዳ መቅረብ የመገናኛ ብዙሃንን ብቻ ሳይሆን የኦህዴድ/ኦዴፓ አባላትንም ትኩረት ሳበ። መድረኩ የህዝብ አስተያየት ማሰባሰቢያ ቢሆንም ቅሉ እሳት ጎርሰው የተገኙት አብዛኛዎቹ የኦዴፓ የምክርቤት አባላት ነበሩ። በተጨማሪም እንደማንኛውም ሰው አስተያየታቸውን ለመስጠት የታደሙ የኦዴፓ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ያልሆኑ አመራሮችም በአዳራሹ ውስጥ ነበሩ።

ስብሰባው እንደተጀመረ የአካሄድ ጥያቄ ተነሳ። በዋነኛነት ከኦዴፓ ሰዎች የተነሳው ጥያቄ በአጭሩ «ከ600 ሺህ በላይ ሕዝባችን በኦሮሚያና ሶማሌ ድንበር በተፈናቀለበት በዚህ ወቅት፣ ሕዝቡም በየደረጃው ባልተወያየበት ሁኔታ ረቂቅ አዋጁ በፓርላማው ለውይይት መቅረቡን አንደግፍም» የሚል ይዘት ያለው ነበር። አብዛኛዎቹ (አብዛኛዎቹ በዕለቱ ስብሰባ የተገኙ የኦዴፓ የምክርቤቱ አባላት ናቸው) የምክርቤት አባላት ይህን አቋም ደግፈው ቆሙ። ከሌላ ስብሰባ ተጠርተው የመጡት የወቅቱ የምክርቤቱ አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የምክርቤት አባላቱን ተቃውሞ ከተረዱ በኋላ በሻይ እረፍት ጭምር ስብሰባው እንዲካሄድ ቢማጸኑም ሰሚ አላገኙም። እናም በአዋጁ ላይ ተይዞ የነበረው የሕዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መድረክ ለሌላ ጊዜ በይደር ሊተላለፍ ግድ ሆነ። እነሆ ከዚያ ወዲህ ረቂቅ አዋጁ በፓርላማው ሼልፍ ላይ ተሰቅሎ አሁንም የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግን ይሁንታ እየተጠባበቀ ነው።

ይህም ሆኖ ግን አጀንዳው ሞቅ በረድ እያለም ቢሆን የተለያዩ ወገኖችን እንካሰላንቲያ መወራወሪያ አጀንዳ የመሆኑ ጉዳይ ዛሬም አልተገታም። የአጀንዳው መዘግየት በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው የለየለት የዘረኝነት መርዝ ለሚረጩ ግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር በምቹ ጫካነት ማገልገሉን ቀጥሏል።

ስለኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ሕገ-መንግሥቱ ምን ይላል?

አቶ ተስፋዬ ነዋይ የተባሉ የሕግ ምሁር አቢሲኒያ ሎው በተሰኘ ድረገጽ ላይ ስለጉዳዩ ካሰፈሩት ሰፊ ሐተታ ውስጥ የሚከተለው ይጠቀሳል። «በሕገ-መንግሥቱ ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከአዲስ አበባ ከተማ ላይ ሊኖረው የሚገባው ልዩ ጥቅም በምን ጉዳዮች ላይ እንደሆነ ደንግጓል። በዚሁ መሠረት የአገልግሎት አቅርቦት፤ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፤ አስተዳደራዊ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም መጠበቁ ግድ ይሆናል»

የአገልግሎት አቅርቦት ጉዳዮችበሕገ-መንግሥቱ ላይ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም አንዱ

ከአገልግሎት አቅርቦት (የእንግሊዘኛው ቅጂ social services በማለት አጥብቦ ይተረጉመዋል) ጋር በተያያዘ ያለው ሲሆን በዚሁ መሰረት ይህ የአገልግሎት አቅርቦት አዲስ አበባ ከተማ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሊሰጣቸው የሚችሉ አገልግሎቶችን የሚያቅፍ ነው። እነዚህም አገልግሎቶች በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች የሚያገኙዋቸው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት በአዲስ አበባ አስተዳደር የሚደጎሙ የትራንስፖርት፤ የመሰረተ ልማት እና ሌሎች አቅርቦቶች ናቸው።

የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምየኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአዲስ አበባ ላይ ያለው

ሌላው ጥቅም ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ያለው መብት ነው። የፌደራል መንግሥቱ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ የማውጣት ስልጣን የተሰጠው ሲሆን የክልል መንግሥታት የፌደራል መንግሥቱ የሚያወጣው ሕግ ላይ በመመርኮዝ የተፈጥሮ ሀብት የማስተዳደር ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። የ ፌ ደ ራ ል መንግሥቱ የሚያወጣውን የተፈጥሮ ሀብት ሕግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ ላይ በሚያውልበት ወቅት ይህ ሕግ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ልዩ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ይሆናል። በዚሁ መሰረት አዲስ አበባ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ከራሷ በማውጣት ስራ ላይ ማዋል ስትፈልግ ይህ በኦሮሚያ ላይ ሊያደርስ የሚችለው አሉታዊ ውጤት ምንድን ነው ብሎ መመልከት አለበት ማለት ነው።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ላይ ሊኖረው የሚችለው ልዩ ጥቅም ሁለት ዓይነት ይዘት ሊኖረው ይችላል። የመጀመሪያው በአዲስ አበባ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች አዲስ አበባ ከተማ ሲጠቀም አጠቃቀሙ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ የጤና፤ የደህንነት ጉዳት የማያደርስ እንደሆነ ማድረግ ሲሆን ይህም ጉዳት ባለማድረስ የክልሉን መንግሥት ልዩ ጥቅም መጠበቅ በሚል ሊታይ የሚችል ነው።

ሁለተኛው አዲስ አበባ ከተማ የሚያስፈልጋት የተፈጥሮ ሀብት በአብዛኛው የሚገኘው ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ነው። ለመኖሪያ ቤት የሚያገለግሉ የተፈጥሮ ሀብቶች፤ ለኢንዱስትሪ እና ለፋብሪካ የሚያስፈልጉ የተፈጥሮ ሀብቶችን አዲስ አበባ በቅርበት የምታገኘው ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ነው።

አስተዳደራዊ ጉዳዮችሕገ-መንግሥቱ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ሊከበር ይገባል በሚል

ካስቀመጣቸው ጉዳዮች አንዱ አዲስ አበባ በክልሉ መሀል የምትገኝ በመሆኑ ሁለቱን የሚመለከቱ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖራት ይገባል የሚል ነው። በሕገ-መንግሥቱ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጉዳይ በተመለከተ ከተማው ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እና ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥቱ እንደሆነ ተደንግጓዋል። ስለሆነም አዲስ አበባን ማስተዳደር self rule በተመለከተ ስልጣኑ ሙሉ በሙሉ የተሰጠው ለአዲስ አበባ እና ለፌዴራል መንግሥቱ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በሌላ መልኩ አዲስ አበባ በክልሉ መሀል ላይ ያለች በመሆኑ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ የክልሉ መንግሥት ልዩ ጥቅም

ያለው ሲሆን ይህም ሁለቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ክልሉ በጋራ የማስተዳደር ልዩ ጥቅም shared rule ይኖረዋል ማለት ነው።

ስለሆነም አዲስ አበባ ከተማ ከማስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚወጡ ህጎች የአዲስ አበባን ራስን በራስ የማስተዳደር እና የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም የሚመለከት የማስተዳደር ስልጣን ያቀፈ ወይም የሚያመለክት መሆን ይኖርበታል።

ረቂቅ አዋጁ ምን ልዩ ጥቅሞችን አካቷል?

ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት በሚኒስትሮች ምክርቤት ጸድቆ ፓርላማ የደረሰው ረቂቅ

አዋጅ ምን ልዩ ጥቅሞችን ይዟል? ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ያስቀመጣቸው ማለትም ከአገልግሎት አቅርቦት ልዩ ጥቅም አኳያ፣ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ልዩ ጥቅሞች አኳያ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የምትገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ማዕከል በማድረግ የኦሮሚያ ክልል ያለው ልዩ ጥቅምን ማስጠበቅ ሲሆን፣ በረቂቅ አዋጁ ይህን ለማሳካት የሚያስችሉ አንቀጾች እንዲቀረፁና እንዲካተቱ ተደርጓል።

በረቂቅ አዋጁ ከተካተቱት መካከል ከትምህርት አኳያ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የአርሶ አደሩ ልጆችን እንዲሁም አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ ምክንያት ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር ለሚፈልጉ ዜጎች የከተማ አስተዳደሩ በአፋን ኦሮሞ፣ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ማደራጀት ይገኝበታል።

በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያለው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ በተለይም የሆስፒታል አገልግሎቶችን ከከተማዋ የማያገኝ በመሆኑ፣ አዲስ አበባ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት በዕቅዷ ውስጥ ማካተት እንደሚኖርባትም ይገልጻል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን እንዲሆን መደረጉንም አስታውሷል።

በዚህ አዋጅ መሠረት የአገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በቋንቋቸው አገልግሎቱ እንዲቀርብ ከአማርኛ በተጓዳኝ አፋን ኦሮሞ በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ቋንቋ ሆኖ እንዲያገለግልም ደንግጓል። በአዲስአበባ ከተማና ዙሪያዋ የሚገኙ ኦሮሞ ወጣቶች በአዲስአበባ ከተማ ውስጥ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደነግጋል።

ከተማዋ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ፣ እንዲሁም አገራዊና የከተማ ነዋሪዎችን ለማገልገል ከምታደርገው ጥረት ባሻገር የኦሮሞ ሕዝብ ማንነት የሚያንፀባርቁ አሻራዎች በከተማዋ ውስጥ በቋሚነት እንዲኖር ከክልሉ ሕዝብ ጋር በተያያዙ ታሪካዊ ክስተቶች ስም መታሰቢያዎች እንዲኖሩ አመቺ የሆኑ እንደ አደባባዮች፣ ጎዳናዎች፣ ሠፈሮችና የመሳሰሉት ቦታዎች እንዳስፈላጊነቱ በቀድሞ የኦሮሞ ስማቸው እንዲጠሩ እንደሚደረግም ተገልጿል። በተጨማሪም የከተማዋ አስተዳደር የኦሮሞ ሕዝብ ባህልና ታሪክ የሚያንፀባርቁ የባህልና ታሪክ ማዕከላት፣ የቴአትር፣ የኪነ ጥበባትና የመዝናኛ ማዕከላት የሚገነቡበትንና የሚተዋወቁበትን ሁኔታዎች እንደሚመቻችም ተመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋ መጠሪያዎች ‹‹ፊንፊኔ›› እና ‹‹አዲስ አበባ›› በሕግ ፊት እኩል ዕውቅና እንደሚኖራቸውም ተገልጿል። መሠረታዊ ነገሩን የሚቀይር ባይሆንም የስሞቹን አጠቃቀም ዝርዝር በደንብ እንደሚወሰንም አስቀምጧል።

አርሶ አደሩ ለልማት ተነሺ ሲሆን፣ በቂ ካሳ የማግኘትና በዘላቂነት የማቋቋም አገልግሎቶችን እንዲያገኝ እንደሚደረግም አመልክቷል። አርሶ አደሩ በልማቱ ማስፋፋት ምክንያት ተጎጂ ሊሆን በጭራሽ ስለማይገባ ለወደፊቱ በቂ ካሳና በዘላቂነት የሚቋቋምበት ሁኔታ እንዲመቻችለት፣ ከዚህ በፊት የተሠራውም ሥራ ተፈትሾ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ፣ እነዚህን ሥራዎች የሚያስተባብር የሚመራና የሚያስፈጽም ጽሕፈት ቤት እንዲደራጅ በአዋጁ እንዲካተት መደረጉን

አመልክቷል። ነገር ግን መግለጫው በአዲስ አበባ ነዋሪ ዜጎች ላይ በብሔር ልዩነት ምክንያት የተለየ ጥቅም እንደማይቀርብ ግንዛቤ ሊያዝበት እንደሚገባ ያሰምርበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃ የሚያገኘው በአብዛኛው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር መገኛዎች በመሆኑ፣ ከዚህ አኳያ ጉድጓዱ የሚቆፈርበት፣ ግድብ የሚለማበት ወይም የውኃ መስመሩ አቋርጠው የሚያልፍባቸው የክልሉ ከተሞችና ቀበሌዎች በአስተዳደሩ ወጪ የመጠጥ ውኃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚደረግም ተቀምጧል።

የከተማ አስተዳደሩ ከባንኮች ጋር በመተባበር የማኅበራዊ ቤቶች የሆኑትን የኮንደሚኒየም ቤቶች አስገንብቶ ከእነዚህ ውስጥ በከተማው ላሉ የመንግሥት ሠራተኞችና ሴቶች በኮታ በዕጣ ውስጥ ገብተው እንዲወዳደሩ እንደሚደረግ፣ በተመሳሳይ ለኦሮሚያ ክልል መንግሥት ሠራተኛ ሆነው በከተማው ውስጥ ለሚኖሩትም ተመሳሳይ ዕድል እንዲሰጥ በአዋጁ ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል።

ከከተማው መሠረተ ልማት አቅርቦት፣ ከመጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ ከደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር የተያያዘ በተፈጥሮ ሀብት ላይና በአየርና ውኃ ላይ የሚደርስ ብክለት እንዳይኖር የሚያደርግና ይህንን መብት የማስጠበቅ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠውም ተገልጿል::

የአንዳንድ ወገኖች ተቃውሞ እና ድጋፍአቶ ተስፋዬ እንደሚሉት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 49

(5) የተቀመጠውን ልዩ ጥቅም የተመለከተው ድንጋጌ፤ አንዳንድ ሰዎች በሀገሪቷ ውስጥ ያሉትን ሰላማዊ የሆኑ ህዝቦች አብረው ሲኖሩ የነበሩትን ግንኙነት ለማበላሸት እና ልዩነትን ለማጉላት በሚል የተቀመጠ ድንጋጌ አድርገው እንደሚመለከቱት ሌሎች ደግሞ ይህ ድንጋጌ በሀገሪቷ ውስጥ የነበረውን ተጨባጭ የሕዝቦች ችግር ለመፍታት በሚል የገባ ችግር ፈቺ እና ምክንያታዊ ድንጋጌ እንደሆነ አድርገው እንደሚያዩት አስቀምጠዋል።

በዚህ ጸሐፊ አተያይ በአዲስአበባ ጉዳይ ሶስት ዓይነት የውዝግብ መነሻ ሃሳቦች አሁንም መቋጫ አላገኙም። ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ ኦሮሚያ በአዲስአበባ ላይ የምታገኘውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ በግልጽ የደነገገ ቢሆንም አንዳንዶች ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌው በሕዝቦች መካከል መቃቃርን የሚፈጥር ነው በማለት አምርረው ያወግዙታል። እነዚህ ወገኖች ከተማዋ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ናት የሚል ሃሳብን ያራምዳሉ።

ሁለተኛዎቹ ወገኖች የሕገመንግሥቱን ድንጋጌ ተገቢነት በመጥቀስ ያለአንዳች ማወላወል ኦሮሚያ በአዲስአበባ ላይ ያላት ጥቅም እንዲከበር የሚወተውቱ ናቸው።

ሶስተኛዎቹ፤ “አዲስአበባ የተወላጆችዋ ብቻ ናት” የሚል አቋም የሚያቀነቅኑ ናቸው።

የኢህአዴግ ቸልተኝነትገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በራሱ መልካም ፈቃድ በ1987ቱ

ሕገመንግሥት ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ጥቅም በሚመለከት ድንጋጌ እንዲሰፍር የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ቢሆንም ሕገመንግሥቱ ከጸደቀ በኋላ ባሉት ሁለት አስርተ ዓመታት ለአፈጻጸሙ ያደረገው ጥረት ቀዝቃዛ ነው። በዚህ ምክንያት ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌው የወረቀት ላይ ጌጥ ሆኖ እንዲኖር ተፈርዶበታል። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ይህን ያደረገው ሆን ብሎ ነው ወይንስ ለአፈጻጸም አመቺ ጊዜ ሲጠብቅ የሚለው የራሱ የሆነ ዝርዝር ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም በሕገመንግሥቱ መሠረት ዝርዝር ሕግ አውጥቶ ማስፈጸም አለመቻሉ ግን ዛሬ እዚህም እዚያም ለሚነሱ አለመግባባቶች መንስኤ እየሆነ መምጣቱን ማስተባበል አይቻልም።

እናም ኢህአዴግ ሥርዓቱን ጠብቆ ሕገመንግሥቱን በሌላ ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌ እስካልሻረ ድረስ ሕጉን አክብሮ የማስከበር እና የማስፈጸም ግዴታ አለበት። ይህም ሆኖ ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌውን ተከትሎ ዘሎ ወደአፈጻጸም ከመግባቱ በፊት በተለይ በጉዳዩ ላይ ትልቁ ባለድርሻ የሆነውን የአዲስአበባን ሕዝብ ማወያየትና ሃሳቡን መስማት ማስቀደም እንደሚኖርበት በርካታ ምሁራን በየጊዜው የሚሰጡት ምክር ነው።

ህአዴግ ያንቀላፋበት የፊንፊኔ አጀንዳ

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በራሱ መልካም ፈቃድ በ1987ቱ ሕገመንግሥት ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ጥቅም በሚመለከት ድንጋጌ

እንዲሰፍር የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ቢሆንም ሕገመንግሥቱ ከጸደቀ በኋላ ባሉት ሁለት አስርተ ዓመታት ለአፈጻጸሙ ያደረገው ጥረት ቀዝቃዛ ነው።

፲፰

Page 19: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

10 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

ሴቶች በሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል። በተለይ ደግሞ በኢኮኖሚ ዘርፉ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ በገጠርም ሆነ በከተማ ለማሳደግ የተደረገው ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤት እያስመዘገበ ነው። የሴት ኢንተርፕሩነሮችን ካፒታል ማሳደግ የሴቶች ሁለንተናዊና ማህበራዊ ችግር መፍታት ብቻ ሳይሆን በሃገር ደረጃም ለሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።

በከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋትስና ኤጀንሲ የሴቶች ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ባንክ እና ከተለያዩ መንግስታት በረጅም ጊዜ ብድር በመውሰድ ተግባራዊ ይገኛል። በዋናነት ሴቶችና ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚና ቀጥታ ተሳታፊ እንዲሆኑ፣ የስራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ እንዲስፋፋ፣ ዜጎች የራሳቸውን ገቢ በማመንጨት የቁጠባ ባህል እንዲዳብር በማድረግ ለቀጣይ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት እየጣለ ይገኛል።

የፌደራል ከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ የሴት ኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት ያለበትን ሁኔታ አስመልክተው በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ እቅድ ትግበራ የተመደበለትን የብድርና የስልጠና ሃብት በመጠቀም ለፕሮጀክቱ የተቀመጡትን ግቦች ማሳካት እንዲቻል እስከ ታህሳስ 2010 የጊዜ ገደብ ውስጥ በዓለም ባንክ በተደረገ ግምገማ መሰረት ሃብቱ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ ውሏል ብለዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ በሀገራችን ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የሴት ኢንተርፕረነሮችን በማፍራት ረገድ ትኩረት ተሰጥቶት እተሰራ ነው። የመንግስት ፖሊሲና አጠቃላይ ስተራቴጂም ሴቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ እንደ ሃገር ከታቀዱት

የእቅድ ክፍል አንዱ ነው። የሴቶች ልማት ኢንተርፕረነርሺፕ ፕሮግራም ስራውን ከጀመረ ጊዜ ጀምሮም ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አከናውኗል።

ሴት ኢንተርፕረነሮች በአበዳሪ ተቋማት በኩል በሚቀርብ የፕሮጀክቱ ብድር ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የመጀመሪያውም ፋይዳ እውቀቱና ገበያው ኖሯቸው የገንዘብ አቅም ላነሳቸው ሴት ኢንተርፕረነሮች የተሻለ ብድር በመስጠት ንግዳቸውን፣ አገልግሎታቸውንና ምርቶቻቸውን ለማስፋፋት፣ ገቢያቸውን ለማሳደግና የስራ እድል ለመፍጠር ያስችላቸዋል።

አክለውም በአሁን ላይ አገራችን በለውጥ ላይ ባለችበት ወቅት በስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የሴቷ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንደ ሃገርም ሃምሳ ሃምሳ ማድረስ ተችሏል ብለዋል። ፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት በሴቷ የሚመሩ ኢንተርፕረነር የንግድ ኢንተርፕራይዞቻቸውን የገንዘብ ችግር ከመፍታት አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

በሴት ኢንተርፕረነርሺፕ የተደራጁትንም የሚደራጁ ትንም ፍላጎታቸውን መነሻ በማድረግ ስልጠና የብድር አገልግሎት መስጠት አንዱና ዋነኛ ተግባር ነው። ባለፉት ጊዜያት ወደ 20ሺ የሚሆኑ ሴቶችን የክህሎት ክፍተት ሊሞላ የሚችል የተለያዩ ስልጠና ለመስጠት እቅድ አውጥቶ ወደ 16ሺ የሚሆኑ ሴቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ተሰርቷል። ስልጠናውን ከወሰዱትም ሴቶች መካከል 10ሺ ለሚሆኑም ወደ ሁለት ነጥብ አራት ስድስት ቢሊዮን ብር ብድር በመውሰድ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ኃላፊው ገልጸዋል።

የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በዋነኝነት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን በተለይም በከተሞች አካባቢ የሚታዩ በድህነት ውስጥ የሚገኙ እና ለተለያዩ የማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ

ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ ለዜጎች በቂ የሥራ እድል በየአካባቢያቸው በመፍጠር እና የማህበራዊ ሴፍትኔት ሥርዓቱን በማጠናከር በከተሞች የሚስተዋለውን የምግብ ዋስትና እጦት ተጋላጭነት ለመቀነስም እየሰራ ነው። በከተሞች ያለውን ድህንትና ሥራ አጥነት ችግር ለማቃለልና ለመፍታት በሚደረገው እንቅስቃሴ የከተሞች ምግብ ዋስትና መርሃ ግብርም ተቀርፆ ሥራ ላይ ይገኛል።

በዚህም ተጠሪ ከሆኑት ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ወስጥ የሴቷን ከብድር በኋላ ውጤታማ መሆን ላይ በተደረገው የዓለም ባንክ ዳሰሳ ጥናት መሰረት 55 በመቶ በላይ ሴቶች ሌላ ተጨማሪ የስራ እድል መፍጠር ችለዋል። ከዚህም ውስጥ ወደ 45 ከመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሃብታቸው የኢኮኖሚ እድገት ማሳየት መቻሉን ጨምረው ገልጸዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ሰለሞን በበኩላቸው ባለፉት አምስት ዓመታት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሆነባቸው ስድስት ከተሞች ከተመዘገቡ ከ25 ሺህ በላይ ሴቶች ውስጥ ለ15 ሺህ ዎቹ በሥራ እድል ፈጠራ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል። የብድር መጠንን በተመለከተም አማካይ የብድር መጠን በግለሰብ ወደ 250 ሺ ብር ለማበደር መቻሉም ከማይክሮ ገንዘብ አበዳሪዎችና ባንኮች ከሚያበድሩት መሃል ላይ ያለ ብሎም መውሰድ እንደሚቻል አቶ ዮሃንስ ገልፀዋል።

አቶ ዮሐንስ እንዳሉት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ሴቶች በጨርቃጨርቅና ልብስ ስፌት፣ በምግብ ዝግጅት፣ በባልትና ውጤቶች፣ በሸቀጣ ሸቀጥና ሌሎች የንግድ ሥራዎች የተሰማሩ ይገኙበታል። ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ዓለም ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት በብድርና በድጋፍ በተገኘ 126 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንም ገልጸዋል።

የብድር አመላለስን በተመለከተ ለዘጠኝ ሺህ 500 ሴቶች 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ብድር መሰጠቱንና በብድር ከተሰራጨው ገንዘብ ውስጥም ከ98 በመቶ በላይ ተመላሽ መደረጉን አስተባባሪው ተናግረዋል። በብድር አመላለሱም

ላይ በየጊዜው ግምገማ የሚደረግ መሆኑን እና ሴቶች የተበደሩትን ብድር ከመመለስ አኳያ የውጤታማነቱ አንዱ መለኪያ እንደሆነ እና በተቋሙም ሆነ በዓለም ባንክ በየስድስት ወሩ በሚደረገው ግምገማ ውጤታማ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

ብድር አመላለሱም ላይ ተበድረው ነው የመለሱት ወይስ በሚለው ላይ በተደረገው በገለልተኛ አካል በተደረገው ጥናት መሰረት የመለሱት በሴቶች የሚመራው ኢንተርፕራይዝ 50 ከመቶ በላይ ተጨማሪ የስራ ዕድል መፍጠር እና 44 ከመቶ ተጨማሪ ሃብት መፍጠር ችሏል። ጥናቱም ውጤታማነቱን የሚያሳየው ብድር መመለሱ ብቻና ባሉበት ብቻም ሳይሆን እድገት አሳይተዋል።

በዚህም ፕሮጀክቱ ውጤታማ እየሆነ በመሆኑ ከዚህ በፊት የብድር አገልግሎትና ድጋፍ የማይሰጡ መንግስታትም ጭምር ለብድር የሚያግዝ ገንዘብ መስጠት ጀምረዋል። ይህም ድጋፍ ፕሮጀክቱን በማራዘም በስፋት ተደራሽ የማድረግ እድል እየሰጠው ነው። ስድስት ከተሞች ላይ የነበረውም አገልግሎት ሌሎች ተጨማሪ 5 ከተሞችን አሳትፏል።

አሁን ላይ ያለው የገንዘብ አቅርቦትም አንደኛው ብድር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መንግስት ገንዘቡን በተዘዋዋሪ መጠቀም እንዲቻል በመፍቀዱ ነው። በመሆኑም ገንዘቡ በብድር ከተሰጠ በኋላ ተመላሸ ሲሆን እንደገና ለሌሎች ተበዳሪዎች ይሰጣል።

ዳይሬክተሩ እንደገለጹትም ሴቶች ብድር መመለስ ላይ የተሻሉ በመሆናቸው የተበደሩትም ገንዘብ ያለምንም ብክነት እየተመለሰ ነው። በመሆኑም አነስተኛ አበዳሪዎችም በዚህ ተበረታተው የልማት ባንክ እስኪሰጣቸው ሳይጠብቁ ከራሳቸው እያበደሩ ነው። ስለዚህም ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚሆን ገንዘብ አነስተኛ ገንዘብ አበዳሪዎች ከራሳቸው ሰተዋል። ይህም የተቋሙ የማበደር አቅም ለማሳደግም ችሏል። ወደፊትም በዚህ መልክ እንደሚቀጥል እምነት እንዳላቸውም አስተባባሪው ገልጸዋል።

ሴት ኢንተርፕረነሮችን ማሳደግ ለስራ ዕድል ፈጠራ ያለው ፋይዳ የላቀ ነውበኃይሉ አበራ

ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በየ15 ቀን ቅዳሜ የሚታተም

ከ.ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በመተባበር በየሳምንቱ የሚቀርብ

ምክር ቤቱ ከዕረፍት ጊዜው በፊት ምን ሠራ

በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ ሁለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት እስከ ሰኔ ድረስ መሆኑን ይደነግጋል። ምክር ቤቱ በሚወስንበት ጊዜም የአንድ ወር ዕረፍት እንደሚኖረው ጭምር ተደንግጓል። በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 (2) መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የዕረፍት ጊዜ ከየካቲት አንድ ቀን እስከ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ለአንድ ወር እንዲሆን ወስኗል።

በዚህ የአሰራር ሂደት ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ ይገኛል። የተከበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ጥር 30/2011 ዓ.ም ድረስ ምን ሰርቶ ፣ በቀጣይ ምን ለመስራት አቅዶ ለዕረፍት እንደወጣ እንደሚከተለው አቅርበናል። በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 (2) መሰረት ህግ የማውጣት ተግባራት አዲስ ህግ ማውጣት፣ ነባር ህግ ማሻሻል ወይም መሻር፣ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ማፅደቅና ውሳኔ ማስተላለፍን ይመለከታል።

የእነዚህ ተግባራት አፈፃፀም በዝርዝር ሲታይ ነባር ህግን በአዲስ መተካት ስድስት፣ ቀድሞ ያልነበረ አዲስ ህግ ማውጣት ሁለት፣ የተሻሻለ ህግ አንድ፣ 16 የሁለትዮሽ ስምምነቶችና 16 ውሳኔ የተላለፈባቸው ህጎችን አፅድቋል፣ ውሳኔም አስተላልፏል። ነባር ህግን በአዲስ በመተካት በኩል የምክር ቤቱ የመጀመሪያው ስራ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 916/2008 ከነማሻሻያው በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 ተተክቷል።

አዋጅ ቁጥር 916/2008 ከነማሻሻያው በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 የተተካበት ዋናው ምክንያት አገሪቱ የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችል አደረጃ ጀትን ለመከተል፤ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በቀሪው ጊዜ

ያልተጠናቀቁ ስራዎችን አካክሶ ለመፈፀም የአስፈፃሚውን ቁጥር በመቀነስ ወጪ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ነው።

ተደራራቢና ስልጣንና ተግባር የያዙ የመንግስት ተቋማትን መቀነስ ወይም ለስራቸው ቅርብ ከሆነ ሌላ የመንግስት ተቋም ጋር እንዲዋሃዱ ማድረግ፤ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተወዳዳሪ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ መወጣት እንዲችሉ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 እንዲተካ ተደርጓል።

ተጠሪ ተቋማት በስፋት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመሆን ይልቅ ለዘርፉ ቅርብ ለሆነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ፣ ሆኖም ከተልዕኳቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ መሆን የሚገባቸው በዚሁ አግባብ እንዲደራጁ ለማድረግም ጭምር ነው።

ተደራራቢና ድግግሞሽ ስልጣንና ተግባር የያዙ የመንግስት ተቋማትን መቀነስ ወይም ለስራቸው ቅርብ ከሆነ ሌላ የመንግስት ተቋም ጋር እንዲዋሃዱ የማድረጉ ስራ ብዙ ተቋማትን ነካክቷል። ከተቀነሱት መካከል የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት፣ የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ይጠቀሳል።

ይህም የአስፈፃሚ አካላትን ቁጥር በመቀነስና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆን በማድረግ በተቻለ መልኩ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና የተቀናጀ ካብኔ ማቋቋምና የማስፈፀም አቅሙን ማጠናከር የሚለውን የአዋጁን አስፈላጊነት የሚያረጋግጥ የስራ አካል ነው። አዋጅ ቁጥር 916/2008 በአዲሱ አዋጅ ከመተካቱ አስቀድሞ ሦስት ጊዜ ማሻሻያዎች ተደርጎበት ነበር። አዲሱ አዋጅ ነባሩን አዋጅና ማሻሻያዎቹንም ጭምር ለውጧል። ይህ የምክር ቤቱ ስራ መሰረታዊ የለውጥ አቅጣጫን የተከተለና ከስራዎች ሁሉ በቀዳሚነት የሚወሰድ ነው።

ከተሻሻሉ ህጎች መካከል አንዱ የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ነው። በአሁኑ ማሻሻያ የምክር ቤቱን ስራዎች ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ አቢይ አማራጭ የሆነውን የሚዲያ አገልግሎት በራሱ

አቋቁሞ መረጃ ለህዝብ በፍጥነት እንዲደርስ ለማድረግ ነው።

በቀደሞው ማቋቋሚያ አዋጅ የጥናትና የምርምር ስራዎችን እንደሚያከናውን በግልፅ ያልተቀመጠ በመሆኑ በደረጃ ምዘናም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን በማስቀረት የጥናት፣ ምርምርና የማማከር ስራን በጽህፈት ቤቱ ስልጣንና ተግባር ውስጥ እንዲያካትት የማሻሻያ አዋጅ አፅድቋል። ማሻሻያ ህጉ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር መርሆዎችን ጠብቆ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ ባለሙያዎች ከገበያ ለማግኘት እንቅፋት ሆኖበት የነበረውን የሰው ቅጥር፣ ደመወዝና ጥቅማጥቅም ጉዳዮች ለመፍታት ምክር ቤቱ በራሱ እንዲወስን ያግዘዋል።

ሌላው በመከላከያ ሰራዊት አደረጃ ጀትና የአሰራር ለውጥ ለማምጣት የወ ጣው የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 ነው። በአደረጃጀት በኩል ከተደረጉ ማሻሻያዎች አንዱ በአዋጅ ቁጥር 809/2006 ያልነበሩ የባህር ሃይል፣ የልዩ ዘመቻዎች ሃይል እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የሚቋቋሙ የስፔስና የሳይበር ሃይሎች መምጣታቸው ነው።

በአሰራር በኩል ከተደረጉ ማሻሻያዎች አንዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚሰጡትን ወታደራዊ አገልግሎት ለማበረ ታታት የተለያዩ ማበረታቻ ድንጋጌዎች በአዲሱ አዋጅ መካተታቸው ነው። ከነዚህ አንዱ፤ አስራ አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገለ ማንኛውም የሰራዊት አባል በተወለደበት የክልል ከተማ የግል የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኝ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ መደንገጉ ነው።

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ ለውጦችን ለማምጣት በቀድሞው ህግ ድንጋጌዎች ላይ ከፍተኛ ሊባል በሚችል ደረጃ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ከሚወስነው ረቂቅ ህግ በቀር በሞሽን ወዲያውኑ የፀደቀ ህግ የለም። የዚህ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በሞሽን ወዲያውኑ እንዲፀድቅ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ረቂቅ ህጉ ወደቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ውሳኔ ተላልፎበታል።

ሌላው የተሻሻለው ህግ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ነው። ህጉ

አዎንታዊ ለውጦችን ያመጣ ቢሆንም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዕድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ በማስከተሉ የህዝብ እሮሮ ከሚሰማባቸው ህግጋት ውስጥ አንዱ በመሆኑ በአዲስ መልክ እንደገና ሊታወጅ ችሏል። በዚህ መልክ የስደተኞች ጉዳይ፣ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማቋቋሚያ ነባር ህጎች ሊሻሻሉ ችለዋል።

በሌላ በኩል ተግባር ውሳኔዎችን ማስተላ ለፍ ሲሆን አብዛኛዎቹ ስራዎች ሹመትን የሚመለከቱ ናቸው። የዕጩ ካብኔ አባላት ሹመት፣ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ መምረጥ፣ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትን መምረጥ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ሹመት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ምደባ፣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ምርጫ፣ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን አባላት ምደባ፣ ለአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች እና ለዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ምደባ እና ለፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሚወከሉ አባላትን ከምክር ቤቱ መመደብ የሹመት ውሳኔዎች ናቸው።

አስፈፃሚው አካል የተዋዋላቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም አፅድቋል። የብድር ስምምነቶችን በሚመለከት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለተወዳዳሪነት እና ስራ ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ፤

ለልማት ፖሊሲ ፋይናንስ ማስፈፀሚያ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ኦፖርቹኒቲይ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የተፈረሙ መጠናቸው 863.33 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሆኑ የብድር ስምምነቶችን ምክር ቤቱ አፅድቋል።

በአየር አገልግሎት በኩል ከሞሮኮ፣ ከእስራኤልና ከፈረንሳይ ጋር የተፈረሙ የተናጠል ስምምነቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበረራ አድማሱን ለማስፋት ለሚያደርገው ጥረት ጠቃሚ ሆኖ በመገኘቱ ምክር ቤቱ ስምምነቶቹን አፅድቋል። ሌሎቹ የፀደቁ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ከተለያዩ አገራት ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ናቸው።

ሌላው መሻሻል የታየው የብድር ስምምነቶች ግልፅነትን በተላበሰ ሁኔታ እንዲቀርብ የምክር ቤት አባላት ያላቸው ፍላጎት ነው። በብድር የመጣው ገንዘብ በትክክል የሚቆጣጠሩት እና ውጤቱንም በትክክል የሚያዩት እንዲሆን በጥብቅ ተሟግተዋል። ከዚህ በፊት ብድር መገኘቱ ብቻ በጥሩ ጎኑ ታይቶ ድልድሉ ግን ግምት የሚሰጠው አልነበረም። ይህ አመለካከት አሁን ተቀይሯል። የህገ መንግስቱ አንቀፅ 54 ንዑስ አንቀፅ 4 የምክር ቤቱ አባላት ተገዢነት ለህገ መንግስቱ፣ ለህዝቡና ለሕሊናቸው ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል።

19የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

Page 20: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

22 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩

በሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር በለጬ በምትባለውና በጫት ምርቷ ያለ አንዳች ማጋነን በመላው ኢትዮጵያ ዕውቅናን ያገኘች ነች። በለጬ የሚለው ስያሜ የጎሳ ስም ሲሆን በዚሁ ጎሳ ስም የተሰየመችው ይህች ቦታ በተለይ ለሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ቅርብ ስትሆን ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ከሚያስጉዘው 275 ኪሎ ሜትር ባነሰ ወይም 260 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ ነው የምትገኘው። ከሻሸመኔ ከተማ በ18 ኪሎ ሜትር የቅርብ ርቀት ላይ ነው ያለችው። በአካባቢዋ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትም አሉ።

በዚህች አካባቢ ቡናና የተለያዩ ፍራፍሬዎች ቢመረቱም በየጉራንጉሩ ሳይቀር በየሄድንበት ሥፍራ ‹‹የበለጬ ጫት አለ›› ተብሎ ነው የሚፃፈው፣ ስሟን በመላው ሀገር ሊያስጠራላት የበቃውና በዓመት ሦስት ጊዜ የሚመረተው ጫት ዋና የገቢ ምንጯ ነው።

ከተማዋ በለጬ ጫት ማምረቻ ብቻ ሳትሆን የጫት ንግድ ማዕከልም ናት። ማዕከሉ ከወንዶ ገነት ከተማ በ200 ሜትር ርቀት ሲገኝ አሁን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በከተማዋ እግር መረገጫ ቦታ እስኪጠፋ ድረስ ከቦርቾና ከሌሎች በከተማዋ ዙሪያ ካሉ ወረዳዎች እንዲሁም ከአሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ከሀዋሳና ከመላ ሀገሪቱ በመጡ የጫት ነጋዴዎች ትሞላለች። ገበያው ይጡዋጡዋፋል።

ከወራቤ የመጣውን ሙዘይን ጀማልን ለዚሁ ለጫት ሸመታ ብሎ ከሀረር ከመጣውና ሃይረዲን አሊ ከተባለው ጓደኛው ጋር ነው በዚያ ቦታ ያገኘነው። ለንግድ ብዙ ሺህ ብሮችን አውጥተው በመግዛት በየፊናቸው አይሱዚ መኪና ላይ ከጫኑት ውጭ ጭብጥ የማትሞላ ጫት ይዘዋል።

ሙዘይን ‹‹ይሄን አምስት መቶ ብር ነው የገዛሁት›› ሲለን ማመን አቃተን። ሃይረዲን በበኩሉ የያዘውን ጭብጥ የማይሞላ ጫት እያሳየን ‹‹ፈታ ዘና ልንልበት ነው›› አለንና ጥለውን ሄዱ። በለጬ ምርቃና ላይ ከገበያ በኋላ በተለይም ቀደም ብለው ገበያ

ተገበያይተው የጨረሱ ወደ የመጡበት ከመበተናቸው በፊት እንደነ ሙዘይን የሚበቃቸውን ሸምተው በመቃሚያና በተለያዩ መሸታ ቤቶች ገብተው ፈታ ዘና ማለታቸው የተለመደ ነው።

ከሻሸመኔ እንደመጣው ደበሌ ቶላ ገለፃ ፈታ ዘና ሲባል ደግሞ ምርቃና፣ ጨብሲና ሌላም፣ሌላም ነገር ይከተላል። አብዛኞቹ የጫት ገበያተኞች ወደ የመጡበት የሚመለሱት ታዲያ ይሄንኑ ተግባር ሲያከናውኑ ቆይተው እኩለ ሌሊት ላይ ነው። በዘና ፈታው ተዘናግተው ሳያስቡት የሚያነጉም አሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንዳንድ በዚሁ በበለጬ ጫት ግብይት ሰበብ የሚያውቃቸው ነጋዴዎች በኤች አይ ቪ የተያዙበት አጋጣሚ መኖሩንም ያውቃል።

‹‹ገበያችን እነሱ ናቸው›› ያለችን ደግሞ በአካባቢው በሴት አዳሪነት ሥራ ላይ የተሰማራችውና ፈገግታ ከፊቷ ያልተለያት ወጣት ማርታ ባቦሬ ነች። እንዳከለችልን በተለይ ያለ ኮንዶም ወሲብ መፈፀም የሚፈልጉ ጫት ነጋዴ ወንዶች ያለ አንዳች ድርድር ዳጎስ ያለ ብር ልክፈላችሁ ችሏል።

እሷ በኤች አይ ቪ ልያዝ እችላለሁ በሚል ስጋት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚሰጧት ቃል ቢገቡላት ከነኝህ ዓይነቶቹ ወንዶች ጋር ግንኙነት ባትፈፅምም በኮንዶም ተጠቅማ የተለያዩ ወንዶችን በማስተናገድ በቀን ውስጥ እስከ አንድ ሺህ 500 ብር የምታገኝበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን በግንኙነት መሀል ኮንዶም ከተቀደደበት ደንበኛዋ ያረገዘችበት ሁኔታ እንደነበርና አጋጣሚ ሆኖ በቫይረሱ እንዳልተያዘችም አጫውታናለች። ሆኖም ሳትፈልግ ወንድ ልጅ ተገላግላለች።

ልጅ መውለዷ ይሄን የያዘችውን ሥራ ለዓመታት ፈታኝ ኑሯዋንም ከባድ አድርጎባት ነበር። ሆኖም አሁን ላይ እሷም ልጇም ጤናማ በመሆናቸው ደስተኛ ነች። በገንዘብ ኃይል ያለ ኮንደም ግንኙነት በማድረጋቸው ዛሬ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሆኑና ሕይወታቸው ያለፈ ጓደኞቿን በማጣቷ ሀዘን ይሰማታል። ራሳቸውን ገልፀው ፀረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ መድሐኒት ቢጠቀሙ ሕይወታቸውን እንደሌሎቹ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ያለ ወገኖች በሌላ ሥራ ተሰማርተውም ሆነ እየተደገፉ ሊኖሩ

እንደሚችሉም ስታስብ ይቆጫታል። ነገር ግን በነሱ የደረሰው ለእሷ ዛሬ እራሷን ከኤች አይ ቪ ምትከላከልበት ትምህርት ሰጥቷት አልፏል።

በሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ማሀበራዊ ዘርፍ ተቋማት ጽሕፈት ቤት በተደጋጋሚ የሰጣትን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰረት በማድረግም ከዚህ ሥራ ለመላቀቅ ሕብረተሰቡን ከኤች አይ ቪ ለመከላከል የሚያበረታታ ነው ብላ ባታምንም ራሷን ለማዳን ስትል ብቻ ነጋዴው አብዝቶ የሚጠቀመውን ከጠላ ጀምሮ አረቄ፣ ቢራና ሌሎች መጠጦችንም በመሸጥ ለመተዳደር ዝግጅት እያደረገች ነች። በእርግጥ ሌላ አማራጭ ካገኘች ይሄን ሥራ መስራት አትፈልግም። በዚሁ ጉዳይም መሰንበቻዋን በሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ጽሕፈት ቤትን ለማማከር አስባለች።

በጫት ንግድ ሥራ የተሰማራው አቶ ማዳ ወጨፎ እንዳጫወተን የትውልድ ቦታው በዛው ክልል በአንዱ አካባቢ ነው። በለጬ ላይ ሰምጦ የቀረው በጫት ንግድ ሰበብ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ በደሙ ውስጥ ይገኛል። መሸጥ ብቻ ሳይሆን አብዝቶ ጫት ይቅም እንደነበርም ያስታውሳል። ከቃመ በኋላ ደግሞ በምርቃና እንዴት የተለያዩ የአልኮል መጠጦችን አብዝቶ ይጠቀም እንደነበርና ይሄኔም ዓለምን በመዳፉ የጨበጣት ያህል ስሜት ይሰማው እንደነበረ ያስታውሳል።

«ወደ ተለያዩ ሴቶች ዘንድ ሄጄ ብዙ ገንዘብ በመስጠት ያለ ኮንዶም በተደጋጋሚ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደርግ የነበረውም ከዚህ በኋላ ነበር» በማለትም ቤት ንብረቱን ትቶ በለጬ ላይ ሰምጦ የቀረበትን ድርጊቱን በፀፀት ያስታውሰዋል። አሁን ላይ እንደ ወጣት ማርታ ሁሉ እሱም በሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ማሀበራዊ ዘርፍ ተቋማት ጽሕፈት ቤት በተደረገለት የምክር አገልግሎትና ሌሎች ተከታታይ የሕክምና ድጋፎች በማገገም መቃሙንም ሆነ መጠጣቱንና አብዝቶ ወደ ተለያዩ ሴቶች ዘንድ መሄዱን እርግፍ አድርጎ ለመተው በቅቷል።

በአሁኑ ወቅትም ወደዚያው ወደ ጫት ንግድ ሥራው ተመልሶ የበለጬ ጫትን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይዞ በመሄድ እየሸጠ ኑሮውን በመግፋት ላይ ይገኛል። በቅርቡ ከዚህ ሥራ የመውጣትና በሌላ ለሕብረተሰቡና ለተተኪው

ትውልድ ጠንቅ ባልሆነ ሥራ ላይ የመሰማራት ሀሳብ መሰነቁንም አውግቶናል። በዚህ በኩል የምክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎት የቸረውን በሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ጽሕፈት ቤትን ያመሰግናል። ከእዚህ ውጭ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ የራሱን ተሞክሮ እያጣቀሰ በኛ ይብቃ ትውልድ ይዳን በማለት እያስተማረ ይገኛል።

አቶ ግርማ ባጮ በሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሲሆኑ እንዳጫወቱን ጽሕፈት ቤታቸው በትምህርትና በጤና ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ ኤች አይ ቪ ላይ እየሰራ ያለው ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል። ታዲያ በለጬ ከሀዋሳ ጀምሮ ኦሮሚያና ሌሎች በርካታ የሀገሪቱና የክልሉ ከተሞች ያለ ማጋነን በመላው ኢትዮጵያ በጫት ንግድ ሥራ የተሰማራ ነጋዴ ጫትን የሚገበያይባት ማዕከል ነች። ጫትን ጨምሮ ቡናና የተለያዩ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙ ምርቶች ስለሚመረትባትም ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ ነች። በለጬን ጨምሮ የወንዶ ገነት ከተማ ራሷ በተጋላጭነት ተለይታ የተያዘች ሲሆን 314 ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖች ይገኙባታል።

ዘንድሮ በጽሕፈት ቤቱና በጤና ተቋም ቅንጅት አማካኝነት በከተማዋ በተደረገ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ሁለት ወገኖች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ በመገኘቱ ቁጥሩ ወደ 316 ከፍ ብሏል። ጽሕፈት ቤቱ እነዚህ ወገኖች በሚደገፉበትና ስርጭቱና ቫይረሱ ወደሌላ በማይተላለፍበትና እዚሁ ላይ በሚቆምበት ተግባር ላይ እርብርብ እያደረገ ይገኛል።

ለዚህ ደግሞ በነዚህ ወገኖችና በሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ነው። በተለይ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች እራሳቸውን ከመንከባከብና እንደማንኛውም የሕብረተሰበ ክፍል ማህበራዊ ጠንቅ ባልሆነ ሥራ መስክ በመሰማራት ኑሯቸውን ከመደጎም ጎን ለጎን እራሳቸውን ገልፀው በአደባባይ እንዲያስተምሩ የማድረጉ ጥረት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በወንዶ ገነት ከተማና በበለጬ ላይም የቫይረሱን ስርጭት ባለበት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት በማገዝም ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው።

የማሕበረሰቡ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭነትና የመከላከል ተግባር

ሰላማዊት ውቤ

ከፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ዓርብና ቅዳሜ ግማሽ ገጽ እንዲሁም እሁድ አጀንዳ ሙሉ ገጽ እየተዘጋጀ የሚቀርብ

38

Page 21: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

19የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ምየካቲት ፲፮/፳፻፲፩ነጻ ሃሳብ >>

አሸናፊ ዘደቡብ

በፖለቲካል ኢኮኖሚ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው። ከ1970ዎቹ መባቻ አንስቶ በኢትዮጵያ ራዲዮ የእሁድ ፕሮግራም ላይ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው በርካታ ፕሮግራሞችን ሰርተዋል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ በአዲስ ዘመን፣ በእንግሊዝኛው አዲስ ስታንዳርድና በሌሎች ጋዜጦች ላይ በመፃፍ ይታወቃሉ።

አሸናፊ ዘደቡብ

‹‹… እኔ እንደው የእርሱ ነገር ይገርመኛል። አይ ለዛው! አይ ጨዋታው! አይ ቀልዱ! ከእርሱ ጋር የዋለ ሰው እኮ ለአፍታ እንኳ ጥርሱ አይከደንም። ቀኑን ሙሉ ቢያወራ፤ለሰዓታት ቢናገር አስቆ!አስቆ! አይ እርሱ አይ እርሱ…!!›› ሲባል አልፎ አልፎ እንሰማለን። በስሜተ ትፍሥሕት የተከሸነ፣ በደስታ ሠሪነት የገነነ፣ በአነጋገሩ ለዛ፣ በቋንቋው መዓዛ የተወደደ በወዛም አንደበቱ፣ በዘይቤያዊ ብልሃቱ፣ በአቀራረብ ስልቱ የተፈቀደ ሰው በሚዘከርበት ወቅት።

አባባሉ ትክክል ነው የተጋነነም አይደል። ሌላው ቀርቶ ክፉኛ ያዘነ የሚያጽናኑ በሳቅ የሚያዝናኑ ሰዎች አሉ። ዝምታን በፈገግታ ለመተካት፤ ሐኬትን ወደ ሐሴት ለመለወጥ የሚችሉ፤ በዚያ ተሰምቶ በማይጠገበው፤ ተደምጦ በማይሰለቸው አነጋገራቸው ልብን በደስታ የሚሞሉ አሉ። በዚህ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ። የተቆጣ የሚያቀዘቅዙ፤ የቆረፈደ የሚያወዙ፤ የደረቀ የሚያለሰልሱ፤ የተኛ የሚቀሰቅሱ አሉ። በአንደበት ብቻም ሳይሆን እንደ ማር በጣፈጠ ቋንቋ ወረቀት ያቀለሙ፤ ሆሄያትን በስሜተ ትፍሥሕት የቀመሙ ጸሐፍያነ ትፍሥሕት በዓለማችን ሕልውናቸውን አስመስክረዋል። ለምሳሌም እነ ስዊፍት፤ እነ ማርክ ትዊይን እነ ፒተር ዲቭሪና መሰሎቻቸው ለጥቅስ ይበቃሉ። ሳይጽፉና ሳይናገሩ እንዲሁ በአኳኋናቸው አስቀው የሚያስቁም አሉ።

ለመሆኑ በሰው ልብ ደስታን ለመዝራት መንፈስን፤ ስሜትን ለማደስ፤ ‹‹ዘራኤ ትፍሥሕት›› (ሒዩመሪስት) ለመሆን የበቁት እኒያ ሰዎች እንዴት ቢያደርጉ ነው ይህን የመሰለ ችሎታ ያገኙት? ‹‹ሒዩመር›› ወይም ‹‹ሴንስ ኦፍ ሒዩመር›› ትፍሥሕት ወይም ስሜተ ትፍሥሕት የተባለው እንዴት ይተነተናል? እነዚህ ጥያቄዎች ናቸው በምድራችን የሠፈሩትን የሥነ ልቡናና የሥነ አዕምሮ ሊቃውንት በእጅጉ ሲያስጨንቁ የኖሩት።

‹‹የሕክምና ጠበብት ሳይቀሩ ትፍሥሕትን ለመተንተን ያላደረጉት ጥረት የለም። ይህን እናውቃለን። በየመስኩ የተሰለፉ ሌሎች ምሁራንም በየጊዜው ስላካሄዱት ምርምር ሰምተናል። በእርግጥ የማይሞከር ነገር የለም። ረብ ያለው ውጤት ይዘው የቀረቡ መተርጉማነ ትፍሥሕት ግን እስካሁን አላየንም።›› ሲሉ የኒውዮርኩ ሊ-ቢ-ኋይትስ የተናገሩት ይጠቀሳል።

ሌላው አሜሪካዊ ዘራኤ ትፍሥሕት ሮበርት ቤን ችሊ ደግሞ ‹‹የትፍሥሕትን ትንታኔ የሚያውቀው ዘራኤ ትፍሥሕት የሆነው ሰው ብቻ ነው። ትንታኔው ራሱ ትፍሥሕት ሆኖ ይገኛልና›› በማለት ነው የደመደሙት።

የሁለቱንም ሰዎች አስተያየት ስንመለከት ‹‹ትፍሥሕት…›› ሲባል ከፅንሰ ሐሳብ ትርጓሜ በቀር ስርፀቱ ሊታወቅ፤ ክስተቱ ሊጠናና ሊተነተን እንዲያ ሲልም በእርሱነቱ የታመነ የምርምር ውጤት ሊቀርብ አለመቻሉን እንረዳለን። ‹‹ትኩረት በትፍሥሕት›› ብለው በየወቅቱ ለምርምር የተነሱ ሊቃውንትም ይህንኑ እውነታ ሳይቀበሉት የቀሩ አይመስልም።

‹‹ትፍሥሕት እንዴት ይሰርፃል? በእርግጥ ደስታ የሚገኘው በዘፈን ብቻ፣ በሙዚቃ ብቻ ወዘተ…›› የሚሉ አሉ። ግን አይደለም፤ ያ ዘራኤ ትፍሥሕት ምን ዓይነት ፀጋ ቢያገኝ ነው እንዲያ የሚናፈቅ፣ የሚወደድ፣ የሚፈቀድ ሊሆን የበቃው? ስሜተ ትፍሥሕትስ እንዴት ይተነተናል?›› ለተሰኙት ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ብዙ ብዙ ጥረዋል። ጥረቱ አንዳች ፋይዳ ያለው ውጤት ስላሳየ ጥያቄዎቹም ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል። አመዛኙም ምሁራን ‹‹ለማወቅ አስቸጋሪ…›› ከሚለው መደምደሚያ ነው የደረሱት።

ያም ሆኖ ግን ያልታከቱ ተመራማሪዎች በባሕር ማዶው አህጉር በየዓመቱ እየተገናኙ በጉዳዩ ላይ መወያየታቸውን አላቋረጡም። በዚያው አውደ ጥናት ዝነኛ ጸሐፍያንና ጸሐፍያት ያቀለሟቸው ወረቀቶች ለጥራዝ ያበቋቸው ትፍሥሕታዊ መጻሕፍት ይነበባሉ፤ ይመረመራሉ፤ ይተረጎማሉ፤ ይተነተናሉ። ታዛቢዎች እንደገለጹት በአሪዞናው የሊቃውንት ስብሰባ የተስተዋለው አውደ ጥናት

የጥራዞቹን ገጽ ከማገላበጥ አልፎ የተጓዘበት ፍኖተ ጥበብ እውን ሊሆን የበቃበት ሁኔታ አልታየም። የተተረጎመው፤ የተመረመረውና የተተነተነው ወረቀቱ እንጂ የትፍሥሕት ሥርዓተ ክስተት የዘራኤ ትፍሥሕት ባሕርይና ብቃት፤ በግለሰብ ደረጃ ከሌላው የተለየ ሊሆን የበቃበት ምክንያት በውል ሊታወቅ አልቻለም።

ያለ ትፍሥሕት በሕይወት መኖራቸውን ከሚጠራጠሩት ሰዎች አንዱ ጆሴፍ ሄለር እንደተናገሩት የትፍሥሕትን ትርጓሜ ለመረዳት፤ በስሜተ ትፍሥሕት ላይ በቂ ግንዛቤ ለማግኘት ወይም ዘራኤ ትፍሥሕት ለመሆን የሚያስችል ሳይንሳዊ ዘዴ እስከ አሁን አልተገኘም። በሄለር አስተሳሰብ ይህ የአንድ ግለሰብ ተፈጥሯዊ ፀጋ ነው። ተምረው የሚመረቁበት፤ በሰው ምክር የሚያከናውኑት፤ በሐኪም ትዕዛዝ የሚፈጽሙት አይደለም። ‹‹እኔ እንዳረጋገጥኩት ትፍሥሕት ያለገደብ ማንኛውንም በሽታ አያድንም። ሥነ አዕምሯዊና ሥነ-ልቡናዊ ችግር ውስጥ ለገባ ሰው ብቻ ፍጡነ ረድኤት ነው›› ሲሉ ሄለር አስምረውበታል። ትፍሥሕትን ከመድኃኒት ቤት እንደሚገዛ ኪኒን መቁጠር፣ ከእርሱ ጋር ማነፃፀር እንደማይቻል ሳይጠቅሱ አላለፉም።

ግና ዳሩ ጆሴፍ ሄለር ይህን ይላሉ እንጂ፤ በተቃራኒ አመለካከት የደነደኑ ሰዎች ከዓመት ዓመት በቁጥር እየጨመሩ መሄዳቸውን ሰነዶች ይጠቁማሉ። በተለይም ‹‹አናቶሚ ኦፍ ኢልነስ›› በተሰኘ ርዕስ ደራሲ ኖርማን ኬት ሪንስ አንድ መጽሐፍ አስጠርዘው አደባባይ ካዋሉ ወዲህ ብዙዎች ናቸው የትፍሥሕትን ፈዋሽነት አምነው ሊቀበሉ የተገደዱት። ‹‹ ከላኤ ተወሳክ›› ብለው በበሽታ ከልካይነት አያድንቁት እንጂ ‹‹ደምሳሴ ደዌ›› ብለው በሕመም አኮስማኝነት የተጠቀሙበት እየበዙ ሄደዋል። ይህ በሚገባ ተመዝግቧል።

በአንድ ወቅት በፅኑዕ ታመው የነበሩት ኖርማን ካዠንስ ከሕመሙ ሥር ሰደድነት የተነሣ በሕይወት ለመኖር ያላቸው ተስፋ በእጅጉ መንምኖ በተገኘበት በዚያን ሰዓት ራሳቸው በቀመሩት ደምሳሴ ደዌ ጥቂት ‹‹እፎይ›› ሊሉ እንደበቁ ተነግሯል። በደም ሥራቸው ከሚሰጠው የብርታት መድኃኒት ጎን ‹‹ሳቅ›› ዓይነተኛ ድርሻ ሊያበረክት በቅቷል። ‹‹ጠዘጠዘኝ፣ከተከተኝ ፣ ቆረጠኝ ፣ቆረጠመኝ…›› እያሉ በሽልብታ እጦት ሲሰቃዩ የከረሙት እኒያው ደራሲ አንዳንድ አስቂኝ የሆኑ አሮጌ ፊልሞች (በተለይም የኮሚኮችን) ፈልገው በየቀኑ እየደጋገሙ ማየት ጀመሩ። ጅማሯቸውም ‹‹ይበል›› የሚያሰኝ ሆነ። ስቆ መሞት ለሕይወት ለጤንነት አገለገለ። ይህን በሚገባ ተረዱ። ፊልሞቹን እየተመለከቱ ለአሥር ደቂቃ ከአንጀታቸው ተንከትክተው መሳቅ! መሳቅ!መሳቅ! ያች የዐሥር ደቂቃ ብርቱ ሳቅ ለሁለት ሰዓት እንቅልፍ ዋስትና ልትሰጥ መብቃቷን አረጋግጠው ሲንከተከቱ ከረሙ።

ሳቁ ያን የሚጠዘጥዛቸውን፤ ያን የሚፈልጥ የሚቆርጣቸውን አደነዘዘው። በሽታውን አፈዘዘው። ከዚያ ወዲህም ነው ሊቃውንት ትፍሥሕት ያለውን ሥነ ሕይወታዊ ትርጓሜ ለመመርመር የፈቀዱት።

በስታንፎርድ የሕክምና ኮሌጅ ርዕሰ ሊቃውንት በዶክተር ዊልያም ፍይ ሊቀ ጉባኤነት የተሠየሙ ጠበብት እንዳረጋገጡት

አንድ ሰው በሚስቅበት ጊዜ በአንጎሉ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሕዋሳት ይፍታታሉ። እንዲህ ሲሆንም ውጥረት ይረግባል፤ ሕመም ይቀንሳል። ‹‹ትፍሥሕት ለጤንነት፣ ለደስታ፣ ለመንፈስ ርጋታ›› በሚል መርሕ በዶክተር ሎውሬንስ ፒተር እና በቢል ዳና የተዘጋጀች አንዲት ትንሽ የሳቅ መመሪያ የአያሌዎች ትኩረት አልተነፈጋትም። በኒውዮርክ የሚታተመው ‹‹ሳይንስ ዳይጀስት›› እንዳመለከተው፤ በዚያው በዩናይትድ ስቴትስ ሚዞሪ በተባለው ክፍለ ግዛት ለሚገኙ እሥረኞች ‹‹አንድ ቀን ይሳቁ›› የተሰኘ ፕሮግራም ወጥቶ ያው ትፍሥሕታዊ ቅስቀሳ ለሥነ ልቡናዊ ትድግና ያደረገው አስዋጽኦ የሚናቅ አልሆነም። በተጨማሪም በካሊፎርኒያ በተቋቋመው የጡረታ ስፍራዎች የተሞከረው ተግባር ማለፊያ ውጤት ማሰገኘቱን ዘጋብያን አረጋግጠዋል።

በእነዚያው የጡረተኛ አምባዎች አዝናኝና አስቂኝ ወጎች እንዲነበቡ፤ ፊልሞች እንዲታዩ፤ ኮሚኮች በውን በመድረክ እንዲቀርቡ፤ ያን አስቂኝ ተውኔታቸውን፤ ጨዋታቸውን ለትርዒት እንዲያበቁ ተደርጓል «ትፍሥሕታዊ በረከት፤ ትፍሥሕታዊ ረድኤት፤…›› ሲሉ የሥነ ልቡና ማዕምራን ያወጡት ይህ ዕቅድ በዘመነ ሕይወት መገባደጃ ላይ የሚገኙትን አዛውንቶች እንደሚጠቅም ሽበት እንደሚያለመልም፤ መንፈስ እንደሚያድስ፤ ብርታት እንደሚለግስ ጠበብት አስምረውበታል። ነምሳዊው የሥነ-ልቡና ተመራማሪ ኢርኖ ጋትሰን ሆእል እንዳሉት ‹‹የሽማግሌዎችንና የባልቴቶችን መንፈስ የሚያበለፅግ ትፍሥሕት ነው። ይህ ስለተባለ ግን ለወጣቱ አይጠቅምም ማለት አይደለም። ይበልጡን በእድሜ ግፊት ሳቢያ በቃን፤ አለቀልን እያሉ ለሚያዝኑ የመንፈስ ጉስቁላን

ትፍሥሕታዊው መድኅን ልዩ ትርጓሜ ይዞ ይገኛል።››

ከዘጠኝ መቶ ያላነሱ ጉባኤተኞች የተሳተፉበትን በቦስተን፤ ማሳቹሴትን የተካሄደውን ‹‹የታላቅ ሳቅ›› ስብሰባ አስመልክተው የዘገቡ ብዕረኞች እንደጠቀሱት፤ በዚያው የውይይት አዳራሽ ‹‹ፍቅርና ሳቅ የሚጫወቱትን የፈዋሽነት ሚና›› በመግለጽ ስምንት በሰሎች በየተራ እየተነሱ ምሁራዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዘጋብያን እንዳሰፈሩት ‹‹ትፍሥሕት ምንድን ነው? እያሉ በምርምር ርቀው የማይጓዙበትን መንገድ ተወት በማድረግ ትፍሥሕት በሥነ ልቡናውም ሆነ በሥነ ሕይወቱ ዘርፍ ፍጡነ ረድኤት ሊሆን የሚበቃበትን ብልኃት ለማጥናት ነው የዘመኑ ሊቃውንት የመረጡት።

ጉዳዩን በቅርብ የተከታተሉ የማህበራዊ ጉዳይ ተመልካቾችና የሥነ ልቡናና የሥነ ሕይወት ተጠባቢዎች እንደጠቆሙት ትፍሥሕትን እንደ ተፈጥሯዊ ፈዋሽ ኃይል በመቁጠር በአውሮፓ ያሉ አንዳንድ የግብረ ሠናይ ተቋማት ቃለ ነቢብ በገቢር የሚተረጎምበትን ዘዴ በመቀየስ ላይ ናቸው። አሜሪካውያን ሊቃውንት ግን ቀደም ብለው ነው የጀመሩት። በየዓመቱ አዳዲስ ‹‹ተቋማተ ትፍሥሕት›› ‹‹ማኅበራተ ትፍሥሕት›› መሠረታቸውን ሲጥሉ ይታያሉ። ለምሳሌም ‹‹የሳቅ ነርሶች›› የተሰኘው ማኅበር ይጠቀሳል። ‹‹ተጠንቀቅ ! ሳቅ በሽታህን ይገድላል!››

በሚለው መርሕ ‹‹ትፍሥሕታዊ በረከት-ለጤንነት›› ሚውልበትን ብልኃት ይሻሉ። በተግባር እንዲተረጎም ያደርጋሉ።

‹‹የትፍሥሕት ፕሮዤ›› ሲሉ የአንድ የተራድኦ ድርጅት የበላይ ሹም የሆኑት ዶክተር ዦየል ጉድማን የመሠረቱት ዕድርም የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። በሥነ-ልቡና ምርምር የተራቀቁት ዶክተር ጉድማን ለየግለሰቡ የበተኑትን ዘዋሪ መጠይቅ ተመርኩዘው አንድ የፍተሻ ሰነድ አቅርበው ነበር።

‹‹ኸረ ለመሆኑ ምን የሚያስቅ ነገር አለ?›› ሲሉ ጆሴፍ ኤፕሽታይን ወረቀት ያስያዙት ቃልም ይጠቀሳል። ኤፕሽታይን እንዳሰፈሩት አንዱ ከትከት ብሎ የሚስቅበትን ትርዒት ሌላው በፈገግታ ብቻ ያልፈዋል። ይኸኛው ፈገግ የሚልበትን ያኛው ዝም

ይሰኝበታል። እንዲያውም ‹‹ ምን የሚያስቅ ነገር አለ?›› ብለው የሳቁትን የሚቆጡ ደስታ እርሙዎች ጥቂት እንዳይደሉ ሳይገልጹ አላለፉም። ጥርስን በእህል ወፍጮነቱ ብቻ ለማወቅ የሚቃጡ እንዳሉ ሳንገነዘብ አልቀረንም።

የኤፕሽታይንን አባባል እንደዋዛ ያልተመለከቱ ፈታሾች እንዳሰመሩበት ትፍሥሕትን ለመተንተን ‹‹አዳጋች›› የሚሆነው ለዚህ ነው። በዴኒስ ሜክ ካርድ የተጻፈው እንደሚነበበው ደግሞ ‹‹የትፍሥሕትን ምሥጢር ለመተንተን እንቸገር እንጂ ያለውን ከሌለው ለመለየት እጅግም አቀበት አይሆንብንም። ጨዋታ የማይወድ ቀልድን በቁም ነገር ማጣፈጫነት የማይወስድ፤ ስልቹና ዝምታን የሚያበዛ ሰው ትፍሥሕት አልባ እንደሆነ እናውቃለን። ለምን እንዲህ ሆነ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አናገኝም። እንዴት ቢሆን ይደሰታል? ለተሰኘው ጥያቄ ግን በጥቂቱ ረብ ያለው ምላሽ እናገኝ ይሆናል። ምናልባት የሚያስቅ በማውራትና በማሳየት ደስተኛ ሊሆን ይችላል። ግና ዳሩ አብዛኛው ሰው የሚስቅበት ጉዳይ እርሱ የሚያዝንበት ሆኖ የሚገኝ ሰው አለና በጥቅሉ እንዲህ ነው ለማለት አንደፍርም። ብዙኃን በሚያዝኑበት አያሌዎች በሚሳቀቁበት ድርጊት የሚስቅ፤ የሚፈነድቅ የሰው ዓይነት አለ። በግብረ ሁከት፤ በግብረ ሐኬት የሚደሰት፤የሚዘፍን ሰው አለ። እንዲያ ያለ ልበ ደንጊያ፤ጨካኝ ግን ምንም የሚደሰትበት ነገር ባይጠፋ በስሜተ ትፍሥሕት ያጌጠ ነው ማለት አንችልም። «ስለምን? ስሜተ ትፍሥሕት ብለን፤ ዘራኤ ትፍሥሕት ብለን የምንወያየው በሰብዓዊ ፍጡር አኳያ ነውና!!›› ይላል። በርግጥም በድሽቀት ምስክርነት አታሞ መደለቅ፤ በውድቀት እማኝነት መፈንደቅ ሰብአዊ ባህርይ የሚታበት ድርጊት ነው ማለት ፈጽሞ አይቻልም።

ጨዋታን ፤ቀልድን ፤ …የማይወድ ሰው ትፍሥሕት አልባ መሆኑን ያስረዱት ተጠባቢ በአንፃሩ ደግሞ ያ በአነጋገሩ ለዛ የሚወደደው በጨዋታው፤ በቀልዱ በአቀራረብ ወዙ የተፈቀደው ወይም እርሱ ራሱ እንኳ ‹‹ዘራኤ ትፍሥሕት›› ለመባል አቅም ቢያንሰው የሰምቶና አይቶ፤ መደሰትን የመሳቅን ጸጋ የተላበሰ ግለሰብ በልዩ ብልኃቱ ጉረኞችን ሲያጋልጥ፤ እውነቱን ሲያገላልጥ፤ ሞገድን ሲያጠፋ፤ መውደድን ሲያስፋፋ ነው የሚገኘው።

ስንፈትን፣ ድክመትን በዘዴ ይጠቁማል አዝናንቶ አስቆ፣ ይተቻል፤ ያመሰግናል፣ ይነቅፋል ሁሉንም በብልኃት ይፈጽማል። ተዋናይቷ ዶሮቲ ሦስት ጊዜ የራሷን ሕይወት ለማጥፋት ሞክራ ሳይሳካ ለውጪ ነፍስ ጥቂት ትንፋሽ ጉዳይ ነው የተመለሰችው። እናም ታዲያ እንዲያ በነበረበት ወቅት ታዋቂው ዘራኤ ትፍሥሕት ቬንችሉ ያሉትን ጸሐፍት በምሳሌነት አስፍረውታል። ይኸውም ‹‹ዶሮቲ! እንዲህ የቀጠልሽ እንደሆን በጠና ትታመሚያለሽና አስቢበት…›› ያሉትን ነው።

እዚህ በሀገራችን ዘራዕያነ ትፍሥሕት መኖራቸውን እናውቃለን። ጥንት የነበሩ፣ ዛሬም ያሉ። ለምሳሌ ነጋድ እራስ ተሰማ እሸቴን ብንወስድ፤ ቀኑን ሙሉ በዚያው ሰም በለበሰ፤ ወርቅ በተንተራሰ ቅኔያቸው በማለፊያ ዘይቤያቸው ሲያጫውቱ ቢውሉ የማይሰለቹ፣ የተቆጣ የሚያበርዱ፣ የተጣላ የሚያዋድዱ እንደነበሩ ይነገራል። በይድነቃቸው ተሰማ ስለ ‹‹ የአራዳ ልጅ›› ትዝታ በሦስት በአራት ተከታታይ ዝግጅት በአንድ ወቅት ድሮ በእሑዱ የራዲዮ ፕሮግራም የተላለፈውን ምልልስ ብንጠቅስ የተገባ ይሆናል። ‹‹ ይደገምልን›› ያለ እንደበረከተ እናስተውላለን። ማን ሰልችቶ? ቀደም ባለው ጊዜም እነ ማኅተመ ወርቅ እሸቴና ብዙዎች ሌሎችም በስሜተ ትፍሥሕት የተሞሉ እንደነበሩ ይነገራል። ዛሬም በቴሌቪዥንና በራዲዮ፣ ቀልድ የሚያቀርቡ በጥቂቱ መኖራቸውን አይተናል ሰምተናል።

በአብያተ ተውኔት ያሉ አንዳንድ ከያንያንም ይጠቀሳሉ። በሙዚቃውም እንዲሁ ነው። በጭራ-ግርፍ ቀኑን ሙሉ ያንኑ ግጥም፤ ያንኑ ዜማ እያመላለሰ ሲቀኝና ሲዘፍን ቢውል የማይሰለች ድምጻዊ አለ። እንደጣፈጠ በደስታ እንደተደመጠ የሚውል።

‹‹ትፍሥሕት-- ስሜተ ትፍሥሕት›› ሲባል ደስታ፣ የደስታ ስሜት ብለን እንውሰደው እና መዝገበ ቃላት አገላብጠው ቢያዩ ይኸንኑ ይረዳሉ። የደስታን ምንነት አውቀናል። ሥርፀቱን ክስተቱን ወቅቱን…መርምረው ያስታወቁ ማዕምራን ገና ባይገኙም። ‹‹ዘራዕያነ ትፍሥሕት›› ለመሆንም መሥፈርቱን ለመቀመር የቻሉ የሉም ትፍሥሕት ደምሳሴ ደዌ፤ (በሽታ አጥፊ ፈዋሴ ሥነ-ልቡና) የሥነ-ልቡና ፈዋሽ መሆኑን ሳይረጋገጥ አልቀረም። ነገር ግን እንዴት ነው የሚሆነው? በሳይንሳዊ ብልኃት እንደ መድኃኒት በሐኪም እየታዘዘ ሊሠራበት የሚችልበት አይመስልም። ‹‹ትፍሥሕት›› የማይመረመር በእጅጉም የረቀቀ ምሥጢር ሆኖ ይቆያል።

ስሜተ ትፍሥሕት

የሽማግሌዎችንና የባልቴቶችን መንፈስ

የሚያበለፅግ ትፍሥሕት ነው። ይህ ስለተባለ ግን ለወጣቱ አይጠቅምም

ማለት አይደለም። ይበልጡን በእድሜ ግፊት ሳቢያ በቃን፤

አለቀልን እያሉ ለሚያዝኑ የመንፈስ ጉስቁላን

ትፍሥሕታዊው መድኅን ልዩ ትርጓሜ ይዞ

ይገኛል።››

'’

፴፱ 39

Page 22: ቁጥር 166 የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ዋጋ 5:75 በፕሮጀክቶች መዘግየት …በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ፕሮፌሰር

ስፖርት 40

አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም

ቦጋለ አበበ

እንደ መነሻከሃያ ዓመታት በፊት ስለነበረው የአገራችን እግር ኳስ

የሚያወጉ ሰዎች አሁን ላይ ኳሱ እንደወደቀና ላዩ ላይ የሚፈሰውን ገንዘብ እንደበዛ ይናገራሉ። ከሃያ ዓመታት በፊት የአንድ ተጫዋች ትልቁ ደመወዝ ቀይ ወጥ መብላትና ሻወር መውሰድ እንደነበር ታሪክ ሰንዶታል። ዘመነኛው እግር ኳስ ከየትኛውም መስክ በበለጠ በወር በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ የሚታፈስበት ሆኖ እንዳረፈው በቁጭት የሚናገሩ ተቆርቋሪዎች ጥቂት አይደሉም። ይህ ቁጭታቸው ግን በተጫዋቾች ዘንድ ከቅናት የመነጨ ተደርጎ ሲቆጠር ይታያል። የቁጭታቸው እውነታ ግን እግር ኳሱ ላይ አንድ ነገር ጠብ ሳይል እንዲሁ በከንቱ ወጪው ጣሪያ በመንካቱ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያጠናክሩትም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች በተለይም የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊዎች የሚያወጡት ገንዘብ ቅጥ ያጣ ስለመሆኑ አያጠራጥርም። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የተጫዋቾች ደመወዝ ዓመታዊ ወጪ መጠን በሚያስደነግጥ መልኩ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱ ለማንም የተደበቀ አይደለም።

ማሳያየኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2010 የሂሳብ ሪፖርት

አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ኢትዮጵያ ቡና ለተጫዋቾች የሚያወጣው የገንዘብ መጠን በአራት ዓመት ልዩነት ውስጥ ከብር 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ወደ 30 ነጥብ 244 ሚሊዮን ብር ንሯል። ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና ዓመታዊ በጀቱን መሙላት ዳገት እየሆነበት መምጣቱን በይፋ ማሳወቅ ከጀመረም ሰንብቷል። የገንዘብ ጉዳይ አሳስቦት የማያውቀው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቢሆን ገቢና ወጪው እኩል መራመድ እየተሳነው ኪሱ እየሳሳ ስለመምጣቱ የአደባባይ ወሬ ከሆነ ቆይቷል።

ከፍተኛ የደጋፊ መሰረት ያላቸው ሁለቱ የአገራችን ታላላቅ ክለቦች ለአብነት ያህል ተነሱ እንጂ ጣሪያ የነካ የደመወዝ ክፍያ በመፈፀም የሚታወቁት በርካታ ናቸው። በውድድር ዓመቱ ከአንድ እስከ አስር ባለው ደረጃ ውስጥ የተቀመጡ የከተማ ክለቦች የፋይናንስ ከፍታው ሰለባ እንደሚሆኑም ጥርጥር የለውም።

የወጪ ዕድገቱ በዚሁ ከቀጠለ በርከት ያሉት ክለቦች በውድድሩ ላይ የመቆየት ዕድላቸው አደጋ ውስጥ እንደሚገባ ከወዲሁ ምልክቶች እየታዩ ነው። በየዓመቱ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ የተጫዋቾች ክፍያና አጠቃላይ የበጀት ጫና ምክንያት አደጋ ውስጥ የገቡ ክለቦች ቁጥር አንድና ሁለት እንደማይሆን ግልፅ ነው። መንግሥት ለእግር ኳሱ የሚመድበው በጀትና የተጫዋቾች ክፍያ ነባራዊውን የአገር ኢኮኖሚ ያላገናዘበ፣ የክለቦች የፋይናንስ

ከፍተኛ ክፍያ ገደል አፋፍ ላይ ያቆመው ሊግ

• አንድ ክለብ ለተጫዋቾች የሚያወጣው የገንዘብ መጠን በ4 ዓመት ውስጥ ከ3 ነጥብ 1ሚሊዮን ወደ 30 ነጥብ 244 ሚሊዮን ብር ንሯል፤

• የሊጉ ተወዳዳሪዎች በየዓመቱ ከ30 እስከ 80 ሚሊዮን ብር ያንቀሳቅሳሉ፤

• በአማካኝ ከ50 እስከ 100 ሺ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ከአንዱ ክለብ ወደ ሌላኛው ለዝውውር ይከፍላሉ፤

• በዓመት በአማካይ 20 ሚሊዮን ብር ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ይወጣል፤ • የሊጉ አሸናፊ ለሚሆን ክለብ 150 ሺ ብር ብቻ ሽልማት ይሰጠዋል፤

የተለዩ አይደሉም። የወጪ ዕድገት ጣሪያው እንዳደጉት አገራት ሊጎች

ክለቦቻችን በነዳጅ ገንዘብ ኪሳቸው ባበጠ የአረብ ባለሀብቶች ካልተደገፈ በስተቀር ቀና ብለው የሚያዩትና ውሉን የሚጨብጡት ዓይነት አይደለም። የፋይናንስ ከፍታው የፕሪሚየር ሊጉን ክለቦች አንደርድሮ ከገደል አፋፍ ላይ አድርሷቸዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም። የገቢ መንገዶች እየቀነሱ ወጪያቸውም ከዚህ በኋላ ይበልጥ እየተመነደገ እንደሚሄድ ከሁኔታዎች ተነስቶ ቢተነበይ ደግሞ ችግሩ ይበልጥ ጥርስ ያወጣ ይመስላል። የፕሪምየር ሊጉ ከከተማ ከተማ ተዟዙሮ የመጫወት መርሐግብር የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መልክዓምድራዊ አቀማመጥ የተራራቁ ያደርጋቸዋል።

ከሁለት ዓመት በፊት አንድ የአዲስ አበባ ክለብ ለሊጉ ውድድር አንድም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል አይጓዝም ነበር። ዘንድሮ ግን አራት ጊዜ መጓዝ ግድ ይለዋል። ባለፉት ሦስት የውድድር ዘመናት በየዓመቱ አንዳንድ የአዲስ አበባ ክለቦች ከሊጉ መውጣታቸውን ተከትሎ (አዲስ አበባ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ደደቢት) ከአምና እና ከካቻምና ይልቅ የአዲስ አበባ ክለቦች ለበለጠ ጊዜያት ወደ ክልሎች እየተጓዙ ለመጫወት ተገድደዋል።

ክለቦቹ ብዙ በተጓዙ ቁጥር ወጪያቸው እየጨመረ መሄዱን ማስተዋል ይቻላል። በቀጣይ ዓመታትም ፕሪሚየር ሊጉን የሚቀላቀሉ ሦስት አዳዲስ ክለቦች ከየትኛውም ክልልና ከተማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ለብዙሃኑ የክልል ክለቦች ችግሩ ይበልጥ ብርቱ እንዲሆን ያደርገዋል።

እነዚህ ክለቦች የህዝብ ሀብት የሚፈስባቸው እንደመሆናቸው «ሚሊየኖችን ዘርተው ምን አጨዱ?» ብለን ብንጠይቅ መልሱ በቀላሉ ምንም ይሆናል። አሳዛኙ ነገር በእግር ኳሱ ይህን ያህል ገንዘብ እየተረጨ ከፋይናንስ ዕድገቱ ጋር ኳሱ አብሮ መራመድ ይቅርና በግማሽ መንገድ እንኳን ሊከተለው አቅሙ አለመፍቀዱ ነው።

ከአስር ጨዋታ ዘጠኙ አንድ ለዜሮ በሆነ ውጤት በሚጠናቀቅበት አሰልቺ ሊግ ሆኗል። የስፖርት ቤተሰቡ ለመዝናናት ካምቦሎጆ ገብቶ ፀያፍ ስድብ ሰምቶ ከመመለስ የዘለለ ያገኘው ነገር የለም። ይህ ሁሉ የገንዘብ ክምር ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ አገራት ከአስራ ስድስት ወደ ሃያ አራት አድጎ እንኳን ተወዳጁ መድረክ ጋር ሊያደርሰው የሚችል አቅም አልፈጠረለትም። የዘወትር ጩኸት ለሆነው የታዳጊ ወጣቶችና ተተኪዎች ላይ ገንዘቡ ባክኖም ቢሆን እሰየው ነበር። ከእነዚህ ሁሉ አንዱ እንኳን ተሳክቶ ቢሆን የስፖርት ቤተሰቡ አሜን ብሎ በተቀበለም ነበር።

ምክረ ሃሳብ ገቢያቸው ከወጪያቸው በእጅጉ የላቀ በሆነበት የአውሮፓ

አገራት ሊጎች ውስጥ አንድ ክለብ ገንዘብ ስላለው ብቻ የፈለገውን መዥረጥ አድርጎ አውጥቶ ያሻውን ተጫዋች ሊገዛ አይችልም። እነርሱ የፈረጠመ የገንዘብ አቅም ያላቸውን ለመቆጣጠርና ጤናማ የገበያ ስርዓት እንዲኖር ለማስቻል (financial fair play)የሚሉት ጠንካራ ህግ አላቸው። ይህ አሠራር ከእኛ ሀገር ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ ተግባራዊ ቢደረግ ችግሩን ለመቆጣጠር ያስችላል።

ከድሃ አገርና ህዝብ የሚገኝ ገንዘብ የጀርባ አጥንቱ ለሆነው የአገራችን እግር ኳስ ግን የፋይናንስ ስርዓትን ለመቆጣጠር የሚያስችል በልካችን የተሰፋ ጠንካራ የህግ አንቀፅ ማስቀመጥ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

መንግሥት ፊፋን በማያስቆጣ መልኩ ለዚህ ችግር መፍትሔ ካላበጀ እንዲህ በቀላሉ እግር ኳሱን መታደግ የሚቻል ባለመሆኑ መፍትሔው ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይኖርበታል። ከዚህ ጎን ለጎን እግር ኳሱን አንቆ የያዘው የወሮበላ ቡድኖች ሰንሰለት እስካልተበጠሰ ድረስ የቱንም ያህል የእግር ኳስ አመራር ቢቀያየር ለውጥ እንደማይመጣ ማረጋገጥ ይቻላል።

ስርዓት የሌለበት፤ ዘመናዊ የእግር ኳስ አመራርና አደረጃጀት የሌለበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ግን ሊጉ ቀጥሏል። ብዙዎቹ ክለቦች ቋሚ ገቢ የሌላቸው ሲሆኑ ከከተማ አስተዳደሮችና በመንግሥት ተቋማት በቀጥታ በጀት የሚመደብላቸው ናቸው። የተጫዋቾች ዝውውርና ሌሎች ክፍያዎቻቸውም ከዚሁ በጀት ላይ የሚታሰብ ሲሆን የሊጉ ተወዳዳሪዎች በየዓመቱ ከ30 እስከ 80 ሚሊዮን ብር የሚያንቀሳቅሱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

የተጫዋቾች የዝውውር ገንዘብ በየዓመቱ እየናረና እያደገ መምጣቱን ተከትሎም በአማካኝ ከ50 እስከ 100 ሺ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ከአንዱ ክለብ ወደ ሌላኛው እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። ዘንድሮ እንኳን በተጫዋቾች የዝውውር መስኮቱ አማካኝ ገንዘብ 100 ሺ ብር ሲሆን አነስተኛው 25 ሺ ብር ነው። አንድ ክለብ በዓመቱ በሚያስፈርማቸውና ውላቸውን የሚያድስላቸው የውጭና የአገር ውስጥ ተጫዋቾች ከአስር እስከ አስራ ሁለት ቢገመቱ፤ ሃያ ሚሊዮን ብር በተጫዋቾች ዝውውር ብቻ እንደሚያወጣ መገንዘብ ይቻላል። ይህም ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ፈተና የአብዛኛዎቹን ክለቦች እንዲሁም የፕሪሚየር ሊጉን ግብዓተ መሬት እያፋጠነው ይገኛል።

የተደቀነው አደጋ

ትናንት እንደ ቀላል በመቶ ሺዎች ለተጫዋቾች ደመወዝ ከፋይ የነበሩና ለገበያው ጣሪያ መንካት ዋና ተዋናይ የሆኑት ክለቦች ዛሬ ላይ ካዝናቸው ተራቁቷል። ለወሳኝ ተጫዋቾቻቸው በጊዜው የሚከፍሉት አጥተው ከዋክብቶቻቸው የተሻለ አቅም ወዳለው ክለብ ሲኮበልሉ እጃቸውን አጣጥፈው መመልከት ዕጣ ፋንታቸው ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ከዓመትና ሁለት ዓመት በፊት ከፍተኛውን የተጫዋቾች ደመወዝ ከፋይ ከነበረው ከደደቢት የበለጠ ማሳያ የለም።

ደደቢት በዚህ ማዕበል ክፉኛ ከተመታ ወዲህ መቀመጫውን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ቀይሯል። ከፍተኛውን የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያም ሃያ አምስት ሺ ብር ለማድረግ ተገዷል። በዚህም ሳይበቃ የተሻለ ውጤታማ የሆነው የሴቶች ቡድኑን ለማፍረስ ሲወስን ሁለት ጊዜ አላሰበበትም። ትንሽ የተባለውን የደመወዝ ጣሪያም በወቅቱ መክፈል ተስኖት እየተንገዳገደ የወንዶቹም ቡድን እንደ ሴቶቹ ተመሳሳይ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው አንድ ሐሙስ ቀርቶታል። ለዚህም ማሳያው በሊጉ አጋማሽ ላይ የሰበሰበው የአንድ ዕጅ ጣቶችን ቁጥር የማይሞላ ነጥብ ነው። ደደቢት በቀጣዩ ዓመት በሊጉ ለመቆየት ተዓምር መፈጠር ይኖርበታል። በሊጉ መቆየት ካልቻለ ደግሞ የሚመጣውን መዘዝ መገመት ቀላል ነው። ምክንያቱም በአገራችን እግር ኳስ እንኳን በፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባ ክለብ ቀርቶ ጠንካራ የፋይናንስ አቅምና ታሪክ ያላቸው ክለቦች ከሊጉ ወርደው ለመውጣት ከመታተር ይልቅ ለመፍረስ ቅርብ ሆነዋል። ለዚህም ኢትዮጵያ

ንግድ ባንክና ሙገር ሁነኛ ማሳያ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

የክለቦች ቅጥ ያጣ የገንዘብ አወጣጥ የኋላ ኋላ ራሳቸውን ጠልፎ እንደሚጥላቸው ማሳያ ደደቢት ብቻ አይደለም። የአምናው ቻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር የዚሁ ችግር ተመሳሳይ ሰለባ ሆኗል። ዋንጫውን ባነሳ ማግስት አሁን እየገጠመው የሚገኘውን የፋይናንስ ቀውስ መመልከት ይቻላል። ጅማ አባ ጅፋር አምና በጉብዝናው ወራት የውጭ ተጫዋቾችን ጭምር ረብጣ ገንዘብ አውጥቶ በመግዛት በሊጉ ማማ ላይ ተቀምጦ እንደነበር አይዘነጋም። ይህም የአንድ ተጫዋች የወር ደመወዝ እንኳን መሸፈን የማይችል የመቶ ሃምሳ ሺ ብር ሽልማት አስገኘለት።

ዘንድሮ ግን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሙሉ ቡድኑን እንኳን ይዞ ባህር መሻገር ተሳነው። ለአሰልጣኝና ተጫዋቾች ከሁለት ወር በላይ ደመወዝ መክፈል አቅቶትም ውዝግብ ውስጥ እንደሰነበተ ይታወሳል። ቀጣይ ጉዞውም እንደ አምናው ዋንጫ ለመሳም ሳይሆን ላለመውረድ እንደሚሆን አሁን ካለበት ቁመና ተነስቶ መናገር ይቻላል። ሌሎቹም ክለቦች ከዚህ

አሳዛኙ ነገር በእግር ኳሱ ይህን ያህል ገንዘብ እየተረጨ

ከፋይናንስ ዕድገቱ ጋር ኳሱ አብሮ መራመድ ይቅርና በግማሽ መንገድ እንኳን ሊከተለው አቅሙ አለመፍቀዱ ነው።

ስፖርት፵

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ