Habeshawi Kana 001

24
ግስት አቅም ለመገንባት መሆኑን ለፕሮ ጀክቱ መሳካት እገዛ እያደረገ ያለው የተ ባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ገልጿል። ከደቡብ ሱዳን ህ ዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ማዕከል የ ተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ዕድሜ ው ለስራ ከደረሰ የሀገሪቱ ህዝብ መካከል 12 በመቶው ብቻ ተከፋይ ሰራተኛ ነው። 8.26 ሚሊዮን ከሚገመተው የደቡብ ሱ ዳን ህዝብ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ዕድሜያ ቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። “ረጅም ዓመታትን የፈጀው ጦርነት በ መንግስት ስራ እና ትምህርት ላይ ከፍተ ኛ ተጽእኖ በማሳረፉ በስራ ክህሎት እና ልምድ ላይ ትልቅ ክፍተት እንዲፈጠር ሆ ኗል” ይላሉ ጁባ በሚገኘው ዩኤንዲፒ ቢ ሮ ውስት በኮሚኒዩኬሽን ኦፊሰርነት የሚ ያገልግሉት ናታሊ ዊልኪንስ ለሐበሻዊ ቃ ና በላኩት የኢ-ሜይል ምላሻቸው። “ይ ህ ኢንሼቲቭ የደቡብ ሱዳንን ሲቪል ሰ ርቪስ አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና ይ ኖረዋል።” በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት ኢትዮጵያ ን ጨምሮ ከጎረቤት ሀገሮች የሚመጡ ባ ለሙያዎች ለደቡብ ሱዳንውያን የስራ ላ ይ ስልጠና እንዲሰጧቸው ይጠበቃል። ፕሮጀክቱ የባለሙያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋ ል ብሎ ከመረጣቸው ቁልፍ ዘርፎች መ ካከል የገንዘብ፣ የሰው ኃይል እና የህዝብ አስተዳደር እንደዚሁም ኢንፎርሜሽን እ ና ኮሚዩኔኬሽን ዘርፎች ይገኙበታል። በ ንግድ እና ኢንዱስትሪ እድገት ዙሪያ የሚ ሰሩ ኤክስፐርቶች፣ ጂኦሎጂስቶች እና ላ ብራቶሪ ቴክኒሽያኖችም በፕሮጀክቱ የሚ ፈለጉ ባለሙያዎች ናቸው። በፕሮጀክቱ አማካኝነት ወደ ደቡብ ሱ ዳን ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ኢት ዮጵያውያን የመንግስትን ሰራተኞችን የ መመልመል ሂደት መጀመሩን የዩኤንዲ ፒዋ ናታሊ ይገልጻሉ። በጁነዲን ሳዶ የ ሚመራው የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ከደቡብ ሱዳን አቻው የሰራተ ኞች እና የህዝብ አገልግሎት ሚኒስቴር ጋ ር በመሆን የምልመላ እና ቅጥር ሂደቱን ያከናውናሉ። እንደ ናታሊ አባባል ከሆነ በአሁኑ ወቅት የምልምላው ሂደት ወደመ ጠናቀቁ ተቃርቧል። “[የሰራተኞቹ] የመጨረሻ ምርጫ ከሶሰ ት ሳምንት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበ ቃል። እነዚህ ሰራተኞች በኢትዮጵያ መን ግስት ፔሮል ውስጥ የሚቆዩ ናቸው። ወ ደ ደቡብ ሱዳን የመምጣታቸው አንድም ታ ለአዲሲቱ ሀገር ባለው የገንዝብ እና የ ቴክኒካዊ ድጋፍ ይገለጻል”ይላሉ ናታሊ። በኢትዮጵያ በኩል ያለው የሰራተኞች ምደባ ባይጠናቀቅም በፕሮጀክቱ የተመ ለመለው የመጀመሪያው የባለሙያዎች ቡድን ግን ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ጁባ ገብቷል። ከኬንያ የመጣው ይህ ቡ ድን 42 አባላትን የያዘ ሲሆን ሃያዎቹ የ ጤና መኮንኖች እና ነርሶች ናቸው። ቀሪ ዎቹ የቡድኑ አባላት በአስተዳር እና ቴክ ኒክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ናቸው። ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ አንደኛ ዓመት ቁጥር 001 ቃና ነጻነቷን ለማወጅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ የቀ ራት ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ን ለመንግስት ስራ ልትቀጥር ነው። የሰራተኞቹ ቅጥር የምስራቅ አፍሪካ በየነ መ ንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የቀጠና ትብብር አካል ነው። በዚሁ የትብብር “ኢንሼቲቭ” ፕ ሮጀክት አማካኝነትም የኢጋድ አባል ሀገራት ከሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ የተው ጣጡ 200 የመንግስት ሰራተኞች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ኮሚሽኖች እና በክልሎች ተ መድበው እንዲሰሩ ይደረጋል። ሰራተኞቹ ሚቀጠሩት ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ያለበትን የደቡብ ሱዳን መን ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያንን ለመንግስት ስራ ልትቀጥር ነው በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና ሳሚ-ዩጋንዳ፣ ተስፋይ-ዛንዚባር አስተያየት፣ ጸሁፍ፣ ጥቆማ… በሐበሻዊ ቃና የኢሜይል አድራሻ [email protected] አድርሱን። +256-778-366936 ይደውሉልን። ገጽ 11- 12

description

First Edition

Transcript of Habeshawi Kana 001

Page 1: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 1

ግስት አቅም ለመገንባት መሆኑን ለፕሮጀክቱ መሳካት እገዛ እያደረገ ያለው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ገልጿል። ከደቡብ ሱዳን ህዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ዕድሜው ለስራ ከደረሰ የሀገሪቱ ህዝብ መካከል 12 በመቶው ብቻ ተከፋይ ሰራተኛ ነው። 8.26 ሚሊዮን ከሚገመተው የደቡብ ሱዳን ህዝብ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። “ረጅም ዓመታትን የፈጀው ጦርነት በ

መንግስት ስራ እና ትምህርት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳረፉ በስራ ክህሎት እና ልምድ ላይ ትልቅ ክፍተት እንዲፈጠር ሆኗል” ይላሉ ጁባ በሚገኘው ዩኤንዲፒ ቢ

ሮ ውስት በኮሚኒዩኬሽን ኦፊሰርነት የሚያገልግሉት ናታሊ ዊልኪንስ ለሐበሻዊ ቃና በላኩት የኢ-ሜይል ምላሻቸው። “ይህ ኢንሼቲቭ የደቡብ ሱዳንን ሲቪል ሰርቪስ አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።” በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት ኢትዮጵያ

ን ጨምሮ ከጎረቤት ሀገሮች የሚመጡ ባለሙያዎች ለደቡብ ሱዳንውያን የስራ ላይ ስልጠና እንዲሰጧቸው ይጠበቃል። ፕሮጀክቱ የባለሙያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሎ ከመረጣቸው ቁልፍ ዘርፎች መካከል የገንዘብ፣ የሰው ኃይል እና የህዝብ አስተዳደር እንደዚሁም ኢንፎርሜሽን እና ኮሚዩኔኬሽን ዘርፎች ይገኙበታል። በንግድ እና ኢንዱስትሪ እድገት ዙሪያ የሚ

ሰሩ ኤክስፐርቶች፣ ጂኦሎጂስቶች እና ላብራቶሪ ቴክኒሽያኖችም በፕሮጀክቱ የሚፈለጉ ባለሙያዎች ናቸው። በፕሮጀክቱ አማካኝነት ወደ ደቡብ ሱ

ዳን ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን የመንግስትን ሰራተኞችን የመመልመል ሂደት መጀመሩን የዩኤንዲፒዋ ናታሊ ይገልጻሉ። በጁነዲን ሳዶ የሚመራው የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ከደቡብ ሱዳን አቻው የሰራተኞች እና የህዝብ አገልግሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የምልመላ እና ቅጥር ሂደቱን ያከናውናሉ። እንደ ናታሊ አባባል ከሆነ በአሁኑ ወቅት የምልምላው ሂደት ወደመጠናቀቁ ተቃርቧል። “[የሰራተኞቹ] የመጨረሻ ምርጫ ከሶሰ

ት ሳምንት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ ሰራተኞች በኢትዮጵያ መንግስት ፔሮል ውስጥ የሚቆዩ ናቸው። ወደ ደቡብ ሱዳን የመምጣታቸው አንድምታ ለአዲሲቱ ሀገር ባለው የገንዝብ እና የቴክኒካዊ ድጋፍ ይገለጻል”ይላሉ ናታሊ። በኢትዮጵያ በኩል ያለው የሰራተኞች

ምደባ ባይጠናቀቅም በፕሮጀክቱ የተመለመለው የመጀመሪያው የባለሙያዎች ቡድን ግን ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ጁባ ገብቷል። ከኬንያ የመጣው ይህ ቡድን 42 አባላትን የያዘ ሲሆን ሃያዎቹ የጤና መኮንኖች እና ነርሶች ናቸው። ቀሪዎቹ የቡድኑ አባላት በአስተዳር እና ቴክኒክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ናቸው።

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድአንደኛ ዓመት ቁጥር 001

ቃናሐበሻዊ

ነጻነቷን ለማወጅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ የቀራት ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመንግስት ስራ ልትቀጥር ነው።የሰራተኞቹ ቅጥር የምስራቅ አፍሪካ በየነ መ

ንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የቀጠና ትብብር አካል ነው። በዚሁ የትብብር “ኢንሼቲቭ” ፕሮጀክት አማካኝነትም የኢጋድ አባል ሀገራት ከሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ የተውጣጡ 200 የመንግስት ሰራተኞች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ኮሚሽኖች እና በክልሎች ተመድበው እንዲሰሩ ይደረጋል። ሰራተኞቹ ሚቀጠሩት ከፍተኛ የሆነ የሰው

ኃይል እጥረት ያለበትን የደቡብ ሱዳን መን

ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያንን ለመንግስት ስራ ልትቀጥር ነው

በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

ሳሚ-ዩጋንዳ፣ ተስፋይ-ዛንዚባር

አስተያየት፣

ጸሁፍ፣ ጥቆማ…

በሐበሻዊ ቃና የኢሜይል አድራሻ

[email protected]

አድርሱን።

በ+256-778-366936

ይደውሉልን።

ገጽ 11- 12

Page 2: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)2 ሀበሻዊ ቃና

ዜና

ቃናሀበሻዊበሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ

የሚታተም ጋዜጣ

ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ዩጋንዳ ካምፓላ

ጋባ ሮድ-ካሳንጋ

ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6

ስልክ +256-778-693669

ከተመሰረተ ስድስት ዓመታት ያስቆጠረው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ ጽህፈት ቤት ከፍቶ የተሟላ ስራ ጀመረ። በኡጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ

ችግሮች ለመፍታት በማሰብ የተቋቋመው ማህበር እስካሁን የራሱ ጽህፈት ቤት አልነበረውም። ማህበረሰቡ ከግንቦት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ግን ካምፓላ ካሳንጋ አካባቢ የራሱን ጽህፈት ቤት ከፍቶ አዳዲስ አባላትን ህጋዊ የአባልነት መታወቂያ መስጠት ጀምሯል፡፡ ከማህበረሰቡ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደ

ሚያመለክተው እስካሁን 150 ያህል አባላት መታወቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 40 ለሚሆኑ ደግሞ እየተዘጋጀላቸው ነው፡፡ ኡጋንዳ ውስጥ በህጋዊነት ስለመኖሩ ማስረጃ የሚያቀርብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለመታወቂያ ዝግጅትና ለመመዝገቢያ ሰባት ሺህ የኡጋንዳ ሽልንግ በመክፈል ማህበረሰቡን መቀላቀል እንደሚችል የማህበረሰቡ የስራ ኃላፊዎች ለሐበሻዊ ቃና ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበሩትን አመራር አባላት በተለያዩ ም

ክንያቶች መዳከም የማህበረሰቡን እንቅስቃሴውን አጓቶት እንደቆየ የማህበረሰቡ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ባንቲሁን ኃይሌ ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት በካምፓላ የደረሰው የቦምብ አደጋ ማህበረሰቡ በአዲስ መንፈስ ተደራጅቶ ለኢትዮጵያውያን ወገኖች አለኝታ መሆን እንዳለበት የማንቂያ ደወል አንደነበር ገልጸዋል። በመሆኑም ፍንዳታውን ተከትሎ በተጠራው ስብሰባ የተጓደሉ የአመራር አባላት ተተክተው እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

ከጤና ቡድን እስከ ማህበረሰብየኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ምስረታ ታሪክ ከኤ

ርትራ ነጻነት በፊት እና በኋላ የተለያየ ታሪክ አለው። ከኤርትራ ነጻነት በፊት ተመስርቶ የነበረ ማህበረሰብ ሁለቱንም ህዝቦች በአንድ ጥላ ስር ያሰባሰበ ነበር። “ያኔ የተቋቋመው ማህበረሰብ በገንዘብም ሆነ በአደረጃጀት ጠንካራ ነበር” ይላሉ የአሁኑ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጉሴ ባልቻ፡፡ ይህ መሰባሰብ ግን ከአንድ ዓመት በላይ መዝለቅ አልቻለም፡፡ “በወቅቱ የነበረው በዘርና በጎሳ የመከፋፈል ችግር ለማህበረሰቡ መፍረስ ምክንያት ነበር” ይላሉ አቶ ንጉሴ፡፡ ይህ ማህበረሰብ ከፈረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ

እ.ኤ.አ በ1996 በኡጋንዳ የሚኖሩ ስደተኞች ማህበረሰብ ተመሰረተ፡፡ ይህም ግን ከቀደመው ማህበረሰብ ጋር በሚመሳሰል ችግር ብዙም ሳይራመድ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመፍረስ በቃ፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ ግን ለዛሬው የኢትዮጵያውያን ማህበረ

ሰብ መገኘት አስተዋጽኦ ያበረከተ ማህበር ተመሰረተ-የኢትዮጵያ የጤና ስፖርት ቡድን፡፡ ይህ የስፖርት ቡድን ሲመሰረት አላማው እየተሰባሰቡ እግር ኳስና ሌሎች የስፖርት ዓይነቶችን ማዘውተር ነበር፡፡“[የተሳታፊዎቹ] ብዛት እያደገ ሲሄድ ግን ለምን ወ

ደ ድርጅት አንለውጠውም የሚለው ሀሳብ መጣልን፡፡ እናም [እ.ኤ.አ] በ2003 ለአብያተክርስቲያናት ድጋፍ ለማድረግ፣ የታመሙትን ለመርዳት እና የሞቱትን ለመቅበር በሰባት የአመራር አባላት ማህበሩ ተቋቋመ” ሲሉ አቶ ንጉሴ እንዴት ማህበሩ አንድ ርምጃ ወደ ፊት እንደተራመደ ያብራራሉ፡፡ማህበሩ በሁለት እግሩ የቆመ ቢመስልም አመራሮ

ቹ ግን በአቅም ማነስ ምክንያት እንዳሰቡት ሊራመድ አልቻለም፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2005

በኡጋንዳ የሚኖሩ 20 ያህል ታዋቂና ተሰሚነት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው የገጠማቸውን ፈተና ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ከመረዳጃ ማህበር የዘለለ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እንዲሚሰረት ጥያቄ የቀረበው። ጥያቄው ተቀባይነት በማግኘቱም ዘጠኝ አባላትን ያካተተ አስተባባሪ ኮሚቴ ተሰየመ፡፡ በዚህ ስብሰባ የተጸነሰው ማህበረሰብ ብዙዎች እ

ንደተመኙት ለወገኖቹ የሚጠበቅበትን ያህል ሊያበረክት አልቻለም፡፡ አሁን በስራ ላይ ያሉት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የስራ ኃላፊዎች በፊት የነበረውን የቅንጅት ማነስን እንደ ምክንያት ያነሳሉ። “ማህበሩ በሶስት የአመራር አባላት ብቻ ነበር የሚንቀሳቀሰው፡፡ በዚህ ላይ በወቅቱ የነበሩት የማህበረሰቡ ሊቀ

መንበር …አልነበሩም፡፡ እሳቸው በድንገት ሀገር [ኡጋንዳን] ለቀው ሲሄዱ ደግሞ ማህበሩ ወደመሞት ተቃረበ” ይላሉ አቶ ንጉሴ፡፡ ይህ ሲባል ግን ማህረሰቡ ምንም አልሰራም ማለት

አይደለም ባይ ናቸው አቶ ንጉሴ፡፡ የኢትዮጵያ ሚሊኒየምን በኡጋንዳ በድምቀት እንዲከበር ማድረጉን፣ በተለያየ ጊዜ በሞት የተለዩ ወገኖችን የቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸሙን፣ ወደ ሀገር ቤት አስከሬናቸው የሚላከውንም በአግባቡ መሸኘቱን በምሳሌነት ያነሳሉ። እንዲህ እንዲህ እያለ ለተጓዘው ማህበረሰብ ባለፈው ዓመት ወርሃ ሐምሌ በኢትዮጵያ ገጠር ምግብ ቤት (ኢትዮጵያን ቪሌጅ) የተከሰተው የቦምብ አደጋ የማንቂያ ደወል ነበር፡፡ ከኢትዮጵያውያን “የእንደራጅ ጥያቄ ያስከተለው” የቦምብ ፍንዳታ ወዲያውኑ አጠቃላይ ስብሰባ ለመጥራትም ምክንያት እንደነበር የማህበረሰቡ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡ በስብሰባውም የተጓደሉ አባላት ተተክተው ማህበረሰቡ በ¬ተደራጀ መልኩ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ማህበረሰብ ለምን?በኡጋንዳ የሚኖሩ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በተለ

ያዩ ምክንያቶች አገራቸውን ጥለው የወጡ ስደተኞች እንደሆኑ ይታወቃል። በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅትም (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ አር) ሆነ በሌሎች የስደተኞችን ጉዳይ በሚከታተሉ ተቋማት በተናጠል የሚደርሱባቸው ችግሮች አሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር በማህበራዊና በኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያት ጥቂት የማይባሉት ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ህመም፣ ከስራ መፈናቀልና ሞት ይጠቀሳሉ፡፡የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ያኔ መጀመሪያ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አላማው እነዚህን ችግሮች በጋራ መፍታት ነው፡፡ አቶ ባንቲሁን እንደሚሉት “ለዓመታት ትንሽ እየሰ

ራ ብዙ የተኛውን” የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ከእንቅልፉ ማንቃት የተፈለገውም ለዚሁ ነው፡፡ እንደ እርሳቸው አባባል በአዲስ መንፈስ ተዋቅሮ ጽህፈት ቤት እስከመክፈት የደረሰው የአሁኑ ማህበረሰብ ረጅም ራዕይ አለው፡፡ ይህንን ለማሳካትም ከዚህ በፊት የነበረው መተዳደሪያ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እየተሻሻለ ነው፡፡ ራስን አስተዋውቆ የአባላቱን ቁጥር በማሳደግ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ ማድረግም የማህበረሰቡ ዓላማ ነው፡፡

የማህበረሰቡ ተግዳሮቶች የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ ሶስት ጊዜ

ተቋቁሞ ሁለት ጊዜ ፈርሷል፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ቢኖርም ህልውናው ፈተና ውስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ማህበረሰቡ አሁን ያለበት ደረጃ አራተኛ

ው ምዕራፍ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ምክንያቱም የአሁኑ ቢያንስ ጽህፈት ቤት መክፈት፣ መታወቂያ ማደልና ከኢትዮጵያውያን ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር መወያየት ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ማህበረሰቡ የተጋረጡበት ፈተናዎች ጥቂት አይደሉም፡፡የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በኡጋንዳ እንደ ብዙዎች

በውጭ ሀገራት እንደሚቋቋሙ ማህበረሰቦች በጥርጣሬ ከመታየት አላመለጠም፡፡ ማህበረሰቡ በቅርቡ ያደረገውን ስብሰባ ተካፍለው ሀሳባቸውን ያካፈሉ የመኖራቸውን ያክል ከዳር ቆመው የማህበረሰቡን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡም አሉ፡፡ በማህበረሰቡ ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ የፖለቲካ ወገንተኝነት ጉዳይ ነው፡፡ የማህበረሰቡ የስራ ኃላፊዎች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም፡፡ እነርሱ እንደሚሉት ማህበረሰቡ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ ዘር እና ሀይማኖት ነጻ የሆነ የኢትዮጵያውያንን ችግሮች ለመፍታትና በተለይም ለስደተኞች ቅድሚያ በመስጠት ለማገልገል የተቋቋመ ነው፡፡ “ከፖለቲካ መሸሽ አይቻልም፡፡ ግን የማንንም ፖ

ለቲካ ፓርቲ ደግፈን ወይም ተቃውመን አንቀሳቀስም” ይላሉ አቶ ንጉሴ “በአንዳንድ የኢትዮጵያውያንን አንድነት በማይፈልጉ ወገኖች በኩል የሚሰራጭ ውዥንብር” ላሉት ትችት ምላሽ ሲሰጡ፡፡ “ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ አናስተናግድም፡፡ ይሁን እንጂ በጋራ የሚያወያየን ጉዳይ ሲኖር እንወያያለን፡፡ ፖለቲካም ከእነዚህ አንዱ ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ለምሳሌ ስደተኞችን የሚጎዳ ጉዳይ ሲኖር ወይም ወደ ሀገራቸው መመለስ ሲፈልጉ ከኤምባሲ ጋር እንነጋገራለን፡፡ በጋራም መፍትሄ እንፈልጋለን፡፡”የበጀት ውስኑነትና የሰው ሀይል እጥረት ማህበረሰ

ቡ አሉብኝ የሚላቸው ችግሮች ናቸው፡፡ የማህበረሰቡ ዋነኛ የገቢ ምንጭ የአባላቱ መዋጮ ሲሆን እያንዳንዱ አባል ሲመዘገብ ከሚከፍለው ሰባት ሺህ ሺልንግ በተጨማሪ ቢያንስ ሁለት ሺህ ሺልንግ ወርሃዊ መዋጮ እንዲከፍል ይጠበቃል፡፡ ይህ ግን የማህበረሰቡ አመራሮች እንደሚሉት ለቢሮም ሆነ ተያያዥ ወጪዎች ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ኡጋንዳ ለስደተኞች ጊዜያዊ ማረፊያ ከመሆኗ ጋ

ር ተያያዞ የሚፈጠረው የሰው ሀይል ውሱንነት እና በቋሚነት ለማገልገል ያለመቻልችግር ለማህበረሰቡ ውጤታማነት የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው ኃላፊዎቹ ያስረዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በኡጋንዳ እነዚህን ተግዳ

ሮቶች መጋፈጥ ቢጠበቅበትም የማህበረሰቡ ኃላፊዎች ግን ከእስካሁኖች የተሻለ ተግባር እናከናውናለን ባይ ናቸው።

የአሜሪካ እና ካናዳ መንግስታት በመልሶ ማስፈር ፕሮግራሞቻቸው የመረጧቸው በኬንያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የሀገራቱ መጓዝ ጀመሩ። ስደተኞችን የመውሰድ ቅድሚያውን የያዘ

ችው ካናዳ ስትሆን የመጀመሪያውን የተጓዦች ቡድን ከሳምንት በፊት ተቀብላለች። አሜሪካም የካናዳን ፈለግ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተከትላለች። ወደ አሜሪካ የሚሄዱት ስደተኞች ሙሉ

ለሙሉ የመጡት በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ከሚገኘው ካኩማ ስደተኞች ጣቢያ ነው። በሁለት አውቶብሶች ተጭነው ከሳምንት በፊት ናይሮቢ የደረሱት ስደተኞች ጊዜያዊ መቆያቸው ወደ ሆነው እና በተለምዶ “ጎል” ተብሎ ወደሚጠራው የዓለም የስደተኞች ድ

ኬንያ ያሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እና ካናዳ እየሄዱ ነው

በካኩማ ያሉ ስደተኞች ለመልሶ ማስፈር ቃለ መጠየቅ እየተደረገላቸው ነው

በዓለም ትልቁ በሆነው የኬንያው የካኩማ ስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሶስተኛ አገር ለመሄድ የሚያስችላቸውን መስፈርት ማሟላት አለማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ቃለ መጠየቅ እየተደረገላቸው ነው። ቃለመጠይቁ እየተካሄደ ያለው በተባበሩት መንግ

ስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) አማካኝነት ነው። ለመልሶ ማስፈር ብቁ የሆኑ ሰዎችን የመለየት ሂደቱ የተጀመረው ከሶስት ሳምንት በፊት ሲሆን ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል።እ.ኤ.አ በ2003 እና በ2004 ካኩማን የተቀላቀሉ ስ

ደተኞች በሙሉ ለቃለመጠይቁ ተጠርተዋል። ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እ.ኤ.አ በ2005 ወደ ካምፑ ከከገቡ ስደተኞች መካከል የተወሰኑትንም ለመልሶ ማስፈር አነጋግሯል። በአሁኑ ወቅት በካኩማ የስደተኞች ጣቢያ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ይኖራሉ። ከስደተኞች መርጃ ድርጅት የተገኘ ቁጥር እንደሚያመለክተው 35 ሺህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬ

ንያ ይኖራሉ። ከእነዚህ ውስጥ 14 ሺህ ያህሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ናቸው። ቃለመጠይቁ የተደረገላቸው የካኩማ ስደተኞች

ውጤታቸውን እንደከዚህ ቀደሙ በሁለት ቀን ልዩነት ሳይሆን ከሳምንት በኋላ እንዲያውቁ እንደተደ

የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ ጽህፈት ቤት ከፈተ

ርጅት (አይ.ኦ.ኤም) ቅጥር ግቢ ተወስደዋል። ከእነዚህ ስደተኞች መካከል የመጀመሪያዎ

ቹ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። ይህ ጉዞ ላለፉት አራት ወራት ተቋርጦ የቆየውን ከኬንያ ወደ አሜሪካ ለመልሶ መስፈር የሚደረገውን በረራ እንደገና ያስጀመረ ነበር። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ እ.ኤ.አ በ2009 ብቻ 75 ስደተኞች በአሜሪካ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። የአሜሪካ ጎረቤት ካናዳ በየዓመቱ ከ10 እስከ 12ሺህ ስደተኞችን በመልሶ የማስፈር ፕሮግራሟ አማካኝነት ትቀበላለች። ከኬንያ ወደ ካናዳ የሚደረገው የስደተኞች የ

መልሶ ሰፈራ ጉዞ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (ጁን 11) እንዲጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል።

ረገ እንደሆነ በካኩማ የሚገኝ እና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ ስደተኛ ለሐበሻዊ ቃና ገልጿል። ከስደተኞቹ መካከል መስፈርቱን አሟልተው የሚገኙቱ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ ወይም ካናዳ እንደሚመደቡም ተናግሯል።

በኬንያ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢበኬንያ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

የካኩማ ስደተኛ ጣቢያ በዓለም ትልቁ ነው

ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ባንቲሁን ኃይሌ

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

Page 3: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 3

ዜና

በቃጠሎ የወደመው ኩሽ ሆቴል እንደገና ሊሰራ ነው

በደቡብ ሱዳን ያገረሸው ግጭት የቀጠናውን ሰላም እንዳያናጋው ተሰግቷል

ደቡብ ሱዳን...

ከአራት ወራት በፊት በደረሰበት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ኩሽ ሆቴል በቅርቡ ስራ ሊጀምር ነው። በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ልዩ ስም አትላባራ በሚባለው ቦ

ታ የሚገኘው ይሄው ሆቴል በአደጋው ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ለመስጠት እድሳት ሲያከናውን ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት እድሳቱ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ስራውንም በዚህ ወር ውስጥ እንደሚጀምር ጁባ የሚገኙ የሐበሻዊ ቃና ምንጮች ገልጸዋል።ኩሽ ሆቴል ንብረትነቱ የአቶ ጌቱ ሽብሩ ሲሆን ለአምስት ዓመታ

ት ያህል ለወይዘሮ አብረኸት በኮንትራንት ተከራይቶ ነበር። ሆቴሉን ከማስተዳደር ባሻገር ምግብ በማዘጋጀት ለሚሳተፉት ወይዘሮ አብረኸት ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ገደኛ ቀን አልነበረም። በዕለቱ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ገደማ ምግብ ይሰሩበት የነበረው ሲሊንደር ፈንድቶ ቤቱን በእሳት ያይዘዋል። የመመገቢያ አዳራሹ የባህላዊ ምግብ ቤት መልክ እንዲይዝ ከጣሪያ በላይ ሳር ለብሶ ስ

ለነበር እሳቱ በፍጥነት እንዲቀጣጠል ምክንያት ይሆናል። በዚህ አደጋ ወይዘሮ አብረኸትን ጨምሮ ሌሎች አራት ሰ

ዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተቃጠሉ ሲሆን ሌሎች ሶስት የሆቴል ቤቱ ሰራተኞች እሳቱ በከፊል አግኝቷቸዋል። አደጋው የደረሰባቸው ሰዎች ወዲያውኑ ወደ ጁባ ቲቺንግ ሆስፒታል ቢወሰዱም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ግን ተጨማሪ እና አፋጣኝ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ስለነበር ወደ አዲስ አበባ እንዲላኩ ይወሰናል። በጁባ የኢትዮጵያውያን ማህበር፣ በከተማይቱ የሚኖሩ ኢ

ትዮጵያውያን እና የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች በጋራ ባደረጉት ጥረት ለአየር ትራንስፖርት የሚያስፈልገውን ወደ አስር ሺህ ዶላር ገደማ ገንዘብ ማሰባሰብ ችለዋል። በተሰበሰበው ገንዘብ አማካኝነትም ከፍተኛ ቃጠሎ የደረሰባቸው አምስቱ ተጎጂዎች ወደ አዲስ አበባ ተልከዋል። በየካቲት 12 እና ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ህክምና እንዲያገኙ ከተደረጉት ተጎጂዎች መካከል ወይዘሮ አብረኸት እና ሌላ እንስት ተጎጂ ህይወታቸው አልፏል።

በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

lኢትዮጵያ በአቤዬ ሰላም አስከባሪ ልታሰፍር ትችላለች

ደቡብ ሱዳን በሚቀጥለው ወር ዘጠነኛው ቀን ላይ ነጻነቷን በይፋ ታውጃለች፡፡ ሀገሪቱ ወደነጻነት ቀኗ እየተጠጋች በሄደች ቁጥር ግን በአቤዬ ያለው ግጭት እየተባባሰ መጥቷል፡፡የተባበሩት መንግስታት እንደሚለው የያዝነው የፈረንጆች ዓመ

ት ከገባ ጀምሮ እስከ አለፈው ወር መጨረሻ ከ1500 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ቢያንስ 96,000 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ሰሜንና ደቡብ ሱዳን በነዳጅ ክምችት የተሞላች ናት የምትባለ

ውን አቤዬን ህዝበ ውሳኔ ተካሂዶ የማንነቷ እስኪለይ ድረስ በጋራ ለማስተዳደር እ.ኤ.አ በ2005 ከስምምነት ደርሰው ነበር፡፡ይህን ስምምነታቸውን መሰረት በማድረግም የባለፈው ጥር ህዝ

በ ውሳኔ አቤዬንም እንዲያካትት በ2008 ከስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡ ሆኖም ህዝበውሳኔው በሚደረግበት አካሄድ ላይ ሁለቱ ወገኖች(ሰሜንና የደቡብ ሱዳን አስተዳዳር)ባለመስማማታቸው የአቤዬ ህዝበ ውሳኔ ላልተወሰነ ጊዜ ሊተላላፍ የግድ ሆነ፡፡ ህዝበውሳኔው ተደርጎ አቢዬ የደቡብ ወይም የሰሜን ሱዳን አካል ናት እሲኪባል ድረስ ግን በጥምር ሀይል እንድትተዳደር ነበር ውሳኔው፡፡ ሰሞኑን ግን የአልበሽር መንግስት በደቡብ ሱዳን ድንገተኛ ጥቃ

ት ተከፍቶ 22 ያህል ወታደሮች ተገደሉብኝ በማለት በታንክ የታገዘ ጦሩን ወደ አቢዬ ልኮ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል፡፡ ይህን ተከትሎ በአካባቢው የነገሰው ውጥረትም ለብዙዎች ሞትና ከቤት ንብረት መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን ቁጥሩ የተባባሩት መንግስታት በተጨባጭ አለኝ ከሚለው ቁጥር ጋር ሲነጻጸር የሚበልጥ ቢሆንም የደቡብ ሱዳን አስተዳዳር 150 ሺህ ያህል ዜጎች ግጭቱን ለመሸሽ ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን አስታውቋል፡፡ “ሁኔታው አስከፊ ነው፡፡ ሰዎች ግጭቱን በመፍራት ማቄን ጨ

ርቄን ሳይሉ እየሸሹ ያለመጠለያ ቀርተዋል” ብለዋል የደቡብ ሱዳን የሰብኣዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮክ ሩኤአ ለቢቢሲ፡፡ሊሴ ግራንዴ የተባሉ ሌላ በደቡብ ሱዳን ተባበሩት መንግስታት

ሰብአዊ ጉዳዮች ከፈተኛ ባለስልጠን በበኩላቸው “96 ሺህ ስደተኞች እኛ ያረጋገጥነው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎቹ በየጫካው እየተደበቁ ስለሸሹ ቁጥሩን ከፍ ሊደርገው ይችላል” ማለታቸውን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡ ይህን ተከትሎ ሁለቱ ወገኖች በሶስተኛ ወገን አማካኝነት በአዲ

ስ አበባ ባደረጉት ወይይት በጋራ ድንበራቸው ላይ ነጻ ቀጠና ለማቋቋም ተስማማተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ስምምነቱ አቤየን በስም ካለመጥቀሱም በተጨማሪ ከመቼ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቀን ባለመቆረጡ የሁለቱን ወገኖች ችግር ስለመፍታቱ ጥርጣሬ አጭሯል፡፡የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ግን “በቂ ጦርነት ስላደረ

ግን ምንም ቢሆን ከእንግዲህ ተመልሰን ወደ ጦርነት አንገባም ነጻነታችንንም አደጋ ላይ አንጥልም” እያሉ ነው፡፡እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ አልበሽር ግን ሳልቫኪር አቢዬ ትገ

ባኛለች ካለ ለደቡብ ሱዳን እውቅና አልሰጥም ባይ ናቸው፡፡እንዲያውም ግዛቷ የሰሜን ሱዳን ናት በሚል ጦራቸውንም ከስፍራው እንደማያስወጡ አስታውቀዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ጥበቃ ምክርቤት ጦራቸውን ከአወዛጋቢዋ አቤዬ እንዲያስወጡ ያቀረበውን ማስጠንቀቂያም ውድቅ እስከማድረግ ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የሰላም አስከባሪ ጦር ጥያቄ ከሁ

ለቱም ወገኖች ከመጣ አዎንታዊ ምላሽ እሰጣለሁ እያለ ነው፡፡ ሀሳቡ በደቡብ ሱዳን በኩል ሙሉ ተቀባይነት ቢያገኝም የአልበሽር መንግስት ግን “ጉዳዩን እያጤንኩት ነው” ብሏል፡፡

አቢዬ ተፈላጊዋ(የሁለት ባል) ሚስትየሰሜንም ሆነ ደቡብ ሱዳን አስተዳዳሪዎች አቢዬ የኔ ናት ይላ

ሉ፡፡ ይህ ብዙዎች እንደሚያስቡት በነዳጅ ምክንያት ብቻ የመጣ አይደለም፡፡ ከነዳጅም ባሻገር ጉዳዩ በጎሳዎች መካካል ያለ የይገባኛል ውዝግብ ነው፡፡ ከኢኮኖሚም አልፎ የዘር ጥያቄ ነው ለአቢዬ እንቆቅልሽ መፍትሄ እንዳይገኝ እንቅፋ የሆነው የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡ አቢዬን ዲንካ ኒጎክ የተባሉ የደቡብ ሱዳን ቡድኖች የእኛ ናት ሲሉ ሚዘሪያ የተባሉት የሰሜን ሱዳን አርብቶአደሮችም አቢዬ የምትገባው ለእኛ ነው ይላሉ፡፡ ሁለቱ ጎሳዎች ብዙ ጊዜ ለከብቶቻቸው በሚፈልጉት ምግብና ው

ሃ ሳቢያ ይጋጫሉ፡፡በእርስ በእርስ ጦርነቱ ወቀውትም ሚዘሪያዎች ከካርቱም መንግስት በሚታጠቁት መሳሪያ ደቡብ ሱዳንን ያጠቁ እንደነበር ይነገራል፡፡ የተባባሩት መንግስታት ሰሞኑን በሄሊኮፕተሮቼ ላይ ተኩስ የከፈቱት የሚዘሪያ ሚሊሻዎች ናቸው ሲል ይወቅሳል፡፡ የሚዘርያ ጎሳ መሪ ወቀሳውን ቢያጣጥሉትም፡፡ከሁለቱ ጎሳዎች እስከ መንግስታት የምትፈለገው አቤዬ በቀላሉ

እንዱን መምረጥ ወይም በአንዱ መመረጥና ሰላማዊ ትዳር መመስረት አልቻለችም፡፡ይህ ደግሞ በአፍሪካ በስፋቷ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ሱ

ዳን ለዓመታት ከነበረችበትና ለ2 ሚሊየን ሰዎች ሞትና ለበርካቶች ስደት ምክንያት ከሆነው ግጭት የመውጣቷን ነገር አጣብቂኝ ውስጥ አስገቶታል፡፡ደቡብ ሱዳናውያንም የሚጓጉለትንና በካርዳችን አገኘነው የሚ

ሉትን የነጻነት ቀን ከናፍቆት ይልቅ በስጋት እንዲጠብቁት እያደረጋቸው ነው፡፡ተንታኞች እንደሚሉት የአቤዬ ጉዳይ በቶሎው እልባት ካላገኘ እነዚሁ ወገኖች ነጻነታቸውን ብዙም ሳያጣጥሙ ዳግ

ም ወደ እልቂት መግባታቸው አይቀርም፡፡ለጋሽ ሀገራት በበኩላቸው የሰሜን ሱዳን መንግስት አቤዬን በሀ

ይሉ ከተቆጣጠረ የእርዳታ እጃችን ያታጠፋል እያሉ ማስፈራራት ይዘዋል፡፡ በሱዳን የአሜሪካ መልዕከተኛ ፕሪንስተን ሌይማን አልበሽር በጉልበቱ አቤዬን ከወሰደ ሱዳን ያለባትን በቢሊየኖች የሚቆጠር እዳ ለመሰረዝ የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ ይጥለዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ አልበሽር ጦራቸውን ከአቢዬ በቶሎ ካላስወጡም አሜሪካ አሸባሪዎችን ይደግፋሉ በሚል ከመዘገበቻቸው መካከል ሱዳንን የመሰረዟ ነገር አጠራጣሪ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ሰላም ለምስራቅ አፍሪካበደቡብ ሱዳንም ሆነ በአጠቃላይ በሱዳን የሚሆነው አዎንታዊ

ም ሆነ አሉታዊ እንቅስቃሴ በምስራቅ አፍሪካ በተለይ በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ለአመታት የዘለቀው ግጭትም አነዚሁን ሀገራት በእንቅርት ላይ እንዲሉ ጫና አሳድሮባቸው ቆይቷል፡፡ ምክንያቱም በተለይ ግጭቱን በመሸሽ የሚሰደዱት ሱዳናውያን የመጀመሪያ መዳረሻቸውን የሚያደርጉት በጎረቤት ሀገራት በመሆኑ፡፡ ከሰሞኑ ያገረሸው ግጭትም በተለይ ኡጋንዳን ኬኒያንና ኢትየጵ

ያን ዳግም የስደተኞች መከማቻ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ይህንን የፈሩ ብሎም የደቡብ ሱዳን ሰላም ለእኛም የገበያ እድ

ል ማስፋት ነው ያሉት እነዚሁ ሀገራትም ለግጭቱ ሰላማዊ(ዲፕሎማሲያዊ) መፍትሄ ለመፈለግ እየጣሩ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ከደቡብ ሱዳን ነዳጅ የማስገባት እቅድ እንዳላት በቅርቡ በፕ

ሬዚዳንቷ በኩል ያስታወቀችው ኡጋንዳ ከነዚህ መካካል ተጠቃሽ ናት፡፡ የኡጋንዳ አለም አቀፍ ግንኙነት ሚንስትር ሄንሪ ኦኬሎ ኦርየም

ለእለታዊው የሀገሪቱ ጋዜጣ ኒው ቪዥን እንደተናገሩት የሙሴቬኒ መንግስት በአቤዬ ያለው ሁኔታ አሳስቦታል፡፡ እናም ለግጭቱ እልባት ለመሻት ዲፕሎማሲያዊ ግፊት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ኦርየም እንዳሉት ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሳልቫኪር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡ ሀገራቸው ዳግም ጦርነት እንደማትጀምርም ገልጸውላቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ከኬ

ኒያው ርዕሰ ብሔር ሙአይ ኪባኪ ጋርም በጉዳዩ ዙሪያ መክረዋል፡፡ ስለ ውይይቱ ዝርዝር ሚኒስትሩ ለጋዜጣው ያሉት ነገር ባይኖርም፡፡ ኢትዮጵያና ኬኒያ በየፊናቸውም ለችግሩ እልባት ያሉትን እሞ

ከሩ ነው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩ ሳሰበው ይመስላል፡፡ ጠቅ

ላይ ሚኒስትር መለስ በቅርቡ ከሱዳን ጋር በተደረገ ስብሰባ መንግስታቸው ለሱዳን ሰላምና መረጋጋት የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ እንደ አቶ መለስ የሱዳን ሰላም ለእነሱ(ለሱዳናውያን)ብቻ ሳይሆን ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ነው፡፡አቶ መለስ ሁለቱ ወገኖች በ2005 የተደረሰው አጠቃላይ ሰላም

ተፈጻሚነት እንዲጥሩም ጥሪ አቅርበዋል ከሰሞኑ ከሱዳን የመከላከያ ሚንስትር ጄኔራል አብደል ራሂም ሁሴን ጋር በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ለደሱዳን ት

ሪቢዩን እንደተናገሩት “በአቤዬ የሰላም አስከባሪ እንዲሰፍር ከሰሜንና ደቡብ ሱዳን ጥያቄ ከመጣ ኢትዮጵያ ጥያቄውን ከግምት ታስገባለች፡፡” ጁባን መዳረሻቸው ያደረጉ በርካታ ኢትዮጵያውያንም የደቡብ

ሱዳንን ሰላም አጥብቀው ከሚፈልጉት መካከል ናቸው፡፡ ምክንያቱም ለሁለት አስርት ዓመታት በደቡብና ሰሜን ሱዳን መካከል የዘለቀው ግጭት ካስከተለው እልቂት ባሻገር በርካቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድረጓል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በደቡብ ሱዳን ይህ ነው የሚባል በቂ የሰው ሀይልም ሆነ የመሰረተ ልማት እንዲሁም አገልግሎት የለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም “ሁነኛ ወዳጄ” ወደሚላት ደቡብ ሱዳን ዘልቆ መግባት ይፈልጋል፡፡ የእቅዱን መሳካት አሁን ላይ ሆኖ መተንበይ ቢያስቸግርም ከደቡብ ሱዳን አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት በመዘርጋት የሁለትዮሽ የገበያ ትስስርን የማሳደግም ፍላጎት አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንም ቢሆኑ ገና ብዙ ባልተበላበት የደቡብ ሱዳን ገብተው ጉልበትና እውቀታቸውን በማፍሰስ በገፍ ይዘዋወራል ከሚባለው ዶላር መጋራት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን የአቤዬ ጉዳይ እልባት አግኝቶ ደቡብ ሱዳን የሰላም አየር መተንፈስ ከቻለች ነው፡፡ ለኤርትራውያንም ቢሆን እንደ ደቡብ ሱዳን ለንግድ የሚመች ሀ

ገር ያለ አይመስልም፡፡ በአንጻሩ የኤርትራ መንግስት ግን የደቡብ ሱዳንን መገንጠል በቀ

ና አይመለከተውም፡፡ እንዲያውም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያወጣው መረጃመረጃ የኢሳያስ አስተዳደር ለደቡብ ሱዳን እውቅና አልሰጥም ማለቱን ያስነብባል፡፡ እንዲያውም ደቡብ ሱዳን መገንጠል አያዋጣም ሲል ይካራከራል፡፡ የሳልቫኪር መንግስት ግን ከውጪም ሆነ ከውስጥ የተደቀነበትን

ፈተና ተቋቁሙ በሁለት እግሯ የቆመች ለራሷም ለጎረቤቶቿም የምትጠቅም ሀገር ለመመስረት እየተጋ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሁሉም ግን በቀጣዩ ወር ደቡብ ሱዳን በይፋ የምታውጀውን ነጻነት ተከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ እስከዚያም ሆነ ከዚያ በኋላ ያለው መንገድ ቀና መሆኑን መመለስ የምትችለው ግን የአቤዬ ግዛት ብቻ ናት፡፡

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

በኡጋንዳ ምድር ለሶስተኛ ጊዜ የተከሰተው ኢቦላ ባለፈው ወር አንዲት የ12 ዓመት ታዳጊ መግደሉን ተከትሎ ኬኒያ የድንበር ላይ የጤና ምርመራዋን ማጠናከሯን አስታውቃለች፡፡የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደሚለው ባለፈው ወር ከካ

ምፓላ 75 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሊዌሮ ታዳጊዋ በኢቦላ እንደሞተች ከተረጋጋጠ በኋላ ለጉዳዩ የተቋቋመ ልዩ ግብረ ሀይል ከሟች ጋር ሊነካኩ ይችላሉ ባላቸው 25 ያህል ሰዎች ላይ ምርመራ አድርጓል፡፡ ሆኖም ሁሉም ከበሽታው ነጻ መሆናቸውን ነው ግብረሃይሉ ያስታወቀው፡፡ይሁን እንጂ ኬኒያ ከኡጋንዳ ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞች ከቫ

ይረሱ ነጻ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ድንበር አካባቢ ላሉ የጤና ባለሙያዎቿ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፋለች፡፡ ይህንን ተከትሎም በተለይ በማላባ ድንበር በኩል ወደኬኒያ የ

ሚገቡ መንገደኞች ከወትሮው በተለየ ጥልቅ የጤና ምርመራ እየተደረገላቸው ነው፡፡ “ወደ ኬኒያ ድንበር የሚሻገር ማንኛውንም መንገደኛ በሚገባ እየ

መረመርን ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ አደገኛ በሽታ ነው” ብለዋል የቴሶ አካባቢ ሀኪም ዶክተር መልሳ ሉቶሚያ፡፡ በድንበሩ አካባቢ ላሉ ነዋሪዎችም ስለቫይረሱ ምንነትና ስርጭቱን ለመግታት ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ እያስተማሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኡጋንዳ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ካምፓላን እንዲያስተዳድ

ሩ የተመረጡት ከንቲባ ኤርያስ ሉካጎም ኢቦላ በዋና ከተማዋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እያደረጉ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ሉካጎ እንዳሉት ቫይረሱ ማንንም የካምፓላ ነዋሪ እንዳያጠቃ ለ

ማስቻል አስተዳደራቸው የኢቦላን መከሰት የሚከታተልና የሚያጣራ ቡድን አቋቁሟል፡፡ በኢቦላ መያዛቸው የሚጠረጠር ህመምተኞችን ለማጣራትም በካምፓላ አስተዳደር ሆስፒታሎችና በየክፍለከተሞቹ የህክምና ማዕከል መዘጋጀቱን አመልክተዋል፡፡ ኢቦላ መድሃኒት ያልተገኘለት ገዳይ በሽታ ሲሆን ምልክቶቹም

ማንቀጥቀጥ፤ተቅማጥ፤ ተከታታይ የደም መፍሰስና ድካም ናቸው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም እነዚህ ምልክቶች ያየ ግለሰብ በአቅራቢያው ላለ የህክምና ተቋም ማሳወቅ እንዳለበት የኡጋንዳ መንግስት አሳስቧል፡፡ በፍጥነት የመዛመት አቅም እንዳለው የሚነገርለት ኢቦላ ከደ

ም፤ከሰገራ እንዲሁም በቫይረሱ ከተጠቃው ግለሰብ ከሚወጡ መሰል ፈሳሽ ነገሮች ጋር በሚደረግ ቀጥታ ንክኪ ይተላለፋል፡፡በኡጋንዳ ኢቦላን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብ

ረሃይል በአሁኑ ወቅት በሽታው በቁጥጥር ስር እንደዋለ ቢያስታውቅም ድንበር አካባቢ ያሉ የኡጋንዳ ከተሞች ግን በሽታው መከሰቱ ከተሰማ ጀምሮ በቻሉት ሁሉ ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ አሜሪካም በሀገሪቱ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል አማካኝነት ወደ ኡጋንዳ ለሚጓዙ ዜጎቿ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች፡፡ ማንኛውም አሜሪካዊ ወደ ኡጋንዳ ከመሄዱ አስቀድሞ ስለበሽታው ግንዛቤ እንዲኖረው በሚል፡፡መድሃኒት አልባውና ገደዩ የኢቦላ በሽታ በኡጋንዳ ሲከሰት ይህ

ለሶስተኛ ጊዜው ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2000 ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ኢቦላ ለ224 ሰዎ

ች ሞት ምክንያት ሲሆን በ2007 ለሁለተኛ ጊዜ ተከሰተውና ምንነቱን ለማወቅ ሶስት ወራትን የፈጀው ደግሞ የ37 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

ኢቦላ ምን አይነት በሽታ ነው?አልም አቀፉ የጤና ድርጅት የኢቦላን ቫይረስ መጀመሪያ ከተነሳ

በት አካባቢ ጋር በማዛመድ ቢያንስ በአምስት ይከፍለዋል፡፡ የዛየር፤ የሱዳን፤ የኮቲዲቯር፤ የቡንዲቡግዮ እና የሬስተን በሚል፡፡

l “ቫይረሱ በካምፓላ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እያደረግን ነው” ከንቲባ ኤርያስ ሉካጎ

የኢቦላ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው እ.ኤ.አ በ1976 በያኔዋ ዛየር በዛሬዋ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ኮንጎ ሞንጎላ ግዛት በምትገኝና ያምቡኩ በምትባል መንደር ነው፡፡ በወቅቱ መምህር የነበረው ማባሎ ሎሌካ የዚህ ቫይረስ የመጀመሪያው ተጠቂ በመሆን በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ ከዚያ በኋላ ዝርያውን በተወሰነ መልኩ ቀይሮ ወደ ሱዳን የተሸገረው ኢቦላ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1989 በአሜሪካ ቨርጂኒያ ሬስተን ውስጥ እንደታየ ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት እንደሚለው ይህ በአሜሪካ የታየው ኢቦላ በሰው ሳይሆን በዝንጆሮ ላይ የተከሰተ ነው፡፡ በወቅቱም ብዙ ዝንጆሮዎች በቫይረሱ ሞተዋል፡፡በ1994 ደግሞ ሌላ የኢቦላ ዝርያ በኮቲዲቯር ተከስቶ አን

ድ ሰውና ለበርካታ ቺምፓንዚዎችን ገድሏል፡፡ ይህ ከሆነ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ኢቦላ መጀመሪያ ወደተከሰተበት ኮነጎ ተመልሶ 250 ሰዎች ለህልፈት ዳርጓል፡፡ ኢቦላ በጋቦንም በ1994 ተከስቶ የዘጠኝ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

ኢቦላና ኡጋንዳጥቂት ኡጋንዳውያን በሩቁ ይሰሙት የነበረውና ብዙዎቹ

ምንነቱን እንኳ የማያውቁት ይህ ቫይረስ በጥቅምት 2000 (እ.ኤ.አ.) ድንበራቸውን ተሻግሮ በሰሜን ኡጋንዳዋ ጉሉ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተና 162 ሰዎችን ገደለ፡፡ ከሰባት ዓመታት በኋላ ደግሞ ቡንዲቡግዮ በሚባለው አካባቢ አዲስ አይነት የኢቦላ ቫይረስ ተከስቶ እንደመጀመሪያው ሁሉ አንድ የህክምና ዶክተርን ጨምሮ 37 ሰዎችን ገድሏል፡፡ከሰሞኑ ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ ኢቦላ በኡጋንዳ ተከስቷል፡፡

በሟቾች ቁጥር የአሁኑ የተሻለ ቢሆንም ገና የቫይረሱ ጨርሶ መጥፋት ስላልተረጋገጠ ነዋሪዎችንና የህክምና ባለሙያዎችን እረፍት መንሳቱ አልቀረም፡፡አንድ ሰው እንደ እድል ብሎ በቫይረሱ ከተጠቃ የህክም

ና ባለሙያዎች ግለሰቡን ለብቻው እንዲቀመጥና ከማንም ጋር ንክኪ እንዳያደርግ ይመክራሉ፡፡ ምክንያቱም አስቀድመው ካልተከላከሉት ኢቦላ እንደ ኤች አይቪ ሁሉ መድሀኒት የለሽ በመሆኑ፡፡ በጥቂት የአፍሪካ ሀገራት ብቻ እንደሚገኝ የሚነገረው የ

ኢቦላ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ ባለቤት የሆነችው ኡጋንዳ ኢንቴቤ በሚገኘው በዚህ መሳሪያ በጠቀም ለቫይረሱ ክትባት ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ የጀመረች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጥረት ተሳክቶ ውጤታማ ክትባት ማግ

ኘት ቢቻል እንኳን ከ አምስት ዓመት በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት ለማድረስ የማይታሰብ መሆኑን በምርምሩ የሚሳተፉት ባለሙያዎች ለተባበሩት መንግስታት የዜና አውታር ተናግረዋል፡፡ተመራማሪዎቹ በረጅም ጊዜ እቅዳቸውም ከቫይረሱ ፈዋሽ

መድሃኒት ለመቀመም ከተቻለም አንድ ሰው በቫይረሱ ከተያዘም በኋላ ሊተርፍ የሚችልበትን መድሃኒት ለመፈለግ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የአሜሪካ የህክምና ጠበብቶች ያገኙት ክት

ባት ከቫይረሱ የመፈወስ አቅም ቢኖረውም ግለሰቡ በኢቦላ ከተጠቃ በ30 ደቂቃ ውስጥ መሰጠት ያለበት በመሆኑ የታሰበውን ውጤት አላመጣም፡፡ እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ ኢቦላ ለመጀመ

ሪያ ጊዜ ከተከሰተበት እ.ኤ.አ 1976 ጀምሮ 1850 ህመምተኞች ሲመዘገቡ 1200 ያህል ሰዎች ደግሞ በበሽታው ህይወታቸው አልፏል፡፡

ኬንያ ኢቦላ ድንበሯን እንዳይሻገር የጤና ምርመራዋን አጠናክራለች

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

Page 4: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)4 ሀበሻዊ ቃና

የስደት ዓለም

ሁለት ልዩ ጓደኞች አሉኝ፡፡ ሁለቱም የራሳቸው አሜሪካ አላቸው፡፡

አንድ ጓደኛዬ ባገኘችኝ ቁጥር ‹‹ከምታስተምረኝ›› ነገር አንዱ ስለ አሜሪካ ነው፡፡ ትምህርቷን የምትጀምረው ‹‹አሜሪካን እኮ አታውቀውም…››ብላ ነው፡፡ ሁልጊዜ የሚገርመኝ ግን እስከአሁን ድረስ ገና ዘንድሮ አሜሪካን እንደረገጥኩ አድርጋ ማሰቧ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ተደዋወልንና ስናወራ ስለ ሕክምና ውድነት ማውራት ጀመርን፡፡ ከዚያ ‹‹አሜሪካን እኮ አታውቀውም…›› ስትል ቶሎ ብዬ ‹‹አሁንማ ገባኝ! ሰሞኑን እኮ የ23000ዶላር ቢል ደረሰኝ›› አልኳት፡፡ ‹‹አላልኩህም! ቀመስከው አይደል›› ትለኛለች ብዬ ስጠብቅ ‹‹ገና ምን አይተህ..›› አለችኝና አረፈችው፡፡ የእርሷ አሜሪካ ስጠጋው የሚሸሽ አይነት ሆነብኝ፡፡የማላውቀው አሜሪካ እንዳለ የምትነግረኝ ግን እር

ሷ ብቻ አይደለችም፡፡ ባለታክሲው ደግሞ አለ፡፡ የዚህ ጓደኛዬ አሜሪካ ደግሞ አስደንጋጭ ነው፡፡ ስንገናኝ ከሚጠይቀኝ ጥያቄ አንዱ ‹‹እነ ስካርብሮው ምንም አላሉህም?›› የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ጆ ስካርብሮ /Joe Scarborough/ አንድ የአሜሪካ ቶክ ሾው ሆስት እንደሆነ የተረዳሁት በቅርብ ነው፡፡ ጓደኛዬ አሜሪካ የመጣ ጊዜ ዝነኛ የነበረ ሰው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ጓደኛዬ ስካርብሮ ሲል ‹‹ፈረንጆቹ›› ማለቱ ነው፡፡ እና ጓደኛዬን ‹‹እስካሁን ምንም አላሉኝም›› ስለው ማሰስፈራሪያውን ይለግሰኛል፡፡ ቆይ ታያለህ! ድንገት We need to talk ወይም can I see you at the conference room ይሉሃል፡፡ እንዲህ ሲሉህ ከሥራ ሊያባርሩህ ነው ማለት ነው! ቁርጥህን እወቅ! ይለኛል፡፡ ጓደኛዬ ፈረንጅ አለቃየን በግሌ የብጽዕና ማዕረግ እንደሰጠሁት ቢሰማ ምን ይሆን ! እላለሁ አንዳንዴ፡፡

አሜሪካዊ መሆን ጨነቀኝ! አለኝ አሜሪካዊ መሆን ጨነቀኝ! ልቤ አመነታብኝ፡፡ አ

ለኝ አንድ ጓደኛዬ፡፡ ለምን? አልኩት፡፡ እንደው ኢትዮጵያን መክዳት ከበደኝ፤ አለኝ፡፡ ለምን? አልኩት እንደገና፡፡ በቃ! ምን ልበልህ! ፎርም በሞላሁ ቁጥር ዜግነት በሚለው ቦታ አሜሪካዊ ብዬ መሙላት ጨነቀኝ አለኝ፡፡ጭንቀቱ አሳዘነኝ፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር ል

ቡ ውስጥ ታማ ተኝታ ስታቃስት የሰማኋት ያህል ተሰማኝ፡፡ ጓደኛዬ በእርግጥ ተጨንቋል፡፡ እኔም ጭንቀቱ ገብቶኛል፡፡ ኢትዮጵያን እስከመጨረሻው ሳያስከዳ፤ ኃጢአትንም እስከመጨረሻው ሳያሰራ የማይለቅ ሀገር መጥተን! አልኩ በሆዴ፡፡ ቢሆንም፤ ጓደኛዬ ዞሮ ዞሮ ዜጋ መሆኑ እንደማይቀር ስለማውቀው ትንሽ በጭንቀቱ መቀለድ አማረኝ፡፡ ስለዚህ ትንሽ ጣዕሩን የሚያበዛ ነገር ነገርኩት፡፡ዜግነት ስትቀበል ምን እንደሚደረግ ታውቃለሁ አ

ልኩት፡፡ አላውቅም አለኝ፡፡ ባንዲራቸውን ይሰጡኋል፤ ከዛ እጅህን ወደላይ አደርገህ፤ ‹‹እኔ….ለሀገሬ ለአሜሪካ….እያልክ ትምላለህ…›› ስለው ‹‹ኡ..!›› ብሎ ራሱን ያዘ፡፡ ‹‹እልልታ ግን አይፈቀድም›› አልኩት፡፡ ተናደደብኝ፡፡ ‹‹እንዴት እላለሁ›› ብሎ፡፡ በድርቅና መልሼ ‹‹እውነቴን ነው! በተለይ ኢትዮጵያውያን እናቶች ዜግነት ሲሰጣቸው፤ እልልታቸውን እያቀለጡ፤ መሬት እየሳሙ፤ ስላስቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜ ልዩ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል አልኩት፡፡›› ‹‹እውነትህን ነው! እውነትህን ነው! በጣም ያሳፍራል! ያናድዳል…እያለ ብዙ ብዙ ነገር ተናገረ፡፡ትንሽ ካጨናነቅሁት በኋላ ለእርሱ የሚሆን ማበረ

ታቻ መድኃኒት የሚሆን ምክር ነገርኩት፡፡ ምክሬን የጀመርኩት ‹‹ኢትዮጵያ ያለችው የት እንደሆን ታውቃለህ?›› በሚል ጥያቄ ነው፡፡ ለመልሱ ግን ብዙም ሳላስጨንቀው ወደ ምክሬ ገባሁ፡፡ ምክሬ ግን እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡አንድ መንፈሳዊ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ ይኼ ጓደኛዬ ሃይ

ማኖታዊ ምግባሩ፤ተፈጥሮአዊ ጸባዩ፤ መንፈሳዊ እውቀቱ ሁሉ እንከን የማይወጣለት ስለሆነ ያስገርመኝ ነበር፡፡ እናም አንድ ቀን ‹‹አስፍዬ! ያንተ እኮ ትክክለኛ ቦታ ገዳም ነው!›› አልኩት፡፡ ‹‹ገዳም የት እንዳለ ታውቃለህ?›› አለኝ አስፍዬ መልሶ፡፡ ታላቅ ነገር ሊመክረኝ እንደሆነ ገባኝ፡፡ እርሱም መልስ ሳይጠብቅ ቀጠለ፡፡ ‹‹ገዳም ያለው ልብ ውስጥ ነው!›› አለኝ፡፡ ‹‹ልብህ ውስጥ ገዳም ከሌለ፤ ገዳም ብትገባም ገዳማዊ አትሆንም፡፡ ልብህ ውስጥ ገዳም ካለ ደግሞ፤ መርካቶ ሱቅ ውስጥ ተቀምጠህም ቢሆን ገዳማዊ ትሆናለህ›› አለኝ፡፡ታሪኩን አሜሪካዊ ለመሆን ለተጨነቀው ተረጎም

ኩለት፡፡ ‹‹ኢትዮጵያም ያለችው ልብ ውስጥ እንጂ! ወረቀት ላይ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነትህን ከልብህ እንዳይጠፋ ኢትዮጵያውያን ጓደኞችህን አጥብቀህ በመያዝ፤ ቤተክርስቲያን በመሄድ፤ በዓላትን በማክበር፤ ሀገር ቤት ዶላር በመላክ፤ ስልክ በመደወል ተንከባከበው እንጂ የወረቀት ላይ ስም ብቻ አታድርገው፡፡››ጓደኛዬ ምክሬ ቢያስደስተውም አሁንም ጥቂት ቅ

ሬታ እንዳለሁ ከአነጋገሩ ገባኝ፡፡ ስለዚህ ማንገራገር አላቆም አለኝ፡፡አሁን ደግሞ መድኃኒት ሳይሆን መርዝ ማሳሳቢያ

ጨመርኩለት፡፡ ‹‹ከዚህ በላይ ያለህ ጭንቀት ምጽድቅ ይባላል! አሜሪካ ለመምጣት የተሳልከውን ስዕለት አታስታውስም፡፡ እዚህ የመጣኸው ለጽድቅ አይመስለኝም፤ ለጥቅም እንጂ፡፡ ለጥቅም ከመጣህ ደግሞ፤ አሜሪካ የሚሰጠውን ጥቅም ሁሉ ማግኘት አለብህ፡፡ ግንጥል ጌጥ አያምርም፡፡ ዜጋ መሆን ጥቅም ስላለው መሰለኝ ለማመልከት ያመነታኸው! ለጥቅም የመጣ ለጥቅም አያመነታም፡፡እንዲህ ስትል ሰው ቢሰማህ በሆዱ ምን እንደሚልህ ታውቃለህ? ግብዝ! ነው የሚልህ››፡፡ደነገጠ!ሲደነግጥልኝ ጊዜ የስድብ ሞራሌ መጣ፡፡‹‹ይሄ የሀበሻ ጉራ ነው!፡፡ የውሸት አሳይለም ሲጠይ

ቅ፤ የውሸት ሲያገባ እና ሲጋባ፤ የውሸት ፎርም ሲሞላ ይኖርና....እንደ ድመት አፉን እያበሰ…ምንም እንዳልሰራ፤ ሀገሩንም መክዳት የጀመረው ገና ኢትዮጵያ እያለ መሆኑን ረስቶ…ዜጋ ለመሆን ተጨነኩ ይላል፡፡›› ‹‹ስጋትህን አደንቃለሁ! ከመጠን በላይ ሲሆን ግን ግ

ብዝነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ የሆንከው በወረቀት ስላልሆነ! በወረቀት ኢትዮጵያዊነትህ አይፋቅም፡፡›› አልኩ እና ተሰናበትኩት፡፡የጓደኛዬ ፊቱ ነጭ ሆነ፡፡እናም አሜሪካዊ ሆነ! በወረቀት ማለት ነው፡፡

አቀባበል ለእርሷ ደስ የሚል ቢሆንም ለእኔ ግን ‹አስቂኝ› ነበር፡፡ የእንክብካቤዋ መጀመሪያ የእናቷን ፀጉር አሳጥራ፤ ጥቁር ቀለም መቀባት ነው፡፡ እናትሽ ደስ ላይላቸው ይችላል እኮ አልኳት… ‹‹ምንም አትልም›› አለችኝ፡፡ እናቷን ከእርሷ በላይ ባላውቅም፤ እሷ የደገሰችላቸውን የቁንጅና ኮተት በቀላሉ የሚቀበሉ አይመስለኝም፡፡ ቢሆንም ግን የልጅቷ ‹ሥልጣን› ግን ይገርማል፡፡የልጅ ሥልጣን መስመር የለቀቀበትም ታሪክ አው

ቃለሁ፡፡ ወላጆቹን በክብር ካመጣ በኋላ፤ ሰድቦ፤ አዋርዶ፤ ከቤት አስወጥቶ፤ በጎረቤት ብቸኛ እርዳታ ወደቤታቸው እና በክብር ወደኖሩባት ኢትዬጵያ ለመመለስ የቻሉ ምስኪን ወላጆችንም አውቃለሁ፡፡ ሁሌ ባሰብኩት ቁጥር የሚያናድደኝ ታሪክ ስለሆነ ሳልጠቅሰው ማለፍ አልቻልኩም፡፡በተቃራኒው ደግሞ የእኔ እናት አለች፡፡አሜሪካ ለ

ሰጠኝ አዲስ ሥልጣን ገና እውቅና አልሰጠችም፡፡ ሥልጣኔን ለመጠቀም የሞከርኩት ‹‹ሁሌ ነጠላ ለምን ትለብሻለሽ›› ብዬ ነው፡፡ የአሜሪካ ዊንተር በረዶ ቢዘንብም፤ እንደ ዛሬው ቀን ሙቀቱ ‹80› ቢደርስም፤ ነጠላ ወይ ረጅም ሻርፕ ሳታደርግ ከቤት መውጣት አትፈልግም ‹‹በስተርጅና ራቁቴን አልሄድም›› ትላለች፡፡ በሙቀት ሻርፕ ስታደርጊኮ ሰው ይታዘብሻል ስላት..ባሕላችንን ስለማያውቁ ነው ትላለች… እኔ ፍላጎቷን እና እምነቷን መጋፋት ባልወደም የሰመርን ሙቀት ግን እንዴት እንደምትገጥመው ለማየት ጓጉቻለሁ፡፡

ምክር በእንግሊዝኛ ቁጣ በአማርኛ ልጆቼን ይዤ ልጆች ወደ ሚጫወቱበት ሜዳ ወ

ጣሁ፡፡ አጋጣሚ በሰፈሬ የነበሩ ሀበሾችም ልጆቻቸውን ይዘው ሲያጫውቱ አገኘኋቸው፡፡ የፈረንጁም፤ የስፓኒሹም፤ የጥቁሩም ልጅ እንዲሁ በየመጫወቻው ላይ ይንጠላጠላል፡፡የልጆች ጨዋታ መቼም መላ ቅጥ የለው አይደል!

አንዱ የአበሻ ልጅ ከመሬት አፈር እየዘገነ የፈረንጁን ልጅ ያለብሰው ጀመር፡፡ የፈረንጁ ልጅ በሚወርድበትን አፍሪካዊ ቦምብ ተደናግጦ እንደ ጨው ሀውልት ተገትሮ ቀረ! ቆራጡ አበሻ ግን ‹‹ጣሊያንን›› ያገኘ አርበኛ መስሎ አፈሩን መዛቅ እና መርጨት ብቻ ሳይሆን አንኳር አንኳሩን እያነሳ ፈረንጁ አናት ላይ ለማስቀመጥ ይንጠራራ ጀመር፡፡ የፈረንጁ ወላጆች አጋጣሚ የሚሆነውን አይመለከቱም ነበር፡፡ሀበሻዋ እናት ግን ልጇን አይተዋለች፡፡ ፈረንጅ አ

ገር ስለሆነች ግን እንደ ሀበሻ እናት ቁጣዋን በጩኸት አልገለጠችም፡፡ መጀመርያ በፈረንጅኛ ለመጥራት ሞከረች ‹No Honey! Come here!”፡፡ ቆራጡ ሀበሻ ወይ ፍንክች አለና ስራውን ቀጠለ፡፡ አንድ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሀበሻ እናት ሌላ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች ‘አንተን እኮ ነው come here!”፡፡ ይሄኛው ትዕዛዝ ጉራማይሌ ቋንቋ ነው ስለሆነ ሀበሻውን ልጅ ጆሮ ደረሰ፡፡ ቢሆንም አየት አደርጓት ስራውን ቀጠለ፡፡ ለነገሩ! እኔም ብሆን እስካሁን ድረስ በእንግሊዝኛ “አንተን እኮ ነው!” ማለት አልችልም፡፡ ያም ሆነ ይህ ቆራጡ አርበኛ ህጻን የአፈር ቦንቡን መበተን ጀመረ፡፡ ነገሩ በተጀመረ በሶስተኛው ሰከንድ እናት ሦስተኛውን እና ፓስ ወርድ ያለበትን ትዕዛዝ ከመቀመጫዋ ብድግ በማለት እንዲህ ስትል አሰማች ‹‹አንተ ሰላቢ! በጥፊ እንዳልልህ!››፡፡ ሶስተኛው ትዕዛዝ ሀበሻውን ልጅ ሶኬቱ እንደተነ

ቀለበት ሮቦት ድርቅ አደረገው፡፡ ትዕዛዙ በትክክል ሊገባው እንደማይችል እርግጠኛ ብሆንም መልዕክቱ ግን ደርሶታል፡፡ ትዕዛዙ ጆሮውን የሚከፍት ፓስወርድ ይዞ ነበር እና፡፡ ስገምተው ፓስወርዱ ‹‹በጥፊ›› የሚለው ቃል መሰለኝ፡፡ከሀበሻው ልጅ ተንኮል ይልቅ የገረመኝ የእናትዬ

ዋ ቋንቀቋዎች ናቸው፡፡ ከዚያ በላይ ግን የአሜሪካን ልጅ መምከር በእንግሊዝኛ፤ መቆጣት ግን በአማርኛ ቢሆን እንደሚመረጥ ተማርኩ፡፡

በናኦድ ቤተሥላሴ

ጥቂት ደግሞ ስለ አሜሪካውያንየአሜሪካ አንደኛ

በተሰማሩበት መስክ ‹‹የመጀመርያው ሰው›› መሆን ከባድ ቢመስልም በአሜሪካ ባሕል ግን ቀላል ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ በአሜሪካ ሁሉ ነገር ‹‹የ

መጀመርያ›› ባይሆንም የመጀመሪያ ነው፡፡ምሥጢሩ ሁሉንም ነገር በመስኩ ካለው ዝቅተኛው ሬከርድ ጋር ማነጻጸር ነውና፡፡ ይህንን በቀላሉ የምታስተውሉት የአየር ሁኔታ

ሲዘገብ ነው፡፡ 1ኢንች በረዶ ቢዘንብ….በሳምንቱ የመጀመሪያው ከፍተኛ በረዶ ተብሎ ይዘገባል፤ 10 ኢንች ቢዘንብ በወሩ የመጀመርያ ነው፤ 100 ኢንች በረዶ ቢዘንብም….በክፍለ ዘመኑ ‹የመጀመርያው› ተብሎ ይዘገባል፡፡ሁሉም የመጀመርያ ነው፡፡ሩጫ ተወዳድሮ መጨረሻ ስለወጣ አሜሪካዊ

ሯጭ ለመዘገብ መጀመርያ ‹አንደኛ› ወይም ‹የመጀመርያው› የሚሆንበት መንገድ ይፈለግለታል፡፡ ከጥቂት ምርመራ በኋላ ወይ በዕድሜው፤ ወይ በጾታው፤ ወይ በትምህርት ደረጃው፤ ወይ በመጣበት ሀገር፤ ወይ መጨረሻ በወጣበት ሰዓት የመጀመሪያ ሰው እንደሆነ ሲረጋገጥ ‹‹በዚያ ሰዓት ለመግባት የመጀመርያው የሰባ ዓመት ዓዛውንት እንደሆነ ይዘገባል››፡፡ በአሜሪካኛ የመጨረሻውም ሯጭ የመጀመሪያ ነው፡፡እኔ እንዳስተዋልኩት ይሄ ባሕል ‹‹ብሔራዊ የአ

ሜሪካ ሚዲያ አመል›› ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የአሜሪካ ዜና ማሰራጫዎች የሚዘግቡትን ወሬ ‹‹አንደኛ›› ወይ ‹‹የመጀመርያ›› በሚል ቃል የማጀብ የቢዝነስ ሞዴላቸው አካል ነውና፡፡ ይህንን ‹መጀመርያ› የማድረግ አመል ያስተዋልኩት ባለፈው ግንቦት ወር ነበር፡፡ ዋናው የግንቦት ዜናው ‹‹ወ/ሮ ኤለና ኬገን የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ተሾሙ›› የሚል ነበር፡፡ ዘጋቢው ግን ይህንን ደረጃ የሌለው ዜና ደረጃ ፈጥሮለት እንዲህ ብሎ ሲያቀርብ ሰማሁት ‹‹ወ/ሮ ኤሊና ኬገን የከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛዋ ሴት ዳኛ ለመሆን የመጀመርያዋ ሰው ናቸው››፡፡ አያችሁ አራተኛ ለመሆንም አንደኛ መሆን አለ፡፡አሜሪካኖች ‹የመጀመርያነትን› በማጉላት የሚፈ

ጥሩትን የመንፈስ ኩራት፤ እኛ ኢትዮጵያ ሳለን በተቃራኒ መንገድ እናገኘው እንደነበረ ሳስብ ይገርመኛል፡፡ እኛ ‹የመጨረሻነታችንን፤ ታናሽነታችንን፤ ደካማነታችንን› በማጉላት ከፍተኛ የመንፈስ ኩራት እና የቀዳሚነት ስሜት ይሰማን ነበና፡፡ እ

ኛ በቤተክርስቲያን ትሕትና እንለዋለን ምንም እንኳን እነርሱ ‹አይናፋርነት ወይም low self esteem › ብለው ቢያስቡብንም፡፡ በእርግጥ በብዙ ነገር አንደኞች ናቸው፡፡ የእነርሱ

ኢምፓየር ተረኛው የዓለም ታላቁ ኢምፓየር ነውና፡፡ ቢሆንም ግን ለእኔ ‹የመጀመርያ ጉረኛ ሕዝብ ለማየት የመጀመሪያዎቼ›› ናቸው፡፡

ሕግ አክባሪው ‹‹ብጹዕ›› አለቃዬ አለቃዬ ሕግ አክባሪ አሜሪካዊ ነው፡፡ ሥራው ብ

ቻ ሳይሆን ጸባዩም በሕግ አክባሪነት ላይ ነው የተመሰረተው፡፡ ከእኔ አንጻር ሳየው አለቃዬ ሕግ በሚባል ሶፍትዌር የሚንቀሳቀስ ማሽን ነው፡፡ ትሕትናው የሚከብድ አይነት ነው፡፡ ሥራ እንድሰራ ሲያዘኝ እየተሸቆጠቆጠ ነው፡፡የሕግ አከባበሩን ደረጃ አንድ ማስረጃ ልስጣችሁ፡

፡ አለቃዬ ባለፈው ዓመት ለእኔ እና ለስራ ባልደረባዬ የገና ስጦታ ሰጠን፡፡ ልክ አለቃዬ ከቢሮአችን ሲወጣ በክሪስማስ ዲዛይን የተንቆጠቆጠ ፖስታውን ከፈት አድርጌ አየሁት፡፡ ውስጡ ያለው የ20ዶላር ነበር፡፡ ለምን 20? ብዬ አሰብኩ፡፡ መልሱ ከሆነ ሕግ ጋር አንደሚገናኝ ግን ጠርጥሬ ነበር፡፡ በሳምንቱ መኪናዬ ውስጥ ሬዲዮ ሳዳምጥ አንድ የ

ፌዴራል መስሪያቤት ባልደረባ ስለ ሥጦታ ሕጎች ሲያብራሩ ሰማሁት፡፡ 20 ዶላሬም እዛ ውስጥ ነበረች፡፡ ለካ በአሜሪካ ፌዴራል ሕግ መሰረት ቀጣሪ ለተቀጣሪ…ከ20 ዶላር በላይ ስጦታ መስጠት አይፈቀድለትም፡፡ ከ20 ብር በላይ የሆነ ሥጦታ እንደ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ ይታሰብበታል፡፡ አለያ ጉቦ ሊባል ይችላል፡፡ አላልኳችሁም! አለቃዬ ሕግ አክባሪ ነው፡፡

የፈረንጅ ውሸት ኤክስፔንሲቭ ነው… ትልቁ አለቃዬ እና ትንሹ አለቃዬ ሲመካከሩ ጥቂ

ት ቆዩና ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎችም በኋላ ትንሹ አለቃዬ ወደ እኔ ቢሮ መጣና ‹‹ሃይ ኔያድ›› አለኝ፡፡‹‹ሃይ ..››አልኩኝ መልሼ፡፡ጥቂት ስለ ዕለቱ ሥራችን፤ ጥቂት ስለ አየሩ ሁኔ

ታ ካወራን በኋላ ትንሹ አለቃዬ ‹‹ዶክተሩ፤ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ከላቦራቶሪው ጎን ያለውን ቢሮ አንተ እንድትገባበት ፈልጓል፡፡›› አለኝ፡፡ ከእኔ መልስ ሳይጠብቅ ቀጠለ ‹‹በእርግጥ ዞሮ ዞሮ ብዙ ስራህን የምትሰራው እዚህኛው ቢሮ ስለሆነ ይሄንን ቢሮህን አትለቅም፤ ነገር ግን አልፎ አልፎ ላይኛው ላቦራቶሪ ለምትሰራው ሥራ አዲሱን ቢሮህን ትጠቀምበታ

ለህ አለኝ፡፡››ጥቂት ቆይቶ ግን የሆነ ነገርም ነገረኝ፡፡ ቆይ! የነገ

ረኝ ምን እንደሆነ እነግራችኋለሁ፡፡በዚያው ሳምነት ውስጥ ቢሮዬን ተረከብኩ፡፡ ስ

ሜ በሩ ላይ ተለጠፈ፡፡ ግድግዳው ምን ዓይነት ቀለም ይቀባልህ ተባልኩ፡፡ ‹‹አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ›› ሳልላቸው ቀድመው የቀለም መምረጫ ‹‹ሜኑ›› ሰጡኝ፡፡ ቶሎ ብዬ የሌሎቹ ቢሮዎች የተቀቡበትን ቀለም ኮረጅኩ፡፡ ነጭ ነው፡፡የቀለም ሜኑው ውስጥ ‹‹ነጭ›› የሚለውን ሳወ

ጣ፤ የትኛው ዓይነት ነጭ የሚል ምርጫ ቀረበልኝ፡፡ ‹‹ነጭም ዓይነት አለው አንዴ?›› አልኩ በሆዴ፡፡ ከዚያ በጣም ነጩ ‹‹ሥጋ ቤት›› እንዳይመስለኝ ለራሴ ሰግቼ ‹‹ኤግ ዋይት›› የሚል መረጥኩ፡፡ በኋላ ሲቀባ ሳየው ‹‹ቆሻሻ ዋይት›› መሆኑን አወቅሁ፡፡ወለሉስ ምን ይሁንልህ፤ ቀለሙስ፤ ኮርነሩስ…ተ

ባልኩ፡፡ በዳበሳ እና በአቦ ሰጡኝ መረጥኩላቸው፡፡ የፈረንጅ ነገር…ሁሉን ነገር ከምር ይቆጥራሉ…የመረጥኩትን ስሙንም ቀለሙንም የማላውቀውን ‹‹ታይል›› ወለል አደረጉልኝ፡፡ለብቻዬ ስልክ መስመር ገባልኝ፤ ተጨማሪ ኮም

ፒውተር፤ መጽሐፍት መደርደሪያ ወዘተ..ተደገረልኝ፡፡ በምርጫዬ ማለት ነው፡፡ይሄን ሁሉ ሳሰራ እና ስሰራ ግን ፕሮፌሰሩ ለኔ ቢ

ሮ ለመስጠት ያሰበበትን ምክንያት ያልሰማሁ መስሎታል፡፡ ትንሹ አለቃዬ ወሬውን መጀመርያውኑ አሾልኮልኝ እንደነበር አያውቅም፡፡ዩኒቨርሲቲው የንብረት ቆጠራ ሲያካሂድ፤ ትርፍ ቢሮዎችን እና ከአቅም በታች ጥቅም ላይ የዋሉ ቢሮዎችን አብሮ ይገመግማል፡ ከዛም ቢሮ ለቸገረው ይሰጣቸዋል፡፡ ተጨማሪ ቢሮ የተለገሰኝም፤ ቢሮው እንዳይወሰድ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ሳለን፤ ባለሥልጣን መጣ ሲባል፤ ወይ

ም በንብረት ቆጠራ ጊዜ የምናደርገው ሁሉ ትዝ አለኝ እና ‹‹ሰዎች ስንባል መሰረታዊ ጠባያችን አንድ ነው! አገላለጹ ይለያያል እንጂ›› የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስኩ፡፡ ቢሮውን ለማዳን ጥሩ ሰበብ ሆኜ ባገለግልም፤ ልጠቀምበት ግን አልቻልኩም፡፡ ለሁለት ቢሮ የሚበቃ ሥራ የለኝምና፡፡ እናም ግርግሩ ሲያልፍ፤ ስሜን ከበሩ ላይ ቀ…ስ…አንስቼ፤ አቀብለው ለተባልኩት ሌላ ጡረተኛ ፕሮፌሰር አቀበልኩት፡፡ አንዳንዴም ፈረንጅ ቤት እንዲህ ይደረጋል፡የፈረንጅ ውሸት ግን ኤክስፔንሲቭ ነው፡፡ ቢሮውን የእኔ ለማስመሰል የወጣውን ብር አስቡ፡፡

ይህ ጹሁፍ ከናኦድ ቤተሥላሴ ጡመራ ናኦድ ላይቭ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ

እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

ወላጆቻችን በአሜሪካ ብዙ ወላጆች ሲያረጁ በልጆቻቸው ፈቃድ ላይ ይ

ወድቃሉ፡፡ በተለይ ወላጆች አሜሪካ ሲመጡ፤ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያለው ስልጣን ገደብ የለሽ ነው፡፡ ይህንን ሥልጣናቸውን በቅጡ የሚጠቀሙበት እንዳሉ ሁሉ፤ ወላጆቻቸው ‹እምቢ› ለማለት እስካይችሉ ድረስ ወላጆቻቸውን የሚጫኑ ልጆችም አሉ፡፡ አንዳንዴ ወላጆች ተራ ነገርን እንኳን ለራሳቸው መወሰን እስካይችሉ ድረስ ሥልጣነ ቢስ ይሆናሉ፡፡ጓደኛዬ አባቱን ከኢትዮጵያ ስላመጣ እንኳን ደስ

ያለህ ለማለት ወደ ቤቱ ሄድኩኝ፡፡ አባቱን ኢትዮጵያ በደንብ አውቃቸው ስለነበረ አባቱን ለማግኘትም ጓጉቼ ነበር፡፡ አባቱ ደስ የሚል፤ ግርማ ሞገስ ያለው፤ ነጭ የበዛበት ረዘም ያለ ጢም አላቸው፡፡ ለእኔም ሆነ ኢትዮጵያ ለምናውቃቸው ሰዎች ያ ጢም መለያቸው ብቻ ሳይሆን ደስ የሚል ግርማ ሞገሳቸውም ነበር፡፡ ‹አሜሪካዊ› ልጃቸው ግን ካደረገላቸው የመጀመርያ እንክብካቤ አንዱ ጢማቸውን እንዲቆረጡ ማድረግ ነበር፡፡ ማለቴ እንዲላጩ፡፡ እኔ በሰው አባት ባያገባኝም..ሽማግሌ ሰላም ልል ሄጄ፤ ወጣት ለመምሰል የሚታገል ሰው አይቼ መመለሱ አላስደሰተኝም፡፡ የልጅ ሥልጣን መስመር የሳተ መሰለኝና ቅር አለኝ…በቅርቡ አንድ ጎረቤቴ ደግሞ እናቷን ልታመጣ ጉ

ድ ጉድ እያለች ነው፡፡ ለእናቷ ልታደርግ ያሰበችው

በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉበ+256-778-693669 ይደውሉልን

ወግ ከሀገረ አሜሪካ

(ታሪኩ አዳፍሬ ከኬንያ)

Page 5: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 5

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ የካምፓላ መንገዶች ጭር ብለዋል። ቀኑ ዕለተ ሰን

በት እንደመኾኑ አብዛኛው የከተማው ማርፈጃውን ከቤቱ እንኳን አልወጣም። ጥቂት ሰዎች በእጃቸው ያንጠለጠሉትን መጽሐፍ ቅዱስ እንደያዙ ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው ያዘግማሉ።በካባላጋላ አቅራቢያ የሚገኘው እና ኪቡሊ ተብ

ሎ በሚጠራው የሙስሊሞች አካዳሚ የነበረው ትዕይንት ግን ለየት ያለ ነው። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያለው አቧራማ ሜዳ በስፖርተኞች ተሞልቷል። እዚህም እዚያም ኳስ የሚጫወቱ ሰዎችይታያሉ። ሰዓቱ ወደ ሦስት ሰዓት ተኩል ግድም

ሲጠጋ በቡድን ተከፋፍለው ሜዳው ላይ ሲጫወቱ የነበሩ አዳጊዎች ገለል ተደርገው ቦታው ለሁለት ቡድኖች ተለቀቀ።በአንደኛው ወገን ቢጫ ማልያ የለበሱ ዩጋንዳውያ

ን ተደረድረዋል። ሁሉም “ሪም ዲስትሪቢዩተር” በተባለ የፔፕሲ ኮላ ምርቶች አከፋፋይ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ናቸው። በሌላኛው ወገን ያሉት ደግሞ ቅይጥ ናቸው። ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና ዩጋንዳውያን “የኢትዮጵያ የጤና ስፖርት ክለብ” በሚል ስያሜ በሚጠራው የእግር ኳስ ክለብ ውስጥተሰባስበዋል። ብዙዎቹ ለልምምድ ስሪቱ የተለያ

የ ባለ ሰማያዊ ቀለም ማልያ ለብሰዋል። ዕድሜያቸው እና አቋማቸውም እንደ መለያ ሹራባቸው የተዥጎረገረ ነው። በሰውነት የገረጀፉ፣ ለመንቀሳቀስ የሚቸገሩ የሚመስሉ እና በዕድሜ የገፉ እንዳሉ ሁሉ፤ ኻያዎቹ ውስጥ እንኳ ያልደረሱ፣ ሮጠው ያልጠገቡም አሉበት።ጨዋታው ተጀመረ። ሐበሾች የተሰባሰቡበት የጤ

ና ቡድን በተቃራኒው ቡድን ላይ ጫናው አይሏል። የዐሥራ ሰባት ዓመቱ ኤርትራዊ ኢሳያስ ዮሐንስ ጥሩ ጥሩ ኳሶችን ይሞክራል። እምብዛም ሳይቆይ ከሙከራዎቹ መካከል ሁለቱ ኳሶች ወደ ጎል ተቀየሩ። ልጁ ከርቀት አክርሮ የሚመታቸው ኳሶች ለግብ ጠባቂዎቹ አስቸጋሪ ናቸው። የሐበሾቹ ቡድን አሁንም ማጥቃቱን ቀጥሏል። ዕረፍት መድረሱን የሚያበስረው ፊሽካ ከመነፋቱ በፊት የጤና ቡድኑ በተቃራኒው ቡድን ላይ ሁለት ተጨማሪ ጎሎች አስቆጠረ።የተዳከመ ይመስል የነበረው የዩጋንዳውያኑ ቡድ

ን በርካታ ተሳላፊዎችን ከከቀየረ በኋላ ነፍስ ዘራ። ሦስት ተከታታይ ጎሎችን በኢትዮጵያውያኑ መረብ ላይ አሳርፎ ድሉን ለመቀማት የተዘጋጀ መሰለ። ጸሐይቱ እየከረረች መጥታለች። የጤና ቡድን አባላት ሙቀት ያስገራቸው ይመስላሉ። ነገር ግን ወደ ጎል እየተጠጉ ማጥቃታቸውን አላቆሙም። ሁለት ተጨማሪ ጎሎችን አከሉ። ጨዋታውንም አምስት ለሦስት በኾነ ውጤት አጠናቀቁ። በእንዲህ ያሉ አነስተኛ ግጥሚያዎችም ኾነ በሌሎች የወዳጅነት ጨዋታዎች ቡድኑ አብዛኛውን ጊዜ ድል የማይለየው እንደኾነ የጤና ቡድኑ መሥራች አቶ ካሣ መንግስተአብ ይናገራሉ።ከፓኪስታን እና ከሶማልያ ማሕብረሰብ የእግር ኳ

ስ ቡድኖች ጋራ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በምሳሌነት የሚጠቅሱት አቶ ካሣ ከአንዱ በስተቀር በሁሉም ጨዋታዎች ማሸነፋቸውን በኩራት ይገልጻሉ፡፡ “አንዱንም ቢኾን ተጋጣሚያችን የነበረው የሶማልያ ማሕበረሰብ ሁልጊዜ እያሸነፍነው ሲቸገር ከናይሮቢ ፕሮፌሽል ተጫዋች አምጥቶ በማስገባት ነው ያሸነፈን”ይላሉ፡፡ ያም ቢኾን ግን በአንድ ጎል ልዩነት ብቻ የተጠናቀቀ ስለነበር “እንደሽንፈት አይቆጠርም” ባይ ናቸው። እርሳቸው ቡድኑን እንዲህ ይመልከቱት እንጂ ለ“ሪም ዲስትሪዩቢተር” ቡድን ተቀያሪ ተሰላፊ የነበረው የሰላሳ ዓመቱ ዩጋንዳዊ ሙሳጃ ያሲን ግን የኢትዮጵያውያኑን ቡድን “ደህና” የሚባል ነው ሲል ይገልጸዋል። የአጥቂውን ክፍል እያደነቀ የሚያወራው ሙሳጃ

ተከላካዮቹ ጋራ ሲደርስ ግን ሳቅ ይቀድመዋል። ሙሳጃ ያልተረዳው ነገር በግንቦት 28ቱ ጨዋታ ወደ ሜዳ የገባው የጤና ቡድን አብዛኞቹ ቋሚ ተሰላፊዎቹን አለማካተቱን ነው። ብዙዎቹ ቋሚ ተሰላፊዎች ከሁለት ቀን በፊት የኤርትራን የነጻነት በዐል ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ጨዋታ ላይ በመሳተፋቸው ወደ ሜዳ ብቅ አላሉም። የመጡትም ቢኾኑ ወደ ሜዳ ለመግባት የሚያስችል ጉልበት አልነበራቸውም። በዕለቱ የነበረው ተሳትፎ እና ጨዋታ ከወትሮው ቀዝቀዝ ይበል እንጂ ቡድኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ያሳካ ነበር- “ኢትዮጵያውያንን እያሰባሰቡ እሁድ እሁድ ኳስ መጫወት።”

የዐሥር ዓመቱ አዳጊ እንዲህ ዘወትር እሁድ ኳስ ይዞ ሜዳ መውረድ የ

ተጀመረውም ያኔ ነበር። ያኔ በቁጥር አነስተኛ የነበሩት ኢትዮጵያውያን በሚገናኙባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ከአፋቸው ከማይነጥሏቸው ወሬዎች መካከል አንዱ እግር ኳስ ነበር፡፡ ስለ አገር ቤትም ኾነ ስለ ውጭ አገር ቡድኖች ወቅታዊ ውጤቶች እና አቋሞች እያነሱ ከመጨዋወት እና እሰጥ አገባ ከማለት ባሻገር ኢትዮጵያ እያሉ በግል ያዘወትሩት ስለነበረው የእ

ግር ኳስ ጨዋታ እየተረኩ በትዝታ መቆዘምንም እንደ ልማድ አድርገውታል። ከቁዘማ ወጥተው ዳግም እግራቸው ከኳስ ጋራ እንዲገናኙ የሚያስችለውን ሐሳብ አቶ ካሣ አቀረቡት።“አስታውሳለሁ ቀኑ ቅዳሜ ነበር፡፡ ያን ቀን የተለመ

ደው ወሬ ሲነሳ ለምን እንዲህ ተቀምጠን ከምናወራ ነገ ጠዋት ተገናኝተን ኳስ እንጫወትም? ሁሉም ሸራ ጫማውን ይዞ ይምጣ። ኳሱን መረቡን እና የመሳሰሉትን እኔ አመጣለሁ አልኩኝ” ይላሉ አቶ ካሣ ወደ ሁዋላ ተመልሰው ሐሳቡ የተጸነሰበትን ኹኔታ ሲያስረዱ። ሐሳቡን የተቀበሉት ትጥቃቸውን አሟልተው ሜዳ ተገኙ። ከእነዚህ ጥቂት ሰዎች መካከል አሁን የሄንከን ዋና አከፋፋይ የኾኑት አቶ ክፍሌ ደገፉ ይገኙበታል። የመጀመሪያው ጨዋታም ያለምንም የቅድሚያ ልምምድ ተደረገ፡፡ ለረጅም ሰዓት በሞራል ሲጫወቱ ያረፈዱት ተጫዋቾች ከፍጻሜው በኋላ መራመድ እንኳ አቃታቸው።“ማን ይንቀሳሰቀስ፤ ሁላችንም ‘ስትራፖ’ በ’ስትራ

ፖ’ ኾንን፡፡ በዚያ ላይ የአንዳንዶቻችን ዕድሜም ገፍቷል፡፡ ሁላችንም የማንደባበቀው ነገር ደግሞ አንዳንድ ሱሶችም አሉብን፡፡ እናም እነርሱን ከ‘ስትራፖው’ ለማስወጣት ሳውና፣ ማሳጅ ማስደረግ እየ

ተባለ ሌላ ወጪ… መከራችንን ስናይ ሰነበትን” ይላሉ አቶ ካሣ ጅማሬውን በፈገግታ ታጅበው እያስታወሱ፡፡ተጨዋቾቹ በመጀመሪያው ዕለት ያጋጠማቸውን

የሰውነት መሳሳብ እና ድካም በቀጣዩ እሁድ ከሜዳ እንዳይገኙ አላደረጋቸውም። እሁድን እየጠበቁ በየሳምንቱ ከሜዳ መገኘት ቀጠሉ። ከእግር ኳስ ጨዋታው ባሻገር ያለው ብሽሽቅ፣ ተረብ እና መተሳሰብ እሁድን ተናፋቂ ቀን እንዲኾን አደረገው። ኳሱ ሜዳ ላይ ቢያልቅም ጨዋታው ግን ምሳ በጋራ እየተበላም ይቀጥላል። በኳስ የደከመ ሰውነትን አሳርፎ ሻይ ቡና እየተባለም አይቋረጥም። ስፖርታዊ ወንድማማችነቱ የፈጠረው ቁርኝት ሁለት ወራትን ተሻገረ። የኑሮ አቅማቸው እምብዛም የማያወላዳ ስደተኞችን በአብዛኛው ያካተተው ይህ ስብስብ ከኳስ ጨዋታ በኋላ ለ“ላብ መተኪያ” የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማሟላት እየከበደው መጣ። በዚህ ወቅት ነው አቶ ካሣ ሌሎችን ማማከር እንዳለባቸው የወሰኑት።አቶ ንጉሴ ባልቻ፣ አቶ ዘላለም ሀብታሙ፣ አቶ ተ

ካልኝ (በቅጽል ስማቸው ሻፍት) ይጠሩና ወደ ቡድኑ እንዲቀላቀሉ ይጋብዟቸዋል። አቶ ክፍሌም ከተጋባዦቹ መካከል ነበሩ። ሐሳቡ የቀረበላቸው ግለሰቦ

ች ምንም እንኳን የአቶ ካሣን ሐሳብ ቢወዱትም ዝም ብለው ሊቀበሉት ግን አልፈቀዱም፡፡ ይልቁንም በቅድመ ኹኔታ ሊያዙ እና ሊታዩ ይገባቸዋል ያሏቸውን ሐሳቦች አስቀመጡ፡፡“ስፖርተኞች ኾነን ስላደግን [ቡድኑን] መቀላቀል

እንፈልጋለን። በቴክኒክም ኾነ በገንዘብ ለመርዳት እንችላለን። ግን ስደተኛ እየበዛ ከመምጣቱ የተነሳ ‘የታባህ’፣ ‘የታባሽ’ መባባል አንፈልግም። ክብራችን እና የቤተሰባችንን ክብር መጠበቅ እንፈልጋለን አሉኝ” ይላሉ አቶ ካሣ የግለሰቦቹን ቅድመ ኹኔታ መለስ ብለው ሲያስታውሱ። አቶ ካሣ የቡድኑን አባላት ማማከር ሳያስፈልጋቸው “ሙሉ ሐላፊነት” ለመውሰድ ይስማማሉ። በስተኋላ የቡድኑ ቁልፍ ሰዎች የኾኑት እነዚህ ስፖርት ወዳድ ግለሰቦች በቀጣዩ እሁድ ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው ሳምቢያ ሜዳ ተገኙ፡፡ሳምቢያ የሚገኘው ሜዳ የጤና ስፖርት ቡድኑ ጨ

ዋታ አሃዱ ተብሎ የጀመረበት ቢኾንም አፈር ይበዛው ስለነበር ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መለወጡ ግድ ነበር። ሌላ ቦታ መፈለግ ተጀመረ። በአህጉራዊ ውድድሮች አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክለቦች ጋራ በተደጋጋሚ የተጫወተው “ቪላ” ሳር ያለው እና ለ

መጫወቻ ምቹ የኾነ ሜዳ እንዳለው እነ አቶ ካሣ ይመለከታሉ። የክለቡን ሐላፊዎች አስፈቅደው የኢትዮጵያውያን ጤና ክለብ አባላት እየተገናኙ በቪላ ሜዳ መጫወት ጀመሩ፡፡

ማሕበራዊ ጤናነገሮች ሁሉ መሥመር የያዘለት የጤና ቡድን

እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም ከዩጋንዳ መንግሥት ሕጋዊ እውቅና አገኘ።ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀረ፤ ሊቀመንበር ሾ

መ። የራሱን ጠበቃም ቀጠረ። የጤና ቡድኑ ስኬት በርካቶችን ሳበ። የተጨዋቾቹ ቁጥርም ሦስት እና አራት ቡድን መመሥረት የሚያስችለው ደረጃ ድረስ አደገ። “የኢትዮጵያውያን ጤና ስፖርት ክለብ በካምፓላ ስሙ ገነነ። በጣም ብዙ ወጣቶች መምጣት ጀመሩ:፡ ቁጥሩ ከአቅም በላይ ኾነ” ይላሉ የአሁ የክለቡ ሊቀመንበር አቶ ንጉሴ ባልቻ።የአባላቱ ቁጥር መጨመር በቡድኑ ውስጥ የነበረ

ውን የአንድነት መንፈስ ይበልጥ እያጠነከረው መጣ። በግል ጉዳይ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት በጠበኝነት የቆዩ ያለማንም ሽምግልና ሜዳው አስታራቂ ኾኗቸው በመካከላቸው ጥል ቀርቶ ሰላም ሰፈነ፡፡ አንዳንዴ ከከተማ ወጣ እያሉ ኳስ መጫወት እና መዝናናትም ታከለበት። ከአባላት መካከል ተሳክቶለት ወደ ሌላ አገር የሚሄድ አባል ሲኖር ውሃ ዳር (ቢች) ተወርዶ፣ በግ ታርዶ እና ስጦታ አዘጋጅቶ መሸኘት ባህል እየኾነ መጣ። “ካልተሳሳትኩ ከእኛ ጋር ሲጫወቱ የነበሩ 100 ያህ

ል ስደተኞችን ወደተለያየ አገር ሸኝተናል፡፡ አቅም ያላቸውን ድግስ ደግሰን ስጦታዎችን አበርክተን፣ አቅም የሌላቸውን ደግሞ ለትራንስፖርት እና መሰል ነገሮች ከቡድኑ አባላት ድጋፍ በማድረግ ሸኝተናል” ይላሉ አቶ ካሣ።በጤና ቡድኑ አባላት ዘንድ የነበረው የእርስ በር

ስ መተሳሰብ እና መረዳዳት ትሩፋቱ ወደ ሌሎችም ተሻገረ።ለቤተክርስቲያን እገዛ ሲያስፈልግ በበገንዘብም ኾነ

በጉልበት መርዳት፤ የተቸገሩትን በአቅም ማገዝ፤ የሞቱትን መቅበር፤ አስክሬናቸውን ወደ አገር ቤት የሚሄደውንም ከቤተሰባቸው ጋራ በመካከር መላክ የጤና ቡድኑ ተጓዳኝ ሥራዎች ኾኑ። በዚያ ላይ በየጊዜው ቁጥሩ የሚጨምረውን ስደተኛ ተቀብሎ ማስተናገድም አለ። ጤና ቡድኑ ከተነሳበት ዓላማ ባሻገር ብዙ ሥራዎችን በማከናወን መጠመዱን ያዩ አባላት መፍትሄ አፈላለጉ።“የሰው ቁጥር ሲጨምር ማሕበራዊ ችግሮችም በ

ጣም እየጎሉ ሲመጡብን ጊዜ ‘ምን እናድርግ?’ አልን” ይላሉ አቶ ንጉሴ። ይህ ጥያቄ አቅም ያላቸውን የተወሰኑ ኢትዮጵያንን ጠርቶ የማማከር መፍትሄን ወለደ። እናም ስብሰባው ተጠራ። በስብሰባው ላይ የተገኙ እና የማሕበራዊ ችግሮቹን አሳሳቢነት የተረዱት ተሰብሳቢዎች በአንድ ድምፅ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ራሱን ችሎ መመሥረት እንዳለበት ይወስናሉ። ይህ ስብሰባ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2005 ዓ.ም ለተመሠረተው በዩጋንዳ የኢትዮጵያውያን ማሕብረሰብ የመሠረት ድንጋይ የጣለ፣ ለጤና ቡድኑ ደግሞ ሸክሙን ያቀለለት ነበር።ማሕበራዊ ጉዳዮችን ለማሕበረሰቡ ያስረከበው የ

ጤና ቡድኑ የተነሳበትን ዓላማ ወደማስፈጸም አዘነበለ። “ቡድኑ ኳሱ ላይ ትኩረት አደረገ። የወጣቶቹ እና ታዳጊዎቹ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እነርሱን ማሰባሰቡ ላይ በጣም ትኩረት ሰጠንበት” ይላሉ አቶ ንጉሴ።

ከኳስ በላይ…ኳስ ተሰባስቦ መጫወት እንደ ቀላል ነገር ተደርጎ መታ

የት እንደሌለበት የሚናገሩት አቶ ንጉሴ ጨዋታው “የላቀ አስተዋጽኦ” ያበረክታል ባይ ናቸው። “ባህላችን ጠንካራ ነው። ነገር ግን የእርስ በርስ ግንኙነታችን ደካማ ነው። ጤና ቡድን ማለት መገናኛ ማለት ነው። በኳሱ ሰበብ ተገናኝተን፣ ተጫውተን ግንኙነት መፍጠር ነው” ይላሉ።የተለያየ አመለካከት ይዞ ወደዚህ አገር የሚመጣ

ው ሰው ከመከፋፈል እና ለብቻ ከመቆም ይልቅ በእግር ኳስ አማካኝነት እንዲሰባሰብ ይደረጋል ሲሉ ያብራራሉ።“ኳስ ራሱ ፍቅር ነው። ሁሉንም በአንድ ያሰባስባ

ል” ይላሉ አቶ ንጉሴ። የዚህን አባባላቸውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። ራሳቸው የሚመሩት ቡድን የዜግነት ስብጥር አንዱ ምስክር ነው። በጤና ቡድኑ ውስጥ የኤርትራ፤ ኡጋንዳ፤ ሩዋንዳ እና ኮንጎ ተጨዋቾች እንደተካተቱበት ከቡድኑ ሰባት የሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ የኾኑት አቶ ካሣ ያስረዳሉ፡፡ በቁጥር ግን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ያመዝናሉ።“ድሮም ጀምሮ ይኼ ኤርትራዊ ይኼ ኢትዮጵያዊ

የሚባል ነገር የለም። ያንን ነገር አታስታውሰውም” ይላሉ አቶ ካሣ ከቡድኑ ታሪክ እያጣቀሱ። የወቅቱ የቡድኑ ሊቀመንበር አቶ ንጉሴም “ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሚባል ነገር የለም። እከሌ እንደ

ከኳሱ ባሻገር

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

የጤና ቡድኑ ሲመሰረት ከነበሩት አባላት አብዛኛዎቹ ወደ አሜሪካ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ ተጉዘዋል

የጤና ቡድኑ መስራች አቶ ካሣ መንግስተአብ በጤና ምክንያት እግር ኳስ ጨዋታ ካቆሙ ሶስት ዓመት ተኩል ቢያልፋቸውም ወደ ሜዳ ብቅ ማለትን ግን አልተዉም

ኢሳያስ ዩሐንስ (ከግራ ወደ ቀኝ ሶስተኛው) እና ሌሎች አዳጊዎች የጤና ቡድኑ የወደፊት ተስፋዎች ናቸው

የጤና ቡድኑ በአነስተኛ ግጥሚያዎችም ኾነ በወዳጅነት ጨዋታዎች አብዛኛውን ጊዜ ድል አይለየውም

በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

ፎቶ

- ካሣ

መንግ

ስተአብ

ፎቶ

ዎች

- ተስፋ

ለም ወ

ልደየ

Page 6: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)6 ሀበሻዊ ቃና

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

የማኅደረ ጊላይ የለጋነት ዕድሜ እንዲሁ እንደ ዐይን ጥቅሻ እያለፈ ነው። ወደ ኋላ ተመልሶ ሲያስብ ደስ የሚል ነገር ትዝ አይለውም።ሕይወት ልክ ከማ

ለዳ ጣፋጭ እንቅልፍ እንደሚያባንኑት አስፈሪ የልጅነት የተረት ጭራቆች የተሞላች ትመስለዋለች:: ተረት የሚመስሉ ታሪኮችን እየኖረ፣ እየሰማ እና እየታዘበ እዚህ ደርሷል። መባረር፣ ስደት፣ ሞት… እና በትዝታ መዋትት በሕይወቱ ውስጥ እስካሁንም ይገለባበጣሉ።

የናይሮቢ እምብርትሰሞኑን ከናይሮቢ 500 ኪሎ ሜትር ርቀ

ት ላይ ከሚገኘው የካኩማ ስደተኞች ካምፕ ወደ ኬኒያ መናገሻ ከተማ ብቅ ብሏል። ለእርሱ ጉዞ አዲስ አይደለም፤ ስንቱን ተጉዟል። ገና የዐሥራዎቹን አጋማሽ በቅጡ ሳይደፍን ከተወለደባት እና አፈር ፈጭቶ ካደገባት አዲስ አበባ እስከ አሥመራ ያለውን 1176 ኪሎ ሜትር አይረሴ ጉዞ አድርጓል። ጉዞው ግን እንደዚህኛው በፍቃዱ የተደረገ አልነበረም። ያልተጠበቀ እና በስሜት ምስቅልቅል የተሞላ ነበር። ደም አፋሳሹ እና ትርጉም የለሹ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ከኢትዮጵያ ተባርሮ አሥመራ ገባ። ከአባቱ ጋር።ትውልደ “ኤርትራዊ” በመኾናቸው ምክ

ንያት የመባረር ዕጣ እንደገጠማቸው የስሚ ስሚ ቢሰማም ለጋ ዕድሜው ከአባቱ ጋራ የተባረረበትን ምክንያት በቅጡ እንዳይረዳው አድርጎት ነበር። “እኔ በወቅቱ እንኳን በሩቅ የማውቃትን ኤርትራን ቀርቶ ተወልጄ ያደግኩባት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ምን እንደሚመስል የማሰላስልበት ብስለት ላይ አልደረስኩም። ከትልቁ የዜግነት ጉዳይ ይልቅ የሠፈር ልጅነት ለእኔ ትርጉም ነበረው” ሲል ወደ ኋላ ተመልሶ ያስታውሳል። “‘የጨርቆስ ልጅ’ መባል ያኮራ ነበር” ይላል ማኅደረ የልጅነት ጣፋጭ ጊዜውን ያሳለፈበትን ሰፈር እያሰበ። “የጨርቆስ ልጅነቴን የምገልጸውን ያህል እንኳ ዜግነት የሚባለው ነገር ሳይገባኝ ነው አሻግረው “አባ ሻውል”(አስመራ ውስጥ የሚገኝ ሠፈር) የወረወሩኝ።”ለማኅደረ የአዲስ አበባው ጨርቆስ እና የ

አሥመራው አባ ሻውል የሚመሳሰሉበት ነገር እንዳላቸው ታይቶታል። ሁለቱ ሰፈሮች ስማቸው ከድህነት ጋራ ተያይዞ ይጠራል። አባ ሻውል በምርጥ ፕላኗ በማትታማው አሥመራ ላይ ያለ ቢኾንም እንደ ጨርቆስ እና መሰል የአዲስ አበባ ሰፈሮች “የድኻ » የሚባል መንደር ነው። ገዛ መንዳ ሐበሻ ከአባ ሻውል ጋራ የሚጠቀስ ሰፈር ነው-በአስመራ። ልክ እንደ አዲስ አበባዎቹ የአራት ኪሎን አሮጌ ቄራ እና የፒያሳው ሠራተኛ ሠፈር አይነት።ማኅደረ አባ ሻውልን ለመልመድ አልተቸ

ገረም። ድህነቱም፣ የ”አራዳ” ልጅነቱም ረድቶታል። ግን አንድ ነገር ሙሉ በሙሉ የአባ ሻውል ልጅ እንዳይኾን ልጓሙን ይይዝበታል። አዲሶቹ ጓደኞቹም እንደ አንዱ የሠፈራቸው ልጅ እንጂ የማንነታቸው አካል አድርገው ለመቁጠር አልፈቀዱም። “ለእነርሱ ኤርትራዊ አይደለሁም፤ ኢትዮጵያዊም አይደለሁም” ይላል። “ለእነርሱ ማኅደረ “አምቼ” ነው። ብዙዎች የሚጠሩትም “አምቼው” እያሉ ነው።

“አምቼ”…? የምን አምቼ?“ይኼን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁ

ት አባ ሻውል ላይ ነው” አለ ማኅደረ “ስለአምቼነቱ” የሰማበትን ቀን እያስታወሰ።“አንዱ ጓደኛዬ በጨዋታ ላይ እንዲህ አለኝ። “ኻብ ሠፈርካ ዕንታይ ከምዝብልካ ትፈልጥ ዶ?” (ምን እንደምታባል ታውቃለህ?) እኔ አዲስ መጤ ምን ሊሉኝ ይችላሉ በሚል ግርምት “አይፈልጥን” ብዬ መለሰኩለት። ያን ጊዜ “አምቼ” መኾኔን ነገረኝ።” የጓደኛውን ገለጻ ተከትሎ ማኅደረ ከሌሎች ኤርትራውያን “የተለየ ዜጋ” መኾኑ ይሰማው ጀመር። ማኅደረ አይወቀው እንጂ “አምቼ” የሚለው ስያሜ እርሱ አዲስ አበባ እያለ አገልግሎት ላይ ውሎ ነበር።

ቢኒያም ፍስሐ...ጁባ የሚኖረው የ40 ዓመቱ ቢኒያም ፍ

ስሐ ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ ጋራ የኖረው አዲስ አባባ 22 ማዞሪያ አካባቢ ነው።

ቢኒያም “አምቼ” የሚለውን መጠሪያ በደርግ ጊዜ አዲስ አበባ እያለ መስማቱን ይናገራል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ለተወለደ ኤርትራዊ የተሰጠ መጠሪያ ነበር። ቃሉ የሚገልጸው ኢትዮጵያ ውስጥ መገጣጠሙን ነው” ይላል። መጠሪያው በአንድ ወገን ኤርትራዊ ከኾኑ ወይም ከሁለት ኤርትራውያን ወላጆች ለተወለዱ ዜጎች የሚውል ነው። ስሙ የተወሰደው አዲስ አበባ ከሚገኘው እና በኢትዮጵያ መንግሥት እና በጣሊያኑ የመኪና አምራች ድርጅት ፊያት መካከል በተደረገው ስምምነት ከተቋቋመው “አምቼ”(AMCE) ኩባንያ ነው። የመኪናው አካላቶች ጣሊያን ተመርተው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገጣጠሙ ሁሉ “አምቼዎች” ኢትዮጵያ ውስጥ “የተገጣጠሙ” የሚል ትርጓሜ ይሰጣል።አምቼነት ከኤርትራ ጋራ ብቻ አይቆራኝ

ም። ከኢትዮጵያ በተለይም ከአዲስ አበባ ጋራ ባለው ጥልቅ ትሥሥርም ይገለጻል። አሥመራ ላይ “አምቼዎች” በነገረ ሥራቸው ተለይተው ይታወቃሉ። “ብዙ ኤርትራውያን አማርኛ ቋንቋን የሚናገረው አማራ ብቻ ይመስላቸው ነበር። ከ1990 ዓ.ም በኋላ ብዛት ያላቸው አምቼዎች ከኢትዮጵያ ተባርረው አሥመራን አጥለቀለቋት” ይላል ቢኒያም። ከዚያ በኋላ አምቼዎችን አሥመራ ውስጥ ለመለየት ቀላል ነበር። አማርኛ የሚናገሩ፣ በአረማመዳቸው፣ በአለባበሳቸው፣ በአንጻራዊ መልኩ በተላበሱት ግላዊ ነጻነት ይታወቃሉ። የአማርኛ ሙዚቃ በአሥመራ እንግዳ በኾነ መልኩ በስፋት የሚያዳምጡትም አምቼዎች ነበሩ።“አምቼ” መባል የመገለል ስሜት የሚፈ

ጥርባቸው እንዳሉ ሁሉ ብዙዎች እንደማንነታቸው መገለጫ ይጠቀሙበታል። እንዲያውም የኩራት ምንጭ አርገው የሚወስዱትም አሉ። ኢየሩሳሌም ኀይሌ የከፈተችው “አምቼነቴን እወደዋለሁ” የሚለው አምቼዎች እየተገናኙ የሚጨዋወቱበት የፌስቡክ ገጽ በየቀኑ አባላቱን እያበዛ ነው። በመላው ዓለም የተበተኑ አምቼዎች እየተገናኙ ስለገጠማቸው እና ስለኾነባቸው ነገር ሁሉ የሚወያዩበት ገጽ ነው።“አምቼ”ዎች በቁጥር ምን ያህል እንደኾኑ

የተጨበጠ ወይም በጥናት የተደገፈ ማስረጃ ባይኖርም በስያሜው የሚጠሩ አንዳንዶች ግን “አምቼ”ን እንደ የኤርትራ 10ኛው ብሔር አድርገው ይቆጠሩታል። የ“አምቼ”ዎች ትክክለኛ አኀዝ ባይታወቅም ከጦርነቱ በኋላ ከኢትዮጵያ የተባረሩ ኤርትራውያኖች ቁጥር 75ሺሕ እንደሚደርስ ኦፌሲሊያዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ማነው የተባረረው?ይፋዊ መረጃዎች በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነ

ት ወቅት የተባረሩ ትውልደ ኤርትራውያን መካከል አብዛኛዎቹ ረዥሙን የሕይወት ዘመናቸውን በኢትዮጵያ የተወለዱ እና ያሳለፉ ናቸው። በ1990 ዓ.ም ወደ ኤርትራ በመጀመሪያ ዙር በተባረሩ ላይ በተደረገ ሰርቬይ 59 በመቶ የሚኾኑት ከ25 እስከ 60 ዓመት የሚኾነውን ጊዜያቸውን ያሳለፉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ሁሉም በሚባል መልኩ የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሲኾኑ ብዙዎቹም በኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ያልተሳተፉ ነበሩ። በ1985 ዓ.ም በተደረገው የሕዝበ ውሳኔ

ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ እና ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገቡ 57,710 ትውልደ ኤርትራውያን መካከል 99.5 በመቶ የሚኾኑት ነጻነትን የመረጡ ሲኾን 204 ሰዎች ብቻ ከኢትዮጵያ ጋራ መኖርን መርጠዋል። ከአምስት ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ለ“አገር ደኅንነት ስጋት ናቸው” በሚል ብዛት ያላቸውን ትውልደ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ አስወጥቷል። ብዙዎቹ ትውልደ ኤርትራውያንን ከአገር እንዲወጡ የተደረገው ህግሐኤ (ህግደፍ)ን በገንዘብ በመደገፍ እና ትሥሥር በመፍጠር ተወንጅለው ነበር። በቀጣዩ ዓመት 1991 ዓ.ም በሳምንት ቢያንስ እስከ 1500 ዜጎች ከኢትዮጵያ ሲባረሩ ነበር።አብዛኛዎቹ ተባራሪዎች ኢትዮጵያ ው

ስጥ በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሠማርተው የነበሩ ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አጣሪ ልዑክ ቁጥራቸው 250 በሚደርስ የትውልደ ኤርትራውያን ቡድን ላይ ባደረገው ማጣራት መምህራን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች፣ ሜካኒኮች፣ ነጋዴዎች እና የዩኒቨርስቲ መምህራንም ጭምር ከ

ል ሂደቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አንድ ውስጥ አዋቂ ተባራሪዎቹ ወደ አሥመራ ሲገቡ የነበረውን ስሜት ለአዲስ ነገር እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ፦ “የመጀመሪያውን ዙር ተባራሪዎች ስንቀበል የነበረው ከፍተኛ የቁጭት ስሜት ነበር። በከፍተኛ ስሜትም ነበር። የመጀመሪያዎቹ ተፈናቃዮች አሥመራ ዩኒቨርስቲ እንዲያርፉ ተደረገ፤ ዘመድ ያላቸው

በየዘመዶቻቸው እንዲሄዱ ተደረገ። በብዙዎቹ ተባራሪዎች ላይ የላቀ ቁጭት እና ግራ መጋባት ይታይ ነበር።” ይላሉ።“ሙሉ ቤት እና ሀብት የነበራቸው አባ

ዎራዎች ብርድ ልብስ እና አንሶላ ለመቀበል ሲሰለፉ ለብዙዎቹ አንገት የሚያስደፋ ነበር። እስካሁን ድረስ ያልሻረ ጠባሳ ነው” ሲሉ የተፈጠረውን ችግር ያስረዳሉ።

የችግሩ መጠን የተባባሰው ደግሞ የተባራሪዎች ቁጥር በየቀኑ እየናረ ሲመጣ እና የአሥመራ አቅም ከሚችለው በላይ ሲኾን ነበር። ያውም ብዙዎች ከመላው የቤተሰባቸው አባላት ጋራ የመምጣት ዕድል ባለገኙበት ኹኔታ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃ

ናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) በሁለት የተባራሪዎ

ፖለቲካ ፣ ማንነት በ“አምቼዎች” ዓለም ውስጥ

“ብዙ ኤርትራውያን አማርኛ ቋንቋን የሚናገረው አማራ ብቻ ይመስላቸው ነበር። ከ1990 ዓ.ም በኋላ ብዛት ያላቸው አምቼዎች ከኢትዮጵያ ተባርረው አሥመራን አጥለቀለቋት” ይላል ቢኒያም።

ተባራሪዎቹ ውስጥ ተካተው ነበር። ከዚህ ቡድን ውስጥ አንድ የሕክምና ባለሞያ እና ሁለት መነኩሴዎችም ነበሩበት። አብዛኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ60 በላይ የነበረ ሲኾን ኤርትራን ረግጠው የማያውቁ እና ትግርኛ ቋንቋ የማይናገሩ ነበሩ።(Case Ma-terial on Ethnic Eritrean Deportees from Ethiopia Concerning Human Rights Violations The Uprooted : Case Material on Ethnic Eritrean Deportees from Ethiopia Concern-ing Human Rights Violations by Prof. Asmarom Legesse on behalf of Citizens for Peace in Eritrea) ተባራሪዎቹ ወደ ኤርትራ የሚወሰዱት በአራት የድንበር አቅጣጫዎች ነበር። ብዙዎቹ ወደ አሥመራ የገቡት በኦምሃጀር- ተሠነይ- አሥመራ ሲኾን፣ የተወሰኑ በቀይ መስቀል ተባባሪነት በአሰብ በኩል ወደ ኤርትራ ተሸኝተዋል። ጥቂቶች የጦርነቱ ግንባር በነበረችው ዛላምበሳ እና መረብ ዓዲዃላ በኩል ወደ አሥመራ ተጉዘዋል። ሌሎች ደግሞ ወደ ኤርትራ ሳይኾን ወደ ኢትዮጵያ የጠረፍ ከተሞች ሞያሌ እና ጅቡቲ ተወስደው ከአገር እንዲወጡ ተደርገዋል። ይህ ብዛት ያላቸውን ዜጎች ከአገር የማስወጣት ተግባር በሁለቱም የፖለቲካ ኀይሎች እንደሞያ የተያዘ ይመስላል። በ1983 ዓ.ም ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ሕግሐኤ ከኤርትራ ሲያስወጣ በወቅቱ የኢህአዴግ መንግሥት ስለ ተፈናቃዮቹ ምንም ዓይነት እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረም። ከ1990 ዓ.ም የደንበር ጦርነቱ መጀመር በኋላም የኤርትራ መንግሥትም “ኢትዮጵያዊ” ያላቸውን ዜጎችበምላሹ ከሀገር አባርሯል።ከካምፓላ 73 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ

ምትገኘው ጂንጃ ከተማ የሚኖሩ እና በወቅቱ ወደ ኤርትራ የገቡትን ዜጎች በመቀበ

Page 7: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 7

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

ጥቶኝ ነጠር ነጠር እያለ ከፊት ለፊቴ ይመራኝ ጀመር” ይላል ማኅደረ ።የገቡት ከሕንጻው ጀርባ ካለች አነስተኛ ክ

ፍል ነበር። ሦስት ወጣቶች አትነጋገሩ የተባሉ ይመስል በፀጥታ ተቀምጠዋል። ሚካኤል ንግግር አላበዛም። “በማለዳ ተነስታችሁ እዚሁ እንገናኛለን፤ ቻው” የሚል ቃል እንደተናገረ አንደኛው ወጣት ለሚካኤል በእጁ አንድ ነገር አስጨበጠው። “ተረጋግታችሁ ውጡ” የሚል ትዕዛዝ ብቻ ሰጥቶ በጥንቃቄ ሕንጻውን ለቀቀው ወጡ። የኮምቢሽታቶውን ጮሌ ዋነኛ የገቢ ምንጩ በድብቅ ከኤርትራ የሚወጡ ዜጎች “መርዳት” መኾኑን ማኅደረ ያወቀው በዚያ አጋጣሚ ነበር።

አሥመራ ከተማየኮምቢሽታቶው ጮሌ ዋና ሥራ ተጓዦ

ቹ ከአሥመራ እንዲወጡ መርዳት ነው፤ ከዚያ በሻገር ስላለው ደግሞ ሌሎች ባልደረቦቹ ይጨነቁበታል። ከተሳካ እስከ ኢትዮጵያ ወይም ሱዳን ድንበር ያደርሳሉ። ከዚያ በኋላ ያለው ጣጣ የስደተኛው ይኾናል። በወቅቱ በርካቶች በውትድርናው ሥራ የመረራቸው፣ ሳዋን የሚሸሹ እና የተሻለ ኑሮ የሚፈልጉ ወጣቶች ነበሩ። ውቧ ግን ሕይወት አልባዋ አሥመራም ሰልችታቸው ነበር። ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ለብዙ አምቼዎች። የመንግሥት ቁጥጥር ከፍተኛ በመኾኑ ዜጎችን ማስኮብለል ቀላል ሥራ አልነበረም። እጅግ ጥንቃቄን የሚሻ ነው። ከሞት ጋራ አንገት ለአንገት ተናንቆ የሚሠራ ነው።ከቀናት ምክክር እና ልምምድ በኋላ ማኅ

ደረ የሚካኤል ረዳት ኾነ። የተሰጠው ሚና ደግሞ ከኢትዮጵያ የተባረሩ እና መመለስን የሚሹ አምቼዎችን ማገናኘት ነበር። ሥራው መልካም ነበር፤ ገቢ አለው። ነገር ግን ሕይወት ከወዲህ ወዲያ የሚያላጋቸውን ለጋ ወጣቶች አደጋ ባለው ጉዞ ማሾለ

በ“አምቼዎች” ዓለም ውስጥች መቀበያ ጣቢያ ባደረገው ሰርቬይ በሰኔ 1990 ወደ ኤርትራ ከተባረሩት ውስጥ 63 በመቶ የሚኾኑት አዋቂ መላሾች ከልጆቻቸው ተለያይተው እንደመጡ ተናግረዋል። ብዙዎቹም ሀብት እና ንብረታቸውን በወጉ ለማደራጀት እንኳ ዕድል አልነበራቸውም። ይህን መሰሉ ትውልደ ኤርትራውያንን ሰብአዊነት በጎደለው መልኩ ከኢትዮጵያ የማስወጣቱ ሂደት በወቅቱ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ዓለም አቀፍ ነቀፋ ያሰነዘረ ነበር። ነቀፋው እና ትችቱ በወቅቱ በነበረው ኹኔታ ላይ ብቻ የተወሰነ እና ተባራሪዎች ከዓመታት በኋላ ሊገጥማቸው የሚችለውን የማኅበራዊ ኑሮ ቀውስ ከግምት ውስጥ የከተተ አልነበረም።ይህ ሁሉ ታሪክ ከተፈጸመ ከዐሥር ዓመ

ት በኋላ ያለው የተባራሪዎች በተለይም የ“አምቼ”ዎች ሕይወት በምስቅልቅል ኹኔታዎች የተሞላ ነው። ለአዲስ ነገር ታሪካቸውን ያጋሩ “አምቼ”ዎችም ይህንኑ እውነታ ይቀበሉታል። ለደኅንነት በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት ኹኔታውን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ የጂንጃው ውስጥ አዋቂም ወደ ኤርትራ የገቡት አምቼዎች የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ ልቡናዊ ችግሮችን መጋፈጣቸውን ይመሰክራሉ።

የአምቼነት ዕዳእንደ ማኅደረ ያሉ ብዛት ያላቸው የትው

ልደ ኤርትራውያን ልጆች እና ወጣቶች አሥመራን ካጥለቀለቁ በኋላ ያጋጠማቸው ያልጠበቁት እና ካደጉበት በብዙ የሚራራቅ ነበር። ብዙዎቹ አሥመራን እና ነዋሪዎቿን ሲያስተውሉ እጅግ ወግ አጥባቂ እና የውጭ ሰው እና አስተሳሰብ በቀላሉ የማያስገባ ዝግ ኾነው አገኙት። እነርሱ ካላቸው አንጻራዊ የኾነ “ተራማጅ” ማኅበራዊ መስተጋብር አንጻር ከአሥመራ ነባር ነዋሪዎች ጋራ መዋሃድ እጅግ ፈታኝ ነበር። የሚናገ

ራሱን ጁባ ከማግኘቱ በፊት ከአገር አገር ዞሯል። ካርቱም- አዲስ አበባ- ናይሮቢ-ሉዋንዳ -ካምፓላ።አሁን ኬንያ የሚገኘው ማኅደረ ድንበር

ከመሻገሩ በፊት ኤርትራውያንን እና አምቼዎችን ማስኮብለል ሥራው ነበር። ከባድ የኾነበትን የአሥመራ ኑሮውን ትንሽ መልክ ያስያዘው ይኼው ሥራው ነበር። ወደዚህ ሥራው ደግሞ ያመጣው የ“ኮምቢሽታቶው ጮሌ” ሚካኤል ነበር። ሚካኤል የአባ ሻወል ሠፈር ልጅ ነው። ነገር ግን ውሎው እና ተግባሩ ኮምቢሽታቶ በመኾኑ ነበር ሚካኤል ኮምቢሽታቶ የሚል ስያሜ ያገኘው። በጣም ተግባቢ ነው።ሚካኤል እና ማኅደረ የተግባቡት የ“ኮም

ቢሽታቶው ጮሌ” ማኅደረ ዘወትር ከማይጠፋባት “በረኸት ሻይ ቤት” በትዝታ ሲናውዝ ያገኘው ቀን ነበር። “አንቺ አምቼ አሁንም ሠፈር አልለመድሽም ?” አለው ማኅደረን! በቀላሉ ተግባቡ። ወዳጅነታቸው ጠነከረ። ሳምንቱን ሙሉ አይነጣጠሉም። ውሏቸው “ካምቦሎ”፣ “ትራቮሎ”፣ “ፊያት”፣ “ሳንፍራቼስኮ”፣ “አክሪያ” እና ሌሎች ሠፈሮች ኾነ። ማኅደረ አዲስ አባባ እያለ ወደ ሲኒማ ኢትዮጵያም ኾነ ሲኒማ አምባሳደር ብቅ የማለት ልምድ አልነበረውም። በአሥመራ ግን ደንበኛ ኾነ። በ“ሲኒማ አዝመሪኖ” እና በ“ሲኒማ ካፒታል” በየቀኑ ይታደማል። ሚካኤል ይከፍላል፤ ማኅደረ ይዝናናል።አንድ ቀን የአሥመራ መለያ የኾነው ካቴ

ድራል ወደ ሚገኝበት ኮምቢሽታቶ ተያይዘው ነጎዱ። አምባሳደር ሆቴል እዚሁ አቅራቢያ ይገኛል። በአቅራቢያው ወደሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ወዳለው ቤት ተያይዘው ሄዱ። “ፈጠን ብለህ ግባ” አለው ሚካኤል ኋላ እና ፊቱን እየተገላመጠ። “የሕንጻውን ዋና በር እንዳለፍኩ ግድግዳ ተደገፌ ጠበቅኹት። ‘ተከተለኝ’ የሚል ትዕዛዝ ብቻ ሰ

እና ስደት

ሩት ቋንቋ አማርኛ በመኾኑ አምቼዎች ሙሉ በሙሉ ከአሥመራ ነዋሪዎች ጋራ እንዳይዋሃዱ አርጓቸዋል።“በአረማመድ ሳይቀር ማን አምቼ እንደ

ኾነ ትለያለህ” ይላል ቢኒያም። “አምቼ”ዎች በሚሰሙት ሙዚቃም ተነጠለው ይታወቃሉ። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጫፍ በደረሰበት ሰሞን እንኳን በአሥመራ እንዲሁም ከረንን በመሰሉ አነስተኛ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ትናንሽ የመዝናኛ ቤቶች ውስጥ ሳይቀር የአማርኛ ሙዚቃ እንደልብ ማጫወታቸው በጤና አልታየም። ይህንን ተከትሎም የአማርኛ ሙዚቃዎችን በየምሽት ክበቦች ማጫወት እንዲቀር ታግዷል።“ከመባረሩ ሂደት ጋራ በተያያዘ ብዙዎቹ

የሥነ ልቡና ተጽዕኖ ውስጥ ነበሩ።” ይላል ቢኒያም። ማንነታቸው ሁለት ቦታ የተሰፋ ነው። አዲስ አበባ እና አሥመራ። ማኅደረም ከዚህ አልወጣም። ከአደገበት ቀዬ ተነቅሎ ያለ ውዴታ እና ፈቃዱ፤ በሚያዋርድ እና የሰውነት ክብርን በሚነካ መልኩ ወደ ኤርትራ መላኩ ያብሰለስለዋል። ዛሬ ልቡ ለኤርትራዊነት ያጋድላል። ግን ኤርትራዊ በመባልም ምሉዕነት አይሰማውም። “የጓደኞቼ ፍቅር እና ወዳጅነታቸው ለአፍታ ባይጓደልብኝም ስያሜዋ(”አምቼ” ) አንዳች ክፍተት በልቤ ውስጥ ፈጠረች። ኤርትራንም እንደ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ መጠለያዬ እንጂ ቋሚ አገሬ ለማለት የማልደፍራት እንደኾነች ገባኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ እንዳልል መባረሬ መልሱን ሰጥቶኛል” ሲል የተፈጠረበትን ግራ መጋባት ያስረዳል። “የማልክደው ነገር ከኢትዮጵያ በመባረሬ ለኤርትራ ያለኝን ፍቅር መጨመሩ ነው።”ማኅደረ ያንን ጊዜ የሕይወቱ “አስጨና

ቂ” እና “አስቸጋሪ” ወቅት አድርጎ ይቆጥረዋል። ከሁሉ ፈተና የኾነበት ገቢ ማግኘት አለመቻሉ ነበር። የአባቱ ዘመዶች የመረዳዳት ጠንካራ ባህል ታክሎበት እንኳ ኑሮን መግፋት እንደ አለት ጠጥሮበት ነበር፡፡ ተንቀሳቅሶ ለመሥራትም የሚያስችል ምንም ዐይነት ቀዳዳ አልነበረም።ለአብዛኛዎቹ “አምቼ”ዎችም ሕይወት እ

ንዲያ ነበረች። ከብሔራዊ አገልግሎት ከተረፉ አሥመራ ውስጥ አለ የተባለውን ማንኛውንም ሥራ በመሥራት ይታወቃሉ። በብዙ የአሥመራ ነዋሪዎች የማይደፈሩ እንደማስተናገድ ያሉ ሥራዎችን ሳይቀር ይሠራሉ። አንዳንድ እንስቶችም ተገደው ወደ ሴተኛ አዳሪነት ገብተዋል። አንዳንዶችም በአሥመራ ባልተለመደ ኹኔታ ለአደገው ዝርፊያ ተጠያቂ የተደረጉት እነርሱው ናቸው። “ሌብነት፣ ማታለል እና በቡድን መደባደብ ከአምቼዎች ጋራ ብቻ እየተያያዘ የሚነሳ ነገር ኾኖ ነበር” ይላል መኖሪያውን ናይሮቢ ያደረገው በፀጋ ሳህለ። ይህ ተደራራቢ ከመጥፎ ነገሮች ጋራ የመዛመድ ችግር የገጠማቸው አምቼዎች የመገለል እና የራሳቸውን ክበብ በመሥራት መራቅን እንዲመርጡ አድርጓቸዋል።የኤርትራ መንግሥት የሚከተለው ዜጎች

ን በወታደራዊ አመለካከት የመቅረጽ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ለአምቼዎች የሚመች አልኾነም። የኤርትራ መንግሥት መሪዎች አክራሪ የኤርትራዊ ብሔርተኝነት አቀንቃኞች ናቸው። ይህ የአምቼ ማንነት ከተገነባበት መሠረት ጋራ የሚፋለስ ነው። የአምቼዎች ብሔራዊ ማንነት በኢትዮጵያም በኤርትራም ፖለቲከኞች እና ልሂቃን ዘንድ እውቅናም ገና አልተሰጠውም። አምቼዎች ማንነታቸው የተገነባው በሁለት ጠንካራ ብሔርተኛነትን በሚያቀነቅኑ (ኢትዮጵያ እና ኤርትራ) ወገኖች መካከል ነው። ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትም ኾነ የኤርትራ ብሔርተኝነት አንዱ ለአንዱ እውቅና የሚሰጡ አይደሉም። ተፎካካሪ ናቸው። የሁለቱም ብሔርተኝነት አቀንቀኞች “ቀናተኞች” ናቸው። አንደኛው ሌላውን አይቀበልም። አሥመራ የሚናኘው የብሔርተኝነት አመለካከት “ለ30 ዓመት ከኢትዮጵያ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት በተደረገውን ጦርነት እና ድል “ ውስጥ የበቀለ እና ያደገ ነው። የኢትዮጵያ ብሔርተኝነትም ለኤርትራ ብሔርተኝነት እውቅና የሚሰጥ ሳይኾን እንደ ስኅትት እና ክህደት ይቆጥረዋል። የአምቼዎች ማንነት የተገነባው ደግሞ የአንዱን የብሔርተኝንት እንቅስቃሴ በመናድ እና የሌላኛውን በመደገፍ ሳይኾን በሁለቱ የብሔርተኝነት አጽናፎች መካከል ያለ

ውን መካከለኛ ቦታ ይመርጣል። አምቼዎች ማንነታቸውን የሚገልጹት በሁለቱ ብሔራዊ “ቤቶቻቸው” ነው። ሁለቱንም እንደቤታቸው ያያሉ። ብዙዎቹ ከሁለቱም ቤቶቻቸው ርቀዋል። ነገር ግን ደግሞ ከሌላኛዋ “ቤታቸው” ኢትዮጵያ በግድ የተነቀሉም ናቸው።

አዲስ አበባአምቼዎች ኑሮ በአሥመራ እጅግ ፈታኝ

ኾኖባቸዋል። ኢኮኖሚው እና ማኅበራዊው ችግርም ቶሎ ሊቀረፍ ያልቻለ ነበር። ብዙዎቹ ከድንበር ጦርነቱ በኋላም አሁንም ብሔራዊ አገልግሎት ከመስጠት አልወጡም። መቼ እንደሚወጡም አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና እግዜር ብቻ የሚያውቁ ይመስላል። አሥመራ ላይ ያለው የአቶ ኢሳያስ አስተዳደር በየጊዜው ፍፁም አምባገነንነቱን እያጠናከረ መሄዱ የአምቼዎችን ሕይወት መፈናፈኛ እንዳይኖረው አድርጎታል። እንደ ማኅደረ ያሉት ግን ተሳክቶላቸው አገራቸውን ጥለው ዳግም ስደት ገብተዋል።

ዳግም ስደት……ዘጸአት ለአምቼ?አሥመራም ያልተመቻቸው ብዙ “አምቼ

ዎች” ኤርትራን ለመልቀቅ ድንበር ማቋረጥ ጀመሩ። መጀመሪያ ወደ የመን፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን። ለደላሎች ብዙ መክፈል ግድ ይላል። ገንዘብ ያላቸው ብቻ ለቀናት የእግር ጉዞ በማድረግ ከኤርትራ ደንበር ጠባቂዎች ተደብቀው ወደ ከሰላ (ሱዳን) በሕገ-ወጥ መንገድ ለመውጣት ይሞክራሉ። የተሠነይ-ከሰላ መንገዱ አንዱ ሲኾን ከኤርትራ ለመውጣት እስከ 4ሺሕ ዶላር የሚቀበሉት አስተላላፊዎች ሌሎችም በሮች አሏቸው። የቻሉ ይወጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ተይዘው ይታሠራሉ ወይም ይገደላሉ።በዚህ መልክ ኤርትራን ለቀው ከተሰደዱ

ት መካከል አንዱ ቢኒያም ነበር። እርሱ እንደ አብዛኛዎቹ አምቼዎች በድንበር ግጭት በተነሳው ጦርነት ምክንያት ራሱን አሥመራ ላይ አላገኘውም። በ1983 ዓ.ም ደርግ ሲወድቅ ወደ ኤርትራ ሄደ። ከአዲስ አበባ አስመራ በአውቶብስ እየተመላለሰ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ሲጋራ እና ማስቲካ ይነግድ የነበረው ቢኒያም የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ አሥመራ ላይ ነበር፤ ድንበርም ተዘጋ። ብዙዎችም ተባረሩ። ያኔ አሥመራ ላይ መቅረት ግድ ኾነ።ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት የነበረ

ው ቢኒያም ንግዱን ቢቀጥልም ከአንድ አስቸጋሪ ነገር ጋር ተፋጠጠ። እንደ ደንቡ የብሔራዊ አገልግሎት ግዴታውን መወጣት ነበረበት። በኤርትራ መንግሥት ሕግ መሠረት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 40 ዓመት የኾናቸው ዜጎች የብሔራዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸው። ሦስተኛ ልጁን እርጉዝ የነበረችውን ባለቤቱን ጥሎ ላለመሄድ ያልፈለገው ቢኒያም ከባለሥልጣናቱ ጋራ ድብብቆሽ ጀመረ። ቁጥጥሩ ጥብቅ እየኾነ ሲመጣ የቀረው ሁለት አማራጭ ነበር። ወደ ብሔራዊ አገልግሎት መሄድ ወይም ከሀገር መውጣት።አገር ጥሎ መውጣት ግን ቀላል አልነበረ

ም። በየቦታው ያሉትን ኬላዎች ማለፍ፣ በአልሞ ተኳሽ ወታደሮች የሚጠበቅ ድንበርን ማለፍ ይጠይቅ ራሱን የቻለ ፈተና ነበር። ከአሥመራ ተሰነይ በአውቶብስ የተጓዘው ቢኒያም ድንበር አቋርጦ ከሰላ ለመግባት የ17 ሰዓት የእግር ጉዞ መሄድ ግድ ኾኖበታል። “እኛ የወጣንበት መንገድ አሪፍ ነበር” ይላል ቢኒያም። የወታደሮች አፈሙዝ የሌለበት፤ ይህን መንገድ የሚያውቁ ሰዎች ግን በወቅቱ “ጫን ያለ” ክፍያ ነበር የሚጠይቁት።የተጠየቀውን 1500 ዶላር ከፍሎ የሱዳን

የድንበር ከተማ የኾነችው ከሰላ የደረሰው ቢኒያም በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች እጅ ላይ ይወድቃል። “ከሰላ ስገባ ጀለቢያ አድርጌ ነበር። ጸጉረ ልውጥ ስለኾንኹ በፖሊሶች ተያዝኩ። በኪሴ 3000 ዩሮ እና 200 ዶላር ነበረ። ፖሊሶቹ ራቁቴን አድርገው ፈተሹኝ” ይላል። የኮሎኔል ማዕረግ ካለው ፖሊስ ፊትም እንዲቀርብ ተደረገ። “የሚያውቁት ገንዘብ ዶላር ስለነበር የያዝኩትን 200 ዶላር ሰጠኋቸው። ዩሮውን ስላላወቁት ለቀቁኝ” ሲል እንዴት ለመቋቋሚያ ብሎ የያዘው ገንዘብ እንደተረፈለት ይናገራል። ዛሬ

ወደ ገጽ 22 ዞሯል

ክ ለህሊናው ፈታኝ ኾኖበታል። ግን ሕይወት ሌላ የተሻለ ምርጫ አልሰጠችውም። “አስገራሚው ነገር በየቀኑ ከሁለት ያለነሰ ሰው ለመኮብለል እንደሚፈልግ ማወቄ ነበር። አገር የሚሰደድ ነው የሚመስለው። እንደዚህ ጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥርም እያለ የሚኮበልል ሰው ማግኘት ሳይኾን እንዴት ለማስኮብለል እንደሚቻል ነው የሚቸግረው” ይላል።ማኅደረ በመጨረሻ ራሱን ለዳግም ስደት

አጨው። አሥመራ ቢቆይ ከአባ ሻውል እስከ ኮምቢሽታቶ…እንደ ልብ ወዲህ ወዲያ ሲል እንደማይኖር ያውቀዋል። ሳዋ አፉን ከፍቶ ይጠብቀዋል። “በአዝመሪኖ ያለው ቆይታዬም በሳዋ ግዞት መጠናቀቁ ስለማየቀር ከወዲሁ ልኮብልል ስል ራሴን መከርኩት” ይላል ውሳኔ ላይ ስለደረሰበት ወቅት እና ኹኔታ ሲያብራራ። ለስደት የመረጠው መንገድ ግን ሌላ ፈተና ይዞ መጣ። ኢትዮጵያን እንደ መሸጋገሪያ ድልድይነት ቢወስዳትም የኤርትራን ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የማንነት ጥያቄው አፍጥጦ መጣበት “እኔ የማን ነኝ?” የሚል።“አሥመራን እስከምለቅ በስጋት ውስጥ ጥ

ያቄውን አዳፈኜው የነበረ ቢኾንም አክሱም ከተማ ስደርስ ዐይኑን አፍጥጦ መጣብኝ” ይላል። ከማኅደረ ጋራ አብረው የኮበለሉት ወደ ሽመልባ መጠለያ ካምፕ ሲገቡ እርሱ ግን ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ። አዲስ አበባ ጥቂት ከሰነበተ በኋላ ወደ ኬኒያ አቀና። ብዛት ያላቸው አምቼዎችም የማኅደረን መንገድ ተከትለዋል።ሥርጭት በምሥራቅ አፍሪካ አምቼዎች ከአዲስ አበባ እና አሥመራ

ውጭ በመላው የምሥራቅ አፍሪካ ከተሞች ተበትነዋል። በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ ከተሞች ካርቱም፣ ጁባ፣ ካምፓላ፣ ናይሮቢ፣ ሞምባሳ፣….እና በመላው ዓለም ይገኛሉ። ምሥራቅ አፍሪካ ላይ ደግሞ በብ

ልዩ ጥንቅር

አዲስ ነገር ኦንላይን

Page 8: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)8 ሀበሻዊ ቃና

ክፍሏን ለመግለጽ ጠባብ የሚለው ቃል ብቻውን የልብ አያደርስም። በአጭሩ የበሬ ግንባር የሚሏት ዐይነት ናት። ጥበቷ እና የታቀፈቻቸው ሰዎች

ብዛት ግን ለተመጣጥኖሽ እንኳ የሚከብድ ነው። በሦስት ማእዘናት የተዘረጉ ፍራሾች፣ ከአንድ ጥግ መደገፍ እንጂ በወጉ መቀመጥ ያልቻለ ቴሌቭዥን፣ ተደራርበው የተቀመጡ ሻንጣዎች፣ ከሻንጣው በላይ የተደረቡ ቀለም ዐልባ ድሪቶዎች . . . መሀል ላይ በትሪ ላይ የተደረደሩ የቡና ስኒዎች፣ ዕጣን ማጤሻ፣ የከሰል ምድጃ . . .ምሽቱ ለብርሃን ተራውን ከለቀቀ አስር ሰዓታት ተ

ቆጥረዋል። በኬንያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አቆጣጠር ግን “ከማለዳው” ሁለት ሰዓት ሊኾን ነው። በዚሁ ፀሐይ እያዘቀዘቀች በመጣችበት ሰዓት ገና እየነጋ የሚመስለው እና የጠዋቱ አራት ሰዓት የሚታሰበው ስደተኛ ካለ በታታሪዎቹ የኬንያ ስደተኞች አቆጣጠር “ማልዶ” ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ተነስቷል ማለት ነው። ይህ ቀትር ላይ ከእንቅልፍ የመንቃት ልምድ የራሱ የኾኑ መላምቶች አሉት።ከአገር ያፋታው እና ቀን ከሌት ሕልም ኾኖ የሚያ

ባዝነው የምዕራብ አውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ጉዞ ስኬታማ እስኪኾን ድረስ “ጊዜ መግደያ ነው” የሚለው የመጀመርያው መላምት ነው። በዚህኛው መላምት አብዛኞቹ ስደተኞች ይስማማሉ። ሁሉም በሚባል ደረጃ ውጭ በሚኖር የወዳጅ ዘመድ ድጎማ የሚኖሩ እንጂ የተለየ የገቢ ምንጭ የሌላቸው ናቸው። ስለዚህ ማልዶ ለመነሳት ምክንያት የላቸውም። ሁለተኛው መላምት ባለሙሉ ተስፈኞች የሚያቀነቅኑት ዐይነት ነው። ወደፊት ምርታማ አሜሪካዊ ዜጋ የመኾን ራዕይን ያዘለ መላምት። በኬንያ ከቀኑ ዐሥር ሰዓት ሲኾን አብዛኛው የአሜሪካ ግዛት ንጋትን የሚያይበት ነው። ቀኑ ሳያመልጠው ራሱን የሩጫው አካል ለማድረግ የሚራወጥበት እና ለመኳተን የሚዘጋጅበት ሰዓት ነው።በኬንያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞችም በአሜሪ

ካ ኑሮ ማልዶ የመንቃት ጥቅም የገባቸው ይመስል እኩል ሰዓት ላይ ይባንናሉ። እናም በተመሳሳዩ ሰዓት አርፍደው (ተግተው) በመነሳት ልምምዳቸውን በኬንያ ምድር ከወዲሁ ተያይዘውታል። በርካታ ሐበሻ በሚኖርባቸው እንደ ኢስሊ ባሉ አካባቢዎች ያሉ የሐበሻ ሱቆች በማለዳ የማይከፈቱትም በእነዚህ እና በእነዚህ መሰል ምክንያቶች ጭምር ነው። “አውሮፓ እና አሜሪካ የሚኖር ዘመድን ለማግኘት አመቺው ሰዓት ከዐሥር ሰዓት በኋላ ነው” የሚለው የተለመደ ንግግር በሦስተኛ ደረጃ የሚገኝ ሌላኛው መላምት ነው።አብዛኞቹ ኬንያ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስ

ደተኞች በአዲስ አበባ ወንደላጤዎች እና ዘመናዊ ቆጣቢዎች ዘንድ “ቁ-ምሳ” (በምዕራባውያን ዘንድ “ብራንች” ተብሎ ይታወቃል) የሚል ማእረግ የተሰጠው ቁርስንም ምሳንም ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ የመመገብ ልማድን ቢኮርጁም የሚጠቀሙበት በራሳቸው የሰዓት አቆጣጠር ነው። የሐበሻዋ “መክሰስ” “የቁምሳን” ቦታ ወስዳለች። እራት ደግሞ በውድቅት ሌሊት ተተክቷል። ድንገት ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ አንድ ስደትን የሚጋራ የአገር ሰው በራችሁን አንኳኩቶ “በዚህ ሳልፍ ሰላም ሳልላችኹ አላልፍም ብዬ ነው” ቢላችኹ ሊገርማችኹ አይገባም። የእራት ሰዓት ላይ መገናኘታችኹ እንጂ። ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ ተመልሶ ቢመጣ ግን ለጠብ ፈልጎዎታል ወይም እነደ አገር ቤት ይትበኻል “መርዶ ነጋሪ” ነው ማለት ነው። ደግነቱ እርሱም “በውድቅት ማለዳ”አይሞክረውም።

ስደት እና ቅፈላ . . .በዚህ ሰዓት እንግዲህ ማለዳ ለእንቅልፍ ያገለገሉ

ፍራሾች አሁንም ብቻቸውን አይኾኑም፤ አይደሉምም። ዘወትር የሚጎበኟቸው እንግዶች ቢያንስ ቀጣዮቹን ስምንት ሰዓታት እንዳሻቸው ያሹዋቸዋል። እረፍት የለሾቹን ፍራሾች። በዚያች “የበሬ ግንባር” በምታህል ክፍል ስምንት ወጣቶች ጥግ ጥጋቸውን ይዘዋል፤ የመንታ ያህል በሚያመሳስላቸው አቀማመጥ። ቡና የምታፈላው ወጣት ከጊዜያዊ ረኸቦቷ ጋራ ለማዕከላዊነት የቀረበውን ሥፍራ ይዛላች። በእያንዳንዱ ተቀማጭ ጭን ሥር በጥቁር ላስቲክ የተቋጠረ ጫት ይገኛል። ሚራ ይሉታል ኬንያውያን እና የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ሰዎች። አዲስ አበቤዎች ከሚያወቁት የተለየ ጫት ነው። ከካርቶን የሚወፍር

ቅጠል፣ ማንጠልጠያ እንጨት እንኳ የሌለው። በሁለት ጣቶች እየተቆነጠረ የሚሰፈር። ከሰላሳ የኬንያ ሽልንግ (አምስት የኢትዮጵያ ብር) ጀምሮ ይገኛል። ለአብዛኛው ስደተኛ ያለ ጫት የምታልፍ ቀን እንደባከነች ትቆጠራለች። ጫት እና ሕይወት ያላቸው ትሥሥር እንደ ሳንቲም ገጽታ ያለ ነው። የሌለው ቢቻል ቀፍሎ (ለምኖ) አልያም ዱቤ የማያውቁትን የኬንያ ጫት ሻጮች አሳምኖ ዕለታዊ ምሱን ያደርሳል።ደምስ ከፕሮፌሽናል ቀፋዮች (PK) የአንደኛነትን

ደረጃ ከሚይዙት መካከል የሚመደብ ነው። ወደጆቹ “ሲቀፍል ጉርሻም ቢኾን አይቀረው” ሲሉ መረር አርገው ይቀልዳሉ። ዛሬም ቡድኑን ለመቀላቀል የዘገየ ቢኾንም በ100 ሽልንግ ለሌሊቱ የሚበቃውን ያህል ጫት አግኝቷል። የደምስ ኑሮ ላለፉት አምስት ይችኑ መደጋገም ብቻ ነው። ቀፍሎ የቤት ኪራይ ይከፍላል፤ ቀፍሎ ይመገባል፤ ቀፍሎ ይጠጣል፤ ቀፍሎ የመረጣትን ኬንያዊ ሴት ይዞ ያነጋል፤ ቀፍሎ ይቅማል . . . በቃ ቅፈላ እስካለ ሕይወት ለደምስ ጎድላለች የምትባል አይደለችም።የኬንያ ምድርን ከረገጠበት ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ለ

ስድስት ዓመታት የቤተዘመዶቹን ድጎማ አልተነፈገም ነበር። በየወሩ እስከ ሦስት መቶ ዶላር ያህል እየ

ተደጎመ ስደተኛ ሳይኾን አምባሳደር መስሎ አሳልፏል። በዓመታቱ ርዝመት ወደ አውሮፓ የመሄዱ ሕልም የከሰመ የመሰላቸው ለጋሾቹ እጃቸው እያጠረ መጣ። ከሦስት . . .ወደ ሁለት . . . አንድ እያለ ወደ ኪሱ ሲገባ የነበረው ዶላር ወደ ዐልቦነት ተሻገረ። በወቅቱ ወደ አገር ቤት የመመለሱም ፍላጎት ተኖ ጠፍቶ ነበርና ኬንያን ከቅፈላ ጋራ እንደ አዲስ ይለማመዳት ጀመር። ሲነቃ ስለ ጫቱ አብዝቶ ያስባል፣ ይጨነቃል፣ ሲለው ይተጋል፤ ሲመረቅን ለአንገት ማስገቢያ የሚላትን ኻያ ሽልንግ ለመጠጡ በመፈለግ ይባትላል። ሲሰክር ደግሞ ቤቱ እንዳይቀዘቅዘው በጭኗ የምታሞቀው ሴት ከንጋቱ 11 ሰዓት ያስሳል። “ሳይደግስ አይጣላም” የሚለው አባባል ለደምስ የተሠራ እስኪመስል ጠይም የሐበሻ መልኩ አግዞት አንዷን ሳያስከትል ገብቶ አያውቅም። ይህ የኑሮ ዑደቱ ለአንድም ቀን እንኳ አልተዛነፈበትም። የሚዛነፍበትም አይመስለውም።ደምስን መሰል አንዳች ደጋፊ የሌላቸው ስደተኞች

ዕለታዊ ዕድላቸውን ተጠልለው በናይሮቢ በሽ በሽ ኾነዋል። ሐበሻ በአብዛኛው በሚኖርባቸው እንደ ኢስሊ፣ ፓንጋኒ እና ሐርሊንግሃም አካባቢዎች አይጠፉም። ብዙዎች ከዐሥር ዓመታት በላይ የቆዩ

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

በመኾናቸው ዘመድ አዝማድ እጁን ማስረዘም ሰልችቶት የተዋቸው ናቸው። ወደ አገር ቤትም የመመለስ ሐሳብ ለብዙዎቹ እንደ መርግ ከብዷቸዋል። አንዳንዶቹ ነገን ተስፋ በማድረግ ቀሪዎቹ ደግሞ “ምን ይዤ ልመለስ” በሚለው ሐሳብ ራሳቸውን እየሞገቱ ጭንቅላታቸው ውስጥ የ”መመለስን” አራት ነጥብ አትመዋል። በፖሊቲካ ጉዳይ የተሰደዱት ደግሞ በአማራጭ ዕጦት ውሳኔያቸው አየር ላይ ነው።

የዐዩ መንገድ . . .ይህ ሁሉ ሕይወት እና ሐሳብ በሚናጥበት የስደተ

ኞች ምድር ወደ አገር ቤት ለመመለስ “የዐዩን ድፍረት ይስጥህ” የምትል ቀልድ ትደመጣለች። ዐዩ ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ 15 ሺሕ ዩሮ ከቤተሰቡ ይዞ የመጣ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነው። 15 ሺሕ ዩሮው በአጠቃላይ ለአሜሪካ ጉዞው (ፕሮሰሱ) ማስፈጸሚያ የተመደበለት ሲኾን ለዕለታዊው ወጪው ደግሞ እስከ አራት መቶ ዶላር የሚደርስ ገንዘብ በየወሩ ይላክለት ነበር። ካልበቃው ደግሞ እጅግ የሚሳሱለት ዘመዶቹ ፈጥነው ይጸድቁበታል።ከቁጠባ ይልቅ አለማባከንን የሚያስተምረው ዐ

ጣ። ለወትሮው የስደተኞችን አርፍዶ መነሳትን የለመደ ቢኾንም ከብክነት አልታደገውም። አራት መ

ቶ ዶላር ለወር አልበቃ እያለው ተቸገረ። ቀዳዳ ለመሸፈኛ ተብለው የሚላኩ ዩሮዎች ሊበግሩት አልተቻላቸውም። ወጪው ባስ ሲልበት ለአሜሪካ “ፕሮሰስ” የተባለችውን 15 ሺሕ ዩሮ ይዳብሳታል፤ ገንዘብ ይላካል- እርሱ ያጠፋል። ከተቀማጭ ዩሮ ላይ ይመዛል። በቀን ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ያስጨነቀው አስቀማጭ ባንክ ተቀማጭ ገንዘቡን እንዲወስድ ዐዩን እሰከ መገሰጥ የደረሰበት ጊዜም ነበር።ለዐዩ ገንዘብ የልውውጥ ሳይኾን የነውጥ መሣርያ

ኾነ። በሄደበት መሸታ ቤት ዶላር ይተኩሳል፤ ዮሮ ይወረውራል። የሚላከውን ጨምሮ ተቀማጩን ዩሮ ለማሟጠጥ ግን ስድስት ወራት በቂ ነበሩ። ይኼን የሰሙ ቤተሰቦች አንድ ዶለርም አንልክ ወደሚል ውሳኔ ተዛወሩ። ለወር ያህል የገዛቸውን የቤት ቁሳቁሶች በመሸጥ ኑሮን ታገላት፤ አልቻለም። አንድ ማለዳ ቆረጠ። የናይሮቢ ቆይታው ዓመት እንኳ ሳይኾነው ወደ እናት ምድሩ ተመለሰ።ለብዙዎች ዐዩ የተጓዘው መንገድ ቀላል እና እኛም

ልንከተለው እንችላለን የሚሉት ዐይነት አይደለም። ፖለቲካው ያስፈራቸዋል፤ ባዶ እጅ መመለሱ አንገ

ተስፋ የማይጨልምበት የስደት ህይወት(ታሪኩ አዳፍሬ ከኬንያ)

አዲስ ነገር ኦንላይን

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

Page 9: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 9

ተምሳሌት

ሐበሻዊ ቃና፡-ወይዘሮ ፍቅርተ ከሀገርሽ መቼ እና እንዴት ወጣሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- በመጀመሪያ የሄድኩት ወደ ናይ

ሮቢ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የሄድኩት በአጋጣሚ ነው ፡፡ ከዚያ በፊት አዲስ አበባ ዜኒት ኮስሞቲክስ የተባለ ድርጅት ውስጥ በተለያየ ስራ ሀላፊነት አስራ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ናይሮቢ ትኖር የነበረችው እህቴ በአጋጣሚ ልትጠየቀን አዲስ አበባ መጣች፡፡ እህቴ ጠይቃን ስትመለስ ታዲያ እኔም ለእረፍት በሚል የእሷን ልጅ ይዤ ወደ ናይሮቢ ሄድን፡፡ በዚህ መካከል ናይሮቢ ሆኜ ካናዳ ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመርኩ፡፡ የአሁን ጊዜ ፕሮሰስ እንደምታውቀው ነው፡፡ ከአንድ ዓመት እስከ አራት ዓመት ይፈጃል፡፡ የኔ አራት ዓመት ነበር የፈጀው፡፡ በዚያ ሁሉ ጊዜ ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ በስነጽሁፍ፡ ድራማና በመሳሰሉት ነገሮች ከማገልገል ውጪ ምንም ስራ አልነበረኝም፡፡ያው ቤት ወስጥ ነበር ቁጭ የምለው፡፡ ምክንያቱም በዚያን ወቅት ናይሮቢ የምትወጣበት ሀገር አይደለም፡፡ስትወጣ በፖሊስ ትያዛለህ፡፡ከአንዴም ሁለት ጊዜ በአጋጣሚ ሱቅ እቃ ልገዛ ስወጣ በፖሊስ ተይዤ ታስሬአለሁ፡፡ በተለይ አንድ ጊዜ ለስለሳ ልገዛ ስወጣ በአጋጣሚ ፖሊሶች ሰዎችን እያፈሱ እስር ቤት ያስገቡ ነበርና እኔም ተይዤ እስር ቤት ገባሁ፡፡ያኔ እጄ ላይ የነበረው 70 የኬኒያ ሽልንግ ብቻ ነበር፡፡ከዚያም ተፈተሸን ያለንን ካስረከብን በኋላ ወደ እስር ቤት ገባን፡፡ገና በሩ ሲከፈት በጨለማ ቤት ውስጥ የታፈገ ሙቀት ከመጥፎ ሽታ ጋር ተቀበለኝ፡፡ከቤት በድንገት እንደወጣሁ ስለነበር ምንም የለበስኩት ነገር አልነበረም፡፡በባዶው መቀመጥ ሲ

መታመኔ ለዚህ አድርሶኛል

ከወይዘሮ ፍቅርተ ሙላት ጋር ቀጠሮአችን እሁድ ዘጠኝ

ሰዓት ላይ ነበር፡፡ ካሳንጋ አካባቢ ከሚገኘው ቤቷ

200 ሜትር ያህል መጥታ ተቀበለችኝና ወደ መኖሪያ

ቤቷ አመራን፡፡ እሷን ተከትየ ወደ ቤት ስዘልቅ ቡናው

ተፈልቶ ቄጠማው ተጎዝጉዞ እውነትም እሁድ ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ

ቴሌቪዥን የእሁድ መዝናኛ ዜና እየተነበበ ነበር የደረስነው፡፡ አንባቢዋ

በአሜሪካ ታዋቂዋና የመጀመሪያዋ ሴት የቶክሾው አዘጋጅ ኦፕራ ዊንፈሬ

ለ25 ዓመታት ከቆየችበት የቶክሾው አለም መሰናበቷን እያነበበች

ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ገና ያልተሰናበተች ይልቁንም ከትንሽ ተነስታ በሰው

ሀገር በስኬት ጉዞ ላይ ስላለች የ35 ዓመት ወይዘሮ የህይወት ተሞክሮ

ቃለመጠየቅ ላደርግ እየተዘጋጀሁ፡፡ ቆይታችን ይህን ይመስላል፡፡

ንደሰራሁ ግን ሰውየው(አከራዩ) በጣም የቤት ኪራይ ጨመረብኝ፡፡በቃ ከዚያ ትቼው ወደዚህ(ካምፓላ) ተመለስኩኝ፡፡ ከዚያ እንደገና ደግሞ ዝም ብየ ቁጭ አልኩ፡፡ ስራ የለ ምን የለ፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵያ የደህና ቤተሰብ ልጅ ነኝ፡፡ ግን እንዴት ብየ እንደገና ከኢትዮጵያ ወደዚህ ገንዘብ ላኩ እላለሁ? እኔ ሰው አልመለከትም፡፡ እዚህ ጋር ወንድም አለኝ እዚህ ጋር እህት አለኝ አልልም፡፡ ነገሮችን በራሴ ማድረግ እንጂ ሰው ማስቸገር አልፈልግም፡፡ አንድ ቀን በጣም ምርር ብሎኝ በረንዳ ላይ ወጥቼ እያለቀስኩ አካራያችን ‹‹ፍቅርተ ምን ሆነሻል?›› አለችኝ፡፡ እስኪ ሱቅ ካለ ትንሽ ሱቅ ፈልጊልኝ አልኳት፡፡ ከዚያ አሁን ያለሁባትን ሱቅ አገኘችልኝ፡፡ግን ገንዘብ እጄ ላይ የለኝም፡፡የተረፈችኝ ገንዘብ 200 ሺህ ሽልንግ አካባቢ ብቻ ነበረች፡፡ሰዎቹ ደግሞ የአራት ወር ካልከፈልሽ አሉኝ፡፡ከዚያም እሺ ላምጣ ብየ ወደ ቤት ስሄድ ሌሎች ሰዎች ቦታውን አይተውት ሄደዋል፡፡እዚህ ሀገር ደግሞ ቦታ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡በዚህ ጊዜ ቤት ውስጥ የተቀመጠ ገንዘብ ነበር ሰርቼ እከፍላላሁ ብየ በድፍረት ገባሁና ሱቁን ጀመርኩ፡፡ከዚያ በኋላ ያለውን ታሪክ እኔ አላውቀውም፡፡ሁሉን ነገር የሰራውም ሆነ የሞላው መድሃኒዓለም ነው፡፡ ሐበሻዊ ቃና፡- የሱቅ ህይወትስ ስትጀምሪ ምን

መልክ ነበረው? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ሱቁን ስጀመር መጀመሪያ በሸቀ

ጣ ሸቀጥ ነበር፡፡ከዚያ እንጀራ አስገባሁ፡፡እንጀራ ምጋግረው ራሴ ነበርኩ፡፡ከጧት እስከማታ ሱቅ ስሰራ እውላለሁ፡፡ ማታ ቤት መጥቼ ሊጥ አቦካለሁ፡፡ አብሲት እጥላለሁ፡፡ እንጀራው ይጋገራል፡፡የነገውም እ

ንደዚያ እየሆነ ይቀጥላል፡፡ አንድ ጊዜ የሆንኩትን ወይም የገጠመኝን ላጫውትህ፡፡ ሌሊት እንጀራ እየጋገርኩ ምጣዱን አስምቼው ቁጭ እንዳልኩ ከመድከሜ የተነሳ እንቅልፍ ወስዶኛል፡፡ ብንን ስል የምጣዱ ቫልቮላ ነዶ ቤቱ በጪስ ታፍኗል፡፡ ቤቱን ከፍቼ እንዳልወጣ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ሆኗል፡፡ ፈራሁ፡፡ያለኝ አማራጭ አፌን በትራስ አፍኜ እንደምንም ታግየ ማሳለፍ ነበር፡፡ ይህን ጊዜ መቼም አልረሳውም፡፡አሁን ግን እግዚአብሄር ይመስገን ጠንክሬ በመስራቴ እዚህ ደርሻለሁ፡፡ሐበሻዊ ቃና፡- የት ደረስሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- አሁን ያለሁበት (ረጅም ሳቅ…)ሐበሻዊ ቃና፡-ወይዘሮ ፍቅርተ መርካቶ ማለት

ናት ይባላል፡፡ አውነት ነው?ወይዘሮ ፍቅርተ፡-አዎ! የሌለ ነገር የለም፡፡ እቃዎ

ችን በሙሉ አስገባለሁ፡፡ ብዙ መደርደሪያ ነው ያለው፡፡ እነዚያ መደርደሪያዎች ጾማቸውን እንዲያድሩ አልፈልግም፡፡እያንዳንዱን እንደ ልጆቼ ነው የማያቸው፡፡ ለስራየ ትልቅ ትኩረት አለኝ፡፡ ሌላ ነገር ብወድም ቅድሚ ግን ሁሌም ለስራየ ነው፡፡ሁሌም ስራየን አክብሬ ስለምሰራው የማከብረውን ያክል ውጤት ይሰጠኛል፡፡ይህ ለነገ ይሄ እንዲህ ይሆናል አልልም፡፡ ሁሉንም በፍጥነት እሰራለሁ፡፡ የስራ ሀሳቦችን የመፍጠር ችሎታም አለኝ፡፡ከሰዎች በቀጥታ አልገለብጥም፡፡ለሌላው የማይታየውን ነገር ይሄን እንዲህ ባደርገው እንዲህ ይሆንልኛል ብየ ያንን አደርጋለሁ፡፡ ውጤትም አገኝበታለሁ፡፡ ከምንም በላይ እ

ያቅተኝ ብትክትክ ያለ ብርድልብስ አገኘሁና እሱ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ እሱም ግን ተባይ የሞላበት በመሆኑ እንዲሁ ቆሜ አደርኩ፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ደግሞ ሴተኛ አዳሪዎችን ሰብስበው ይዘዋቸው መጡ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእነሱ ጋር ቀላቀሉኝ፡፡ ሴተኛ አዳሪዎቹ በጣም ጠጥተው ስለነበር ያስመልሳቸው ነበር፡፡በህወቴ ከተማረርኩባቸው ጊዜ አንዱ ነበር፡፡ ጥዋት ደግሞ ውጡ ተባልንና ሽንትቤት እንድንጠርግ ታዘዝን፡፡ ቤተሰቦቼ ደግሞ የት እንደታሰርኩ እንኳን ጠፍቼባቸው በስንት ሰው አፈላልገውኝ በታሰርኩ በሳምንቱ 3 ሺህ የኬኒያ ሽልንግ ከፍየ ከእስር ቤት ወጣሁ፡፡ይህ ጊዜ በጣም አስከፊ ጊዜ ነበር፡፡በዚህ መሃል አብሬአቸው እኖር የነበሩት እህቴና ወንድሜ በሰራ ምክንያት ወደ ኡጋንዳ መጡ፡፡ እኔ ግን የጀመርኩትን የካናዳ ፕሮሰስ መጠበቅ ስለነበረብኝ ብቻየን ናይሮቢ ቀረሁ፡፡አራት ዓመት ሙሉ ጠብቄ ውጤቱ ስመጣ ግን ጥያቄየ(ፕሮሰሱ) ውድቅ ሆነ፡፡ ቃለ ምልልሱን አላላፋችሁም ተባልን፡፡ከዚያ የነበረኝ አማራጭ እህትና ወንድሜ ወዳሉበት ካምፓላ መምጣት ነበር ፡፡ ሐበሻዊ ቃና፡-ካምፓላ እንዴት ተቀበለችሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ካምፓላ መጥቼ አንድ ዓመት እ

ንደቆየሁ እህቴ ከባለቤቷ ጋር ወደ አሜሪካ ወንድሜ ደግሞ ወደ ካናዳ ሄዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ህይወት በ…ጣም አስከፊ ነበር፡፡ በተለይ ምርር ብየ ያለቀስኩት እህቴ ስትሄድ ነበር፡፡ልገልጽልህ ይከብደኛል፡፡አንዳንድ ጊዜ የምትገልጸው አለ አንዳንዴ ደግሞ መግለለጽ የማትችለው አለ፡ ውስጥህ ዝም ብሎ የሚቀመጥ፡፡ ማንም አጠገቤ አልነበረም፡፡ ያደግሁት ከቤ

ተሰብ ጋር ነው…እና…(አይኗ እንባ አቅርሮ ንግግሯን አቋርጣ ነበር)፡፡መጀመሪያ ያገባሁት ባል ነበር፡፡ እሱም….(አሁንም ንግግሯን መጨረስ አልቻለችም)፡፡ አስበው እዚህ ጋር አይዞህ ባይ ቤተሰብ የለህም፡፡ እዚህ ጋር ባል ብየ ያገባሁት ከድቶኛል፡፡ ምን ውስጥ ነው ምገባው? በቃ ብቻ በጣም ችግር ውስጥ ነበርኩ፡፡ በጣም መራራ ህይወት ነበር፡፡ የማደርገው ሳጣ ፋሲካ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ተቀጠርኩ፡፡ ያም ሁሉ እየሆነ ግን ስራየን በደንብ እሰራ ነበር፡፡ ይሄ የሰው ቤት ነው ይሄ የኔ ነው አልልም ነበር፡፡ ጭንቅላቴም በጣም ፈጣን ስለሆነ ነገሮችን በደንብና ቶሎ ቶሎ መስራ እችላለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የማገኘው ገንዘብና የቤት ኪራይ የምከፍለው ሊመጣጠንልኝ አልቻለም፡፡ፋሲካ አራት ወር ያክል እንደሰራሁ የሆነ ሰው በሀሳብ እረዳኝ፡፡ ‹‹ፍቅርተ ለምን የሆነች ትንሽ ምግብ ቤት ለራስሽ አታቋቁሚም፡፡ በጣም ጎበዝ ስለሆንሽ ይሳካልሻል››ሲለኝ እሺ አልኩ፡፡ከዚያ ኪሲኒ አካባቢ ናይል ኮች የሚባል ጋራዥ አለ፡፡ጋራዡ ውስጥ ትንሽ ሜዳ ሰጡኝ፡፡ሜዳዋን እኔ ራሴ ጣራ ሰርቼ በሰሌን ሸፍኜ ምግብ ማብሰል ጀመርኩ፡፡ ብዙ ተመጋቢዎች ነበሩ፡፡ በተለይ ሾፌሮች ይሄዳሉ፡፡ ይመጣሉ፡፡ ቁርስ ምሳ ራት ይበላሉ፡፡ ይህም ሁሉ ሲሆን ግን ብቻየን ነበርኩ፡፡ገባህ? አንዱ እንጀራ አዝዞኝ ሳልጨርስ አንዱ አምባሻ ሲለኝ በጎን ደግሞ እንጀራ እጋግራለሁ፡፡ ያቺ ጊዜ በጣም የውጥረት ነበረች፡፡ ለሁለት ወር ያህል በዚህ መልኩ እንደሰራሁ ወደ ኮቦኮ(ሱዳን መስመር) ሄድኩ፡፡ በዚያም የጋራ ስራ አግኝቼ እየሰራሁ ጥሩ ገበያም እያገኘሁ ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ሶስት ወር ያክል እ ወደ ገጽ 18 ዞሯል

Page 10: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)10 ሀበሻዊ ቃና

ጥበብ

ሳሚ-ኡጋንዳ ተስፋይ-ዛንዚባር

ልቡ ጥፍት እስኪል ድረስ ሙዚቃ ይወዳል። የ23 ዓመት ኡጋንዳዊ ወጣት ነው። ሪቻርድ ቱኻሂሮ ይባላል። የሙዚቃ ዝግጅቶችን ሥራውን ትቶ

ም ቢኾን ያያቸዋል። እንደ ጆሴ ካሚሊዮን ያለ ዘፋኝ የሚገኝበት ከኾነ ደግሞ ከዝግጅቱ ላይ ተዐምር እንኳ ቢፈጠር አይቀርም። ባለፈው ጥር መጨረሻ ኢንቴቤ ወደሚገኘው ሪዞርት ቢች ሲሄድም የዘፋኞቹን ማንነት ተመልክቶ ነበር። “ባትል ኦፍ ዘ ቻምፒዩንስ” (የአሸናፊዎቹ ጦርነት) የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ሁለቱ እውቅ የኡጋንዳ ዘፋኞች ካሚሊዮን እና ቦቢ ዋይን አብረዋቸው የሚጫወቱ ዘፋኞችን አስከትለው መድረክ ላይ ተሰየሙ። የካሚሊዮን ወገን በኾነው “ሊዮን አይላንድ” በኩ

ል በኡጋንዳ መድረክ ያልተለመደ ፊት ታየ። በዚህ ወጣት ዘፋኝ የሚቀርበው ሙዚቃ ያልተለመደ ምት ያለው ነው። ቋንቋውም የተለየ። ዳንኪራ ወዳዶቹ ኡጋንዳውያን ቋንቋውን ከቁብ ሳይቆጥሩ ምቱን እየተከተሉ ለመውረግረግ ሞከሩ። ለሪቻርድ ግን የወጣቱ አዘፋፈን በአገሩ ዘፋኞች እንደለመደው ፈጠን ያለ አልነበረም። ዘፋኙ ሙዚቃውን ሲያበቃ ታዳሚው በድጋፍ ጩኸት አጀበው። ይኼኔ ካሚሊዮን ወደ መድረክ ወጥቶ ወጣቱን አስተዋወቀው። ሪቻርድ የዘፋኙን ስም በቅጡ አልሰማም። ዜግነቱን ግን አልዘነጋውም። ኤርትራዊ። ይህ በኾነ በወሩ የዚህን ኤርትራዊ ዘፈን እንደገና ሰ

ማ። ምክንያቱ አሁንም ካሚሊዮን ነበር። ከበርካታ የውጭ አገር አቀንቃኞች ጋራ በጋራ የሚዘፍነው ካሚሊዮን ከኤርትራዊው ጋራ አዲስ ነጠላ ዜማ በመሥራቱ ነበር ሪቻርድ ዘፈኑን ሊሰማ የቻለው። ሪቻርድ ዘፈኑን አብዝቶ ከመውደዱ የተነሳ ሞባይሉ ላይ አስጫነው። ዘፈኑ “ክበቡዋ” ከሚለው ርዕሱ ጀምሮ በአብዛኛው በትግርኛ ቋንቋ የተዜመ ቢኾንም ሪቻር

ድን ከማድነቅ አላገደውም። “የማውቀው ነገር ቢኖር ስለፍቅር እንደሚዘፍን ነ

ው” ይላል ኤርትራዊው ዘፋኝ በስንኞቹ ውስጥ የሚለውን እየገመተ። ግምቱ ደግሞ ካሚሊዮን በዘፈኑ ጣልቃ እየገባ በእንግሊዘኛ ከሚያዜመው የተመዘዘ ነው። ካሚሊዮን “አንቺ ንግስቴ ስትኾኚ እኔ ደግሞ ንጉስሽ እኾናለሁ” ሲል ሪቻርድም አብሮት ይወጣዋል። ካሚሊዮን ይቀጥላል። “በፍቅር ስታከንፊኝ ያለኝን ሁሉ እሰጥሻለሁ። ዳይመንድም ቢኾን።” ሪቻርድ እነዚህን ስንኞች ቃል በቃል ይላቸውና አዝማች የኾነውን “ክበቡዋ”ላይ ሲደርስ ቀጥ ይላል። ግን ዘፈኑን ከመስማት አያቋርጥም። “ቤቴ ደግሞ የዘፈኑ ቪዲዮ ክሊፕ አለኝ” ይላል። ሪ

ቻርድ የዘፋኙን ስም ያወቀው በዚያ የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ተጽፎ ካነበበ በኋለ ነበር። የዘፋኙ ስም ተጽፏል። ለማስታወስ ቀለል ያለ ስም ነው። ሳሚ።

ከ“ክበቡዋ” እስከ “ፎር ኦል ታይም” የ“ክበቡዋ” ዘፈን የሙዚቃ ቪዲዮ የቀረበው የካሚ

ሊዮን በኾነው የሙዚቃ አሳታሚ “ሊዮን አይላንድ” ነው። የሙዚቃ ቪዲዮው የሚጀምረው “ምሥራቅ አፍሪካን እመራለሁ” የሚል ጽሑፍ ያለበትን ቲሸርት ያደረገውን ካሚሊዮንን በማሳየት ነው። እንደካሚሊዮን ሁሉ መነጽር ያደረገው ሳሚ ተከትሎት ይመጣል። ስሙ እና የኤርትራ ባንዲራም አልቀረም። ቪዲዮው በጥቁር እና ነጭ ቢጀምርም ቀለም ያለባቸውን ትዕይንቶች እያሳየ ይቀጥላል። ሳሚ እና ካሚሊዮን እየተፈራረቁ በሚያቀነቅኑበት በዚህ ክሊፕ የዩጋንዳውያን እንስቶች ምስል በየጣልቃው ይገባሉ። በዘፈኑ መጨረሻ ለኤርትራዊው ዘፋኝ ዮሐንስ ትካኽቦ (ወዲ ትካኽቦ) ምስጋና የሚቀርብበት ጽሑፍ ይነበባል። ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ ለሳሚ የመጀመርያው አይደ

ለም። ይህ ሙዚቃ ለሕዝብ ዕይታ ከመብቃቱ ሁለት ወራት በፊት ሳሚ ከሌላ እውቅ ኡጋንዳዊት ዘፋኝ ጋራ የቪዲዮ ክሊፕ ሠርቶ ነበር። አብራው የሠራችው አቀንቃኝ ጃኪ ቻንዱሩ ትባላለች። “ብሉ 3” ተ

ብሎ የሚታወቀውን የሴቶች የሙዚቃ ቡድን ከመሠረቱ ዘፋኞች አንዷናት። ሲንዲ የተባለችው የቡድኑ አባል ለብቻዋ መዝፈን መጀመሯን ተከትሎ ዝናው የደበበዘውን “ብሉ 3” ገሸሽ አድርጋ የራሷን ሥራዎች እያቀረበች የምትገኝ ነች። ካሚሊዮንን ጨምሮ ከተለያዩ ዘፋኞች ጋራ በጥምረት የምትሠራው ጃኪ ከሳሚ ጋራ የተገናኘችው በአጋጣሚ ነው። ጃኪን ከሳሚ ጋር ያገናኛት የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሯ ነ

በር። ያን ጊዜ ጃኪ እና የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሯ ለየት ያለ ነገር ለመሥራት የተነጋገሩበት ወቅት ነበር። መነሻቸው ደግሞ እንግሊዛዊው ሙዚቀኛ ስቲንግ ከአልጄሪያዊው ሼብ ማሜ ጋር በጋራ የተጫወቱት “ዴዘርት ሮዝ” (የበረሃ ጽጌረዳ) የተሰኘ ዝነኛ ዘፈን ነው። እ.ኤ.አ በ1999 የተሠራው ይህ ዘፈን በዐረብኛ እና እንግሊዘኛ ቅልቅል የተሠራ ነበር። በአንድ ወቅት በአሜሪካ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ ከምርጥ ዐሥሮች ተርታ ውስጥ መግባት የቻለ ነበር። “መቀየጡን ወደድኩት” ትላለች ጃኪ ስለዘፈኑ ስ

ታነሳ። ጃኪ እንዲህ ዐይነት ቅይጥ ዘፈን ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት የተረዳው ፕሮዲዩሰሯ በሥራ አጋጣሚ የሚያውቀውን ሳሚን አግኝቶ እንዲያነጋግራት ይመክረዋል። ሳሚ እንደተባለው ያደርጋል። ጃኪም ከሳሚ ጋራ በጥምረት የመሥራት ሐሳቡን ትቀበላለች። በምን ጉዳይ ላይ አተኩረው እንደሚዘፍኑ ከሳሚ ጋራ ከተነጋገሩ በኋላ ዜማውን ደርሳ፣ ራሷ የምትዘፍነውን ግጥም ጽፋ፣ የዘፈኑን አዝማች አውጥታ በአጭር ጊዜ ጨረሰች። ሳሚ በበኩሉ በትግርኛ የሚያወርደውን ስንኝ አዘጋጅቶ አመጣ። ስቲንግ ሼብ ያዘጋጀውን የዐረብኛ ስንኞች መረዳት እንደማይችል ሁሉ ጃኪም የሳሚን የትግርኛ ግጥም አንዱንም ቃል አታውቀውም። ልክ እንደ ስቲንግ እና ሼብ የየድርሻቸውን ይዘው

የመጡት ሳሚ እና ጃኪ ስቱዲዮ ተገናኙ። ከሦስት ሰዓት ቆይታ በኋላ “ፎር ኦል ታይም” የተባለው ዘፈን በጃኪ ፕሮዲዩሰር አቀናባሪነት ለጆሮ የሚመች ጥዑም ዘፈን ኾኖ ብቅ አለ። ሁሉም ሙዚቃውን ወደዱ

ኢትዮጵያዊው ተስፋይ ከታንዛኒያዊው ማቶና ጋር የተጣመረበት ሙዚቃ በአድማጭ እና ተመልካች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል

የታንዛኒያ አካል በኾነቸው ዛንዚባር የሚኖረው ማቶና ቫዩሊን እና ኡድ የተሰኙ መሣሪያዎችን ይጫወታል

ፎቶ

- ሴንት

ሪክስ

ፊልም

ፎቶ

- ከቪ

ዲዮ

ክሊ

ፑፎ

ቶ- ከ

ቪዲ

ዮ ክ

ሊፑ

በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

Page 11: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 11

ጥበብት። እናም የሙዚቃ ቪዲዩ ሊሠሩለት እዚያው ስቱዲዮ እያሉ ወሰኑ። “የተለየ ዐይነት ሙዚቃ በመኾኑ ይበልጥ በቪዲ

ዮ ለመግለጽ ፈለግን። በኡጋንዳ ሰው ሙዚቃህን የሚቀበለህ በቪዲዮ አስቀረጽህ ካቀረብክለት በኋላ ነው” ስትል ክሊፑን ወዲያውኑ መሥራት ያስፈለገበትን ምክንያት ለሐበሻዊ ቃና ታስረዳለች።

ከባዱ ቀረጻ የሳሚ እና የጃኪ ቪዲዮ ክሊፕ ሥራ እንደ ዘፈን ቀ

ረጻው በቀላሉ የተከናወነ አልነበረም። የሙዚቃ ክሊፑን እንዲሠራ የተመረጠው “ሴንትሪክስ ፊልምስ” የተሰኘው ድርጅት ነበር። ከተመሠረተ ስድስት ዓመት ያስቆጠረው ይህ ድርጅት የጃኪን እና የ“ብሉ 3”ን ቀደምት ሥራዎች የቀረጸ ነው። የዚህ ድርጅት መሥራች እና የጀርባ አጥንት የኾነው ዴኒስ የአገሪቱን እውቅ ዘፋኞች ሙዚቃ ቪዲዮ ያዘጋጀ ነው። የጃኪ እና ሳሚ ምርጫም ኮምፒዩተር ኢንጀነሪንግ አጥንቶ ሙዚቃ ክሊፕ ወደማዘጋጀት የዞረው ዴኒስ ነበር። “በጋራ ኾነው ደወሉልኝ እና ስለዘፈናቸው ነገሩኝ”

ይላል ዴኒስ የመጀመሪያ ቀን ግንኙነታቸውን ለ“ሐበሻዊ ቃና” ሲያስታውስ። “ሁሉንም ነገር ተነጋገርን።” ቪዲዮውን እንዴት እንደሚቀርጽ የተለያዩ ሐሳቦ

ችን ሲያወጣ እና ሲያወርድ የሰነበተው ዴኒስ በስተመጨረሻ በሁለት አማራጮች ይረጋል። ከሁለቱ ዘፋኞች ጋራ በተደረገ ውይይት አንዱ ይመረጥ እና ወደ ቀረጻ ለመግባት ቦታ መረጣ እና መሰል ዝግጅቶች ይጀመራሉ። ከሦስት ሳምንት ዝግጅት በኋላ በአንድ ቀዝቃዛ ምሽት ሳሚ እና ጃኪ “ካዌምፔ” ተብሎ ወደሚጠራው የካምፓላ ክፍል ያመራሉ። መዳረሻቸው ፋብሪካ ነው። በቦታው ሲደርሱ አካባቢው በመብራት ደምቆ ካሜራዎች ተጠምደዋል። የዕለቱ የአየር ጸባይ ግን ቀረጻውን ለማከናወን አመ

ቺ አልነበረም። በቪዲዮ ክሊፑ ለተካተተው ወገብ ንቅናቄ ሲባል የተመረጡት አልባሳት ደግሞ ሰውነትን የሚያጋልጡ ነበሩ። “ይዘንብም ስለነበር አየሩ ቀዝቃዛ ነበር። አካባቢ

ውም ጭቃማ ኾኗል። ሁሉም ነገር በተሳሳተ አቅጣጫ የሚሄድ ይመስል ስለነበር በጣም ተናድጄ ነበር። ደስተኛ አልነበርኩም” ትላለች ጃኪ በዕለቱ ስለነበረው ኹኔታ ስታስረዳ። ቀረጻው ግን በዚያው ዕለት መካሄድ ነበረበት እና

ተደረገ። አብዛኛው ቀረጻም በትልቅ የብረት ቱቦ ውስጥ እና አጠገብ ተከናወነ። ጃኪም ልብሶቿን እየለዋወጠች፣ የሳሚን ስም በቁልምጫ እየጠራች፣ ሲያሻትም ፊቱ እየተውረገረገች ተቀረጸች። ሙሉ ጥቁር ኮት እና ሱሪ የለበሰው ሳሚም የት ድረስ መተወን እንደሚችል አሳየ። ቀረጻው አበቃ።

የዝና ጣሪያ ቀረጻው የተጠናቀቀው እ.ኤ.አ ነሐሴ 2010 አካባቢ

ቢኾንም ተመልካቾች ዘንድ ለመድረስ ግን አምስት ወር ግድም ዘግይቷል። መውጫው ቢዘገይም ለመጀመሪያ ጊዜ በ“ዩ ቲዩብ” ድረ ገጽ ሲለቀቅ የአድናቆት አስተያቶች ጉረፉለት። ወራት ዘግየት ብሎ በቴሌቪዥን ለተመልካች ሲቀርብም ከፍተኛ ተወዳጅነትን አተረፈ። እንደ ኤን.ቲ.ቪ የመሳሰሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሙዚቃ ዝግጅቶቻቸው ደጋግመው የሚመርጡት ዘፈን ኾነ። ዘግይቶ ተወዳጅነት ማትረፉን በተመለከተ ጃኪ የምትለው አላት።“በኡጋንዳ በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ የሙዚቃ ቪዲ

ዮዎች ስለሚወጡ የተመልካቾችን ቀልብ ለመግዛት ከባድ ነው” ትላለች።የቪዲዮው ተወዳጅ መኾን ሳሚን በበርካታ መድ

ረኮች ላይ ከጃኪ ጎን እንዲቆም አደረገው። የግል ድርጅቶች በባለ ኮኮብ ሆቴሎች በሚያዘጋጇቸው ድግሶች ላይ ጃኪን የሚጋብዙ ከኾነ ሳሚ የማይቀር ተጣማሪ ኾነ። ከመጀመሪያው ቪዲዮ በኋላ ጥቂት ቆየት ብሎ የወጣው “ክበቡዋ”ም እንዲሁ ተወዳጅነት በማትረፉ የሥራ ጥሪዎች ይበዙለት ጀመር። የሁለቱ ሙዚቃዎች ተወዳጅነት ይበልጥኑ ሳሚን ተጠቃሚ ቢያደርጉትም ለካሚሊዮን እና ጃኪም ያልተጠበቀ ግብዣ አምጥቶላቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው። ኻያኛውን የኤርትራ የነጻነት በ

ዓል በደመቀ ኹኔታ በአሥመራ ለማክበር ከታቀዱት ዝግጅቶች አንዱ ከውጭ አገር የሚመጡ አርቲስቶች የሚሳተፉበት ታላቅ ኮንሰርት ማዘጋጀት ነበር። ካሚሊዮን እና ጃኪ ከሳሚ ጋራ ያስቀረጹትን ቪዲዮ የተመለከቱት የኮንሰርቱ አዘጋጆች ሁለቱን ኡጋንዳውያን ለነጻነት በዐሉ ይጋብዟቸዋል። “ኤኬ 47” በተሰኘው የመድረክ ስሙ የሚታወቀው የካሚሊዮን ወንድም እና ዲጄ አሉዳ ከኡጋንዳ የተጋበዙ ሌሎች ሙዚቀኞችም ነበሩ። እነዚህ አራት ኡጋንዳውያን ዝግጅቶቻቸውን ለማቅረብ ከፍተኛ ክፍያ መቀበላቸውን የኡጋንዳ ሚዲያዎች ቢዘግቡም ወደ አሥመራ የተጓዘችው ጃኪ ብቻ ነበረች። ጃኪ ከኤርትራ የነጻነት ቀን አራት ቀናት ቀደም ብ

ሎ በሮማ ሲኒማ በተካሄደው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የራሷን ዘፈን አቅርባለች። የመግቢያ ዋጋው 700 ናቅፋ የነበረው ይኼው ዝግጅት በኤርትራ መንግሥታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ኤሪ ቲቪ) አማካኝነት በቀ

ጥታ ተላልፏል። ሳሚ አብሯት ወደ ኤርትራ ባለመጓዙ ምክንያት የጋራ ዘፈናቸውን ሳታቀርብ ብትቀርም በዳንስ የታጀበው የጃኪ እንቅስቃሴ ከተመልካች አድናቆትን አስገኝቶላታል። እርሷም ከሕዝቡ ባገኘችው አቀባበል ደስ መሰኘቷን ገልጻለች። “በኤርትራ የነበረኝ ቆይታ አስደሳች ነበር። በሌላ ጊ

ዜ ተመልሼ እሄዳለሁ” ትላለች። ፔንታቶኒክ ወንዝ ይሻገራል?

ጃኪ በአንድ ነጠላ ዜማ ምክንያት በሌላ አገር ያገኘችው ተቀባይነት አስደምሟታል። በትግርኛ፣ በአማርኛም ኾነ በሌላ ቋንቋ ከሚዘፍኑ ዘፋኞች ጋራ በጥምረት እንድትሠራ ማበረታቻ ኾኗታል። ተጨማሪ ሥራዎችን ለመሥራት ግን የሚጣመሯት አርቲስቶች ለአዲስ ዐይነት የአዘፋፈን ስልት የተዘጋጁ መኾን እንዳለባቸው ትናገራለች። ኤርትራውያንም ኾኑ ኢትዮጵያውያን የሚከተሉት የሙዚቃ ስልት “ፔንታቶኒክ” እንደመኾኑ መጠን ሌሎች አድማጮችን ለመሳብ ዘፈናቸውን ከሌሎች የዘፈን ስልቶች ጋራ መቀየጥ እንዳለባቸው ትመክራለች። “እኔ የተለያየ ሙዚቃ መስማት ስለምወድ የፔንታ

ቶኒክ ሙዚቃ እወዳለሁ። በፔንታቶኒክ ስልት የሚቀርብ ዘፈን ሳቢ ቢኾንም ሁሉም የሚደስትበት አይደለም” ትላለች። ለዚህ መፍትሄው “መካከለኛውን መንገድ” ማግኘት እንደኾነ ታብራራለች። መካከለኛ መንገድ የምትለውን ለማብራራት የእርሷን እና የሳሚ ቅንጅት ትጠቅሳለች። የሁለቱንም አገራት የአዘፋፈን ስልት ያለቀቀ ግን ደግሞ የተቀየጠ ዘፈን መሥራት ወንዝ ያሻግራል ባይ ነች። እንደሳሚ ሁሉ በዚህ ፈለግ የተመራው ኢትዮጵያ

ዊው ተስፋይ ገብረ ዮሐንስ ወንዝ ተሻግሮ ተሳክቶለታል። ከታንዛንያዊው ሙዚቀኛ ጋራ በሠራው “ቢንቲ ዛንዚባር” ዝነኛ ኾኗል። ዘፈኑ ብዙዎቹ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በሚጋሩት በኪስዋሂሊ ቋንቋ እና በትግርኛ ተቀይጦ የተሠራ ነው። ሁለቱንም ቋንቋዎች የሚጫወተው ተስፋይ ይኹን እንጂ የኪስዋህሊው የዘፈኑ ክፍል ድርሰት የአገሬው ሰው በኾነው ሙሐመድ ማቶና የተሠራ ነው። ማቶና የታንዛኒያ አካል በኾነቸው ዛንዚባር የሚኖር ሲኾን የሙዚቃ አስተማሪ ነው። ቫዩሊን እና ኡድ የተሰኙ መሣርሪያዎችንም ይጫወታል። የተስፋይ እና ማቶና ጥምረት የተወለደው “ኡሞጃ”

በተሰኘው የሙዚቃ ቡድን አማካኝነት ነው። “ኡሞጃ” በሰባት አፍሪካ አገራት ያሉ በባህል እና ጥበብ ዙሪያ የሚሠሩ ቡድኖች ያቋቋሙት ነው። ኢትዮጵያን ወክሎ የ“ኦሞጃ” አባል የኾነው ሰርከስ ኢትዮጵያ ነው። ከመንፈቅ በፊት የሰርከስ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኾኖ የተሾመው እና የሰርከስ ትግራይ መሥራች የኾነው ተስፋይ ለልምድ ልውውጥ ታንዛኒያ ይጓዛል። የ“ኡሞጃ” አባል በኾነው እና ተቀማጭነቱን ዛንዚባር ካዳረገው “ዳው ካንትሪስ ሚዩዚክ አካዳሚ” አስተማሪዎች ጋር ይገናኛል። ማቶና ከተባለው ሙዚቃ አዋቂ ጋራ ይግባባል። መግባባቱ ሙዚቃ በጋራ የመሥራት ሐሳብን ይወልዳል። የታንዛኒያ ቆይታውን ያጠናቀቀው ተስፋይ የሙዚ

ቃውን ሐሳብ ከግብ ሳያደርስ ወደ አገሩ መመለስ ነበረበት። ሙዚቃ የመሥራት ሐሳቡን በቁም ነገር የወሰደው ተስፋይ ማቶናን ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣ እና በጋራ ወደ ስቱዲዮ ይገባሉ። ቫዮሊን እና ኡዱን ተሸክሞ ወደ አዲስ አበባ መጣ። ማቶና ሁለቱን የክር መሳሪያዎች ተጠቅሞ አረብኛ ቅላጼ ያለው የትግርኛ ሙዚቃ ከተስፋዬ ጋር ሰርቶ አጠናቀቀ። ሙዚቃው ዛንዚባር በሄደ ጊዜ የአገሬውን ቆንጆ ዐ

ይቶ በፍቅሯ ስለወደቀ ኢትዮጵያዊ የሚተርክ ነው። ፍቅሩን መግለጽ ግን አቃተው። ኪስዋህሊ ቋንቋ አያውቅ ነገር ምን ብሎ ያናግራት። መፍትሄ መስሎ የታየው ቋንቋውን ማጥናት ነው። እናም አደረገው። አጥንቶም ፍቅሩን በኪስዋህሊ ተነፈሰ። “ናኩፔንዳ” እያለ። እንዲህ ለተሠራ ሙዚቃ ከመልእክቱ ጋራ የሚሄድ ጥሩ የሙዚቃ ቪዲዮ ለማዘጋጀት ተስፋይ ይወስናል። እንደገና ወደ ታንዛኒያ እና ዛንዚባር ሲጓዝ ከነማቶና ጋራ ኾኖ ክሊፑን ቀረጸ። ለሥራ ጎራ ያለባቸውን ኬንያ እና ሞዛምቢክም አልቀሩት። የክሊፑ ሥራ አንድ ዓመት ግድም ፈጅቷል። የዛሬ

ሦስት ወር አካባቢ ተጠናቆ ለዕይታ ሲበቃ ግን በአጭር ጊዜ ተወዳጅ ኾነ። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በታንዛኒያ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቪዲዮው መተላለፍ ሲጀምር ደግሞ የተስፋይን ስም አገነነው። በተለያዩ አገራት ያሉ የሙዚቃ አፍቃሪያን አድናቆታቸውን ገለጹ። “ዘፈኑን ብዙዎች ወደውታል። መዓት ሰው ነው የ

ሚጽፍልኝ” ሲል ተስፋይ ከመቀሌ በስልክ ለ“ሐበሻዊ ቃና” ተናግሯል። ተስፋይ ይህን ዘፈኑን የሠራው የአፍሪካን አንድነት ለማሳየት እንደኾነ ይገልጻል። “ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ ኾና ሳለ በአፍሪካ አንድነት ዙርያ ግን ምንም የተሠራ ሙዚቃ የለም” ይላል። ተስፋይም ኾነ ሳሚ ድንበሩን ሻገር ብለው ከምሥራቅ አፍሪካ አርቲስቶች ጋራ በጥምረት የመሥራትን ጅምር አሳይተዋል። ሌላውን የአፍሪካ ክፍል ማዳረሱን እንደ ቤት ሥራ ወስደው . . . ።

ጃኪ ከሳሚ ጋር በተጫወተችበት ቪዲዩ የተካተተውን የወገብ ንቅናቄ ዳንስ ከዩ-ቲዩብ ተመልክታ የተለማመደችው ነው

ጃኪ እና ሳሚ የሙዚቃ ክሊፑ ዳይሬክተር ዴኒስ የቀረጻውን ወዲያውኑ እየተመለከቱ ለዳግም ቀረጻ ይዘጋጁ ነበር

ፎቶ

- ሴንት

ሪክስ

ፊልም

ፎቶ

- ሴንት

ሪክስ

ፊልም

Page 12: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)12 ሀበሻዊ ቃና

ጥበብ

የግጥም ጥግ

ብዙ አላስብም፤ ሃሳብ እፈራለሁ፤አብዝቼም አልወድም፤ መውደድ እሸሻለሁ፤የልቤንም እምነት፤ በአፌ እክደዋለሁ፤

ራሴን ቆጥቤ፤ አዋድደዋለሁ፤ስበዛ እንደምረክስ በዕድሜዬ ስላየሁ፡፡

ናኦድ ቤተሥላሴሲልቨር ስፕሪንግ-ሜሪ ላንድ ጃንዋሪ 29 2011

ቁጠባ

ከሶስት አመት በፊት የረዥም ጊዜ የአሜሪካ ቆይታውን በመቋጨት ለእናት ሀገሩ በቃ፡፡ ‹‹አገሬ›› የሚል ነጠላ ዜማ ይዞ መጣ፡፡ ኑሮውንም በእናት አገሩ አደረገ፡፡ አዲስ አልበም አጠናቆ በመስራት ለአምባሰል ሙዚቃ ቤት አቀረበ፡፡ ከዛሬ ነገ ይወጣል የሚለው ይህ የቴዎድሮስ አልበም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለሁለት አመታት ዘግይቷል፡፡ ‹‹ጓዳ›› የተሰኘው አዲሱ አልበሙ መስከረም ላይ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ቴዎድሮስ አገር ቤት ጤናው ብዙም አልተመለሰለትም፡፡ ዳግም

ወደ አሜሪካ አቀና፡፡ ከሰሞኑ ታዋቂ የሙዚቃ ባልደረቦቹ ሊጠይቁት ወደ ቤቱ ሄደው ነበር፡፡ ከበር መልሷቸዋል፡፡ እኔ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኜ እንድታዩኝ አልፈቅድም ነው ያላቸው፡፡ እነርሱም ይህንን ሰምተው ከደጅ ተመልሰዋል፡፡ቴዎድሮስ ታደሰ በመጠነኛ የአእምሮ አለመረጋጋትና የድብታ ስ

ሜት እየተሰቃየ ነው፡፡ ቀን ቀን በር ዘግቶ ብቻውን ነው የሚኖረው፡፡ በፋና ኤፍ ኤም ሬድዬ የሚተላለፈውን የ “ኢትዮፒካሊንክ” “ውስጥ አዋቂ” ፕሮግራምን ጠቅሶ ይህንን የዘገበው አዲስ ነገር ኦንላይን ነው።

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ደህና አይደለም

በካምፓላ የሙዚቃ ዝግጅት አቀረበ

የሰራዊት ፍቅሬ “ሂሮሽማ” ፊልም በቅርቡ ተመረቀ

በአቀራረቡ ለየት ፊልም እየተሰራ ነው

ዝነኛው የማስታወቂያ ስራ ባለሙያ እና ተዋናይ ሰራዊት ፍቅሬ “ሂሮሽማ” የተሰኘ አዲስ ፊልሙን ሰኞ ግንቦት 29 ቀን በተለያዩ የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስመረ

ቀ። ፊልሙ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ የኒውክለር ቦምብ በመጣል ከፍተኛ ጉዳት ካደረስባቸው ሁለት የጃፓን ከተሞች በአንዷ ስም የተሰየመ ነው። ሰራዊት ፊልሙን “ሄሮሽማ” ሲል ስያሜ የሰጠውም ጭብጡ ከኒውክለር ጋር ስለሚገናኝ ነው። የአውሮፕላን አብራሪ ሆኖ በ“ሂሮሽማ” የሚተውነው ሰራዊት የ

ኒውክለር ዝቃጭ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ ሲጠየቅ አስቀድሞ በተለቀቀው የፊልሙ ማስታወቂያ ላይ ይታያል። በፊልሙ ላይ ወታደራዊ ትዕይንቶች ተካተውበታል። ሰራዊት ከፊልሙ ተቀንጭቦ በተሰራው ማስታወቂያ ላይ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ ኤ.ፍ.ቢ. አይ እና ሲ.አይ.ኤ አይደለም የምትዘረጋው” እሺ ብሎ በኃይለ ቃል ሲነገር ይደመጣል። በቅርቡ የለቀቀው የ“ትዝታ” ነጠላ ዘፈኑ ተወዳጅነት ያስገኘለት ሚኪኤል በላይነህም ይህንኑ ዘፈን በመድረክ ሲያቀነቅን በፊልሙ ላይ ይታያል። በዚህ ዓመታትን በፈጀው ፊልም በ“ገመና” ድራማ ምርጥ ተዋና

ይት ተብላ የተሸለመችው መሰረት መብራቴ፣ በ“ኦቴሎ” ትያትሩ የሚታወቀው የሕግ ባለሙያው አበበ ባልቻ፣ በአምስተኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ረዳት ተዋናይ ሆኖ የተሸለመው ፈለቀ አበበ ይተውኑበታል። “ስምንቱ ሴቶች” በተሰኘው ትርጉም ትያትሯ የምትታወቀው አዜብ ወርቁም ከፈረንሳዊው ባሏ ጋር በዚህ ፊልም ተጫውታለች። “ሂሮሽማ” ከ“ሰማያዊ ፈረስ” ቀጥሎ ለሰራዊት ሁለተኛ ፊልሙ

ነው።

“የጸሀይ መውጫ ልጆች” የሚል ርዕስ የተሰጠው እና አዲስ አቀራረብ ይዞ እንደመጣ የተነገረለት ፊልም በኢትዮጵያ እየተሰራ ነው። ፊልሙ የሁለት ሰዎች ታሪክ ሲሆን መንገድ ላይ ተጀምሮ መንገድ ላይ የሚያልቅ ነው። የመንገድ ጉዞው ናዝሬት ተጀምሮ መተሃራ፣ አዋሽ፣ አፋር እና ሂርናን ያካትታል። “አባይ ወይስ ቬጋስ” በተሰኘው የቴዎድሮስ ተሾመ ፊልም ላይ በጋራ የተወኑት ሰለሞን ቦጋለ እና ግሩም ኤርሚያስ የሁለቱን ዋና ገጸ ባህሪያት ሚና በመያዝ በ“የጸሀይ መውጫ ልጆች” ላይ ይተውናሉ። ሰለሞን አሁን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እየታየ ባለው “ሰው ለሰ

ው” ድራማ ጨምሮ በበርካታ ፊልሞች ላይ የተጫወተ ወጣት ተዋናይ ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ በተሰራው “ሄርሜላ” ፊልምአድናቆትን ያገኘው ግሩም በተከታታይ በሰራቸው ሌሎች ፊልሞች በአጭር ጊዜ ዝናን ለመጎናጸፍ የበቃ ነው። በዚህ ዓመት በተካሄደው አምስተኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ “ትዝታው” እና “ይሉኝታ” በተሰኙት ሁለት ፊልሞች ላይ ባሳየው አተዋወን “የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ” ተብሎ ተሸልሟል። “የጸሀይ መውጫ ልጆች” የጻፈው ቢኒያም ወርቁ ሲሆን ሰሞኑ

ይሰማል አዘጋጅቶታል። ፊልሙ ሰማንያ በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሁለት እስከ ሶስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ለዕይታ ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ግሩም ኤርሚያስ በዚህ ፊልም ላይ ከተሳሉት ሁለት ዋና ገጸባህሪያት የአንዱን ወክሎ ይጫወታል

ፎቶ

- ትዝ

ታህ

ፊልም

ቴዎድሮስ ታደሰ በአእምሮ አለመረጋጋትና የድብታ ስሜት እየተሰቃየ ነው

ፎቶ

-ሊበን

ወርድ

ፕሬ

ሰራዊት ፍቅሬ አዲስ ፊልም ኦፊሴላዊ ፖስተር

ፎቶ

- ሰራ

ዊት

መልቲ

ሚዲ

ያ ፕ

ሮዳክሽ

ታዋቂው ኤርትራዊ ዘፋኝ ዳዊት ሽላን የሙዚቃ ዝግጅቱ

ን በካምፓላ አቀረበ። ዳዊት ዝግጅቱን ያቀረበው ኤርትራ ነጿነቷን ያገኘችበትን 20ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀው የሙዚቃ ድግስ ላይ ነው። ዝግጅቱ የቀረበው በሎጎጎ ሾው ግራውንድስ ኢግዚቢሽን አዳራሽ ውስጥ አርብ ግንቦት 28 ቀን 2003 ዓ.ም(ጁን 3 2011) ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነው። ዳዊት በብዙዎች የሙዚቃ አ

ፍቃሪዎች ዘንድ የሚታወቀው በፍቅር ዘፈኖቹ እና ባለስድስት ስትሪንግ ክራር ተጨዋችነቱ ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ ከዳዊት ሽ

ላን በተጨማሪ ሳሙኤል ተአገስ፣ ይስሐቅ ገብረ እግዚኣ፣ ገላን እድሪስ እና ሾንቂ ተሳትፈዋል።ይህንን ዝግጅት ለመድረክ እ

ንዲበቃ ያደረጉት የኤርትራ ቆንስላ ከኤርትራውያን ማሕብረሰብ (ማሕብረኮም) ጋር በመተባበር ነው። ዳዊት ሽላን

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

በፍኖት አልባ አገር በጎግ ማንጉግ ምድርእግር በጣለው ወፍ፣ በጠፋው መድረሻምንጩን በማይለይ፣ በዐልቦ መነሻእንዲሁ ተጸነስኩ፣ ከአለት ጋር ከተምኩከገደል ሣር ጋራ፣ ወዳጅነት ጀመርኩ።እንዲህ ነው የሰው ልጅ ፣ከአረም ይወለዳልበወፍ አር ተረግዞ እንደ መጋቢት ጠል ከሰማይ ይዘንባል።የዘሪው ግምት ነው ፤ሲገኝ ከጎዳናው፤ ሲወድቅ ከመሬቱሲቆራኝ ከጭንጫው፣ ሲጠጋ ከአለቱ ።

…. ቅንጣት ነ ኝ ላገሩሰበዝ ነኝ ለምድሩ። “እፉዬ ገላ” ነኝ ነፋስ የሚነዳኝ….ነፋስ የሚመራኝ…..*** ጤዛ እየላሰ፣ ዳዋ ተንተርሶ፣ከሰው ተለይቶ፣ዓለም በቃኝ ብሎ፣ ሌላ ብርሃን ሽቶ፣ በባዕት ተከቶእንደ ሚኖር መናኝ፣ ሱባዔ እንደያዘ፣ስለዓለም ሞቶ“እግዚኦ ውስተ መንሱት..” እያልኩ እኖራለሁ..የዚህ አገር መንገድ፣ የዚ’ አገር ጎዳና ወዴት ተሸሸገበስንተኛው ቀን ነው…ወደ ምድረ ራማ፣ በለቅሶ ያረገ..ስል እቆዝማለሁ….* * *

ሀገሩ እንግዳ ነው፣ ነፋስ ነው ሙዚቃውሹክሹክታ ቀረርቶው፣ ትካዜ እንጉርጎሮውነፋሱ እያፏጫል፣እያንጎራጎረ ትዝታ እያዜመአንቺ ሆየ፣ ባቲን በፉከራ መንፈስ እያጉረመረመሲጠራኝ ሰማሁት….መናኒ ሆይ ስማመናኒ ሆይ ስማ…..“ድንጋዮች አመፁ ድንጋዮች ሮጡከድንጋይ ተፈጥሮ፣ አፈንግጠው ወጡ”…..መናኒ ሆይ ስማ“ከጥንት መሠረቱሰው መሆንን ሸሽተውድንጋይ መሆን ጓጉተው…ከመጡ በኋላ….እንዴት ወደ ኋላ…..”…ይመስለኝ ነበረ ሰው ብቻ የሚመንንለካ ሀገር ሲከፋው ሀዘን ሲጫጫነውይሸሻል ከአድባሩ ይደበቃል ከሰው…..ሰውም አልነበረው? ይህ ባእድ መሬትእንክርዳድ የሞላው፣ቁጫጭ የናኘበትአሻራ እንዴት አጣ፣ ሕልሙስ የት ደረሰመንገዱ ፍኖቱ፣እረ እንዴት ፈረሰ…..?

በፈረሰው መንገድ ሳዘግም…

ግርማ ተስፋው

Page 13: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 13

ሃኒ እና ዳኒ ይባላሉ፤ የቁልምጫ ስማቸው ነው። በትምህርት ቤትም መዝገብ ላይም ኾነ ፖስፖርታቸው ላይ የተጻፈው መጠሪያቸው ግን ሐና መኩሪያ እና ዳንኤል ካሣ በሚል ነው። ሃኒ የ22 ዓመት ወጣት ስትኾን ዳኒ ደግሞ 34 ዓመቱ ነው። ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው። በመላው አፍሪካ በርካቶች ወጣቶች በሚከታተሉት ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያን የወከሉ ናቸው። ከተጀመረ አንድ ወር ያለፈው ይህ የቴሌቭዥ

ን ፕሮግራም ከ14 አገራት የመጡ 26 ወጣቶችን በአንድ ግቢ ያሰባሰበ ነው። ከዚህ ቀደም ፈጽሞ የማይተዋወቁት እነዚህ ወጣቶች ለ91 ቀናት በአንድ ግቢ ተቆልፎባቸው እያንዳንዷን ደቂቃ እና ሰዓት በጋራ ለማሳለፍ የተስማሙ ናቸው። በሦስት ወር ቆይታቸው ከውጭው ዓለም ጋራ ምንም ዐይነት ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድላቸውም። ሞባይል፣ ጋዜጣ፣ ቴሌቭዥንም ኾነ ሬድዮ በአጠገባቸው የለም። በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ደንብ መሠረት ብቻቸውን እንዲኾኑ የተዘጋባቸው ናቸው። ብቻቸውን ቢኾኑም ሚሊዮኖች ግን አብረዋቸ

ው አሉ። በሚኖሩበት ቤት የተገጠገጡት 54 ካሜራዎች እና 120 ማይክራፎኖች የሚሉ፣ የሚያደርጓትን ሳምንቱን ሙሉ፣ 24 ሰዓት ያለማቋረጥ ለሚልዮኖች ያስተላልፋሉ። ይህ ቢግ ብራዘር አፍሪካ ነው። እውነተኛ ትዕይንቶች እና ድርጊቶች በቀጥታ የሚተላለፉበት የቴሌቭዥን ፕሮግራም። ከቢግ ብራዘር አፍሪካ ምንም የሚደበቅ ነገር የ

ለም። ከከንፈር ለከንፈር ግጥሚያ እስከ ሻወር ቤት የራቁት ቆይታ ድረስ ሁሉም በቢግ ብራዘር ካሜራ ዐይን ውስጥ ናቸው። ማን አንድ ብርጭቆ መጠጥ ጠጥቶ ከ“ጨዋታ ውጭ” እንደሚኾን በቀጥታ መኮምኮም ይቻላል። እዚህ ምስጢር የለም። ናሚቢያን ወክላ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ የምትካፈለው ብሬናዲና ድንግል መኾኗን ስትናገር ሚልዮኖች እየሰሟት ነው። በርግጥ የአምስተኛ ዓመት የሕግ ተማሪዋ ኢትዮጵያዊቷ ሃኒም ድንግል መኾኗ ቀደም ሲል ታውቋል። ታንዛኒያዊቷ ሎተስ ደቡብ አፍሪካዊውን ሉክሌይ በጥፊ ስትማታም በርካቶች የአገሯ ዜጎች በድንጋጤ ተመልክተዋል። በፕሮግራሙ ደንብ መሠረት አንድ ተሳታፊ ሐይል የተቀላቀለበት ድርጊት በሌላኛው ላይ ከፈጸመ ከውድድሩ በቀጥታ ይባረራል።

“ታላቁ ወንድም” በአፍሪካ እንዲህ ዐይነት ሽፍንፍን የሌሉባቸው ትዕይን

ቶች በ42 አገራት ለየአገራቱ በሚስማማ መልኩ እየተዘጋጀ ለተመልካች መተላለፍ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። “ቢግ ብራዘር” ወደ አፍሪካ የመጣው ከስምንት ዓመት በፊት ነበር። ፕሮግራሙን በተለያዩ አገራት የሚሠራው “ኤንዴሞል” የተሰኘው ድርጅት መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ላይ አድርጎ ወጣት አፍሪካውያንን ማወዳደር ጀመረ። ውድድሩን ለሚያሸንፉም ዳጎስ ያለ ገንዘብ ይበረከት ጀመር። ተሳታፊነቱን እና አሸናፊነቱን ተከትሎ የሚመጣው ዝናም ሌላው የፕሮግራሙ ማማለያ ነበር። ፕሮግራሙ ለሦስት ተከታታይ ሲዝኖች ሲተላ

ለፍ ከ12 አገራት የመጡ 12 ተሳታፊዎችን ብቻ ነ

በር የሚያካትተው። እ.ኤ.አ በ2009 የነበረው አራተኛው ሲዝን የአገራቱን ቁጥር በሁለት ጨምሮ የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 25 አሳደገ። ኢትዮጵያ ወደ ቢግ ብራዘር አፍሪካ የተቀላቀለችው በዚህኛው ሲዝን ነበር። የኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው ደግሞ ያዕቆብ ነበር። ያዕቆብ የቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ ባለቤት የኾኑት የአቶ አቢሴሎም ይህደጎ ልጅ ነው። ኢትዮጵያዊ ተወካይ የሌለበት ባለፈው ዓመት

ሐምሌ የተካሄደው አምስተኛው ሲዝን ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሲዝኖች የተሳተፉ 14 ምርጦች የተሳተፉበት ነበር። የያዕቆብ ፈር ቀዳጅ ተሳትፎ ሃኒን እና ዳኒን በስድስተኛው እና “ቢግ ብራዘር” አምፕሊፋይድ እንዲሳተፉ አነቃቅቷቸዋል። ለዚህም ነው እስከዛሬ ከነበሩ የቢግ ብራዘር ተሳታፊዎች ማንን ታደንቃላችሁ ሲባሉ ሁለቱም የያዕቆብን ስም የሚጠሩት።

ሁለቱ ወጣቶች እነማን ናቸው?በአዲስ አበባ የተወለደችው ሃኒ እንደብዙዎቹ

እንስት ኢትዮጵያውያን ራሷን ለመግለጽ የምትቸገር ዐይነት አይደለችም። “ጨዋታ ወዳድ፣ አስቂኝ እና ተወዳጅ” እንደኾነች ትናገራለች። ለጓደኛነት የምትመች እና ለአዳዲስ ፈተናዎች ምንጊዜም ራሷን አዘጋጅታ የምትጠብቅ መኾኗንም አትደብቅም። መዝፈን የምትወደው ሃኒ ለሬጌ ሙዚቃ ጥልቅ ፍቅር አላት። የ“ፉጂስ” የሙዚቃ ቡድን አባል የነበሩትን እና በየግላቸው የተዋጣላቸው ዘፋኝ ለመኾን የበቁት ላውረን ሂል እና ዋይክሌፍ ዣን፣ የቦብ ማርሌይን ልጅ ዳሜይን ከምትወዳቸው ዘፋኞች ይመደባሉ። ከፊልም ኮሜዲ፣ ከመጽሐፍ ደግሞ የዳን ብራውንን ድርሰቶች ትመርጣለች። አሁን ያለችበት ወቅት ስለራሷ ይበልጥ ማወቅ የምትፈልግበት እንደኾነ የምትናገረው ሃኒ በዚህም ምክንያት በ“ቢግ ብራዘር” መወዳደር እንደፈለገች ታስረዳለች። የግሉን ሥራ እንደሚሠራ የሚናገረው ዳኒ እን

ደ ሃኒ ሁሉ አላገባም። “ጀብድ ወዳድ፣ ተጨዋች፣ ተግባቢ፣ የሁሉ ወዳጅ እና የሚመኩበት ዐይነት” ሰው እንደኾነ ይናገራል። ኢ-ልቦለድ ሥራዎችን ማንበብ የሚያስደስተው ዳኒ ከዜና እስ

ከ መዝናኛ፣ ከስፖርት እስከ እውነተኛ ትዕይንቶች የሚስተናገዱበት “ሾው” ድረስ ያሉ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን መከታተል ያዘወትራል። በድርጊት የተሞሉ እና ጅብድ ቀመስ ፊልሞችን መመልከት ይወዳል። ባራክ ኦባማ፣ ኔልሰን ማንዴላ እና ዲያጎ ማራዶና የሚያደንቃቸው ዝነኛ ሰዎች ናቸው። የ“ቢግ ብራዘር” ቀረጻ የሚከናወንባት ደቡብ

አፍሪካ ለዳኒ እንግዳ አይደለችም። ከዚህ ቀደም ለዓመታት በአገሪቱ ኖሯል። ወደ ደቡብ አፍሪካ ከማቅናቱ በፊት በናይሮቢ ኬንያ ለጥቂት ጊዜያት መቆየቱን እና ዝቅተኛ በሚባለው የሕይወት ጎዳና ሳይቀር ያለፈ እንደነበር የሚናገሩ አሉ። በዚህ ፈታኝ ሕይወት ውስጥ ያለፈው ዳኒ ለ“ቢግ ብራዘር” መድረክ በመመረጡ መገረሙን ተናግሯል። ውድድሩን ካሸነፈም በእውቅ ዲዛይነሮች የተሰፉ ልብሶች የሚሸጡበት ሱቅ በአዲስ አበባ ላይ የመክፈት የሁልጊዜም ህልሙን እውን የማደርግ ሐሳብ አለው።

አያያዛቸው እንዴት ነው?በ“ቢግ ብራዘር” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ደንብ

መሠረት በተሳታፊዎች በራሳቸው በሚሰጥ ድምፅ ከመካከላቸው የተወሰኑት ከውድድሩ እንዲወጡ በዕጩነት ያቀርቧቸዋል። በእነዚህ እንዲወጡ በተፈረደባቸው ተሳታፊዎች ላይ ድምፅ እንዲሰጡ ተመልካቾች ይጋበዛሉ። ተመልካቾች በከፍተኛ ድምፅ ይባረር ያሉት ከውድድሩ የመሰናበት ዕጣ ይገጥመዋል። ሚያዝያ 23 ቀን 2003 ዓ.ም የተጀመረው የቴሌቭዥን ፕሮግራም በሳምንቱ ስድስት ዕጩ ተባራሪዎችን አቀረበ። ኢትዮጵያዊው ዳኒ አንዱ ነበር። ድምፅ ተሰጠ። ፍርዱ የናሚቢያው ጆሲ ላይ ደረሰ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ደግሞ ሃኒ ዕጣው ደረሳ

ት። በተባራሪ ዝርዝሮች ውስጥ ብትገባም በወቅቱ የተሳታፊዎቹ ቤት አለቃ በነበረው ሰው ከዝርዝሩ ውጭ ተደርጓል። በዙር የሚደርሰው ይኼ የአለቃነት ሹመት ዕጩ ተባራሪዎችን የማዳን ሥልጣን ያጎናጽፋል። እስከባለፈው እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ከ25ቱ ተሳታፊዎች መካከል ስድስቱ ለቀጣይ ሁለት ወራት

ከዓለም ተገልሎ ከሚቆየው ቤት ተባረዋል። ሃኒ እና ዳኒን ጨምሮ ዐሥራ ዘጠኝ ተሳታፊዎች ተፋጠዋል። ሃኒም ኾነች ዳኒ ለጊዜው ከመባረር ተርፈዋ

ል። የ“ቢግ ብራዘር” የየዕለት ውሎዎችን ሥራዬ ብለው በሚዘግቡ ድረ ገጾችም ኾነ ጋዜጦች ያላቸው ዝና ያን ያህል መኾኑ ግን አደጋውን ቅርብ ያደርገዋል። ከእነዚህ ድረ ገጾች አንዱ የኾነው ዩጋንዳ ኦንላይን ከአንባቢዎቼ ሰበሰበኩት ባለው ነጥብ አሰጣጥ መሠረት አንዳንድ ተሳታፊዎች ምንም ዐይነት ነጥብ ማስዝገብ እንዳቃታቸው አንዳንዶቹ ደግሞ አንድ ወይም ሁለት ፐርሰንት የኾነ ነጥብ ብቻ ማግኘታቸውን ጠቁሟል። ምንም ነጥብ ካለስመዘገቡት መካከል አንዱ ዳኒ ሲኾን አንድ ፐርሰንት ካስመዘገቡት መካከል ደግሞ ሃኒ ተቀምጣለች። አዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊው የእንግ

ሊዘኛ ጋዜጣ “ፎርቹን” የሃኒን እናት ስለ ልጃቸው ምን እንደሚሰማቸው ጠይቋቸው ነበር። የሃኒ እናት ወይዘሮ በላይነሽ አባተ ይባላሉ። ከልጆቻቸው ሁሉ የመጨረሻዋ የኾነችውን የሃኒን ውሎ በየዕለቱ በዲ.ኤስ.ቲ.ቪ ቻናል 198 ይከታተላሉ። ወይዘሮ በላይነሽ ፕሮግራሙ የተጀመረ ዕለት በልጃቸው መሳተፍ መደሰታቸውን ቢናገሩም በመመረቂያ ዓመቷ ላይ የምትገኘው ሃኒ ትምህርቷን ጨርሳ ማየቱን ይበልጥ እንደሚፈልጉ ለ“ፎርቹን” በስተኋላ ገልጸዋል። “እርሷ መደሰት እንደምትፈልግ ነው የነገረች

ኝ። ለጓደኞቼም ኾነ ለዘመዶቼ አሊያም ለጎረቤቶቼ እየተሳተፈች እንደኾነ አልተናገርኩም” ይላሉ የልጃቸውን ምርጫ ያከበሩት ነገር ግን ተሳትፎዋን ምስጢር ያደረጉት እናት። ፕሮግራሙን ሲከታተሉ ምን እንደሚሰማቸውም ለጋዜጣው ሳይደብቁ ተናግረዋል። “የሚነጋገሩበትን ቋንቋ አላውቀውም። የሚተረጉምልኝም የለም። ነገር ግን ሌሎቹ ሴቶች በተደጋጋሚ ሃና እያሉ ሲያወሩ እሰማቸዋለሁ። እርሷን እያሙ እንደኾነ ስለምረዳ ለልጄ እሰጋላታለሁ። ምክንያቱም አግኝቼ ምክር ልሰጣት አልችልምና። ምን እንደሚሏት ስታውቅ እንድትጎዳብኝ አልፈልግም” ይላሉ።

ጥበብሰሞነኛ ፊልሞች

ሰሞነኛ ፊልሞች

ተዋንያን፦ ግሩም ኤርሚያስ፣ ሃረገወይን ተሾመ፣ ቴዎድሮስ ስዩም፣ ዋሲሁን በላይ እና ሌሎችም ዳይሬክተር፦ አንተነህ ግርማ የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ

አማላዩ

ፔንዱለምተዋንያን፦ እጸህይወት አበበ፣ አማኑኤል ይልማ፣ ረቂቅ ተሾመ፣ መስፍን ኃይለእየሱስ፣ ሚካኤል ሚሊዮን እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ሄኖክ አየለየፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ

ግሩም የተሰኘ ወጣት የፋሽን ዲዛይነር በአንዲት ሞዴል ፍቅር ይወድቃል።። ያፈቀራት ልጅ ለማግኘት ወደ መኖሪያ ህንጻዋ ሲሄድ ከእርሷ ስመ ሞክሼ ጋር ይተዋወቃል። በሙያዋ አርክቴክት የሆነችው ይህቺ እንስት ደግሞ ቀስ በቀስ ግሩምን ትወደዋለች። ፊልሙ እንዲህ በሶስትዮሽ ስለተሰናሰለው የፍቅር ሁኔታ የሚተርክ ይሆናል። ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ አማኑኤል ይልማ በዚህ ፊልም ላይ ግሩምን ሆኖ ይጫወታል። በወንዶች ጉዳይ ፊልማቸው ዕውቅና ያተረፉት ረቂቅ፣ መስፍን እና ሚካኤል በዚህ ፊልም ላይ ሳቅ ለማጫር ተጣምረዋል።

ኤፍ.ቢ.አይ

ኤፍ.ቢ.አይ የሚባል የግል ድርጅት አለ። ኤፍሬም (ነጻነት ወርቅነህ) የድርጅቱ ቁልፍ ሰው ነው። የማይሰራው የ “ቢዝነስ” ዓይነት የለም። የሞባይል ካርድ ከመሸጥ ጀምሮ የጠፋ ውሻ እስከ ከማፈላለግ ድረስ ይሰራል። በ“ቢዝነሱ” እንዲጠቀሙ ሴቶችን “ያበረታታል”። አግልግሎት እየሰጠ ሞባይል ቁጥራቸውን መቀበሉን አይረሳም። እንዲህ አንዲህ እያለ በርካታ ሴቶችን ይተዋወቃል። ከአንዲት እንስት ጋር የነበረው ትውውቅ ግን ጣጣ ያመጣበታል። አፍሬም ከጣጣው እየሸሸ የእንስቱን ጓደኝነት የሚያጠብቅበት አካሄድ ካልተለመደው የ“ቢዝነሱ” አሰራር ጋር ተመልካችን ለሳቅ ይጋብዛሉ።

ተዋንያን፦ ነጻነት ወርቅነህ፣ ቤተልሄም ደምሴ፣ ህይወት አበበ፣ ግርማ ታደሰ እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ነጻነት ወርቅነህየፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ

ይህ ፊልም ሳምሶን ስለሚባል እና ሴቶችን የማማለል ብቃቱ ከፍተኛ እንደሆነ ስለሚነገረለት ወጣት የሚተረክ ነው። ሳምሶን ከኢትዮጵያ ውጭ በነበረበት ወቅት የተመኛትን ሴት እንደልቡ የሚያገኝ ነበር። ወደ ሀገር ቤት ሲመለስም ተመሳሳይ አቀባበል ነበር የጠበቀው። የሀገሩ ሴቶች በቀላሉ የማይበገሩ መሆናቸውን ከጓደኛው ቢያደምጥም መቀበል አልፈለገም። በእርግጥም ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ያሰበውን አሳካ። በራሱ ድርጅት ውስጥ በህግ ባለሙያነት ተቀጥራ ከምትሰራው ማህደር ዘንድ ሲደርስ ግን እንደለመደው አልሆነም። የጓደኞቹን ተረብ መቋቋም ያቃተው ሳምሶን ማህደርን ሊያንበረክክ በአምስት ሺህ ብር ተወራረደ። ከዚያስ…? መልሱን ከፊልሙ ለማግኘት በቪሲዲ እና በዲቪዲ እስኪወጣ መጠበቅ ነው።

በህግ ወጥ መንገድ እየተባዙ ገበያ ላይ በሚውሉ ዘፈኖች ምክንያት መቀዛቀዝ ለሚታይበት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ማነቃቂያ የሚሆኑ ሁለት አልበሞች ከሰሞኑ ገበያ ላይ ውለዋል። የሁለቱም አልበሞች ባለቤቶች ወጣቶች ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በሰሯቸው ነጠላ ዜማዎች ይታወቃ

ሉ። ድምጻውያኖቹ “ነይ ማታ ማታ” እና “ነይ ሳሚኛ” በተሰኙት ዘፈኖቹ ይበልጥ የሚታወቀው አቤል ሙሉጌታ እና “የኔ ድሃ” እና “ዽሬ ድሬ” በተባሉት ነጠላ ዜማዎቹ ህዝብ ጆሮ የገባው ሚኪያስ ቸርነት ናቸው። አቤል ሰሞኑን ያወጣው አልበም “ተገርሜ” የሚል ስያሜ የሰጠው ሲሆን አስራ ሁለት አዳዲስ ዘፈኖችን

ይዟል። ከአንድ ዘፈኑ በስተቀር የሁሉኑም ዘፈኖች ግጥም እና ዜማ የደረሰው ራሱ ነው። የሙዚቃ ቅንብሩን ግን በአራት ሰዎች አሰርቷል። አስቻለው ዲሮ እና ሚካኤል ኃይሉ አስር ዘፈኖች ሲያቀናብሩ ታዋቂው ኤልያስ መልካ አንድ ኪሩቤል ተስፋዬ ደግሞ ቀሪውን ሰርተውታል። የሙዚቃ ቅንብሩ እንደ አብዛኞቹ የዘመኑ ዘፈኖች በኪቦርድ ተጀምሮ በኪቦርድ መጨረሱን ያልወደደ የመሰለው አቤል ሊድ ጊታር፣ ሳክስ፣ ማሲንቆ ተጨዋቾችን በአልበሙ አካትቷል። “ተገርሜ” ለአቤል ሁለተኛ አልበሙ ነው። የአልበሙን መጠሪያ “ሰላም አላት” ሲል የሰየመው ሚኪያስ እንደ አቤል ሁሉ አስራ ሁለት ዘፈኖችን ይዞ

መጥቷል። ግሩም ታምራት፣ መላኩ ጥላሁን፣ ኤሊያስ አሰፋ እና ድምጻዊ ቴዎድሮስ ሞሲሳ በግጥም ደራሲነት ተሳትፈዋል። የሙዚቃ ቅንብር እና ሚኪሲንጉን የወሰደው መሀመድ ኑር ሁሴን ነው። በቮካል ሪከርድስ አማካኝነት ለገበያ የዋለው ይህ አልበም ሚኪያስን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቁትን “የኔ ድሃ” እና “ዽሬ ድሬ”ን አካትቷል። አልበሙ በፍቅር ዘፈኖች የተሞላ ነው።

ሁለት ወጣት ድምጻውያን አዲስ አልበሞቻቸውን አወጡ

ሁለቱ ኢትዮጵያውያን በ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ”በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

አቤል ሙሉጌታ ሚኪያስ ቸርነት

ሃኒም ኾነች ዳኒ ለጊዜው ከመባረር ቢተርፉም የ“ቢግ ብራዘር” የየዕለት ውሎዎችን ሥራዬ ብለው በሚዘግቡ ድረ ገጾችም ኾነ ጋዜጦች ያላቸው ዝና ያን ያህል መኾኑ ግን አደጋውን ቅርብ ያደርገዋል

ፎቶ

- ቢግ

ብራ

ዘር አ

ፍሪካ

ፎቶ

- ላይ

ፍ መ

ጽሔ

ፎቶ

- ንግስ

ት መ

ጽሔ

Page 14: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)14 ሀበሻዊ ቃና

ትረካ

እሙድሬ “Number One” በፍቅር ድብን ብዬ የ

ሰከርኩባት መንደር ብቻ አይደለችም፤ የልጅነት ቡረቃዬን በመንደሩ ሰዎች አጀብ እና ልዩ ቤተሰባዊ ፍቅር ያጣጠምኩባት ሰፈሬ ነች፡፡ እንደ እኔ ደስተኛ ማን ነበር?! ሕይወት እንዴት እንደምትጣፍጥ ለማሳየት ከኔ በላይ ምስክር ያለ አይመስለኝም፡፡ ባለ ክንፍ ሕጻን ነበርኩ፤ አዎ የምበር እንጂ የምራመድ አልመስልም ነበር፡፡ የረገጥኩት ሁሉ ያነጥረኝ ይመስል ከፍልቅልቅ ፈገግታ ጋር ጉዞዬ ከአንዱ እቅፍ ወደ ሌላው እቅፍ የታጀበ ነበር፡፡

Y Y Y ትንሿ “እሙ” የሠፈሩ ፈርጥ የኾነች ያህል እ

ንዲህ እንደፈነጠዘች፣ ከአንዱ እቅፍ ወደ አንዱ እቅፍ እንደተሸጋገረች 16ኛውን የልደት ሻማ “እፍ” አለች፡፡ የፍቅር ዘመን እንዴት አጭር ነው ‘ባካችሁ!የ17ኛው ጉዞ ታዲያ እንዲህ በብዙ መታቀፍን፣

በብዙ ጉያዎች መሸጎጥን ያስከተለ እንዳይመስላችሁ፡፡ የያኔው የ“እሙ” ዘመን’ኮ የልጅነት ወዟን እና ጠረኗን ለማየት እና ለመካፈል በሚሹ ቤተሰባዊ ፍቅር ባነወዛቸው ወዳጆች የደመቀ ነበር፡፡ ብዙሃን ለአንዲት የሰፈሩ ትንሽ “ጣዖት” ያላቸው ፍቅር በሉት፡፡ 17ኛው የእመቤት ዘመን ግን አንድ ትንፋሽን የሚናፍቅ ነበር፡፡ በአንድ ትከሻ ላይ መንተራስን፤ መሳ’ምን ብቻ ሳይኾን መሳምን የሚሻ ነበር፡፡

Y Y Y

እሙድንገት እድግ አልኩኛ! እናም በፍቅር ክንፍ አ

ልኩ-ከአቤልዬ ጋር! ከብዙ እቅፍ ወደ አንድ እቅፍ-ግን የሚነዝር እቅፍ፡፡ እንዴት ያለ የሚጣፍጥ ፍቅር ነበር?! አሁንም በፍቅር ክንፍ አወጣሁ፡፡ እናም እንደ ትንሿ “እሙ” ክንፍ አልኩ፡፡ የድሬዋ ትንሽ መንደር “Number One” ጥብብ አለችኝ፡፡ በወቅቱ አቤል በአሥር አመት የሚበልጠኝ መልከ መልካም ነበር፡፡ በቃ “የእኔ ጌታ” ብዬ ስጠራው ብውል የማልጠግበው ለግላጋ ወጣት፡፡ አቤል ኤርትራዊ ነው፡፡ ለወሬው ነው እንጂ የ

ዜግነት ጉዳዩን ማንሳቴ፤ “ማፍቀርም መፈቅርም የሚችል ሰው” የሚለውን ስያሜ ብሰጠው በቀለለኝ ነበር፡፡ በርግጥ ለእኔ ከሁሉም በላይ አቤል ብቻ መኾኑ በቂ ነበር፡፡ ሲበዛ አፈቀረኝ፤ ትንሿ ልቤ የዘወትር ሥራዋን ታቆም ይመስል ትርታዋን በእጥፍ እንደጨመረች የእኔንም የፍቅር ብርታት ገለጸችልኝ፡፡ አዬ የልጅነት ነገር፣ ዓለም ሁሉ ቢደመር አንድ አቤልን የሚሠራ አይመስለኝም ነበር፡፡ አንዳንዴ የፍቅር ድራማ በቴሌቪዠኑ መስኮት ስመለከት የኾነ ነገር የጎደለው ይመስለኛል፡፡ አዎ አቤል! እንዴ ከምሬ’ኮ ነው፡፡ አቤል የሌለበት የፍቅር ታሪክ የባዶ ገረወይና ጩኸት ይመስለኛል፡፡ አቤል ለእኔ ሙሉ ነበር፡፡ ግን ደግሞ አልጠግበውም፡፡ ፍቅር ስስት ነው ለካ! በሙሉ መዳፍ የሚፈልጉ

ትን አስገብቶም ያለመርካት፡፡ በእጁ ያለውን መጨዋቻ ላለማጣት ከሌላ ሰው እጅ ያለውን እንደሚሻ ሕጻን መኾን፡፡ አቤልን አቅፌ በሙሉ እጄ የያዝኩት ያህል አይሰማኝም ነበር፡፡ ከደረቱ

ተለጥፌም ጥሎኝ የሚበር ያህል ጥፍሬ እንደ ምስማር አካሉን ዘልቀው ሊገቡ ምንም አይቀራቸው ነበር፡፡ የትንፋሹ ግለት ነፍሴን እንዳሞቃት ቀኑ መሽቶ ይነጋ ነበር፡፡ ሁሌ የሚቆጨን ነገር “አፈቅርሃለሁ” የሚለው ቃል ከእሱ የአፍታ እቅፍ የማገኘውን እርካታ ያህል እንኳ ሚዛን ላይ ሳስቀምጠው የልቤን አለማድረሱ ነው፡፡

ጦርነት እና ፍቅርቀደም ሲል አቤል ኤርትራዊ ነው አይደል ያልኩ

ት!? ይህ ለእኔ ምን ስሜት ነበረው? ምንም፡፡ የእኔ አይደል ከየትም ቢኾን፡፡ ይህ ስሜት ግን ከእኔ ምስኪኗ ግለሰብ አልፎ ለሌሎች ምንም አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ ለመንግስታት፡፡ በተለይ. . . በተለይ . . . በተለይ. . . ደግሞ ለሻቢያ እና ለወያኔ፡፡ የሁለቱ አገር ጉዳይ እንግዲህ ትልቁን ጦርነት ወለ

ደ፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ሕይወት ቀጥፎ አለፈ፡፡ ዛሬም ድረስ የማይሽር ጠባሳ ደግሞ በእኔ የፍቅር ሕይወት ላይ ጥሎ አለፈ፡፡ “የአይነ ውሃቸው ያላማረ” ሁሉ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ማማር ብቻ ሳይኾን የፍቅር ጨረር የሚያንጸባርቁ መኾናቸውን ሚልዮን ጊዜ የምመሰክርለት አቤልም “አይኑ አላማራቸውም” መሠል ከአገር እንዲወጣ ተገደደ፡፡ ቀድሞ የመንግስትን አዝማሚያ የተገነዘቡት ዘመዶቹ በሞያሌ በኩል የኬንያን ድንበር እንዲሻገር አደረጉ፡፡ ናይሮቢ በሠላም መድረሱን መስማቴ በጎ ቢኾንም

ለእኔ ግን ዓለም ጨለመች፡፡ የፍቅር ከዋክብት ረግፈው ሰማዩ ጥላቻን የሚያንጸባርቅ መሰለኝ፡፡ ዘወትር “ጌታዬ” የምለውን ፍቅሬን ከእኔ ነጠቁ፡፡ ሁሉን ነገር ጠላሁ፡፡ ያለ ፍቅር መኖር ማለት ያለውን ባዶ ስሜት ተከናነብኩት፡፡ መብላት መጠጣት ያለፍቅር ሲኾኑ ምን ያህል አስጨናቂ እንደኾኑ ያንጊዜ አየሁ፡፡ አምስት ዓመታት ያህል “በልምጣ አትምጪ” ትግ

ል ቆየሁ፡፡ አቤል ከእኔ ቢርቅም ለእኔ ያለውን ፍቅር ዘወትር ሳይገልጽ አድሮ አያውቅም ነበር፡፡ ዘመዶቹ ድጎማ ብለው ከሚልኩለትም እየቆነጠረ እኔን ለማስደሰት መላኩ አልቀረም ነበር፡፡ ነገር ግን “ወደ አንተ መጥቼ አብረን እንኑር” የሚለው ጥያቄ ዘወትር አይቀበለውም ነበር፡፡ “ለአንቺ አይመችም፣ ያለ ሥራ መቀመጥ መቆመጥ ነው” ዓይነት ምክንያት ነበር የሚሰጠኝ፡፡ ለእኔ ግን ከአቤል ጋር ኾኜ ውሃ እ

ና መብል መቼ ይታየኝና! እናም ሦስት ዓመታት ያህል “አብረን እንኑር” ከሚለው ኃሳቤ ጋር ከታገልኩ በኋላ ጥያቄውን ችላ ብዬ በልቤ ውስጥ ያለውን ፍቅር ብቻ ማብሰልሰል ጀመርኩ፡፡ አቤልም ዘወትር መደወሉን አላቆመም፡፡ ይህ ለእኔ ትልቅ ደስታ ነበር፡፡ ርቀቱን የሚያቀርብልኝ በየምሽቱ የምሰማው የፍቅር ትረካው ነበር፡፡ ያዜምልኛል ማለት ሳይቀል አይቀርም፡፡ ፍቅር ለካ እያደር እየጨመረ ይሄዳ

ል! በቃ “ውድድድ” አደረኩት፡፡ እያደር ፍቅርቅርቅር . . . እነሱ በጦርነት እኛን ለያዩ ደግሞም አገር አፈረሱ፣ እኛ ደግሞ በቃላት እያደር ፍቅር እንገነባለን፡፡

በናይሮቢ ሰማይ ሥርከተለያየን አምስተኛው ዓመት አካባቢ መቼም አ

ስበውኝ የማያውቁት የአቤል ዘመዶች አልፎ አልፎ መደወል ጀመሩ፡፡ በተለይ ካናዳ የምትገኘው ታላቅ እህቱ አልፎ አልፎ ገንዘብ ትልክልኝ ጀመር፡፡ስትደውልም አቤል ጋር መሄዴን እንደምትሻ ሳትገልፅልኝ አታልፍም ነበር፡፡ በካናዳ “ፕሮሰስ” ውስጥ እኔን አግብቶ የሚሄድበት ኹኔታ እንደሚኖርም ትገልጽልኝ ያዘች፡፡ ‹‹አቤል ስለእኔ እየደጋገመ ነግሯታል ማለት ነው›› አልኩ፡፡ ‹‹አቤል ናፍቆቴን መሸከም አቅቶታል ማለት ነው›› ብየ ትራስ አቅፌ አነባሁ፡፡ የኔው ሳያንስ እሱም በሰው ሃገር በፍቅሬ እየተሰቃየ መሆኑን ሳስብ ክንፍ አውጥቶ መብረር አማረኝ፡፡ ዘወትር የድኻዋ እናቴ ጉዳይ ቢያሳስበኝም ከካናዳው ጉዞው ይልቅ አቤልን ማግኜቴ ትልቁ ድል ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ‹‹አቤል የኔ ተስፋ ሩቅ ሀገር ያለኸውበርሬ ልምጣና ትንፋሽህን ልማገው›› እያልኩ አን

ጎራጎርኩ፡፡‹‹ከቀይባህር ማዶ ያገኘሁህ ቆንጆውሰድና አኑረኝ በትንሿ ጎጆ›› ብየ ምኞቴን በዜማ

ለወፏ ተናገርኩ፡፡

እንጉርጉሮየን የሰማች ወፍ ሄዳ ነገረችው መሰል አቤልም እኔን ለመቀበል ዝግጁ መኾኑን ነገረኝ፡፡በ’ቅፉ የገባሁ ያክል በጣም ተደሰትኩ፡፡ በቃ አዲስ ሕይወት አዲስ ፍቅር በናይሮቢ ሰማይ ሥር፡፡ ዘወትር ታዛዡ ኾኜ ለማገልገል የምሻውን ፍቅሬን ማግኘቴ ልዩ ደስታ ነበር ያጎናጸፈኝ፡፡ ወዳጅ ዘመድ በወጉ ስለመሰናበቴ የማስታውሰው ነገር የለም፡፡ ማቄን ጨርቄን ሳልል ከነፍኩ- ወደ ናይሮቢ፡፡ አቤ

ልን ለማየትና በፍቅር እንደገና ለመክነፍ፡፡ ጆሞኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ደረ

ስኩ፡፡ ከአውሮፕላኑ እየወጣሁ አቤል እንዴት እየጠበቀኝ እንደሆን መሳል ጀመርኩ፡፡ በእቅፉ የያዘው አበባ፤ አበባውን ያቀፈባቸው ለዓመታት የናፈቁኝ ክንዶቹ፤ በሰው መካከል ሁሉ ነግሶ የሚታየኝ ግርማ ሞገሱ፤ ሁሉም ከደቂቃዎች በኋላ የእኔ መሆናቸውን እያሰብኩ ዳግም ፈነደቅሁ፡፡ ከአውሮፕላን

ማረፊያው ወጥቼ አይኖቼ አቤል ላይ እንዲያርፉ በግራና በቀኝ ላክኋቸው፡፡ አይኖቼ በሁሉም አቅጣጫ ተንከራተቱ፡፡ እንዳሰብኩት ግን አቤል ላይ ማረፍ አልቻሉም፡፡ አቤል ሊቀበለኝ አልመጣም፡፡ ጓደኞቹን ልኮ ኖሮ

እኔነቴን አረጋግጠው ጓዜን ተቀበሉኝ፡፡ ለምን እርሱ እንዳልተገኘ መጠየቄ አልቀረም፡፡ “ትንሽ አመም አድርጎት ነው” የሚል ምላሽ ብቻ አገኘሁ፡፡ ቅር አላለኝም፡፡ እንዲያውም ምን ኾኖ ይኾን ስል ስጋት ገባኝ፡፡ ጉጉቴ አሁንም ጨምሯል፡፡ ልክ እንደተገናኘን በመንፈስ ሀይል ከደዌው እንደተፈወሰው ሰው ከአልጋው ዘሎ ላየ ላይ ሲጠመጠም፤ ለህመሙ መድሃኒት ስሆን፤ እኔም ለዓመታት ከቆየሁበት የናፍቆት እስርቤት ስፈታ እያለምኩ ጉዞየም የልብ ትርታየም ፈጠነ፡፡ ናይሮቢ የጠበቅኳትን ያህል በትላልቅ ሕንዎችና

ውብ ሠፈሮች አልተቀበለችኝም፡፡ ይልቁንም አቧራ መንገዶች እና ወከባ የበዛባቸው ተራ መንደሮች፡፡ ቀጥታ ብዙ ሐበሻ ወደሚኖርበት “ቻይሮድ” ነበር ያመራነው፡፡ የማየው ነገር ሁሉ ባይማርከኝም፣ ጉጉቴ አቤልን በማየት ላይ ነበርና ሁሉን ዋጥ አድርጌ በዝምታ እርሱ ካለበት “ቻይሮድ” ደረስን፡፡ አቤል አንድ ክፍል ውስጥ አልጋ ላይ ጥቅልል ብሎ

ተኝቶ አገኘሁት፡፡ ደነገጥሁ፡፡የኔው አቤል እንዲህ አይደለም፡፡ የኔው አቤል ከአልጋ ይልቅ ሳር የሞላበት ሜዳ እጅጉን ይመቸዋል፡፡ እኔ ደግሞ ከለምለሙ ሜዳ ይልቅ ሰፊው ደረቱ ላይ ፈልሸሽ ብሎ መተኛት እስከ ዓለም ፍጻሜ ደረስ ለእኔ ተብሎ የተቀመጠውን ደስታ ሁሉ በአንድ ጊዜ ይሰጠኛል፡፡ ለእኔ የአቤል ደረት ከስፕሪንግ ፍራሽ ምቾት ጋር ሊነጻጸር ቀርቶ ከእግሩ ጫፍም አይደርስም፡፡ አሁን ፊት ለፊት የማየው ደረት ግን ይህ አይደለም፡፡ በእንባ በተጋረደ ዓይኔ እያሁት በትዝታ የኋልዮሽ

ተጓዝኩ፡፡ ያኔ ዘመኔን እንዳዲስ በጀመርኩበት በፍቅራችን ዘመን “እሙ” ብሎ ሲጠራኝ “ወየ ጌታየ” ብየ ዞር ስል የናፍቆት ህመም በሚፈውስው ፈገግታው ውስጥ የበረዶ ያህል ነጽተው የሚያጓጉኝ ጥርሶች በህሊናየ ተመላለሱ፡፡ አሁን እነርሱ የሉም፡፡ ሙ

ቀቱ በዶሮ እቅፍ እንዳለ እንቁላል፣ የሚመቸው ትንፋሹ የሚጣደፍ መንገደኛ መስሏል፡፡ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋውን ተደግፌ ተንሰቀሰቅሁ፡፡እጅጉን አዘንኩ፡፡ የእንባየ ዘለላዎች ሀዘኔን ብቻ ሳይሆን የመጣሁበትን ምክንያትም አውጥተው ነገሩኝ፡፡ ለካ የአቤል ቤተሰቦች ነገሮችን ሁሉ ቶሎ ቶሎ ያጣድፉ የነበሩት እርሱን እንዳስታምምላቸው እንጂ ለፍቅራችን አስበው አልነበረም፡፡ በድርጊታቸው ብበሳጭም አቤልን ማግኘቴ ለእኔ ትልቅ ደስታ ነበር እና ስለፍቅር ሁሉን ቻልኩት፡፡

አራት የጭለማ አመታትእንግዲህ የ”ቻይሮድ”ን ኑሮ “ሀ” ብዬ

አቤልን በማስታመም ጀመርኩ፡፡ በየቀኑ ሐኪም ዘንድ ማመላለሱ የእኔ ብቻ ስራ ኾነ፡፡ ከእኔ ውጪ አጠገቡ ሰው አልነበረም፡፡ ጊዜ እየገፋ ሲሄድ ሰዎች ዘወትር ሲያሽ

ሟጥጡ እና ለእኔ ከንፈራቸውን ሲመጡ እመለከት ጀመር፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ሆኖ ነ

ገሩ ለእኔ ባይገባኝም መናደዴ አልቀረም፡፡ የኋላ የኋላ ግን መርዶውን ራሴ አረጋገጥኩ ‐ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ፡፡ ይህ ለእኔ ትልቁ መርዶ ነበር፡፡ ቢኾንም ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡ አሁንም አቤል ለእኔ የፍቅር ምሳሌ ነው፡፡ ሀገሬን በፍቅሩ የለወጥኩበት፡፡ ድሃ እናቴን የተካሁበት፡፡ መሞትን ሳይሆን ዘላለማዊነትን የተማርኩበት ነው፡፡ እናም ከጎኑም መሬትም እየተኛሁ አራት አመታትን አብረን አሳለፍን፡፡ አሰገራሚው ነገር የሰው መጠቋቆሚያ መኾኔ ነ

ው፡፡ ብዙዎች ከእሱ ጋር አንሶላ የምንጋፈፍ ይመስላቸዋል፣ እናም ሕመምተኛ፡፡ አቤል ስህተት ሰርቶ ለሕመሙ ቢዳረግም ለእኔ ግን እጅጉን ይጠነቀቅ ነበር፡፡ አራት አመት ሙሉ ስንኖር አንድም ቀን ሰዎች ያሰቡትን አልፈጸምንም፡፡ ይልቁንም የሰዉን አፍ ችዬ ለፍቅር ታማኝ ኾኜ ማስታመሜን ቀጥያለሁ፡፡የጉድ ቀን ቶሎ አይመሽም እንደሚባለው የካና

ዳውም ፕሮሰስ ሳይሳካ ቀረ፡፡ እንግዲህ የእኔ ሕይወትም ለፍቅር መቅለጥ ኾኖ ድኻ እናቴን አንድ ቀን ሳልረዳ እያልኩ በሃሳብ ማዕበል እዋልላለሁ፡፡ ስለራሴ የኑሮ ለውጥም ማሰቤን አልተውኩም፡፡ ብዙ አሰልቺ ነገሮች ውስጥ ኾኜም ቢኾን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የኑሮ ነገ እና የፍቅር ፈተና አቤልም ይሄ የኑሮ ለውጥ መሻቴ የገባው ይመ

ስል አዲስ አመል አመጣ፡፡ ዘወትር እርሱን ትቼ፤ ሌላ ሰው አግብቼ፤ ለተሻለ ኑሮ ወደ ሌላ አገር እንድሄድ ይገፋፋኝ ጀመር፡፡ ነጋ ጠባ ይወተውተኛል፡፡ በርግጥ ይህ ግፊት ከእርሱ ዘንድ የበረታ ይኹን እንጂ በቅርብም በርቀትም ያሉ ወዳጅ ዘመዶች የእለት ተግባር ነበር፡፡ አቤል ሌላ ሰው በ“ፕሮሰስ” አግብቼ ወደ ው

ጭ አገር መሄድ እንዳለብኝ ግትር አቋም ያዘ፡፡ ከዚህ በኋላ እኔም ልቤ ለሁለት ይከፈል ጀመር፡፡ ቢያንስ የፍቅር ሕይወቴ የተዋጣለት ባይኾን እንኳን ስለ ነገው ኑሮዬ ማሰብ እንዳለብኝ ህሊናዬ ይሞግተኝ ጀመር፡፡ ፈተናው ለአእምሮዬ ከምችለው በላይ ነበር፡፡ ግን መወሰን ነበረብኝ፡፡ እናም በመጨረሻ ወሰንኩና አንድ ፕሮሰሱ የተ

ጠናቀቀለት ሰው አግኝቼ የቀለበት ሥነ ስርዓት ለማድረግ ተገደድኩ፡፡ በመጀመርያ ገንዘብ ልከፍለው ነበር የተስማማነው። ነገር ግን በጊዜ ሂደት “ተላመድንና” ክፍያው ቀርቶ በወዳጅነት ተጠናቀቀ፡፡ እግዜር ይመስገን የውጭ ጉዞዬም ከጫፍ ደረሰልኝ፡፡ ነገሮች እንዲህ ቢሄዱም ሙሉ ደስታ አልነበረኝም፡፡ በ“ፕሮሰሱ” ምክንያት የተለየሁት አቤል ጥሩ ነገር አልተሰማውም ነበር፡፡ ከእለት እለት ህመሙ እየባሰበት ከአልጋ የሚነሳበት ቀናት እየመነመኑ መጡ፡፡ የእኔ ከእርሱ ዘንድ መራቅ ህመሙን እንዳባሰበት አልክድም፡፡ በመጨረሻም እኔ ወደ ሶስተኛ አገር ለመሻገር

በማኮበኩብበት ወቅት አቤል በሞት ተለየኝ፡፡ ሞቱ የፈጠረብኝን መረራ ሐዘን በምን ቋንቋ መግለጽ እንደምችል አላውቅም፡፡ ልቤ ክፉኛ ተሰበረ። እንባዬ ተዥጎደጎደ። ሁሉ ነገር አስጠላኝ። ከአቤል ጋር በነበረኝ ፍቅር አልቆጭም። በሚ

ገባ አፍቅሬዋለሁ፡፡ ለፍቅርም የሚከፈለውን ያህል ከፍያለሁ፡፡

“ጌታ ሆይ ነፍሱን በገነት ተቀበላት”።

እንዲህም ይፈቀራል

‹‹አቤል የኔ ተስፋ ሩቅ ሀገር ያለኸውበርሬ ልምጣና ትንፋሽህን ልማገው››

‹‹ከቀይባህር ማዶ ያገኘሁህ ቆንጆውሰድና አኑረኝ በትንሿ ጎጆ››

ከምርጥ የኢትዮጵያ ቡና እና ማኪያቶ ጋር

ናፍቆት ኢንተርኔት ካፌ-ፈጣን ኮኔክሽን- ፎቶ ኮፒ- የሕትመት አገልግሎት- ስካኒንግ

አድራሻ፦ ካሳንጋ/ ጋባ መንገድ ከጆን ሱፐር ማርኬት አጠገብ

በቅርብ

ቀን

Page 15: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 15

የከተማ ቧልት

እንደ ትናንት ምሳ የተመገብንባት ቤት እንደ ዛሬ ሄደን ምሳ አዘዝን፡፡ ከሌሎች ምግብ ቤቶች አንፃር ዋጋዋ ደህና ናት ተብሎ በኛ ዘንድ ሞገስ ያገኘች ቤት ነበረች፤ ይህቺ ምግብ ቤት፡፡ ከአቅም አንፃር ደግሞ በጣም ደህና እንዲሆንልን አምስት ስድስት ሆነን በማኅበር አዝዘን እንመገብ ነበር፡፡ ምግቡ መጣ፤ ከጥሩ የምሳ ጨዋታ ጋር ተበላ፤ በጥርስ እንጨት ጥርሳችንን እየጎረጎርን ሂሳብ እንዲቀበለን አስተናጋጃችንን ጠራን፡፡ እስኪመጣም ዐይናችንን ወደ ተከፈተው ቴሌቪዥን ሰደድን፡፡ “የቢን ላደን ሞት አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው!” ይላል ዘገባ

ው፡፡ ለበላነው ምግብ ማወራረጃ ይሆን ዘንድ የኛም የውይይት ርዕስ ቢን ላደን ሆነ፡፡“ለመሆኑ ቢን ላደን የሚባል ሰው በህይወት ነበረ?”“እንዴ ምን ነካህ አለ እንጂ!”“እውነት ግን ለምን ሬሳውን አያሳዩንም?”“ያልነበረ ሰው መቼም ሞተ ተብሎ አይነገርም!”“ቢን ላደን ለኦባማ ስልጣን ማራዘሚያ ጠቀመው!”አስተናጋጁ ከቆይታ በኋላ እንደ መጽሐፍ ተገላጭ የሂሳብ

መቀበያ ውስጥ ቢል ሸጉጦ ሰጠን፤ ቢሉ ቢነበብ ትናንት በበላነው በእያንዳንዱ ምግብ ላይ በትንሹ ስድስት ብር ተጨምሯል፡፡ “ምንድነው ይሄ?” ቢሉን እያየ ያለው ወዳጃችን ፊቱን አኮሳ

ትሮ ጠየቀ፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች የተሰላቸው አስተናጋጅ ፊቱን አዙሮ የዋጋ ዝርዝር የተጻፈበትን ነጭ ሰሌዳ አሳየን፡፡ የዋጋ ጭማሪው እውነት ነው፡፡ 34 ብር የነበረው የበግ ጥብስ 40 ብር ብሎ ይጀምራል ዝርዝሩ፡፡

‹‹ስሜ ሙሉነህ ይባላል፡፡ ተወልጄ ያደኩት በቀድሞው ቅጠል ሰፈር በአሁኑ ኢንቨስተር ሰፈር ነው፡፡ ለረዥም ዓመታት ከድህነቴ ጋር ተስማምቼ የኖርኩት በዚህ የበለፀጉ ግለሰቦች በሚጠሩበት ስም ተከልዬ ነው፡፡ ‹‹ሙሉነህ›› ተብዬ ያልሞላ ኑሮ መኖሬ ብቻ ሳይሆን ድሃ ሆኜ መገኘቴ ወንጀል መሆኑን አምኛለሁ፡፡ ለረዥም ዓመታት ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀልን ስፈፅም የኖርኩት የሞላለት ሐብታም በመምሰል ነው፡፡ ነጋ ጠባ ተመስገን ስል የአካባቢያችን ነዋሪዎች ቢሞላለት ነው ፈጣሪውን የሚያመሰግነው ብለው በቸልታ ያልፉኝ ነበር፡፡››‹‹አንድ ቀን፤ ንጋት ለፀሐይ ቦታዋን ልልቀቅ አልልቀቅ ብላ በምትሟ

ገትበት ማለዳ ከቤቴ ወጥቼ የሚያማምሩ የመኖሪያ ህንፃዎች በተገነቡበት በኢንቨስተር ሰፈር መሃል በመሄድ ላይ ነኝ፡፡ ራትም ሆነ ቁርስ አልበላሁም፡፡ በባዶ ሆዴ አልጋዬ ላይ ስገላበጥ ወይም የደሃ እንጉርጉሮ ሳሰማ ወይም ስነጫነጭ ጎረቤቶቼ እንዳይሰሙኝ በጠዋት ከቤቴ ወጣሁ፡፡ በጉዞዬ ላይ በጣም ራበኝና ድንገት አዛጋሁ፤ በእድሜ ጠና ያሉ አንድ አዛውንት አይተውኝ ተገረሙ፡፡ ‹‹ይህ የምን በሽታ ምልክት ነው?›› አሉኝ ግራ ተጋብተው፡፡ ደነገጥኩ፡፡ በዚህ ድህነት ተረት በሆነበትና ጥጋብ በየቤቱ በገባበት ዘመን ተርቦ መገኘት ወንጀል መሆኑን አውቃለሁና በጣም ደነገጥኩ፡፡ ‹‹ማታ ትንሽ አንድ አሥር መለኪያ ውስኪ ጠጥቼ ነበር፡፡ እቤቴ ከገ

ባሁ በኋላ ምሳ ሰዓት ላይ ያስተረፍኩትን ቅቤ የበዛበት ክትፎ በዛ አድርጌ በልቼ ተኛሁ፡፡ አሁን ደግሞ ከቤት ስወጣ ቤት ያፈራውን ክሽን ተደርጎ የተሠራ ሁለት ሰሃን ሙሉ ጥብስ ፍርፍር ነገር በላሁና ጭማቂ ነገር ጠጥቼ ወጣሁ፡፡ የማታው ውስኪ ክትፎውን አልወደደውም መሰል ይኸው በየደቂቃው ያዛጋኛል!››አዛውንቱ በጥሞና ከሰሙኝ በኋላ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተመገበ

ያለው አሁን አንተ እንዳልከው ነው፤ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ሰምቼ አላውቅም!›› ብለው ትተውኝ ሄዱ፡፡ እንዲህ ባለው ታላቅ ማጭበርበር ከርሃቤ ጋር ተስማምቼ በዋልኩበ

ት በዛ ምሽት ቤቴ ገባሁና ቀኑን ሙሉ እህል ያላየ ሆዴን እያሸሁ ተኛሁ፡፡ እንቅልፍ ከየት ይምጣ? ብገላበጥ ብገላበጥ እንቢ አለኝ፡፡ በጣም ከመበሳጨቴ የተነሳ ኑሮዬን አማረርኩ፡፡ ‹‹ከድህነቴ ጋር ተስማምቼ ለዓመታት ኖርኩ፤ አሁን ግን አልቻልኩም! አልቻልኩም! እውነቱ ይውጣ፤ አልቻልኩም!›› አልኩ በታላቅ ሃዘን፡፡ከአምስት ደቂቃ በኋላ በሬ ተንኳኳ፡፡ ‹‹ማነው?›› አልኩ ደንግጬ፤

ፖሊሶች ነበሩ፡፡ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ፡፡ ሦስት ከረቫት ያሰሩ ዘናጭ ፖሊሶችና ድንበር የሚጋራኝ ጎረቤቴ ወደ ቤቴ ዘልቀው ገቡ፡፡ በላዬ ላይ ያለቀ ግልገል ሱሪ እንደለበስኩ፣ ከወገብ በላይ ራቁቴን እንደሆንኩ ፈዝዤ ቀረሁ፡፡የሠራሁትን ወንጀል አላወቅሁም ነበርና፣ ‹‹ምነው ምን አደረግኩ?››

አልኩ፤ ‹‹ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል በመፈፀምህ በቁጥጥር ስር ውለሃል!›› አለኝ አንዱ ፖሊስ፡፡ ቅድም ሳማርር ጎረቤቴ ሰምቶኛል ማለት ነው፡፡ ‹‹እሺ›› ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ የድህነት አከርካሪ በማያዳግም መልኩ በተመታበት በዚህ ዘመን እኔ ከድህነቴ ጋር ተስማምቼ መኖሬ ታላቅ ወንጀል ነውና ጥፋቴን አምኜ ለፖሊሶች ቃሌን ሰጠሁ፡፡ መጀመሪያ ፍርድ ቤት የቆምኩ ዕለት እንዲህ ሲል ነበር ጎረቤቴ ቃሉን የሰጠው፡፡ ‹‹በእውነቱ ይሄ ተዓምር ነው፡፡ /ከራቫቱን እያስተካከለ/ ማመን አቅ

ቶኛል፡፡ እንዲህ ዓይነት ወንጀለኛ በጉያችን መኖሩ ገርሞኛል፡፡ …ይኸው ግለሰብ በተያዘበት ምሽት አልጋው ላይ እየተገላበጠ ኑሮውን ሲያማርር በመስማቴ ደነገጥኩ፡፡ ‹‹ከድህነቴ ጋር ተስማምቼ ለዓመታት ኖርኩ፤ አሁን ግን አልቻልኩም! አልቻልኩም!›› ሲል ሰማሁት፡፡ ወዲያው ፖሊሶችን በመጥራት ቤቱ ይዤያቸው ገባሁና ላሲዘው በቃሁ፡፡”ደሃ ሆኖ የመኖርን ወንጀል ለመፈፀም የበቃሁት የፀረ ልማት ኃይሎ

ችንና የነጭ ለባሾችን ፕሮፓጋንዳ በመስማት ነው፡፡ የፀረ ልማት ኃይሎችና የነጭ ለባሾች ፕሮፓጋንዳ ድህነትን የሚያበረታታ፣ የልማት እቅዱን የልፋት እቅድ ብሎ የሚያጣጥል፣ ብልፅግናን እንደ ኩነኔ የሚቆጥር፣ የልማት እቅዶች ላይ የሚያሾፍ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የትራንስፎርሜሽን እቅዳችን እውን ሆኖ ሳይና ከእቅዱ ጋር አብሬ ባለመጓዜ የሠራሁት ወንጀል በእጅጉ ሲፀፅተኝ ይኖራል፡፡

በናዝሬት (አዳማ) የሚገኘው ይልማ ስጋ ቤት ከአዲስ አበባ ጭምር ስጋውን ፈልገው የሚመላለሱለት ደንበኞችን ያፈራ አንጋፋ ድርጅት ነው። ይሄው ስጋ ቤት በዋና ከተማይቱ አዲስ አበባ እንኳ ባሉ በርካታ ስጋ ቤቶች በማይታይ ሁኔታ የተደራጀ ነው። ዘመናዊ ህንጻ፣ ንጹህና ማራኪ ስጋ መደርደሪያ፣ አፍንጫ የማይቆርጥ ሽንት ቤት፣ ከተፎ አስተናጋጆች ይዞ አፍ ውስጥ የሚሟሟ ስጋ ለተመጋቢዎች እንደየምርጫቸው ያቀርባል። ይሄ ተወዳጅ ስጋ ቤት ታዲያ በቅርቡ በመላው ኢትዮ

ጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የዋጋ ተመን መቋቋም ያቃተው ይመስላል። በኪሎ ይህን ያህል ብቻ መሸጥ የሚቻለው ተብሎ ከመንግስት የወረደውን ትዕዛዝ ላለመጣስ ተጠንቅቆ ግን ደግሞ የሚሰጠውን አገልግሎት ባገናዘበ መልኩ የገንዘብ ማካካሻ ጨምሮ ማስታወቂያ ያዘጋጃል። ማስታወቂያው የአንድ ኪሎ ጥሬ/ጥብስ ስጋ ዋጋ 40 ብር መኾኑን ይገልጽ እና የስጋውን ዋጋ ያህል ክፍያ ከደንበኞቹ ይጠይቃል። የይልማ ደንበኞች በ90 ብር ብቻ አልተገላገሉም። 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስም በቢሉ ውስጥ ይካትታል።

መስተንግዶ ከስጋ የተወደደበት ሀገር

“ለምንድነው በአንድ ቀን ይሄ ሁሉ ጭማሪ!?”“ቢል መቁረጥ ዛሬ ስለጀመርን!” በታከተ ድምጽ አስተናጋጁ

መለሰ፡፡“ቢል ከምትሉት ቢላ ብትሉት አይሻልም!?” በምሬት ተናገረ

ሌላው ወዳጃችን፡፡ሻዩ፣ ማኪያቶው፣ ሽሮው፣ ቀይ ወጡ… /ሆድ ስለባሰኝ በዚሁ

ልቀጥልበት፡- ትራንስፖርቱ፣ ስኳሩ፣ ዘይቱ፤ ወይ ዘይት፤ ዘይት የቅቤ ረዳት ተዋናይ ተደርጎ መጠራት ከጀመረ ጀምሮ ዋጋው የማይቀመስ ብቻ ሳይሆን በፈለጉት ዋጋ ታስሶ የማይገኝ ሆኗል፡፡ “ሸኖ ቅቤ፤ ሸኖ ለጋ፣ ሻዲ ለጋ…” ያኔ ሲሉት መጠርጠር ነበረብን፡፡ …ነዳጁ፣ ሰዉ፣ ሥጋው፣ ግብረ ሥጋው… አዪዪ… ምን ይሻላል?/ ሁሉ ነገር በየቀኑ ይጨምራል፤ “የዚህ የኑሮ ውድነት ጦስ መጨረሻው ምን ይሆን?” ስጋት ባጀበውና ዝግ ባለ ድምፅ ራሴን ጠየቅኩ፡፡ “ወይ ጉድ!” አለ አንዱ ወዳጃችን በመሃል አንዳች የታወሰው ነ

ገር ያለ በሚመስል፡፡ “ምን ሆንክ?”“ቢል ላደን መቼ ሞተ?”“እንዴት?”“በህይወት አለ እኮ፤ ያውም እዚችው እኛው ምድር!”“ምን ማለት ነው?”“ቢል ላደን መጥቶ ይኸው እኛን እየጨረሰን እኮ ነው፡፡” አለ

ንግግሩን ይበልጥ እያሻሻለ፡፡ የጓደኛችን ንግግር ሁላችንም የገባን ዘግይቶ ነው፡፡ ነገሩ ቅኔ መሆኑ ነው፤ ቢል ላደን፡፡ እውነትም ቢል ለአደን፡፡“እንገዛ ነበረ እቃ በጥሩ ዋጋ፣ቢል ላደን መጣና ኑሯችን ተናጋ፡፡”

በ2010 ዓ.ም በበለፀገችው እና በታላቂቱ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳች አስደንጋጭ ዜና ተሰማ፡፡ የልማትና የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ እውን ሆኖ ሕዝቡ በታላቅ ተድላ በሚኖርበት፣ ድህነት ተረት በሆነበት፣ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ እንደ ልቧ መጠቀም በጀመረችበት በዚያ ዓመት አንድ ግለሰብ ድሃ ሆኖ መገኘቱ የኢትዮጵያውያንን አንገት ያሰበረ አሳዛኝና አሳፋሪ አጋጣሚ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የምንጨዋወተው 2010 ዓ.ም ላይ ቆመን ይሆናል፡፡

አንድ ደሃ በኅብረተሰቡ ድጋፍና በፖሊስ ያላሰለሰ ጥረት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ‹‹ድሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል ፈፀመ›› ተብሎም ሕግ ፊት ቀረበ፡፡ የወቅቱ የፕሬስ ነፃነት የወለዳቸው፣ በሚሊዮን ኮፒ የሚሸጡት ጋዜጦችና መጽሔቶች ዜናውን በፊት ገፆቻቸው ይዘውት ወጡ ፡፡አንድ፡- ድህነትን ተረት ባደረግንበት በዚህ ጊዜ አንድ ድሃ ሆኖ የተገኘ ወንጀለኛ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ሁለት፡- ድሃ ሆኖ በመገኘት ያገራችንን መልካም ገፅታ ያጠፋው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፤ ሦስት፡- ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ያወጣነውን ‹የትራንስፎርሜሽን› እቅድ በቸልታ በመመልከት እስከ ድህነቱ የዘለቀው ግለሰብ

በቁጥጥር ሥር ዋለ! ወንጀሉም ከአገር ክህደት የማይተናነስ ትልቅ ወንጀል ነው ተባለ፡፡ እነዚህ ዘገባዎች በወጡ በሳምንቱ የወንጀለኛውን የሕይወት ታሪክ የያዘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ ወንጀለኛው አንገቱን በታላቅ

እፍረት ወደ ምድር ሰብሮ በመጽሐፉ ሽፋን ላይ ታየ፡፡ ርእሱ፣ ‹‹ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል የፈፀመው ወንጀለኛ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ›› ይላል፡፡ እነሆ ከመጽሐፉ የተቀነጨበ ታሪክ፤

‹‹ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል የፈፀመው ወንጀለኛ ታሪክ››በእግዜር /ከአራት ኪሎ/

ሰበር ዜና፡- ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ መኖሪያ ቤት፣ በፖሊሶች ሲፈተሽ ባለአንድ ሺህ ብር የአባይ ግድብ ማሠሪያ ቦንድ መገኘቱን የኢንቨስተር ሰፈር ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ የቦንዱ ወረቀት ግንቦት 11 ቀን 2003 ዓ.ም የተገዛ እንደነበረ ምርመራውን ሲያካሂድ የነበረው ኢንስፔክተር አስታውቋል፡፡

ቢላደን አልሞተም!

መቼ፦ ዘወትር ማክሰኞ እና ሀሙስየት፦ ናኩማት ሞል አጠገብ ካለው ኤፌንዲስ (ሴንቲነሪ ፓርክ) እና ከብሔራዊ ትያትር ታችኛው መግቢያ በተቃራኒ ባለው ፓን ወርልድ የመኪና መሸጫ ቦታ ሰዓት፦ ከምሽቱ ሁለት ሰዓትየመግቢያ ዋጋ፦ 10ሺህ ሽልንግ እና አምስት ሺህ ሽልንግ

የዩጋንዳ ታዋቂ “ስታንድ ኦፕ” ኮሚዲያን የሆነው ፓብሎ በበሳል ቀልዶቹ ይታወቃል። ከእንግሊዘኛ ጋር ሉጋንዳ እና ሌሎች የሀገሪቱን ቋንቋዎች እየቀላቀለ በሚያቀርባቸው ቀልዶች ጥርስ አያስከድንም ይሉታል። ፓብሎ በ“ኦብዘርቨር” ጋዜጣ የሐሙስ እትም ላይ የራሱን አምድ ከፍቶ አንባቢዎችን ዘና ያደርጋል።

በአብዛኛው ወጣቶች የተሰባሰቡበት የ“ፈን ፋክተሪ” አበላት ድራማዊ ይዘት ባላቸው ቀልዶቻቸው ይታወቃሉ። እንግሊዘኛ እና የተለያዩ የዩጋንዳ ቋንቋዎችን የሚጠቀሙት “ፈን ፋክተሪዎች” በእንቅስቃሴያቸው ብቻ ሳቅ የሚያጭሩ ናቸው። አብዛኞቹ የ“ፈን ፋክተሪ” አባላት በአሁኑ ወቅት በ“ኤንቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ እየተላለፈ በሚገኘው “ሆስቴል” ድራማ ላይ ይተውናሉ።

ኮሜዲ ፊልም

ዩጋንዳየት ሄደን እንዝናና?

መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ጋርደን ሲቲ ከኡቹሚ ሞል በላይ አንደኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ) ለካምፓላ ብቸኛ የሆነው ሲኒማ ቤት ሲኒፕሌክስ በሶስት የተለያዩ አዳራሾቹ የአሜሪካ እና የህንድ ፊልሞችን ሳምንቱን ሙሉ ለተመልካች ያቀርባል። በጁን ወር ከሚያስመጣቸው ፊልሞች ጥቂቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ናቸው።

ኮሜዲ አፍቃሪ ለሆኑ

የአፍሪካ አሜሪካውያንን ፊልም ለሚወዱ የሚመረጥ በሁለት ፍቅረኛ ቤተሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ሁነቶች ዙሪያ የሚያጠነጥን

ፍቅር፣ፖለቲካ እና ድርጊት የተሞላበት ፊልም

የኩንጉ ፉ ፓንዳ ቀጣይ ክፍል፤ ለህጻናት እና ካርቱን ፊልም ለሚያፈቅሩ

በእግዜር /ከአራት ኪሎ/

ጃማይካዊው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሾን ኪንግስተን ከካምፓላ ሙዚቃ አፍቃሪያን ጋር ለመገናኘት ለጁላይ 29 ቀጠሮ ይዟል። በቅርቡ በደረሰበት አደጋ የካምፓላውን ዝግጅት ሊሰርዘው ይችላል የሚል ግምት አሳድሮ ነበር። ሆኖም ከኮንሰርቱ አዘጋጆች የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው አቀንቃኙ በተያዘለት ቀን ዝግጅቱን ያቀርባል። ቦታው ሎጎጎ የሚገኘው የክሪኬት መጫወቻ ሜዳ ነው። ታዋቂው አሜሪካው አቀንቃኝ አር ኬሊ በካምፓላ ዝግጅቱን ያቀረበውም በዚሁ ቦታ ነው። “ክለብ ቢራ” ስፖንሰር ያደረገው ይሄው ዝግጅት የመግቢያ ዋጋው ስንት እንደሆነ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

>>>ሾን ኪንግስተን በካምፓላ ሙዚቃ

Page 16: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)16 ሀበሻዊ ቃና

መጽሐፍ

የሙሉ ጊዜ ስመ ጥር ደራሲ ነው። አሳታሚዎች ሰላምታ ካቀረቡለት በኋላ የሚያስከትሉት የሁልጊዜ ምክር ተመሳሳይነት ይገርመዋል። “ጎበዝ ደራሲ ነህ

ግን… እንዲህ ብጥስጥስ ያለ ሳንቲም ከምትሰበስብ ለምን ሸጋ የኾነ የወሲብ ሳይኮሎጂ አትጽፍም። ላንተም ለኛም ጥሩ የሚኾነው እርሱ ነው፣ ካንተ ያነሰ ችሎታ ያላቸው ልጆች ይኸው ለገበያ የሚኾን ነገር እየጻፉ ቀድመውህ ሀብታም እየኾኑ ነው፤ እስኪ ስብበት።”ይህ አሳታሚዎች ለደራሲዎች የሚያቀር

ቡት አባታዊ ምክር እንደዋዛ የሚታይ አይደለም፡፡ የኅብረተሰባችንን ድብቅ ሥነ-ልቡናዊ ፍላጎት የሚያመላክት ነው። የምክሩ ትርጉም ግን ከዚህም ይዘላል።

የወሲብ ሰልፍየዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በ1980ዎቹ አጋማ

ሽ እና መጨረሻ በተለምዶ “ወመዘክር” በሚባለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት እና ቤተ-መዛግብት የጋዜጣ ክፍል ውስጥ የነበረውን ኹኔታ ፈጽሞ አይዘነጋውም። በጣውላ የታነጸው በቢጫማ ቀለም የተዋበው ክፍል በወቅቱ በአገሪቱ የሚታተሙትን የመንግሥት ኾኑ የግል ጋዜጦችን እና መጽሔቶችን ለጋዜጣው ክፍል ታዳሚ ያቀርብ ነበር። ኾኖም በወቅቱ ይወጡ ከነበሩት የኅትመት ውጤቶች አንባቢው ቀዳሚ ትኩረት ይሰጥ የነበረው እንደ “ጥንቅሽ”፣ “ማዶና”፣ “የፍቅር ማኅደር”፣ “ኤሮቲካ”፣ “እንኮይ” እና “እውነተኛ ፍቅር” ላሉት ወሲብ ተኮር ጋዜጦች እና መጽሔቶች ነበር። በዚሁ ጋዜጣ ክፍል ውስጥ ይታደሙ ከነበሩት መካካል 75 መቶ የሚኾኑት ወሲብ ነክ የኅትመት ውጤቶችን የመኮምኮም ልማድ አዳብረው ነበር። የጋዜጣ ክፍሉ በጊዜ ስለሚሞላ ብዙ አንባቢያን በመጡበት እንዲመለሱ ይገደዱም ነበር። አንዳነድ ደንበኞች ግን እነዚህን የወሲብ ጋዜጦች ለማግኘት በትእግስት ይጠባበቃሉ፤ እየተፋፈሩ። ኹኔታው የወሲብ ፊልምን ለመታደም በአንድ ክፍል እንደመገኘት ዐይነት ስሜት ነበረው።በወቅቱ “ማዶና” ጋዜጣ የአንዲት ኢትዮ

ጵያዊት ሴትን በእውን ዓለም ይሆናል የማይባል የወሲብ ገድል የሚተርክ “ኢትዮጵያዊቷ ማዶና” የሚል ዐምድ የነበረው ሲኾን የቅንዝረኛዋን ሴት ገድል ከሰማንያ ሳምንት በላይ በጋዜጣው ላይ ተስተናግዷል። ጋዜጣው በወሲብ አራራ በእጅጉ የተለከፈች

ውን ሴት አንድ ልዩ ገድል በየሳምንቱ ይዞ ይቀርብ ነበር። “ጥንቅሽ” ጋዜጣ በበኩሉ “የሴተኛ አዳሪዋ ገመና” በሚለው ዐምዱ ወጣ ያሉ እና ማኅበረሰቡ ዘንድ ፀያፍ ተደርገው የሚቆጠሩ ወሲባዊ ኹነቶችን ልብን በሚሰቅል እና ለወሲብ በሚያማልል ኹኔታ ያቀርብ ነበር። ለእነዚህ ሁለት ዐምዶች ነበር የወመዘክር ቤተ መጻሕፍት በወሲብ ሲቃ ጡዘት ላይ ትዋልል የነበረው። የጋዜጣው ክፍል ታዳሚዎች እነዚህን ወሲባዊ ትርክቶች ቀድሞ ለማንበብ ብርቱ ትግል ያደርጉ ነበር። ከቤተ መጻሕፍቱ አስተናጋጆች እስከመሻረክ ድረስ። እነዚህ ጋዜጦች ከሌሎች በዚህች ክፍል ይገኙ ከነበሩ ጋዜጦች በተለየ መልኩ ይሟሽሹ ነበር። የሰው እጅና ዐይን ስለሚበዛባቸው።

የሌተናል ኮሌኔሉ መፈንቅለ- ወሲብ

በሕይወት የሌሉት ሌ/ኮሎኔል ጌታቸው መኮንን ሐሰን ከላይ ከተጠቀሱት ወሲብ ተኮር የኅትመት ውጤቶች በዋናዎቹ ውስጥ የመሥራችነት እና የባለቤትነት ሚና ነበራቸው። በ1987 ዓ.ም አካባቢ በርካታ ሴቶች “እንኮይ” መጽሔትን ጨምሮ ሌሎች ወሲብ ነክ ጋዜጦች “ሴቶችን ወሲባዊ ሸቀጥ አድርገው ያቀርባሉ” በሚል “በሴቶች እኩልነት የሚያምነው መንግሥታችን በአሳታሚዎች እና በአዘጋጆች ላይ ሕጋዊ ርምጃ ይውሰድልን” ብለው ሰላማዊ ሰልፍ እስኪወጡ ድረስ ኮሎኔሉ በኢትዮጵያ የጋዜጣ እና የመጽሔት ኅትመት ታሪክ ከፍተኛ ሊባል የሚችል ትርፍ አጋብሰዋል። በወቅቱ ከነበሩት ወሲብ ተኮር ኅትመቶች ከሲሶ በላዩ የሌተናል ኮሌኔሉ ንብረቶች ነበሩ።ሌ/ኮሎኔል ጌታቸው ከጋዜጦች እና መ

ጽሔት ዕገዳ በኋላም ቢኾን እጃቸውን አጣምረው አልተቀመጡም። በወሲብ ተኮር ጋዜጦቹ እና መጽሔቶቹ የተደረገባቸውን መፈንቅል ለመቀልበስ ወጠኑ። የወሲብ ነክ የኅትመት ውጤቶችን ገበያ እና የኅብረተሰቡን ታማኝ አንባቢነት በዉሉ ያጠኑት ሌ/ኮሎኔሉ ማርሻቸውን ወደ መጻሕፍት ቀየሩት።ኮሎኔሉ ቀድሞ እጃቸውን ያሟሹባቸው

ን የነአጋታ ክሪስቲን፣ ሼርሎክ ሆልምስን እና ሌሎችም ዝነኛ ወንጀል ነክ ታሪኮችን ወደ አማርኛ የመተርጉሞን ነገር ለጊዜው ጋብ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ወሲብ ዘመም መጻሕፍት አዞሩ።በመጀመርያ ወደ አማርኛ የተረጎሙት የ

ኸርቪንግ ዋላስን “የደፈረሰ እንባ” ሲኾን መጽሐፉ ዐሥራ አንድ ጊዜ ኅትመት ቤትን ጎብኝቷል። የዚህ መጽሐፍ ሽፋን ከወገቧ በላይ ርቃኗን የኾነች ወጣት በወሲባዊ

አቀማመጥ ጡቶቿን ወድራ የምትታይበት ምስል ነበር። የመጽሐፉ ጭብጥ አንዲት ወጣት ሴት ወሲብን እንደምትወድ በሚዲያ ከገለጸች በኋላ በአራት ወንዶች ተጠልፋ ተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃት ሲደርስባት እና ከዚህ ለማምለጥ የምታደርገውን ብርቱ ትግል ይተርካል። ይህ የትርጉም መጽሐፍ በወቅቱ ብዙ ሺሕ ኮፒ በመሸጥ መነጋገርያ ኾኖ ቆይቷል፡፡ኮሎኔሉ ከዚህ መጽሐፍ በኋላ የተረጎሟ

ቸው “የባሎች ገመና” እና “የዘቪራ ሆላደርን” ግለታሪክ ናቸው። ዛቬራ ለዚህ ግለ ታሪክ መጽሐፍ የሰጠችው ኦሪጅናል ርእሰ “the happy hooker” ይሰኛል። ከዚህ ሥራ በተጨማሪ “አልሎት” /the bitch/፣ “መንታዋ አነር” /13 at dinner/ እና “ኮርማው” /the stud/ የተሰኙት ወሲብ ተኮር የኾኑት የትርጉም ሥራዎቻቸው በተደጋጋሚ ታትመውላቸዋል። የኮሌኔሉ ሁሉም የትርጉም ሥራዎች ጡት መያዣ እና የውስ

ማ ለመኾን ችለው ነበር።በ1994 ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ ለኅትመት

የበቃው “የፍቅር ጥበብ” የተሰኘው መጽሐፍም ቢኾን አሁን 12ኛ ዕትም ላይ ነው ያለው። ይኸው ማኅሌት ጥላሁን በሚል የብእር ስም የተተረጎመው መጽሐፍ ልቅ የወሲብ መጽሐፍ ባይኾንም በርካታ ገጾቹን ለወሲብ ተኮር ጉዳዮች ሰውቷል። በተመሳሳይ የወሲብ ተኮር ሥነ-ጽሑፍ ላይ የተሰማሩ አሳታሚዎች እና አስተርጓሚዎች እንደሚያምኑት የትኛውም የፖለቲካም ኾነ የታሪክ መጽሐፍ እንደ ወሲብ ተኮር መጻሕፍት ሰፊ ገበያን ማሸነፍ አልቻሉም።

የ“ዘ” ዘመንየካዛንቺስ ሴተኛ አዳሪዎች እና የደንበኞ

ቻቸውን ግንኙነት በተዋንያኑ ልቅ ቋንቋ የሚተርክው “መኀልየ መኀልየ ዘ-ካዛንቺስ” ለኅትመት ገብቶ ለገበያ በቀረበ ጊዜ በኅትመት ሚዲያዎች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብን አስነስቶ ነበር። መጽሐፉ በፊት ገ

ን ፈር ቀዳጅ መጽሐፍ በብዛት ሸጠዋል። አሁንም ድረስ መጽሐፉ በገበያ ላይ በቀላሉ አይገኝም።በአዲስ አበባ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸ

ው መጻሕፍት አከፋፋይ መደብር ባለቤት ከኾኑት አንዱ እንደሚሉት የአሳታሚዋ የስንዱ አበበ ቸልተኝነት እና ስንፍና እንጂ መጽሐፉ እስከአሁን ከዐሥር ዕትም በላይ መሄድ ይችል ነበር። “ይህ ሥራ ያለውን ሰፊ ተቀባይነት ስለማውቅ ሙሉ የኅትመት ወጪውን እኔ እንድሸፍን ጠይቄ ምላሽ አላገኘሁም” ይላሉ እኒሁ አሳታሚ። ውልደቱ እና እድገቱ ካዛንቺስ የኾነው የመጽሐፉ ደራሲ ተድባበ ጥላሁን ይህንኑ ሥራውን ከአመርቂ ክፍያ ጋራ ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ መመለሱ ይታወቃል።የዚህን የ“ዘ”ዘመን መሥራች ወሲብ ሙ

ሊት ሥራ ስኬት የተረዱ አሳታሚዎች የደራሲ ያለህ ማለት ጀመሩ። በዚህም የ“ዘ” ዘመን መጀመር ታወጀ።የቼቺንያን የሌሊት ግብር በቺቺንያ ወሲ

ብ ሸማች ደንበኞች ልቅ ቋንቋ የሚተርከው እና በደረጄ አያሌው የተጻፈው “መኀልየ መኀልየ ዘ ቼቺኒያ” የወሲብ ገበያው ውስጥ ለመግባት የመጀመርያው ነበር። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አሁን አራተኛ ዕትም ላይ እንደደረሰ ለአሳታሚው ቅርብ የኾኑ ምንጮች ይገልጻሉ። መጽሐፉ የሰፈሩን የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች አስከፊ ገጽታ በጥልቀት ለማሳየት ይሞክራል።የዚህን መጽሐፍ ስኬት ተከትሎ ከጥቂ

ት ወራት በኋላ ለገበያ የቀረበው እና ትኩረቱን በተመሳሳይ መቼት ላይ ያደረገው “የቺቺኒያ ምስጢራዊ ሌሊቶች” የተሰኘው መጽሐፍ አሁን ሦስተኛ ዕትም ላይ ደርሷል። የዚህ መጽሐፍ ባለታሪኮች ጥቂት ቢኾኑም በሤራ አወቃቀር፣ በገፀ-ባሕርይ አሳሳል እና በሥነ-ጽሑፋዊ ዉበቱ ሲመዘን ይህ መጽሐፍ ከሁሉም ወሲብ ተኮር መጻሕፍት የላቀ እንደኾነ የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም።ባሳለፍነው ክረምት ለገበያ የቀረበው እና

በጋዜጠኛ ሚልዮን ሹሩቤ የተጻፈው “ወሲባዊ ውስልትና ዘ አዲስ አበባ” የተሰኘው መጽሐፍ የመጀመርያ ዕትም በአከፋፋዮች ዘንድ ያለቀው ዐሥር ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። ይህ መጽሐፍ እስከ አሁን ከጠቀስናቸው በተቃራኒ መልኩ የሚተርከው ስለ ቤት ልጆች እና ባለትዳሮች ወሲባዊ ሕይወት ነው። መጽሐፉ አሁን ሁለተኛ ዕትሙ እየተሸጠ ይገኛል። ደራሲው ከሚተርካቸው እውነታዎች በተጨማሪ ከበርካታ የቤት ልጆች እና ባለትዳሮች ጋራ በቴፕ የተቀረጸ ቃለ-መጠይቅ አድርጓል።

ወሲብ ያበላልባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለገበያ ከ

ቀረቡ የወሲብ ሥነ-ልቡና መጻሕፍት በአመዛኙ ኤሮቲክ ፊልሞች እንዲመስሉ አድርጎ ማቅረብ ተጨማሪ ገበያን እንደመፍጠር እየታየ ነው። በጨዋ ቃላት እና መንገድ ወሲብን ማውራት በአዋጅ የታገደ ይመስል የብዙዎቹ መጻሕፍት አፈጣጠር ልቅነት ይታይበታል። ይህም ከልባሳቸው ይጀምራል። ፈረንጅ ሴት ሞዴሎች ጡቶቻቸውን ወድረው የሚታዩባቸው መጻሕፍትን ቁጥር ሼልፍ ይቁጠረው።በቅርብ ጊዜ በትርጉም ሥራዎች ደረጃ

ያሉትን እንኳ ብንቆጥር ከ20 በላይ እንሄዳለን። ከኒኮል ቤላንድ “the girl next door” የሚለው መጽሐፍ “የሴቶች ገመና’ በሚል ርእስ ወደ አማርኛ ከተመለሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምንተኛ ዕትም ላይ ደርሷል። የዚህ መጽሐፍ ቋሚ ደንበኞች የሁለቱም ፆታ አባላት ናቸው። የጆን ግሬይ “Mars and Venus in the Bedroom” የተሰኘው መጽሐፍ “የወሲብ ጥበብ” በሚል ርእስ በመዓዛ ቴዎድሮስ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲኾን ገና መንፈቅ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሦስተኛ ዕትም ደርሷል፡፡በኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ላይ ሰዓት እላ

ፊ በሚለው “ተወዳጅ” ዐምድ ሥር ለአንድ ዓመት የቀረቡትን የአዲስ አበባ ሴተኛ አዳሪዎችን ሕይወት የሚዳስሱ ስብስቦች “ሰዓት እላፊ” በሚል ርእስ በመጽሐፍ ያሳተመው የዐምዱ አዘጋጅ ኤርምያስ ስዩምም ገበያው ሰምሮለታል። ጋዜጣው በሁለት እግሩ እንዲቆም ያስቻለውም ይኸው ዐምዱ እንደኾነ የሚናገሩ ብዙ ናቸው።አንጋፋው ደራሲ ስብኀት ገብረ እግዚአ

ብሔር የጀመረው የ“እንደወረደ” የወሲብ ሥነ-ጽሑፍ ዛሬ ዛሬ ተስፋ የሚጣልባቸው ወጣት ደራሲያን ሳይቀሩ የብእር ስም እየፈጠሩ እንዲገቡበት እያደረጋቸው ነው። ስብኀት በዚህ ርእስ ሥር መጠራት ከሌለባቸው ኾኖም የወሲብ ወላፈን ከነካቸው ድንቅ ሥራዎቹ መሀል አምስት ጊዜ የታተመለት “ሌቱም አይነጋልኝ” እና ሦስት ጊዜ የኅትመት ብርሃን ያገኘለት “ትኩሳት” ይጠቀሳሉ። እነዚህ ወጥ ድርሰቶቹ ያገኙት ተቀባይነት በወሲብ ሥነ-ጽሑፍ የራሳቸውን ተጽዕኖ አልፈጠሩም ለማለት ግን ያዳግታል። ኾነም ቀረ የኢትዮጵያ የኅትመት ታሪክ በኮሎኔሉ አብዮት ተጀምሮ፣ በ“እንደወረደ” የስብኀት መንገድ አሳብሮ ዛሬ የ“ዘ”ዘመን ላይ ደርሷል። የሚያቆመው ያለ እስከማይመስል ድረስ፤ የኀትመት ዋጋ መናርም እንኳ ቢኾን።

የወሲብ መጻሕፍት የገበያ ሃድራ

ቋንቋ በየፈርጁ

ሙሳ ያሲንአዲስ ነገር ኦንላይን

በሰዋሂሊ ከ G(g) በስተቀር ሁሉም ተነባቢ ፊደላት የሚነበቡት ልክ በእንግሊዘኛው እንደሚነበቡት ነው፡፡

እንደ እንግሊዘኛ ሁሉ ስዋሂሊም አምስት አናባቢዎች አሉት፡፡ እነሱም a,e,I,o,u ሲሆኑ እያንዳንዳቸው አንድ ድምጽ ብቻ አላቸው፡፡ምሳሌ፡-Baba ባባ አባትWewe ዌዌ አንተ/አንቺSisi ሲሲ እኛSoko ሶኮ ገበያKuku ኩኩ ዶሮአንዳንድ ጊዜ ሁለት አናባቢዎች በተከታታ

ይ ይመጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ሁለቱም አናባቢዎች የየራሳቸው ድምጽ ስላላቸው በተናጠል መነበብ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የትርጉም መዛባትን ያስከትላል፡፡ለምሳሌ፡-Kufa (ኩፋ) የሚለው ቃል kufaa (ኩፋአ)

ከሚለው ጋር የተለያዩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያው “ለመሞት” ማለት ሲሆን ሁለተኛው ግን “ይጠቅማል” እንደማለት ነው፡፡ለመግቢያ ያህል ስለስዋሂሊ ቋንቋ መሰረ

ታዊ ነግሮች በጥቂቱ ይህን ያህል ካልን በዚህ የመጀመሪያ እትማችን የሰላምታና ተያያዥ ቃላትን ትርጉም እንደሚከተለው እናስከትላላን፡፡

n Hodi ሆዲ - ሰው ቤት ሄደው በር ሲያንካኩ የ

ሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ “እዚህ ቤት ወይም ቤቶች አላችሁ?” እንደማለትn Hongera ሆንጌራ - እንኳን ደስ ያለህ/ያለሽ/ያላችሁn Pole ፖሌ - አዝናለሁ(ያዘነን ወይም የተጎዳን ሰ

ው ለማጽናናት)n Penda ፔንዳ - ፍቅር(መውደድ)n Kupenda ኩፔንዳ - ማፍቀርn Na kupenda ናኩፔንዳ - አፈቅርሻለሁ/ አፈቅርሃለሁ

ስዋሂሊ ባንቱ ከሚባለው የቋንቋ ምድብ የሚገኝ ሲሆን ለመማር ብዙም ከባድ ያልሆነ ቋንቋ ነው፡፡ የጾታ ገላጭ እና መስተዋድድ እጥረት ከቋንቋው መለያ ባህሪያት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ስዋሂሊ የሚለው ስም ራሱ ሳዋሄል ከሚለው የአረበኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜውም ጠረፍ እንደማለት ነው፡፡ በመሆኑም ስዋሂሊ በምስራቅ አፍርካ ጠረፍ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች በብዛት የሚነገር የጠረፍ ቋንቋ ነው፡፡

የሰላምታ ቃላትጃምቦ፡ ይህ ቃል በምስራቅ አፍሪካ

እጅግ የተለመደና ከወዳጅ ዘመድ ጓደኛ ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ የሚያገለግል ሲሆን ጥያቄውም ምላሹም ራሱ ጃምቦ ነው፡፡ በአማረኛ ጤና ይስጥልኝ እንደማለት፡፡ ይህ ቃል የተወሰደው ሁጃምቦ ከሚለው ሙሉ ሰላምታ ነው፡፡ ይህንና ሌሎችን የሰላታ ቃላት እንደሚከተለው እንመልከት፡፡Hujambo ሁጃምቦ - እንደምን አለህ/አለሽSijambo ሲጃምቦ - ደህና ነኝ፡፡Hamujambo ሀሙጃምቦ -እንደም

ን ናችሁ?Hatujambo ሀቱጃምቦ - ደህና ነንUmzima ኡሙዚማ- ደህና ነህ/ነሽ?Nimzima ኒሙዚማ -ደህና ነኝVipi ቪፒ - እንዴት ነህ/ታዲያስ?Sawa ሳዋ - ደህና ነኝ/አለሁHabari yako ሀባሪ ያኮ -እንዴት ነህ/ነሽ?Nzuri/Njema ንዙሪ/ኒጄማ - ደህና ነኝSubalkheri ሱባሊሄሪ- እንደምን አደርህ/አደርሽ? (ምላሹም ራሱ ነው)Subalkheri habari asubuhi ሱባሊሄሪ ሃባሪያ አሱቡሂ - እንደምን አደርህ/ሽ? ደህና ነህ/ሽ?Njema ኒጄማ -ደህና ነኝ Masalkheri ማሳልሄሪ - እንደምን ዋልህ/ሽ?/ እንደምን አመሸህ/ሽ?Lalaselama/Alamsiki/Usiku Mwe-ma ላላሰላማ/አላሙሲኪ/ኡሲኩ ሙዌማ- ደህና ደር/ሪ/ሩ ለማለት የሚያገለግሉ ቃላት ሲሆኑ ምላሸቸውም አላሙሲኪ ነ

ው፡፡ አሜን ሰላም እደሩ አንደማለት:: Shikamoo ሺካሞ- በእድሜ ለገፋ ወይም በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ላለው ሰው የሚቀርብ ሰላምታ ነው ፡፡ ምላሹም፡ Marahaba መርሃባ ነው፡፡Kwaheri ኩዋሄሪ -ደህና ሁን/ኝ/ኑ ቻውKwaheri yakonana ኬዋሄሪ ያኮናና- ደህና ሁን/ኝ/ኑ ቻው በሰላም ያገናኘንAsanti አሳንቲ - አመሰግናለሁKaribu ካሪቡ - እንኳን ደህና መጣህ/ሽKaribuni ካሪቡኒ - እንኳን ደህና መጣችሁKaribu ndani ካሪቡ ኒዳኒ - ወደ ቤት ግባ/ኖር/ጎራ በል Karibu kiti ካሪቡ ኪቲ - ተቀመጥ እንጂ/አትቀመጥም? ( እነዚህ እንግዳ ሲመጣ ለመቀበል የሚውሉ የሰላምታ ቃላት ናቸው)

ምራቂ

(ቦናሲ-Bonasi)

ትንሽ ስለ ስዋሂሊ ቋንቋ

ት ሱሪ ባደረጉ እጅግ አማላይ እና ወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶች የተሞሉ ነበሩ። የፊት ገጽ ሽፋኖችን አማላይ አድርጎ የማቅረብን ስልት በስፋት ያስተዋወቁት ኮሎኔሉ እንደኾኑ መጻሕፍት አሳታሚዎችም አሌ ሳይሉ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው።

ድኅረ ኮሎኔል ከኮሎኔሉ መፈንቅለ ወሲብ ቀጥሎ የእርሳ

ቸውን አርዐያ ይዘው የቀጠሉ ብዙ ደራሲዎች እና ተርጓሚዎች ተፈጠሩ። የወሲብ ተኮር መጻሕፍት የገበያ ሃድራ የማያባራ እንደኾነ የተረዱ አያሌ አሳታሚዎች ውጭ አገር የሚሄዱ ነጋዴዎችን እና የበረራ አስተናጋጆችን ወሲባዊ መጻሕፍት እንዲያመጡላቸው በማባበል ሥራ ተጠመዱ። የሚመጡላቸውን መጻሕፍት ገነጣጥሎ ለብዙ ወጣት ተርጓሚዎች በማደል ቶሎ “ለጥብስ” የማድረስ ሥራ ላይ ተሰማሩ። ስኬታ

ጹ ላይ “ከ17 ዓመት በታች የኾኑ ሰዎች እንዲያነቡት አልተፈቀደም” የሚል ማስገንዘብያ ቢኖረውም በልቅ የቋንቋ አጠቃቀሙ ከፍተኛ ውግዘት ገጥሞት ነበር። መጽሐፉ ከልማዳዊው የማኅበረሰቡ የወሲብ አመለካከት የሰማይ ያህል የራቁ፣ ያፈነገጡ እና የተቃረኑ የካዛንቺስ የሌሊት የወሲብ ገጠመኞችን በካዛንቺስኛ የቡና ቤታ ቋንቋ ይተርካል። በቶሎ ከገበያ እያለቀ አሁን 6ኛ ዕትሙ ላይ ደርሷል። አሳታሚዋ ስንዱ አበበ “የአገራችን ወጣት በኤድስ እየተቀጠፈ ያለው ግልጽነት በማጣቱ ነው” የሚል ይዘት ያለው የሞራል ማለዘቢያ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የጻፈችበት ቢኾንም ውዝግቡን ለማብረድ በቂ ማስተባበያ ኾኖ አልተገኘም። ውዝግብ ለመጽሐፍ ገበያ የማቀጣጠያ አንዱ ስልት መኾኑን የሚያውቁ የመጽሐፍ አከፋፋዮች ይህ

ባሳለፍነው ክረምት ለገበያ የቀረበው እና በጋዜጠኛ ሚልዮን ሹሩቤ የተጻፈው

“ወሲባዊ ውስልትና ዘ አዲስ አበባ” የተሰኘው መጽሐፍ የመጀመርያ ዕትም

በአከፋፋዮች ዘንድ ያለቀው ዐሥር ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር።a b

d c

Page 17: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 17

የሀገር ቤት ጨዋታ

የገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነኝ፡፡ መታወቂያዬ ላይ ከስሜ ትይዩ “ሌክቸረር” የሚል ማዕረግ አለበት፡፡ ኑሮ እና ሕይወቴ ግን

ማዕረግ አልባ ነው፡፡ ደሞዜ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ብር ይደርሳል፡፡ ይህ ብር ግርማ ሞገሱ አፍ ይሞላል፡፡ ሲኖሩበት ግን ወፍ ነው፤ ይበራል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድሮ የገቡትን ቃል እሳቸው ባያሟሉትም እኔ በራሴ ልወጣላቸው ብዬ በቀን ሦስቴ ያማረኝን ልብላ ብዬ በተውተረተርሁ ቁጥር ወር ሳይደርስ በዱቤ እጥለቀለቃለሁ። አስተማሪ ካልበላና ካላነበበ ራሱንም ትውልድንም ይገድላል፡፡ በርግጥ ማንበብ ከተውኩ ዘመን የለኝም፡፡ መብላት ግን መተው የማኢቻል ኾኖብኝ ይኼው አለሁ።በደሞዜ ላይ 160 ብር የቤት አበል ጠብ

ይደረግበታል፡፡ አንዲት አነስተኛ ክፍል ተከራይቼ፣ አነስተኛ ምግብ በልቼ፣ ጎረቤት ቲቪ እያየሁ እኖራለሁ፡፡ ለነገሩ የተከራየሁት ክፍል ብቻም ሳይኾን እውቀቴም አነስተኛ ነው፤ በግሌ ለዩነቨርሲቲ መምህርነት የሚያበቃ ዝግጅትም ኾነ ክምችት ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ትችላለህ ካለኝ ግን ምን አደርገዋለሁ፡፡ ለምን መንግሥትን “ዋሾ” አስብላለሁ፡፡ ትችላለህ ካለኝ እችላለሁ፡፡ እኔ ከመንግሥቴ በላይ ስለ’ኔ ካወቅኩ ቡዳ ነኝ ማለት ነው፡፡የገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ በመኾኔ

ብቻ ሰዎች ትልልቅ ጉዳዮችን ያማክሩኛል። እናቴ ሲያማት ሐኪም ቤት ሄዳ ላልተፈለገ ወጪ መዳረግ አትወድም፡፡ የተማረ ልጅ አለኝ እያለች ሰፈራችን አቅራቢያ በሚገኝ “ኪዮክስ” እየሄደች “ሚስኮል” ታደርግልኛለች፡፡ ለእርሷ እኔ ዶክተርም ጭምር ነኝ፡፡ እስካሁን ያልተገለጠላት ነገር ቢኖር ለምን በየወሩ ብዙ ብር እንደማልክላት ነው፡፡ ለምን ትልቅ ቤት እንደማልገዛላትም በደንብ አልገባትም፡፡ ግን ተስፋ ታደርጋለች፡፡ በእውነት እላችኋለሁ እንኳን ቤት ባለቆቡን ሚስማር ልገዛላት አልችልም፡፡ ለእማዬ ግን ይህን ማስረዳት ቅስሟን መስበር ነው፡፡አሁን አሁን ዩኒቨርሲቲ ማስተማሬን ተከ

ትሎ ሰዎች በተዘዋዋሪ በሚያሳዩኝ አክብሮት እጅግ እየተሰቃየሁኝ እገኛለሁ፡፡ ቢያንስ ክብሬን የሚስተካከል ብር ሊኖረኝ ይገባል ስል አስባለሁ፡፡ በዚህ ረገድ መንግሥትን ተቀይሜዋለሁ፡፡ ደመወዝ እጨምራለሁ እያለ ሲያወራና ሲያስወራ ይኸው ስንት ዘመኑ፡፡አብረውኝ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋራ

በትርፍ ሰዓታችን ስለ ደመወዝ ጭማሪ ማውራት አይታክተንም፡፡ ሁለት ዓመት ሙሉ እንዴት ሰው ስለደሞዝ ጭማሪ ብቻ ያወራል? ወሬውን ማን እንደፈጠረው አላውቅም፡፡ ሆኖም ከአጎራባች ዩኒቨርስቲዎች እንደተሰማ እገምታለሁ፡፡ ወይም ደግሞ ለማስተርስ ትምህርት አዲስ አበባ ሄደው የተመለሱ መምህራን ወሬውን ከዲግሪያቸው ጋራ ይዘውት መጥተው ሊኾን ይችላል የሚል መላምት አለ፡፡ምንም ይኹን ምን እንዴት ለሁለት ዓመ

ት ሰው አንድ ወሬ ያመነዥካል? ደመወዝ ጭማሪ፤ ደመወዝ ጭማሪ፣ ደመወዝ ጭማሪ. . .፡፡ አንድ ወቅት ሁላችንም ተሰላችተን ይህን ጉዳይ ላናነሳ ተማምለን ነበር፡፡ አዲስ የተቀጠረ አንድ “ጥላቢስ” የኾነ አስተማሪ “ጓደኛዬ ጋዜጣ ላይ ደመወዝ እንደሚጨመር አነበበ” ብሎ በማውራቱ የደመወዝ ወሬ በዩኒቨርሲቲው ዳግም አገረሸ፡፡ ጋዜጣውን አነበበ የተባለውን ልጅ ስልክ እንዲሰጠን ተማጸንነው፡፡ በጄ አላለም፡፡ “ላውድስፒከር” አድርጎ ራሱ ጓደኛውን እንዲያወራው ለመንነው፡፡ በሰበብ ላይ ሰበብ እያበዛ ነገ ዛሬ እያለ አሸን፡፡ በዚሁ ተናደን አገለልነው፡፡ ሲያንሰው ነው፤ በሰው ሕይወት ይቀልዳል እንዴ፡፡ ገጠር ውስጥ ማግለልን የመሰለ ቅጣት አይገኝም፡፡

ሐሳብ ተከሰተሰሞኑን ባልተለመደ ኹኔታ የምኖረው ኑ

ሮ እጅግ መረረኝ፤ አንገሸገሸኝ፡፡ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ ኾኖም እንደ ድንገት ድንቅ ሐሳብ ተከሰተልኝ፡፡ ዲቪ መሙላት፡፡ ቢንጎ!! ይህ ሐሳብ ለምን እስከዛሬ እንዳልተከሰተልኝ ገረመኝ፡፡ ያን ቀን ምሽት ደስ ብሎኝ አመሸሁ፡፡ ለመጀ

መርያ ጊዜ የገጠር ሕይወቴ በተስፋ ተሞላች፡፡ ሌሊቱን ደስ ደስ የሚሉ ህልሞችን አየሁ፡፡ በተከታታይ ያየኋቸው ህልሞች መቼታቸው ሁሉ በአሜሪካ ከተሞች ላይ ኾነ፡፡በነጋታው ጠዋት ስነቃ ግን ሞራሌና ወኔ

ዬ ከዳኝ፡፡ እንዴት ዲቪ እሞላለሁ፡፡ የት ሄጄ እሞላለሁ፡፡ ሰው ቢያየኝስ፡፡ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እንደ ተራ ሰው ዲቪ ይሞላል እንዴ!በመሠረቱ ዲቪ ከእኔ ስብእና ጋራ በፍፁ

ም አይሄድም፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ መለመንና የሰው መመኘት አልወድም፡፡ እናቴ እንጀራ ከጎረቤት ተበድረህ ይዘህ ና ስትለኝ እንኳ በጀ ብያት አላውቅም፡፡ ጦሜን ማደር እመርጣለሁ፡፡ ትምህርት ቤትም ቢኾን ላጲስ ተውሼ አላውቅም፡፡ የተሳሳትኩትን ጽሑፍ በምራቄ አክኬ ፈትጌ አጠፋለሁ፡፡ እከካም ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ግን እውነቱ ይኸው ነው፡፡ ሁለተኛ ክፍል አብረውኝ ይቀመጡ የነበሩ ልጆችን መቅረጫ ብያቸው አላውቅም፡፡ እርሳሴን ከግድግዳ ጋር እያፋጨሁ አሾላለሁ፤ እቀርጻለሁ፡፡አሁንም እከካም ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ግን እውነታው ይኸው ነው፡፡ዲቪ አገርህን ትተህ የሰው አገር አኑሩኝ

እያልክ የምትለማመጥበት ሕጋዊ ማመልከቻ ነው፡፡ ይህን ማመልከቻ ሞላሁ ማለት የአሜሪካ መንግሥትን ተንበርክኬ ውለታ ዋልልኝ እያልኩት ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ፍፁም ከኔ አፈጣጠር እና ስብዕና ጋራ አብሮ የሚሄድ አይደለም፡፡ የአሜሪካ መንግሥትን በማመልከቻ ከምለምን በእግር ወደ አሜሪካ ብሄድ ይቀለኛል፡፡ የዲቪ መሙላት ሐሳብ ውስጤ ላይ ከፍተኛ መናወጥን ሊያስከትል የቻለው በዚህ የተነሳ ነው፡፡ ራሴን የከዳሁት ያህል ተሰማኝ፡፡የተፈጠረብኝን ድብታና የስሜት መላሸ

ቅ ለማስታገስ የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ሄድኩኝ፡፡ የዲቪ ወሬን እንዴት ብዬ እንደማነሳባቸው እያውጠነጠንኩ፡፡ ቀድሜ ጉዳዩን እኔው ካነሳሁት “አጅሬው! ዲቪ ሞላሽ እንዴ” እያሉ ዓመቱን ሙሉ መዘባበቻ ሊያደርጉኝ ይችላሉ፡፡ በዘዴ ነገሩን ማንሳት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ዘወትር የምንጎለትበት ቦታ ደረስኩ፡፡ ሁሉንም እዚያው

ተሰብስበው አገኘኋቸው፡፡ ያው እንደተለመደው የደሞዝ ጭማሪን ጉዳይ እያመነዠኩ ነበር፡፡ ጋሽ ግርማ ወ/ጊየርጊስ በፓርላማ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ የደሞዝ ጭማሪ ጉዳይን አንስተዋል የሚል አዲስ መረጃ በመሰማቱ የሁሉም ፊት ፈካ ፈካ እንዳለ ለማስተዋል ቻልኩ፡፡ ኾኖም ጭማሪው ለዩነቨርሲቲ መምህራን ብቻ ሳይኾን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሠራተኛ መኾኑ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አንዳንድ ሂሳብ-ዘመም መምህራን ለጉባዔው ለማስረዳት ሞከሩ፡፡ በደስታችን ላይ ዉኃ ቸለሱበት፡፡ የደሞዝ ጭማሪው ወሬ እየበረደ ሲመጣ የዲቪውን ጉዳይ ለኮስ ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡“አናንተ! የዘንድሮ ተማሪዎች ደግሞ ጭ

ራሽ የእንግሊዝኛ ፊደል ሳይጨርሱ ነው እንዴ ዩኒቨርስቲ የላኳቸው?” አልኩ ድምፄን ጎላ አድርጌ፡፡ ቀጥል የሚል ምልክት ተሰጠኝ፡፡ አንዱ ስሙን ሲጽፍ አይቼው በጭራሽ “ቫውል” አይጠቀምም፤ ታምናላችሁ? ስሙ ተሻለ ነው፡፡ እንዴት “ስፔል” እንዳደረገ ታውቃለህ “ቲ፣ኤስ፣ኤች፣ኤል”፡፡ ባወራሁት ነገር ማንም አልተገረመም፡፡ ይልቁንም ሁሉም ከዚህ የባሰ የሚሉትን እያነሱ ማስረዳት ጀመሩ፡፡ አሁን ወደ ዲቪው ጉዳይ መግቢያ ሰዓት እንደኾነ ተሰማኝ፡፡ የ“ስፔሊንጓን” ወሬ ኾነ ብዬ እንጀመርኳት አልገባቸውም፡፡“ስሙኝማ! ከተማ ትናንት ተለጥፎ ያየሁ

ትን ልንገራችሁ፡፡ ዲቪ እንሞላለን የሚለው ጽሑፍ ላይ “Good Luck” የሚለውን ቃል እንዴት ጽፈውት ዐየሁ መሰላችሁ፣ “Good Lack”፡፡” ከገመትኩት በላይ ሳቁልኝ፡፡ ሳቃቸው እንደበረደ ከመሐላችን አንዱ “ዲቪ ተጀመረ እንዴ?” ሲል ጠየቀ፡፡ በቀጥታ ሊመልስለት የደፈረ ግን አልነበረም፡፡ ቀለል አድርገው፣ “እኔንጃ”፣ “መሰለኝ”፣ “ኸረ!”፣ “ይባላል” አሉ፤ የተወሰኑት፡፡አውቀው ነው፡፡ ሁሉም መቼ እንደተጀ

መረ አይደለም ስንት ሰዓት ላይ እንደተጀመረ ያውቃሉ፡፡ ዲቪ ሞላ ላለመባል ነው፡፡ ተነቃቅተናል፡፡

DV regardless of CVያለንባት ከተማ በኦባማ ፎቶዎች ከተጥ

ለቀለቀች ሁለት ሳምንታት አልፈዋታል፡፡ ዲቪ እንሞላለን የሚሉ ማስታወቂያዎች የትም ነው የተሰቀሉት፡፡ ከሁሉም የገረመኝ ግን ይህን ማስታወቂያ ዩኒቨርስቲያችን ውስጥ በትልቅ ባነር ተሰቅሎ ማየቴ ነው፡፡ የተማሪዎች ካውንስል በቅናሽ ዋጋ ዲቪ መሙላት በመጀመሩ የካፌ ሰልፍን የሚያስንቅ ረዣዥም ሰልፎች በዩኒቨርስቲው ተፈጥረዋል፡፡ ዲቪ ለመሙላት ረዥም ሰልፍ፡፡ ልክ አዲሳባ ኢሚግሬሽን ጠዋት ጠዋት አየው የነበረውን ሰልፍ አስታወሰኝ፡፡ ይህን ያየሁ ቀን ከፍተኛ ድንጋጤም ከፍተኛ ግርምትም ተፈጠረብኝ፡፡

ነገሩ ስላስደነቀኝ ተጨማሪ ነገር ለማግኘት በዩኒቨርስቲው ግቢ መዘዋወር ጀመርኩ፡፡ የዲቪ ማስታወቂያዎች በተማሪዎች ካፌ፣ በመማርያ ክፍሎች ደጅ ባሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ በቤተ መጻሕፍቱ በር ላይ ወዘተ ተለጣጥፎ አየሁ፡፡ የማስታወቂያው ይዘት ተማሪዎች ዕድሉ እንዳያመልጣቸው እና እንዲጠቀሙበት የሚያባብል ነው፡፡ የተማሪዎች ካውንስል ነው ይህንን የሚስተባብረው፡፡ በኔ ጊዜ የነበረው የተማሪዎች ካውንስል የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ ያስተባብር እንደነበር ትዝ አለኝ፡፡ወደራሴ ጉዳይ ተመለስኩ፡፡ በእርግጥ አ

ሳፋሪ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሳያውቅ ዲቪ መሙላት አለብኝ፡፡ እንዴት? በትንሽ ከተማ ውስጥ እንኳን እኔ ያለሰፈሯ የመጣች ዝንብ እንኳ ትታወቃለች፡፡ ለማንኛውም አማራጮችን ለማየት ከዩኒቨርሲቲው ወደ መሀል ከተማ የሚወስድ ታክሲ ለመያዝ ተንቀሳቀስኩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዋና በር ላይ ታክሲው እስኪሞላ ብዙ ነገር ለመታዘብ ቻልኩ፡፡ ቀድሞ የተማሪ “ሃንድአውት” በማባዛት ይጠመዱ የነበሩ ፎቶኮፒ ቤቶች መስኮቶቻቸው በዲቪ ማስታወቂያ አሸብርቋል፡፡ እዚህም ዲቪ ለመሙላት ብዙ ተማሪዎች ተሰልፈዋል፡፡ በእጆቻቸው የሚባዙ ሃንድ አውቶች ሳይኾን የዲቪ ፎርሞችን ነበር የያዙት፡፡ከተማ ደርሼ ከታክሲው እንደወርድኩ

ወደ አንድ ኢንተርኔት ካፌ ጎራ አልኩኝ፡፡ ከተደረደሩት ኮምፒውተሮች ወደ አንዱ ጠጋ ብዬ ኢንተርኔት የምበረብር መስዬ የቤቱን ደንበኞች መበርበር ጀመርኩ፡፡ ሰዎች ነጭ አቡጀዲ እየተደገፉ በወረፋ ፎቶ “ቀጭ” ይደረጋሉ፡፡ ብዙ ወጣቶች፣ ጥቂት ጎልማሶች፣ ጥቂት ትልልቅ ሰዎች፣ ባልና ሚስት፣ ባል ሚስት እና ሰባት ልጆቻቸው፣ ጋዝ ልትገዛ የተላከች የቤት ሰራተኛ፣ መካኒክ ከነሽርጡ፣ ያስተማርኳቸው ተማሪዎች ወዘተ፣ ቤቱ የማያስተናግደው ዐይነት ሰው የለም፡፡ ሁሉም ለዲቪ የጭንቅ አማላጇን ስም ይጠራል፡፡ ይህ ሕዝብ አገሪቱን አይፈልጋትም እንዴ፡፡ ለምን አንድነቱን በግልፅ ጨረታ ሽጧት አይሄድም?

በዚህ ኢንተርኔት ቤት ጠረጴዛ ላይ ዲቪ የተሞላበት ወረቀት ተከምሯል፡፡ በአመቱ መጨረሻ የማርማቸውን የተማሪዎቼን ፈተና ወረቀቶች አስታወሰኝ፡፡ ለነገሩ የዚህን ዘመን ተማሪዎች ፈተና ከማረም የሰሊጥ እርሻ ማረም ይሻላል፡፡ ወይም ደግሞ ይህንን የዲቪ ክምር ማረም ሳይሻል አይቀርም፡፡ ሁለቱም ‹‹ስቤሊንግ›› ማረም ስለሆነ ብዙም አይራራቁም፡፡ የአሜሪካ መንግስት ዲቪ አራሚ አድርጎ ቢቀጥረኝስ ብዬ አሰብኩ፤ ለአፍታ፡፡ ሐሳቤ በራሱ ፈገግ አሰኘኝ፡፡ አይ አሜሪካ ስላንቺ ማሰብ በራሱ ፈገግታን ይፈጥራል ለካ፡፡በዚህ ኢንተርኔት ካፌ ብዙ ሰው ዲቪ ለ

መሙላት የሚሽቀዳደመው ከዚህ ቀደም በዚህ ቤት ዲቪ የሞሉ አራት የከተማዋ ነዋሪዎች ዲቪ ደርሷቸዋል በመባሉ ነው፡፡ ገድ አለው ይባላል ይህ ቤት፡፡ወደራሴ ጉዳይ ልመለስ፡፡ ዘንድሮ እንዴ

ትም ብዬ ዲቪ መሙላት እንዳለብኝ የተነጋገርን መሰለኝ፡፡ ስለዚህ እዚሁ ገድ አለው የሚባልለት ቤት ለምን አልሞላም፡፡ የማስተምራቸው ልጆችና የሚያውቀኝ ሰው በቤቱ አንደሌለ ሳረጋግጥ ፎቶ የምታነሳዋን ልጅ ዲቪ መሙላት ፈልጌ እንደመጣሁ ነገርኳት፤ የሞት ሞቴን፤ በሹክሹክታ፡፡“ይቻላል፣ አስር ብር ከፍለህ ፎቶ ትነሳ

ና ይህን ፎርም ሞልተህ ነገ ማረጋገጫ እንሰጥኻለን፡፡” አለችኝ ጮኽ ብላ፡፡አሳቀቀችኝ፤ምን አለ እኔ እንደማወራው ቀስ ብላ ብታወራ፡፡ ተማሪዎቼ እንዲሰሙ ነው? ምቀኛ!እንደተረዳሁት ከሆነ የኢንተርኔት ፍጥነ

ቱ ቀን ቀን ቀርፋፋ ስለሆነ ኢንተርኔት ቤቶቹ ዲቪ ፎርሙን በወረቀት ብቻ እያስሞሉ ሌሊት ሌሊት በኢንተርኔት ይልኩታል፡፡ በነጭ ወረቀት ለሞሉት ሰዎች በነጋታው የማረጋገጫ ደብዳቤ ይታደላቸዋል፡፡ በዚህ መሀል የስም ስህተት ቢከሰት ግን ማን ተጠያቂ እንደሚሆን አልገባኝም፡፡ እድሌን ማበላሸት የለብኝም፡፡ “እመለሳለሁ” አልኩና ሹልክ ብዬ ወጣሁ፡፡በከተማዋ ያሉ ሁሉም ኢንተርኔት ቤቶች

ደንበኞቹ እያዩ ዲቪ እንደማይልኩ ተረዳሁ፡፡ ይህ መልካም ነገር አይደለም፡፡ ስለዚህ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝ፡፡ በከተማዋ ወደሚገኘው አንድዬ ፖስታ ቤት አመራሁ፡፡ በሩ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅና ፀብ የሚመስል ግርግር አየሁ፡፡ በቅርቤ ያገኘኃትን የገጠር ልጅ ስለጉዳዩ ጠየቅኳት፡፡ ዲቪ ለመሙላት ጠዋት ወረፋ የያዙ ሰዎች ጎረምሶች ያለወረፋቸው እየገቡ አስቸግረዋቸው ረብሻ እንደተፈጠረ ነገረችኝ፡፡ የፖስታ ቤቱ ሰራተኞች ደግሞ በስነስርዓት ወረፋ ካልተያዘ አናስተናግድም ብለው ማመፃቸውን ጨምራ አብራራችልኝ፡፡ፖስታ ቤት በር ላይ ያሉትን ማስታወቅ

ያዎች ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ዲቪ ዘንድሮ ለአንድ ወር ብቻ እንደሚቆይ፣ የቀሩት ቀናት ጥቂት እንደሆኑ፣ ዲቪ በፖስታ ቤት መሙላት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት፣ ለምሳሌ ዲቪው ሲመጣ የስም ስህተት ቢኖረው ፖስታ ቤት ለአሜሪካ ኤምባሲ ቀጭን ደብዳቤ የመፃፍ ብቸኛ ባለመብት እንደሆነ ወዘተ ይናዘዛል፡፡ፖስታ ቤት መንግስታዊ ድርጅት ነው፡፡ ዜጎቹን በተዘዋዋሪ ሌላ አገር እንዲሄዱ ተግቶ እየሰራ እንደሆነ ነቃሁበት፡፡ለነገሩ እኔ ብቻ ሳልሆን የመንግስት ባለስ

ልጣናትም ዲቪ ይሞላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ዲቪ ደርሷቸው ቀስ ብለው ሊሄዱ ሲሉ አይደል እንዴ የተደረሰባቸው፡፡ እኔ የምሰራበት ዩኒቨርሲቲ የ‹‹ሪሰርች›› ፕሬዝዳንትም ሰሞኑን ዲቪ ሲሞሉ እንደታዩ በወሬ ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ ሰውየው እድሜያቸው ገፍቷል እኮ፡፡በዚያ ላይ አሜሪካ ነው የተማሩት ሲባል ነበር፡፡ ተንቀዥቅዠው መጥተው ነው ጉድ የሆኑት ማለት ነው፡፡ ዲቪ ሲቪ እንደማይመርጥ ተረዳሁ፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዲቪ መሙላት ይፈልጋል፡፡ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሚባለው ውስጥ ደግሞ እኔ እገኛለሁ፡፡ ስለዚህ ዲቪ እሞላለሁ፡፡ ቅድም ወደነበርኩነት ኢንተርኔት ካፌ ሄድኩኝ፡፡ ፈገግ ብዬ ፎቶ ተነሳሁ፡፡ኮስተር ብዬ ፎርሙን ሞላሁ፡፡ ከኢንተርኔት ቤቱ ስወጣ ከሸሌ ጋር ያደርኩ ያህል ቀፋፊ ስሜት ተሰማኝ፡፡ አገሬ ኢትዮጵያ ሆይ አንቺም ዲቪ ሞልተሸ ብትሄጂ ይሻልሻል አልኩ በሆዴ፡፡

ዲቪ እና ሲቪ

በገጠራማይቱ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ፍጥነት ቀን ቀን ቀርፋፋ ስለሆነ ኢንተርኔት ቤቶቹ ዲቪ ፎርሙን በወረቀት ብቻ እያስሞሉ ሌሊት ሌሊት በኢንተርኔት ይልኩታል

(ፎቶ

- ፍ

ሊከር

)እንደ ላሊበላ ባሉ ገጠራማ ቦታዎች ከጎጆዎች አጠገብ ዳሳሳ ኢንተርኔት ካፌዎችን መመልከት

እንግዳ መሆኑ ቀርቷል

ፎቶ

- ሪቻ

ርድ ሁ

ባታካ

በዲቪ ሰሞን ወደ ኢንተርኔት ካፌ ጎራ ያለ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዲቪ ለመሙላት ተገጥግጦ ይመለከታል

<<< ወደ 14 ሚሊዩን የሚጠጋ

ህዝብ ይህንን ካርድ ለማግኘት እ.ኤ.አ በ2010

የዲቪ ማመልከቻ ሞልቷል

ፎቶ

-አፍ

ሪካ ኒ

ውስ

አሮን ፀሐዬ- አዲስ ነገር ኦንላይን

ፎቶ

- ሆ

ቦ ት

ራቭ

ለር

7%ከአንድ ሀገር የሚመረጡ የዲቪ ዕድለኞች ቁጥራቸው ከአጠቃላይ አሸናፊዎች ከሰባት በመቶ በላይ እንዳይበልጥ ገደብ ይጣልበታል

ዲቪ በቁጥር 7.67 ሚሊዮን

ባንግላዴሻውያን ዲቪ ሎተሪን በመሙላት እ.ኤ.አ በ2010 የመሪነት ደረጃውን ተቆጣጥረዋል

58,0000ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ በ2010 ዲቪ ሞልተዋል። ግማሽ ሚሊዮን የደረሰው የኢትዮጵያውያን አመልካቾች ቁጥር ከዓለም በአራተኛነት ተመዝግቧል።

8,752ጋናውያን እ.ኤ.አ በ2010 ዲቪን በማሸነፍ ከዓለም አንደኛ ሲሆኑ ጎረቤታቸው ናይጄሪያውያን በሁለተኛነት ተከትለዋቸዋል።

50,000ዕድለኞች ብቻ ናቸው በዓመት ዲቪ ሎተሪን ማሸነፍ የሚችሉት

ምንጭ፦ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ስቴት ዲፓርትመንት፣

Page 18: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)18 ሀበሻዊ ቃና

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካውያን ዓይን

እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው አድርጎ ፈጠረው የሚለው ቃል በሰዎች መካከል ያሉ ተመሳሳይነቶችን እና ልዩነቶችን እስክንመለከት ድረስ እንደ አፈ ታሪክ የሚቆጠር ነበር። ዓለማችን ቁጥራቸው የበዛ ጎሳዎች የሚርመሰመሱባት፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም እና ሃይማኖት ባላቸው ሰዎች የተሞላች ነች። ስለ እነዚህ ሰዎች ግን አብራችሁ መኖር እስክትጀምሩ ድረስ የምታውቁት ነገር ጥቂት ብቻ ነው። ባለፉት ዓመታት ዩጋንዳ የስደተኞች መናኸሪያ በመኾን አገልግላለች። ከታላላቅ ሐይቆች አካባቢ የሚመጡ ስደተኞችንም አስተናግዳለች። የኢትዮጵያውያን በኡጋንዳ መገኘት ግን ሁሌም ተፈላጊ ነው።

ማህበራዊ ህይወት ኢትዮጵያዊ ጓደኛዬ ስለ አገሬ እንዲህ አለኝ “ዩጋን

ዳ በዓለም ላይ ካሉ አገሮች ነጻነት የተሞላባት አገር ናት።” ይህን ሲነግረኝ ከፊቱ ላይ ምቾት እና መፍለ

ቅለቅ ይነበብበት ነበር። በዚህ የተጀመረው ጓደኝነታችን እየጠነከረ መጥቶ እንዲህ ነው ብዬ ልኩን ከምገልጸው በላይ እየፈካ መጥቷል። ወዳጅነታችን እና ዝምድናችን ከቤተሰብ የሚመዘዝ ሳይኾን ከመግባባት የመነጨ ነው። ከኢትዮጵያውያን ጋራ ይህን የመሰለ ጓደኝነት እን

ዳለኝ ስገልጽ ጥሩ ማሕበራዊ ግንኙነት የሚኖረኝ ይመስላችኹ ይኾናል። ኢትዮጵያውያን የሚያደርሱትን መገለል ያልቀመሰ ነው ይህን ሊል የሚችለው። የትም ቦታ በግልጽ እንደሚታየው ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውን ማሳለፍ የሚፈልጉት ከራሳቸው ሰው ጋራ ብቻ ነው። ያኔ ነው ለስላሳ እና ረጋ ያሉ ናቸው ብዬ ከምገምታቸው ኢትዮጵያውያን ጀርባ ሌላ እውነታ እንዳለ የተረዳኹት። ማሕበራዊ ቅርበቱ ወደ ሴቶቹ ሲመጣ ይበልጥ እያ

ራቀ ይሄዳል። ከምዕራብ ዩጋንዳ የመጣው እና ሙሱዙንጊ የተሰኘው ጓደኛዬ ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ያለውን ላካፍላችሁ። “ኢትዮጵያዊ የሴት ጓደኛ ማግኘት ከአለት ውሃ እንደመጭመቅ ነው” ነበር ያለው። ሴቶቹ ለምን እንደዚያ እንደኾኑ ደግሞ ምክንያቱን ያውቀዋል። “ሴቶቹ ከባህላቸው ጋራ እጅጉን የተጣበቁ ናቸው” ይላል። በዩጋንዳ ማንኛውም ሰው የፍቅር ግንኙነት መመሥረት ይችላል። ቀለም እና ጎሳ እንቅፋት አይደሉም። ለዚህም ነው ዩጋንዳዊ ወንዶች ከኢትዮጵያ ሴቶች ጋራ ከሚኖራቸው ግንኙነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ ወንዶች ከዩጋንዳ ሴቶች ጋራ በቀላሉ ግንኙነት የሚመሠርቱት። እንዲህም ኾኖ ዩጋንዳውያን በ“ለስላሳዎቹ” ኢትዮጵያዊ ሴቶች ከመማረክ ወደ ኋላ አላሉም። ወደ ሰላምታ አሰጣጣቸው ልሻገር። ወንዶቹ እጅ

ለእጅ ይጨባበጡና ትከሻቸውን ያጋጫሉ። ጠንካራ ወዳጅነታቸውን የሚያሳየው ይኼ የሰላምታ አሰጣጥ በሴቶቻቸው ላይም ይንጸባረቃል። ሴቶቹ ይተቃቀፉና ጉንጫቸውን በስሱ ይሳሳማሉ። ይህ ሰላምታቸው በከተሞች አካባቢ ለሚኖሩ ዩጋንዳውያን እንግዳ ነገር አይደለም። ከከተሞች ውጭ ግን ያልተለመደ ነው። እንዲያውም በሁሉም የዩጋንዳ ባ

ህል ማለት ይቻላል ከተቃራኒ ጾታ ወይም ከአማት ጋራ የሚደረግ የሰውነት ንክኪ ወይም መተቃቀፍ ነውር ነው። ቀለል አሊያም ጠበቅ ያለ የእጅ መጨባበጥ ለተራዎቹ ዩጋንዳውያን ሴቶች እና ወንዶች (በገጠር ለሚኖሩት ጭምር) ተቀባይነት ያለው ነው።

ቁንጅና አካላዊ ውበትን አደንቃለሁ። በተደላደለ የፍቅር

ግንኙነት ውስጥ እንዳለ ሰው አካላዊ ውበት ብቻውን ትርጉም እንደማይኖረው አውቃለሁ። ውስጣዊ ውበትም አስፈላጊ ነውና። በኢትዮጵያዊ ሴቶች ላይ በአብዛኛው የሚታዩ የውበት ቅንጣቶች ግለጽ ብባል ጸዳል ያለው ፈካ ያለ የቆዳ ቀለማቸውን፣ ጥቁር ዞማ ጸጉራቸውን፣ ለስላሳ እና ቀጠን ያለ ተክለ ቁመናቸውን እጠቅሳለሁ። እነዚህ የአካላዊ ውበት መገለጫዎች ናቸው የዩጋንዳ ወንዶችን በኢትዮጵያዊ ሴ

ቶች እንዲማረኩ የሚያደርጋቸው። ከልጅነታቸው ጀምሮ እየተንከባከቡ የሚያቆዩት ጸጉራቸውም ለቋሚ ውበታቸው ሌላው መገለጫ ነው። በሰብዕና ደረጃ ከመዝንናቸው ደግሞ ኢትዮጵያውያን እንስቶች በራስ መተማመናቸው ከፍ ያለ፣ ተፈቃሪ እና በራሳቸው የሚቆሙ ናቸው።

ዓመት በዓሎች ኢትዮጵያውያን ጓደኞቼ እ.ኤ.አ መስከረም 12 ቀን

2011 የዘመን መለወጫ በዐላቸውን ያከብራሉ። በእነርሱ ዓመተ ምህረቱ 2004 ይኾናል። ይህ ለዩጋንዳውያን እንግዳ እና አስገራሚ ነው። የዘመን አቆጣጠራቸው በሰባት ዓመት ከስምንት ወር የዘገየ ነው። ለዩጋንዳውያን አዲስ ዓመት ማለት በየ12 ወራቱ ልዩነት የሚመጣ እና ማንም የሚያወቀው ነገር ነው። ያው በዓመቱ የመጀመሪያ ወር በኾነው ጥር፣ የመጀመሪያ ቀን የሚከበር ነው። ርችት፣ ሙዚቃ፣ እንደ ውሃ የሚፈሰው መጠጥ፣ ጭፈራ እና ግርግር በበዐሉ ኹነኛ ስፍራ ይሰጣቸዋል። ዘመን መለወጫን እንዲህ ለሚያከብሩት ዩጋንዳውያን በመስከረም ላይ ሰዎች ተሰብስበው አዲስ አመት እንደሚያከብሩ ሲሰሙ የማይታመን ይኾንባቸዋል።

ምግብ እና መጠጥ አንድ ዩጋንዳዊ ቤተሰብ ወደ ቤቱ ለመጣ እንግዳ

ምግብ አዘጋጅቶ የሚያቀርበው በቀላሉ ነው። ምግቡም “ማቶኬ” ወይም “ካሎ” ሊኾን ይችላል። ካሎን ለማታውቁ ከካሳቫ ወይም ከዳጉሳ ዱቄት የሚሠራ ምግብ ነው። ይህን ምግብ ግን ለኢትዮጵያዊ እንግዳችሁ ብታቀርቡለት ንክች አያደርገውም። የቀረበለትን የሚቀምስም ካለ ምናልባት ከምግቡ ጋር አብሮ የሚቀርበውን “ቻፓቲ” ወይም “ሾርባ” ለካክፎ ሊተወው ይችላል። አለበለዚያ ግን ባዶ ሆዳቸውን መሄድ ይመርጣሉ። በተቃራኒው ግን የእነርሱን “እንጀራ” እንድትቀምሱ የተቻላቸውን ጥረት ሁሉ ያደርጋሉ። በቀላሉ ሊግባቡ በሚችሉ ማሕበረሰቦች ውስጥ ያለ ትንሽ አለመግበባት ማለት ይኼ ነው።

ምነት አለኝ፡፡ ከምንም በላይ መታመንን በጣም እፈልገዋለሁ፡፡በመታመኔም እዚህ ደርሻለሁ፡፡ሰዎች በስም አውቀው ብቻ እቃ በዱቤ ይሰጡኛል፡፡ ያንን እቃ ሸጬ እመልሳለሁ፡፡ በዚህ በኩል በተለይ እዚህ ደረጃ እንድደርስ በጣም የረዳኝ አሁን ካናዳ የሚገኝ አቶ ቹቹ የሚባል ሰው አለ፡፡ እቃዎችን በሙሉ በዱቤ ሰጥቶኝ ሸጬ እመልሳለሁ፡፡ በዚያ ላይ በጣም በብዙ ሚሊየኖች ነው የማንቀሳቅሰው፡፡ አቶ ንጉሴ የሚባልም እንዲሁ ቀይ ልሁን ጥቁር ሳያውቀኝ ለሁለት ዓመት ያክል በስልክ ብቻ እየተገናኘን በዱቤ እቃዎችን ይሰጠኝ ነበር፡፡ እንዲሁም አቶ ይደግ ከናይሮቢ እዚህ ደረጃ እንድደርስ ብሎም ለህይወቴ ከፍተኛ እገዛ አድርገውልኛል፡፡እናም እምነትን በጣም እወደዋለሁ፡፡ መታመንን እግዚአብሔር የሰጠኝ ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ ለወደፊቱም እንዳይቀይርብኝ ምፈልገው እምነትን ነው፡፡ እምነት ካለ ሁሉም ነገር አለ፡፡ መታመን በእግዚአብሔር፡መታመን በራስ፡ መታመን በሰዎች ዘንድ ካለ ሁሉ ነገር አለ፡፡አሁን በህይወቴ ከሚገባው በላይ ደስተኛ ነኝ፡፡ሐበሻዊ ቃና፡ ያኔ የቤት ኪራይ እንኳ

ን ለመክፈል እስከመቸገር የደርሰችው ፍቅርተ እዚህ ትደርሳለች ብለሽ ታስቢ ነበር?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- የቤት ኪራይን ተወ

ው፡፡ የምትበላው እንኳን …የሰው ቤት ድረስ የተቀጠርኩት እኮ ለዚያ ነው፡፡ ግን ደግሞ ትልቁ ነገር ስራን አለመናቅ ነው፡፡ እሰታውሳለሁ በቤተክርስቲያን ስርዓት ከገባሁት ባለቤቴ ጋር አንድ ቀን አብረን አላደርንም፡፡አላውቅም የሞራል መውደቅ ነበር፡፡ የአእምሮ መነካት ነበር፡፡የበታችነት ስሜት ነበር፡፡ በተለይ በሴት ልጅ ላይ እንዲህ አይነት ነገር ሲፈጸም ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው፡፡ከዚያ በኋላ ሰው ሱቅ ሁሉ መጥቶ አንች ነሽ ፍቅርተ ይሉኛል አዎ እላቸዋለሁ አንች ነበርሽ የየከሌ ሚስት… በቃ እንደዚህ፡፡ይህ ሁሉ ግን

በውስጤ ጠንካራ እንድሆን አደረገኝ፡፡አንድ ጊዜ አስታውሳለሁ እንደዚህ አይነት ቤት ስራ ተቀጠርኩ ስለው እዚያ ቤት መሄድ አቆመ፡፡ ከዚያ ምነው ሲሉት እሷ ሰራተኛ የገባችበት ቤት እንዴት እሰደባለሁ ይል ነበር፡፡ ያ ነገር የበለጠ እንድተጋና የስራ ክቡርነትን ፤ የሴትነትን ጠንካራ እንዳሳይ አደረገኝ፡፡እኔ ስራ አለመናቄ ለእሱ ውርደት ከሆነበት እኔ ደግሞ በስራየ እቀጥላለሁ አልኩ፡፡ይህ ውሳኔየ ዛሬ ትልቅ ቦታ እንድደረስ አደረገኝ፡፡ የእኔና የባለቤቴ ግንኑነትም ያኔ አበቃ፡፡ ሰዎች ለምን ያገኛችሁትን እየበላችሁ አንድ ላይ አትኖሩም ሲሉት እንዴት የቤት ኪራይ እየከፈልኩ እሷን አስተዳድራለሁ ይል ነበር፡፡ ያ ነገር የሩቅ ቢመስልም ለእኔ የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ሁሌም ጆሮየ ውስጥ ያቃጭላል፡፡ የተጣለች ሴት ነበርኩ፡፡ በዚያ ወቅት እነ ማሜ(የኢትዮጵያ መንደር ምግቤት ባለቤት)ና ሌሎችም አይዞሽ በርቺ ይሉኝ ነበር፡፡ ሰው በሞራል እየመጣ እቃ ይገዛኛል፡፡ስለሁሉም ነገር

እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ሐበሻዊ ቃና፡ በሰው ሀገር ስኬታማ መ

ሆን ቀላል ነው ትያለሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- በጣም ከባድ ነገር አ

ለው፡፡ ለምሳሌ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ይደውሉና እቃው መጥቷል አራግፊ እባላለሁ፡፡የሚቀጥሩኝ ደግሞ መሀል ከተማ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚያ ላይ ሰው የለኝም፡፡ ብቸኛ ነበርኩ፡፡ መኪናው ላይ ወጥቼ እቃውን አራግፋለሁ፡፡ ምክንያቱም ካልተራገፈ በፖሊስ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ብዙ ብዙ ችግር አለው፡፡ ሱቅ ውስጥ ተቀምጦ መሸጥማ በጣም ቀላሉ ነገር ነው፡፡አንዳንዴ እንቅልፍ ከማጣቴ የተነሳ ጧት ስነሳ ሰው ጉም መስሎ ይታየኛል፡፡ከዚያ በኋላ ግን ቀስ በቀስ የተወሰነውን ስራ ለሌሎችም ማጋራት ጀመርኩ፡፡ ምክንያቱም እኔ ሳገኝ ለሌላውም ማሰብ ስላለብኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ ስራው ከባድ ነው፡፡ ግን ተስፋ ካለቆረጡና ጠንክረው ከሰሩ ውጤታማ መሆን ይቻላል፡፡ ጠንካራ ሴት ደስ ትለኛለች፡፡ እኔም

ሁሌም ስራየን ማየት ስለስራየ ማሰብ ያረካኛል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ሱቅ እየመጡ ፍቅርተን ፈልገን ነበር ይሉኛል፡፡ እኔ ነኝ ፍቅርተ አልመስልም እንዴ እላቸዋለሁ፡፡ እንግዲህ እነሱ ሚጠብቁት ዘናጭ ፍቅርተን ይሆናል፡፡ እኔ ደግሞ ዝም ብየ ድብልብል ያልኩ ነገር(ረጅም ሳቅ…)ሐበሻዊ ቃና፡ በትንሽ ገንዘብ ስራ መጀ

መርም ሆነ ስኬታማ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ቢያማክሩሽ ምን ትያቸዋለሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- የራስ ተነሳሽነት መኖ

ር አለበት፡፡ እኔ ጋር ብዙ ሰዎች ይመጣሉ፡፡ ምን እንስራ ይሉኛል፡፡አንዳንዴ ደርሰህ እንዲህ ስሩ ማለት ይከብዳል፡፡ በራሳቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት የተመሰረተ ከሆነ ግን ውጤት ያስገኛል፡፡እንዲህም ሆኖ ያልተሰሩ ብዙ ነገሮች ስላሉ እነሱን እንዲሞክሩ እመክራቸዋለሁ፡፡አዲስ ስራ ሲሆን ትሰራበታለህ ታገኝበታለህ ብዙ ነገርም ትማርበታለህ፡፡ ብዙ ገንዘብ ስለበዛ ስላልበዛ አይደለም፡፡ ቅድም ታማኝነት ብ

የሃለሁ፡፡መታመን ከቻልክ ብዙውን ነገር በዱቤ ማንቀሳቀስ ትችላለህ፡፡ለምሳሌ እኔም እስከአሁን ይህንኑ እጠቀማለሁ፡፡ እቀበላላሁ፡፡ እሸጣለሁ፡፡ እመልሳለሁ፡፡እኔ ሃሳቡን አካፍያቸው ከእኔም በብዙ ሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ በዱቤ የሚወስዱ ብዙ አሉ፡፡ለምሳሌ ደቡብ ሱዳን በብዛት እልካለሁ ግን አንዳንድ ጊዜ ከሚመጣው የሚቀረው ይበልጣል ፡፡ ስለዚህ መታመን ወሳኝነት አለው፡፡ ሐበሻዊ ቃና፡ ማህበራዊ ህይትሽ ምን

ይመስላል?ወይዘሮ ፍቅርተ፡-ማህበራዊ ህይወቴ ቆን

ጆ ነው፡፡ እሁድ እለት የታመመ የወለደ ካለ እጠይቃለሁ፡፡ የሞተ ካለ ለቅሶ እደርሳለሁ፡፡ ካልቻልኩ ደግሞ በስልክ ይቅርታ ስጠይቃቸው ፍቅርተ በአንቺ ማን ቂም ይይዛል ይሉኛል፡፡እኔ ለህዝቡ ሳይሆን ህዝቡ ለእኔ ነው፡፡ እኔም የካምፓላን ህዝብ በፍቅር ነው ምወደው፡፡እቃ እንኳን ገዝተው ካልተስማማቸው መልሱት እላቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ገንዘቡን እንዴት እንደሚመጡት ስለማውቅ እቃ በሚጨምርበት ሰዓት ስቅቅ እላለሁ፡፡ ነጋዴ ብሆንም ከህዝቡ ውስጥ እኔ አለሁ፡፡ከህዝቡ ልወጣ አልችልም፡፡ ከሰው ጋር መግባባት አይዞሽ በርቺ በር

ታ መባባል ለእኔ ርካታ ይሰጠኛል፡፡ ከህይወቴ የተማርኩት ነገር ቢኖር በተለይ አንድ ሰው በተከፋ ሰዓት እነዚህ ቃላት እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን ነው፡፡ሰዎች እኔ ጋር ሲመጡ የምላቸውም ይህንኑ ነው፡፡ አይዟችሁ በርቱ እጅ አትስጡ፡፡ እኔም ቢሆን አገኘሁ ብየ አልኩራራም፡፡ ብዙ ጊዜ የምሄደው በእግሬ ወይም በቦዳ ነው ስለሆነ አንዳንድ ሰዎች ሲያገኙኝ “ፍቅርተ ዘንድሮም በእግርሽ” ይሉኛል:: ለአለባበስ ለራስና ለመሳሰሉት ከመጨነቅ ይልቅ ብዙ ጊዜ ሀሳቤንና ጊዜየን ስራ ላይ ባጠፋ እመርጣለሁ፡፡ይሄ ሞላ ይህች ጎደለች ሩጫየ እዚያ ላይ ነው፡፡ ልጆቼ የምላቸው መደርደሪያዎቼ በልተው እንዲያድሩ ማድረግ፡፡ሐበሻዊ ቃና፡-ቅድም ስናወራ ስነጽሁ

ፍ እንደተማርሽ ነግረሽኝ ነበር፡፡ እስኪ

ስለእርሱ አጫውችንወይዘሮ ፍቅርተ፡- አዎ አራት ኪሎ ከእነ

ሽመልስ አበራ ጆሮ፤ከእነ አልማዝ ልመንህ፤መሰረት በቀለ፡ ስመኝ ግዛው ከሚባሉ የስነጽሁፍ ሰዎች ጋር የአንድ ክፍል ተማሪዎች ነበርን፡፡ አሁን የደራሲያን ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ጌታቸው በለጠ፤ ደራሲና ገጣሚ ፀሀይ መላኩ ደግሞ መምህሮቼ ነበሩ፡፡እነሱ በሙያው ሲቀጥሉ እኔ ይሄውልህ እሱን ትቼ ወደ ንግዱ አለም ገባሁ፡፡ሐበሻዊ ቃና: ለየትኛው የስነጽሁፍ ዘ

ርፍ ታደያለሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ግጥም እጽፋለሁ፡፡ ግ

ጥሞች አሉኝ ሌሎች ጽሁፎችም አልፎ አልፎ እጽፋለሁ፡፡ሐበሻዊ ቃና: የእረፍት ጊዜ ሲኖርሽ

ምን ታደርጊያለሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ማታ ቤት ስገባ ዜና እ

ከታተላለሁ፡፡ ማንኛውም ዜና ለእኔ ጠቃሚ ነው፡፡ መጀመሪያ የዚህን ሀገር(ኡጋንዳን) ዜና አያለሁ ከዚያ ደግሞ የኢትዮጵያን ዜና እከታተላለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ከቻልኩ አነባለሁ ካቻለኩ እተኛለሁ፡፡አብዛኛውን ጊዜ ግን ሱቅ ቁጭ ስል መጽሄቶች አነባለሁ፡፡ሐበሻወዊ ቃና፡ካነበብሻቸው መጽሃፍ

ት የምታስታውሽው ይኖራል?ወይዘሮ ፍቅርተ፡-አዎ የፀሀይ መላኩ ቋሳ

ና የበዓሉ ግርማ ከአድማስ ባሻገር፡፡ በተለይ ከአድማስ ባሻገር ውስጥ ‹‹ከሚያነቡ ጭንቅላቶች የሚሰሩ እጆች ደስ ይሉኛል›› የሚለው አባባል ከእኔ ህይወት ጋር የሚሄድ ይመስለኛል፡፡ሐበሻዊ ቃና፡ የስደተኛ ህይወትን እን

ዴት ትገልጭዋለሽ?ወይዘሮ ፍቅርተ፡-በጣም ከሚያሳዝነኝ ነ

ገር አንዱ የስደተኛ ህይወት ነው፡፡ አሳዛኝም አለ፡፡ አስደሳችም አለ፡፡መካከለኛም አለ፡፡ የተለያየ ነው፡፡ በዋናነት ግን በሁለት የተከፈለ ነው ከተማ ያለውና ካምፕ ውስጥ ያለው፡፡ እዚህ(ከተማ ውስጥ)ካለው ስደት ግን ካምፕ ውስጥ ያለው ስደት በጣም የሚያሳዝን ህይወት አለው፡፡እኔም እንዳየሁት፡፡

ፒተር ኦክዋሊንጋ*

ኢትዮጵያውያን ባያገልሉ ጥሩዎች ነበሩ “እንጀራ” እና “ወጥ” ለመብላት ከምፈልጋቸው ም

ግቦች መካከል ናቸው። “ወጥ” ወፍራም፣ በቅመም የተለወሰ ስጋ እና አትክልት የሚጨመርበት እንደኾነ አውቃለሁ። ይህም ጠፍጣፋ ከኾነው፣ ኾምጣጣ ጣዕም ካለው እና ለመብላት ከሚያስጎመጀው “እንጀራ” ጋር ይቀርባል። ይህን መቅመስ እፈልጋለሁ። ዩጋንዳውያን ኢትዮጵያኖች የራሳቸውን አልኮል

መጠጥ የሚያዘወትሩ አድርገው ይወስዷቸዋል። በዚያ ላይ እንዲዘወተር “የማይመከር” የትምባሆ ዐይነት እንደሚያጨሱ ያስባሉ። እነዚህን የሚጨሱ ነገሮች በቡና ቤቶች እና አልኮል መሸጫዎች ማዘውተራቸው ከዩጋንዳውያን ጋራ ያመሳስላቸዋል። ይህን የሚጨስ ነገር መውደዳቸው በተለይ ከዩጋንዳ ራስታዎች ጋራ በአንድ ገጽ ላይ ያስቀምጣቸዋል። በዐፄ ኃይለ ሥላሴ የሚያምኑ የዩጋንዳ ራስታዎች “ራስተፈሪያንስ” መነሻቸው ከኢትዮጵያ ነው ብለው ያምናሉ።

ንግድ ዕድሉን ካገኘ ተራው ኢትዮጵያዊ ከአቧራ “ወርቅ”

ማውጣት ይችላል። ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ሠራተኞች፣ ሐይለኞች፣ ብልጣ ብልጦች እና የሚያዋጣ ንግድን የመለየት ችሎታ ያላቸው ናቸው። ጥሩ ከባቢ ካገኙ ወደ ባለጸጋነት በቶሎ የሚለወጡ ናቸው። ይህ የኢትዮጵያውያን ችሎታ ዩጋንዳውያን ለንግድ አጋርነት/ሽርካነት እንዲመርጧቸው ያደርጋቸዋል። በአጠቃላይ ዩጋንዳ ጨዋታ ወዳድ አገር ነች። ኢ

ትዮጵያውን ለዚህ ቅመም መኾን ይችላሉ። ይህ ታዲያ ማግለላቸውን ከተዉት የሚመጣ ነው። ለኢትዮጵያውያን ወንዶች ማለት የምፈልገው አንድ ነገር አለ። ይህ ቤታችሁ ነው። ማግባት ካለባችሁ ሴቶቻችን እንድታገቡ እጋብዛችኋለሁ። ለኢትዮጵያውያን እንስቶች ደግሞ ይህን እላለሁ። ነጻነት ይሰማችሁ። በቅጡ መወዳጀት እንችላለን።

* ፒተር ኦክዋሊንጋ በፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ሥር በሚገኘው ዩጋንዳ ሚዲያ ሴንተር የሚሠሩ ናቸው

ኢትዮጵያዊ የሴት ጓደኛ ማግኘት ከአለት ውሃ

እንደመጭመቅ ነው:: ሴቶቹ ከባህላቸው

ጋር በጣሙኑ የተጣበቁ ናቸው።

“መታመኔ ለዚህ...... ከገጽ 9 የዞረ

Page 19: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 19

ቢዝነስ

የአስመራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ወደ ካምፓላ መጣ

ማን ምን እየሰራ ነው?

አዶማያስ በኬንያ እየተስፋፋ ነው

በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን በብዙዎች ዘንድ ሙገሳ ያስገኘላቸውን የሪፈረንደም ሂደት ለጦርነት እንደተካሄደ የቀብር ሥነ ሥርዐት ቆጥረውታል። ምን ያህል በጦርነት እን

ደተሰላቹ ከሪፈረንደሙ በፊት፣ በድምፅ መስጫ ቀናት እና ውጤቱ እስኪገለጽ ባሉት ቀናት ውስጥ ሲያሳዩ ሰንብተዋል። እነርሱ በተደጋጋሚ ወደ ጦርነት እንደማይመለሱ ቢያውጁም ደጃፋቸው ላይ ግን ሌላ ዐይነት “ጦርነት” ሲካሄድ እያስተዋሉ ነው። ይህኛው ጦርነት ግን ሕይወትን የሚጠይቅ ሳይኾን በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ዶላር የሚፈልግ ነው። “ጦርነቱ” የታወጀው ደቡብ ሱዳን ላላት ያልተነካ

ቅምጥ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ለድንግል መሬቷ፣ ለነዳጇ፣ ብረት እና መዳብ የመሳለሱትን ማዕድኖቿን ለመቀራመት የሚደረግ ነው። “ጦርነቱ” ከትምህርት እስከ ጤና፣ ከግንባታ እስከ ገንዘብ ተቋማት ባሉ የተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እስከሚደረግ ሩጫ ይዘልቃል። እዚህ “ጦርነት” ወታደሮች ደግሞ ኢንቨስተሮች፣ የልዩ ልዩ ባለሞያ ባለቤቶች እና ኤክስፐርቶች ናቸው። መነሻቸው ደግሞ ሩቅ አይደለም። ቅርብ ነው- ከጎረቤት አገሮች።በይፋ ያልታወጀው ይህ ጦርነት አሃዱ የተባለው

በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ለሁለት ዐሥርት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሲቋጭ ነው። የሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ወገኖች እ.ኤ.አ በ2005 የሰላም ስምምነት ከተፈራራሙ ወዲህ በከፊል ራሷን የማስተዳደር መብት ባገኘቸው ደቡብ ሱዳን ላይ ሰላም ሰፈነ። ይህን ተከትሎም አደጋን ለመጋፈጥ የቆረጡ ባለሀብቶች ወደ አገሪቱ መምጣት ጀመሩ።የደቡብ ሱዳንን በር ለማንኳኳት ከጎረቤቶቹ ዩጋን

ዳውያን እና ኬንያውያን የቀደመ አልነበረም። ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያንም ዘግየት ብለው የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ኾና ወደተሰየመችው ጁባ መትመም ጀመሩ። በመጀመሪያ ዩጋንዳውያን እና ኬንያውያን ነበሩ ሽንኩርት እና ቲማቲም ሳይቀር ሁሉንም የምግብ ሸቀጦች በብቸኝነት ሲያቀርቡ የነበሩት። በስተኋላ ግን ኤርትራውያን አብዛኛዎቹን የንግድ ዐይነቶች ተቆጣጠሯቸው። “ሁሉንም ነገር ማለት ይቻላል ኤርትራውያን ተቆ

ጣጥረውታል” ላለፉት ስድስት ዓመታት በጁባ የኖረው ኢትዮጵያዊው ቢኒያም ዮሐንስ ነው ይህን የሚለው። “ከዩጋንዳውያን እና ከኬንያውያን በተሻለ ነው እየነገዱ ያሉት።”

የጎረቤቶች ጦርነት

የአስመራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶቹን የሚያከፋፍልባቸው ሁለት ዘመናዊ የአልባሳት መሸጫዎች በናኩማት ኦአሲስ ሞል እና ፎረስት ሞል ከፈተ። ሁለቱ የአልባሳት መሸጫዎች በ”ኢጣሊያን ስታይል” የተመረቱ እና “ዶልቼ ቪታ” የሚል መለያ የያዙ ሸሚዞችን፣ ሱሪዎችን፣ አንሶላዎችን፣ ምቾት ያላቸው ብርድ ልብሶችን፣ ለኩሽና ስራ የሚውሉ ሽርጦችን እና ጓንቶችን ለገበያ አቅርበዋል። ሱቆቹ ከጠዋት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ክፍት ናቸው። ሃምሳ አምስት አመታት ያስቆጠረው አስመ

ራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የተመሰረተው በጣሊያናዊው ሮቤርቶ ባራቶሎ አማካኝነት ነበር። እ.ኤ.አ በ1975 ፋብሪካው ሲወረስ ባራቶሎ ሀገር ለቆ ቢወጣም እስካሁንም ድረስ ፋብሪካው ያለበት ቦታ “እንዳ ባራቶሎ” ተብሎ ነው የሚጠራው። በዚያን ወቅት ፋብሪካው ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞች ነበሩት። በመንግስት ስር የቆየው ፋብሪካ እ.ኤ.አ በ2004 ዛምባቲ ግሩፕ ለተባለ የኢጣሊያን ኩባንያ ይሸጣል። ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት እየተዳደረ የሚገኘው “ዜድኤ. ኢአር” በተሰኘ የዛምባቲ ግሩፕ እህት ኩባንያ ነው። አስመራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አሊጊደር አካ

ባቢ የጥጥ እርሻ አለው። ፋብሪካው ምርቶቹን በአስመራ ከተማ በሚገኙ ሶስት ማከፋፈያዎች ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን በከረን፣ ደቀመሃሪ እና መንደፈራም መሸጫ ሱቆች አሉት።

ከፋብሪካው ምርቶች መካከል አንዱ

ፎቶ

ዜድ

ኤ.ኢ

አር ፒ

ኤል

ስያሜው አዶማያስ ይሰኛል። የኢትዮጵያውያንን የባህል አልባሳት እና እቃዎች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለኬንያ ገበያ የሚያቀርብ ድርጅት ነው። የቤት ኪራይን እና ተቀማጭ ገንዘብን ሳይጨምር ቦታ ለማግኘት ብቻ ወደ 1.2 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በሚጠየቅበት “ዌስት ጌት” ሞል ውስጥ ስራ ከጀመረ ቆይት አለ። ጅማሮው በሸማቾች መተላለፊያ ኮሪደር ላይ በምትገኝ ኪዮስክ ውስጥ ነበር። በእዚያ የባህልና የሀይማኖት ቁሳቁሶች ለሽያጭ ይቀርቡበታል። ድርጅቱ በአነስተኛ ሱቅ የተገደበውን ስራውን በ

ቅርቡ አስፋፍቷል። የባህል አልባሳት፣ የእጅ ቦርሳዎች እና ጫማዎች የሚሸጡበት ሱቅ በተጨማሪ ከፍቷል። ይህንን ሱቅ ለማግኘት ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። እዚያው “ዌስት ጌት” ሞል ውስጥ ነው የሚገኘው። የእነዚህ ሁለት ሱቆች ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ህሊና አሰፋ ትሰኛለች። እ.ኤ.አ በ1998 የኬንያን ምድር ከረገጠችወዲህ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድን አልፋለች፡፡ ከብዙ ድካም በኋላም በናይሮቢ ካሉ የኢትዮጰያ የባህል ቁሳቁሶች፣ አልባሳት እና ምግቦችን ከሚያስተዋውቁ ጥቂት ኢትዮጰያውያን መካከል ዋነኛዋ ለመኾን ችላለች፡፡በ2006 ዓ.ም ዛሬ “ሐበሻ የኢትዮጵያ ሬስቶራን

ት” ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የመጀመሪያውን የባህል ቁሳቁሶች መሸጫ ከፈተች፡፡ ዋነኛ አላማዋም የኢትዮጰያውያንን የባህል ቁሳቁሶች ለተቀረው ዓለም ማስተዋወቅ እንደነበረም ትናገራለች፡፡ ገበያውም አዋጪ መኾኑን ስታስተውል ከአምስት ዓመታት በኋላ የቱሪስቶች መናኸሪያ በኾነው እና ለአብዛኛው ሸማች እንደ ቅንጦት ወደሚታየው “ዌስት ጌት” ሞል አምርታለች።

ፎቶ

-ዌስት

ጌት

ሞል

የአዶማያስ የዌስት ጌት ሱቅ

ኤርትራውያን መጀመሪያ የገቡበት የሥራ መስክ የሆቴል አገልግሎት መስጠት ነበር። በወቅቱ በጁባ የነበሩት ሆቴሎች በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ። ኤርትራውያኑ ቆየት ብሎ ሸቀጣ ሸቀጦችን ወደ ማስመጣት ተሸጋገሩ። ከደቡብ ሱዳን የሕዝብ ቆጠራ እና የስታትስቲክስ ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከኾነ በዐሥሩ የደቡብ ሱዳን ክልሎች ውስጥ ባሉ ዋና ከተማዎች የተመዘገቡ ነጋዴዎች ቁጥር 7333 ነው። ከዚህ ውስጥ 84 በመቶውን የሚወስዱት ሱቆች እና ምግብ ቤቶች ናቸው። ከሌሎች ከተሞች ጋራ ሲወዳደር የአገሪቱ መዲና በርካታ ነጋዴዎችን በማስተናገድ ቅድሚያውን ይዛለች። በጁባ 2683 የተመዘገቡ ነጋዴዎች አሉ። ምንም እንኳ የነጋዴዎቹ ቁጥር አናሳ ቢመስልም ጎ

ረቤት አገሮች ግን የደቡብ ሱዳንን ገበያ ለመቆጣጠር ያለመታከት ሠርተዋል። ከዓመታት በኋላም የላባቸውን ፍሬ መቅመስ ጀምረዋል። የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከኾነ ኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን የምትልካቸው ምርቶች ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ አድጓል። ኬንያ ከሱዳን ጋራ የነበራት የውጪ ንግድ በ2009 እ.ኤ.አ 158 ሚልዮን ዶላር ደርሷል። ይህ ቁጥር ከአራት ዓመት በፊት 84 ሚልዮን ዶላር ብቻ ነበር። እንደ ኬንያ ንግድ ባንክ (ኬ.ሲ.ቢ) ያሉት ትልልቅ

የኬንያ ተቋማት የአገሪቱን ጥቅም በደቡብ ሱዳን ውስጥ በፊታውራሪነት ያስጠብቃሉ። ይህ የኬንያ ባን

ክ በሱዳን እህት ድርጅቱን ኬ.ሲ.ቢ (ሱዳን) ሊትድ በሚል ስያሜ ያቋቋመው የሰላም ስምምነቱ በተፈረመ በዓመቱ ነበር። የኢትዮጵያ አቻው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደቡብ ሱዳንን ገበያ የተቀላቀለው ግን ከኬ.ሲ.ቢ ሦስት ዓመት ዘግይቶ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁንም ቢኾን ሥራውን የሚያከናውነው ያለምንም ቅርንጫፍ ጁባ ታውን በሚገኘው ዋና መሥርያ ቤቱ አማካኝነት ሲኾን ኬ.ሲ.ቢ ግን የቅርንጫፎቹን ቁጥር 18 አድርሷል። የኬንያው ባንክ ከአራት ዓመታት በኋላ የቅርንጫፎቹን ብዛት ወደ 28 ለማሳደግ ግብ አስቀምጧል። ሌላኛዋ ጎረቤት አገር ዩጋንዳም ብትኾን በደቡብ

ሱዳን ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። ኦፊሴሊያዊ ቁጥሮች እንደሚያሳዩት ከኾነ አገሪቱ ከኬንያም በተሻለ ተጠቃሚ ኾናለች። እ.ኤ.አ በ2009 ብቻ ዩጋንዳ 184.6 ሚልዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ደቡብ ሱዳን ልካለች። በደቡብ ሱዳን ምርቶቿን በመላክ የቀዳሚነትን ስፍራ ብትይዝም ይኼ ብቻ በቂ ነው ብላ አልተገታችም። ይልቅስ እያደገ የመጣውን የደቡብ ሱዳን ገበያ ፍላጎት ለማርካት የመሠረት ሥራዎች ከወዲሁ መሥራት ጀምራለች። የዩጋንዳ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ከደቡብ ሱዳን ድንበር 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጉሉ ከተማ ላይ ለአምራቾች የሚኾን “ኢንዱስትሪያል ፓርክ” ለማቋቋም በሂደት ላይ ነው። የዚህ ፓርክ ዒላማ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ናት።

“ባለሥልጣኑ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ የሚቋቋምበትን መሬት ለማግኘት ከጉሉ ከተማ ምክር ቤት ጋራ እየተደራደረ ነው። ምንም እንኳ ኢንዱስትሪያል ፓርኩን እምብዛም ሳይዘገይ ለማቋቋም ዕቅድ ቢኖረውም እስካሁን ግን በመሬት ላይ የተሠራ ሥራ የለም” ብለው ነበር የባለሥልጣኑ የኮሚዩኔኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የኾኑት ዶሪስ ሚቲ ኪሚሉ። የዩጋንዳ መንግሥት ለወደፊቱ ከመዘጋጀት ባሻገር

በሁለቱ ጎረቤት አገሮች መካከል የሚካሄደውን ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ለማቅለል ርምጃዎችን ወስዷል። በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ መሠረተ ልማቶችን ከመዘርጋት አንስቶ የውጭ ንግድ ማበረታቻ እስከማቅረብ ድረስ ያሉ ርምጃዎችን በመውሰድ በደቡብ ሱዳን መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ ዩጋንዳውያን መንገዱን ጠርጎላቸዋል። “የዩጋንዳ መንግሥት በደቡብ ሱዳን ለመሥራት ለ

ሚፈልጉ ነጋዴዎች የውጪ ንግድ ማበረታቻ ይሰጣል” ይላሉ ዶሪስ። ይህ ማበረታቻ የሚሰጠው ወደ ውጪ የሚላኩ ም

ርቶችን የሚያመርቱ ነጋዴዎችን ለመደገፍ በተነደፈው እና “ኤክስፖርት ፕሮሞሽን ስኪም” ተብሎ በሚጠራው የዕገዛ ዐይነት ነው። በዚህ ውስጥ ከሚካተቱት አንዱ “ማኑፋክቸሪንግ አንደር ቦንድ” የተባለው ማበረታቻ ሲኾን ይህም አምራቾች የጉምሩክ ፈቃዳቸውን በመጠቀም ቀረጥ ሳይከፍሉ ጥሬ ዕቃ ከውጭ እንዲያስገቡ የሚያስችል ነው። የገባው ጥሬ ዕቃ ግን ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማምረት ብቻ የሚውል መኾኑ ይረጋገጣል። ይህ አሠራር በውድ ዋጋ ጥሬ ዕቃ ከውጭ የሚያስመጡ አምራቾች ወዲያውኑ ለታክስ ይከፍሉ የነበረውን ገንዘብ በማስቀረት የመሥሪያ ገንዘብ (ወርኪንግ ካፒታል) እንዲኖራቸው ያደርጋል። ሌላኛው የማበረታቻ ዐይነት ከውጭ ተገዝቶ ለገ

ባ ግብዓት የተከፈለን ግብር በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መመለስ ነው። ይህም ግን እንደመጀመሪያው ማበረታቻ ሁሉ ተግባራዊ የሚኾነው ግብአቱ ወደ ውጭ ለሚላክ ምርት መዋሉ የተረጋገጠ እንደኾነ ብቻ ነው። ብዙዎቹ የደቡብ ሱዳን ጎረቤቶች የአገሪቱን ገበያ

እየተቀራመቱ ቢኾንም ኢትዮጵያ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ በጉልህ ስትሳተፍ አትታይም። ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ከትልቁ ኬክ እያገኙ ያሉት ትንንሽ ቁርስራሾችን ነው። በደቡብ ሱዳን ሁለት ሺሕ የሚኾኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይገመታል። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የተሠማሩት በሸቀጥ ንግድ አ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

በ“ቡፋሎ” ባንክ ውስጥ የዋናው ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ሰይፉን ጨምሮ 10 ኢትዮጵያውያን ይሰራሉ

በደቡብ ሱዳን ውስጥ ካሉ ሀገር በቀል አምስት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው “ቡፋሎ” ባንክ ላስመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይመሰክራሉ

በተስፋለም ወልደየስ

ፎቶ

ዎች

- ተስፋ

ለም ወ

ልደየ

Page 20: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)20 ሀበሻዊ ቃና

ኤፍሬም እሸቴ

ትዝታ

ብላቴ በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር፣ ከሐዋሳ ከተማ ወደ 90 ኪ.ሜትር, ከአዲስ አበባ ደግሞ 395 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ነው። ከባሕር ጠለል በላይ 1000- 1400 ሜትር በበረሃማው የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ ሞቃት ቦታ። በበጋ ወቅት እጅግ በጣም ሞቃት እና ደረቅ ሲሆን በክረምት ደግሞ ዝናባማ እና የሚተነፍግ ውሃ አዘል አየር (rainy and humid) ይበዛበታል። የዛሬ 20 ዓመት በወቅቱ በአገራችን የሚ

ገኙ የኮሌጆች እና የዩኒቨርሲቲዎች በጠቅላላው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በዚህ ወታደራዊ ካምፕ ከትመው ነበር። በእስክሪፕቶ ፈንታ ጠመንጃ፣ በወረቀት ፈንታ ጥይት፣ በዶርሚቴሪ ፈንታ ወታደራዊ “ኬስፓኖች”፣ በሲቪል ፕሮፌሰሮች ፈንታ መለዮ ለባሽ ወታደሮች ተተክተዋል።ተማሪው የቀለም እና የሙያ ትምህርቱ

ን ትቶ መሣሪያ መግጠም እና መፍታት፣ መሣሪያ አያያዝና አተኳኮስ፣ የሰውነት ማጎልመሻ ስፖርት፣ የቦንብ አያያዝ እና አወራወር፣ ድንገተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት ሰው ሊያገኘው ስለሚችለው ጊዜያዊ ርዳታ አሰጣጥ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ በምሽግ የተደበቀ ጠላት እንዴት ማጥቃት እንደሚቻል፣ በፈንታው ራሱ ምሽግ ውስጥ ቢሆን እንዴት መከላከል እንደሚችል፣ ሌሊት ቢሆን እንዴት እንደሚያጠቃ ወይም እንደሚከላከል ወዘተ ወዘተ ትምህርት ይሰጠው ነበር። እኔም እዚያ ነበርኩ። ዘንድሮ 20 ዓመት በሞላው በዚያ ለብዙዎቻችን አዲስ በሆነ የሕይወት አጋጣሚ ካየሁት እና ትዝ ከሚለኝ ላካፍላችሁ ወደድኹ።

* * *ወቅቱ በመላዋ ኢትዮጵያ “የጦር ወሬ”፣ የ

ምጥ ጣር የሚሰማበት ከባድ ወቅት ነበር። መንግሥትም ሕዝቡም ተጨንቋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በአንድ በኩል የመንግሥት ለውጡ ደግ ነገር ይዞ ይመጣ ይሆናል በሚል ተስፋ ሲጠብቁት በሌላ በኩል ደግሞ “ኤርትራ ትገነጠላለች” ከሚለው ጀምሮ ሰሜነኞቹ ይዘውት

ሊመጡት የሚችሉት መአት እያስፈራው በመንታ ልብ ይጠብቃል። “ከወንበዴዎቹ” ከድተው የገቡት ሁለቱ መሪዎቻቸው አብርሃም ያየህ እና ገብረ መድህን አርአያ ይናገሩ የነበሩት ነገር ሊመጣ ያለውን መከራ እጅግ አክብደው አቅርበውት ነበር። ሰሎሞን የተባለ ፀሐፊ ከሱዳን ለአዲስ ዘ

መን ጋዜጣ ያደርስ የነበረው እና የኢትዮጵያ ሬዲዮ ያነበው የነበረው ጽሑፍ ድባቡን በማክበድ ረገድ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል። በዚህ መካከል ኮ/ል መንግሥቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሊያናግሩ ወደ 6 ኪሎ ግቢ ተጓዙ። እናም ተማሪዎቹን በአንድ ቀን ከፀረ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምነት ወደ ፀረ-“ወያኔነት” ቀይረው “እንዘምታለን” አስባሏቸው። ፕሬዚደንቱም “ይኼው ነው” ብለው ተነሡ። ከዚያማ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ተባለ። “ወንበዴዎች” የሚባሉት በረኸኞችም በበኩላቸው “አሁን ወደ ብላቴ የሚገባው ወታደር ከሌሎቹ የሚለየው እንግሊዝኛ በመናገሩ ብቻ ነው” ሲሉ ቀለዱ ተባለ።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “እን

ዘምታለን” ማለታቸው እንደተሰማ በብዙዎቻችን ውስጥ የፈጠረው የተመሰቃቀለ ስሜት ነበር። አንዳንዱ መንግሥት ሌላውን ለማበረታታት እንጂ እነዚህን ሕጻናት አይማግዳቸውም ሲል ሌላው ደግሞ ሚሊሻውንም፣ አባት ጡረተኛውንም፣ ወጣቱንም ከላከ በኋላ የቀረው ተማሪው ስለሆነ ያንን ከማድረግ እንደማይመለስ በማስረገጥ ጭንቀታቸውን መግለጽ ጀመሩ። ተማሪው ግን ድጋፉን በየግቢው መግለጽ ቀጥሎ የመዝመቱ ነገር ቁርጥ ሆነ። መንግሥትም ነገሮችን ቶሎ አመቻቸ። ተማሪው በሁለት የተከፈለ ሐሳብ እንዳ

ለው ግልጽ ነበር። መሔድ የሚፈልግ ተማሪ ያለውን ያህል መቅረቱን የሚመርጠውም ብዙ ነው። መሔድ የፈለገው ሁሉ ግን “ወንበዴዎቹን ለመዋጋት” ቆርጦ አልነበረም። ከቀረ በኋላ እንደሚባረር እርግጠኛ በመሆን ከዚያ ለማምለጥ መሔዱ ላይ የወሰነ ብዙ ነበር። በስንት መከራ የተገኘ ዩኒቨ

ርሲቲ እና ኮሌጅ እንዲህ በቀላሉ የሚተው አልሆነም። እናም ጭንቅ ሆነ።ከቆይታ በኋላ መሔድ የሚፈልገውም ወ

ሰነ፤ መቅረት የሚፈልገውም ወሰነ። እኔ መሔድ መረጥኹ። ለምን ለመሔድ ወሰንኩ? የማስታውሰው ለመቅረት አስቤ እንደማላውቅ ነው። በዚያን ወቅት ግን ብሰለጥንም ጦርነት ውስጥ እገባለኹ የሚል ስጋት አልነበረኝም። ብዙም አላሰላሰልኩትም ልበል። ተማሪው በሙሉ ሲሄድ መቅረት ግን ሌላውን ተማሪ እንደመካድ ሳልቆጥር አልቀረኹም።

ጉዞ ወደ ብላቴ … ሽንጣም የክፍለ ሀገር አውቶቡሶች መጥ

ተው ኮሌጁ ግቢ ውስጥ ተገጥግጠዋል። ዕለቱ ሐሙስ ነው። የቀን ቅዱስ። መጋቢት 19/ 1983 ዓ.ም። የቅዱስ ገብርኤል መታሰቢያ። ሻንጣዎቻችንን አሰናድተን በሌሊት ተነሥተናል። አውቶቡሶቹ የኮሌጁ ኳስ ሜዳ ላይ ተዘርግፈዋል። ተማሪው ሁሉም ተሰናድቷል። ተሳፈርን። ሁሉም ወጣት ነው። ብዙዎቻችን ገና 20

ዓመት እንኳን አልሞላንም። እኔ የማውቀው አብዛኛው ተማሪ ከቤተሰቡ የተለየው ኮሌጅ ሲገባ ነው። ለኮሌጁም ቢሆን መን

ግሥት እንደ ቤተሰብ እንደሚንከባከበው ስለሚታሰብ ወላጅ ልቡ ማረፉ እርግጥ ነው። በወላጆቻችን ዘንድ መንግሥት አባት ነው፤ መንግሥት ወላጅ ነው የሚል ጽኑ አስተሳሰብ አለ። ለእነርሱ (ፈረንጆቹ እንደሚሉት) “we are in good hands”። አዬ ቤተሰቦቻችን አለማወቃቸው፣ አንድ ነገር ትንፍሽ ካልን የመንግሥት ፖሊስ ቆመጥ እንደሚያሯሩጠን። ይህንን ደግሞ በየዓመቱ ቀምሰነዋል። አውቶቡሶቹ እስከ ቃሊቲ እስኪደርሱ ድ

ረስ የሰርገኛ ስሜት አልለቀቃቸውም። ቃሊቲ ላይ ስንደርስ ከግቢው ጀምሮ ሊሸኙን በአንድ መኪና አብረውን የመጡት መምህራኖቻችን ተሰናብተውን ተመለሱ። የእኛ የልጆቹ ብቻ ሳይሆን የትልልቆቹም ልብ አብሮን ጉዞ ጀምሮ ነበር። ምናልባት እነርሱ ሊመጣ ያለውን ነገር የበለጠ አመዛዝነውትም ይሆናል። ወይም ወጣቶቹ መምህራኖቻችን አንድም ለ“ዕድገት በኅብረት” ፣ አንድም ለ“መንደር ምሥረታ” “ዘመቻውን” የቀመሱ ሆነው አዝነውልን ይሆናል። ለተማሪያቸው ለማዘን በርግጥ ከዘመቻ ውለው መከራውን ማየት የለባቸውም። የአስተማሪ አንጀታቸው፣ የወንድምነት አንጀታቸው

አልችል ብሎም ይሆናል። አንዳንዶቹ መምህራን የታላላቅ ወንድሞቻችን እኩያዎች የሚሆኑ “ለጋ ምሩቃን” ስለነበሩም የተማሪነቱ መንፈስ ገና ተሟጦ አላለቀባቸውም። እኛም አንድ አራት ዓመት ቆይተን ከአስተማሪነት ትውውቅ ወደ ወዳጅነት ትውውቅ ያደረስናቸው አሉን።መምህራኑ ከተመለሱ በኋላ መንገዱ ሰተ

ት አድርጎ ይወስደን ጀመር። እስከ ዝዋይ ያለውን መስመር ከዚያ በፊትም አውቀዋለኹ። እናም አሁን እስከ ዝዋይ ድረስ ምንም የባዕድነት ስሜት አልተሰማኝም። ዝዋይን አልፈን ስንዘልቅ አየሩም፣ ምድሩም አዲስ እየሆነብኝ ሄደ። በዝና የማውቃቸውን ሻሸመኔን እና አዋሳን (አሁን ሐዋሳ ነው የምትባለው) አልፈን ትንሽ እንደተጓዝን ለምሳ እረፍት ሆነ። ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ይሆናል። በርግጥ የሁዳዴ ሰሞን እንደመሆኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት አጾሙን ማለት ነው ብዬ ልውሰደው? ነገሩ ምሳ ይሁን እንጂ ምሳ ነው ለማለት

ይከብዳል። በቆርቆሮ የታሸገ እንዲሁም ኮቾሮ መሰል ኩኪስ ነገር አደሉን። የጠጣነውን አላስታውሰም። ጠጥተን ይሆን? መቸም ባንጠጣ ውሃ ጥሙ ይገድለን ነበር። ከአዲስ አበባ ስወጣ ሁሌም ጭንቅ የሚለኝ የዝዋይ-ማዶ ውሃ ነው። ውሃው ከጉሮሮዬ አይወርድም። ይቅርታ የዝዋይ ማዶ ሰዎች። ሰው በተለይ የኮተቤ ኮሌጅን (የሆለታን) ውሃ ለምዶ የዝዋይን፣ የሐዋሳን ውሃ ልጠጣህ ሲሉት …። መቸም ሰው እንደ ልማዱ ነው። ሙቀት አገር የመኖር ልማዱ ስለሌለን መሰለኝ። አለበለዚያ ከቅንጦት መቆጠሩ አይቀርም። በተለይ ነገር ተበላሽቶ አገር ከፈረሰ በኋላ ከብላቴ ስንበተን የጠጣነውን ውሃ ሳስታውሰው የዝዋይ ግፍ ነው እላለኹ።ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ። ምሳችንን

በልተን መጠነኛ ዕረፍት ከተደረገ ዘንዳ ጉዞ ተጀመረ። ከሐዋሳም ከወጣን በኋላ ዋናውን መንገድ ይዘን ጥቂት እንደተጓዝን ትንሿን የሞሪቾን ሰፈር እናገኛለን። እዚያ ላይ ወደ ቀኝ ታጥፈን አቧራማውን የብላቴን መን

ገድ ተያያዝነው። ከዚያ ጀምሮ ቢያንስ 60 ኪሎ ሜትር የተጓዝን ይመስለኛል። ለእኔ ፍፁም አዲስ አገር ነውየጎጆዎቹ አሠራር፣ የግቢዎቹ ሁኔታ ወዘ

ተ ወዘተ እኔ ከማውቀው ገጠራማ አካባቢ የተለየ ነው። ለገጠሩ ለገጠሩ ሴት አያቴን እና ሌሎች ዘመዶቼን ለማየት ከሆለታ ወደ ዱፋ (ወደ ሜታ ሮቢ፣ ሙገር መስመር) የሦስት እና የአራት ሰዓት የእግር መንገድ ስንጓዝ አውቀዋለኹ። ጎጆ ቤቶቹ፣ ማሳዎቹ፣ በመንገድ ላይ ለማረፍም፣ ውሃ ለመጠጣትም የምንጠጋባቸው “ምንጭ” ያላቸው ተረተሮቹ በሙሉ ትዝ ይሉኛል። ብላቴ መስመር ላይ ያሉት የተለዩ ሆነውብኛል። አውቶቡሶቹ ያንን ሞቃታማ አየር እየሰነጠቁ፣ የትንባሆውን ተክል አልፈው፣ ተአምረኛውን የጨሪቾ ሚካኤልን አልፈው ከብላቴ ግቢ ደረሱ።

ከሜንስ ቤት እስከ ኬስፓንብላቴ የገባነው ከመሸ ነው። እንደደረስን

አንድ አዳራሽ መሰል ግማሽ ጨረቃ ቅርጽ ባለው የብረት መጋዘን ወይም ኬስፓን ውስጥ ሰልፍ ይዘን ቆምን። ተራዬ ሲደርስ የሚመዘግበን ሰው አንዲት ክኒን እና ውሃ ሰጠኝ። የወባ መከላከያ ናት። ዋጥኩ። ዋጥን። መዋጥ ነው። ይህ የጦር ካምፕ ነው እንጂ ከተማ አይደለም። ገዳይ ቢጫ ወባ ያለበት በረሃ እንጂ አዲስ አበባ አይደለም። እኛም ወታደሮች እንጂ “ምሁራን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሊቃውንት” አይደለንም። ከክኒናው ጋር የሚያስፈልገን ነገር ተሰጠን። ሰዓቱ የራት ሰዓት ስለሆነ ወደ “ሜንስ ሜት” (መመገቢያ ቤት) ሄድን። “ሜንስ ቤት” የምን ቋንቋ ነው? በአማርኛ

ችን ውስጥ የተሰባበሩ አረብኛዎች፣ ጣሊያንኛዎች፣ ስፓኒሽኛዎች፣ አራማይኩም፣ ቅብጡም፣ ግሪኩም፣ ሱርስቱም፣ አረብኛውም፣ ስለሞላበት አንዳንዱን ቃል ፍቺ ለማወቅ ወይ ሊቅ መጠየቅ ወይ መዝገበ ቃላት ማማከር ይጠይቃል። ይቺ “ኬስፓን” እና “ሜንስ ቤት” የምትለው ከየት እንደተገኘች አሁን አላወቅዃትም። ሆለታም ሆኜ ወታደሮቹ ምግብ ቤታቸውን “ሜንስ ቤት” እንደሚሉ አውቃለኹ። ከሌሎቹ ተማሪዎች በዚህ በዚህ “እልቃለኹ” ማለት ነው (ለፈገግታ)።ወራቱ ወርሃ ጾም ያውም ዐቢይ ጾም በመ

ሆኑ የምግባችን ነገር ጭንቅ ሆነ። ደግሞም ጾሙ ሊፈታ አንድ ሳምንት ነው የቀረው። ዓይጥ ወልዳወልዳ … እንዳይሆን። ያንን ማታ እንጀራ በሻይ እና በውሃ እያማግን በላን። ፍርሃታችን “የምን ጾም ነው? ቀበጦች!! ትበላ እንደሆን ብላ!!!” የሚል ወፍራም የወታደር ድምጽ እና ቁጣ ጠብቀን ነበር። አልመጣም። ስለዚህ እንጀራ በውሃ እያማግን መብላታችንን እንደ ትልቅ ሥጦታ ቆጠርነው። ተመስገን። ከዚያ ወደየተመደብንበት ማደሪያ ቦታ ተ

ጓዝን። የደረሰኝ አልጋ ከታች ነው። ከላይ አንድ ልጅ ይተኛል። በኬስፓኑ ውስጥ ብዙ ተማሪ ነው ያለው። መኝታ ክፍል ሳይሆን የአልጋ አነጣጠፍ ማስተማሪያ ወርክ ሾፕ ይመስላል። ኮተቤ እንደገባኹ ከመኝታ እጥረት የተነሣ ብዙ ተማሪ ካለበት ሰፊ ክፍል ውስጥ ማደር ስለለመድኹ አሁን አዲስ አልሆነብኝም። እናም ጥቅልል ብዬ ተ

የዛሬ ሃያ ዓመት ወቅቱ ዘመነ ፋሲካ ነበር። የጂማ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም አስተዳደር ድንገተኛ ትእዛዝ አስተላለፈ። በአዲስ አበባ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማ

ት የሚገኙ ተማሪዎች ባደረጉት ዉሳኔ መሠረት ዕጩ መምህራኑ ወደ ብላቴ የአየር ወለድ ማሰልጠኛ መሄድና መሰልጠን አለባችሁ በማለት ከጭራ የቀጠነ ትእዛዝ አስተላለፈ። ለተማሪው የመወያያ ጊዜና ዕድል እንኳን አልተሰጠም። በዚህ ዉሳኔ መሠረት ወደ 400 የምንሆን ዕጩ መምህራን ከጂማ ወደ ብላቴ ተጓዝን። ብላቴ ከደረስን በኋላ መጠሪያችን “ብርጌድ አንድ” የሚል እንደ ሆነም ተነገረን።አንደኛ ብርጌድ ልዩ መገለጫዎች ነበሩት። የብርጌ

ዱ አባላት ወጣቶች ነን። የምንበዛው የተለያዩ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ብንሆንም በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ይማሩ የነበሩ ነገር ግን ዘመቱ ሲባል በቤተ ሰብ ተፅዕኖ፣

በፍርሃት፣ በፖለቲካ አቋም ልዩነት….አንዘምትም ብለው ቀርተው የነበሩና በኋላ ደግሞ መንግሥት ርምጃ ሊወስድባችሁ ይችላል ሲባሉ ዘግይተው የመጡ ዘማቾች ግራ የተጋቡ ግራ የሚያጋቡ መሃል ሠፋሪዎች……የነበሩበት ብርጌድ ነበር። ይህ ብርጌድ “ ሽነድ” የሚል ምሕፃረ ቃላዊ ስያሜ ተሰጥቶትም ነበር።“ሽነድ” ሽብር ነዢ ድርጅት ማለት ነው። በዘማች

ተማሪዎች አካባቢ የሚነገሩ መረጃዎች እውነትም ይሁኑ የተፈበረኩ መነሻቸው ሽነድ ነበር። አንዱ የነሣና ዛሬ ወደ ጦር ግንበር ሊያዘምቱን ነው ይላል፤ ሌላኛው ደግሞ ትናንት ማታ የወያኔ ታጣቂ ሰላዮች ቦንብ እንደ ታጠቁ ትምባሆ ሞኖፖል ተያዙ ይላል፤ ሌላኛው ድግሞ ለጥቆ ከዘማች ተማሪዎች መካከል ለወያኔ በመገናኛ ሬድዮ መልእክት ሲያስተላልፉ ተያዙ ይላል። አንዳንዱ ደግሞ ከመተኛታችሁ በፊት መኝታችሁን ፈትሹ የወያኔ ደጋፊዎች ፈንጂ ሊያኖሩባችሁ ይችላሉና ይላል። ይህ ከሽነድ የመነጨው

የሽብር ወሬ በቀላሉ ወደ ሌሎቹ ብርጌዶች ቀንድና ጭራ ተበጅቶለት ይናኛል።ተኩስ ወረዳ ወርደን ዒላማ ስንለማመድ የሆነው

ን ላውጋችሁ። ተኝቶ መተኮስን እየተለማመድን ነበር። በሁለት

ተማሪዎች መካከል አንድ አሰልጣኝ ይቆማል። በሁለቱ ተማሪዎች መካከል ያለው ርቀት ምናልባት ሜትር ከግማሽ የሚሆን ይመስለኛል። ልምምዱ በእውነተኛ ጥይት ነበር። ከፊት ለፊታችን በቅርብ ርቀት የተተከሉ እንጨቶች ላይ የተሰኩ ካርቶኖች ነበሩ። ልምምዱ እነዚያን ካርቶኖች ዓልሞ መምታት ነበር። አሰልጣኙ “ተዘጋጅ ጀምር” ብሏል፤ ተኩሱ ተጀመረ። ሁሉም እንደየችሎታው እያለመ ይተኩሳል። በእኔና በሌላኛው ጓደኛዬ መካከል አንድ ተካ የሚባል የግቢያችን ተማሪ ነበረ። እርሱ ገና እያነጣጠረ ሳለ ከጎኑ ያለው ዒላማው እንደገባለት ምላጭ ይስባል። የጥይት እርሳስ ወደ ተላከችበት ስ

ትስፈነጠር ቀለኽ ትፈናጠርና ከተካ አፍንጫ ታርፋለች። ትኩስም ስለነበረች ትንሽ አፍንጫውን እንደማድማት ትላለች። ተካ ጥይት የመታው ይመስለውና ደንግጦ “ተሠዋሁ እኮ” እያለ ወደሚተኮስበት ሊገባ ሲል ቆሞ የነበረው አስተኳሽ ይዞ አስቀረው። በብዙዎች ተማሪዎች ዘንድም ስሙ “ተሠዋሁ” ሆኖ ነበር።

የመልስ ጉዞግንቦት 18/1983 ዓ.ም ያ ማሰልጠኛ የኀዘን ድባብ

አጥሎበት ነበር። የተወሰኑ ሰልጣኞች ግንቦት 16 ወይም 17 ይመስለኛል ከብላቴ የወጡት። ከሽነድ ብርጌድ ከነበርነው መካከል ግን ይህን ዕድል ያገኙት ጥቂቶች ናቸው። የሚወራው ነገር ሁሉ መያዣ መጨበጫ የሌለው ነበር። እኔ በራሴ የማደርገውን አላውቅም። የሽነድ አባላት በዚያች ቀውጢ ሰዓት ስንኳ ቀድመው ስለወጡት ተማሪዎች ብዙ ይሉ ነበር።አንዱ በሰላም አዲስ አበባ ገብተዋል ሲል ሌላኛ

ው ወያኔ መንገድ ላይ ይዞአቸው ወደ እስር ቤት አስገብቷቸዋል ይላል። አዋሳ እየጠበቁን ነው የሚል የመኖሩን ያህል ኬንያ ገብተዋል የሚልም ነበር። ሌላው ደግሞ ከደቡብ ዕዝ ጋር ተቀላቅለው ወያኔን ሊወጉ እየተዘጋጁ ነው ይላል። እነዚህን ምንጭ አልባ ዜናዎች እየሰማን ቁርስና ምሳ በላን።ከምሳ በኋላ አጭር ስብሰባ ተደረገና ወዲያዉኑ

መውጣት እንዳለብን ተስማማን። ወዴት መሄድ እንዳለብን ግን በውል የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም። ብቻ አዲስ ወደ ተሠራው አውሮፕላን ማረፍያ ሄድን። አንድ ነግር ግን እንዳትረሱ ፤ በዚያች ግቢ ከ17 ጀምሮ ተጠያቂነት ያለው አካል አልነበረም። አንዲት ሄሊኮፕተር እንደምትመጣና ወደ ድሬዳዋ እንደምትወስደን ሲነገር ሰማሁ። እርሷን ጥበቃ በአውሮፕላን ማረፍያው ላይ ታች ማለት ጀመርን። ወይ የመከራ ጊዜ ሰዓት ርዝመቱ!!! ለስልጠና ብላቴ ከቆየሁት ጊዜ ይልቅ ያቺን ሄሊኮፕተር ጥበቃ እዚ

ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ

የዛሬ ዓመት20

“ሽነድ” እና ፍርሃትብላቴ በጅማ መምህራን ኮሌጅ ዕይታ

ስንታየሁ አባተ(ቀሲስ)-ካይሮ፣ ግብፅ

Page 21: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 21

ኛዅ። “እንዴ በር የለውም እንዴ ቤቱ? በዚህ በረሃ?” ጉድ ፈላ! ደግነቱ ለመመራመር ድካሙ ጊዜ አልሰጠኝም። እንቅልፉ ይዞኝ ጭልጥ አለ። ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የፊሽካ እና እንደ ብራቅ የሚጮኽ ሰው ድምጽ ነው። ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት አካባቢ። ሥልጠናው ተጀመረ በቃ?ወይኔ እንቅልፌ ….

ሥልጠናው?ሥልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ ለዚያ

የሚያስፈልጉ ነገሮች ተሟልተው ተሰጥተውናል። አንድ ጫማ፣ ቱታ፣ ካልሲ፣ ካናቴራ፣ አዣክስ ሳሙና፣ “ብሬዢኒቭ” የሚሉት ቁምጣ። ቁምጣውን በቀድሞ የሶቪየት ሕብረት ፕሬዚደንት ስም ለምን እንደተሰየመ አላውቅም። አለ ነገር ግን እንደዚያ አላሉትም። የኛ ሰው እንዲህ ነገሮችን እያገናኙ ስም የመስጠት ልዩ ሥጦታ አለው። ይቺ ብሬዢኔቭ ቁምጣ ተማሪው በከፍተኛ “የዲያሪያ” (ሸርተቴ) ወረርሽኝ በተቸገረ ጊዜ ብዙ ውለታ ውላልናለች። ወታደራዊ ሥልጠና ከሥርዓት ነው የሚ

ጀምረው። አስቀድሞ ተማሪው በብርጌድ፣ በሻለቃ፣ በሻምበል፣ በመቶ እና በጓድ ይከፋፈላል። የአንድ ሰው ወታደራዊ አድራሻው ይህ ነው። ከፍተኛ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር … እንደማለት ነው። አንድ ብርጌድ 3 ወይም 4 ሻለቃ ሊኖረው ይችላል። ብርጌዱ 4 ሻለቆች የሚኖሩት “አጥሻ” ከሚባለው ከአስተዳደርና ጥበቃ ሻለቃ ጋር ሲደመር መሆኑን አንድ ሰው በቅርቡ ነግሮኛል። አንድ ሻለቃ 3 ሻምበሎች፣ አንድ ሻምበል ደግሞ 3 ወይም 4 የመቶዎች ሊኖሩት ይችላሉ። አንድ የመቶ 32 ሰው ይይዛል። ሁሉም የየራሱ ተጠሪ እና ኃላፊ አለው። ጠዋት በሌሊት ስንነሣ የመጣውና ያልመ

ጣው የሚታወቀው በዚሁ መሠረት ነው። የታመመው፣ በሥንፍና የቀረው ሁሉም ሁሉም “ሪፖርት” የሚደረገው በዚሁ የአደባባይ ሥርዓት ነው። ጦርነት ሜዳ ውለን ቢሆን ኖሮ የሞተው፣ የቆሰለው፣ የከዳው፣ የገባበት ያልታወቀው፣ የተማረከው በዚሁ ከብርጌድ እስከ ጓድ ድረስ በተዘረጋ የዕዝ ሰንሰለት የሚለይ ይመስለኛል። ጠዋት ተነሥተን የምንሰለፍበት እና ቆጠራ የሚደረግበትን ሥነ ሥርዓት “ፎሌን” ቆጠራ ይሉታል። ቦታው ደግሞ “ፎሌን ሜዳ” ይባላል። ትርጉሙን አትጠይቁኝ። ሰልጣኙ በመጀመሪያ ጠዋት የሚያከና

ውነው አካል ማጎልመሻ ወይም ስፖርት ነው። በወታደር ቤት “ላብ ደምን ያድናል” የሚለው አባባል የተለመደ እና አካል ማጎልመሻን የሚያሳይ ነው። በስፖርት ያልተገነባ እና በብቃት ያልቆመ ወታደር ዋጋ የለውም። በአንድ ጊዜ ከ25 ኪሎ ግራም ያላነሰ ሸክም ተሸክሞ ተራራውን ለመውጣት፣ ቁልቁለቱን ለመውረድ ሰውነቱ ብቁ መሆን አለበት። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ያሉ ወታደሮች አብዛኛውን መንገድ በእግራቸው የመጓዝ ግዴታ ስለሚኖርባቸው ጥንካሬ መኖሩ የግድ ነው። አሜሪካን የመሳሰሉ ያደጉ አገሮች ወታደሮቻቸው ከ50 እስከ 90 ፓውንድ ሸክም ቢኖራቸውም በእግራቸው የሚጓዙት መጠነኛ ስለሚሆን ሸክሙ ይህንን ያህልም አይጎዳቸው ይባላል። ለዚህ ሁሉ ግን ወታደር እና

ትዝታ

ስፖርት መዛመድ አለባቸው።የወታደሮች ስፖርት ትዝ የሚለኝ ገና ከ

ሆለታ ጀምሮ ነው። ቤታችን ከከተማ ወደ ጦር ካምፑ ባለው ዋና መንገድ ላይ በመሆኑ ሁል ጊዜ ጠዋት ጠዋት (ከሌሊቱ 10 እና 11 ሰዓት አካካባቢ) ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅሰን አንደኛው የወታደሮቹ ሩጫ ነው። የብዙ ወታደር ኮቴ ከጥቁሩ አስፓልት ጋር ሲጋጭ የሚፈጠረው ድምጽ ሌሊቱን ያደምቀዋል። በመካከል በመካከሉ የአሰልጣኛቸው ድምጽ ወይም ፊሽካው ይሰማል። ከዚያ ውጪ ያለው “እረም-እረም” የሚለው የብዙ ሰዎች እግር ነው። በብላቴ ግን እረም እረም የሚያደርግ አስፓልት የለም። አፈር ብቻ። ብላቴ ቀስ ብሎ ከሚደረገው ጉዞ በመለስ

ተኛ ሩጫ በ“ሶምሶማ” የሚደረገው ይበልጣል። ከሥልጠና መልስም ሆነ ወደ ሥልጠና ሲኬድ ዱብ ዱብ እያሉ መሔድ የተለመደ ነው። በተለይም ከቀን ሙሉ ድካም በኋላ ወደቤት መልስ ሲሆን “ሞራል እያወጡ” (የጋራ ዘፈን እየዘፈኑ) የሚደረገው የሶምሶማ ሩጫ መንገዱን አጭር፣ ድካሙን ቀላል ያደርገዋል። አለበለዚያ እንደ ከተማ ሽርሽር በ“ዎክ” እየተንቀራፈፉ ልሒድ ካሉት እግርም ከመሬት አይነሣ፣ መንገዱም ማለቂያ አይኖረው። ወታደሮች በጋራ ዘፈን እየዘፈኑ በሩጫ የሚያደርጉት ጉዞ ነው “ሞራል ማውጣት” የሚባለው።

ቢጫ ወባ፣ ሸርተቴ፣ “ሻምበል ደቤ” እና ዱካክ

የትንሣኤ ዕለት ግሩም ምሳ አበሉን። ምሳ ሰዓት ላይ “የወባ ክኒን ነው” ተብሎ ሁለት-ሁለት ክኒን እንድንውጥ ተሰጠን። ዋጥን። ከዚያ በኋላ ግን ሁላችንም ደንዝዘን ዋ

ት ወሩ ለሥልጠና ይገባ ከነበረው በሺዎች ከሚቆጠረው ምልምል ወታደር ውስጥ ቁጥሩ ጥቂት የማይባለው በዚሁ “ቢጫ ወባ” ያልቅ እንደነበር አሰልጣኞቻችን ሲናገሩ ሰምቻለኹ። ከቢጫው ወባ ውጪ የግቢው ዋነኛ በሽ

ታ የሆድ መታወክን የሚያስከትለው እና በተማሪው አጠራር “ሸርተቴ” የሚባለው ተቅማጥ/ Diarrhoea ነው። (በሌላ አማርኛ መግለጽ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ‘ስለተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ይቅርታ’ እንዲል የኢትዮጵያ ሬዲዮ):: ይህንኑ በሽታ ነፍሱን ይማረውና ገጣሚ እና ጋዜጠኛ የነበረው መስፍን አሸብር ግሩም በሆነው ግጥሙ፣ “ሸርተቴ”፣ በማይጠፋ መልኩ አስቀምጦት አልፏል። ተማሪውም የዚህን ግጥም ዋና ዋና አንጓዎች እና አዝማቾች በቃሉ አጥንቶት ነበር። በተለይም ከዚህ በታች ያለውን ብዙዎቻችን ዛሬ ድረስ እናስታውሰዋለን።

“ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረትቀጭን ኩታ መሳይአረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።” እያለ ይቀጥላል። (ሙሉውን ግጥም ከጎን ባለው ሳጥን ስር ያንብቡ)

መቸም እንዲህ ባለው ነገር፣ ያውም ታሞ ባለ ሰው፣ መቀለድ ደግ አይደለም። ግን ደግሞ ችግሩንም በሽታውንም እያሳሳቁ እና እያዋዙ ካላለፉት፣ ቢያለቃቅሱ ምን ይገኛል እንጂ ሸርተቴስ ቀላል ተማሪው ላይ አልተጫወተበትም።ገጣሚው መስፍን እንዳለው “Diar-

rhoea” የሆድ በሮች እና መስኮቶች የማይገቱት ቀጭን እና ፈጣን ሯጭ ነው። መጣሁ ሲል ወዲያው ካላስተናገዱት፣ በር ካልከፈቱለት “ግምኛ” ሰውን ያበላሻል፤ ያዋርዳል። ሲመጣ ቦታ አይመርጥም። ጊዜ አይለይም። ከች ሲል ታማሚው እንደ ጥይት ተተኩሶ ከሽንት ቤት ወይም ከአንድ ዛፍ ሥር መገኘት አለበት። ለዚህ እንዲረዳ ታማሚው ልብሱን ማስተካከል አለበት። አንዳንድ ሰልጣኞች “ሽርጥ” ያደርጉ ነበር። ለሌላቸው ደግሞ “ብሬዢኔቭ ቁምጣ” ምቹ ነው። ባለ ሽርጡ ታማሚ ሸርተቴው ሲመ

ጣ የሚጠበቅበት ወደ ዛፍ ሥር መሮጥ እና ሽርጡን በፍጥነት መግለጥ ብቻ ነው። ሱሪ ማድረግ ለመበላሸት ካልሆነ በስተቀር ተመራጭ አይደለም። ብሬዢኔቭ ቁምጣ እግሩ ሰፋፊ፣ ቶሎ ለማውለቅ ምቹ ስለሆነ የተማሪው ባለውለታ ሆኗል። ብዙው ታማሚ ሰልጣኝ ቀን ቀን አየር ለመቀበል፣ ለሽንት ቤት እንዲቀርበውም ውጪ ጎጆዎች ውስጥ መቀመጥን ይመርጣል። በዚህ ጉዳይ ላይ “AN INVEST-

GATION OF DIARRHOEAL DIS-EASE OUTBREAK AT BILATE MILITARY TRAINING CENTRE” በሚል ጥናት ያደረጉት ዶ/ር መኮንን አድማሱ እና አበራ ገይድ (Makonnen Admassu, MD & Abera Geyid, MSc) እንዳስቀመጡት ከሆነ በወቅቱ

ያ አየር ማረፍያ የቆምሁት እንደሚበልጥ ይታሰበኛል። ሽነድ አሁንም ይሸንዳል።ከብዙ ጥበቃ በኋላ ሄሊኮፕተሯ በአቧራ ተከባ ዐ

ረፈች። ተማሪው እንደ እናት ንብ ከበባት። በውስጧ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ መሣርያ የያዛችሁ ተማሪዎች መሣርያችሁን ጣሉ፤ ያለበለዚያ መሣርያ ይዛችሁ ልናሳፍራችሁ አንችልም” ሲል መመርያ ሰጠ። ተሜ ለሁለት ተከፈለ። መሣርያ የያዘው አንጥልም፤ ያልያዘው ጣሉ። ስምምነት ጠፋ። ጩኸት ብቻ ሆነ። አብራሪውም ተማሪዎቹ እንዳልተስማማን ባየ ጊዜ እየኮበኮበ ጥሎን ሄደ።ቀኑ መሸ፤ ፀሐይም ጠለቀች። አሁን ወያኔ ዙርያ

ውን ከብባለች ተባለ፤ ሽነድ። ሁላችንም በፍርሃት ወደ ኬስፓናችን ተመለስን። ግን ምን ተበልቶ ሊታደር? ማሠሰልጠኛው አሁን ተፈትቷል። እስቲ ምግብ ቢገኝ ብለን ወደ መመገቢያ ክፍል ገባን። ባልተከደነ ጎላ ድስት ውስጥ ከምሳ የተረፈ ማካሮኒ በነፍሳት ተወሮ አገኘን። ጎበዝ ሳይንስ አሁን አይሠራም፤ ሰባ ሰባት ሆነን ያችን ምግብ እንደ ነገሩ ተቃመስናት።ሌላው ሥጋት ተረኛ ዘብ የለ፤ ማን ይጠብቅ? ለካ

የሽብር ሌሊት ይረዝማል የሚባለው እውነት ነው።

ከአሁን አሁን ወያኔ መጥታ አፈነችን በሚል ስጋት ስንባንን አደርን። ጠዋት ሁሉም ከየኬስፓኑ ወጥቶ ከፎለን ሜዳ ሳንደርስ ዝቅ ብሎ ካለው አዳራሽ መሳይ ትልቅ ቤት አጠገብ ተገናኘን። በእግር ወደ አዋሳ መሄድ እንዳለብን ተወያየን።

ጥይት እንደ ቆሎ…የተወሰንን ልጆች ምናልባት ከመንገድ የሚያገኘን

ን ስለማናውቅ ጠብ መንጃ መያዝ እንዳለብን ተስማማንና ወደ መሣርያ ግምጃ ቤት ተጓዝን። ወደዚያ ከመጓዛችን በፊት መጋዘኑ መሰበሩን ሽነድ አብስሮናል። መሣርያ ለመውሰድ እንሂድ እንጂ ፍርሃት ግን በልቡናችን መልቶ ነበር። ብቻ ስንፈራ ስንቸር ከመጋዘኑ ገብተን አንዳንድ ነፍስ ወከፍ መሣርያ (ኤስ ኬ ኤስ?) ወሰድን። የጥይቱን ቁጥር አላስታውሰውም። ጠብ መንጃው ከነ ጥይቱ ተስተካክሎ ተያዘ። የቀረው መጓዝ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ጉዞ በአየር ማረፍያው በኩል አቋራጭ ነው ስለ ተባለ በዚያ አቅጣጫ ተጀመረ። አንድ ኪ.ሜ እንደ ተጓዝን ጓዝ መቀነስ እንዳለብን ተነጋገርን። ስለዚህ ቅያሪ ልብስ ብቻ አስቀርተን ሻንጣዎቻችንን ሁሉ ከሜዳው ላይ ወረወርናቸው። ቻዎ ብላቴ!!! ጉዞ ወደ አዋሳ።የግንቦት 19/1983 ዓ.ም ፀሐይ ከወትሮዋ ይልቅ የ

ደመቀችና የፈካች መስላለች። ፀሐይ ከማለት ይልቅ ሀሩር ተብላ ብትጠራ ይሻላል። ላብ እንደ ጅረት በመላው ሰውነታችን እየጎረፈ ሃያ አምስት ኪ.ሜትሮች ተጉዘን ዲምቱ ከምትባለው መንደር ደረስን። ዲምቱ የገጠር ከተማ ብትሆንም ስደተኛውን ተማሪ ለመቀበል ግን አቅም ነበራት። በየ ደሳሳ ቤቶች ውስጥ የመብልና የመጠጥ ንግድ የሚጧጧፍባት መንደር ናት። እህል ውኃ ፈልገን ቀመስን። አሁን ትንሽ በርትተናል። ከሰውም ተቀላቅለናል።ቀጣዩን ጉዞ ከመጀመራችን በፊት ከፊት ለፊታች

ን ስላለው ነገር መረጃ ማግኘት ግድ ነው። ስለሆነም የከተማዋን ሰዎች ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ጠየቅናቸው። የሚያውቁትን ያህል ነገሩን። ከብላቴ የመጡ ጥቂት የአየር ወለድ አባላት ከድልድዩ አጠገብ ሆነው ማንኛውንም ዓይነት መሣርያ ከያዘ ሰው ቀምተው እንደሚወስዱ አረዱን። “ጓዛችንን ሁሉ ጥለን የያዝነውን መሣርያ፣ ከሃያ አምስት ኪ.ሜትሮች በላይ በዚያ በረሃ በመሸከም የደከምንበትን መሣርያ እንዴት ይቀሙናል?”፣ “አሁን ምን እናድርግ?”፤ ሌላ ጭንቀት። ጦርነት ልንከፍት? ጊዜው የከፈተብንን ጦርነት መች ተወጣነውና?በኋላ መሣርያዎቻችንን መሸጥ እንዳለብን ተስማ

ማን። አንድ ጠብ መንጃ በ250 ብር፣ አንዲት ጥይት በ0.40 ሣንቲም ተሽጠ። አሁን ከውትድርና ጋር የሚያይዘን ምናልባት ለታሪክ የያዝኳት ቱታ(ሰማያዊዋ) ብቻ ካልሆነ እኔ ዘንድ አንዳች ነገር የለም። ብቻ በመንገድ የመቁሰል አደጋ ቢደርስብን ለመጀመርያ ርዳታ መስጫ ይሆናል ብየ የያዝኩት አንድ ጠርሙስ አዮዲን እጄ ላይ ነበር። አሁን ሳስበው ጠርሙስ ሙሉ አዮዲን ተሸክሜ ያን ሁሉ መንገድ መጓዜ ይገርመኛል። ጠብ መንጃችንን ሸጠን ብራችን ቋጥረን ፀሐይ ማዘቅዘቅ እንደ ጀመረች ለቀጣዩ ጉዞ ተነሣን።

የቅርብ ሩቅእረኞች ከብቶቻቸውን እየነዱ ወደየቀዬያቸው እ

የተመለሱ ነው። ከቁመታቸው በላይ ዘለግ ያለና ሰፋፊ ጦር የያዙ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ልዩ ፍጥረት ተገርመው ያዩናል። ይህ ደግሞ ሌላ ፍርሀት ፈጠረብን። ቀደም ሲል ከሞሪቾ እስከ ብላቴ ባለው መንገድ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ከባህል የተነሣ ወንድ ገድለው ይሰልባሉ የሚል ዜና ሰምተን ነበር። ይህን ዜና በሚያጠናክር መልኩ ያን አስፈሪ ጦር ያዘው በልዩ ትኩረት ሲያዩን ደግሞ በውስጣችን ከፍርሃት የላቀ ፍርሃት ተሰማን። ፀሐይዋ ከእኛ ጋር

ውድድር የያዘች ትመስላለች። እርሷም ወደ ማደርያዋ ለመግባት ትቻኮላለች። ዓይኖቻችን በጨለማው መያዝ ጀምረዋል። የምናየው ከአጠገባችን ያለውን ብቻ ነው። እነዚያ ባለ ጦሮች ይጠራሩ ጀመር። ምን እንደሚነጋገሩ አናውቅም። ብቻ ፍርሃት የነገሠበት ልባናችን እኛን ሊገድሉ እየተነጋገሩ እንደሆነ አድርጎ ነገረን። ተስፋችን ተሟጥጦ የእነዚያ ሰዎች አስፈሪ ጦሮች

ካሁን አሁን ተወርውረው ከሰውነታችን ላይ ተተከሉ እያልን በምንሸማቀቅበት ሰዓት የቀይ መስቀል ድርጅት ተሳቢ ካላብረስ መኪና ከመቅጽበት ከፊታችን ድቅን አለ። ሾፌሩ በዚያ ጨለማና ወጣ ገብ የገጠር ማሳ ውስጥ እንዴት እንዳዞረው አላውቅም። ብቻ “ቶሎ ቶሎ በሉና ከላይ ውጡ “’ ሲለን የፍርሃት ካባዬ ከላዬ ሲወድቅ ታወቀኝ። ሁለተኛው መኪና ከኋላ ያሉትን ተማሪዎች ሊሰበስብ ከነፈ። ሾፌሩ ከካርቶን ውስጥ ያለውን “ጋሌጣ” ወይም “ኮቸሮ” እንድንበላውም አዘዘን።መኪናው ሞሪቾ ከተማ ካለ አንድ የቀበሌ ጽ/ቤት

ቅጽር ግቢ ገባና” ውረዱ” ተባልን። እኛ ወርደን እ

“ሸርተቴ”እንቅልፍ የምትነሳ፣ ሌት የማታስተኛህሊና ሞጋቹ፣ ክፉ ወንጀለኛመቼም አንላቀቅ፣ አንተ ተንኮለኛክስ አቅርቤያለሁኝ፣ ለፈራጁ ዳኛሳትታይ አድፍጠህ፣ ተሰውረህ ከ’ኛገብተህ የተገኘህ፣ ከዚች ከብላቴበላ ልበልሃ፣ ተጠየቅ ሸርተቴ!ይዘን የመጣነው፣ የጠራ ሆድ ነበርአምጦ ሚያገሳ፣ ድምፁ የሚያሸብርሲሻው የሚያሽካካ፣ ልክ እንደመትረየስአሊያም እንደ ፈንጂ፣ ሙት የሚቀሰቅስወይም እንደ ጎማ፣ ምስማር እንደበሳውብሶት ‘ሚተነፍስ፣ ሰው ሳያይ ሳይሰማው።ሸርተቴ ባንተ ግፍ፣ ተንኮል ሳይሰራሆዳችን ነበረ፣ የኮራ የደራልሳኑ ያማረ፣ ኮስታራ ቀብራራ፤ምን ያደርጋል ታዲያ በጦርህ ተወጋድምጹ ጥፍት አለ ልሳኑ ተዘጋህገ-ሥርዓቱ፣ ፈረሰ ተናጋ።

አቤት ያንተ ተንኮል፣ አቤት ያንተ ሥራአብሪ ጥይት የለህ፣ መንገድ የሚመራ።ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረትቀጭን ኩታ መሳይአረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።አይ አወራረድህ፣ አይ አተኳኮስህቴትራ ሳይክሊን፣ ሚዝል አይመልስህ“ብሬዢኔቭ ቁምጣ”፣ ሱሪ አያግድህሆድን ፈለጥለጥለጥ፣ ቁርጥ ቁርጥርጥርጥሸርከት ሸርከትከትከት፣ ዓይናችንም ፍጥጥሸራ ለመሸረር፣ ፋታ የማትሰጥበቀላው አሸዋ፣ በሚቆረቁረውጀግናን በባዶ እግር፣ ይዘህ ያሯሯጥከውሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑሸርተቴ ጅንኑ፣ ኩሩ ዘለግላጋው፣ ስንቱን አደረከው አጉል ኩራተኛ?ሰው የማያናግር ሌሊት የማይተኛ።….ከሞቀ ጨዋታ፣ ወጉ ከደራበትስንቱ ፈረጠጠ፣ ዘለለ በመስኮት?ከመኖሪያ ታዛ፣ ከኬስፓኑ ነቅለህከጎጆ ከተትከው ፍራሽ አስነጥፈህ።ሆዱን ሊያስታግሰው ተርቦ ተጠምቶእጁን ሲሰነዝር፣ ‘ከሜስ’ ቤት ገብቶአንተ መጣህና፣ ገበታውን ትቶስንቱ ፈረጠጠ፣ ሾርባውን ጎልቶ?አንጀቱን ሰርስረህ፣ ከግርጌ ከስሩአይ አፈጣጠንህ፣ የሥራህ ነገሩ።ሲሻህ አረንጓዴ፣ ሲልህ ትቀላለህወይም ቢጫ ሆነህ፣ ትቀይረዋለህአንዳንድ ጊዜማ፣ ድብልቅልቅ ትልናትመሳሰላለህ ከቀስተ ደመና።

ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረትቀጭን ኩታ መሳይአረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።” (መስፍን አሸብር፣ በ1983 ዓ.ም ብላቴ ጽፎት፣ “ጠብታ ፍቅር” በሚል ከታተመው መ

ጽሐፉ የተወሰደ።)

ወደ ገጽ 22 ዞሯል

ወደ ገጽ 22 ዞሯል

ልን። ግማሹ በመኖሪያው አዳራሽ (ኬስፓን) ግማሹ በየዛፉ ሥር ውድቅድቅ ብሎ ዋለ። ከመጠን በላይ የሆነ ነገር ሰጥተውን ይሁን ወይም ሌላ ምክንያት ይኑረው አላወቅኹም። ብቻ ጅላጅል ሆነን ማሳለፋችን ትዝ ይለኛል። “ቢጫ ወባ እንዳያጠቃችሁ” የሚለው አባባል ብዙ ጊዜ ስለሚነገር ከፍተኛ ፍርሃት ነበረብን። ዝዋይ ለጥቂት ወራት በነበርኩበት ጊዜ

ወባ አልያዘኝም። የብላቴውንም “አውጣኝ፣ አውጣኝ” እያልኩ ከረምኩ። በተለይ የብላቴው “ጭንቅላት ላይ የሚወጣ እና ቶሎ ሕክምና ካላገኘ አሳብዶ የሚገድል ነው” (cerebral malaria) ስለሚባል በሕጻንነታችን እንፈራው የነበረው “ጭራቅ” ዓይነት ስሜት ፈጥሮብን ነበር። በየስድስ

Page 22: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)22 ሀበሻዊ ቃና

ዛት ይገኛሉ። በተለይ ጁባ እና ናይሮቢ።ናይሮቢን ከሞይ ጎዳና ዳር ቆሞ ለሚመ

ለከት በግልጽ በሚታይ ኹኔታ ከተማዋ በሁለት ተከፍላ ትታያለች። ዌስትላንድ (Westland) እና ኢስትላንድ (Eastland) በሚል። ምዕራቡ የከተማዋ ክፍል በአረንጓዴ የተሸፈነ፣ አልፎ አልፎም ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች ያሉበት፣ በብዛት ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የኬንያ ዜጎች፣ ሕንዶች እና የሌሎች አገራት ዜጎች የመኖሪያ ሥፍራ እና መዝናኛዎች የበዙበት ነው። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚኖሩባቸው የኬኒያ መንደሮች መካከል አንዱ የኾነው “ሐርሊንግሃም” በዚሁ ምዕራባዊ የናይሮቢ ክፍል (ዌስትላንድ) ይገኛል።ወደ “ያያ የንግድ ማዕከል” የሚወስደው

ን መንገድ ተከትሎ ለሚጓዝ ሁሉ ከዳገቱ ላይ ኾኖ “ሐርሊንግሃም” የሚባለው አካባቢ ይቀበለዋል። የአካባቢው ሰላማዊ መኾን እና ማራኪነት አቅሙ ያላቸውን ሐበሾች የሚስበውን ያህል፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ በአነስተኛ ዋጋ በጋራ ለመኖር ለቆረጡ የሐበሻ ስደተኞችም መሰባሰቢያ ስፍራ ነው። ሐርሊንግሃም ለመድኀኒዓለም ቤተክርስቲያን ቅርብ ኾኖ መገኘቱም የበለጠ ተመራጭ አድርጎታል። ዐይንዎን በአካባቢው በማይጠፉት ሐበሾች ላይ ያሳርፉ። ምን አልባት ለናይሮቢ አዲስ ከኾኑ ኤርትራዊ፣ ኢትዮጵያዊ ከሚለው መለያ በተጨማሪም “አምቼዎችንም” እዚህ ያገኟቸዋል። አብዛኞቹ አምቼዎች በሁለቱ ወገኖች መካከል የመዋለል ስሜት ይሰማቸው እንጂ ወደ ኤርትራዊነት ማጋደላቸው አልቀረም፡፡ በተለይም ግማሽ ኤርትራውያኑ በቂ የሚሉትን ምክንያት ያሰቀምጣሉ፡፡ ለአብዛኞቹ ከኢትዮጰያ ወገን ካሉ ዘመዶቻቸው ይልቅ ከኤርትራ በኩል የሚዛመዱ የመረዳዳት ባህላቸው ጠንካራ መኾን ለዝንባሌያቸው ምክንያት ነው፡፡ በፀጋም ይሄን ሃሳብ ያጠናክራል፡፡ “በስመ ኤርትራዊ እርዳታ ብት

ጠይቀ የሚነፍግህ የለም፡፡ አገር ቤት ብትሄድ ደግሞ ሰርጉም ሃዘኑም ለብቻህ ስለማትወጣው መደጋገፉ የጠነከረ ነው”በናይሮቢ ያለው የስደተኞች የአኗኗር ዘ

ይቤም ይሄን የሚያሳይ ነው፡፡ ኤርትራውያኑ (አምቼዎቹን ጨምሮ) በአንድ ስፍራ አጀብ ብለው መኖርን ይመርጣሉ፡፡ ለአንዱ በተላከው የድጎማ ገንዘብ የተቸገረ ወገናቸውን ጭምር ይረዱበታል፡፡ መጠለያ የሌላቸውን በዙር በየቤታቸው ከማስጠለል አንስቶ ወርሃዊ የቤት ኪራይ በመክፈል ጭምር አለኝታነታቸውን ያሳያሉ፡፡ ያያ መድኀኒዓለም- ናይሮቢየሐርሊንግሃም ጉዳያችንን ከጨረስን “አ

ምቼዎች” በስፋት ወደሚኖሩበት ወደ ምሥራቃዊው ናይሮቢ እናዝግም፤ ከአምቼው ማኅደረ ጊላይ ጋራ። የናይሮቢ ምሥራቁ ክፍል ከምዕራቡ በተቃራኒው ብዙ ለምለም ነገር የማይታይበት፣ ድህነት የደቆሳቸው መንደሮች በብዛት የሚገኙበት እንዲሁም ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸውን ሥፍራዎች አካቶ የያዘ ነው። ከ“ኢስሊ” ሌላ “ቻይሮድ” ወደ ሚባለው ሰፈር ቢያቀኑ ብዛት ያለቸውን ሐበሾች ችምችም ባለው መንደር መካከል ያገኟቸዋል። በዚህ ሥፍራ ዳር እና ዳር በአማርኛ የተጻፉ ማስታወቂያዎችን ይመለከታሉ።ከ“ካተሪና ሎጅ” ፊት ለፊት “አሥመራ ሆ

ቴል” ጎላ ብሎ ይታያል። ኢትዮጵያውንም በብዛት ቢገኙም የኤርትራውያኑን ያህል አይኾኑም። ብዙኀኑ በምግብ ሥራ፣ በችርቻሮ እና በመጠጥ ንግድ ራሳቸውን ያስተዳድራሉ። አካባቢው ከኪስዋሂሊ እና ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ይልቅ ትግርኛ እና አማርኛ ጎልተው የሚነገሩበት ነው።ካሪያኮር እና ፓንጋኒ የሚሉት አካባቢዎ

ች በሐበሻ የሚዘወተሩ ቢኾንም የኤስሊን ያህል ግን ሐበሻን አያስተናግዱም። ኤስሊ የሶማልያውያን የበላይነት እየነገሠ የመጣበት ትልቁ የንግድ ሥፍራ ነው። በብዙ መ

ልኩ ከአዲስ አበባው መርካቶ ጋራ ይቀራረባል። ይኹንና ኤስሊ የሚንቀሳቀሰውን የዶላር መጠን መርካቶ በዓመት ለማንቀሳቀስ አቅም ያለው አይመስልም። በዚህ ወከባ እና ግርግር በበዛበት ሥፍራ ሐበሾችም የራሳቸው ድርሻ አቸው። ሁለተኛ፣ ዘጠነኛ፣ ዐሥረኛ እና ዐሥራ አንደኛ የሚባሉት መንገዶች በብዛት ሐበሾችን የያዙ ክፍሎች ናቸው። ሚሚ ሱቅ፣ ቴዲ ሙዚቃ ቤት፣ የባህል መደብር . . የመሳሰሉት የአማርኛ ማስታወቂያዎች ጎልተው የሚታዩት ግን በተለይ በዘጠነኛ እና በዐሥረኛ መንገዶች ነው።በናይሮቢ ጉራንጉሮች ውስጥ የእሱን መ

ሰል ታሪክ ያላቸው አሚቼዎች ጉዞ ገታ ያድርጉ እና ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ይጓዙ። ከናይል ወንዝ አቅራቢያ ከተሠራው እና የጁባ ዐይን ከኾነው “ብሪጅ” ሆቴል ተነስተው ጉዞዎን ቢያደርጉ እዚህም እዚያም ሐበሾችን ይመለከታሉ። “ኮኞ ኮኞ”፣ “ገበል ኩጁ”፣ “ኒው እና ኦልድ ከስተመስ”..እንዲሁም በመላዋ ጁባ ቢዘዋወሩ እንደልብ የሚያገኙት እነርሱኑ ነው። ጁባ ሮድ በሚገኘው “ኩሽ ሆቴል” ገብተው ዐይንዎን ጣል ቢያደርጉ እዚህም እዚያም ሐበሾች ክብ ሠርተው ሲያወጉ ስልክ ሲደውሉ፣ ጥሪ ሲቀበሉ ያያሉ።

ጁባ...ደቡብ ሱዳንጁባ የደቡብ ሱዳን ልብ የኾነች የንግድ ከ

ተማ ነች። ወደ ምግብ ቤቶች ጎራ ሲሉ የሚያስተናግዱዎትም አዲስ አባባ የሚያውቋቸው ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ሊኾኑ ይችላሉ። ጁባ ነፍስ የምትዘራው በኤርትራውያን እና በኢትዮጵያውያን ነው። ከከፍተኛ የመንግሥት አማካሪዎች እስከ ሾፌር፣ ነጋዴ፣ አስተናጋጅ፣ ወያልነት….ድረስ ጁባ ትዘወራለች። አምቼዎች ከኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን መሳ ለመሳ ኾነው ሕይወታቸውን ይገፋሉ። ቢኒያም እዚህ ይኖራል። ማኅደረ ደግሞ ኬንያ። ብዙዎች “አምቼዎች” እንደ ቢኒያም አሊያም እንደ ማኅደረ ዕድለኞች አልነበሩም። ዛሬ በሕይወት ተርፈው ታሪካቸውን ለማውራት ዕድሉን አላገኙም።

አሳዛኙ ዕጣ አንዳንዶቹ እጅግ ዘግናኝ በሚባለው የባ

ድመ ጦርነት ከለብ ለብ ሥልጠና በኋላ እንዲሳተፉ ተደርገዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ያባረራቸው ብዛት ያላቸው አምቼዎች አሥመራ በገቡ በስድስት ወር ጊዜ ወስጥ ወደ ሳዋ ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንዲሄዱ ይደረጉ ነበር። የሳዋ ስምንተኛ እና ዘጠነኛ ዙር ሠልጣኞች ብዙዎቹ አምቼዎች ናቸው። ሥልጠናውን እንደጨረሱ እጅግ ዘግናኝ እና ለሰው ሕይወት ደንታ ባልነበረው የባደመ ጦርነት ተማገዱ። ብዙዎቹም ሕይወታቸውን እና አካላቸውን አጥተዋል። አሳዛኙ ዕውነታ ደግሞ “አምቼ”ዎች በጦርነቱ ወቅት በሁለቱም ወገኖች የማይታመኑ መኾናቸው ሕይወታቸውን የበለጠ ያከፋው እንደነበር አዲስ ነገር ዩጋንዳ -ጂንጃ ውስጥ ያነጋገራቸው ለጉዳዩን ቅርበት የነበራቸው ግለሰብ ያስረዳሉ። “ጦርነቱ ላይ ስለ ተሳተፉት ወጣት ትውልደ ኤርትራዊ ዜጎችን (አምቼዎችን) አስብ። በተለይ አንዳንዶቹ ወጣቶቹ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የሚያስቡ፤ ከአዲስ አባባ ውጭ ሌላ ከተማ ዐይተው የማያውቁ ነበሩ” ይላሉ ውስጥ አዋቂው። “በሕይወትህ አስበህ እና ገምተህ በማታውቀው መልኩ ለማታውቀው አገር ወታደር ኾነህ ራስህን ብታገኘው ምን ይሰማኻል? ከእኛ ወዲያ የአበደ አለ?” ሲሉ በወቅቱ የነበረውን ኹኔታ በጥያቄ መልክ ያስቀምጡታል።ማኅደረ ይህን መሰል ታሪኮችን ኖሯቸዋ

ል። ተረት የሚመስሉት እውነተኛ የትራጄዲ ታሪኮች ቁጥር ስፍር የላቸውም። “ከአዲስ አባባ ወጥቶ የማያውቅ የ18 ዓመት ልጅ ከአባቱ ጋራ ወደ ኤርትራ ተባረረ፤ ለምን እንደተባረረም በቅጡ ያልተረዳ ወጣት። አሥመራ በገባ በስድስት ወሩ ሳዋ ገባ፤ ባድመ ላይ ሞተ። ለምን ሞተ?…” ማኅደረ ይጠይቃል። አባቱ የልጃቸውን ሞት ከሦስት ዓመት በኋላ ሰሙ። ባዶ ሕይወት። የ

ማኅደረ- አምቼ ትዝታዎች፤ በናይሮቢ።ከ10ኛ ብሔረሰብ ወደ አምቼዎች

ዓለም?“አምቼ”ዎችን አንዳንዶች “ግራ የተጋቡ”

ሲሉ ይገልጿቸዋል። የአዲስ ነገር ዘጋቢዎች ይህን ዘገባ ለማጠናቀር በተንቀሳቀሱባቸው የምሥራቅ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ናይሮቢ፤ ካምፓላ፣ ጁባ፤ ካርቱም፣..እና ሌሎች ትንንሽ ከተሞች ግን “አምቼ”ዎች ያላቸው ማኅበራዊ ፋይዳ አይተዋል። አምቼዎች “ድልድዮች”፣ “ሰላም አስከባሪዎች” የሚሉ ስያሜዎች ያገኙትም በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ባላቸው አበርክቶት ነው። “አምቼ”ዎች የኢትዮጵያን እና የኤርትራን ሕዝቦች የሚያገናኙ፤ በሁለቱም ውስጥ የሚገኘውን ደካማ እና ጠንካራ ጎን የሚረዱ ናቸው። በሁለቱ ሕዝቦች መካከል አንዱ ለአንዱ ያለውን አሉታዊ ግምት ለመፋቅ በአንድ ተመሳሳይ ወቅት ለኤርትራም፤ ለኢትዮጵያም ወግነው የሚከራከሩ ናቸው።በጁባ፣ ናይሮቢ፣ ካምፓላ፣ በመሳሰሉ የ

ምሥራቅ አፍሪካ ከተሞች በምድር ወገብ ፀሐይዋ ማዘቅዘቅ ስትጀምር ሐበሾች ወደ ከፈቷቸው ቡና ቤቶች እና ባሮች ጎራ በሉ። የአብርሃም አፈወርቂን ሙዚቃ እንደሰማችሁ የቴዎድሮስ ካሳሁንን “ኻብ ዳህላክን” ወዲያው ልታደምጡ ትችላላችኹ። ሌላም ዘፈን …፤ “አዲስ አበባ ቤቴ” የሚለውን ዘፈን ጭምር ሁሉ። እነዚህን ዘፈኖች ሲሰሙ ያስከፈቱትን የላጋር ቢራ ቶሎ ቶሎ የሚጎነጩ …ሲጋራቸውንም በላይ በላዩ የሚያጨሱ ወጣቶች ልትታዘቡ ትችላላችሁ። በሙዚቃው ውስጥ ሕይወታቸውን እያነበቡ ትላንትን፣ ዛሬን እና ነገን እያሰቡ እንደሚኾን አትጠራጠሩ።ብዙዎች “አምቼ”ዎች እንዲህ ዐይነት ሙ

ዚቃ ሲያደምጡ በትዝታ እና በቁጭት ወደ አዲስ አበባ በሐሳብ መመለሳቸው አይቀርም። በአንዳንዶች ሕሊና ከዐሥር ዓመት በፊት ያዩዋትን አዲስ አበባ በዐይነ ሕሊናቸው ድቅን ትላለች። “አምቼ”ዎች ላደጉባት አዲስ አበባ ልዩ ፍቅር እና ግምት አላቸው። ከአዲስ አበባ የተነጠሉበት መንገድ

ደግሞ አዲስ አበባን በበጎ ብቻ እንዳያስታውሷት አድርጓቸዋል። ጁባም ኾነ ናይሮቢ፣ ካምፓላም ኾነ ካር

ቱም ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን አብረው የሚታደሙባቸው የምሽት ክበቦች አንዳንድ ጊዜ ጸብ አያጣቸውም። በአንድ ዜማ አብረው ሲደንሱ የነበሩት እና ራሳቸውን “ሀበሻ “ እያሉ የሚጠሩት ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ከአፍታ ቆይታ በኋላ ሊጣሉ ይችላሉ-እንደ ድንገት። “በሀበሾቹ” መካከል ፀብ ከተነሳ “ሰላም አስከባሪዎች” በገላጋይነት ከተፍ ይላሉ። “ጁባ ላይ አምቼዎች ‘ሰላም አስከባሪዎች’ ተብለው ይታወቃሉ” ይላል ቢኒያም።በመላው የምሥራቅ አፍሪካ ከተሞች ተበ

ትነው የሚገኙት ከኢትዮጵያውያን እና ከኤርትራውያን ስደተኞች ወገኖቻቸው መሳ ለመሳ የስደት ኑሮቸውን እየገፉ የሚገኙ “አምቼ”ዎች ልክ በመላው ዓለም እንደተበተኑ የስያሜ ተጋሪዎቻቸው ሁሉ እርስ በእርስ ባላቸው ትሥሥር ይታወቃሉ። “I Love being Amiche” በተሰኘው የአምቼዎች ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አስተያየቱን የሰጠ አንድ ወጣት እንዲህ ሲል ምኞቱን አስቀመጠ። “አምቼዎች አንድ ላይ የምንኖርበት ዓለም ቢኖረን እንዴት ደስ ባለኝ።”ሕልማቸው በእነርሱ ምኞት ብቻ እንደ

ማይሳካ ያውቁታል። ሥልጣን ላይ ያሉት የፖለቲካ ቡድኖች ለጥያቄዎቻቸው የሚኾን መልስ ይዘዋል። ጉዳዩን ለማየት የሚያስችል ፍፁም ፈቃደኝነት ባይታይባቸውም። ማኅደረ ግን ለማንነት ጥያቄው መፍትሄ ያለው ይመስላል። “ከኢትዮጵያዊነት እና ኤርትራዊነት በላይ የጨርቆስ እና የአባ ሻወል ልጅ መባል ይበልጥብኛል” ይላል። ብዙ አምቼዎች በሚገናኙበት የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ሰለሞን ዘርዐይ የሚባል አባል ይህችን ግጥም አሰፈረ።ብለነው ብለነው ካልኾነ ነገሩአምቼና ዶላር የትም ነው አገሩ።

ንዳበቃን መኪናው ለሌላ ተልእኮው ሄደ። የሞሪቾን የአየር ንብረት ሁኔታ ባለውቅም የዚያን ሌሊት ግን ሊዩ የሆነ ብርድ ነበር ያደረባት። ለተማሪው የሚበቃ ክፍል ባለ መኖሩ ያደርነው ሜዳ ላይ ነው። እንኳን ያቺን የሞት ቀጣና አለፍናት እንጂ ብርዱስ ምንም እንደማይለን ተረድተናል። ደግሞም በመንገድ የዛለ ሰውነት በቀላሉ በእንቅልፍ ስለሚሸነፍ ስጋት አልገባንም። ሁላችንም “ሿ” ብለን ተኛን።እኩለ ሌሊት ካለፈ በኋላ አንድ ኀይለኛ

ድምፅ ቀስቀስን። አንድ ተማሪ ነው፤ ያለቅሳል፤ ይጮኻል፤ ይስቃል፤ በሀገሪቷ ላይ፤በተማሪው ላይ፤ በራሱ ላይ ስለሆነው ነገር ይናገራል።መጀመርያ ላይ እንቅልፍ እምቢ ብሎት መስሎን ነበር። በኋላ ግን የአእምሮ ጭንቀት አግኝቶት እንደ ሆነ ተረዳን። ያለቅሳል፤ ያንጎራጉራል። የሚናገረው ቃል ሕሊናን ይረብሻል። በዚህ ጉዳይ የምናደርገው ነገር ጠፍቶን ግራ እንደ ተጋባን ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ሲሆን ሁላችንም ወደ አዋሳ ጉዞ ጀመርን።በጧቱ ብዙ ገሰገስን። ፀሐይ ወጥታ ሰማ

ይ ምድሩን ስናይ አዋሳ እጅግ ቅርብ ሆና ስለ ታየችን በተስፋና በሞራል ብንራመድም እርሷ ግን እንዳንደርስባት የምትሸሽ ይመስል በቀላሉ ልትደረስ አልቻለችም። እኛም ጉልበታችን መዛል ጀምሯል። መቼም የተጀመረ መንገድ ሳይፈጸም ከመሃል መቅረት የለ ጥርሳችንን ነክሰን ተጉዘን አዋሳ ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ገባን። ግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም።

ባዶዋ ከተማአዋሳ ጭር ብላለች። ምግብ ቤቶቿ ተግ

ባራቸውን ያቆሙ ይመስላሉ። ሻይ ለመጠጣት ብንፈልግ እንኳ ዬት ተገኝቶ? ቡና ቤቶችና ሆቴሎች በፍርሃት ስለ ተዘጉ መኝታ ማግኘት አልተቻለም። ስለዚህ ማረፍያ ቢገኝ ብለን ወደ አዋሳ እርሻ ኮሌጅ አቀናን። ኮሌጁ ከብላቴ የተመለሱ ተማሪዎችን ለመቀበል በሩን ክፍት አድርጓል። ያ ግቢ ላለፉት ሁለት ወራት ግን ዝግ መሆኑን ልብ ይበሉ። አሁን የሚታየኝ ምግብ ውኃ አይደለም፤ ብቻ ጎኔን የማሳርፍበት ቦታ። እግሮቼ ተላልጠዋል። ከዚህን በላይ እንኳን መራመድ መቆም ከማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። ውስጥ እግሬ አብጧል።ከኮሌጁ ግቢ እንደ ገባሁ እንደ ምንም ወደ አንድ የተማሪዎች ማደርያ ክፍል አመራሁና ካገኘሁት ተደራራቢ አልጋ ከላይኛው ቆጥ ላይ “ዧ” ብዬ ወደቅሁ።

እንደ ሞት የከበደ እንቅልፍ ወሰደኝ። ምን ያህል ሰዓት ወይም ደቂቃ እንደ ተኛሁ አላስታውስም። ብቻ ከዚያ ጣፋጭ እንቅልፍ ከታችኛው ተደራቢ ተኝቶ የነበረው ጓደኛዬ (ሲሳይ ለማ) ሲገላበጥ ባንኜ ተነሣሁ። “ለምን ቀሰቅስኸኝ?” ብዬም ጮኹበት። እስቲ ጎንህን እየው? አለኝ። ልብሴን ገልጬ ጎኔን ባየው ጤፍ ላይ ተኝቼ ገላዬ ላይ የተደመደመ ይመስል ትኋኑ እላዬ ላይ ተደምድሟል። የመጨረሻ አዘንሁ።አይደል ክፍሉን ግቢውን ጠላሁት። በል

ብሴ ውስጥ የተሰገሰጉት ትኋኖች እንደ ረመጥ ይለበልቡኝ ጀመር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ትኋኖችን ይዤ ከዚያ ግቢ ወጣን።የት እንሂድ?የት እንግባ? ማን ያስጠጋና

ል? ከተማዋ ውስጥ መንከራተት ጀመርን። ከብዙ ድካም በኋላ አንድ የአኢሴማ ጽ/ቤት (03?) አገኘንና እንዲያሰጠጉን ለመናቸው። የጽ/ቤቱ ወለል ሊሾ የሚባለው ነው። ምንጣፍ ወይም ሰሌን ነገር አልነበረውም። ሴቶቹም በዚያ ሊሾ መሬት ላይ ገብታችሁ ተኙ ማለቱ ከብዷቸዋል። ግን የሊሾው ቅዝቃዜ ከድካማችን ስለማይብስ እሽ እንዲሉን ተማጸናቸው። ሲፈቅዱልን ገብተን አቧራዋን እፍ ብለን ተኛን። ግንቦት 20፣21። ደስታ ከረሜላ የምታክል ዳቦ በ0.25 ገዝተን ረሃባችንን ማስታገስ ጀመርን።ግንቦት 21 ጠዋት ከመኝታችን ተነሥተ

ን በር ላይ ቆመን የዕለቱን እንቅስቃሴ እየተመለከትን ነው።ከእኛ በፊት ከብላቴ የወጡት ተማሪዎች በሰላም ኬንያ መግባታቸው ተወራ። አንድ የአየር መቃወሚያ መሣርያ ያለበት መኪና ካለንበት በር አጠገብ ሆኖ ወደ ኬንያ መሄድ የሚፈልግ እንዳለ ይጠራ ጀመር። ጓደኛዬ የኔወንድም እንየው ካልሄድን ብሎ ሞገተን። ብቻ እንደ ምንም አሸነፍነውና አስቀረነው። ግንቦት 22፣ 23። ወያኔ ሀገሪቱን መቆጣጠሯ እውን መሆኑ እየታመነ መጣ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ እስካሁን ደቡብ ዕዝ እጁን አልሰጠም፤ ተማሪውም ወደ ኬንያ አልገባም፤ነገር ግን ከደቡብ ዕዝ ጋር ተቀላቅሏል ብለው ያወሩ ጀመር። ለእኔ የሁሉም ነገር አልታይህ ብሎኛል። የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ መኪና አግኝቼ አዲስ አበባ ከቤተሰቤ ዘንድ መድረስ።

እንስቷ “ወያኔ” ግንቦት 23/1983 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 አካባ

ቢ የአንዲት አይሱዙ መኪና ረዳት ሻሻመኔ የሚሄድ ሰው እንዳለ ጠየቀን። ጎበዝ ትንሽም ብትሆን መቅረቡ ይሻላል በሚል አሳብ ሦስት ሦስት ብር ከፍለን ወደ ሻሻመኔ ተጓዝን። ሻሻመኔ የደረስነው 8፡00 አካ

ባቢ ይመስለኛል። ገና ከመኪናው ሳንወርድ አንዲት ሚኒባስ ታክሲ አዲስ አበባ ልትሄድ ረዳቷ ሲጣራ ሰማንና ሃያ ሆነን ተሳፈርን። በአርባ አርባ ብር ከፍለን ጉዞ ወደ አዲስ አበባ። አሁንም ግን ፍርሃት በውስጤ ነበር። ወያኔ በመንገድ ብትይዘንስ? እርሷን ልንወጋ እንደ ዘመትን አይደል የምታውቀው? ብታስረንስ? ብትገርፈንስ? ዘማች ተማሪዎች መሆናችንን እንዴት ታውቃለች? ቢያንስ ለማስታወሻ ብለዬ የያዝኩት ሰማያዊ ቱታ ከእኔ ጋር አለ። ደግሞ ያ ጠርሙስ ሙሉ አዮዲንም አልተጣለ። ሌሎቹም እንዲሁ አንድ ነገር አያጡ። ብቻ መንገዳችን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥተን መጓዝ ጀመርን።ወያኔን በቴሌቪዥን መስኮት ከማየት በስ

ተቀር በአካል አይቼ አላውቅም ነበር። በደርግ መገናኛ ብዙኃን የሚነገረንም ነገር ወያኔን ልዩ ፍጥረት እንደ ሆነች አድርጎ የሚያቀርብ ነበር። እንኳን ሌላ “አንቺ” የሚለውን ቅጽል እንኳን ውስጤ እንዴት ገብቶ እንደ ቀረ አላውቀውም። ያችን ልዩ ፍጥረት አድርጌ የሳልኋትን ጉድ ወያኔን ለመጀመርያ ጊዜ ያየኋት በዚያች ሚኒባስ ሃያ ሆንን ወደ አዲስ አበባ እየመጣን ሳለ ሞጆን አልፈን ደብረ ዘይት አየር ኀይል ሳንደርስ በመካከል ካለው ስፍራ ነበር። ልክ ስናያት ከእኛ የምትለይበትን ነገር ለማወቅ ነበር የጓጓሁት። ግን ከጠጉራቸው መንጨባረር ውጪ የኔው አምሳያዎች ነበሩ። ፊታቸው እንደኔው ፊት የማይፈታ ፈገግታ የተለያቸው የዓመታት ጦርነት ያንገላታቸው ሰዎች ነበሩ። “ቃል የለም። ሚኒባሷ ከአቅሟ በላይ እስ

ቲ መስል ድረስ በሃያ ሰው ታጭቃ ትከንፋለች። አዲስ አበባ ጭል ጭል የምትል መብራቷን እያበራች በቅርብ ርቀት መታየት ጀመራለች። “ ጓድ መሪ?” አለ አንዱ። ሌላኛው ተቀብሎ “ቀጥል ይሰማኛል” ሲል መለሰ። የመጀመርየው “አዲስ አበባ መብራቷን እያበራች በቅርብ ርቀት ትታያለች” አለ። ተቀባዩ ምን ነበር ያለው? ጠፍቶብኛል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ግንቦት 23/1983 ዓ.ም እስታዲየም አጠገብ ሃያ ሰዎች ከአንዲት ሚኒባስ ተራገፍን።ታክሲ ወደ ቸርችል ጎዳና እንዴት እንደ

ያዝኩ አላውቅም። ብቻ ወደ ቀኝ ወደ ግራ ገልመጥ ሳልል ተረት ሰፈር ቀበሌ 16 ካሉት ቤተሰቦቼ በሰላም መድረሴን ብቻ ነው የማውቀው።

በብላቴ ገብቶ የነበረው እንዲህ ቀላል በሽታ ሳይሆን “ወረርሽኝ” ነው።ጥናቱ ያተኮረው ከMarch 5 to 22,

1991 ድረስ ብቻ ያለው ጊዜ ላይ በመሆኑ ከዚያ በኋላ የታመሙትን አልተመለከተም። ለዚያውም ቢሆን 1616 ተማሪ መታመሙ ጥቂት የሚባል አይደለም። በዚያው ተመሳሳይ ወቅት ደግሞ በሌሎች በሽታዎች የተጠቁ 3582 ተማሪዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል (THE ETHIOPIAN JOURNAL OF HEALTH DEVELOP-MENT )። ሸርተቴ ሰው ቢሆን ኖሮ “ምን አቅብጦኝ እነዚህ ተማሪዎች ጋር መጣሁ፣ ምነው ባልያዝኳቸው ኖሮ” ሳይል አይቀርም። ምክንያቱስ? ቀለድንበት፣ አሾፍንበት፣ ብዙ ሳቅንበታ። ገጣሚውም በግጥሙ እንዲህ አሞግሶ ተሳለቀበታ።ከሸርተቴው እና ከወባው ባሻገር ዱካኩ

እና ቅዠቱ ብላቴ ላይ ሰልጥኗል። ወታደሮቹ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ መንፈስ “ሻምበል ደበበ ወይም ሻምበል ደቤ” ይሉታል። እንደዚያ የተባለበት ታሪክ አለው። ነገሩ እንዲህ ነው። በግቢው ውስጥ አንድ ሻምበል ደበበ የ

ሚባሉ መኮንን ነበሩ አሉ። መኮንኑ እጅግ ቁጡ እና በበታቾቻቸው ዘንድ እጅግ የሚፈሩ ነበሩ። ታሪኩን የተረኩልን ሰዎች እንደሚያቀርቡት ከሆነ ጥፋት ያለበት ወታደር ከተገኘ ሻምበል ደቤ እንዲህ በቀላል አይለቁትም። በወታደሩ ቤት እንደተለመደው አንድ ሻምበል ወደታች ወርዶ አንድ ተራ ወታደር ቁጭ በል፣ ብድግ በል እያለ አ

ይቀጣም። ግን ያስቀጣል። ትዝ እንደሚለኝ ሆለታ ጦር ካምፕ ውስ

ጥ አስር አለቃ በቀለ የሚባሉ አንድ ረዥም ወታደር፣ በመቅጣት የሚታወቁ ነበሩ። ከርሳቸው ከፍ ሲል ደግሞ መቶ አለቃ (ምትኩ ይመስለኛል ስማቸው) በጣም ይፈሩ ነበር። አስር አለቃ በቀለ ሲቀጡ በመጀመሪያ ወታደሩን ቀበቶውን ያስፈታሉ። የጫማውን ማሰሪያ ያስወልቃሉ። ከዚያም በሩጫም ይሁን ብዙ ፑሽ አፕ በማሠራት ልቡን ያጠፉታል። አስር አለቃ በቄ የሚታወሱት “ኢኔ ዲረስ፣ ቦንባ ዲረስ፤ እኔ ድረስ፣ ቧንቧው ድረስ” በሚለው ወዲያ ወዲህ የሚያሯሩጥ ስፖርታቸው ነው። የብላቴውም ሻምበል ደቤ እንዲሁ የሚፈሩ መኮንን ኖረዋል። ሻምበሉ መቅጣት ከፈለጉ አንዱን ሻለቃ ጦር፣ ወይም አንዱን ሻምበል ጦር፣ ወይም አንዱን የመቶ ጦር በስፖርት ልቡን ያጠፉታል። አንድ ወታደር ብቻውንም እንደዚያው።ታሪኩ እንደሚያትተው፣ አንድ ቀን ጦሩ

ሁሉ ለጥ ብሎ ከተኛበት “የሻምበል ደቤ ፊሽካ” በቀጭኑ ትሰማለች። ጦሩ በርግጎ ተነሥቶ ይወጣል። ሻምበል ደቤ አንድ ሰበብ ፈጥረው ብቻ ያንን ጦር በጭለማ ሲያሯሩጡት ያድራሉ። ከዚያም ቅጣቱ ያልቅና ውልቅልቅ ያለው ጦር ወደ አልጋው ተመልሶ ይዘረራል። ቆየት ብሎ፣ “ፎሌን ሲነፋ” የሚነሣ ሰው ይጠፋል። አለቆች ወደ ጦሩ ቢመጡ ሁሉም ወዳድቋል። “ተነሥ!” ቢባል ማን ይነቃነቅ። “ምን ሆናችሁ?” ሲባል “ሻምበል ደበበ ሲቀጡን አደሩ” ይላል ጦሩ። በነገሩ ሻምበል ደበበ ራሳቸው ይገረማሉ። ለካስ በሻምበል ደቤ ተመስሎ የመጣው “አጅሬ ሰይጤ” ኖሯል። ከዚያን ጊዜ

ወዲህ “ሰይጣን፣ ዱካክ” ማለት ቀረና በቁልምጫ “ሻምበል ደቤ” ተባለ።ወታደሮቹ የሚናገሩት ሌላም ብዙ ነገር

አላቸው። ለምሳሌ ጦሩ ቀን ቀን ሲዘፍን የሚውለውን ዘፈን ሻምበል ደቤ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ የራሱን ጦር ሲያዘፍን ሰምተናል ይላሉ። “ቡቄሳ ኮረብታ” የምትባለውና ወታደሩ የሚማርባት ትንሽ ጉብታ መሬት ቀን ቀን ጦሩ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የሻምበል ደቤ ጦር ይዘፍኑባታል እየተባለ ይቀለዳል። እንግዲህ ሰይጣን “ሞራል እያወጣ” ወደየትኛው ውጊያ እንደዘመተ እግዜር ይወቀው። በደፈናው ግን “ውሸት ነው፤ ሲጋነን ነው፤” ማለቱን አልመረጥኹም።እኔ የማውቀውን ግን ልንገራችሁ። ተማ

ሪው ሌሊት ሌሊት በጣም ይቃዥ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ሙቀቱ ይሁን፣ ሻምበል ደቤ ይሁን፣ ወይም የሁለቱ ጥምረት ይሁን እንጃ። እናም ቤተ ክርስቲያን እንደምንሔድ የሚያውቁ የሌላ እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ “እባካችሁ ዱካክ አስቸገረን እኮ” ይሉን ነበር። ያለችንን ውዳሴ ማርያም አካፍለን “ትራስህ ሥር አድርገኸው ተኛ” እንላቸዋለን። እውነትም “ሰላም አደርን ዛሬ” ይላሉ - ሌላ ጊዜ።እንደማስታውሰው እኔም ራሴ አንድ ቀን

አሞኝ ከሥልጠና ቀርቻለኹ። ሐኪም ቤት አልሄድኹም። ለጥ ብዬ ዋልኩ። ጉልበት አጥሮኝ ነበር። መቸም የፀሐዩ ነገር አይነሣ። ቆዳችን በዋዕዩ ክስል ብሎ ያረረ የጥቁር ጤፍ ቂጣ ይመስላል።

ከገጽ 21 የዞረ

ከገጽ 21 የዞረ

ብላቴ ወታደራዊ...

“ሽነድ” እና ፍርሃት...

ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት

ተደርጎበታል

ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት

ተደርጎበታል

በ“አምቼዎች”...ከገጽ 7 የዞረ

አምቼዎች አንድ ላይ የምንኖርበት ዓለም ቢኖረን እንዴት ደስ ባለኝ“

Page 23: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011) ሀበሻዊ ቃና 23

ሊያም በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ ነው። ጥቂቶች ብቻ ናቸው ትልልቅ ንግድ ውስጥ የገቡት። በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራ

ል የኾኑት ኮሎኔል ነጋሽ ለገሠ ግን ደቡብ ሱዳን እንደ አገር ከቆመች መጪው ዘመን ለኢትዮጵያውያን ብሩህ ነው ባይ ናቸው። “ደቡብ ሱዳን በጦርነት የተጎዳች ናት። ያ

ን ያህል ሊጠቀስ የሚችል ኢንዱስትሪም ኾነ መሠረተ ልማት የላትም። የተማረ የሰው ሐይል እጥረትም አለ። እኛ በአቅም እና ተቋማት ግንባታ ላይ መሳተፍ እንችላለን። ወደ ውጭ ለምንልካቸው ምርቶችም ቢኾን እዚህ ሰፊ ገበያ አለ” ይላሉ። ቆንስላ ጄነራሉ ይህን አባባለቸውን በቁ

ጥር ያስደግፋሉ። ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች በላቀ ከደቡብ ሱዳን ጋራ ረጅም ድንበር ትጋራለች። የኢትዮጵያ ክልሎች ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ እና ደቡብ ሕዝቦች በደቡብ ሱዳን ከሚገኙት አፐር ናይል፣ ጆንግሌይ፣ ዌስተርን ኢኳቶሪያል እና ብሉ ናይል ክልሎች ጋራ ድንበር ይጋራሉ። አሁን በመሬት ላይ በሚታየው እውነታ ግን ኢትዮጵያ በዚህ ረጅም ድንበር እምብዛም ተጠቃሚ አይደለችም። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ከድንበሩ ርቅው በከተሞች የተገደቡ ናቸው። በሚሠሩት ሥራ ረገድም ቢኾን ጥንካሬያቸው ጎልቶ የሚታየው በኤክስፐርት ደረጃ በተቀጠሩት ዘንድ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን በተባበሩት መን

ግሥታት ድርጅቶች እና መንግሥታዊ ባልኾኑ ድርጅቶች ተቀጥረው ይሠራሉ። አንዳንዶች ድርጅቶችን ይመራሉ፤ በቁልፍ ቦታዎችም ይገኛሉ። ጥቂት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በመንግሥት መሥርያ ቤቶች ውስጥ ይሠራሉ። በጣት የሚቆጠሩቱ ደግሞ የሚኒስትሮች አማካሪ የመኾን ዕድል አግኝተዋል። በአሁኑ ወቅት የደቡብ ሱዳን መንግሥት (ጎስ) 31 ሚኒስቴር መሥርያ ቤቶች አሉት። የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናት

እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ኤክስፐርቶች በአገሪቱ ውስጥ መገኘት መንግሥት ያለበትን ስር የሰደደ የሰው ሐይል ችግር በመፍ

ታት ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከደቡብ ሱዳን ሕዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ማእከል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ዕድሜው ለሥራ ከደረሰ የአገሪቱ ሕዝብ መካከል 12 በመቶው ብቻ ተከፋይ ሠራተኛ ነው። ደቡብ ሱዳን እንደ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት ሁሉ ለሥራ ያልደረሱ አዳጊዎች በብዛት የሚገኙባት ናት። 8.26 ሚልዮን ከሚገመተው የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። “የቀጠርናቸው ኢትዮጵያውያኖች ኤክ

ስፐርቶች ናቸው። የደቡብ ሱዳን መንግሥት አማካሪዎች እና ኮንሰልታንቶችም አሉ” ይላሉ የሱዳን ሕዝቦች ነጻ አውጪ ጦር (ኤስ.ፒ.ኤል.ኤ) ጠቅላይ አዛዥ የኾኑት ጄነራል ጄምስ ሆት ማይ። የኢትዮጵያውያን ኤክስፐርቶች ቁጥር ከ

መንግሥት ተቋማት ውጭ በግል ተቋማት እየበረከተ መጥቷል። “ቡፋሎ” በተሰኘው የአገሬው ባንክ እና የሞባይል ስልክ አገልግሎት በሚሰጠው “ቪቫ ሴል” ያሉ ሠራተኞችን የተመለከተ ድርጅቶቹ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የተያዙ ሊመስሉት ይችላሉ። በደቡብ ሱዳን ውስጥ ካሉ አገር በቀል አምስት ባንኮች መካከል አንዱ የኾነው “ቡፋሎ” ውስጥ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ

ን ጨምሮ 10 ኢትዮጵያውያን ይሠራሉ። “ቪቫ ሴል” በበኩሉ 30 ኢትዮጵያውያንን ቀጥሮ ያሠራል። በቡፋሎ ባንክ ተቀጥረው ከሚሠሩት መ

ካከል አንዱ የኾነው ሙሉጌታ ሰይፉ የዋናው ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ነው። ወደ ጁባ ከመምጣቱ በፊት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዐሥር ዓመት ያህል ሠርቷል። ከንግድ ባንክ ቆይታው ከባንክ ክለርክነት አንስቶ እስከ ደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅነት የደረሰው ሙሉጌታ ወደ ጁባ የመጣው በጋዜጣ ላይ የወጣ የሥራ ማስታወቂያ ከተመለከተ በኋላ ነው። ከንግድ፣ አቢሲኒያ፣ ንብ፣ ኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንኮች እንደመጡት የአሁን የሥራ ባልደረቦቹ ሁሉ ለሥራው ተወዳድሮ ወደ ጁባ ለመምጣት ችሏል። እነ ሙሉጌታ እ.ኤ.አ የካቲት 2009 ላይ

ጁባ ሲገቡ በዚያች አቧራማ እና ያላደገች ከተማ ረጅም ጊዜ እንደማይቆዩ ነበር የገመቱት። ከሁለት ዓመት በኋላ ግን ሙለጌታ የራሱን “ቢዝነስ” በከተማዋ ስለመክፈት የሚያስብ ኾነ። የቡፋሎ ዋና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅነትን ቦታ ካገኘ በኋላ የሚከፈለው ደሞዝ ደግሞ ራሱን የቻለ ማባበያ ነበር። ሙሉጌታ አሁን የሚያገኘው ደ

ሞዝ አዲስ አበባ ያገኝ ከነበረው ሰባት እጥፍ ይልቃል። እንደ እርሱ እምነት ከኾነ አገሪቱ ሰላም እንደኾነች ከዘለቀች በደቡብ ሱዳን “ቢዝነስ” መሥራት ተስፋ ሰጪ ነው። “አንድ ሰው እንደ ሻይ ቤት ካለ ተራ ንግ

ድ እንኳ በቂ ትርፍ የሚያገኝበት አገር ነው” ይላል ሙሉጌታ። እርሱ በሚሠራበት ዘርፍም ገና ብዙ ይጠ

በቃል። በማደግ ላይ ባለችው ደቡብ ሱዳን፤ ከአጠቃላዩ ሕዝብ አንድ በመቶ ብቻ የባንክ ሂሳብ ባለቤት በኾነባት አገር፤ የባንክ ዘርፍ የወደፊት ጉዞ እጅጉን አትራፊ ይመስላል። ጦርነት ከመፈንዳቱ ከ20 ዓመት በፊት በደቡብ ሱዳን አንድ ባንክ ብቻ ነበር። በጦርነቱ ጊዜ የባንኮች ቁጥር ወደ አራት አደገ። የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ የአገሬው የአገር በቀል ባንኮች ቁጥር አምስት የደረሰ ሲኾን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ሦስት የውጭ ባንኮች ዘርፉን ተቀላቅለዋል። ቡፋሎ ባንክ በስተመጨረሻ ወደ ዘርፉ

ከመጡ ባንኮች አንዱ ነው። በስድስት ደቡብ ሱዳናውያን ነጋዴዎች አማካኝነት በተከፈለ ስድስት ሚልዮን ዶላር ካፒታል በእ.ኤ.አ በ2008 የተመሠረተው ቡፋሎ በአሁኑ ወቅት ሦስት ቅርንጫፎች አሉት።

ከጥንስሱ ጀምሮ ባንኩ እየተመራ የሚገኘው ቀድሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሥራ አስኪያጅነት አገልግለው በነበረው አቶ ዓለሙ አበራ አማካኝነት ነው። አቶ ዓለሙ በምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የንግድ እና ብሔራዊ ባንኮች ውስጥ ለ30 ዓመታት ያህል የሠሩ ናቸው። አሁን የሚመሩትን ቡፋሎ ባንክ ደግሞ መደበኛ የባንክ አገልግሎት ከኾነው ገንዘብ ማስቀመጥ፣ ማውጣት እና ማዘዋወር በተጨማሪ ብድሮች የሚሰጥ እና የንግድ ልውውጦችን ፋይናንስ የሚያደርግ እንዲኾን አድርገውታል። የቡፋሎ ባንክ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የ

ኾኑት አንድሪው ማያን አኩአክ ባንኩ ላስመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደኾነ ይመሠክራሉ። በተለይም ኢትዮጵያውያኖቹ በዓለም አቀፍ ባንኪንግ ዘርፍ ያላቸውን ብቃት ያደንቃሉ። እንደ እርሳቸው አባባል ከኾነ ኢትዮጵያውያኖቹ በዓለም አቀፍ ባንኪንግ እና “ትሬድ ፋይናሲንግ” ዘርፍ ያላቸው የካበተ ልምድ በአስመጪ እና ላኪ ንግድ ውስጥ የነበረው የዘልማድ አሠራር አስቀርቷል፡፡ ከዚህ ቀደም አስመጪ እና ላኪ ነጋዴዎች “ሌተርስ ኦፍ ክሬዲት” በመጠቀም ፈንታ ዕቃ ለመግዛት በርካታ ገንዘብ ተሸክመው ወደ ዩጋንዳ እና ኬንያ ይሄዱ እንደነበር መለስ ብለው ያስታውሳሉ። “ኢትዮጵያውያን በሥራቸውም እምነት

የማይጎድሉ፣ ታማኝ እና ታታሪ ናቸው” ሲሉ አንድሪው ሠራተኞቻቸውን ያሞካሻሉ። “ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለሥራው የሚያስፈልገው በቂ ዕውቀት አላቸው።”ኢትዮጵያውያን የሚደነቁበት በሥራቸ

ው ላይ ያላቸው ዕውቀት በቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፉ ይበልጥ የተፈለገ ይመስላል። ለዚህም ነው የሊባኖሱ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ድርጅት “ቪቫ ሴል” በርካታ ኢትዮጵያውያንን ወደ ጁባ በማምጣት በቴክኒክ እና ፋይናንስ ክፍል ውስጥ በማሠራት ላይ የሚገኘው። በዚህ ድርጅት የኢትዮጵያውያን አሻራ በተለይ ጎልቶ የሚታየው በቴክኒክ ክፍሉ ነው። ኢትዮጵያውያኑ ከኢንተርኔት እስከ ፕሮግራም፣ ከሲስተም አድሚኒስትሬሽን እስከ ኔትወርክ ሲስተም ዝርጋታ እና ጥገና ድረስ የማይሠሩት ነገር የለም:፡

ኢትዮጵያውያን በዚህ ድርጅት መሥራት የጀመሩት “ቪቫ ሴል” ሥራውን በደቡብ ሱዳን “ሀ” ብሎ ከጀመረበት እ.ኤ.አ ከየካቲት 2009 ጀምሮ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዚህ ድርጅት ሲሠሩ የቆዩ ሲኾን የተወሰኑት ለከፍተኛ ትምህርት ሌሎች ደግሞ ለተሻለ ሥራ ፍለጋ ወደ አውሮፓ እና ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዘዋል። በድርጅቱ የሚሠራ እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ አንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኞች የሚለቁበት ሌላም ምክንያት እንዳለ ያስረዳል። “ደምወዙ ያን ያህል ሳቢ አይደለም” ይላል። በጁባ ባሉት ሁለት ቢሮዎቹ እና በመላ

ው አገሪቱ ባሉት መሸጫ ቦታዎቹ “ቪቫ ሴል” ከሌሎች አምስት የሞባይል አገልግሎት አቅራቢዎች ጋራ በመኾን በማገልገል ላይ ይገኛል። እንደ ባንክ ዘርፍ ሁሉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍም በደቡብ ሱዳን በአግባቡ አላደገም። የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ማእከል ባወጣው መረጃ መሠረት በደቡብ ሱዳን 15 በመቶ አባ ወራዎቸ (ሀውስ ሆልድ) ብቻ ስልክ አላቸው። ይህ ቁጥር በከተማ አካባቢ በሚኖሩት ዘንድ ወደ 59 በመቶ ከፍ ይላል። ደቡብ ሱዳን ከታመመችው የጦርነት ሕ

መም አገግማ የራሷን ዕድል በራሷ ወደ መውሰን በደረሰችበት በዚህ ሰዓት እንደ ዩጋንዳ ያሉ የጎረቤት አገሮች የንግድ መስመራቸውን በማጠናከር ከእድገቷ ተጋሪ ለመኾን አቆብቁበዋል። ኢትዮጵያ እንደ አገር በንግድ ትስስር እና በተቋማት ደረጃ ብዙ ገፍታ ባትሄድበትም ጥቂት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ግን በራሳቸው ተነሳሽነት ጁባን እያሳደጉ ራሳቸውን የመለወጥ ጉዞ ውስጥ ይገኛሉ። ብዙዎች የሥራ ዕድልን ለማግኘት እና የተሻለ አማራጭ ፍለጋን እውን ለማድረግ የምዕራቡን ዓለም ብዙ ኪሎ ሜትር አቋርጠው ያልማሉ፤ በጉርብትናው የእድገቱ ጦርነት ተካፋይ እንዲኾኑ ጥሪዋን የምታስተጋባ የምትመስለው ደቡብ ሱዳን “ከአፍንጫችሁ ስር ያለሁት እኔም ዕድል መስጠትን አውቅበታለሁ” የምትል ትመስላለች። ማነው ባለሳምንት?

ይህ ጹሁፍ የተወሰደው ከሳምንታዊው “ፎርቹን” ጋዜጣ ነው

ከገጽ 19 የዞረ

የጎረቤቶች...

ዚህ ነው፣ ይኼ ከዚህ ጎሳ መጣ የሚባል ነገር የለም” ሲሉ የአቶ ካሣን አስተያየት ያጠናክራሉ።

ቀዝቃዛው መንፈስበቡድኑ የሚሳተፉ የተለያዩ አገር ተጫዋ

ቾች ቁጥር ይደግ እንጂ አጠቃላይ ቁጥሩ ግን ከድሮው ጋራ ሲነጻጸር ቀንሷል።በአንድ ወቅት 45 የነበረው የተጫዋቾች

ብዛት አሁን ወደ 25 አሽቆልቁሏል። ለዚህ የሚቀርበው ዋናው ምክንያት የአባላት በየጊዜው ወደ ሌላ አገር የመሄድ ጉዳይ ነው። በፍቅር ከቆዩበት ቡድን ወጥተው ወደ ሌላ አገር የተሸኙት አባላት ኑሯቸውን ካመቻቹ በኋላ አልፎ አልፎም ቢኾን ኳስ እና ትጥቅ ይልካሉ። የገንዘብ ድጋፍም ያደርጋሉ።ብዙ ነገሮች ለማሕበሩ ይልካሉ፡፡ በአብዛ

ኛው ወደ ካናዳ፣ አሜሪካ እና አውስትራሊያ የተጓዙት አባላት እዚያም ራሳቸውን አደራጅተው መጫወታቸውን ቀጥለዋል።የእነርሱ ከቡድኑ መለየት ጉዳት ቢኾን

ም ከዓመታት በፊት የነበረው የጤና ቡድን ጥንካሬ እና እንቅስቃሴ አሁን መቀዝቀዙን የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች አሉ። ቡድኑ ያለፈባቸውን ሂደቶች የሚዘግቡ ፎቶዎችን የያዘው አልበም ለእዚህ ሁነኛ ምስክር ነው። ፎቶዎቹ ታሪክ መዝግበዋል። የጤና ቡድኑ ወደ ኡጋንዳ ለአህጉራዊ ውድድር የመጡየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (የወንዶች

ም፣ የሴቶችም) እና ክለቦችን ተቀብሎ ያስተናግድ እንደነበር ያሳያሉ። በአንድ ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ወደ ካምፓላ ብቅ ሲል የጤና ቡድኑ አባላት የክለቡን ማልያ ከዝነኛው “ቪ” አርማው ጋራ አሠርተው ደግፈዋል። በቅርቡ በሞት የተለየው ዝነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች መንግሥቱ ወርቁ ለሥራ ጉዳይ ወደ ኡ

ጋንዳ በመጣበት ወቅት ተቀብለው አስተናግደውታል። የጤና ቡድኑን ለማሳደግ የገቢ ማሰባሰቢ

ያ ፕሮግራም አዘጋጅተው ጥሩ ድጋፍ አግኝተዋል። ለዚህ ፕሮግራም ድምቀት ሲባል የኮሚቴ አባላት በራሳቸው ወጪ የአገር ባህል ልብስ እስከማሰፋት ደርሰው ነበር። የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ከኪሳቸው አውጥተው ናይሮቢ ተጉዘዋል። ዓመታዊ በዐላቸውንም በውድድር ያከብሩ ነበር። ዛሬ እነዚህ ሁሉ የሉም።ምቾት ያለው የ“ቪላ” ክለብ መለማመጃ

በአቧራማው የኪቡሊ የሙስሊም ትምህርት ቤት ሜዳ ተተክቷል። አሁን ወደ ውሃ ዳር ወርዶ መዝናናት ታሪክ ኾኗል። ሁለት ሺሕ የኡጋንዳ ሽልንግ ብቻ ይጠየቅበት የነበረው መዋጮም እንዲቀር ተደርጓል። አብዛኞቹ መሥራቾችም ወይ ከአገር ወጥተዋል አሊያም ከጨዋታ ርቀዋል።የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት

አቶ ተካልኝ እና አቶ ደሳለኝ ወደ አሜሪካ እና ካናዳ ተጉዘዋል። በቡድኑ የተከላይ አ

ማካይ ሚና ይዘው ይጫወቱ የነበሩት አቶ ካሣ ሜዳ ከገቡ ሦስት ዓመት ተኩል አልፏቸዋል። “አሁን 45 ዓመቴ ነው። ከጎረምሶቹ ጋራ እኩል አልጋፋም። የኡጋንዳ አየር ደግሞ ቀላል አይደለም” ይላሉ በቀልድ መልክ።የዕድሜው ጉዳይ እንዳለ ኾኖ “ታኬታ”

የመስቀላቸው ዋና ምክንያት ግን የ“ጤና ጉድለት” እንደኾነ ይገልጻሉ። እንደ እርሳቸው ሁሉ መሥራች የነበሩት አቶ ክፍሌም ከተጨዋችነት ወደ ተመልካችነት ዞረዋል። ሁለቱም ግን ቡድኑን በየሜዳው እየተገኙ ከማበረታት አልተቆጠቡም። እንደ ቀድሞው ዘመን አይኹን እንጂ በሥራ አስፈጻሚነት ያላቸውንም ድርሻ ከመወጣት አልቦዘኑም።ቡድኑ እንደድሮው ያልኾነበትን አንዱ ም

ክንያት የኑሮ ኹኔታ እንደኾነ አቶ ንጉሴ ያስረዳሉ። “የአፍሪካ ኑሮ አስቸጋሪ ነው። አብዛኞቹ አባላቶቻችን የዕለት ሩጫቸው ያመዝናል። አብዛኛው ስደተኛ ስለኾነ ኳስ ተጫውቶ ደክሞት ምግቡ፣ ትራንስፖ

ርቱ እና ሌሎችም ወጪዎች መሸፈን አለባቸው። በፊት የኑሮውም ኹኔታ እንዳሁኑ የጠነከረ አልነበረም። አሁን ኑሮ እየተወደደ መጥቷል። ያ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው” ይላሉ። አቶ ካሳም በዚህ ይስማማሉ። የቡድኑ ገቢ በግለሰቦች መልካም ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መኾኑ እና ኑሮው እንደ ጥንቱ የሚያወላዳ አለመኾኑን እንደ ችግር ያነሳሉ።

የት ይደረሳል?እንዲህም ኾኖ ጨዋታው ቀጥሏል። ተተ

ኪዎችም ማልያቸውን ለብሰው ከቡድኑ ጋራ ወደ ሜዳ መውረዳቸውን በደስታ እየተገበሩት ነው። አንዳንድ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶችም እግር ኳሱን ከትምህርታቸው እና ከስደት ሕይወታቸው ጋራ አጣጥመው ለመሄድ ሲሞክሩ ይታያሉ። እነዚህ ወጣቶች መጀመርያቸውም መጨረሻቸውም ጤና ቡድን ሊኾን ነው? ወይስ ቡድኑ ወደ ፕሮፌሽናል የማደግ ተስፋ አለው? የቡድኑ የሥራ ሐላፊዎች ግን ይህ የማይኾንባቸው ምክንቶች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡“ከእኛ ጋራ የሚጫወቱት ልጆች ዛሬ ይሂ

ዱ ነገ አናውቅም” ይላሉ አቶ ካሣ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ አመልክተው የሚጠባበቁ መኾናቸውን በማስታወስ። “ሁለተኛ የሚጫወቱት ልጆች ራሳቸው የየዕለት ጉርሳቸውን ስለሚፈልጉ የልምምድ ሰዓት ሊኖራቸው አይችልም።” እነዚህን ወጣቶች መደበኛ ልምምድ አድርጉ ማለት እንደ አቶ ካሣ አባባል ጎሮሯቸው ላይ እንደመቆም ነው።ማሕበሩ እንደሚያንከባልላት ኳስ መድ

ረሻው በቅርብ ያለው የግብ መረብ አይደለም፡፡ ሁሉም ካለማንም ግፊት በራሱ የስፖርት እና የወገን ፍቅር ያሰባሰበው ነው። ትናንትን እንደኖረ ሁሉ ዛሬንም ተሻግሮ ስለ ነገ ማሰብ ይጠብቀዋል። ይኹን እንጂ ለሚመጣው ትውልድ ሐሳቡን፤ አንድነቱን እና ፍቅሩን ከኳሷ ጋራ የማስረከብ ራዕዩን እንዳነገበ።

“ቪቫ ሴል” በጁባ ባሉት ሁለት ቢሮዎቹ እና በመላው አገሪቱ ባሉት መሸጫ ቦታዎቹ ከሌሎች አምስት የሞባይል አገልግሎት አቅራቢዎች ጋራ በመኾን በማገልገል ላይ ይገኛል

ከገጽ 5 የዞረ

ከኳሱ...

ፋና ወጊው ቡድን

ፎቶ

- ካሣ

መንግ

ስተአብ

ት ያስደፋቸዋል። የያዟት ተስፋ ታጓጓቸዋለች፡፡ ያን ተስፋ መጠበቅ ደግሞ የረጂ ወገንን እጅ ማየትን ያስከትላል። ዶላርን በተስፋ መጠበቅ ለብዙዎች ፈተና ነው። በተለይ ዘመድ አዝማድ ለሌላቸው ከሚታሰበውም በላይ ከባድ ነው። በስደት ላይ ያለ ሌላ ስደት፤ ሁለተኛ ደረጃ ስደተኝነት የኾነባቸው ብዙ ናቸው።

የቢቸግር መፍትሄዎች . . . የሰው እጅ ጥበቃ የሰለቻቸው ብልኀትን

ፈጥረዋል። አንዳንዶቹ ብልኀቶች ዛሬ ነፍስን ከማዳን ነገን ደግሞ ተስፋ ከማድረግ ብቻ የመነጩ ናቸው። ብዙ የታሰበባቸው የሚመስሉ አይደሉም። ሴቶቹ የምሽት ዳንስ ቤቶችን በመጎብኘት የሚመጣውን የማታ ሲሳይ ይጠብቃሉ። ጥቂት የማይባሉ ወንዶች ደግሞ በፌስ ቡክ እና መሰል የማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካይነት አውሮፓ የሚገኙ እና ለትዳር እና ለውሲብ የሚጓጉ በዕድሜ ገፋ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋራ ግንኙነት በመመሥረት ተስፋ ላይ ራሳቸውን ይጥላሉ። የዕለት ወጭያቸውን ከመሸፈን ባሻገር የአውሮፓ ጉዞ ተስፋቸውን ብሩህ ለማድረግ ያታትራሉ።በአብዛኛውን ጊዜ ጥንድ መኾን በብዙ

ዎች የተመረጠ ነው። ጥንዶቹ ፍቅረኛ ወይም የትዳር አጋር ከኬንያ ውጭ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ግን አብሮ ከመኖር አያግዳቸውም። ካልተስማሙ በሳምንት ውስጥ በመለያየት ከቅርብ ጓደኛ ጋራ ሌላ ግንኙነት ቢመሠረት የሚገርም አይደለም። ዋናው ኑሮን ማሸነፍ ነው።ለስድስት ዓመታት በናይሮቢ የቆየችው

እና ወደ ካናዳ ለመብረር በዝግጅት ላይ ያለችው ሐረግ ይኼን መፍትሄ ከተጠቀሙት መካከል አንዷ ናት። በአንድ ወር ውስጥ ከሁለት ወንዶች ጋራ “ትዳርን” ሞክራው ታውቃለች። “ሁሉም በር ሲዘጋብህ ሰ

ብረህ ከመውጣት ውጭ የተሻለ አማራጭ የለህም” ትላለች። ማንም ረዳት ያልነበራት ሐረግ ከለላ ለኾናት ኹሉ ጊዜያዊ ሚስት በመኾን ስድስቱን ዓመታት አሳልፋለች። “የእኔ አይግረምህ፣ ሕጋዊ ባሎቸው እንኳን አሜሪካ የሚኖሩ ጓደኞቼ እኔ ባለፍኩበት አልፈዋል።”ይህ ዐይነቱ ፈጣን “የትዳር” ዝውውር ግ

ን ኹሌ እንደታሰበው ኑሮን በመደጎም ብቻ አይጠናቀቅም። በተለይ የትዳር አጋሮቻቸው አሜሪካ ወይም ሌላ አገር የሚገኙ ስደተኞች ሌላ ያልተጠበቀ ውጤት በመፍጠር ተስፋቸውን ይሠብራል። ወዳጆቻቸው ናይሮቢ የሚያደርጉትን በመስማት ቃል የገቡትን የአውሮፓ ጉዞ ይሰርዛሉ። ቀለበት ያወልቃሉ፤ ትዳርቸውንም ያፈርሳሉ። ብዙዎች በጊዜያዊው መፍትሄ ክፍተት ዕድሎቻቸውን አበላሽተዋል። ይህ ሁሉ ግን በአብዛኛው የሚኾነው የተገባው የቤተዘመድ የዶላር ድጎማ ሲጓደል ወይም ጭርሱኑ ሲቋረጥ ነው። . . .

ምርቃና ደጉአሁን ይህን ሁሉ ባለ ታሪክ ያቀፈቸው የ

በሬ ግንባሯ ክፍል መጋል ጀምራለች። ብዙኀኑም በቡናው ታጅቦ ወደ ምርቃናው ጥግ እየሄደ ነው። ይኼን ጊዜ ብዙኀኑ ሞባይሉን ይጎረጉራል። ፌስቡኩን ይከፍታል። የሚጽፋቸውን ቃላቶች ይመርጣል። ጥያቄዎች ከወዲያ ወዲህ ይወናጨፋሉ። “ለዚያች አሮጊት ምን ብዬ ልጻፍላት”፣ “አቦ አሁን ምን ኬዝ ፈጥሬ ገንዘብ ልቀበላት?” . . . ምርቃና ደጉ ሁሉን ደፋር ያደረጋል። ሙሉ ተስፋም ያስታጥቃል። አሁን ስለብዙ ጉዳዮች የሚታለምበት፤ ተስፋ የሚደረግበት ነው። ብርሃናማ ነገሮች ብቻ ወለል ብለው የሚታዩበት ክፍለ ጊዜ ነው። ጎላ ያለ ድምፅ አይሰማም። ሁሉም በራሱ ሐሳብ ተውጧል። ቅድምን የሚያስታውስ የለም። ነገን ግን በሙሉ ኀይላቸው እየሳሉ ነው፡፡ ዶላር . . . አሜሪካ . . . ካናዳ . . . አውስትራሊያ . . . ። ኢትዮጵያ?

ከገጽ 8 የዞረ

ተስፋ ...

Page 24: Habeshawi Kana 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)24 ሀበሻዊ ቃና

R ንጹህ እና ምቾት ያላቸው መኝታዎች

ከዲ.ኤስ.ቲ.ቪ አገልግሎት ጋር

R ካፍቴሪያ

R እጅ የሚያስቆረጥም የኢትዮጵያ ምግብ በተመጣጣኝ ዋጋ

R ለሰርግ እና ለተለያዩ ድግሶች ብፌ እናዘጋጃለን

R Self contained accommodation with DSTVR Bar and restaurant R Delicious Ethiopian food R Cater for weddings and events

HOTEL HARAMBE ሆቴል ሐራምቤ

+256 774 883 833, +256 703 944 315

Address:- Nakivubo road, near Shoprite Clock tower Kampala Uganda አድራሻ፦ ኡጋንዳ ካምፓላ- ክሎክ ታወር ሾፕ ራይት ሞል አካባቢ- ናቺቩቡ መንገድ ወደ አዊኖ ገበያ መሄጃ

Technical Management Solutions Ltd

CALL NOW Email: [email protected]

+256 777 202833, +256 701 202833

Expert on maintenance and renovations of guest houses, hotels, bars, restaurants, apartments & residential houses

q General plumbing q Carpentry q Electrical work q Painting

Innovation and Excellence