የፌስቡክ ትሩፋት ፪ (Ye'Facebook Tirufat 2)

36
፲፩ Aጫጭር ግጥሞች E፳፪ Aጫጭር መጣጥፎች 2 2 0 0 0 0 5 5

description

በ2005 በፌስቡክ ላይ የጻፍኳቸው ፲፩ አጫጭር ግጥሞችና እና ፳፪ አጫጭር መጣጥፎች ስብስብ!This is a collection of poems and stories I shared on facebook during 2005 of Ethiopian year.

Transcript of የፌስቡክ ትሩፋት ፪ (Ye'Facebook Tirufat 2)

የየፌፌስስቡቡክክ ትትሩሩፋፋትት ፪፪ ፲፲፩፩ AAጫጫጭጭርር ግግጥጥሞሞችች EEናና ፳፳፪፪ AAጫጫጭጭርር መመጣጣጥጥፎፎችች

በበፍፍቃቃዱዱ ዘዘ ኃኃይይሉሉ

22000055  

 

መቅድም

Eነዚህን ግጥሞች Eና መጣጥፎች በAንድ ጠርዞ ማስቀመጥ ለምን Aስፈለገ? የራሴን ጊዜ ለማባከን? - Aይደለም፤ የAንባቢውን ጊዜ ለማባከን? - Aይደለም፡፡

በ2004 ፌስቡክ ላይ የጻፍኳቸውን ግጥሞች ሰብስቤ ‹የፌስቡክ ትሩፋት› የሚል ‹I-ቡክ› ፈጥሬ ነበር፡፡ መነሻው Eሱ ነው፡፡ ዘንድሮ ለኔ የግጥም ዓመት Aልነበረም፤ ፌስቡክ ላይ ግን ብዙ የጦፉ ውይይቶች ነበሩ፡፡ Eነዚህ ክርክሮች የሚካሄዱት በAብዛኛው በጽሑፍ ነው፡፡ ጽሑፎቹን ለማሰብ፣ ለመጻፍ፣ ለመወያየት ጊዜ ተከፍሎባቸዋል ታዲያ ለምን ተጠርዘው Aይቀመጡም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ያደረግኩት ሙከራ የመጀመሪያው ምክንያት ነው፡፡ ሌላኛው ምክንያት Eነዚህን የወቅቱን ሐሳቤን፣ Eምነቴን የሚያንፀባርቁ መጣጥፎች በማስቀመጥ ወደፊት በመመልከት ምን ያህል ተለወጥኩ፣ ምን ያህል Aደግኩ፣ ምን ያህል ወረድኩ Eያልኩ መጠየቂያ Eና መመዘኛ Eንዲሆነኝ ነው፡፡ Eነዚህ ሁለት ምክንያቶች ጽሑፎቹ የተጠረዙበትን ምክንያት ለኔ ለራሴ ያደርጉታል፡፡ ሆኖም የኔ ብቻ Aይደሉም፡፡ ነገር ግን ሌሎችም፣ የፌስቡክ መደበኛ ተጠቃሚ የሆኑትም ያልሆኑትም፣ Eነዚህን ጽሑፎች Eያዩ Eና Eነርሱን ተከትለው የሚመጡትን ውይይቶች Eያሰቡ በፌስቡክ የባከነው ጊዜ ተገቢ ነው ወይስ Aይደለም የሚለውን Eንዲበይኑ Eድል መስጠት ነው፡፡ ግን ይህም ብቻ Aይደለም፤ የተጻፉት ታስቦባቸው Eንደመሆኑ ሰው በፈለገ ግዜ Eያገላበጠ Eንዲያነባቸው የዋህ ምኞት በማሳደርም ጭምር ነው፡፡

ቁጭቴ፤ Eያንዳንዱ ጽሑፍ በርካታ ጠንካራ የነቀፋ Eና የማጠናከሪያ Aስተያየቶችን Aስተናግደዋል፡፡ ከነዚህ Aስተያየቶች ውስጥ ቢያንስ ጥቂት ጠንካራ የሚባሉትን Eንኳን ማካተት Aለመቻሌ ይቆጨኛል፡፡ Aስተያየቶቹ ከጽሑፎቹ የሚበልጡበትና ምናልባትም Aቋም የሚስለውጡ የሚሆኑበት ጊዜ Aለ - ግን Aላካተትኳቸውም፡፡ ለምን? Aሁንም ሰበቡ ጊዜ ነው፡፡ በተጨማሪም ጽሑፎቹ ላይ የሆሄያት ካልሆነ በቀር ሌላ ለውጥ ሳላደርግ Eንደወረዱ ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ፡፡

መልካም ንባብ

  

  

ማውጫ

የባለሥልጣናት ግጥም ................................................................................................................................. 1 (ርEስ Aልባ 1) ........................................................................................................................................... 1 Aጭር መጣጥፍ ፩፤ Aዲዮስ የትጥቅ ትግል ................................................................................................. 1 Aጭር መጣጥፍ ፪፤ Sex Eና Proxy: የሁለት ቃላቶች ወግ ......................................................................... 3 Aጭር መጣጥፍ ፫፤ ስም ያለው ሞኝ ነው .................................................................................................... 3 ማነው Aምባገነን? ....................................................................................................................................... 6 Aጭር መጣጥፍ ፬፤ የAማርኛ ፊልም ፊታውራሪዎች .................................................................................... 6 Aጭር መጣጥፍ ፭፤ ቁንጅና Eና ብስለት ...................................................................................................... 7 Aጭር መጣጥፍ ፮፤ የጾም ወግ ................................................................................................................... 9 Aጭር መጣጥፍ ፯፤ ቃለምልልስ ከጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝጋ ..................................................... 10 Aጭር መጣጥፍ ፰፤ ምናባዊ ቃለምልልስ ከመለስ ዜናዊጋ ........................................................................... 13 Aጭር መጣጥፍ ፱፤ “American Dream” ................................................................................................. 15 Aጭር መጣጥፍ ፲; “የሕዳሴው” ግድብና ደሞዜ .......................................................................................... 16 ?! ............................................................................................................................................................ 17 Aጭር መጣጥፍ ፲፩፤ ከተሜነትን ከገጠሬነት ለማስታረቅ ............................................................................. 18 የሦስት ዓመት ድርሳን .............................................................................................................................. 19 ፍሬ ሕይወት ............................................................................................................................................ 20 Aጭር መጣጥፍ ፲፪፤ ጨቋኝ ተጨቋኞች ................................................................................................... 20 Aጭር መጣጥፍ ፲፫፤ የፈረንሳይ ልጆች ...................................................................................................... 21 Aጭር መጣጥፍ ፲፬፤ ትልቁ ድኻ ትንሹን ድኻ ይንቀዋል ............................................................................ 21 Aጭር መጣጥፍ ፲፭፤ Belonging-ness .................................................................................................... 22 ጫወታ ፩ ............................................................................................................................................... 23 Aጭር መጣጥፍ ፲፮፤ ‹‹ጥቁር Eና ነጭ›› ................................................................................................... 24 Aጭር መጣጥፍ ፲፯፤ የኮሌጅ ተማሪነትና Eና ሴቶቻችን በAማርኛ ፊልሞች .................................................. 25 ርEስ Aልባ 2 ............................................................................................................................................ 26 የነጻነት ትግል ........................................................................................................................................... 27 የIድ’ለት ቁዘማ 1 Eና 2 ........................................................................................................................ 27 ጫወታ ፪ ................................................................................................................................................. 27 Aጭር መጣጥፍ ፲፰፤ መለስን ከቀዳሚዎቻቸውጋ የማወዳደር ሽቀላ ............................................................. 28 Aጭር መጣጥፍ ፲፱፤ መለስ ዜናዊ ባይሞቱ ሥልጣን ይለቁ ነበር? .............................................................. 29 Aጭር መጣጥፍ ፳፤ መለስ ዜናዊ ዴሞክራት ወይስ Aምባገነን? ................................................................... 30 Aጭር መጣጥፍ ፳፩፤ የመለስ ዜናዊ የውጭ ግንኙነት Aያዎ ...................................................................... 31 Aጭር መጣጥፍ ፳፪፤ COINTELPRO Eኛም Aገር ይኖር ይሆን? .............................................................. 32

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

1  

የባለሥልጣናት ግጥም

Eኒህ ጋዜጠኞች ሽብር የለመዱ Eየመሰላቸው መንግሥትን የጎዱ ቦምብ ሐሳባቸውን ሰርክ Eየጠመዱ በየጋዜጣው ላይ ስለሚያፈነዱ

ወይም ይታሰሩ ወይም ይወገዱ፡፡ ጥቅምት 20፣ 2005

(ርEስ Aልባ 1)

በፍርሃት ቀንበር፣ Aንገቱን የደፋ በAካል ተቀምጦ፣ በመንፈስ የጠፋ

ባለበት Aገር ላይ የታሰረ ሰው ሳይ

መከሰስ ያምረኛል… Eስር ያጓጓኛል፡፡

የገዛ ፍርሐቴ፣ Eስረኛ በመሆን፣ በቁም ከምረታ ይኸው ፀሎቴ ነው - Aካሌ ታስሮለት መንፈሴ Eንዲፈታ፡፡

ጥቅምት 27፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፩፤ Aዲዮስ የትጥቅ ትግል (በመጀመሪያ) የIትዮጵያ ሕዝብ ተበድሏል፤ ነጻ Eናውጣው በሚል በትጥቅ ትግል IሕAዴግን ሊታገሉት በሕይወታቸው ለቆረጡት ግለሰቦች ያለኝን ትልቅ ክብር በመግለጽ ልጀምር፡፡ ይህ (ሕይወታቸውን ለነጻነት የመስጠታቸው ነገር) ቢያስደንቀኝም ቅሉ የመረጡት መንገድ ትክክለኛ ነው ብዬ Aላምንም፡፡ ለዚህ ጉዳይ የኔ ሐሳብ ምን Eንደሚጠቅም ባይገባኝም ዝም ከማለት ይሻላል በሚል Eጽፋለሁ፡፡

1. ‹‹ነጻነት ያለመስዋEትነት Aይገኝም›› ቢባልም ጦርነት ግን የሚፈጀው ሕይወት Eጅግ ከሚገባው በላይ ነው፤ ያውም፡-

2. በጦርነት ለውጥ Eንደሚመጣ Eርግጠኛ መሆን Aይቻልም፤ ለምሳሌ ሕወሓት ከ17

ዓመት ትግል በኋላ ያመጣውን ‹‹ነጻነት›› Eናስተውል፤

3. ጦርነት ረዥም ጊዜ ይፈጃል፤ በዚህ ዘመን የግል ሕይወቱን ከማደራጀት Aልፎ ለሕዝብ ነጻነት ሸፍቶ የሚታገል ‹‹ፋኖ›› ማግኘት ይከብዳል፡፡ ያንን ሰብረው የሚመጡት ሰዎች ቁጥር ማነስ ጦርነቱን በበቂ ኃይል ማራመድ ስለማይቻል… IሕAዴግን በትጥቅ ትግል

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

2  

ለመጣል፣ IሕAዴግ ደርግን ለመጣል ከፈጀበት የበለጠ ጊዜ ይጠይቀዋል የሚል ስጋት Aለኝ፤

4. ጦርነት Iኮኖሚን ወደኋላ ያራምዳል፤ በደርግ-ሕወሓት ጦርነት ወቅት የIትዮጵያ

Iኮኖሚ ቁልቁል Eያደገ ነበር፡፡ Aሁንም ቢሆን ‹‹ታጣቂዎቹ›› Eየበረቱ ከመጡ Eና IሕAዴግ ያንን መመከት Eንዳለበት ካመነ ‹‹ሁሉም ነገር ወደጦር ግንባር›› ሆኖ በEንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የተሰኘ የIኮኖሚ ቀውስ Eንደማይገጥመን Eና Aገሪቱን ወደማትወጣው Aዘቅት ማስገባታችን Aይቀርም፤

5. በጦርነት የሕዝብን የነጻነት ግንዛቤ ማሳደግ Aይቻልም፤ ሕዝብ በጦርነት ወቅት

ፍርሐት Eንጂ ነጻነትን Aይማርም፡፡ ጦርነት በባሕሪው ሰው በመግደል ሰው ነጻ የማውጣት ሒደት ነው፡፡ ጦርነት ሕዝቦች ነጻነትን Eንዲያገኙ ጥቂቶች የሚታገሉላቸው Eንጂ ሕዝቦች ነጻነታቸውን የሚጠይቁበት መንገድ Aይሆንም፡፡

ማለትም፡-

1. ሕዝብ ነጻ ለመውጣት ካልጠየቀ በቀር Eውነተኛ ነጻነት Aይመጣም፤ ስለዚህ፡-

2. ሕዝብ መጨቆኑን Aውቆ (Eውነተኛ ነጻነትን Aውቆ) መጠየቅ Eንዲጀምር Eስኪጀምር ድረስ ማስተማር/ማንቃት ያስፈልጋል፤ Aለበለዚያ፡-

3. ሕዝቡ ያላመጣው ለውጥ… ነጻነት Eንደሚያመጣ ማረጋገጫ መስጠት Aይቻልም፤

ስለዚህ፡-

4. ማሰብ ነው Eንጂ የሕዝቡ የነጻነት Eይታ Eንዲሻሻል Eና የገዛ ነጻነቱን Eንዲጠይቅ ማድረግ ይቻላል፤ Eንዴት፡-

5. በሕዝባዊ Aብዮት፤ ይሄማ ተሞክሮ Aልተቻለም ለምትሉ Aልተሞከረም፡-

5.1. ከምርጫ 97 ጀምሮ Eዚያ ነበርኩ፤

5.1.1. ምርጫው ሙሉ ታዛቢ የነበረው ከተማዎች ውስጥ Eንጂ ገጠሮች ውስጥ

Aልነበረም ስለዚህ፤ ለመጭበርበሩ ተጨባጭ (Aንጀት Aርስ) ማስረጃ Aልነበረም (መጭበርበሩን ማስቆም ቀርቶ)፣

5.1.2. ድኅረ ምርጫው Aመጽ ውስጥ ድንጋይ ከየቀበሌያችን ወረወርን Eንጂ የተደራጀ፣ Aመጽ-Aልባ Eንቅስቃሴ Aላደረግንም፣

5.1.3. Eንደኔ፣ Eንደኔ… ነፍጥ ሸክፎ ጫካ ለመግባት ከተቆረጠ… ከተማው ጫካ ነው… ገንዘቡን Eና የሰዉን ኃይል Aስተባብሮ ብዙ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡

ሕዝብ መራሽ ለውጥ ያስፈልገናል! ይኖረናልም!

ታኅሳስ 23፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

3  

Aጭር መጣጥፍ ፪፤ Sex Eና Proxy: የሁለት ቃላቶች ወግ በቅርቡ sex የሚለውን ቃል በጉግል በኩል የሚፈልጉ Iትዮጵያውያን ቁጥር በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ደርሷል የሚል ሪፖርት ቢጤ (Aወዛጋቢ ስለሆነ ነው ቢጤ ያልኩት) ወጥቶ ነበር፡፡ Eርግጥ ነው ‹‹ያልተፈሳው Aይሸትም›› Eንዲሉ ውጤቱ ያለነገር Eንዳልመጣ ይገባኛል፡፡ ይታያችሁ! ጊዜያችንን ይህንን ቃል ጉግል ላይ በመጻፍ Eና ውጤቱን በማስስ ፈጅተነዋል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ጽሑፍ መነሻነት ያነሳሳኝ ግን ሌላ ነው፤ sex ብሎ ጉግል ላይ መፈለግ proxy ብሎ ከመፈለግ የተሻለ ውጤት Aለው፡፡ በIትዮጵያ Aንድም የታገደ ‹ፖርኖግራፊክ› ነክ ‹ዌብሳይት› የለም፡፡ በነገራችን ላይ Aገራት Eንዲህ ያሉትን ‹ዌብሳይቶች› የሚያግዱት ለጤናማ ማኅበረሰብ ማፍራት ሲሉ ነው፤ ፊልሙ ላይ የሚሳተፉ፣ ያለEድሜያቸው ሰለባ የሚሆኑ ሕፃናት ቁጥር ማደጉ Aይቀርም በሚል ስጋት… Eኛ Aገር ግን በተቃራኒው፣ proxy የሚለውን ቃል በጉግል ፈልጋችሁ ለማግኘት ብትሞክሩ በIትዮጵያ ውጤቱን ማየት Aትችሉም፤ ምክንያቱም ውጤቱ Eንዳይመጣ ታግዷል፡፡ የProxy ‹ዌብሳይት› ማንነትን ቀይሮ ‹Iንተርኔት› የሚያስሱበት ወኪል ‹ዌብሳይት› ነው፡፡ Aገልግሎቱ በዴሞክራሲያዊ Aገራት ውስጥ ሠራተኞቻቸው Eንዳያዩ የሚፈልጉትን ‹ዌብሳይቶች› በግል መረባቸው ውስጥ ያገዱ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሆኖ Eገዳውን Aሳብሮ ‹ዌብሳይቶቹን› ለማሰስ ነው፡፡ EንደIትዮጵያ ባሉ ‹‹I-ዴሞክራሲያዊ›› Aገራት ደግሞ ብዙዎቹ ፖለቲካዊ ሕፀፅ፣ ትችት Eና Aስተያየት የሚሰነዝሩ ‹ዌብሳይቶች› Eና ‹ብሎጎች› ይታገዳሉ፡፡ ስለዚህ ባብዛኛው proxy Iትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግለው Eነዚህን ‹ዌብሳይቶች› ለማየት ቢሆንም proxy ‹ዌብሳይቶች› Eየተለቀሙ ከመታገዳቸውም ባሻገር፣ ሌላ proxy ‹ዌብሳይት› Eንዳትፈልጉ Eንኳን ቃሉ ጉግል ላይ ተቆልፏል፡፡ Aንዴ፣ ‹Iንተርኔት ካፌ› ውስጥ Iንተርኔት ስጠቀም፣ Aንድ Iትዮጵያ ውስጥ Eንዳይነበብ የታገደ ‹ብሎግ› መጎብኘት Aስፈለገኝ፡፡ የሚሠራ proxy ከየት ላምጣ? ትዝ ያለኝ ነገር ቢኖር sex የሚለው ቃል Aለመታገድ ነው፡፡ ስለዚህ ሌላው ዓለም ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚታገደው Eና በproxy የሚያዩት Eሱን ነው በሚል በsex ስም የተዋወቀ proxy Eንደማይጠፋ ገመትኩና ጉግል ላይ Eንዲህ ብዬ Aሰስኩ “website that helps me to visit blocked sex sites” ውጤቱ Aመርቂ ነበር፤ ከመጡልኝ Aማራጮች ውስጥ thickstraw.com (ቃሉ?) የሚለውን መርጬ መጠቀም ጀመርኩ፡፡ ሆኖም ምን ገጠመኝ መሰላችሁ? የመጣልኝ proxy ‹ድረገጽ› ተጠቅሜ የምፈልገውን ‹ብሎግ› ስጎበኝ Aንድ ‹ክሊክ› ባደረግኩ ቁጥር የsex ፊልሞች Eና ስEሎች የያዙ ‹ፖፕ Aፕ› ማስታወቂያዎቂያዎች ብልጭ፣ ድርግም Eያሉ ይወጣሉ፡፡ Aስቡኝ… ከኋላዬ ወረፋ የሚጠብቁ ሰዎች በተሰበሰቡበት - Aፋርነቴን ያልጨረስኩ ጎልማሳ - ‹Iንተርኔት ካፌ› ውስጥ የ‹ፖፕ Aፕ› ማስታወቂያዎቹ ሳይታዩ በፊት ለመዝጋት ስራወጥ…

ጥር 28፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፫፤ ስም ያለው ሞኝ ነው ስምን መልኣክ ያወጣዋል ቢሉም ቅሉ የEኔን ስም ያወጡልኝ ግን Aያቴ ናቸው - በፈቃዴ ወጥቼ፣ Eንደፈቃዴ Aውርቼ፣ በፈቃዴ Eገባለሁ - ይሄ ነው Eንግዴህ በፍቃዱ ማለት፡፡

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

4  

Eርግጥ ነው Aያቴ ይህን ስም ሲያወጡልኝ ፈቃጅ ብለው ያሰቡት ‹‹ፈጣሪ››ን ነበር፤ ሸወድኳቸው Eንጂ! 1. ብዙዎች Eንደሚሉት ‹‹በፍቃዱ›› ብሎ ስም የፋራ ነው፡፡ ስለዚህ ብዙዎቹ ጓደኞቼ በፋራ ስም Eንዳይጠሩኝ ብለው ‹‹በፍቄ›› Eያሉ ነው የሚጠሩኝ፡፡ Eኔም ከፋራው ስሜ የወጣውን የAራዳ ስሜን ስለምወደው ራሴን ሳስተዋውቅ ራሱ ‹‹በፍቄ›› የምልበት ጊዜ Aለኝ፡፡ የምጠቀምባቸው የበይነመረብ መለያዎች (internet identity) በሙሉ በበፍቄ ተሞልተዋል - befeqefication of Befeqadu ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ ከፋራው መሬት ወደAራዳው Iንተርኔት ስወጣ የተጠቀምኩት Aራዳውን ስሜን ነው፡፡ ይሁን Eንጂ Aሁንም ስሜን ለውጭ ዜጎች የመንገር ችግር Aለብኝ፤ ምክንያቱም Aይገባቸውም፡፡ ስለዚህ ሁለቴ Eሞክርና በሦስተኛው ‹‹በፍ›› Eላቸዋለሁ - ግልግል፡፡ 2. Terje S. Skjerdal ለዶክትሬት ድግሪያቸው ማሟያ በAገራችን የመንግሥት ሚዲያዎች የታማኝነት ሥራ ላይ በጻፉት ወረቀት መግቢያ ላይ ‹‹ስለIትዮጵያ ስሞች ማስታወሻ›› Aስፍረዋል፡፡ Eንዲህ ይነበባል ‹‹The dissertation follows Ethiopian naming tradition by using first name as the primary reference, although the second name (the person’s father’s name) is habitually added for clarification. The work makes no use of designations such as ‘ato’ and ‘weyzero’, even if this is customary when referring to prominent persons in Ethiopia. This should not be read as a sign of impoliteness, but rather as a principle of treating all persons on an equal basis.›› በፈረንጅ ባሕል ዋና ስም የሚባለው የቤተሰብ ስም የሚባለው ሲሆን፣ ማርከስ ከሆነ… ከዘመን ዘመን የልጆቹ ሁሉ ዋና ስማቸው ማርከስ ሆኖ መጠሪያ ስማቸው ብቻ ሲቀያየር ይኖራል፡፡ ምንጅላቴም፣ ቅድም Aያቴም፣ Aያቴም፣ Aባቴም፣ Eኔም - ሚ/ር ማርከስ Eንባላለን፡፡ Iትዮጵያዊ ባንሆን ኖሮ በAንድ ቤተሰብ ውስጥ የስም ልዩነታችን በተሰጠን Eና በመሐከለኛ ስማችን ነው፡፡ O… ይቅርታ ያልገባኝን ነገር ላስረዳችሁ Eየሞከርኩ ነበር፡፡ ግን Aሁንም Eቀጥላለሁ… ፈረንጅ ወንዶች (Eንደዛሬው በጥቂቱ ሳይስተካከሉ በፊት) ከIትዮጵያውያን የባሰ የሴት ንቀት ነበረባቸው፡፡ ሴት ልጅ በAባቷ ከዛም በባሏ ጥበቃ ኖራ የምታልፍ ፍጡር ናት - ለነርሱ፡፡ ማረጋገጫዬ ስም Aወጣጣቸው ነው፡፡ Eንበል ክላራ ማርከስ የማርከስ ቤተሰብ ያፈራት ቆንጆ ልጃገረድ ናት - ሚስ ማርከስ ይሏታል፡፡ ከሚ/ር ዲከንስ (ማርክ ዲከንስ) ጋር ስትጋባ ሚስስ ዲከንስ ትሆናለች፡፡ Aለቀ፤ የክላራ ታሪክ መጀመሪያ የማርክስ ልጅ ቀጥሎ የዲከንስ ሚስት መሆን ነው፡፡ 3. የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ፓርላማ በስም Aሰያየም ላይ ተሰይሞ ሲወያይ ነበር፡፡ ታዲያ ያኔ የAውሮጳ ማደግ መመንደግ Eያስቀናቸው የነበሩ የፓርላማ Aባላት Iትዮጵያን በAንዴ Aስመንድገው Aውሮጳ ላይ ለማድረስ Aውሮጳ ውስጥ ሁሉ የሆነው Eንዲሆን ይመኙ ነበር Eና ስም Aሰያየማችንም EንደAውሮጳውያን ይሁን ‹‹የቤተሰብ ስም ይኑር፤ ቤተሰቡ Aንድነቱ በAንድ ስም ይገለጽ፤›› ብለው ተከራከሩ፡፡ የዚህች ክርክር ነገር ወ/ሮ ገብሩ Eንደሚያሰኛቸው የገባቸው Aርበኛ ስንዱ ገብሩ ግን Aይሆንም ብለው በመከራከራቸውና መኳንንቱን በማሳመናቸው - ስንዱ ገብሩ ምስጋና ይግባቸውና - ሁላችንም በስማችን ለመጠራት በቅተናል፡፡

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

5  

4. ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ‹‹መክሸፍ EንደIትዮጵያ ታሪክ›› ባሉት መጽሐፋቸው ላይ Aሜሪካን Aገር የገጠማቸውን Eንዲህ ይተርካሉ፤ ‹‹…በሥራው ላይ የነበረችው ሴትዮ ሙሉ ስምህን ጻፍልኝ Aለችኝና ጻፍኩላት፣ በቴሌፎን ማውጫው ላይ የሚገባው ስምህ ማርያም ነው Aለች፤ Aንደኛ ማርያም የኔ ስም Aለመሆኑን፣ ሁለተኛ ወልደማርያም የኔ ስም Aለመሆኑን፣ ሦስተኛ ስሜ መስፍን መሆኑን Aስረድቼ ስጨርስ Eንደሱ ከሆነማ ሙሉ ስምህ የሚጻፈው ወልደማርያም መስፍን ተብሎ ነው Aለችኝ፤ ከፍተኛ ክርክር ጀመርን፤ በክርክር የማይገፋ መሆኑን ከተረዳሁ በኋላ ኮስተር ብዬ ስሜን የማውቀው Eኔ ነኝ፤ ማን Eንደሆንህና ማን ተብለህ Eንደምትጠራ Aታውቅም ካላልሺ በስተቀር Eኔ የምነግርሽን Aድርጊ ብዬ ክርክሩ ቆመ፤…›› ብለው ጽፈዋል፡፡ 5. Bewketu Seyoum ‹‹Eንቅልፍና Eድሜ›› ባሰኛት ልቦለዱ ላይ ስለስም Eንዲህ ቀልዷል ‹‹…ሰውየው ግን ተሰውሮ የኖረ ወንጀል ምስጢር Eንደተገለጠለት መርማሪ ፖሊስ፣ ድንገት ዓይኑን Aጥብቦ፣ ራሱን በጣም Eየነቀነቀ፣ ‹‹ስሜን ረስተኸዋል ልበል?›› ይለኛል፡፡ ዝም Eላለሁ፡፡ መቼም ስሙን Eንደገና ከምጠይቀው ብድር ብጠይቀው ይመርጣል፡፡ ራሱን ወደጎን Eየወዘወዘ ‹‹በገዛ ጋዜጣህ ላይ ስሜ ቁልጭ ብሎ ወጥቶ ዘነጋሁት Eንዳትለኝ›› ይለኛል፡፡ ምን ልበለው? Eሠራበት የነበረው ጋዜጣ ላይ ስሙ መውጣቱም ሆነ ስሙን መርሳቴ Aያስገርመኝም፡፡ After all ጋዜጣ ማለት የስም ማጎሪያ ማለት ነው፡፡ የዘንድሮ የፊዚክስ ኖቤል ሎሬት Eና የAፋልጉኝ ማስታወቂያ የወጣለት ጎረምሳ ስማቸው ባንድ ገጽ ላይ ይወጣል፡፡…›› 6. ተረትና ምሳሌዎች - ስለስም

ስምህ ማነው ለAገር Aይመች ማን Aወጣልህ ጎረቤቶች ስምሽ ማነው ቢሏት ቂጤ ትልቅ ነው Aለች ስምን መላክ ያወጣዋል ስም* ከመቃብር በላይ ይውላል ስም ያለው ሞኝ ነው ስም ይሸታል ከስብ ስም ይወጣል ከቤት ይሄዳል ጎረቤት

* ስም የሚለው ቃል Aንዳንዴ መጠሪያ ቃል ከሚለው ትርጉም በላይ Eንደሚኖረው ተረትና ምሳሌዎቻችንን ዋቢ በመጥራት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስም የሚለው ቃል ምናልባት በEንግሊዝኛው brand ከሚለው ጋር ሊመሳሰል ይችላል - ስም ያለው Eቃ ስንል፡፡ ሁሉም ስም Aለው ግን መልካም ስም ያለው፤ ክብር ያለው (ለሰውም ይሆናል) - ስመጥር Eንዲሉ፡፡ ለምሳሌ ‹‹Abe Tokichaw Eባክህ ለስምህ ተጠንቀቅ፤ ታገል ሰይፉን Aትውቀስ›› Eንዳሉት ሰዎች፡፡ ለመሆኑ የታገል ሰይፉም Eንዲሁ ነው፤ Aሁን፣ Aሁን ስሙ ከስብ ይሸታል፡፡

መደምደሚያ፤ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሞኝነት ነው፤ ምክንያቱም ስም ያለው ሞኝ ነው፡፡

የካቲት 8፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

6  

ማነው Aምባገነን?

ሰው ሁሉ Eንደሚያስብው፥ መጣጥፉም Eንደሚለው፣ መንግሥት ማለት ሕዝቡ፥ ሕዝቡም ማለት…

……….ያው መንግሥት ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ኀልዮት፥ በtransitivity law፣ ይህንን ትርጉም ይዤ፥ Eኔም Eናገራለሁ፣

መንግሥት Aላግባብ ገንኖ፥ Aምባገነን የሚሆነው፣ ሕዝቡ ቀድሞ ሲገ’ንን፣ ስሜቱን መግታት ሳይችል ነው፡፡

ግለሰብ ጭቆና በቅቶት፥ Eምቢ Aሻፈረኝ Eያለ፣ ሕዝቡ ግን በፍራት ታስሮ፥ Aብሮት Eምቢ ካላለ፣

ነጻ ‘ሚወጣም Aይኖር፥ ነጻነትም ባገሩ የለ፣ ስለዚህ የሚበጀው፥ የመጀመሪያው ቁምነገር፣ Aምባገነኑን ሕዝብ፥ ስለነጻነት ማነጋገር፡፡

የካቲት 12፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፬፤ የAማርኛ ፊልም ፊታውራሪዎች የAማርኛ ፊልሞች ፊታውራሪዎች ሁለት ናቸው፤ ፊልሞቹን የሚያይ ቀርቶ ፖስተሮቹን የሚገርብ ሳይቀር ያውቃቸዋል፣ ፊልሞቻቸውን ተመልካቹ ‹‹በግፊያ›› ይገባላቸዋል ይባላል፣ Eነዚህ ሁለት ‹‹ተዋንያን›› ነፃነት ወርቅነህ Eና ዓለምሰገድ ተስፋዬ ናቸው፡፡ የነቶሎ፣ ቶሎ ፕሮዳክሽን ፊልሞቻችን የሁለቱን - ሁሉም ፊልም ላይ ተመሳሳይ Eንቶ ፈንቶ ባሕሪ የሚጫወቱ ‹‹ተዋንያን›› ግንባር ለማስገባትና ‹‹ገበያ ለመጨመር›› ሲሉ ከሁለት Aንዱን ይጠቀማ፤ ሲጠቀሙ ታዲያ Eነዚህ ሰዎች ዋና ገፀባሕሪ ካልሆኑ በቀር ከታሪኩ ጋር ግንኙነት በሌለው ግንጣይ Aስቂኝ ባሕሪነት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በ‹‹ባለታክሲው›› ፊልሟ ያደነቅናት ዳይሬክተር ‹‹ሲቲ ቦይስ›› ባለችው ፊልሟ ነፃነትን ይዛ ‹‹በሳቅ ልትገድለን›› ሞክራለች፡፡ ይሄን፣ ሌሎችን Eና Eንደምሳሌ ነፃነት በ‹‹ታስጨርሺኛለሽ›› Eና ዓለምሰገድ በ‹‹ያረፈደ Aራዳ›› ላይ የተጫወቱዋቸውን ሚናዎች ቆርጣችሁ ብታወጡት ከፊልሙ ታሪክ ውስጥ ምንም Aይጎድልም፤ Eንዲያውም Aንዳንዴ ፊልሙን ጽፈው ከጨረሱ በኋላ የሚያስገቡዋቸው ይመስለኛል፡፡ Eኔ ከሁለቱ የማይችሉ ተዋንያን Aንዱን ምረጥ ብባል ዓለምሰገድን Eመርጣለሁ፡፡ ሆኖም ነፃነት የበለጠ ‹‹ተወዳጅ›› Eንደሆነ ይነገርለታል፡፡ Eርሱ ግን ለፊልም [Eና ተመልካቹ] ያለውን ንቀት ‹‹በሳምንት ሁለት ፊልም Eሰራለሁ›› በማለት ገልጾታል፡፡ ብዙዎቹ ፊልሞች የሚሠሩት ቀደም ሲል በመጠኑ የተሳካለት ፊልም Eና ገፀ ባሕሪ ላይ ተመሥርተው ስለሆነ ፊልሞቹ የሚጻፉት ለተዋንያኑ የAጨዋወት ችሎታ Eንዲስማሙ ሆነው Eንጂ ለታሪኩ Eንዲስማሙ የተመረጡ ተዋንያንን ማግኘት ይከብዳል፡፡ Eንዲያውም Aንዳንዴ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

7  

የፊልሙን ታሪክ የሚጽፉት የተዋንያኑ ራሳቸው የየራሳቸውን ድርሻ የጻፉ ይመስል… ሁሉም ተዋንያን የቀደመ ፊልማቸው ላይ ያለውን ባሕርያቸቸውን ይዘው ‹‹Aዲሱ›› ላይ ይመጣሉ፡፡ ዓለምሰገድ Eና ነፃነትም ሁሉም ፊልማቸው ላይ ያለው ባሕርያቸው፣ ቃላት Aጠቃቀማቸው Eና Aተዋወናቸውን ዓይቶ Aንዱን ካንዱ መለየት ባለመቻል ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ‹‹ዝነኞች›› ናቸው፡፡ ---- ማሳሰቢያ፡- ብዙ ፕሮዲዩሰሮች የነዚህን ፊልሞች ታዳሚ Eየተመለከቱ ‹‹every audience deserves its own movie industry›› የሚመስል ተረክ ይነግሩናል፡፡ ይሄ ፊልም ተመልካች Eነዚህን ፊልሞች ካላየ የሚቀረው Aማራጭ ቤት መቀመጥ ነው - ምን ያድርግ? ይሄ ተመልካች ‹‹ኮሜዲ›› ብቻ የሚወድ ከሆነ ለምን ‹‹ውሳኔ››ን በድብድብ ገብቶ ተመልክቶ Aለቀሰለት? Eርግጥ ነው፣ Aንዳንድ የማይረቡ ሌላ genre ያላቸው ፊልሞች ተሞክረው ከገበያ ወጥተዋል፡፡ ነገር ግን ከማይረባ ትራጄዲ፣ የማይረባ ኮሜዲ Eንደሚሻል ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ተመልካቾች የሚፈልጉት ጥሩ ፊልም ነው፡፡ ጥሩ ፊልም ደግሞ የጥሩ ታሪክ፣ የጥሩ ተዋንያን፣ የጥሩ ዳይሬክተር፣ የጥሩ ካሜራ፣ የጥሩ ኤዲቲንግ Eና የጥሩ ማስታወቂያ ውጤት ነው፡፡ በትንሽ ወጪ ብዙ ብር ለማግበስበስ ከማሰብ በላይ ማሰብ ይፈልጋል፡፡

የካቲት 18፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፭፤ ቁንጅና Eና ብስለት ቁንጅና Eና ብስለት inversely proportional ናቸው ወደሚል መደምደሚያ Eየተንከባለልኩ Eገኛለሁ፡፡ ዓይኔን ጨፍኜ Aንድ ሰዓት በትEግስት ላዋራት የምችላት ቆንጆ ሴት ያለች Aይመስለኝም፡፡ ገና በሁለት ዓረፍተ ነገር ብዙ ቆንጆዎችን Eንዳበሳጨሁ በመገመት Eቀጥላለሁ፡፡ ማኅበረሰባዊ Eሴት ነውና ቁንጅና ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ላይ ዋጋው ይበረታል ብዬ ስለሴቶች ቁንጅና ብቻ ማውራቴንም Eቀጥላለሁ፡፡ ሀ). Eንከን የለሽ ቆንጆ ሴት ሆና ትልቅ የስኬት ጣሪያ ላይ የደረሰች ሴት የለችም Aልልም፤ ነገር ግን ትልልቁ የስኬት ጣሪያ ላይ ለመውጣት Eያንዳንዷን የመሰላል Eርከን Eየረገጡ የሚወጡት ሴቶች ባብዛኛው ቆንጆ ያልሆኑ ሴቶች ናቸው ነው Aባባሌ፡፡ በነገራችን ላይ ‹ቆንጆ ያልሆኑ› ማለት Aስቀያሚ ማለት Aይደለም፡፡ Aስቀያሚነት ከቆንጆነት ያልተናነሱ ብዙ Aስቀያሚ ገመናዎች Aሉት፤ ደግነቱ ይኼ ጫወታ ስለቁንጅና ነው፡፡ ለ). ‹‹beauty is in the eyes of the beholder›› ብላችሁ Aትከራከሩኝም ብዬ Aላስብም፡፡ Eርግጥ ነው የተለያዩ ማኅበረሰቦች የተለያዩ የቁንጅና መለኪያዎች Aሏቸው (የግለሰቦች የቁንጅና መለኪያ ደግሞ ካሳደጋቸው ማኅበረሰብ ርቆ Aይርቅም)፤ ሦስት ነጥብ Eዚህ ተረክ ላይ ማፍሰስ ይኖርብኛል፡፡ የመጀመሪያውን ቁንጅና Eንደየማኅበረሰቡ የተለያየ ነው ብለነው Eንጀምር፡፡ ዞሮ፣ ዞሮ ያቺ ሴት Eዚያ ማኅበረሰብ ውስጥ ተወልዳ Eስካደገች ድረስ በዚያ ማኅበረሰብ ውስጥ ቁንጅናዋ በሰጣት ሚና መሠረት ብስለቷ በላይኛው ነጥቤ መሠረት ዝቅ ያለ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው፤ ቁንጅና Eንደምናስበው I-ሳይንሳዊ Aይደለም፡፡ ሳይንቲስቶቻችን የቁንጅና ውጤት face symmetry ነው Eያሉ ነው፡፡ ፊትን ለሁለት ከፍላችሁ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

8  

የግራና ቀኙ Eኩል የሚገጥም ከሆነ ቆንጆ ፊት ገጥሟችኋል ማለት ነው፡፡ ከፈለጋችሁ ደግሞ ይህንን የሚለካ ሶፍትዌርም ስለተሠራ ጉግል Aድርጉት፡፡ በነገራችን ላይ Eነፓይታጎራስ የAፍንጫ Eና የAፍ ስፋት ንፅፅር 1.6 ከሆነ ቆንጆ Eንደሚያሰኝ ተናግረዋል፡፡ የቶሮንቶ ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎች በዓይንና በAፏ መካከል ያለው ርቀት የፊቷን ርዝመት 36 በመቶ የሆነች ቆንጆ ነች ብለዋል፡፡ ሌሎች ተመራማሪዎች የወገብ Eና የዳሌ ንፅፅር 70 በመቶ ሲሆን በወንዶች ዓይን ወዲያው Eንደሚገባ Eየተናገሩ ነው፡፡ ሌላኛው Eውነታ ደግሞ ሰዎች ለራሳቸው መልክ የቀረበ መልክ ሲመለከቱ ቆንጆ ብለው የሚያስቡ መሆኑ ነው፡፡ ይህኛው ነው በተለይ ቁንጅናን በተመልካቹ ዓይን የሚያስቀምጠው፡፡ ሐ). ቁንጅና ያበላሻል፤ ያውም ወንዱንም ሴቷንም፡፡ Aሁንም ተመራማሪዎች Eንዲህ ይላሉ፤ Aራስ Eናቶች በface symmetry ቆንጆ የሆነውን ሕጻናቸውን ቆንጆ ካልሆነው ይልቅ ረዥም ሰዓት Aቅፈውት ይቆያሉ፡፡ ይሄንን ስታነቡ ነው የቁንጅና ኃይል Eና ስልጣን የሚገባቸሁ፡፡ ጎዳና ላይ ከሚለምኑ ሕጻናት መካከል ቆንጆዎቹ ሲለምኗችሁ ለቆንጆዎቹ ባትለግሷቸው Eንኳን ከንፈር ትመጡላቸዋላችሁ፤ Aስቀያሚዎቹ ግን ትዝም ሳይሏችሁ ነው የምታልፉት፡፡ በየመንገዳችን Aጎንብሰን Eንድንስማቸው የሚያነሳሱን ሕጻናት ቆንጆዎች ናቸው፡፡ የቁንጅና መዘዝ Eንዲህ ያድጋል፡፡ በልጅነቷ ‹‹ብረት መዝጊያ የሆነ ባል›› ታመጣለች ትባላለች፣ ወንድ ተማሪዎች Eሷን ለማናገር፣ ሴቶቹም ጓደኞቿ ለመሆን Eንዳመሏ ይችሏታል፡፡ ዩንቨርስቲ ውስጥም ጌጥ ነች፡፡ በዩንቨርስቲ ውስጥ ‹‹መምህሬ ጠይቆኝ Eምቢ ስለው ግሬድ ቀነሰብኝ›› ከሚሉ ባለታሪኮች ይልቅ የሚበዙት ማንም ሳይሰማ በጓዳ ተጠናቅቀው የማይገባቸውን ግሬድ የሚያገኙት ሴቶች ናቸው፡፡ ሥራ መቀጠር ላይም ቢሆን ቀጣሪዎች ቆንጆ ይመርጣሉ፡፡ ቆንጆ ሴት የምትናገረው ቀሽም ነገር ለወንድ Aድማጭ ቆንጆ ያልሆነች ሴት ከምትናገረው የረባ ነገር የሚበልጥበት ጊዜ Eልፍ ነው፡፡ ምEራባውያን ቆንጆዎች በደሞዝ ቆንጆ ካልሆኑት በተወሰነ መጠን Eንደሚበልጡ ብቻ ሳይሆን ቁንጅና ለሥራ ተመራጭ Eንደሚያደርግም Aረጋግጠዋል፤ Eንዲያውም በቁንጅና ማግለል በሕግ ይከልከል የሚሉም Aልጠፉም፡፡ ሳስበው፤ ቆንጆ ሴት ስትናገር ወንድ የሚሰማው ድምፅዋን ብቻ Aይደለም፤ ውበቷንም ጭምር ነው፡፡ ይህን ስለምታውቅ Eሷም Aብዛኛው Eውቀቷ Eና ሐሳቧ ውበቷ ነው የሚሆነው፡፡ ዞሮ፣ ዞሮ ቆንጆ ሴትን ውበቷን የሚመኙ ወንዶችም ሆኑ ውበቷ ራሱ (obsess ስለሚያደርጋት) በቀላሉ ትበላሻለች፡፡ መ). ሻሮን Oስቦርን የተባለች Eንግሊዛዊት የቴሌቪዥን ፕሮግራም Aቅራቢ፣ ደራሲ Eና የሙዚቃ ማኔጀር ‹ሳይኮሎጂስ› ለተባለ መጽሔት የተናገረችው የAንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ ነበር - ‹‹ስኬታማ የሆንኩት ቆንጆ ባለመሆኔ ነው፤›› በማለቷ፡፡ ሻሮን የተሳሳተች Aይመስለኝም፡፡ ‹‹Eንከን የማይወጣላቸው›› ቆንጆ ሁነው፣ ብስለታቸውም ያንኑ ያክል ጣሪያ የነካ ሴቶች ከገጠሙኝ ደስታውን Aልችውም፤ ነገር ግን ለዚህ ቆንጆዎችን የሚያበሳጭ፣ ሌሎችን የሚያወዛግብ ሐተታ መደምደሚያ የምመርጠው ጥያቄ Eሱን Aይደለም፡፡ የክሊዮፓትራ የተወራለት ‹‹ኃይል›› ምንድን ነው፡- ቁንጅና ወይስ ብልሐት?

የካቲት 26፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

9  

Aጭር መጣጥፍ ፮፤ የጾም ወግ Aብይ ጾም ልክ Eንደስሙ Aብይ ነው፤ Eንኳን ጧሚዎቹን Eኛንም ያጾመናል፡፡ ምግቦች ሁሉ ወደበየዓይነት፣ ሴቶች ሁሉ ወደመነኩሴነት ይቀየራሉ፡፡ የI.O.ተ.ቤ.ክ.* ሲኖዶስ ካወጃቸው ሰባት Aጽዋማት Aንዱ Eና ዋነኛው ይህ ነው፡፡ ከAብይ ጾም ተከትሎ 40 ቀን የሚዘልቅ ፋሲካ ይመጣል፡፡ በዓመት ውስጥ ረቡE Eና Aርብ የማይጾምባቸው ቀናት Aብይ ጾም ሲያልቅ የሚመጡት የፍሰካ ቀናት ብቻ ናቸው፡፡ ነገርዬው በጾም ያደከሙትን ሰውነት መልሶ ወደመገንባት የመመለስ ስትራቴጂ ነው የሚመስለኝ፡፡ ለማንኛውም Aሁን ጾም በመጣ ቁጥር የሚታሰቡኝን ወጎች Eንደወረዱ፡- ሀ). የጾም ምግብ የI.O.ተ.ቤ.ክ. ጾም የምግብ ዓይነት ይለያል፡፡ ለቬጂቴሪያኖች የተስማማ የምግብ ዓይነት መሆኑን Eና Aትክልት ለጤና ተስማሚ መሆኑን ሳይንስ የሚደግፍ መሆኑን Eየጠቀሱ የሚጎርሩብኝ ጓደኞች Aሉኝ፡፡ Aሳ ከፊሎች የሚጾሙት ከፊሎች የማይጾሙት የስጋ ዓይነት ነው፡፡ Aሳ ለምን Eንደማይጾም በልጅነቴ የሰማሁት ተረት ይተርካል፡፡ Aንድ መነኩሴ በሶ ጨብጠው Eና በሶ የጨበጡበትን Eጃቸውን ወደላይ Aርገው በዋና ወንዝ ሲያቋርጡ ጭብጦው በሶ Aምልጦ ውኃ ውስጥ ገባ Eና Aሳ ሆነ፤ ስለዚህ Aሳ ጾም የለውም፡፡ ሌሎች ደግሞ፤ የድሮ ነገሥታቶቻችን ጮማ የለመዱ በመሆናቸው Eነሱን ለማስጾም ላላ ያለጮማ ያስፈልግ ነበር፤ ስለዚህ Aሳ ተፈቀደላቸው፡፡ ዞሮ፣ ዞሮ… በAብዛኛው ሌላኛው ዓለም ጾም ማለት ምግብ Aለመብላት ማለት Eንጂ ምግብ መምረጥ Aይደለም፡፡ የጾም Eና የፍስክ ተብለው ምግቦች የተለዩባቸው ጥቂት Oርቶዶክሶች Eና ጥቂት ካቶሊክ ቤተክርስትያናት ብቻ ናቸው፡፡ የሆነ ሆኖ… EንደI.O.ተ.ቤ.ክ. ከሆነ ስጋ Eና የስጋ ውጤቶች የተከለከሉት ሰውነትን ለማድከም Eና በጥጋብ ወደEብሪት Eና ትምክህተኝነት Eንዳንገባ ነው፡፡ ነገር ግን (1). ወተት በተቀዳበት ብርጭቆ ውኃ ቢጠጡበትም ያው ጾም የነካው ጠጡ ማለት ነው፤ ይቺም ገብታ Eንዳታበረታ ነው? (2). የባቄላ ሽሮ ከስጋ ያልተናነሰ ገንቢ ንጥረነገር ያለው መሆኑንስ ሃይማኖት Eንዴት ያየዋል? ለ). ጾታዊ ተላጽቆ ጾታዊ ተላጽቆ ያልኩት ‹ወሲብ› የሚለውን ቃል ነው፤ ቃሉ ለጾም ወቅት ተስማሚ ይሆናል Eንድል ያደረገኝ መጀመሪያ ያየሁት የOርቶዶክስ መጽሐፍ ላይ በመሆኑ ነው፡፡ ጾታዊ ተላጽቆ በEስልምና ጾምም ቢሆን ምግብ በማይበላበት ሰዓት ይከለከላል፡፡ በAሁኑ ጾምም Aርባ ቀን ሙሉ በዞረበት መዞር Aይፈቀድም፡፡ ለነገሩ የጾም ዓላማ Aካልን ማድከም ከሆነ… ጾታዊ ተላጽቆ መፈቀድ ነበረበት፡፡ Eርግጥ ነው፤ ከተላጽቆ የሚገኘው ፍስሐ Eንዳይኖር ተብሎ ነው የሚከለከለው… Eንዲያ ከሆነ ደግሞ፤ መሳሳምስ ይፈቀዳል? (በነገራችን ላይ የሱም ነገር የጾም Eና የፍስክ የሚባል ነገር መኖሩን ሰምቻለሁ፤ በኮንዶም Eና ያለኮንዶም መሆኑ ነው፡፡) በነገራችን ላይ የI.O.ተ.ቤ.ክ. Eምነት ተከታይ ምንጮቼ Eንደነገሩኝ ከሆነ በቤተክርስትያን ሥርዓት Aዲስ የተጋቡ ሙሽሮች ለ40 ቀናት ያክል ለጾታዊ ተላጽቆ ሲባል ጾም ማፍረስ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

10  

ይችላሉ፡፡ Eንግዲህ ትላንት Eሁድ የተጋቡትን Aስቧቸው፡፡ ሰማንያ ቀን ሙሉ… ትርፉ ድካም ነው! ሐ). መግቢያ Eና መውጫ የጾም መግቢያ Eና መውጫ ላይ የስጋ Eና የAልጋ ነገር ይበዛል፡፡ ጾም ሲገባ የመሰናበቻ፣ ሲወጣ ደግሞ የEንኳን ደህና መጣህ፡፡ በቤተክርስትያን ሰዎች ጾም በደስታ Eና በፍላጎት Eንጂ በግድ የሚጾም Eንዳልሆነ ይሰበካል፡፡ ታዲያ ጾም ሲወጣ ‹‹Eንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታልሽ/ህ›› የሚሏት Aባባል ታስገርመኛለች… ‹‹Eፎይ…ግልግል›› የማለት ያክል ነች፡፡ ለመደምደሚያ ምናልባት የሰማችሁትን Aንድ ቀልድ ልንገራችሁ፡፡ የሁዳዴ ጾም ሲገባ ከጾም መያዣ የተረፈውን Aላስችል ብሏት የበላች Aንዲት ሴት ሔዳ ንስሐ Aባቷጋ ተናዘዘች፡፡ ‹‹ግዴለም ካሁን በኋላ ጹሚ›› ተባለች፡፡ Aሁንም በፋሲካ ዋዜማ… ለፋሲካ መፈሰኪያ ስታሰናዳ Aላስችል ብሏት በላች፡፡ ድጋሚ ንስሐ Aባቷጋ በመሄድ ስትነግራቸው፤ ንስሐ Aባቷ ተበሳጭተው… ‹‹ኤዲያ Aንቺ ደግሞ፤ ጾሙን Aላስገባ Aላስወጣ ነው Eንዴ የምትዪው?›› Aሏት ይባላል፡፡ መልካም ጾም ለጹዋሚዎች! * የI.O.ተ.ቤ.ክ - የIትዮጵያ Oርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን

መጋቢት 2፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፯፤ ቃለምልልስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ’ጋ* Eኔ፡- በመጀመሪያ የተናጠል ቃለ መጠይቅ Eንዳደርግ ስለፈቀዱልን Aመሰግናለሁ፡፡ ኃ/ማ፡- Eኔም ከዚህ ሁሉ ባለሥልጣን Eኔን መርጠህ ቃለ መጠይቅ ልታደርግልኝ በመፈለግህ

Aመሰግናለሁ፡፡ Eኔ፡- Eንዴ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር በሥልጣኑ Eርከን የመጨረሻው Eኮ Eርስዎ ኖት? ኃ/ማ፡- Eውነቱን ልንገርህ፤ [ዙሪያ ገባውን ገልመጥመጥ Eያሉ…] Eኔም መጀመሪያ Eንደዛ

መስሎኝ ነበር፡፡ Eየቆየሁ ግን ከመለስ ሞት (…ይቅርታ ከባለራEዩ መሪያችን መሰዋት በኋላ በል ተብዬ ነበር… ) በኋላ Aገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ብሎ ነገር የላትም፡፡

Eኔ፡- Eንዴ Eርስዎስ? ኃ/ማ፡- Eኔማ… የገባሁበትን Aትጠይቀኝ? Eኔ፡- ጠቅላይ ሚኒስቴርም ያማርራል Eንዴ?

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

11  

ኃ/ማ፡- ጠቅላይ ሚኒስቴርም Eኮ የሚኒስትሮቹን ምሬት ሁሉ ጠቅልሎ ነው የሚያማርረው፤ ችግሩ የኔ የተለየ መሆኑ ላይ ነው፡፡

Eኔ፡- የEርስዎ የተለየው በምንድን ነው? ኃ/ማ፡- Eኔማ ስሜ ከብዶኝ ነዋ… Aይገባህም Eንዴ? [የሌባ ጣታቸውን Eያወዛወዙ ሲያወሩ

ያስፈራሉ፡፡] Eኔ፡- ይቅርታ Aድርጉልኝ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ፤ የበለጠ ግራ Eያጋቡኝ ነው፡፡ ሰው Eንዴት

ስሙ ይከብደዋል፡፡ ኃ/ማ፡- ኤዲያ… Aንተን ብሎ ጋዜጠኛ… ስሜ ያልኩህ ማEረጌን ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር

ተብዬ Eንኳን ሚኒስትሮቹን ልጠቀልል፣ የፓርላማ ንግግሬ Eንኳን ተጽፎ ነው የሚሰጠኝ፡፡ በገዛ Eጄ የገባሁት የተሸመቀቀ ገመድ ው… ስ… ጥ… ነው! [የመጨረሻዎቹን ቃላት በቁጣ Eርግጥ Eያደረጉ…]

Eኔ፡- ሕገ መንግሥቱ Eኮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን በግልጽ ይደነግጋል፡፡ Eንደሕገ

መንግሥቱ ከሆነ Eኮ ከፈለጉ Aምባገነን መሆን ይችላሉ… ሁሉ በጅዎ… ሁሉ በደጅዎ….

ኃ/ማ፡- ሕገ መንግሥት…? የምን ሕገ መንግሥት…. የደላው ሙቅ ያኝካል ነው የምትሉት?

… ሕገ መንግሥቱን ቤተ መንግሥት ማን Aስገብቶት? ከቤተመንግሥት ሕገመንግሥታዊ ነገር ሲወጣ ዓይተህ ታውቃለህ? ተናገር…. ታውቃለህ? ቤተመንግሥት ውስጥ ያለው መሣሪያና ባለመሣሪያ ብቻ ነው… Aራት ነጥብ Aለ መለስ፡፡ ቂቂቂቂ…. [ድምፃቸውን ዝቅ Aድርገው፡፡]

Eኔ፡- Eንዴ…. ሕገ መንግሥቱ Eኮ ታዲያ በዋነኝነት መግዛት ያለበት መንግሥትን ነው? ኃ/ማ፡- ምን Eያልኳት ምን ትላለች Aሉ… Eኔ፡- ይቅርታ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ ግራ ግብት ቢለኝ Eኮ ነው፤ ታዲያ Eንደዚህ ከመረርዎት

ለምን ሥልጣን Aይለቁም፡፡ በዚያውም Eኮ ሥልጣኑን በገዛ ፈቃዱ የለቀቀ የመጀመሪያው የIትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ፡፡

ኃ/ማ፡- Aንተ ደግሞ… የዘንድሮ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከመውጣቱ ይልቅ መውረዱ ይብዳል? Eኔ፡- Aልገባኝም… ኃ/ማ፡- በቃ… Aሁን Eኔን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ብሎ ማን ጠበቀ?... ማንም!... ግን

ለመለስ ሞት ምስጋና ይግባውና በድንገት Eና ባጋጣሚ ሆንኩ፤ ምን ዋጋ Aለው? ለካስ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያዩት ያምር ሲይዙት ያደናግር ነው… ግራ ግብት Aለኝ… ጌታ ጠላትህን ግራ ያጋባውና፡፡

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

12  

Eኔ፡- ሥልጣን ደግሞ መያዙ Eንጂ መልቀቁ ምን ግራ ያጋባል? ኃ/ማ፡- Aይ መሬት ያለ ሰው!.... መያዝ መሰለህ Eንዴ የኔ Aያያዝ? መይያዝ ነው፡፡ ልክ

EንደEስረኛ መይያዝ… ያዝ ተብለህ ስትይዝ Eና ልያዝ ብለህ ስትይዝ ይለያያል፡፡ በዚያ ላይ ግራና ቀኝ ምክትል Aለቆቼ ያዋክቡኛል፣ በዚህ ላይ ሥልጣኔን መጠቀምም ያምረኛል፡፡ Aሁንማ Aታስዋሸኝ… ጥለህ ጥፋ… ብረር፣ ብረር ነው የሚለኝ፡፡

Eኔ፡- Eኔም Eኮ ጥያቄዬ Eሱ ነው? ኃ/ማ፡- [ተከዝ Aሉና]… በየት በኩል?... ንገረኝ Eስኪ በየት በኩል?... ቤተመንግሥቱ በወታደር

ተከቧል፣… ነጋዴዎች ሳነጋግር ተከብቤ ነው፣ ውጪ Aገር ስሄድ ተከብቤ ነው… በየት በኩል… Eስኪ ንገረኝ በየት በኩል?

Eኔ፡- [Eያሳዘኑኝ] … Eሺ በቃ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ ወደሌላ ርEስ Eንለፍ… ኃ/ማ፡- Eሺ! Eኔ፡- ባለቤትዎ Eንዴት ናቸው? ኃ/ማ፡- ማ? Eኔ፡- ወ/ሮ ሮማን? ኃ/ማ፡- …ግራ ገብቶኝ ረሳኋት Eኮ… ደህና ነች፤ Eሷ ምን ትሆናለች? Eኔ፡- Aይ… Eምብዛም Aይታዩም ብዬ ነው፡፡ Eንዲያውም ብዙ ሰዎች Eስካሁን ወ/ሮ Aዜብን

ነው ቀዳማይ Eመቤት የሚሏቸው፡፡ ኃ/ማ፡- ነገርኩህ Eኮ Aገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር የላትም፤ ካላትም የበፊቱ ነው (ማለቴ…

ናቸው፡፡) Eኔ፡- O!... Eሺ ለሰጡኝ ቃለ ምልልስ Eያመሰገንኩ፣ ምናልባት ከተነጋገርነው ውስጥ ቆርጬ

Eንዳወጣው የሚፈልጉት ካለ ይንገሩኝ… ኃ/ማ፡- ሁሉንም ቆርጠህ ጣለው… ምንም Eንዳታስቀር… Eኔ፡- Eንዴ የተከበሩ… [Aቋረጡኝ] ኃ/ማ፡- ታስጨርሰኛለህ…. ታ..ስ..ጨ..ር..ሰ..ኛ..-ለ..ህ..! *April The Fool!

መጋቢት 23፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

13  

Aጭር መጣጥፍ ፰፤ ምናባዊ ቃለ ምልልስ ከመለስ ዜናዊ’ጋ ከኑሮ ውድነቱ’ጋ ውድድሩ ከብዶኛል፡፡ ስለሆነም Aንድ ቀን መሞቴ ላይቀር ለምን ብዙ ቀን Eቸገራለሁ የሚል ክፉ ሐሳብ ውልብ Aለብኝ፡፡ ከዚያም Eግዜር Eስኪጠራኝ ለመጠበቅ ትEግስቱ ስላልነበረኝ ራሴ ወደEርሱ ለመሄድ Aሰብኩ፡፡ በAጭሩ ራሴን ለማጥፋት ወሰንኩ ማለቴ ነው፡፡ ከዚያም ቁጭ ብዬ ራሴን ካጠፋሁ በኋላ ስለሚኖረኝ ሕይወት ሳስብ Eንደማልፀድቅ ታወሰኝ፤ ራሱን ያጠፋ ሰው Aይፀድቅም፡፡ በቃ ገሃነም መግባቴ ነው ብዬ Aሰብኩ፡፡ ከዚያም ገሃነም ከገባሁ በኋላ ብቻዬን ነው የምሆነው ወይስ Aብሬው የምደበረው ቀድሞ የማውቀውሰ ሰው Aገኝ ይሆን ብዬ ሳስብ፣ ያው መቼም ፖለቲከኛ Aይፀድቅምና መለስ ዜናዊን Eንደማገኝ ታሰበኝ፡፡ Eናም ስንገናኝ ቃለመጠይቅ ላደርግላቸው ወሰንኩ፡፡ ሆኖም ቃለ ምልልሱን ተመልሼ ለናንተ ወዳጆቼ Eንዳላስነብባችሁ ሰማይ ቤት ፌስቡክ የለም፡፡ ስለዚህ ቃለምልልሱን በምናቤ Aዘጋጅቼ Eንደሚከተለው ላስነብባችሁ ወሰንኩ፡- Eኔ፡- ጤና ይስጥልኝ?

መለስ [Eያነበቡት ካሉት መጽሐፍ ላይ Eንዳቀረቀሩ ላፍታ በግምባራቸው Aዩኝና ምንም ሳይሉ ወደንባባቸው ተመለሱ፡፡ የሚያነቡት መጽሐፍ ሰረቅ Aድርጌ ሳየው ‹ገሃነማዊ ዴሞክራሲ› ይላል፡፡]

Eኔ፡- Aወቁኝ፣ መለስ፡- [በንዴት መጽሐፋቸውን Aጥፈው] ማንነህ Aንተ? Eኔ፡- በፍቃዱ ዘ ኃይሉ ነኝ፤…. ጦማሪው፣… Aሁንስ Aወቁኝ? መለስ፡- Eንኳን ጦማሪ ቆማሪም ብትሆን Aላውቅህም፣ የማወቅም ግዴታ የለብኝም፡፡

የመጣህበት ጉዳይ ለቃለ መጠይቅ Eስከሆነ ድረስ ግን ጥያቄዎችህን Eመልስልሃለሁ… Eኔ፡- ለመንደርደሪያ ያክል Eስኪ ስለሚያነቡት መጽሐፍ ምንነት ጥቂት ይንገሩኝ? መለስ፡- ነሐሴ ወር ላይ (Aንዳንዶች ሐምሌ ነው ይላሉ፤) ገሃነም Eንደገባሁ በAስተዳደሩ

Aካላት የAፈፃፀም ችግር በመኖሩ፣ በርካታ በደሎች በሃጥኣን ላይ ሲፈፀም Eንደነበር በማስተዋል፣ የገሃነምን Aስተዳደር በስር ነቀል ለውጥ ትራንስፎርም ለማድረግ የነደፍኩት Aስተዳደራዊ ሥርዓትን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ገሃነም ውስጥ Aንድ ሰው የሚቃጠልበትን Eሳት ነዳጅ ሒሳብ Eንዲከፍል ይገደድ ነበር፣ Aሁን ግን ሁሉም ሰው በነጻ የሚቃጠልበትን መንገድ Aመቻችተናል፡፡ በመሆኑም በፊት በጉልበት ይቃጠሉ የነበሩ ሰዎች፣ ዛሬ በገዛ ፈቃዳቸው፣ በመከባበር መቀጣጠል ጀምረዋል፡፡ ቢሆንም ግን ገሃነም ገና ብዙ ሕዳሴ ያስፈልገዋል፣ ያ ሕዳሴ የሚመጣው ደግሞ በገሃነማዊ የዴሞክራሲ ርEዮተ ዓለማችን ብቻ ነው፤ Aራት ነጥብ፡፡

Eኔ፡- ለዚህ ሥርዓት ግንባታ ከበለፀጉት የገነት ነዋሪዎች ልምድ ለመቅሰም፣ ወይም ድጋፍ

ለማግኘት የሞከሩት ነገር Aለ?

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

14  

መለስ፡- Eኛ የውስጣዊ Aሠራራችን ላይ ጣልቃ ለሚገቡ ማንኛውም Aካላት በራችንን Aንከፍትም፡፡ የገነት ነዋሪዎች Eጃችንን በመጠምዘዝ ለEነርሱ Eንድናጎበድድ ይፈልጋሉ፡፡ Eኛ ግን መቼም Aናደርገውም፤ Eኛ ገሃነማውያን ከራሳችን የተሻለ ማንም Aያውቀንም፡፡

Eኔ፡- Eስኪ Aንዳፍታ ከሞት በፊት ስለነበረው ሕይወታችን Eናውራ፡፡ Aገራችንን መምራት

ምን ይመስላል? መለስ፡- የምን Aገር? Eኔ፡- የIትዮጵያ መሪ ነበሩ፣ መቼም Aይዘነጋዎትም? መለስ፡- ብዙዎቻችሁ የEውነተኛ መሪ Aድርጋችሁኝ Eንደነበር ይሰማኛል፡፡ Eኔ Eናንተ

ስለምታስቡት ነገር ደንታ የለኝም፣ ሐሳባችሁን ይዛችሁ በሊማሊሞ ማቋረጥ ትችላላችሁ፡፡ Eኔ በምድር Eያለሁ፣ በጠቀስከው ጄOፖለቲካዊ ክልል ውስጥ ሥልጣን መቆናጠጥ የምችልባቸውን Eንደብሔር፣ ሃይማኖት Eና Iኮኖሚያዊ ልዩነቶችን Eያነሳሁ ኃይል ሁሉ ወደኔ Eንዲፈስ ለማድረግ፣ ብሎም የግል የበላይነት ሕልሜን ለማሳካት Eንጂ Eንደሌላው የዓለም መሪ መምራት የሚባለው ነገር… በውኔም በሕልሜም Aልነበረም፣ Eንዲኖርም የሚያስገድደኝ Aልነበረም፣ Aይኖርምም፡፡…

Eኔ፡- ይቅርታ Aድርጉልኝ Aቶ መለስ፣ ግን Eኮ Aሁን የEርስዎ ራEይ ምናምን Eየተባለ

Eየተቀወጠ ነው? መለስ፡- Eሱማ የታወቀ ነው፤ ተረኞች በራሳቸው መንገድ ኃይልን Eንደሚቆናጠጡ

ይታወቃል፡፡ የኔ ራEይ የሚባለውን ነገር ለሕዝቡ ሰጥተውት፣ ሕዝቡ የመለስ ራEይ Eያለ ሲያወራ Eነርሱ በጓዳ ሥልጣናቸው ጉዳይ ላይ Eጣ ይጣጣላሉ፡፡ Aሠራራችንን በፊትም ቢሆን Eንዲህ Eንደነበር ማወቅ Eና መረዳት ያስፈልጋል፡፡

Eኔ፡- ወይ ጉድ Aቶ መለስ፡- Eሺ በቅርቡ ደግሞ ወ/ሮ Aዜብ ደሞዝዎ 4,000 ብር ብቻ

Eንደነበር ተናግረዋል፤ Eውነት ነው Eንዴ? መለስ፡- Aራት ሺሕ መሆኑን Aላውቅም፤ ከ1983 ወዲህም ሆነ ወዲያ ደሞዝ ተቀብዬ

Aላውቅም፡፡ Eኔ፡- Eንዴ Aቶ መለስ፣ Eንዴት? መለስ፡- Eንደሚታወቀው ደሞዝ በኔ ቤት ዋጋ Aልነበረውም፡፡ በተጨማሪም Aዜብ ነች Eንጂ

Eኔ ለገንዘብ ደንታም Eንዳልነበረኝ፣ ፓርቲዬ የሰጠኝን ብቻ የምሠራ ሰው Eንደነበርኩ በተደጋጋሚ ተናግሬያለሁ፡፡ Eኔ ሁሉም ሰው Eስከታዘዘልኝ ድረስ.. በቃ ምንም Aልፈልግም ነበር፡፡ በዚያ ላይ ገንዘቡን ቢሰጡኝም የማጠፋበት Aጋጣሚ Aልነበረኝም፡፡ የጦርሜዳም ሆነ የቤተመንግሥት ኑሮ Eየተንቀሳቀሱ ገንዘብ ለማጥፋት Aይመችም፣ ሁሉም በሕዝብ ገንዘብ ነው፡፡ መቼም ይሄንን የማያውቅ Aይኖርም፡፡

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

15  

Eኔ፡- [Aላውቅም ማለትን Eንደውርደት ስለቆጠርኩት ጭንቅላቴን Eንደገባው ሰው ወዘወዝኩ] ወደሌላ ጥያቄ Eንለፍ Eና Aንዳንዶች Aሁንም ድረስ Aቶ መለስ የሞቱት ደንግጠው ነው የሚል Eምነት Aላቸው፤ Eውነት ነው?

መለስ፡- Eስካሁን ድረስ… በመላው ዓለማችን ደንግጦ የሞተ መሪ የለም፤ በIትዮጵያም ቢሆን

ደንግጦ የሞተ መሪ Aልነበረም… ስለዚህ የኔ ደንግጦ መሞት Aለመሞት ለተመሳሳይ Aጋጣሚ ተጨማሪ ግብኣት ይሆናል ብዬ ስለማላምን… በተጨማሪም በገሃነማዊ ዴሞክራሲ መርሖች ላይ ሰዎች በምን ምክንያት Eንደሞቱ መናገር የለባቸውም የሚል ስምምነት ስለAለን… ይህ Eውነት Aፈንግጦ ቢወጣ ኒዮ ሊበራሎች…

Eኔ፡- [Aቋረጥኳቸው] Eሺ በቃ Aሁንም ወደሌላ ጥያቄ Eንለፍ፤ ከIትዮጵያ Eና ከገሃነም

የትኛው ለAገዛዝ ይቀላል? መለስ፡- Eንደሚታወቀው Eዚያም ሆነ Eዚህ Aብዛኛው ሰው ለመገዛት ዝግጁ ነው፤ Iትዮጵያ

ውስጥ Eንኳን ቆመህ ሞተህም የሚገዛልህ Aታጣም፤ Eዚህም ያው ነው፡፡ ልዩነቱ Eዚህ ተፎካካሪ Aለብኝ፡፡

Eኔ፡- ማነው ተፎካካሪዎ? መለስ፡- ሳጥናኤል!

ሚያዝያ 2፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፱፤ “American Dream” ‹Aሜሪካን ድሪም› የሚለው ዝነኛ ሐረግ በተለይ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩና Aሜሪካንን የሚያጥለቀልቁ ስደተኞችን የሚወክል ነው፡፡ ‹‹የነጻነት Eና የመበልፀግ ሕልም›› ነው ብለን ልናጠቃልለው Eንችላለን፤ ወደAሜሪካ የሚሰደድ ማንኛውም ሰው ‹Aሜሪካዊ ድሪም› Aለው፡፡ በርካታ Iትዮጵያውያን Eንኳን ባሕር Aቋርጠው ምድረ Aሜሪካን ሲረግጡ፣ ገና ዲቪ ሲሞሉ ሳይቀር ‹Aሜሪካዊ ድሪም› Aላቸው፡፡ Eኔ ግን በተቃራኒው፣ Eዚሁ Aገሬ ውስጥ ቆሜ ‹Aሜሪካዊ ድሪም› ለIትዮጵያ Aለምኩኝ፡፡ ይህንን ‹Iትዮጵያዊ ሕልም› ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ Aሜሪካ ገዢና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሏትም፤ ገዢ ማን? ተቃዋሚ ማን? ትልልቆቹ ፓርቲዎቿ ዴሞክራቶች ወይም ሪፐብሊካኖች ነው የሚባሉት፡፡ ሁለቱም ለኔ Aንድ ዓይነት ናቸው፡፡ ሁለቱም ቢመረጡ ለAሜሪካ ጥቅም ነው የሚሠሩት፣ ሁለቱም ዴሞክራቶች ናቸው፣ ሁለቱም ኮንግረስ ውስጥ በጥምረት የወሰኑበት ጉዳይ ነው ፖሊሲ የሚሆነው፡፡ በቢሊዮን ዶላር ፉክክር የሚመረጠው ፕሬዚደንት በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ (‹ጌይ ራይት›፣ ምናምን…) ጥቂት ተጽEኖ ማሳደር ይችል ይሆናል Eንጂ በIኮኖሚያዊ Eና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ የሚኖረው ሚና ፈፅሞ የተናጠል ሊሆን Aይችልም፤ ባጭሩ ሥልጣኑ ገደብ Aለው፡፡ በAሜሪካ ፓርቲዎች

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

16  

ገዢና ተቃዋሚ Aይደሉም፡፡ ገዢ የላቸውም፣ ምክንያቱም ተገዢ የለም፡፡ ተቃዋሚም Aያስፈልግም፣ ምክንያቱም ገዢ ከሌለ ማንን ይቃወማሉ? ይልቁንም የAሜሪካን ጥቅም Eና Eድገት ለማስከበር Eየተሟገቱ Aብረው ይሠራሉ፡፡ ሪፐብሊካኖች ዴሞክራቶች Aሜሪካን ሊበታትኗት ነው ብለው Aያምኑም፣ ዴሞክራቶችም Eንዲሁ፡፡ ይህ ዓይነቱ የAንዳንዶች ፍፁም ፖለቲካዊ የበላይነት የሌለበት (የEኩልነት) ልምድ ነው የኔ ‹Iትዮጵያዊ ሕልም›! የዓለም ሕዝብ Eየተሰደደ ወደAሜሪክ የሚጎርፈው ፖለቲካዊ ነጻነቱን ብቻ ፍለጋ Aይደለም -Iኮኖሚያዊውንም ጭምር Eንጂ (Eንዲያውም Iኮኖሚውን መርጦ ቢባል ይሻላል)፡፡ ካፒታሊስቷ Aሜሪካ Aንድ በመቶ የሚሆኑት ሀብታሞቿ የሚያሾሯት Aገር ናት Eየተባለች ብትታማም፣ በAሜሪካ ሀብታም የመሆን Eድሉ በAንድ ቤት ውስጥ Aልተቆለፈበትም፡፡ Aሁንም በAሜሪካ በየዓመቱ መቶ ሺሕ ሰዎች ከመካከለኛ ገቢ ወደሀብታምነት ይሸጋገራሉ፡፡ ጠንክሮ መሥራት ብቻ ነው Aስፈላጊው ነገር፡፡ ይህ ዓይነቱ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ የመበልፀግ Eኩል Eድል የሚሰጥ ባሕል ነው የኔ ‹Iትዮጵያዊ ሕልም›! ለመሆኑ ‹Iትዮጵያዊ ሕልም› የሚባል ነገር Aለ፤ በያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ያለው ሕልም ምንድን ነው? የሕልማችን Iትዮጵያ ምን ዓይነት ናት?

ሚያዝያ 22፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፲፤ "የሕዳሴው" ግድብና ደሞዜ ከስድስት ወር በፊት Eሠራበት የነበረው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለግድቡ መዋጮ የፈለግነውን ያክል ገንዘብ የምናዋጣበት ባዶ ቅጽ ላከልን። ብዙዎቻችን የወሩን ሦስት Aራተኛ በጥልፍልፍ ብድር የምናሳልፍ በመሆኑ ገሚሶቻችን በትሕትና ማዋጣት Eንደማንችል ስንገልጽ ቀሪዎቹ ደግሞ "መቶም፣ ሁለት መቶም በዓመት ክፍያ ይቆረጥብን" ብለው ፈረሙ። ይህ ያላስደሰታቸው Aለቆች ከቆይታ በኋላ 50% ደሞዛችንን በዓመት ክፍያ Eንድናዋጣ የተጻፈበት ቅጽ ሊያስፈርሙን ሲያመጡ የፈቃደኝነታችን ሥርዓተ ቀብር ተከናወነ። Eኔ Aልፈርምም Aልኩኝ። የድኅረ ምረቃው ት/ቤት ም/ፕሬዚደንት ቢሮዬ ድረስ መጥቶ ተማፀነኝ - "የተቋማችን ስም ይጎድፋል" በማለት። Eኔም Aልኩት "ወር በገባ በ10ኛው ቀን ከሚያልቀው ደሞዜ ላይ የማዋጣው ገንዘብ የለኝም፣ ከቻሉ የገቢ ግብሬን ይጠቀሙበት - ለማይወክለኝ ግንቦት 20 ድግስ ርችት የሚተኩሱበትንና ከAፌ ነጥለው የወሰዱትን ታክስ መጀመሪያ ባግባቡ ይጠቀሙበት። Aሁን ግን Aዋጣ ከምትሉኝ ልቀቅ ብትሉኝ Eመርጣለሁ። በEኔ ገንዘብ Eየተሠራ IሕAዴግ ራሱን በIቴቪ ሲያሞግስ ማየት Aልችልም" ብዬ ተንጣጣሁ። Aስብበት ብሎ ቅጹን Aስቀምጦልኝ ሄደ። 30 ደቂቃ ቆይቼ ሄድኩና "Aሰብኩበት ግን Aላዋጣም" Aልኩት። ነገሩ በዚህ ያበቃ መስሎኝ ሳለ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ በግል ጉዳዬ ተቋሙን ልለቅ ሳመለክት Eና ‘ክሊራንስ‘ ሳዞር የሕዳሴው መዋጮ ቀሪ Aምስት መቶ ምናምን ብር Aለብህ ተባልኩ። "I was like 'what?!'" ይሉ ነበር ፈረንጆቹ ቢሆኑ። ድንግጥ Aልኩ። "ያ Aሲዳም ደሞዜ ወትሮም ከብድር ከፋይነት የትም Aላደረሰኝ። ለካስ በየወሩ Eየተቀነጠበ ነበር የባሰ መቅኖ ያጣብኝ" Aልኩና ባሳቤ "በማን ፈቃድ ቆረጣችሁት?" Aልኳት ሒሳብ ሠራተኛዋን። የሆነ ዶሴ ፈልፍላ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

17  

Aወጣችና "Aቶ በፍቃዱ .... Eስካሁን ስላልተቆረጠባቸው ... ከዚህ ወር ጀምሮ ..." ደብዳቤው Eንደቃለጉባኤ ያለ ሲሆን ከግርጌው ፊርማዎች ሰፍረውበታል። ም/ፕሬዚደንቱ ቢሮ ብስጭቴን ይዤ ሄድኩ። "Eኔ የለሁበትም" ተባልኩ። የፋይናንስ ኃላፊውጋ ሄድኩ "ተቋሞች በሙሉ የሠራተኞቻቸውን ደሞዝ Aምሳ በመቶ ለማዋጣት ስለተስማሙ ሁሉም ሠራተኛ ግዴታ ማዋጣት Aለበት ተብሎ ተወስኗል" Aለኝ። "በገዛ ደሞዜ ማን የመወሰን ሥልጣን Aለው? የኔ ደሞዝ የመንግሥት ፓሊሲ ለማውጣት የማይተገበረው የድምፅ ብልጫ ለምን ይተገበርበታል?" በማለት Aማረርኩ። በጩኸት "Eከሳችሀኋለሁ" Eያልኩ ዛትኩ። ከዚያ በኋላ ግን Aንደኛ "Aባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ" መሆኑን Eያወቅኩ ለማን Eከሳለሁ? ሁለተኛ መቼም ጉዳዩ የAገር ጉዳይ ነው፣ Eስኪ ከፕሮፓጋንዳ ተርፏቸው ከሠሩት ይሥሩበት በማለት ቀሪውን ከ‘ፕሮቪደንት ፈንዴ‘ ላይ ከፍዬ ለቀቅኩ። ምናልባትም ከከሰስኩ ተቋሜን ሳይሆን መከሰስ የሚገባውን የምከስበት ቀን ይመጣል! ይህ ከሆነ ጀምሮ ያተረፍኩት ነገር ብስጭት ነው። ከጉሮሮዬ ነጥዬ ያዋጣሁት Eኔ Eያለሁ፣ "Aባይን የደፈረ ጀግና" ሌላ ነው። Eኔ ካሁን Aሁን ግድቡ Aለቀ ብዬ በጉጉት Eጠብቃለሁ፣ የግድቡ ፅንሰት Eየተባባሉ በገንዘቤ ደግሰው ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይጨፍራሉ። ይህንንም በIቴቪ ያስተላልፋሉ።

ግንቦት 24፣ 2005

?!

ስመለከት… ሰው ሁሉ ይወጣል፥ ላይ-ታች ይሮጣል፤

ስጠይቅ…

ሁሉም በበኩሉ፥ ሕልም Aለው ይላሉ፤

ሳስበው…

ከዚህ ሁሉ መሐል፥ ከሚርመሰመሰው፣ ምናልባት ያለ’ንደሁ፥ ትርፍ ሕልም ያለው ሰው፣

ሕልም ለቸገረው፥ ምናለ ቢያውሰው?!

ግንቦት 29፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

18  

Aጭር መጣጥፍ ፲፩፤ ከተሜነትን ከገጠሬነት ለማስታረቅ ከተሜነት ብዝኃነትን ይወክላል። ገጠሬነት ደግሞ ወገንተኝነትን። በዚህ ዓረፍተ ነገር ያስከፋሁዋችሁ ጥቂት የማብራራት Eድል ስጡኝ። ለመንደርደሪያነት የሚሆነኝ ጥሩ ምሳሌ ጋሽ ስብሐት Aንዴ የተናገረው ነው — "ልጅ Eያለሁ ዓለም ሁሉ ትግርኛ የሚናገር ይመስለኝ ነበር" ብሏል። ነገሩ በደንብ የሚገባኝ ከራሴ ልጅነት‘ጋ ሳየስተያየው ነው። Aማርኛ መናገር የማይችሉ የAባቴ ቤተሰቦች Eኛ ቤት ሲመጡ Eና መግባባት ሲያቅተን፣ ‘Eንዴት ቋንቋቸውን ወደAማርኛ መተርጎም ያቅታቸዋል? Eኛስ የነሱን ቋንቋ ስለማንችል ነው‘ Eል ነበር። በልጅነት Eሳቤ ለኔ Aማርኛ universal ቋንቋ ነበር። ከተማና ገጠር – Aስተዳደጉ ለየቅል ከተሜ ስትሆኑ የድኻ ልጅ ከሆናችሁ፣ ከቤታችሁ ጥቂት ፈቀቅ ስትሉ በምርጥ ቪላ ውስጥ የሚኖሩ፣ "የሃብታም ት/ቤት" የሚማሩ ... Eኩዮቻችሁን Eያያችሁ ታድጋላችሁ። የክርስቲያኖች ቤተሰብ ውስጥ ብትሆኑም Aብረዋችሁ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ልጆች ያሉበት ሙስሊም ጎረቤት Aላችሁ። ከተማ ውስጥ ጎረቤታሞች ከAንድ Aካባቢና የዘር ግንድ የወጡ Aይደሉም – ከየቦታው በኑሮ Aጋጣሚ የተሰባሰቡ ሰዎች ናቸው። Eንደብዛታቸው የተለያዩ ናቸው። ገጠር ለሚያድጉ ግን የተለየ ነው። Aንድ መንደር ውስጥ፣ Aንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ፣ Aንድ ዓይነት Aለባበስ፣ Aጨፋፈር፣ ምግብ፣... Aንድ ዓይነት ብዙ ነገር ያላቸው ሰዎች መሐል ስለሚያድጉ ከዚያ ውጪ ያለውን ሁሉ የመጸየፍ፣ የማግለል Eና የመናቅ ልማድ Eንዲያዳብሩ ይገደዳሉ። ብሔረተኝነት Eና ኅብረ—ብሔረኝነት Eርግጥ Eኛ ገና በብሔር ትርጉም ላይ መግባባት Aልቻልንም። (1ኛ) ብሔር የሚለው ቃል ግEዛዊ ትርጉሙ Aገር ማለት ነው፣ (2ኛ) Nation የሚለውም የEንግሊዝኛ Eኩያው ያው Aገር ማለት ስለሆነ Aገራችን (ብሔራችን) Iትዮጵያ ናት ሲሉ ባንድ ወገን፣ በሌላ ወገን ደግሞ Eነዚህ ሰዎች የIትዮጵያን የብሔረሰቦች ቤትነት ይክዳሉ፣ ወደAንድ ብሔርነት ሊጨፈልቁን ይፍጨረጨራሉ ብለው "Eኛ Eንትናዊ ነን Eንጂ፣ Iትዮጵያዊ Aይደለንም" ይላሉ። ብዙ ግዜ የዘር ሐረጋቸው ከሚመዘዝበት ይልቅ Iትዮጵያዊነታቸው Eንደሚገልጻቸው የሚናገሩት Aማራዎች (ወይም "Aማርኛ ተናጋሪዎች") Eና የደቡብ ብሔረሰብ Aባላት Eንደሆኑ ነው የሚነገረው። ነገር ግን በዚህ መሐል ከተሜው ተዘንግቷል። በመሠረቱ Aማራነት ምንድን ነው? (Aማራ ብሎ ብሔር የለም የሚሉትን ለራሳቸው Eናቆያቸውና) Aማራ ጎንደሬ ነው? ጎጃሜ ነው? ሸዋዬ ነው? ወሎዬ ነው? Oሮሞስ ማነው? የወለጋው? የባሌው? የሸዋው? የሐረርጌው? Eነዚህ Eርስበርስ በባሕልም፣ በፆታም፣ በጂOግራፊም የተጋቡ ሕዝቦች ናቸው። ተራ ኀልዮት የሚገልጻቸው ቁጥሮችና የልሂቃን ቡፌ Aይደሉም።

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

19  

መቼም የዘውግ–ብሔረተኞች ያለፈበት ጫወታ፣ ኅብረ–ብሔራውያን ደግሞ ከፋፋይ ሐሳብ Eያወራህ ነው ልትሉኝ Eንደምትችሉ ባይጠፋኝም ዝም ማለት Aላስቻለኝም። ይልቁንም ዓላማዬ የሁለቱም ወገን Aቀንቃኞች የዘነጉትን Eውነታ ለማስተናገድ ነው። ሁለቱም Eንደሚያስቡት/Eንደማያስቡት የብሔረተኞቹ ጥያቄም/የኅብረ–ብሔራውያኑ ፍራቻም Eውነት ናቸው። (ችግሩ ሁለቱም ወገኖች ሕዝቡን ግራና ቀኝ Eየጎተቱ ማስጨነቃቸው ነው።) መፍትሔው ግን መሐል ላይ ነው — ከተሜነት — ብዝኃነት (plurality)። ወደድንም ጠላንም፣ ብሔረተኛም ሆንን ኅብረ—ብሔራዊ ያለን ገበታ Aንድ ነው፣ ምግቡም ማኅበራዊ። ገበታው ላይ ክትፎው፣ ቆጮው፣ ጭኮው፣ ጨጨብሳው፣ ዣልዎው፣ ካሽካው፣ ዶሮው፣ Aምባሻው፣ ጠላው፣ ጠጁ፣ (ዳዺው፣ ፋርሲው)፣ ቦርዴው... ሁሉም Aለ፣ ያለን Aማራጭ ከብበን በፍቅር መብላት Eና መጠጣት ነው።

ሰኔ 4፣ 2005

የሦስት ዓመት ድርሳን

ካቻምና፣… Aፍርጬ ስነግርሽ በፍቅርሽ መጥፋቴን ንቀሽኝ ብትሄጂም ለክተሽ ቁመቴን

ወይ‘ሷ ታጥራለች፣ ወይም Eኔ Aድጋለሁ Eያልኩኝ ከርሜ መታጨትሽን ሰማሁ። Aምና፣… መቼም የተጫጨ የተጋባ Aይደለ፣

Eስከሚለያዩ ብጠብቅ ምናለ ወዲያውም ላጽናናት Eቤቷ ገብቼ

ብዘልቅስ ማን ያውቃል፣ የልቧን Aግኝቼ Eያልኩኝ ስጠብቅ ማግባቷን ሰምቼ ተሰብሬ ነበር የቁም ሞቴን ሞቼ።

ዘንድሮ፣…

ቤት የለሽም Aሉ፣ ቤት መሥራት ይከብዳል ለ20/80... ሰው ትዳር ይፈታል

Aንቺስ የኔ ቆንጆ፣ ምንድን Aስበሻል?

ሰኔ 6፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

20  

ፍሬ ሕይወት

ብርቱካን Aማረኝ፣ ጠረኑ ናፈቀኝ Eንጆሬ ጣEሙ፣ ባፌ ውል Aለብኝ የብስል ቲማቲም፣ ልስልስ ያለ ገላው ትሙክ Aባባሉ፣ ለጣት የሚደላው ጠረኑና ጣEሙ፣ ምቾቱ ናፈቀኝ

ማሽተትና መቅመስ መዳበስ Aማረኝ።

ከዚያ... Aምሮቴ ሲፈታ፣

በAምሮት ፈች‘የኔታ ብርቱኳን ጠረንሽ Eንጆሬ ከንፈርሽ ቲማቲሙ ጡትሽ ሁሉም Aንቺ ራስሽ

መሆንሽን ነገሩኝ፣ Aምሮተ—ነገሬ የኔ ፍሬ ሕይወት፣ የኔ ፍራፍሬ።

ሰኔ 10፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፲፪፤ ጨቋኝ ተጨቋኞች Victimology ይሉታል — ተበዳይ ነኝ Eያሉ ጯኺነትን። ከተበዳይነትና ከተጨቋኝነት ለመውጣት የሚደረገው መፍጨርጨር የመጀመሪያው የነጻነት ጉዞ ርምጃ ቢሆንም፥ ከተጨቋኝነት ስሜት ወደጨቋኝነት ምኞት ላለማደጉ ዋስትና Aይሰጥም። ከብዙ የጾታ Eኩል Eድል ጠያቂዎች፣ የተሳታፊነት መብት ያላገኘ ዘውግ ተቆርቋሪዎች Eና በሌላው ልEልና የተጋረደ ሃይማኖት ጠበቆችጋ ያወራሁባቸው Aጋጣሚዎች Aሉ። ሁሉም መነሻቸው ባብዛኛው Eውነተኛና ትክክል ቢሆንም የሚያልሙት መድረሻ ግን የሁሉም ተጨባጭና ትክክለኛ (righteous) ነው ለማለት የሚያስደፍር Aልገጠመኝም። Eስከዛሬ Eኩል መብት Aላገኘንም የሚሉት የበለጠ መብት ለማግኘት፣ ተሳታፊ Aልነበርንም የሚሉት በተራቸው ላለማሳተፍ፣ ተጋርደናል የሚሉት ለመጋረድ የሚሠሩበት Aጋጣሚ ብዙ ነው። (ሁሉንም ላይወክል ይችላል።) ስለዚህ ትግሉ ተጨቁነናልና በተራችን ጨቋኝ Eንሁን Eንጂ ጭቆና ይብቃ Aይደለም (ይቺን Aባባል ፕሮፌሰር መስፍን በተደጋጋሚ ይገልጿታል።) Eናም፣ ይህ ዓይነቱ ትግል የማይሳካባቸው ምክንያቶች Aሉ። ዋነኛው ግን የሚከተለው ነው፦

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

21  

ጨቋኝ Eና ተጨቋኝ የሚባለው ትውልድ Aልፎ ሳለ "ጨቁነውናል Eንጨቁናቸው" ሲባል፣ ይህ ትውልድ ያባቱን Eዳ መክፈል Eንዳለበት* ሲረዳ ያባቱን ይዞታ (የጨቋኝነት ሚና) ይዞ ለመቀጠል Eና ራሱን ለማዳን የሚፍጨረጨር ትግሉን የሚያጨናግፍ ታጋይ ይሆናል። ---- * በበደል ፈፃሚ ግለሰቦች ላይ በነፃ ፍርድ ቤት የሚካሄድ ዳኝነትና ፍርድ ቤት ማለቴ Aይደለም።

ሰኔ 18፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፲፫፤ የፈረንሳይ ልጆች ፒያሳ የAዲስ Aበባ Eምብርት ናት። ነዋሪዎቿም ራሳቸውን "የAራዳ ልጅ" ብለው ይጠራሉ። ፍቅሩ ኪዳኔ "የፒያሳ ልጅ" ብለው የሕይወት ታሪካቸውን Aስታከው ጽፈውላታል። መሐመድ ሰልማን "ማሕሙድጋ ጠብቂኝ" ብሎ Aንቆለጳጵሷታል። ይሄ ሁሉ ግን በተለምዶ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተብሎ የሚጠራው Aካባቢ — የፈረንሳይ ልጆች ሰፈራችሁን በፒያሳ ቀይሩ ቢባሉ Eሺ Eንዲሉ Aያደርጋቸውም። የፈረንሳይ ልጆች ሰፈራቸውን Eንደልዩ Aካባቢ ይቆጥሩታል። "የፈረንሳይ ልጅ ነኝ" የሚል ቲሸርት Aሠርተው፣ ለብሰው የሚሄዱ የሰፈር ጓደኞች Aሉኝ። ሌላው ቀርቶ Eኛ ሰፈር ሁኖ ብርቱካን ሚዴቅሳን የማይወዳት ማግኘት ይከብዳል። ከፖለቲከኛነቷ ይልቅ የፈረንሳይ ልጅነቷ በፈረንሳይ ልጆች ዋጋዋን Aሳድጎላታል። (መቼም ትኬት ሸጠው መኪና በስጦታ Eንዳበረከቱላት Aይዘነጋም።) ባለፈው ደግሞ Aንድ የፈረንሳይ ሰው መንግሥት ሰፈራችንን ችላ Aለብን ብሎ በጋዜጣ ላይ ጽፏል። መንግሥት ሰምቶት ይሁን ወትሮም Aስቦበት Aላውቅም ያን ልብ የሚያጠፋ ዳገት ለጥ የሚያደርግ መንገድ Eየተሠራላት ነው። Eንግዲህ ለኑሮ ባሕር ማዶን የመረጡ ሰዎች ማን EንደIትዮጵያ Eንደሚሉት ለውሎ ፒያሳን የመረጡ የፈረንሳይ ልጆችም፣ ማን Eንደፈረንሳይ ይላሉ። ሰዎች በቀበሌና ቀዬ ሲደራጁ Eና ሲቆረቆሩ ስመለከት መለስ ብዬ የማስበው ይህንን ነው፤ ሰዎች ያደጉበትን Aካባቢና የበቀሉበትን ‘ሶሻል ፋብሪክስ‘ ማፍቀራቸው ተፈጥሯዊ ነው። ችግሩ ሌሎች Eንደኛ መሆን Aይችሉም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሱ ብቻ ነው።

ሰኔ 22፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፲፬፤ ትልቁ ድኻ ትንሹን ድኻ ይንቀዋል "ትልቅ ድኻ" የሚባለው በጣም ድኻው ነው? ለረዥም ዘመናት ድኻ የነበረው ነው? ወይስ የተሻለው? የሆነ ሆኖ ትልቁ ትንሹን ይንቀዋል።

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

22  

Aገራችን Iትዮጵያ (ቢያንስ Eኔ የማውቃት ከተማ ቀመሷ Iትዮጵያ) የመናናቅ Aገርነቷን ሳስብ፥ "ሃይማኖት"፣ "ሥነ—ምግባር" የሚባሉት የ"መልካምነት መለያዎች" የት Eንደሚገቡ ግራ ይገባኛል! የተማረው መሓይሙን፣ ሊቁ ደቂቁን፣ ሀብታሙ ድኻውን፣ ከተሜው ገጠሬውን፣ ቄሱ ዲያቆኑን የሚንቅበት Aገር ማለት የኛ የራሳችን Aገር ነች። ሁሉም የገዛ ሕይወቱን መምራት የሚያስችል በቂ Eውቀት Eያለው Aንዱ ከግዜያዊ/ቀበሌኛ ምቾት በላይ (ብቻውን በምድር) መኖር ይችል ይመስል Eየተበላለጠ ይናናቃል። Eናታችሁ ጥሩ ሥራ ይዛችሁ፣ ጥሩ ደሞዝ Eየበላችሁ፥ በቁስ Eሳቤ ከናንተ ያነሰ ሁኔታ ካላቸው ሰዎች‘ጋ ጓደኝነት መሥርታችሁ ካየች "ከEኩዮቻችሁ‘ጋ Eንድትገጥሙ" ትመክራችኋለች። Eዚህ‘ጋ ነው የሰው ልጅ ማንነትና ምንነት የሚፈተሸው። በሚታይና በማይታይ ቁስ ቆጠራ የሰው ልጅ Eኩያ ከተፈለገለት — የሰው ልጅ Eኩልነት፣ ተረት ተረት።

ሐምሌ 1፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፲፭፤ Belonging-ness Belonging - ለሚለው ቃል ተስማሚ የAማርኛ ትርጉም ፈልጌ Aጣሁለት። Eስኪ በሌላ የIትዮጵያ ቋንቋ ትርጉም ካለው ንገሩኝ። I belong to Ethiopia የሚለውን ምን ልበለው? ለማንኛውም I belong to Ethiopia። ጥያቄው ጋምቤላው፣ ቤንሻንጉሉ፣ ሶማሌው… ከኔ Eኩል ‘ቢሎንጊንግነስ‘ ይሰማዋል ወይ? Eኔ ማነኝ? Eኔ በመሐል Aገር፤ የወል Iትዮጵያዊነትን Aምኜ Eና Aምልኬ ያደግኩ Iትዮጵያዊ ነኝ። የIትዮጵያ የባሕል ሙዚቃ መሣሪያ ስጠየቅ ክራርና ማሲንቆን፣ የባሕል ጭፋሮን Eስክስታን… ስጠቅስ ኖሬያለሁ። Aሁን ግን ከመሐል Aገር Aሻግሬ ለመመልከት ስፍጨረጨር Iትዮጵያዊነቴ የሚያጎናፅፈኝ ቁንፅል Eውቀቴ ካጎናፀፈኝ በላይ መሆኑ ገባኝ። የIትዮጵያ የባሕል የሙዚቃ መሣሪያ ክራርና ማሲንቆ ብቻ ሳይሆን ዙምባራና ሌሎችንም Eንደሚጨምር፣ የIትዮጵያ ባሕላዊ ጭፈራ Eስክስታ ብቻ ሳይሆን Iቫንጋዲንና ሌሎችንም Eንደሚያካትት ተረዳሁ። Aለኝ ብዬ ከማስበው በላይ (Eጅግ በላይ) ስላለኝ ደስ Aለኝ፣ ግን ቀደም ብዬ ያጠፋሁት ጥፋት ነበር፤ ታሪክ የመጻፍ ታሪካዊ Eድል ገጥሞኝ የጻፍኩት የIትዮጵያ ታሪክ Eና የበየንኩት Iትዮጵያዊነት ጠባብ ነበር። Aንድ ወዳጄ Eዚሁ ፌስቡክ ላይ የIትዮጵያዊነትን ትርጉም ባሰፋነው ቁጥር ውስጡ ሰው Eናጣለን ብሎ ነበር፤ Eኔ ግን ባጠበብነው ቁጥር ነው ውስጡ belong የሚያደርጉ ሰዎች የምናጣው ባይ ነኝ። Eናም Iትዮጵያዊነት በኔ ብያኔ ሳስቀምጣት ባልሳሳትም Aጥብቤያት ነበር። Eኔ Eንግዲህ ባለማወቅ ራሴን በጠባብ Aጥር የከበብኩ ሰው ነበርኩ ማለት ነው። ሆኖም ባለማወቄ ፍርድ ቤት Aልቆምም፣ ይልቁንም ሳላውቅ ያባከንኩትን ‘ትሬዠር‘ Eያወቅኩ Eንድደነቅ Eድል ሊሰጠኝ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

23  

ይገባል። Eኔ ይህን Eድል ሳገኝ ሌላውም የኔን ያክል ‘ቢሎንጊንግነስ‘ ይሰማው ዘንድ ማንነቱን የሚገልጽ ብያኔ በIትዮጵያዊነት ብያኔያችን ውስጥ ማኖር Aለብን። Moral of the story: we are far behind from drawing/defining an Ethiopia where everyone feels belonged to.

ሐምሌ 2፣ 2005

ጫወታ ፩ ድሮ፣ ድሮ ቅኔና ተረት የምንተርተው ተፈጥሮ ተንተርሰን ነበር። ለምሳሌ Aባይን ተሻግሮ Aንዷን ያፈቀረ ኮበሌ ሰኔ ሲያስገመግም Eንዲህ Aለ ይባላል:—

"Aባይ ጉደል ብለው Aለኝ በትሣስ፣ የማን ሆድ ይችላል Eስከዚያ ድረስ?"

Aሁን ግን “የዓለም ባንክ በ2020፣ Aይኤምኤፍ ደግሞ በ2025 Iትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው Aገራት ተርታ ትሰለፋለች” ስላሉ፥ “ልማቱ" ላይ ተንተርሰን ለምንቀኛቸው ቅኔዎች ከAሁኑ የራሴን Aዋጣለሁ። Eናንተም የራሳችሁን Aዋጡ! ባቡር ጣቢያ ከጠበሳት ቆንጆ‘ጋ በክረምት የተኳረፈ ጎረምሳ Eንዲህ ይላል:—

“ያው ዝናቡ መጣ፤ ያጉረመርም ጀመር፣ ጠቆረ ሰማይ፣ ሰብ ስቴሽኑ ውስጥ፣ ቆሜ ስጠብቅሽ Aትመጪም ወይ?"

Eሷም ያው Eንደሱ መታረቅ መፈለጓ ስለማይቀር (ክረምት Aይደል?):—

“ዝናብና ባቡር ይመጣል ይሄዳል፣ ያንተ ፍቅር ብቻ ከልቤ ይኖራል።"

ወይም

“‘ሸከተፍ፣ ሸከተፍ’ የሚለው ባቡር፣ ነፍስ ያለው ይመስላል Aንተ ስትኖር።”

ትለዋለች። Aንዷ ደግሞ Eጮኛዋ Aኩርፎ Eየሄደ፣ ተመልሶ Eየመጣ ሲያስቸግራት Eንዲህ ትለዋለች:—

“Aይግደረደርም ወንድ ልጅ ከወጣ፣ ቀለበት መንገድ ነው ዞሮ የሚመጣ።"

“ልማቱ" ካፈራቸው ባለፀጎች Aንዱን ወዳ ለከዳችው ሚስቱ ሌላው ደግሞ ፍርድ ቤት ቀርቦ Eንዲህ ይገጥማል:—

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

24  

“ኮርቶ ‘ሚኖርበት ዘመናይ ነው ቤቱ፣ የሚጓጓዝበት የግል ነው ጀቱ፣ ተቆጥሮ ባያልቅም ሀብትና ንብረቱ፣ ዳኛ ሆይ Eመኑኝ ሙስና ነች ሚስቱ።"

ሐምሌ 5፣ 2005

Aጫጭር መጣጥፍ ፲፮፤ “ጥቁር Eና ነጭ” የፌስቡክ ባለቤት (ማርክ ዙከርበርግ) ቀለም መለየት Aይችልም (colorblind ነው)፡፡ መለየት የሚችለው ቀለም ሰማያዊ ብቻ ነው፤ ለዚያ ነው ፌስቡክ ሰማያዊ የሆነው፡፡ ሌላው ሁሉ በነጭና በሰማያዊ ቅልቅል የተሠራ ምስል ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ ቀለም መለየት የማይችል ሰው ሆኖ ጥቁር Eና ነጭ ብቻ ማየት የሚችል ሰው Aለ፡፡ የሚያየው ጥቁር ቢሆንም የሚያየውን Aንድ ነገር ከሌላ መለየት Aያቅተውም፤ ዓለምን በጥቁርና ነጭ ቴሌቪዥን Eንደማየት ነው፡፡ ምክንያቱም በጥቁር Eና ነጭ መካከል ብዙ ግራጫዎች Aሉ፡፡ ያንን ግራጫ ማየት የተሳናቸው ሰዎች ቢኖሩስ? ያ ማለት ዓለም በሙሉ ድፍን ያለች ጥቁር (ወይም ነጭ) ብቻ ትሆንባቸዋለች? ይህ ከሆነ ዓይነ ስውርነት ይባላል፡፡ የዓይንን ሥራ ለዓይን Eንተወውና AEምሮ ‹ጥቁር Eና ነጭ› ማሰብ ሲጀምር ምን ይባላል? ‹ጥቁር Eና ነጭ› Aስተሳሰብ Eንዲህ ካልሆነ Eንዲህ ነው ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ዴሞክራት ካልሆነ ዲክታተር ነው፣ ፃድቅ ካልሆነ ኩንን ነው፣ የIሕAዴግ ደጋፊ ካልሆነ የተቃዋሚዎች ነው፣ ‹Iትዮጵያኒስት› ካልሆነ ‹ኤትኖናሽናሊስት› ነው - ይህ ዓይነቱ ‹የኛ ወዳጅ ካልሆነ ጠላት ነው› የሚል Aስተሳሰብ - Aክራሪነት/ፅንፈኝነት ይባላል፡፡ Iትዮጵያውያን ከሌላው የተለየ ፅንፈኝነት Aለብን የሚል ደፋር ንቀት የለብኝም፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ጊዜያት፣ የተለያዩ ጉዳዮችን የምንመለከትበት ዓይን ያሳስበኛል፡፡ ግራጫውን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ምልከታ Aለን፤ ለፍረጃ Eንጣደፋለን፡፡ ብዙዎቻችሁን ይህ Eሳቤዬ ብዙዎቻችሁን ባያስደስታችሁም፣ ለዚህ ዓይነቱ የጋርዮሽ Aስተሳሰባችን ሃይማኖተኝነታችን ተጠያቂ ይመስለኛል፡፡ በሃይማኖት Eሳቤ ይቅርታ Aድራጊነት ትልቅ ቦታ Eንደሚሰጠው ቢነገርም በተቃራኒው በAንዲት ስህተት ገሃነም Eንደሚያስጥለው Aካሄድ፣ በAንድ ሥራ መካብ Eና ማፍረስ በጣም ይዘገንናል፡፡ የፍረጃችን ክፋቱ ደግሞ የፈረጅናቸውን ሰዎች ወደፅንፉ የበለጠ የምንገፋቸው መሆኑ ላይ ነው፡፡ ከዚህ የጋርዮሽ Aስተሳሰብ ሁላችንም Aንተርፍም፡፡ ፍላጎቴ ግራጫዊ Aስተሳሰብ በማዳበር ከAሳብ-ስውርነት Eንድንተርፍ ነው፡፡

ሐምሌ 9፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

25  

Aጭር መጣጥፍ ፲፯፤ የኮሌጅ ተማሪነት Eና ሴቶቻችን በAማርኛ ፊልሞች ስለAማርኛ ፊልሞች ተማርሬ Aይበቃኝም፤ ምክንያቱም መብቴ ነው — Eየከፈልኩ Aያቸው የለ! Aሁን ግን በባች፣ በባች Eየከፋፈልኩ ብተቻቸው ሳይሻል Aይቀርም። ይህን Eንደ Aንድ ቁጠሩት! የAማርኛ ፊልም ሠሪዎች (ደራሲዎች፣ ዳይሬክተሮች…) ብዙዎቹ ኮሌጅ ባይገቡም ስለ“ካምፓስ ሕይወት” ፊልም መሥራት ይወዳሉ፤ መውደዳቸው ግን የማያውቁትን ሕይወት የማስመሰል Eና የመክሰር ጣጣ ውስጥ ይከታቸዋል። ከተዋናይ መረጣ ስንጀምር ተማሪ ተደርገው የሚሳሉት ጎልማሶች ሲሆኑ፣ የኮሌጅ ተማሪዎች ደግሞ በEውነታው ዓለም ገና ዓለምን በቅጡ ያልተረዱ በመፈንዳት ላይ ያሉ ወጣቶች ናቸው። ከዚህም በላይ የሚያሳዝነው ግን ባገራችን ፊልሞች ውስጥ ያሉ የኮሌጅ ተማሪዎች በየመሸታ ቤቱ Eየሄዱ Aሸሸ ገዳሜ ሲሉ ያሳያሉ፤ ይህም የሚመስለው ተማሪዎቹ Aጫጭር ቀሚስ ለብሰው በየክለቡ Eየጨፈሩ ሦስት ወይም Aራት ዓመት ይቆዩና ከዚያ ተመርቀው የሚመጡ ፍጡሮች Eንደሆኑ ነው። Eውነታው ግን ችስታዎቹ ተማሪዎች ከስንት Aንዴ በምትገኝ ገንዘብ መዋጮ/ፈለጣ ጥርቅም ጥቂት ሌሊቶችን፣ ደረጃቸው በወረዱ መሸታ ቤቶች ይጠጡና ወደ ቴንሽን ይመለሳሉ። ለጥናት ብለው ጫት ይጀምሩና በዚያው ትንባሆና መጠጥ ለምወደው የሚቀሩት ያው ጀዝባዎቹ ናቸው። ፊልሞቻችን ግን Aንድ ተማሪ በዓይናፋርነት ካምፓስ ገብቶ Eንዴት በጅዝብና Eንደሚመረቅ Aያሳዩንም። ይልቁንም በኮሌጅና ቡና ቤት ሴቶች መካከል ልዩነት የሌለ Eንዲመስለን ያደርጋሉ። (Refer: በቅርቡ 3D ነኝ ብሎ የወጣውን ‘ኮሌጅና ውበት’፣ ወይም ‘ፍቅርና ገንዘብ’…) ደራሲዎቹ ባብዛኛው ወንዶች መሆናቸው የወንዶች ‘ፖፑላር Iማጂኔሽን’ የሆነውን ‘ሴት ሸቀጥ ወንድ ሸማች’ Aስተሳሰብ ያስተምራሉ፣ ተመልካች ያስቁበታልም። የፊልም ሠሪዎቹ ልክ Eንደቡና ቤት ማስታወቂያ ፖስተሮቻቸው ላይ የሴት ጡት፣ ዳሌ Eና የተራቆተ Eግር Eየለጠፉበት ተመልካች ይጠራሉ። ለምሳሌ ‘ቺኮሎጂ’ የሚል ፊልም ፖስተር ላይ Aንዱ የመቶ ብር ኖቶች Eንደ ካርታ በEጁ መዥርጦ ደርድሮት ይታያል፤ ከፊት ለፊቱ ባለ ሚዛን ላይ ያሉት ሁለት ሴቶች Aንዷ በጣቶቿ መሐል ሲጃራ ይዛለች፣ ሌላኛዋ መጠጥ በብርጭቆ ጨብጣለች — ሲግናሉን ተመልከቱት። የጭፈራ ቤት ትEይንት የሌለው ፊልም ከስንት Aንድ ነው። የፊልሞቻችንን ታሪክ በAጭሩ ለመጥቀስ Aጭር ቀሚስና መጠጥ በቂ ናቸው። በዚህ ጉዳይ ከጓደኛዬ’ጋ ስናወራ፣ ‘ሴቶቹ Eንደዛ ከሆኑ ደራሲዎቹ ምን ያድርጉ?’ Aለችኝ። Eኔ ግን ሴቶቻችን Eንደዚያ ናቸው ብዬ Aላምንም። Aጭር ቀሚስ፣ ገንዘብና መጠጥ የሚገልጻቸው ከሆነ ከሰው በታች ናቸው ማለት ነው። በፊልም ላይ ‘ፖርትሬት’ የሚደረጉት ‘ኤክሰፕሽናሎቹ’ ናቸው። ከነዚህ ቡና ቤት Aዘውታሪ ‘ኤክሰፕሽናሎች’ ውስጥም ‘ኤክሰፕሽናሎች’ መምረጥ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

26  

የፊልም ባለሙያዎች ሥራ ነው። ‘U–ገርልስ’ ከሚባሉት ደስታ ወዳጅ ሴቶች ጀርባ ስንት ሊዘነጉት የሚፈልጉት ‘ትራጄዲ’ Aለ፤ ለምን ስለሱ ፊልም Aይሠሩልንም?

ሐምሌ 11፣ 2005

(ርEስ Aልባ 2)

ምስኪኑ Eኔ፣ ባለ’ሌለኝ Aቅም፣ “LIKE ስለቃቅም፣

Comment ሳጠራቅም፣” ያመለጠኝ ዓለም ስንት ይሆን? — Aላውቅም።

ከEለታት Aንድ ቀን ዓለም Aሰኝቶኝ፣

ደሞም Eንደገና፥ Logout የሚለው የት Eንደሆን ጠፍቶኝ፣ ፈልጌ Aስፈልጌ Aንዱ ስርቻ ስር ከተወተፈበት፣

Aቧራ Aራግፌ Logout በማለት፣ የወጣሁኝ Eንደሁ ዓለም ለመመልከት፣

EነEከሌ Aግብተው፣ EነEከሌ ወልደው፣ EነEከሌ ተምረው፣ EነEከሌ ከብረው፣ EነEከሌ መጥቀው፣ ተራቀው ተራቀው ያፈራሁትን ሀብት

LIKE Eና Comment ሁሉም ንቀው፣ ንቀው…

ታሰበኝ። … ይህንንስ ከማይ፥

የፌስቡክ ፈጣሪ ችግሬን ስታውቀው፣ Logout Eንዳልል፥ Eባክህ ደብቀው!

ሐምሌ 19፣ 2005

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

27  

የነጻነት ትግል

ይሄ… ያንድ Aገር ሕዝብ፥ ተከብሮለት መብቱ፣ ነጻ ሆኖ Eንዲኖር ዘወትር በየለቱ፣

የዋህ ነጻ Aውጪዎች ሲደክሙ በከንቱ፣ Aንዴ ሲታሰሩ Aንዳንዴ ሲፈቱ፣

መብታችሁን Aምጡ፥ ሂዱና ንጠቁ፣ በሚል ለሁሉም ሰው፥ ነፍጥ ቢያስታጥቁ፣

በመጨረሻው ቀን ሲጠናቀቅ ትግሉ፣ ለመታሰቢያነት…

‘ነጻነት’ን ማርከው፥ ሕዝብ ፊት ሰቀሉ።

ሐምሌ 23፣ 2005

የIድ‘ለት ቁዘማ 1 Aላህ ሆይ ከቤቴ ሮሮዬን ስማ፣

ፖሊስ መስጅድ ገብቷል፥ ፀሎቴን ሊቀማ።

የIድ‘ለት ቁዘማ 2 Eስከዛሬ ድረስ፣ Eኛ በምናውቀው

ከርቸሌ ቋንቋ‘ንጂ* ሃይማኖት Aያውቀው፤ IሕAዴግ ግን ቸሩ፣… ጭር ሲል Aይወዴ

Eስርቤቱን ሁሉ Aሰለመው ባንዴ። ነሐሴ 2፣ 2005

* Aቶ ስዬ በOነግ ስም የታሰሩትን መብዛት ለማመልከት፥ “Eስር ቤቱ Oሮምኛ ይናገራል” ማለታቸው ይታወሳል።

የዘመን Eጣ (ጫወታ ፪) የተያዩት…

Aንዱ ምግብ ቤት ውስጥ፥ ፊት ለፊቱ ተቀምጣ፣ Eሱ ቢራውን ሲለጋ፥ Eሷ ለስላሳ ጨብጣ።

Aብረው ያደሩት…

በስድስት ወራት ልመና፥ ለስላሳዋን Aስቀምጣ፣ 6 ብርጭቆ ወይን፥ Eንደዋዛ ጨልጣ።

የተጋቡት…

በየ28 ቀኑ፥ ተመላላሹ የሷ Eጣ፣ ሦስት ወር ያለፈው ጊዜ፥ ተመልሶ ሳይመጣ።

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

28  

የተፋቱት… ወይራ ታጥና ሳትጨርስ፥ ከAራስ ቤት‘ንኳ ሳትወጣ፣ የከንፈር ቀለም Aሻራ፥ ሸሚዙ ላይ ይዞ ሲመጣ።

---

(ከ ፮ ወራት በኋላ) Eሱ ተፀፅቶ…

“Aንድ ቀን Aጥፍቼ፥ ስንት ዓመት ልቀጣ? ለምን በኔ ስተት፥ ልጄስ Aባት‘ትጣ?

በEመቤቴ ማርያም ተመልሼ ልምጣ…”

Eሷ… “ስድስት ወራት ጠፍተህ፥ ድንገት ስትመጣ፣

____________________ ____________። (በጎደለው Eየሞላችሁ Eንዝናናበት።)

Aስቂኝ ምላሾች

Kuku A. Eb፡ Eኔ Eየመነመንኩ ልጅህ ጥርስ Aወጣ.... Binyam Yonas፡ ሰው ያስባል Aትልም? በል Aልጋ ላይ ውጣ Zelalem Kiberet: ረስተህ Eንዳይሆን ሱሪ ወይም ሻንጣ Aፍቃሪ ከሆነች:— ምነው ከሳህ ሆዴ፥ ፊትህም ገረጣ፣ ፀጉርህና ልብስህ፥ Eንዲህ ቅጡን Aጣ? Natnail Feleke: Aማኝቷ ደግሞ:— Eመቤቴን ጠርተህ Eንዴት Eምቢ ልበል፣ Eንዴትስ ልቆጣ? Yehulualem Teshome፡ የወተቷን ከፍለህ፣ቀጥ ብለህ ውጣ፡፡

ነሐሴ 4፣ 2005 Aጭር መጣጥፍ ፲፰፤ መለስን ከቀዳሚዎቻቸው’ጋ የማወዳደር ሽቀላ Aቶ መለስ መሞታቸው በIቴቪ ከተነገረ Aንድ ዓመት ነገ ይሞላዋል፡፡ መንግሥት Eንደስትራቴጂ በስማቸው (‹‹በሙት መንፈሳቸው››) ማስተዳደር ከጀመረም Eንዲሁ Aንድ ዓመት፡፡ ይህንን Aጋጣሚ በመከተልም ስማቸውን ለማግዘፍ የሚደረገውን ፕሮፓጋንዳ ለመቋቋም የራሴን ድርሻ በዚህ ሳምንት በAጫጭር ማስታወሻዎች ለመወጣት Eሞክራለሁ፡፡

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

29  

የመለስን ‹‹ታላቅነት›› ለማግዘፍ ከሚደረግባቸው ሙከራዎች Aንዱ ካለፉ Aምባገነኖችጋ ማወዳደር Aንዱ ነው፡፡ ይህንን ዘዴ መለስ ራሳቸው በሕይወት Eያሉ ጀምረውት ነበር፡፡ ለምሳሌ በጥር ወር 2003 ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከተማሪዎችጋ ባደረጉት ቃለምልልስ በAስተዳደራቸው ያመጡትን ዴሞክራሲ ለመግለጽ የተናገሩት ‹ዜጎች ለተገደሉበት ጥይት ወላጆች የጥይት ሒሳብ Eንዲከፍሉ የሚጠየቁባት Aገር ነበር የተረከብነው› በማለት ነበር፡፡ ይህ በመለስ ይሁንታ 193 ሰዎች በAደባባይ በተገደሉበት Aገር የተሳሳተ ምሳሌ ነበር፡፡ ያለፉት ገዢዎች Aምባገነንነትም ቢሆን ለመለስ ለዘብተኛ Aምባገነንነት መመዘኛ ሊሆን Aይችልም፡፡ የሚያሳዝነው… የመለስን Aስተዳደር በAምባገነንነቱ ወደር ካልተገኘለት ከደርግጋ በማወዳደር ለማግዘፍ የሚሞክሩት ወደኋላ ርቀው ከንጉሡ ጋር ለማወዳደር ግን Aይሞክሩም፡፡ በንጉሡ ጊዜ ተማሪዎች ሲያምፁ የሞተው ሰው ቁጥር 12 ሰው ብቻ ነበር፤ Aሁንስ? በንጉሡ ግዜ የነበሩት ትላልቅ ምሁራንን የሚያክሉ ባለሥልጣናት ቦታ Aሁን በካድሬዎች ተሞልቷል፡፡ ካድሬዎቹም ከዚያ ዘመን መጥፎውን ብቻ Eየመዘዙ የመለስ ማግዘፊያ የማድረግ ሽቀላውን Aጧጡፈውታል፡፡ ዶ/ር ዳኛቸው Aሰፋ ‹Eያንዳንዱ Aስተዳደር በራሱ ዘመን መመዘኛ ይመዘናል Eንጂ ካለፈው Aንፃር መመዘኑ ትክክለኛ Aካሄድ Aይደለም› ይላሉ፡፡ Aዎ፤ ከንቱ ሽቀላ ነው፡፡ የመለስ Aስተዳደር ስር የሰደደ፣ ዘመናዊ Aምባገነናዊ Aስተዳደር ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ የፓርቲው Aባላት ሳይቀሩ በAንድ ሰው የሚገዙበት የAንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት የገነነበት ክፉ Aስተዳደር ነበር፡፡

ነሐሴ 13፣ 2005 Aጭር መጣጥፍ ፲፱፤ መለስ ዜናዊ ባይሞቱ ሥልጣን ይለቁ ነበር? የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቤተ መንግሥት Eንደገቡ ከገቧቸው ቃልኪዳናት መካከል ‹ሥልጣን ላይ Aለመክረም› Aንዱ ነበር፡፡ ግንቦት 1983 የቤተመንግሥቱን ደጃፍ ስትጠብቅ ያገኛትን ታጋይ ቃለመጠይቅ ያቀረበላት ጋዜጠኛ ያገኘው መልስ ‹‹ይህ ቤት ከዚህ በፊት የመንግሥቱ Eንደነበረው የመለስ Aይሆንም የIትዮጵያ ሕዝብ Eንጂ›› የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ገና በማለዳ ትልቁ የሽግግር መንግሥቱ ባለሥልጣን የነበሩት ፕሬዚደንት መለስ ሕገ መንግሥቱ ሲፀድቅ Eና ዋነኛው ሥልጣን (ሥልጣኑና ጊዜው ገደብ ለሌለው) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲተላለፍ ፕሬዘንዳንቱ መለስ የAዲሱ Aስተዳደር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡ የዚያ በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውን የተነጠቁት ታምራት ላይኔ በብስጭት ዓይናቸውን ሲያጉረጠርጡ የሚያሳየውን ቪዲዮ ከIቴቪ ገዝቶ መመልከት ይቻላል፡፡ በዚህ የተጀመረው የሥልጣን ጉዞ መለስን Eስከ Eለተ ሞታቸው ተከትሏቸዋል፡፡ ሊቀናቀኗቸው የሚችሉትን በሙሉ ስም ሲያጠፉ Eና ሲያባርሩ መክረማቸውን የሚክድ ይኖራል ብዬ Aልገምትም፡፡ በተለይ በAዲስ Aበባ ነዋሪዎች ተወዳጅነትን ለማትረፍ የበቁትን ብቸኛውን የሕወኀት Aባል - Aርከበ Eቁባይን - በግልጽ ጠምደዋቸው ነበር፡፡ Aርከበ የኤች.Aይ.ቪ ምርመራ ማድረጋቸውን ለመቀስቀሻነት ለመጠቀም በAደባባይ ቢልቦርድ ላይ መሰቀሉን Aስመልክተው ሲያሾሙሩ ‹‹Eኛም ማስታወቂያ Aልሰቀልንም Eንጂ ተመርምረናል›› ዓይነት የመንደር ትችት ሰንዝረዋል፤ የኋላ ኋላም Aርከበን ለሕዝብ ወደማይታዩበት ኃላፊነት በመሾም Aባርረዋቸዋል፡፡

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

30  

E.ኤ.A. በ2008 የወጣ የዊኪሊክስ መረጃ Eንደሚያመለክተው በሕወኀት ጉባኤ ላይ Eኚሁ መለስ ያልወደዷቸው Aርከበ ሊቀመንበር Eንዲሆኑ ቢመረጡም ‹‹በAርከበ Eምቢተኝነት›› መለስ በሊቀመንበርነታቸው ቀጥለዋል ይለናል፡፡ Eዚህጋ Aርከበ Eውን ‹‹Eምቢ›› ብለዋል? ለምን? የሚሉትን ጥያቄዎች Eንተውና ሌሎች መረጃዎችን Eናንሳ፡፡ Aቶ መለስ ምርጫ 1997 ከመካሄዱ በፊት ሥልጣን Eንደሚለቁ ሲናገሩ ነበር፤ Aልለቀቁም፡፡ በምርጫ 2002ም ሥልጣናቸውን Eንደሚያስረክቡ ተናግረው የነበረ ቢሆንም፣ ‹በመተካካት Aስፈፃሚነት› ስም Aራዘሙት፡፡ በሥልጣን ማራዘሙ ወቅት መለስ የሚነግሩን ‹‹በEርሳቸው ፍላጎት ሳይሆን በፓርቲያቸው ትEዛዝ ሥልጣናቸውን Eንደቀጠሉ›› ነበር፤ ‹Eባክህ ቆይልን› የሚሉት ተማፅኖዎች (ለኔ ድራማዎች) ከመሞታቸው በፊትም፣ ከምርጫ 2002 በኋላ ቀጥለው ነበር፡፡ ስለዚህ መለስ ባይሞቱ ኖሮ በሥልጣን የሚቀጥሉ ይመስለኛል፡፡ በመሞታቸው ከምቆጭባቸው ምክንያቶች ውስጥ Aንዱ ‹የድራማውን መጨረሻ Aለማየታችን› ነው፡፡ ነሐሴ 14፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፳፤ መለስ ዜናዊ፤ ዴሞክራት ወይስ Aምባገነን? በኛ ዘመን ያሉ የተመሰከረላቸው Aምባገነኖች “ምርጫ"ን ተገን Aድርገው ነው ሥልጣናቸውን Aስጠብቀው የሚኖሩት። ለምሳሌ ሙጋቤ በቅርቡ በ90 ዓመታቸው መባቻ ላይ “ምርጫ Aሸንፈው" ሥልጣናቸውን ለሠላሳ ምናምንኛ ዓመት Aስቀጥለዋል። ብዙዎቹ Aምባገነኖች ዴሞክራሲን በመዝገበ ቃላቶቻቸው ስላኖሩ በባሕሪ ዲሞክራት ይመስላሉ፤ በተግባር ግን የተለዩ ናቸው። መለስ ዜናዊ በትውልድ ስፍራቸው በAብላጫ ድምፅ ለምክር ቤቱ ይመረጣሉ (ምናልባትም ያለምንም manipulation ማሸነፍ የሚችሉት ምርጫ ይሄው ብቻ ይመስለኛል)። በIሕAዴግ ውስጥ ሊቀምበርነት 8 ግዜ “ተመርጠዋል"፣ ሕወኀትን ከAቦይ ስብሐት ከተረከቡ ወዲህ ለሌላ Aላስረከቡም፣ ከግንቦት 1983 ጀምሮ ትልቁን የIትዮጵያ ሥልጣን ይዘው ኖረዋል። የIትዮጵያ ሕገ መንግሥት በባለሙያዎች ቢዘጋጅም የሕወኀትን ሕልም Eንዲያሟላ በሕወኀት (መለስ) ግምገማ ስር በማለፉ ያመቻመቻቸው (compromised) ነገሮች Aሉ። ለምሳሌ ከትEምርትነት (symbolism) በላይ ትርጉም ለሌለው ፕሬዚደንት የሥልጣን ዘመነ ገደብ ሲያስቀምጥ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ግን ያለገደብ Eንዲገዛ ይፈቅድለታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን በሕገመንግሥቱ ውስጥ ገደብ Aያውቅም፤ በምርጫ የተገነባ ምክር ቤት Eስከመበተን ድረስ የሚዘልቅ መብት ያጎናፅፈዋል። ስለዚህ መለስ ይህንን በራሳቸው ትEዛዝ የተነደፈ የሕገ መንግሥታዊ Aምባገነንነት ስትራቴጂ በAግባቡ ተጠቅመውበታል። ይሁን Eንጂ ከደጓሚዎቻቸው ምEራባውያንጋ ለመሞዳሞድ Eንዲያመቻቸው የዴሞክራሲ ባርኔጣም መልበሳቸው Aልቀረም። ከሽምቅ ተዋጊነት ሲመጡ ዴሞክራት ይሆናሉ ብሎ ያመነ ስላልነበረ ተቀባይነት Eስኪያገኙ፣ ጠንካራ ተቃዋሚ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

31  

Eስኪመጣና ሕዝቡ የደርግ Aስተዳደር ከፈጠረበት “የፍርሐት ቆፈን" Eስኪወጣ ድረስ ዴሞክራት ለመሆንም ሞክረው ነበር። ነገር ግን “የስኒ ማEበል" ፈጣሪ የነበሩት ተቃዋሚዎች በምርጫ 97 “ሱናሚ" ሆነው ሲመጡ፥ መለስም ባርኔጣቸውን Aውልቀው Aስቀመጡ። ምርጫ 97ን ተከትሎ መለስ ወጣቶችን በAደባባይ ከማስገደል ጀምሮ፣ የግል ፕሬሱን Eና ሲቪል ማኅበረሰቡን Aሽመደመዱ። ይህም Aልበቃ ብሏቸው “ከሕገመንግሥቱ የሚፃረሩ" Aንቀፆች ያሉትን የፀረሽብር Aዋጅም Aወጡ። በፀረ ሽብር ዘመቻ ስም ከሶማሌጋ ይፋዊ ጦርነት Eስከመግጠም በመድረሳቸው የምEራባውያንን ድጋፍ ያላጡት መለስ፥ በሕጉ ሽፋን ተቃዋሚዎቻቸውን Eያደኑ ማሰር ቀጠሉ። Aቶ መለስ ስለሙጋቤ በውጭ ጋዜጠኛ ሲጠየቁ “ሙጋቤ የሚለው Aፍሪካውያን ዴሞክራሲ Aያስፈልጋቸውም ሳይሆን፥ ለAፍሪካውያን የሚያስፈልጋቸው የተለየ ዴሞክራሲ ነው” በማለት የሙጋቤን Aቋም የገዙትም ከዚያ ወዲህ ነው፤ ዴሞክራሲን የምEራባውያን የቅንጦት ንብረት በማድረግና ቅንጦቱ ለAፍሪካውያን Eንደማያስፈልጋቸው በማመን። መለስ ከስኒ ማEበልነት በላይ Aቅም የሌላቸው ተቃዋሚዎች ባሉበት ዴሞክራት ለመምሰል ሞክረዋል። ይህ ግን Aያስመሰግናቸውም። ተቃዋሚ በሌለበት ሁሉም ዴሞክራት ነው። ችግሩ ተቃውሞን Eንደጤናማ Eውነታ መቀበል Aለመቻላቸው ነው። መለስ ዴሞክራት Aልነበሩም፤ ይልቁንም የIኮኖሚስት መጽሔትን Aፍ ልዋስና “Aምባገነንነት ተቀባይነት Eንዲያገኝ የሞከሩ መሪ” ነበሩ። ነሐሴ 15፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፳፩፤ የመለስ ዜናዊ የውጭ ግንኙነት Aያዎ Aቶ መለስ በምEራባውያን የተወደዱ የAፍሪካ መሪ ነበሩ ማለት ይቻላል። ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቀጥሎ የውጭ ግንኙነት ሞገስ ያላቸው የAገር ሰው ነበሩ። ድጋፍ ጠይቀው የሚያሳፍራቸው ምEራባዊ Aገር Aልነበረም። ይሁን Eንጂ በAፍሪካ ቀንድ Aገራት መካከል የIትዮጵያን ጥቅም በማስጠበቅና ፀጥታን በማረጋገጥ ግን ተሳክቶላቸዋል ብዬ Aላምንም። ምክንያቶች Aሉኝ:— 1) በIትዮኤርትራ ግጭት ከ70 ሺሕ በላይ ዜጎች የሞቱለት መሬት (ባድመ) በሔግ ድርድር

Eና ውሳኔ ለኤርትራ ቢሰጥም የሁለቱ መንግሥታት ቅራኔ ግን Eልባት Aላገኘም፣ (የAሰብ ጉዳይም ቢሆን የIትዮጵያን ጥቅም Eና የባለቤትነት መብት ባገናዘበ መልኩ መፍትሔ Aልተፈለገለትም፣)

2) ቀድም የIትዮጵያ ክልል ውስጥ የነበረ የመተማ መሬት “ቀድሞም የነሱ ነበር" በሚል የIትዮጵያ ሕዝብ Eንዲያውቅ ሳይደረግ በሱዳን ክልል Eንዲካተት መደረጉ፣

3) የሶማሊያ ጣልቃ ገብነት — መለስ በድኅረ ምርጫ 97 ቀውስ ከገቡበት የምEራባውያንን ድጋፍ የማጣት Aደጋ ያተረፋቸው ይህ ነበር። በፀረሽብር ዘመቻ ስም መቋዲሾ ድረስ

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

32  

በመዝለቅ ጊዜያዊ መንግሥት በIትዮጵያ ወታደሮች መስዋEትነት ቢመሠርቱም Aልሻባብን በመጠቃት ስሜት የተሻለ ድጋፍ ያለው ዝነኛ Aሸባሪ ማድረጋቸው ግን Aልቀረም። Aገሪቱ ተረጋግታለች ከተባለ በኋላም ሠራዊቱ ሶማሊያን ለቆ በወጣ በዓመቱ ተመልሶ ለመግባት ተገዷል፣

የAቶ መለስ Iትዮጵያ ራሳችንን ከነርሱ ባናወዳድር ከሚሻሉን የቀንዱ Aገራት Aንፃር ሠላማዊ ነበረች/ነች። ለመለስ በምEራባውያን ዘንድ ተወዳጅነት በዚህ “Aደጋ ያንዣበበበት" Aካባቢ Aንፃራዊ መረጋጋት ያለው መሆኑ፣ የልማታዊ መንግሥት ሙከራ (experiment) ላይ መሆናቸው Eና ይህም Aካዳሚያዊ ቀለም ስላለበሳቸው፥ በIትዮጵያውያን መስዋEትነት (ወይ በጦርነት Aሊያም ሉኣላዊ ግዛትን Aሳልፎ በመስጠት) ምEራባውያንን ማስደሰትና ተመራጭነትን Aስገኝቶላቸዋል። የውጭ ግንኙነታቸው ግን ከሥልጣን ማራዘምና የዓመት በጀት መሙያ ገንዘብ ከማግኘት በላይ የማትደፈር፣ መልካም ገጽታ ያላት ታላቂቷን Iትዮጵያ ከመቅረጽ Aንጻር የትም Aላደረሰንም።

ነሐሴ 16፣ 2005

Aጭር መጣጥፍ ፳፪፤ COINTELPRO* Eኛም Aገር ይኖር ይሆን? Aሜሪካውያኖቹ COunter INTELligence PROgram የሚለውን በAጭር ቃል ሲጠሩት COINTELPRO ይሆናል። COINTELPRO E·ኤ·A· በ1971 Eስኪነቃበት ድረስ ምስጢራዊ የኤፍቢAይ ፕሮግራም ነበር። ነገርዬው ሕገወጥነት ባሕሪ ያለው የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ገብቶ የማፈራረሻ ፕሮግራም ነው። በፕሮግራሙ የAሜሪካ ኮሙኒስት ፓርቲ፣ (ማርቲን ሉተር ኪንግን ጨምሮ) የጥቁሮች Eኩልነት Aራማጆች፣ የዘረኛ ነጮቹ ቡድን (KKK)፣ የሴቶች መብት Aቀንቃኞችና ሌሎችም (ጥሩዎቹም መጥፎዎቹም ተጨፍልቀው) ሰለባዎች ሆነውበታል። የCOINTELPRO ዓላማ ኤፍቢAይ “Aገር Aጥፊ” ናቸው ያላቸውን የፖለቲካ ቡድኖች “ማጋለጥ፣ ማወክ፣ Aቅጣጫ ማሳት፣ ወይም ማሽመድመድ" ነው። ይህንንም የሚያደርገው:—

1. የቡድኑን መልካም ገጽታ በማበላሸት (ለምሳሌ Aራማጆችን በመሰለልና Aሉታዊ የግል መረጃዎቻቸውን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ)፣

2. ውስጣዊ መዋቅራቸውን በማፈራረስ፣

3. በቡድኖች መካከል ቅራኔ በመፍጠር፣

4. ሕዝባዊ ንብረት ተጠቃሚ Eንዳይሆኑ በማድረግ፣

5. ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን Eንዳያደርጉ በማገድ Eና

6. የግለሰቦችን በቡድኖቹ ውስጥ የመሳተፍ Eድል በማገድ ነው።

የፌስቡክ ትሩፋት (ሁለት) 2005 

33  

ኤፍቢAይ ይህንን የሚያደርገው በተለይ ጎልተው የወጡ የቡድኖቹ Eና Eንቅስቃሴዎቹ መሪዎች ላይ በማነጣጠር ነበር።

ከዘዴዎቹ ውስጥ:—

1. ቡድኖቹ ውስጥ ራሱን Aመሳስሎ የሚሳተፍ ሰው ሰርጎ በማስገባት፣

2. በAራማጆቹ ላይ የሥነልቦና ጦርነት በመክፈት፣

3. በሕግ ስም በማጉላላት፣

4. ሕገ ወጥ የኃይል Aጠቃቀም በመተግበር ጭምር ነበር።

Eኛም ታዲያ Eነዚህኑ የሚመስሉ ድርጊቶች በዛሬይቱ Iትዮጵያችን ላይ Eያየን ነው። ጥያቄው ‘የደኅንነት ቢሮ ፕሮግራም ነድፎ Eየተንቀሳቀሰበት ነው ወይስ ተራ የፓርቲ ካድሬዎች ሥራ ነው?’ የሚለው ብቻ ይሆናል።

* ስለ COINTELPRO ያስተዋወቀኝ በEስር ላይ Eያለ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሰለባ የሆነው ጋዜጠኛ Eስክንድር ነጋ ቃሊቲ ልጠይቀው የሄድኩ ጊዜ ነው፡፡

ነሐሴ 21፣ 2005