ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

20
ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 4 ቁጥር 4-ሰኔ 2008 ዓ.ም www.ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar ጣፋጭ ኢትዮጵያን ከስኳር ኢንዱስትሪው የላቀ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፍኖተ ካርታዎች ላይ ወርክሾፕ ተካሄደ * ፍኖተ ካርታዎቹ በሆርቲካልቸር፣ በእንስሳት ሀብት፣ በባዮ-ኬሚካል፣ በባዮማስ እና በከተሞች ልማት ላይ አተኩረዋል ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ወደ ውጪ ሀገር በመላክ 1 ሚሊየን 35 ሺህ ዶላር ተገኘ፡፡ በቀጣይም በየወሩ 10ሺህ ቶን ሞላሰስ ለውጪ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዷል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ከስኳር ተረፈ ምርት አንዱ የሆነውንና በስኳር ፋብሪካዎች በብዛት ተከማችቶ የሚገኘውን ሞላሰስ በሀገር ውስጥና በውጪ ገበያ ለመሸጥ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረት ምርቱን በሀገር ውስጥ ለከብት አድላቢዎችና ለኢንዱስትሪዎች እያቀረበ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ወደ ውጪ ለመላክ በሞላሰስ ንግድ ከተሰማራው ሮውኔት ቢዝነስ ከተባለ የግል ኩባንያ ጋር የካቲት 2008ዓ.ም የሞላሰስ ሽያጭ ስምምነት አድርጎ ምርቱን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ተጀምሯል፡፡ ኩባንያው ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ወደ እንግሊዝ ሀገር መላኩን ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ወደ ውጭ ሀገር ተላከ * ከሽያጩ 1 ሚሊየን 35 ሺህ ዶላር የውጪ ምንዛሬ ተገኝቷል » ወደ ገጽ 3ዞሯል » ወደ ገጽ4ዞሯል በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ዶ/ር ካሱ ይላላ ወርክሾፑን ሲመሩ » ወደ ገጽ4ዞሯል በውስጥ ገጾች ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ>>16 “የለውጡ የመጀመሪያው ዓላማ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍን ማስቀጠል ነው” >>8 ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ” >>13 የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አብዛኛዎቹ የሲቪልና የፋውንዴሽን ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ * የቁጥር ሶስት ፋብሪካ ግንባታም እየተካሄደ ነው በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከሚገነቡት አራት ስኳር ፋብሪካዎች አንዱ የሆነው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አብዛኛዎቹ የሲቪልና የፋውንዴሽን ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ፡፡ የፋብሪካ ቁጥር ሁለት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለም ከበደ እንደገለጹት፣ የሲቪል ሥራው ነሐሴ 2007 ዓ.ም የተጀመረው የፋብሪካው አብዛኛዎቹ የሲቪልና የፋውንዴሽን ሥራዎች ተጠናቀዋል። በዚህም የስቲል ስትራክቸር ፋውንዴሽን፣ የኬን ፕሪፓሬሽን፣ የወፍጮ፣ የፓወር ኮጄነሬሽን፣ የስቲል ስትራክቸር፣ የሀውሲንግ፣ የኬሚካል ዎተር ትሪትመንትና ሌሎች በርካታ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡ የፋብሪካው ግንባታ በ2009ዓ.ም ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ የሚናገሩት አቶ ዓለም፣ መጀመሪያ ላይ ፋብሪካው ጥሬ ስኳር (raw sugar) በማምረት ሥራ እንደሚጀምርና በሂደት የተጣራ ነጭ ኢትዮጵያን ከስኳር ኢንዱስትሪው የላቀ ተጠቃሚ ማድረግ በሚያስችሉ ፍኖተ ካርታዎች ላይ የተዘጋጀው ወርክሾፕ ከሰኔ 22–23 ቀን 2008 ዓ.ም በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተካሄደ፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ከኢፌዴሪ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር ባካሄደው ወርክሾፕ ላይ ከስኳር ኢንዱስትሪው የሚገኙ ተረፈና ተጓዳኝ ምርቶችን ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ የፋብሪካ ቁጥር ሁለት ግንባታ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለም ከበደ

Transcript of ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!

ቅፅ 4 ቁጥር 4-ሰኔ 2008 ዓ.ምwww.ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar

ጣፋጭኢትዮጵያን ከስኳር ኢንዱስትሪው የላቀ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፍኖተ ካርታዎች

ላይ ወርክሾፕ ተካሄደ* ፍኖተ ካርታዎቹ በሆርቲካልቸር፣ በእንስሳት ሀብት፣ በባዮ-ኬሚካል፣ በባዮማስ እና በከተሞች ልማት

ላይ አተኩረዋል

ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ወደ ውጪ ሀገር በመላክ 1 ሚሊየን 35 ሺህ ዶላር ተገኘ፡፡ በቀጣይም በየወሩ 10ሺህ ቶን ሞላሰስ ለውጪ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዷል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን ከስኳር ተረፈ ምርት አንዱ

የሆነውንና በስኳር ፋብሪካዎች በብዛት ተከማችቶ የሚገኘውን ሞላሰስ በሀገር ውስጥና በውጪ ገበያ ለመሸጥ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረት ምርቱን በሀገር ውስጥ ለከብት አድላቢዎችና ለኢንዱስትሪዎች እያቀረበ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ወደ ውጪ ለመላክ በሞላሰስ ንግድ

ከተሰማራው ሮውኔት ቢዝነስ ከተባለ የግል ኩባንያ ጋር የካቲት 2008ዓ.ም የሞላሰስ ሽያጭ ስምምነት አድርጎ ምርቱን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ተጀምሯል፡፡

ኩባንያው ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ወደ እንግሊዝ ሀገር መላኩን

ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ወደ ውጭ ሀገር ተላከ* ከሽያጩ 1 ሚሊየን 35 ሺህ ዶላር የውጪ ምንዛሬ ተገኝቷል

» ወደ ገጽ 3ዞሯል

» ወደ ገጽ4ዞሯል

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ዶ/ር ካሱ ይላላ ወርክሾፑን ሲመሩ

» ወደ ገጽ4ዞሯል

በውስጥ

ገጾች

ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ>>16

“የለውጡ የመጀመሪያው ዓላማ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍን ማስቀጠል ነው” >>8

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ” >>13

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አብዛኛዎቹ የሲቪልና የፋውንዴሽን ሥራዎች

መጠናቀቃቸው ተገለጸ * የቁጥር ሶስት ፋብሪካ ግንባታም እየተካሄደ ነው

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከሚገነቡት አራት ስኳር ፋብሪካዎች አንዱ የሆነው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አብዛኛዎቹ የሲቪልና የፋውንዴሽን ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ፡፡

የፋብሪካ ቁጥር ሁለት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለም ከበደ እንደገለጹት፣ የሲቪል ሥራው ነሐሴ 2007 ዓ.ም የተጀመረው የፋብሪካው አብዛኛዎቹ የሲቪልና የፋውንዴሽን ሥራዎች ተጠናቀዋል። በዚህም የስቲል ስትራክቸር

ፋውንዴሽን፣ የኬን ፕሪፓሬሽን፣ የወፍጮ፣ የፓወር ኮጄነሬሽን፣ የስቲል ስትራክቸር፣ የሀውሲንግ፣ የኬሚካል ዎተር ትሪትመንትና ሌሎች በርካታ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡

የፋብሪካው ግንባታ በ2009ዓ.ም ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ የሚናገሩት አቶ ዓለም፣ መጀመሪያ ላይ ፋብሪካው ጥሬ ስኳር (raw sugar) በማምረት ሥራ እንደሚጀምርና በሂደት የተጣራ ነጭ

ኢትዮጵያን ከስኳር ኢንዱስትሪው የላቀ ተጠቃሚ ማድረግ በሚያስችሉ ፍኖተ ካርታዎች ላይ የተዘጋጀው ወርክሾፕ ከሰኔ 22–23 ቀን 2008 ዓ.ም በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተካሄደ፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን ከኢፌዴሪ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር ባካሄደው ወርክሾፕ ላይ ከስኳር ኢንዱስትሪው የሚገኙ ተረፈና ተጓዳኝ ምርቶችን ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ

የፋብሪካ ቁጥር ሁለት ግንባታ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለም ከበደ

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም2

የስኳር ኮርፖሬሽን አመራር ከመተሓራና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በወቅታዊ የስኳር ኮርፖሬሽን እና የፋብሪካዎቹ ሁኔታ ላይ ተወያየ፡፡

በፋብሪካዎቹ በመገኘት የውይይት መድረኮቹን የመሩት የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ እንደተናገሩት፣ በዘንድሮ ዓመት በኤሊኒኖ ሳቢያ ከተከሰተው የድርቅ አደጋ ጋር ተያይዞ በተለይም በመተሓራና በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ለመስኖና ለፋብሪካ የሚሆን የውሃ አቅርቦት ችግር በማጋጠሙ የስኳር ምርትና የአገዳ ምርታማነት ቀንሷል፡፡

ከዚህ ባሻገር በ2008 ዓ.ም ተንዳሆን ጨምሮ ወደ ስራ መግባት የነበረባቸው አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ሥራ ባለመጀመራቸው ምክንያትም በዘርፉ የታቀደውን ያህል የስኳር ምርት ለማግኘት አልተቻለም ብለዋል፡፡

ከውሃ እጥረት በተጨማሪ አልፎ አልፎ በሚያጋጥሙ የቴክኒክ ችግሮች፣ የግብዓት አቅርቦት እጥረት እና የባለሙያ ፍልሰት የመተሓራና የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች የእቅድ አፈጻጸም እንደታሰበው አለመሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የነባሮቹ ስኳር ፋብሪካዎች ምርት ዝቅተኛ መሆንና የአዳዲሶች ፋብሪካዎች ሥራ አለመጀመር የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ከችግሩ ለመውጣትም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በስኳር ልማት ዘርፍ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡

ለስኬቱም በቀጣይ አመታት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዘርፉ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ ያሳሰቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ያለው ዋንኛ አማራጭም ይህ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱም ነባር ስኳር ፋብሪካዎች ውይይት በተደረገበት ወቅት በጊዜያዊነት የሚሰሩ የአገዳ ቆራጭ ሠራተኞች ያነሱት የቀን ውሎ አበል ማስተካከያ ጥያቄ ተገቢ ነው ያሉት አቶ እንዳወቅ፣ ከሐምሌ ወር 2008ዓ.ም ጀምሮ ማስተካከያው ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ ለሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ሠራተኞች ከዚህ በፊት ላስመዘገቡት ውጤት ማትጊያ (ቦነስ) ይሰጣችኋል ተብሎ የተገባላቸውን ቃል ኮርፖሬሽኑ በ2009ዓ.ም

ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደረግ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

በመተሓራ ስኳር ፋብሪካ ውይይት በተደረገበት ወቅት በመልካም አስተዳደር ችግር ዙሪያ የሠራተኞች ቅሬታ በስፋት የተነሳ ሲሆን፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማጣራትና ጥናት በማድረግ በአመራሩ ታዩ የተባሉት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደሚፈቱ አስታውቀዋል፡፡ በሚገኘው ውጤት መሰረትም አስፈላጊው ማስተካከያና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም በሁለቱም ፋብሪካዎች ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የህክምናና የትራንስፖርት ችግሮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በውይይቶቹ ወቅት ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኮርፖሬሽኑ እና በፋብሪካዎቹ አመራሮች እንዲሁም በሠራተኛ ማህበራት ሊቀመንበሮች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በሁለቱም መድረኮች ማጠቃለያ ላይ የየፋብሪካዎቹ ሠራተኞችና አመራሮች በጋራ ባወጡት የአቋም መግለጫ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ለመፍታትና የስኳር ልማት ዘርፍ ግቦችን ለማሳካት በሙሉ ፍላጎትና ቁርጠኝነት እንደሚረባረቡ ቃል ገብተዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ አመራር ከመተሓራና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ተወያየ

በመተሓራ ስኳር ፋብሪካ ከሠራተኞች ጋር የተደረገ ውይይት

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከሠራተኞች ጋር የተደረገ ውይይት

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 3

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

የወርክሾፑ ተሳታፊዎች ያደረጉት ጉብኝት

ተጠቃሚነት የሚያሸጋግሩ ፍኖተ ካርታዎች ቀርበው በውይይት ዳብረዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት እና በምርምር ተቋማት ምሁራን የተዘጋጁ ፍኖተ ካርታዎች በቀረቡበት በዚህ ወርክሾፕ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ዶ/ር ካሱ ይላላ እንደተናገሩት፣ የኢፌዴሪ መንግሥት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከፍተኛ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት ዘርፎች መካከል የስኳር ልማት ግንባር ቀደም ነው፡፡

ከዚህ ግዙፍ ኢንዱስትሪ ዘርፈ ብዙ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እንዲሁም ተጓዳኝ ምርቶችን በማልማት ኢትዮጵያን የላቀ ተጠቃሚ የሚያደርጓት ተግባራት ላይ መንግሥትና የሚመለከታቸው ተቋማት ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ዋነኛው ተዋናይ ደግሞ ስኳር ኮርፖሬሽን ይሆናል ብለዋል ዶ/ር ካሱ ይላላ፡፡

ሚኒስትሩ መንግሥት የባዮ-ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማቋቋሙን ጠቁመው፣ ስኳር ኮርፖሬሽን ይህንን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ ከስኳር ምርት ባላነሰ ተጓዳኝና ተረፈ ምርቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በመለወጥ ግንባር ቀደም ሚና መጫወትና ገቢውንም በከፍተኛ መጠን ማሳደግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ከስኳር ኢንዱስትሪው የሚገኙ ተረፈና ተጓዳኝ ምርቶችን ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሸጋገርና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ አሰራርን መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ደረጃቸውን በጠበቁ የዘርፉ በርካታ ምርቶች አማካኝነት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንድትሆን ኮርፖሬሽኑ ተግቶ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ስኳር ኮርፖሬሽን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ወጣቶች ሠፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር፣ ዘመናዊና በርካታ ዜጎች የሚኖሩባቸው መንደሮችና ከተሞች እንዲመሰረቱ አስተዋጽኦ የሚያደርግ እንዲሁም ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ማዕከል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው በበለፀጉ ሀገሮች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ለኢንዱስትሪዎች የጀርባ አጥንት በመሆን ለሀገሮቻቸው ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት መደላድል እንደፈጠሩ አውስተው፣ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አካዳሚ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እንዲሁም የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከስኳር ኢንዱስትሪው ጋር በጥምረት መስራታቸው ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ለላቀ ውጤት በሚያበቁ ተግባራት ላይ ኮርፖሬሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከምርምር ማዕከላት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ አቶ እንዳወቅ ጠቁመዋል፡፡

በስኳር ምርት ሂደት ለዘመናት ጥቅም ላይ ያልዋሉትን ተረፈ ምርቶች ሀብት ለማመንጨት፣ ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠርና የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን እንጠቀምባቸዋለን ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ፡፡

ኮርፖሬሽኑ በፍኖተ ካርታዎቹ የተቀመጡትን አቅጣጫዎች አቅሙ በፈቀደ መጠን እንደሚተገብራቸውና በልማቱ አካባቢ ከሚገኘው ማህበረሰብ ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር ሀብት እንዲያፈራ ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠሩም ነው የተናገሩት፡፡

በዘርፉ ያለውን አንጡራ ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ መቀየር የሚያስችሉ ፍኖተ ካርታዎች ዝግጅት ላይ መንግሥት ለሰጠው ድጋፍና የተለያዩ አካላት ላደረጉት ከፍተኛ ተሳትፎም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት እና በምርምር ተቋማት ምሁራን የተዘጋጁት ፍኖተ-ካርታዎች ስኳር ኢንዱስትሪው አድማሱን በማስፋት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ብሎም ለሀገራዊ የህዳሴ ጉዞ የላቀ ሚና እንዲጫወት በሚያስችሉት ወርቃማ አማራጮች ማለትም

በሆርቲካልቸር፣ በእንስሳት ሀብት፣ በባዮ-ኬሚካል፣ በባዮማስ እና በከተሞች ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

የቀረቡት ፍኖተ ካርታዎች በስኳር ምርት ሂደት የሚገኙ ተረፈ ምርቶችን ማለትም ባጋስ፣ ሞላሰስ፣ ፊልተር ኬክ፣ እንዲሁም በተጓዳኝ ምርቶች ረገድ ከእንስሳት ርባታና ተዋፅኦ፣ ሆርቲ ካልቸርና ፍራፍሬ ልማት ጋር የተያያዙ ዘርፈ ብዙ ምርቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ መለወጥ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን አመላክተዋል፡፡

በስኳር ተረፈና ተጓዳኝ ምርቶች የግብዓትና ውጤት ሰንሰለት ላይ አፅንኦት በመስጠት የላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚ የሆኑ ሀገሮች ተመክሮዎችንም ፍኖተ-ካርታዎቹን ያዘጋጁት ምሁራንና ባለሙያዎች አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለስኳር ልማት ምቹ የአየር ፀባይ፣ የውሀ ሀብትና በመስኖ ሊለሙ የሚችሉ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች ያሏት ቢሆንም፣ የዘርፉ ኢንዱስትሪ አዝጋሚ በመሆኑና ተረፈ ምርቶቹም ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ጥቅም ባለመዋላቸው የዘርፉ አትራፊነቱ እስካሁን አስተማማኝ ደረጃ ላይ አለመሆኑ ነው በወርክሾፑ የተመለከተው፡፡

የወርክሾፑ ተሳታፊዎች የቀረቡትን ፍኖተ-ካርታዎች የሚያዳብሩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበዋል፤ ማብራሪያዎችንም ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን የምርት ክፍል፣ የኢታኖል ማምረቻ ፕላንት፣ የባዮ ኮምፖስት ዝግጅት፣ የሸንኮራ አገዳ እና የፍራፍሬ ልማት እንዲሁም የቲሹካልቸር ላቦራቶሪን ጎብኝተዋል፡፡ በመስክ ጉብኝታቸውም ጠቃሚ ተመክሮዎችን መቅሰማቸውን ገልፀዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳ የሚገኘው አንጋፋው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከስኳር ምርት ባሻገር ከሞላሰስና ከፊልተር ኬክ ተረፈ-ምርቶች ኢታኖልና ባዮ ኮምፖስት ያመርታል፡፡ በ132 ሄክታር መሬት ላይ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን በማልማት ላይም ይገኛል ፡፡

ኢትዮጵያን ከስኳር ኢንዱስትሪው ... » ከገጽ 1 የዞረ

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም4

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ...

ሰባት ሺህ ቶን ሞላሰስ ...

እና በየወሩም 10 ሺህ ቶን ሞላሰስ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ማቀዱን የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲዋሀብ ረሺድ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ሀገሪቷ ከሽያጩ በወር ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት እንደምትችል ታውቋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ኮርፖሬሽኑ ለሮውኔት ኩባንያ በመጀመሪያ ዙር 20ሺህ ቶን ሞላሰስ በሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ በቀጣይ በዓመት ውስጥ እስከ 120ሺህ ቶን ሞላሰስ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

በሞላሰስ ንግድ በዓለም ከታወቀው ዩናይትድ ሞላሰስ ሊሚትድ ጋር ስምምነት ተፈራርመው እንደሚሰሩ የገለጹት የኩባንያው ሥራ አስኪያጁ፣ ምርቱ የሚላከው የዓለማችንን 80 በመቶ ሞላሰስ ወደሚያጣሩት የአውሮፓ ሀገራት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

» ከገጽ 1 የዞረ

ስኳር (white refined sugar) ወደ ማምረት እንደሚሸጋገር ገልጸዋል።

የፋብሪካውን ግንባታ እያካሄደ የሚገኘው የቻይናው ኮምፕላንት ኩባንያ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ከጅቡቲ ወደብ እያጓጓዘ መሆኑንም አቶ ዓለም አመልክተዋል፡፡ አክለውም የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ከኦሞ ኩራዝ 1 ስኳር ፋብሪካ 15 መሐንዲሶች እንዲመጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሶስት ስኳር ፋብሪካ የቦይለር ፋውንዴሽን፣ የፋብሪካው ፓወር ጄነሬሽንና የውኃ ማጣሪያ ታንከር

ግንባታዎች መጀመራቸውንና የሲቪል ሥራውም እየተፋጠነ መሆኑን ግንባታውን እያካሄደ የሚገኘው የኮምፕላንት የሲቪል ምህንድስና ዲፓርትመንት ሓላፊ ሚ/ር ሎው ሊን ተናግረዋል።

የግንባታ ሥራው የካቲት 2008ዓ.ም እንደተጀመረ የሚገልጹት ሚ/ር ሎው ሊን ኩባንያው የፋብሪካ ግንባታ ሥራውን በ2009ዓ.ም አጠናቆ ወደ ምርት ለማስገባት እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አክሊሉ አዳኝ በበኩላቸው፣ ለፋብሪካው ግብዓት የሚውለውን የሸንኮራ አገዳ ለማልማት የዋና ካናል ግንባታና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ለሶስት ድርጅቶች ኮንትራት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የፌደራል ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን የ5ሺ 200 ሄክታር የዋና ካናልና ተጓዳኝ ሥራዎችን እንዲሁም የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የ5ሺ 500 ሄክታር የዋና ካናልና ተጓዳኝ ሥራዎችን

በማከናወን ላይ ይገኛሉ። በተመሳሳይ JANGXJ የተባለ የውጭ ኩባንያ የ6 ኪሎ ሜትር የዋና ካናልና ስትራክቸሮች ሥራን እንዲያከናውን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከፋብሪካው በቅርበት የሚገኘውን የሻርማ ወንዝ በመገደብና የመስኖ ሥራውን በፕሮጀክቱ አቅም በማከናወን የአገዳ ልማቱን ለማፋጠን እየተሰራ እንደሚገኝና ሥራውም 70 በመቶ መጠናቀቁን አቶ አክሊሉ አመልክተዋል።

» ከገጽ 1 የዞረ

የሞላሰስ ሽያጩ ከመጀመሩ በፊት የወንጂ ሸዋ እና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎች የሞላሰስ ናሙና ወደ ስፔን፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትና ኔዘርላንድ ተልኮ ምርቱ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የአውሮፓ ሞላሰስ አጣሪዎች ከቅርበት አንጻር የኢትዮጵያን ሞላሰስ እንደሚመርጡ አቶ አብዲዋሀብ አመልክተው፣ ከዚህ ቀደም ምርቱን ከብራዚል እና ከሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት ያስገቡ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ሞላሰስ ለእንስሳት መኖ፣ ለነዳጅ፣ ለህክምና፣ ለአልኮሆል መጠጥ፣ ለቀለም መስሪያ ወዘተ አገልግሎቶች ይውላል፡፡

በ2007 በጀት ዓመት በወንጂ ሸዋ፣ በመተሓራና በፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች 150ሺህ 278 ቶን ሞላሰስ ተመርቷል፡፡

ሚ/ር ሎው ሊን የኮምፕላንት የሲቪል ምህንድስና ዲፓርትመንት ሓላፊ

አቶ አክሊሉ አዳኝ የፋብሪካ ቁጥር 3 ዋና ሥራ አስኪያጅ

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 5

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት፣

በአካባቢ ጥበቃና ሙያ ደህንነት ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ* የዓለም አካባቢ ቀን በስኳር ኮርፖሬሽን ተከበረ

በአካባቢ ጥበቃና የሙያ ደህንነት ዙሪያ ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት፣ ከስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለተውጣጡ 31 የሥራ ሓላፊዎችና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዋናው መ/ቤት ከሚያዚያ 13 እስከ 14/2008 ዓ.ም ድረስ የተካሄደውን ስልጠና ያዘጋጀው ኦፕሬሽንስ ሥር የተቋቋመው የአካባቢ ጥበቃና የሙያ ደህንነት አገልግሎት ነው፡፡ በስልጠናው ወቅት የኮርፖሬሽኑ የአካባቢ ጥበቃና የሙያ ደህንነት አገልግሎት ሓላፊ አቶ ብርሃኑ ራቦ እንደገለጹት፣ የኮርፖሬሽኑን ዓላማዎች ለማሳካትና ኢንዱስትሪውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃና የሙያ ደህንነት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፡፡

የስኳር ልማት ዘርፍ ለአገሪቱ ምጣኔ ሀብት እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ሓላፊው፣ ኮርፖሬሽኑ ልማቱን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ለአካባቢ ጥበቃና ለሙያ ደህንነት ልዩ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በየዓመቱ ግንቦት 28 ቀን (June 5) ተከብሮ የሚውለው የዓለም አካባቢ ቀን በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ተከብሯል፡፡ በዓለም ለ43ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ የተከበረው የዓለም አካባቢ ቀን “ለሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ትዕግስታችን አልቋል” በሚል መሪ ቃል ነው፡፡

ቀኑ በኮርፖሬሽኑ በተከበረበት ወቅት የአካባቢ ጥበቃ እና የሙያ ደህንነት አገልግሎት

ሓላፊ አቶ ብርሃኑ ራቦ ዕለቱን አስመልክቶ ለተሳታፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም በማንኛውም ደረጃ የሚከናወን ልማት ወይም ሥራ የአካባቢ ጥበቃን ከግንዛቤ ውስጥ ሲያስገባ ትርፋማነቱ እጥፍ ድርብ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ለማቅረብ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ 10 የሸንኮራ አገዳ አብቃይ የህብረት ስራ ማህበራት ለፋብሪካው የሸንኮራ አገዳ ለማቅረብ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከፋብሪካው ጋር ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓ.ም በሰመራ ከተማ ተፈራረሙ፡፡

ማህበራቱ በዱብቲ ወረዳ የሚገኙ 449 አባ/እማ ወራዎችን በአባልነት አቅፈዋል፡፡

ለሶስት አመታት በስራ ላይ የሚውለውን ስምምነት የፈረሙት በፋብሪካው በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ ኮሎኔል መላኩ ድጋፌ ሲሆኑ፣ በማህበራቱ በኩል ደግሞ የማህበራቱ አመራሮች ናቸው ፡፡

የፋብሪካው የህዝብ አደረጃጀት፣ ህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች አገልግሎት ሓላፊ አቶ አብዱ ሀሰን እንደገለፁት፣ የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈረመው ከሚያዚያ 3-5/2008 ዓ.ም የፋብሪካው እና የማህበራቱ አመራሮች በዱብቲ ከተማ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል መላኩ ድጋፌ በስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት፣ በሁለቱ አካላት መካከል የተፈረመው የሁለትዮሽ ስምምነት ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ፡፡

አክለውም የሸንኮራ አገዳ አብቃይነትና አቅራቢነት ስምምነት ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ምርታማነት እና ለአርብቶ አደሩ ተጠቃሚነት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ፋብሪካው ከዚህ ቀደም ከሌሎች ስድስት የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ስራ ማህበራት ጋር መዋዋሉን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ የአሁኑን ጨምሮ ከሁሉም ማህበራት ጋር የተደረገው ስምምነት የፋብሪካውን ብቻ ሳይሆን የክልሉንም ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዱብቲ ወረዳና በክልሉ ማህበራት ማደራጃ እውቅና የተሰጣቸው የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ማህበራቱ ከፋብሪካው ጋር ለመስራት መስማማታቸውን የሚያረጋግጥ ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውም ታውቋል፡፡

ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከሚለማው የሸንኮራ አገዳ መሬት ውስጥ 25 ሺህ ሄክታሩ በአካባቢው በሚገኙ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ አርብቶ አደሮች እንደሚለማ ይጠበቃል፡፡

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም6

በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የኤች አይ ቪ/ኤድስ የአቻ ለአቻ አመቻቾች ስልጠና ተሰጠ

የግንቦት 20 የድል በዓል በስኳር ኮርፖሬሽን ተከበረ• የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶችም በተለያዩ ዝግጅቶች በአሉን አክብረዋል

በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ኤች አይ ቪ/ኤድስን አስመልክቶ ለ197 ሰዎች የአቻ ለአቻ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዝያ 14/2008 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር በተሰጠው ሥልጠና ከሠራተኞች መካከል የተመለመሉ የአቻ ለአቻ ውይይት አመቻቾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፕሮጀክቱ የሰው ሃብት አመራርና አስተዳደር

ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ሄኖክ በለጠ፣ ስልጠናው ከዚህ ቀደም በፕሮጀክቱ ሲካሄድ ቆይቶ መቋረጡን አስታውሰው የአሁኑ ሥልጠና የአቻ ለአቻ ውይይቱን በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ያስችላል ብለዋል፡፡

ለዚህም ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለ30 ባለሙያዎች የአመቻቾች

አሰልጣኝነት ሥልጠና መመቻቸቱን ጠቁመዋል፡፡

ከፕሮጀክቱ የሥራ ባሕርይ እና የአኗኗር ሁኔታ አንጻር በርካታ ሠራተኞች ከቤተሰብ ርቀው የሚገኙ በመሆናቸው የአቻ ለአቻ ውይይቱ ኤች አይ ቪ/ኤድስን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ጠቄሜታ እንዳለው የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡

የግንቦት 20 የብር ኢዮቤልዩ የድል በዓል በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡ በተመሳሳይ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የድል በዓሉን ሸንኮራ አገዳ በመትከል፣ ስፖርታዊ ውድድሮችን በማካሄድና የተለያዩ ዝግጅቶችን በማከናወን አክብረውታል፡፡

“በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የግንቦት 20 ክብረ በዓል ላይ ንግግር

ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ የስትራቴጂያዊ ድጋፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በዛብህ ገብረየስ እንደገለጹት፤ የዛሬ 25 ዓመት የደርግ ሥርዓት በኢሕአዴግ መሪነትና በመላ የሀገሪቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከፍተኛ ትግልና መስዋዕትነት ተገርስሶ በሀገሪቱ በሁሉም መስኮች ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡

ለውጡም ሀገሪቷን ወደ ሁለንተናዊ ፈጣን እድገት እንድትሸጋገር አድርጓታል ያሉት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ለድሉ መገኘት

ኢሕአዴግ ትክክለኛ መስመር፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ ለተግባራዊነቱ መላውን ሕዝብ አስተባብሮ ሀገሪቱን በቁርጠኘነት በመምራቱ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ህዳሴ ለማረጋገጥ ከተወጠኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ መሆኑን የጠቀሱት አቶ በዛብህ፣ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በዘርፉ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ በ2016 ዓ.ም በዓለም ላይ ከሚገኙ 10 ከፍተኛ » ወደ ገጽ 7 ዞሯል

አቶ በዛብህ ገብረየስ አቶ ወዮ ሮባ አቶ ህቡር ገ/ኪዳን

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 7

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

የግንቦት 20 የድል በዓል ...

የስኳር አምራች አገሮች ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን የሚያደርጉ መደላድሎችን ለመፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አክለውም “በዚህ የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት ቀን በዘርፉ አስቀድመው የተጀመሩ ሰፋፊ ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የሁለተኛው ዕቅድ ዘመን ግቦችን ለማሳካት በሙሉ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ቃል ስንገባ የትግሉ ሰማዕታት ለሰላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ የከፈሉትን የሕይወት መስዋዕትነት ከዳር ለማድረስ ነው ” ብለዋል፡፡

በወቅቱ “የማሽቆልቆል ምዕራፍ ተዘግቶ የእድገት ምዕራፍ የተከፈተበት የሩብ ምዕተ ዓመት የትግልና የድል ጉዞ” በሚል ርዕስ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንስ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ቀርቦ በበዓሉ ተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በክብረ በዓሉ መክፈቻ ላይ ከደርግ ሥርዓት ጋር ሲፋለሙ የተሰዉ ሠማዕታትን ለመዘከር

የሻማ ማብራትና የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጎል፡፡

በተያያዘ ዜና በአሉ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶችም አገዳ በመትከል፣ በስፖርታዊ ውድድሮችና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች የግንቦት 20 የብር ኢዮቤልዩ የድል በዓልን በ12 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ በመትከል አክብረዋል፡፡ ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ የፋብሪካው ሠራተኞች የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብቶቻቸውን ያስጠበቀላቸውን የድል ቀን በልማት ስራ ለማክበር በወሰኑት መሰረት በዘመቻ የሸንኮራ አገዳ ተክለዋል፡፡

በሸንኮራ አገዳ ተከላው ላይ ከተሳተፉት ሠራተኞች መካከል አቶ አሰግድ ጌታቸው እና አቶ ጋሮማ ከበደ በሰጡት አስተያት የድል ቀኑን በማስመልከት በዘመቻ ሥራው ላይ በመሳተፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ

አቶ ካባ መርጋ በበኩላቸው ሠራተኛው በዓሉን አስመልክቶ የፋብሪካው ዋንኛ ችግር የሆነውን የሸንኮራ አገዳ እጥረት በመቅረፍ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ወስኖ በተከላው ላይ መሳተፉ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም የፋብሪካውን ዕቅድ ለማሳካት ሠራተኛው በየስራ መስኩ ጠንክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

በተመሳሳይ በዓሉ በከሰም ስኳር ፋብሪካ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጭምር ባሳተፈ መልኩ በስፖርታዊ ውድድሮችና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ “የማሽቆልቆል ምዕራፍ ተዘግቶ የእድገት ምዕራፍ የተከፈተበት የሩብ ምዕተ ዓመት የትግልና የድል ጉዞ” በሚል ርዕስ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተገኑ ገነሞ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዓሉ በሌሎች ስኳር ፋብሪካዎችና የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችም በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ከየተቋማቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍሎች የተላከው መረጃ ያመለክታል፡፡

» ከገጽ 6 የዞረ

በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ

ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ ከስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለተውጣጡ 38 የፋይናንስ ሓላፊዎች እና ባለሙያዎች በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2008ዓ.ም ድረስ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ተሰጠ፡፡

የኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም እንደገለጹት የተሰጠው ሥልጠና ዋነኛ ዓላማ፣ በሀገሪቱ ሕጎች፣ በሂሳብ አያያዝ መርህ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) መሠረት የግልጽነትና ተጠያቂነት አሠራርን የተከተለ የኮስትና በጀት፣ የሂሳብ አያያዝ፣ የንብረት አመዘጋገብና አያያዝ እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ የፋይናንስ ሪፖርት ሥርዓት በመዘርጋት የማምረቻ ዋጋ ለማወቅ የሚያስችል የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡

አቶ ምስጌ ቢራራ

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም8

“የለውጡ የመጀመሪያው ዓላማ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍን ማስቀጠል ነው” አቶ በዛብህ ገብረየስ የስትራቴጂዊ ድጋፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ከመጋቢት 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ

የመዋቅር ለውጥ አድርጓል፡፡ የመዋቅር ለውጡን በተመለከተ

ከኮርፖሬሽኑ የስትራቴጂያዊ ድጋፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ከአቶ

በዛብህ ገብረየስ ጋር ጣፋጭ ዜና መጽሔት ቆይታ አድርጋለች፡፡

ጥያቄ፡- በኮርፖሬሸኑ ዋና መስሪያ ቤት በቅርቡ አዲስ የመዋቅር ለውጥ ተደርጓል፡፡ ለውጡን ለማድረግ ያስገደዱ ምክንያቶች ምን ነበሩ?

አቶ በዛብህ፡- ወደ መዋቅሮቹ ከመሄዴ በፊት መዋቅሮቹ መሠረት የሚያደርጉትን ሂደቶች መግለጽ ያስፈልጋል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት በመሠረታዊነት ሦስት ዋና ዋና /ወሳኝ/ የሆኑ የስራ ሂደቶች /ኮር ፕሮሰስ/ ያሉት ተቋም ነው፡፡ አንደኛው የኢንቨስትመንትና ልማት ነው፡፡ ይኸ በዋንኛነት በጥናት ላይ ተመስርቶ ለፋብሪካ የሚሆን ዲዛይን ከመስራት፣ ቦታ ከመምረጥ፣ ሕዝብን ከማንቀሳቀስ /ሞቢላይዝ ከማድረግ/

እና ፋብሪካውን ከመገንባት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን የሚሰራ የስራ ሂደት ነው፡፡

ሁለተኛው የሥራ ሂደት የምርት ወይም የኦፕሬሽን የሥራ ሂደት ነው፡፡ ኦፕሬሽንስ ውስጥ የፋብሪካ የስኳር ምርት ሂደቱ እንዳለ ሆኖ በምርት ሂደት ከእያንዳንዱ ከፊል ምርት እስከ ዋና ምርት ድረስ ባለው ሂደት የሚገኙት ልዩ ልዩ ተረፈ ምርቶች በራሳቸው የተለያየ ምርት የመሆን እድል ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ በኦፕሬሽንስ ውስጥ ተረፈ ምርትንም የምናይበት የስራ ሂደት ነው፡፡ እንደ ኤታኖል፣ ባጋስ፣ ሞላሰስ የመሳሰሉትን ተረፈ ምርቶች አንዳንዶቹ እንደወጡ ለገበያ የመዋል እድል ያላቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደገና ግብአት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ለስኳር ዋነኛ ግብአት የሆነው የአገዳ ተከላ እዚህ ውስጥ ይታያል፡፡ ስለዚህ የእርሻ ኦፕሬሽንም በዚህ ውስጥ ይታያል ማለት ነው፡፡ የእርሻ ኦፕሬሽን ለየት ያለ ባህርይ በግንባታ መጀመሪያ ምዕራፍም /በኢንስፔክሽን ፌዝ/ ሊታይ ይችላል፡፡ የመሬት ዝግጅትና የመጀመርያውም አገዳ ተከላ በኢንቨስትመንት እና ልማት ውስጥ ነው፡፡

ኦፕሬሽኑ እነዚህን ነገሮች ከያዘ የሚቀጥለው ወሳኝ የሥራ ሒደት ማርኬቲንግ ነው፡፡ ማርኬቲንግ እስካሁን በስኳር ኢንደስትሪአችን ንዑስ ዘርፍ ውስጥ የስኳር ማርኬቲንግን የሚመለከተው ሥራችን በአብዛኛው በሀገር ውስጥ የኮታ አሰራርን

ወቅታዊ

» ወደ ገጽ 9 ዞሯል

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 9

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

“የለውጡ የመጀመሪያው•••” » ከገጽ 8 የዞረ

በመጠቀም ምርት እና ፍላጎትን ማጣጣም ላይ የሚሠራው ሥራ ነው ጎልቶ ይታይ የነበረው፡፡

የስኳር ልማት ኢንደስትሪ ንዑስ ዘርፍ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ አመንጪና ተወዳዳሪ መሆን አለበት፡፡ ይህ በራዕያችን ላይም በቀጣዮቹ ዓመታት የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን አሟልተን ወደ ኤክስፖርት የምንገባበት ነው በሚል በግልጽ ተቀምጧል፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለማለፍ የማርኬቲንግ የሥራ ሒደት አደረጃጀት፣ የሰው ኃይል ምጣኔውና የሰው ኃይል ጥራቱ ኤክስፖርትን መሰረት ያደረገ ይሆናል፡፡

እንደ ጀማሪ ወደዓለም ዓቀፍ ገበያ ስንገባ ሰፊ ዝግጅት አድርገን ካልገባን ተወዳዳሪ መሆን አንችልም፡፡ የማርኬቲንግ አደረጃጀታችን በአጠቃላይ በዓለም ዓቀፍ ገበያ ውስጥ ገብቶ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ዓቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡፡

እነዚህ ሁሉ ተያያዥነት ያላቸው ሒደቶች ናቸው ብለን እናስቀምጥና ኢንቨስት እናደርጋለን፣ እናለማለን፣ እንሸጣለን፡፡ ለእነዚህ ሂደቶች ሁሉ ማዕከላዊ ሚና የሚጫወት የምርምር፣ ሥልጠናና ስርፀት ማዕከል ይኖራል፡፡ ይህም ምርምርን ማዕከል ያደረገ ዘላቂ የስኳር ኢንደስትሪ ልማት ማረጋገጥ ያስችላል፡፡ ማዕከሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ያመጣል፣ ያመጣቸውን ቴክኖሎጂዎች ያላምዳል፣ ካላመደም በኋላ ያስፋፋል፣ ካስፋፋም በኋላ ምርጥ የሆኑትን ያከማቻል፣ የተከማቹትን አዋጭነታቸውን እየፈተሸ በሀገር ውስጥ ዳግም ያስፋፋል፤ ወደ ውጭም ኤክስፖርት ያደርጋቸዋል የሚል ታሳቢን የያዘ ነው፡፡

በተጨማሪም ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ በዚህም የዩኒቨርሲቲ ወጣት ምሩቃንን ያሰለጥናል፣ በማዕከሉም እንዲመራመሩ ያደርጋል፣ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን ይለያል፣ ያዳቅላል እንዲሁም የስኳር መጠን የሚያሳድጉና ሌሎች ምርምሮችን ያደርጋል፡፡ የፋብሪካ ኦፕሬሽኑንም ይደግፋል፡፡

እነዚህን ሁሉ የስራ ሂደት ትንተናዎች ካየን መዋቅር በባህሪው መነሳት ያለበት ከስራ ሒደት ነው፡፡ በስራው ተፈጥሮአዊ ባህርይ ላይም ይመሠረታል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ

ችግሮችን ለመፍታት ሲባል የሚወሰድ የአደረጃጀት ማሻሻያ ይኖራል፡፡ እነዚህ እንዳሉ ሆነው ከዚህ ቀደም የነበረው አደረጃጀት ምን ይመስላል? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው መዋቅር ከላይ የተጠቀሱት የስራ ሂደቶች እንዳሉ ሆነው ነገር ግን ለአብነት የኢንቨስትመንትና ልማት ሒደትን ብናይ በውስጡ ንዑስ ሂደት/ሰብ ፕሮሰስ የምንላቸው/ መጋቢ የሆኑ የስራ ሂደቶቹ በተከታታይነት አንዱ ለሌላው በሚመግብ መልኩ ሳይነጣጠሉ መደራጀት ሲገባቸው የመስኖ ዘርፍ ለብቻው፣ አገዳ ተከላና ፋብሪካ ግንባታ ዘርፍ ለብቻቸው ሁለት ሆነው የተደራጁበት፤ በነዚህ ውስጥ ደግሞ የቤቶች ግንባታና የመስኖ መሠረተ ልማት ለብቻቸው፤ በተመሳሳይ በፋበሪካ ግንባታ የአገዳ ተከላ፣ የፋብሪካ ግንባታና የኮንትራት አስተዳደሩ ለብቻቸው ሆነው ተበትነው የነበሩበት ሁኔታ ታይቷል፡፡ በኦፕሬሽንም ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡ ግብይትንም ስንመለከት አንዱ ወገን ላይ ብቻ ነበር ያተኮረው፡፡ ኤክስፖርቱን አሳስቶ ነበር ያይ የነበረው፡፡ መዋቅሩም ጠባብ ነበር፡፡ ምርምርም በዋናነት እርሻ ላይ ነበር አትኩሮ ሲሰራ የነበረው፡፡

እነዚህን የተበታተኑ ሁኔታዎች ለማስተካከል አዲሱ አደረጃጀት አስፈላጊ ነበር፡፡ አዲሱ አደረጃጀት በዋናነት መዋቅሩን ከስራ ሒደት ጋር ተናባቢ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ በቀድሞው አደረጃጀትና አጠራር ለዋና ዳይሬክተር ተጠሪ የነበሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ 23 ተጠሪዎች ነበሩ፡፡ የአንድ ከፍተኛ የስራ መሪ ከፍተኛው የቁጥጥር አድማሱ ከስምንት መብለጥ የለበትም ከሚለው ዓለም አቀፍ የአደረጃጀት ሳይንስ ጥበብ አንጻር ሲታይ ቅቡል አልነበረም፡፡ ስለዚህ ይህንን ማስተካከል በዋናነት የተጠሪነትን ጉዳይ መቀነስ ሳይሆን ትልቁ ግቡ የስራ ሂደቶቹ የተሳለጡና እየተመጋጋቡ እንዲሄዱ ማድረግ ቀዳሚ ሆኖ እግረ መንገዱን ለዋና ስራ አስፈጻሚው ተጠሪ የሚሆኑ ክፍሎችን በዚያው ልክ የተመጠኑ እንዲሆኑ የማድረግ አቅጣጫን የያዘ ነው፡፡ ይህ ከስራ ሒደት አንጻር ሲታይ የነበረው ነው፡፡ ሌላው በመዋቅር ፍተሻ ጊዜ የታየው በ2003 ዓ.ም የተጠናው መሰረታዊ የስራ ሂደት

ለውጥ ጥናት ያስቀመጣቸው የስራ ሒደቶች በሳይንሳዊ መንገድ የተጠኑና ትክክለኛም የነበሩ ቢሆኑም ወደ መዋቅር ሳይመነዘሩ መሀከል ላይ ተቋርጠው መቅረታቸውን ነው፡፡ ተቋርጠው በመቅረታቸው ወይም ወደ አደረጃጀት ባለመመንዘራቸው የስራ ሒደትና /ፕሮሰስ/ የአደረጃጀት ትስስሩን አላልተውታል፡፡

መሰረታዊ የስራ ሂደቱን ወደ መሬት ማውረዱ በሳሳው ልክ በወቅቱ በነበረው የአደረጃጀት አነሳስ ላይ አዳዲስ ዘርፎች መጥተዋል፡፡ ጸደቁ ተብለው መተግበር ከጀመሩ በኋላም ስራው እየተፋጠነ፣ እየጨመረ ሲመጣ አዳዲስ ተለጣፊ መዋቅሮችም ተፈጥረዋል፡፡ ለምሳሌ በወቅቱ የነበረው የመስኖ ዘርፍ ይባል የነበረው መዋቅር በጣም ዘግይቶ የመጣ ነው፡፡

ሌላው የተፈጠረው መዋቅር ደግሞ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ይባል የነበረው አደረጃጀት ነው፡፡ ይህም በኋላ የተለጠፈ ነው፡፡ የአይቲ የስራ ክፍል በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የስራ ክፍሎች ስር እንዲደራጅ የተደረገበት ሁኔታም ነበር፡፡ በዚህ መልኩ በርካታ የተለጠፉ የሚመስሉ መዋቅሮች ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን ፍላጎትን መሰረት አድርጎ ቢሆንም የተጓዳኝ ዘርፍ የሚባለውም በኋላ የመጣ ነው፡፡

እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮች ሲታዩ መዋቅሩ ሳይንሳዊ የሆነ የስራ ሒደትን ተከትሎ የመሔድ ችግር ነበረው፡፡ በዚህ ውስጥ እነዚህ የመዋቅር ችግሮች የሚወልዷቸው የሰው ሀይል አመዳደብ፣ የደረጃ መዘበራረቅ፣ የደመወዝና የአበል መለያየትና እንዲሁም የቢሮ አጠቃቀም ችግሮች ነበሩ፡፡ ይህም ምስቅልቅል ሁኔታ መኖሩን ይጠቁማል፡፡

ከሁሉም በላይ ስራው ሒደቱን ተከትሎ ተናቦ መሄድ ባለመቻሉ የአሰራር ማኑዋሎችና ፕሮሲጀሮች አልነበሩም፡፡ ሁሉም ነገሮች መነሳት የነበረባቸው ከስራው ሒደት ሆኖ ሳለ፣ ነገር ግን ተቋማዊ ቁመናው ይነሳ የነበረው እነዚህን ካላገናዘበ መዋቅር ነበር፡፡

የቀድሞው መዋቅር ከፋብሪካዎችና ከፕሮጀክቶች ጋር የነበረው ተናባቢነትም አስቸጋሪ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የስራ ክፍሎች ወደ ፋብሪካና ፕሮጀክት ሲሄዱ የሚቀበላቸው ወ ይ ን ም » ወደ ገጽ 10 ዞሯል

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም10

የሚተሳሰራቸውም አካል የሌላቸው እንደነበሩ ጥናቶቹ ያሳያሉ፡፡

ከሁሉም በላይ መዋቅር ለውጡ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ኮርፖሬሽኑ እነዚህ በግልጽ የማይታዩ ከስራ ሒደት ጋራ የተጣበቁ እንዲሁም ከስልጣን ውክልናና ክፍፍል ጋር የተያያዙ ችግሮች ከሌሎች ኢኮኖሚዊ ችግሮች ጋር ተያይዘው ኮርፖሬሽኑን በከፍተኛ የመውደቅ አደጋ ላይ መጣላቸው ነው፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች በተጨማሪ ከፍተኛው አመራር “ኮርፖሬሽኑ የውስጥ አደረጃጀቱን፣ ቀጥሎ የአሰራር ሂደቱን ፈትሾ ከዚያም መመሪያና ማኑዋሎችን አውጥቶ የተማከለና ያልተማከለ አስተዳደራዊ ፍልስፍና ቢከተል ቢያንስ መስርያ ቤቱ እዳውን ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ ትርፋማ መሆን ባይችል እንኳን እንደተቋም መቀጠል ይችላል” ብሎ የሰጠው መሰረታዊ አቅጣጫ ነው ወደዚህ የመዋቅር ለውጥ ያመጣን፡፡

ጥያቄ፡- የመዋቅር ለውጡ ምን ምን ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል?

አቶ በዛብህ፡- የለውጡ የመጀመሪያው ዓላማ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍን ማስቀጠል ነው፡፡ ይህ ማለት ቀደም ሲል የነበሩ አስተሳሰቦችን መለወጥን የግድ ይላል፡፡ በማንኛውም የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ የሰው ሀብት ወሳኝ ነው፡፡ ይህ የሰው ሀብት ሰራተኛውን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን አመራሩንም የሚመለከት ነው፡፡

ለውጡ ሲጀመር አመራሩ በአመለካከቱ፣ በክህሎቱና በእውቀቱ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመው ለትርፍ ነው የሚለውን እና ስኳር ኢንደስትሪ ንዑስ ዘርፍ አገራዊ ልማትን ለማሳለጥ የሚሰራ የልማት ተቋም ነው የሚሉትን ሀሳቦች በውል ከመገንዘብ አንጻር ክፍተት ነበር፡፡

ለዚህም ማሳያዎቹ ለትርፍ እንደተቋቋመ ተቋም ስራን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መምራት፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግና ገቢ ለሚያሳድጉ ተግባራት ትኩረት በመስጠት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ዲሞክራሲያዊ ልማትን አንድ ላይ አድርጎ ይዞ በመሄድ ረገድም ክፍተት ነበር፡፡ ከሶስቱ ወደአንዱ ከተጋደለ ሌላው ይጎዳል ማለት ነው፡፡ እነዚህን ሚዛናዊ አድርጎ

ከመምራት ረገድም ችግሮች ነበሩ፡፡ ወደ የትኛው ይሄዳል የሚለውም በግልጽ የወጣ አልነበረም፡፡

በሌለ አቅም “ራሳችን እንሰራለን” ተብሎ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ለመጠቀም የተደረገው ሙከራ ያመጣው የራሱ የሆነ ችግር አለ፡፡ ስለዚህ ይህንን ለመቀልበስ የተቋሙ የኮንትራት አስተዳደር አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማደግ ይኖርበታል፡፡ አቅሙ ካደገ በኋላ ማንኛውንም ስራ በዚህ አግባብ ለመምራት ያስችላል፡፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁለት ነገሮች ተደባልቀው አይሄዱም፡፡

በመሰረታዊነት ሁለቱ ስራ ሒደቶቻችን ማለትም የኢንቨስትመንትና ልማት በጠንካራ የኮንትራት አስተዳደር ላይ እንመሰርታቸዋለን፡፡ እንደድሮው ስኳር ኮርፖሬሽን እየሄደ በራስ አቅም የሚሰራው ስራ አይኖረውም፤ ቢኖረውም በእጅጉ የተመጠነ ይሆናል፡፡ ይህ ለኪራይ ሰብሳቢነት የመጋለጥ አደጋን ይቀንሳል፤ የገንዘብ ብክነትን በከፍተኛ ሁኔታ መከላከል ያስችላል፤ በሌላ ጎኑ አገራዊ የመፈጸም አቅምንም ያጎለብታል፡፡ ለዚህ መንገድ የሚከፍት ለውጥ ነው በኮርፖሬሽኑ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ለውጡ በሁለተኛ ደረጃ የቴክኒካል እና የፕሮሰስ ችግሮችን ይፈታል፤ የተሳለጠ ግንኙነትን ያመጣል፤ ውክልናን ያወርዳል፤ ስራዎች በፍጥነት የመወሰን እድላቸውን ያሰፋል፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም ይፈታል፡፡

ጥያቄ፡- ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት ከፊቱ የተጋረጡ ፈታኝ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው? እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡ መፍትሄዎችን ቢገልጹልን?

አቶ በዛብህ፡- እነዚህ ስራዎች ሲሰሩ ኮርፖሬሽኑ ከፊቱ የተጋረጡ ፈታኝ ሁኔታዎች አሉበት፡፡ ከነዚህ መካከል አንዱ ውስጣዊ አቅሙ የሳሳ መሆኑ ነው፡፡ አንደኛው ከኮንትራት አስተዳደርና ከፕሮጀክት አመራር አንጻር የማስፈጸም አቅም ክፍተቶችና ከኋላ ተያይዘው የመጡ ያደሩ ፕሮጀክቶችን አቃንቶ ለማስቀጠል ያጋጠሙ ፈተናዎች ሲሆኑ፤ ሌላው ደግሞ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም የሚያስችል የግብዓት አቅርቦት፣ በነባር ፋብሪካዎች የባለሙያ ፍልሰት፣ የአመራርና የማህበረሰብ

ችግሮች፣ የማምረቻ ወጪ መናር ወዘተ ክፍተቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ችግሮች ፈጥነን ለመውጣት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችን ተከትሎ መስራትን ይጠይቃል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከተጋረጡበት ችግሮች ሁለተኛውና ትልቁ የእዳዎች መብዛትና እዳውን ለመክፈል የስኳር ልማት ፈንድ በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመሆኑ ነው፡፡

ሶስተኛው ችግራችን በጅምር ላይ ያሉ በአገር በቀሎችም ሆነ በውጭ ተቋራጮች በመገንባት ላይ የሚገኙት ፋብሪካዎች በአብዛኛው በተለያዩ ምክንያቶች በተቀመጠላቸው መርሐ ግብር መሰረት መጠናቀቅ አለመቻላቸው ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በቶሎ ከዘርፉ ያሰብነውን ገቢ ማግኘት አልቻልንም፡፡

ሌላው ትልቁ ችግር ኮርፖሬሽኑ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀስ እንደመሆኑና ኢንደስትሪው ውስብስብ ገፅታ ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም አካባቢዎች የመሰረተ ልማት በተገቢው ሁኔታ ተሟልቶ አለመገኘት ነው፡፡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የሚፈልጉት ገንዘብ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በዚህ ረገድ ያሉት ችግሮች በጣም እየጎዱን ይገኛሉ፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡት አቅጣጫዎች በአጭር ጊዜ የኮርፖሬሽኑን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በተለመደው የኦፕሬሽን እቅድ መሄድ ማቆም ነው፡፡ ለዚህም አዳዲስ የማሻሻያ ፓኬጆችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ዋና ዋና ፓኬጆቹም፡-1. የማስፈጸም አቅም ግንባታ

ፓኬጅ፡- በዚህ ፓኬጅ የሰው ሀብት ልማታችን ቅድሚያውን ይይዛል፡፡ ይህ በሁለቱም እርከኖች ማለትም በአመራሩና በፈጻሚው በኩል ያሉትን ያካትታል፡፡ ይህም ከአመለካከት፣ ከክህሎትና ከእውቀት አንጻር የሚታይ ሆኖ ስራውም ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ይህንንም ለማድረግ አንደኛ የአንድ ለአምስትና ካይዘን ልማት ቡድኖች አደረጃጀቶችን የሚጠቀም ሲሆን፣ ሁለተኛው በቀጣናዊ ትስስር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ያለው ግንኙነት

“የለውጡ የመጀመሪያው•••” » ከገጽ 9 የዞረ

» ወደ ገጽ 11 ዞሯል

ወቅታዊ

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 11

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ነው፡፡ ሦስተኛው የምርምርና ስርጸት ማዕከል ለዚሁ ተግባር የሚጠናከርበት ነው፡፡ የሴክተሩን የዕውቀት ባንክ በዘላቂነት ለማልማትም ከኮርፖሬሽኑ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የወጡ ባለሙያዎችን መልሶ በመንግስትና በግሉ ሴክተር ሽርክና አግባብ (Pubic private partnership/PPP) መጠቀምም ይታያል፡፡

2. የአሰራር ስርአት ማሻሻያ ፓኬጅ፡- ይህ ስርአት አራቱንም የስራ ሒደቶች የሚመለከት ይሆንና እንደተለመደው ከዕለት ተዕለት የኦፕሬሽን ስራዎች ባሻገር የተመረጡ ፕሮጀክቶችም በዚህ ውስጥ የሚካተቱበት ነው፡፡ በመሰረታዊነት ሁሉም አሰራሮች ሀብት ማመንጨት፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን መታገል በአጠቃላይ ኮርፖሬሽኑን ትርፋማ ማድረግ የሚያስችሉ ናቸው፡፡

3. የኮርፖሬት አስተዳደር (ገቨርናንስ) እና መልካም አስተዳደር ፓኬጅ፡- ይህ በአጠቃላይ ውጤት በሚያመጣ መልኩ የዜጎች ቻርተር ተቀርጾ ተአማኒነትን ለመፍጠር የሚያስችል ነው፡፡ ሁለተኛ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን በግልፅነትና በተጠያቂነት መርሕ የሚፈታበት፣ የስነ ምግባር እሴቶች የሚገነባበት፣ ለዚህም ራሳቸውን የቻሉ የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮች የሚፈጠሩበት እንዲሁም ኪራይ ሰብሳቢነትን መታገል ሳይችሉ ሰለባ የሆኑ ካሉ ወደፍርድ የማቅረብ ሒደት የሚታየበት ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ይመጣበታል ተብሎ ይታሰባል፡፡

4. የግብአት አቅርቦትና የንብረት አስተዳደር ፓኬጅ፡- ይህን በአስተዳደራዊና በኦፕሬሽን ብሎ በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል፡፡ አስተዳደራዊውን ስንመለከት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙትን የኮርፖሬሽኑን ንብረቶች በትክክለኛው የመንግሥት የንብረት አያያዝና አስተዳደር መዝገብ መመዝገብ፣ አጠቃቀማቸውን መመርመር፣ ኮምፒተራይዝድ የሆነ ዳታ ቤዝ መመስረት፣ የሚወገዱ ንብረቶችን ለይቶ የሚወገዱበትን ስርአት ማበጀትና የሚሸጡትን መሸጥ የሚቻልበት ስርአት የሚፈጠርበት ነው፡፡ ይህ በመሰረታዊነት ኮርፖሬሽኑ

ያሉበትን በጣም የተዘበራረቁ ነገሮች የሚያስተካክል ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ የራሱን ሕንጻ የሚገነባበት ሁኔታም በዚህ ፓኬጅ ይታያል፡፡

5. የኦፕሬሽን፣ የጥገናና የፋብሪካ ግብአት አቅርቦት ፓኬጅ ፡- የፋብሪካ ግብአት አቅርቦትን በሚመለከት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ እስከ ኦፕሬሽን ድረስ በከፍተኛ ቅንጅትና በመሪ እቅድ የሚመራበት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የተበጣጠሱ እቅዶችን ይዘን የምንሰራበትን አሰራር የምንቀይርበት ነው፡፡ በፋብሪካዎች ኦፕሬሽን ላይ ስታንዳርዳይዜሽን በከፍተኛ ደረጃ የምናመጣበትም ይሆናል፡፡ ወደ አለም አቀፍ አሰራር የሚወስደንና የማምረቻ ወጪ ቅነሳ እንደ አንድ ፕሮጀክት ተይዞ የሚሰራበት እንዲሁም በሰው ሀብት ልማቱ ውስጥ ከተቀመጠው በተጨማሪ ልምድ ያላቸውና ከመስሪያ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች የወጡ ባለሙያዎች ተሰባስበው ምናልባትም የስኳር ባለሙያዎች ማህበር አደራጅተው ከውጭ የሚመጣውን አማካሪ ተክተው መስራት የሚችሉበትን ሁኔታዎች የሚያይም ፓኬጅ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በፋብሪካዎች ያሉ ብክነቶችን ማስወገድ የሚቻልባቸውንም አሰራሮች ያካትታል፡፡

6. የኢንቨስትመንትና ልማት ፓኬጅ፡- በዚህ ውስጥ በመሰረታዊነት የፕሮጀክትና የኮንትራት አስተዳደር አቅም የሚገነባበት ነው፡፡ በለውጥ ሰራዊት አግባብ አገር ውስጥ ካሉና ከኮርፖሬሽኑ ጋራ ከሚሰሩ መንግስታዊ ባለድርሻ አካላት ጋራ በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን በማሳደግ እግረ መንገዱን አቅም እየተገነባ የሚኬድበት ነው፡፡ ሁለተኛ በመደበኛ የኮንትራት አመራርና አስተዳደር ስልጠናዎች ለአመራሩና ለሰራተኛው ይሰጣሉ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ተዝረክርከው የቆዩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በውጤት የሚጠናከሩበት ሁኔታ የሚመቻችበት ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊያዙ የማይገቡትን ማስወጣት፣ የሚያዙትን ደግሞ አጠናክሮ መቀጠልን ያካትታል፡፡ ከዚህ አኳያ በእንጥልጥል ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን የማነሳሳት ስራዎች የሚሰሩበት ነው ማለት ነው፡፡

7. የማሽነሪ ጥገናና ቴክኒክ አቅምን ማሳደጊያ ፓኬጅ፡- በዚህ ስር

በስኳር ኮርፖሬሽን ያሉት ማሽኖች ከሁሉም የአለም ክፍሎች የመጡ፣ በአይነታቸው እጅግ በጣም ብዙ፣ የዚያኑ ያህል የተለያየ አይነት መለዋወጫ የሚፈልጉ በመሆናቸው ወጥ ያልሆነ የመለዋወጫ ግዥ ስርዓት ያላቸውና ለአስተዳደር አስቸጋሪ የሆኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም ይህንን ስታንዳርዳይዝ አድርጎ ወደ አንድ ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ ማሽኖችን ለኦፕሬሽን በሚሆን መልኩ መመዝገብና ያሉበትን ሁኔታ ለይቶ የሚጠገኑትን መጠገን፣ የሚወገዱትን ማስወገድ የመሳሰሉ ስራዎች የሚሰሩበት ፓኬጅ ነው፡፡ የማሽነሪ ስምሪትን በሚመለከትም አጠቃላይ መመሪያና አሰራር የሚዘረጋበት ይሆናል፡፡

8. የኮርፖሬት አስተዳደር (ገቨርናንስ) እና ፋይናንስ ሪፎርም ፓኬጅ፡- አንደኛ የፋይናንስ ስርአቱ ያሉበት ክፍተቶች የሚታይበት ነው፡፡ ክፍተቶቹ ከተለዩ በኋላ እነዚህን የሚደፍኑ ራሳቸውን የቻሉ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ የሚደረጉበት ነው፡፡ አካውንትስ፣ ኢንተርናሽናል ፋናንሺያል ሪፖርቲንግ ሲስተም የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ኦዲት ያልተደረጉ ሂሳቦችን ኦዲት ማስደረግና ዝግጁ የማድረግ ስራዎችም ይኖራሉ፡፡ ይህ በአጠቃላይ የኮርፖሬሽኑን የፋይናንስ አያያዝ ሥርዓት የሚቀይር ነው፡፡

ይህ የሚነግረን መስሪያ ቤቱ ሁለንተናዊ ወደሆነ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ይገባል ማለት ነው፡፡ ከዚህ ተግባር ጎን ለጎን መደበኛ የኦፕሬሽን ሥራዎችን ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡ ለዚህ የአመራሩና የፈጻሚው እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት፣ የግል ጥቅማ ጥቅምንና የመሳሰሉ መብቶችን ከማስከበር በላይ የሆነ አመለካከትን ማዳበር፣ ኮርፖሬሽኑ ውጤታማ ሲሆን ከውጤቱ እጠቀማለሁ የሚል አመለካከት መያዝ ከአመራሩም ከሰራተኛውም ይጠበቃል፡፡

እነዚህ የማሻሻያ ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በኩል ተግባራዊ የሚደረጉ የማስፈጸም አቅም ግንባታ እቅዶችን የመጋራትና ከዚያም ተጠቃሚ የመሆንን አጋጣሚ ታሳቢ አድርገን ነው የምንሰራው፡፡

በ አ ጠ ቃ ላ ይ » ወደ ገጽ 12 ዞሯል

“የለውጡ የመጀመሪያው•••” » ከገጽ 10 የዞረ

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም12

መንግሥት ልዩ ልዩ ከአቅም በላይ በሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ምክንያት እየተንገዳገደ ያለውን የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ለማንቀሳቀስ እስካሁን እንዳደረገው ሁሉ በቀጣይም መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሊያደርግ የሚገባው መሆኑን በታሳቢነት እንወስዳለን፡፡ የፖሊሲ አመራር ድጋፍም እንፈልጋለን፡፡

እነዚህ የአመራር ድጋፎች በመሰረታዊነት ቀደም ሲል በራሳችን ሁሉን ነገር እንሰራዋለን ከሚለውም ወጣ ያለ ምናልባትም ስራዎችን ከሌሎች አካላት ጋር በጋራ የምንሰራበትን እድል በፖሊሲ መልክ የሚታይበት ሁኔታ ይፈጥራል ብለን እናስባለን፡፡ እኛም ሀሳቡን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ሌላው ከሕዝብ ክንፉ በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉን ማህበራዊ ግንኙነቶች የተሻሻሉ እንዲሆኑ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች አብረውን ይሰራሉ የሚለውን ታሳቢ እናደርጋለን፡፡

የፌደራልና የክልሎች የልማት ተቋማት ማለትም የመስኖ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮሚዩኒኬሽን፣ የቤቶች፣ የመንገድ የመሳሰሉ ተቋማት እንደ መንግሥት ክንፍ አብረውን ይሰራሉ፡፡ እንዲሁም ያለብንን የፋይናንስ ክፍተት በመቻቻልና በአገራዊ እይታ በማየት አብረውን ተጋግዘው ይሄዳሉ የሚል ታሳቢም እንይዛለን፡፡

ሲጠቃለል በምጣኔ ሀብት፣ በማሕበራዊና በፖለቲካ ሚዛናዊ የሆነ የስራ አመራር ፍልስፍና ይዘን ልማታዊ ትርፋማነትን እናረጋግጣለን ብለን ነው የምንሰራው፡፡

ጥያቄ፡- የኮርፖሬሽኑ አመራር በቅርቡ በኮርፖሬሽን ደረጃ ከተቋቋመው የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል? ከማህበሩስ ምን ይጠበቃል?

አቶ በዛብህ፡- በሁሉም ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ቀደም ሲል ያልነበረ መሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር እንዲቋቋም ኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ማህበሩንም እንደ ትልቅ አቅም ነው የሚቆጥረው፡፡

ማህበሩ በቅርጹና በይዘቱ ልማታዊ የሆነ ማህበር ነው ብለን ከጅምሩ ልንናገርለት እንችላለን፡፡ ለዚህ እንደ ማሳያ የሚሆነን በህብረት ስምምነት ድርድር ወቅት በአገሪቱ የህብረት ስምምነት ድርድር ሒደት ያልተለመደ ሚዛናዊ የሆነ አስተሳሰብና አመለካከት የያዘ እንዲሁም ቅድሚያ ለተቋሙ የሚል ቁርጠኝነት ያለው መሆኑን በማየታችን ነው፡፡ ማህበሩ እንደቀድሞው “አሰሪና ሰራተኛ አይጥና ድመት” የመሆን አካሄድን አለመምረጡን ኮርፖሬሽኑ በእጅጉ ያደንቃል፡፡

ማህበሩ ልማታዊ የሆነውን አካሄድ እስከመረጠ ድረስ በማንኛውም ጉዳዮች አብረን እንሰራለን፡፡ አሁን በገጠሙን ችግሮቻችን ላይም ግልጽ ውይይት አድርገናል፡፡ ከማህበሩ ጋር ያለን ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን አመራሩ እንደ ተጨማሪ አቅም ቆጥሮ ነው እየተንቀሳሰቀሰ ያለው፡፡ አንዳንድ ግን የግል ጥቅማቸውንና ምናልባትም ከአደረጃጀት ማሻሻው ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም የነበራቸው አልባሌ ጥቅሞች ይቀሩብናል ከሚል ስጋት የተነሳ የተወሰኑ ሰዎችን የሚያንቀሳቅሱ ጥቂት አካላት ይኖራሉ የሚል ግምት አለን፡፡

ዋናው ጉዳይ እነዚህ አስተሳሰቦችና አካላቱ ልማታዊ ጉዞውን በሚያደናቅፍ አግባብ ሊሄዱ አይገባም የሚለው ነው፡፡ ይህንን እስካልነኩ ድረስ ሀሳባቸውን የመግለጽ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እናከብራለን፡፡

ለማህበሩና ለኮርፖሬሽኑ ማዕከላዊ ሆኖ የሚያገለግለው የሕብረት ስምምነት መጽደቁ ትልቅ ጥቅም ነው፡፡ ነገር ግን ሕብረት ስምምነት ጸደቀ ተብሎ ውጤት በሌለበት ጥቅማ ጥቅሞችን አላግባብ መጠየቅ ደግሞ ትክክል አይሆንም፡፡ ጥቅማ ጥቅሞችን ከመጠየቅ በፊት “ምን ሰራን? ኮርፖሬሽኑ ምን ተጠቀመ? የፋብሪካዎቹ ገቢ ምን ያህል አደገ?” ብሎ ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ኮርፖሬሽኑ ከተጋረጠበት ችግር ለማውጣት ከስኳር ፋብሪካዎች፣ ከፕሮጀክቶችና ከዋናው መስሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ምን ይጠበቃል?

አቶ በዛብህ፡- ኮርፖሬሽኑን ከተጋረጠበት ችግር ለማውጣት የፋብሪካዎች፣ የፕሮጀክቶችና የዋናው መስሪያ ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በዋናነት ከላይ የተገለጹትን የማሻሻያ ፓኬጆች ከዋና መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር በሙሉ ልብ መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተጨማሪ ቀደም ሲል ከነበረው ትንሽ የተዝናና እና ለቀቅ ያለ የወጪ አወጣጥ ሥርዓት መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በአመለካከትም “ለውጥ የሚመጣው ሰራተኛና አመራር ተደጋግፎ ሲሄድ ብቻ ነው” የሚለውን መውሰድና ይህንንም በመልካም አስተዳደር ማረጋገጫና ማስፈኛ መሳሪያዎች አግዞ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ ካይዘንን ከአገራችን የስራ ባህል ከሆነው ደቦና በፋብሪካዎች ካለው ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ጋራ አዋዶና አጣጥሞ መምራትን ይጠይቃል፡፡

“የለውጡ የመጀመሪያው•••” » ከገጽ 11 የዞረ

ወቅታዊ

“መዋቅሩ ሳይንሳዊ የሆነ የስራ ሒደትን ተከትሎ የመሔድ ችግር

ነበረው፡፡ በዚህ ውስጥ እነዚህ የመዋቅር ችግሮች የሚወልዷቸው የሰው ሀይል አመዳደብ፣ የደረጃ መዘበራረቅ፣ የደመወዝና የአበል

መለያየትና እንዲሁም የቢሮ አጠቃቀም ችግሮች ነበሩ፡፡

ይህም ምስቅልቅል ሁኔታ መኖሩን

ይጠቁማል፡፡” አቶ በዛብህ ገብረየስ፡ የስትራቴጂዊ ድጋፍ ምክትል ዋና

Page 13: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 13

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦ ካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህን ኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማነቱን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡

በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚ አየር ንብረት፣ በመሰኖ ሊለማ የሚችል ሰፊ የእርሻ መሬት (ከ500ሺ ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት በመሆኑ ዘርፉ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግሥት የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚከተለው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በወንጂ ሸዋና መተሓራ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪ በተለይም ከ2003ዓ.ም ወዲህ በደቡብ ብ/ብ/ሕ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡

በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት ይህ ኢንዱስትሪ ስኳር ከማምረት ጎን ለጎን ተረፈ ምርቶቹን ለሃይል ማመንጫ (ከባጋስ)፣ ለእንስሳት መኖ (ከሞላሰስ)፣ ለነዳጅ (ከፓወር አልክሆል፤ ኤታኖልን ከቤንዝል ጋር በማደባለቅ)፣ ለማዳበሪያ (ከፊልተር ኬክና ቪናስ)፣ ለወረቀት መስሪያ (ከባጋስ)፣ ለህክምና (ከቴክኒካል አልክሆል)፣ ለአልክሆል መጠጥ (ከሬክቲፋይድ አልክሆል)፣ ለቀለም መስሪያ

(ከሞላሰስ)፣ ለብርጭቆ መስሪያ (ከቦይለር አሽ) ወዘተ አገልግሎቶች ያውላል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 62 ዓመት ገደማ በላንድሮቨር መኪና በየገበያው በመዘዋወር ስኳርን ለማስተዋወቅ ብርቱ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡ በወቅቱ ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡

በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ ታሪኩን በመቀየር ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለችው ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት ሆኗል፡፡ በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት ከ1943ዓ.ም አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሥራውን የጀመረው ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በወንጂ ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946ዓ.ም ስራ አስጀምሯል፡፡

በመቀጠልም በ1955ዓ.ም እዛው ወንጂ ላይ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡ ወንጂ ሸዋ

ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750 ሺህ ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንጂና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ካገለገሉ በኋላ በእርጅና ምክንያት እንደ ቅደም ተከተላቸው በ2004ዓ.ም እና በ2005ዓ.ም መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣ በምትካቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል።

በኢትዮጵያ የስኳር አዋጭነትን የተረዳው የሆላንዱ ኩባንያ በተመሳሳይ የመተሓራ ስኳር ፋብሪካን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መርቲ ከተማ ሰኔ 26 ቀን 1957ዓ.ም በአክሲዮን መልክ በመመስረት በ1962ዓ.ም ፋብሪካውን ሥራ አስጀመረ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በፊንጫኣ ሸለቆ በ1967ዓ.ም በተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት አካባቢው ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ በመገኘቱ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ተገንብቶ በ1991ዓ.ም ማምረት ጀመረ፡፡

ሀገሪቱ ለስኳር ልማት ያላትን ምቹ ሁኔታ የተረዳው የኢፌዲሪ መንግሥት ልማቱን ለማስፋፋት በማቀድ በአፋር ክልል በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ ያለውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98 አቋቋመ፡፡ ፋብሪካው በ50

የመስኖ መሰረተ ልማት በወንጂ ስኳር ፋብሪካ

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ

» ወደ ገጽ 14 ዞሯል

የማህበረተስብ ተጠቃሚነት በኦሞ ኩራዝ

Page 14: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም14

ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀም ሲሆን፣ በዓመት 6 ሚሊዮን 190 ሺ ኩንታል ስኳር እና 63 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል እንዲያመርት ታቅዶ የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ የሙከራ ምርት አምርቷል፡፡

ምንም እንኳ የስኳር ኢንዱስትሪው ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም፤ የስኳር ልማቱ በሚፈልገው ፍጥነት አለማደግ፣ ሀገሪቱ በተከታታይ እያስመዘገበች ካለቸው ፈጣን የኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣት፣ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች የሚያመርቱት የስኳር መጠን እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ማርካት አለመቻል፣ የሕዝብ ቄጥር ማደግ እና ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ከመስፋፋት ጋር ተያይዞ የስኳር ፍላጎትና አቅርቦት ሊጣጣም አልቻለም፡፡

ከዚህ አንጻር መንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም በየአመቱ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ ሀገር እያስገባ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ክፍተቱን ለመሙላት ስኳር ከውጭ መግዛት ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑና በዚህ ሁኔታም መቀጠል ስለማይቻል ከመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አንስቶ በሀገራችን ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንዱ የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሊሆን ችሏል፡፡

መንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም ከሚያደርገው ርብርብ ባሻገር በዘርፉ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ በተለይም በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ከመገንባት አንስቶ “የስኳር አብዮት” በሚያስብል ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች ከፍተኛ መዋለ ነዋይ የወጣባቸውን መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የወንጂ ሸዋና የፊንጫኣ ነባር ስኳር ፋብሪካዎችን በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ተችሏል፡፡ በማስፋፊያ ሥራዎች አማካይነትም ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠንን በ2002ዓ.ም መጨረሻ ከነበረበት 2 ሚሊዮን 903 ሺ 740 ኩንታል በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (2007ዓ.ም) ወደ 4 ሚሊዮን ኩንታል አድጓል፡፡

በሌላ በኩል የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ማስጀመር የተቻለውም በዚሁ የመጀመሪያ እቅድ ዘመን ነበር፡፡ ምንም እንኳ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ፋብሪካውን ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ውስጥ ማስገባት ባይቻልም የሙከራ ምርት ለማስጀመር ግን ተችሏል፡፡ በቀጣይም ፋብሪካውን ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ለማስገባት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

የአገዳ ልማትን በተመለከተም በዕቅድ ዘመኑ ተጨማሪ 65ሺ 363 ሄክታር መሬት በአገዳ ለምቷል፡፡ ይህም በእቅዱ መነሻ ከነበረው 30ሺ 397 ሄክታር ጋር ሲነጻጸር የ215 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የኤታኖል የምርት መጠንም በ2002ዓ.ም ከነበረበት 7 ሚሊዮን 117 ሺ ሊትር በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ወደ 19 ሚሊዮን 804 ሺ ሊትር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ 18 ሚሊዮን 480 ሺ ሊትር ከቤንዝል ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ እንዲሁም በሃይል ማመንጨት ረገድ የወንጂ ሸዋና ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች ካመነጩት ሃይል ውስጥ ለራሳቸው የሚያስፈልጋቸውን ሃይል ተጠቅመው የተረፋቸውን 31 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ ብሔራዊ የሃይል ቋት ማስገባት ጀምረዋል፡፡

የአገዳ ምርታማነትን ያሳደጉ በርካታ የምርምር ሥራዎችም የተከናወኑ ሲሆን፣ የጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር ዳም) እና የውሃ መቀልበሻ (ዊር)፣ የሰፋፊ መስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የቤቶች እና የግዙፍ አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንዲሁም የመሬት ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተካሂደዋል፡፡ ልማቱን ተከትሎም አነስተኛ ከተሞችና በርካታ መንደሮች ተመስርተዋል፡፡

በማህበረሰብ ተጠቃሚነት ረገድም በርካታ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ ወፍጮ ወዘተ) እና የመሰረተ ልማት አውታሮች (ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ) ተገንብተው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተጠቃሚ በመሆን የኑሮ ደረጃቸው መሻሻል ጀምሯል፡፡ እንዲሁም ለአካባቢው ተወላጆች ልጆች ቅድሚያ

ወቅታዊ

» ወደ ገጽ 15 ዞሯል

የማህበረተስብ ተጠቃሚነት በተንዳሆና ኦሞ ኩራዝ

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ... » ከገጽ 13 የዞረ

Page 15: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 15

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

በመስጠትና በትራክተር ኦፕሬተርነት፣ በግምበኛነት፣ በአናጺነት፣ በጥበቃና በመሳሰሉት ሙያዎች በማሰልጠን በየፕሮጀክቶቹ ተመድበው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡

የአካባቢው ወጣቶችም በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው በልማቱ ስራ ውስጥ እንዲሳተፉና ገቢ እንዲያገኙ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በመስኖ የለማ መሬት ለአካባቢው ነዋሪዎች አመቻችቶ በማስረከብ በተለይም በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢ የሚገኘው ማህበረሰብ እንደ በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎችን አምርቶ እንዲጠቀምና በቀጣይም በዘላቂነት ሸንኮራ አገዳ አልምቶ ለፋብሪካ እንዲያቀርብ ለማስቻል በወንጂ አካባቢ አገዳ ከሚያበቅሉ አርሶ አደሮች (አውት ግሮወርስ) ልምድ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

በስራ ዕድል ፈጠራም ባለፉት አምስት ዓመታት በስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች ከ350ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንትራት የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት ባይቻልም እንኳ፣ በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ በ2016ዓ.ም በዓለም ላይ ከሚገኙ 10 ከፍተኛ የስኳር አምራች

ሀገሮች ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መደላድሎችን ለመፍጠር ተችሏል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመንም ተንዳሆን ጨምሮ በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች የሚገኙ ስምንት አዳዲስ ፋብሪካዎችን ማለትም የኦሞ ኩራዝ 1፣ 2፣ 3 እና 4፤ የጣና በለስ 1 እና 2 እንዲሁም የወልቃይት ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ አጠናቆ ስራ ለማስጀመር ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በማጠናቀቂያ ምእራፍ ላይ ይገኛል፡፡ በእነዚህ መጠነ ሰፊ ሥራዎች አመታዊ የስኳር መጠንን በማሳደግ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማርካት ባሻገር ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ታቅዷል፡፡ የሸንኮራ አገዳ ልማትን ከማስፋፋት አኳያም በዕቅድ ዘመኑ 211 ሺ 564 ሄ/ር በመትከል በ2012ዓ.ም መጨረሻ በአገዳ የተሸፈነውን መሬት 307ሺ 324 ሄክታር ለማድረስ ነው የታቀደው፡፡

በተጨማሪም በኤታኖል ምርት፣ በሃይል አቅርቦት፣ በመስኖ መሰረተ ልማትና በቤቶች ግንባታ ረገድ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመስራት ታቅዷል፡፡ የህብረተሰቡን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ከማሳደግ አኳያም

በእቅድ ዘመኑ ልማቱ በሚፈጥረው የስራ ዕድል በቋሚነት፣ በጊዜያዊነት፣ በኮንትራትና በማህበራት ከ637 ሺ በላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡

በአጠቃላይ ጥቅምት 2003 ዓ.ም ተቋቁሞ የዘርፉን ልማት እየመራ የሚገኘው የስኳር ኮርፖሬሽን የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት የስኳር ልማቱ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቦችን የልማት ተጠቃሚ በማድረግ፣ የተለያዩ የመሠረተ ልማት አውታሮችና ማህበራዊ ተቋማትን በመገንባት፣ መጠነ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ ልማት በማካሄድና ከፍተኛ የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም ማረጋገጡን ማየት ቢቻልም፤ የፋብሪካ ቁጥር፣ ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶችን በማሳደግ ረገድ ገና ብዙ ሥራ መስራት እንደሚገባ መገንዘብ ተችሏል፡፡

ከዚህ አንጻር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ኮርፖሬሽኑ የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ለውጦችን ማድረግ እንዳለበት በመንግሥት ታምኖበታል፡፡ ከእነዚህ ለውጦች መካከል ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስችል አዲስ አደረጃጀት መፍጠር አንዱ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ኮርፖሬሽኑ የስኳር ልማትን በሀገሪቱ በስፋት ለማካሄድ በሚያስችል በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ወቅታዊዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ... » ከገጽ 14 የዞረ

ቤቶች ልማት የመስኖ ዋና ቦይ -ተንዳሆ

Page 16: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም16

ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ…

ቆይታ

ሰው ከተሰጡት የተፈጥሮ ችሮታዎች መካከል አንዱ ጠያቂነት ነው፡፡ ዘወትር ይጠይቃል፤ ለምን? ምን? እንዴት? መቼ? የት? ማን? እያለ፡፡ ለዚህ የጠያቂነት ተሰጥዖው ደግሞ ምላሽን እራሱ ይፈልጋል፤ በምጡቅ አዕምሮው ያሰላስላል፤ መፍትሄም ያበጃል፡፡ ይህ ደግሞ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን መስተጋብር ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ደግሞ መጪው የተሻለ እንዲሆን የሚያስችለው ምጡቅና ረቂቅ ተሰጥዖ ነው፡፡

እንዲያም ሆኖ ተፈጥሮ ያላሰበችውን ታላቅና ውስጣዊ ሀይል የሚያበራ ወይንም የሚያጨልም አዎንታዊ ወይንም አሉታዊ አመለካከት ይታገሉታል፡፡ አዎንታዊ አመለካከትን የተላበሰ የጠያቂነትና መፍትሄ የማፈላለግ ሀይሉ ይገዝፋል፡፡ ከእራሱ አልፎ ለአካባቢው መድህን ይሆናል፡፡ አሉታዊ አመለካከት ደግሞ የጨለምተኝነት አስተሳሰብን ይወልዳል፡፡ ይህ ደግሞ የራስን፣ የአካባቢን፣ ብሎም የሀገርን እጣ ፈንታ ጐስቋላ ያደርጋል፡፡ አዕምሮዬ በማለዳ ይህንን እያብሰለሰለ ከማሳ የሚቀርብለትን ሸንኮራ አገዳ እየፈጨ፣ እየጨመቀ እንዲሁም እያጣራ ወደ ስኳርነት ወደሚቀይረው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ እየተጓዝኩ ነው፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች በማለዳ ወደ ሥራ ገበታቸው ፈጥነው ሲሄዱ “ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ በዋለበት ሜዳ አይቀርም ማፍራቱ” የተሰኘውን ዜማ አስታወሰኝ ፡፡በዚሁ ማለዳ ወደ ፋብሪካው የፋብሪኬሽን ወርክሾፕ አቀናሁ፡፡ የክፍሉ ሠራተኞች የዕለት ተግባራቸውን ማልደው ጀምረዋል፡፡ ወደ ወርክሾፑ ያመራሁት የፈጠራ ባለቤት ከሆኑት አቶ ደምረው ደገፉ ጋር ቃለ ምልልስ ለማድረግ ነበር፡፡

አቶ ደምረው በፋብሪካው የቴክኒክ ክፍል ለ12 ዓመታት በመካኒክነት አገልግለዋል፡፡ እኚህ ባለሙያ ፋብሪካው ገጥሞት የነበረውን የመበየጃ ማሽን ችግር ለመቅረፍ በጠያቂነት አስተሳሰብ የራሳቸውን ዘዴ የፈጠሩ ሰው ናቸው፡፡ የፈጠራ ሥራቸውን እየቃኘሁ እንዴት እንደተነሳሱ፣ ምን እንዳከናወኑ ጠየኳቸው፡፡ እሳቸውም በትሁት አንደበታቸው እንዲህ በማለት አወጉኝ፡፡

ጊዜው የ2007 ዓ.ም የፋብሪካ ጥገና ወቅት ነበር፡፡ የፋብሪካውን የጥገና ሂደት በጥራትና

በሲሳይ ደርቤ

የአቶ ደምረው አካልና አዕምሮ አሁንም እየተጉ ናቸው

በጊዜ ለመከወን መላው ሠራተኛ እንደ ንብ ይታትራል፡፡ በዚህ ወቅት ግን አንድ ችግር ይገጥማል፤ የመበየጃ ማሽን እጥረት፡፡ ከነበሩትም መካከል ከፊሉ በብልሽት ምክንያት አገልግሎት እንደማይሰጡ በትውስታ አወጉኝ፡፡ በፋብሪካው ጥገና በተለይ በአቶ ደምረው መሪነት በሚከናወነው የክላርፊኬሽን ፕላንት ላይ የብየዳ ማሽን እጥረቱን አጅግ አሳሳቢ አድርጐት ነበር፡፡

ይህንን ችግር ለማቃለል ከተለያዩ ተቋማት በትብብር ተውሶ ማምጣት የመፍትሄ አማራጭ ነበር፡፡ ይህንን ችግር ልብ ያሉት አቶ ደምረው በእራስ መተማመን ብሎም እራስን በመስጠት አስተሳሰብ እራሳቸውን ለፈጠራ ያዘጋጃሉ፡፡ ሀሳባቸውን ለሚመለከታቸው አካላት ካሳወቁና የሚያስፈልጋቸው ግብዓት ከተዘጋጀላቸው በኋላ ሥራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ የወዳደቁ ብረቶችንና በርሜሎችን በመጠቀም አንድ ለቀላል ብየዳ የሚውል የመበየጃ ማሽን እውን አደረጉ፡፡ የመጀመሪያው የፈጠራ ስራቸው በባለሙያዎች ተፈትኖና በሙከራ ተረጋግጦ ወደ ስራ ሲገባ የአቶ ደምረው ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነትና የይቻላል አመለካከት ግለቱ ጨመረ፡፡ በዚህም ከዚህ ቀደም ለአመታት አገልግለው በብልሽት የተጣሉ የሆላንድና የእንግሊዝ ስሪት መበየጃ ማሽኖችን ማማተር

ያዙ፡፡ የፈጠራና የማሻሻያ ሥራዎችን በማከል ሦስቱን ለአገልግሎት አበቋቸው፡፡

አቶ ደምረው እንዳወጉኝ ከሆነ የመጀመሪያ የፈጠራ ስራቸውን የሥራ ሓላፊዎች ተመልክተው “ከእንግዲህ ቀላል ብየዳዎችን ለማከናወን የሚረዱ የብየዳ ማሽኖች ለመግዛት በጀት አይያዝም “ እንዳሏቸውና አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው በብልሽት ምክንያት የተጣሉ የብየዳ ማሽኖች ዳግም ስራ ላይ የሚውሉበትን ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ እዳበረታቷቸው አስታውሰዋል፡፡

የአቶ ደምረው የፈጠራ ውጤቶችን እየቃኘሁና ከአንደበታቸው የሚወጡ የተዋዙ ንግግሮችን እያደመጥኩ የመጨረሻ ጥያቄአ አነሳሁላቸው፡፡ ለመሆኑ የወደፊት ዕቅድዎት ምንድነው? አልኳቸው፡፡

“አብዛኛው የፋብሪካ ጥገና ሥራ በተለይም በክረምት ወቅት ብየዳ ነው፡፡ ለብየዳ ሥራ ዋነኛው ግብዓት ደግሞ ኤሌክትሮድ ነው፡፡ ፋብሪካው ለኤሌክትሮድ ግዥ በዓመት በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት ይመድባል፡፡ እናም በፈጠራ፣ ምርምርና ጥናት በራስ አቅም ማምረት ይቻላል” የሚል ሃሳብ አለኝ ይላሉ፡፡ እስካሁንም ይህንን ሃሳባቸውን እውን ማድረግ የሚያስችል ግማሽ መንገድ ያህል መጓዛቸውንም

Page 17: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 17

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a r

ነግረውኛል፡፡ ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ተግባራዊነት ደግሞ ከፍተኛ ድጋፍና ስልጠና እንዲሁም ልምድ የሚቀስሙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ይፈልጋሉ፡፡

በፋብሪካው ያሉ ልበ ብርሃን ባለሙያዎች የአቶ ደምረው ደገፉን መሰል የፈጠራና የማሻሻያ ሥራዎች ለበርካታ ጊዜያት አከናውነዋል፡፡ በዚህም ፋብሪካው ግዥ ቢፈፅም ያወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጭ ማዳን ችለዋል፡፡ ይህንን እያውጠነጠንኩ የአቶ ደምረው የፈጠራ ሥራዎች ምን ያህል ወጭ እንዳዳኑ የሚያረጋግጥ የተቀመረ መረጃን ፍለጋ ወደ ፋብሪካው የካይዘንና የለውጥ ሥራ አመራር ቡድን አቀናሁ፡፡

ቡድን መሪው አቶ ብሩክ ወልቀባ በአቶ ደምረው ደገፉ የተከናወኑ የአነስተኛ ብየዳ ስራዎች ማከናወኛ የፈጠራ ማሽኖች ወደ 60 ሺህ ብር እንደሚገመቱ፤ ከዚህ ቀደምም የ”ዲያፍራም ቫልቭ” ላይ እንዲሁም ጥራት ያለው ስኳር ለማምረት ወደ ሰልፋይተር የሚገባ የጋዝ መስመርን ሞዲፊኬሽን የሰሩ መሆናቸውን ጨመሩልኝ ፡፡

የአቶ ደምረው የእስካሁኑ የፈጣራ ስራዎች ተደምረው ድርጅቱን ወደ ግማሽ ሚሊዮን ብር ከሚጠጋ የገንዘብ ወጪ ታድገውታል ያሉት ቡድን መሪው፣ አያይዘውም በ2008 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ድረስ ብቻ በተለያዩ የፋብሪካው ባለሙያዎች አማካኝነት ፋብሪካውን ከወጭ ማዳን ያስቻሉና ስራቸው የተቀመረ የ144 ሚሊዮን ብር የማሻሻያና የፈጠራ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል ፡፡

ለመሆኑ ለፋብሪካው ለየት ያለ የፈጠራ እና የማሻሻያ ሥራዎችን ላበረከቱ ሠራተኞች ዕውቅናና ማበረታቻ ለመስጠት ምን ታስቧል ? ለአቶ ብሩክ ያቀረብኩት ቀጣይ ጥያቄ ነበር፡፡

ፋብሪካው አቶ ደምረው ደገፉን የመሳሰሉ ትጉሃንና የለውጥ ሐዋሪያዎች ሚና በእጅጉ የጎላ መሆኑን ያምናል፡፡ እነዚህ የፈጠራ ባለቤቶች የሀገር ጭምር ዕንቁ እና ፈርጦች ናቸው ማለትም ይቻላል፡፡ በፈጠራ እና በማሻሻያ ሥራዎቻቸው የላቀ ድርሻ ለነበራቸው ሠራተኞች ከዚህ ቀደም የዕውቅናና የማበረታቻ መርሐ ግብር ተካሒዷል፡፡ ዘንድሮም ለእነዚህ ባለውለታዎቻችንን አክብሮታችንን የምናሳይበት፣ የምናወድስበት፣ የምናበረታታበትና የምንሸልምበት ፕሮግራም ለማካሔድ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡

እኔም አቶ ደምረው ደገፉ እና ሌሎች የፈጠራ ባለውለታዎች ጀግኖቻችን ተብለው ሲወደሱ፣ ሲከበሩ፣ አርዓያነታቸው ወደ በርካቶች ሲተላለፍ በሃሳቤ እየቃኘሁ የምልከታ መጣጥፌን ቋጨሁ፡፡ መነሻዬ ላይ በውስጤ ያንጎራጎርኩትን ዜማ ለዚህ ፅሁፌ መቋጫ አደረግሁ፡፡

ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ፣በዋለበት ቦታ አይቀርም ማፍራቱ...

“የስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር የኮርፖሬሽኑን ተልዕኮና ራዕይ እንዲሳካ እንዲሁም የስኳር ኢንዱስትሪው ሰላምና ደህንነት ተጠብቆ በገበያ ላይ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡” አቶ ተመስገን ወልደመስቀል የስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ሊቀመንበር

የስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ተቋቁሞ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም ሥራ ጀምሯል፡፡ በቅርቡም በኮርፖሬሽኑ እና በማህበሩ መካከል የተደረገው የህብረት ስምምነት ፀድቆ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

ይህንን በማስመልከት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል የማህበሩን ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ወልደመስቀልን አነጋግሯቸዋል፡፡

ጥያቄ፡- ስለ ስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር አመሠራረት ቢገልፁልን?

አቶ ተመስገን፡- ቀደም ሲል በየፋብሪካው የተቋቋሙ የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበራት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ የወንጂ፣ የመተሐራና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበራትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ ስር ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡ ነባሮቹና በቀጣይ ወደ ስኳር ምርት የሚሸጋገሩት ፕሮጀክቶች እያንዳንዳቸው በተናጥል የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ይኑራቸው ቢባል የሠራተኛውን መብትና ግዴታዎች ከማስጠበቅ አንፃር የአሠራር ክፍተቶች ሊፈጥር እንደሚችል በመታመኑ በኮርፖሬሽን ደረጃ አንድ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተመስርቷል፡፡

ማህበሩ በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ህጋዊ እውቅና አግኝቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀደም ሲል በፋብሪካዎች የነበሩ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበራት ፈርሰው የዘርፍ ማህበራት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በኮርፖሬሽኑ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር ሲመሰረት ከሁሉም ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የተወከሉ የጉባኤ

አቶ ተመስገን ወልደመስቀል የስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ሊቀመንበር

» ወደ ገጽ 18 ዞሯል

Page 18: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 4 | ሰኔ 2008 ዓ.ም18

የስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ...

አባላት ጋር በተደረገ ውይይት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ጥያቄ፡- በኮርፖሬሽኑ እና በማህበሩ መካከል የተደረገው የህብረት ስምምነት አስፈላጊነትና ዓላማ ቢያብራሩልን?

አቶ ተመስገን፡- በሀገራችን የሠራተኛ ማህበራት ህብረት ስምምነት ቆየት ያለ እና ሰፊ ታሪክ ያለው ነው፡፡ በተጨማሪም ዓለም ዓቀፍ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) ስምምነትን ተቀብለው ከፈረሙ ሀገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ የህብረት ስምምነቱ አስፈላጊነትም ይህንኑ መሰረት በማድረግ የሠራተኞችን መብቶችና ጥቅሞችን ለማስከበር እንዲሁም አለም አቀፍ ስምምነቶችንና ህጐችን መሠረት ባደረገ ሁኔታ አሠሪና ሠራተኛ እጅና ጓንት ሆነው ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማስቀጠል እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡ አላማውም የኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ እና ራዕይ እንዲሳካ እንዲሁም የስኳር ኢንዱስትሪው ሰላምና ደህንነት ተጠብቆ በገበያ ላይ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡

ጥያቄ፡- ማህበሩ ምን ያህል አባላት አሉት?

አቶ ተመስገን፡- ገና በውል አልታወቀም፡፡ ምክንያቱም በስኳር ፕሮጀክቶች ላይ ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ ሥራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ወደ ምርት ሲገቡ የሚይዙት የሠራተኛ ቁጥር ከፍተኛ ስለሚሆን አሁን ላይ ሆኖ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ ስለዚህ የነባር ፋብሪካዎች እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ እየተቋቋሙ ያሉት ስኳር ፋብሪካዎች ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራውን በማጠናከር የሚኖረንን የአባላት ቁጥር ወደፊት የምናውቀው ይሆናል፡፡

ጥያቄ፡- ህብረት ስምምነቱ ተግባራዊ የተደረገው ከመቼ ጀምሮ ነው?

አቶ ተመስገን፡-ስምምነቱ ከመጋቢት 20/2008 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

ጥያቄ- ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ምን እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል?

አቶ ተመስገን፡- መሠረታዊ ማህበሩ በይፋ ሥራውን ጀምሯል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን አመቻችነት አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው ፊሊፕስ ህንፃ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ጽ/ቤቱን ከፍቷል፡፡ አመራሮቹ ቋሚ የሥራ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሙሉ ጊዜያቸውን በማህበሩ ተግባራት ላይ እያዋሉ ይገኛሉ፡፡ በሌላም በኩል በሁሉም የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች

ለሚገኙ የዘርፍ ማህበራት በቀጣይ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ በተጨማሪም በህብረት ስምምነቱ ዙሪያ ለሠራተኞች ግንዛቤ የማስጨበጫ የውይይት መድረኮች ለማመቻቸት ታቅዷል፡፡

ጥያቄ፡- የማህበሩ ሥራ ማስፈፀሚያ በጀት ምንጭ ከየት ነው?

አቶ ተመስገን፡- የማህበሩ ሥራ ማስፈፀሚያ በጀት ምንጭ ከሁለት አቅጣጫ ነው፡፡ የመጀመሪያውና ዋናው የአባላት መዋጮ ሲሆን፣ ይኸውም እያንዳንዱ የማህበሩ አባል የሚያዋጣው የደመወዙ አንድ በመቶ ነው፡፡ ሁለተኛው ምንጭ ደግሞ በቀጣይነት የምንሰራበት ሆኖ ከድጐማና እርዳታ የሚገኝ ይሆናል፡፡

ጥያቄ፡- በየፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የዘርፍ ማህበራት መኖራቸው ጠቀሜታው ምንድነው? አዎንታዊ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅማቸውስ እስከምን ድረስ ነው?

አቶ ተመስገን፡- የዘርፍ ማህበራት ከቀድሞው የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበራት የተለዩ አይደሉም፡፡ ዋናው መለያቸው የስም ለውጥ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የቀድሞ ሥራቸውን በሙሉ ይሰራሉ፡፡ ይህም ማለት በፋብሪካዎችም ሆነ በፕሮጀክቶች የሠራተኞችን መብቶችና ግዴታዎች በማስከበር ላይ በቁርጠኝነት ይሰራሉ፡፡ ችግሮችና ግጭቶች ቢከሰቱ የህብረት ስምምነቱን መሠረት በማድረግ ተነጋግረው ይፈታሉ፡፡ በዕድገት፣ በዝውውር፣ በምደባ፣ በቅነሳ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡ የሠራተኛውን መብቶችና ግዴታዎች ከማስከበር ባሻገር ተቋማዊ የለውጥ ትግበራዎች ግለታቸውን ጠብቀው እንዲጓዙና ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ የላቀ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ጥያቄ፡- በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?

አቶ ተመስገን፡- ለማህበሩ መመስረት በርካታ አካላት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ለስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ መሪዎች፤ ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች፣ ለመንግሥት አካላት፣ ለፌዴራል ማህበራትና ሌሎች ድጋፍ ላደረጉልን ሁሉ በኮርፖሬሽኑ መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ስም ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

ቆይታ » ከገጽ 17 የዞረ

Page 19: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ 19

e t h i o p i a n s u g a r. c o m@ e t s u g a rእናስተዋውቃችሁ

በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ስራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የደች ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡

ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ስልጠና መስጠት እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋምም ለምርምርና ስልጠና ተግባራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሥራው በዘርፍ ደረጃ እንዲመራ ተወስኖ ከ2003ዓ.ም ጀምሮ የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ • ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ

ምርምር (applied research) በማካሄድ ለኮሜርሽያል አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ፤

• ምርታማነትን በማሳደግ ምርትን

መጨመርና ወጪን መቀነስ፤• የአመራረት ቅልጥፍናን ለማሻሻል

የተገኘውን የምርምር ውጤት በእያንዳንዱ ስኳር ፋብሪካና ማሳ ላይ በአግባቡ እንዲውል ማስረጽ፤

• በአመራረት ሥርአት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃዎች (optimization) እንዲወሰዱ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት መስጠት፤

• ስራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ለኢንዱስትሪው ያስገኙትን ፋይዳ እና በአካባቢው ላይ ያደረሱትን ተጽዕኖ መገምገምና አዳዲስ የምርምር አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂዎችን መንደፍ፤

• ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ፣ በሽታ የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውና ቶሎ የሚደርሱ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን እንዲሁም የተሻሻሉ የሸንኮራ አገዳና የስኳር አመራራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎችን ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች

ማስተዋወቅና በስራ ላይ ማዋል፤• በኦፕሬሽን ላይ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች

ደረጃቸው (ስታንዳርድ) ሳይጓደል ትግበራቸው የሚቀጥልበትን አሰራር መቀየስ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስተግበር፤

• ኢንዱስትሪውን በሰለጠነና ውጤታማ በሆነ የሰው ኃይል ለመደገፍ ሥልጠናዎችን በማመቻቸትና በማሰልጠን ቁልፍ ሚና መጫወት፡፡

ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ወንጂ ላይ የሚገኘው የምርምርና ልማት ማዕከል እነዚህን ተግባራት በብቃት ለመወጣት በ2008ዓ.ም በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡ ማዕከሉ በወንጂ ሸዋ፣ መተሓራ፣ ፊንጫአ፣ ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በጣና በለስ፣ ኦሞ ኩራዝ እና ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የምርምር ጣቢያዎችን አቋቁሞ የሸንኮራ አገዳ፣ የዝርያ ልማት እና የስኳር ቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምርምርና ልማት ማዕከል

Page 20: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008

www.ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar

አዳ

ዲስ

ስኳ

ር ፋ

ብሪ

ካዎ

ችበ

መገን

ባት

ላይ

የሚ

ገኙ ስ

ኳር

ፋብ

ሪካ

ዎች

ከሰም ስኳር ፋብሪካ

እርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ

ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ጣና በለስ ቁጥር 1