Tithe & Law of Earth

115
7/29/2019 Tithe & Law of Earth http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 1/115 የምድር ሕግና አሥራት 2017 1 ww.tlcfan.org በመጋቢ  ሊዮን  ኢማኑኤል  የምድር  ሕግ  አሥራት፣ መባ፣  በኩራትና የፍቅር ስጦታ  መስጠ  

Transcript of Tithe & Law of Earth

Page 1: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 1/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

1ww.tlcfan.org

 

በመጋቢ 

ሊዮን 

ኢማኑኤል 

የምድር ሕግ አሥራት፣ መባ፣ በኩራትና የፍቅር ስጦታ 

መስጠት 

Page 2: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 2/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

2ww.tlcfan.org

 

የምድር ሕግአስራት፣ መባ፣በኩራትና የፍቅር ስጦታ 

መስጠት 

የመጀመሪያ እትም 

Copyright ©2/ 2008 

REVISED 2017

መብቱ የተጠበቀ ነው፦ 

All rights Reserved to:

Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF

THE LION’S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY

 

ለንግድ ካልሆነ በቀር ይህን መጽሐፍ ማባዛት ሆነ በነፃ ማደል ይቻላል 

Page 3: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 3/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

3ww.tlcfan.org

 

ማውጫ

1. መግቢያ ................................................................................................... 4

2. የእግዚአብሔር ሕግ ................................................................................. 7

3. የምድር ክፍፍል ...................................................................................... 15

4. የምድር ሕግ .......................................................................................... 20

5. 

አዳምና ምድር ...................................................................................... 27

6. የኢዮቤልዩ ሕግ ..................................................................................... 33

7. በ490ኛው (ጊዜ) ዘመን የሚደረግ ምሕረት ........................................ 37

8. የመቤዠት ሕግ ..................................................................................... 42

9. የአሥራት ሕግ ....................................................................................... 46

10. የአሥራት ጥያቄና መልስ .................................................................... 70

11. ቃርሚያ ሕግ ...................................................................................... 89

12. የበኩራት ሕግ ..................................................................................... 91

13. የመባ ሕግና መርህ  ............................................................................ 95

14. አሥራ አምስት መባ የመስጠት መርሆች ......................................... 100

Copyright © 2008

All rights Reserved to Pastor Leon Emmanuel

Page 4: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 4/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

4ww.tlcfan.org

 

መግቢያ 

መጽሐፍ ቅዱሳችን የሚጀምረው እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ በማለት ነው። ምድር

በፍጥረት መካከል የመጀመሪያውን ስፍራ ትይዛለች። እግዚአብሔር ምድርን ያወጣው ከራሱ ውስጥ ነው።ይህም የተከናወነው በእግዚአብሔራዊ የመናገር ሕግ ነው። እግዚአብሔር ይሁን ብሎ ቃል ይናገራል

የተናገረውም ይሆናል የተባለውንም ይፈጥራል ቅርጽንና አካልን ይይዛል። የእግዚአብሔር ቃል የሚታየው ነገር

ሁሉ ምድርና በውስጧ ያለውን በሙሉ ያመጣው ከማይታየው ከመንፈሳዊው አለም እንደ ሆነ ይናገራል።

ይህንንም እውነታ መረዳት የምንችለው ደግሞ በእምነት ብቻ እንደሆነ ይነግረናል።

“1. እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንምነገር የሚያስረዳ ነው።

2. ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። 3 ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥

ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።”

ዕብ.11፥3 

እምነት የሚመጣው ቃል ከመስማት ነው። መስማትንም ልናገኝ የተገባው በእግዚአብሔር ቃል

ነው።(ሮሜ.10፥17) ቃሉ ጥልቅና ሁሉ ሊቀበሉትና ሊኖሩበት የሚገባውን መርህን በግልጽ ያስተምረናል። እኛም

ለዚህ ትምህርታችን መሰረት የምናደርገው የእግዚአብሔርን ቃል ነው። የእግዚአብሔር ቃል መሰረት ያላደረገ

መስማት እምነትን፣ የእውነት እውቀትን እና መረዳትን አያመጣም። ከዚህ አያይዘን የምንማረው ትምህርት

ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ሊጸና ደግሞ ይገባዋል። በተጨማሪም ቃሉን ስንማር የመንፈስ ቅዱስን

ምስክርነት በልባችን ልናደምጥ ይገባል። ሌላው ደግሞ ልናውቅ የሚገባው የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት

እራሳቸውን የቻሉ ሁለት ምስክሮች ናቸው። በብሉይ ኪዳን የምንማረውን በአዲስ ኪዳንም ውስጥ ልናገኘው

ይገባል ማለት ነው።

ኢየሱስ በሁለት ምስክር ሁሉ ነገር እንደሚጸና ያምናል ደግሞም ያስተምራል። ስለዚህም

ምክንያት ደቀመዛሙርቱን እንኳ ለምስክርነት ሲልክ የላከው ሁለት ሁለት በማድረግ ነው። ይህም

ምስክርነታቸው የጸና እንዲሆን ነው። ሙሴ ለሕዝበ እስራኤል በምድረ በዳ ሳሉ ሰማይንና ምድርን በእናንተ

ላይ አስመሰክራለሁ በማለት ምድርና ሰማይ ራሳቸው የቻሉ ሁለት ምስክሮች እንደ ሆኑ በሕዝበ እስራኤል

ላይም እንደ ምስክር ተጠርተው እንደ ነበር ቃሉ ይነግረናል። (ዘዳ.4፥26) እኛም በዚህ ዘመን አማኝ የሆኑን ሁሉ

በትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል በምስክር የተረጋገጠ እውነትና ምስክርን ልንቀበል ይገባል።

Page 5: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 5/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

5ww.tlcfan.org

 

እኔም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለምስክር በቂ የሆኑ ጥቅሶችን ሁለት ወይም ሥስት ለምናገረው

እውነት ምስክርነት ይሆን ዘንድ ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አስቀምጣለሁ። 

“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማድረግም ስለ ሠራት ኃጢአት ሁሉ በማንም ላይ አንድ ምስክር

አይቁም፤ በሁለት ምስክሮች ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ነገር ሁሉ ይጸናል።”

ዘዳ.19፥15 

“ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትናበሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።”

2.ቆሮ.13፥1 

ምድር በውስጥዋ ብዙ ነገሮችን ይዛለች። በውስጥዋም ያለው ነገር እስከ ዛሬ ድረስ በሙላት

ገና አልተገለጠም። ምድር የሰው ልጆች ሥጋ የተበጀባት ከእግዚአብሔር የወጣች የእግዚአብሔር ፍጥረት

የአካላችን መሰረት ነች። የሰው ሥጋ ከምድር ተገኝቷል። ሰውም በሚሞት ወቅት ሥጋው ወደ ምድር አፈር

ይመለሳል። ሰውም በሕይወትም በሚኖርበት ወቅት ሁሉ ከምድር በሚገኝ ንጥረ ነገርን በተለያየ መንገድ

በመመገብ በሥጋው በሕይወት ይኖናል። ከዚህ የተነሳ ለዚህ መጽሐፍ መግቢያ እንዲሆነን ምድር የሰው ልጆች

ሥጋ ምሳሌ እንደ ሆነች ልናውቅ ይገባል። ሰለዚህ የምድር ሕግ ስንል የሥጋች ሕግ ማለት ነው። የሥጋችን ማለት

የምድር ሕግ ከአሥራታችን ጋር የተያያዘ ነው። እግዚአብሔር የልቦናችንን አይን እንዲከፍት ከሕጉ ማስተዋልን

እንዲስጠን ጸሎቴ ነው። ይህም ከሕጉ ጀርባ የሚገለጠውን ፀጋ መመልከት እንድንችል ነው። 

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከምድር ይልቅ ስለ አሥራት እውነትና ለለ አሥራት ሕግ ትርጉምና ፍቺ

በጥልቀት እንመለከታለን። ምድና አሥራት በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን የተያያዙ የማይነጣጠሉ ናቸው።

በብሉይ ሰው አሥራቱን አወጣ ቢባል የሚያወጣው ምድር ከምትስጠው ፍሬ ፣ ዘርና ከምድር እንስሳት ሁሉ

ነው። በአዲስ ኪዳንም ሰው አሥራቱን የሚያወጣው ከምድር አፈር ከተበጀው ከሥጋው በጉልበቱ ጥሮ ግሮ

በላቡ ካመጣው ሃብቱ ነው። የዚህ መጽሐፍ የተጻፈበት ዋና አላማው አማኞችን ሁሉ ትክክላኛ ስለ አሥራትና

መስጠትን እግዚአብሔር እንደሚለው መረዳት እንዲችሉ ለማድረግ ነው። ምናልባት ይህን ስል ከዚህ በፊት

አሥራት አውጥተናል ስለ አሥራትም በክትትል ትምህርት ተምረናል የምትሉ አይመለከተኝም ልትሉ

ትችላላችሁ። ለእነዚህ አሁን ለምጠይቃችሁ ጥያቄዎች መልስ እውነት እንደ እግዚአብሔር ቃል በመረዳት

ከመለሳችሁ ይህ ትምሕርት እናንተን አይመለከታችሁም። ነገር ግን ጥያቄውን በሙሉ በመረዳት መመለስ

ካልቻላችሁ ይህ መጽሐፍ ላንተ፣ ላንቺ ፈጽሞ አስፈላጊና ጠቃሚ መርሆችን መገብያ እንደሚሆን አምናለሁ። 

Page 6: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 6/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

6ww.tlcfan.org

 

አሥራት የማን ነው? አሥራቴን የት ማምጣት ነው ያለብኝ? የእግዚአብሔር ቃል አሥራትህን

በአምላክህ ፊት ብላው ይላል እንዴት እንብላው? አሥራት በቃሉ መሰረት ይዋጃል ይላል። ታዲያ አሥራቴን

እንዴት ልዋጀው? መሪዎች አሥራት ማውጣት አለባቸውን ወይስ የለባቸውም? እንዴትና ከየት ያውጡ?

አሥራት፣ በኩራትና መባ ልዩነታቸው ምንድን ነው? አሥራትን ማን መክፈል ይገባዋል? አሥራቴን መቼ

ልክፈል? ሰው የእግዚአብሔር አሥራትና በኩራት እንዴት ነው የሚሰርቀው? አሥራት ከሕግ መሰጠት በፊት

ነበርን? አብርሃም ደግሞም የአብርሃም የልጅ ልጅ ያቆብ አሥራት አወጣ እንዴት? ለማን? ከምን? የት? ይህን

ሁሉ ጥያቄ እንደ እግዚአብሔር ቃል መመለስ ይኖርብናል። ይህ ካልሆነ ግን ይህን መጽሐፍ አንብበው ሲጨርሱ

ከምትማሩት ከእግዚአብሔር ቃል የተነሳ ሕሊናችሁ ይነጻል። በእውነተኛው በእግዚአብሔር ሕግና ስርዓትም

እንደሚገባው መኖር እንጀምራለን። 

ይህን መጽሐፍ አንብበን ስንጨርስ ስለ አሥራት፣ መባ መስጠት፣ የፍቅር ስጦታ እየተባለ

በዘመኗ ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ላብ ለግል ጥቅማቸው ከሚበዘብዙ በዝባዥ የሃስ ገልጋዬችና አቢያተ

ክርስቲያናት የሚጠብቀንን የቃል እውነት ከእግዚአብሔር ቃል እንማራለን። በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቃል

ጋር በተያያዘ በገንዘብ ነክ ጉዳይ ላይ ላሉን ዋና ዋና ጥያቄዎች መልስን እናገኛለን። እግዚአብሔር በማስተዋል

መንፈስ ይደግፈን። የልቦናችንን አይንም ይክፈትልን። በሃሰትም ትምህርትና ንፋስ ከመወሰድ እግዚአብሔር ነፃ

ያውጣን። 

Page 7: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 7/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

7ww.tlcfan.org

 

የእግዚአብሔር ሕግ 

ምንም እንኳ ሕይወት ያላቸው ቃሎች በሚለው መጽሐፌ ላይ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ምንነት

ዓላማ በጥልቀት ባስቀምጥም መጽሐፉን ላላነበቡ አንባቢያን ለዚህ ትምህርታችን መሳኝ ሰለ ሆነ ስለ

እግዚአብሔር ሕግ አንዳንድ ነገር ባጭሩ ላስጨብጥ እወዳለሁ።

የእግዚአብሔር ሕግ ቅዱስ፣ ጻድቅና በጎም ነው። (ሮሜ.7፥12) የመለኮታዊ የእግዚአብሔር ሕግ

አላማ በትክክልና በትክክል ባልሆነው መካከል መለየት ነው። በሌላ አባባል ሕግ ሃጢያትን በግልጽ ምን እንደ

ሆነ ያብራራል። ሕግ ሃጢያተኛ ካልሆኑት በቀር ማንንም አያድንም ማንንም አያጸድቅም ነገር ግን ሃጢያተኛ

መሆኑን በሕግ የተረዳ እንደ ሕጉ ደግሞ እንዴት ምሕረትን ማግኘት እንደሚችል በሕጉ ይማራል። ሌላ ደግሞ

ሕጉ ወደ ክርስቶስ መልክ የሚያመጣን ብቸኛ መንገድ እውነኛ አስተማሪ ነው። ሙሴ ሕዝቡን ወደ ኢያሱ ሥር

እንዳመጣ ማለት ነው። 

ሁሉ ሃጢያትን ሰርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጐሏቸዋል። ሮሜ 3፥23 ስለዚህም ሕጉ

ለማዳን ወይም ለማፅጸቅ አላማ እንዳልተሰራ ግልጽ ነው። ይሁንና ሕጉ እግዚአብሔር ሃጢያትን ምን እንደ ሆነ

የሚያሳውቅበትና ሰው እንዴት መዳን እንደሚችል የሚያስረዳበት ወደ ቅድስናና ወደ ልጁ መልክ አማኙን

የሚያመጣበት፣ አሮጌውን ሰው የሚገድልበት፣ መንፈሳዊ ስይፍ ነው። በሕግ ሃጢያት ምን እንደ ሆነ

ይታወቃል። ሮሜ.3፥20,7፥7 እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝበ እስራኤል ሕጉን ሲሰጥ የጀመረው አስርቱን

ትእዛዛት በመስጠት ነው። እነዚህ የተሰጡት ሙሴም ሆነ ሕዝቡ እንዲታዘዙ እንዲያደርጉት ነው። ሕግን በቢሮና

በቤት ውስጥ ጌጥ እንዲያደርጉት ለሰው ታይታ ብቻ እንዲሰቅሉት እግዚአብሔር አልሰጠም። ይልቁኑ

እንድንታዘዝ ነው። ይህም ሕግን መጠበቅ እግዚአብሔርን የመታዘዝ ፈተናና የምድረበዳ ትምህርት ነው። 

“አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።” ዘዳ.8፥2 

ማንም እስራኤላዊ ጣኦት እያመለከ፣ ዝሙት እየሰራ፣ ጎረቤቱን እየሰረቀ፣ ቤተሰቦቹን እያዋረደ

እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ ሊል ፈጽሞ አይችልም። ሕጉ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ባሕሪ ለመረጠው ሕዝቡ

መገለጫና ከሰው ምን እንደሚጠበቅም ማስረጃ ነው። ሌላው የሕግ አላማ ሰው እግዚአብሔር እንደሚፈርድ

ትክክለኛ ፍርድ በሕዝቡ መካከል ለመፍረድ ብቃት የሚሰጥ ነው። የሌባው ፍርድ፣ የአመንዝራው ፍርድ፣ የባለእዳው ፍርድ የመሳሰሉትን የሚያጠቃልለሉይ በዚሁ በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ ነው። 

Page 8: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 8/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

8ww.tlcfan.org

 

“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም

አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥

በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን

ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።” ማቴ.23፥23 

ኢየሱስ ጻፎችና ፈሪሳውያንን ግብዞች ወዮላችሁ ያላቸው አሥራት ስለማያወጡ አይደለም።

ነገር ግን የሕጉ ዋነኛ ነገር የሆኑትን ፍርድን፣ ምሕረትንና ታማኝነትንም ሰለማያደርጉ ነው። በሕጉ ያለውን ዋነኛ

የሆኑትን ፍርድ፣ ምሕረትንና ታማኝነትንም አሥራት ማውጣታቸውንም ሳይቆሙ በቀዳሚነት ሊያደርጓቸው

ሲገባቸው ፍርድን፣ ምሕረትንና ታማኝነት በሕዝቡ መካከል ስላላደረጉላቸው ነው። 

ሕግ ሁሉ እንደሚገባ ቢሰራበት መልካም ነው።1.ጢሞ.1፥8 ሰለዚህ አሥራትን እንኳ አንድ ሰው

ሲስርቅ የሚቀጣው ስለ ሌባው በተሰጠው የእግዚአብሔር ፍርድ ሕግ ነው። እግዚአብሔር በአሥርቱ ትዕዛዛት

ውስጥ አትስረቅ ብሏል። ነገር ግን አንድ ሰው ቢሰርቅ ምን መደረግ እንዳለበት አሥርቱ ትዕዛዛት ምንም

አይገልጽም ወይም አያብራራም። ፍርድና ምሕረትን ታማኝነትን የሚገልጡትን የቀሩትን ሕጎችን ሕዝቡ

ከእግዚአብሔር ሊሰማና ሊታዘዛችው አልወደደም። ይህ በአሁን ጊዜም እንዲሁ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር

ወደ እርሱ ለመጠጋትና ከእርሱ ከአፉ ሕጉን ለመስማት ለወደደው ለሙሴ የሕጉን ማብራሪያ አፍ ለአፍ

ከመናገር አልፎ በገዛ እጁ ጽፎ በጹሁፍ ለሙሴ አስረክቦታል።

እነዚህ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር አፍ ያልሰማቸው ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ የሰማቸው 603

ሕግጋት ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም በግልጽ እንዴት መተግበር አንዳለባቸው በግልጽ ያሳያሉ። አስርቱ

ትዕዛዛት ግን ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትን በግልጽ አያሳዩም። በአጠቃላይ 10ቱ ትዕዛዛት መሪ ርዕሶች ናችው

ማለት ነው። ሕዝበ እስራኤል እንደዚህ ዘመን አማኝ እግዚአብሔርን ሕግ በጠቅላላው ለመስማት አይፈቅዱም።

ከእግዚአብሔር ቀጥታ ከመስማት ይልቅ እግዚአብሔር በሰው በኩል እንዲናገራቸው ይፈልጋሉ። ይህ ብቻ

አይደለም። በዚህ ባለንበት ዘመን ሕግ በፀጋ ተሽሯል እያሉ በአንድ ጎን ደግሞ እንደ ሕጉ ያሉ ትዕዛዛትን

የሚጠቅማቸውን ብቻ እንደ ፈለጋቸው እንደ ጻፎችና ፈሪሳዊያን እየነቀሱና እየቦጨቁ እየወሰዱ በራሳቸው ላይ

የእግዚአብሔር ቁጣ እያጠራቀሙ ያሉ ብዙዎች ናቸው። እነዚህ አይነት ሰዎች ሕጉን በራሳቸው ሃሳብ

በማስተካከል በሕጉ ለግላቸው ይጠቀማሉ። ይህ በእግዚአብሔር ፊት ፈጽሞ የሚያስቀጣ ነው። ኢየሱስ

ለእንደነዚህ አይነት ባሕሪ ላላቸው ሰዎች ወዮላችሁ አለ።

Page 9: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 9/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

9ww.tlcfan.org

 

ይህ ከእግዚአብሔር የሚመጣባቸው ቅጣት የከፋ መሆኑን ያሳያል። ሳኦል የእግዚአብሔር

ትዕዛዝ በመተላለፉ የሆነበትን እንድታስታውሱ እወዳለሁ። ሰለ እግዚአብሔር ሕግ ልናውቅ የሚገባን ብዙ ነገር

አለ። በመጀመሪያ ደረጃ ሕግ በእምነት ወይም በፀጋ አልተሻረም። ይልቁንም ሕግን በፀጋና በእምነት አብልጦ

ጸንቷል። (ሮሜ.3፥31) ፀጋ እንዲበዛም በሃጢያት ጸንተን ልንኖር ደግሞ ፈጽሞ አይገባም። በሃጢያት ብንጸና

በሕግ ደግሞ አሁንም ቢሆን ይፈረድብናል። ከሕግም በታች እንወድቃለን እግዚአብሔር በሕጉ መሰረት

ይፈርድብናል። በሕጉም የሚጠበቅብንን ሳናደርግ ከሕግ በላይ ወይም ከሕግ ነፃ ልንሆን አንችልም። (ሮሜ.6፥

1) ሕግ የለም ተሽሯል ካልን ሃጢያት የለም ፍርድ የሚባልም ነገር የለም ማለት ነው? ይህ ከሆነ በውጭ ባሉትስ

ለምን እንፈርዳለን? ወንጌልንስ መስበክ ለምን አስፈለገ? ንስሃ ግቡ የሚለው የሐዋርያት ስብከት ከንቱ ነው

ማለት ነዋ? 

ሕግ ከሌለ ምንም አይነት ፍርድ የለም። ይህ ከሆነ ደግሞ እንዴት አድርገን የነጩ ዙፋን ፍርድ

እንጠብቃለን? አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም ከሕጉ አንዲቷ ከምታልፍ ከምትጠፋ ምድርና ሰማይ

ቢያልፉ ለእግዚአብሔር ይቀለዋል። ሕጉ ከእግዚአብሔር በምድር ላሉ የሰው ልጆች ይምጣ እንጂ አመጣጡ

ከእግዚአብሔር መንግሥት ከራሱ ከእግዚአብሔር ነው። ይህ ሕግ በሁሉ ስፍራ በሁሉ ጾታ በሁሉ እድሜ

አወቅነውም አላወቅነውም እንደ ምድር ስበት ሕግ የሚስራ ነው። የእግዚአብሔር ሕግ ትንቢታዊ ነው። ሕጉ

ያለፈውን እየሆነ ያለውን የሚሆነውን በግልጽ ያሳያል። ሕጉ እግዚአብሔር ራሱ በመንፈሳዊው አለም

የሚኖርበት የእግዚአብሔር የልብ ትርታውና መርሁ ነው። 

ይህን ሕግ አልሰማሁም አላየሁም የሚል ሰው ፈጽሞ በምድር አይኖርም ሊኖርም አይችልም።

ሕግ ሰጪው ባለበት ሕጉ አለ። እያንዳዱ ሰው መንፈሱ በእግዚአብሔር አምሳል ስለተፈጠረ በስጡ

የእግዚአብሔር ሕግና መርህ ይኖራል። ሮሜ.2፥12-16 ኢየሱስ ወደ ምድር ከመጣባቸው ብዙ አላማዎች አንዱ

የእግዚአብሔር ሕግ በመጠበቅ ሕጉን ለማስከበር ከፍ ለማድረግና ለማጉላትም ጭምር ነው። (ማቴ.15) ይህ

ብቻ አይደለም የእግዚአብሔር ሕግ በራሳቸው ሕግ እንደሚመቻቸው የለወጡትን በአደባባይ ሊያዋርድ

የእግዚአብሔርን ሕግ በትክክለኛ ትርጉሙ ሊያስቀምጥም ጭምር ነው። ክርስትና ያለ እግዚአብሔር ሕግ

ምንም ነው። ሕግ በሌለበት ሕይወትና ስርዓት የለም። 

Page 10: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 10/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

10ww.tlcfan.org

 

ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው እንደ ሕጉ ነው። የኖረው እንደ ሕጉ ነው። የሞተና የተነሳው እንደ

ሕጉ ነው። ደግሞም ተመልሶ የሚመጣው እንደ ሕጉ ነው። ሁሉ ከሕጉ አይወጣም። ይህን ግን ለመቀበል

ለደቀመዛሙርቱ ከሙሴ ጀምሮ እንደ ተረጎመላቸው ሕጉን እንደ እግዚአብሔር ልብና ሃሳብ የሚተረጉምልን

የእግዚአብሔር ልጅ ወይም ልጁ የላከው መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል። ሕጉ የቃል ኪዳን ቃሎች ወይም ሕይወት

የሚገኝባቸው ቃሎች በመባልም ይታወቃሉ። እነዚህ የቃል ኪዳን ቃሎች ደግሞ የሁላችን የሰው ልጆች ሁሉ

ናቸው። እኛም ዘር ቋንቋና ጾታ ሳንለይ ልንታዘዛቸው ይገባል። ይህን የእግዚአብሔር ቃል አስረግጦ እንዲህ

ይለናል። 

“9፤ ስለዚህ በምታደርጉት ሁሉ ትከናወኑ ዘንድ የዚህን ቃል ኪዳን ቃሎች ጠብቁ

አድርጉም። 10፤11፤ ሁላችሁ፥ አለቆቻችሁም ነገዶቻችሁም ሽማግሌዎቻችሁም

ሹማምቶቻችሁም፥ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ልጆቻችሁም ሴቶቻችሁም በሰፈራችሁም

ያለ እንጨትህን የሚቈርጥ ውኃህንም የሚቀዳ መጻተኛ፥ ዛሬ በአምላካችሁ

በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤ 12፤13፤ ይኸውም ዛሬ ለእርሱ ሕዝብ አድርጎ ያስነሣህ

ዘንድ፥ እርሱም ለአንተ እንደ ተናገረ ለአባቶችህም ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም

እንደ ማለ አምላክ ይሆንልህ ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ዛሬ

በሚያደርገው ቃል ኪዳን ትገባ ዘንድና የአምላክህን የእግዚአብሔርን መሐላ ትሰማ

ዘንድ ነው። 14፤ እኔም ይህን ቃል ኪዳንና ይህን መሐላ የማደርገው ከእናንተ ጋር ብቻ

አይደለም። 15፤ ነገር ግን ዛሬ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ

ከሚቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ።…”

ዘዳ.29፥9-15 

እግዚአብሔር ሕጉን ሲሰጥ ሰው ልጆችን ሁሉ አሻግሮ እየተመለከተ ነበር። ምንም እንኳን ከሲና

ተራራ ስር ባንገኝም እግዚአብሔር በቀደመ እውቀቱ ቃልኪዳኑንና ተሰፋው ደግሞ ቅዱስ የሆነውን ሕጉን ለኛም

አደረገው። ሕግ ቅዱስ፣ ክቡርና እጅግ መልካም ነው። ሰው ያለ ሕጉ ወደ ቅድስና መምጣት አይችልም። ይህን

ስል ሕጉ ይቀድሳል እያልኩ አይደለም። ሕጉ እንዴት መቀደስ እንደምንችል ሰለሚያስረዳ፣ ያለመረዳትና እውቀት

ደግሞ ቅድስናን ራሱ ልናውቅ ስለማችል ነው። ምድረ በዳን ጨርሰው ከነዓን የገቡት ሕጉን የታዘዙ ሰዎች ብቻ

ናቸው። ከንዓን የምንገባው ሕጉን በመታዘዝ እለት እለት መዳናችንን በመፈጸም ነው። ሕጉን የምንጠብቀው

ለመዳን ሳይሆን ተስፋውን ለመውረስ ነው።

Page 11: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 11/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

11ww.tlcfan.org

 

ሕጉን ከፋሲካው በግ በኋላ ከግብፅ ወጥተን የምንቀበለው ነው። ከግብፅ ያልወጣ ሕግን

መማር ወይም መቀበል አይችልም። ከግብፅ ደግሞ በሕግ ሳይሆን የሚወጣው በበጉ ደም ወይም በኢየሱስ

ክርስቶስ የመስቀሉን ሥራ በመቀበል ነው። ተስፋው ለእኛ ዛሬ የከንዓን ወተትና ማር የሚያፈልቅ ምድር ጥላ

አካል የሆነው የትንሣኤ አካላችን ነው። ይህን ርስት ለመውርስ የሥጋችንን ቤዛነት ወይም መቤዠት ለመጠባበቅ

ሕጉን ጠንቅቀን ማወቅና ትርጉሙን ተረድተን ልንታዘዝ ይገባል።

ጳውሎስ ይህን በሮሜና በቆሮንጦስ ላይ ጠንቅቆ አስተምሯል። በእስራኤላዊያን ያለፈው ነገር

ሁሉ እኛን ለማስተማር ለአሁን ዘመን ይጠቅመን፣ ያርመን ፣ የገስጸን ዘንድ ነው። ደግሜ እላለሁ ሕጉ

ትንቢታው ነው። ሰለዚህ የእግዚአብሔር ሕግ የተፈጸመና ያልተፈጸመ ትንቢት ይዟል። እነርሱ እንደ ወረሱ እኛም

የምንወርሰው እንደዚያው እንደ ሕጉ በሕጉ እንደተጻፈው ትንቢት መሰረት ነው። ክብሩና አሰራሩ አደራረጉ ግን

የተለያየ ነው። (ሮሜ.8፥11,20-25, 1.ቆሮ.10፥6,11) 

“6፤ በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ

እንድትወድድ አምላክህ እግዚአብሔር ልብህን የዘርህንም ልብ ይገርዛል። … 11፤ እኔ ዛሬ

የማዝዝህ ይህች ትእዛዝ ከባድ አይደለችም፥ ከአንተም የራቀች አይደለችም። 12፤ ሰምተን

እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል

በሰማይ አይደለችም። 13፤ ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕሩን ተሻግሮ እርስዋን

የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል ከባሕሩ ማዶ አይደለችም። 14፤ ነገር ግን ታደርገው ዘንድ

ቃሉ በአፍህና በልብህ ውስጥ ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው። 15፤ ተመልከት፤ ዛሬ በፊትህ

ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ። 16፤ በሕይወትም እንድትኖር

እንድትባዛም፥ አምላክህም እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር እንዲባርክህ፥

አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙንና ሥርዓቱን

ፍርዱንም ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ። 17፤ ልብህ ግን ቢስት አንተም ባትሰማ፥

ብትታለልም፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድ ብታመልካቸውም፥ 18፤ ፈጽማችሁ እንድትጠፉ

እኔ ዛሬ እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመናችሁን

አታስረዝሙም። 19፤ በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ

ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ

Page 12: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 12/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

12ww.tlcfan.org

 

ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ 20፤ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም

እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት

ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ።”

ዘዳ.30፥6,11-20 

“5 ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና።

6.ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል። በልብህ። ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ

ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ 7 ወይም። በልብህ። ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ

ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። 8 ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ

ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። 9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ

ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ 10 ሰው

በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። 11 መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ

አያፍርም ይላልና። 12 በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ

ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ 13 የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። 14

እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ

ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? 15 መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ

ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ?”

ሮሜ.10፥5-15 

ሕጉን መጠብቅ የሚችለው በደሙ ከሞት የዳነ በጉን በመንፈስ እሳት ጠብሶ በመብላት

ከግብፅ የወጣ እንደ መንፈስ ፍቃድ የሚመላለስ በመንፈስ የሚመራ ማለትም ዳግም የተወለደ

የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ነው። በበጉ ደም ከኋጢያቱ ያልነጻና ከባርነት ያልወጣ ወደ ሲና ተራራ ሊመጣ፣ ሊጠጋ

ደግሞም ከእግዚአብሔር ሕግ ሊማር እግዚአብሔርን እርሱ ካልፈቀደ በቀር ሊሰማ አይችልም። ወደ ሲና ተራራ

ደግሞ መጠጋትም ብቻ ሕጉን ሁሉ መስማትና መታዘዝን አያመጣም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ ከአፉ

ተጠግቶ ሳይሸሹ፣ ሳይፈሩ፣ ስምቶ ማድረግ የአሮጌው ባሕሪ የመስቀል ወይም የመግደል ሕይወት ነው። 

“1 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። 2 በክርስቶስ ኢየሱስ

ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።

Page 13: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 13/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

13ww.tlcfan.org

 

3-4 ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን

በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ

መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ

የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።” ሮሜ.8፥1-4 

የሕይወት መንፈስ ሕግ በቃሉ ውስጥ የሚገኘው ከ613 ሕግጋት ጀርባ የሚገኘው መንፈስ  

ውስጥ ነው። ይህም ፀጋና መንፈስ ከሃጢያትና ከሞት ሕግ አርነት ያወጣል። ሕጉ የራሱ የሆነ መንፈሳዊ አስራርና

መርህ አለውና ነው። የሕይወት መንፈስ ሕግ ይገድላል ነገር ግን የሚገድለው ግን እኛን ሳይሆን የአሮጌውን ሰው

ባሕሪ ነው። በአሮጌ ማንነት ሆኖ ሕጉን መጠበቅ ፈጽሞ የማይቻል ነገር ነው። ይህ ሞት ግን በዚህ ባሕሪ ላይ

የሚመጣበት በውስጣዊው ማንነታችን በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ጳውሎስ ደስ የምንሰኝና የምንታዘዝ

ለውጫዊው ማለትም ለአሮጌው እለት እለት እንድንሞት ነው። ያን ጊዜ ጳውሎስ እንዳለው እንደ መንፈስ ፍቃድ

እንጂ እንደ ሥጋ ፍቃድ በማንመላለስ በእኛ አማኞች የሕግ ትዕዛዝ ይፈጸማል። ይህ እንዲሆን ደግሞ ሰለ እኛ

ኢየሱስ በሥጋ ተገልጦ ሃጢያትነ በስጋ ኮነነ፣ አወገዘ፣ መጥፎ እንደ ሆነ አሳየ፣ አዋረደ፣ ደመሰሰ። በደሙ የሆነን

ማስተሰረይንና ይቅርታን ንስሃ ለሚገቡ ሁሉ በደሙ በኩል ለሁሉ አዘጋጀ። 

የእግዚአብሔር ሕግ ሃጢያት ምን እንደ ሆነ ከማሳየት ባሻገር የተሰራ ሃጢያት እንዴት

መደምሰስ እንደሚገባው ያስረዳል። ይህ ማሰረዳቱ በአሮጌው ማንነታችን ባሕሪ ላይ ሞትን ያመጣል። ይህ

ሲሆን ደግሞ የእግዚአብሔር ሕግ በልባች ይፃፋል እኛም በትዕዛዛቱ መሄድ ጀመርን ይባላል። ያን ጊዜ በትንቢት

የተጻፈ ቃል በሕይወታችን ይፈጸማል። ኤር.31፥31-34 በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምናጠናው ከእግዚአብሔር 613

ሕግጋት መካከል የአሥራት ሕግ በልባችን ይጻፋል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም በኤርሚያስ ላይ ለሕዝቡ፣

ለፈጠረው የሰው ልጆች በሙሉ ተስፋን የገባው እግዚአብሔር ነው። ኤር.31፥31  እግዚአብሔር ሕጉን በልብ ላይ

ሲጽፍ ከዛ በመቀጠል በትዕዛዛቱ ደግሞ ያስኬዳል።

የአሥራትን ሕግ እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ በልባችን ሲጻፍ የእግዚአብሔርን የልብ ሃሳብ

እንድንታዘዝ፣ እንድናደርግ ያደርገናል። ይህ ደግሞ እምነታችንን ሕያው ያደርገዋል። እምነት ከሥራ ከተለየ

የሞተ ነውና። እግዚአብሔር በልባችን በመፃፍ እንደ ተስፋው ቃሉ ይረዳን ዘንድ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ነው።

“አማኑኤል” እኛ ግን ከዚህ በፊት በሰበርነው የልባችን ጽላት ፋንታ አሁን ልባችንን እንደገነ በንስሃ ልብ በደሙ

አንጽተን እንደ ተጠረበ ሊጻፍበት እንደተዘጋጀ ልብ ልባችንን አለስልሰን ወደ እግዚአብሔር እናቅርብ

እግዚአብሔር ደግሞ ለመጻፍ አሁንም ፍቃዱ ነው። 

Page 14: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 14/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

14ww.tlcfan.org

 

“8 እነርሱን እየነቀፈ ይላቸዋልና። እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን

የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል ጌታ፤ 9 ከግብፅ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት

ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል

አልኋቸው ይላል ጌታ። 10 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና

ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ

እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። 11 እያንዳንዱም ጐረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን። ጌታን እወቅ

ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና። 12 ዓመፃቸውን

እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ደግሜ አላስብም። 13 አዲስ በማለቱ ፊተኛውን

አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።” ዕብ 8፥8-13,10፥16 

እግዚአብሔር ሌላ የሚለው ይህን ነው። መጀመሪያ ካባቶቻችን ጋር የገባው ኪዳን በትዛዛቴ

ሂዱ የሚል ሲሆን ይህ አሮጌው ኪዳን ነበር። እነርሱም በትዕዛዛቱ አልሄዱም። እግዚአብሔር አዲስን ኪዳን ገባ

ይህ ደግሞ ትዕዛዙን ቀየረ ማለት አይደለም። ነገር ግን ትዕዛዛቱ ወይም ሕግጋቱ ያው ሆኖ ሂዱ በማለት ፋንታ

በትዕዛዛቴ አስኬዳችኃለሁ ብሎ አዲስን ኪዳን ተስፋን ለሰው ልጆች አቆመ ወይም ሰጠ።

የአሮጌው ኪዳን ቃል “ሂዱ” የሚል የእኛ ሃላፊነት የሚጠይቅ ሲሆነ የአዲሱ ኪዳን ግን ከእርሱ

ሃላፊነት የሚመነጭ፣ ከእርሱ ብቃትን የሚያቀብል፣ በእግዚአብሔር ችሎታ ሃጢያትን ወደ መተው የሚያመጣ

“አስኬዳችኃለሁ” የሚል ተስፋና ኪዳን ነው። ይህም እግዚአብሔርን ከመስማት የሆነ መታዘዝ ነው። ሮሜ.1፥

5 እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከእኛ ጋር እንደገባው መሰረት ሕጉን በሚገባን መልኩ በማስተማር በትዕዛዛቱ

እንድንሄድ ያደርገናል፣ በልባችን ላይ ያለመታከት ሕጉን እንደ ፈጣን ብዕር ጸሃፊ ይጽፈዋል። 

Page 15: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 15/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

15ww.tlcfan.org

 

የምድር ክፍፍል 

እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ተስፋ በገባው መሰረት ማርና ወተት ወደ ምታፈልቀው ምድር

ሊያስገባቸው ሲል የሚገቡበትን ምድር እንዴት እንደሚከፋፈሉትና ማን እንደ ሚያከፋፍላቸው በባሪያውበሙሴ በኩል ለሕዝበ እስራኤል ማህበር (ቤተ ክርስቲያን) አስታወቀ። ሕዝበ እስራኤል በኢያሱ ምድርን

ሲከፋፈል እኛ ደግሞ በሥጋ በመወለድ ከአሁን ያለን ከምድር አፈር የተሰራውን ሥጋ ተካፈልን። ደግሞ እንደ

ትንቢቱ መሰረት ጊዜውን ጠብቀን ደግሞ አዲሱንም አካል በትንሣኤ እንደ እርሱ ያለት ትንሣኤን ከእርሱ

እንካፈላለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጣ። የታሰሩትን ነፃ እንዲያወጣ በሥጋና በደም ከእኛ ጋር ተካፈለ።

አሁን ደግሞ እኛ የትንሣኤ አካል ከእርሱ ለመካፈል ደግሞ በተስፋ በመጠባበቅ እንገኛለን። ኢየሱስ

ለእያንዳዳችን የገዛ ሥጋችን ያከፋፍለናል። 

“እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት

እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ

የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።”

ዕብ.2፥14-15 

“38 እግዚአብሔር ግን እንደ ወደደ አካልን ይሰጠዋል ከዘሮችም ለእያንዳንዱየገዛ አካሉን ይሰጠዋል።39 ሥጋ ሁሉ አንድ አይደለም፥ የሰው ሥጋ ግን አንድ ነው፥

የእንስሳም ሥጋ ሌላ ነው፥ የወፎችም ሥጋ ሌላ ነው፥ የዓሣም ሥጋ ሌላ ነው።

40 ደግሞ ሰማያዊ አካል አለ፥ ምድራዊም አካል አለ፤ ነገር ግን የሰማያዊ

አካል ክብር ልዩ ነው፥ የምድራዊም አካል ክብር ልዩ ነው።41 የፀሐይ ክብር አንድ

ነው የጨረቃም ክብር ሌላ ነው የከዋክብትም ክብር ሌላ ነው፤ በክብር አንዱ ኮከብ

ከሌላው ኮከብ ይለያልና።42 የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው። በመበስበስ ይዘራል፥ባለመበስበስ ይነሣል፤43 በውርደት ይዘራል፥ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፥

በኃይል ይነሣል፤44 ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፥ መንፈሳዊ አካል ይነሣል።

ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ።” 1.ቆሮ.15፥38-44 

“50፤ እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ

ብሎ ተናገረው።51፤ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን

በተሻገራችሁ ጊዜ፥52፤ የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም

Page 16: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 16/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

16ww.tlcfan.org

 

ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥

በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤53፤ ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት

አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም።54፤ ምድሪቱንም

በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ

ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ

ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።55፤ የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥

ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥

በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።56፤ እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ 

ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።” ዘሁ.33፥50-55 

ኢያሱ የኢየሱስ ምሳሌና ጥላ ነው። የስሙ ትርጓሜ አዳኝ ወይም ደህንነት ማለት ነው። ኢያሱ

ሕዝበ እስራኤልን ዮርዳኖስን እሻግሮ ምድሪቱን ለእያንዳዳቸው በእጣ አከፋፈለ። ይህ ኢየሱስ በሚከተሉ ሁሉ

ላይ የሚሰራ መለኮታዊ ወደ ፊት የሚፈጸም ትንቢታዊ የምድር ሕግ ነው። ዮርዳኖስ ከአዳም ጀምሮ የሚፈስ

ሞት ማለት ነው። ይህ ወንዝ ከዳም ጀምሮ እሰከ ሙት ባሕር የሚፈስ ነው። (ኢያሱ.3) ይህ ከአዳም አለመታዘዝ

ጀምሮ በስው ልጆች ሁሉ ላይ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የሞት ምሳሌ ነው። በአንዱ ሕግ አለመታዘዝ ሁሉ

ሞቱ። ዮርዳኖስ መጨረሻው የሙት ባሕር እንደ ሆነ አሁን እንኳን በማየት ልናረጋግጠው የምንችለው ነገር

ነው። ሞት መጨረሻው ሕይወት አልባ ማድረግ ነው። የሙት ባሕር በውስጡ ምንም አይነት ሕይወት

አይገኝበትም ዮርዳኖስ ስሙንም ያገኘው ከዚሁ ሳይሆን አይቀርም ነው። 

ኢየሱስ ሞትን በሞትና በትንሣኤ ድል በመንሳት አሁን እኛን ሞትን ተሻግረን የማይሞተውን

ወተትና ማር የሚያፈልቀውን የትንሳኤ አካል ሊያስወርሰን እንደ ሕጉ እየመራን ይገኛል። እያንዳንዱ የራሱየሆነውን ምድር በዚያን ጊዜ እንደተቀበለ እኛ እግዚአብሔር እንደ ወደደ የራሳችንን ሥጋ ይሰጠናል። እያንዳዳችን

የብሉይ ኪዳን ፃድቃን እነ ዳንኤልን ጨምሮ በመጨረሻው ዘመን በእጣ ክፍላችን በሆነው በትንሣኤ አካል

በምድር ውስጥ እንቆማለን። (1ቆሮ.15፥38) ዛሬ ሰላለን ደካማ ሥጋዊ አካል በምንም አይነት መልኩ ልናማረር

ፈጽሞ አይገባም። ምክንያቱም ይህ ከምድር አፈር የተበጀው ሥጋችን የተሰጠን ከእግዚአብሔር ነውና ነው።

እግዚአብሔር ደግሞ የፈጠረውን እጅግ መልካም ያለውን ከምድር አፈር ያበጀውን ሰውን ክፉ ነው መጥፎ

ነው ልንል ፈጽሞ አይገባም። አሁን ያለን ሥጋ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው።

Page 17: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 17/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

17ww.tlcfan.org

 

እግዚአብሔር በዚህ ሥጋችን ማክበር እንችላለን። ይህ የሚሞተው ሥጋችን እግዚአብሔር

እንዲከብርበት በእኛ ውስጥ በሚኖረው መንፈሱ እግዚአብሔር ለሚሞተው ሥጋችን ሕይወትን ይሰጠዋል።

(ሮሜ.8፥11) የሚሞተው በማይሞተው ይዋጣል። የሚበሰብሰው በማይበሰብሰው ይዋጣል። (ፊል.3፥21,

2ጢሞ.1፥11, 1ቆሮ. 15፥28,54) ይህ የሚከናወነው በሥጋችን ላይ ያሉትን ማንኛውም ሥጋዊ አስተሳሰብ

በማፍረስና ገድሎ በማስወገድ ወደ ትንሣኤው ወደ ታላቁ መጥራት በመምጣት ነው። ኢያሱ ከነዓን በመውረስ

በዚያች ምድር መኖርና የቻለው 31 ነገስታት ከከነአን ላይ ገድሎ በማስወገዱ ነው። እነዚህ ነገስታት ጥላነታቸው

በሥጋዊ ሃሳባችን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ባሕሪዎች ነው። ለሚሞተው ሥጋችን በእኛ በሚኖረው መንፈሱ

ሕይወትን እንዲሰጥ ከፈለግን ነገስታቱን እኛም ድል ልንነሳቸው ይገባል። እንድ በአንድ ከሕይወታችን ቀስ በቀስ

በመንፈስ በመመራት በቃሉ ሰይፍ ልናስወጣቸው ልናስወግዳቸው ይገባል።

እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤልን ምድርን ሊወርሱ በተዘጋጁበት ጊዜ እንዲህ አላቸው።

“የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር

ይሆኑባችኋል። በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን

በእናንተ አደርግባችኋለሁ።” አለ። ብዙ በሥጋችን የሚገለጠው በሽታና የጎን ውጋታችን በሥጋችን ካስቀረነው

ሥጋዊ ሃሳብ የሚመነጭ ነው። ስለዚህ ሥጋዊ ሃሳብ የእግዚአብሔር ጠላት ስለ ሆነ ልናሳድደው ይገባል። ሮሜ.8

በሥጋዊ ሃሳብ መራራት አይገባም። እግዚአብሔር አጥፋ ካለ አጥፋ ነው። ሳኦልን አሁንም ደግማችሁ አስቡት። 

ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ሕዝበ እስራኤል የእግዚአብሔር ሕግ መጠበቅ ነበረባቸው።

ይህም ከእግዚአብሔር ጋር በሲና ተራራ የገቡት ቃል ኪዳን ነው። ነገር ግን ከግብፅ የወጣ ከካሌብና ከኢያሱ

በቀር የተስፋውን ምድር የወረሰ ሰው ማንም የለም። ምክንያቱም በሕጉ ስላልኖሩ እግዚአብሔር ስላልሰሙና

ስላልታዘዙ ደግሞም እምነትን ከእግዚአብሔር በመስማት ስላላገኙ ነው። (ዕብ.4) ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ

ቃል ሁሉ ሕጉን ጨምሮ መኖሪያችን እና የእምነታችን ምንጭ ነው። ይህ ውርስና ርስት የሚበልጠው ትንሣኤ

አካል ምሳሌ ነው። ምንም እንኳን ኢያሱ ወደ ተስፋይቱ ምድር ቢያስገባቸውም ጥላ ስለ ነበር አላሳረፋቸውም።

እውነተኛው የስንበት እረፍትና የትንሥኤ አካል የሚጠይቅ ሲሆን ይህን ደግሞ የምንቀበለው በኢየሱስ በኩል

ነው። እነርሱ ቢገቡም ፍጥረታዊውን እንጂ መንፈሳዊውን አካል አይም ምድር አልወረሱም። ምክንያቱም

ኢየሱሰ ወደ ምድር መጥቶ ገና አልሞተም ነበር ደግሞም ዘመኑም ይህን የትንሣኤ አካል የምንወርስበት

ዘመንና ሰዓት አልነበረምና ነው። 

Page 18: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 18/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

18ww.tlcfan.org

 

ነገር ግን በአባቶቻችን በኢያሱ ዘመን የተስፋውን ምድር በወረሰው ሕዝብ ያለፈው እውነተኛ

ታሪክ ለትምህርታችን ሊገስጸን ሊያስጠነቅቀን ሊያዘጋጀን ለሁላችን ተጽፏል። የእነርሱን ሕይወት

ለትምሕርታችን ነው። ስለተበጀው ሥጋችንና እንዴት መውረስ እንደሚገባን በጥንቃቄ እንማራለን። ከነዓን

ምድር በኢያሱ ከመወረስዋ በፊት ያላት ማንነትና መልክ እንዲሁም የግብፅ ምድር በውርደት የሚዘራውን

የአሮጌው አሁን ያለንን ሥጋ ምሳሌ ናቸው። ኢያሱ ከወረሳት በኃላ ደግሞ ያላት መልክ አዲሱን የትሣኤውን

በክብር የሚነሳውን የክርስቶስን አይነት የትንሣኤ አካል ትመስላለች። ደግሜ እላለሁ! ሰው የእግዚአብሔር ሕግ

እየጠበቀ ቢኖር ዮርዳኖስ እንደ እግዚአብሔር ሕግ መሻገር ይችላል። ይህም የሚሆነው በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ

በመታገዝና በመንፈስ ቅዱስ በመመራት ነው። 

አንድ ሰው ወይም አማኝ ዮርዳኖስንም ተሻገረ ማለት ወረሰ ማለት አይደለም። በከነዓን ምድር

ማለት በሚሞተው ሥጋችን ምሳሌ በሆነው አካላችን ውስጥ የሚኖሩ 31 ነገስታትን አሉ። ስለዚህም በኢያሱ

(በኢየሱስ) መሪነት ልናጠፋቸው በቃሉ ሰይፍ ልንገድላቸው ይገባል። እነዚህ ሰላሳ አንድ ነገስታት በሥጋችን

ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሊጠፉ የሚገባቸው የሥጋ አዳማዊ ባሕሪዎች ምሳሌዎች እንደሆኑ ቀደም ብለን አይተናል።

ይህ እግዚአብሔር ባለመታዘዝ በአንዱ አዳም ወደ ሰው ልጆች ሁሉ የመጡ ባሕሪዎች ሁሉ የሚጠቀልሉ ናቸው።

ሰላሣ አንዱ ነገስታት ፈጸመው ሲመቱ ያን ጊዜ ከንዓንህን እንወርሳለን። የሚሞተው በማይሞተው ይዋጣል።

የክስትና ጉዞ እንግዲህ ፍጻሜው ይህ ነው። ይህ ሲሆን የሚሆነው እንደ ቀደሙ አባቶቻች ነው። ለዚህም ሕይወት

ምስክርንት ሄኖክንና ኤልያስን ማየት ይቻላል። 

“8፤9፤ እንግዲህ እንድትጠነክሩ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሻገሩባት ምድር እንድትገቡ

እንድትወርሱአትም፥ እግዚአብሔርም ለእነርሱና ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ በማለላቸው

ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ዛሬ ለእናንተየማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ።10፤ ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት

ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ

ግብፅ ምድር አይደለችም።11፤ ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት

ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት አገር ናት፤ በሰማይ ዝናብ ውኃ ትረካለች። 12፤ አምላክህ

እግዚአብሔር የሚጐበኛት አገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ

የአምላክህ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።”ዘዳ.11፥8-12 

Page 19: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 19/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

19ww.tlcfan.org

 

እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት ከንዓን ካወረሳቸው በኃላ በምድሪቱ ላይ ሊጠብቁት የሚገባ

የምድር ሕግ በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ስጥቷቸዋልና እንደ ምድር ሕግ ሊኖሩ ይገባቸዋል። እነዚህ ሕጎች

ለእኛም ዛሬ አልተለወጡም። ምክንያቱም በኢየሱስ አማካኝነት እርሱን ብቻ የምንከተል አማኞች ምድሪቱን

ወይም የትንሣኤውን አካል ለመውረስ በሂደት፣ በጉዞ ከሃጢያት ጋር ደም እስከማፈሰ በመዋጋት ላይ አሁን

እንገኛለን። ውጊያችን ግን ሥጋዊ የጦር እቃችንም እንደነ ኢያሱ ፍጥረታዊ አይደለም። ነገር ግን መንፈሳዊ የሆነ

በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ጌታች ከሰጠን በምድር ከተመሰለውና በምድር

አፈር በተበጀው አካላችን ጋር ማለት ከሥጋችን ጋር የተያያዙ የእግዚአብሔር ሕጎች አሉ። እነዚህን ሕጎች ማወቅ

በጣም አሁን ላለንበት መንፈሳዊ እድገት ትልቅ ስፍራ አለው። በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ሕጎቹን በቅደም ተከተል

እንመለከታለን። 

ስለዚህም በቃሉ ውስጥ ከምድር ጋር ተያይዘው ስለ ሥጋችን የተቀመጡ ብዙ የእግዚአብሔር

ቃሎችን እናገኛለን። የራእይ መጽሐፍ በተለይ ትልቅ ስለ ምድር የአካል ምሳሌነት በግልጽ የተቀመጠበት

መጽሐፍ ነው። ምድር የአካላችን ምሳሌና ጥላ መሆኑን መረዳት የእግዚአብሔርን ሕግ ሆነ በቃሉ ውስጥ

ያሉትን ስለምድር ወይም ስለ አካላችን የተጻፉ ቃሎችን በግልጽ መመልከት እንድንችል መረዳታችንን

ይከፍታል። 

Page 20: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 20/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

20ww.tlcfan.org

 

የምድር ሕግ 

እግዚአብሔር በምድረ በዳ ሕዝቡን ሁሉ በመራቸው ጊዜ ከሰማይ በሚወርድ እንጀራ

አኖራቸው። ነገር ግን እግራቸው ከነዓን ከረገጠችና የምድሪቱን ፍሬ ከቀመሱ በኃላ ከሰማይ የሚወርደው

እንጀራ ተቋረጠ። ከዚያ በኃላ ሕዝቡ የራሱን ምግብ ማዘጋጀት ተገባው። ይህም የሚሆነው እግዚአብሔር

የሰጠውን ማንኛውም አይነት ምድር ሰው በማረስ በመዝራትና በማጨድ ለመብል እንዲጠቀም ነው። 

እግዚአብሔር እንደተናገረው ምድር የእርሱ ስለ ሆነች ምድርን እንደ ፈለጉ ማረስ፣ ማጨድ

ወይም መሸጥ አይቻልም። በስባተኛው አመት ላይ እንደ እግዚአብሔር የምድር ሕግ መሰረት ማንኛውም ሰው

የወረሰውን ምድርን ለአንድ አመት ማሳረፍ ይጠበቅበታል። ይህም ብቻ አይደለም ምድርን የሚያርሱላቸውን

ባሪያዎች እንኳን ሳይቀር በስባተኛው አመት ያሳርፋሉ። ይህም ለአንድ አመት የሚቆይ እረፍት ነው። ይህ

ለእኛም በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚሰራ የምድር ሕግ በሲና በጌታ እንድንታዘዘው የተሰጠ ሕግ ነው። በሥጋችን

የፈለግነውን ማድረግ አንችልም። ምክንያቱም ሥጋችን የእግዚአብሔር ነው።

ዛሬ ባለንበት ዘመን ስው ሁሉ እንደ ፈለገ በሥጋው የሚያዝበትና ሥጋውን ለብዙ ነገር አሳልፎ

ሰጥቶ የምንመከትበት ዘመን ላይ እንገኛለን። ሰው በሥጋው እግዚአብሔር ማክበር ሲገባው በሥጋው ገንዘብን

ለማከማቸት ሥጋውን ያለ ልክ የሚያጎስቁልበት ለሥጋው ረፍት ያጣበት ዘመን ይህ ነው። ይህ ነገር ግን አማኞች

የእግዚአብሔር ሕግ በማወቅ ከእንደዚህ አይነት ውድቀት የሚወጣበት እድልን አሁን እግዚአብሔር በቃሉ በኩል

ሰቷል። ይህም እግዚአብሔር የሰጠውን የምድር ሕግ ለሥጋችን ምሳሌ መሆነኑ በቃሉ ተገንዝበን በንስሃ

ተመልሰን ለእግዚአብሔር ራሳችችን እድናስገዛ ነው። ሥጋ የጌታችን ነውና ለምን እያዋልነው እንዳለ ልናስተውል

ፈጽሞ ይገባናል። 

“13….ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤

14 እግዚአብሔርም ጌታንም አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል። 15 ሥጋችሁ የክርስቶስ

ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ

የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም። 16 ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ

እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና። 17 ከጌታ ጋር የሚተባበር

ግን አንድ መንፈስ ነው። 18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ

ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።

Page 21: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 21/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

21ww.tlcfan.org

 

19-20 ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ

ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ

በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” 1ቆሮ.7፥13-20 

ስለዚህም በምንገባበት ምድር/በሥጋህ/ እንደፈለግን መኖር አንችልም ምክንያቱም፦ 

“1. እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው። 2፤ ለእስራኤል ልጆች

እንዲህ ብለህ ንገራቸው። እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር

ሰንበት ታድርግ። 3፤ ስድስት ዓመት እርሻህን ዝራ፥ ስድስት ዓመትም ወይንህን ቍረጥ

ፍሬዋንም አግባ። 4፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር

ሰንበት፥ ትሁን፤ እርሻህን አትዝራ፥ ወይንህንም አትቍረጥ። 5፤ የምድራችሁን የገቦ

አትጨደው፥ ያልተቈረጠውንም የወይንህን ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት

ዓመት ይሁን። 6፤ የምድርም ሰንበት ለአንተ፥ ለወንድ ባሪያህም፥ ለሴት ባሪያህም፥

ለምንደኛውም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ይሁን። 7፤ ለእንስሶችህም፥

በምድርህም ላሉት አራዊት ፍሬዋ ሁሉ መኖ ይሁን።” ዘሌ 25፥1-21 

የእግዚአብሔር ቤትና መቅደስ ሥጋችን ነው። ሥጋችን በምንም አይነት ነገር ልናረክስ

አይገባም። ሕዝበ እስራኤል ግን ለገቡባት ምድር የሚገባትን ረፍት እንደ ሕጉ አልሰጡም። በምድራቸው

እግዚአብሔርን አላከበሩም። ምድራቸውንም ላረሱላቸው ባሪያዎችም እረፍትን የሚገባቸውን አልሰጡም።

(2.ዜና.36, ኤር.34፥8-22) በግልጽ ይናገራል። ከዚህ የተነሳ በዳዊት 38ኛው የንግስና አመት ላይ ለእያንዳንዱ

አመት የባሪያ እረፍት 1,000 ሰው ለሰባው አመት 70,000 ከእስራኤል እግዚአብሔር ቀሰፈ ገደለ። ይህ

እግዚአብሔር ምን ያህል በሕጉ የማያወላውል መሆኑ የሚያሳይ ነው። 

የወረሷት ምድር ደግሞ ለ70 ዓመት ረፍት አላረገኘችምና ለ70 አመት እንድታርፍ ሕዝበ

እስራኤልን ለ70 ዓመት ከምድሪቱ ወደ ግዞት አግዞ ወደ ባቢሎን ለባርነት አመጣቸው። ይህን በማድረጉ ምድር

ለ70 ዓመት እረፍትን በእግዚአብሔር እንድታገኝ ነበር። እግዚአብሔር ፈጥኖ ወደ ሥጋ ሞት እንዳያመጣን

ልንኖረው ልንታዘዘው የሚገባ ከሃጢያት የራቀ የሕይወት መንፈስ ሕግ ማለት ይህ ነው። ምክንያቱም ሞት

የሚገባው ሃጢያት አለ። ሞት የማይገባውም ሃጢያት አለ። ይህ ሃጢያት ደግሞ በሕጉ ይታወቃል። ይህ ምድርን

አለማሳረፍ በሰው ልጆች ላይ ያልተገባን የሥጋን ሞት የሚያመጣ እንደሆነ ከእግዚአብሔር ቃል እንማራለን። 

Page 22: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 22/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

22ww.tlcfan.org

 

“ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥

ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ። 

ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው። ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።”

(1.ዮሐ.5፥16-17)

ይህም ሃጢያት የሚታወቀው በሕጉ ነው። ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔር ባወረሳቸው ምድር 

እንደሚገባ  አልተመላለሱም።  ስለዚህም  ከምድሪቱ  ፈጥኖ  አስወገዳቸው።  ምክንያቱም  በገቡበት  ምድር 

እንደፈለጉ  መኖር  አይችሉም  ነበርና  ነው።  እኛም  እንደፈለግን  ዳግም  በተወለደው  ማንነታችንን  ልንኖር 

አንችልም።  እንደ  ፈለግን  ብንኖር  ሞት  የሚገባው  ሃጢያት  ላይ  እንወድቃለን  የወንድሞችም  ጸሎት  እንኳ 

አይመልሰንም ፈጥነን ከሥጋችን በሞት ያለ ጊዚያችን እንለያለን። 

“ጻድቅ ይሞታል ነገሩን በልቡ የሚያኖር የለም” ይላል፦ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ማለቱ ጻድቅ

ሆኖ ምን አገኘው የሚል ሰው የነገሩም ምንጭ መርምሮ የሞቱን መንስኤ የሚመረምር ሰው የለም ማለቱ

ነው። እኛ ግን በቃሉ እየመረመርን እዳገኘነው ሞት ከሚገባው ሃጢያት መካከል አንዱ በሥጋችን እንደፈለገን

መኖር ነው። ይህን እንደ ፈለግን መኖር የሚለውን በተለያየ መልኩ ልንመለከተው እንችላለን። ሰው

ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ከምድር አፈር የተበጀው አካሉን የእግዚአብሔር መቅደስ መሆኑን ባለማወቅ

በተለያየ ነገር ሲያፈርሰው የመቅደሱ ባለቤት ደግሞ ያንን ሰው ያፈርሰዋል ማለት በሞት ይሰበስበዋል ማለት

ነው። ንጉሥ ሳኦል ይህ ገጥሞት ነበር። የሳሙኤል ጸሎት እንኳን ሊመልሰው አልቻለም። 

በተጨማሪም በቆሮንጦስ ላይ ጳውሎስ ሥጋን ለሞት አሳልፎ የሰጠውን በሥጋው የከፋ ዝሙት

የሚያደርገውን ሰውም እንደ ምሳሌ መመልከት እንችላለን። ሰው በሥጋ እንደፈለገው መኖር ፈጽሞ

አይችልም። በተለይ አማኝ በደሙ ዋጋ ተገዝተናልና የራሳችን አይደለንም። ሁል ጊዜ አማኝ ሊያስብ የሚገባውበሥጋዬ እንዴት አድጌ ጌታዬን ላክብረው ብሎ ሊሆን ይገባዋል። 1.ቆሮ.3፥16-17, 5፥1-5 በሞት ከመቀጣት

በንስሃ መመለስ ማስተዋል ነው። የእግዚአብሔር ቤትና መቅደስ በሆነው አካላችን እንደ ቃሉ እንኑር። 

“14፤ ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኵሰት ሁሉ መተላለፍን

አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም የቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤት አረከሱ። 15፤ የአባቶቻቸውም

አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በመልእክተኞቹ እጅ ወደ

እነርሱ ይልክ ነበር። 16፤ እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥

Page 23: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 23/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

23ww.tlcfan.org

 

ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥

በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር። 17፤ ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም

ጕልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን

ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው። 18፤ የእግዚአብሔርንም

ቤት ዕቃ ሁሉ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የአለቆቹን

መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ። 19፤ የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፥

የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠሉ፥ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ

አጠፉ። 20፤ ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ

ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ፤ 21፤ በኤርምያስም አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል

እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥

ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች፣” 2.ዜና.36፥14-21 

ይህ ሁሉ የሚያሳየው ሰው በምድሩ ማለት በሥጋው የፈለገውን ማድረገ እንደማይችል ነው።

አማኝ ሁሉ ለሥጋው የሚገባውን እረፍትና እንክብካቤ መስጠት እንዳለበት፣ በሥጋው እግዚአብሔር ማክበር

እንዳለበት እንመለከታለን። ይህ አንዱ የምድር ሕግ ነው። ምድርህን ወይም ሥጋህን እንደ ፈለግን ስንጠቀም

እግዚአብሔር ጊዜውን ጠብቆ እንደ ሕጉ ሊፈርድ ወደ ምድርህ ወደ ሥጋችን ይመጣል።

ሕጉ ማንንም ሃጢያት የሚገባውን ሳያደርግ ዝም ብሎ ምሕረትን አይምርም። ምሕረት ግን

የሕጉ ዋነኛ ክፍል ነው። ማቴ.23፥23 ምድርን እግዚአብሔር በመፍጠሩ ባለ ሙሉ መብትና ባለቤቷ እርሱ ብቻ

ነው። ሰድስት ቀን ምድርንና በምድር ውስጥ ያለውን ፈጥሮ ለሰው በሃላፊነት እንዲኖርበት ደግሞ በዚያች

ምድር እግዚአብሔር እንዲያከብርበት ሰጠው። ምድር ከእግዚአብሔር ጋር የቀደመ ሕብረት አላት። 

ምድር ለሰው የምትገዛው እግዚአብሔር ተገዥ ካለት እንጂ ምድርን መግዛት ማንም በራሱ

አይችልም። ሥጋችንም እንዲሁ ነው። የበላይ የሌው ስው የበታች የለውም። ምድርን ለመግዛት ወይም ሥጋህን

ለመግዛትና በሥጋችን እድሜን እንድንጠግብ ከፈለግን የምድርን ሕግ ከእግዚአብሔር ጠንቅቀን ልናውቅ

ይገባል። አባትና እናታችን መንፈሳዊ አባቶቻችንን ጨምሮ ልናከብር ይገባል። ምድር የእግዚአብሔር ከመሆኗ

የተነሳ ከምድር ሰው ሁሉ የሚያገኘውን ወይም በላቡ በሥጋው ጥሮ ግሮ በላቡ ካመጣው 1/10 ኛው

የእግዚአብሔር ነው። 

Page 24: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 24/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

24ww.tlcfan.org

 

“30፤ የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር

ነው። ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።31፤ ሰውም አሥራቱን ሊቤዥ ቢወድድ፥ አምስተኛ

ይጨምርበታል።32፤ ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ

በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።33፤ መልካም ወይም

ክፉ እንዲሆን አይመርምር፥ አይለውጥም፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ

ይሆናሉ። አይቤዠውም። 34፤ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለእስራኤል ልጆች ሙሴን

ያዘዘው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።” (ዘሌ.27፥30-34) 

ምድር የእግዚአብሔር ከመሆንዋ የተነሳ እግዚአብሔር 6ቱን ቀን የሰራበትን የሰራውን ዋጋ

ማንኛውም ከምድር ዛፍ ፍሬና ዘር ከእንሰሳ የምናገኘው 1/10ኛው ለእግዚአብሔር የተቀደስ ነው። 

ከምድራችን ብቃትና ጉልበት የተነሳ የምናገኘው 9/10ኛው ደግሞ ላረሰው፣ ለኮተኮተው፣ ለተንከባከበው፣

ለጠበቀው ላረባው ሰው ነው። እግዚአብሔር የምድር ባለቤት ከመሆኑ የተነሳ ከምድር የሚገኘው ማንኛውም

አይነት ውጤት 1/10ኛው የእርሱ ነው። እግዚአብሔር አስራሩና ጥበቡ ጥልቅ ነው። እግዚአብሔር 1/10 ለምን

እንደ ጠየቀ በይበልጥ በሚቀጥሉት ክፍሎች በጥልቀት እንመልከታለን። ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀቱ

ምን ያሕል እንደ ሆነ በይበልጥ እንረዳለን። እግዚአብሔርን ከልባችን ስለ ሰጠን የአሥራት ሕግ በጣም

እንወደዋለን እናመሰግነዋለን እንዲሁም አሳቢ አባት እንዳለን በእውነት እንገነዘባለን። 

የምድር ውጤት አንድ አስረኛው ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው። የተቀደስ ማለት የተለየ ማለት 

ነው። ስለዚህ አንድ አስረኛውን ማንኛውም እግዚአብሔር የምድር ባለቤት መሆኑን የሚያምን ሰው ለይቶ 

ለእርሱ  ለእግዚአብሔር ሊቀድሰው  ይገባል።  ስንቶቻችን  የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር እንደምንስጥ

ባለውቅም የእግዚአብሔር የሆነ ነገር ሁሉ የኛ ሳይሆን የእግዚአብሔር እንደ ሆነ ልናውቅ ግን ይገባል። ሕዝበ

እስራኤል ምድር የምትሰጣቸውን የእግዚአብሔር የሆነው ባልመቀደሳቸው ለምድርም ረፍት ባለመስጠታቸው

የሆነውን ከላይ ተመልክተናል። ሕጉ ተረዳነውም አልተረዳነውም በላያዝን ላይ የሚሰራ ሕግ ነው።

ለምሳሌ የተፈጥሮ ምድር ስበትን ሕግን ብንወስድ የምድር ስበት ሕግ ስፍራ፣ እድሜ ፣ፆታ

ሳየለይ ያገኘውን ሁሉ ወደ ታች ይስባል። ሕጉም እንዲሁ ነው። ሕግ የለኝም ብንል ያለ ሕግ ይፈረድብናል

ምክንያቱም እኛ ለራሳችን ሕግ ነን። የምንሰራው ትክክል እንዳልሆነ ልቦናችን ያውቀዋል ህሊናችንም

ይመሰክርብናልና ነው። ደግሞ ሕጉ በልባችንና በአፋችን ላይ በእግዚአብሔር ለእኛ ቀርቧልና ነው። 

Page 25: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 25/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

25ww.tlcfan.org

 

“1 ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር

ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።2 እንደዚህም በሚያደርጉት ላይ

የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን።3 አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ

ያንም የምታደርግ ሰው ሆይ፥ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?4 ወይስ 

የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም

ባለጠግነት ትንቃለህን?5 ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን

ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።6 እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው

ያስረክበዋል፤ 7 በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ

የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ 8 ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች

ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።9 ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት

ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤ 10 ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ

ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው። 11

እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና። 12 ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤

ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ 13 በእግዚአብሔር ፊት ሕግን

የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና። 14 ሕግ የሌላቸው አሕዛብ

ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ 15

እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ

በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ። 16 ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል

እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።” ሮሜ.2፥1-16

ኢየሱስ አሥራትን አልሻረም አጸናው እንጂ። ይህ ብቻ አይደለም መልካም ስራ መስራት

እንዳለብንና ይህ መልካም ሥራችን ደግሞ እግዚአብሔር እንደሚያስከብር፤ ብሎም ሕጉ ብዙ የሚፈጸም ነገር

እንዳለውና በሕጉ የተፃፈው ሁሉ ሳይፈጸም ምንም ነገር ከሕጉ እንደማያልፍ አስረግቶጦ ኢየሱስ አስተምሮናል።

ሕጉን ለሰዎች ከማስተማር መቆጠብ እንደሌለብናና ማንም ሕጉ ተሽሯል ብሎ የሚያስተምር በእግዚአብሔር

ፊት ትንሽና ሲመዘን ቀሎ የሚገኝ ታናሽ ሰው እንደሚባል በማለት ኢየሱስ በማቴ.5 ላይ አስተምሮናል። ከዛም

በመቀጠል ማስጠንቀቂያ ቃል ኢየሱስ ይናገራል። ይህን ማስጠንቀቂያ ከጻፎችና ከፈሪሳዊያን ጽድቃችሁ

ካልበለጠ ወደ መንግሥተ ስማያት ልትገቡ ከቶ አትችሉም የሚል ነው። ከቶ የሚለው ቃል ነገሩን ያጠብቀዋል። 

Page 26: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 26/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

26ww.tlcfan.org

 

ጻፎችና ፈሪሳዊያን አሥራት ከከሙን ሳይቀር የሚያወጡ ናቸው። ኢየሱስ ይህን መልካም

ሥራቸውን ማድረግ ሳያቆሙ በሕግ ያለውን ዋነኛውን ነገር ማድርግ እንደሚገባቸው ባለማድረጋቸው ግን

ይገስፃቸው ነበር። እነርሱ አሥራት በማውጣት በኩል ፍጹም ነበሩ። ነገር ግን አሥራት ማውጣት ሳያቆሙ

የሕጉን ዋንኛ ነገሮችም ሊያደርጉ ሊፈጽሙት ይገባቸው እንደነበረ አስተማራቸው።

“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት

ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥

ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር፣” ማቴ.23።23 

“16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ

እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። 17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም

እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። 18 እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ

አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ። 19 እንግዲህ ከነዚህ

ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው

በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ

በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል። 20 እላችኋለሁና። ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ

ካልበለጠ፥ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” ማቴ.5፥16-20

ከምድር ሕግ ጋር የሚያያዘው ሕግ የኢዮቤልዩ ሕግ ነው። ይህንን ሕግ አዳምና ምድር በሚለው 

ርዕስ  ስር ቀጥለን አብራርተን  እንማራለን  ይህ  ከሕጎች ከሁሉ  ዋነኛ የሆነው  የምሕረት  ሕግ  ነው። ይህ  ሕግ 

ከምድር ጋር  ከአካላችን ጋር በብዙ መልኩ የተያያዘ ነው። ከሕጎች ዋነኛ ተብሎ በኢየሱስ ሰለ ተጠራ ከኢየሱስ 

ከራሱ ትምሕርት በመነሳት በዝርዝር ቀጥለን እናየዋለን። የኢዮቤልዩ ሕግ የእግዚአብሔር ምሕረትንና ፀጋውንያለክ የሚያሳይና የሚያጎላ ታላቅ የምሕረት ሕግ የእግዚአብሔር እቅድና አላማ የሚጠቀለልበት ሕግ ነው።

ምሕረት በፍርድ ላይ ይመካል የሚለው የሐዋርያው ያቆብ ቃል የሚገባን ይህን ሕግ ስንረዳ ብቻ ነው። 

Page 27: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 27/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

27ww.tlcfan.org

 

አዳምና ምድር 

እግዚአብሔር  አዳምን  ከምድር  አፈር  አበጀው  የአዳም  1/3 የሰውነቱ  ክፍል  ከምድር  አፈር 

የተበጀ ነው። አዳም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከተላለፈ በኃላ እግዚአብሔር አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ 

ሲለው  እንሰማለን።  ሰውና  ምድር  ከዘፍጥረት  ጀምረው  የተያያዘ  ነገር  እንዳላቸው  እንመለከታለን።  ሰውን 

እግዚአብሔር መጀመሪያ ሲፈጥረው የምድርና በውስጡዋ በላይዋ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ገዥ አድርጎ ነው። ሰው 

ግን ሃጢያትን ከሰራ በኃላ እግዚአብሔር ለምድር ባሪያ አድርጎ ሰጠው። 

ምድርም ከአዳም የተነሳ የተረገመች ሆነች። ነገር ግን አዳም ለምድር እንዲስራ ለምድር ታልፎ 

ተሰጠ። ምክንያቱም ከሃጢያት በኃላ የቀረበች ወዳጁ እሷና በእሷ ላይ በቀለው ዛፍ ቅጠል ነበረና ነው። አዳም 

ለምድር  ሲስራ ተገባው። በደንብ  ካልኮተኮታት፣  ካልተንከባከባት  ፍሬዋን  በፍጹም  አትሰጠውም ነበር። 

ስለዚህም ምድር ከአዳም ሃጢያት አንስቶ በሰው ላይ ገዥ ሆነች። ሰው በላቡ ሰርቶ ከእርሷ ሊበላ ተገባው።

ስትፈግም እንደ አመጸኛ ጌታ እሾክና አሜኬላ ታበቅልበታለች። ምድር ከውድቀት በኃላ ለሰው ልጆች መቼም

ምቹ ሆና አታውቅም። ይህ በሥጋችንም እንዲሁ ነው። ሰው ሩጫውን ሲጨርስ ወደ እርስዋ በመመለስ ከእርስዋ 

ጋር ይዋሃዳል። በውርደት በመበስበስ ወደ እርስዋ ይወርዳል። በእርስዋ ማንነት ውስጥ ፈጽሞ ይዋጣል። 

ወደ አዳም ልጆች ዞር ብለን ከምድር ጋር ያለን ግኑኝነት ስንመለከት አቤል በቃየን ሲገድል ደሙ 

ወደ ሰማይ እግዚአብሔር ድረስ ድምፁን አስተጋባ። ምድርም የአቤልን ደም ልትቀበል አፉዋን ከፈተች ይላል። 

ይህን ደም መቀበሏን የሕይወቱ ባለቤትነትን መብቷን የሚያሳይ ነው። ደግሞም ሁሉ ወደ ወጣበት ይመለሳልና

ነው። በእስራኤል የመስዋዕት ዘመን ሁሉ ደም ሁሉ ለምድር ተሰጠ። በመጨረሻ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ኢየሱስ 

ደሙን በምድር ላይ በማፍሰስ ሰው ከእርሱ በኃላ የስው ሕይወት በምድር ተውጦ እንዳይቀር ጌታችን በቀራኒዬ

ታላቅን ድንቅ ከምድር ባርነት ነጻነትን አደረገልን። የምድር መርገምን እሾክም በራሱ ላይ ተሸከመ። ሞት በሞቱ 

ድል  ነሳ።  ወደ  አፈር  መግባትን በምድር ውስጥ መበስበስን  ድል  ነሳ።  ኢየሱስ  ሊበሰብስ  አልቻለም።  ሰው 

ከምድር ባርነት በኢየሱስ ነፃ ወጣ። የተቀባው መበስበስን ያይ ዘንድ ፈጽሞ አይችልምና ነው። 

ቃየን ከሰራው ስራ የተነሳ ምድርም ሃይልዋን እንደማትሰጠው እግዚአብሔር ነገረው በምድር 

ላይ  ቀሪው  ዘምኑን  ሁሉ  ተቅበዝባዥ  እንደሚሆን  አስረዳው።  በሙሴ  በኩል  ለሕዝበ  እስራኤል  የመጣው 

እግዚአብሔር ሕግ ማንም ሰው ደምን እንዳይበላ ከማዘዙ በተጨማሪ ደምን ማንም በቤቱ ቢያፈስ ለምድር 

እንዲስጣት ማለት በምድር አፈር እንዲሸፈን አዟል። 

Page 28: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 28/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

28ww.tlcfan.org

 

ማንም  ሰው  ማንኛውንም  አይነት  እንስሳ  ሲያርድ  ደሙን  በምድር  አፈር  ይሽፍነው  ብሎ

እግዚአብሔር አዘዘ።  ይህ  ለሕዝቡ  ብቻ  ሳይሆን  ካህናቱ  ሳይቀር  በመሰዊያው  ላይ  ከፈሰሰው  ደም  ባሻገር 

በመሰዊያው ስር የሚፈሰውን ደም በምድር አፈር እንዲሸፍኑት ያዛቸዋል። ይህም የሥጋ ሁሉ ሕይወት በደም

ውስጥ ስለሆነና የሥጋ ሕይወት ለምድር የተሰጠ ስለነበር ነው።”የሥጋ ሁሉ ሕይወትና ደሙ አንድ ነውና ስለዚህ

ለእስራኤል ልጆች፦ የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደሙ ነውና የሥጋውን ሁሉ ደም አትብሉ፤ የሚበላውም ሁሉ ተለይቶ

ይጥፋ አልኋቸው።” ዘሌ.17፥14 

ምድር የሥጋችን አምሳል  ነች።  የምድር ሕግ ከኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ በኃላ  ወደ  እኛ አካል 

ተለውጧል። ይህም የሕጉ ትርጉም ወይም ፍቺ ነው። የምድር ሕግ ትርጉሙ አሁን የሥጋችን ሕግ መሆኑን

በማወቅ የሚጀመሪያ እርምጃ ነው።  እግዚአብሔር  በሕጉ  ስለ  ምድር  የታናገረው  ነገር  ሁሉ  ሰለ  ሥጋችን 

የተናገረው እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ። ይህን ስል ደግሞ ስለ ፍጥረታዊም ምድር ምንም ተስፋ የለም ወይም 

ስለ ፍጥረታዊው ምድር እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ወይም ሕግ የለም እያልኩ አይደለም። ይህንን ሁለቱን

ከቃሉ ውስጥ ለመለየት በሥራ የለመደ ብስለትንና መንፈሳዊ ሽምግልናን ማለት መንፈሳዊ ዕድገትን

የሚጠይቅ ነው። 

ምድር  በፍጥረቷ  የእግዚአብሔር  ክብር  ልታንጸባርቅ  የተፈጠረች  ነች።  ይህ  እውነታ  ደግሞ 

በእኛም ላይ ይሰራል። ምድር በክብሩ እንደምትሞላ፤ የእኛም አካል ክርስቶስን በመልበስ በእግዚአብሔር ክብር 

ይሞላል ክብሩን ያንጸባርቃል። ( ሰለዚህ ምድር የበለጠ ለመረዳት ዘፍጥረት በሸመገለው አይን የሚለውን ቁጥር 

አንድ መጽሐፌን ያንብቡ።)

አዳም ሃጢያትን በመስራቱ ለምድር ባሪያ፣ ለሥጋዊ ፍላጎት፣ ለአዳማዊ ባሕሪ፣ ለሃጢያት ባሪያ

ሆኖ ተሽጠ። ማንኛውም ስው አንድ ነገር ጠብቅልኝ ተብሎ አደራ ቢሰጠው የተሰጠውን አደራ ባይጠብቅ

ባለቤቱ በመጣ ጊዜ ያስቀመጠውን እንደ ነበር ሳይጎድል ካላገኘው አደራ ተቀባዩ ለባለ ንብረቱ የሚገባውን ዋጋ

ሊከፍል እንደሚገባው የእግዚአብሔር ሕግ ይደነግጋል። ነገር ግን ይህ ሃላፊነት የተቀበለ ሰው ያጠፋውን ንብረት

ለመመለስ ብቃት ባይኖረው ለባለንብረቱ እንደ ባሪያ ሆኖ እንዲሸጥ ንብረቱ የጎደለበት ሰው ያጎደለውን

እንዲገዛው ለእርሱ እንደ ባሪያ በሕጉ መሰረት ይሽጣል። የተሸጠውም ሰው የመጨረሻዋን ዋጋ ሳይከፍል

ከባርነቱ ፈጽሞ ነፃ አይወጣም። 

Page 29: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 29/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

29ww.tlcfan.org

 

“ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት፤ ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤

የሚከፍለውም ቢያጣ ስለ ሰረቀው ይሸጥ።” ዘጸ.22፥3 

“10፤ ሰው በባልንጀራው ዘንድ አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ

እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥11፤

በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል

ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት መሐላውን ይቀበል፥ እርሱም ምንም አይክፈል። 12፤ ከእርሱም

ዘንድ ቢሰረቅ የጠፋውን ያህል ለባለቤቱ ይመልስ።13፤ ተቧጭሮም ቢገኝ ለምስክር

ያምጣው፤ በመቧጨሩም ምክንያት አይክፈል።14፤ ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ

ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ፈጽሞ ይክፈለው።” ዘጸ.23፥10-14 

“ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ

የሥጋ (የምድር) ነኝ።” ሮሜ.7፥14 

እግዚአብሔር የገነት ባለቤት ነው። አዳም ግን እንዲጠብቃት ከእግዚአብሔር አደራ ተቀብሎ

ነበር። አደራውን ግን እንደሚገባ ባልመወጣቱ እግዚአብሔር እዳይበላ የከለከልውን፣ ያዘዘውን ለራሱ የለየውን

ዛፍ ፍሬ በስይጣን አነሳሽነት ዘርፏል። ባለንብረቱ የሆነው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር አልነበረም ከእርሱ ጋር

ለመሆን ሲመጣ አደራ የሰጠው ንብረት እንደ ነበር ሙሉውን አላኘውም። ከዛፉ ላይ ሁለት ፍሬ ጎድሎት ነበር።

ያን ጊዜ አዳምን እንዲመልስለት እግዚአብሔር ቢጠይቀው ኖሮ ሰርቀው የበሉትን ፍሬ ሊመልሰው ፈጽሞ

አይችልም። ሁለቱን ፍሬ በሆዳቸው ገብተው ተዋሕደው ስራቸውን ጀምረዋል። እግዚአብሔር የዛፉ ባለቤት ስለ

ሆነ አዳም እንደ ተቀበለው አደራ ጠብቆ ሰላልተገኘ ከተሰጠው ሰላጎደለ እንዲከፍልም ቢደረግ ሊከፍል

ስለማይችል እዳውን እንሰክሚከፍል ድረስ ለምድር፣ ለሞት፣ ለሃጢያት ባሪያ እንዲሆን አሳልፎ ሸጠው።

ከምድር በላብህ ትበላለህ የሚለው ቃል ለምድር እንደ ተገዛ እንደ ተሸጠ ያሳያል። የአዳም

መጋቢው ጌታ ምድር ሆነች። ነገር ግን አዳም ሳይጥር በላቡ ሳይሰራ ዝም ብላ ፍሬዋን አትሰጠውም። በጭካኔም

ትገዛዋለች ይህም ለፍቶ ለፍቶ ፍሬ ሲጠብቅ እሾክናን አሜክላን ታበቅልበታለች። በፊቱ ወዝ በላቡ እንዲበላ

ተደረገ ይህ ሁሉ እዳውን እኪከፍል ድረስ ነው። 

Page 30: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 30/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

30ww.tlcfan.org

 

“17፤ አዳምንም አለው። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም

በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም

ከእርስዋ ትበላለህ፤18፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።

19፤ ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤

ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።” ዘፍ:3፥17-19 

“16 ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት

ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ

የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።17-18 ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥

ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት

ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።19 ስለ ሥጋችሁ ድካም

እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች

አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ

አሁን አቅርቡ።20 የኃጢአት ባሪያዎች ሳላችሁ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁና።21 እንግዲህ ዛሬ

ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና።22

አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ

አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤

የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”

ሮሜ.6፥16-23 

ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ከጴጥሮስ የተጠየቀውን ጥያቄ ከመለስ በኃላ ከመልሱ በማያያዝ ሰለ

መንግሥተ ሰማያት ሕግ ፍርድ እንዴት እንደ ሆነ በምሳሌ ይመስልና ያስተምር ጀመር። ይህ ምሳሌ ከላይ

የተመለከትነውን ባለ እዳውን አዳም ሚስቱን ከእርሱ የተወለዱትን ልጆች ሁሉና እንዲገዛው የተሰጠውን

ፍጥረት ሁሉ በእዳ እንዴት እንደ ወደቁና እዳቸው ሳይከፈል መቼም ነፃ ሊወጡ እንደማይችሉ ኢየሱስ

በምሳሌው አሳየን።  ነገር ግን ከጴጥሮስ ጥያቄ ተያይዞ ይህ ትምሕርት በመቅርቡ ይህ አዳም ከልጆቹና

ከሚገዛው ፍጥረት ጋር መቼ ምሕረትን እንድሚያገኝ ኢየሱስ ሕጉን መሰረት በማድረግ ተናገረ። መጀመሪያ

ኢየሱስ በመለሰው መልስ ውስጥ ያለውን ከመመልከታችን በፊት አዳም ከእርሱ የተወለዱ የሰው ልጆች ሁሉና

ፍጥረት ለከንቱነት እንዴት እንደተገዛ በቃሉ እንመልከት።

Page 31: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 31/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

31ww.tlcfan.org

 

“21 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ

ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።22 ኢየሱስ እንዲህ አለው። እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ

እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን

ንጉሥ ትመስላለች።24 መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን

አንድ(አዳም) ሰው ወደ እርሱ አመጡ።25 የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ (አዳምና

ሔዋን) ልጆቹም (እኛ) ያለውም ሁሉ(ፍጥረታት) እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።

26 ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና። ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።27

የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት።28 ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ

ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና። ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና

አነቀው።29 ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ። ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ

ለመነው።30 እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።31

ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ

ለጌታቸው ገለጡ።32 ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ። አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ

ሁሉ ተውሁልህ፤33 እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ

አይገባህምን? አለው።34 ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ

ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።35 ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ

ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል፣” 

ማቴ.18፥21-35

“20 ፍጥረት ለከንቱነት(ባሪያ ሆኖ)ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ

አይደለም፤21 ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር

ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።22 ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ

በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።23 እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ

በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን(የስጋችን) ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን

ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።24 በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር

ቢታይ ተስፋ አይደለም፤የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?”

ሮሜ.8፥20-24

Page 32: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 32/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

32ww.tlcfan.org

 

ኢየሱስ የተናገረው ነገር ቀላል አይደለም። ነገር ግን የሁሉ ቁልፍ የሆነውን የሕጉ ዋንኛ የሆነውን

በፍርድ ላይ የሚመካውን ምሕረትን ነው። ይህ እውነት ደግሞ ከላይ እንዳየነው የሕጉ ዋነኛው ክፍል ነው። ሕጉ

ትሁታንን ይምራል ትዕቢተኞችን ግን ይቃወማል። ትሁታን የሚታወቁት መሃሪዎች በሆናቸው ነው። ኢየሱስ

ወንድሙን ይቅር የማይል በማለት ከእኛ ጋር ያያይዘዋል። ኢየሱስ ባልጀራችንን እንድንወድና እንድንምር

ይፈልጋል። ይህ ከባርነት የመውጫ ቁልፎች መካከል አንዱ ነው። 

ጳውሎስ ይህ ባርነት ፍጥረትን ብቻ ሳይሆን ሥጋችንን ጭምር እንደያዘ ይናገራል። ከዚያም

በማያያዝ ተስፋ እንዳለ ይናገራል ይህም ተሰፋ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ሊፈጽመው የገባው ተስፋ ነው።

ይህን የሰውነታችንን የሥጋችንን ቤዛ እስከምንቀበል ድረስ ግን በተስፋ እንደዳንን ይናገራል። ተስፋው ደግሞ

ገና እንዳለተገለጠ ያስረዳናል። ምክንያቱም የሥጋችንን ቤዛነት ተቀብለን ቢሆን ኖሮ ተስፋው ተስፋ ሊሆን

አይችልም። የሚታይ ነገር ተስፋ ሊባል ሰለማይችል ነው ብሎ ሁሉን በግልጽ ያስረዳናል። 

“8 ነገር ግን መጽሐፍ። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ

መልካም ታደርጋላችሁ፤9 ለሰው ፊት ግን ብታደሉ ኃጢአትን ትሠራላችሁ፥ ሕግም እንደ

ተላላፊዎች ይወቅሳችኋል።10 ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም

ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ። አትግደል ብሎአልና፤11

ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል።12 በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ

ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ።13 ምሕረትን ለማያደርግ

ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።” ያቆብ.2፥8-13 

ኢየሱስ ለጴጥሮስ የተናገረው የምሕረት ሕግ ሚስጥር እንዲህ የሚል ነው። “በዚያን ጊዜ

ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።

ኢየሱስ እንዲህ አለው። እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።” 70 x 7 = 490 ጊዜ አለው።

ይህንን ቁጥር ለመረዳት አንድ የእግዚአብሔር ሕግ መመልከት ይኖርብናል። ኢየሱስ የተናገረውን ለመረዳት

የራሳችንን አዕሮ ሃሳብ መከተል አይገባንም። ይህም ቁጥር የተያያዘው ከኢዮቤልዩ ሕግ ጋር ነው። ይህ የምድር

ዋንኛው ሕግ ሲሆን የእግዚአብሔር ፀጋ ያለልክ ጎልቶ የሚታየው በዚህ ሕግ ውስጥ ነው። ምሕረት በፍርድ

ሲመካ የምንመለከተውም በዚህ ሕግ ውስጥ ነው። ይህ ሕግ የበራለትና የተፈታለት ሰው ሁሉ የትህትናን

መንፈስና ፍፁም የአዕምሮ ረፍትንና ሰላምን ይቀበላል። ይህን ሕግ ቀጥለን እንመለከተዋለን። 

Page 33: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 33/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

33ww.tlcfan.org

 

የኢዮቤልዮ ሕግ 

“8፤ ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቍጠር፤ የሰባት ዓመታትም

ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቈጥራለህ። 9፤ ከዚያም በኋላ በሰባተኛው ወር

በአሥረኛው ቀን በቀንደ መለከት ታውጃለህ፤ በማስተስረያ ቀን በምድራችሁ ሁሉ

በቀንደ መለከት ታውጃላችሁ። 10፤ አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም

ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ነው፤

ሰው ሁሉ ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለስ።11፤ ያ አምሳኛው ዓመት ለእናንተ

ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፥ የገቦውንም አትጨዱ፥ የወይኑንም ፍሬ አታከማቹ።

12፤ ኢዮቤልዩ ነውና የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ በሜዳ ላይ የበቀለውን ብሉ። 13፤

በዚች በኢዮቤልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመለሳል።” ዘሌ.25 

እግዚአብሔር ሕግ የሆነው ኢዮቤልዩ ከመዋጀት ሕግ ጋር የተያያዘ የምሕረት ሕግ ነው። አንድ

እስራኤላዊ በእዳ ሆነ በድህነት ምድሩን ቢያጣ። ምድሩን ለመመለስ ምድሩን ለገዛው በባርነት ያገለግለል።

ይህም እዳውን ለመክፈል ነው። ነገር ግን ይህ ሰው እዳውን ሊከፍል ባይችል ምን ያህል ያልተከፈለ እዳ ቢኖርበት

ወደ ርስቱ መመለሱ እንደ ሕጉ ፈጽሞ አይቀርም። ለዚህ ነው የትንሣኤ አካል ለሁሉ የሚሰጠው። ሃጢያንም

ሆኑ ጻድቃን ይህ የትንሣኤ አካል ይወርሳሉ። ነገር ግን እንያንዳንዱ በራሱ ሰዓትና ጊዜ ይቀበላ። ይህም

በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛው ትንሣኤ ነው። ስለ ትንሣኤ የበለጠ እውቀት ከፈለጉ ትንሣኤ ሙታን

የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡ። ሃጢያን ግን በፍጻሜው ወደ ነጩ ዙፋን ፍርድ ሲያልፉ ጻድቃን ወደ ሕይወት

ይገባሉ። 

“በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይቤዥ በኢዮቤልዩ ዓመት እርሱ ከልጆቹ ጋር ይውጣ።”

ሌዋ.25፥54 

ይህ ሕግ በመቤዥት ዘመን ምድሩ ሳይቤዥ ለሚቀር ሰው የምስራች ነው። ኢዮቤልዩ እንዲህ

ያለውን ሰው በመጨረሻ ወደደም ጠላም ነፃ ያወጣዋል። ምክንያቱም ይህ የምሕረት ሕግ በፍርድ ሁሉ ላይ

ይመካልና ነው። ይህ ሰውም ለምን አልተቤዠህም አይባልም። ነገር ግን ወደ እዚህ አይነቱ ነፃነት የሚደርሰው

የኢዮቤልዩ ዘመን ሲመጣ ነው። ይህን የኢዮቤልዩ የምሕረት ሕግ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃዊያን መሪዎች ትተውት

ነበር። ዛሬም በዚህ ዘመን እንዲሁ ነው።

Page 34: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 34/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

34ww.tlcfan.org

 

ይህ ሕግ እንዳለ የሚያውቁ በተለይ ደግሞ የሕጉ ትርጉም በመንፈስ የተፈታላቸው ሰዎች

ጥቂቶች ናቸው። በማቴ.23፥23 ስላለው ቃል በአሁን ዘመንም ያሉ ሃይማኖት መሪዎች በይበልጥ ስለዚህ

የምሕረት ሕግ ያላቸው እውቀት በጣም ውስን ነው። እንደ ጴጥሮስ ግን ጌታን በመጠየቅ ሊማሩ ይገባቸዋል።

የሚጠይቅ ይማራል ኢየሱስን በ12 ዓመቱ የነበረውን ሕይወት ለመማር በመፈልግ ይጠይቅ ነበር። የራሳችንን

እድሜ ስናይ በጣም የሚያሳፍር አይመስላችሁም። የማያውቁትን ጠይቆ መማር ማስተዋል ነው። 

ይህ የኢዮቤልዩ ሕግ ፀጋውን በከፍተኛ ጉልበቱ ይገልጸዋል፣ ያሳየዋል፣ ያንጸባርቀዋል። ማንም

ሰው ይህን ሕግ አልፎ ምድሩን (ሥጋውን) ለጥፋት አሳልፎ ሊሰጥ ሊጠፋው ሆነ ለዘላለም ሊሸጠው አይችልም።

መገኘት ተፈቅዶልናል መጥፋት ብትፈልግም የለም። ምክንያቱም ምድር ሆነ የሰው ሥጋ የእግዚአብሔር ነው።

አንተም የእግዚአብሔር ነህ/ነሽ። ኢዮቤልዩ ይህን ነጻነት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን የግድ እንዲሆን ይጠይቃል ያዛል፣

ይወስናል፣ ቀን ቀጥሮ ይህ ዘመን እስኪፈጸምና ሁሉ ነፃነቱን እንስከሚቀበል ይጠብቃል። 

እንደምናየው ብዙ ሰዎች የክርስቶስን የመቤዥት ስራ ያልተቀበሉና ሳይቀበሉ በሥጋም የሞቱ

በምድር ያለፉ ሃያሌዎች ናቸው። ሳይቀበሉ የሞቱት መጨረሻቸው ምንድን ነው? ለዘላለ እስከ ዘላለም መጥፋት

ነውን? ወንጌል የመስማት እድል ሳያገኙ የሞቱስ? ሕጻናትስ? ለሃጢያት፣ ለሞትና ለሥጋ ባሪያ ሆነው ለዘላለም

ይቀራሉን? መልሱ በፍጹም ይህ በሁሉ ላይ አይሆንም ነው። ሕጉ ስለባርነትና ስለ እዳ የሚናገርው ብዙ

የምሕረት ሕግና ፍርድ አለው። ይህም የፀጋ ሕግ የሆነው ኢዮቤልዩ ነው። 

“ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።

ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥

በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው።” 1.ቆሮ.15፥22-23 

“31 እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ 

እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። 32 እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ 

ዘግቶታልና። 33 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ …

…..ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። 34 የጌታን ልብ ያወቀው

ማን ነው? 35 ወይስ አማካሪው ማን ነበር?  ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ 

የሰጠው ማን ነው? 36 ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ 

ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን፣” ሮሜ.11፥31-36 

Page 35: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 35/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

35ww.tlcfan.org

 

“ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ 

በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።” 1.ጢሞ.2፥3-4 

“9 ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥

ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን 

በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።11-12 ይህን እዘዝና አስተምር።

በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥

ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።” 1.ጢሞ.4፥9-12 

ይህ እኛ የተማርንበትን ምሕረት እነርሱ ደግሞ በኢዮቤልዩ ምሕረትን ያገኛሉ። ይህም

የሚሆነው እግዚአብሔር ከሰጠው ኢዮቤልዮ ሕግ የተነሳ ነው። ኢዮቤልዮ ይህ ነገር ለእነርሱ እንዲሆን ያዛል።

ይህ የእግዚአብሔር የፀጋው ባለጠግነት ክብር ማሳያ የሆነ የጽድቅ የእኩልነት አድሎ የሌለበት ስራው ነው።

ኢዮቤልዩ የእግዚአብሔር ፀጋ ከነሙሉ ጉልበቱ ይገልፀዋል። ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም።

ከሚምር ከአንዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው። 

እግዚአብሔር ሕግ ምሕረት አልባ አድረገው የሚያምኑ በሕጉ ያለውን ዋና የሆነውን ፍርድ ላይ 

ሳይቀር የሚመካውን ከእግዚአብሔር ታማኝነት የተነሳ የሚሰራውን የሕግ መንፈስ የሳቱ ሰዎችን ብቻ ናቸው።

ጳውሎስ ይህን የእግዚአብሔር ሕግ መርህ ጠንቅቆ ያውቃል። ፍጥረት ሁሉ ግን በመቃተት ላይ እንደሚገኝ ወደ 

እዚህ ነፃነት እንዳልደረስ ሳይጠቁም አላለፈም። ይህ ነጻነት ግን በዘመኑ ፍጻሜ በእግዚአብሔር ይታወጃል። 

“21 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ

ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።22 ኢየሱስ እንዲህ አለው። እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ

እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን

ንጉሥ ትመስላለች።24 መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን

አንድ(አዳም) ሰው ወደ እርሱ አመጡ።25 የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ (አዳምና

ሔዋን) ልጆቹም (እኛ) ያለውም ሁሉ(ፍጥረታት) እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።

26 ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና። ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።27

የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት።28 ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ

ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና። ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና

Page 36: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 36/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

36ww.tlcfan.org

 

አነቀው።29 ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ። ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ

ለመነው።30 እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።31

ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ

ለጌታቸው ገለጡ።32 ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ። አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ

ሁሉ ተውሁልህ፤33 እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ

አይገባህምን? አለው።34 ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት

አሳልፎ ሰጠው።35 ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ

የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።” ማቴ.18፥21-35 

Page 37: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 37/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

37ww.tlcfan.org

 

በ490ኛው ዘመን የሚደረግ ምሕረት 

ከላይ በማቴ.18፥21-22 ኢየሱስ እዚህ ጋር በእኔ አጠራር የተወደደ  ዘመን የምለውን ቁጥር 

ሲገልጽ  ነው። ይህ ዘመን የእግዚአብሔርን ትግስትና ታማኝነት ምሕረት የሚያሳይ ነው። ይህም የሚሆነው

ኢዮቤልዩ ከሚባለው የእግዚአብሔር ሕግ በመነሳት ነው። ሰው ሃጢያትን ሲሰራ እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ

አይገድለውም። ሰዋዊ ሰዎች ግን ሰው ሃጢያት ሲሰራ እንዲሞት ወዲያው ይፈልጋሉ። ይህ እንደ ጴጥሮስ

የምሕረትን ሕግ ሚስጥርና ዘመን ቁጥር ካለማወቅ የሚመጣ እኩልነት ነው። 

490 ዓመት አስር ኢዮቤልዩዎች ናቸው። ይህ የሕጉ በቁጥር ውስጥ ለሰው ልጆች ተጠብቆ

የተቀመጠ ትንቢት ነው። ይህ ቃል ለምክርና ለትምህርታችን ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ

ውስጥ ሦስት ጊዜ ጽፎ አስቀምጦልናል። ሦስት ጊዜ በመጻፉ ደግሞ ጽኑ ምስክር ነው። በዘፍ.4፥24, ማቴ.18፥

22, ዳን.9፥24 ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን። የመጨረሻው የፍጥረት ኢዮቤልዩ ወይም ነፃነት የእግዚአብሔር ሕግ

መንፈሳዊ ግቡ ነው። ይህ በእግዚአብሔር የዘመን አቆጣጠር መሰረት ነው። የእግዚአብሔር ዘመን አቆጣጠር

በሚለው መጽሐፌ ላይ ሰለ እግዚአብሔራዊ የዘመን አቆጣጠር ከዘፍረት ጀምሬ በቅደም ተከተል

አስቀምጫለሁ። ሰለዚህ ስለ ዘመን ወይም ስለ እግዚአብሔር ካላንደር በዚህ ላይ ብዙ አልናገርም። እኔ

ባደረኩት የዘመን ጥናት ላይ ከአዳም መፈጠር ጀምሮ ስንቆጥር በ1986 ኤ/አ ላይ 120ኛው ኢዮቤልዩ ነበር።

ይህም ከአዳም መፈጠር ጀምሮ ተነስተን ብንቆጥር የምናገኘው ዘመን ነው። 

ይህን በፍጥረት ቀኖች ሚስጥር ስናየው ደግሞ የስድስተኛው ቀን ሥራ መጠናቀቂያው ዘመን

አቅራቢያ የሆነ ነበር። ይህም 5,880 ዓመት ከአዳም መፈጠር አንስቶ ነው። ነገር ግን የስድስተኛው ቀን ሥራ

እዲፈፀም መሆን ያለበት 6.000 ዓመት ነው። (ሰለ ስድስተኛው ቀን ስራ በዝርዝር ለማወቅ ዘፍጥረት

በሸመገለው አይን የሚለውን ቁጥር አንድ መጽሐፌን ያንብቡ)

እንግዲህ ወደ ስድስተኛው ቀን ሥራ ዝግጅት ውስጥ ገብተናል ነገር ግን ገና ሙሉ ቀን አልሆነም

ማለት 6,000ጨ ውስጥ አልገባንም ደግሞ እርሱን ጨርሰን ወደ 7,000 ዓመት ወደ ሰንበት እረፍት ዘመን

አልደረስንም። ብንደርስ ኖሮ ወደ እረፍቱ እንገባ ነበርና ነው። ሰባተኛው ሺ የፍጥረት የሰንበት እረፍት ሰይጣን

ለ1,000 የሚታሰርበት የንግሥና የሃሴትና የእረፍት ዘመን ነው። ይህን የምንመለከተው አንድ ቀንን እንደ 1,000

ዓመት እያየን በዘፍጥረት አንድ ውስጥ ያለውን የፍጥረትን ትንቢታዊ ሚስጥር በመግለጥ ስንተረጉምና ስንረዳ

ብቻ ነው። 

Page 38: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 38/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

38ww.tlcfan.org

 

ፍጥረት 49,000 ኢዮቤልዩ ሲያልቅ ወደ ሙሉ ነፃነት እንደሚገባ እንደእግዚአብሔር ሕግና

ተስፋ ቃል ሙሉ እምነቴ ነው። ይህም ከዳም መፈጠር ከ50,000 ዓመት በኃላ ነው። (1,000 x 49= 49,000)

ሲሆን 1,000 ዓመት የዝግጀት ነው። አሁን ያለነው ግን ገና ወደ 6,000 ውስጥ የመግባት ዝግጅት ላይ ነው።

ስድስተኛው ቀን ወይም ሺ ዘመን የሰው ልጅ መልክ በእግዚአብሔር አምሳል የሆነው መልካችን መገለጥ

የሚጀምርበት ዘመን ነው። 

ኢየሱስ ጴጥሮስን 490 ጊዜ ይቅር ማለት እንደሚገባው ነገረው። ይህን ለማብራራት ወዲያው

ኢየሱስ ከጥያቄው በቀጠል ምሳሌን ይመስል ጀመር። የማቴ.18፥21-35 ይህ በጣም ወሳኝ የሆነ ምሳሌ ነው።

ኢየሱስ በዚህ ምሳሌው ውስጥ በሕዝቡ ላይ በታሪክ ውስጥ የሚሆነውን ሁሉ በአንድ አጭር ታሪካዊ ምሳሌ

አስቀምጦታል። 

ይህ በኢየሱስ እንደ አዳም የተመሰለው ሰው ያለበት እዳ በጣም ብዙ በመሆኑ ሊከፍለው

የማይችለው ሰለ ሆነ የግድ ይህ ሰው ወይም አዳምን እስከ ትውልዱ ነፃ ለመውጣት የኢዮቤልዩ ሕግ መፈጸሚያ

ዘመን 490 ቀን መጠበቅ ይገባዋል። ኢየሱስ ከዚህ ቀደም ብሎ ሃጢያት ማለት እዳ እንደ ሆነ በስለ ጸሎት 

ባስተማረው ትምህርቱ ላይ አስተምሯቸዋል። ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማረውን የጌታ ጸሎት የሚባለውን

በእንግሊዘኛው ብትመለከቱት ይህን በቀላሉ ያረጋግጣሉ። በደላችን ወይም እዳችንን ይቅር በለን ብሎ በሁለት

ሃሳን አስተሳስሮ ያስቀምጠዋል። 

ይህ ታላቅ እዳ ያለው ሰው ታላቅ ሃጢያት የሰራው ሰው አዳም ነው። ታሪኩ ግን ሰለ ባሪያው

ሰለሚናገር ባሪያው ሊከፍል 490 ቀን አለው። ይህ 490 ቀን መሃል ላይ የሚከፍልለት ቢያገኝ ነፃ ይወጣል።

ካልሆነ ግን ነፃ ለመውጣት 490 ቀን መጠበቅ ይገባዋል። ይህ ንጉሥ እዳው እንዲከፈለውና ምህረትን

እንዲያደርግ ዘመንና ጊዜን ወስኗል። ይህን 490 ዘመን የፀጋው ሙላት ዘመን እንለዋለን። ይህ የፀጋ ዘመን

ሙላት እዳን ለመክፈል የተሰጠ በንጉሱ የተወሰነ ዘመን ነው። ጴጥሮስ የዚህ ዘመን ሚስጥር እውቀት እንሶት

እናገኘዋለን። ምክንያቱም እርሱ ይቅር ሊል የፈለገው ሰባት ጊዜ ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ የኢዮቤልዩ ሕግ እውቀት

እንደሌለው በኢየሱስ ፊት ባዶ ማድጋውን አሳየ ኢየሱስም የእውነት ዘይት እውቀትን ከእግዚአብሔር ሕግ

ሞላለት።

Page 39: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 39/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

39ww.tlcfan.org

 

ኢየሱስም በማታውቀው ነገር የሚከስ አምላክ ስላልሆነ ጊዜ ሳይሰጥ ጴጥሮስን ማስተማር

ጀመረ። ይህን ጥያቄ ጴጥሮስ ባያቀርብ ኖሮ እኛም ይሄኔ የኢዮቤልዩ ሚስጥር እውቀት የጎደለን እንሆን ይሆን

ነበር ብዮ አምናለሁ። በሕጉ መሰረት ሦስት የእረፍት ጊዜዎች አሉ። 7ኛ ቀን፣ 7ኛ ዓመትና 7 x 7 የኢዮቤልዩ

ዓመት ናቸው። የሰባተኛ ቀን እረፍት ወሳኝ ረፍት ነው። በዚህ ቀን ባሪያዎች፣ አገልጋዬች እንስሳት ሳይቀሩ እረፍት

ይሰጣቸዋል። ይህ በእዳ የተያዙትንም ባሪያዎች ሁሉ የሚጨምር ለሁሉ የሆነ እረፍት ነው። 

ሰባተኛው ዓመት እረፍት ደግሞ የምድር እረፍት ነው። ዘሌ,25፥4-5 ደሆች በዚያን ጊዜ በምድሩ

ላይ የበቀለውን ይበላሉ። ይህም ዘር ራሱ ምድር የሚያበቅለውን እንጂ ማንም በምድር አይዘራባትም። ዘጸ23፥

11 በሬ እረፍት ይሰጠዋል ከሥራና ከእስራቱ ይፈታል። ወደ ሜዳም ይለቀቃል እርሱም እንደ ደሃው በምድሩ

ላይ የበቀለውን ይመገባል። ዘጸ.21፥2 ይህም ለሰራተኞች ትክክለኛ እረፍት ለመስጠት ነው። ይህም ደሞዛቸው

ሳይቆረጥ ነው። ይሁንና በእዳ የተሸጠ ባሪያ የሆነ ሰራተኛ የእረፍቱ ዓመት ሲያልቅ ተመልሶ ባርነቱን ይቀጥላል።

ይህም እዳውን እስከሚከፍልበት ቀን ድረስ ነው። እነዚህ እዳ ከፋዮች ኢዮቤልዩ እስኪመጣና ነፃ

እስከሚወጡበት ሰዓት ዓመትን ድረስ በየመሃሉ ያርፋሉ ማለት ነው። ይሁንና እነዚህ የሳምንቱ ሆነ የሰባቱ

ዓመት እረፍት የኢዮቤልዩ እረፍት ቅምሻ እንጂ ዘላለማዊ የሆነ እረፍትና ነጻነት አይደሉም። 

በመሃል ግን እዳቸውን ከጨረሱ ወይም የሚበዥ ወንድም ካገኙ ነፃ ይወጣሉ። ካልጨረሱ

የሚቤዥ ካላገኙ 7ኛውን አመት እረፍት እደ ጨረሱ ወደ ጌታቸው ይመለሳሉ። ባሪያዎቹ እንደገናም እስከ

ኢዮቤልዩ ዘመን ስረስ በባርነት የገዛቸውን ያገለግላሉ። የስባተኛው ዓመት ረፍት ከስባተኛው ቀን ረፍት ይልቅ

በጣም የከበረ ነው። ነገር ግን እጅግ እጅግ የከበረው እረፍት ግን የኢዮቤልዩ እረፍት ነው። ይህ 50ኛው ዓመት

እረፍት ከ49 የእረፍት ዓመት በመጀመር በ50 ዓመት እስኪፈጸም የሚሆን ኢዮቤልዩ ሲሆን ሙሉ እዳ

የሚደመስስበት ዓመት ነው። 

በ50ኛው ዓመት ማንኛውም ሰው ከባርነት ነፃ ይወጣል። ማንኛውም የተሸጠ መሬት ወደ

ባለቤቱ ይመለሳል። ይህ ነው የኢዮቤልዩ እረፍት እጅግ ከሌሎቹ እረፍቶች የሚያከብረው። ሙሉ ምሕረት ሙሉ

ነፃነት የሚታወጅበት ቀን በመሆኑ ነው። ይህ ሰው የሚቤዥው ወንድም አገኘ አላገኘ በዚህ ዘመን አጠያያቂ

አይደለም ዋናው ዘመኑ ኢዮቤልዩ መሆኑ ነው። ያኔ ምንም እንኳን እዳውን ያልጨረሰው ያልከፈለው እዳ ቢኖር

እንኳን በነፃ ወደ ምድሩ ይመለሳል ሁሉ ይደመሰስለታል። እስቲ ለጥቂት ጊዜ እራሳችንን እንደ ባሪያ አድረገህ

እንመልከት ያን ጊዜ 50ኛውን ዓመት የመናፈቅ መንፈስ ምን እንደ ሆነ ማየት ትችላላችሁ። 

Page 40: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 40/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

40ww.tlcfan.org

 

በ50 ዓመት በኢዮቤልዩ ሁሉ በአዲስ ነፃነት ወደ አዲስ ሕይወትና ኑሮ ይገባል። ፍጥረት

ለእግዚአብሔር ልጆች እንደሆነ ሁሉ ወደ አርነት ይፈታል። ከዚህ በፊት ያሉት ሁለት እረፍቶች እዳ ያለበትን ሰው

ፋታ ለጥቂት ጊዜ የሚሰጡ ሲሆኑ ይህ የ50ኛው ዓመት እረፍት ግን ፈጽሞ ሙሉ ነፃነትን የሚያቀዳጅ ነው።

ይህ ሰው ከዚያን በኃላ እዳው ለዘለለም አይታስብበትም ፈጽሞ ጌታው የእዳውን ድህፈት በዚያን ቀን ቀዶ

ያጠፋዋል። ጌታውም ባሪያውን ነፃ ነህ ምንም እዳ የለብህም ይለዋል። ሰውየውም ምድሩን በድህነት ወይም

በእዳ ሸጦት ቢሆን እንኳን ወደ ሸጠው ምድር ይመለሰል። ሁሉ ይታደሳል ሁሉ እንደ መጀመሪያው ይኖራል።

ሁሉ ወደ ወጣበት ይመለሳል። 

ኢየሱስ ይህን ትምህርት በሚያስተምርበት ወቅት የሳምንቱን የሰበት እረፍት እያደረጉ ነበር። 

ደግሞም ከባቢሎን ግዛት 534 B.C ከ70 ዓመት በኃላ ተመልሰው እረፍት እያደረጉ ሰለነበር እየሱስ የሚናገረው

ነገር ወዲያው እደሚገባቸው እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን ይህን ሕግ የሁልጊዜ የሕይወታቸው መርህ አድርገው ይኖሩ

አንዳልነበረ ግን ከጴጥሮስ ጥያቄ በመነሳት እንረዳለን። ለዚህ ነው ጴጥሮስ ሰባት ጊዜ ብቻ ያለው። ይህ ሕግ

በምን ሁኔታ እንደሚተገበር ወይም ትንቢታዊ አስራሩን በታሪክ ውስጥ መመልከት ተስኗቸው ነበር። 

ኢየሱስ ግን ይህን የኢዮቤልዩ ሕግ ከ50 ወደ 490 ወሰደውና የጠቅላላውን ፍጹሙን ምሕረትና

ነፃነት አሳያቸው። ኢየሱስ እግዚአብሔር ለኢዮቤልዩ ያለውን የተሰወረ የዘመን ሚስጥር ለጴጥሮስ ገለጠ እኛም

ይህን ለመማር በቃን። 490 ዓመት 10 ኢዮቤልዩ ነው። ይህን ኢየሱስ የገለጸው ለእኛ ያበራው በመጽሐፍ ቅዱስ

ያለውን ትንቢት ሕይወት ለመስጠት ነው። ይህን ለማረጋገጥ የዳንኤልን ትንቢት መመልከት እንችላለን። 

የዳንኤል 70 ሳምንት 490 ዓመት ነው። ብዙዎች የእግዚአብሔር የኢዮቤልዩ ሕግ ካለማወቅ

የተነሳ 490 ውን ዓመት በዳንኤል ትንቢት ያለውን ምን እንደሆነ አይገነዘቡትም ወይም በእነርሱ ዘንድ የጎላ

ስፍራ የለውም። ነገር ግን የኢዮቤልዩ ሕግን ሚስጥርና ትርጉም እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ለቆልናል። ይህን

ሕግ በግል ሕይወታችን ለመተግበር የጠለቀ ሕግ ጥናትና ከመንፈስ የሆነ መለኮታዊ መገለጥ ይጠይቃል። በሕጉ

የተፃፈ ሊተረጎም ይግባዋልና የሚተረጉመ ጌታ ጋር እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ማድረግን የሚጠይቅ

ነው። ይህ የነፃነት ሕይወት ከአሁኑ ለመለማመድና ለመኖርም በመንፈስ መመራትንና አዳዲስ የሆነ የሰማይ

እንጀራን መመግብ ይጠይቃ።

Page 41: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 41/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

41ww.tlcfan.org

 

ኢዮቤልዮ ብርቱ የሆነ የምሕረት ፀጋ ሕግ እንደሆነ ካወቅን ለጊዜው ይበቃናል። በመንፈስ

የጎለበትን ግን በዚህ እንዳንገደብ ወደ ውስጥ ጠለቅ ብለን ቃሉን እንድመረምር አበረታታለሁ። መንፈስም

በእኔው ውስጥ ሆኖ ሰዎችን እየጋበዘ እንደሆነም በመንፈሴ ያደረው መንፈስ ቅዱስም በሕሊናዬ

ይመሰክርልኛል። 

21 እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም 

ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።……25 እርሱም። እናንተ 

የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤26 ክርስቶስ ይህን 

መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።27 ከሙሴና 

ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።…….30

ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤

31 ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።32 እርስ በርሳቸውም። 

በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?

ተባባሉ።…… እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ 

እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።

45.በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፣

ሉቃ.24፥21-32 

Page 42: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 42/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

42ww.tlcfan.org

 

የመቤዠት ሕግ 

እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሃጢያት እዳ እንደ ሆነ በብዙ ስፍራ እናገኛለን። ለምሳሌ

ሰው በመስረቅ ሃጢያትን ሲስራ የሰረቀው ሰው ለተሰረቀው ሰው ያለበትን እዳ እንዲከፍል ይደረጋል። የሰረቀውነገር እንደ እዳ ይሆነበታል። ይህን እዲከፍል ሲደረግ የመመለስ ሕግ ይባለል። ይህ ራሱን የቻለ ሌላ

የእግዚአብሔር ሕግ ነው። ይህ የመቤዠት ሕግ ከመመለስ ሕግ ጋር የተያያዘ ነው። አንድን ሰው መቤዠት ማለት

የእዳ መዝገባቸውን መግዛት ማለት ነው። ኢየሱስ ከሃጢያታችን ሊቤዥን ወደ እኛ መጣ። መጥቶም እዳችንን

በሙሉ ከፈለ፣ ለሃጢያታችንን የሚገባውን ዋጋ ከፈለ፣ ኢየሱስ እኛን ሰለተቤዠ በሕጉ የተሰጠውም መብት

አለ። ይህም መብት እንደ ቃሉ እንደ ሚከተለው ይነበባል፦ 

“47፤ በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ 

አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥48፤ 

ከተሸጠ በኋላ መቤዠት ይችላል፤ ከወንድሞቹ አንዱ ይቤዠው፤49፤ ወይም አጎቱ ወይም 

የአጎቱ ልጅ ይቤዠው፤ ወይም ከወገኑ ለእርሱ የቀረበ ዘመድ ይቤዠው፤ ወይም እርሱ እጁ 

ቢረጥብ ራሱን ይቤዠው። 50፤ ከገዛውም ሰው ጋር ከገዛበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ 

ዓመት ድረስ ይቍጠር፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሁን፤እንደ ምንደኛውም 

ዘመን ከእርሱ ጋር ይሁን። 51፤ብዙ ዓመታትም ቢቀሩ 

እንደ እነርሱ ቍጥር ከሽያጩ ብር የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ።52፤ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት 

ድረስ ጥቂቶች ዓመታት ቢቀሩ ከእርሱ ጋር ይቈጥራል፤ እንደ ዓመታቱም መጠንየመቤዠቱን 

ዋጋ ይመልስ 53፤ በየዓመቱ እንደ ምንደኛ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ በፊትህ በጽኑ እጅ አይግዛው።

54፤ በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይቤዥ በኢዮቤልዩ ዓመት እርሱ ከልጆቹ ጋር ይውጣ።” 

ዘሌ.25፥47-54 

እግዚአብሔር ሕግ እንደሚያሳየው እዳ ያለበት ሰው እዳውን ራሱ ለመክፈል ከቻለ ነፃ

ለመውጣት መብት እንዳለው ያሳያል። ደግሞም የቀረበ ወንድምና ዘመድ ካለው ከእዳው ሊቤዠው እዳውን

ከፍሎለት ነፃ ሊወጣ ይችላል ብሎ መብትን በሕጉ በእዳ ለተያዘውም ሆነ ለሚበዠው ሰው አስቀምጣል። ይህን

ባለእዳ የገዛው ባለቤት ወይም ጌታ ይህ የመቤዥት ሕግ እንዲፈጸም ከማድረግ በቀር ባሪያዬ ነፃ አይወጣም

ማለት ወይም መከልከል ፈጽሞ አይችልም። እዳው ይከፈለው እንጂ ባሪያው ምን ጊዜም ነፃ መውጣት ፈጽሞ

ይችላል። ነገር ግን የቀረበ ዘመድ ከሌለው ግን ይህ ጌታ ባሪያውን አልለቅም የማለት መብት አለው። ይህም

ደግሞ ከላይ በቀደመው ክፍላችን እንዳየነው እስከ ኢዮቤልዩ ዘመን መፈጸሚያ ድረስ ብቻ ነው። 

Page 43: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 43/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

43ww.tlcfan.org

 

ኢየሱስ ይህ ነገር ወሳኝ ሰለሆነ በሕጉ መሰረት በነገር ሁሉ እኛን ሊመስል ወንድማችን የቀረበ

ወዳጃችን ሊሆን ተገባው። በሥጋና በደም ከእኛ ተካፈለ የመለአክትን ሳይሆን አብርሃምን ዘር ይዞ በሥጋ

ተወለደ። ይህን ስፍራ መያዙ የሰው ልጆችን ለመቤዠት ትልቅ ስልጣንን በእግዚአብሔር ሕግ ፊት አቀዳጀው።

ሕጉ ዘመድ ወይም ወንድም ካልሆነ በቀር ለመቤዠት ለማንም ከባለቤቱ ውጭ መብትን አይሰጥም። ይህን

መብት ኢየሱስ እንዲያገኝ በሁለት በኩል ኢየሱስ አለፈ። 

1.  የአብርሃም ዘር ወሰደ ይህም ሕዝበ እስራኤልን በሙሉ መቤዠት መብት እንዲኖረው ነው። ሮሜ.11

2.  በደምና በሥጋ ደግሞ ተካፈለ ይህም የምድርን ሰዎች ሁሉ መቤዠት መብት እንዲኖረው ነው። በሞት

ፍርሃት ለባርነት የተገዙትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ ነው። ሮሜ.5 እና 8 

“13 ስለዚህም ምክንያት። ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል

በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም። እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም። እነሆኝ እኔን

እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። 14-15

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን

በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት

በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። 16

የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። 17 ስለዚህ የሕዝብን

ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት

እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።”ዕብ.2፥13-17 

እግዚአብሔር በሕጉ እደደነገገው በወንድሙ የተቤዥው አዳ የነበረበት ሰው ነፃ ላወጣው

ለተቤዠው ወንድሙ የፍቅር የጽድቅ ባሪያ ይሆናል። እዳውንም በፍቅር እየተገዛ መክፈል ይቀጥላል። ዘሌ25፥

53 እንግዲህ ወንድምህ ተቤዠህ ማለት የእዳህን መዝገብ ገዛው ማለት ነው። እዳው ግን ወንድምህ ካልማረህ

እዳለ ነው። በወንድምህ ሰር በመሆነ በፍቅር ቀሪውን መክፈል ትቀጥላለህ ይህ ግን ለቀደመው ጌታ ሳይሆን ነፃ

ላወጣህ ወንድምህ ነው። ኢየሱስ ግን እዳውን ደምስሶ እኛን የእርሱ ባሪያዎች አጸረገ ይህ ደግሞ የጌታው

ፍላጎትና መብት ነው። ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገዛን ሁሉ የእርሱ ሥራ የሆነውን ጽድቅን ለማድረግ

ባለ እዳዎች ነን። ስለዚህ የእርሱ ሥራ በፍቅር እየተገዛን ጽድቅን እናደርጋለን። 

Page 44: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 44/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

44ww.tlcfan.org

 

ሰራተኛው ወይም ባሪያው ወንድሙ ሲበዠው ጌታ ቀየረ እንጂ ሁሌ ባሪያ ነው። አሁን ጌታው

የተቤዥው ወንድሙ ወይም ወድጁ ነው። ምንም እንኳን ወንድሙ ቢቤዠውም ፈጽሞ እንደ ፈለገው

በሃጢያት ለመኖር ወይም በእዳ ውስጥ ደግሞ ለመግባት ነፃ አይደለም። ጳውሎስ ይህ የመቤዠት ሚስጥር

ተገልጦለታል። በሮሜ 6 ላይ ከፀጋ በታች ነን ብለን ሃጢያት መስራትን መቀጠል እንደሌለብን ከተናገረ በኃላ

በመቀጠል እንዲህ ይላል፦ 

“15 እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን?

አይደለም።16 ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ

ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም

ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።17-18 ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥

ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ

ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።19 ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ

እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥

እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ።20 የኃጢአት

ባሪያዎች ሳላችሁ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁና።21 እንግዲህ ዛሬ ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ

ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና።22 አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ

ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።”

ሮሜ.6፥15-22 

የእግዚአብሔር ቃል ከላይ እንደሚያሳየን ሃጢያት ጨካኝ ጌታ እንደ ነበርና የእርሱ ባሪያዎች

እደነበርን ነው። ለእርሱም እንገዛ የነበረው በወንድማችን ኢየሱስ እኛን ከመቤዠቱ በፊት ነው። ኢየሱስ የቅርብ

ወንድማችን ሆኖ መጥቶ ልንከፍለው ከማንችለው እዳችንን ከፍሎልን ተቤዠን። ይህም ከጨካኙ የሃጢያት

ባርነት ወይም ከጨካኝ ገዥ ነፃ ወጥተን ለእግዚአብሔር ባሪያዎች እንድንሆንና እግዚአብሔርን ሕግ

እንድንጠብቅና እንድንታዘዘው በኑሯችን ሁሉ ጽድቅን እንድናደርግ ነው። 

ሕጉን በመጠበቅና በመታዘዝ የጽድቅ ባሪያዎች እንሆናለን። ሕጉም ለመቀደስና ፍሬ ለማፍራት

ብቃትን እንዲኖረን ያደርጋል። የምድርንም በረከት እንወርሳለን። የዚህም መጨረሻው የዘላለም ሕይወት ነው።

ሰለዚህም ሕጉ ለአሁን ዘመንም ክርሰቲያኖች ጠቃሚና መመሪያ መርህ የሚሰጥ እንደ ሆነ በቀላሉ

እንመለከታለን።

Page 45: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 45/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

45ww.tlcfan.org

 

ሕጉ በፀጋው አልተወገደም ወይም አልተሻረም። ኢየሱስ እንደ መቤዠት ሕግ ሃጢያት ከሚባል

ጨካኝ ጌታ ተቤዠን። በዚሁ ሕግ አሁን ደግሞ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን። ለእግዚአብሔር ሕግ ደግሞ

እንገዛለን ምክንያቱም እና በእርሱ ነፃ የወጣን ሁሉ ባሪያዎቹ ነን። የእግዚአብሔር ባሪያ ነኝ የሚል ይን ያውቅ

ዘንድ ፈጽሞ ይገባዋል። ሕግ የለሽ ኑሮን ከመኖር እግዚአብሔር ይጠብቀን። ያለ እግዚአብሔር ሕግ ከእሱ ጋር

በዙፋን ላይ ለመፍረድም ሆነ ለመቀመጥ ፈጽሞ አትችልም። ሕግን የማንወድና በልባችን እንዲጻፍ የማንፈልግ

የማንታዘዝ ሰዎች ከሆንን የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን ብለን አፋችንን ሞልተን አንናገር። እርሱ አላውቃችሁ

ከእኔ እራቁ ሕግ የለሾች አመጸኞች ይለናልና። 

እንግዲህ ከላይ አንዳንድ ከምድራችን ወይም ከሥጋችን ጋር የተያያዙትን ሕጎች በጥቂቱ

ከተመለከትን አሁን ደግሞ ወደ ዋናው በልባችን እንዲጻፍ ወደምፈልገው ሕግ ወደ አሥራት ሕግ እንሄዳለን።

ይህን ሕግ በዝርዝር እንመለከተዋለን። ከላይ ያየናቸው አንዳድ የእግዚአብሔር ሕጎች አዕምሮአችንን ለአሥራት

ሕግ የሚያነቃቁና አንዳን መለኮታዊ ሚስጥራትን የሚጭሩ ነበሩ። በሚቀጥለው ክፍላችን የአሥራትን ሕግ

በዝርዝር እንመለከታለን። 

“ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።”

1.ዮሐ.3፥4 

“  Whosoeuer committeth sinne, transgresseth also the lawe:

for sinne is the transgression of the lawe.” 

“Every one that practises sin practises also lawlessness;

and sin is lawlessness.” 

Page 46: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 46/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

46ww.tlcfan.org

 

የአሥራት ሕግ 

“30፤ የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር 

ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።31፤ ሰውም አሥራቱን ሊቤዥ ቢወድድ፥ አምስተኛ 

ይጨምርበታል። 32፤ ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ 

በግና ፍየል ሁሉ  ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።33፤ መልካም ወይም ክፉ 

እንዲሆን አይመርምር፥አይለውጥም፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ፤ 

አይቤዠውም። 34፤ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለእስራኤል ልጆች ሙሴን ያዘዘው 

ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።” ዘሌ.27፥30-34 

አሥራት ማለት ከማንኛውም ከተፈጥሮ ውጤት ከምታገኘው ነገር ለእግዚአብሔር የተቀደስ

1/10ኛው ማለት ነው። ዘሌ.27፥30 ከላይ እንደ ተመለከትነው አሥራት የእግዚአብሔር የሆነበት ምክንያት

ሁሉን እርሱ ስለፈጠረ የሁሉ ባለቤት፣ ባለ ንብረት እግዚአብሔር ስለ ሆነ ነው። በብሉይ ኪዳን እንዳሁን ዘመን

አይነት ሥራዎች በብዛት የሉም ሰለዚህም አንድ እግዚአብሔር የሚያምን ሰው አሥራቱን የሚያመጣው

ካረሰው የምድር ውጤት 1/10ኛውን ከእንስሳት ርቢ 1/10ኛውን ከባሕር ከሚያገኛቸው ማንኛውም ውጤቶች

1/10ኛውን ነው። 

አሥራት በብሉይ ኪዳን ከምድር ፍሬ፣ ከእንስሳት ርቢና፣ ከአሳ ማጥመድና ዶሮና እርግብ እርቢ

ውጤት ከሚገባው ሁሉ የሚወጣ ነበር። ለምሳሌ አንድ ሰው እርሻ ቢኖረው እርሻውን የሚሰሩ ሰራተኞች

ቢኖሩት አሥራት የሚሰጡት ሰራተኞቹ ሳይሆኑ የእርሻው ባለቤት ብቻ ነው። ይህም ደሞዝ የሌላቸው ከሆኑ

ነው። ሰራተኞቹ ከቀጣሪያቸው ደሞዝ ካላቸው አሥራት የሚያወጡት ደግሞ ከደሞዛቸው አንድ አሥረኛውን

ነበር። ስለዚህም በጥቅሉ ከሦስት ክፍል በብሉይ አሥራት ይወጣ ነበር። 

1.  ከምድር ዘር 2. ከዛፍ ፍሬ እና 3. ከምድር እንስሳት ከእነዚህ ከሥስቱ አሥራት እንዲወጣ በሕጉ

እግዚአብሔር ያዛል። 

“የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው፤ 

ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው፣…… ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች 

ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፣።”

ዘሌዋ.27፥30-32 

Page 47: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 47/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

47ww.tlcfan.org

 

ስለ አሥራት ስንናገር አሥራት መውጣት የጀመረበትን የመጀመሪያውን መሰረት ልናገኝ

ይገባል። ደግሞ ከአሥራት ጋር የተያያዙ ታሪኮችንና አሥራት ያወጡትን አባቶቻችን ሕይወት ልናይ ይገባል።

የተለያዬ የአሥራት አወጣጦችን በስፋት ስንመለከት በመግቢያው ላይ የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች መልስ በሙሉ

እናገኛል። አሥራት በአዲስ ኪዳን የጀመረ ሳይሆን መሰረቱ ከዘፍጥረት ያደረገ መለኮታዊ የእግዚአብሔር ሕግ

ነው። በብሉይ ኪዳን አሥራትን ያወጡ ሰዎችንና ለምን እንዴት እንዳወጡ ለማን እንዳወጡ፣ ደግሞ ከአሥራት

ጋር የተያያዙ ሃሳቦችን በዝርዝር በመመልከት ስንገነዘብ ሰለ አስራት ያለን ሃሳባችን እየተስተካከለና

እግዚአብሔር የሚፈልገውን መልክ እየያዘ ይመጣል። ከዚያም በትክክል አሥራት ማውጣት እችንላለን። 

አብርሃም ያወጣው አሥራት፦ 

የእግዚአብሔር ቃል ስለ አሥራት የሚያስተምረን ነገር ብዙ ነው። በዚህ በአሥራት ትምህርት

ቀደምት ተጠቃሽ የሚሆነው የእምነት አባት የሆነው አባታችን አብርሃም ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ

አሥራት የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገኘው አብርሃም ለመልከ ጸዲቅ የሰጠውን አሥራት ሲነገር ነው።

የእግዚአብሔር ካህንና የሰላም ንጉስ የሆነው መልከ ጸጺቅ ከአብርሃም አሥራትን ተቀበለ። አብርሃም ከጦርነት

ከበዘበዘው ለእግዚአብሔር አሥራትን ሰጠ። እዚህ ጋር ልንመልከተው የሚገባው አብርሃም አሥራትን የስጠው

ከሁሉ መሆኑን ጭምር ነው። ይህ የበዘበዘውን ገንዘብን ሁሉ ይጨምራል። 

“ የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ 

እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።19፤ ባረከውም። አብራም ሰማይንና ምድርን 

ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው፤20፤ ጠላቶችህን በእጅህ 

የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔርም የተባረከ ነው አለውም። 

አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።” ዘፍ.14፥18-20

የእግዚአብሔር ቃል እዚህ ጋር ያሳየው ሌላ ነገር አለ። ይህም አብርሃም አሥራቱን

ለእግዚአብሔር ካህን በስጠ ጊዜ ገና ስሙ አልተለወጠለትም ነበር። እግዚአብሔር በባሕሪው ከተለወጠም ገና

ካልተለወጠም አማኝ አሥራትን ይቀበላል። ሌላው ደግሞ ምንም እንኳ አብርሃም ለእግዚአብሔር ከእርሻው፣

ከዛፍ ፍሬና ከእንሳት አሥራትን ቢያወጣም ከዚህ ከሚሰጠው በላይ ከሚያገኘው ማንኛውም በእግዚአብሔር

አጋዥነት ከተገኘ ብዝበዛም አሥራቱን በስርዓት ያወጣ ነበር። ይህን በማድረግ የእግዚአብሔርን የምድር ሕግ

አብርሃም ይጠብቅ ነበር። 

Page 48: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 48/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

48ww.tlcfan.org

 

“4.ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤

የምድርም አህዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤5. አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥

ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።” ዘፍ.26፥5

የሚደንቀው ነገር አብርሃም ከጦርነት ያገኘውን ብዝበዛ አሥራት ካወጣለት በኃላ የቀረውን

90/100 የሰጠው በግፍ ተበዝብዞ ደሃ ለሆነው ለስዶም ንጉስ፣ አብረውት ለተዋጉት መብልና ድርሻ ነው።

ከብዝበዛው አብራሃም ወደ አንዱ እንኳ እጁን አልሰደደም ነበር። ምክንያቱም አብርሃም ሲናገር ባለጠገ

አደረኩት ብሎ የስዶንም ንጉስ እንዳያወራና የእግዚአብሔርን ክብር እዳይይጋፈበት ነበር። 

“አንተ። አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር 

ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ 

እንዳልወስድ፤አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።” ዘፍ.14፥23-24 

የእግዚአብሔር ቃል በዕብራውያን መጽሐፍ ምዕራፍ ሰባት ላይ በመቀጠል ስለ አብርሃም

አሥራት ይናገርና። ሌዋውያን ደግሞ ከሕዝቡ አሥራትን እንዲያስወጡ ስልጣን ነበራቸው ይላል። 

“1 የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን

ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤2 ለእርሱም ደግሞ አብርሃም ከሁሉ አስራትን

አካፈለው። የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ

ማለት የሰላም ንጉሥ ነው።3 አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት

ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ

ይኖራል።4 የአባቶች አለቃ አብርሃም ከዘረፋው የሚሻለውን አስራት የሰጠው ይህ ሰው

እንዴት ትልቅ እንደ ነበረ እስኪ ተመልከቱ።5 ከሌዊ ልጆችም ክህነትን የሚቀበሉት ከህዝቡ

ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ ከእነርሱ አሥራትን

በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው፤6 ትውልዱ ከእነርሱ የማይቈጠረው ግን ከአብርሃም

አሥራትን አውጥቶአል፥ የተስፋ ቃል የነበረውንም ባርኮአል።7 ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ

ክርክር የሌለበት ነገር ነው።8 በዚህስ የሚሞቱ ሰዎች አሥራትን ያስወጣሉ፥ በዚያ ግን

የሚያስወጣ በሕይወት እንዲኖር የተመሰከረለት እርሱ ነው።9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥

Page 49: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 49/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

49ww.tlcfan.org

 

አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤10 መልከ ጼዴቅ

በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና።11 እንግዲህ ህዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ

ተቀብለዋልና በዚያ ክህነት….. ….ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥

እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል?12 ክህነቱ

ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ (የአስራት አወጣጥ ሕግ ማለቱ ነው እንጂ የእግዚአብሔር ሕግ 

ሁሉ ማለቱ አይደለም፣) የግድ ነውና።13 ይህ ነገር የተነገረለት እርሱ በሌላ ወገን

ተካፍሎአልና፥ ከዚያም መሠዊያውን ያገለገለ ማንም የለም፤14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ

እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም።15-

16 በማያልፍም ሕይወት ኃይል እንጂ በሥጋ ትእዛዝ ሕግ ሳይሆን ሌላ ካህን በመልከ ጼዴቅ

ምሳሌ ቢነሳ፥ይህ እጅግ አብልጦ የሚገለጥ ነው።” ዕብ.7፥1-16 

የእግዚአብሔር ቃል በዕብራውያን ላይ አሥራት ስለሚያስወጡት ከመናገር አልፎ አሥራትን

ስለሚቀበለው መልከ ጸዲቅ ማንና ምን እንደሆነ ይናገራል። ይህም ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ሕግ እንደ ሆነ

በትክክል ያስቀምጣል። አብርሃም ለጦርነት ወጣ ይህ የወንድሙን ልጅ ሎጥንና የሎጥን ሚስቶች፣

የተዘረፈውን ንብረቱን ለማስመለስ ነው።

አብርሃም አሥራቱን ያወጣው ከዘረፋው የሚሻለውን ነው። ይህም እግዚአብሔር ከባረከው

ሃብቱ ጭምር ማለት ነው። ምክንያቱም አብርሃም ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር የተባረከ አባት

ነው። አሥራቱን ለእግዚአብሔር ለመስጠት መዝረፍ አላስፈለገውም። እግዚአብሔር ሰርቶ የሚያከማችበትን

ሥጋን ጥረትን ሰጥቶታል አብርሃም ትጉ ገበሬና ሰራተኛ ነው። 

አብርሃም ለእግዚአብሔር እግዚአብሔር ከባረከው ነገር ሁሉ አሥራትን አወጣ። ነገር ግን

ከዘረፋው ካመጣው ሃብትና በረከት ለመካፈል ወይም ለመውስድ አልወደደም። ይህም አብርሃምን ባለጠጋ

አደረኩት ብሎ ሰዶም ንጉስ እንዳይመካ እንደሆነ አይተናል። ጳውሎስ ይህ እውነት የገባው ስለሆነ እግዚአብሔር

የሰጠውን እየሰራ ማገልገልን ትምክቱ አድርጓል። ይህም ማንም ጳውሎስን ባለጠጋ አደረኩት እንዳይል ነው።

እንደ አገልጋይ የሚገባውን ገንዘብ መቀበል ሲህል እንቢ አለ። ይህ እውቀት ሚስጥር እጅጉን ታላቅ ነው።

ሰራተኛም ደግሞ ደሞዙ ይገባዋል። ይሁንና ለእግዚአብሔር የባርኪያለው የሚል ከደሞዝ ነፃ ነው።

እግዚአብሔር በእጃችን ስራ ይባርከናል። እኛ ደግሞ እግዚአብሔር በባረከን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር አንድ

አስረኛውን አሥራታችንን በመስጠት እንባርከዋለን። 

Page 50: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 50/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

50ww.tlcfan.org

 

አብርሃም ለመልከ ጸጺቅ አሥራቱን ሰጠው እርሱም ከአብርሃም ተቀበለ። ልብ ልንል አሚገባው

መልከ ጸጺቅ ክህነት አሥራት ይቀበላል እንጂ አያስወጣም። ሌላው ደግሞ ለእግዚአብሔር ተባርኪያለሁ የሚል

ሰው ሁሉ አሥራትን ይሰጣል። ለዘላላም ሕያው የሆነው የማይሞተው እውነተኛው ሕያው ሰለሆነ መልከ

ጸጺቃችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም አሥራትን ይቀበላል። እንዴት እንደምንሰጠው ግን ማወቅ ማስተዋል ነው።

ይህ መልከ ጸጺቅ ታላቅ ነው። አሥራት የሚያስወጣው ሌዊ ሳይቀር በአብርሃም ውስጥ ሆኖ አሥራትን ለዚህ

ለመልከ ጸዲቅ ሰጥቶታል። ገና ሳይወለድ በአብርሃም ዘር ወይም ወገብ ውስጥ ነበርና ነው። 

ከአብርሃም ታሪክ እንደምንረዳው አብርሃም ሕግን የሚጠብቅ ሰው መሆኑን ደግሞ ከሕግም

መካከል አሥራትንም ይጠብቅና ይታዘዝ እንደነበር እንመለከታለን። አብርሃም አሥራት ለማን እንደሚሰጥያውቃል። የአሥራት ባለቤት ለዘላለም ሕያው ሆኖ በመልከ ጸዲቅ ተመሶ የሚኖር ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ

ነው። አብርሃም አሥራት እግዚአብሔር ከባረከው ነገር ሁሉ እንደሚወጣ ተገንዝቧል። የሚወጣውን አስቀድሞ

ወንጌልን ለሰበከለት ለኢየሱስ ክርስቶስ ለሰላም ንጉሥ መሆኑ ገብቶታል። 

ስለዚህ እግዚአብሔር ከባረከው ነገር ሁሉ አሥራትን ለእግዚአብሔር ይስጥ ነበር። ደግሞም

አብርሃም የሰውን ገንዘብና ለሰዎች ተዋግቶ ያገኘውን ገንዘብ አሥራቱን ካወጣለት በኃላ የቀረውን 90%

ለባሪያዎቹና ለባለንብረቶቹ ባለቤት የሚመልስ በመስጠት መንፈስ በአምላኩ መንፈስ የተሞላ ሰው ነበር።

አብርሃም የሰዎችን ገንዘብ ቤቱ የማያስገባው ወይም ቢቀበልም የተቀበለውን አሥራቱን አውጥቶ የቀረውን

ለባሪያዎቹ አብረውት በጦርነት ለሚደክሙ ያካፍላል። የሚያከፍለው የእግዚአብሔር ባርኮት ብቻውን

ለአብርሃም በቂ እንደሆነ ስለሚያውቅና ሰዎች ገንዘብ ለአብርሃም በመስጠታቸው አብርሃምን ባለጠጋ ያደረጉት

እንዳይመስላቸው ነው። ሌላው ደግሞ ሕይወቱን ከሃጢያት ሥር ከሆነው ከገንዘብ የበላይ ከማድረግ ለማንጻት

ነው። የእግዚአብሔር ሕግ በልቡ የተጻፈ ሰው ይሏችኃል እንግዲህ እንዲህ ያለ ታላቅ የእምነት አባት ነው።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የዚህን የእምነት አባት የልጅ ልጅ የሆነውን ያቆብን እንመልከት። 

Page 51: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 51/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

51ww.tlcfan.org

 

ያቆብ ያወጣው አሥራት፦ 

“20.ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም

በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥

21 ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤ 22. ለሐውልት የተከልሁት

ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን

እሰጥሃለሁ። ”ዘፍ.28፥20-22 

ሰለ አሥራት ሰው ሲያስተምር ብዙውን ጊዜ የያቆብን አሥራት ለመጠቀም አንደፍርም።

ምክንያቱም ብዙ አጠያያቂ ነገሮችን በውስጡ ስለ ያዘ ነው። ያቆብ የአብርሃም የልጅ ልጅ ነው። በእርግጠኝነት

ስለ አሥራት ሕግ ከአያቱ ብዙ ትምህርትን ተምሯል። ደግሞ እንደ ሌዊ በአብርሃም ወገብ ውስጥ ሆኖ አሥራትን

ለሰላም ንጉስ ለሚበልጠው መልከ ጽጺቅ ሰጥቷል። አያቱ የእምነት ሰው ነው። ደግሞ እግዚአብሔር አትረፍርፎ

የባረከው ሰው ነው። እግዚአብሔር በቃሉ ይህን ለትምህርታችን ማስቀመጡ አሥራት የመስጠት መሰረቱና የት

መውጣት እንዳለበት በትክክለኛ ለማሳየት ነው። በያቆብ የተገለጠው የአሥራት አወጣጥ መሰረታዊ መርህን 

የያዘ ታሪክ ነው። 

ራሳችንን እስቲ እንደ ባለ አዕምሮ እንጠይቅ። ያቆብ አሥራቱን ለእግዚአብሔር እንዴት ሰጠው?

ለእግዚአብሔር በእጁ ሰጠውን? አይደለም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን ያየው አንድስ እንኹዋ የለምና። ያቆብ

ለመላአክት አሥራቱን ሰጠን? አልሰጠም። ምክንያቱም መላአክት ወደ እርሱ አሥራት ሊወስዱ አልመጡም።

አሥራቱን ወደ መንግሥተ ሰማይ ላከውን? አላከም። ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንስ ወሰደውን? አልወሰደውም

አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የለም ነበር። ወደ መቅደስ ወሰደውን? አልወሰድውም መቅደስ የለምና። ለካህኑ ለሌዊ

ሰጠውን? አልሰጠውም። ገና ሌዊ ካህን ሆኖ አልተመረጠምና። ያቆብ ገና ሌዊን አልወለደውም እርሱም እንደሕጉ አሥራትን ማስወጣት አልጀመረም ነበር። ታዲያ ያቆብ እንዴት አሥራቱን ለእግዚአብሔር አወጣ? ያቆብ

አሥራት ከአሥር አንድ እጅ እንደሆነ ገልጦልናል ይህ በአብርሃም ዘመን አልተገለጠልንም ነበር። 

ያቆብ አስራቱን እንዴት እንዳወጣ እንደ እግዚአብሔር ቃል ከላይ ያነሳናቸውን ጥያቄዎች

መልስ ከሰጠን መልሳችን ያቆብ አሥራቱን ለእግዚአብሔር ያወጣው በሁለት መልኩ እንደሆነ ከእግዚአብሔር

ሕግ በመነሳት እንገነዘባለን። 

Page 52: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 52/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

52ww.tlcfan.org

 

አንደኛው በእግዚአብሔር ፊት ከቤተስቡ ጋር በላው፦ 

“6፤ ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላ መሥዋዕታችሁንም፥

አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቍርባን፥ ስእለታችሁንም፥

በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኵራት ውሰዱ።7፤ በዚያም

በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም በምትዘረጉበት፥ አምላክህ

እግዚአብሔር በባረከህ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ፣”

ዘዳ.12፥6-7 

ሁለተኛው ደግሞ ለደሃ፣ ለመበለት፣ ለመጻተኛ ይበሉት ዘንድ ሰጠው፦ 

“ ሌዋዊውም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በአገርህም ደጅ ያለ መጻተኛ

ድሀ አደግም መበለትም መጥተው ይበላሉ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር

በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው፣” ዘዳ.14፦29 

የእግዚአብሔር ሕግ እንደሚያሳየን በእውነት ያቆብ እንደ አያቱ በእግዚአብሔር ሕግ የሚኖር

ከሆነ አሥራቱን ያወጣው በዚህ በላይ በእግዚአብሔር ሕግ ተጽፎ በሚገኘው ምርህ መሰረት ነው። ስለዚህ

በያቆብ አሥራት አወጣጥ ላይ ጠለቅ ያለ መረዳትን ሰለ አሥራት እናገኛለን። ያቆብ አሥራቱን አውጥቷል።

አሥራት የእግዚአብሔር ነው። ያቆብ ደግሞ አሥራት ከአስር አንድ እንደሆነ በግልጽ ያስቀመጠልን የእምነት

የሚታዘዝ አባት ከመሆኑ ባሻገር እስራት እንደሚበላ ያሳየ አባት ነው። 

ያቆብ በላባ ቤት የባረከውን በጎች ወደ ቤተልሄም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዞ በመምጣት

ለእርሱ መጽዋዕት አድርጎ አቀረበ ደግሞ ከቤተ ሰቦቹ ጋር በእግዚአብሔር ፊት በመብላት አሥራቱን በዚህ

መልኩ አውጥቷል። ያለውንም ሃብት ለወንድሙ ለዔሳው ለመሰጠት ሳይሰስት እጁን ሲዘረጋ

እንመለከተዋለን። 

Page 53: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 53/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

53ww.tlcfan.org

 

ርስት የሆነ አሥራት፦ 

እግዚአብሔር ለሌዋውያ አሥራትን ርስት አድርጎ ሰጥቶ እንደነበር በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ

እንመለከታለን። ይህም አሥራት የማስወጣት መብታቸውም በእግዚአብሔር ሕግ የተጠበቀ ነበር። በአሁን

ወቅት ግን አንድ ሰው ሌዊ ለመሆን ከሌዊ ዘር መወለድ ብቻ ሳይሆን የአሮን ልጅ ሊሆን ይገባዋል። አሁን ማንም

ከሕዝበ እስራኤል ውጪ በትውልዱ ሌዊ ዘር የሆነ የለም። እግዚአብሔር ለሌዎዊያ የሰጣቸው ሕግ ለእነርሱ ብቻ

የተወሰነ ነበር። ይሁንና በዚያን ዘመን መቅደስ ስለሌለ የሌዋዊ ዘር ሁሉ አሥራትን እንደ ብሉይ ኪዳን

አይቀበሉም ወይም አያስወጡም። ዕብራውያን ሰባት የሚያሳየው ይህን ነው። ከሌዊም ወገን ሆኖ ካህን ያልሆነ

የአሮን ልጅ ያልሆነ ሁሉ አሥራትን የማስወጣት መብት ሊቀበል ፈጽሞ አይችልም ነበር። 

በኢየሱስ የአሮንን ክህነት ወስደናል እንዳንል እንኳ ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ ነው። ለዚህ ነው

ኢየሱስ እንደ መልከ ጸጺቅ የሰላም ንጉስ ሊሆን የቻለው። መልከ ጸጺቅ ከይሁዳ እንጂ ከሌዊ ዘር ግንድ አይደለም

አይደለም። ሌዊ ሳይወለድ መልከ ጸዲቅ ከአብርሃም አሥራት ተቀብሏል። ሰለዚህም ኢየሱስ ብቸኛው

የእግዚአብሔር መንግሥት ሊቀ ካህን ነው። ይህም ክህነት የመልከ ጸጺቅ ክህነት ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ተነስቶ

እኔ ካህን ነኝ የእግዚአብሔር አሥራት ለእኔ ይገባኛል ማለት ፈጽሞ አይችልም። 

እኔ አሥራትን ለሚያስወጡና አሥራትን ለሚያወጡ እግዚአብሔራዊ የሆነ ምክር አለኝ ይህም

የእግዚአብሔርን ቃል አሥራት ማውጣት ከመጀመራችሁ ሕጉን ከማድረጋችሁ በፊት ቃሉን መርምሩ፣ አደራረጉ

አወጣጡን ተማሩ እላለሁ። በአሁን ወቅት ፍጥረታዊ መቅደስ የለም። ሌዋዊ ክህነት የለም። በዚህ ዘመን ይህ

አይነት መቅደስና ስርዓት ክህነትም አስፈለጊ አይደለም። ይህ ባይሆን ኖሮ ክህነቱና የክህነቱ ሕግ ሊለወጥ

አይገባውም ነበር። ነገር ግን ክህነቱም ሆነ የክህነቱ ሕግ ተለውጧል። ይህ ስንል ግን ሕጉ ተሻረ ሳይሆን ሕጉ ከፍ

ወዳለ ሃሳብ አደገ ጸና ከበረ ለማለት ነው። ለሌዊ የተገባው ኪዳን በአዲሱ ኪዳን ተለውጧል። የአዲስ ኪዳን

የእውነተኛው የእግዚአብሔር መቅደስ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

“11 እንግዲህ ህዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና(አስራት የማስወጣት ሕግ

ቃል ኪዳን) በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ

መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል? 12 ክህነቱ

ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ የግድ ነውና።(የማስወጣት ሕግ እና መቀበል ሕግ) 13 ይህ

ነገር የተነገረለት እርሱ በሌላ ወገን ተካፍሎአልና፥ ከዚያም መሠዊያውን ያገለገለ ማንም

Page 54: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 54/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

54ww.tlcfan.org

 

የለም፤ 14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም

እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም። 15-16 በማያልፍም ሕይወት ኃይል እንጂ በሥጋ ትእዛዝ ሕግ

ሳይሆን ሌላ ካህን በመልከ ጼዴቅ ምሳሌ ቢነሳ፥ ይህ እጅግ አብልጦ የሚገለጥ ነው። 17 አንተ

እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ይመሰክራልና። 18-19 ሕጉ ምንም

ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ

(አሥራት አስወጡ የምትለው ቃል) ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል

ተስፋ ገብቶአል። 20-21 እነርሱም ያለ መሐላ ካህናት ሆነዋልና፤ እርሱ ግን። ጌታ። አንተ እንደ

መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሐላ

ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን እንዳልሆነ መጠን፥ 22 እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን

ዋስ ሆኖአል። 23 እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ 24

እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ 25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ

ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ

ሊያድናቸው ይችላል። 26 ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ

ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤ 27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ

ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን

ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። 28 ሕጉ

ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል

ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል፣” ዕብ.7፥11-28 

ሰለዚህ ማንም ከአሮን ወገን ካልሆን በቀር አሥራትን እንደ ሕጉ ማስወጣት በቃሉ መሰረት

መብት የለውም። ነገር ግን እንደ መልከ ጸዲቅ ክህነት ያለን ክህነት ከጌታ በመወለድ የተቀበለ አሥራትን

የመቀበል መብት አለው። ነገር ግን ይቀበል እንጂ የማስወጣትም መብት እንደሌለው ልናውቅ ይገባል። መቀበል

በስጪው ፍላጎትና ቸርነት ላይ የተመሰረተ እንጂ በተቀባዩ ማስፈራራት ላይ አይደለም። በመቀበል ሕግ ግን

ከመልከ ጸዲቅ የተወለዱትን ልጆች በመሃላ ለመቀበል ይሾማል። ሰለዚህ የሌዊ አይነት ክህነት ከእንግዲህ በኋላ

በስራ ላይ ሊውል ፈጽሞ አይገባውም። በግድ ማንም አሥራትን የማስወጣት መብት ማንም ሰው እንዳይኖረው

መብት የተስጠበትን ሕግና ክህነቱ በኢየሱስ በቆመው አዲሱ ኪዳን ተለውጧል። የተለወጠበትንም ምክንያት

ኢየሱስ ሆነ ጳውሎስ ይህ ሚስጥር ጠንቅቀው አስተምረውናል። 

Page 55: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 55/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

55ww.tlcfan.org

 

1.  ኢየሱስ መቅደሱ እንደሚፈርስ ተናግሯል። ማቴ.24፥1-2 

2.  በአዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር እጅ በስራው መቅድስ ውስጥ አያድርም። ሐዋ.17፥24 

3.  እውነተኛ አማኞች በአሁን ወቅት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደሶች ናቸው። 2.ቆሮ.6፥16, 1ቆሮ.3፥15,19 

4.  ቲዮሎጂያንም መቅደሱ ሲያልፍ ስርዓቱም እንዳለፈ ፈጽመው ያውቃሉ፣ ልክ እንደ ፈሪሳዊያን የተቀደደ

መጋረጃ ይሰፋሉ እንጂ። 

5.  እያንዳንዱ አማኝ ደግሞ ከጌታ ሰለተወለደ የመለከ ጸጺቅን ክህነትና ሕግና መብት ተካፈይ ነው።

ስለዚህ እያንዳንዱ አማኝ አሥራትን የመቀበል መብቱ እንደ ካህን የተጠበቀ ነው። ይህ ግን ምን

ማለት ነው?

”እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ

የተመረጠ ትውልድ፥ (የይሁዳ) የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ።”

1.ጴጥ.2፥9

የአሥራትን ተካፋዬች፦ 

“6፤ ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላ መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥

በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቍርባን፥ ስእለታችሁንም፥ በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና

የበጋችሁንም በኵራት ውሰዱ። 7፤ በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም

በምትዘረጉበት፥ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ። 8፤

ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፤ 9፤

አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና። 10፤

ዮርዳኖስን ግን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ

ጊዜ፥ ያለ ፍርሃትም እንድትኖሩ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ፥ 11፤ በዚያን ጊዜ

አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን

ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላ መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁ

ያነሣችሁትንም ቍርባን፥ ለእግዚአብሔርም ተስላችሁ የመረጣችሁትን ስእለታችሁን ሁሉ ውሰዱ። 12፤

እናንተም፥ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ባሪያዎቻችሁም፥ ገረዶቻችሁም፥ ከእናንተ ጋር

ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ ውስጥ የተቀመጠው ሌዋዊም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊትደስ ይበላችሁ። 13፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በሚታይህ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።

Page 56: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 56/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

56ww.tlcfan.org

 

14፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን

መሥዋዕትህን አቅርብ፥ በዚያም የማዝዝህን ሁሉ አድርግ። 15፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንደ

ሰጠህ በረከት፥ ሰውነትህ እንደ ፈቀደ፥ በደጆችህ ሁሉ ውስጥ አርደህ ብላ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ

ሰው እንደ ሚዳቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው። 16፤ ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሰው

እንጂ አትብላው። 17፤ የእህልህን የወይን ጠጅህን የዘይትህንም አሥራት፥ የላምህንና የበግህንም

በኩራት፥ የተሳልኸውንም ስእለት ሁሉ፥ በፈቃድህም ያቀረብኸውን፥ በእጅህም ያነሣኸውን ቍርባን

በደጆችህ ውስጥ መብላት አትችልም። 18፤ ነገር ግን አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም፥ ባሪያዎችህና

ገረዶችህም፥ በአገርህም ደጅ ያለው ሌዋዊ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ በአምላክህ

በእግዚአብሔር ፊት ብሉት፤ እጅህንም በምትዘረጋበት ነገር ሁሉ

በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።’’ (ዘዳ12፥6-18) 

የሥስራት ተካፋዬች ማን እንደሆኑ ሙሴ በዝርዝር ከእግዚአብሔር እንደተቀበለው

ስላስቀመጠው ምንም ማብራሪያ ስለማያስፈለገው ይህን ክፍል ቃሉ ብቻ ደጋግመን እንድናጠና እያመለክትኩ

መደሚቀጥለው ክፍል አልፋለሁ። 

ከሚገኘው ሁሉ በየአመቱ አሥራት አውጣ፦ 

ኢየሱስ በሕጉም ሆነ በትምህርቱ አሥራት እንደናወታ ያዘናል። “እናንተ ግብዞች ጻፎችና

ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥

በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።” ማቴዎስ

23፥23 

“ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ።”

ዘዳ.14፦22 

“አሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የፍሬህን ሁሉ አሥራት

አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ በአገርህ ደጅ ውስጥ ይበሉ ዘንድ ይጠግቡም ዘንድ

ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም ስጣቸው።”

ዘዳ.26፦12 

Page 57: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 57/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

57ww.tlcfan.org

 

አሥራታችን የምናወጣው እግዚአብሔር ከሰጠን ከምናገኘው ሁሉ ነው። ጻፎችና ፈሪሳዊያን

ከከሙን ሳይቀር አሥራትን ያወጡ ነበር። ከሙን ማለት ከጤፍ የምታንስ ዘር ነች። ነገር ግን አሥራት ወጣላት።

እግዚአብሔር ስድስት ቀን ከሰራው ስራ ሁሉ አሥራትን ከእኛ ይፈልጋል። ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ የሚለው

ቃል እግዚአብሔር ስጥቶ ከዘራኸው ዘር ከሚመጣው ውጤት ሁሉ ለእግዚአብሔር አሥራትን ልናመጣ ይገባል

ማለቱ ነው። ምክንያቱም የዘሩም፣ የምድርም፣ የዝናብም፣ የጸሃዩም ፈጣሪ እርሱ ነው። በብሉይ ኪዳን በዓመት

ሦስት ጊዜ አሥራትን ሕዝቡ ያወጣሉ። ይህም ሦስቱን የእግዚአብሔር በዓላትን ለማድረግ ወደ መቅደሱ

በሚሄዱበት ወቅት ነው። 

ይህ ብቻ አይደለም በድሮ ዘመን አንድ መቅደስ ነበርና ከመቅደሱ ውጪ ወደ ሌላ ስፍራ

አሥራት እንዳይወሰድ እግዚአብሔር በሕጉ ስለሚያዝም ነበር። ደግሞ የሚያመርቱት ምርት በየወሩ የሚገኝ

ስላልሆነ የሚወልዱትም እንስሳቶች በየወሩ ስላልሆነ በአመት ሦስት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት

በሚወጡነት ቀን ነበር። ይህም በፋሲካ በዓል፣ በበዓለ አምሣ በዓልና በዳስ በዓል ወቅት ነበር። ይህ

በመጀመሪያው ወር ገብስ በሚታጨድበት ወቅት፣ ከዚያም በበዓለ አምሣው ስንዴ በሚታጨድበት ወቅትና

በመጨረሻም በሰባተኛው ወር በዳስ በዓል ወቅት ወይን በሚቆረጥበት ወቅት ነው።

አሥራት ከምድር ጋር የተያያዘ መሆኑ በዚህም እንመለከታለን። እንስሳት በሁሉም ወሮች

ሊወለዱ ይችላሉ። እንደ አጸናነሳቸው ነው። ነገር ግን እነዚህ እጽዋቶች ገብስ፣ ስንዴና ወይን በአመት በሦስት

በተለያየ ወቅት የሚበቅሉና የሚታጨዱ ስለሆኑ አሥራት እንዲወጣ በእነዚህ መታጨድና መቆረጥ ወቅትና ወር

ላይ ነው። “በዓመት ሦስት ጊዜ፥ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንዶችህ ሁሉ በአምላክህ

በእግዚአብሔር ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።” ዘዳ.16፥

16

አሥራት የሚያወጡለት ከእግዚአብሔር ከሚያገኙት እግዚአብሔር የሰጣቸን መከርና እንስሳት

በጃቸው በትጋት በመስራት የእግዚአብሔር የአሥራት ሕግ በአመት ሦስት ጊዜ ይጠብቁ ነበር። በዚህ በአዲስ

ኪዳን ግን ይህ ሕግ እንዳገኘን በሚለው ይተካል። ምክንያቱም እግዚአብሔር አሁን መከርን አይጠብቅምና

ነው።  ሰው እንዳገኘው እግዚአብሔር እንደሰጠው መጠን ለእግዚአብሔር የሚገባውን የእግዚአብሔርን

አሥራት ያወጣል። ነገር ግን አሥራቱ መውጣት ያለበት እንደ ሕጉና እግዚአብሔር በሚያዘው ስፍራ ነው። 

Page 58: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 58/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

58ww.tlcfan.org

 

የሕዝቅያስና የሕዝቡ አሥራት፦ 

‘’5፤ ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥

የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በኵራት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት አብዝተው አቀረቡ።6፤ በይሁዳም

ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም

ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፥ ከምረውም አኖሩት።7፤ በሦስተኛው ወር

መከመር ጀመሩ፤ በሰባተኛውም ወር ጨረሱ።8፤ ሕዝቅያስና አለቆቹም መጥተው ክምሩን ባዩ

ጊዜ እግዚአብሔርና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ። 

9፤ ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቀ።10፤ ከሳዶቅም ወገን የሆነ ዋነኛው

ካህን ዓዛሪያስ። ሕዝቡ ቍርባኑን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፥

ጠግበናልም፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ የተረፈውም ይህ ክምር ትልቅ

ነው ብሎ ተናገረ።11፤ ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤት ጐተራ ያዘጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም

አዘጋጁ።12፤ ቍርባኑና አሥራቱን የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡት። ሌዋዊውም ኮናንያ

ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤13፤ በንጉሡም በሕዝቅያስና

በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣሄል፥ ይሬሞት፥

ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች

ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።14፤ የሌዋዊውም የይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን

መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ ለእግዚአብሔር በፈቃድ ባቀረቡት ላይ ተሾመ።

15፤ በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ክፍላቸውን

በእምነት ይሰጡ ዘንድ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ ከእጁ በታች ነበሩ።

16፤ ከሦስትም ዓመት ወደ ላይ ላሉ በየሰሞናቸው ለሥራቸውና ለአገልግሎታቸው ዕለት ዕለት

ወደ እግዚአብሔር ቤት ለሚገቡ ወንዶች ሁሉ፤17፤ በየአባቶቻቸውም ቤት ለተቈጠሩ ካህናት፥

ከሀያ ዓመትም ወደ ላይ ላሉ በየሥርዓታቸውና በየሰሞናቸው ለተቈጠሩ ሌዋውያን፥18፤

በማኅበሩም ሁሉ በየትውልዳቸው ለተቈጠሩ ለሕፃናቶቻቸውና ለሚስቶቻቸው ለወንዶችና

ለሴቶች ልጆቻቸውም ይሰጡ ነበር፤ በእምነት ተቀድሰዋልና።’’

2.ዜና.31፥5-12 

Page 59: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 59/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

59ww.tlcfan.org

 

ከምዕራፍ 29 ጀምረን ብናነበው ሕዝቡን ከላይ ላየነው ጥቅስ መከናወን ያገዛቸው ያነሳሳቸው

ምን እንደሆነ በቀላሉ እንገነዘባለን። ከዋና ዋናዎቹ ነገር ቅድስናና የእግዚአብሔር በዓል የሆነውን ፋሲካን በሚገባ

ማድረግና የቅዱሳን ትብብር ወይም ሕብረት ነው። ፋሲካን በዓል በሚግባ ያደረገ አሥራት ማውጣት ለእርሱ

ምጥ አይደለም። 

ሕዝቅያስ ለመልካም ለሆነ ነገር እንደ አባቱ ዳዊት ስለጭከነ፣ በዘመኑ ሁሉ የእግዚአብሔር

የሆነውን ነገር አስከበረ። ከዚህ በፊት በትውልድ መካከል ሆኖ የማይታወቅ ነገር በዘመኑ ተከናወነ። ዛሬ አቢያተ 

ክርስቲያናት ለቅድስና እንደ ሕዝቅያስ የጨከኑ መሪዎች ያስፈልጓታል። ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር

የሚገባውን በደስታ ከሚጠበቀው በላይ ሕዝቡ ያመጣል። የሚገርመው በሕዝቅያስ ዘመን በእምነት

መቀደሳቸው ነው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል። ያለ እምነት እግዚአብሔር ማስደሰት

አይቻልምና።

ዛሬም ባለንበት ዘመን ሕዝቡ ለእግዚአብሔር አሥራቱን እንዲያመጣ መጨቅጨቅና

አገልግሎት መከልከል ሳይሆን መጀመሪያ ባሪያዎቹ ነን የምንል ለቅድስና ራሳችንን ሕዝቡን በእግዚአብሔር

በማመንና በመታዘዝ ወደሚገኘው ቅድስና ሕይወት ልናመጣቸው ይገባል። እግዚአብሔር በእምነት እርሱን

በመታመን የሚቀድሱትን ሁሉ ያከብር፣ ያስፋ፣ ያበለጥግና ያነግስ ዘንድ ደስታው ነው። የሕዝቅያስና የሕዝቡ

አሥራት የሚያሳየው ይህን ነው። 

ነህሚያን ሕዝቡ አሥራት፦ 

’’37፤ የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቍርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም

ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ

አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። 38፤ ሌዋውያኑም

አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት

ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።39፤ የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም

የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣት ቍርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት

በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።

…………..43፤ እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት

አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።

Page 60: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 60/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

60ww.tlcfan.org

 

44፤ ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ

እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቍርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ

ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ። 45፤ እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት

የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ። 46፤ አስቀድሞም

በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።

47፤ እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን

በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን

ልጆች ሰጡ። ……………1፤ በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ አነበቡ፤ አሞናውያንና

ሞዓባውያንም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘላለም እንዳይገቡ የሚል በዚያ ተገኘ። 2፤ የእስራኤልን

ልጆች በእንጀራና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና ይረግማቸው ዘንድ በለዓምን ስለ ገዙባቸው ነው፤ ነገር

ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት መለሰው። 3፤ ሕጉንም በሰሙ ጊዜ ድብልቁን ሕዝብ ሁሉ

ከእስራኤል ለዩ። 4፤ ከዚህም አስቀድሞ በአምላካችን ቤት ጓዳዎች ላይ ተሾሞ የነበረው ካህኑ

ኤልያሴብ ከጦቢያ ጋር ተወዳጅቶ፥ 5፤ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን

የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም

የሆነውን የማንሣት ቍርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር። 6፤ እኔ ግን

በባቢሎን ንጉሥ በአርጤክስስ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበርና በዚህ ጊዜ

በኢየሩሳሌም አልነበርሁም። ከጥቂት ዘመንም በኋላ የንጉሡን ፈቃድ ለመንሁ፤ 7፤ ወደ

ኢየሩሳሌምም መጣሁ፤ ኤልያሴብም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦብያ ጓዳውን በማዘጋጀት

ያደረገውን ክፉ ነገር አስተዋልሁ። 8፤ እጅግም አስከፋኝ፤ የጦብያንም የቤቱን ዕቃ ሁሉ ከጓዳ ወደ

ውጪ ጣልሁ። 9፤ ጓዳዎቹንም እንዲያነጹ አዘዝሁ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃዎች የእህሉንም

ቍርባን ዕጣኑንም መልሼ በዚያ አገባሁ። 10፤ ለሌዋውያንም እድል ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥

የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄዱ ተመለከትሁ። 11፤

እኔም። የእግዚአብሔር ቤት ስለ ምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥

በየስፍራቸውም አቆምኋቸው።12፤ ይሁዳም ሁሉ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት ወደ ዕቃ

ቤቶች አመጡ። 13፤ በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም

ፈዳያን ሾምሁ፤ ከእነርሱም ጋር የመታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነርሱም የታመኑ ሆነው

ተገኙ፥ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።’’ ነህ.10፥37-38,12፦44,13፥5-12 

Page 61: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 61/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

61ww.tlcfan.org

 

በነህሚያና በሕዝቡ ላይ የሆነው ነገር ሕዝቅያስ ዘመን ጋር የመሳሳይ ነው። የእግዚአብሔርን

ነገር ለእግዚአብሔር ለዩ ቀደሱ። ሌላው ደግሞ ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕግ አነሳ። ሕጉ በሕዝቡ ጆሮ መነበብ

ተጀመረ ያን ጊዜ የተደባለቀ ትውልድ በጉባኤው መካከል በቃሉ ብርሃን ተገለጠ። ይህ ድብልቅ ትውልድም

ከሕዝቡ እንዲለይ ተደረገ። ይህ ብቻ አይደለም በእግዚአብሔር ነገር ላይ ተሹሞ የነበረው ሰው ከአሕዛብ ጋር

ተመሳጥሮ የእግዚአብሔር ሃብትና ንብረት ለጦቢያ ያስበዘብዝ ነበር። ይህ የእግዚአብሔር ሕግ ሲነበብ ሕጉን

የሚያከብሩ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሲመጡ ይህ አጭበርባሪ ሰው ተገለጠ። ይህን የክፋት ስራውን

እንዳይቀጥል ተደረገ። 

ስለዚህም ቅድስና በሕዝቡ መካከል መጣ። ከተደበላለቀ ትውልድ ጋር አንድ ጊዜ አለምን አንድ

ጊዜ እግዚአብሔርን ከሚል ትውልድ ጉባኤው ከነጻ በኃላ ሌዋውያኑ ሳይቀሩ እግዚአብሔር እንደደነገገው እድል

ፈንታቸውን እንደሚገባ ማግኘት ጀመሩ። አጭበርባሪ በሌለበት የእግዚአብሔር ቤት አሥራት ለባሪያዎቹ

ለጠራቸውና ለመረታቸው ከበቂም በላይ ነው። አሥራቱም እንደ ስርዓቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት

ጀመር። ካህናቱም የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያገለሉትም የሚገባቸው ድርሻቸውን ከመቅደስ ማግኘት ጀመሩ። 

ከላይ 6ኛና 7ኛው ሃሳባችን ላይ እንደተመለከትነው። ከአሥራት የሚቀድመው ቅድስናና

የእግዚአብሔርን ሕግ በሚገባ መስማትና ማመን ከክፋትም ሁሉ መራቅ ነው። ጽድቅን ስንወድ አመጻን ደግሞ

ስንጠላ የሚገባውን ነገር ስናደግ ለሰው ፊት ማድላትንና ሰውን መፍራትን ትተን እግዚአብሔር ስንፈራ

በረከትና እውነተኛ ስርዓት የእግዚአብሔር መገኘት ሃይል በሕዝቡ መካከል ይሆናል። ይህ ካልሆን የምናደርገውና

የሚሆነው ወሮበላ የሞላበት፣ ሻጭና ለውጭ የበዛበት ዋሻ የሆነ ወደዚያ የወረደ ምድኪን ሁሉ ማጅራቱን

የሚመታበትና እጅ ወደላይ ሃያማኖታዊ ድርጅት ይሆናል።

በሕዝቅያስ.44 ላይ እንደሚገኙ ጣኦታቸውን በልባቸው እንደያዙ ስርዓት ጠባቂ ብቻ ሆነው

እንደቀሩ ወደ እግዚአብሔር ወደ ተቀደሰው ነገር እንደማይቀርቡት ሰዎች እንዳንሆን በጊዜው እንደ ንጉስ

ሕዝቅያስና እንደ ነህሚያ ዘመን ወደ እግዚአብሔር ሃሳብ እንመለስ። የእግዚአብሔር እውነተኛ የሕግ ስርዓት

በቤቱ ሲሰፍን ሁሉ እንደሚገባው አሥራቱን መስጠትን ይማራል። ማስፈራራትና ማስጨነቅ ማስገደድ

በብሎም ከህብረት ማገድ ግን ከማጅራት መቺዎች ዋሻ የሚወጣ እንጂ ከእግዚአብሔር ቤት የሚወጣ ነገር

በፍጹም  ሊሆን አይችልም። ሰው እግዚአብሔርንና ሕጉን ወቆ ገብቶት እንጂ በግድ ወይም በፍርሃት

እንዲያቀርብ የእግዚአብሔር ፍቃድ አይደለም። ለማቅረብ መጀመሪያ ስርዓቱን ማወቅና በጽድቅ መኖርን

ይጠይቃል። “ ከማቅረብህ በፊት ከወንድምህ ጋር ተስማማ።” አለበለዚያ ሁሉ ከንቱ ነው። 

Page 62: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 62/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

62ww.tlcfan.org

 

የሚልኪያስ መልክት አሥራትና ሕግ ለማይጠብቅ ትውልድ ፦ 

‘’6፤ እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

7፤ ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምር ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ

ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን።

የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።8፤ ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን

ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። 9፤

እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። 10፤ በቤቴ ውስጥ መብል

እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም

አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 11፤ ስለ እናንተ ነቀዙን

እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥

ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 12፤ የተድላ ምድር ትሆናላችሁና አሕዛብ ሁሉ ብፁዓን ብለው

ይጠሩአችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 13፤ ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥ ይላል

እግዚአብሔር። እናንተ ግን። በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው? ብላችኋል። 14፤

እናንተም። እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ

በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል? 15፤ አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች

ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፤ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥

ያመልጣሉም ብላችኋል። 16፤ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤

እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ

መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ። 17፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ

እግዚአብሔር፤ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ። 18፤

ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና

በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ፣’’ ሚል3፥8-10 

‘’13፤ የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፤ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ

ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ ሎሌ ይመጣ ነበር፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፤

14፤ ወደ ድስቱም ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ቶፋው

ይሰድድው ነበር፤ ሜንጦውም ያወጣውን ሁሉ ካህኑ ለእርሱ ይወስደው ነበር። ወደዚያም

Page 63: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 63/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

63ww.tlcfan.org

 

በመጡት በእስራኤላውያን ላይ በሴሎ እንዲህ ያደርጉ ነበር።15፤ ደግሞም ስቡን ሳያቃጥሉ

የካህኑ ሎሌ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው። ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ

አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ ይለው ነበር።16፤ ሰውዮውም።

አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት ኋላም ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ ቢለው፥ እርሱ።

አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ እንቢም ብትል በግድ እወስደዋለሁ ይለው ነበር።

17፤ ሰዎቹም የእግዚአብሔርን ቍርባን ይንቁ ነበርና የጎበዛዝቱ ኃጢአት በእግዚአብሔር

ፊት እጅግ ታላቅ ነበረች።18፤ ሳሙኤል ግን ገና ብላቴና ሳለ

የበፍታ ኤፉድ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር፣’’

1ሳሙ.2፥13-17 

ሚልክያስ የእግዚአብሔርን ሕግ ስለሚንቅ ትውልድ ብቻ ሳይሆን እኛ የዘመን መጨረሻ ላይ

ለደረስን ለዚህ ዘመን ትውልድ ሳይቀር ትንቢታዊ መልዕክቶችን ከእግዚአብሔር ተቀብሎ አስተላልፎልናል። ዛሬ

በዚህ ባለንበት ወቅት በሌዋዊያን ክህነት የሚስተዳደር ምንም አይነት መቅደስ የለም። 

እዚህ ጋር ሚልክያስ ለቤተ ክርስቲያን አስራት ገንዘባችሁን መስጠት አለባችሁ እያለ ፈጽሞ

እያስተምረንም። ደግሞም ይህ እውነተኛው ነገር በሚልክያስ ዘመን የነበረ ሲሆን አሁን ግን ለእኛ ጥላና

ትምህርትን የሚሰጥ ነው። ለቤተ ክርስቲያ አሥራትን ከማውጣት ያለፈ ነገርን ያቀፈ ከእግዚአብሔር ለሕዝቡ

የተሰጠ ትንቢታዊ መልዕክት ነው። ይህ በእስራኤልና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው ችግር አሁንም

ከትንሣኤውና ከመንፈስ ቅዱስ መውረድ በመቀጠል በወንጌል የተጠሩ አማኞችን ችግር ያሳያል። ችግሩ ምን

እንደነበር በዝርዝር እንመልከት፦ 

እግዚአብሔር፦ እንዲህ ይላል። ‘’ወድጃችኋለሁ”

ሕዝበ እስራኤል፦(አማኞች) ግን። “በምን ወደድኸን?” ሚል.1፥2 

እግዚአብሔር፦ “እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔስ

አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል”

ሕዝበ እስራኤል፡- አማኞች ስምህን በመን አቃለልነው? “እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው?

ብላችኋል” ሚል.1፥6 

እግዚአብሔር፦ ‘’በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ።’’

ሕዝበ እስራኤል፦ ‘’እናንተም፦ ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኃል።” ሚል.1፥7

Page 64: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 64/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

64ww.tlcfan.org

 

እግዚአብሔር፦ “ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ

ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ፤ አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፤ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ

ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን?” ሚል.1፥8-9 

እግዚአብሔር፦  “በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው 

በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም። ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም። ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”

ሚል.1፥10

እዚህ  ጋር  እናቁምና  እግዚአብሔር ምን እያለ  እንደሆነ  እንመልከት።  ካህናቱ  የእግዚአብሔር 

ሥምና ሕግ ንቀዋል። የሚያቀርቡትም መስዋዕት ዕውር፣ በሽተኛና ሽባ የሆነ መስዋዕት ነው። የእግዚአብሔር 

ነብይ ስለዚህ እግዚአብሔር የእነርሱን ስጦታ ምንም እንደማይቀበል ይነግራቸዋል። ይህ ስናይ በእውነቱ ከሆነ 

ሕዝቡ  አሥራትን  እያወጡ  ነውን? የአሥራታቸው  ጥራት  በእግዚአብሔር  ዘንድ  ተቀባይነት  አለውን?

እግዚአብሔር የሚፈልገው መስዋዕት እዲህ ያለውን ደካማ መስዋዕት ነውን? በፍጹም አይደለም። 

ይህ  አይነቱ  መስዋዕታቸው  የሰዎቹን  ችግር  ያሳያል።  እግዚአብሔር  ይህን የመስዋዕታቸውን 

ውጫዊ ነገር ያሳያቸው እንጂ እግዚአብሔር ሊያሳያቸው የወደደው የልባቸውን መቆሸሽ ለእግዚአብሔር ሕግ 

በልባቸው ያላቸውን ስፍራ ለማሳየት ነው። እግዚአብሔርም እንዲያዩት የወደደው በልባቸው ያለውን ሃጢያትና 

ለእግዚአብሔር ስርዓት ሕግ ያላቸው የቀለለ አስተሳስብ ነው። 

እግዚአብሔር፦ ‘’ ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ

ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል። እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል፤ በሕግም

ብዙ ሰዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊንም ቃል ኪዳን አስነውራችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ

መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት

የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።’’ ሚል.2፥7-9 

እግዚአብሔር፦ “ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምር ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ

ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’’

ሕዝበ እስራኤል፦ “እናንተ ግን። የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል፣” ሚል.3፥7

Page 65: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 65/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

65ww.tlcfan.org

 

እግዚአብሔር፦ “ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን?እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል፣”

ሕዝበ እስራኤል፦ ‘’ እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል፣’’ 

እግዚአብሔር፦ “በአሥራትና በበኵራት ነው።’’ 

እግዚአብሔር አሥራትና በኵራትን መስረቃቸውን ለእግዚአብሔር ሕግ በልባቸው ያላቸውን

ክብርና ከመስጠታቸው ጀርባ ያለውን የተዛባ የልባቸውን ሃሳብ ለማሳየት ነው። አሥራትም ሆነ መኵራት

እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲሰጠው የጠቀው የራሱ ድርሻ ነው። የቀረውን ሁሉ ትርፍ ግን ለራሳቸው እንዲወስዱ

እግዚአብሔር ትቶላቸዋል። ሰለ እዚህ ሁሉ ስጦታው እግዚአብሔርን ምንም ያህል አይወዱትም።

አለመውደዳቸውን እርሱን ባለመታዘዝ ያሳያሉ። እግዚአብሔር ስለሰጠን ሰለ በዛው ነገር ምን ያህል

እናመሰግነዋለን? ለእግዚአብሔር ያላቸው ግንዛቤ ለእግዚአብሔር ሕግ ያላቸው ስፍራ ምን ያህል ነበር?

እግዚአብሔር አሥራታቸውንና መባቸን ሲያቀርቡለት እግዚአብሔር የረከሰ እንጀራ ነው አላቸው። ለምን? 

ይህን ሁሉ ስጦታ አሥራት መባ በኩራታቸን አቀረቡ በእግዚአብሔር ፊት ግን ርኩስ ተቀባይነት

የሌለው ነበር። ሚልኪያስ ነብይ ነው። ሙሴ ነብይ ነበር። (ዘዳ.34፥10) ኢየሱስ ደግሞ የነብያትንና ሕጉን

ትዕዛዛት ሊያፈርስና ሊሽር አልመጣም ሊያጸናው እንጂ። ማቴ.5፥17 ከነብዮ ሙሴ በታች እግዚአብሔር

የእስራኤልን ሕዝብ መምድረበዳ እንጀራ መገበ። ዮሐ.6፥31 በነብዮ በሚልክያስ ደግሞ እግዚአብሔር

አሥራቱናና ብኩራቱን ወደ ጎተራዬ አስገቡ አለ። ይህም፦ 

“በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤

የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ

በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’’ ሚል.3፥10 

እዚህ ጋር ልናተኩር የሚገባው እግዚአብሔር የሚያፈሰውና የሚያተረፈርፈው በረከቶችን

ሳይሆን አንድ በረከትን እንደ ሆነ ነው። ብዙ ሳይሆን አንድና ነጠላ ነው። ይህ ጥቅስ እንደ እኔ መረዳት በብዙ

ሰዎች ትክክለኛ መረዳትን ያላገኘ ጥቅስ ነው። 

"…meat in My house, and prove me now herewith, says the Lord of hosts, if I will not open you the

windows of HEAVEN, and pour you out A [keep in mind that this blessing is

singul r

 

blessing

]

blessing that there shall not be room enough to receive IT [again, singul r] (Mal. 3:10).

Page 66: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 66/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

66ww.tlcfan.org

 

በዕብራይስጡ ቃል በእንግሊዘኛው ”̀ሚት” የሚለውን ታራፕ taraph  ይለዋል። ጠንካራው

የዕብራይስጥ መዝገበ ቃላት ትርጉሙን እዲህ ያስቀምጠዋል፦ “The word "meat" taraph means "to pluck off

or pull to pieces; to supply with food (as in morsels)" (Strong’s Hebrew Dictionary, p. 105, 2963).”

 ይህ

ሁሉ ቃል ባንድ ላይ ስንወስድው የሚሰጠን ዳቦ መቆራረስ ማለት ነው። ከዚህ ተነስተን በዚያን ወቅት በጎተራው

ውስጥ ሊቆራረስ የሚችል ዳቦ እንደነበር በቀላሉ እንረዳለን።

ኢየሱስ በምድረበዳ አባቶቻቸ ስለ በሉት እንጀራ ምን እንዳላቸው ላስታውስ እወዳለሁ።

ምክንያቱም እርኩስ እንጀራ የምናውቀው ቅዱስ የሆነ እንጀራ ምን እንደሆነ ካወቅን ነው። እግዚአብሔር ደግሞ

የእርኩስ እንጀራ መስዋዕትን ሆነ ስጦታን አይቀበልም። 

‘’31 ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ አባቶቻችን

በምድረ በዳ መና በሉ አሉት። 32 ኢየሱስም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥

እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ

የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ 33 የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ

ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው። 34 ስለዚህ። ጌታ ሆይ፥

ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን አሉት።’’ ዮሐ.6፥31-34 

ምን? ኢየሱስ እንዴት ይህ ሊል ይችላል? በቃሉ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎ? አይሁዶች አባቶቻችን

የሰማይ እንጀራ በሉ አሉት። ሙሴ በእውነት ከሰማይ እንጀራ እኔ ስጠኃችሁ ብሏቸዋልን? በእውነት ይህ ተብሎ

ተጽፎ ቢሆን ኢየሱስ ይህን ባልተናገረ ነበር። ያልተፃፈውን ተጽፏል ብሎ ከሚናገር ይጠብቃችሁ። ከቃሉ አትለፍ

የሚለውን ጠንቅቃችሁ ተማሩ። ኢየሱስ ግን ራሱ ቃል ስለ ሆነ ሙሴ ከሰማይ ምንም እንጀራ እንዳልሰጣቸው

ተናገረ። እውነተኛ እንጀራ ደግሞ እግዚአብሔር ከሰማይ የሚሰጠው እርሱን ብቻ እንደ ሆነ አስረግጦ

አስቀመጠ። ኢየሱስ ብዙዎች እንደሚሉት ቃሉን አይቃረንም። ውሸተኛ አስተማሪዎችን እንጂ፣ ልክ በማቴ.5፥

17 እንደተናገረው የነብያትንም ሆነ የሕጉን ትዕዛዝ በመታዘዝ ይፈጽማል ወይም ያደርጋል። 

በምድረበዳ የበሉት እንጀራ ለእውነተኛው እንጀራ ለኢየሱስ ጥላ ነበር። እውነተኛው ከሰማይ

የወረደው እንጀራ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህ እውነት በሚልክያስም ላይ ለተነገረው ትንቢትም ጭምር ነው።

እርኩስ እንጀራ ካለ እግዚአብሔር የፈለገው ደግሞ እርኩስ ያልሆነ እንጀራ አለ ማለት ነው። እርሱ ደግሞ

ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ የወረደው ኢየሱስ ነው።

Page 67: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 67/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

67ww.tlcfan.org

 

ይህንን አንዱን በረከት እንዴት እንደምናገኝ የሰማይ መስኮት እንዴት እንደሚከፈትልን ነብዩ

ሚልክያስ ሲናገር። የእግዚአብሔር የሆነውን አሥራቱንና በኩራቱን ወደ ጎተራው በማስገባት ነው ይለናል። ይህን

እንጀራ ዘወትር ስጠን በማለት የሚመጣ ብቻ አይደልም። ምድረ በዳህን የሚያሻግር ሰማያዊ እውነት ባለህበት

ምድረበዳ ጠንክረህ በውድህ ላይ ተደግፈህ ከምድረ በዳ እንድትወጣ የሚያደርግህ የእግዚአብሔር ሕግ ሁሉ

በምድረ በዳ የሰጠህን ያስተማረህን ስትታዘዝ ስትፈጽመው ነው። ያልፈጸ ያልታዘዘ ስላልሰማ ስላላመነ

የተስፋውን ምድር ሳይወርስ በምድረ በዳ አለቀ። ይህ እንዳይሆን የእግዚአብሔር ሕግ ሁሉ እናክብር እንታዘዝ።

የሰማይ መስኮት የሚከፈተው ወደጎተራ ላስገባ ሰው ብቻ ነው። 

ሰለዚህ እግዚአብሔር የረከስ ገንዘብ ይፈልጋልን? በፍጹም አይፈልግም። እግዚአብሔር ግን

ሁለንተናችን በፍጹም ልባችን ከወደድነው ሕጉን በደስታና በማክበር እንድንጠብቀው ይፈልጋል። ሰለዚህ

እግዚአብሔር በልብህ ያለውን ነገር እንጂ ከረጢት ውስጥ የምትጥለውን አያይም ማለት ነው። ይህን ስንል ግን

አሥራት መስጠት የለብንም ማለት አይደለም። ኢየሱስ በማቴዎስ እንደተናገረው ይህንን ሳትተው የሚለው

እንደ ጻፎችና ፈሪሳዊያን አሥራት ማውጣታችሁን ማለቱ ነበር። ማቴ.23 

እኛ ክርስቶስን እርኩስ ያልሆነውን እንጀራ እንድንሆን እርሱን እንድንመስል እግዚአብሔር

ወስኖብናል። ስለዚህ ይህ ከሰማይ የወረደ እንጀራ የእግዚአብሔር ሕግ የሚጠብቅ የሚታዘዝ ነው። አንተስ /  

አንቺስ ይህ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ትመስለዋለህን? ቃሉን ሕጉን ሰምቶ የሚያደግ ብቻ ቤቱን በዓለት ላይ

የሰራውን ኢየሱስን ልባሙን ሰው ይመስለዋል። ሌላው ግን እርኩሱን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት

የሌለውን የወደቀውን አዳምን ይመስላል። ንፋስም በሚነፍስ ጊዜ ተጠርጎ ይወሰዳል። ይህ ደግሞ

የመንግሥቱም ፍጻሜ ይሆናል። አሥራት ወደ ጎተራ መግባት አለበት ይህም በቤቱ መብል እንዲሆን ነው። ቤቱ

የት ነው? ይህ ደግሞ አስራቱን ለሚያስገባው ሰው አንዱ በረከት የሆነውን የሰማይ እንጀራ ወደኛ እንዲወርድ

መስኮትን ያስከፍታል። ጌታ ስለዚህ ምን ይላል? 

የጌታ ትዕዛዝ ሰለ አሥራት፦ 

”እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥

ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤

ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር፣” ማቴ.23፥23 

Page 68: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 68/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

68ww.tlcfan.org

 

ኢየሱስ የትም ቦታ ሕግን ሻርኩ። ሕግ መጠበቅ አያስፈልግም ብሎ አላስተማረም። ይልቁንም

ብዙን ጊዜ እንዲ ሲል ይሰማል። ከሕግ አንዲት አትወድቅም ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ። የሚወደኝ እርሱ ትዕዛዜ

የሚጠብቅ ነው። ትዕዛዜን የሚጠብቅ እኔም አባቴም እናውቀዋለን። ትዛዜን የሚጠብቅ እኔን ይመስላል የሚሉ

ቃላቶችን ኢየሱስ ደጋግሞ ይጠቀማል። 

ይህ መጽሐፍ ግን ስለ አሥራት ስለሆነ ኢየሱስ ስለ አሥራት ያስተማረውን ሕግ እንመለክታለን።

ከላይ ባየነው ጥቅስ መሰረት ኢየሱስ ሰው አሥራቱን እንዲያወጣ ይፈልጋል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ

ዋንኛው ነገር ፍርድ፣ምሕረትና ታማኝነት እንደ ሆነም ይናገራል። ስለዚህ በአሥራታችን ታማኞች እንድንሆንና

በራሳችንም ላይ መፈረድን መማር አለብን። እግዚአብሔር  1/10ኛውን ሲጠይቀን እኛ 9/10ውን

እንደምንወስድ መዘንጋት የለብንም። አምጡ የሚለን ደግሞ ለራሳችን ጥቅም እንደሆነ ካወቅን አስተውለን

እግዚአብሔር እያከበርን በደስታ ልናደርገውም ይገባል። 

‘’40 እናንት ደንቆሮዎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን?41 ነገር ግን በውስጥ

ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል። 42 ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን፥

ከአዝሙድና ከጤና አዳም ከአትክልትም ሁሉ አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና እግዚአብሔርን መውደድ

ስለምትተላለፉ፥ ወዮላችሁ፤ ነገር ግን ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉት ይገባችሁ ነበር። 43 እናንተፈሪሳውያን፥ በምኵራብ የከበሬታ ወንበር በገበያም ሰላምታ ስለምትወዱ፥ ወዮላችሁ። 44 እናንተ

ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ሰዎች ሳያውቁ በላዩ የሚሄዱበት የተሰወረ መቃብር ስለምትመስሉ፥

ወዮላችሁ። 45 ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ። መምህር ሆይ፥ ይህን ማለትህ እኛን ደግሞ መስደብህ

ነው አለው። 46 እርሱም እንዲህ አለ። እናንተ ደግሞ ሕግ አዋቂዎች፥ አስቸጋሪ ሸክም ለሰዎች

ስለምታሸክሙ፥ ራሳችሁም በአንዲት ጣታችሁ ስንኳ ሸክሙን ስለማትነኩት፥ ወዮላችሁ። 47 አባቶቻችሁ

የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፥ ወዮላችሁ። 48 እንግዲህ ለአባቶቻችሁ ሥራ

ትመሰክራላችሁ ትስማማላችሁም፤ እነርሱ ገድለዋቸዋልና፥ እናንተም መቃብራቸውን ትሠራላችሁ። 49

ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች። ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥

ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል፥ 50 ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም፥ 51 ከአቤል

ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ፥ ከዚህ

ትውልድ እንዲፈለግ አዎን እላችኋለሁ፥ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል። 52 እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን

መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ,,,, ,,,ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ።’’ 

ሉቃ.11፥41-52

Page 69: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 69/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

69ww.tlcfan.org

 

ጻፎችና ፈሪሳዊያን የእግዚአብሔርን ሕግ አላዋቂዎች በኢየሱስ ተገስፁ። ከለይ በትንቢተ

ሚልክያስ ትንቢታዊ መልዕክት እንዳየነው ገንዘናቸውን ብቻ ሳይሆን አስቀድመው ልባቸን ለእግዚአብሔር

መስዋዕት አድርገው መስጠት እንዳለባቸው ነገራቸው። ልክ እንደ ዘንድሮ ልብን እንዳጠነከረ አማኝ ተገሰጹ።

ሕግ የለሽ አማኝ፣ ሕግን የማያውቅ አማኝ አስቀድሞ ልቡ ለእግዚአብሔር ከመስጠትና ሕጉን

ሁሉ በመታዘዝ እግዚአብሔርን ከመውደድ ይልቅ ገንዘቡን ያመጣል። አንዳዶች ደግሞ አሥራት የሚሰጡት

ይህ ተግባራቸው እንደ ፈሪሳዊያን ለታይታ ነው። ይህ ሰው በሰዎች ዘንድ አሥራት ይከፍላል ይሰጣል የሚልን

ከበሬታና አንዳንዶች ደግሞ ታማኝ አሥራት ከፋይ ተብሎ የሚለጠፈውን የስም ዝርዝር ለማሟላት ሲሉ

አሥራታቸውን የሚሰጡ፣ አንዳዶች ደግሞ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለማግኘት ብለው አሥራት የሚስጡም

አልታጡም። የባሰው ግን የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ተብሎ ለአገልግሎት ብቃት አሥራትን ማውጣት

አለበት የሚል መርህ ያላት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ከሁሉ የባሰች ናት። ቃሉ ላይ ባንጨምር ወይ ባንቀንስ

መልካም ነው። 

ያልተገባ አሥራት አወጣጥ ሕግ የለሽ አስተማሪዎችንና መሪዎችን በገንዘባቸው በመደገፍ

ሃጢያትና ውሽት ሃይማኖታዊ ስርዓት በምስኪኑ ሕዝብ መካከል እንዲስፋፋ ያደርጋል። ይህ ደግሞ አሥራት

የሚያወጣውን ሰው እንኳን የሰማይ መስኮት ሊከፍት ሰማዮን ነሃስ ምድሩን ብረት ያደርግበታል። ሕግ

አላዋቂዎች ኢየሱስ እንዳለ ከሕዝቡ የእውቀትን መክፈቻ የሚወስዱ ናቸው። እውቀት ከሌለ ደግሞ ስሕተት

ይበዛል። ሕግ አላዋቂዎች ወይ ገብተው በስርዓት የእግዚአብሔር ሕግ አውቀውና ተረድተው ራሳቸው

አያደርጉትም ደግሞም ሰዎችም እንዲያደርጉት አይገፋፉም። መንገድን ይዘጋሉ። የእግዚአብሔር ሕግና ስርዓትን

ሊያስከብሩ በሕዝቡ መካከል ለሕዝቡ የሚልካቸውንም ከሕዝቡ መካከል እንዳይገቡ በአደባባይ ከንቱ ስምንና

የሃሰት ትንቢትን በሚከፍሏቸው አገልጋዬች በቃል በሚያስቷቸው ነብያት በማስነገር ጻድቃንን የተቀቡትን

ባሪያዎች ያሳድዳሉ፣ ይገድላሉ፣ ሃሰትንና ክፋት በቤቱ ያበዛሉ። 

ጌታ ግን ሕግን በሚያውቅ ሰው ደስ ይሰኛል። ያ ብላቴና እንዃን ሕግን ሁሉ ጠብቂያለሁ ሲለው

ደስ ተሰኘ ይላል። እግዚአብሔር ሕግ መጠበቃችን ደስ ይሰኛል ደግሞ ገና ያልጠብቅነው ሕግ ካለ ለኛ በመግለጥ

እንድነጠብቀው ይመክረናል። ነገር ግን መታዘዝም ሆነ ማድረግ የእኛ ፋንታ ነው። እግዚአብሔር ከመስዋዕትና

ከአሥራት ቀድሞ የልብ መማረክን ይመልጣል። ኢየሱስ ስለ አሥራት ሲያስተምር አሥራት ማውጣት እንዳለ

ያስተምረንና ነገር ግን አሥራቱን ከመስጠታችን በፊት ልባችንን ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ሕግ አሳልፈን

ልንሰጥ እንደሚገባ ያስጠነቅቃል። ቀድመን ከሰዎች ጋር ሁሉ በሰላም በእርቅ መኖር እንደሚገባንም አስተማረ። 

Page 70: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 70/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

70ww.tlcfan.org

 

የአሥራት ጥያቄና መልስ 

1.  አስራታችንን የት እናምጣው? 

መልሱ በአጭሩ የእግዚአብሔር ሥም በሚጠራበት ስፍራ ነው። ወደ እግዚአብሔር ጎተራ ነው።

ይህ እግዚአብሔር ሥሙ የሚጠራበት ስፍራ የእግዚአብሔር ጎተራ በመባል ይታወቃል። ሚልክያስ.3፥10 ይህን

የእግዚአብሔር ጎተራ የት እናዳለ? ምን እንደሚመስል? እንዴት ማስገባት እንደምንችል? ከማየታችን በፊት

ኢየሱስ ሰለ አንድ ባለጠጋ የተናገረውን ምሳሌ እንመልከት። ታሪኩ የሚጀምረው ከሕዝቡ አንድ ሰው ወደ

ኢየሱስ መጥቶ መምህር ሆይ ከእኔ ጋር እንዲካፈል ለወንድሜ ንገረው አለው። ኢየሱስስም ለሰውየው መልሶ

አንተ ሰው ፈራጅና አከፋፋይ በላያችሁ እንድሆን ማን ሾመኝ? አለው። ከዛም ወደ ሕዝቡ ዞር በማለት የሰው

ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ። ከመጎምጀትም ሁሉ ተጠበቁ። አላቸው፦ ይህም የጎተራ

ሚስጢር የተገለጠበት ምሳሌ ነው። በመቀጠል ኢየሱስ የሃብታሙን ሰው ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦

“16 ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል። አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም

ሆነችለት።17 እርሱም። ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ

በልቡ አሰበ።18 እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥

በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤19 ነፍሴንም። አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን

የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።20

እግዚአብሔር ግን። አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤

ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው።21 ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥

በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።22 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ

አለ። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት

አትጨነቁ።23 ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና።24 ቍራዎችን ተመልከቱ፤

አይዘሩም አያጭዱምም፥ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፥ እግዚአብሔርም

ይመግባቸዋል፤ እናንተስ ከወፎች እንዴት ትበልጣላችሁ?25 ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ

ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?26 እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ

የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ?27 አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ

ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ

በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም።28 እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም

Page 71: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 71/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

71ww.tlcfan.org

 

ወደ እቶን የሚጣለውን በሜዳ የሆነውን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ

እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?29 እናንተም የምትበሉትን

የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤30 ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ

ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል።31 ዳሩ ግን

መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን

ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።33 ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ፤

ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን

የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤34.መዝገባችሁ ባለበት

ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፣” ሉቃ.12፦16-34 

እዚህ ምሳሌ ላይ ኢየሱስ ሊያስተምር የፈለገው ነገር የእግዚአብሔር ጎተራ የማያውቅን ሰውና

መጨረሻው በእግዚአብሔር ፊት ምን እንደ ሆነ ነው። በአንጻሩም የእግዚአብሔር ጎተራ የት እንደሚገኝ ነው?

ሰውየው ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁ ይላል። እግዚአብሔር ብልም በማያጠፋበት በሰማይ የማያልቅ

መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮሮጆ (ጎተራ) አድርጉ በማለት የእግዚአብሔር ጎተራ በሰማይ እንደሚገኝ

በቃሉ ያስረዳል። ሰማይ ሲል ይህ በለያችን ያለው የተንጣለለው ሰማያዊውን ማለቱ አይደለም። ነገር ግን

እርሱም ቢሆን ሰማይ በመባል ነው የሚታወቀው። ሰማይ ግን ከዚህ ከፍጥረታዊው ሰማይ ያለፈ ነው። 

ይህ በአይናችን የምናየው ሰማይ የእግዚአብሔር ጎተራ ሊሆን አይችልም። ሰለ ሰማይ ዘፍጥረት

በሸመገለው አይን በሚለው መጽሐፌ ላይ በጥልቀት ያስቀመጥኩ ሲሆን። ይህን መጽሐፍ ያለነበባችሁ ሁሉ

እንድታነቡ አበረታታለሁ። እግዚአብሔር ሰማይ የሚለው መንፈሳችንን መሆኑን አሁን እንድታውቁ እወዳለሁ።

ስለዚህ ብዙ መረዳት ከፈለጋችሁ መጽሐፉን አንቡቡት። መንፈሳችን እግዚአብሔር ያደረበት ሰማይ ነው። 

እግዚአብሔር የሚኖርበትና የሚያድርበት ሥፍራ ሰማይ ነው። ጳውሎስ ሥስተኛ ሰማይ ብሎ

ይጠራዋል። ይህ ሰማይ የእግዚአብሔር ዙፋን ነው። ማለትም የእርሱ መቀመጫ ነው። በጌታ ዳግም የተወለዱ

ሁሉ መንፈሳቸው የእግዚአብሔር ዙፋን ነው። ስለዚህም በሌላ አባባል ወይም ስም ብንጠራው ሰማይ ነው።

የውስጠኛው ሦስተኛው ክፍል ሰማይ። ይህን ስንል ግን የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ግዛት ወይም መንግሥት

የለም እያልኩ አይደለም።

Page 72: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 72/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

72ww.tlcfan.org

 

የእግዚአብሔር ጎተራም የሚገኘው እግዚአብሔር በሚገኝበት ስፍራ ነው። ኢየሱስም ይህን

ግልጽ ባለ አባባል መዝገባችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናል ይላል። ይህ ማለት የያንዳዳችን ልብ ሰማይ

ላይ ተንጠልጥሏል ማለት አይደለም። የከበረ መዝገብ ያለበት ይህ ሽክላ የሆነው ሥጋችን ውስጥ ሲሆን ይህ

ጎተራ ደግሞ የሚገኘው እንደ ሥጋ መታየት በማይችለው መንፈስ ውስጥ ነው። 2.ቆሮ.4፥6-10 ልባችን ውስጥ

ነው። ሰለዚህ መዝገብና ልብ ሊነጣጠሉ የማይችሉ መሆናቸውን ጌታ ኢየሱስ ያስተምራል። ለራሱ በፍጥረታዊ

ስፍራ ገንዘብ የሚያከማች በእግዚአብሔር ፊት ደሃ እርሱ ነው።ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ለነፍሳችሁ የምትበሉት

አትጨነቁ አለ እንጂ ለሥጋችሁ የምትበሉት እንዳላቸው በትኩረት ከኢየሱስ ትምህርት ልንማር ይገባል።

የነፍስ መብል መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ መብልና መጠጥ አይደልም። ምክንያቱ ነፍሳችን

የሚያስፈልጋት የእግዚአብሔር መንግሥት ሕግ ነው። ይህ ደግሞ የሚመጣው በእግዚአብሔር ቃል ነው።

መንግሥቱ የሚጸናው በቃሉ ነው። እንድንፈልግም የታዘዝነው ይህንኑ መንግሥቱን ነው። የእግዚአብሔር

መንግሥት ደግሞ መብልና መጠጥ አይደለችም። ጽድቅ፣ ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነች ደስታ እንጂ። ይህ

ሁሉ የሚሆነው በመንፈስና በነፍስ ውስጥ ነው። ይህ ክብር በሁለቱ ክፍል ሲጠናቀቅ ወደ ውጭ በመውጣት

በሥጋችንን ይገለጣል። ከምድር የሆነው ሥጋችን በክብሩ ያንጊዜ ይሞላል። ወይም ምድር የእግሩ መርገጫ

ማለትም መራመጃው ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግላል። ይህን ስል ስለ ሥጋችን ስለ ፍጥረታዊው አካላችን

እላለሁ። 

ሰነፍ የሆነው ባለጠጋ ግን ልክ እንደ አምስቱ ሰንፍ ደናግል ገንዘቡ በቅባት ሊለውጠው ሲገባ

ባለመለወጡ ያለውን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አጣ። የሥጋው ድካም ለሞቱ ሆነ። ምክንያቱም ሰው በእንጀራ

ብቻ መኖር አይችልምና ነው። ነፍሳችን የምትወሰደው አንደኛው የእግዚአብሔር ጎተራ ባለማወቅ ሲሆን

ሁለተኛው ደግሞ አውቀን ገንዘባችንን በጊዜው እንደ ልባሞቹ ደናግልት በእግዚአብሔር ጎተራ ሳናከማች ስንቀር

ነው። የእግዚአብሔር ጎተራ የሚገኘው የእግዚአብሔር ሥም በሚጠራበት ስፍራ ነው። የከዚህ በታች ያለው

ጥቅስ መጽሐፍ ቅዱሱን ከፍተው ያርጋግጡ ደንግሞም ደጋግመው ያንብቡት ያሰላስሉት። 

“22፤ ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ። 23፤ ሁልጊዜ

አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ

በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን የወይን ጠጅህንም የዘይትህንም አሥራት

የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ። 24፤ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥

መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ አምላክህም እግዚአብሔር ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ

Page 73: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 73/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

73ww.tlcfan.org

 

ቢርቅብህ፥ ይህን ወደዚያ ለመሸከም ባትችል፥ ትሸጠዋለህ፥ 25፤ የዋጋውንም ገንዘብ

በእጅህ ይዘህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳለህ። 26፤ በዚያም

በገንዘቡ ሰውነትህ የፈለገውን፥ በሬ ወይም በግ ወይም የወይን ጠጅ ወይም ብርቱ

መጠጥ ሰውነትህም የሚሻውን ሁሉ ትገዛለህ፤ በዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት

ትበላዋለህ፥ አንተና ቤተ ሰብህም ደስ ይላችኋል፣” ዘዳ.14፥22-29

አሥራት የሚመጣው የእግዚአብሔር ሥም በሚጠራበት ስፍራ ነው። የእግዚአብሔር ሥም

ለመጀመሪያ ጊዜ መጠራት የጀመረው ሴት ከተወለደ ጀምሮ ነው። “አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ፤ ወንድ

ልጅንም ወለደች። ስሙንም፦ ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት

አለችው። ለሴት ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት ስሙንም ሄኖስ አለው፤ በዚያን ጊዜም በእግዚአብሔር ስም

መጠራት ተጀመረ።” ዘፍ.4  የእግዚአብሔር ሥም ስፍራን ይዞ ግን መጠራት የጀመረው በሴሎ ነው። ከዛም

በኃላ ከሴሎ ተነስቶ በኢየሩሳሌም መጠራት የእግዚአብሔር ሥም መጠራት ተጀመረ። እግዚአብሔር ሕዝበ

እስራኤል የእግዚአብሔር ሕግ ካለመታዘዛቸው የተነሳ ስሙን ከሴሎ እንዳነሳ ከኢየሩሳሌምም ላይ ሥሙን

አነሳ። ሕዝቅኤል 11ና ኤር.7 ላይ ቃሉ እንደሚናገርው የእግዚአብሔር ክብር ከመቅደሱ ወጥቶ ወደ ደብረ ዘይት

ተራራ ሄደ። 

“1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።2

በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር። እግዚአብሔርን

ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።3

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ

በዚህም ስፍራ አሳድራችኋለሁ።4 የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥

የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ።5 መንገዳችሁንና

ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥6

መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትገፉ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥

ክፉም ሊሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥7 ከዘላለም እስከ ዘላለም

ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ 8. እነሆ፥ በማትረቡበት

በሐሰት ቃል ታምናችኋል።9 ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፥ በሐሰትም

ትምላላችሁ፥ ለበኣልም ታጥናላችሁ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት

Page 74: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 74/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

74ww.tlcfan.org

 

ትከተላላችሁ፤10 መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ። ይህን

አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም አላችሁ።11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት

በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።12 ነገር ግን

በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፥ ከሕዝቤም

ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ።13 አሁንም ይህን ነገር ሁሉ ስላደረጋችሁ፥

በማለዳም ተነሥቼ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ

ስላልመለሳችሁ፥14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት

በምትታመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ አደርጋለሁ።15

የኤፍሬምንም ዘር ሁሉ፥ ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፥ እንዲሁ ከፊቴ

እጥላችኋለሁ።16 እንግዲህም አልሰማህምና ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም

ልመናና ጸሎት አታድርግ፤ አትማልድላቸው።” ኤር.7፥1-16 

ነገር ግን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብር ሆኖ በደብረ ዘይት ተራራ ተገለጠ። እግዚአብሔር የሰው

እጅ የሰራው ውስጥ መኖሩን አቁሞ በስው ውስጥ መኖሪያውን አደረገ። ይህ ማለት የእግዚአብሔር በፍጥረታዊ

ስፍራ መጠራቱ ቀርቶ በሰው ልጆች ውስጥ መጠራት ጀመረ። እንግዲህ የእግዚአብሔር ሥም ሆነ

እግዚአብሔርም ያለው በስው ውስጥ ነው። ሥሜን እጽፍባቸዋልሁ በእነርሱም ላይ እኖረዋልሁ እንዳለ

ኢየሱስን ከሙታን በማስነሳት ለኛና ለልጆቻችን ይህንን ፈጸመው።  እርሱም ሥሙ አስታወቀን ደግሞም

ያስታውቀናል። 

“12 ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ

አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ

የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።3

ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ

ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥ 4 ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል። 5

ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት

ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።” 

ራዕይ.3፥12,22፥3-5 

Page 75: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 75/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

75ww.tlcfan.org

 

ኢየሱንን በፍርድ ፊት የቆሙት የት አይተን እንቢ አልንህ ከለከልን ባሉት ጊዜ ለአንዱ

ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረሃችሁት ነው አላቸው። ይህም የሚይሳየው እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ማድሩን

ሥሙም በዚያ መጠራቱን ነው። ማቴ.25፥40,45 በምድር የምናየው ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ሥም የተሸከመ

ነው። ምክንያቱ እርሱ ፈጥሮታልና ነው። እንግዲህ አሥራት የሚመጣው እግዚአብሔር ሥም በሚጠራበት

ስፍራ ከሆነ እንግዲህ አሥራት የሚመጣው ወይም የአሥራት ፍጻሜው ወደኛው ውስጥ ነው።

ይህን ስንል ደግሞ አሥራት የእኛ ነው ማለታች አይደለም። እዚህ ጋር ጥንቃቄ ልናደርግ

እወዳለሁ። ነገር አሥራት ግን በእኛ ውስጥ የሚኖረው የእግዚአብሔር ነው። ታዲያ እንዴት አድርጋን አሥራቱን

እቤቱ ጎተራው እናስገባ? 

በብሉይ ኪዳን ማንኛውም አማኝ አሥራቱን በዓመት ሦስት ጊዜ ይዞ የእግዚአብሔር ሥም ወደ

ሚጠራበት ስፍራ ይሄዳል። ስፍራው ቢርቀው አሥራቱ እህል ቢሆን እንስሳ ቢሆን መሸከም ስላማይችል በገንዘብ

ይለውጠዋል። ገንዘቡን ግን ይዞ ወደ እግዚአብሔር ሥም ወደሚጠራበት ስፍራ 2ኛ እጅ ጨምሮበት ይመጣል።

ይህ የሆነበት ምክንያት በሃገሩ ውጭ በማንኛውም ሥሙ በማይጠራበት ስፍራ ላይ አሥራትን ማውጣት

በእግዚአብሔር የተከለከለ ስለ ሆነ ነው። 

“17፤ የእህልህን የወይን ጠጅህን የዘይትህንም አሥራት፥ የላምህንና የበግህንም

በኩራት፥ የተሳልኸውንም ስእለት ሁሉ፥ በፈቃድህም ያቀረብኸውን፥ በእጅህም

ያነሣኸውን ቍርባን በደጆችህ ውስጥ መብላት አትችልም። 18፤ ነገር ግን አንተ፥

ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም፥ ባሪያዎችህና ገረዶችህም፥ በአገርህም ደጅ ያለው ሌዋዊ

አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ብሉት፤

እጅህንም በምትዘረጋበት ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።”

ዘዳ.12፦17-18 

ሁለተኛ እጅ የሚጨምርበት ምክንያት የእግዚአብሔር አሥራት ሥሙ በሚጠራበት ስፍራ

ተሸክሞ ላማምጣት ስላልቻላ ወይም እንዳይደክምና እንዳይሞት ብሎ የሸጠና በገንዘብ የለወጠ ሁሉ 2ኛ እጅ

ይጨምር ዘንደ የእግዚአብሔር ሕግ ያዛል። 10 ከሆነ አሥራቱ ሰለሸጠው 12 ይሆናል ማለት ነው። ይህ አሥራትን

መቤዥት ይባላል። ሲበዥ ግን አምስተኛ እጅ ይጨምራል ይህም 15 ይሆናል ማለት ነው። “ሰውም አሥራቱን

ሊቤዥ ቢወድድ፥ አምስተኛ ይጨምርበታል።” ዘሌዋ.27፥30-34 

Page 76: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 76/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

76ww.tlcfan.org

 

ይህ ሁሉ የሚያሳየው አሥራት የእግዚአብሔር ሥም ከሚጠራበት ስፍራ ውጭ ፈጽሞ

መምጣት እንደሌለበት ነው። እግዚአብሔር በሕጉ በኩል የማያመቻምች ነው። ይህን የማያደርግ እንደ ሕጉ

መሰረት የእግዚአብሔር ሕግ ተላልፏልና ልክ እንደ ሕዝበ እስራኤል ቅጣቱን እና ፍርዱን ይቀበላል። ስለዚህ ሁሉ

አማኝ አሥራቱን የት እንደሚያመጣ ከገባው ለምን እንደሚያመጣው ቀጥሎ ሊረዳ ይገባዋል። 

2. 

አሥራታችንን ለምን እና ለማን እናውጣው? 

“የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው።”

ዘሌ.27፥30 

ሀ) “22. ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ። 23፤ ሁልጊዜ

አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ

በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን የወይን ጠጅህንም የዘይትህንም አሥራት

የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ። 24፤ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥ መንገዱ ሩቅ

ቢሆን፥ አምላክህም እግዚአብሔር ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅብህ፥ ይህን

ወደዚያ ለመሸከም ባትችል፥ ትሸጠዋለህ፥ 25፤ የዋጋውንም ገንዘብ በእጅህ ይዘህ አምላክህእግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳለህ። 26፤ በዚያም በገንዘቡ ሰውነትህ የፈለገውን፥

በሬ ወይም በግ ወይም የወይን ጠጅ ወይም ብርቱ መጠጥ ሰውነትህም የሚሻውን ሁሉ

ትገዛለህ፤ በዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፥ አንተና ቤተ ሰብህም ደስ

ይላችኋል።” 

ለ)  “27. ድርሻና ርስት ከአንተ ጋር ስለሌለው በአገርህ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊ ቸል አትበል” 

ሐ)  “በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን አሥራት ሁሉ አምጥተህ በአገርህ

ደጅ ውስጥ ታኖረዋለህ፤ 29፤ ሌዋዊውም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በአገርህም

ደጅ ያለ መጻተኛ ድሀ አደግም መበለትም መጥተው ይበላሉ ይጠግባሉም፤ ይኸውም

አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው።”

በመጀመሪያ ደረጃ አሥራትን የምናመጣው የእግዚአብሔር ሰለ ሆነ ነው። በአሁን ዘመንም

ቢሆን ይህ ሕግ ፍጽሞ አልተቀየረም። ነገር ግን በፊት አባቶቻችን በተወሰነው ስፍራ ማለት የእግዚአብሔርበሚጠራበት ስፍራ በድንኳኑ በመቅደሱ በአመት ሦስት ጊዜ ያመጡለት ነበር። 

Page 77: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 77/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

77ww.tlcfan.org

 

አባቶቻችን ማምጣት ብቻ ሳይሆነ የመጣው ለምን እንደ መጣ ስለሚያውቁ በአሥራታቸው

እግዚአብሔር የሚያዘውን ሁሉ ያደጋሉ። አባቶቻችን አሥራታቸውን በእግዚአብሔር ፊት ይዘው ይመጣሉ

በፊቱ ይበሉታል። ከቤተስባቸውም ጋር ሆነው ደስም ይላቸዋል። ከላይ በጥቅሱ ደግመን ብንመለከተው

አሥራታችንን ለምን እንደ ምናመጣው መልስ ይሰጠናል። እርሱም፦ 

1.  ልንበላው ነው። 

2.  ሁለተኛ ለሌዋዊው ቸል እንዳንል ለሌዊው ሕጉን በማስተማረ ለሚተጋው ካህን እንድንሰጠው ነው። 

3.  በሦስተኛ ደረጃ ለመበለት፣ ለመጻተኛ፣ ለደሃ አደግና ለሌዊ መብል እንዲሆን ነው። 

ሀ) ልንበላው 

አሥራታችንን እግዚአብሔር ሥሙ እንዲጠራ በመረጠው ስፍራ ስናመጣው የመጀመርያ

ትእዛዙ በፊቴ ብሉት አንተና ቤተሰቦችህ ደስ ይበላችሁ አለን። በብሉይ ኪዳን ይህ ምንም ችግር አልነበረውም

ሁሉ ከከብትና ከእጽዋእት አሥራቱን ሰለሚያወጣ በእግዚአብሔር ፊት አርዶ ወይም ጋግሮ ይበላል።

በኦርቶዶክስ እምነት ይህ የተለመደ ነው። ባልሳሳት ዝክር ይባላል እርግጠኛ አይደለሁም። ነገር ግን በቤተ

ክርስቲያን ውስጥ ካህናትና ቀሳውስቱና ጳጳሳቱ እስከ አሁን ድረስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ይጠጣሉ ይበላሉ

በአምላካቸውም ፊት ደስ ይላቸዋል። ይህ አንዳን ምዕመናንንም ያጠቃልላል።

በአዲስ ኪዳን ሥሙ የሚጠራው እኛ ውስጥ ነው። እግዚአብሔርም ያለው እኛ ውስጥ ነው።

የምናመጣው አሥራት በሙሉ ገንዘብ ነው። መቼም ሰው ገንዘብን ጠቅልሎ አይጎርስም ነገር ግን እንዴት

እንብላው ብሎ መጠየቅ ግን ተገቢ ነው። በብሉይ ኪዳን የሚመገቡት ፍጥረታዊ ነው ምክንያቱም ሥሙ

የሚጠራበትም ስፍራ ፍጥረታዊ ነበርና ነው። አሁን ግን ሥሙ የሚጠረበት ሥፍራ መንፈሳዊም ፍጥረታዊም

ነው። ስለዚህ የምንበላው ነገር ፍጥረታዊ ብቻ ሊሆን አይችልም። 

ይህን ከመልከታችን በፊት ይህ ብሉት የሚለው የሕጉ ትዕዛዝ በአዲስ ኪዳን በዮሐንስ ወንጌል

ምዕራፍ 6 ላይ ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ መብላት ምን እንደ ሆነ በግልጽ ያስቀምጣል። መብላት ማለት

የእግዚአብሔር ቃል መስማት ማለት ነው። መጠጣት ማለት ደግሞ ማመን ነው። ይህን የዮሐንስን ወንጌል

ምዕራፍ ስድስትን በትክክል ካነበብን የምንረዳው ነው። ሕዝበ እስራኤል አሥራታቸውን የሚያወጡትና

የሚበሉት በዓመት ሦስት ጊዜ በሦስቱ በዓላት ቀኖች ላይ ነበር። 

Page 78: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 78/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

78ww.tlcfan.org

 

ሦስቱ የእግዚብሔር በዓሎች የራሳቸው የሆነ ሥም አላቸው (ሮሜ8፥30, ዘዳ16፥16) 

1. 

ፋሲካ (መቤዠት፣መጽደቅ) መጠራት ከግብፅ መውጣት በዓል። ዕብ11፥27-28,1ጴጥ1፥19-

21,ኤፌ2፥1-10, ዘዳ7፥6-8 

2.  በዓለ አምሣ (የመቀደስ) የሕግ መሰጠት በዓል የሚከበርበት ነው። ሕዝቡ 10 ብቻ ከእግዚብሔር

አፍ ሰማ የቀረውበቀለም ተጻፈለት። ዘዳ4፥1,8,9,11-13,20,36,5፥4-5፥22-23 ሕጉን ሚጠብቅ

ብቻ እግዚብሔርን ታዛዥ ይባላል። የሚወርስ እርሱ ነው። ከግብፅ ከወጡ ሕዝብ ሁሉ ከነዓን

ገብተው የወረሱ ሁለት ብቻ ናቸው። (ካሌብና ኢያሱ) 

3. የዳስ በዓል (መክበር) ከነዓን የመውረስ በዓል በአዲስ ድንኳን የመኖር አዲሱ የትንሣኤ አካልን

የመውረስ በዓል ነው። ይህ ከአሮጌው ድንኳን በመውጣት የሚከናወን ነው። ስለ እነዚህ በዓልት

ከሕይወታችን ጋር ያላቸውን መያያዝ በግልጽና በዝርዝር ማወቅ ከፈለሁ የእግዚአብሔር በዓላት

የሚለው መጽሐፌን ያንብቡ። 

በብሉይ ኪዳን ሥስት ዋና ዋና የእግዚአብሔር በዓሎች አሉ። እርሻ ፍሬያቸውን የሚሰጡት

በዓመት ሦስቴ ነው። ስለዚህም አባቶቻችን አሥራታቸውን የእግዚአብሔር ሥም በሚጠራበት ስፍራ ሊበሉ

የሚመጡት በዓመት 3 ጊዜ ብቻ ነው። ይህም አንደኛ ለፋሲካ በዓል ከግብዕ የወጡበትን ቀን ለማክበር ሲመጡ

ነው። ሁለተኛው ደግሞ ለበዓለ አምሣ (ጴንጤቆስጤ) በዓል ይህም እግዚአብሔር ሕጉን በሲና ተራራ የስጠበትን

ቀን ለማክበር ሲመጡ ነው። ሦስተኛው  ደግሞ  በዳስ በዓል ነው። ይህ ደግሞ ዮርዳኖስን ተሻግረው በዳስ

የኖሩበትን ቀን ለማሰብ ነው። 

እነዚህ በዓሎች አንድ አማኝ አወቀውም አላወቀውም ከሦስቱ አንዱን በማክበር ላይ አሁን

ይገኛል። በውጭ ያሉት ደግሞ አንዱንም በዓል ገና በግል አላከበሩም። ሰው የፋሲካን በዓል አከበረ የሚባለው

የፋሲካውን በግ በአምላኩና በምስክር ፊት ሥሙ በሚጠራበት ስፍራ የበላ እንደ ሆነ ነው።(ዘጸ.12) የፋሲካው

በግ ደም ከሞት መልአክ ያለምንም ጥያቄ በእምነት ብቻ በመቃኑ ላይ ሰላኖርነው ደሙ ከሃጢያትና ከሞት

አዳነን። ይህ የሚያሳየው ኢየሱን በመንፈስ ውስጥ የግል አዳኝ አድርጎ መቀበልን ዳግም መወለድን ነው። ነገር

ግን ከግብጽ ለመውጣት የፋሲካውን በግ በእሳት ጠብሶ ራሱን (እዕምሮ) ሆዱን (የልብ ፍቃዱ) እግሩን

(እርምጃና አካሔዱን) የፋሲካውን በግ ኢየሱስን ሊበላ ይገባዋል። ይህ ነበር የዮሐንስ 6 የኢየሱስ ትምህርት

ብዙዎች ግን ጭንቅ ጭንቅ አላቸው። 

Page 79: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 79/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

79ww.tlcfan.org

 

ይህ የፋሲካ በዓል በብሉይ የሚከናወነው የሚበላውም በግ የሚገዛው ሰውየው

ለእግዚአብሔር ከሚያወጣው አሥራት ነው። ዛሬ ደሙን ብቻ አምነው በጉን ሳይበሉ በበር ውስጥ ተዘግተውም

በግብፅ ያሉ ብዙዎች ናቸው። እነዚህ የግብፅ በኩር ሁሉ መሞቱን ያላዩ የግብፅን በረከት በዝብዘው ያልወጡ

ምስኪኖች ናቸው። ብዙሃኑ ገና ከዚህ ያለፈ ሕይወት ስለማይኖር የማተኩረው እዚሁ በዓል ላይ ነው። እንግዲህ

ሰው የእግዚአብሔር አሥራት ሲያመጣ አንደኛ ሊጠቀምበት የሚገባው የፋሲካውን በግ ለመብላት ነው።

እነዚህ ሦስቱን ከላይ የተመለከትናቸው በዓሎች የአማኙን ሰው ሁለንተና ሦስቱን የሰውነት

ክፍሉ ውስጥ የሚደረገውን በዓል ያመለክታል። በመንፈስ፣ ነፍስና ሥጋውን ነው። በዚህ ዘመን ሰው አሥራቱን

1/10 ለእግዚአብሔር ከለየ በኃላ በእግዚአብሔር ፊት ሊበላው ይገባል። ይህ የሚሆነው በተለያየ መንገድ ሊሆን

ይችላል። እግዚአብሔር አሥራትን ማወጣን ሳይሆን የሚያየው ሦስቱ በዓላት በሁለንተናችን በእግዚአብሔር

አሥራት ገንዘብ መፈጸሙን ነው። እግዚአብሔር ከአስር አንዱን እንድንለይ የፈለገልው ለራሳችን ለመንፈሳዊ

እድገታችን ብቻ እንድንተቀመው እንድንበላውና እንድንጠጣው ነው። 

የክርስቶስን አዕምሮ፣ እርምጃና ፍቃድ የሚያሳይን ትምህርት ካሴት በመግዛት። ቅዱስ

መንፈስን ሊሰጡ የሚችሉ መጻፍትን በመግዛት ነው። እውነተኛ ልጆሮ የሚመችን ሳይሆን የሚያስተምረን

በመቅጠር ወይም በዘመኑ አጠራር ያሰተማሩንን እንድንባርክበት ነው። አሥራት ከመብል ጋር የተያያዘ ሰለ

ሆነ አሥራትን የምንጠቀምበት አንደኛው መንገድ መንፈሳዊ ነገሮችንን ገዝተንም ሆነ ከፍለን በመመገብ ነው።

ይህ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው። 

ይህ ስንል ደግሞ ቃሉን የምንመገብባትን ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ሰዎች አሥራታችንን

ከመስጠት ቸል እንዳንል የእግዚአብሔር ቃል ያዛል። በአጠቃላይ ሦስቱ በዓላቶች በሕይወታችን ውስጥ

ለማክበር አሥራቱ ለዚህ ሥራ የሚውል ነው። ስለዚህ አሥራት የሚወጣ ሌላው አላማ ለመንፈሳዊ እድገት

በዓላቱን በሕይወታችን ለመፈጸም ነው። በዓሉን የመጠበቅና የማድረግ ሕግ ዛሬም ለእኛ አልተሻረም። ነገር

ግን የበለጠ ክብርን አግኝቷል። ይህም እጅ በስራው መቅደስ ውስጥ መሆኑ ቀርቶ በሰው ልጆች ውስጥ በመሆኑ

ነው። 

ሰው ግን የእውነተኛ ቤተ ክርስቲያን አባል ከሆነ ስለምትመግበውና ስለምትንከባከበው

አሥራትን ለእርሷ ይሰጥ ዘድ እግዚአብሔር ይጠብቅበታል። ነገር ግን የሚገባውን መብል የማትሰጠው ከሆነ

ለዚያች ቤተ ክርስቲያን አሥራቱን እንዲሰጥ እግዚአብሔር ፈጽሞ አያዝም።

Page 80: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 80/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

80ww.tlcfan.org

 

አማኝ ሰው አሥራቱን በአምላኩ ፊት የሚመግበው ወይም የሚበላው እግዚአብሔር አምላኩን

በይበልጥ በማወቅ ለእግዚአብሔር እንዲገዛና በሥጋው አምላኩን እግዚአብሔር እንዲያከብር ነው። ይህን ስል

ደግሞ ለሥጋችሁ ምክንያት አድርጋችሁ እንዳትጠቀሙ እስጋላችኃለሁ ከፍርዱን ግን ማንም አያመልጥም።

በእምነት በማስተዋልና አፍርሃት ማድረግ ግን በረከት የሰማይን መስኮት የሚያስከፍት ነው። 

“22፤ ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ። 23፤ ሁልጊዜ

አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ

በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን የወይን ጠጅህንም የዘይትህንም አሥራት የላምህንና

የበግህንም በኵራት ብላ። 24፤ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥

አምላክህም እግዚአብሔር ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅብህ፥ ይህን ወደዚያ

ለመሸከም ባትችል፥ ትሸጠዋለህ፥ 25፤ የዋጋውንም ገንዘብ በእጅህ ይዘህ አምላክህ እግዚአብሔር

ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳለህ። 26፤ በዚያም በገንዘቡ ሰውነትህ የፈለገውን፥ በሬ ወይም በግ

ወይም የወይን ጠጅ ወይም ብርቱ መጠጥ ሰውነትህም የሚሻውን ሁሉ ትገዛለህ፤ በዚያም

በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፥ አንተና ቤተ ሰብህም ደስ ይላችኋል።” 

ነገር ግን ልንናውቀው የሚገባ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር አሥራትን እንድንጠቀም ያዘዘው መንገድ

ይህ ብቻ አለ መሆኑ ነው። ብዙዎቻችን አሥራትን የምናወጣው ሁሉንም በአንዴ ለቤተ ክርስቲያን ነው። ይህ

ግን ትክክል አይደለም። የመጀመሪያውና ዋናው አሥራትን የእግዚአብሔር ሥም በሚጠራበት ቤቱ ፊት

ማምጣታችን ልንመገበው ነው። ይህም ጥቅሙ ለቤቱ ለእውነተኛው ማደሪያውና መቅደሱ እድገትና ጥንካሬ

ነው። እኛ ቤቱ ነንና እግዚአብሔር ከእኛ የወሰደውን አሥራት ቤቱን ለመገንባት የሚጠቀመው በመጀመሪያ

ደረጃ ነው። ይህን ያላስተዋለች ቤተ ክርስቲያን ግን የሰዎችን አሥራት ወስዳ እውነተኛውን መቅደስ መገንባት

ትታ ፍጥረታዊ መቅደስ ለመገንባት ሕይወት የሚያሳጣ ጎተራን ፍጥረታዊ መቅደስን ኢየሱስ በምሳሌው

እንደመሰለ ሰው ትገነባለች።

የእግዚአብሔር ትኩረት 1/10 ከሕዝቡ መቀበል ሕዝቡ የእግዚአብሔር በዓላትን እንዲያደርጉ

ሰለሚፈልግ በዓላቱን ደግሞ በራሱ በእግዚአብሔር ድርሻ እንዲደረግለት ሰለወደደ ነው። ይህን የሚያደርግ ሰው

ብል በማይበላው ስፍራ የማያከማች ሰው ነው። ፍጥረታዊ ሕንጻ ለመገንባት የሥጋውን ልፋት ገንዘብ የሚበትን

ምስኪን የእግዚአብሔርን ጎተራ ያላወቀ ምንም ትርፍ የማያገኝ እግዚአብሔርን የማያስደስት ሰው ነው። 

Page 81: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 81/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

81ww.tlcfan.org

 

በመመገባችን ለእግዚአብሔር የምንመች እርሱ በእምነት የምናስደስት የበሰልን ልጆች እንሆናለን።

ፍጥረታው ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ እድገታችንንም እንድንጠብቅ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚወድ

ከአሥራት ሕግ እናያለን።  የምናመልከው አምላክ እንዴት እንደሚወደንና ከእኛ ይበልጥ ለእኛ አንዴት

እንደሚያስብ ስናይ ወደንና ፈቅደን አሥራትን እንድንሰጠው ያደርገናል። ፍቅሩ እንዴት ጥልቅ ነው። አሰራሩም

ድንቅ ነው። ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር በዓላት እንዲያከብር ከግብፅ ይወጣል። ከግብፅ የመውጣት ሚስጥርና

አላማ ይህ ነው። 

ከግብፅ ያልወጣ ግን በሲና የሕጉን ጥቅም ፈጽሞ ማየት አይችልም። ካልተቀበለ ደግሞ ለአስራት

ሕግ ሚስጥር መገለጥ ያልታደለ ነው። ከግብፅ ለመውጣት ምንም ቁልፍ የለም ብቸኛው መንገድ የፉሲካውበግ ኢየሱስን መብላት ወይም መስማት ነው። የእግዚአብሔር አስራት በትክክለኛ ባልሆነ መልኩ የሚጠቀሙ

ሰዎች ሆኑ መሪዎች መጨረሻቸ በኢየሱስ ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው ሰው አይነት ነው። ጎተራውንና ወደ ጎተራው

እንዴት እንደምናስገባ እንወቅ። 

ለ) ለሌዋዊ ልንሰጠው 

ሌዋዊ ስንል ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ አገልጋይን ሁሉ ማለታችን ነው። እግዚአብሔር

በእስራኤል ሁሉ በኩር ፋንታ ሌዋዊያንን ውስዷል። የሌዊ እድል ፍንታ እግዚአብሔር እራሱ ነው። ሰለዚህን

ከሕዝቡ ጋር ምንም ነገር አልተካፈለም። ሌዋዊ ካህን ማለት በእግዚአብሔር በሰው መካከል ሰዎችን ወደ

እግዚአብሔር ለማቅረብ የሚቆም ባሪያ ነው።

ሌዋዊያን ሁሉ የተቀቡ ወይም ካህናት አይደሉም። ካህናት የነበሩት አሮንና ልጆቹ ብቻ ናቸው።

ነገር ግን ሌሎቹ ሌዋዊያን የተቀቡትን ካህናት በመርዳት ያገለግላሉ። ለካህናትና የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው።

የነቆሬን ታሪክ ሁላችን እናውቃለን ሳይቀቡ እንደ ተቀባ ሰው በተቀባው ፊት ሲፎካከሩ መሬት ተስንጣቃ

ዋጠቻቸው። ሌዋውያን ናቸው ነገር ግን ሁሉ ሌዋውያን የተቀቡ አይደሉም። በአሁንም ዘመን ይህ ነው

እግዚአብሔር የሚመርጣቸው የተለያዮ ሰዎች ለልዮ አገልግሎት የአገልግሎት ቅባትን የተቀቡና የተቀበሉ ሰዎች

አሉ። አማኝ ነኝና የመልከ ጸዲቅ ክህንት እኔም በኢየሱስ ተቀብያለሁና ከማን አንሳለሁ ማለት ተገቢ አይደለም። 

እግዚአብሔር የሰጠንን ሰው ማክበርና በአሥራት መባረክ እራሳችንንም ወደ መከበር ያመጣናል።

በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የበታችን የበላይ የሆነ ስልጣን የስጦታ ጥሪ አለ። በመወደድና በኢየሱስ በመጠራት

በእርሱ የሆነውን ቅባት በመቀባት ግን ሁላችን አማኞች እኩል ነን።

Page 82: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 82/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

82ww.tlcfan.org

 

ይህ ማስጣንቀቂያ በአዲስ ኪዳንም ለአማኞች በግልጽ በይሁዳ መልክት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

አሥራትን ማስወጣት የሚችለው በብሉይ ብዙ ሌዋውያን ቢኖሩም የተቀባው ሌዊ ካህን ብቻ ነበር። ያልተቀባ

አሥራትን ሊያስወጣ ፈጽሞ አይችልም ነበር። 

“1፤ እግዚአብሔርም አሮንን አለው። አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ቤት የመቅደስን

ኃጢአት ትሸከማላችሁ፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ የክህነታችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ። 2፤

ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ከአንተ ጋር አቅርብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት

ይሁኑ፥ ያገልግሉህም፤ አንተ ግን ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ። 3፤

እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሁሉ አገግሎት ይጠብቁ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም

ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ። 4፤ ነገር

ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ይጠብቁ፤

ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ። 5፤ እንደ ገና በእስራኤል ልጆች ላይ ቍጣ እንዳይሆንባቸው

እናንተ መቅደሱንና መሠዊያውን ጠብቁ። 6፤ እኔም፥ እነሆ፥ ሌዋውያንን ወንድሞቻችሁን

ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያደርጉ ዘንድ

ለእግዚአብሔር የተሰጡ ለእናንተ ስጦታ ናቸው። 7፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ

ለመሠዊያው ሥራ የሚሆነውን ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን ታደርጉ ዘንድ

ክህነታችሁን ጠብቁ፥ አገልግሉም፤ ክህነቱን ለስጦታ አገልግሎት ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው

ቢቀርብ ይገደል። 8፤ እግዚአብሔርም አሮንን ተናገረው እንዲህም አለው። እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች

ለእኔ የቀደሱትን የማንሣት ቍርባኔን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ ስለ መቀባትህ ለአንተና ለልጆችህ

ድርሻ እንዲሆን…. ….ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ። 9፤ በእሳት ከሚቀርበው ከተቀደሰው ይህ ለአንተ

ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ የእህሉ ቍርባናቸው ሁሉ፥ የኃጢአታቸውም

መስዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ለአንተ ለልጆችህም የተቀደሰ ይሆናል። 10፤

በተቀደሰ ስፍራ ብላው፤ ወንዶች ሁሉ ይብሉት፤ የተቀደሰ ይሆንልሃል። 11፤ ይህም ለአንተ ነው፤

የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የማንሣትና የመወዝወዝ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር

ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ

ሁሉ ይብላው። 12፤ ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከእህልም

የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። 13፤ ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡት በምድራቸው

ያለው ሁሉ የፍሬ መጀመሪያ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። 14፤

Page 83: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 83/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

83ww.tlcfan.org

 

በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። 15፤ ከሰው ወይም ከእንስሳ ቢሆን፥

ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ ማኅፀን የሚከፍት ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን

በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትቤዠዋለህ። 16፤ ከአንድ ወር ጀምሮ

የምትቤዠውን እንደ ግምትህ ትቤዠዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል

ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው። 17፤ ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም

የፍየል በኵራት አትቤዥም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፥

ስባቸውንም ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለእሳት ቍርባን ታቃጥለዋለህ። 18፤

ሥጋቸውም ለአንተ ይሆናል፤ እንደ መወዝወዝ ፍርምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአንተ ይሆናል። 19፤

የእስራኤል ልጆች ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም

ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት

ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ የጨው ቃል ኪዳን ለዘላለም ነው። 20፤ እግዚአብሔርም አሮንን

አለው። በምድራቸው ርስት በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል

ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ። 21፤ ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት

ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ። 22፤ ከዚህም በኋላ

ኃጢአትን እንዳይሸከሙ እንዳይሞቱም፥ የእስራኤል ልጆች ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረቡ።

23፤ ሌዋውያን ግን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ይሥሩ፥ እነርሱም ኃጢአታቸውን

ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት

አይወርሱም። 24፤ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን የሚያቀርቡትን የእስራኤልን ልጆች አሥራት

ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህ። በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም

አልኋቸው። 25፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። 26፤ ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ

ንገራቸው። ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥

ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ። 27፤ የማንሣት

ቍርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል። 28፤

እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት አሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት

ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ የእግዚአብሔርንም የማንሣት ቍርባን ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ። 29፤

ከምትቀበሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከተቀደሰውም ድርሻ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን የማንሣት

ቍርባን ሁሉ ታቀርባላችሁ። 30፤ ስለዚህ ትላቸዋለህ። ከእርሱ የተመረጠውን ባነሣችሁ ጊዜ እንደ

Page 84: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 84/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

84ww.tlcfan.org

 

አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ለሌዋውያን ይቈጠራል። 31፤ እናንተም ቤተ

ሰቦቻችሁም፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የማገልገላችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበሉታላችሁ።

32፤ የተመረጠውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም

የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታረክሱም፣” ዘሁ.18 

እግዚአብሔር ለሌዋውያን የእስራኤልን በኩራት መባና አሥራት እንዲ በሉ ፈቅዶላቸዋል።

ሌዋውያን ካህናት አሥራቱን ለመብላት ያበቃችው ከሕዝቡ ጋር ምንም ርስት ስላልተካፍሉ፣ ሕዝቡን

የእግዚአብሔርን ሕግ ስለሚያስተምሩ፣ ሌላው ደግሞ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅና ወደ

እግዚአብሔር ለማቅረብ በመካከል ስለሚቆሙ ነው። ለእኛም ይህን የማማለድ ስራ አኑሯል። ሌላው ደግሞ

አብዛኛዎቹ አገልጋዬች ለራሳቸው የሚበሉት ወይም አገልግሎታቸውን የሚያሰፉበት ምንም ገንዘብ ስለሌላቸው

ሥራም ስለማይሰሩ ነው። በአዲስ ኪዳን ዘመንም ይህ ሕግ አይለወጥም። አሥራትን እንደ ደሞዝ ሊበሉት

የተገባቸው የተቀቡና በተቀቡት ቤት ያሉ ንጹሃን አገልጋዬች ናቸው።

ባለንበት ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ማለት ቅዱሳንን የሚያገለግሉ በጌታ የተለዩ አገልጋዬች

አሉ። እነዚህ በአንዳዶች አጠራል የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ተብለው ያታወቃሉ። እንደ እግዚአብሔር ቃል ግን አምስቱ

ቢሮዎች ናቸው። ሐዋርያት፣ አስተማሪዎች፣ እረኞች፣ ወንጌል ሰባኪዎች፣ ነብያቶች ናቸው። ሌዋውያን

የእግዚአብሔርን ሕግ በዝማሬ የሚዘምሩትንም መዘምራን የሚጠቀልል ነው። ልብ ልንል የሚገባው ግን

የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ነኝ ባዬች ሁሉ የተቀቡ አለመሆናቸውን። ነገር ግን ያልተቀቡ ሰዎች እግዚአብሔር ማገልገል

ይችላሉ። ነገር ግን ወደ ጠለቀው ነገር ወደ ውስጥ የሚገቡ የተቀቡ ብቻ ናቸው። አሥራትም የሚገባቸው

የተቀቡት ብቻ ናቸው። 

አሥራታችንን ልንሰጣቸው የሚገባው ለተቀቡት ሰዎች ብቻ ነው። ይህንን በመፈሳችን ምስክር

የሚሰጠን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ደግሞም በፍሬያቸው ልናውቃቸው ይገባል። ሌላው ደግሞ እኛንና

እግዚአብሔር የሚያገለግሉ ከሆነ ሰዎችን ወደ ሙላት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ ሲሆን ነው። ነገር ግን

የራሳቸውን ሃሳብና የራሳቸውን ራእይ ለሚያገለግሉት አሥራታችንን ልናቀምሳቸውም አይገባም። እንደዚህ

አይነት የተቀቡ ሰዎች ሰዎች የሌሉበት ስፍራ ካለን አሥራታችንን በጠቅላላ እንበላዋለን ማለትም ለመንፈሳዊ

እድገታችን እገዛ ብቻ እናውለዋለን። ይህም የመጀመሪያውን የአሥራት ሕግ ማውጣትን መርህ በመጠቀም

ነው። አለበለዚያም አሥራታችንን በማስቀመጥ ለድሆች በመመጽወት ነው። 

Page 85: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 85/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

85ww.tlcfan.org

 

ሌዋውያ ካህናት አስራትን ከተቀበሉ በኃላ አስራቱን በመመገብ ሕዝቡንና እግዚአብሔርን

ያገለግላሉ። በአዲስ ኪዳን አንዳንድ ሰዎች ለራሳቸው የሚመች አስተማሪ ያዘጋጃሉ ይላል። ሰው ለራሱ

ከእግዚአብሔር የሆነ አስተማሪ ቢያዘጋጅ ወይም ቢቀጥር ችግር የለውም ነገር ግን ለራሱ ጆሮ የሚመቸውን

አስተማሪ እንዲያዘጋጅ የእግዚአብሔር ፍቃድ አይደለም። 

ሐ) ለመጻተኛ፣ ለደሃ አደግ፣ ለሌዊ፣ ለመበለትና ወላጅ ለሌላቸው 

እግዚአብሔር የሦስተኛ ዓመት አሥራታችንን ሰስብስበን በበራችን ደጃፍ እንድናኖረው

ይፈልጋል። ይህም ደሃ አደጉ፣ መበለትዋና ምንም የሌለው ሌዋዊ መጥተው እንዲመገቡ ነው። ይህ የሦስተኛው

ዓመት አሥራት በአሥራት አውጪው ፈጽሞ አይበላም። ነገር ግን ሌሎች በዓልን ማድረግ እንዲችሉ ሙሉ

በሙሉ ለሰዎች ለደሃዎች ይሰጣል። ነገር ግን ይህ አሥራት አስጣጡ ሰዎቹ ያሉበት ድረስ በመሄድ ሳይሆን ሰዎቹ

ራሳቸው ይህን አሥራት ለመውስድ ወደ ደጃፋችን ወደ እኛ ቤት መምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ሌዋውያኑንም

ይጨምራል። ስለዚህ በሌላ አባባል እግዚአብሔር በፊታችን ይልካቸዋል ወይም በልባችን ላይ ያስቀምጣቸዋል

ማለት ነው። 

“በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን አሥራት ሁሉ አምጥተህ በአገርህ ደጅ

ውስጥ ታኖረዋለህ፤ 29፤ ሌዋዊውም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በአገርህም ደጅ

ያለ መጻተኛ ድሀ አደግም መበለትም መጥተው ይበላሉ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ

እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው።” 

ይህ ብቻ ሳይሆን ለደሃደጉና ለመበለቲቱ ወላጅ ለሌላቸው እግዚአብሔር ሌላ ተጨማሪ ሕግን

ሰጥቶናል ይህም የቃርሚያ ህግ በመባል ይታወቃል። ይህ በሦስተኛው አመት ከምንሰጣቸ አሥራታችን

በተጨማሪ ለድሆች እንደሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘን ነው። ስለዚህ አሥራት በሦስት አይነት መልኩ ይወጣል

ማለት ነው። አንደኛ አውጪው በእግዚአብሔር ፊት ይበላዋል፣ ሁለተኛ ለሌዋዊያን ይሰጣቸዋል፣ ሦስተኛ ለድሃ

አደጉና ለመበለቶች ደግሞም ለሌዋዊያን በዓላቱን እኩል ከአሥራት አውጪው ጋር ማድረግ እንዲችሉ

ይሰጣቸዋል። ስለዚህ አሥራታችንን የምናወጣው ለእነዚህ ለሦስቱ ሥራዎች ነው። 

Page 86: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 86/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

86ww.tlcfan.org

 

3. 

አሥራት መቼ ይከፈል? 

አንድ ሰው አሥራትን የሚከፍልበት ወቅት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተጽፎ ይገኛል። አንድ

ሰው ገና ጌታን እንደ ተቀበለ አሥራትን እንደማይከፍል የእግዚአብሔር ቃል በተለያዩ ሕጎቹ እግዚአብሔር

ያሳያል። ይህ ግን በይበልጥ ለመረዳት አንድ ነገር ቀድመን እንድናይ እወዳለሁ። ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ

በእንጨት በዛፍ ተመስሎ ይገኛል። እግዚአብሔር ሰለ ዛፍ ሲናገር ሰለ ሰው መናገሩ ነው። ነገር ግን ይህን ሁል

ጊዜ አይደለም። ይህ ማለታችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው ዛፍ ሁሉ የሰው ምሳሌ አይደለምና ነው ወይም

በሰው ብቻ የተመሰለ አይደለም። በሌላም ነገሮች ተመስሎ እንደ ማንነቱም ዛፍ ሆኖ ተቀምጦም ይገኛል።

ለምሳሌ ዳዊት በመዝሙሩ መጀመሪያ ምዕራፍ አንድ ላይ እንዲህ ይላል፦

“1 ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ 

በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።2 ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ 

ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።3 እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ 

ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ 

የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።” መዝ.1፥1-3

“ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።” መዝ.37፦35

“12 ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል። 

3 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ። 

14 ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ። 

15 አምላኬ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይነግራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም።”

መዝ.92፥12-15

23፤ ወደ አገሩም በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ፥ 

ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት እንዳልተገረዘ ይሆንላችኋል፤ 

አይበላም። 24፤ የአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ቅዱስ ይሁን። 

25፤ ፍሬውም ይበዛላችሁ ዘንድ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ፤ 

እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።” ዘሌ.19፥23-25

Page 87: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 87/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

87ww.tlcfan.org

 

ከላይ ያየነው የእግዚአብሔር ሕግ እንደሚናገረው በእግዚአብሔር አደባባይ የተተከል አዲስ ዛፍ 

አማኝ ለሦስት አመት ከእርሱ ምንም እንደማይበላ ያሰተምራል። ይህን ለአሥራት መቼ እንክፈል ለምንለው 

ጥያቄ በቂ ምላሽ ነው። ሰው ካመነ በኃላ በገዛ ፍቃዱ አሥራትን ማረግ ይችላል። ነገር ግን አሥራቱን ከአመነት 

ቀን አድንስቶ እስከ ሦስተኛው አመት እርሱ ብቻ ይበላዋል። 

አንድ ሰው ጌታን ከተቀበለ በኃላ ለሦስት አመት አሥራትን የመክፈል ግዴታ ግን የለበትም። 

ነገር ግን ዛፉ በላዩ ያለን በዛፉ ስር እያራገፈ ተመልሶ እንደሚመገበው ለሦስት አመት አዲስ አማኝ አሥራቱን 

ያወጣል ነገር ግን እርሱ ብቻ በላይ ባየነው አሥራትን በመብላት ሕግ ይመገበዋል።  ማለትም የራሱን መንፈሳዊ 

እድገት  ደረጃ  በሚገባ  ያሳድግበታል።  የዚህ  ሰው  አሥራት  ወደ  እግዚአብሔር አገልጋዬችም  ሆነ  ለምን  ሥራ 

እንዲውል እግዚአብሔር አይፈቅድም። እግዚአብሔር እንዳልተገረዘ ትቆጥሩታላችሁ ይላል። ይህም እንዳልበሰለ 

ከባሪያ እንደማይለይ ሕፃን እደማለት ነው። 

በአራተኛው አመት ፍሬው ወይም አሥራቱ በሙሉ አምጥቶ ግን እግዚአብሔርን ያመስግንበት 

ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ፊት ያመጣዋል። ይህ ሰው ከቅዱሳን ጋር ሕብርት የሚያደርግ አማኝ ከሆነ በሁሉ ፊት 

አምጥቶ እግዚአብሔር ያመስግንበታል። የተቀባውም አገልጋዬም የምስጋናን ጊዜ ያዘጋጅበታል እንጂ ከእርሱ 

ምንም አይበላም የእግዚአብሔር ነውና ነው። እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ነገር ይዘጋጅበታል። እንደዚህ ዘመን 

ኮንፍረንስ  ፣የአምልኮ  ኮንሰት፣  የትምህርትና  አምልኮ  ጊዜ  የሚዘጋጀም  ሦስት  አመት  በሞላቸው  አማኞች 

ከሚመጣው አሥራት ነው። 

በአምስተኛው አመት ልክ እንደማንኛውም አይነት ሰው አሥራቱን ከላይ ለተማርናቸ ለሦስቱ 

ነገሮች ማዋል ይጀምራል። ይህ ከላይ ያየነው ሕግ የሰውየውን አሥራት ብቻ የሚመለከት ሳይሆነ በሕይወቱ 

የሚወልዳቸውን መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ለሦስት አመት ተቀባይነት በጉባኤ መካከል ፈጽሞ አይኖረውም። 

ወይም አንድ የዳነ አማኝ ለሦስት አመት ምንም ማስተማር አይገባውም። እንደ ዛፍ ሊበላ አይገባውም። 

በዳነ  በሦስት  አመቶቹ  ውስጥ  በምንም  አይነት  አገልገሎት  ውስጥ  ተጠምዶ  ማገልገል 

የለበትም። እግዚአብሔር እንዳልተገረዘ ቁጠሩት ነው ያለው። ያልተገረዘ አይደለም ነገር ግን እንደ አልተግረዘ 

ይቆጠራል። በዚህ በሦስት አመት ውስጥ ራሱን በመንፈሳዊ ነገር እንዲያሳድግ የሚያስፈልገው ማንኛውም 

አይነት እንክብካቤ ይደረግለታል። ለዚህ ነው በሰይጣን እንዳይፈተን አዲስ አማኝ አትሹም የሚለው። 

Page 88: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 88/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

88ww.tlcfan.org

 

ለዚህ ትክክለኛ ምሳሌያችን ጳውሎስ ነው። ጳውሎስ በጌታ ካመነ በኃላ ለሦስት አመት ሙሉ 

በዓረባ ምድር ከጌታ ሲማር ቆየ በአራተኛው አመት በእግዚአብሔር ፊት ማለት በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር 

ምስጋናን  አቀረበ።  ከዚያ  በመንፈስ  ለእግዚአብሔር  ሥራ  ተለይቶ  በአምስተኛው  አመት  የከበረ  በሰውም 

በእግዚአብሔር ዘንድም ተቀባይነት ያለውን አገልግሎት እያገለገለ አለም ዞረ። 

“1 ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል 

የታመነ ነው።2 እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ 

የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ 

ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥3 የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር 

የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥4 ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ 

የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤5 ሰው ግን የራሱን ቤት  እንዲያስተዳድር 

ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? 6 በትዕቢት 

ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።”

1ጢሞ.3፥1-6

“15-16 ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር 

በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ 

በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥17 ከእኔም በፊት 

ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር 

ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።18 ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ 

ኬፋን ልጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ፤ 

19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።20

ስለምፅፍላችሁም ነገር፥ እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት አልናገርም፣”

ገላ.1፥15-20

Page 89: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 89/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

89ww.tlcfan.org

 

የቃርሚያ ሕግ 

“18፤ አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ 

አስብ፤ ስለዚህ ይህን ነገር ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።19፤ የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ 

ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር 

በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ አደግ ለመበለትም ተወው።20፤ 

የወይራህን ፍሬ ባረገፍህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ ማርገፉን ለማጣራት አትመለስ፤ 

ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን።21፤ የወይንህን ፍሬ በቈረጥህ ጊዜ 

ቃርሚያውን አትልቀመው፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን።22፤ አንተም 

በግብፅ አገር ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።”

ዘዳ24፥19-22

“የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ 

የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። 10፤ የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ 

የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ 

እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።” ዘሌ19፥9-10

ለዚህ ምሳሌያችን ሩት ነች። ሩት በቦዔዝ እርሻ እድትቃርትም ቦዔዝ ፈቀደላት እርሷም መበልት

ነበረችና ነው። ልናውቀው የሚገባ ግን ይህ የምንሰጣቸው ነገር ራሳቸው ሰርተው ወይም ቃርመው መውሰድ

አለባቸው። እኛ በር ከፋቾች ብቻ ነን። ለምሳሌ አማኝ ሆነን የራሳችን የግል እንቅስቃሴ ያለን ከማንኛው ሰው

ከመጠበቅ በፊት ለእንደነዚ አይነት ሰዎች ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል። 

አንድ ሰው የቃል ሙላት ይኖረው ይሆናል። ሌሎች ደግሞ ይህን ቃል ይራቡ ይሆናል። መብላት

ፈልገው ወደ እርሱ ቢመጡ ደሃም መበለትም ናቸው ብሎ ላለማገልገል መሸሽ አይገባውም። ሰርተን

ወደምናገኘው ደሞዝ ልምጣና  ለሰው ስራን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። የእጆችንም ሥራ የሚባርክ

እግዚአብሔር ነው። ባለቆች ፊት ሞገስን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። ሰለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዛል

የሥራህን ውጤት በሰበስብክ ወቅት እስከ ጥጉ እስከ ድንበሩ ድረስ ለራስህ ብቻ አትጨድ ያላል። በሌላ አባባል

ደሞዝህን ሁሉ ምንም እንኳ አሥራትህን ብታወጣ ሙሉ ለሙሉ ለራስህ አትጠቀምም ማለቱ ነው። ለደሃ

አደጉና ለመበለቲቱ ለመጸአተኛው ትኝሽ ተውለት፣ በቻልከው መጠን ያልህን አካፍል፣ እጅህን በወንድምህ ላይ

አትጨብጥ ብሎ እግዚአብሔር ያስተምረናል።

Page 90: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 90/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

90ww.tlcfan.org

 

“7፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ 

አንዱ ቢደኸይ፥ ልብህን አታጽና፥ በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ። 

8፤ ነገር ግን እጅህን ለእርሱ ክፈት፥ የለመነህንም አስፈላጊውን ነገር አበድረው። 

9፤ ሰባተኛው ዓመት የዕዳ ምሕረት ዓመት ቀርቦአል ብለህ ክፉ አሳብ በልብህ 

እንዳታስብ፥ ለድሀውም ወንድምህ አንዳች የማትሰጥ እንዳትሆን፥ ዓይንህም በእርሱ 

ላይ ክፉ እንዳይሆን፥ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ እንዳይጮህ፥ ኃጢአትም 

እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ።10፤ እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር 

ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፥ በሰጠኸውም ጊዜ በልብህ አትጸጸት። 

11፤ ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ። በአገርህ ውስጥ ላለው 

ድሀ ለተቸገረውም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ፣”

ዘዳ.15፥7-11

ስለ ሩት ቃርሚያ ሕይወት ማወቅ ከፈለጉ መጽሐፈ ሩት ትርጉማ ፍቺው የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡ። 

Page 91: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 91/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

91ww.tlcfan.org

 

የበኩራት ሕግ 

በኩራት  ማለት  ከእርሻ  የመጀመሪያው  ከማጭድ  ስር  የሚያልፈው  ሲሆኝ፣  ከእንስሳ  ደግሞ 

መጀመሪያ የሚወለደው ነው። አሥራት እና በኩራት ፈጽሞ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ሰው አንድ እርሻ ቢገዛ 

የመጀመሪያው የሚበቅለው ለምድሯ በኩር ነው። ምክንያቱም እርሻዋ ከዚህ በፊት ሌላ አብቅላ አታውቅምና 

ነው። ነገር ግን የቆየ እርሻ ከሆነ ደግሞ በኩራቱ ልክ የተዘራው ሲበቅል ከተዘሩት እርሻ ዘር የተሻለው ወይም

በመጀምሪያ በማጭድ ውስጥ የገባው ነዶ ማለት ነው። ይህ ግን ሁሉ እርሻ ማለት አይደለም። በማጭድ አጫጁ 

ሲያጭድ በመጀመሪያ በእፍኙ የገባው ማለት ነው። ከእርሻው አንድ የመጀመሪያው ነዶ ነው። 

ለሰውና  ለእንስሳ  ደግሞ  ማሕጸን  የሚከፍት  ማለት  ነው።  ያልወለደች  ሴት  ሆነ  ያልወለደች 

እንስሳ  ለመጀመሪያ  ጊዜ  ስትወልድ  የመጀመሪያ  ልጃቸው  በኩር  በመባል  ይታወቃል።  በኩር  ለሰውም  ሆነ 

ለእንስሳ አንድ ነው። ነገር ግን በኩር ለምድር አንድ አይደልም። አንድ እርሻ ስንዴ አብቅሎ የስንዴውን በኩር 

ከሰጠ በሌላ ጊዜ ደግሞ ገብስ ቢያበቅል የገብሱን በኩራት ወደ እግዚአብሔር ሊያመጣ ይገባዋል። 

ኢየሱስ ለማርያም የመጀመሪያ ልጅ ስለሆነ በመወለድም ጭምር ኢየሱስ በኩር ነው። ለዚህም

ነው ለእግዚአብሔር መስዋዕት ሆኖ ለመቅረብ በቂ የሆነው። አማኝ ሰው እግዚአብሔር የሥራ እድል ከፍቶለት

አዲስ ሥራ ሲገባ የሚያገኘው የስራው ውጤት በመጀመሪያ በእጁ የሚገባው የእግዚአብሔር ነው። ነገር ግን

ይህ ሰው ይህን ሥራ እግዚአብሔር አሳድጎት ሌላ ከፍ ያለ ስፍራ አግኝቶ እስከሚቀይር አንዴ በኩራቱን

ለእግዚአብሔር ካመጣ ሥራ እስኪቀይር ነፃ ነው። ሰውነታችንን ለእግዚአብሔር ቅዱስና ሕያው መሰዋዕት

አድርገን ማቅረብ የቻልነው እግዚአብሔር የበኩሩ የኢየሱስ አይነት እንድንሆን አስቀድሞ በቃሉ ዳግን በመንፈስ

ቅዱስ ስለወለደን ነው። 

‘’እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም 

መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ 

የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። 2 የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም 

የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ 

እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።’’ ሮሜ.12፥1-2

“17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ 

ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። 

18 ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን፣’’ ያቆብ.1፥17-18

Page 92: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 92/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

92ww.tlcfan.org

 

16፤ በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኵራት የመከር በዓል፥ ዓመቱም ሳያልቅ 

ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ። 17፤ በዓመት ሦስት ጊዜ በአንተ 

ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ። 18፤ የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ 

እንጀራ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስኪነጋ አይደር። 19፤ የተመረጠውን 

የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ፣”

ዘጸ.23፥16-19

‘’የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ታገባለህ፣’’

ዘጸ.34፥26 

“9፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። 10፤ ለእስራኤል ልጆች 

እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም 

ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር  በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤፣’’ ዘሌ.23፥9-10

ይህን  ከላይ  ስለተናገርኩት  ማረጋገጫ  የሆነውን  ጥቅስ  ከተመለከትን  በኩራቱ  ደግሞ  ወደ 

እግዚአብሔር ቤት ከገባ በኃላ ለምንና ለማን? እንደሚሆን ልናውቅ ይገባል። የእግዚአብሔር ቃል ለዚህ ቁልጭ 

ያለ ትእዛዝ ያስቀምጣል። እግዚአብሔር አሮን ይህ ሕዝቡ የሚያመጣው የምጀመሪያ ፍሬ የሆነው በኩራት 

የእርሱና የቤተስቡ ድርሻ እንደ ሆነ ነገረው። ይህም ከላይ እንደተማርነው ደግሞ እርሱና ቤተስቡ በእግዚአብሔር 

ፊት እንዲበሉት ነው። ይህ ለእነርሱ የሆነበትን ምክንያት እግዚአብሔር ሲናገር ሰለ መቀባትህ ነው ይለዋል። 

ዛሬ የተቀቡ ሰዎች የሕዝቡን በኩራት ይወስዱ ዘንድ እግዚአብሔር ያዛል። ነገር ግን የተቀባው 

መንፈሳዊ  ነገሩን  እንጂ  ሥጋዊ  ነገሩን  እንዲያወፍር  እግዚአብሔር አያዝም። ምክንያቱም  እግዚአብሔር 

የተቀበልከውን በኩራት በተቀደሰ ስፍራ ብላው ይላልና ነው። ይህም መንፈስን የሚያመለክት ነው። ሰለዚህ

ካህኑ ከሥጋው ይልቅ መንፈሳዊ ሕይወቱን በተቀብለው በኩራት ሊያደልብ ይገባዋል። በዚህ ዘመን ግን

ተገላቢጦሽ ነው።  አገልጋዬ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ከማሳደግ የሚያሳድጉት የባንክ ቡካቸውን ነው። 

ይህ  የሚያሳየው  ደግሞ  የተቀባው  ሰው  በመንፈሳዊ  ሕይወቱ  የበለጠ  ለመጎልበት 

ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ሥራ  በሚገባ  በንፅህና  መስራት እንዲችል ያስችለዋል። የተቀባ  ሰው መንፈሳዊ 

እድገቱን እግዚአብሔር የደነገገለትን በኩራት እየበላ ሲጠብቅ እርሱንና የሚስሙትን የሚጠቅም ብርቱ ባሪያ 

ይሆናል።

Page 93: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 93/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

93ww.tlcfan.org

 

መኪናና ሱፍ የሚለዋውጥ ካህን ከሆነ ግን ለራሱም ለሚሰሙትም ኪሳራ ነው። ይህን ስንል

ግን በግሩ ይኒድ ማለቴ አንዳልሆን እንደምትረዱኝ አምናለሁ። ከልክ ያለፈ የሥጋው ፍላጎት መጨረሻው ሞትና

ውርደት ጥፋትም ነው።  ይህ  የተቀባ  ሰው  በቤቱ  የእግዚአብሔር  ነገር  የማያከብር  ልጅ  ቢኖረው  ከዚ  ነገር 

ተጠቃሚ  አያደርገውም።  ምክንያቱም  እግዚአብሔር  አሮንን  እንዳዘዘው  በቤትህ  ንጹህ  የሆነ  ሁሉ  ይብላው 

ይላልና ነው። የካህኑ ልጅ አለማዊ ቢሆን ይንን ገንዘብ ይመገብ ዘንድ እግዚአብሔር አያዝም። 

‘’8፤ እግዚአብሔርም አሮንን ተናገረው እንዲህም አለው። እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ 

የቀደሱትን የማንሣት ቍርባኔን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ ስለ መቀባትህ ለአንተና 

ለልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ። 9፤ በእሳት ከሚቀርበው ከተቀደሰው 

ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ የእህሉ ቍርባናቸው ሁሉ፥ 

የኃጢአታቸውም መስዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ለአንተ ለልጆችህም 

የተቀደሰ ይሆናል። 10፤ በተቀደሰ ስፍራ ብላው፤ ወንዶች ሁሉ ይብሉት፤ የተቀደሰ 

ይሆንልሃል። 11፤ ይህም ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን 

የማንሣትና የመወዝወዝ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች 

ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ 

ይብላው። 12፤ ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን 

ከእህልም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። 13፤ ወደ እግዚአብሔር 

የሚያመጡት በምድራቸው ያለው ሁሉ የፍሬ መጀመሪያ ለአንተ ይሆናል፤ 

በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው፣’’ 

ዘሁ.18፦12

‘’1፤ አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህም ጊዜ፥ 

በወረስሃትም በኖርህባትም ጊዜ፥ 2፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር 

ከምትሰበስበው ፍሬ ሁሉ በኵራት ውሰድ በዕንቅብም አድርገው፥ አምላክህ 

እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደ መረጠውም ስፍራ ይዘህ ሂድ። 3፤ በዚያም 

ወራት ወደሚሆነው ካህን መጥተህ። እግዚአብሔር ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን ወደ 

ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አስታውቃለሁ 

በለው። 4፤ ካህኑም ዕንቅቡን ከእጅህ ወስዶ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠውያ ፊት 

Page 94: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 94/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

94ww.tlcfan.org

 

ያኑረው። 5፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር። አባቴ 

የተቅበዘበዘ ሶርያዊ ነበረ፤ በቍጥር ጥቂት ሳለ ወደ ግብፅ ወረደ በዚያም ተቀመጠ፤ 

ታላቅ የሆነ የበረታም ቍጥሩም የበዛ ሕዝብ ሆነ። 6፤ ግብፃውያንም ክፉ ነገር 

አደረጉብን፥ አስጨነቁንም፥በላያችንም ጽኑ ከባድ ሥራን ጫኑብን፤7፤ ወደ 

አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፥ 

ጭንቀታችንንም ድካማችንንም ግፋችንንም አየ፤ 8፤ እግዚአብሔርም በጸናች እጅና 

በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤ 9፤ 

ወደዚህም ስፍራ አገባን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን። 10፤ 

አሁንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ። 

አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት 

ስገድ። 11፤ አንተም በመካከልህም ያለ ሌዋዊና መጻተኛ አምላክህ እግዚአብሔር 

ለአንተና ለቤትህ በሰጠው ቸርነት ሁሉ ደስ ይበላችሁ፣’’

ዘዳ. 26

Page 95: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 95/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

95ww.tlcfan.org

 

የመባ ሕግና መርህ 

እግዚአብሔር ሕግ ፍጻሜው ወይም ግቡ ፀጋ ነው። ፀጋው ደግሞ የመባ ወይም የመስጠት 

ቁልፍ ነው። መባ መስጠት እግዚአብሔር የማምለኪያ አንዱ መንገድ ነው። ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ ብሎ

ለፈኦን ተናገረ። ከግብጽ የወጣውም ሕዝብም ለመቅደሱ ስራ መባውን መስጠር  እግዚአብሔር በመስጠት

አመለከው።  በምድረ በዳ የወጣው ሕዝብ በብዙ መልኩ ማምለክ መስጠት እንደ ሆነ እግዚአብሔር በሕጉ 

አስተምሯቸል። 

ስለ መባ የተናገረን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መስጠት ከሁሉ የበለጠውን እግዚአብሔር እንዲሁ

የሰጠንን ስጦታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስታውስ ያደርገናል። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለሰው ልጆች ሁሉ

በመስጠቱ እኛም እግዚአብሔር በሰጠን በስጦታው በኩል መዳንና ወደ እርሱ መቅረብና የመመልስን ብቃትን

አግኝተናል።  መስጠት  ከልብ ፍላጎት  የሚመነጭ ነገር  ሲሆን  የተሰጠው  ስጦታ  ግን  የሚሰራው  ነገር  አለ። 

እግዚአብሔር ስለ ስጦታው የተመስገነ ይሁን። 

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር 

አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”ዮሐ.3፥16

“ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።”2.ቆሮ.9፥15

መስጠት እግዚአብሔር ለእኛ የስጠውን የልጁን ሕይወትና ባሕሪም የምናንፀባርቅበት አንዱ 

መንገድ ነው። መስጠት የሚባለው ነገር እርዳታ ከማድረግ ጋር ፈጽሞ አይገናኝም። ምክንያቱም መባ መስጠት 

ለአማኙ  አምልኮ  ነው።  አምልኮ  ደግሞ  ከልብ  ጋር  እንጂ  ከባንክ  ካለህ  ሃብት  ብር  ጋር  የተገናኘ  አይደለም። 

መስጠት  ካለን  ሃብት  ይልቅ  የልባችንን  ፍላጎት አጉልቶ  የሚያሳይ  ነገር  ነው። መዝገባችን ወይም ሃብታችን

ባለበት ልባችን በዚያ ይኖራልና ነው። መባን መስጠት ከአምልኮ ጋር የተያያዘ ኢየሱስም እንዲህ ይለናል፦ 

“እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ

እንዳለው ብታስብ፥በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም

ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።  አብረኸው በመንገድ ሳለህ

ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ

ወህኒም ትጣላለህ፤እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል

ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።” ማቴ.5፥23-26 

Page 96: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 96/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

96ww.tlcfan.org

 

ኢየሱስ መባ ከመስጠት በፊት የሚቀድመው የልብ ንጽሕና መሆኑን ይናገራል። ከሰዎች ሁሉ

ጋር በሰላም መኖር እንዳለብን። ቂም፣ ጣላቻ በአጠቃላይ በሃጢያት ኑሮ እየኖርን ወደ እግዚአብሔር ምንም

መባ ይዘን እንዳንቀርብ ያሳስበና። ይህም ዋጋ ያስከፍላልና ነው። በሃጢያት ተይዘን ወደ ፍርድ ከመጣን

የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክንከፍል ፈጽሞ ከእስር ወይም ከፍርድ አንወጣምና የጽድቅና የቅድስና ኑሮ

ከመስጠት በፊት የሚቀድም ነው። መባችንን የሚቀበለው እርሱ ክቡርና ቅዱስ ነው። ኢየሱስ በሌላው ስፍራ

ጠንከር አድርጉ ሲናገር እንዲህ ብሎ ይጠይቃል። “እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው

ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?” ማቴ.23፥19 መሠዊያው ላይ የእግዚአብሔር እሳት

ይወርድበትና የሚቀርበውን መባና ስጦታ እንደ አቤል እግዚአብሔር ይቀበለዋል።

ስለዚህም እግዚአብሔር የሚቀበለው የመባ ስጦታ መሠዋዕት በንጹህ ልብ የሚቀርብ ሊሆን

ይገባዋል። ቃየን ፦ “እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ?  መልካም

ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ

ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።” ዘፍ.4 እግዚአብሔር ቃየን ከወንድሙ አቤል ጋር ቀድሞ እንዲስማማና

መስዋዕቱ እንዲያቀርብ ይፈልጋል። ሰው በልቡ ያለው በፊቱ ላይ ይንጸባረቃል። የቃየን የፊቱ ጥቁረት

የሚያሳየው የልቡን ጥቁረት ነው። ቃየን መልካም ማድረግ እያመቀ መልካምን አያደርግም። መልካም ማድረግ

ከወድሞች ጋር ሁሉ በሰላምና በፍቅር መኖር ነው። ይህ ደግሞ ከመባና ለእግዚአብሔር ከመስጠት የሚቀድም

ነው። ከሁሉ አስቀድመን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የገባል። 

“ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤ከክፉው

እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው

ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው። ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ 

እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤

ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ

ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።”

1 ዮሐ. 3፥11-15 

ዛሬ ግን ብዙ ስዎች ከእግዚአብሔር የሆነ ነገር ለማግኘት ሲሉ ይሰጣሉ። እንደ ጻፎችና ፈሪሳዊያን

ለታይታ ይሰጣሉ። ይህ አይነቱ መስጠት ደግሞ እንደ ቃየን አይነት መሠዋዕት ነው። እግዚአብሔር 

አይቀበለውም። ስለዚህ ቀድመን ልባችንንና መንገዳችንን ከሃጢያትና ከአመጽ መንገድ እናንጻ። 

Page 97: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 97/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

97ww.tlcfan.org

 

ለእግዚአብሔር  የምንሰጠው  እርሱን ለማምለክ ፊቱን ለመፈለግ ነውና  ከእርሱ  ምንም 

ለማግኘት  አይደለም።  መስጠት  አምልኮ  ከሆነ  አምልኮችንን  ለሚገባው  አምላክ  በንጹህ ልብ ሆነን በደስታ

እንደጣለን። መባረክ ግን ከእኛ ፍላጎት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፍላጎት የመነጨ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ 

የምትፈልገውን ሳይሆነ በጊዜው የሚያስፈልህን ብቻ እርሱ እንደወደ ይሰጥሃል። ሰው በራሱ የተለያያዩ ፍላጎቶች 

በመመራት  ሊስጥ  ይችላል።  ነገር  ግን  ከፀጋው  የመነጨ  የመስጠት  አምልኮ  ግን  ምላሽ  ለማግኘት  ሳይሆን 

እግዚአብሔር ስለሚገባው ከፍቅርና ንጹህ ልብ በመነሳት የሚደረግ መሆኑን ከተረዳ ማንነት የሚወጣ ነው። 

ለእግዚአብሔር  መባን መስጠትና ማቅረብ ደግሞ የንጉስ ካህን ለሆንን አማኞች ሁሉ በኢየሱስ

ክርስቶስ የተሰጠን መብት  ነው።  ስለዚህም እግዚአብሔር  ከእኛ  ለመቀበል  በመቻሉ  እኛ  የታደልን  አድርገን 

ራሳችንን  ልንቆጥር  ይገባል።  እውነተኛ  አምልኮ  በመንፈስ  ሙላት ከጽድቅ ሕይወት  የሚመጣ  እንጂ  ከኪስ 

ሙላት የሚመጣ አይደልም። የእግዚአብሔር ትዕዛዝን የሚያምን ይታዘዛል ያደርጋል ይህ የሁል ጊዜ የማያቋርጥ 

አምልኮ ነው። መባ መስጠት እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንዲያመልኩት ከግብፅ ነፃ ለወጡ ሁሉ ልጆቹ የስጠው 

እርሱን ማምለኪያ የሆነ አንድ መንገድ ነው። እኛም ከሃጢያት ባርነት ነፃ ስላወጣን በመንፈስ በመመራት

በንጹህ ልብና ሕይወት በመሆኑ እግዚአብሔርን በመስጠት ወደና ፈቅደን እናመልከዋለን። 

“እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ስጦታ ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆችተናገር፤ በገዛ እጁ ሊሰጠኝ በልቡ ከሚያምረው ሰው ሁሉ መባ ተቀበሉ።ከእነርሱም

የምትቀበሉት መባ ይህ ነው፤” ዘጸ.25 

መባ ከተለያየ ነገር መውጣት ወይም ለእግዚአብሔር መሰጠት እንደሚችል ዝርዝሮችን ለሙሴ

በመስጠት እግዚአብሔር አስተምሮናል። ደግሞ መባ ከአሥራት ከመማውጣት ጋር ፈጽሞ የተለያየ መሆኑንም

እንድንገነዘም ያደርገናል። ምክንያቱም አሥራት ከእግዚአብሔር የሚጠበቅብን ምንም ምርጫ የሌለበት ሲሆን 

መባ ግን በፍጹም  በስውየው  የልብ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመስረተ  ስለሆነ ነው።  ትክክለኛ ምርጫንና የልብ 

ፈላጎትን  የሚጠይቅ  ነው።  መባ ሊወጣ  የሚገባውም  እግዚአብሔር  ስላደረገልን  ነገር  እግዚአብሔርን 

ለማመስገን ለማክበር ነው። የወጣውንም መባ የሚቀበሉ እንደ ሙሴ ያሉ በእግዚአብሔር የተመረጡና የተቀቡ

ባሪያዎቹ ደግሞ የእግዚአብሔር እውነተኛ መቅደስ ሊያንጹበት ይገባል። መባ በምን ጥቅም ላይ እንደሚውል

ከዘጸአት 25 ጀምረን ተነስተን ብናነብ በግልጽ መረዳት እንችላለን። መሪዎች ሕዝቡ በፍላጎቱ የሰጠውን መባ

ከዚህ በተለየ መኩ ከተጠቀቡበት ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድንና ቅጣትን ይቀበላሉ። እንደ ይሁዳ እግዚአብሔር

አምኖ በገንዘቡ ላይ ሲሾመን እጃችንን የምንሰድ ከሆነ ለሰይጣን ታልፈን እንሰጣለን። 

Page 98: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 98/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

98ww.tlcfan.org

 

መባ እንደ አሮንም ሰብስበን ሰዎችን ከእግዚአብሔር መንገድ የሚያወጣን ጥጃ ልገነባበትም

የተሰጠን በፊታችን መልካም መስሎ እንደታየን የምናደርግበት ነገር አይደለም። ሙሴን እግዚአብሔር

ያመጡልኝ ዘንድ እንዳለ መባ እንደ ሥራት የእግዚአብሔር ብቻ ነው። ነገር ግን በዘጸአት ላይ እግዚአብሔር

እርሱ ለሚያድርበት ለመቅደሱ እና ከመቅደሱ ጋር ተያይዘው ላሉት ነገር እንደተጠቀመው በዚህም ዘመን

የእግዚአብሔርን መባ ከዚህ በተለየ መልኩ መጠቀም ፈጽሞ አንችልም።

በዚህ ባለንበት ዘመን እግዚአብሔር ማደሪያው ያደረገው የሰው ልጆችን ነው። ስለዚህ

የእግዚአብሔር መባ ዛሬ ሊውል የሚገባው በዚህ በመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለሆነው ለሰው ልጅ ሕይወት

መገንቢያ ላይ ነው። የተራበው በነፍሱም በሥጋውም ሊበላበት፣ የታረዘው ሊለብስበት፣ የተጠማው ሊጠጣበትእና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዲችን የእግዚአብሔር ሕግና ቃል እንዲማርበት ስለዚህን በመቅደሱ ዙሪያ

ባጠነጠኑ ነገሮች ላይ ብቻ ሊውል ይገባዋል። 

አዳኑ ሲወለድ ስባ ስገሎች መባና ስጦታቸውን ለነገስታት ንጉሥ ይዘውለት መጡ።  ሄሮድስም

ሰጦታ ለመስተት እንደሚፈልህ ለሰባ ሰገሎች ነግሯቸው ነበር። እግዚአብሔር ግን ከአፉ ይልቅ ልቡን ያውቅ

ነበር። ሄሮድስ ግን የት እንዳለ ቢነገሩት ግቡ ትክክል ያልሆነ ስጦታ መባ ሊስጥ ይዞ ይመጣ ነበር። ቢመጣ ኖሮ 

መባውን አስቀምጦ ልጁን በያዘው ሰይፍ ይገድለው ነበር። ዛሬም መባ በተቀቡት ፊት አስቀምጠው ዞር ብለው

አንደበት አፍ በጥላቸው የሚገድሉ ሄሮድሶች በመካከላችን አሉ። ፍጻሚያቸው እንደ ሄሮድስ የሚያሳዝን ፍጻሜ

ነው። ትክክለኛ የመስጠት ፍላጎት ግን ንጹህ ልብና ፍቅር ነው። ለመልካም ነገር ለማድረግ ከሚነሳሳ ማንነት 

የሚወጣ መስጠት ነው። 

‘’23 የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፤ የኀጥኣን ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው። 24 ያለውን 

የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፤ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም። 

25 የምትባረክ ነፍስ ትጠግባለች፥ የረካም እርሱ ደግሞ ይረካል። 26 እህልን የሚያስቀር ሰው 

በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፤ በረከት ግን በሚሸጠው ራስ ላይ ነው። 27 መልካምን ተግቶ 

የሚሻ ደስታን ይፈልጋል፤ ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል። 28 በባለጠግነቱ 

የሚተማመን ሰው ይወድቃል ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፣’’

ምሳሌ.11፥24-28

Page 99: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 99/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

99ww.tlcfan.org

 

የመባና  የመስጠት  መርህ  በሁለተኛ  ቆሮንጦስ  ዘጠኝ  ሰባት  ላይ  ይገኛል።  ይህም  ቃል  መባ 

መስጠት  ከአሥራት  ማውጣት ጋር  ፈጽሞ  የተለያየ  እንደሆነም  ያረጋግጥልናል።  በምዕራፍ  ስባት  ላይ 

ስላስተማራቸው  ትምሕርት  የሚገባውን  የመታዘዝ  ምላሽ  ለእግዚአብሔር  እንደሚስጡ  እየተረዳ  ቀጥሎ 

የመስጠትን  መርህ  በሁለቱ  ቀጣይ  ምዕራፎች  ጳውሎስ  ለቆሮንጦስ  ቅዱሳን  አስተማረ።  በዚህ  በትምህርቱ 

ውስጥ ሁሉ አማኝ ይከተለው ዘንድ የሚገባውን አሥራ አምስት ድንቅ መርሆችን እናገኛለን። አስቀድማችሁ 

2.ቆሮ.8 ና 9 በሙሉ ደጋግማችሁ ያንብቡት። 

‘’6 እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን 

መጠን ትንቢት እንናገር፤7 አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ 

የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤8 የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ 

የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር፣’’

ሮሜ.12፥8

በሐዋርያው ጳውሎስ ትምህርት መሰረት መባ መስጠት ትልቅ የሆነ መለኮታዊ ሚስጥርና

የመንፈሳዊ ብስለት ውጤት መሆኑን እንገነዘባለን። ከዚህ በመቀጠል አስራ አምሥቱን የመባ መስጠት መርሆች

እስከጥቅሱ እንመለከታለን። ይህ ግን ይህን መጽሐፍ ከማንበብ ያለፈ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎትና በጾም

በመውደቅ ልንማረው የሚገባ መለኮታዊ ሚስጢር በውስጡም ያለው ነው። 

Page 100: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 100/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

100ww.tlcfan.org

 

አሥራ አምስት መባ የመስጠት መርሆች 

በሐዋርያው በጳውሎስ ትምህርት መሰረት አሥራ አምስት መባ የምስተት መርሆችን በሁለተኛ

ቆሮንጦስ ላይ ተጽፎ እናገኛለን። ትምህርት ከማንበባችሁ በፊት ከላይ እንደጠየኩ ሁለቱን ምዕራፎች

ደጋግማችሁ በታማኝነት እንዳነበባችሁ በማመን በቀጥታ ወደ አሥራ አምስቱን መርሆች ከዚህ ቀጥዬ በዝርዝር

አስቀምጣለሁ። አሥራ አምስቱ መርሆንች እነዚህ ናቸው፦ 

1.  የተሰጠው ጸጋ… 2.ቆሮ.8፥1-2 

2.  የነፃ ፍላጎት ስጦታ…2.ቆሮ.8፥3 

3.  ለቅዱሳን የሆነ አገልግሎት…2.ቆሮ.8፥4 

4.  ራስን መስጠት…2.ቆሮ.8፥5 

5.  በመስጠት መትረፍ…2.ቆሮ.8፥6-7 

6.  የፍቅር ፈተና….2.ቆሮ.8፥8 

7. 

ከጌታ ሕይወት መማር…2.ቆሮ.8፥9 

8.  የተማርነውን በሥራ ማዋል…2.ቆሮ.8፥10-11 

9.  ቅን የሆነ መረዳት…2.ቆሮ.8፥12-14 

10. በስርዓት ገንዘብን መጠቀም.. 2.ቆሮ.8፥15 

11. የመስጠት ቅንዓት…..2.ቆሮ.9፥1-4 

12. ሳይጎተጎቱ መስጠት…2.ቆሮ.9፥5 

13. የመስጠት በረከት…2.ቆሮ.9፥6 

14. የመስጠት ልብ…2.ቆሮ.9፥7 

15. ለቅዱሳንና ለእግዚአብሔር የሚበዛ ምስጋና...2.ቆሮ.9፥12-15 ናቸው። ከዚህ በመቀጠል

ደግሞ እያንዳንዱን መርህ በዝርዝር ጠጋ ብለን እንመለከታቸዋለን። 

Page 101: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 101/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

101ww.tlcfan.org

 

1.  የተስጠው ጸጋ 

“ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን

የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን፤2 በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉየደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፣’’

2.ቆሮ.8፥1-2 

ታሪክ እንደሚናገረው ይህን ጸጋ ለሜቄዶንያ ሰዎች በተሰጠበት ወቅት እነርሱ የነበሩበት

የኢኮነሚ ሁኔታ በጣም የከፋና ያሽቆለቆለ ነበር። ሮማውያን መጥተው አገራቸው ብዙ ነገር ከማውደማቸው

ባሻገር ያላቸውን ሃብት ሁሉ ሳይቀር በጉልበት በዝብዘዋቸው ነበር። በዚህ የጦር ወረራ በሮም ወታደሮች ዝርፊያ

የወደቀባቸው የጠለቀ ድህነት በኢየሩሳሌም ላሉ አማኞች መታነጽ እንዲለግሱ አልከለከላቸውም። ይህም

እግዚአብሔር የስጣቸው ጸጋ ነው። ይህ ከእግዚአብሔር የተቀበሉት ጸጋም ከድህነታችው ይልቅ ለጋስነታቸውን

እጅጉን አብዝቶታል። ስለዚህ መባ ለመስጠት የእግዚአብሔር ጸጋ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል። እግዚአብሔር

ጸጋውን ደግሞ ለትሁታን ይሰጣል። 

የመቄዶንያ ስዎች መባን የስጡት በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ለተቸገሩ ቅዱሳን ነው። እግዚአብሔር

መቼም ቢሆን በአካል ወርዶ ገንዘብ ከስዎች አይወስድም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝና ሥም ለስዎች

ስናደርግ ለእግዚአብሔር እንዳደረግነው ልናውቅ ይገባል። በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ሃያ አምስት ላይ ኢየሱስ

ተርቤ፣ ተጠምቼ፣ ታርዤ… ወዘተ ምንም አላደረገችሁልኝም ለሚላቸው ሰዎች መልሱ አንድና ግልጽ የሆነ ነው።

በሥሜ ለማንኛው ስው የምታደርጉት ለእኔ እንደምታአርጉት ነው አላቸው። ይህን ያላወቀ አማኝ አስቀድሞ

ይህን እውነት ሊያውቅ ይገባዋል።

“ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ

አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ

አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ፦

እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ

አደረጋችሁት ይላቸዋል።” ማቴ.25፥37-40 

በኢየሩሳሌም ያሉ አማኞች በዝርፊያ  ከወደቀባቸው ድህነት ይተነሳ የመመገቡት እንኳን

አጥተው ነበር። በሕይወት እንዲኖሩ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር። ይህ ከጳውሎስ የተላከው ደብዳቤ

ላሉበት ሁኔታ የጊዚያዊ እርዳታ ለማድረግ ነው።

Page 102: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 102/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

102ww.tlcfan.org

 

በዚህም ከችግር ምክንያት እንዳይሞቱና ከጌታ የተሰጣቸው ሥራቸው እንዳይስተጓጎልም ነው።

ምንም እንኳ በሜቄዶንያና በኢየሩሳሌም አማኞች መካከል ትልቅ ልዮነትና ርቀት ቢኖረውም። ከሕዛብ የዳኑ

አማኞች በኢየሩሳሌም ያሉትን አይሁድ አማኞችን እረዱ። የመቄዶንያ አማኞች ምንም አይነት ክፉ ነገር ሰለ

አይሁድ አማኞች እንደ ዘመኑ ጸረ አይሁዶች “Antisemitic” አልተናገሩም። ይህን ከሜቄዶንያ አማኞች ልንማር

ይገባል። 

የሜቄዶንያ አማኞች በመንፈስ የተሞሉ የእግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታ የሆነው ደስታ በቃል

ሙላት የሚመጣው ደስታ በማይመች ሁኔታ ውስጥ የበዛላቸው ስዎች ነበሩ። ኤር.15፥16, ዮሐ.13፥

17,1ዮሐ.1፥14 ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ስዎች ይህን ያለበት ምክንያት በአንደኛ ቆሮንጦስ ላይ የገለጸውን ነገር

ሊያሳስባቸው ጭምር ነው። የቆሮንጦስ አማኞች እኔ የእንትና ነኝ በማለት በአገልጋይ ስር መሮጥ ይወዳሉ።

አንዱን የአማኝ ሕብረት ከአንዱ የአማኝ ሕብረት የሚከፋፍል መንፈስም ገብቶባቸው ነበር።

ስለዚህም የመቄዶኒያ አማኞች ለቆሮንጦስ ስዎችና እንደ ቆሮንጦስ ሰዎች ዛሬም ባለንበትም

ዘመን ለሚያስቡ ሰዎች ጥሩ ምሳሌ የሆኑ መማሪያችን ናቸው። ምንም እንኳ ደሃ ቢሆኑ ደህነታቸውን በመናገር

እርዳታውን ከማድረግ አልተከለከሉም።  የእግዚአብሔር ጸጋ ስለበዛላቸው ጸጋውም ወደፊት

የሚያስፈልጋቸውንም ነገር እንደሚረዳቸው በመገንዘብ ለገሱ፣ ሰጡ። መስጠት ከሰውም ሆነ ከእግዚአብሔርለመቀበል የሚያስችል ጉቦ አይደለም። 

መስጠት ከፍቅር በእግዚአብሔር ጸጋ አነሳሽነት የሚመጣ ከልብ ውስጥ የጠለቀ ፍላጎት ነው።

በተሳሳተ ፍላጎት ለስው ከመስጠት ይልቅ ገንዘቡ የራሳችን ሰለሆነ ቀድሞውኑ አለመስጠትም እንችላለን።

ሃናኒያና ሰጲራን የገደላቸው ሞት የሚገባው ሃጢያት የተሳሳተ አሰጣጥ ነው። ሰለዚህ አማኞች ከራሳቸው

ተነሳስተው ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ ተነሳስተው እንዲስጡ በትሕትና ጸጋን ከሚሰጠው እግዚአብሔር ይህን

ለመቄዶንያ ስዎች የተሰጠውን ጸጋ አስቀድመው ይቀበሉ እላለሁ። 

ጳውሎስ በመቄዶንያ አማኞች ላይ የበዛውን ጸጋ የእርሱን የጸጋ ሕይወት ልምድ ለምስክርነት

ይህን ብዙ ጊዜ በተለያያ ስፍራ ይደግመዋል። ሐዋ.24፥17, ሮሜ.15፥25-28, 1.ቆሮ.16፥1-5,ገላ.2፥10ን

ይመልከቱ። የቆሮንጦስ ሰዎች መባን መስብሰብ ጀምረው ነበር። ነገር ግን ገና አሰባስበው አልጨረሱም ነበር።

ምን እንደተፈጠረ ባይታወቅም ይህን የማሰባሰብ ሥራ ቲቶ እንዲፈጽመው ለመኑ። 2.ቆሮ.8፥6

Page 103: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 103/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

103ww.tlcfan.org

 

ይህ ለቆሮንጦስ ሰዎች የነበሩበት ሕይወትን ያስረዳል። ጳውሎስም ትምህርቱን የላከላቸው ቲቶ

ሥራው የበለጠ እንዲቀላጠፍለትና ሕዝቡ ትክክለኛውን መስጠት የሚሰጠው መስጠት ምን እንደ ሆነ መርዳቱ

ሲመጣለት እንደ ሆነ ስላመነ ነው። የመቄዶንያውያን ደስታ የቃል ሙላትንና የመንፈስ ሙላትን የተቀበሉ

አማኞች መሆናቸውን ያሳያል። 

2.  የነፃ ፍላጎት ስጦታ 

‘’3 እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ

እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና።’’ 2.ቆሮ.8፦3 

በጸጋው የሆነ መባ መስጠት ምንም አይነት ግዴታን አይጨምርም። በማንም ሰው ተነስቶ

ሌላውን ሰው ለምን አልሰጠህም ሊል አይችልም። መባ የባለንብረቱ ፍጹም ፍላጎትና ፍቃድ ላይ የተመሰረተ

ስጦታ ነው። ሰው በስሜቱ ተገፋፍቶ ሊሰጥ ይችላል መጨረሻው ግን ፀጸት ነው። መባ ከክስ ለመንፃት፣

ለታይታ፣ ከሰው ላለመለየት ተብሎ፣ እውቅናን ለማግኘት፣ ጎሽ ለመባል፣ ለመሸንገል ፈጽሞ አይሰጥም። ይህ

ከሆነ መባ ሳይሆን ጉቦ ነው።

ምሳሌ ላይ የእግዚአብሔር ቃል “ጉቦ የጻድቁን አይን ታሳውራለች፣” ይላል። ስለዚህ በዚህ

አይነት ስሜታዊ ሥጋዊ መገፋፋትና መነሳሳት የሚስጥ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ሐዋርያት ሥራ አምስትን

አንብቡ።  አንድ አማኝ መባን ሊስጥ የሚገባው በውስጡ ባደረው መንፈስ ቅዱስ አነሳሽነትና በነፍሱ ላይ

በተተከለው የእግዚአብሔር ቃል መርህ መሰረት ሊሆነ ይገባዋል። መስጠት የአንድ ሰውና የእግዚአብሔር የግል

የልብ ንግግር ነው። 

እያንዳንዱ አማኝ የንጉስ ካህን ስለሆነ ለእግዚአብሔር የሚገባውን የመባ መስዋዕት በልቡ

ለእግዚአብሔር የማቅረብ መብት አለው። ሰው በልቡ የሚመጣለትን እግዚአብሔራዊ የጊዜውን ትዕዛዝ

መቀበል ወይም አለመቀበልም መብት አለው። ይህን ሰለ መባ ያለን መብት ነው። ፍጹም የሰውየው ፍላጎት

ቀዳሚ የሚያደርግ ነው። እግዚአብሔር ጸጋውን ትዕዛዙንና መንፈሱን ብሎም በረከቱን ይሰጣል። 

የሜቄዶንያ ስዎች ወደውና ፈቅደው ከአቅማቸው የሚያልፈውን እንኳ ሰጡ። ይህን

ሥራቸውን ደግሞ የእምነት አባቶች በየስፍራው መስከሩላቸው። መልካም ምግባር ምስክርነት በየስፍራው

መቀበል ያስቻላቸው ገንዘባቸው ሳይሆነ ከእግዚአብሔር የተቀበሉት ጸጋና መንፈስ ነው። ሲሰጡ የነበሩበት

ሁኔታና የልባቸው ንጽሕና ነው። 

Page 104: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 104/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

104ww.tlcfan.org

 

3.  ለቅዱሳን የሆነ አገልግሎት 

‘’ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት

በብዙ ልመና ከእኛ ይለምኑ ነበር።’’ 2.ቆሮ.8፥4 

ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት ለመተባበር መለመን ነውር አይደለም። ምክንያቱም ቅዱሳንን

ማገልገል ከንቱ ነገር ሳይሆን የከነበረ ነገር ሰለሆነ ነው። የመቄዶንያ አማኞች ይህን ቸርነት በብዙ ልመና

ከእግዚአብሔር ባሪያዎች ጠየቁ። መስጠት በመንፈስ ለተሞሉና የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለሚረዱ ሰዎች

ትልቅ እድልና ቸርነት ነው። ይህን ሚስጢር የመቄዶንያ ስዎች ገብቷቸዋል። ይህ እድል በእግዚአብሔር በጸጋው

በኩል ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ ነው። 

እኔነት ለሞላቸው አማኞች ይህ ትልቅ ሊወጡት የማይችሉት ዳገት ነው። ይህ ነገር በሰዋዊ

አዕምሮ ልንረዳው የምንችለው ነገር አይደለም። ምንም አንኳ አንዳንድ ሰዎች ለመስጠት ቢሞክሩም ፈጽሞ

በመንፈስ ከልብ የመነጨን ፍላጎትን ፈጽሞ ሊተካ አይችልም። ለመስጠት መለመን በእግዚአብሔር መንፈስ

እንጂ በሰው አይቻልም። ይህ የመባ እንድል በመንፈስ ለተሞሉ በቃሉ ለሚኖሩ የተሰጠ እድል ነው። ግብፃዊ

መባ እንዲያወጣ አልተጠየቀም ይህ የእኛ ያማኞች ብቻ እድል ነውና ደስተኛ ልሆን ይገባል። 

በእግዚአብሔር መባን ለመስጠት እንደ ሕዝበ እስራኤሎች በምድረ በዳ በሙሴ

እንደቀረበላቸው ጥያቄ ለእኛም ሲቀርብልን እንደ ታላቅ መታደል ልንቆጥረው ይገባል። ሕዝበ እስራኤል

ለመቅደሱ የሚውለውን መባ እግዚአብሔር ከሚፈልገው በላይ በማምጣታቸው ከዚያ በኋላ እንዳያመጡ

ተከለከሉ። ይህ ለእኛ ትልቅ ልንከተለው የሚገባ ሕይወት ነው። እግዚአብሔር ሲጠይቀን ብቻ ሳይሆን እንደ

ሜቄዶንያ ሰዎች ለቅዱሳን ለሚሆነው አገልግሎት ለመተባበት መጠየቅም ታላቅ ጸጋንና ንጹሕ ልብን የሚያሳይ

ነው። እግዚአብሔር ሳንጨቀጨቅና ሳንጎተጎት መስጠትን የሚያበዛውን መንፈሱንና ጸጋውን ያብዛልን። 

4. 

ራስን መስጠት 

‘’አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ

ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም።’’ 2.ቆሮ.8፥5 

የመቄዶንያ ስዎች ጳውሎስ ከጠበቀው በላይ ያደረጉበት እንዴት ነው? የልግስናቸው ባለጠግነት

ማለት አብልጠው እዲስጡ ያደረጋቸው ሚስጥሩ ምንድን ነው? ሚስጢሩ አንድ ነው። በሰው ፍቃድ ሳይሆን

በእግዚአብሔር ፍቃድ አስቀድመው ራሳቸውን ለጌታ ሰጥተዋልና ነው። ከዛም ራሳቸውን ለጌታ ስለ ሰጡ

ለእነጳውሎስም ሆነ ለኢየሩሳሌም አማኞች ራሳቸውን መስጠት አላቃታቸውም።

Page 105: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 105/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

105ww.tlcfan.org

 

አንድ ሰው ራሱን ለጌታ ስጠ ማለት በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጎለበተ አደገ ማለት ነው። የእድገት

ምልክት የሆነው የሜቄዶንያ ሰዎች ተግባር ስጦታን ለምዕመን ለቤተ ክርስቲያን ከመጠት አስቀድሞ ራሳቸውን

ለጌታ ሰጥተዋል። ሰው ራሱን ለጌታና ለጌታ ባሪያዎች ሳይስጥ ገንዘቡን ሊያካፍል ወይም ሊስጥ ይችላል። ይህ

አይነት ስው ግን ከጌታ አንዳች አይቀበልም። ነገር ግን አንድ አማኝ ገንዘብ ሰጠ ማለት መንፈሳዊ ነው ማለት

አይደልም። ነገር ግን አማኝ ከሁሉ አስቀድሞ ራሱን ሙሉ በሙሉ ለጌታ አሳልፎ መስጠት ግን ትልቅ

መንፈሳዊነት ነው። ስጦታችን መለኮታዊ መልካም ተግባር መሆኑን ከመንፈስ የመነጨ መሆኑ የሚታወቀው

ራሳችንን ለጌታ በሰጠንበት መጠን ነው። ራሱን ለጌታ የሰጠ ሰው ሲሰጥ ይህ ድርጊቱ ከመንፈስ የመነጨ

መሆኑን ያሳያል። ከመለኮታዊ መልካምነት መስጠትና ከኪስ ሙላት አንስቶ መስጠት ፈጽሞ ይለያያል። 

በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መለኮታዊ መልካምነት እንጂ የሰዎች ፍጥረታዊ መልካምነታችን

አይደለም። ከመንፈስ መለወጥ ራስን ለጌታ ከመስጠት የሚወጣ መልካምነት መለኮታዊ መልካምነት ይባላል።

ሰው በመንፈስ እለት እለት ሲሞላና የእግዚአብሔር ትምህርት ብቻ በአዕምሮ ሲሞላና ቃሉን እየታዘዘ ሲኖር

የሚሰጠው ስጦታ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ተቀባይነትን ያገኘ ነው። ስጦታችን ከስሜታዊ መገፋፋት

ሊሆን አይገባውም። ተረድተንና አውቀን በመንፈስ እንደ ቃሉ ልንሰጥ ይገባል።

በኮንፍረንስ ጊዜ የሚዞሩ የመባ እቃዎች በስሜት የሰውን ኪስ ሲያራግፉ ማየት የተለመደሆኗል። ደግሜ እላለሁ በሰሜት ከመስጠት ተጠበቁ። ይህም መልካም የሆነን በረከት ለማጨድም ተስፋ

በማድረግ ነው። በስሜት የተዘራ ገንዘብ በአየር ላይ እንደተበተን ገለባ ነው። በመንፈስ ስላልተተከለ

የሚያበቅለው አንዳች የለውም። መንፈስን እንጂ ስሜትን አትከተሉ። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ቁልፍ ራስን አስቀድሞ

ለጌታ መስጠት ነው። 

5. በመስጠት መትረፍ 

‘’ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ እንደ ጀመረ እንዲሁ ደግሞ ይህን ቸር ሥራ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ሊፈጽም

ለመንን። ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነትና በቃል በእውቀትም በትጋትም ሁሉ ለእኛም በፍቅራችሁ

እንደ ተረፋችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ትረፉ።’’ 2.ቆሮ.8፥6-7 

የቆሮንጦስ ስዎች ጋር ቲቶ ገንዘብ ማሰባሰብን ጀምሮ ነበር። ነገር ግን የቆሮንጦስ አማኞች

ምንም እንዃ መንፈሳዊ ነገር የበዛላቸው ቢሆኑም በመስጠት ላለው ትርፍ አልበቁም ነበር። በእነርሱ ፍቅር

የመነጨ መስጠት ቢገለጥ ብዙ አማኞችን እውቀታቸው እንዳተረፈ ያተርፍ ነበር። ነገር ግን ቲቶ ራሱ ሄዶ ይህን

ገንዘብ ማሰባሰብ ለሁለተኛ ጊዜ ለመሥራት ተለመነ። 

Page 106: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 106/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

106ww.tlcfan.org

 

ይህም የሚያሳየው በመጀመሪያ አገልግሎቱ የሰጡት ምላሽ አሳዛኝ እንደ ነበር የሚያሳይ ነው።

ይህ የቆሮንጦስ ሰዎች በጌታ ቢሆኑም የሥጋ ስለነበሩ ነው። ትክክለኛ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት እምነትና

ትጋት አንድ አማኝ ላይ ሲያመጣ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ሕይወት ከዚያ አማኝ ሰው ይወጣል። በቀላሉ

ለሌሎችም መትረፍ ይችላል። 

የመቄዶንያ አማኞች ይህ ሁሉ የበዛላቸው ስለነበሩ አስቀድመውም ይህን ከእውቀትና

ከእምነት የመነጨ ትጋታቸውን በመስጠትም አሳይተዋል። በፊት ለእንዲህ አይነቱ አገልግሎት ተርፈው ነበር።

አሁንም ደግሞ ይህን አገልግሎት እንዲካፈሉ ራሳቸው ይህ እድል እንዲስጣቸው ይጠይቃሉ። የእግዚአብሔር

እውቀትና እምነት ከትጋት ጋር የገባበት ምእመን ሲገኝ መባ እቃ ማዞር ይቀራል። ያኔ ሰው ደስ ብሎት ጠይቆ

እንጂ ተጠይቆ መስጠት ያቆማል። 

ጳውሎስ የቆሮንጦስ ሰዎች ምንም እንዃን በመንፈሳዊ ስጦታ የተሞሉ ምዕመናን ቢሆኑም

በእነርሱ ዘንድ እንደ ሚቄዶንያ ሰዎች የበዛ የእግዚአብሔር ፍቅር ስለሌላቸው ገና ወተትን የሚጋቱ ስለነበሩ

በእነርሱ ዘንድ መለኮታዊ መልካምነት ያለው መስጠት አልተከናወነም። ምክንያቱም ምንም እንዃን

መንፈሳዊና ፍጥረታዊ በረከት ከመቄዶንያ አማኞች እጅግ የተሻለ ሁኔታ ላይ ቢገኙም ልባቸውን የሚያነሳሳ

እምነትና የእግዚአብሔር እውቀት ሰራ ላይ እንደሚገባ አላዋሉትም ነበር። 

ሰው የእግዚአብሔር እውቀት በውስጡ በእምነት ካላደረ ቢኖረውም መስጠት አይችልም።

ቢስጥም የሚሰጠው በጌታም ሆነ በሰዎች ዘንድ አሳዛኝ በሆነ አስጣጥ ነው። ለሚሰበስበውንም ሰው ልብ

ያሳዝናል። እንዲ አድርጌላቸው ማለቱ በኃላ የማይቀር ሰለሆነ ነውና ነው። የሚሰጠው ወይ ለታይታ ወይም

ያደርጋል እንዲባል የቤተ ክርስቲያን አባልነቱን ግዴታ ለመፈጸም እንጂ በእውነት ቃል ተረድቶ ስለማይሆን

ፍፃሜው የከፋ ነው። አንድ አማኝ ሊሰጥ የሚገባው ከመንፈሳዊ ሕይወት እድገት በእምነትና በእግዚአብሔር

እውቀት ሲሞላ ብቻ ሊሆን ይጋባዋል። ይህ አይነቱ መስጠት ሰው ሲበዛለት በመስጠት ወዳለው መትረፍውስጥ ይገባል። 

6. የፍቅር ፈተና 

‘’ትእዛዝ እንደምሰጥ አልልም፥ ነገር ግን በሌሎች ትጋት

በኩል የፍቅራችሁን እውነተኛነት ደግሞ ልመረምር እላለሁ።’’ 2.ቆሮ.8፥8 

Page 107: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 107/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

107ww.tlcfan.org

 

ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ስዎች ስለ ፍቅር አስተምሯቸዋል። ጳውሎስ መስጠታቸውን ፍቅር

የሚባለው ትምህርት ገብቷቸው እንደ ሆነና እንዳልሆነ መስጠትን የፍቅራቸው መፈተኛ መመርመሪያ

መሳሪያው አደረገው። እዚህ ጋር ጳውሎስ እንዲሰጡ ምንም ሲያዛቸው ወይም ሲያስገድዳቸው አናይም። ነገር

ግን በውስጣቸው የተተከለውን ፍቅር ለመግለጥ እንዲችሉ ይህን በመስጠት የሚገለጠውን ፍቅር እንዳላቸውና

እንደ ሌላቸው ሊያውቅ ወደደ። 

ይህ ፍቅር በመቄዶንያ ሰዎች ያለና የተገለጠ ነው። ሰለዚህ ስድስተኛው የመስጠት መርህ

እንደሚያሳየው መስጠት ለጌታ ያለንን ፍቅር የምናሳይበትና ለጌታ ፍቅር እንዳለን ወይም እንደ ሌለን

የምንፈተንበት ነው። መስጠት ግዴታ አይደለም ውዴታ እንጂ መስጠተት አንድ ሰው ካለው መለኮታዊ እይታና

መረዳት የሚመነጭ በመንፈስና በጌታ እውቀት አነሳሽነት የሚደረግ የግል አምልኮ ነው። 

የመቄዶንያ ሰዎች የድህነታቸ ጥልቀት ለጋስነታቸውን አላሳነሰውም ምክንያቱም የሚስጡት

በእምነትና ፍቅር እንጂ ኪሳቸውን በማየት አይደልም። እምነት ደግሞ ጌታን እጅግ ያስደስተዋል። በመንፈስ

ምሪት እንደ መቄዶንያ ሰዎች የሚስጥ አማኝ ሁሉ ለጌታ ያለው ፍቅር ከማመን ባለፈ ሁኔታ ለሰዎች ሁሉ

መግለጥ የቻለ የበሰለ አማኝ ነው። ጳውሎስ ለፊልጲስዩስ ስዎች ያለውን ጸሎት ሲናገር። 

“ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ

ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ

የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል

ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።’’ አለ። ፊል.1፥9-11 

7.  ከጌታ ሕይወት መማር 

‘’የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥

እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ፣’’ 2.ቆሮ.8፥9 

መስጠት ነጻ ፍላጎት ወይም በጸጋ ነው። ከጸጋ ስጦታ አንንዱ ከላይ እንዳየነው መስጠት ነው።

ኢየሱስ እኛ በብዙ ነገር ማለት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ነገር ባለጠጎች እንድንሆን ራሱን ስለ እኛ ባዶ አደረገ።

ማንም ስለ ሰው ልጆች ከኢየሱስ ሌላ በመስቀል ላይ የሞተ የለም። እርሱ የሰጠን ሕይወቱን ነው። ሕይወቱን

ለስጠ ጌታ እርሱ እራሱ የባረከንን ጉልበታችንን ጊዜያችንንና ያለንን ነገር ሁሉ ብንሰጠው ምንም አይደለም። 

Page 108: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 108/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

108ww.tlcfan.org

 

ጌታ ለሰራው ሥራ ክፍያ የሚጠይቅ ቢሆን ኖሮ ስንቶቻችን ዛሬ መዳን እንደምንችል

አላውቅም። ነገር ግን ጌታ ፍቅር ስለ ሆነ ፍቅር ደግሞ አንዱ ባሕሪው መስጠት ስለ ሆነ ኢየሱስ ለእኛ ከአባቱ

ዘንድ እንዲሁ ተሰጠን። እርሱም ሕይወቱ ስለ እኛ አሳልፎ በመስቀል ላይ ሰጠ። እንግዲህ መስጠት የሚባለው

ነገር ይህን እውነት ከመረዳት የመነጨ ሊሆን ይገባዋል። ጌታ ለአባቱ፣ ለሕዝቡ፣ ለሚጠሉት ለሁሉ ስጪ ነበር

አንተስ? አንቺስ? እንግዲህ መስጠትን ከጌታ ሕይወት እንማር። ወንጌል የኢየሱስን አጋስነት በልግጽ ያሳየናልና

እርምጃውንና ኑሮውን በማየት በሁሉ ልንመስለ ራሳችንን እናትጋ። 

8.  የተማርነውን በተግባር ማዋል 

‘’በዚህም ነገር ምክር እሰጣለሁ፤ ከአምና ጀምራችሁ ለማድረግ ብቻ

ያይደለ ነገር ግን ለማሰብ ደግሞ አስቀድማችሁ የጀመራችሁት ይህ ይጠቅማችኋልና፤

አሁንም ለማሰብ በጎ ፈቃድ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እንዳላችሁ መጠን

መፈጸም ደግሞ ይሆን ዘንድ፥ ማድረጉን ደግሞ ፈጽሙ።’’ 2.ቆሮ.8፥10-11 

መማር አንድ ሲሆን የተማሩት በተግባር ማዋል ደግሞ ሌላ ነው። አንድ አማኝ የእግዚአብሔርን

መርህ ተምሮ በሕይወቱ የማይተገብር ከሆነ ትልቅ ችግር ውስጥ ነው። ምክንያቱም ከሥራ የተለየ እምነትየሞተ ስለሆነ ነው። ጌታ ሲያስተምረን በንፋስ ጊዜ የሚቆመው ቤት ቃሉን ሰምቶ የሚያደርግ እንጂ ሰምቶ

የማያደርገው ወይም በተግባር ላይ የማያውለው አይደልም። 

የስህተት ትምህርት ንፋስ ወዲህና ወዲህ የሚያደርገው መሰረት የሌለውን አማኝ በተማረው

ትምህርት የማይኖርና የማይጸና ነው። ቃሉን እንደሚሰማበት መጠን አንድ አማኝ ያንን ደግሞ በሕይወቱ

ለመኖር ለመተግበር ሊተጋ ይገባዋል። ቃሉን ሰምታችሁ የምታደርጉ እንጂ ራሳችሁን የምታስቱ አትሁኑ ብሎ

ቃሉ ይመክረናል። ራሱን የሚያስት አማኝ የሰማውንና የተማረውን የጌታን ቃል የማይኖር በሕይወቱ

የማይተረጉም ሰው ነው። 

የቆሮንጦስ ስዎች ጳውሎስ ቃሉን እንደሚያስቡት ያረጋግጥላቸውና ነገር ግን ቃሉን መተግበር

ላይ ግን የሚጎላቸው ነገር እንዳለ ይነግራቸዋል። ዛሬ ብዙ አማኞችን ያጠፋው አለማወቅ ሳይሆን ያወቁትን

እውቀት አለመኖር ነው። ይህ ሁሉ ነገር ከአንድ አማኝ መንፈሳዊ ኑሮ ፍላጎት የሚመነጭ ነው። መታዘዝ ወይም

አለመታዘዝ ማለት ነው። መታዘዝ ደግሞ እግዚአብሔር የሚያስደስት ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር

የምንገልጥበት ብቸኛው መንገድ ነው። “ ብትወዱኝ ትዕዛዛቴን ጠብቁ” ብሎ ይነግረና። 

Page 109: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 109/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

109ww.tlcfan.org

 

የቆሮንጦስ ስዎች ይህ ለማድረግ ማሰብ በፊት ነበራቸው አሁንም ጳውሎስ ይህ ፍላጎት እስከ

አሁን እንዳላቸው ይናገርና። ለምንና እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው ይነግራቸዋል። መታዘዝ ከመንፈስ በፍላጎት

የመነጨ ካልሆነ ትልቅ ችግር ነው። ስለዚህ የሰማነውን፣ ያወቅነውንና የታዘዝነውን በሕይወታችን በመተርጎም

እንኑረው። ጠላትን የሚያበሳጨው መስማት ሳይሆን የሰሙትን ማድረግ ነው። “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ

ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤

” ራእይ.12፥17 

“ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ

ማንም ቢሆን፥ እምነትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።’’ 1.ጢሞ.5፥8 

9.  ቅን የሆነ መረዳት 

‘’በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ

እንደሌለው መጠን አይደለም።13 ለሌሎች ዕረፍት ለእናንተም መከራ

እንዲሆን አይደለም፥ ትክክል እንዲሆን ነው እንጂ፤14 የእነርሱ ትርፍ

ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ

የእነርሱን ጉድለት ይሙላ፤ በትክክል እንዲሆን፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ። 

15 ብዙ ያከማቸ አላተረፈም፥ ጥቂትም ያከማቸ አላጎደለም።..’’ 2.ቆሮ.8፥12-14 

ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን የሚደረገው ይህ መባ አማኙን ወደ ሚገባው መንፈሳዊ እድገትና

ከማንኛውውም ጉድለት አካሉን ለማውጣት እንደ ሆነ ያውቃል። ስለዚህም ከብሉ ኪዳኗ በሙሴ ስር በምድረ

በዳ መናን ከሰማይ ከተቀበለችው ጉባኤ / ቤተ ክርስቲያን ጋር በማያያዝ መንፈሳዊ ምክሩን ይለግዛቸዋል። ነገር

ግን የቆሮንጦስ አማኞች መካከል እነርሱ በመስጠታቸው ሌሎችን ባለጠጋ ሲያደርጉ እነርሱ ደግሞ ደሃ የሚሆኑ

የመሰላቸው ሰዎች ነበሩ። ስለዚህ ከላይ ያለውን ቃል ጳውሎስ ጻፈላቸው። 

አማኝ መስጠቱ አንድን ሰው ወይም እርሱን መከራ ውስጥ ሌላውን ደግሞ በረከት ውስጥ

እደሚያስገባ አድርጎ ካሰበ፤ ያ ግለሰብ ትክክለኛ መስጠት መርሕ እየተከተለ እንዳልሆነ ሊያውቅ ይገባዋል። ቃሉ

እንደሚል ብዙም ያከማቸ አላተረፈም ጥቂትም አከማቸ አላጎደለም። እንደሚል በመንፈስ የሆነ መስጠትና

መቀበልም እንዲሁ ነው። እንደ አንዳድ እምነት እንደ ጎደላቸው መናውን ከሚገባቸው በላይ እንዳከማቹት

እስራኤላዊያን በምድረ በዳ የሆነባቸውን እናውቃለን። ያከማቹት ተላ ለእነርሱም ሆነ ለሌላው አልተቀመም። 

Page 110: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 110/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

110ww.tlcfan.org

 

ከዚህ አይነት እግዚአብሔር ይጠብቀን። ስለዚህ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን የሚስጥም

አያጎድልም የሚቀበልም አያተርፍም። ሁሉ ለጌታ ሥራና ቅዱሳን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲያድጉ

ለማድረግ የሚውል ስለሆነ ነው። በኢየሩሳሌምና በመቄዶንያ ያሉ አማኞች ይህ ነገር ስለገባቸው መስጠትን

የሕይወታቸ አንድ ክፍል አድርገው ሰለተቀበሉና ይህንንም እውነት በደስታ የሚያደርጉ አማኞች በመሆናቸው

ነው።

ዛሬ በዚህ ዘመን ያለን መስጠት ከፍቅር የመነጨ መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን እኛ

በመስጠታችን ሌሎችን ባለጠጋ እኛን ደግሞ ደጋ ላይ እየጣልን ያለን እንዳይመስለን መጠንቀቅ ማወቅ

ይገባናል። ደግሞ ይህ መስጠታችን ደሃ የሚያደርገን ከመሰለን መስጠትን አቁመን። የጌታ አይነት የሆነ መስጠት

በሕይወታችን እንዲመጣ ልንማር በጸሎአት ይህን ጸጋ ከጌታ ልንቀበልና ትጋትን ሁሉ ልናሳይ ይገባል። 

ጳውሎስ ይህ ነገር ከዘጸ.16 በመነሳት አስተማረ። ሕዝበ እስራኤል መባን መስጠት

ከመጀመራቸው በፊት ይህን ብዙ በመሰብሰብ ማትረፍ እንደሌለና ትንሽም በመስብሰብ ማጉደል እንደሌለ

ከእግዚአብሔር ተምረው ነበር። ይህን በመማራቸው ለመቅደሱ ሥራ የሚውል መባ እንዲያመጡ ሲጠየቁ

ከተጠበቀው በላይ በማምጣት እንዲችሉ አድርጓቸዋል። ይህ ሕይወት ለእኛም ይብዛልን። 

10. በስርዓት ገንዘብን መጠቀም 

“16 ነገር ግን በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያንን ትጋት የሰጠ አምላክ ይመስገን፤17 ምክራችንን

ተቀብሎአልና፥ ትጋት ግን ስለ በዛበት ወዶ ወደ እናንተ ይወጣል።18 ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል

ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤19 ይህም ብቻ

አይደለም ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ

ቸር ሥራ ከእኛ ጋር እንዲጓደድ በአብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ተመረጠ።20 ስለምናገለግለው

ስለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን፤21 በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን

በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና።22 ብዙ ጊዜም በብዙ ነገር መርምረን ትጉ

እንደ ሆነ ያገኘነውን፥ አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ

የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን።23 ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር ስለ እናንተ

አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖርም የአብያተ

ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።24 እንግዲህ የፍቅራችሁንና ስለ እናንተ

ያለውን የትምክህታችንን መግለጫ በአብያተ ክርስቲያናት ፊት ለእነርሱ ግለጡ።”

2.ቆሮ.8፥16-24 

Page 111: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 111/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

111ww.tlcfan.org

 

ጳውሎስ ከላይ ባለው ጥቅስ መሰረት ለቆሮንጦስ ሰዎች የሚላቸው። ገንዘባችሁን ለማን

እንደምትሰጡ ማወቅ አለባችሁ ነው። እኛ ሰዎች ገንዘብ እዲሰበስቡ ስንልክ የምንልከው ከረጢት የያዙ ሰዎች

ብቻ ሳይሆን በወንጌላቸው የተመሰከራለቸውንም ሰዎች ነው አላቸው። ይህ ብቻ አይደለም ቲቶ ለቅዱሳን

በሚሆን ገብዘብ መሰብሰብ ሥራ ላይ የተሰማራው ከጌታ ዘንድ ትጋት ስለበዛለት አንደ ሆነ እንጂ እንዲሁ

በስዎች ምርጫ ብቻ እንዳልሆነ እንዲያዉቁም ነበር።

ምክንያቱም ሰው ገንዘብን በአምላኩ መንፈስ ተመርቶ የማያሰባስብ ከሆነ የአምላኩን ፍቃድ

ማከናወን አይችልም። በጌታም በሰውም የተመረጠ የገንዘብ ሰብሳቢና አስተዳዳሪ በጌታም በሰውም ፊት ያለ

ነቀፋ ማገልገል ይችላል። እንደ አሮን በስሜትና በሰዎች ፍርሃት በመገፋፋት የሕዝብን የጆሮና የእጅ ወርቅ

አስወልቆ ጥጃ አይደራም። አሮን በዚህ አገልግሎት ተሰማርቶ ነበር ጣጃን በሰዎች የጆሮ ጉትቻና ወርቅ ሰርቶ

ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው እንዳለ ሁሉ ዛሬም የብዙዎችን ወርቅ እያስወለቁ ራሳቸውን በጌታ የተባረኩ

ለማስመሰ የቤታቸውን ኑሮና ሥጋዊ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉ አሳች መሪዎችም ብዙ ናቸውና ተጠበቁ። ገንዘብ

የሚጠይቃችሁ ማን እንደሆነና? ለምን እንደ ሆነ? ከየት ተልኮ እንደ ሆነ? ብቻውን ይምጣ ወይም

ከተመሰከረለት ወንጌል ሰባኪ ወይም አስተማሪ ጋር ይምጣ አይምጣ ማየት መመርመር ይገባናል። 

መንፈሳዊ ነገር የሚዘሩ ሁሉ ሥጋዊ ነገር እንዲያጭዱ ጌታ በሕጉ ይደነግጋል። እኛ አማኞች

በመንፈሳዊ ነገር የሚያገለግሉንን በሥጋዊ ነገር ልናገለግላችው ፈጽሞ ይገባል። ከጌታ የተላከ ብቻ ገንዘብን

በታማኝነት መያዝ ብቻ ሳይሆን ገንዘብን ጌታ እንደሚያዝ ይጠቀማል፣ ያከፋፍላል እንጂ አይቀብርም። አገሬ

በሰማይ ነው የሚል መሪና ምዕመን ሁሉ በቅዱሳን ብር ወንጌልን ይስብካል እንጂ ሕንጻ በምድር ላይ አይገዛም።

የሰዎችን አዳራሽ እየተከራየና በእምነት እየወረስ ቃሉ በጊዜውም አለጊዜውም ያገለገለግላል። 

ኢየሱስ በቅዱሳን ብር ፍጥረታዊ ሕንፃ  ቤተ  ርስቲያን ሲያስራ የትም ቦታ አይታይም

ሃዋርያትም የትም ቦታ ቤተ ክርስቲያን ሲገዙ ሆነ ሲገለቡ አይታይም። ነገር ግን አንዳንድ አማኞች ቤታቸውን

ለቤተ ክርስቲያንነት ስጥተዋል። እውነትን በመያዝ እስከ ሞት ድረስ በመቁረጥ ሙኩራብ ገብተው ወንጌልን

ሰብከዋል። ዛሬም የሚያስፈልገን ይህን ብቃት የሚሰጠን መንፈስ ነው። ሄደን መስበክ ስላቃተን በቅዱሳን ብር

ቤት መስራትና ሃይማኖታዊ ስርዓት ማስፋፋት አይደለም። በገንዘቡ ወንጌልን ስበኩበት ድሃውን እርዱበት

እምነት የጎደለውን በእምነቱ አበርቱበት ይላል የጌታ መንፈስ። የጌታን ሕዝብ ገንዘብ በስርዓት መጠቀም

እንድንችል ቃሉን ማወቅና መጸለይ ይገባናል።

Page 112: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 112/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

112ww.tlcfan.org

 

ዛሬ የአማኞች ችግር በብዙ ስፍራ የገንዘብ አስተዳደር ነው። ይህ ሁሉ ብጥብጥና ጸብ ገንዘቡ

የሚገባው ሥራ ሳይሰራበት ሰለተከማቸ የገንዘቡ ክምችት በስዎች ውስጥ ምኞትና ስስትን ስለሚፈጥር ነው።

ጌታ ከዚህ ሁሉ ይጠብቀን። የጌታ መባ ውስጥ እጁን የሚስድ ሁሉ የይሁዳ እድል ፈንታ ያገኘዋል።

እንደሚገባውም የጌታን ሃብት ያልተጠቀመ ወይም አለበለዚያም ለሚሰራበት ያልሰጠ በጌታ ፊት ይጠየቃል። 

“እነሆ፥ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥

የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቶአል።” ያቆብ.5፥4

11.የመስጠት ቅንዓት 

“1 ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት ልጽፍላችሁ አያስፈልግምና፤

2 በጎ ፈቃዳችሁን አውቄአለሁና፤ ስለዚህም። አካይያ ከአምና ጀምሮ

ተዘጋጅቶአል ብዬ ለመቄዶንያ ሰዎች በእናንተ እመካለሁ፥ ቅንዓታችሁም

የሚበዙቱን አነሣሥቶአል።3 ነገር ግን ለእነርሱ እንዳልሁ፥ የተዘጋጃችሁ ትሆኑ

ዘንድ በዚህም ነገር ስለ እናንተ ያለው ትምክህታችን ከንቱ እንዳይሆን

ወንድሞችን እልካለሁ፤4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡ፥

ያልተዘጋጃችሁም ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ፥ እናንተ እንድታፍሩ

አላልንም እኛ ግን በዚህ እምነታችን እንድናፍር አይሁን። 2.ቆሮ.9፥1-4 

የመቄዶንያ ስዎች በድህነታቸው ሳሉ ለመስጠት ያለቸው ፍላጎትና ቅንዓት ሌሎችን አማኞች

አነሳሳ። ይህ አይነት የመስጠት ተሃድሶ ቤተ ክርስቲያን ያስፈልጋታል። ነገር ግን መጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን

የጌታን ብር እንዴት መጠቀም እንዳለባት በደብ መገንዘብ ይኖርባታል። የመቄዶንያ ሰዎች ሰጪዎች ብቻ

ሳይሆኑ በመንፈሳዊው የመስጠት ኑሯቸው ብዙዎችን የሚያሳፍሩ ናቸው።

ዛሬም እንደዚህ አይንት ሰዎች እንዲያበዛልን ከጌታ የተላክን ባሪዎች ሁሉ ጸሎታችን ሊሆን

ይገባል። ይህን አይነት ነገር በመቄዶንያ አማኞች የጨመረው ጌታ ነው። የተቀበሉት ጸጋና መንፈስ ነው። ይህ

ብቻ አይደለም እነርሱ ራሳቸው ይህን ጸጋ በሕይወታቸው ለመለማመድ ራሳቸውን ለጌታም ለሰውም ሁሉ

የሰጡ ናቸው። ጌታ ይህን ጸጋ ዛሬ ለትሁታን ይሰጣል። የመስጠት ቅንዓት በያንዳዳችን ላይ ይመጣ ዘንድ ጸሎቴ

ነው። 

Page 113: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 113/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

113ww.tlcfan.org

 

12.ሳይጎተጎቱ መስጠት 

‘’እንግዲህ እንደ በረከት ሆኖ ከስስት የማይሆን ይህ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ

አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን

በረከት አስቀድመው እንዲፈጽሙ ወንድሞችን

እለምን ዘንድ እንዲያስፈልገኝ አሰብሁ።’’ 2.ቆሮ.9፥5

ጳውሎስ አስቀድሞ የቆሮንጦስን ስዎች እንደሚገባ እንዲስጡ ይመክራቸዋል። ጳውሎስ ብዙ

ዋጋን የከፈለባቸው እነዚህ አማኞች ሳይጎተጎቱ ሊስጡ እንደሚገባቸው አስተማራቸው። ይልቁንም አንዳዶች

ከመቄዶንያ ድንገት ከገንዘብ ሰብሳቢዎች ጋር ወደ እናንተ ሊጎተጉቱ ከመጡ ያሳፍራል እያለ ይመክራቸዋል።

ሰለዚህ እነርሱ ከመምጣታቸው በፊት ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ ይልቁም ተስፋ አስቀድማችሁ ስለገባችሁ

አስቀድማችሁ ገንዘቡን አዘጋጅታችሁ ጠብቁ ይላቸዋል።

ዛሬ ለመስጠት እንደ ቆሮንጦስ አማኞች የምንጎተጎት አማኞች አንሁን። በደስታ በፍላጎት

እንስጥ ተስፋ ከገባን ደግሞ ተስፋ የተገባለት ሊሰበስብ ሳይመጣ ሰብስበን ለመስጠት ተዘጋጅተን እንጠብቅ።

ጌታ በዘራነው መጠን ያሳጭደናልና። በጌታ ብቻ እንታመን ሰውንና ሁኔታዎችንን አንመልከት። ሁኔታዎችን

የሚመለከት ዘር መዝራት ትቶ ዘሩን ቀብሮ ፍሬ ቢስ ይሆናል። 

13. የመስጠት በረከት 

“ይህንም እላለሁ። በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥

በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል፣’….8-9 በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥

ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ

ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ

ይችላል።10 ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም

የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ

ያሳድጋል፤11 በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን

ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ።

12 የዚህ ረድኤት አገልግሎት ለቅዱሳን የሚጎድላቸውን

Page 114: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 114/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

114ww.tlcfan.org

 

በሙሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና፥ ነገር ግን ደግሞ

በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይበዛል።’’ 2.ቆሮ.9፥6-12 

ከላይ ያለ ጥቅስ በደንብ አድርጎ የመስጠትን በረከት ያስቀምጣል። ነገር ግን ልናውቅ የሚገባው

ይህን በረከት ለማግኘ ብሎ መስጠት ስሕተት መሆኑን ነው። ምንም እንዃን ጌታ የዘራነውን በእጥፍ

እንደሚያሳጭደን ብናውቅም የመስጠታችን ቀስቃሽ ሊሆን የሚገባው የምናገኘው ትርፍ ሳይሆን

የእግዚአብሔር መንፈስና ጸጋ ለእርሱ ያለን ፍቅር ለቅሱሳን ያለን ፍቅር ነው። 

14.የመስጠት ልብ 

‘’እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ

ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።’’ 2.ቆሮ.9፥7 

ሰው ለመስጠት ሲነሳ የመነሻው ሃሳብ ሊሆን የሚገባው ደስታና ንፁ የመስጠት የልብ ፍላጎት

ነው። ሰው በልቡ ደስ ሳይለው ቢሰጥ ስጦታው እርኩስ ነው። እግዚአብሔርን ደስ አያሰኝም። ሰው በግድና

በሃዘን ምንም አይነት ነገር ለሰውም ሆነ ለእግዚአብሔር መስጠት አይገባውም። ይህን የሚያደርግ ሰው አሻሮን

ይበቅላል ብሎ የሚዘራን ሰውን ይመስላል። 

ሰው ንጹህ የሆነ የመስጠት ልብ ሊኖረው ይገባል። ንጹህ ልብን የሚፈጥረው ደግሞ

የእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ ነው። ሰው ቃሉን ማጥናት የመንፈስን ሙላት ደግሞ እለት ከእለት ለመሞላት

በቅድስና ለመመላለስ የጌታን ትዕዛዛት መጠበቅ ይገባዋል። ይህን ከሚያደርግ ሰው የሚወጣ ማንኛውም

አይነት ስጦታ እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ ነው። ልባችን ላይ እግዚአብሔር የሚያስቀምጠውን ነገር ማድረግን

እንለማመድ። የእግዚአብሔር መንፈስ አሁንም ቢሆን አማኞችን እንደሚገባ እንዲስጡና በረከትን እንዲወርሱ

ለማድረግ በልብ ውስጥ ሆኖ ይናገራል፣ ይመራል፣ ያሳስበናል። እኛ ከምናስበው ሁሉ በላይ የእግዚአብሔር

መንፈስ የሚያሳስበን ይበልጣል። ለድምጹ እንድንታዘዝ ጌታ ይርዳን። 

15. ለቅዱሳንና ለእግዚአብሔር የሚበዛ ምስጋና 

‘’የዚህ ረድኤት አገልግሎት ለቅዱሳን የሚጎድላቸውን በሙሉ የሚሰጥ ብቻ

አይደለምና፥ ነገር ግን ደግሞ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይበዛል፤

Page 115: Tithe & Law of Earth

7/29/2019 Tithe & Law of Earth

http://slidepdf.com/reader/full/tithe-law-of-earth 115/115

የምድር ሕግና አሥራት  2017 

13 በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ፥ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ

ስለሚሆን መታዘዝ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና እግዚአብሔርን

ያከብራሉ፥14 ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ

ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።

15 ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።’’ 2.ቆሮ.9፥12-15 

መልካም ልግስና በበዛበት የእግዚአብሔር ሥም ከፍ ከፍ ይላል። ዛሬ አማኞች ገንዘብ

የማያባክኑ እንጂ ለጋሶች እንደሆኑ የትም አይሰማም፣ እንደውም በውጭ ባሉት የሚባለው ገንዘብህን መያዝ

ከፈለክ አማኝ ሁን ነው። ይህ የሚያሳየው ጠንቃቃነታችንን ብቻ ሳይሆን ንፉግነታችንንም ነው። በውጭ ያሉ

እኛ የጌታ እንደ መሆናችን መጠን እንደ ጌታችን ሰጪዎች እንደ ሆንን በሥራችን ሊያውቀን ይገባል። ዛሬ የሚሰጥ

በመጠፋቱ ብዙ ለእግዚአብሔር የሚገባ ምስጋን ቀንሶ እናያለን። ዛሬ ምስጋና ለጌታችን እንዲበዛ ለጋሶች

እንሁን። በስሜት የሚገፋፋ ለጋስ ሳይሆን ገብቶን ተረድተን የምንለግስ ሰጪዎች እንሁን። ለልግስና የግድ

ባለጠጋ መሆን እንደማያስፈልግ የተማርን ይመስለኛል። 

እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የሚሹትን ይወዳል። ለዚህም ነው እግዚአብሔር ከመስጠት ጋር

የተያያዙ የተለያዩ ሕግጋትን ለአማኞች የሰጠው። ይህች መጽሐፌ ከሞላ ጎደል የእግዚአብሔር እይታ በጥቂቱ

ፈንጥቃለች ብዬ አምናለሁ። ጌታ በነገር ሁሉ ማሰዋሉን ከታዛዥነት ጋር ይሙላባችሁ፣ ያብዛላችሁ። አስጀምሮ

ላስጨረሰኝ ለእግዚአብሔር መንፈስ ክብርና ምስጋና ከሁሉ አስቀድሞ ይሁን። መለኮያዊውን መስጠት

የሚያመጣው የጌታ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።