Semir Kedir Biniyam Sahlu Yonas Andualem ሚethiopianforethiopian.org/onewebmedia/ሀሃገ...

25
መጋቢት 2007 ዓ.ም አራተኛ አመት 4ኛ እትም ቁጥር 11 Third year 4th Edition volume 11 March 2015 ሰሚር ከድር Semir Kedir ቢንያም ሳህሉ Biniyam Sahlu ዮናስ አንዱአለም Yonas Andualem ሰልሞን Mikey solmon አማኑኤል አሰፋ Amanuil Assefa የማነ አበራ Yemane Abera ዳዊት መላኩ Dawit Melaku ጴጥሮስ ተሰማ Petros Tessema ሩት መኮንን Rute Mekonene አርሴማ ዮናስ Arsema Yonas ሞሃመድ አሊ አብዲ Mohammed Ali Abdi ዳዊት ባራኪ Dawit Baraki ኤሚ ተስፋሁነኝ Emy Tesfahunge ሊድያ አስፋው (ትእግሰት ጀማል) Lidya Asfawe(Tigest jemal ) ሚካኤል አሰፋ Michael Asefa ዜድ በቀለ Zed Bekele ሚኪያስ አለነህ መንግስቱ Mikias Alene Mengistu ህሊና ዳዊት Hilina Dawit ዮናስ በረከት Yonas Bereket ፈቃደ እንደሻው Fekade Endeschaw ካሳ ኤባ ያቤሎ Kassa Eba Yabelo ሳሙኤል ደመረ Samuel Demera ምንዋር አብዱል ዋህድ ከማል Minewer Abdulwahid Kemal

Transcript of Semir Kedir Biniyam Sahlu Yonas Andualem ሚethiopianforethiopian.org/onewebmedia/ሀሃገ...

መጋቢት 2007 ዓ.ም አራተኛ አመት 4ኛ እትም ቁጥር 11 Third year 4th Edition volume 11 March 2015

ሰሚር ከድር Semir Kedir ቢንያም ሳህሉ Biniyam Sahlu ዮናስ አንዱአለም Yonas Andualem ሚኪ ሰልሞን Mikey solmon

አማኑኤል አሰፋ Amanuil Assefa የማነ አበራ Yemane Abera ዳዊት መላኩ Dawit Melaku

ጴጥሮስ ተሰማ Petros Tessema ሩት መኮንን Rute Mekonene አርሴማ ዮናስ Arsema Yonas ሞሃመድ አሊ አብዲ Mohammed Ali Abdi

ዳዊት ባራኪ Dawit Baraki ኤሚ ተስፋሁነኝ Emy Tesfahunge ሊድያ አስፋው (ትእግሰት ጀማል) Lidya Asfawe(Tigest jemal ) ሚካኤል አሰፋ Michael Asefa ዜድ በቀለ Zed Bekele

ሚኪያስ አለነህ መንግስቱ Mikias Alene Mengistu ህሊና ዳዊት Hilina Dawit ዮናስ በረከት Yonas Bereket ፈቃደ እንደሻው Fekade Endeschaw

ካሳ ኤባ ያቤሎ Kassa Eba Yabelo ሳሙኤል ደመረ Samuel Demera

ምንዋር አብዱል ዋህድ ከማል Minewer Abdulwahid Kemal

Inhalt ................................................................................................................................................................. 1

ከአዘጋጆች ለአንባብያን .................................................................................................................................... 3

From Us to You ........................................................................................................................................ 4

ርእሰ አንቀፅ .................................................................................................................................................. 5

ወያኔና አገዛዙ ............................................................................................................................................... 8

ወያኔና መድሎቹ ............................................................................................................................................ 9

Im Wandel der Zeiten ................................................................................................................................. 9

የወያኔ ግፍና መከራ ...................................................................................................................................... 10

ዲሞክራሲው የታለ?የሀይማኖት ነፃነቱስ? ............................................................................................................ 10

ማዕከላዊ እስር ቤት(ምድረ ሲዖል) ................................................................................................................... 11

በደም የጨቀየው የወያኔ ሥርዓት ..................................................................................................................... 13

ነፃነት ........................................................................................................................................................ 13

ወያኔን ለምን ጠላሁ ...................................................................................................................................... 14

FORCED EVICTION AND ARBITRARY ARREST : Current Ethiopia ............................................................. 15

ዓላማው ምንድን ነው ? ............................................................................................................................... 17

እኛንስ ማን ገዝቶን ይሆን ? ........................................................................................................................ 17

ካንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ .......................................................................................................................... 18

ፍርድ ቤቶችን ለፍርድ የሚያቀርብ ማን ነው ? ................................................................................................ 19

ስለ ኢትዮጵአኖች ......................................................................................................................................... 20

አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ................................................................................................................ 20

የሰሞኑ ወግ ................................................................................................................................................ 22

አድዋ ........................................................................................................................................................ 23

ነጻነት… ነጻነት… ነጻነት… ................................................................................................................................. 23

ከአዘጋጆች ለአንባብያን

ውድ የሃገሬ ታዳምያን! የናንተው የሆነችው የሃገሬ መፅሄት ሀ...ሁ ብላ በእናንተው ድጋፍ ይኸው ሶስተኛ አመቷን አክብራለች ይህ ሶስተኛው አመት ሶስተኛ እትማችን ነው፡፡ ለዚህም በሃገሬ አዘጋጆች ስም ልባዊ ምስጋናችን የበዛ ነው፡፡ ሃገራችን ኢትዮጵያ የሁላችን መኖርያ እንጅ ጥቂት የወያኔ መሪዎች እንደፈለጉ የሚሆኑባት ሃገር አይደለችም፤ አትሆንምም፡፡ ለዚህም እኛም በተቻለን አቅም ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረሰ ያለውን በደል ለአለም መንግስታት ለማሳወቅ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የምትሰጡን አስተያየቶች ስራችንን በበለጠ አጠናክረን እንድንሰራ ስለሚያደርገን በኛ ላይ ያላችሁን ቅሬታም ሆነ ጠንካራ ጎን በማሳየት ድጋፋችሁን እንድትለግሱን በአክብሮት ጭምር ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ውድ ታዳምያን ሃገሬ መፅሄት ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነፃ የሆነች መድረክ መሆኗን በአፅንኦት ለመግልፅ እንወዳለን፡፡ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ በነፃነት በማሳተፍ ሁሉም የበኩሉን ለሃገራችን ኢትዮጵያ ይጠቅማል ብሎ የሚያስበውን ሃሳብ ሁሉ በነፃነት ማንሸራሸር የሚችልባት መድረክ እንደሆነች ልንገልፅ እንወዳለን፡፡

እንደሁልጊዜው ሁሉ የሃገሬ መፅሄት PDF ኮፒዎችን በሙሉ በዌብ ሳይታችን www.ethiopianforethiopian.org ማግኘት እንደምትችሉ ሳናሳስብ አናልፍም፡፡

ውድ ታዳምያን፤

በዚህ መፅሄት ውስጥ ከርእሰ አንቀፅ ፣ሃተታዊ ዜናዎች እንዲሁም ሪፖርቶች በስተቀር ማንኛውም ፅሁፎች የፀሃፍቱ ሃላፊነት እንጂ የሃገሬ መፅሄት አዘጋጆች እንዳልሆነ ልንገልፅላችሁ እንወዳለን፡፡

መልካም ንባብ!

ሃገሬ መፅሄት አስተባባሪ ኮሚቴ

From Us to You

Dear readers, Hagere celebrated its third year with your full support, which makes our edition

number 10. On this special occation, we would like to thank you all for your endavor support. We are

rendering our best for the better of our land, Ethiopia. We wish to see an ideal Ethiopia, in which

human rights and democracy are treasured, as all of you do. That is why we are trying our best to

show the world about the tyranny of Woyane, E.P.R.D.F.

Please keep on writing us about our weaknesses and strengths, since your suggestions have great

value to us, to keep up our effort.

Dear readers, please note that hagere is free from all political parties. Every political party member

can participate and express its idea freely, which you believe benefit our beloved country.

As usual you can use our website www.ethiopianforethiopian.org to find all the PDF copies of

Hagere.

Dear Readers, “Kindly note that except editorial, news and reports, Hagere do not take responsibility

claim for the articles written by individuals.”

Sincerely

Hagere coordinating committe

ርእሰ አንቀፅ የወያኔ የምርጫ ቧልት

ዲሞክራሲ የሚባለውን ቃል መተንተንና በውስጡ የሚያካትታቸውንና ማሟላት የሚገባውን

መስፈርቶች ስናስብ እያንዳንዱ ዕሳቤ ጥልቅ የሆነ ማብራሪያ የሚጠይቅና ለተግባራዊነቱም የሰው ልጅ

ከተፈጠረበት ግዜ አንስቶ ባለፈባቸው የህብረተሰብና የታሪክ የእድገት ደረጃዎች እያበለፀጋቸው የመጣ

በትግልና በመስዋዕትነት ዕውን የሆነ የህብረተሰብ ግንኙነት ፣ አስተዳደራዊ ፣ አስተዳደራዊ ፣ ማህበራዊ

፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕምነቶች የነፃነትና ሰው የመሆን ትርጓሜ ዕውን ማድረጊያ ስርአተ

ህብረተሰብ ነው ፡፡

የሰው ልጅ በታሪክ ውስጥ በተጓዘባቸው ሂደቶች በጋርዮሽ ስርዓተ ማህበር ውስጥ የመገልገያና

የማደኛ መሳሪያዎችን ከድንጋይ ጠርቦ መስራት ከጀመረበት ግዜ አንስቶ በተደረጉ የስራ ክፍፍሎች

በጋራ በመኖር ከተሞችን በመገንባት ከአደን ባለፈ በእርሻ ስራም በመሰማራት አስተዳደርን ግድ የሚሉ

ሁኔታዎችን ፈጠሩ ፡፡ በነዚህም እድገቶች ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ አይነት ስልጣኔዎች

ዕድገት ማሳየትና የተሻለ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ዕውን አደረገ ፡፡

የሰው ልጅ ስልጣኔ የአባይን ወንዝ ተከትሎ ከተሞችን በመከተም ዛሬ ጥንታዊ ስልጣኔ ብለን

የምንጠራቸውን ለዛሬዋ አለማችን ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ብሎም ደግሞ ሳይንሳዊ

ዕድገቶች ከፍተኛ አስዋፅዖ ያበረከቱ ማኅበረሰቦች ፖለቲካዊ መስተዳደርን ጀመሩ ፡፡ እነዚህም

የተመሰረቱ አስተዳደሮች ሰፋፊ ግዛቶችን በመመስረት በንጉሳዊ አገዛዝ ኢኮኖሚያዊ መሰረቶቻቸውን

በማጠናከር ለአገዛዛቸው በወቅቱ አመቺ የሆኑ እንደ መንግስት የሚያቆያቸውን ህግጋት በማውጣት

የጦት ኃይሎችን በመገንባት የመገበያያ ገንዘብን ወይም ገበያ መወሰኛ ቁሶችን በመወሰን ግዛቶችን

በማስፋፋት ትልልቅ ለዕለ ሀያላን ለመሁን በቅተዋል ፡፡

ከነዚህም ጥንታዊ ልዕለ ሀያላን ሙከል ከባቢሎን ፣ ከፋርስና ሜዶን ፣ ከጥንታዊቷ የታላቁ

እስክንድር ግሪክ ፣ ከሮማ ፣ ከግብፅ ፈርዖን መንግስት ፣ የቻይና እና የንጉስ ዳዊት ዘመን እስራኤል

ብሎም የኢትዮጵያ የአክሱም ስርወ መንግስት ለዓለም ከነ ብዙ ጉድለቶቻቸውም ቢሆኑ ያበረከቱት

አስተዋፅዖ በቀላል የሚታይ አይደለም ፡፡ በነዚህ አገሮች ውስጥ በየዘመኑ ታላላቅ ፈላስፋዎች ፣ የስነ-

ህዝብ ልሂቃን ፣ የህግ አዋቂዎች ፣ የሂሳብ ሊቆች ፣ የህክምና ጠበብት ፣ የሥነ-ፅሁፍና የቴአትር ፀሀፌ

ተውኔቶች ፣ የሙዚቃ ሊቆችና የኢኮኖሚ ጠበብት ፈልቀዋል ፡፡ በዘመናቸውም ዛሬ ዓለማችን

ለደረሰችበት የዕድገት ደረጃ መሰረት ጥለዋል ፡፡ አሁን የሰው ልጅ ለደረሰበት ስልጣኔም ሀገራችን

ኢትዮጵያ ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክታለች ፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ካላት የገዘፈ ታሪክ ባሻገር በሁለቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች ያላት ቦታ

ትልቅ ከመሆኑም ባሻገር በቁርዓንና በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥም ተደጋግማ የተፃፈች ህዝቧም ተስፋ

የተሰጠው መሁኑ በራሱ ለጥንታዊነቷ ትልቅ ምስክር ነው ፡፡ ይህ ክብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ

ታሪክ በህዝቡ መሀል በመከባበር በመቻቻልና በመደጋገፍ ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተን

አስተሳሰብ በማስረፅ ይህ አስተሳሰብ ህብረተሰባዊ ባህል ሆኖ እስከዛሬ እንዲዘልቅ አስችሎታል ፡፡

ታዲያ ይህ ትስስር በቀላሉ ላይበጠስ አብሮ በመኖር በመጋባት በመዋለድ አንድ ራዕይ ሰንቆ አንድ

አገራዊ አስተሳሰብ በመፍጠር ለሀገር የላቀ ፍቅርን መሰረት በማድረግ የነፃነትን ፣ የመስዋዕትነትንና

በክብር ኖሮ በክብር ስለ ክብር ስለ ነፃነትና ስለ ሀገር ሰማዕት የመሆንን ጥልቅ አስተሳሰብ እውን ያደረገ

የማንነታችን ውጤትና መሰረት ነው ፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን በፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ታሪክ ውስጥ ያላት ስፍራ በቀላሉ የሚታይ

አይደለም ፡፡ አድዋ ላይ በአፄ ምኒሊክ ተመርቶ ከመላው ሀገሪቱ ተሰባስቦ በመዝመት ስለ ሀገርና

ስለነፃነት የተሰዉት አባቶቻችን በሰማዕትነታቸውና በጅገናቸው በዚያ የጦርነት ውሎ ድል የመቱት

ጣሊያንን ብቻ አልነበረም ነገር ግን የቅኝ ገዢዎችን የበላይነት ያንበረከከ ለፀረ ቅኝ ግዛት ትግልም ፈርን

የቀደደ በባርነትና በቅኝ ግዛት ለሚማቅቁ የአለማችን ህዝቦች ተስፋን የፈነጠቀና በትግልና

በመስዋዕትነት ነፃነትን መዋጀት እንደሚቻል ያስረገጠ አንፀባራቂ ድል ነበር ፡፡ ይህም ድል ከካሪቢያን

ጀምሮ በላቲን አሜሪካ በኢስያና በአፍሪካ የፀረ-ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴውን የጫረና የቀጣጠለ ከመሆኑ

ባሻገር ለአፍሪካ ደግሞ ሀገራችን ታጋዮችን ከማሰልጠን ገምሮ በነፃነት ትግሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ

በማበርከት የአፍሪካ አህጉር ነፃነትን የተጎናፀፈ ክፍለ ዓለም እንዲሆን አብቅታለች ፡፡

በዚህ ሁሉ የታሪክና የሰው ልጅ የስልጣኔ ዑደት ውስጥ አገራችን በታሪኳ ብዙ ጦርነቶችን

አስተናግዳለች ፡፡ በአውሮፓም ሆነ በተቀሩት ዓለማት እንደነበረው የርስ በርስ የስልጣን ሽኩቻዎች

በውጭ ሀይሎች ኢትዮጵያን የማዳከምና የመከፋፈል ከተቻለም የማጥፋት እቅድ በተለያዩ ጊዜአት

በተለያዩ ሀይሎች የሚረዱ ነገስታት መሳፍንት መኳንንትና ሱልጣኖች ብዙ ደም መፋሰስን ያስከተሉ

ውድያዎችን አካሂደዋል ፡፡ ኢትዮጵያችንም ልክ በአለማችን እንዳሉ ዕንደ ማናቸውም ሀገሮች

በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ መልከዓ ምድራዊና ባህላዊ ትስስሮችና በሀያላን መሀከል በሚደረጉ

ግጭቶች አልፋ የተፈጠረችና እንደ ጠላቶቿ ሀሳብና እነደ ከሀዲ ቅጥረኛ ጠባብ ልጆቿ ምኞትና ተረት

ተረት ባትጠፋም ብዙ ግዛቶቻችንን በግፍ ተነጥቀን ዛሬ የቀረችልን ኢትዮጵያ ልትቀጥል ችላለች ፡፡

የለፉት ገዢዎች በግዛት ዘመናቸው በህዝብ ላይ የተለያዩ ግፎችን ፈፅመዋል ፡፡ የለፉትን ሶስቱን

ስርዓቶች እንኳን ብንመለከት በፊውዳላዊቷ ኢትዮያ የመሬት ስሪቱን የሀብት ክፍፍሉንና ሰው በሀገሩ

ላይ እንደ ዜጋ ከመከበር ወርዶ ሰው መሆን በራሱ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የገባበት ስርዓት ነበር ፡፡ ያም

ስርዓት በህብረተሰብ ሳይንስ ትንተና መሰረት አንድ ነገር የወለዳል ያድጋል ያረጃል ይሞታል ፡፡

ማንኛውም ስርዓትም ጥገናዊ ለውጦችን በማድረግ ከግዜው ጋር ካልተራመደና ጥያቄዎችን መመለስ

ካልቻለ በተፈጥሮ ህግ ስለሚገዛ እጣው ከዚያ የዘለለ ባለመሆኑ የንጉሱ አገዛዝ በየካቲቱ ህዝባዊ ዐመፅ

ላይመለስ ሊገረሰስ በቅቷል ፡፡

ይህንን ፊውዳላዊ ሥርዓት ከስሩ መንግሎ የጣለው በተማሪዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ ግቡን

መትቶ ንጉሱን ካስወገደ በኋላ በግዜው በእጃቸው መሳሪያ የነበረ የበታች መኮንኖች በሀይል የነጠቁት

የህዝብ የትግል ውጤት የነበረውን ድል የራሳቸውን ፍፁም ጨለምተኛ የነበረና የህዝብን ጥያቄዎች

ሁሉ የጨፈለቀ ፈላጭ ቆራጭ ስርዓትን በመመስረት የመሬት ስሪቱን ከፊውዳል የመሬት ከበርቴዎች

ወደ መንግስት ይዞታ በማዛወር መሬትን በመጨቆኛ መሳሪያነት መጠቀሚያ አደረገው ፡፡ ይህ አልበቃ

ብሎ ቀድሞ እንኳን በከፊል ይታዩ የነበሩ አንዳንድ የመንቀሳቀሻ መንገዶችን ጥርቅም አድርጎ

በመዝጋት ጭቆናውን አባባሱት ፡፡ በግዜው በተማሪዎች የተጀመረው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጥያቄውን

በማሳደግ ህዝባዊ መንግስት አሁኑኑ የሚል ጥያቄን በማንሳቱ ከግማሽ ሚሊዮን የማያንስ ሀገሬን እና

ህዝቤን የለውን አንድ ምርጥ ትውልድ በጠራራ ፀሀይ በቀይ ሽብርና በነፃ እርምጃ በመፍጀት

የተረፉትንም በየእስር ቤቱ በማጎር ቀሪዎቹንም አገር ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል ፡፡ በሀገሪቱ ታሪክ

ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ ሰቆቃን ማሰቃያ ቦታዎችን በማዘጋጀት በመፈፀም ሰውን መግደልና

ማሰቃየት ዕንደ መብት በህግ የታወጀበት ግዜ ነበር ፡፡ ይህ መንግስትም አፈናውንና ጭቆናውን

በማባባስ ሀገሪቱን በጦርነት እሳት ይማግዳት ገባ ይህ እድሜውን የማራዘሚያ አንዱ መንገዱ ነበር ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባካሄዳቸው ትግሎች የደርግ መንግስት ስልጣኑን

ለወያኔ አስረክቦ ቆራጡና ጀግናው በመባል የሚቆላመጠው መሪ ከውጭ ሀይሎች ጋር በተደረገ ድርድር

ወደ ዚምባቡዌ ሲፈረጥጥ አብዛኞቹ ባለስልጣናቱ ደግሞ ዛሬ ዒትዮጵያን እየገዛ ላለው ለወያኔ

እጋቸውን ሲሰጡ አንዳንዶቹም በተለያየ ሀዴ ከሀገር ሊፈረጥጡ ሲሉ ተይዘው ዘብጥያ ወርደዋል ፡፡

ይህኛው የስልጣን ሽግግር ኢትዮጵያውያንን ያገለለና በውጭ ሀይሎች የተቀነባበረ ሲሆን የሀገሪቱ

ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነትን ህዝቡንና ያገባኛል የሚሉ ሀይሎችን ሁሉ ያገለለ የሀገሪቱ ታሪካዊ

ጠላቶች ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ በኢትዮጵያና በህዝቧ ላይ በሊግ ዖፍ ኔሽን ከተፈፀመው

የበለጠና የከፋ ክህደት የአለም መንግስታትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፈፀሙበት ሁኔታ

የስከተለ ነበር ፡፡

እነዚህን ሶስት አገዛዞች ያነሳሁበት ምክንያት በመጪው ግንቦት ወያኔ አካሂደዋለሁ ብሎ

የሚለፍፍለት የቧልት ምርጫ ምን ዓይነት ይዘት ይኖረዋል የሚለውን ለመመልከት ነው ፡፡ንጉሱን

ትተን ደርግንና ወያኔን የተመለከትን እንደሆነ ሁለቱን ስርዓቶች የሚለያያቸው ነገር ቢኖር ደርግ ሁሉን

ነገር በአዋጅ ማገዱ ሲሆን ወያኔ ደግሞ በአዋጅ ሁሉን ነገር ፈቅጃለሁ ቢልም በግብር ግን በጣም አፈኝ

ስርዓትን ማራመዱ ነው፡፡

ወያኔ ለስሙ ዲሞክራሲን አራምዳለሁ ፌደራላዊ ስርዓትን መስርቻለሁ የፕሬስ ነፃነት ተከብሯል

የብሄር ብሄረሰብ መብት ተከብሯል በማለት በዜና አውታሮቹ ሌት ተቀን ይለፍፋል ፡፡ አንፃራዊነት

የተመለከትን እንደሆነ በመጀመሪያ የአገዛዙ ዘመን የተሸለ የሚባሉ ሁኔታዎች ነበሩ ፡፡ በ1997

በተካሄደው ምርጫም ሽንፈትን ከተከናነበ በኋላ ምርጫውን በጉልበት ቢነጥቀም ብዙዎችን

በመግደልና በማሰር ሀገሪቱንም ትልቅ እስር ቤት አድርጓታል ፡፡አሁን በሀገሪቱ ጦር ሀይሉን ምርጫ

ቦርድን ፍርድ ቤቶችን የዜና አውታሮችን በተቆጣጠረበት ሁኔታ ምን ዓይነት ነፃ ምርጫ ነው

የሚካሄደው? ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች በታሰሩበት ሁኔታስ ምርጫው ነፃና ዲሞከራሲያዊ የሆናል

ማለት ምንን ለማታለል ነው? ወያኔ እድሜውን በዚህም ምርጫ ማራዘም ነውና የሚፈልገው የፖለቲካ

እስረኞች እና ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እስካልተፈቱ ድረስና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች

የታገዱት ጭምር ካልተፈቀደላቸው ምርጫውን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ቦይ ኮት ማድረግ ጊዜ

የማይሰጠው ጉዳይ ነው ፡፡ በተደራጀና በተባበረ ክንድ ወያኔን ተባብረን እናስወግድ ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ወያኔና አገዛዙ

Binyam Sahlu, Thalmassing

በደደቢት በሻዕቢያ ተቀፍቅፎ የተወለደው ህወሀት

ወያኔ ክ 40 ዓመታት በፊት ይዞት የተነሳውን አላማ

ከግቡ ለማድረስ ባደረገው ጉዞ የኢትዮጵያን ህዝብ

የትግል ውጤት የሆነውን አንባገነኑን የደርግ ወታደራዊ

መንግስት ከስልጣን ያስወገደውን የህዝቡን ድል

በጠመንጃ ኃይል ከነጠቀበት ግዜ አንስቶ ላለፉት 23

ዓመታት በሀገሪቱ ለይ ያሰፈነው ፍፁም አንባገነናዊ

አገዛዝ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች

ፍፁም አሀዳዊ በሆነ መንገድ ሁሉን ነገር በመቆጣጠር

የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በተለያዩ መንገዶች

በመጠቀም ሀገሪቱን ቋንቋንና ብሄርን መሰረት ያደረገ

የፌደራል ስርዓት በመዘርጋት የጥላቻን ፕሮፖጋንዳ

በመንዛት በተወሰነ ደረጃ የተሳካለት በሚመስል

መንገድ የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካውን ሲያራምድ ባጅቷል

፡፡ ይህ የፖለቲካ አይዲኦሎጂው ጠባብ ዘረኛና ፀረ

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አቋም ላይ ያጠነጠነ

መሆኑና የራመዳቸው አቋሞች ካሰፈነው ስርዓትና

የፖለቲካ አካሄዱ አንፃር ለተመለከተው በ21ኛው ክፍለ

ዘመን እንዲህ በጣም ኋላ ቀር የሆነ የአፓርታይድ

አገዛዝን በህዝብ ላይ የጫነ ጨካኝ ስርዓት ነው ፡፡

ወያኔ የሀገሪቱን ቁልፍ የኢኮኖሚ አውታሮች

በመቆጣጠር በግዙፍ ኩባንያዎቹ በኩል የሀገሪቱን

ከ80% በላይ ኢኮኖሚ በመቆጣጠር ሀገሪቱን

ያለአግባብ እየዘረፈ ይገኛል ፡፡ ስለ ብሄር መብት ሌት

ተቀን እየለፈፈ የብሄሮችን መብት ከማፈን አልፎ

ከአንድ ብሄርም ባለፈ መንገድ የአንድ መንደር

(የአድዋ) ልጆች ሁሉን ነገር የሚቆጣጠሩበት ስርዓት

በማራመድ ላይ ይገኛል ፡፡ ይህም የሀገሪቱን ቁልፍ

የፖለቲካ ስልጣን ጠቅልለው በሞኖፖል በመቆጣጠር

አገሪቱን እንዳሻቸው እቀለዱባት ይገኛል ፡፡ ወያኔ

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት እያለ የሚጠራው ጦር

ልክ እንደ ፓርላማው ሁሉ ከ96% በላይ ከአንድ ብሄር

በመጡ ጀነራሎች የተሞላ መሆኑ ፣ የሀገሪቱ ብሄራዊ

የመረጃና ደህንነት ድርጅት የሚባለው የደህንነት ተቋም

ሙሉ በሙሉ ከአንድ አካባቢ ብቻ በመጡ የወያኔ

ሰዎች የሚመራና በነሱ ቁጥጥር ስር የወደቀ የድርጅቱን

አላማ ማስፈፀሚያ ተቋሞች ናቸው ፡፡ የፍትህ አካሉና

የህግ አስፈፃሚው ማለትም ፍርድ ቤቶችና የፖሊሱ

ሀይል የገዢውን አላማ ከማስፈፀም ያለፈ ምንም

ዓይነት ህግንና ስርዓትን የማስከበር ስራ የማይሰሩ

የአገዛዙ የአፈና ተቋም አስፈፃሚ አፋኝና በግፍ ንጹሀን

ላይ እየፈረዱ ብዙዎችን የስርዓቱ ሰለባ ያደረጉ ተቋማት

ናቸው ፡፡ የወያኔ አለቃ የነበረው ለገሰ ዜናዊ (መለስ)

ከ20 ዓመታት በላይ የገዛትን ሀገር ፕሬዚዳንት ሆኖ

በሚመራው ቡድን ስም አስተዳድረዋለሁ የሚለውን

አገር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ ፅፎ

14ኛዋን ክፍለ ሀገር ኤርትራን አስገንጥሎ እንደ ሀገርም

እውቅናን ከመስጠቱም በዘለለ ህዝቡንም በተቻለው

አቅም በዘርና በቋንቋ ከፋፍሎ የቀደውን ታላቋን

የትግራይ ትግሪኝ ሪፐብሊክ ሳይመሰርትና

ኢትዮጵያንም እንደ ምኞቱና እቅዱ ሳያፈርሳት

የኢትዮጵያ አምላክ ቀድሞት ወደማይቀርበት

ተሰናብቷል ፡፡

ባለፉት 23 የመከራ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ

በወያኔና በኦነግ ወይም ወያኔ ሰራሽ በሆኑ ህዝብ አፋጅ

ግጭቶች በተለያዩ ግዜያት የዘር ማፅዳትና የዘር

ማጥፋት ወንጀሎችን በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች

ከመፈፀም አልፎ በተለይ በአማራው ህዝብ ላይ

የሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በተጠና ዘዴ

የአማራ ሴቶች እንዳይወልዱ በመርፌ እስከማምከን

የደረሰ ወንጀል እየፈፀመ መሆኑና ይህንንም በፓርላማ

ተብዬ ዕጅ ከማውጣት የዘለለ ምንም ዓይነት አስተዋፅኦ

በሌለው ስብስባቸው ከጥቂት አመታት በፊት

የአማራው ህዝብ ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን በላይ

መቀነሱን በሪፖርት መልክ አቅርበዋል ፡፡ ክልል 5

እየተባለ በሚጠራው የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል

ማለትም በኦጋዴን አካባቢና ክልል 4 እያሉ በሚጠሩት

የኦሮምያ ክልል ከፍተኛ የሆነ አፈና ፣ ግድያና ስየል

(ቶርች) ማየትና መስማት ያደባባይ ሚስጥር ነው ፡፡

በነዚህ አካባቢዎች ልዩ ኮማንዶ ጦር በማዝመት በልዩ

ሀይል ውስጥ ደፋሪ ወታደሮችን በማዘጋጀት ሴቶችን

በባሎቻቸውና በልጆቻቸው ፊት መድፈር ከዚህም

ባለፈ ሁኔታ እጅግ አስፀያፊ በሆነ ሁኔታ ወንዶችን

ሳቀር በልጆቻቸውና በሚስትና ቤተሰቦቻቸው ፊት

በመድፈር የህዝቡን ቅስምና ሞራል በመስበር ለዘላለም

ባሪያ አድርገው ለመግዛት ትልቅ ግፍ እየፈፀሙ ይገኛሉ

፡፡

አሁን ባለንበት በዚህ ወቅት ደግሞ ያንኑ የተለመደ

የቧልት ምርጫ ተብዪ ድራማቸውን ለማካሄድ

በመራወጥ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ምንም ዓይነት ነፃ ፕሬስ

በሌለበት ወያኔ ምርጫ ቦርዱን በሚቆጣጠርበት እና

አሳፋሪ በሆነ ሁኔታም ይህ ገለልተኛ እየተባለ

የሚወራለት ቦርድ በድርጅቶች የውስጥ ገዳይ እንኳ

ሳቀር በመግባት ድርጅትን እከፋፈለ ባለበት ሁኔታ ላይ

ምርጫ ማካሄድ በራስ መቀለድና ወያኔን በማጀብ

ለአንገነን አገዛዙ ህጋዊነትን ከማላበስ ያለፈ ፋይዳ

ስለማይኖረው ትግሉን ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር

የተባበረ እና ህዝብን በበቂ ሁኔታ ያደራጀ ትግል

ማካሄድ ግዜው ግድ የሚለው ወቅታዊ ጥያቄ ነው ፡፡

ስለዚህ እጅ ለእጅ በመያያዝ ኢትዮጵያችንን

ከተደቀነባት አደጋ እንታደጋት ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ወያኔና መድሎቹ

Saba Nigussie, Rednitzhembach

በሀገራችን የኮንስትራክሽንና የመንገድ ስራዎች

በከፍተኛ ፍጥነት ቁጥራቸው በመበራከት ላይ ይገኛል

፡፡ እነዚህ ግንባታዎች የጥራት ደረጃቸው ምን

ይመስላል ብለን የጠየቅን እንደሆነ በጣም በሚያሳፍር

ሁኔታ በሙስና በዘፈቁ የስርዓቱ አባላት በሚዘወሩ

የግንባታ ኩባንያዎች ስለሚገነመቡና በሙስና

የተጨማለቀ ስራም ስለሚሰራና ተቆጣጣሪም

ስለሌለባቸው እናዳሻቸው የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት

እያባከኑ ይገኛሉ ፡፡

በነዚህም ግነባታዎች መንግስት የአካል ጉዳተኞችን

ለመርዳት ለነሱ አመቺ በሆነ ሁኔታ ተገንበቷል ብሎ

ቢዋሽም ህንፃዎቹ ምንም ኣይነት ሊፍት የሌላቸው

ሲሆኑ ይህ ደግሞ በሀገሪቱ ያሉትንና በስማቸው

የሚነገድባቸውን ከ 8 ሚሊዮን የሚበልጡ አካል

ጉዳተኞችን ያለካተተ መሆኑ በጣም አሳፋሪ ነው ፡፡

ሌላው ቀርቶ ቢያንስ የታችኛው ለአካል ጉዳተኞች

ይሰጣል ተባለ እንጂ ተጠቃሚዎች ሌሎች ናቸው ፡፡

ከዚህም ባለፈ የትምህርት ተቋማት ባለ ህንፃዎች

በመሆናቸው አካል ጉዳተኞች በትምህርት ገበታ

እንዳይገኙ ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል ፡፡ በየጊዜው

የሚቆፋፈሩት መንገዶች ደግሞ ለዊል ቸር

ተጠቃሚዎች አስቸጋሪና እነሱንም ያላገናዘበ ነው ፡፡

ብሎም ለአይነ ስውራን እንዲሁም ማየት ለተሳናቸው

አዳዲስ ግንባታዎች ምን አይነት አስከፊ ሁኔታዎች

ውስጥ እየጣላቸው እንደሆነ የየለቱ ትዝብታችን ሆኗል

፡፡ በነዚህና በተለያዩ ምክንያቶች ኢህአዴግ በነዚህ

ዜጎች ላይ ግልፅ የሆነ በደል እየፈጸመባቸው ይገኛል ፡፡

Im Wandel der Zeiten

Yemane Abera, Rednitzhembach

Die Pflanze blüht, trägt Frucht, welkt dann

und trocknet aus.

Die Sonne machte der Wasserlache den

Garaus.

Die Kleidung, neu und schön, wird unmodern

und alt.

Der Mensch, des Lebens froh, zerfällt zu Erde

bald.

Die Diktatur, sie quält, nutzt grausam ihre

Macht.

Im Putsch Demokratie löst ab sie über Nacht.

Den Pflanze, Wasser, Kleidung, Mansch und

Diktatur

Sind wie die Zeit im Werden und Vergehen

nur.

11 Stufen zum Faschismus

1. Aufruf zu einer Drohung

2. Einrichtung von geheimen

Gefängnissen

3. Entwicklung zu paramilitärischer

Macht

4. Überwachung von auffälligen Bürgern

5. Infiltrierung in Gruppen von Bürgern

6. Willkürliche Inhaftierung von Bürgern

7. Schlüsselindividuen zur Zielscheibe

machen

8. Presseüberwachung und

Pressebeschränkung

9. Wertung von anderen Meinungen als

Verrat

10. Untergrabung der Regeln des Gesetzes

11. Entmachtung der Bürger

Die Äthiopische Regierung hat längst alle 11

Stufen erreicht!

11 Steps of Fascism

1. Invoke a threat.

2. Establish secret Prisons.

3. Develop a Paramilitary Force.

4. Survey Ordinary Citizens.

5. Infiltrate Citizen’s groups.

6. Arbitrarily detain Citizens.

7. Target Key individuals.

8. Restrict the Press.

9. Cast dissent at treasons.

10. Subvert the rule of low.

11. Disarm the Citizen.

አበባም አብቦ ሲበቃው ይደርቃል

የውሀም ገበቴ እያደር ይደርቃል

ልብስም ቢያጌጡበት እያጠቡት ያልቃል

ኢህአዴግም ይክረም እንጊ ቦታውን ይለቃል!

የወያኔ ግፍና መከራ

Abdrahman Buser Ali, Würzburg

የወያኔ መንግስት ኢትዮጵያን በግፍ መግዛት

ከጀመረበት ወቅት አንስቶ እስካሁን በአንባገነንነት

እያስተዳደረና ጭቆናውም ከለት ወደ ለት እየባሰበት

መጥቷል ፡፡ የኢትዮጵያም ህዝብ ከቀን ወደ ቀን

ስቃዩም መከራውም እየባሰ ይገኛል ፡፡ ይህንንም የወያኔ

መከራና ግፍ መቻል የታከተው የሀገራችን ህዝብ በሀገሩ

የዜግነት ክብሩ ተገፎ ከቆሙተ በታች ከሞቱተ በላይ

የስቃይ የውርደትና የመከራ ኑሮን ለመግፋት ተገዷል

፡፡ ውጣቱ ትውልድ በሀገሩ የመማር ሰርቶ የመኖር

ነግዶ የማትረፍ መብቱ ተገፎ እነዚህ ሁሉ መብቶቹ

ለወያኔ አባላት እንዲሁም በተለጣፊ ድርጅቶቹ ውስጥ

ላሉ አባላቱና ከአንድ ብሄር ለመጡ ሠዎች ተሰጥቷል

፡፡ በዚህም ምክንያት ይህንን ግፍና መከራ መቻል

የታከተው ውዱ የሀገራችን ህዝብ የወያኔን ግፍ በመሸሽ

የሰሀራ በረሀ እና የባህር ሻርክ እራት ለመሆን ተገዷል

፡፡ የተረፈውም በተለያዩ ሀገራት የስደት ህይወትን

ለመግፋት ተገዷል ፡፡

በሀገር ውስጥ የሚኖረው በወያኔ ነበልባል

እየተለበለበ ሲሆን ይህንንም መከራና ግፍ በመቃወም

መብቱን የጠየቀው ወይም ሀገሩንና ህዝቡን ነፃ

ለማውጣት የታገለው አገር ወዳዱ ህዝብ እየታደነ

እየተገደለና በየእስር ቤቱ ታጉሮ ይገኛል ፡፡ ህዝቡ

በሀገሩ ላይ እምነቱን በነፃ የማመን ሃሳቡንም በነፃነት

የመግለፅ መብቱ መገፈፉ አልበቃ ብሎት የወያኔ ካድሬ

ወይም አሽከር ካልሆነ ስራ መስራትና ራሱንና

ቤተሰቡን ማስተዳደር የማችልበት አሳፋሪ ወቅት ላይ

እንገኛለን ፡፡ ወያኔ ይህ ሁሉ ግፍ አልበቃ ብሎት

በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው አማካይነት ተዋድዶ

ተከባብሮና ተቻችሎ ለዘመናት የኖረውን የኢትዮጵያ

ህዝብ በብሄር ብሄረሰቦች መብት ስም ለማጋጨት

ወይም ለመከፋፈል ከመጣር አልተቆጠበም ፡፡

የወያኔ ግፍ በዚህ ብቻ አላበቃ ብሎ ዜጎችን

ከቀያቸው በማፈናቀል በኢንቨስትመንት ስም መሬቱን

ለባዕዳን ኩባንያዎች የነፃ ያህል በመቸርቸርና

የሀገሪቱንም ማዕድናት በመቸብቸብ ወደግል ካዝናቸው

እያስገቡ ይገኛሉ ፡፡ በተጨማሪም የሀገሪቱን ትላልቅ

የንግድ ዘርፎች በብቸኝነት ይዘውታል ፡፡ ሀገራችን

በዚህ ወቅት በወያኔ ዘመናዊ ቅኝ አገዛዝ እየተገዛች

ትገኛለች ፡፡ ስለዚህ ሀገራችንን ከዚህ ግፈኛና አረመኔ

መንግስት እንዴት ልናላቅቃት እንችላለን ? ሀገራችንስ

ከኛ ምን ትጠብቃለች ? እኛስ እንደ ወጣት ለሀገራችን

ምን ለማድረግ ተዘጋጅተናል ? ወገን ከዚህ ግዜ

ከማይሰጥ መከራና ግፍ አገራችንን ሁላችንም አንድ

ሆነን ይህንን አንባገነንና ግፈኛ ስርዓት ዛሬ ነገ ሳንል

ሀገራችንንና ውዱ ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እንነሳ ፡፡

ዲሞክራሲው የታለ?የሀይማኖት ነፃነቱስ?

Munira Mohammed Mustefa, Nürnburg

ኢትዮጵያ ረጅም የሀይማኖት ፣ የታሪክና የባህል

ቁርኝት ያለባት አገር ናት፡፡ አገሪቱ ጥንታዊ እንደመሆኗ

መጠን ብዙ ሺህ አመታትን ባስቆጠረው ህልውናዋ

ውስጥ ሁለቱ ዓበይት ሀይማኖቶች የተጫወቱት ሚና

ከምንም በላይ የጎላ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

ምንም እንኳን የቀደሙት ገዢዎች ሀይማኖትን እንደ

መጨቆኛ መሳሪያ በመጠቀም ህዝብን ከእምነቱ

ሊያፈናቅሉት የተለያዩ ጫናዎችን በመፍጠርና የፖለቲካ

መሳሪያቸው ሊያደርጉት ቢጥሩም ፣ ህዝቡ ግን

ሀይማኖቱን ጠብቆ ለመኖር በቅቷል ፡፡ በተለያዩ

ጊዜያት እነዚህ አንባገነን ገዢዎች ሙስሊሙ

ህብረተሰብ ሀይማኖቱን እንዲጥል ከማስገደድ አንስቶ

ዜግነትን እስከ መንፈግ የደረሰ ግፍን ሲፈፅሙ የኖሩ

መሆኑ የቅርብ ግዜ ታሪካችን ነው ፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በቁጥር ሰፊና

በስብጥሩም ቢሆን በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን

ያካተተ ነው ፡፡ ይህ ህብረተሰብ ሲያምንበት የቆየውን

እምነት የመንግስት አካላት በቁጥጥር ስር ያስገቡትን

የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተብዬ ምንም

የሙስሊሙን ውክልና ያላገኘ አካል በመጠቀም በይፋና

በድብቅ አዲስ የሀይማኖት ቅጂ ለማስተዋወቅ

መሞከራቸው በምንም መልኩ ተቀባይነት ያለው

ባይሆንም የችግሩ አንዱ መሰረት መሆኑ ምንም ጥያቄ

ውስጥ የሚገባ አይደለም ፡፡ ይሄ የሰው ልጆች መብት

ጠላት የሆነ አገዛዝ በ2002 እና 2003 አደረኳቸው

ብሎ ባቀረባቸው መሰረት የለሽ ጥናቶችን ተመርኩዞ

የኢትዮጵያን ሙስሊም ማህበረሰብ የለ ፈቃዱ በግዳጅ

መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም

የሚለውን ራሱ ያወጣውን ህግ እንኳን በመጣስ

ለአንድ በሊባኖስ መሰረቱን ላደረገ ፅንፈኛ የሀይማኖት

አንጃ አስተምህሮ ለማጥመቅ የሄደበት መንገድ በታሪክ

በአስተዳደርም ሆነ በፖለቲካ ምንም ብስለት የሌለው

ከመሆኑ ባሻገር በሀገሪቱ ያለውን አንባገነናዊ አገዛዝ

ጭካኔና ፍፁም አይን ያወጣ ግፍ ያመላከተ ሆኗል ፡፡

በዚህም ምክንያት በሂደቱ የታዩት አጠቃላይ

ትዕይንቶች ወያኔን ከሰራው ስህተት ከመመለስ ይልቅ

በስህተት ላይ ስህተት እየደጋገመና እየደመደመ

የሄደባቸውን ሁኔታዎች መታዘብ ተችሏል፡፡

ሙስሊሙ ህብረተሰብ በእምነቱና በህልውናው

ላይ የተቃጣበትን አስከፊ ሁኔታ በዝምታ ከመመልከት

ይልቅ መንግስትን ከገባበት ስህተትእንዲመለስ

ከመምከርና ከመማፀን አንስቶ ጥያቄዎቹን በትይንተ

ህዝብ እስከመጠየቅ ደርሶአል፡፡ ጥያቆው መላውን

ሙሰሊም ህብረተሰብ በቀጥታ የሚመለከት እንደመሆኑ

ሂደቱ አብዛኛውን የገጠርና የከተማ ነዋሪ ቀልብ የገዛና

መንግስት እየወሰደ ያለውን በእምነት ጉዳይ ጣልቃ

የመግባት ህገ ወጥ ተግባር የማሳረምን አላማ የተከተለ

ነው፡፡ እነዚህ ስህተቶች እንዲታረሙ ህዝቡ

በያካባቢው ያሉ ባለስልጣናትን ከመጠየቅ አንስቶ

የመንግስት ሀላፊዎችን ፊርማ አሰባስቦ ችግሮችን

በማስረዳት ቀጥሎም ተወካዮችን መርጦ ችግሮቹን

ለመፍታት ረጅም መንገድ ሄዷል ፡፡ መንግስት

በጀመረው መንገድ በመቀጠል በተሳሳተ ፖለቲካዊ

ስሌቱ ሂደቱ ወደ መካረር እስከመለወጥ ደርሷል ፡፡ ይህ

እልህ የተሞላበት የመንግስት አካሄድ ለቀጣይ መከሰት

በጀመሩት ተከታታይና አይን ያወጣ የመብት

ጭፍለቃዎች በስፋት ታይቷል ፡፡

ህዝቡ በሰላምና በዲሲፕሊን የጀመራቸው

ትዕይንቶች አንዳንዶቹ በአሰቃቂ የመንግስት ታጣቂዎች

የግፍ ድርጊት ሲቋጭ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ

በትዝብት ተመልክቶታል፡፡ በአስርና በመቶ ሺዎች

የሚቆጠሩ ሰዎች በተሳተፉባቸው ህዝበ ትዕይንቶች

ሁከት የተነሳባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የወያኔ የደህንነት

አባላት ትግሉን ለማክሸፍና ለራሳቸው አላማ ሲሉ

ህዝብ ላይ ፍጅትን ለማካሄድ የቀሰቀሷቸው እንጂ

ከህዝብ የመነጩ አልነበሩም ፡፡ ህዝቡ መፈትሄን

ለመሻት የመረጣቸው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ

አባላት የሆኑ የህዝብ ተወካዮች በማሰር የተጀመረው

የመብት ጥያቄን በሀይል የማፈን ተግባር በሽብርተኝነት

ክስ ምስረታን አሀዱ ብሎ የጀመረውና እራሱ እያሸበረ

ንፁሀንን አሸባሪ የሚለው ወያኔ በመላ ሀገሪቱ እምቢ

ለመብቴ የሉ በብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀንን

በየሰውር እስር ቤቶች በማሰር ፣ አሰቃቂ ድብደባዎችን

እና እንግልት በመፍጠር እና ህዝቡን በማዋከብ

የሚየደርጋቸው አንባገነናዊ ግፍና ሰቆቃዎች ወያኔን ገና

ክ 23 አመታት አገዛዝ በኋላ አንኳን የመንግስትነት

ባህሪ የሌለውና መሰልጠን ያቃተው ከመሆኑ ባሻገር

በእልህ ምላጭ ላይ የሚረማመዱ ግብዞች መሆናቸውን

አመላካች ነው፡፡

እንደ መንግስት ‹‹ ሰላማዊ ትግሉን ተቆጣጥሬያለሁ

አልተቆጣጠርኩም›› ከሚል ማቆሚያ የለሽ አዙሪት

ውስጥ ከመግባት ‹‹የህዝብን ጥያቄ መልሻለሁ ወይስ

አልመለስኩም›› በሚለው መስፈርት ራሱን መመዘን

ተገቢም ግዴታም ነው ፡፡ ይህ ችግር መቀረፍ

እስካልቻለና ወያኔ ራሱ ያወጣውን ህገ መንግስት

ተብዬ ህግ አክብሮ ያለመሄዱ ዳተኝነት እስካለ ድረስ

ሙስሊሙ ህብረተሰብ የትግሉን ሰላማዊነት

እንዳሰጠበቀ የዘትና ስልቱን ቀይሮ እንደሚቀጥል በዚህ

በትግሉ ሶስተኛ አመት ዋዜማ እናረጋግጣለን ፡፡

ምክንያቱም የተናቀና የተገፋ ህዝብትግል አቁሞ

አያውቅምና፡፡

ትግላችን እስከ ድል ደጃፎች በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!

ድምፃችን ይሰማ!

እናቸንፋለን

ማዕከላዊ እስር ቤት(ምድረ ሲዖል)

Wondwosen Assefa, Hilpoltstein

ማዕከላዊ እስር ቤት በተለያዩ ተከታታይ

መንግስታት ዘመን መንግስት በወንጀል የሚከሳቸውን

በተለይም መንግስት ጉዳያቸውን ሊያጠብቅባቸው

የሚፈልግባቸውን ታሳሪዎች በጥብቅ እስርና ምርመራ

የአካል የመንፈስ ሰቆቃ የሚፈፀምበት ቦታ ነው፡፡

ማዕከላዊ እስር ቤት በስቃይ ቦታነት ዝናው

የገነነው ከደርግ ዘመን ጀምሮ ነው፡፡ ደርግ ወድቆ

የወያኔ መንግስት ስልጣን ሲይዝ ለፕሮፖጋንዳና

ለማስመሰል ሲባል በማዕከላዊምርመራ ህዝቡን

በመግረፍና በማሰቃየት የታወቁት ጥቂት ግለሰቦች

ተይዘው ወህኒ እንዲወርዱ ቢያደርግም ደርግ

እንደፈጸመው ሁሉ ወያኔም ቀድሞ ከነበረው ስርዓት

የመረጣቸው መርማሪዎች በበቂ መድቦ በመንቀሳቀስ

ለይ ይገኛል፡፡ ጥቂቶቹም ዛሬ ወያኔ በማዕከላዊ

ምርመራ ለሚፈፅመው ሰቆቃ በባለሙያነት ተቀጥረው

እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ የአሁኑ ማዕከላዊ ምርመራ ካለፉት

መንግስታትና ዘመናት ልዩ የሚያደርገው የምርመራ

ተቋሙን በከፍተኛ ደረጃ የሚመሩትግለሰቦች በሙሉ

ከአንድ የትግራይ ዘር የተውጣጡ መሆናቸው ነው፡፡

የማዕከላዊ መምሪያው ለዚህ ዘረኛ እምነቱ

ማስፈፀሚያ እንዲመቸው በወያኔ ድርጅታዊ መዋቅር

ስር ያደራጃቸው በፈለገው ሰዓትና ግዜ የፈለገውን

ወንጀልና ሀጢያት የሚያስፈፅማቸው በተለያየ ልዩ ልዩ

ጥቅሞች ያቆራኛቸው በዘረኝነታቸው ያበዱ ልዩ ቡድን

አለው፡፡ ይህም የዘረኛ መዋቅር በሰራዊቱ ፣ በፖሊሱ ፣

በደህንነቱ እና በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሁሉም

መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋሞች ውስጥ

የተዘረጋ ነው፡፡ ዛሬ በሀገራችን ውስጥ በአደባባይ

የኢትዮጵያ መንግስት ተብሎ ከሚታወቀው መንግሥት

ስር ያለው ምንም ህግ የማይገዛው የዘራፊዎች

የጨካኞች ነብሰ በላ የሆኑ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት

ትግራይ (ህወሀት) ድርጅታዊ መዋቅር የተሳሰሩ አባላት

ያሉበት መንግስት አለ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሀገራችንን ጉዳይ አሳሳቢ

የሚያደርገው ሰራዊቱን፣ ደህንነቱን፣ መደበኛውን

ፖሊስና የፌደራል ፖሊሱን እንዲሁም በወንጀል

ምርመራ ሌሎችም የስልጣን ዋልታ የሆኑትን ወሳኝ

የሀገሪቱን የስልጣን ሙሉ በሙሉ በበላይነት

የተቆጣጠሩት የፈለጉትን ወንጀል ቢፈጽሙ እንዳሻቸው

ቢገድሉ፣ ቢገድሉ፣ ቢያስሩ፣ ቢቀጠቅጡ ጠያቂ

የላቸውም ከአንድ ዘር የተውጣጡ አረመኔዎች ጉዳይ

ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የወያኔ የደህንነት አባላት

በሚቆጣጠሯቸው የየክልሉ የምርምር ጣቢያዎች

የታሰሩ እጅግ አሰቃቂ ሰቆቃ የሚፈጸምባቸው የሰራዊቱ

የፌደራል ፖሊስ ፣ የመደበኛው ፖሊስ አባላትና

የሲቪሎች ቁጥር ከመቼውም አልፎ ወደ ሺዎች

እንደሚጠጋ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በቀጣይነትም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በተሰማሩ ወጣት

ምሁራን፣ በጎልማሶች፣ በአረጋውያን፣ በሴቶችና

በወንዶች ላይ አፈናው ቀጥሏል፡፡ በተለይም

ለማስመሰያ ሆን ተብሎ ከተቀነባበረው የጥቂቶች

እስረኞች አያያዝ በስተቀር ብዙዎቹ እስረኞች ያለምንም

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተያዙና ያለምንም የፍርድ ቤት

ትዕዛዝ ቤታቸው የተሰበረባቸው ንብረታቸው

የተዘረፈባቸውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡እዚህ ላይ ስለፍርድ

ቤት ሲነሳ የዳኞችን ጉዳይ ስንመለከት በሀገሪቱ ህግ

መሠረት አንድ ግለሰብ በመርማሪ ፊት ቀርቦ የሰጠው

እምነት ወይም የክህደት ቃል ተመርማሪው የለምንም

ጫና ወይም ተጽዕኖ የሰጠው ለመሆኑ ተመርማሪው

ወይም ተጠርጣሪው ከዳኛ እስረኞች ፊት ቀርቦ

በዳኛው ሳይረጋገጥ በማስረጃነት በፍርድ መቅረብ

አይችልም፡፡ እንዲህ አይነቱን ማረጋገጫ እንዲሰጥ

ወያኔ የመረጣቸው ዳኞች የታወቁ የወያኔ ካድሬዎችና

ፍትህን በመጣስ ሀገርን የሚያስለቅሱ ዳኞች ከማዕከላዊ

ምርመራ በመርማሪዎች የሚቀርቡላቸው እስረኞች

ደማቸው እየፈሰሰ ፊታቸው አብጦ በደረሰባቸው

ድብደባ መሄድ አቅቷቸው ሲመጡ እያዩ እነዚህን

እስረኞች በመርማሪዎች ፊት ይህ የሰጣችሁት ቃል

በፈቃዳችሁ ነው አይደለምን? …………በማለት ጥያቄ

የሚጠየቅ ከዱላ ለመገላገል፣ አዎ ያሉትን ደግ

አድርጋችኋል የሚያመሰግኑ …….. ተገደን ነው ብለው

ደፍረው የተናገሩትን ደግሞ ውሰዱና እንደገና

መርምሯቸው ብለው መመሪያ የሚሰጡ

ያስተማራቸውን ህዝብ ውለታ በዚህ መልኩ የሚከፍሉ

አድርባዮች የወገንና የሀገርደም መጣጮች ናቸው፡፡

ወያኔ በየጊዜው ለማሰር ሚፈልጋቸውን ግለሰቦች

የሚሰጣቸው ምክንያቶች እንደወቅቱ ሁኔታ

እንደሚቀያየሩ የታወቁ ቢሆንም አሁን እየተጠቀመበት

ያለው ሽብርተኛ፣ ህገ-መንግስቱን በሀይል ለመናድ፣

ቫትና ግብር ባለመክፈል፣ የግንቦት 7 አባል፣ የኦነግ፣

የኦብነግ …ወዘተ የሚባሉ የመወንጀያ መነሻ ነጥቦች

ሲሆኑ አያያዝን በተመለከተ ደግሞ አንዳንዶቹ

ከስራቸው ቦታ ላይ በድንገት የተወሰዱ አንዳንዶቹ

በደብዳቤ ተጠርተው የታሰሩና የደረሱበት የማይታወቅ

ከንግድ ቤቶቻቸው ላይም እጅግ አስደንጋጭና አሸባሪ

በሆነ ሁኔታ በመትረየስና በክላሽ ያነገቡ በሀያዎችና

በሰላሳዎች የሚቆጠሩ የደህንነትና የፌደራል ፖሊስ

አባላት ከበውና አዋክበው የተያዙም አሉ በዚሁ አንፃር

ደግሞ ከመደበኛ ስራቸው የተባረሩ ዜጎች ለዘመናት

ከኖሩበት መኖሪያ አፈናቅሎ ቤተሰቦቻቸውን አደጋ ላይ

ጥሏል፡፡ በማዕከላዊ ምርመራ መርማሪዎች እስረኞችን

በማሰቃየት የቀረበባቸውን ክስ እንዲያምኑ ጥያቄ

የሚቀርብላቸው እጃቸውና እግራቸውን በካቴና

እየታሰሩ አይናቸውን በጨርቅ ታስረው በብረት

ማንጠልጠያ ላይ አንጠልጥለው በተለምዶ በወፌ ላላ

እስር ታስረው ውስጥ እግራቸውን በመግረፍ ከስቃይ

የተነሳ ጩኸታቸው ወደ ውጭ እንዳይሰማ አፋቸውን

በጎማና በጨርቅ በመጠቅጠቅ ጭንቅላታቸውን

እጆቻቸውን በካቴና በማሰር በሽጉጥና በዱላ

በመቀጥቀጥ በኤሌክትሪክ ገመድ በመግረፍ በማሰቃየት

እንገድልሃለንበማለት በማስፈራራት ብንፈልግ ሬሳህን

መንገድ ላይ ነው እምንጥለው፣ ዘርን መሰረት

በማድረግ አእምሮን በሚነካ ስድብ የሥነ-ልቦና ሰቆቃ

ጭምር ይፈፀምባቸዋል፡፡ በዚህም መርማሪዎቹ

ያዘጋጁትን የእምነት ቃል እና ምስክርነት ላይ

እንዲፈርሙ ይደረጋል፡፡

ይህ ሁሉ የሚፈፀመው በታችኞቹ አካላት ፍላጎትና

እውቅና ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ከህ.ወ.ሀ.ት

ባለስልጣናትና የደህንነት ሹማምንቶች እንዲሁም

ከፍተኛ ዳኞች እያወቁት የተፈፀመና እየተፈፀመም ያለ

ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታሰሩ

እስረኞች ድብደባ ይደርስብናል የሚሉት ሀሰት ነው

ብለው ያለ ሀፍረት ሲናገሩ ከዱላም በላይ ያለፈ

ስቃይበቀጥታ ራሳቸው በሚሰጡት ትዕዛዝ

እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

እና ወገኖቼ ይህ ተረት ተረት ሳይሆን በትክክል

እየተፈፀመ ያለ የወገኖቻችን ሥቃይ እስከመቼ ከንፈር

በመምጠጥ ይዘለቅ ይሆን? በተለይም በኢትዮጵያ

አንድነት የምናምን ልዩነታችንን በማቻቻል ይህንን

ዘግናኝ ትዕይንት በቃ ብለን ለማስቆም መነሳት የግድ

ነው፡፡ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ!

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ወንድወሰን አሰፋ አጐናፍር

በደም የጨቀየው የወያኔ ሥርዓት

Mikiyas Alene. Windsbach

ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት በሀገራችን የተስፋፋው

የአንድ ጎሳ ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ማብቂያ

ያልተበጀለት የግፍ አዘቅት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ወያኔ በሃገራችን የዘረጋው በዘር የከፋፍለህ ግዛ

አሳፋሪ ሥርዓት ህዝባችንን እርስ በርስ ለማናከስና

በዚያም ሳቢያ የራሱን ዕድሜ ማራዘሚያ አድርጎ

እየተጠቀመበት ሲሆን ይህን በመቃወም ፊት ለፊት

የሚጋፈጡትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች እየጨፈለቀ

በንፁሀን ደም እየተጨማለቀ ያለ ሀገር ሻጭ ሀገር በቀል

ቀንደኛ የህዝብና የሀገር ጠላት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ዛሬ ወጣቱ በሀገሩ ሠርቶ በነፃነት መኖር ባለመቻሉ

ስደትን እንደ አንድ አማራጭ አድርጎ እየተጠቀመበት

ቢሆንም ይህም አልጋ ባልጋ ሣይሆን ፈተናና ሞት

የበዛበት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የምፅአት ዘመን

ሆኖብናል፡፡በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ ድንበር በቁጥር

70 ኢትዮጵያውያን የሚደርስላቸው አጥተው በባህር

ሲሰጥሙ በወገን እልቂት ደስታ የሚሰማው ወያኔ ግን

የብሄር ብሄረሰብ ቀን በሚል በዓል አዘጋጅቶ በደስታ

ፈንጠዝያ ሲምነሸነሽ እንደነበር ግልፅ ነው፡፡

ከዚህ በፊት በሳውዲ አረቢያ ወገኖቻችን

ሲጨፈጨፉ በሏቸው እያለ በወገን ሞትና ሥቃይ

የሚደሰተው ወያኔ በዚያ ተርበው ፣ ተዘርፈው ፣

ተደፍረው ወደ ሀገር የገቡ ከ100 ሺህ በላይ

ኢትዮጵያውያን ከዚያም የስቃይ ኑሮ ስለጠበቃቸው

እየሄድን እንሙት በማለት ለዳግሚያ ስደት

ተዳርገዋል፡፡

በአጠቃላይ ሀገራችን በግፈኛው ወያኔ የሞት ፣

የእስራት ፣ የስደት የመከራ ምድር ሆናለች፡፡ የህ የአንድ

ጎሳ ሥርዓት የተመቻቸው ለነሱና ለጥቂት ሆድ አደሮች

ብቻ ነው፡፡የዚህ አረመኔ የወንበዴ ሥርዓት መገታት

አለበት፡፡ይ ሊሆን የሚችለው በኛ በኢትዮጵያውያን

የተባበረ ትግል ነው በመሆኑም አንድ ሆነን ጠንካራ

ሥራ ልንሠራ ለጋራ ነፃነት የጋራ ትግል ወሳኝ በመሆኑ

በአንድነት እንነሳ እላለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ነፃነት

Yibeletal Kefelgne, Bad Sooden Allendorf

ነፃ ሰው ነፃነቱን የሚያስከብርለት ስርዓትን

ይንከባከባል፡፡ በአንጻሩም ደግሞ ነፃነቱን

የሚያከብርለትን ስርዓት ይታገላል ታግሎም

ይለውጣል፡፡ ለሰው ልጆች የተፈጥሮ መብቶቻቸው

ሰው የመሆናችን ፀጋዎች ናቸው፡፡ወያኔን የምንታገለው

ነፃነታችንን እንዲሰጠን አይደለም፡፡ትግላችን በተፈጥሮ

የተቸርናቸውን መብቶች እንዲከበሩ ነው፡፡ነፃነታችን

ዘላለማዊ ከወያኔ እድሜ ቀድሞ የኖረና ከወያኔም ሞት

በኋላ የሚኖር ነው፡፡ሆኖም ግን ነፃነታችንን ማስከበር

ካልቻልን ከሰውነት ደረጃ ወርደን ባርነትን መቀበል

አይቀሬ ነው፡፡ ነፃ ሆ ኖ መገኘትን ይጠይቃል፡፡

ከዚህ አንፃር ከብዙዎቻችን ይበልጥ እነ አቶ

አንዳርጋቸው ፅጌ እና ሌሎችም ሰዎች ነፃ

ናቸው፡፡ለየራሳቸው ህሊና ታማኝ ሆነው ተገኝተዋልና

የሰው ልጅ ነፃነት በማይከበርበት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ

ሀገራት ሰው ኑሮው ወይ እስር ቤት አልያም ጦር ሜዳ

ነው፡፡ ለነፃነት መታሰር መታገልና መሞት ከምቾት

ባርነት በብዙ እጥፍ የበለጠ ነው የነፃነት ስሜቱ፡፡

እነ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌና ሌሎችም ብዙዎች ዛሬ

የወያኔን ሰንሰለት ሰብረውና በጣጥሰው

ወጥተዋል፡፡ነፃነትን በማይወድ ስርዓት ፊት

ነፃነታቸውን ስመስክረዋል፡፡ ወያኔና አሻንጉሊት ዳኞቹ

ለእነዚህ ነፃነት ፈላጊ አርበኞች የሞት ቅጣትና እድሜ

ልክ እስራትን አመቻችቶላቸዋል፡፡ነገር ግን

መንፈሳቸውንና አላማቸውን ፈፅሞ ሊገድሉት

አይችሉም፡፡ የነፃነት መንፈስ ወያኔ ባሰለፈው ጦር እና

ፍርድ ቤት ወይም በወያኔ ጉልበት ሊታሰር

አይችልም፡፡ይህ የነፃነት መንፈስ ደግሞ የአብዛኛው

የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡

የብዙ ሚሊዮኖች የነፃነት ጥያቄ አንድ ወይም

ሁለት ጀግናን በመግደል ወይም በማሰር ሊገታ

አይችልም፡፡ ከእነርሱ ባሻገር እኛስ ምን እያደረግን

ነው?መስራት የሚገባንንስ እየሰራን ነው?እስከመቼስ

ነው የወያኔን ገደብ የለሽ ግፍ በህዝባችን ላይ

መውረዱን እንዲቀጥል የምንፈቅደው ያስሩናል ፣

ይገድሉና ፣ ያሳድዱናል ፣ ይዘርፉናል ፣ ያሳድዱናል፡፡

ይህንን የነፃነት ትግል ግን እኛ ማሸነፍ እያለብን

ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር የለብንም፡፡

ድል ለእትዮጵያ ህዝብ!

ወያኔን ለምን ጠላሁ

ይድረስ

ለፖለቲካ ኮማሪቶች

በህዝብ ስም ፖለቲካን ለማትረፊያነት መጠቀም ለሚፈልጉ

ለሆግ ደሮችና አድረባዮች

Habtamu Jemal . Nürnburg

ወያኔን የምጠላው የድሮ ሚስቴን ስለሚመስለኝ

ነው፡፡የድሮ ሚስቴ ለጥቁርነት የተጠጋች ጠይም ናት››

ተቀባብታ ስትወጣ ከቤት ውጭ የምትታወቀው

በቀይነቷ ነው፡፡እኔም ያገባኋት በቀይነቷ ነው ቀይ

አለመሆኗ የገባኝ አንድ ቤት ውስጥ አብረን መኖር

ከጀመርን በኋላ ነው፡፡አቤት እሷ ….! ስንት መልክ

አላት መሰላቹ ፤ ጠዋት አስቴርን ሆና ከሰዓት ከበቡሽን

ትሆናለች ፤ ከበቡሽነቷን ስትለምዱት ደግሞ አቶ

እርገጤን ሆና ታገኟታላቹ፡፡ እናቴን ፤ አባቴን ፤

አያቶቼንና ዘመዶቼን ሁሉ አትወድልኝም ………

የምትፈልገው የእሷን ጥፍር እንድከረክምላት ወይም

ቅንድቧን እንድቀነድብላት ብቻ ነው፡፡ እኔንም

ተንከባክባኝ አታውቅም ፡፡ ለኔ ቁራሽ እንጀራ በንፍገት

እየሰጠችኝ በራችንን ለሚያንኳኩ ለማኞች ፤ ለሌሎች

ጠያቂዎቿ እና ለአላፊ አግዳሚው ሁላ ሙሉ እንጀራ

ከነወጡ ታቀርባለች፡፡ ከእኔ ጋር ከነቀሚሷ እየተኛች

ለሌሎች ራሷን ገልጣ ትሰጣለች፡፡

በባልትና ጉዳይ ነካነካ ናት ተበድራ ስለገዛችው

ስኳር መጣፈጥ ለማውራት አመት የማይበቃት

ሽንኩርት መክተፍ ስለቻለች አፏን የምትከፍት ሴት

ናት ፡፡ ቤት ውስጥ ነገረኛ ናት ………. ከቤት ውጪ

በጎረቤቶቻችን እና በአልፎ ሂያጆች የሚወረወረው

ድንጋይና ጠጠር ካደረሰብን ጉዳት በላይ እሷ

የሰባበረችው መስታወት ይበልጣል ፡፡ በቤት ውስጥ

ያለ ያልሰባበረችው ስብርብር ……. ንክትክት ያላረገችው

መስታወት ካለ እንኳን ሰነጣጥቃ ለወደፊቱ

እንዲሰባበር የተወችው ነው ፡፡ ብዙ ቅርሶቻችንን ሸጣ

ስታበቃ የጋብቻ ወረቀታችን እንዳይቀደድ

ታንገራግራለች ፡፡ ሀብትህን ባዶ አደርገዋለሁ ፤ የግል

ልጆችህም ሆኑ የጋራ ልጆቻችን ብትንትናቸው ይወጣል

እያለች ፍርሀትን ትፈጥርብኛለች ፡፡

እሷ ከላይኛው አንሶላ እኔ ከውስጠኛው አንሶላ

እየተኛን አካላችን ሳይነካካ …. መንፈሳችን ሳይተቃቀፍ

እሷ ሚስቱ (ባለቤቱ) ነኝ እያለች እኔ ሚስት እየናፈቀኝ

በአንድ ቤት ውስጥ ኖርን ፡፡ አብሮ መኖራችንን

ሳስታውሰው በአያቴ ቤት ግድግዳ ላይ በሚስማር

የተመታ ትልቅ መስታወት ነበር ፡፡ የ ግድግዳ በዚያ

ትልቅ ሚስማር ባይመታ ……..ያ ትልቅ ሚስማር

ባይገባበት የን ትልቅ መስታወት መሸከም ይችል ነበር

ይሆንን እያልኩ ለብዙ ግዜ ራሴን ጠይቄአለሁ ፡፡

ከድሮ ሚስቴ ጋር ለብዙ ግዜ በአብሮነት የመቆየት

ምስጢርም ባስገባችብኝ የፍርሀት ሚስማር ይመስለኛል

፡፡ አጋጣሚው ፈቀደና ከዛች ክፉ ሚስቴ ጋር ተለያየን

…… ከዚያ ጊዜ ወዲህ ወየኔን ሳየው እሷ ትዝ ትለኛለች

፡፡ …አቤት መመሳሰላቸው …አሁን አሁንስ የድሮ ሚስቴ

ብዜ ሆና የመጣች እስኪመስለኝ ወያኔ ሚስቴን መሰለ

፡፡

ወያኔ ቆሜለታለሁ የሚለውና ሌት ተቀን የህዝቡን

ልብ ዝቅ በሚያደርግበት የቸከ ፕሮፖጋንዳ በሬዲዮ

ቴሌቪዥን እና በተለያዩ ድህረ ገጾች የሚያሰራጨው

አይነ ያወጣ ውሸት በውጭ ጌቶቹ ዘንድ ሊያሳየው

የሚሻው ገጽታውና ተጨባጩ እውነታ ለየቅል

መሆናቸው ፤ስለ ዲሞክራሲ ሰብዓዊ መብትና የህግ

የበላይነት እያወራ በየቀኑ የሚያካሂደው አፈና ስየል እና

ግድያ ለቁጥር ማታከቱ ፤ ቆሜለታለሁ ድግሞም

አስከብሬዋለሁ የሚለው የብሄር እኩልነት በየበዓላቱ

ከአደባባይ ዳንኪራ እና ህዝቡን የመከፋፈያ መርዘኛ

አላማውን ግብ ከማሳካት በዘለለ ለህዝቡ የፈየደው

አንዳች ነገር አለመኖሩ ፤ በህገ-መንግስት ተብዬው

የወያኔ ህገ ወንበዴ የሀይማኖት በመንግስት እና

የመንግስትም በሀይማኖት ጣልቃ አለመግባት ተደንግጎ

ሳለ ቤተ እምነቶችን በካባ ለባሽ ካድሬዎችና ሼኮች

በመሙላት የሀይማኖት ነጻነትነ ከመግፈፍ አልፎ

እምቢኝ ለመብቴና ለዕምነቴ ያለውን ሁሉ የፀረ-ሽብር

ህግ በሚለው የማፈኛና የማሸበሪያ ህጉ ሙሉ ለሙሉ

የዕምነት ነፃነትን መግፈፉ ፤ የሰንደቅ አላማ ቀን እያለ

በብዙ መቶ ሚሊዮን ብር እያፈሰሰ በግዳጅ ህዝቡን

ሰልፍ እያስወጣ የኢትዮጵያ ህዝብ የማይቀበለውን

ባንዲራ በግድ ማውለበደለቡ ዐለም ያወቀው ፀሀይ

የሞቀው ሀቅ ነው፡፡

ይህ በደደቢት በጠላቶቻችን ተቀፍቅፎ የተፈጠረ

ቡድን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ፤ ባህላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና

ልዩ ልዩ ዕሴቶቻችንን በማጠልሸትና ኢትዮጵያዊ

ተቋማትንም በማፈራረስ ሌት ተቀን እየሰራ በዜና

አውታሮቹና በተለያዩ ተቋማቱ ግን ሀገሪቱ ከገነት ይልቅ

የተዋበች ፤ መብት ፤ ፍትህ-ርትዕ ፤ የህግ የበላይነት

የሰፈነባትና ብሎም የዓለም ህዝብ ተምሳሌት

እንደሆነችይለፍፋል፡፡

ወያኔ አበው “የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ” እንዲሉ

የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት የሚለምን

(ለሱዳን የተሰጠውን መሬትና መለስ ዜናዊ ለተባበሩት

መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ ፅፎ ኤርትራን

ማሰገንጠሉ የሚታወስ ነው)የሀገሪቱን ጥቅም

ለማሰከበር ግዜ ግን ምክንያትን የሚደረድር

የኢትዮጵያና የህዝቧ ጠላት ስለሆነ በተባበረ ክንድ

ከጫንቃችን ላይ አሽቀንጥረን ልንጥለው ይገባል ፡፡

ለዚህ ደግሞ ፍርሀታችንንም ሽቀንጥረን ልንጥል ይገባል

፡፡ ፍርሀታችንን አውልቀን ጥለን አስመሳዮችንና

አድርባዮችንም ጭምር ልንታገል ይገባል ፡፡ አንተ

ከድሮ ሚስቴ ያፋታኧኝ አጋጣሚ ሆይ ……እባክህ ና

……እባክህ ና …….(ህዝባዊ አመፅ)!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

ሀብታሙ ጀማል(ኑረምበርግ)

FORCED EVICTION AND ARBITRARY

ARREST : Current Ethiopia

Shewaye Girmay Tsfay, Rednitzhembach

Generally speaking, the current Ethiopian

economic policies have been bringing many

positive changes. We have also been

Witnessing improvements on the overall image

of the nation. It is not reasonably fair to

blindly disregard the changes which have been

Achieved, for example, in Access to education

,health care ,electricity and transportation . on

the other side ,ther has been widespread of

gross human right violations, corruption

,favoritism and mal administration across the

nation. It is also painfully true that the ruling

part(EPRDF) adamantly disregards feed back

of its subjects concerning its policies and

programs . in fact ,EPRDF IS Known for

ridiculing its subject for their genuine opinion

on fundamental issues of their country. The

above mentioned problems get Worse at

regional states .The corruption

maladministration, favoritism and degrading

human dignity have been At level of crisis at

the lowest administrative units .Generally

,political and administrative perversions

increase up-to bottom dramatically.

Let me share my experience in

TIGRAY REGION in order to substantiet at

least some of the allegation. In Tigray region

citizens are completely ignored and are

subjected to forceful implementation of any

order which comes from above . This is clear

and plain to any one who happens to stay ther

even for days. The people are allowd to utter

words in public if and only if they have some

statements to praise TPLF party or to the ever

proud but obsolete cadres. The public and

public servants must doggedly wag their tails

to the authorities of their heroic achievement

in fighting against the dictator DERG. The

relationship between the people in power and

their subjects has nothing to do with elected

to elector kind of correlation. Good

governance is in all its forms is in all its forms

practically none existence. corruption and

nepotism on the other hand are plainly

practiced as if they are working principles. I

mean everyone knows it, and ther is nothing

one can do about it! everybody is familiar with

all the cynical deeds of the archaic authorities

who do not have basic knowledge of

fundamental concepts of human rights,

democracy and good.

The issues of favoritism and degrading

human dignity have been enormously in

practice at the lower administrative unit .The

incompetence of officials and key public

servant appointees is the other critical

predicament as criteria of selection is not

merit based. Political loyalty is the only

criterion.

The problems are even more serious in the

south part of the region other Weise known as

Raya classic examples for the case at hand

ALAMATA and RAYA Azebo Weredas

(districts).In these areas ,citizense routinely

deal With deliberate moral and economic

exploitation in a daily basis.

Recently, the government has enacted a new

law which declares the demolation of illegally

built houses throughout Ethiopia. This law has

been issued to addrese problem which have

been lingering for dicades Even. The

government could have addressed crisis

decades ago. Even Worse, the process of

implementation has been desperate move

which swiftly and arbitrarily attempts to solve

the long pending multifaceted problem.

The implementation of this law has been

accompanied by chaos and loss of lives across

the Nation. People of mehoni and alamata

have also been the victims of the hasty

enforcement. The settlers ,who had been living

in the conteseted houses for about twenty

years, were orderd to immedietly demolish

their houses .Documents shows that most of

the houses had been built twenty years ago.

almost all of the owner of the houses have

legal document which are adamantly

disregarded by then government. Majority of

the dwellers are able to produce receipts

which prove that they have been legally

getting state owned services such as water and

electricity.

Shortly after the alamata´s violent

demonstration held in January 2013,

representatives of Mehoni town began the

process of exhausting administrative remedies.

I was Working with the representatives in the

whole process. We took the case from wereda

to the top TPLF Head bureau. I and the

reperesentatives discussed on the legal ground

of their demands and the possible remedies.

Finally we agreed on the following points .

1. Illegal Houses must be demolished

according tot he new proclamation.

2. The owners of houses which supported by

official documents should seek administrative

or judicial remedy.

3. Irrespective of the above mentioned two

points ,in case the government decides against,

the convenants on economic, social and

cultural Rights (ICESCR) should be considered

.According to the ICESCR; both legal and

illegal settlers should be provided with

alternative area when they are subjected to

eviction.

We finally submit our application, above 1-3

points included, to the EPLF Head quarter .We

emphasized that the government should

guarantee the provision of alternative land in

case of possible eviction, We also claimed

special focus on and priority to HV Carriers ,

disabled person, womens and children during

the possible eviction. In general, we claimed

that government should at least considered

the minimum standard set forth by

international human rights covenants.

The head office, receiving the

compliant, told the representatives to go home

and wait until decision is delivered. How ever ,

the government was using the time to single

out who are the main organizers and how

should it make them silence.

Unfortunately, the decision of the government

didn’t consider the above mentioned demands

of the complainants. The government

decided for the immediate demolish of the

houses within numbered days. This was

physically impossible for most of the settlers.

As it was also raining ,it was extremely

difficult for children ,women disabled and

people within HIV. Significant number of the

settlers contained mothers with average of

four children. Hearing the final decision, I

together with my colleagues in the

department of Mekelle Univercity

department of law started processing to take

the case to court by representing the Settlers.

On the other hand ,the representatives were

organizing demonstration .unexpectedlly ,the

police began to apply arbitrary arrest. All the

representatives were immediately

disappeared. The government jailed them

simply because they seek justice i.e. for just

asking remedies from the authorities they

elected.

The authorities began to implement their

merciless eviction i.e. demolition the houses of

the poor who had no alternatives shelters. By

the time when Ethiopia is able to provide

shelter for immigrants, its citizens have been

facing forceful eviction without getting

alternative shelter. The citizens were

completely denied due process of law while

their basic rights are being violated by ill-

trained cadres. It is really pain full to see

people suffering from the evil action of the

people who ”elect” them.

ዓላማው ምንድን ነው ?

Yonas Andualem Girma ,Thalmässing

ባሳብ ባህር ዘፍቆ የሰው ልጅ ሲጨነቅ

ሀይማኖት ሲራባ ፍና ሲረቅ

ነፍስ ዕምነትን አጥታ መንምና በችጋር

እውነቱ ሲያሳፍር ሲያስጠላ ሲያስመርር

ሀይል ክፋት ሲሆን የደካሞች ጭነት

ፍቅር ጥንቡን ጥሎ ሲገዛ እንደ ኩበት

ፍርሀት ትግስት ሆኖ ድንቁርና ኩራት

ዉርደትም ትህትና ጮሌነትም ዕውቀት

ትምህርትም ጌጥ ሆነ ያውም የተውሶ

ስንፍናም ጨዋነት ሰውነት ረክሶ

ማህተም ክርስትና ነጭ ጥምጣም ክህነት

ሐብት ብልፅግና ምቾት ትልቅነት

ምኞት ተስፋ ሁኖ መቃብርም ኑሮ

እንጉርጉሮ ዘፈን ፣ዘፈን እንጉርጉሮ

ባዳ ዘመድ ሆነ ፣ባለቤቱ እንግዳ

ገንዘብ ዳኛ ፣ሲሆን ወንጀል ከሣሽ ሁኖ

ግብዝነት ደላዉ ፣ፅድቅ ተኮንኖ

ወጣትነት ጫጨ እርጅና እየለማ

የሗሊት መገስገስ የጊዜው አላማ

ከራስ በላይ ንፋስ ፣ትልቁ ሀይማኖት

ዘረፋን ሲያውጀው ፣ቂም ሲያረግዝ ጥቃት

ዓይን አያይም አሉ ፣ጆሮም አያዳምጥ

በቁንጣን ፣በስካር ጥቂቶች ሲንሩ

ብዙዎች ደግሞ በርሀብ መንምነው በቁንጫ ሲያርሩ

የድሀ እምባ ሲጎርፍ ፣መሬቱ ሲሸበር

ፍትህ በሌለው ፍርድ ሚዛኑ ሲሰበር

ዝብርቅርቁ ወጣ

ሕይወት ትርጉም አጣ

ኧረ የት ነው ጉዞው ?አላማው ምንድን ነው?

የትገቡ ? የትጠፉ ? ፋና እንኳን አይታይ

ቀድመው የሄዱትን ፣ምነው አናያቸው !

ብልጭ የሚል የለ ከመሬት ከሰማይ

መንገዱ ጠበበ ትርምስምሱ በዛ

አሪታው ፣ኡኡታው ፣ቀለጠ እንደዋዛ

መሬቱም ፣አየሩም በክፋት ጠነዛ

ጥላቻና ቂሙ በሰፊው ተነዛ

እምቢልታው ሲጣራ ነጋሪት ሲያጋሳ

የአለው ሁሉ ሞቶ የሞተው ሲነሳ

በግና ፍየሉ ሊለዩ ነው በገሃድ

ምፅዐት መድረሱ ነው ሊስተካከል ነው ፍርድ

እኛንስ ማን ገዝቶን ይሆን ?

Zed Bekele, Hilpotstein

1717በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ግዜ ገዥው

ፓርቲ ወይም ወያኔ እያደገረገ. ያለው መጥፎ ድርጊት

በህገ መንግስቱ

በራሱ ካስቀመጠውና በየ መድረኩ ከሚለፈልፈው

በተቃራኒ የእምነት ተቋም መሪዎችን ፣ካዲሬዎች

በማድረግ ፡ ሥልጣኑን፡

በድጋሚ የግሉ ለማድረግ ፡እና አሁንም እንደለመደው

የኢትዮጽያዉያንን ህዝብ ደም እየመጠጠ

ለሚቀጥለዉ አምስት አመት

ለመቆየት እየጣረ ይገኛል፡፡ ይህንን የገዥዉን ፓርቲ

(የወያኔን) አካሄድ የተቃወሙ ምእመናን እና

አንዳንድ ጋዜጠኞችን በአሸባሪነት ፣በፀረ ሰላም ሀይል

በአፍራሽነት እና በሌሎች ስርአቱን ለመናድ ብሎ

በመፈረጃነት በሚጠቀምባቸው ሰሞች -ሲከስ ሲያስር

እና እርምጃ፡ሲወስድ እያየን ነው፡፡ ለአብነት ያህልም

የሙስሊምና ፣የክርስትያን፣እንዲሁም ጦማርያን

፣ጋዜጠኞችን ፣

ኢትዮጵያውያን ስርአቱ ከሚፈልገው ውጭ

እምነታቸውን አና ነጻነታቸውን ተከትለው

እንዳያመልኩ እና እንዳይኖሩ እያደረገ እንደሚገኝ

መጥቀሱ በቂ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዐት ደግሞ በጣም የሚገርሙ

ጉዶችን እየሰማን ነው ፡መቼም ጉድ መስማት

ጆሮአችን ለምዷል ፡ ኅሊናችንም ደንዝዟል፡፡እያየን

ሀውልቶች ፈረሱ ፣ እያየን ዕልቂትን የሚያነሱና

፡ብሔርን ከብሔር የሚያጋጩ በዜጎች መሀከል ቅሬታን

የሚፈትሩ ሀውልቶችን ሲገነቡ አየን ፣ሰዎች

ከተወለዱበት እና ካደጉበት ቀዬ ሲፈናቀሉ አየን ፣

አንድ ሺሕ ቤተሰብ እየተፈናቀሉ አንድ ኪሎ ሜትር

ሲሰራም አየን ፣ ለእያንዳንዱ ሰማ ጠቀስ ሕንፃ አንድ

መቶ ቤተሰቦች ድንጋይ ሲከብር እና የሰው ልጅ ወደ

መንገድ ላይ ሲጣል አየን ፣ በፊት በፊት ፡ኢትዮጵያ

ን የባህር በር የሌላት ሐገር ሲያደረጏትም

ዝም ብለን፡ አይተናል የኢትዮጵያን ህዝብ እና

የኢትዮጵያን ጥቅም ታሪካዋን ፡ ሲያጠፉ እና የስሟን

መጠሪያ ቅርሶችን ሲያጠፉ ተመለከትን ፣በትዕግስት

አየን ኤርሚያስ ለገሰ ፊደል ያስቆጠራቸው ፡ ሰዎች ዛሬ

በጥቂት አመታት ውስጥ አድገው ለፈላጭ ቆራጭነት

እና ሀብትን በቀላሉ ለመያዝ በቁ፡ይህንንም እያየን ዝም

አልን ፣ የዛሬው ወሬ ደግሞ ሀገርን ለእነ ሱዳን እና

ተጎራባች አገሮች የሚሸጥን መንግስት ሾመን በደላች

አበሳችንን ስንቆጥር 23 ዓመታት አለፉ ፡ዛሬ ግን በቃ

ይብቃን

ካንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ

Meteku Endeschaw Fekade, Greeding

ኢትዮዽያዊነት ክብር ኢትዮዽያዊነት

ጌጥነው ፣ኢትዮዽያ በዘመናት ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች

፣ሀገር ፣ ኢትዮዽያ የሰው ዘር መገኛ የሆነች ሀገር ፣

የዛሬን አያድርገውና ኢትዮዽያ የዳቦ ቅርጫት የነበረች

ሀገር ነበረች ህዝቦቿ አትንኩኝ ባይና ፣ለሃገራቸው

ቀናኢ ፣እርስ በርስ ተከባብሮና ተሳስበው

የሚኖሩባት ሃገር ነች

አሁን ባለንበት ዘመን የተፈጠሩ አራሙቻዎች

ይህችን የተቀደሰች ሀገር በማፍራረስ አንድነቷን

በማናጋት ታች ፣ላይ ሲሉ ይስተዋላሉ ፣ህዝብ እንደ

ህዝብ ተባብሮና ተሳስሮ ይኖር የነበረን ህዝብ በብሄር

በጎሳ በነገድ በመከፋፈል ሀገርንና ህዝብን የማዳከም

ተግባር ሲፈፀም እተመለከትን ነው፡፡

ኢትዮዽያውያን በሀገራቸው ለመኖር

ባለመቻላቸው ተምረው ሀገራቸውንና ፣ህዝባቸውን

ማገልገል እንዳይችሉ በመደረጋቸው ፀሀፊያን

፣ጋዜጠኞች ስለ ሀገራቸው አንዳይጽፉ ፖለቲከኞች

ስለሀገርና ስለ ሀገራቸውና ስለ ወገናቸው እንዳይናገሩ

አፋቸውን ሸብቦ ሰብአዊ ክብራቸውንና መብታቸውን

ገፎ ገሚሱን ስደተኛ ቀሪውን ደግሞ በድብቅና

በሚታወቁ እስር ቤቶች ፣አጉሮ ፣ንፁሃን ዜጎችን

በሰቆቃ ውስጥ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ፡፡

አምባገነኖች የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ

መብቶችን አያከብሩም እንደ ኢትዮዽያ ያሉ ሀገሮች

፣የይስሙላ ፣ህገ መንግሰት ፣በማውጣት ሰብአዊና

ዲሞክራሲያዊ መብቶችን እንደሚያከብሩና

እንደሚያስከብሩ ደንግገዋል ፣ሆኖም ግን ብሶቱን

እንዳይናገር ፣እንዳይጽፍ ፣በሰላማዊ ሰልፍ

፣እንዳይጠይቅ ፣የስልጣን ጉልበታቸውን መብት

በማድረግ በአዋጅ ፣በመመሪያና በደንብ ፣ህገ

መንግሰቱን ፣ሲጥሱት ማስተዋል ፣የእለት ተዕለት

ትእይንት ከሆነ ሰነባብቷል ፡፡ለዚህም እንደ ዋና

ማስረጃ የፀረ ሽብር ህግ በማውጣት ንፁኃን ዜጎችን

በማሰር ፣በማሰቃየት ፣ ከሃገር ፣በማባረር

፣እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ፡፡

ከዚህም አልፎ ፣ተርፎ ለፖለቲካ ጥቅም

ሲባል ተከባብሮ የኖረን ህዝብ ፣በብሔር በመከፋፈል

፣የሌለ ታሪክ በመፃፍ እርስ በርሱ እንዲጠፋፋና

፣እንዲራራቅ በማድረግ ፣የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ፣

23ዓመት ደክመውበታለ ፣በተለይም በአማራው

ህዝብ ላይ ፣ታሪክ ይቅር የማይለውና ፣ በ 21ኛው

ክፍለ ዘመን ፣ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ጭካኔ

፣የተሞላበት ጭፍጨፋ ፣ ማፈናቀልና የንብረት ዘረፋ

፣አሁን ያለው ፣ዘረኛ መንግሰት በፊት አውራሪነት

ፈፅሟ ል አስፈፅሟል ፣

እንግዲህ እንዲህ አይነት ፈተናዎች ፣ በሀገርና

በህዝብ ፣ላይ ተደቅነዋል ፣አያቶቻችንና ቅድመ

አያቶቻችን በጀግንነት ያስረከቡንን ፣ተሪካዊት ሀገር

የመጠበቅ ሐላፊነት ለዚህ ትውልድ ተጥሎበታል ፣

ይኸውም

1ኛ - ለፖለቲካ ፍጆታ ይጠቅመናል ያሉትን

ህዝብ ፣ከህዝብ የማጋጨት ተግባር በሰለጠነ መንገድ

ተወያይቶ መፍትሄ

ማበጀት

2ኛ - አሁን ያለው አምባገነን መንግሰት

በዲሞክራሲ ስም እየፈፀመ ያለውን ግፍ ማጋለጥና

የአደጉ ሀገሮችን

በማታለል ለገንዘብ ማግኛ ዘዴ

እየተጠቀመበት መሆኑን ማጋለጥ

3ኛ - በኢትዮጵያነት ማእቀፍ ውስጥ

፣የጋራ ሀገር ለመገንባት ሁሉም የየድርሻውን

መወጣት ይጠበቅብናል

በመጨረሻም ፣ለዚህ ሁሉ መፍትሄው

እጅ ለእጅ በመያያዝ የሀገርንና የህዝብ ህልዉና

፣ማሰጠበቅ ይቻል ዘንድ

በጋራ አላማ ፣የጋራ ትግል ወሳኝ ነው

Meteku Endeschaw Fekade

ፍርድ ቤቶችን ለፍርድ የሚያቀርብ ማን ነው ?

Semir Kedir, Thälmassing

አገራችን ኢትዮጽያ በታሪኳ ታላላቅ ስዎችን አፍርታለች

ወደፊትም ታፈራለች፡

በዚህ ታሪካዊ ጉዞዋ ህዝቦቿ ወደ ታላቅነት ማማ ላይ

ለማዉጣት የታተሩ እና

ከነበረቸበት እንዲሁም ካለችበት የጭቆና አገዛዝ

የድህነት አዘቅት ዉሰጥ ለማዉጣት

ብዙ አእላፋት ራሳቸዉን እሰከ ህይወት ፍጻሜ ድረሰ

ህይወታቸዉን የገበሩ ዉድ የኢትዮድያ

ልጆች ጥቂቶች አይደሉም

እነዚህ ዉድ የኢትዮድያ ልጆች ሀገራቸዉ

የምትፈልገውን ወቅቱ የሚጠይቀዉን ጀግንነትና ወኔ

የሰነቁ ለሀገር‹ለሀገራቸው ብሎም ለአፍሪካ እና

ለተቀሩት ዓለማት ተምሳሌት የሆኑና የሚሆኑ ዉድ

ልጆቿ

እየታገሉና እያታገሉ የሚገኙ › የህዝባቸዉ ፣የወገናቸዉ

ሰቃይ ተሰምቶአቸው በወረቀት ላይ የተፃፈ ወይም

የሚፃፍ ሳይሆን በተግባር ሊታይ እና ሊተገበር

የሚችል ዲሞክራሲን ፣ለህዝባቸዉ .ለማሳየት ከራስ

ይልቅ የህዝብና

የሀገር ጥቅም የሚያስቀድሙ..ምሁራን ፣ጋዜጠኞች፣

የሀይማኖት አባቶች ፣እንዲሁም አገዛዙን የሚቃወሙ

ወጣቶች፣

የፖለቲካ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው በየ እሥር ቤቱ

ታጉረው የሠሚ ያለህ እያሉ ባለሉበት ወቅተ ህዝብና

ሀገር አቀፍ

ጥያቄአቸው ምላሽ ተነፍጎት . በእንግልት ላይ

ይገኛሉ፡፡

ሀገሪቱን ያለ ህዝብ ተሳትፎና ፍላጎት

መንበረ ሥልጣኑን በመያዝ እና በመከፋፈል በኪራይ

ሠብሣቢዎች አልጠግብ

ባይ ሙሠኞች የምትመራ ሃገር ሆናለች ፡፡

ኪራይ ሠብሣቢነትና ሙሰና ለአንድ ሀገር

ፀረ ልማት ፣ፀረ እድገት ከመሆኑም በላይ በህዝብ

ላይ

የሚያደርሠዉ ፡ ጉዳት ዘመናትን ተሻግሮ የማያገግም

አስከፊ ጉዳት አስረክቦ ይቀመጣል፡፡

ያለምንም ርህራሄ ያልደከሙበትን የህዝብ ገንዘብ

ወደ ኪሣቸዉ በማሥገባት የግል ጥቅማቸዉን ብቻ

በማሣደድ

ህዝቡን ንቀዉት የራሣቸዉን ፣የተድላ ኑሮ ይኖራሉ

፡፡

ቀድሞዉንም የህዝብና የሀገር መሪ ሆነን እንሠራለን

ብለዉ በተጨጭበረበረ የህዝብ ድምፅ

ሥልጣኑን የተቆናጠጡ በመሆናቸዉ ስለ ህዝብና

፣ስለ ሀገር ነፃነት እና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር

ይተገብራሉ ማለት አይቻልም

በህዝብ ነፃነት ፣ ዲሞክራሲ የማያምኑ

በመሆናቸዉ፣እነሱን የሚቃወም የፖለቲካ

ድርጅትም ሆነ ግለስብ.፡

በፀረ አሸባሪነት ስያሜ ተሰጥቶት እጣ ፈንታዉ ወህኒ

ቤት ይሆናል ፡፡

ይሁን እንጂ ህዝብን በማሠርና በማሰቃየት

እዉነትን መደበቅ አይቻልም ፡፡

ዛሬ ዛሬ የህግ አዉጭዉና አሥፈፃሚ አካል

የሚመደቡት በኢ ህጋዊነት ከተቀመጠዉ እና ህዝብ

ካልተቀበለዉ መንግሥት ጋር

ቁርኝት ያላቸዉ በመሆኑ የከሣሽና ፡የተክሳሽ ጉዳይ

በአግባቡና በትክክል ህጉን እንዳያስፈጽሙ የህዝብ

አለኝታ እንዳይሆኑ

የገዥዉ ሀይል ቁጥጥር ሥር በመዋላቸዉ የሙያዉ

ሥነ ምግባር የማይፈቅድ ብያኔ ሲበይኑ ይታያል፡፡

በመሆኑም ፡ በየትኛዉም ፍትሃዊ ሥርዐት

የመንግሰት ጣልቃ ገብነት ህገ አዉጭዉ ፣ህግ ተርጋሚ

፣ ህግ አሥፈ-

ፃሚዉ ነፃ ያለመሆናቸዉ ድምር ፍርድ ሲያዛቡ

፣ህዝብ ሲያጉላሉ እነሱን የሚጠይቅ ሌላ ፍትኃዊ የሆነ

የህግ አካል

እንዲመሰረት ፡ የግድ .ይላል ለምን ?ቢባል ሀገራችን

ኢትዮጽያ የሚያስፈልጋት ፡በህግና በህግ ፤ቢቻ

የሚመራና-

የሚመራ ዳኛ ሁኖ ፡ወይም የህግ ማዕቀፉ ፣በሚያዘው መሠረት የሚሠራ ዳኛ ያሥፈልጋታል ፡፡

ስለ ኢትዮጵያኖች

lidya Asfaw (Tigest jemal aman), Mainhausen

በኢዉነቱ ከሆና ስለ ኢትዮጵአኖች መርከስ ብንናገር

አንጨርሰዉም ፤ ለምን ብባል ሀገርዩን በልቶና ዘርፎ

ለመሄድ የመጣ መን በኢዉነቱ ከሆና ስለ

ኢትዮጵአኖች መርከስ ብንናገር አንጨርሰዉም ፤ ለምን

ብባል ሀገርዩን በልቶና ዘርፎ ለመሄድ

የመጣ መንግስት ነዉ ዉያኔ ።በአሁኑ ግዙ በኢትዮጵያ

በሀይማኖት፤በቤሕረ ስብ ስያጋጭ ቈይቶ እድሜዉን

ለማራዘም አሁን ደግሞ ከፍተኛ ዝርፊያ ጀምሮዋል

፡ትግሬዎች የሀብት ባላቤቶች ሆነዉ አንድ ሰዉ ግብር

መክፈል ካልቻለ

ቦታዉን ለባለ ሀብት ልቀቅ እያላ ህዝቡን እየበዘበዛ ነዉ

፡፤በቅርብ ግዜ በባሌ ሮቤ ላይ አንድ ድሃ ግብር ክፈል

ስባል የለኝም ስል ኢሺ ቦታዉን ልቀቅ ስባል ግራ

ተጋብቶ ራሱን ሰቀለ።

በጣም ምገርም ጉዳይ ደግሞ ከሉብናኖች የሀበሺ

ሀይማኖት ላማስፋፋት ለኢትዮጵያ መንግስት ባደረጉት

ፈንድ

፡ሙስልሞችን እአስገደደ በግድ የሀበሺ ሀይማኖት እነድ

ወስድ እያደረጋ ነዉ ፤ይህንን ሀይማኖት ያልወሰዳ

፡፤አሸባሪ እየተባለ ።ለእስር እየተዘጋጃ ነዉ ።እኔ

ያልገባኝ ጉዳይ እትዮጵያ ሰዉን ሀይማኖት ላማስቀየር

ላማስቀየር ማጠር ድሞክራሲ ይባላል ።እኔ እንደ

ምገባኝ መዉደቂአዉ ግዜ ደርሶዋል ።በጣም

የምገርማዉ እትዮጵያ

ማብራት ለዉጭ እየሸጠች ያኢትኦያ ከተሞች

ተራበተራ ይጠቀማሉ ። አረ እናንቴ ሌቦች ሁሉ ሰዉ

ነቅቶዋል እፈሩ

እናንቴ የሰባሰባችት ገገንዘብ በመላዉ ያኢትዮጵአ

ህዝብ አንድ ቀን መመለሱ አይቀርም ፡ለምን ደሃዉ

ህዝብ ሰላማዊ

ሰልፍ አያደርግም ። የኢትዮጵያ መንግስት ለሀብታኦች

ብቻ ነዉ የቆማዉ ። ለምን አይነሳም ሰዉ ? ተቀምጦ

በረሃብ

ይሞታል እንዴ?

እያድግ በምርጫ አይወድቅም ለምን ብባል ፡ምርጫዉ

ሁሉ በማችበርብር ነዉ እንዴት ብትለኝ፤በለፈዉ

ምርጫ አስወቀድሞ

ሳትኑ ተሞልተዉ ነዉ ፡ከዝያ ምርጫ ተካሄደዉ።አንድ

ወንድሜ አብዮት ጥበቃ ነዉ እንደ ነገረኝ ፤እያንዳንዱ

አብዮት

ጥበቃ አስቀድሞ በቀበሌ ዉስጥ ያሉትን ህዝቦች አነድ

አብዮት ጥበቃ 25 ሰዎችን አስፈሞ ሞሉበት ብዙ

ቦታዎች ላይ

አስቀድሞ የተሞላ ስለ ሆና ምንም በምርጫ ቀን ሰዎች

አልረቡም ።ስለዝህ እሃድግ ፤ስራዉ ሁሉ ማጭበርበር

ስለ ሆና

ፈጣሪ ብቻ ያንሰዉ።ሌባና አጭበርባሪ መንግስት

አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ

Helina Dawit, Nürnberg Zed Bekele

የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ጋዜጠኞች ከሕዝባዊ ግንባር መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታተልነው፡፡ ያው አስቀድሜ እንደገመትኩት በአሮጌው ድሪቶ ላይ አሮጌ ጨርቅ ድረታና እብለት ክህደት እንጅ የነበረውን አሮጌውንና ያላዋጣውን በመተው በአዲስና በተመከረ በተማረ ልብ አዲስ ሐሳብ አዲስ መንገድ ለመቀየስ አልተፈለገም፡፡ የሚጠበቀውና አስፈላጊው ግን ይሄኛው ነበር፡፡ ለነገሩ ከአንባገነን ሥርዓት ባለሥልጣናት ይሄ የሚጠበቅ አይደለም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንኳን በአንድ ሰው ዕድሜ ሽህ ዓመታት የመኖር ዕድል ቢሰጣቸው እንኳን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ሱሪያቸውን በአንገት ለማጥለቅ እንደታገሉ ያልፋሉ እንጅ አይ ሐሳቤ መንገዴ ይሄንን ያህል ዘመን ብታገልም ሊሠራ አልቻለም፡፡ ሊሠራ ያልቻለበትም የራሱ ምክንያት ችግር ስላለበት ሳይሆን አይቀርምና እስኪ ወይ ለሌላው ዕድሉን ልስጥ ወይ አስተሳሰቤን ቀየር ላድረገው አይሉም፡፡ ተፈጥሯቸው አይፈቅድላቸውምና ግትሮች ናቸው፡፡ ሰውየውን አላያቹህትም? ጓደኞቹን ሰጥ ለበጥ አድርጎ እንቢ ያለውን አጥፍቶ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ብቻውን ገኖ መግዛት በመቻሉ የሚነበብበትን የእርካታ ስሜት አልታያቹህትም? የተሳካላት የሞላላት ሀገር መሪ እንጅ በተወሳሰበ ችግር ውስጥ ያለች ከዕለት ወደ ዕለት እየተመሰቃቀለች የሕዝቧ ኑሮም እየከፋ ያለች ሀገር መሪ ይመስል ነበር?

እናም ከቃለ ምልልሱ አንድም እንኳን ፍሬ አላገኘሁበትም፡፡ እንዲህ ይባላል እንዲህ ይባላል ስለሚባሉ ነገሮች ተወራ እንጅ በፖለቲካዊ (በእምነተ አሥተዳደራዊ) ጉዳዮች ላይ ግብራዊ (ቴክኒካል) የሆኑ ጥያቄዎች ለምሳሌ በአሰብ ወደብ ዙሪያ ያለውና የመሳሰሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ስላልተዳሰሱበት በግሌ ቅር ብሎኛል፡፡ ሲጀመር ቃለ መጠይቁ የቃለ መጠይቅ አሠራርናንና ሒደትን የተከተለ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞቹ ትግርኛን ባለማወቃቸው ጥያቄዎችን መጠየቃቸውን እንጅ የጠየቁት ጥያቄ በአግባቡ ስለመመለሱና

አለመመለሱ ማረጋገጥ እንዳይችሉ አድርጓል፡፡ ሰውየው ማውራት የምፈልገው በትግርኛ ነው ካሉ መብታቸው ነው ነገር ግን የሚመልሱትን ለጋዜጠኞቹ የሚተረጉም አስተርጓሚ በመሀል መኖር ነበረበት፡፡ ይሄ ባልሆነበት ሁኔታ እንዴት ቃለ ምልልሱን ለማድረግ እንደፈቀዱ አልገባኝም፡፡ አስተርጓሚ ከሌለም ጠያቂዎቹና ተጠያቂው በጋራ በሚያውቁት ቋንቋ መደረግ ነበረበት፡፡ ወደ ኋላ ላይ አቶ ኢሳይያስ ከትግርኛ ወደ እንግሊዝኛ በመሔዳቸው ለጋዜጠኞቹ ሰውየው የሚሉትን ነገር ምንነት ለመረዳት የተሻለ ዕድል የሰጣቸው ቢሆንም የተጠቀሙበት ግን አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ይጠየቃል ሰውየው የፈለገውን ሰዓት ያህል ወስዶ ሌላ ነገር ሲቀበጣጥር ቆይቶ ሲጨርስ ሌላ ጥያቄ ደሞ ይጠይቃሉ እንጅ ከጭብጥና ከነጥቡ ውጭ ሲወጣባቸው መመለስ፣ በአግባቡ ያልተመለሰውን እንዲመልስ ማድረግ፣ በዋሸባቸው ወይም በካዳቸው ባበለባቸው ጉዳዮች መሞገት የተባሉ የጋዜጠኛ ሥራዎች ሲሠሩ ባለማየቴ ከፍቶኛል፡፡ ኢሳት ኢሳትን እንጅ ኢቴቪን መሆን አልነበረበትን፡፡ በእርግጥ እነዚህ የኢሳት ጋዜጠኞች ከብቃት ማነስ ሳይሆን ከአቶ ኢሳይያስ ጋራ በገለጽኩት መልኩ ቃለ መጠይቅ ማድረግ እንደ ሌሎቹ ሁሉ እነሱንም እንዳይመለሱ አድርጎ ወኅኒ ሊያስወርዳቸውም ይችላልና ይሄንን ከመፍራት ሳያደርጉት ቀርተው ከሆነ ልንረዳላቸው ይገባል፡፡ አስቀድሞ እንዲህ ዓይነት ሥጋት ከነበራቸው ደግሞ ቃለመጠይቁን ማድረጉ አስፈላጊ አልነበረም፡፡

አንዴ ብቻ አቶ ኢሳይያስ 90ሽህ የደርግ ወታደሮችና ባለሥልጣናት ከባሕረምድር ተሸንፈው በሚወጡበት ወቅት “እንኳን የበቀል እርምጃ ስድብ እንኳን የተናገራቸው አንድ ሰው እንኳን የለም” በማለት የሰውየውን የውሸታምነት ደረጃ የሚያሳይ አስቂኝ ቃል በተናገሩ ጊዜ ፋሲል ምንም እንኳን ሰውየው ተናግረው ጨርሰው ሌላ ጥያቄ ለመቀበል በተዘጋጁበት ሰዓት ቢሆንም “እዚህ ላይ ይቅርታ ላቋርጥዎት” በማለት እነዚህ አቶ ኢሳይያስ 90 ሽህ ናቸው ያሏቸው የደርግ ወታደሮችና ባለሥልጣናት ጥርሳቸውን ሳይቀር እንዲወልቅ እንደተደረገ የእጅ ሰዓት የአንገት ሀብልና ሌሎች ንብረቶች ሁሉ እንደተዘረፉ በታሪክ እንደሰማ አሁን እሳቸው ያሉት ደግሞ ከዚህጋር እንደተለየበት ጠይቋቸው ነበር፡፡ ምንም እንኳን አቶ ኢሳይያስ ለዚህ ጥያቄ ምን እንደመለሱ ኢሳት ባያስደምጠንም ቅሉ፡፡ ለመሆኑ የዚህን ጥያቄ መልስ እንዳንሰማው የተደረገው ለምንድን ነው?

አቶ ኢሳይያስ የገረሙኝ ነገር ቢኖር ፖለቲካዊ ጉዳዮችንስ እሽ መደበቅ የሚፈልጉት ጉዳይ ስለሚኖር ለመሸሽ ሌላ ሌላ ነገር ቀበጣጥረው አለፉ እንበል እሳቸው እኮ ቢናገሩት አድማጩን ምንም የማይጠቅመውንና የሚያውቀውን ጉዳይ ሁሉ እኮ ነበር ሊናገሩ ያልቻሉት፡፡ ለምሳሌ ስለ ራሳቸው ስለ ልጆቻቸው ተጠየቁና ሲመልሱ ይሄም ቁም ነገር ሆኖባቸው ልጆቻቸው ማን ማን እንደሚባሉና ስንት እንደሆኑ ምን እንደተማሩ አንድም ነገር ሳይናገሩ ተፈላሰፍኩ አሉና “ዘለው የባለ ሥልጣን ልጆች ስለሆኑ ከሌላው በተለየ ሊታዩ አይገባም እነሱም ሰው ናቸው

ሁለት ዐይኖች እንጅ አራት ዐይኖች የላቸውም ሁለት ጆሮዎች እንጅ አራት ጆሮዎች የላቸውም ሁለት እግር እንጅ ሁለት እጅ እንጅ አንድ አፍንጫ እንጅ አንድ ምንትስ ሁለት ቅብርጥስ” እያሉ በመዛዛት ስንት ነገር ሊሠራበት የሚችለውን ወርቃማ ጊዜ እንዲያው በከንቱ አባከኑብን፡፡ ከሰው ልጅ ከተወለዱ ሁለት አንድ እያሉ የዘረዘሯቸውን የሰውነት አካላት እንደሚይዙ ማን ያጣዋል ብለው ነው አቶ ኢሳይያስ? መጀመሪያ እነማን እንደሆኑ መች አስተዋወቁንና? ስለነሱ ልናወራ የምንችለው መጀመሪያ ልጆች እንዳሏቸው ሲያሳውቁን አልነበረም እንዴ? ያሉት ነገር እውነት በሆነ በእውነት ከፍልስፍና በቆጠርኩልዎት ነበር እርስዎንም ለሕዝብ እንደሚያስብ ቅን አሳቢ ቡቡ መሪ በቆጠርኩዎት ነበር፡፡ አቶ ኢሳይያስ እንዲያው ግን ሰው ይታዘበኛል የሚባል ኅሊናም የለዎት? አሁን ማን ይሙትና እርስዎን ጨምሮ ልጆችዎ የእርስዎ ልጆች ኑሮ ከተራው ዜጋ ኑሮ ምንም ያልተለየ ነው? እርስዎና የእርስዎ ልጆች አብዛኛውን ጊዜ የሚበላውን አጥቶ በቀን አንዴ እንደሚበላው ባስ ሲልም ጦም እንደሚያድረው እንደአብዛኛው የገጠር ሕዝብዎና እንደከፊሉ የከተማ ሕዝብዎ ጦም አድራቹህ ወይም በቀን አንዴ ብቻ ተመግባቹህ ታውቃላቹህ? የምትቀይሩት ልብስ አጥታቹህ በአንድ ልብስ ላይ ተጣብቃቹህ ታውቃላቹህ? መኝታቹህን ትኋን ቁንጫና ቅማል ይዘልበታል? ባለው ከፍተኛ የውኃ ችግር እንደሌላው ሁሉ ልብሶቻቹህ ሳይታጠቡ ንጽሕናቹህ ሳይጠበቅ በክታቹህ ትሰነብታላቹህ? የማይመስል ነገር እየቀባጠሩ ሲወሸክቱ ምን ያህል ግብዝና አስመሳይ አታላይ መሆንዎ ነው ቁልጭ ብሎ የታየኝ፡፡

የጥያቄዎችን ጭብጥና ነጥብ ሳይጠብቁ የሰውነት አካላትን ሁሉ አንድ ሁለት እያሉ እርባና የሌለውን ዝባዝንኬና የባጥ የቆጡን ወሬ እየቀበጣጠሩ ረጅም ሰዓት ማውራት ችሎታና ብቃት መስሎዎት ነው አቶ ኢሳይያስ? ለዛ ነው እንዴ “በዚህ ጉዳይ ላይ ለሰዓታት ላወራ እችላለሁ!” ሲሉ ደረትዎን ነፍተው የተናገሩት? አየ አቶ ኢሳይያስ! እንደ ማን የሆኑ መስሎዎት ነው? እንደ ኩባው ፊደል ካስትሮ? ነው ወይስ እንደ ሊቢያው ጋዳፊ? እንዲህ ጊዜ ወርቅ በሆነበት ከወርቅም አልማዝ ከአልማዝም ዩራኒየም በሆነበት ዘመን በዝባዝንኬ ወሬ እርስዎም ሥራ ፈተው እኛንም ቁምነገር ያወራሉ መስሎን ሥራ አስፈትተው ይሆናል ብለው ነው? ነው ወይስ “ጊዜ ወርቅ ነው” የሚለው ብሂል ገና እርስዎ ላይ አልደረሰም? አዎ በሥራዎ በአስተሳሰብዎ ሁሉ እያየነው አይደል? አሁን ሌላ ጊዜ አቶ ኢሳይያስ ቃለ መጠይቅ አላቸው ቢባል ማን ነው ቁጭ ብሎ የሚሰማልዎት? አየ አቶ ኢሳይያስ! ለሌላው ጊዜ ግን ሲጠየቁ በነጥቡ ላይ ብቻ አተኩረው ከጭብጥ ሳይወጡ ጥያቄውን መመለስ ነው እንጅ ያልተጠየቁትን የሰውነት አካላት በመዘርዘር የሰው ውድ ጊዜ አያባክኑ እሽ? መመለስ የማይፈልጉት ጥያቄ ካጋጠመዎት ደግሞ እንደሌሎቹ መዝለል ነው እንጅ የማይረባ ዝባዝንኬ መቀበጣጠር ያስገምትዎታል፡፡

አቶ ኢሳይያስ በጣም አስገራሚ ሰው ነዎት፡፡ ፍልስፍናው እንደሱ አይደለም፡፡ ቅዠት በሆነና የትም

ቦታ ባልታየ ሊታይ ሊተገበር ባልቻለ የኮሚውኒዝምና (መደባዊ ያልሆነ ሥርዓተ ማኅበር) የሶሻሊዝም (የኅብረተሰባዊነት) ፍንስፍና እየዳከሩ ጊዜዎን በከንቱ ባያቃጥሉ ሕዝቡንም ባያደክሙ ባያንገላቱት መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም ይሄ ፍልስፍና ሲበዛ ተምኔታዊ (Ideal) በመሆኑና ማንም ሀገር በትክክል ሊተገብረው ስላልቻለ ሊተገበርም ስለማይቻል፡፡ ሲሰሙት ደስ ይላል አማላይም ነው ተግባራዊ ማድረግ ግን ፈጽሞ የሚቻል አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ትንሽ የጭንቅላት እጥበት (brain wash) ላደርግዎት እፈልጋለሁ፡፡ ይሄውልዎት አቶ ኢሳይያስ እያንዳንዱ ሰው የልፋቱን ያህል ማግኘት ካልቻለና ጠንካራውም ደካማውም ምሁሩም መሀይሙም እኩልና ተመሳሳይ የኑሮ ደረጃ እንዲኖረው ከተደረገ ውጤቱ ሰውን ከአቅም በታች እንዲሠራ እንዲለግም ያደርጉታል በዚህም ሀገር ትጎዳለች እንጅ እንዲተጋ፣ አቅሙን አሟጦ እንዲፈጋ፣ እራሱን በሥራ እንዲጠምድ፣ ለጥራት ትኩረት እንዲሰጥ ሊያደርጉት አይችሉም ንግድን ጨምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ሁሉ አይነቃቁም፣ ኑሮ ፉክክር የሌለበትና አሰልች ይሆናል ፈጠራ ግኝትና ፍልሰፋን የመሰሉ የንቁ ጭንቅላት ፍሬዎችማ ጨርሶ የሚታሰቡ አይሆንም፡፡ ሰው አዳዲስ ነገር ሊፈጥር ሊያገኝ ሊፈለስፍ የሚችለው የሚበረታታው የድካሙን የልፋቱን የጥረቱን ያህል ሲከፈለው ዕውቅናና አክብሮት ሲቸረው እንጅ ያንን ያህል ደክሞ ለፍቶ ጥሮና ግሮ ከተራው ዜጋ ጋር በተመሳሳይ የኑሮ ደረጃ እንዲኖር ሲደረግ አይደለም፡፡ ይሄ የሥራ መነቃቃት ስሜትን ይገላል፡፡ ለብርቱው ለታታሪው ለጠንካራው የየጥረቱን ያህል ዳጎስ ዳጎስ ያለ ክፍያ ሲከፈለው ግን መነቃቃት ይፈጠራል፡፡

አንድ ቀላል ምሳሌ ልስጥዎት አቶ ኢሳይያስ፡- በአንድ ክፍል ውስጥ ተማሪዎች ብቃታቸውና ችሎታቸው የተለያየ ሆኖ እያለ እኩል ነጥብ ልስጥ ይላሉ እንዴ? ሁሉም ተማሪዎች እኩል የመቀበልና የመረዳት አቅም ችሎታ ሊኖራቸው አይችልምና ወይም አንደኛው ከሌላኛው ሊጎብዝና ሊሰንፍ ይችላልና እኩል ነጥብ ልንሰጥ አንችልም አይገባምም ካደረግነውም አሠራራችን ፍትሐዊና አመክንዮአዊ አይሆንም፡፡ የተፈጥሮ ጉዳይ ነውና ሁሉንም እኩል ማጎበዝ እኩል እንዲያስቡ ማድረግም አይቻልም፡፡ ልናደርግ የምንችለው ሁኔታዎችን በማመቻቸትና በመርዳት የሚሰንፍ ሰው እንዳይኖር ምርጥ ብቃቱን ችሎታውን እንዲጠቀም ማድረግ፡፡ እንዲህ አድርገን ከረዳናቸው በኋላ ችሎታቸው ብቃታቸው በፈቀደላቸው መጠን የሚያመጡትን ውጤት ግን የየችሎታቸውንና ውጤታቸውን ያህል ነው ሊሆን የሚገባው፡፡ ይሄ ካልሆነና ለሁሉም እኩል ነጥብ የሚሰጥ ከሆነ ግን የሚጎብዝ ተማሪ ሊወጣ አይችልም፡፡ ምን አለፋውና? በሥራም ዘርፍ ያለው ነገር እንዲሁ ነው፡፡ ስለሆነም ጠንክሮ በርትቶ የሠራ ሀብታም የሚሆንበት የተሰጠውን ዕድልና ድጋፍ መጠቀም ሳይችል ቀርቶ የወደቀው ደግሞ ደህይቶ በድህነት የሚቀጣበት ሁኔታ ክፍት መሆን አለበት፡፡ ባለፀጋው በድካሙ በጥረቱ በልፋቱ አግኝቷልና የድካም ፍሬውንም እንዲበላ ሊፈቀድለት ይገባል፡፡ ሰው የሚደኸየው በስንፍናው

ብቻ አይደለምና ባለጸጋው በሰብአዊነት በራሱ ፈቃድ ድሆችን መርዳት ከፈለገ ግን የፈቀደውን ያህል ያለውን ማካፈል መብቱ ነው፡፡ የሞራል (የቅስም) ግዴታም አለበት፡፡ በግድ ግን ያለህን አምጣ ከሌላው የተለየ የላቀ ኑሮ ልትኖር አትችልም ሊባል አይገባም፡፡ በዚህ ዓይነት አሥተዳደር ሀገር ልትገነባ ዜጎች ሊለወጡ አይችሉም፡፡

የሀገራት መሪዎች ሊጠነቀቁ የሚገባው ነገር ቢኖር ለሁሉም ዜጋ ሠርቶ ሊለወጥ ሊበለጽግ የሚችልበት እኩል ዕድል የመኖሩን ጉዳይና ሕግ ከፈቀደው መንገድ ውጪ ሊበለጸግ የሚቻልበትን ሙስናን የመሰለ አግባብ ያልሆነና ሕገ ወጥ አሠራር ኖሮ ዜጎች ሠርተው መለወጥ የሚችሉበትን ዕድል አጥተው ጥቂቶች ወንጀለኞች ብቻ ደግሞ የሚበለጽጉበት ሁኔታ እንዳይፈጠር እንጅ በነጻና ፍትሐዊ ፉክክር የጠነከሩት የበረቱት ሠርተው ማግኘት መለወጥ የሚችሉት ዜጎች መኖራቸው አይደደለም ሊያሳስባቸው የሚገባው፡፡ ይሄማ ሥጋት ነው ሊሆን የሚችለው የአንባ ገነን መሪዎች ሥጋት፡፡ በበረቱ በበለጸጉ በነቁ በበቁ ሰዎች እንዋጣለን ጥቅማችን ይጎዳል ሥልጣናችንን ሁሉ ልናጣ እንችላለን የሚል የሀገርን ጥቅም ሳይሆን የግል ጥቅማቸውን ማዕከል ያደረገ ሥጋት፡፡ ሲመስለኝ የእርስዎም ሥጋት ይሔው ነው ምክንያቱም ከላይ እንደገለጽኩት እርስዎ የተናገሩትን እርስዎም ሆኑ ልጆችዎ አትኖሩትምና ነው፡፡ ጉርድ ሸሚዝና ክፍት ጫማ አድርገው መታየትዎ ወደ ኋላ ላይ ተስቶዎት እውነቷን እንደተናገሩት ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ስለሚወዱ እንጅ መግቢያዎ ላይ ለማወናበድ ይታሰብልኛል ብለው እንደገመቱትና እንደተናገሩት ከተራው ሕዝብ የተለየ ኑሮ እንዲኖርዎት የማይፈልጉ ስለሆኑ አይደለም፡፡ ባሰኘዎት ጊዜና ቦታ ደግሞ እንዴት እንደሚዘንጡ በሚገባ እናውቃለንና፡፡ በእርግጥ አንዳንድ የዋሀንን ሊያታልሉ ይችሉ ይሆናል የሆነ ሆኖ ግን እውነት ያልሆነና የማስመሰል ነገር መሠረታዊ የሆነ ለውጥ አያመጣምና እንዲህ ዓይነቱን ነገር ቁም ነገሬ ብለው ባይይዙት መልካም ነው፡፡ እርስዎንም ማንንም አይጠቅምምና፡፡

የሰሞኑ ወግ

Rute Mekonene, Zeil Hilpoltstein

መጽሐፈ ገጽ (በፌስ ቡክ) ጓደኝነት ጥቂት የማልላቸው የኢትዮጵያዊነትን የሀገር የወገን የማንነት የቅርስ ተቆርቋሪነትን ስሜት የተላበሱ የሚያስቀናና የሚንቀለቀል ወኔ የተሞሉ እኅቶች ወንድሞች የመጽሐፈ ገጽ ጓደኝነት እየጠየቁኝ እየተቀበልኳቸው በተቻለኝ መጠንም እያበረታታሁ በጉድኝነታችንን እስከአሁን ቀጥለን ነበር፡፡ ለካ እነኝህ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱና ወኔ የተሞሉ ቁጭት የሚበላቸው እያልኩ የማወድሳቸውና የተቻለኝን ያህልም ሳበረታታቸው የነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ወያኔዎች ያሁሉ ስሜትና ተቆርቋሪነታቸውም ጭንብል ወይም ሽፋን ኖሯል ለካ ሰሞኑን እነኝህ ሰዎች በዘመቻ በየአቅጣጫው “ከአሁን በኋላ አማራ ስለ ራሱ ብቻ ማሰብ ይኖርበታል፣

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ስለራሱ ማሰብ ትቶ ለ80 ምናምን ብሔረሰብ ሁሉ ማሰብ ለድንበር መበላሸት አለመበላሸት ማሰብ የለበትም፣ አሁን 30 ምናምን ሚሊዬን አማራ ሕዝብ እስከ መኖሩም ለተዘነጋው በችግር በዘረኝነት በረሀብ በሥደት አለንጋ ለሚገረፈው የራሡ ቤተሰብ ብቻ ማሰብ መቻል አለበት፣ ሀገር ማንነት ምናምን እያለ የራሱን ህልውና አደጋ ላይ መጣል የለበትም” ከማለትም አልፈው ካርታ ሠርተው ጎንደር ጎጃም ወሎንና ሸዋን አካለው “መገንጠል ይኖርብናል” በማለት መገኝጠልን በማቀንቀን የምትገነጠለዋንም ሀገር “አማራ፣ ቤተ አማራ፣ አቢሲኒያ፣ ኢትዮጵያ፣ ግዮን” የሚሉ ስሞችን ለምርጫ አቅርበዋል፡፡ ስለ ወደብ አገልግሎት ጥያቄ ሲመልሱም “እኛ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሀገር ድንበር ማንነት ምንትስ የሚለውን ትተን እራሳችንን ብቻ ካሰብን በራሳችን ጉዳይ ላይ ብቻ ካተኮርን ከሌሎች ጋር ሰላም ስለምንሆን የወደብ አገልግሎትን በጎንደር በኩል ከኤርትራ ማግኘት እንችላለን” ይላሉ፡፡ አንዳንድ ወገኖችንም ይሄ ሴራ የወያኔ መሆኑን ካለማወቅና የጨነቃቸው ወገኖች ያቀረቡት ሐሳብ መስሏቸው ለመደገፍ የዳዳቸው ሁሉ ነበሩ፡፡ ለአንደኛው ምን አልኩት፡- ወንድሜ ምን ነካህ? ምን ሆንክ? ይሄ እኮ ተሸናፊነት ነው እጅ መስጠት እኮ ነው፡፡ እስኪ አሁን አንተን ከወያኔ ምን እንደሚለይህ ንገረኝ? ኢትዮጵያን ስለተውክ እንዴት ነው እራስህን ልታድን የምትችለው? ውጊያው እኮ አማራ ኢትዮጵያን እስኪተው እስኪጥል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን እስኪክድ ድረስ ብቻ ሳይሆን ጨርሶ ዘሩ እስኪጠፋ ድረስ እኮ ነው፡፡ ምን ነው ሲበዛ የዋህ ሆንክብኝ? የትኛውንስ ክፍል ነው የምትገነጥለው? ወያኔ ከጎንደር ከጎጃም ከወሎ ውስጥ አገዎችን ቅማንቶችንና ሌሎች ወገኖችን እያነሣሣ ምን እንዲሉ እያደረገ እንደሆነ አታውቅም? ይሄ አስተሳሰብ የመጨረሻዎቹ የደናቁርቱ የድንቁርና የድንቁርና ብቻም ሳይሆን የጠላትነት አስተሳሰብ ነው የኢትዮጵያ ጠላት አስተሳሰብ፡፡ አንድነት ወይም የኢትዮጵያ ህልውና በምንም ተአምር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለሱም እንደ እናት አባቶቻችን ሁሉ የማንከፍለው የመሥዋዕተነት ዓይነት ሊኖር አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ ነፍስ ያለው በአንድነቷ ውስጥ ነው አንድነቷ ከፈረሰ በድን ትሆናለች ትሞታለች፡፡ ኢትዮጵያ ከሞተች በኋላ ደናቁርቱና የጠላት ቅጥረኞች ይመስላቸዋል እንጅ በየትኛውም የፈራረሰ አካሏ ላይ ሰው መኖር የሚችልበት ዕድልና ሁኔታ አይኖርም፡፡ ለኢትዮጵያ መፈራረስ ተባባሪ የሆነ ሰው የሚጠየቀው በታሪክ ፊት ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቃሉ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ከ70 ጊዜያት በላይ በክብር በፍቅር በሞገስ በሚጠራት በእግዚአብሔር ፊትም ነው፡፡ ለኢትዮጵያ (ለእግዚአብሔር ሀገር) ጠላት መሆን ያስኮንናልና ተጠንቀቅ፡፡ አልኩት፡፡ ብቻ ምን አለፋቹህ በመጽሐፈ ገጽ ሰሞኑን እያያቹህት እንዳላቹህት ይህ ዘመቻ እንደኛ ናቸው ብለን እናስባቸው በነበሩ አሁን ግን ባልጠበቅነው መንገድ በራሳቸው ጊዜ ማንነታቸውን በገለጡት በወያኔ ካድሬዎች በሰፊው የተያዘ ዘመቻ ሆኗልና እንዳትሳሳቱ እንዳትሰናከሉ ማስጠንቀቅ እወዳለሁ፡፡ ይህ ዘዴ ወያኔ

እስከዛሬ የያዘው የአማራን ብሔራዊና የባለአደራነት ስሜት ለማጥፋት የደከመው ድካም በፈለገው ፍጥነትና መጠን ውጤት እንዳላመጣለትና ብዙም ውጤታማ እንደማያደርገው ካወቀ በኋላ አዲስ የቀየሰው ስልት ነው፡፡ ነገር ግን በእኔ እምነት ይሄ የወያኔ አዲሱ የኢትዮጵያዊነትንና የባለአደራነትን ስሜት ከአማራ የማጥፋትና ሀገሪቱን ባለቤት ባለአደራ ተቆርቋሪ የማሳጣት እኩይና ሰይጣናዊ ዘመቻ እንደቀደመውና ሲሠራበት እንደቆየው ዘመቻው ሁሉ ይከሽፋል እንጅ ይሠራለታል ብየ አላስብም፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከሌሎቹ ብሔረሰቦች በተሳካ መልኩ አጥፍቻለሁ ብሎ ያስባል የቀረኝና ያቃተኝ አማራ ብቻ ነው ብሎ ያስባል፡፡ መስሎት እንጅ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከኢትዮጵያዊያን አጠፋለሁ ማለት ቅዠት ነው፡፡ ከደሙ ጋር ተቀላቅሎ ያለ ነውና፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

አድዋ

Eden Getahun, Nürnberg

እ.አ.አ. በየካቲት 1896 ባልተጠበቀና እጅግ አስገራሚ በሆነ መንገድ፤ ኢትዮጵያ፤ እስከዚያ ድረስ በየትኛውም ኣሕጉር ተደርጎ የማይታወቀውን፤ አንድ በመልማት ላይ ያለች ሐገር፤ የአንድ ጠንካራ የሆነ የአውሮፓ መንግሥትን፤ የኢጣልያን የጦር ወረራ በድል የተወጣች መሆኑ ለምን ጊዜም ቢሆን በውጭ ጠላት የማትበገር፤ የነጻነት ጮራ ሐገር መሆኗን አረጋግጦላታል። ስለዚህ ታሪካዊ አኩሪ ድል፤ ብዙ ተጽፏል፤ የአድዋ ክብረ-በዓል በሚዘከርበት ጊዜም፤ ዝርዝር ታሪኩና አንድምታው በሰፊው ይነገራል፤ ይጻፋል። የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግን፤ በመጀመሪያ፤ የአድዋው ጦርነት ዋናው መንሰኤ ኢጣልያ ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛቷ ለማድረግ የነበራት አጉል ምኞት ቢሆንም፤ የቀሰቀሰው አንደኛው ምክንያት የትርጉም ጠንቅ የነበረበት የውጫሌው ውል ስለ ነበር፤ ውሉ በአጼ ምኒልክና በኢጣልያኑ ተወካይ በአንቶኒሊ እንደ ተፈረመ፤ ወዲያውኑ በራስ መኮንን የተመራ አንድ የልዑካን ቡድን ወደ ኢጣልያ ተጉዞ ስለ ፈጸመው ጠቃሚ የዲፕሎማሲ ተግባር፤ ሁለተኛም አድዋ ላይ ለተከናነበችው እጅግ አሳፋሪ ሽንፈት፤ ኢጣልያ 40 ዓመት ሙሉ ጠብቃና ተዘጋጅታ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸመችው አሰቃቂ የበቀል የጦር ወንጀል፤ ዳግመኛ ድል ብትነሳም፤ ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ፍትሕ ስለ አለመገኘቱና በመኪያሔድ ላይ ስላለው ትግል አጭር ዘገባ ይቀርባል።

ነጻነት… ነጻነት… ነጻነት…

Michael Asefa

TPLF በአገሩ ሁሉ ለሚኖሩት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ታላቅ ግብዣ አድርጓል። በዚህ ቤት ሁሌ ደስታ ነው

ሁሌ ፌሽታ ነው። ለድግሱ የተጠሩት ሁሉን ማድረግ የሚችሉ፣ ባለብዙ ህንጻ ባሌቤቶች፣ የፈለጉትን የሚወስኑ፣ ራእይ አስፈጻሚ ናቸው። በሚሰሩት ስተት ንጉሱ ከመረጧቸው ከድግሱ ተጠሪዎች ውጪ ማንም ሊጠይቃቸው የማይችል፣ የሚሰሩትን ግፍዊ ስራ እንደ ጀብዱ ደጋግመው የሚናገሩ፣ በአዳራሹ ውስጥ ለተሰበሰቡት መገለጫቸው ነው። በዚህ መሃል ንጉሱ እንዲህ አሉ ለድግሱ ታዳሚዎች በአዳራሽ ውስጥ ላሉት። ህልም አልሜአለው ብለው ተናገሩ። ህልሜም ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለድግሱ የተጠራችሁ ወዳጆቼ በሙሉ ሃላፊነት አለባችሁ ከአዳራሹ ውጪ ያልወጣ የንጉሱ ራእይ እንደፈለጉ ሊበሉ ሊጠጡ ለተመረጡት ተነገረ። ወዳጅ ዘመዶቻቸው የተጠሩት ሁሉ ገብቶአቸው ይሁን ሳይገባቸው በጭብጨባቸው አጸደቁላቸው። ሳይገባቸው ነገሮች እንዲወሰን የሚያደርጉ ሁሉ ታሪክ በኃላ በአጨብጫቢነታቸው እንደሚዘክራቸው ሊያውቁት ይገባል። ህዝቡም የማያውቀው ራእይ ይነገረው ጀመረ። አዲሱ ንጉሳችን የንግስናው ወንበር በጭንቀት ይሁን በኑዛዜ አልያም በራእይ ታይቶላቸው ወይም ግራ ገብቷአቸው ንግስናውን እንዴት እንደተሰጣቸው ባይገባንም ቅሉ ብቻ አዲሱ ንጉሳችን ንግግራቸውን ሲጀምሩ እንዲ አሉ። የቀድሞ ንጉሳችንን ራእይ እናስፈጽማለን። ይሄንን ቃል ደግመው ደጋግመው ይነግሩናል። በመቀጠልም በመቀባበል በተለያዩ ሚዲያዎች እና አጋጣሚዎች የቀድሞ ንጉሳችንን ራእይ እናስፈጽማለን ይሉ ጀመር የአዳራሹ ታዳሚዎች። ራእዩን ያዩትም ሳይነግሩን ሄዱ ራእዩም የተነገራቸው የድግሱ ታዳሚዎችም ስለራእዩ ምንነት ሳይገልጹልን ራእዩን ለማስፈጸም እሩጫ ሆነ። ለህዝባችን ይፋ ሆኖ ያልተነገረው ራእይ ምን ይሆን?

በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ብዙ ጥያቄዎች ተነሱ ጥያቄዎች በሙሉ በሚያለያይ እና ተቀባይነት በሌለው መልኩ በኃይል ተፈጻሚ ሆኑ። ገዳማዊያን ሳይቀሩ አለም በቃኝ ብለው አፈር ምሰው ጤዛ ልሰው ቅጠል በጥሰው ድንጋይ ተንተርሰው እግዚአብሔር በማመስገን የሚኖሩት ገዳማዊ አባቶች የግፍ በትር አረፈባቸው ታላቅ ተንኮል ተሰርቶባቸው በማያውቁት ነገር ባህታቸው ድረስ ሄደው ገፏቸው ደበደቧቸው። ይሄ ቦታ የናንተ አይደለም ልቀቁ ተብለው ተዘባበቱባቸው እውን በቤተ ክርስቲያን እና አለም በቃኝ ባሉት አባቶች ላይ የግፍ በትር ማሳረፍ እና ቤተክርስትያንን ማፍረስ ይሆን ራእዩ?

በእስልምና እምነት ላይ ብዙ ሴራ ተሰራ የእምነት መሪያቸውን እንዳይመርጡ የመለያየት ስራ ተደረገ ይመሩናል ያሉትን ትተው ያላሰቡት መሪ ሆኖ በግዳጅ ተጫነባቸው። የለም መሪዎቻችንን እኛ እንምረጥ ባሉት ህዝብ ላይና ጥያቄ ያነሱትን በሙሉ የግፍ በትር ያርፍባቸው ጀመረ። ድምጻችንን ስሙን መሪዎቻችንን እኛው እንምረጥ ያሉትን ህዝብ ላይ ጥያቄውን ከመመለስ ይልቅ የሃይል ዱላ ያሳረፉና ያሰቃዩ ቀጠሉ። እስልምናን መከፋፈል ይሆን እንዴ ራእዩ?

ነጻነት… ነጻነት… ነጻነት… ዲሞክራሲ… ዲሞክራሲ… ዲሞክራሲ…. ፍትህ… ፍትህ…. ፍትህ… ብለው በተናገሩት ነጻ ሰዎች ላይ ቤተሰባቸውን ማሰቃየት ከስራ ገበታቸው ማባረር የመሰብሰቢያ ቢሮአቸውን በሃይል መዝጋት ስቃይና እንግልት መጫን። ምን አልባትስ በነጻተት የሚናገር ህዝን እንዳይኖ ስለነጻነቱ የሚቆም ትውልድ እንዳይኖር ይሆን ራእዩ?

ወንድም ከወንድሙ አጠላልፎ ገንዘብ አምላኪ አድርጎ ትውልዱን መቅረጽ ለምን ተፈለገ?። ስለ ጥቅሙ እንጂ ስለ አገር ክብር ስለ ወገን በደል እንዳያስብ ተደርጎ ያስተምሩታል እንጂ ወደፊት አገሩ ከዚህ ትውልድ ብዙ ነገር እንደምትጠብቅ እና ሃላፊነት እንዳለበት እንዲነገረው ያልተፈለገበት ምን ይሆን ምስጢሩ? የወገን ፍቅር፣ ያገር ፍቅር፣ ከልቡ እንዲወጣ እና እንዳይሳልበት ተደርጎ ትውልድን ማስተማር የድግሱ ታዳሚዎች ምን ይሆን የሚያመጣላቸው ጥቅም? ። አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር የማጋጨት ስራን መስራት፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በብሔር፣ እንዲጠላለፍ ሴራ ማሴር ትርፋቸው ምን ይሆን? ሲሻቸው ማሰር፣ ሲሻቸው ማሰቃየት፣ ሲሻቸው መግደል፣ ባጠቃላይ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ ሲበላላ፣ ሲጠጣላ፣ እና ሲሰቃይ ማየት ድንገት ይሄ ይሆን እንዴ ራእዩ?

ጥቂቶች ተፈርተው ብዙሃኖቹ ተሸማቀው ማኖር ይሆን ሃሳባቸው። ጥቂቶች ባለስልጣን ሆነው ህዝቡ ለባለስልጣኑ ተገዢ ማድረግ ይሆን እቅዳቸው። ጥቂቶች ሃብታም አድርጎ ብዙኃኑን አደህይቶ የጥቂቶቹን እጅ ጠባቂ ማድረግ ይሆን ፍላጎታቸው። ጥቂቶች ፈላጭ ቆራጭ ህዝብ ግን ተፈላጭ ተቆራጭ እንዲሆን ማድረግ ይሆን ትግላቸው። አገር የቤተሰብ መምሪያ እስከሚመስል ድረስ በአንድ ጎጥ መያዝ ይሆን ራእያቸው?

እንዲህ እንዲህ እያልኩኝ ሃሳቤን የማወርደው ራእዩን ያዩት ባለራእዩ መሪ ራእያቸውን ሳያሳውቁን ስለሄዱ ነው። ራእዩም የተነገራቸው የድግሱ ታዳሚዎች የአዳራሹ ስብስቦች ምን እንደሆነ ባልነገሩን እና ባላሳወቁን ራእዩን አስፈጻሚ እንደሆኑ ደጋግመው ይነግሩን ስለጀመሩ ነው። ታዲያ እየተፈጸሙ ያሉት እነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው። ንጉሱ ያዩት ራእይ ለህዝቡ ሳይነግሩ ለምን ሄዱ? ወይስ ጥሩ አማካሪ አልያም ጥሩ ወዳጅ አልነበራቸው ይሆን? ጥሩ አማካሪ አልያም ጥሩ ወዳጅ ቢኖራቸው ያዩትን ራእይ ሊፈቱት የሚችሉ በአገሩ እንዳሉ ይነግሯቸው ነበረ። ያሉት አማካሪ ጥሩ ስላልነበሩ እና የንጉሱን ህልም የሚፈቱትን የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረባቸው የሚመጣውንም ያለፈውንም እግዚአብሔር የሚገልጥላቸው እንቆቅልሽን የሚፈቱ በገዳም የሚኖሩትን መነኮሳት አባቶችን እንኳን አቅርቦአቸው ችግራቸውን ሊያስፈቱ ቀርቶ ገዳማቸው ድረስ ሄደው ማሰቃየትን ነው የመረጡት። ህልም ፈቺዎችን ኢማን ያላቸውን በአላህ መንገድ ያሉ ለአላህ የተገዙ ሼሆችን እያራቁ እና እያሰቃዩ መልካም ነገር መጠበቅ ከባድ ነው። ቅዱሳን አባቶችን ንጉሱ ካጠገባቸው

ሊያቀርቧቸው ቀርቶ በገዳማቸው እና በመስኪዳቸው እንዳይኖሩ ታላቅ በደል እያደረሱባቸው ራእዩ እንዴት ሊፈታ ይቻላል? ማንስ ይፍታው?።

ንጉሱ ያዩትን ራእይ አዳራሽ ውስጥ የተሰበሰቡ የኔ ናቸው ያሉአቸው እንዲበሉ የተፈቀደላቸው በሙሉ ሊፈቱት አይችሉም። ታዲያ የንጉሱን ራእይ ማን ይፍታው? ግፍ ሲበዛ እግዚአብሔር እራሱ እንዲህ ይፈርዳል።

የእግዚአብሔር እጅ በግፈኖች እና በጨቋኞች ላይ ይወርዳል በእውነትም ፍርዱን እንዲህ ይፈርዳል።

ንጉስ ብልጣሶር ትልቅ ግብዛ አድርጎ ከመኳንቶችን ጋር ከሚስቶቹ ጋር ከእቁባቶቹ ጋር እየጠጣ እና እየጨፈረ ከእንጨት እና ከድንጋይ የተሰሩ አማልክትን ማመስገን ጀመረ። በዚህ ሰአት የሰው እጅ ጣት የንጉሱን አዳራሹን ጥሳ ገባች ግድግዳው ላይ ጽሁፍ ጻፈች። ንጉሱም የሰው ጣት በቤቱ ግድግዳ ላይ ስትጽፍ ተመለከተ። ያን ግዜ የንጉሱ መልክ ተለወጠ፣ ልቡ ታወከ፣ የወገቡ ጅማት ተፈታ፣ ጉልበቶቹም ተብረከረኩ። ንጉሱም አስማተኖች እና ጠቢባኖች ወደ ንጉሱ ይመጡ ዘንድ አዘዘ። ሁሉም ወደ ንጉሱ ቤት መጡ።ጽፈቱን ያነቡና ፍችውን ይነግሩት ዘንድ ተናገረ። ይሄን ጽፈት እና ፍቺውን የነገረኝን ሐምራዊ ግምጃ ይለብሳል በመንግስቴም ላይ ሶስተኛ ገዢ አድርጌ እሾመዋለው ብሎ ተናገረ። በግዛቱ ውስጥ ያሉት አስማተኞች፣ ጠቢባኖች ጽህፈቱን ሊያነቡት አልቻሉም ፍቺውንም ሊያውቁት አልቻሉም። የዚህን ግዜ ንጉሱ ደነገጠ ፊቱም ሲለዋወጥ ባዩት ግዜ መኳንቶቹም ደነገጡ። በአገሩ ጥሩ መካሪ አይጥፋ ጥሩም ወዳጅ አያሳጣን ይባላል። ንግስቲቷ የንጉሱንና የመኳንቶቹን ጭንቀት አይታ እንዲህ አለች። አሳብህ አያስቸግርህ ፊትህም አይለውጥ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያለበት ሰው በመንግስትህ ውስጥ አለ። ማስተዋልና ጥበብ በፊቱ የሆነ እውቀቱ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ህልምህን የመተርጎም እንቆቅልሽን የሚገልጥ የታተመውን የሚፈታ ዳንኤል የሚባል ቅዱስ አለና እርሱ ሁሉን ይነግርሃል አለችው። ንጉሱም ተጨንቆ ስለነበረ በአስቸኳይ ይመጣ ዘንድ አዘዘ።

ዳንኤል ወደ ንጉሱ ቤት ገባ። ንጉሱም የጽህፈቱን ቃል ይፈታለት እና ይተረጉምለት ዘንድ ዳንኤልን ጠየቀው። ንጉሱ ለዳንኤል ሲናገረው በግዛቴ ያሉትን ጠንቋዮች፣ ጠቢባኖች፣ ፈላስፎች፣ እና ሟርተኖች ጭምር የጽህፈቱት ፍቺ ሊነግሩኝ አልቻሉም። አንተ ግን ሁሉን እንደምታውቅ ተነግሮኛል ጽህፈቱን አንብበህ ከፈታህልኝ ቀይ ግምጃ አልብሼህ በግዛቴ ሶስተኛ ገዢ አድርጌ እሾምሃለው አለው። ዳንኤልም ያንተን ቀይ ግምጃ እና ሹመት አልፈልግም።

ስጦታህም በሙሉ ላንተ ይሁን ነገር ግን ጽህፈቱን አንብቤ ትርጉሙን እነግርሃለው አለው። ጽህፈቱ እንዲህ ይላል ማኔ ቴቄል ፋሬስ የሚል ሲሆን የነገሩም ፍቺ እንዲህ ነው።

ማኔ ማለት እግዚአብሔር መንግስትህን ቆጠራት ፈጸማትም ማለት ሲሆን።

ቴቄል ማለት በሚዛን ተመዘነች ቀላም ተገኘች

ፋሬስ ማለት መንግስትህም ተከፈለች ለመዶንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠች ማለት ነው። ብሎ ቅዱስ ዳንኤል ቃል በቃል ፈታለት። ንጉስ ብልጣሶርም እጅግ ተደሰተ ቀይ ግምጃም አልብሶት በመንግስቱ ላይ ገዚ አድርጎ ሾመው።