[email protected] ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ...

9
1 ቁጥር ŦƋ - ነሐሴ ፪ሺህ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected] ጤና ይስጥልኝ፤ በዚህ የዕዝራ ስርጭት የእግዚአብሔርን አሳብ ማገልገል በሚል ካለፈው ከክፍል አንድ የቀጠለውን መጨረሻ ክፍል፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በሚል የፊልጵስዩስን ጥናት እንዲሁም ነቢይነት ሹመት ነው ጸጋ? በሚል የተጻፉ አጫጭር መጣጥፎችን አቅርቤአለሁ። ሁለት አጫጭር ግጥሞችም አሉ። መልካም ንባብ። ዕዝራ ስነ ጽሑፍ፥ ዘላለም መንግሥቱ

Transcript of [email protected] ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ...

Page 1: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

1

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

ጤና ይስጥልኝ፤

በዚህ የዕዝራ ስርጭት የእግዚአብሔርን አሳብ ማገልገል

በሚል ካለፈው ከክፍል አንድ የቀጠለውን መጨረሻ

ክፍል፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በሚል የፊልጵስዩስን

ጥናት እንዲሁም ነቢይነት ሹመት ነው ጸጋ? በሚል

የተጻፉ አጫጭር መጣጥፎችን አቅርቤአለሁ። ሁለት

አጫጭር ግጥሞችም አሉ።

መልካም ንባብ።

ዕዝራ ስነ ጽሑፍ፥

ዘላለም መንግሥቱ

Page 2: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

2

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

ክፍል 2

ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤

ሐዋ. 13፥36

ባለፈው የእግዚአብሔርን አሳብ ማገልገል በሚል በክፍል አንድ በተካፈልነው የተለያዩ አሳቦች ወይም ፈቃዶች እንዳሉና ሰዎችም ከእነዚህ የአንዱ አገልጋዮች መሆናቸውን ተመልክተን ነበር። እነዚህ ፈቃዶች፥

የሰው ወይም የራስ ፈቃድ፥ የሌሎች ሰዎች ፈቃድ፥ የሰይጣን ፈቃድ፥ እና የእግዚአብሔር ፈቃድ ናቸው።

ቁም ነገሩ የተለያዩ ፈቃዶች መኖራቸውን ማወቁ ሳይሆን የእግዚአብሔርን አሳብ ለይቶ አውቆ፥ ያንን ያወቁትን ማገልገሉ ነው። ጌታ እንዴት መጸለይ እንደሚገባቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን ብለው እንዲጸልዩ አስተማራቸው፤ ማቴ. 6፥10። ፈቃዱን ማወቅ ፈቃዱ በምድር እንድትሆን መሳሪያ እንድንሆን ያግዘናል። ፈቃዱን ማወቅና ማገልገል ደግሞ በምርጫ ክርስቲያን ከሆንን በኋላ እርሱን የመከተል ሕይወት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ፈቃዱን እንድናውቅና ያንን እንድናደርግ ያሳስበናል።

ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። ኤፌ. 5፥17

ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም። ቆላ. 1፥9

የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ዕብ. 10፥36

ፈቃዱን ማድረግ እንጂ ጌታን በአፍ ብቻ መጥራት በቂ አይደለም። በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። ማቴ 7፥21። እነዚህ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም? አጋንንት አላወጣንም? ተአምራት አላደረግንም ያሉ ናቸው። በእርግጥም በስሙ ያሉትን ሁሉ አድርገዋል። ጌታም ለስሙ ሲል ሠርቶአል። እነርሱ ግን አልታወቁም። ከቶ አላወቅኋችሁም ነበር ያላቸው። አላውቃችሁም ሳይሆን አላወቅኋችሁም ማለቱ ቀድሞም ያልታወቁ እንደነበሩ ያሳያል። አይገርምም ያልታወቁ ሆኖ ማገልገል፥ በስሙ አጋንንት ማውጣት፥ ትንቢት መናገርና ተአምራት ማድረግ?

እነዚህ የእግዚአብሔርን ሳይሆን በማወቅ ወይም ባለማወቅ የራሳቸውንና የሰይጣንን ፈቃድ እያደረጉ የነበሩ ሰዎች ናቸው። ለኛ ጥሩ የመሰለን፥ ደስ ያለን፥ የተመቸን፥ የደላን ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው

ማለት አይምሰለን። ከመከራና ከስደት፥ ከሥጋ ሕመም ወይም ጉስቁልና፥ ከነቀፌታና ከእጦት የጸዳ ኑሮ መኖር የኛ ምኞትና ፍላጎት ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰባኪዎች ይህ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑንም ይሰብኩናል። ይህ ለሥጋዊ ክርስቲያን የሚጥም መብል ቢሆንም የኛ ምኞት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ማለት ነው? ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው። ምሳ. 14፥12፤ 16፥25።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ውብ ነው፤ ተፈትኖ የሚታወቅም ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ውብ ነው። ለኛ፥ ማለት ለሥጋችን የሚመች መስሎ ባይታየንም እንኳ የጌታ ፈቃድ በጎና ደስ የሚያሰኝ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፥1-2።

በጎ፥ ደስ የሚያሰኝ፥ ፍጹም ነው። በጎ ነው፤ መልካም ነው። ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ዕረፍትና ሐሴት ያለበት ነው እንጂ፥ ኀዘን፥ ትካዜ፥ መበሳጨት፥ ወደ ኋላ ተመልክቶ ቅር መሰኘት፥ ጸጸትና መቆጨት፥ የለበትም። ፍጹም ነው፤ አቻ፥ ተመሳሳይ፥ ቀራቢ፥ ልዋጭ የለውም። እንከን የለበትም፤ ፍጹም ነው፤ እንደ እርሱ አሳብ ያለ ሌላ የለም።

የሚታወቀው ደግሞ ተፈትኖና ተረጋግጦ፥ በመታደስና በመለወጥ ዓለምን ባለመምሰል ነው፤ . . . ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምን እናውቃለን? በመጀመሪያ ሁለት ነጥቦች አሉ። አንደኛ፥ በጣም ግልጽ የሆኑና ግልጽ የሆኑ ግን በጣም ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች የመኖራቸው እውነት ነው። በጣም ግልጽ የሆኑት እንደ ጥቁርና ነጭ ግልጥ ሆነው የሚታዩ፥ የሚታወቁ ናቸው። እነዚህ ምንም ጥያቄ የማይፈጥሩብን በግልጽ የሚታዩ ናቸው።

ሌሎች ደግሞ አሉ፤ ግልጽ አይደሉም ወይም ግልጽ ሆነው ግን አሻሚ ናቸው። ጥቁርና ነጭ ሳይሆኑ ግን ግራጫ ናቸው። ለምሳሌ፥ ሥራ መሥራት ወይም ማገልገል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፤ ግን ምን ወይም የት መሥራት ወይም ማገልገል ጊዜ የሚጠይቅ ፈቃድ ነው። ማግባት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፤ አለማግባት ወይም ካገቡ ማንን ማግባት ምሪት የሚፈልግ ፈቃድ ነው።

እነዚህን ግልጽ ያልሆኑትን የምናውቀው እንዴት ነው? ግልጽ ያልሆኑትን የምናውቅበትን መንገዶች ከማየታችን አስቀድመን ግልጽ የሆኑትን እንመልከት። በእውነቱ የብዙዎቻችን ችግር የእግዚአብሔርን ፈቃድ አለማወቅ ሳይሆን ያወቅነውን አለመኖር ነው። ግልጽ የሆኑት የጌታ ፈቃዶች ወይም አሳቦች ምንድርናቸው? ብዙ አሉ ጥቂቶቹን እና በግልጽ የተጻፉትን ጉልሆቹን በትንሹ እንይ። ከሁሉ አስቀድመን ግን አንድ ነገር እናስተውል፤ እርሱም፥ ግልጽ ፈቃዱን በዚህ ዘመን የምናውቅበት ብቸኛ መንገድ ቃሉ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ግልጽ ፈቃዶቹ ይታወቃሉ፤ መደረግ ነው ያለባቸው። አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ፈቃዶች ግልጽ ናቸው። እነዚህን ግልጽ የሆኑትን ፈቃዶቹን ለድርድር ማቅረብ አንችልም። መርጠን የሚስማማን ከሆነ ተቀብለን የሚከብደንን ወይም ለሥጋዊ ስብእናችን የማይጥመንን ከሆነ አለማድረግ ወይም በይደር ለከርሞ ወይም ለሚመቸን ጊዜ ማስቀመጥ የለብንም። የሚጠበቅብን ማድረግ ብቻ ነው። ዋና ዋና የሆኑቱን ጥቂቶች እንመልከት።

Page 3: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

3

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

1. ልጁን መምሰላችን

ክርስቶስን መምሰላችን ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብቻ ሳይሆን እንዲያውም ውሳኔ ነው። ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። ሮሜ 8፥29-30

2. ደስታ ጸሎትና ምስጋናችን፤

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ተሰ. 5፥16-18። እነዚህ ነገሮች ስነ ልቡናዊ ልምምድ አይደሉም። እውነታን መካድም አይደሉም። ከእግዚአብሔር ጋር ከኖረ ግንኙነት የተነሣ የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው።

3. መቀደሳችን፤

በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤ 1ተሰ. 4፥1-8። እግዚአብሔር ቅዱስ አምላክ ነውና የእርሱ የሆኑቱም ባህርይውን እንዲጋሩ ይወድዳል።

4. የሥራ ተግባራችን፤

ተግባራችንን፥ ሥራችንን፥ ኃላፊነታችንን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች ሆነን ማከናወናችን ፈቃዱ ነው፤ መልካም ሥራችን፥ በጎ አድራጎታችን ፈቃዱ ነው፤ አገልግሎታችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እነዚህን በሦስት ረድፍ እንያቸው፤

ሀ. ሥራችን (የግል ሥራ ይሁን፥ የመንግሥት ይሁን፥ የድርጅት) ታታሪነታችን ፈቃዱ ነው። ሰው መጀመሪያ ሲፈጠርም ለሥራ፥ ለተግባር ነው የተፈጠረው። አዳም ከወደቀ በኋላ ሥራ ልፋትን አስከተለ እንጂ ሥራ ለደስታ ነው የተፈጠረው።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ኤፌ. 6፥6

ለ. በጎ አድራጎታችን፥ ለሌሎች መዘርጋታችን፥ መልካም ማድረጋችን ፈቃዱ ነው፤

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። ዕብ. 13፥21

በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤ 1ጴጥ. 2፥15

ዕብ. 13፥16 ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና። ይላል። እንዲያውም መስዋዕት ይለዋል።

ሐ. ሥራና ተግባር ብቻ አይደለም፤ አገልግሎታችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

የጸጋ ስጦታ የተሰጠን እንደ ፈቃዱ ነው በ1ቆሮ. 12 የጸጋ ስጦታዎችን ከቁ. 8-10 ከዘረዘረ በኋላ ቁ. 11 ላይ ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል። ይላል። ማገልገላችንና ጸጋችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ጸጋ ስጦታ ስለሆነ አገልግሎት ኃላፊነት ነው እንጂ የምርጫ ጉዳይ አይደለም።

ሮሜ 12፥1 ስለ ራሳችንን ቅዱስ መስዋዕት አድርገን ስለማቅረብ ከተናገረ በኋላ ስለ አገልግሎት ይናገራል። እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። ከዚያ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ተናግሮ የአገልግሎት ዝርዝሮችን ያቀርባል፤ ሮሜ. 12፥2-8። አገልግሎት ጸጋና ኃላፊነት ነው እንጂ የምርጫ ጉዳይ አይደለም።

ሲመቸኝ አገለግላለሁ፤ ስወጣጠር፥ ባተሌ ስሆንና ሌላ ሥራ ሲበዛ እተዋለሁ፤

ሰዎች ጎሽ ሲሉኝና ሲያመሰግኑኝ አገለግላለሁ፤ ዝም ሲሉኝና ሲዘጉኝ ወይም ፊት ሲነሱኝ እተዋለሁ፤

ውስጤ ሲሰማኝ፥ ስሜቴ ደስ ሲለው፥ ደስ ሲለኝ አገለግላለሁ፤ ሲከፋኝ፥ ቅር ሲለኝ፥ ስሜቴ ሲቀዘቅዝ፥ ሙቀቴና ግለቴ ሲወርድ እተዋለሁ፤

ለኔ የሚሆን ጥቅም ካለበት፥ ገንዘብ ይሁን ዝና ወይም ሥልጣን ወይም ሌላ ከኖረበት አገለግላለሁ፤ ካልሆነ አላገለግልም ማለት ምንደኝነት ነው፤

ቢገባን ማገልገላችን መታደላችንና በረከታችን ነው። ቅዱሳንን ማገልገላችን በእግዚአብሔር ዘንድ የማይረሳ ነጥብ ማስመዝገባችን ነው። እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና። ዕብ. 6፥10። የማይረሳ ብቻ ሳይሆን ሽልማት ያለው፥ ዋጋ ያለው፥ ሰማያዊ ደመወዝ ያለው ሥራ መሥራታችን ነው።

5. በመከራ ማለፍ

መከራ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ይህች እንኳ ለሥጋ አትጥምም፤ ቢሆንም ቃሉ የሚለውን እንይ፤ ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ። 1ጴጥ. 4፥19 ከቁጥር 12 ጀምሮ ያለውን ክፍል ብናነብብ የመከራ ምንነት ግልጥ ይሆንልናል። መከራ ማለት ድኅነትና እጦት፥ ወይም በሽታና ሕመም፥ ወይም መንገላታትና መንከራተት፥ ወይም እስራትና ድብደባ ብቻ አይደለም። እነዚህ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴ ራሳችን በራሳችን ላይ የምናመጣቸው ስደቶችና መከራዎች፥ በሽታዎችና ድኅነቶችና ጉስቁልናዎች አሉ። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም።

አንዳንዴ መከራ ከሌሎች የሚወረወርብን ሊሆን ይችላል። ይህንን መመዘን አለብን በኔ መዘዝ ነው ወይስ በሌሎች? ስደትንና ቅጣትን ግን አናምታታ። ቅጣት ግን እኛ መጥፎ ሆነን በመልካም ሰዎች የሚደረግብን እርምጃ ነው። ስደት ደግሞ እኛ መልካም ሆነን በመጥፎ ሰዎች የሚደርስብን ነገር ነው። ስለ ክርስቶስ ስም የምንነቀፍበት ማናቸውም ነገር መከራ ነው። የእርሱ ስለሆንን፥ ስሙ በኛ ላይ ስለተጠራ፥ ባይጠራ ኖሮ የማያገኘን ነገር ካገኘን ያ መከራ ነው፤ ያ መከራ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ያንን አንፍራ።

Page 4: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

4

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

እንዲህ ያለው መከራ ደግሞ ዓላማና ግብ አለው። እግዚአብሔር ይከብርበታል፤ እኛም ፍጹማን እንሆንበታለን። በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል። ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። 1ጴጥ. 5፥10-11።

ግልጽ ያልሆኑት ፈቃዶቹን እንዴት እናውቃለን? ከላይ እንዳየነው ግልጽ የእግዚአብሔር ፈቃዶች ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ ግልጽ ያልሆኑ አሉ፤ ግልጽ ሆነውም አሻሚ የሆኑም አሉ። እነዚህ ጥቁርና ነጭ ሳይሆኑ ግን ግራጫ ናቸው። ለምሳሌ፥ ቀጥሎ ያለው መስመር ላይ ያለው ዕረፍተ ነገር ከደማቅ ወደ ደብዛዛ ያመራል፤ ምን እንደሚል እርግጠኛ አንሆንም፤

የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን ይሆን? ግን ይህ ጽሑፍ በWord ቢላክላችሁና ቀለሙን ብትቀይሩት የተጻፈው ይታያል። አንዳንድ የእግዚአብሔር ፈቃዶች ጊዜ፥ ጸሎት፥ ምሪት የሚሹ ናቸው።

- ሥራ መሥራት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፤ ግን ምን መሥራት፥ የት መሥራት ጥቁርና ነጭ አይደለም፤ እና ግልጽ መሆን ይኖርበት ይሆናል።

- ማግባት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፤ አለማግባት አንዳንዴ ፈቃዱ ሊሆን ይችላል፤ እና አለማግባት ወይም ሲያገቡ ማንን ማግባት ምሪት የሚፈልግ ፈቃድ ነው።

- አንድ ውሳኔ የሚጠይቅ፥ እርምጃ የሚጠይቅ መልእክት፥ ወይም በተለምዶ ትንቢት ወይም ራእይ የምንለው ወይም ሌላ ቃል ከሰማይ በወረደ መልአክም ይሁን ወይም በትንቢት ተናጋሪ ወይም በሌላ በማናቸውም እንደ በለዓም አህያ በመሰለ እንሰሳም ይሁን ወይም በግዑዝ ነገርም እንኳ ቢመጣ፤ ምን እናድርግ? መልእክቱ አሻሚ ላይሆን ይችላል። ምንጩ ግን የማን መሆኑን ማወቅ ፈተና ሊሆን ይችላል።

እነዚህን ግልጽ ያልሆኑትን የምናውቀው እንዴት ነው? በርካታ የማወቂያ መንገዶች አሉን። ሁኔታዎቹ ልዩ ልዩ እንደመሆናቸው መጠን እኛም የምንወስዳቸው የማጣሪያ መንገዶች ብዙና ልዩ ልዩ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው፤

1. ቅዱስ ቃሉ፤ አንዳንዱ ፈቃድ በግልጽ በተጻፈው ቃሉ ተነጻጽሮ ይፈተሻል። ከተጻፈማ ግልጽ ነው፤ ካልተጻፈ ግን የተጻፈውን እውነት የማይጻረር መሆኑ መረጋገጥ አለበት። ከሰማይ አንጸባራቂ መልአክ ቢወርድና ቢናገር እንኳ ያ ቃል መፈተሽ አለበት፤ በምን? በቃል፥ በመጽሐፍ ቅዱስ። በገላ. 1፥8-9 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። ማንም ምንም በምንም መንገድ ቢናገር ያንን የተነገረ ነገር በቃሉ መፈተሽ ይቻለናል። ቃሉ ሚዛናችን ነው፤ ቃሉ ማንጠሪያ ወንፊታችን ወይም ማጥሪያ እሳታችን ነው።

2. መንፈስ ቅዱስ፤ በውስጣችን የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ተገቢው ቦታ ይኑረው። በተለይ ምሪትን ስናስብ ወደ

እውነት ሁሉ የሚመራን መንፈስ እርሱ መሆኑን እንረዳ፤ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። ዮሐ. 13፥16። ውሳኔያችን ትክክል መሆኑን ወይም ያለመሆኑን ይህ ውስጣዊ አማካሪና መሪ ያረጋግጥልናል።

3. ጸሎት፤ ዳዊት እንዲህ ጸለየ፤ አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ። መዝ. 143፥10። እግዚአብሔር ከፈቃዱ ጋር ድብብቆሽ እንድንጫወት የሚፈልግ አምላክ አይደለም። ግን ጸሎት ማለት ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ነው። ብዙ ጸሎት ማለት ደግሞ ከእርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ማሣለፍ ማለት ነው። እግዚአብሔር ይህን ይወድዳል። ደጋግሞ መጸለይ መጠራጠር አይደለም። እንቢ ለማለት ጊዜ መግዛትም አይደለም። ጌዴዎን ለማረጋገጥ ይህን አደረገ፤ ጸለየ፤ ምልክት ለመነ፤ እግዚአብሔርም ደጋግሞ አረጋገጠለት እንጂ፥ ‘አንት ተጠራጣሪ’ ብሎ አልገሰጸውም፤ መሳ. 6፥36-40። ጌዴዎንም ያረጋገጠውን አደረገ እንጂ ከማድረግ ወደኋላ አላለም።

4. ጊዜ መውሰድ፤ ከተጠራጠርን ግልጽ እስኪሆንልን መጠበቅ ስሕተት አይደለም። የምንጠራጠረውን ነገር ፈጥኖ ከመፈጸም እርግጠኛ የሆንንበትን ነገር ተረጋግተን ማድረግ ይሻላል። ዳዊት በመዝ. 40፥1 ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። አለ። ጊዜ ያለፈብን፥ ነገሩ የሚያመልጠን ሊመስለን ይችላል። ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ለቀርፋፋ ዔሊ የታሰበውን ፈጣን ንስር አይወስደውም። ግልጽ እስከሆነልን ድረስ ሄደን ቆመን ማረጋገጥ ከኖረብን እናረጋግጥ። የምንሻገርበትን ውኃ ጥልቀት እንድናይ ውኃው ጠለል እስኪል እንቆይ።

አንድ ጊዜ በነበርኩባት ከተማ (ደብረ ዘይት) መብራት ጠፍቶ ድቅድቅ ጨለማ ነበረ፤ በዚያ ላይ ዝናብ ሊወርድ ተንጠልጥሎአል። ለሌሊት የአዳር ጸሎት መሄድ ነበረብኝ። የጸሎቱ ቤት ሩቅ አይደለም። የውስጥ አሳባሪ መንገድ አለው። ደግሞ በውኃ የተሸረሸሩ ቦዮችና የሚዘለሉ ጎድጓዳዎችም አሉበት። እና እንደምንም ደረስኩ። ባትሪ አልነበረኝም። የደረስኩት በመብረቅ ብልጭታ መንገዱን እያየሁ ነበር! አንዴ ብልጭ ሲል ወለል ብሎ ይታየኛል፤ ያየሁትን ያህል እሄዳለሁ። ያየሁት ያህል ካለቀ በኋላ እንደገና ብልጭ እስኪል እቆማለሁ ወይም በቀስታ እራመዳለሁ። ከዚያ እንደገና ብልጭ ሲል ያየሁትን ያህል እሄዳለሁ። እንዲያ እያልኩ ደረስኩ። የታየንን ያህል እየሄድን እንራመድ፤ እንደርሳለን።

5. አእምሮ፤ ልቡና ወይም ልብ ማለት ፈቃዱን ለመለየት ይረዳናል። በሮሜ 12፥ 1 በልባችሁ የሚለው ቃል በአእምሮአችሁ እንደማለት ነው በተጻፈበት ቋንቋ። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፥1-2። በውሳኔ ውስጥ አእምሮን ድርግም አድርጎ ዘግቶ የልብን ትርታ ብቻ ማድመጥ፥ ማስተዋልን ጥሎ ስሜትን ብቻ መስማት ወደ አደጋ ይጥላል። አእምሮ ቃሉ ራሱ በአማርኛ አእመረ ከማለት የወጣ ነው፤ መረዳት፥ ማወቅ፥ ግራ ቀኙን ማየት፥ ማስተዋል፥ ማመዛዘን፥ ከመምረጥ በፊት መመዘን ማለት ነው።

ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ። 1ጴጥ. 4፥7። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ

Page 5: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

5

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

አበዛልን። ኤፌ. 1፥8። በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ። ኤፌ. 4፥23። ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ቆሮ. 14፥20። አእምሮ የመንፈስን ቦታ መውሰድ የለበትም እንጂ በአእምሮስ ማሰብ አለብን። ፈቃዱን ስንፈልግ እንደ ባለ አእምሮም እናስብ፤ ማስተዋላችንን አገልግሎት ላይ እናውለው። ስናስብ የአማራጩን ውጤትና መዘዝም እናስብ። ይህን ባደርግ ብቻ ሳይሆን ባላደርግስ ብለንም እናስብ።

6. ፈቃዱን የሚፈልግ የታደሰ ሕይወት፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፥1-2። እግዚአብሔር የምንለምነውን ልመና ብቻ ሳይሆን የምንለምንበትን ምክንያትም የሚሰማ አምላክ ነው። ምክንያቱንም ይሰማል። ልባችንን ወይም አእምሮአችንን እንመርምር፤ ለራሳችንም ታማኞች እንሁን፤ ፈቃዱን ለማወቅ፥ ለመቀበል፥ ወይም ላለመቀበል የሚገፋፋንን ግፊታችንን እንወቅ። ዓለማዊ ፍላጎት ነው የሚገፋፋን ወይም መንፈሳዊ ጥማት?

7. የሌሎች ቅዱሳን ምክር፤

አንድ ሰው አንድ ጊዜ በአንድ ትልቅ ከተማ ውስጥ መንገድ ጠፋበት። ቢል፥ ቢሄድ የባሰውኑ እየጠፋ ሄደ። ከቦታው የባሰ እየራቀ መሄዱን ተረድቶ ወደሚሄድበት ቦታ እንዲደርስ ባቡር ጣቢያውን ቢያገኝ ከዚያ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ አንድ ሰው አቁሞ ጣቢያውን እንዲያመለክተው ጠየቀው። የተጠየቀው ሰውም፥ “በዚህ መንገድ ትሄድና የመጀመሪያው መገንጠያ ስትደርስ ግራውን መንገድ ውሰድ፤ ከዚያ አንድ 10 ደቂቃ ሄደህ መስቀለኛ መንገድ ታገኛለህ። እዚያ ስትደርስ ሌላ ሰው ጠይቅ” አለው። የቻለውን ያህል በትክክለኛው መንገድ መራና ከዚያ ደግሞ ሌላ ሰው እንዲመራው እንዲጠይቅ ነገረው።

ምክር ሁሉ ትክክል ላይሆን ይችላል። ትክክለኛ ምክር ደግሞ አለ። ምሳ. 24፥6 በመልካም ሥርዓት ሰልፍ ታደርጋለህ ድልም ብዙ ምክር ባለበት ዘንድ ነው ይላል። ግር ካለን ቅዱሳንን መጠየቅ ክፋት የለበትም። ምክራቸውን ባንቀበለውም እንኳ እንጠይቅ፤ ምክንያቱም የራሳችንን ውሳኔ እንድንመዝን ያደርገናል።

8. እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው ሁኔታዎች፤ አንዳንዴ የሚዘጋቸው በሮች፥ ሌላ ጊዜ የሚከፍታቸው በሮች ይኖራሉ። በሐዋ. 16፥6-10 በማይመስል ሁኔታ አንድ የወንጌል በር ሲዘጋ አናያለን። በተለይ ቁጥር 7 በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤ ይላል። ‘ለወንጌል በር እንዲዘጋ እግዚአብሔር እንዴት ያደርጋል?’ ብለው በእልከኝነት አልቀጠሉም። ሌላ የተከፈተ በር ነበረ! መቄዶንያ። ወደዚያ ሄደው ነዶ በነዶ ሆኑ።

እግዚአብሔር ፈቃዱን በማወቅ ጥበብ እና ፈቃዱን በማድረግ ታዛዥነት ይባርከን።

ጌታ ከአርያም ይባርካችሁ።

ዘላለም መንግሥቱ © 2012 (፪ሺህ፬) ዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት

ዝፈንልን አሉኝ፤

የአሁን የአሁኑን

የትናንት ወዲሁን፤

ዝፈንልን አሉኝ፥ ዝፈንልንሣ

. . . ዱሮ የሆንከውን፥ ቀድሞ ያረከውን

አንዱንም አታንሣ።

. . . አሉኝ . . . ይበሉኝ

ከወፍጮው እመጅ ላይ ከተነሣው ገላ

ከመሰለቂያው ላይ ከዛለው ሰቀላ፥

ከውስጡ ያለውን ጨርሶ ሳያውቁ

. . . በሰው መጨረሻው በአምላክ ውዳቂ

ባልሞተው ሙትቻ በኔ ሊሳለቁ፤

እኮ መች ታያቸው? መቼ ተሰማቸው?

ለተላጨው ሞገስ፥ ለማያየው የሚያይ

የእንደገና አምላክ፥ የእንደገና ጌታ እንዳለ በሰማይ፤

ምነው አልተሰማ? ምነዋ አልታያቸው?

መጨረሻዬና መጨረሻቸውን

የኔን ሌሊትና ውሎ ማምሻቸውን፤

ገምደው ሊቋጥሩ በገዛ እጃቸው

ዝፈንልን ማለት ቀረርቶ ማዘዙ፥ ሽለላን ማገዙ

ዝምታን ለመውለድ ጩኸትን ማርገዙ

ምነው በታያቸው!

ዘመ September 1998

Page 6: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

6

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

ፊል. 2፥12-13

ክርስቶስ ታዛዥ፥ ክርስቲያን ታዛዥ

ባለፈው በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ አሳብ በእነርሱ በፊልጵስዩስ ሰዎችም እንዲሆን ጳውሎስ እንዳስተማረ ተመልክተን ነበር። ኢየሱስ ራሱን ያለ ልክ ዝቅ አድርጎ ያለ ልክ ከፍ ያለ ጌታ ነው። ጌታ በምድራዊ አገልግሎት ዘመኑ አንዱ መታወቂያው ታዛዥነቱ ነው። ሉቃ. 2፥51 ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር ይላል። ሕጉ እንደሚያዝዘው እንደ ማንም ለወላጆቹ የሚታዘዝ ልጅ ለአሳዳጊው ዮሴፍና ለእናቱ ማርያም ይታዘዝ ነበር። ባለፈው መጣጥፍ በተመለከትነው በተአምረ ማርያም ኢየሱስ በጎች ይጠብቅ እንደነበረ፥ ትክክል የሆነውንም ያልሆነውንም ማርያም የምትለውን ሁሉ እየታዘዘ ተአምራት በማድረግ ይታዘዝ እንደነበረ የተጻፈው ኋላ የተፈጠረና ክፍተትን ለመምረግ የተሞከረ ምርጊት መሆኑን እያስተዋልን በጠቅላላው ግን በቤት እንደሚታዘዝ እንደማንም ልጅ ከተአምራቱ በታች ያሉትን ነገሮች ሁሉ እየታዘዘ መኖሩን ይታዘዝላቸውም ነበር ከሚለው ቃል መረዳት እንችላለን። እነዚያ በተአምረ ማአርያም የተጻፉት በልጅነቱ አደረጋቸው የተባሉት ተአምራት ውሸት መሆናቸውን የምናውቀው በዮሐ. 2፥11 ያደረገው የቃና ዘገሊላው ስተአምር የምልክቶች መጀመሪያ ተብሎ የተጻፈ በመሆኑ ነው።

ባለፈው ጥናት የተመለከትነው በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን የተባለው ይህ አሳብ የዝቅታ፥ የመዋረድ፥ የመታዘዝም አሳብ ነው። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም የተባለው ይህ እውነት ክርስቶስ ፍጹም ምንም ያልጎደለው መለኮት መሆኑንና ለዓላማ ብሎ ግን ይህንን ሥልጣን ወደ ጎን ገፍቶ የታዘዘ፥ የተገዛ መሆኑን ያሳየናል።

ይህ ወገዛት ወይም መታዘዝ (ὑποτασσόμενος ሁፖታሶሜኖስ) የተሰኘው ቃል ከገዥነት በታች፥ ከሥልጣን ሥር መሆን ማለት ነው። ለምሳሌ፥ በሮሜ 13፥1 ለበላይ ባለሥልጣን ስለመገዛት፥ በሉቃ. 10፥17-20 አጋንንት እንደተገዙላቸው በተናገሩበት እና በሌሎችም መሰል ቦታዎች (ዕብ. 2፥5-8፤ ኤፌ. 1፥22፤ 1ጴጥ. 3፥22) የተጻፈው ቃል ነው። ይህ ከሥልጣንና ከገዥ በታች የመሆን ሁኔታ ነው። ይህ መገዛት የሚለው

ቃል በፍቅርና በፈቃድ መገዛትንም የሚያመለክት ቃል ነው፤ ለምሳሌ፥ በኤፌ. 5፥21-24፤ 1ጴጥ. 3፥5፤ ዕብ. 12፥9፤ ወዘተ፥ የፍቅርና የፈቃድ ተገዢነትን ያመለክታሉ። ሁለቱም የተገለጡበት ቃል ተመሳሳይ ሆኖ የአገዛዙ ሁኔታ ነው ልዩ ልዩ የሚያደርጋቸው።

ጌታ ክርስቶስ ለወላጆቹ ብቻ ሳይሆን ፈቃዱን ለአብ ያስገዛ ጌታም ነው። እርሱ የአብን ፈቃድ ያደረገና እኛ ፈቃዱን እንድንለምን ያስተማረን ጌታ ነው። በመጨረሻዋ ቀውጢ ሰዓት እንኳ፥ ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና፥ አባቴ፥ ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን አለ አለ፤ ማቴ. 26፥42። ክርስቶስ ፈቃዱን ያስገዛ ለአስከፊው የሞት ቅጣት እንኳ የታዘዘ ጌታ ነበረ። በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ፤ ፊል. 2፥8። ጳውሎስ ይህንን የክርስቶስን መታዘዝ ገልጦ ካብራራ በኋላ ነው የፊልጵስዩስን ምዕመናን እነርሱም ይበልጥ እንዲታዘዙና ከፊት ይልቅ ታዛዦች እንዲሆኑ የመከራቸው። ጌታ ታዛዥ ነበረ። የዕብራውያን ጸሐፊ ስለ ጌታ መታዘዝና የመታዘዙ ውጤት ሲናገር በዕብ. 5፥8-10፥ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው። አለ።

ጌታ ታዛዥ እንደነበረ ካስረዳ በኋላ እነርሱም ሁሌም ታዛዦች እንደነበሩ ያንን እንዲቀጥሉ ነው የሚነግራቸው። መታዘዝ ፈቃድን ማስገዛት ስለሆነ ለሰው ተፈጥሮ የማይጥም ይመስላል። ግን የምንታዘዘው ፈቃድ የማን ፈቃድ፥ ትእዛዙም የማን ትእዛዝ መሆኑን ስናውቅ ትክክል ማድረጋችንን እንረዳለን። እግዚአብሔር በመታዘዛችን የሚደሰት አምላክ ነው። መታዘዝ ለእርሱ ከመስዋዕት ይበልጣል።

12 ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ 13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

ካለፉት ጥናቶች በአንዱ ዩጂን ስለተባለ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን ልጅ አካፍዬ ነበር። ዩጂን በመኪናው ከቤተ ክርስቲያናችን ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲወስደኝ መኪናው የስፖርት መኪና ናትና ከመንገዱ ፍጥነት እጅግ አስበልጦ (በሰዓት በ90 ኪሜ በሚነዳበት አውራ ጎዳና በሰዓት በ120 ኪሜ) ይነዳ ነበር። እመኪናው ውስጥ የተገጠመችው የሬዳር ጠቋሚ (radar detector) ከፊቱ በቅርብ ርቀት የፖሊሶችን መኖር ስለጠቆመችው ከ120 ወደ 90 ወርዶ ፖሊሶቹን ካለፈ በኋላ እንደለመደው ዝቅ ብሎ መብረሩን ቀጠለ። ለትንሽ ጊዜ በ90 መሄዱ ጉዞ ፍታት ነው የሆነበት።

ልክ እንደዚሁ አንዳንድ ሰዎች ሕግ የሚጠብቁት ፖሊስ ሲያዩ ብቻ እንደሆነው አንዳንድ ክርስቲያኖችም ክርስትናቸውን የሚለማመዱት የሚያያቸው፥ የሚታዘባቸው፥ የሚፈትሻቸው ሲኖር ወይም እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ይህ ሌላውን ማታለል ነው። ክርስትና በተመልካች ፊት ስንኖር ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር አይታለልም እንጂ እርሱንም ለማታለል መሞከር ነው። ይህ ግብዝነት ነው። ግብዞች የሆኑትን ደብቀው ያልሆኑትን መስለው የሚታዩ ተዋናዮች ናቸው። በተለይ ያልሆኑትን ለመምሰልን አጥብቀው ይሹታልና ስለዚህ ጸሎታቸው የአደባባይ፥ ጾማቸው ፊታቸውን የሚከሰክስ፥ ምጽዋታቸውና ስጦታቸው በመለከት የታጀበ ሰዎች ናቸው (ማቴ. 6)። የተቀባ፥ ያውም በስሱ ብቻ የተቀባ ሃይማኖት የለበሱ አስመሳዮች ናቸው (ማቴ. 23)። ለሰው መታየትና በሰው መመስገን የሚሹ በሰው ፊት ብቻ መንፈሳዊ የሆኑ

Page 7: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

7

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

ግብዞች ናቸው። በአዲስ ኪዳን ቋንቋ ግብዝ (ὑποκριταί ሁፖክሪታይ ወይም ሁፖክሪቴስ) በቴያትር ቦታ ያልሆነውን ወክሎ፥ ሌላውን በመሆን ጭንብል ለብሶ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ ደግሞ እውነተኛ ማንነቱን የሚኖር ማለት ነው። ይህ ሰው አንድ ሆኖ ግን ሁለት ነው። ክርስትናን በእንደዚህ ያሉ ሰዎች መለኪያ ሲለኩት ተፈትኖ የወደቀ ይሆናል። የተናቀና የማይቀበሉት ይሆናል፤ የጌታ ስምም የተሰደበ ይሆናል።

እውነተኛ ክርስትና ግን እንደ ውስጡ ውጪውም፥ እንደ ውጪው ውስጡም መሆን አለበት። የፊልጵስዩስ ምዕመናን ጳውሎስ አብሮአቸው በነበረ ጊዜ ታዛዦች መሆናቸው የተረጋገጠ ነው። ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ ይላቸዋል። ግን መታዘዛቸው ጳውሎስ አብሮአቸው ስለነበረ ነው ወይስ ባይኖርም የሚታዘዙ ነበሩ? ያኔ አብሮአቸው ሳለ ሁሌ እንደታዘዙት አሁን እርሱ ከፊታቸው ሲርቅ የተለየ ባህርይ እንዲታይባቸው ስላልፈለገ፥ ቴያትረኞች እንዳይሆኑ ስለፈለገ፥ አሁንም እንደቀድሞው በመሆን ቀጥሉ፥ ታዘዙ፥ መዳናችሁን እንደጀመራችሁት ጨርሱት ይላቸዋል። በፊል. 1፥27ም ይህንን የሚመስል ተመሳሳይ ነገር ነግሮአቸው ነበር፤ እንዲህ ሲል፥ ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ። በእውነቱ የፊልጵስዩስ ምእመናን እምነት በጳውሎስ በመካከላቸው መገኘት ላይ የተደገፈ አልነበረም፤ ጳውሎስም ይህንን ያውቀዋል። ግን እንደ ክርስቲያን አገልጋይ አብሮአቸው በመኖሩ እንደነበሩት ያለ እምነት ባለመኖሩም እንዲያሳዩ፥ በፊት የሆኑትን አሁንም፥ እንዲያውም ከዚያ ባለፈ ክርስትናቸው የጠራ እንዲሆን ያሳስባቸዋል።

ፈሪና ተንቀጥቃጭ ክርስቲያን ክርስትናቸውን እንዲፈጽሙም ይነግራቸዋል። መፈጸም ሲል እስከ መጨረሻ ድረስ መያዝን መጠበቅን መግለጡ ነው። ይህ እዚህ የተጠቀሰው መፈጸም አንድን ዕቃ ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ መድረስ ያለበት ስፍራ ማድረስ እንደማለት ነው። ይህ የሚፈጸም ነገር ቀድሞውኑ የተጀመረ ሥራ ነው። በእነርሱ መልካምን ሥራ የጀመረው ደግሞ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ጳውሎስ ቀድሞ ነግሮአቸዋል። ይህ የሚፈጸም ነገር እኛ የምንሠራው፥ በእኛ ፈቃድ የሚደረግ ነገር ቢሆንም ይህንን በእኛ አድርጎ የሚሠራውና የሚፈጽመው እግዚአብሔር ነው።

መዳናቸውን እንዲፈጽሙ ብቻ ሳይሆን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ እንዲፈጽሙ ያሳስባቸዋል። ይህ በመበርገግ መኖር ሳይሆን ጤናማ ፍርሃት ነው። ራስን በመግዛት፥ ከውስጣዊ ርኩሰት ለመራቅና በመንፈሱ በመደገፍ የመኖር ፍርሃት ነው። በፈተና መከበባችንን ተረድቶ፥ ኅሊናችን ንቁ ሆኖ፥ የሰው ልብ ክፉ መሆኑን አውቆ የመኖር ፍርሃት ነው። ጳውሎስ በሮሜ 11፥20 ስለ አይሁድ ሲናገር፥ ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ እንዳለው ከትዕቢት የመራቅና የቆምን መስሎን እንዳንወድቅ የመጠንቀቅ የጥንቃቄ ፍርሃት ነው። እግዚአብሔርን ከሚያስከብር ነገር ጋር ለመቆምና ከማያስከብር ነገር ለመራቅ የመቁረጥ ውሳኔ ያለበት የአክብሮት ፍርሃት ነው። ክርስቲያን የመሳቀቅን ፍርሃት እየፈራ የሚኖር አይደለም። አጉል ደፋርም ደግሞ አይደለም። ነገር ግን ቀኑን ሁሉ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖር ገና ፍጹም ያልሆነ ሰው ነው።

መዳናችንን በተመለከተ ሁለት የተራራቁ አመለካከቶች አሉ። አንዱ መዳኔን እርግጠኛ የምሆነው ሄጄ ፊቱን ሳየው ብቻ ነው። አሁን ብድንም ወይም የዳንኩ ብሆንም እንኳ ደኅንነቴ ሊጠፋና እኔም የገሃነም እራት ልሆን የምችል ሰው ነኝ የሚል ነው። ሁለተኛው፥ አንዴ ዳንኩ ለሁሌም ድኛለሁ፤ እና ኃጢአትን ብለማመድም ደኅንነቴ ዋስትና ያለው ነው የሚል ነው። ሁለቱን ያፈነገጡ ነጥቦችንና ከፊል እውነቶችን የያዙ ናቸው። የመጀመሪያው እዚያም ሄደን ፊቱን ስናይ እርግጠኛ ብንሆንም ያንን እርግጠኝነት አሁንም መለማመድ እንችላለንና ስሕተት አለበት።

ደግሞም ደኅንነታችን የእውነት ደኅንነት እስከሆነ ድረስ ከእጁ ነጥቆ የሚያወጣን ምንም ኃይል የለም። ስለዚህ በመዳናችን መደሰትና ሳንሳቀቅ የመኖርን እርካታ ከመዳናችን እርግጠኝነት ጋር ልንለማመደው ይቻለናል።

የሁለተኛው ነጥብ ችግር የመዳናችንን እርግጠኝነት ኃጢአትን እንድንለማመድ የፈቃድ ወረቀት ማድረጉ ነው። በእውነት የዳነ ሰው፥ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ሰው ኃጢአትን ይጸየፋል እንጂ በኃጢአት አይደሰትም። ፍጹም ነው ወይም በኃጢአት አይወድቅም ማለትም አይደለም። ግን በኃጢአት ውስጥ ተመቻችቶ አይኖርም።

እንዲህ ከሆነ ክርስትና ሚዛናዊ ሕይወት መሆኑን እንገነዘባለን። ክርስትና ደኅንነት ነው። ደኅንነቱም የተረጋገጠና የሚፈጸም ነው። ሲፈጸም ደግሞ ንጽሕናና አክብሮትን፥ አምልኮና ቅድስናን የተቀዳጀ እውነተኛ ፍርሃት ያለበት ነው። ይህ መዳንን መፈጸም ደኅንነትን እስከ መጨረሻው፥ እስከ ፍጻሜው ኮስተር ብሎ አጥብቆ መያዝን የጨበጠ ትምህርት ነው። የመዳናችን ፍጻሜ የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው። በክርስትና ሕይወታችን የኛ ንቁና ፈቃደኛ ተሳትፎ የሚጠበቅ ቢሆንም መዳናችንን ፍጹም አድራጊው እግዚአብሔር ነው።

ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። በዚህ ጥቅስ ማድረግ የሚለው ክርስቲያኖቹ የሚያደርጉት ማድረግ እና የሚሠራ የሚለው የእግዚአብሔር አሠራር ተመሳሳይ ቃላት ናቸው። ሁለቱም ቃላት ጉልበትን ኃይልን የሚጠይቅ ነገርን ማድረግ እንደማለት ነው። ክርስቲያኖቹ ለሚያደርጉት ነገር ጉልበትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። ጉልበትን፥ ዕድል ወይም አጋጣሚን፥ ጸጋና ስጦታን፥ ኃይልና ችሎታን የሚሰጥ እርሱ እግዚአብሔር ነው። መሻትንና መመኘትን ብቻ አይደለም፤ ያ መሻትና ፍላጎት ተግባራዊ የሚሆንበትን ኃይል ሰጪ እርሱ ነው። የሚሰጠውም ስለ በጎ ፈቃዱ ነው።

ይህ በጣሙን አጽናኝ ጥቅስ ነው። አንዳንዴ የአንድ መልካም ነገር ፍላጎት ኖሮን አቅም ያንሰናል። ያኔ ይህን አንድ ነገር እንወቅ፤ ለመልካሙ ምኞት ተፈጻሚነት ጉልበትን መስጠት የሚችል አምላክ አለን። ይህ ጥቅስ ይህንን ያስተምረናል። አንዳንዴ ደግሞ ትክክለኛውን ነገር የመፈለግ ፍላጎትም እናጣለን። ያኔም ይህ እውነት ያጽናናን፤ እግዚአብሔር ትክክለኛውን ነገር መፈለጉንም በኛ ውስጥ መሥራት ይችላል።

መልካም ነገርን፥ መልካም ምኞትን፥ መፈለግን፥ መሻትን በውስጣችን እንዲያደርግ ብንለምንና ብንፈቅድ ይህን ማድረግ ይቻለዋል። እግዚአብሔር ለመልካም ነገር ሊያነሣሳንም፥ ለዚያ መነሣሳት የሚሆን ጉልበት ሊሰጠንና ሊያስደርገንም የሚቻለው አምላክ ነው። ይህንንም የሚያደርገው ስለ በጎ ፈቃዱ ነው። በጎ ፈቃድ የተሰኘው ቃል በሁለት የአማርኛ ቃላት ተሠራ እንጂ በምመጀሪያው ቋንቋ አንድ ቃል ነው። ይህ

ቃል (εὐδοκία ኤውዶኪያ) εὖ ወይም εὖς (መልካም) እና δοκέω (ማሰብ) በሚሉ ሁለት ቃላት የተሠራ ሆኖ መልካም አሳብ፥ ውብ ምኞት፥ ወይም እዚህ እንደተጻፈው በጎ ፈቃድ ማለት ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ቃሉ በተጠቀሰባቸው ቦታዎች የሰውን መልካም መሻትም የእግዚአብሔርን ፈቃድም ለመግለጥ ተጠቅሶአል። ለምሳሌ፥ በማቴ. 11፥26፤ ሉቃ. 10፥21፤ ኤፌ. 1፥5 እና 9 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሲገልጥ፤ በሉቃ. 2፥14፤ ሮሜ 10፥1፤ 2ተሰ. 1፥11 የሰውን ፈቃድ ይገልጣል። በፊልጵስዩስ ውስጥ ቃሉን ጳውሎስ ሁለቴ የተጠቀመው ሲሆን አንዴ በፊል. 1፥15 የሰውን ፈቃድ በዚህ በ2ኛው የጌታን ፈቃድ ለመግለጥ ጽፎታል። እግዚአብሔር ለእኛ ፈቃዱና አሳቡ በጎ ነው። እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ወይም በእኛ አማካይነት የሚሠራውን ሥራውን ሁሉ የሚሠራው በመልካም አሳብ፥ በበጎ ፈቃድ ነው። ይህ የሚያስደስትና የሚያሳርፍ እውነት ነው።

ጌታ ከአርያም ይባርካችሁ።

ዘላለም መንግሥቱ © 2012 (፪ሺህ፬) ዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት

Page 8: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

8

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤ ማንም የማያውቅ ቢኖር ግን አይወቅ።

1ቆሮ. 14፥37፥38

በጣም ጥንት የ3ኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ስሜ የሚባል የክፍላችን ተማሪ ነበረ። በመጀመሪያው የትምህርት ቀን የክፍል አስተማሪያችን ስማችንን ሲመዘግብ እኔ አጠገብ የተቀመጠው የስሜ ተራ ደረሰ። አስተማሪው፥ “ስምህ ማነው?” አለው። “ስሜ ሲአሞ” ብሎ መለሰ። “ሲአሞ ማን?” የአያቱን ስም ተናገረ። እስከ አያቱ ተጠይቆ መናገሩ ገርሞናል። ልጁ ስሙን ከነአባቱ ሲናገር አስተማሪው፥ “ስሜ ሲአሞ ነው” ያለው ነበር የመሰለው። ከዚያ በኋላ በደንብ እስኪያውቀው ድረስ ለብዙ ሳምንታት አስተማሪያችን ስሜን በአባቱ ስም ሲአሞ እያለ ይጠራው ነበር። አሁንም በልጅነቴ አንድ ሰው አባቴን የሚጠራው አጠራር ከነድምጹ ይታወሰኛል። ሲጠራው “ጋሼ ሻምበል” ይለው ነበር። ሻምበል ስሙ መስሎታል፤ ወይም ከማዕረግ በፊት ሌላ የማዕረግ ፎቅ መደረቡ ነው።

በቅርብ ደግሞ አንድ ዲቪዲ ላይ ይሰብክ የነበረ ሰውን ሲመለከቱ አንድ ቤት ደረስኩና ማን መሆኑን ስለማላውቅ ጠየቅኩ። ስሙን፥ “ነቢዩ ይባላል፤ ነቢዩ እገሌ” አለችኝ አንድዋ እኅት። ሌላዋ ደግሞ፥ “የለም ስሙ እገሌ ነው እንጂ ነቢዩ አይደለም፤ ነቢዩ ሹመቱ ማዕረጉ ነው” ብላ አብራራች። አስተማሪያችን ልጁን በአባቱ ስም ጠራ። እዚህ ደግሞ ማዕረጉና የሰውየው ስም ተምታቱ። የተምታቱ ነገሮች ዘመን ላይ ነን።

ባለፉት 3 እና 4 ዓመታት ሐዋርያው እገሌ የሚባለውን ሹመት ተከትሎ አምናና ዘንድሮ ደግሞ ነቢዩ እገሌ የሚባሉ ሰዎች መታየት ጀምረዋል። “እውነት ሐዋርያት በዚህ ዘመን አሉ?” ተብሎ ለተነሣው ጥያቄ በሁለቱም አቅጣጫ ሰፋ ያሉ ነገሮች ተብለዋል። ከፊልጵስዩስ ጥናቶች በአንዱ (1፥1-2) ስለ ሐዋርያ በጥቂቱ ጽፌ ነበር። እኔ ከቃሉ እንደምረዳው ሐዋርያ የሚባል አገልግሎት አለ። አንዳንዶቹ ‘ቢሮ’ (office) እንደሚሉት ግን ሹመት አይደለም። ሐዋርያ ማለት ወንጌልን ይዞ ቤተ ክርስቲያን ልካው ወንጌል ወዳልተነገረበት ጠፍ ምድር ወንጌልን ሊሰብክ የሄደ ቤተ ክርስቲያን ቆርቋሪ ወይም ተካይ ሰው ነው። የሄደ ሰው። በአማርኛ ቃሉ ራሱ የሄደ ማለት ነው። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ቋንቋ ደግሞ የተላከ ማለት ነው። ሐዋርያ ማለት ይኸው ነው። ይህንን የሚያደርጉ ሐዋርያ ቢባሉ ትክክል ነው። ይህ እንግዲህ በዚህ ዘመን ነው። ያኔም ሆነ አሁንም ሐዋርያነት የጸጋ ስጦታም ነው፤ ይህ ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡበት ሁኔታም ነው። ሁለቱም ነው። በዘመናችን እንደሆነው ግን ሐዋርያነት የብዙ ዘመን አገልግሎት መለዮ ወይም ከፍተኛ የሹመት እርከን ወይም የክብር ማዕረግ አይደለም።

ያኔ ጌታ የሾማቸውና በቀጥታ የላካቸው ሐዋርያት በራሱ የተሾሙ ናቸውና መደባቸውም ሹመታቸውም የተለየ ነው። ጌታን ያወቅንባቸውን ቃሉን የጻፉልን ብቻ ሳይሆኑ በእጆቻቸው ድንቆችና ምልክቶች የተደረጉባቸው ሰዎችም ናቸው። ከአምናና ካቻምና ወዲህ የሚታዩት ሐዋርያት የሐዋርያነትን ሹመትና ማዕረግ ከሚያሳድዱ ይልቅ የሐዋርያን አገልግሎት ቢሹ ኖሮ ምንኛ ድንቅ ነበር። ዘንድሮ ስማቸውንም ሳይቀር እየቀየሩ ሐዋርያው ጳውሎስ እና ነቢዩ ዳንኤል ተብሎ መጠራት ወግ

እየሆነ ነው። ዝም ከተባለ ይህኛው ሥልጣን ከዓመት ወይ ከሁለት ዓመት በኋላ ይነፍስበትና በሚቀጥለው ደግሞ ንጉሡ ዳዊት ሳይሆኑ ይቀራሉ? አሁንም እንኳ ‘የንጉሥነት ቅባት’ የሚሉትን የጀመሩ የቃል-እምነት ሰባኪዎች ብቅ ብቅ ብለዋል። እኛስ ደህና፤ ብቻ ይህ ከምድራዊ መንግሥትም ጋር እንዳያጋጫቸው ያስፈራል። አሁንም ዝም ከተባሉ ሞዓ አንበሣ ምናምን ማለትም ይከጅላቸው ይሆናል።

አሁን ደግሞ ስለ ነቢያት እንይ። እነዚህ ሰዎች እውነት ነቢያት ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቃችን በፊት ነቢይ ምንድርነው? ምን ያደርጋል? ብለን መጠየቅ ለንጽጽር ይረዳናል።

ነቢይ ማለት ትርጉሙ እግዚአብሔርን ወክሎ የሚናገር ወይም ለእግዚአብሔር የሚናገር ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን ቋንቋ ነቢይ የሚናገር (ናቢ) ወይም የሚያይ (ሮዔ) ይባላል። ሮዔ ባለ ራዕይ እንደሚባለው ማለት ነው። ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም ሲናገር ያ የሚናገረው ነገር የራሱ አይደለም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ነውና ሥልጣን አለው፤ ከተጻፈም ዘመናትን የማለፍ ኃይል አለው። ነቢዩ ሲያይ ወይም ሲሰማም በተራ ዓይንና ጆሮ ከሚቀበሉት ያለፈ ነገርን የተቀበለ ሰው ነው። እንደ እግዚአብሔር ወካይነቱ በተወከለለት ኃይል ለሁሉ የሚታዩ ግልጽ ዓላማቸውም የላከው ክብር፥ ግባቸውም የሕዝቡ ጥቅም የሚሆኑበትን ተአምራት ያደርጋል። የብሉይ ኪዳን ነቢያት ይህን የሆኑ፥ እነዚህንም ያደረጉ ናቸው።

በዘመናችን እየታዩ የመጡት ነቢያት ከአገልግሎት አንጻር ስለሆነ ከዚህ መነሻ ትርጉም ተንደረደርኩ እንጂ በብሉይ ኪዳን ነቢይ የሚለው ቃል ከዚህ ሌላ አሳብንም የያዘ ነው። ከላይ እንዳየነው ወክሎ ቃልን የመናገር ወይም አይቶ የማሳየት ነገር ያላደረጉ ሰዎችም ነቢይ ተብለው ተጠርተዋል። ምናልባት ተናግረው ይሆናል አልተጻፈም እንጂ የሚለውን አልተጻፈምና አናነሣውም። በዚህ ተርታ አብርሃም ነቢይ ተብሎአል፤ ዘፍ. 20፥7፤ አሮንም ነቢይ ነበር፤ ዘጸ. 7፥1። ሌሎችም የአሮንን እኅት ማርያምን፥ ሰፋኒቱን ዲቦራን፥ ናታንን፥ ጋድን፥ የኢሳይያስን ሚስት ጨምሮ ነቢያት ናቸው። ነቢያት ሲታሰቡ በብሉይ ኪዳን ዘመንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ሐሰተኞች ነቢያትም መኖራቸውና እውነተኛ ነቢያት ከሐሰተኞቹ ተለይተው የሚታወቁባቸው የተዘረዘሩ መፈተሻዎች መኖራቸውም መረሳት የለበትም።

ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ በአዲስ ኪዳን ነቢያት መኖራቸው እውን ነው። ነቢይ ሲባል በዘልማድ የሚመጣልን ትርጉም ወደፊት የሚሆነውን የሚናገር የሚል ነው። ይህ ነቢይ ከሚያደርጋቸው ነገሮች አንዱና ዋና ያልሆነው ነው። ይህ ዋናው የነቢይ ትርጉም አይደለም። ይህንን ለመረዳት የነቢያትን መጻሕፍት ማንበብ ብቻ በቂ ነው። የአብዛኞቹ ነቢያት አብላጫው ይዘታቸው የቀደመው ወይም በጊዜው የነበረው ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንጂ ወደፊት የሚሆነውን የሚናገር አይደለም። ስለወደፊት የሚናገረው የፍርድም ይሁን የበረከት ቃል በአንድ አንቀጽ ወይም በአንዲት ጥቅስ ብቻ ተጽፎም የሚገኝባቸው የትንቢት መጻሕፍት አሉ።

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ቋንቋ ነቢይ ወይም ትንቢት ተናጋሪ ገልጦ የሚናገር፥ አውጥቶ፥ ወደፊት አምጥቶ የሚናገር ማለት ነው። ነቢይ ቤተ ክርስቲያንን ለራእይዋ፥ ለተልእኮዋ፥ ለጥሪዋ የሚያነሣሳ መልእክት የመናገር ስጦታ ያለው ወይም ከላይ እንደተገለጠው እውነትን ገልጦ በማሳየት መነሣሳትን የሚያመጣ አገልጋይ ነው።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግልጽ እንደምናየው ነቢያትም ነበሩ፤ የትንቢት ስጦታም ነበረ። ነቢይነት ግን ሹመት ሆኖ እነዚህ ሰዎች “ነቢዩ እገሌ” ሲባሉ አይታይም። በሐዋ 13፥1 በአንጾኪያ ነቢያትና መምህራን እንደነበሩ ተጽፎ ስማቸውም ተዘርዝሮአል። ግን ነቢዩ በርናባስ፥ መምሬ ስምዖን፥ መጋቢ ሉክዮስ፥ ወዘተ እየተባለ አልተጻፈም። ጸጋው አላቸው ጸጋው ግን ሹመታቸው አልነበረም። በሐዋ. 15፥32 ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ነበሩ። ግን ነቢዩ ይሁዳና ነቢዩ ሲላስ አልተባሉም። ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው በማጽናታቸው ጸጋቸው ከአገልግሎታቸው ጋር በጉልህ

Page 9: ezralit@gmail.com ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረትdeqemezmur.com/wp-content/uploads/2016/02/Ezra-Literature-Mag... · የተፈጠሩ ፍሬዎች ናቸው። 3. መቀደሳችን፤

9

ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2012 [email protected]

ተጽፎአል። በሐዋ. 21፥10 ነቢይ የነበረ አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተብሎ ተጽፎአል። ነቢዩ አጋቦስ ግን አልተባለም። ምንድርነው ልዩነቱ ነቢዩ አጋቦስ እና አጋቦስ የሚሉት ነቢይ ቢባል ልዩነቱ ትኩረቱ ነው። ነቢይ እና ነቢዩ የተለያዩ ናቸው። ሐዋርያና ሐዋርያው የተለያዩ እንደሆኑ ማለት ነው። በነገራችን ላይ፥ ነቢዩ የሚባል ወይም የተሰኘ ነቢይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የለም። ከኢየሱስ በቀር። አዲስ ኪዳን ነቢዩ የሚለውን ቃል ሲጠቅስ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ሲገልጥ ብቻ ነው።

በ1ቆሮ 12፥28-29 እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ነቢያትንም ማድረጉ ተጽፎ ነቢያት ምን ማድረግ እንዳለባቸውም ተጽፎአል። በ14፥29 ደግሞ ነቢያት ሁለት ወይ ሦስት ሆነው በጉባኤ እንዲናገሩ ሌሎችም እንዲለዩአቸው ተጽፎአል። ነቢይ የሆነ ወይም የመሰለው ማንም ስጦታውንና ስፍራውን ለመረዳት ጠንቅቆ መረዳት ያለበት ምዕራፍ ይህ 1ቆሮ. 14 ነው። ነቢይነት ሥልጣን ከቶም አይደለም። ለነገሩ የአዲስ ኪዳን ወይም የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን በሰው ትከሻ ላይ ተረማምዶ ወደ ቆጥ ወጥተው የሚሰቀሉበት ሳይሆን ትኅትናን እንደ ልብስ ተላብሰው እርስ በርስ እየተዋረዱ ዝቅ በማለት የሚያገለግሉበት ነው።

አንዳንዶች ዛሬም ከቀደሙት ተርታ ብቻ ሳይሆን ከቀድሞዎቹ የበለጡ ሐዋርያትና ነቢያት በዘመናችን እንዳሉ ወደፊትም እንደሚነሡ ይናገራሉ። በምዕራቡ ዓለም ሐዋርያው ወይም ነቢዩ የሚባሉት እንዲያውም ከቀደሙት ነቢያትም አቻ ብቻ ሳይሆን የላቁ መሆናቸውን ለማሳየት ሐዋርያትና ነቢያት ብቻ ሳይሆን “Super Apostles and Prophets” እየተባሉ ነው የሚጠሩት። ከቃሉ እንደምንረዳው የቀደሙቱ ሐዋርያትና ነቢያት በምልክትና በድንቆች ማንነታቸው የተገለጡ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን እናጢን፤ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ የሐዋርያነት ምልክት ሊሆኑ ያለመቻላቸው ወይም በሰይጣንም ሊደረጉ የሚችሉ መሆናቸው አንዱ ነው። ሌላው ደግሞ፥ በዘመናችን ተደረጉ የሚባሉት ምልክቶች አንዳንዶቹ በቅርበት ሲጤኑ ያሉ የመሰሉ ግን ከቶም ያልኖሩ መሆናቸው ነው።

እነዚህን ነጥቦች ይዘን የዘመናችን ነቢያትና ሐዋርያት ከቀድሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያትና ሐዋርያት ተርታ የማይሰለፉ መሆናቸውን ከሌላም አንጻር እናያለን። ይህን የአሁኖቹ በላጮች መሆናቸውን የሚያስተምሩ ሰዎች ትልቅ ስሕተት እዚህም ላይ ነው። የቀድሞዎቹ ነቢያትና ሐዋርያት የእምነታችን መሠረቶች ናቸው። በሐዋርያትና ነቢያት መሠረት ላይ ተመሥርተናል፤ የማዕዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ነው፤ ኤፌ. 2፥20። ከዚህ አንጻር የዛሬዎቹ ሐዋርያትና ነቢያት እነዚያን ሊሆኑ ከቶም እንደማይችሉ እናያለን። ሌላ አዲስ ነገር እየመሠረቱ ካልሆነ በቀር። መሠረቱ አንዴ ተመሥርቶአልና በየዘመናቱ እንደገና አይመሠረትም።

ነቢያት ነን የሚሉ ሰዎችን ነቢይነታቸው ጸጋ ወይም ሥልጣን መሆኑን እንዲናገሩ ማድረግ ተገቢ ነው። ጸጋ ከሆነ ነቢዩ እገሌ መባል የለባቸውም። ከሆነ የመስጠት ጸጋ ያለው “ለጋሱ እገሌ” የፈውስ ስጦታ ያለውም “ፈዋሹ እገሌ” እውቀትን መናገር የተሰጠው “አዋቂው እገሌ” በልሳን መናገር የተሰጠውም “ልሳናሙ ወይም ባለ ልሳኑ እገሌ” ሊባሉ ነው። እነዚያ ነቢዩ ከተባሉ እነዚህም እንዲህ የማይባሉበት ምክንያት የለም። እንዲህ ያሉ ሰዎችን በቃሉ መሠረት መርታት ካልቻልን መራቅ አለብን።

ሌላው በነዚህ ራሳቸውን በራሳቸው በሚሾሙ ሰዎች ዘንድ የሚታይ ከፍተኛ የሥልጣን ጥም አለ። ከገንዘብ ጋር ክፉኛ የመቆራኘትና ሰዎችን መጠቀሚያ ለማድረግ ሥጋዊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ጠምዶ የማቆየት ሥርዓትም አለ። እንዲህ ከሆነ እነዚህ እውነተኞች ሳይሆኑ ሐሰተኞች ነቢያት ናቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ በመልእክቶቻቸው አጽንተው የገለጡልን ሐሰተኞች ነቢያትም እንደሚነሡ ነው፤ 2ጴጥ. 2፥1 እና 1ዮሐ. 4፥1። እና ነቢዩ እገሌ ሲባል እናጢን፤ እንጠንቀቅ፤ እናስተውል፤ እንጠይቅ።

ጌታ ከአርያም ይባርካችሁ። ዘላለም መንግሥቱ © 2012 (፪ሺህ፬) ዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት

ልቀቃት

የወደድካትን . . .

የወሰድካትን . . .

ወፍ ነገር

ልቀቃት ትብረር፤

እያት ፈትናት

ከመጣች ያንተ ናት፤

ካልመጣችም. . .

ከሄደችም

ትሂድ ጦስክን ይዛ

አንተ ግን አደብ ግዛ፤

አደብ ገዝተህ

እጅህን ከፍተህ

ጠብቅ ጌታህን

እንዲያነጋው ማታህን፤

እንዲቸርህ በራሱ ጊዜ . . . በራስህ ተራ

ከለጋስ እጁ . . . ከሞላው ጎተራ። ዘ. መ. የካቲት ፥