78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን...

9
በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! 78ኛ ዓመት ቁጥር 177 ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር የማህበራዊ ዋስትና በሀገራችን ከተጀመረ ግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የዕቅድ ሽፋኑ በመንግሥት ሠራተኞች፤ በመከላከያና በፖሊስ ሠራዊት አባላት ላይ ብቻ ተወስኖ ቆይቷል። ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ብሎም የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራሞችን ማጠናከርና ማስፋት የሚለውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማሳካት ይቻል ዘንድ የግል ድርጅቶች ሠራተኞችን የማህበራዊ ዋስትና የሚደነግግ የጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ወጥቶ ተግባር ላይ እየዋለ ይገኛል። የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አዋጁን በማስተገበር በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎችን የማህበራዊ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚሰራ የመንግሥት ተቋም ነው። በዚህም የማህበራዊ ዋስትና መስፋፋት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስችላል የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሌላ በኩል ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን እውን በማድረግና የዜጎችን የቁጠባ ባህል በማሳደግ ዘላቂና የተረጋጋ ሀገራዊ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ችሏል። ባለፉት ዓመታት፣ በኤጀንሲው ስለፕሮግራ ሙና ስለአሰራሩ ለዜጎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ መረጃዎችን ተደራሽ የማድረግ፣ የምዝገባ ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን የማጠናከር፣ የዕቅድ አባላትን ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ፣ የኢንቨስትመንትና ፈንድ አስተዳደር በተጨማሪም፣ በድጋፍ ላይ ውጤታማ ስራዎችን አከናውኗል። ይህን ስኬታማ የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራም የማስተገበር ሂደት ስርዓቱን ጠብቆ ለማስቀጠል በየጊዜው እየታደሰ በሚሄድ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይመራል። የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራሙ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው የዜጎችን ማህበራዊ ደህንነትና የሰብዓዊ መብት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው። ሀገሪቱ በምትከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲና እየተመዘገበ ካለው እድገት አንጻር ሲታይ፣ ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ ከሚከናወኑ ሥራዎች አንዱና ዋነኛው ተግባር ሲሆን፣ በዚህ ፕሮግራም የገቢ መቋረጥ እንዳይከሰት የማህበራዊ ዋስትና ሽፋን በመስጠት ዜጎች ለችግር እንዳይጋለጡ ማድረግ ይቻላል። ይህም የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ ዋነኛ መሳሪያ ነው። ሊሳካ የሚችለውም በርካታ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በዕቅዱ እንዲታቀፉ በማድረግና በዕድሜና በሌሎች ምክንያቶች ሊደርስ የሚችለውን የገቢ መቋረጥ በማስቀረት የገቢ ድጋፍ በመፍጠር ድህነትን በመቀነስ ረገድ የሚደረገው ጥረት ነው። በእስካሁኑ የትግበራ ሂደት የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋንን አስፈላጊነት የተረዱ፣ ጥቅሙም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የገባቸው የግል ድርጅቶች አዋጁን ተቀብለው ኃላፊነታቸው እየተወጡ ይገኛሉ፤ ይሁን እንጂ አዋጁ የጣለባቸውን ግዴታዎች በተገቢው የማይወጡ ጥቂት የግል ድርጅቶች ዛሬም አልጠፉም። የዜጎችን ማኅበራዊ ዋስትና የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት ማስከበር ይቻል ዘንድ ኤጀንሲው ግዴታቸውን የማይወጡ የግል ድርጅቶች ሲገጥሙት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ወደ ሕግ አስገዳጅነት ይገባል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የማኅበራዊ ዋስትና መስፋፋት የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚኖረውን ወሳኝ ሚና በመረዳት ሁሉም የግል ድርጅቶች ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። አድራሻ- አራት ኪሎ ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት አጠገብ ስ.ቁ-011 1 55 03 67/68/76 ነጻ ስልክ ቁጥር 888/1/2/7 ድረ ገጽ- www.poessa.gov.et ኢ ሜይል [email protected] ማኅበራዊ ድረ ገጽ- www.Facebook.com/poessa ፖ.ሳ.ቁ. 33921 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የፓርቲዎች... በ2ኛው ገጽ ዞሯል የፓርቲዎች ውህደትና ጥምረት ለተሻለ አማራጭ ዘላለም ግዛው በመጪው ምርጫ 2012 ዓ.ም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ እንዲያገኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውህደት ወይም ጥምረት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ምሁራን ይገልጻሉ። ተመሳሳይ ፍላጎትና ፕሮግራም ያላቸው ፓርቲዎች ቢሰባሰቡ የሚያስቡትን ግብ ከማሳካትና የፖለቲካ ስልጣን ከመቆጣጠር አንጻር አቅም እንደሚፈጥሩ፣ ጥምረታቸው ለአገርም ለህዝብም እንደሚጠቅም ያስረዳሉ። በግጭት አፈታት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ኮሚቴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እየጠበቀ ነው አንተነህ ቸሬ አዲስ አበባ፡- የዓድዋን ድል ለመዘከር ለሚገነባው የዓድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚያስችል ዝግ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆኑን የዓድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የምስረታ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ። የኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ቢተው በላይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የዩኒቨርሲቲው... በ2ኛው ገጽ ዞሯል ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በሩን ከፍቷል • ከአጋር ፓርቲዎች ጋርም በቅርቡ ውህደት ይፈጽማል አጎናፍር ገዛኸኝ አዲስ አበባ፦ ኢህአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመቀላቀል በሩ ከፍት መሆኑን እና ከአጋር ፓርቲዎችም ጋር ውህደቱ በቅርቡ እውን እንደሚሆን አስታውቋል። የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ፤ ለአዲስ ዘመን በሰጡት ማብራሪያ ድርጅቱ ማሻሻያ እያደረገ ነው። ማሻሻያ ሲያደርግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በሩን ዘግቶ አይደለም። አብሮ መሆን የሚወሰነው ግን በተፎካካሪ ፓርቲዎች ፍላጎት ነው። በዓላማ የሚጣጣም ካለና ዓላማውን የሚደግፍ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ አብሮ ለመስራት ከፈለገ የኢህአዴግ በር ክፍት መሆኑን ገልጸው፤ ግን አብረን እንሁን ብሎ ማንንም አያስገድድም ብለዋል። ኢህአዴግ የህዝብ ድርጅት ነው ያሉት አቶ መለሰ፤ በባህሪይው ተራማጅ በመሆኑ እንደየጊዜው ስልቶቹን በመንደፍ አገሪቱን ከኋላ ቀርነት በማውጣትና የዳበረ ዴሞክራሲ በመፍጠር የበለጸገች ኢትዮጵያ ለመገንባት ይሰራል። ይህ ረጅም ጊዜ የሚወስድና በኢህአዴግ ብቻ የሚያልቅ ሳይሆን የሌሎች ፓርቲዎችንና ግለሰቦችን የትግል አስተዋፅኦ የሚጠይቅ ነው። እንደ አንድ ፓርቲ የትውልዶችን ትግል ለሚጠይቀው ጉዞ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ካሉ ኢህአዴግ የእኔ ብቻ የሚልበት ምክንያት የለም። ከአጋር ፓርቲዎች ጋር ለመዋሀድ የሚደረገው ሂደት ቀደም ብሎ ጥናቱ ተጠናቅቋል። የጥናቱ ውጤት ለፓርቲዎቹ ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ በቅርቡ የኢህአዴግና የአጋር ድርጅቶች ውህደት ይፈፃማል። ፓርቲዎች ሰብሰብ ብለን ለአገር የሚጠቅም ሥራ ማከናወን አለብን። መሰባሰቡ አገሪቱ የምትፈልገውን ውጤት ለማምጣት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል። ከአቶ መለሰ አለሙ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በገጽ 11 ላይ ያንብቡ። የአምቦ ከተማ የቱሪስት መዳረሻዎች በጽህፈት ቤቱ እጅ አይደሉም ዳንኤል ዘነበ አምቦ በአምቦ ከተማ የቱሪስት መዳረሻ ተብለው የተለዩ ስፍራዎች በባህልና ቱሪዝም እጅ እንደማይገኙ የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጉሬ ታሱ ገለጹ። የአምቦ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለመለየት በተደረገው እንቅስቃሴ አምስት ስፍራዎች፤ ማለትም የአምቦ ውሃ፣ ፊንጫ ኦብሴ (ፏፏቴ )፣ የእግዜር ድልድይ፣ ፍልውሃ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት የተለዩ ሲሆን፤ በሁሉም ላይ ጽህፈት ቤቱ አያዝባቸውም፤ ብለዋል። አያያዘውም፤ የተለዩትን ቦታዎች አስከብረን ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ የማድረግና ወጣቶች ተደራጅተው እንዲሰሩ የማብቃት እቅድ ቢኖርም አምስቱም የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች በአሁኑ ወቅት በከተማው የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ስር አይገኙም ብለዋል። ከተለዩት የቱሪስት ቦታዎች የአምቦ ውሃ፣ የፊንጫ ኦብሴ (ፏፏቴ )፣ ፍልውሃ በግለሰብ እጅ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጸው፤ የከተማው ህዝብ ሀብት በምን መንገድ ለግለሰብ እንደተሸጠና የአምቦ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል ስፍራዎቹ እንዴት በግለሰብ እጅ እንደወደቁ የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ደግሞ የመከላከያ ካምፕ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ትልቅ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚችል ጠቅሰው፤ • ቢሮው ከእጁ የወጡትን የቱሪስት መዳረሻዎች ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ፎቶ- ገባቦ ገብሬ አቶ መለሰ አለሙ

Transcript of 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን...

Page 1: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር!

78ኛ ዓመት ቁጥር 177 ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር

የማህበራዊ ዋስትና በሀገራችን ከተጀመረ ግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የዕቅድ ሽፋኑ በመንግሥት ሠራተኞች፤ በመከላከያና በፖሊስ ሠራዊት አባላት ላይ ብቻ ተወስኖ ቆይቷል። ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ብሎም የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራሞችን ማጠናከርና ማስፋት የሚለውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማሳካት ይቻል ዘንድ የግል ድርጅቶች ሠራተኞችን የማህበራዊ ዋስትና የሚደነግግ የጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ወጥቶ ተግባር ላይ እየዋለ ይገኛል።

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አዋጁን በማስተገበር በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎችን የማህበራዊ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚሰራ የመንግሥት ተቋም ነው። በዚህም

የማህበራዊ ዋስትና መስፋፋት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስችላል

የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሌላ በኩል ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን እውን በማድረግና የዜጎችን የቁጠባ ባህል በማሳደግ ዘላቂና የተረጋጋ ሀገራዊ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

ባለፉት ዓመታት፣ በኤጀንሲው ስለፕሮግራ ሙና ስለአሰራሩ ለዜጎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ መረጃዎችን ተደራሽ የማድረግ፣ የምዝገባ ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን የማጠናከር፣ የዕቅድ አባላትን ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ፣ የኢንቨስትመንትና ፈንድ አስተዳደር በተጨማሪም፣ በድጋፍ ላይ ውጤታማ ስራዎችን አከናውኗል። ይህን ስኬታማ የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራም የማስተገበር ሂደት ስርዓቱን ጠብቆ ለማስቀጠል በየጊዜው እየታደሰ በሚሄድ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይመራል።

የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራሙ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው የዜጎችን ማህበራዊ

ደህንነትና የሰብዓዊ መብት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው። ሀገሪቱ በምትከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲና እየተመዘገበ ካለው እድገት አንጻር ሲታይ፣ ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ ከሚከናወኑ ሥራዎች አንዱና ዋነኛው ተግባር ሲሆን፣ በዚህ ፕሮግራም የገቢ መቋረጥ እንዳይከሰት የማህበራዊ ዋስትና ሽፋን በመስጠት ዜጎች ለችግር እንዳይጋለጡ ማድረግ ይቻላል። ይህም የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ ዋነኛ መሳሪያ ነው። ሊሳካ የሚችለውም በርካታ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በዕቅዱ እንዲታቀፉ በማድረግና በዕድሜና በሌሎች ምክንያቶች ሊደርስ የሚችለውን የገቢ መቋረጥ በማስቀረት የገቢ ድጋፍ በመፍጠር ድህነትን በመቀነስ ረገድ የሚደረገው ጥረት ነው።

በእስካሁኑ የትግበራ ሂደት የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋንን አስፈላጊነት የተረዱ፣ ጥቅሙም

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ

የገባቸው የግል ድርጅቶች አዋጁን ተቀብለው ኃላፊነታቸው እየተወጡ ይገኛሉ፤ ይሁን እንጂ አዋጁ የጣለባቸውን ግዴታዎች በተገቢው የማይወጡ ጥቂት የግል ድርጅቶች ዛሬም አልጠፉም። የዜጎችን ማኅበራዊ ዋስትና የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብት ማስከበር ይቻል ዘንድ ኤጀንሲው ግዴታቸውን የማይወጡ የግል

ድርጅቶች ሲገጥሙት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ወደ ሕግ አስገዳጅነት ይገባል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የማኅበራዊ ዋስትና መስፋፋት የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚኖረውን ወሳኝ ሚና በመረዳት ሁሉም የግል ድርጅቶች ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት አጠገብስ.ቁ-011 1 55 03 67/68/76

ነጻ ስልክ ቁጥር 888/1/2/7ድረ ገጽ- www.poessa.gov.et

ኢ ሜይል [email protected]ማኅበራዊ ድረ ገጽ- www.Facebook.com/poessa

ፖ.ሳ.ቁ. 33921አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የፓርቲዎች... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

የፓርቲዎች ውህደትና ጥምረት

ለተሻለ አማራጭዘላለም ግዛው

በመጪው ምርጫ 2012 ዓ.ም ህዝቡ የተሻለ

አማራጭ እንዲያገኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውህደት ወይም ጥምረት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ምሁራን ይገልጻሉ።

ተመሳሳይ ፍላጎትና ፕሮግራም ያላቸው ፓርቲዎች ቢሰባሰቡ የሚያስቡትን ግብ ከማሳካትና የፖለቲካ ስልጣን ከመቆጣጠር አንጻር አቅም እንደሚፈጥሩ፣ ጥምረታቸው ለአገርም ለህዝብም እንደሚጠቅም ያስረዳሉ።

በግጭት አፈታት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን

የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ኮሚቴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እየጠበቀ ነው

አንተነህ ቸሬ

አዲስ አበባ፡- የዓድዋን ድል ለመዘከር ለሚገነባው የዓድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚያስችል ዝግ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆኑን የዓድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የምስረታ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።

የኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ቢተው በላይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣

የዩኒቨርሲቲው... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በሩን ከፍቷል

• ከአጋር ፓርቲዎች ጋርም በቅርቡ ውህደት ይፈጽማልአጎናፍር ገዛኸኝ

አዲስ አበባ፦ ኢህአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመቀላቀል በሩ ከፍት መሆኑን እና ከአጋር ፓርቲዎችም ጋር ውህደቱ በቅርቡ እውን እንደሚሆን አስታውቋል።

የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ፤ ለአዲስ ዘመን በሰጡት ማብራሪያ ድርጅቱ ማሻሻያ እያደረገ ነው። ማሻሻያ ሲያደርግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በሩን ዘግቶ አይደለም። አብሮ መሆን የሚወሰነው ግን በተፎካካሪ ፓርቲዎች ፍላጎት ነው። በዓላማ የሚጣጣም ካለና ዓላማውን የሚደግፍ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ አብሮ ለመስራት ከፈለገ የኢህአዴግ በር ክፍት መሆኑን ገልጸው፤ ግን አብረን እንሁን ብሎ ማንንም አያስገድድም ብለዋል።

ኢህአዴግ የህዝብ ድርጅት ነው ያሉት አቶ መለሰ፤ በባህሪይው ተራማጅ በመሆኑ እንደየጊዜው ስልቶቹን በመንደፍ አገሪቱን ከኋላ ቀርነት በማውጣትና የዳበረ ዴሞክራሲ በመፍጠር የበለጸገች ኢትዮጵያ ለመገንባት ይሰራል። ይህ ረጅም ጊዜ የሚወስድና በኢህአዴግ ብቻ የሚያልቅ ሳይሆን የሌሎች ፓርቲዎችንና ግለሰቦችን የትግል አስተዋፅኦ የሚጠይቅ ነው። እንደ አንድ ፓርቲ የትውልዶችን ትግል ለሚጠይቀው ጉዞ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ካሉ ኢህአዴግ የእኔ ብቻ የሚልበት ምክንያት የለም።

ከአጋር ፓርቲዎች ጋር ለመዋሀድ የሚደረገው ሂደት ቀደም ብሎ ጥናቱ ተጠናቅቋል። የጥናቱ ውጤት ለፓርቲዎቹ ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ በቅርቡ የኢህአዴግና የአጋር ድርጅቶች ውህደት ይፈፃማል። ፓርቲዎች ሰብሰብ ብለን ለአገር የሚጠቅም ሥራ ማከናወን አለብን። መሰባሰቡ አገሪቱ የምትፈልገውን ውጤት ለማምጣት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል። ከአቶ መለሰ አለሙ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በገጽ 11 ላይ ያንብቡ።

የአምቦ ከተማ የቱሪስት መዳረሻዎች በጽህፈት ቤቱ እጅ አይደሉም

ዳንኤል ዘነበ

አምቦ ፦ በአምቦ ከተማ የቱሪስት መዳረሻ ተብለው የተለዩ ስፍራዎች በባህልና ቱሪዝም እጅ እንደማይገኙ የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጉሬ ታሱ ገለጹ።

የአምቦ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤

በከተማዋ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለመለየት በተደረገው እንቅስቃሴ አምስት ስፍራዎች፤ ማለትም የአምቦ ውሃ፣ ፊንጫ ኦብሴ (ፏፏቴ )፣ የእግዜር ድልድይ፣ ፍልውሃ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት የተለዩ ሲሆን፤ በሁሉም ላይ ጽህፈት ቤቱ አያዝባቸውም፤ ብለዋል።

አያያዘውም፤ የተለዩትን ቦታዎች አስከብረን ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ የማድረግና ወጣቶች

ተደራጅተው እንዲሰሩ የማብቃት እቅድ ቢኖርም አምስቱም የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች በአሁኑ ወቅት በከተማው የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ስር አይገኙም ብለዋል።

ከተለዩት የቱሪስት ቦታዎች የአምቦ ውሃ፣ የፊንጫ ኦብሴ (ፏፏቴ )፣ ፍልውሃ በግለሰብ እጅ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጸው፤ የከተማው ህዝብ ሀብት በምን መንገድ ለግለሰብ እንደተሸጠና የአምቦ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

ስፍራዎቹ እንዴት በግለሰብ እጅ እንደወደቁ የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ደግሞ የመከላከያ ካምፕ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ትልቅ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚችል ጠቅሰው፤

• ቢሮው ከእጁ የወጡትን የቱሪስት መዳረሻዎች ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል

ፎቶ

- ገባቦ

ገብ

አቶ መለሰ አለሙ

Page 2: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

2 የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

የሀገር ውስጥ ዜና

ዳንኤል ዘነበ

አምቦ፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለ547 ችግረኛ ወገኖች የነጻ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገለጸ። «ኡቡንቱ» ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ መስጫ ድርጅት ለ100 ቤተሰቦቹ የመኖሪያ ቤት ሊገነባ ነው። የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዩኒቨርሲቲው መሰብሰቢያ አዳራሽ አክብሯል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው። መሰረቱን በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ካደረገው «ኡቡንቱ» ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ መስጫ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመሆን በድህነት ለሚኖሩ 547 ወገኖች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የነጻ ህከምና አገልግሎት ይሰጣል። «ኡቡንቱ» ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ መስጫ ድርጅት በዩኒቨርሲቲው በሚገኙ መምህራንና በሌሎች ባልደረቦች በሚንቀሳቀስ የበጎ አድራጎት ድርጅት በሚሰጣቸው ድጋፎች ላይ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል። ድርጅቱ ባለፉት አራት ዓመታት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ከኡቡንቱ ጋር በአብሮነት የሚያደርገውን ትብብር የሚቀጥል መሆኑንና እርሳቸውም በግላቸው በአባልነት ተመዝግበው ከደሞዛቸው 100 ብር ተቆራጭ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለ547 ችግረኞች የነጻ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው

በአሁኑ ወቅት ቤተ መንግስቱ የመከላከያ ካምፕ ተደርጓል። አግባብ ያለው አያያዝና ጥበቃ ስለማይደረግለትም በውስጡ ያለው ሀብትና ንብረት በሙሉ ጠፍቷል። ታሪካዊ ቅርሶች ወድመዋል ብለዋል። በወቅቱ በተደረገው እይታ ሁሉም ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን ለመታዘብ ተችሏል። በአሁኑ ወቅትም የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ራሱ የመግቢያ ደብዳቤ/ፈቃድ ካልያዘ ወደ ቤተመንግስቱ መግባት እንደማይችል አረጋግጠናል።

ኃላፊዋ እንደገለጹት፤ ቤተ መንግስቱን ማስተዳደር ለሚገባው አካል ስለሚመለስበት ሁኔታና በቤተ መንግስቱ የነበሩ የተሰባበሩና የጠፉ የባህል እቃዎችን በተመለከተ የማን ሀላፊነት ነው በሚሉት ጉዳዮች ዙሪያ ከቀድሞው የከተማዋ ከንቲባ ጋር የተነጋገሩ ቢሆንም፤ ጉዳዩ እልባት ሳያገኝ ከንቲባው ከስልጣናቸው ተነስተዋል ።

ወይዘሮ ጉሬ የከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ወደ ቢሮው ከመጡ ገና ሁለት ወር መሆኑን ጠቅሰው፤ ቢሮው ከእጁ የወጡትን የቱሪስት መዳረሻዎች ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል። የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ጉዳዩን በሚገባ አጢነው መፍትሄ ሊያበጁለት ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

የአምቦ ከተማ የቱሪስት…

ለዩኒቨርሲቲው ምስረታ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ ለመስጠት ፍላጎት አሳይተዋል። ኮሚቴው ድጋፉን ለመቀበል የሚያስችል የገንዘብ ማስገቢያ የባንክ አካውንት እንዲከፈትለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለሦስት ጊዜያት ያህል ጥያቄውን ለጽሕፈት ቤቱ ቢያቀርብም እስካሁን ድረስ ምላሽ አላገኘም፡፡ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚገኘውን ድጋፍ ለመቀበል እንዲሁም ሕዝቡ ከድጋፉ ስለሚገኘው ገንዘብ ማወቅና ገንዘቡም ሕጋዊ አሰራርን ተከትሎ ኦዲት መደረግ ስላለበት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከፈት ዝግ የባንክ አካውንት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ባለፈው ዓመት የፌዴራል መንግሥት ለዩኒቨርሲቲው ግንባታ የገባውን የ200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በቅርቡ ይሰጣል የሚል ተስፋ አለን›› ያሉት ሰብሳቢው፣ የትግራይ ክልል መንግሥት 250 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል መግባቱንና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ሌሎች ክልሎችም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ስለመግባታቸው ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ‹‹በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የሌሎች አገራት ምሁራንን አነጋግረናል፤ የተለያዩ ኮርሶችን ለማስተማርና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግም ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸውልናል›› ብለዋል፡፡ በ2010 ዓ.ም በአዲስ አበባና በዓድዋ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች መካሄዳቸውን አስታውሰው፣ በወቅቱ ከበርካታ አካላት ጋር ግንኙነት መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡ አስተባባሪ ኮሚቴው ካሉት ዐቢይ ኮሚቴዎች መካከል በአሁኑ ወቅት በንቃት እየተንቀሳቀሱ ያሉት የስርዓተ-ትምህርት ቀረፃና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴዎች እንደሆኑም አቶ ቢተው ተናግረዋል፡፡ ለግንባታው 10 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል የተባለው የዓድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የመሰረት ድንጋይ በሚያዚያ ወር 2009 ዓ.ም በቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና በኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ አማካኝነት መቀመጡ ይታወሳል፡፡

የዩኒቨርሲቲው…ከ1ኛው ገጽ የዞረ

የፓርቲዎች ውህደትና…

᎐ «ኡቡንቱ» ለ100 ቤተሰቦቹ የመኖሪያ ቤት ይገነባል

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኡቡንቱ ቤተሰብ አቀፍ የልጆች ድጋፍ ሰጪ ድርጅት መስራችና ኃላፊ አቶ ሰለሞን አለሙ በበኩላቸው፤ «ኡቡንቱ» በድህነት ምክንያት ልጆቻቸውን ማስተማር ያልቻሉ ቤተሰቦችን የመደገፍን አላማ በመሰነቅ በ12 የዩኒቨርሲቲው

መምህራን ከአራት ዓመት በፊት የተመሰረተና በአሁኑ ወቅት 360 አባላትን አቅፎ የሚንቀሳቀስ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተቋቋመ ቀዳሚው የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አቶ ሰለሞን ማብራሪያ፤ ድርጅቱ በየአመቱ

የሰሩት የመልታይ ዳይሜንሽናል ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ቀጄላ፤ ጥምረት የተበታተነን ኃይል ማሰባሰብ፣ የግብ እና የአመለካከት አንድነትን መፍጠር መሆኑን ይጠቅሱና፤ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መፍጠራቸው አመለካከታቸውን እና አማራጫቸውን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለማስገንዘብ ቀላል ይሆናል።ጉልበት፣ ጊዜና ገንዘብ እንደሚቆጥብ ያመለክታሉ።

ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ጥምረት በመፍጠራቸው ዕውቀታቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና አመለካከታቸውን አጣምረው የተሻለ ውጤት የሚያገኙበት እንደሚሆን ይጠቁሙና፤ በመጣመራቸው ጉድለቶቻቸውን እየተሞላሉ በአቅም፤ በገንዘብና በዕውቀት እየተደጋገፉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆነው ለመቀጠል ይችላሉ ሲሉም ያስረዳሉ።

በህግና በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በልማት ጥናት /Development Stud-ies/ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት አቶ ዘሪሁን ጋሻውም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓላማቸው በዋናነት የፖለቲካ ስልጣን በመያዝ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ጥቅሞችና ፍላጎቶች እንዲጠበቁ መስራት፣ የሚታዩ ችግሮች እንዲቀረፉ የፖሊሲ አማራጭ አቅርበው መታገል መሆኑን ይጠቅሳሉ።

ፓርቲዎች ፍላጎታቸው ከተቀራረበ ተለያይተው የሚሰሩበት ምክንያት አለ ተብሎ አይታሰብም የሚሉት አቶ ዘሪሁን፤ ተመሳሳይ ፍላጎትና ፕሮግራም ያላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሰባስበው ቢንቀሳቀሱ የሚያስቡትን ግብ ከማሳካትና የፖለቲካ ስልጣን ከመቆጣጠር አንጻር አቅም ሊፈጥሩ ይችላሉ ባይ ናቸው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች በጥምረት መንቀሳቀሳቸው ለህዝቡም ጥቅም እንዳለው ይጠቁማሉ። ብዛት ያላቸው ፓርቲዎች ከተንቀሳቀሱ ህዝቡም ለመለየት እንደሚቸገር ያመለክታሉ። መሰባሰባቸው ግን ፓርቲዎቹን በቀላሉ ለይቶ ለመምረጥ የሚቻልበት ዕድል እንደሚፈጥር ይመክራሉ። አገርንና ህዝብን የሚጠቅም አጀንዳ ካላቸው መሰባሰቡ እንደሚመረጥም ያመለክታሉ።

ለውጡ በፈጠረው መልካም አጋጣሚ ከ100 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን የሚጠቅሱት አቶ ከበደ፤ ተበታትኖ መቀጠሉ ጠንከር ላሉ ፓርቲዎች ዕድል በወርቅ ሳህን እንደማቅረብ ይሆናል ይላሉ። እንደ ፓርቲ ተበታትኖ መቀጠሉ የሚጠቅማቸው ነገር እንደሌለም ያብራራሉ። ተበታትነው መቀጠላቸው አቅም ይበታተናል፣ ጊዜ ያቃጥላል፣ ለመራጩ ህዝብም ግርታ ይፈጥራል። ለአገርም ለመራጩ ህዝብም ከጠቀሜታው ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና ሌሎችም ሰዎች ፓርቲዎች ቢሰባሰቡና ቢጠናከሩ የተሻለ መሆኑን ሲገልጹ መቆየታቸውን በማስታወስ፤ ይህንን ምክር በመንተራስ ፓርቲዎች ለመሰባሰብ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጥሩ መሆኑን ይገልጻሉ። ያልተሰባሰቡ ፓርቲዎችም በፕሮግራም እቀራርባለሁ ከሚሉት ጋር ቢሰባሰቡ፣ ቢዋሃዱና ጥምረት ቢፈጥሩ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው አቶ ዘሪሁን ይናገራሉ።

ላለፉት 30 እና 40 ዓመታት በአገር ውስጥ የተሞከረው ብሄርን መሰረት ያደረገው የፖለቲካ ፓርቲዎች አካሄድ ብዙም ውጤት አላስገኘም። ጥምረቱ ወደ ርዕዮተ ዓለማዊ አደረጃጀት ቢሄድ ይመረጣል ሲሉ አቶ ከበደ ይጠቁማሉ።

በብሄር የሚደራጁ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማንነትን አጉልተው በማውጣት እንደሚደራጁ በመጥቀስም፤ ለማንነታቸው ምክንያታዊነትን ያቀርቡና ለብሄራቸው ማስገኘት የሚፈልጉት ላይ ያመዝናሉ እንጂ አጠቃላይ ህብረተሰብ ላይ አያተኩሩም ሲሉ ይወቅሳሉ። በርዕዮተ ዓለም መሰባሰቡ ግን አገራዊ አመለካከት እንዲኖር ያግዛል፣ ፓርቲዎቹ የሚያማልል ነገር እንዲኖራቸው ያደርጋል ይላሉ።

የሚያስገድድ ጉዳይ ከሌለ ስስ በሆኑ አጀንዳዎች ተመስርቶ መደራጀት አይመከርም፣ ለአገርም ጠቃሚ አይደለም፤ ያሉት አቶ ዘሪሁን፤ ብሄርን መሰረት አድርገው የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደራጁት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እስከሆነ ድረስ ችግሮቹን መነሻ አድርገው ቢደራጁ እንደሚመረጥ ይጠቁማሉ።

የፌዴራል ሥርዓቱ በተወሰነ መልኩ በብሄር ላይ የተመሰረተ መሆኑ አንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎችም በእዛው ላይ ተመስርተው እንዲደራጁ ዕድል

መስጠቱን ያስታውሳሉ። በቀጣይነት ሁኔታው እየቀነሰ መምጣት አለበት። አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ መሰባሰቡ እንደሚመረጥ ይገልጻሉ።

በርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ትግበራ በዓለም አቀፍ ተመራጭና የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሁኔታን መነሻ የሚያደርጉ መሆናቸውን በመጠቆምም፤ ይህም የአገሪቱን ህዝብ የፖለቲካ ወይም ኢኮኖሚ ተጨባጭ፤ ወቅታዊ ችግሮች ላይ እንዲመሰረት ያደርጋል ሲሉ ነው አቶ ዘሪሁን የሚጠቅሱት። በብሄር ላይ የሚመሰረተው ባብዛኛው ‹‹የእኔና የእነሱ›› በሚል አስተሳሰብ ላይ እንደሚያጠነጥንና የእኔ ተብሎ የሚመሰረተው ሌሎችን በሚያቀርብ አንድነት ላይ ሳይሆን በልዩነት ላይ ሆኖ በተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያተኮረ ይሆናል ሲሉ ያስረዳሉ።

ሰሞኑን በጥምረትና ግንባር ፈጥረው ለመስራት የተስማሙት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ህብረት(ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት (ኢብአ)፣ የአፋር ህዝቦች ፍትሀዊ (አህፍ)፣ የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርቲ እና የኦሮሞ ህዝብ ፍትሃዊ ፓርቲ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት 24 አገራዊና 42 ክልላዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቷቸው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ለውጡን ተከትሎም በጥቅሉ 104 የሚደርሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ፓርቲዎቹ ጥምረትና ግንባር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ በተለያዩ አጋጣሚዎች እየተገለጸ ይገኛል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ጥምረት ባይመጡ እና እንደተለመደው በተበታተነ አካሄድ ቢቀጥሉ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያጣል። ህዝቡ የተሻሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለመለየት ይቸገራል። ያልፈለገውን እንዲመርጥም ይገደዳል። ህዝቡ በበቂ ሁኔታ አይወከልም፣ ባልፈለገው አካል እንዲተዳደርም ይገደዳል። ችግሮችም ይቀጥላሉ። ግራ የሚያጋባና ምስቅልቅል ሁኔታ ይፈጠራል። ብዙ የባከኑ የምርጫ ወረቀቶች ይፈጠራሉ። ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት ያላግባብ ይባክናል።

የአሰብ ወደብ መዳረሻ መንገድ ጥገና ተጠናቀቀ

ወደ አሰብ ወደብ መዳረሻ ያለው 60 ነጥብ6 ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ። ከኤሊዳር -ማዳ ያለው 30 ነጥብ ስድስት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተጠግኗል። ሁለተኛውና ከማንዳ-ቡሬ ያለው 30ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው መንገድ ደግሞ በኢኮስኮ ጥገና የተደረገለት መሆኑ ታውቋል።

የካቲት 26 ቀን 2011ዓ.ም (ኢፍቢሲ)

በህገ ወጥ አሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ እገዳ ተጣለባቸው

በአዲስ አበባ ከአንድ ሺህ በላይ ህገ ወጥ አሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች እገዳ እንደተጣለባቸው የከተማ አስተዳደሩ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው ህጋዊ አሰራርን ተከትለው የሚሰሩ የአሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች 315 መሆናቸውን ቢሮው አመልክቷል። ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ማስታወቂያ በመለጠፍና ህጋዊ በማስመሰል ሲንቀሳቃሱ የነበሩ በአንድ ሺህ ስድስት ኤጀንሲዎች ላይ በጥናት በመለየት እርምጃ እንደተወሰደ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ተናግረዋል።

የካቲት 25 ቀን 2011ዓ.ም (ኢቢሲ)

በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት

ቃጠሎ ደረሰበት

በፓርኩ የተከሰተው የእሳት አደጋ 4ኛ ቀኑን ይዟል:: የአደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም አደጋውን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአደጋው መንስኤም እየተጣራ እንደሚገኝ የፓርኩ የሥራ ኃላፊዎች ገልፀዋል ። በፓርኩ ላይ የደረሰውን አደጋ መጠን የሚያጣራ የባለሙያ ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩም ተገልጿል።

የካቲት 25 ቀን 2011 ዓ.ም(ኢቢሲ)

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የራት ግብዣ ምላሾች እየመጡ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ አነሳሽነት ለአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት ገቢ ማሰባሰቢያነት በተጠራውና ‹‹ገበታ ለሸገር›› በተሰኘው የአምስት ሚሊዮን ብር (በአንድ ሰው) የራት ግብዣ፣ በርካታ ምላሾች ከወዲሁ እያስተናገደ እንደሚገኝ ታወቀ። ‹‹ገበታ ለሸገር›› ለተሰኘው እንቅስቃሴ ምላሽ የሚሰጥባቸው የድረ ገጽና የኢሜል አድራሻዎች ይፋ በተደረጉ በመጀመሪያው ዕለት፣ ከ100 በላይ ቃል የገቡ ግለሰቦች በኢሜል ፍላጎታቸውን አስታውቀዋል። ከአገር ውስጥ በተጨማሪ የውጭ ዜጎችና ድርጅቶችም ፍላጎት ማሳየታቸው እየተሰማ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ገበታ ለሸገር›› ፕሮግራም፣ በጥቂቱ ከአንድ ሺህ በላይ ታዳሚዎችን እንደሚያሳትፍ ሲጠበቅ፣ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገኝበትም ግምቶች እየወጡ ነው። ይህም ማለት የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማትን ለማሳመር ከታቀደው ሸራተን ሆቴል አካባቢ ለሚገነባው የ2.5 ቢሊዮን ብር የመነሻ ፕሮጀክት አኳያ ከእጥፍ በላይ ሊገኝበት እንደሚችል አመላካች ነው። የካቲት 24 ቀን 2011 ዓ.ም (ሪፖርተር)

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ለላሊበላ ዕድሳት ቃል የገቡት ድጋፍ ይፋ እንደሚደረግ

ይጠበቃልጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ

አህመድ ፈረንሣይን በጎበኙበት ወቅት ፈረንሣይ ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዕድሳትና ጥገና ድጋፍ እንድታደርግ በመጠየቃቸው ምክንያት፣ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ እንደሚሰጡ በገቡት ቃል መሠረት ከሳምንት በኋላ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝት ወቅት ይፋ እንደሚያደርጉት ይጠበቃል ተባለ። መጋቢት በመጪው ሳምንት ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሚጠበቁት ፕሬዚዳንት ማክሮን፣ እግረ መንገዳቸውን ላሊበላን እንደሚጎበኙ ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቀደም ብለው የተያዙ የጉብኝት ቀናት ሲለዋወጡና የቆይታ ጊዜያቸውም ከሁለት ቀናት ወደ አንድ ቀን ማጠሩንም ለማወቅ ተችሏል። ይሁንና በጉብኝታቸው ፈረንሣይ ለላሊበላ ዕድሳት ቃል የገባችውን የገንዘብ ድጋፍ ይፋ ከማድረግ በተጨማሪ፣ በፓሪሱ ስምምነት ወቅት ይፋ በተደረጉ ሦስት መሠረታዊ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ጋር እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል፡

የካቲት24 ቀን 2011ዓ.ም (ሪፖርተር)

ድጋፍ የሚሹትን ወገኖችን በመቀበል ለአራት አመታት የተጓዘ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ዙር 26 ቤተሰቦች ተቀብሏል፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ 27፣ በሶስተኛው 39 ቤተሰቦችን ሲቀበል በአራተኛው ዙር ደግሞ 43 ቤተሰቦችን ተቀብሏል።አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች በእናት ብቻ የሚተዳደሩ ናቸው። ለእነዚህ ቤተሰቦች አምስት ሺህ ብር ለመስሪያ የሚሆን መነሻ ገንዘብ በመስጠት ለማቋቋም ጥረት ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪ የሚያስፈልጉ አልባሳት እንደ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ። ኡቡንቱ ቤተሰቦችን ለመደጎም በቀጣይም ሰፊ እቅድ እንደያዘ የተናገሩት አቶ ሰለሞን ፤ የቤተሰቦቹን መሰረታዊ ችግር በመረዳት ለ100 ቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት ለመገንባት እቅድ ይዟል። በዚህም «ኡቡንቱ ቪሌጅ »በሚል በአነስተኛ ወጪ ለ100 ቤተሰቦች የሚሆን መኖሪያ ቤት ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸው፤ የከተማ አስተዳደሩ መሬት እንዲሰጠን እየተነጋገርን ነው። የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በማንቀሳቀስና ከአጋር ድርጅቶችም ጋር በመሆን ለቀጣዩ አመት ቤቱን ሰርቶ ለማስረከብ መታቀዱን ገልጸዋል። አክለውም የዚሁ አካል የሆነ 40 አረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን የሚደገፉበት ተቋም እንደሚገነባም ተናግረዋል ። ኡቡንቱ በአሁኑ ወቅት 135 ቤተሰቦችን በማቀፍ ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ በዚህ ቤተሰብ ውስጥ በአማካኝ 4 ነጥብ 5 ህጻናት ሲኖሩ፤ አጠቃላይ የተጠቃሚ ቤተሰብ ቁጥር 547 መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። “ኡቡንቱ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል፤ “አንዱ እያዘነ ሌላው እንዴት ደስተኛ ይሆናል” የሚል ትርጉም እንዳለው ለማወቅ ተችሏል።

ከ1ኛው ገጽ የዞረአጎናፍር ገዛኽኝ

አዲስ አበባ ፦ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያለውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ፤ ጥናት ለማድረግና ለማገዝ ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን ትናንት በባንኩ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ሲፈረም የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ሊንሳ መኮንን እንደተናገሩት፤ ባንኩ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ዘርፍ በጥናት በመለየት በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን አካሄዶች ፍኖተ ካርታ ያስቀምጣል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ተቋማዊ መዋቅር ለመዘርጋት እገዛ ያደርጋል።

በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ይስተናገዳሉ። ከዚህ ውስጥ ቱሪስቶች 10 በመቶ ብቻ ናቸው። አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ብትሆንም የስብሰባ ቱሪዝሙ ዝቅተኛ ነው። ስምምነቱ በቦሌ አየር ማረፊያ የሚመጡ ቱሪስቶችን ቁጥር ወደ 20 በመቶ ለማሳደግ፤ እንዲሁም የስብሰባ ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመለየት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ባንኩ በሚያደርገው ጥናት ለቱሪዝሙ ዘርፍ እንቅፋት የሆኑ የመሰረተ ልማት፣ የባለሙያዎች ጉድለት፣ የአልሚዎች መጓደል፣ የገበያ ሥርዓት፣ የተቋማት አደረጃጀትና የዓለም አቀፍ ገበያ ስነ ዘዴ መጓደልና ሌሎች ችግሮችን በማጥናት ለችግሩ መፍትሄ የሚሆኑ አሰራሮችና ሀሳቦች ለድርጅቱ ያቀርባል።

የባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮና የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ጁሞኪ ጃግነዶኩሙ፤ በባንኩና በድርጅቱ መካከል የተደረገው ስምምነት ሶስት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ በጥናቱ ዓለም አቀፍ አማካሪዎችና ባለሙያዎች ድጋፍ ያደርጋሉ። ለድጋፉ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደሚደረግም አመላክተዋል።

የሚደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያ ሰፊ ዕድል እያላት በአግባቡ ያልተጠቀመችበትን ሀብቷን ወደ ጥቅም ለመቀየር መሰረት ይጥላል። መረጃዎችን የማደራጀት ስራም ይሰራል። ይህም በቀጣይ የግሉና የመንግሥት አካላት መስራት ስላለባቸው አቅጣጫ በማስያዝ የዘርፉ ዕድገት እንዲፋጠን ያደርጋልም ብለዋል።

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የቱሪዝም

ዘርፍ ሊደግፍ ነው

አቶ ቢተው በላይ

Page 3: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

በየነ ሞገስ (ገላውዲዮስ)

አንድ ሀገር የሚመራው በህግ መሆኑ አያጠያይቅም። የሕግ የበላይነት ይከበር ሲባል የሀገሪቱ ዜጋ ሕግን አክብሮ መንቀሳቀስ አለበት ማለት ነው። ይሁንና፤ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በርካታ የሕግ ጥሰቶች እየተስተዋሉ ናቸው። የሀገሬ ሕዝብ (በተለይ የገጠሩ) የህግ መተላለፍ ሲያጋጥም ዱላ ከመምዘዙ በፊት “በሕግ አምላክ” ይላል። ይህ ማለት የገጠሩ ህዝብ ከከተሜው የላቀ የሕግ ግንዛቤ አለው ማለት ነው። በአንጻሩ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ስለሕግ የበላይነት የተሻለ ግንዛቤ አለን የምንል ከተሜዎች ሕግ ስንጥስ እንታያለን። ለዚህ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፤

አዲስ አበባ በተለያዩ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ምጣኔ ሀብታዊ ተግዳሮት ተወጥራ መያዟ ሀቅ ነው። በየትኛውም የመዲናይቱ ማዕዘናት የሚንቀሳቀሰው ሰው ብዙ ትዕይንቶችን መመልከቱ የተለመደ ነው። አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል አውቆም ይሁን ባለማወቅ በርካታ የሕግ ጥሰቶች ይፈጽማል። ለምሳሌ፤ አንድ በንግድ ሥራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልግ ዜጋ ሕጉ በሚፈቅድለት መሰረት ፈቃድ አውጥቶ መነገድ ይችላል። እንደነጋዴው ፍላጎትና አቅም በፈለገው የንግድ መስክ ተሰማርቶ መስራት መብቱ ነው። የልብስ፤ የጫማ፤ የምግብ፤ የመጠጥ…ወዘተ. ህግ አክብሮ መስራት ይችላል።

ነገር ግን፤ በአሁኑ ወቅት በመዲናይቱ በየአደባባዩ ከፍተኛ ትርምስ የሚታይበት የገበያ ሥራ ይታያል። በተለይ በመገናኛ፤ በሜክሲኮ አደባባይ፤ በካዛንችስ፤ በአራት ኪሎ፤ በስድስት ኪሎና በሌሎችም አደባባዮች በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሲገበያዩ መመልከት ተለምዷል። እንደመገናኛ ያሉት አደባባዮችማ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ለእግር መርገጫ እስኪጠፋ ድረስ ሸቀጥ በዘረጉ ነጋዴዎች ተሞልቶ ማየት ተለምዷል፤ መብትም ሆኗል። የተለያዩ የወንድና የሴት ልብሶች፤ ጫማዎች፤ ጌጣጌጦች፤ ቦርሳዎች፤…ወዘተ. ይሸጣሉ። ዜጎች ኑሯቸውን ለማሻሻል በመደራጀትም ይሁን በተናጠል የሚያደርጉትን ጥረት በግሌ እደግፋለሁ። መንግሥትም ቢሆን ዜጎች በፈለጉት እና በሚችሉት የሥራ መስክ እንዲሰሩ ማድረግ አለበት።

እኔ ያልተመቸኝ ግን የሥራው ሂደት ነው።

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም 3

ይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው፡፡በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም፡፡

ርዕሰ አንቀፅ

አዲስ ዘመን

አጀንዳ

በ1933 ዓመተ ምህረት ተቋቋመ በየዕለቱ እየታተመ የሚወጣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም

አድራሻ:- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 001 የፖ.ሣ.ቁ፡- 30145

ዋና አዘጋጅ - ፍቃዱ ሞላ ኢ ሜይል - [email protected] አድራሻ - የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ - 13 የቤት ቁጥር - B402 H11 ስልክ ቁጥር - 011-126-42-40 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ስልክ - 011-126-42-22 የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍ የኢሜይል አድራሻ [email protected] ስልክ - 011- 156-98-73 ፋክስ - 011- 156-98-62 የማስታወቂያ መቀበያ ክፍል ስልክ - 011- 156-98-65 የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያ ስልክ - 011-1-26-43-39 ማከፋፈያ ስልክ - 011- 157-02-70

የዕለቱ ምክትል ዋና አዘጋጅ፡- ዳንኤል ታምሩ ፈረደ ስልክ ቁጥር- 011-126-43-19 አዘጋጆች፡- ፍሬህይወት አወቀ ጌትነት ምህረቴ አጐናፍር ገዛኽኝ አንተነህ ቸሬ ዘላለም ግዛው ዳንኤል ዘነበ

website www. press.et email. [email protected]

Facebook Ethiopian Press Agency የዝግጅት ክፍል ፋክስ- 251-011-1-56-98-62

በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ህልውና/ዕድሜ ብዙ የሚባል አይደለም፡፡ ከንጉሱ መውደቅ በኋላ በደርግ ዘመን ከተመሰረቱትና መኢሶንንና ኢህአፓን ጨምሮ፤ በኋላም በራሱ በደርግ ውስጥ ተመስርተውና እርስ በርስ ተባልተው ከጠፉት አራት ድርጅቶች ውጭ ከሩቅ የሚጠቀስ ፓርቲም፤ ታሪክም የለንም፡፡

የ1983ቱን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች ብዙ ሆኑ፡፡ በተለይ በሰኔ1983 ዓ.ም የነበረው የመጀመሪያው የሽግግር መንግሥት ምስረታ ላይ የታደሙት የፖለቲካ ፓርቲዎች በርካቶች ነበሩ፡፡ በእንዲህ አይነት መንገድ የተጀመረው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስረታና ህልውና ዛሬ ከ27 ዓመታት በኋላም ቁጥሩ ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አልታየም፡፡ በመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓላማ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ነው፡፡ ለዚህም እርስ በርስ ይፎካከራሉ፡፡ ሲፎካከሩም በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ ችግሮችን ለመቅረፍ፤ ህብረተሰቡን በተለይም እወክለዋለሁ የሚሉትን የህብረተሰብ ክፍል ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ በመስራት ነው። ለዚህም የፖሊሲ አማራጭ በማቅረብ ለአሸናፊነት ይታገላሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡና እውቅና ያላቸው 24 አገራዊና 42 ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ አገራዊውን ለውጥ ተከትሎ ከውጭ ወደ አገር የገቡትና በዚህም በውስጥ አዲስ የተመሰረቱትን ጨምሮ ይህ ቁጥር ከአንድ መቶ እንደሚበልጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ሁሉ ተሰባስቦ ግን መቋጫው አንድ ነገር ነው፡፡ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ መፎካከር። የፖለቲካ ስልጣን ግን እንዴት ይያዝ የሚለው ደግሞ የግድ መመለስ አለበት፡፡

ይህ ከላይ የጠቀስነው የአገራችንን የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ስልጣነ መንግስቱን ከያዘው ኢህአዴግ ጀምሮ አብዛኛዎቹ በብሄር/ዘውግ ላይ በሚያጠነጥን አስተሳሳብ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ በአብዛኛዎቹ ነባርም ይሁኑ አዲስ ተመስራቾች የሚታየው ተመሳሳይ አወቃቀር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አወቃቀርና አካሄድ ግን ከስር ተነስቶ ወደ መድረክ ከገባበት ካለፉት 27 ዓመታት ጀምሮ ለህዝቡም ለአገርም ብዙም አልጠቀመም፡፡ የወቅቱ የለውጥ ምክንያትም በዋናነት ይህ የፖለቲካ አካሄድ ያመጣው ችግር ነው፡፡

ሁሌም በብሄር/በዘውግ ሲታሰብ የሚያደላው ለ“እኔ” የሚለው ሀሳብ ነው፡፡ የእኛ የሚለው የሚገኘው ከህብረት ነው፡፡ ይች አገር አሁን የሚያስፈልጋት ደግሞ በህብረት የቆሙ ከ“እኔ” ይልቅ “እኛ”ን የሚያቀነቅኑ መሪ ድርጅቶች እንዲኖሯት ነው፡፡ አገሪቱም ወቅቱም የሚፈልጉት ይህንን ነው፡፡ ይህ እውነት አሁን ላይ በገዥው ፓርቲም ይሁን በተፎካካሪ ፓርቲዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ይመስላል።

ሁሉም ወገኖች ዘርዘር ብለውና በተናጠል ከመቆም ይልቅ መሰባሰብ ጀምረዋል። ቀድሞውንም ፓርቲዎቹ/ድርጅቶቹ የቆምነው ለሕዝብ ነው ካሉ፤ ለምንስ ይለያያሉ? ዓላማቸው እንወከለዋለን የሚሉትን ሕዝብ ወይም ማህበረሰብ ጥቅምና መብት ለማስከበር ከሆነስ በአንድ ሕዝብ ወይም ማህበረሰብ ስም ለምን በርካቶች ሆነው ቀረቡ? እውነትም ለሕዝብ የሚታሰብ ከሆነ መሰረቱ አንድ ነው ማለት ነው። በአንድ መሰረት ላይ ደግሞ በአንድ ጊዜ የተለያየ ነገር አይቆምምና መጣመሩ ወይም አንድ መሆኑ ይደገፋል።

አዎን መሰባሰቡ በርካታ ጥቅሞች ይኖሩታል። በአንድ በኩል በህዝብ ዘንድ የነበረውን ግርታና

ይበል የሚሰኝ ርምጃ!

ሕገ-ወጥነት እስከመቼ?አዲስ አበባ የበርካታ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ከተማ በመሆኗ በዚሁ መጠን ጽዳቷና መጠበቅ አለበት። የመዲናዋ ውበት ከሚጠበቅበት መንገዶች መካከል ደረጃቸውን የጠበቁ የገበያ ሥፍራዎች መኖር፤ የአደባባይ ፋውንቴኖች፤ ዛፎች፤ ሰፋፊ መንገዶችና መዝናኛዎች ይጠቀሳሉ። ይህ ሥራ በከተማይቱ የተወሰኑ አካባቢዎች ጅማሮ ቢኖርም ገና ብዙ ስራ ይጠበቃል። ዛሬም በአዲስ አበባ አደባባዮች መጸዳዳት፤ ቆሻሻን በተገኘበት ሥፍራ መጣል፤ እንስሳትን በተከለከሉ ቦታዎች መልቀቅ፤ እንደጉልት ያሉ አነስተኛ ንግዶች አልጠፉም።

እነዚህን ሕገወጥ ግብይቶች ሥርዓት ማስያዝ የሚመለከተው አካል ኃላፊነት ይመስለኛል። ሠርቶ መብላት የዜጎች መብት ቢሆንም ህግን በጣሰ መልኩ ሊሆን ግን አይገባም። አደባባይ ደግሞ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለሚመጡ መተላለፊያ ነውና የህገ ወጥ ንግድ ትርምሱ አደብ ሊገዛ ይገባል። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ እንኳን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ታክሎበት ሁሉም መንገድ ከመጠን በላይ ህዝብ የሚንቀሳቀስበት ከሆነ ሰነባብቷል። ይህንን ትዕይንት መታዘብ የፈለገ ሰው በየትኛውም ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ እስከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል በየአደባበዩ ቢገኝ ሁኔታውን ማረጋገጥ ይችላል።

አንዲት ሀገር በሕግ እስከተዳደረች ድረስ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎቸ ህግ አክብረው መስራት ይጠበቅባቸዋል። ምንም ያህል የህግ ዕውቀት ባይኖረንም መንገድ ዘግተን እግረኛ መንቀሳቀስ እስኪሳነው ድረስ ማወክ ስህተት መሆኑ አይጠፋንም። እውነት ነው ህዝቡ ቅናሽ ዋጋ ይፈልጋል። የቡቲክ ዕቃ ዋጋ ሰማይ በነካበት ጊዜ በእንደነዚህ ዓይነት አካባቢዎች ደግሞ ሽያጩ ቅናሽ ነው። ይሁን እንጂ፤ መተላለፊያ እስኪጠፋ ድረስ መንገድ ዘግቶ መነገድ አይገባም። የከተማ አስተዳደሩ ለነዚህ ዜጎች የተለያዩ አካባቢዎች ከመንታ መንገዶች መካከል አንዱን በመዝጋት ቅዳሜና እሁድ ያለምንም ችግር እንዲሰሩ መፍቀዱን አስታውሳለሁ። በተለይ በስድስት ኪሎ፤ በካዛንችስ እና በሌሎችም አካባቢዎች እየተሰራበት ነው።

ይሁንና አሁንም በየአደባባዩ የሚካሄደው ትርምስ ተባብሶ ቀጥሏል። አንዳንድ ጊዜ ቀልድ በሚመስል ሁኔታ ደንብ አስከባሪዎች ከተወሰነ

ቦታ ሲያስነሷቸው ትንሽ እልፍ ብለው ምንጣፍ ዘርግተው ይሰራሉ። በዚህ ያባራሪና የተባራሪ ድራማ በነጋዴዎችም ሆነ በሌሎች ዜጎች ላይ የመኪና አደጋ ቢደርስ የማን ያለህ ይባላል? ህግ ባለበት ሀገር ይህ እንዴት ይሆናል? ችግሩ ለረጅም ጊዜያት ሲንከባለል የመጣ ቢሆንም፤ ለዚሁ ሲባል በህግ የተቋቋመው ተቋም ለምን መላ አይፈልግለትም? ኑሮን ለመቀየር የተገኘውን ሥራ መስራቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ህግ ከሁሉም

በላይ ነውና ህጉን ማክበርና ማስከበር ተገቢ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ባልተጻፈ ህግ ለዘመናት መተዳደራችን ይታወሳል። ይህ አኩሪ ባህላችን ተንዶ ግን የተጻፈውን ህግ ማክበር ተስኖናል።

ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በአምባገነን መሪዎች አበሳዋን ስታይ መኖሯ እውን ነው። እነዚህ አምባገነን መሪዎች ህዝባቸውን የመሩት በፍቅር ሳይሆን እንደብረት ቀጥቅጠው እንደሰም አቅልጠው ነው። ይህ ያለፈ ታሪካችን ስለሆነ እናስታውሰዋለን። ነገር ግን እኛም መልካም ነገር አልስማማ እያለን መቸገራችን ግልጽ ነው። በህግ አታድርጉ ስንባል አንቀበልም። በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት ጥሩ የሚባል ሀሳብ ቢያመጣም ቶሎ የመረዳት ችግር አለብን። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ይቅርታ፤ ፍቅር፤ መደመር የተባለ አዲስ አስተሳሰብ ለህዝቡ ለማስረጽ ቢሞክሩም ለተግባራዊነቱ ብዙ ስንጥር አንስተዋልም። ይህንን ቀና አስተሳሰብ ቀደም ካሉት መሪዎቻችን ሰምተነው አናውቅም። ከዚህ ይልቅ ፍለጠው፤ ቁረጠው የተባለውን የዱላ አገዛዝ ተሸክመን ኖረናል።

ሀገር የምትመራው በህግ ስለሆነ ፍቅሩ አልስማማን ካለ ያው የለመድነውን የኃይል አገዛዝ ጎትተን ማምጣታችን አይቀሬ ነው። በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ በሚባል ደረጃ ህገወጥነት ተንሰራፍቷል። ሰበብ እየፈለጉ መጋደል፤ ህገወጥ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ ማድረግ፤ ያለአሳማኝ ምክንያት በሸቀጦች ላይ ዋጋ መጨመር፤ መደለያ መቀበል በተለይ ለፍቶ አደሩን ህዝብ እያሰቃዩት ነው። በቀድሞው መንግስት (ደርግ) ወቅት በርበሬ ነጋዴዎች ከተተመነላቸው ዋጋ በላይ አስበልጠው ሲሸጡ በመገኘታቸው አስከፊ ርምጃ ተወስዶባቸዋል። ታዲያ፤ ሰዎች ከአግባብ ውጭ ይቀጡ ሳይሆን፤ አጥፊዎች ተከስሰው በፍርድ መታረም አለባቸው ለማለት ነው።

የቀድሞው መንግሥት (ደርግ) ወድቆ ኢህአዴግ ሀገሪቱን እንደተቆጣጠረ በተለይ የአዲስ አበባ ህዝቡ ራሱ ህግ አስከባሪ ሆኖ ለአንድ ዓመት ያህል ራሱን አስተዳድሯል። መደባደብ የለ፤ ስርቆት የለ፤ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ነው። ነጋዴውም በስርዓት ይሸጥ ነበር። ይህን ያህል አስተዋይ ህዝቦች ነበርን። ታዲያ ዛሬ የተሻለ መሪ ባገኘንበት ወቅት ለምን ህገ ወጥነት እንዲስፋፋ በር እንከፍታለን?

ነጋዴው መንግሥት የተመነለትን ግብር በሀቅ

እየከፈለ በተወሰነለት ቦታ ይስራ። በትራንስፖርት ንግድ የተሰማራውም በወጣለት ታሪፍ መሰረት ህግ ያክብር፤ በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ የተሰማሩት ነጋዴዎችም የዋጋ ተመን ባይወጣላቸውም ለህሊናቸው ሲሉ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሽጡ፤ ዳሩ ግን በሸቀጥ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይህን ቅን አሰራር ሲተገብሩ አይስተዋሉም። የፍጆታ እቃዎች ምክንያቱና ሰበቡ በማይታወቅ ሁኔታ በየቀኑና በየሳምንቱ ጭማሬ ይስተዋልባቸዋል። ህዝቡም በገቢው ላይ ለውጥ ሳይመጣ የየቀኑ የዋጋ ጭማሪ ሰለባ ሆኗል።

ባደጉት ሀገራት ገበያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግር የለውም። የህዝቡ ገቢና የመግዛት አቅም ያደገ ስለሆነና እንደአቅምም የሚገዛ ስለሚገኝ በፈለጉት ዋጋ መሸመት ይችላሉ። ያም ሆኖ ግን ነጋዴው በፈለገው ዕቃ ላይ የፈለገውን ዋጋ ለጥፎ አይሸጥም። ሥርዓት ተከትለው ነው የሚሰሩት፤ እኛ ኑሮአችን ከእጅ ወደአፍ ሆኖ ሳለ፤ ነጋዴው አጋጣሚ እንደፈለገው ዋጋ ቆልሎ ይሸጣል። ሀይ ባይ የለውም። ይህ ሥርዓት የለሽ ግብይት አደብ የሚገዛው መቼ ነው? በተለይ በመንገድ ላይ እየተሯሯጡ የሚነግዱ ወገኖቻችን በተዘጋጀላቸው የመስሪያ ቦታ ህግ አክብረው ቢሰሩ ለነሱም ከመሯሯጥና ከመገፋፋት ይድናሉ።

አንድ ቀኑን በማላስታውሰው እለት የሆነው እንዲህ ነው። መገናኛ አካባቢ መንገድ ላይ ዘርግተው የሚሸጡ ነጋዴዎች ደንብ አስከባሪዎች ሲመጡባቸው ዘልለው መኪና መንገድ ውስጥ ይገባሉ። በወቅቱ የነበረው የተሽከርካሪዎቹ ፍጥነት በመኪኖች ብዛት የተገደበ ባይሆን ኖሮ ወደመንገዱ ውስጥ ከነሸቀጣቸው እየተሽቀዳደሙ በገቡት ቁጥርና የድንግርግር ሩጫ አንጻር ከፍተኛ አደጋና እልቂት ሊደርስ ትችል ነበር።

በመሆኑም ፤ ነጋዴውም ከዚህ ዓይነት አስከፊ አደጋ ለመዳን ህግንና ህግን ብቻ አክብሮ መስራት አለበት። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነዚህ በየመንገዱ ዳር ምንጣፍ ዘርግተው ለሚሰሩ ወገኖች የጀመረውን ህጋዊ የማድረግና በአካባቢ እና በጊዜ ተወስነው የመስራት ልምድ እንዲገፉበት ክትትል ሊያደርግ ይገባል። “መንገድ ዳር አትስሩ” ግን ብቻውን መፍትሔ አይሆንም። እናም፤ ይህን ሥርዓት ያጣ የንግድ ሂደት መልክ ለማስያዝ መንግሥት ባለድርሻ አካላት አጋር ድርጅቶች እና ህብረተሰቡ፤ ራሳቸው ነጋዴዎችም ሊተባበሩ ይገባል።

ሠርቶ መብላት የዜጎች መብት ቢሆንም ህግን

በጣሰ መልኩ ሊሆን ግን አይገባም።

አደባባይ ደግሞ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለሚመጡ

መተላለፊያ ነውና የህገ ወጥ ንግድ ትርምሱ አደብ ሊገዛ ይገባል።

ብዥታ አጥርቶ “ልንመራህ አስበናል” የሚሉትን ፖርቲዎች ቁጥር ያሳንስለትና በእውቀቱና በክትትሉ ስር ያደርግለታል። የሚፈልገውንም እንዲመርጥ ያስችሉታል። በሌላ በኩል፤ እነርሱም ላንተ ቆመናል የሚሉትን ሕዝብ የምርጫ ድምጽ ከመበጣጠስና ከመነጣጠል ያድኑታል። በዚህም ቀደም ሲል በተመሳሳይ ችግር ተጋርጦበት ከነበረው ባልመረጠው ፓርቲ ወይም ድርጅት ከመተዳደር/ከመገዛት ይታደጉታል። ይህ ደግሞ ድርብ ውጤት ነውና መለመድ ይገባዋል።

በርግጥም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች/ድርጅቶች እንደዓላማቸው ቅርበትና እንደፍላጎታቸው አንድነት መሰባሰባቸው የማይታለፍ ወቅታዊ ጉዳይ ነው። በተለይ መጪውን የ2012 ምርጫ በሁሉም ወገን ተቀባይነት ያለው እንዲሆን የመጀመሪያው ርምጃ እና ተፈላጊ ጉዳይ የፖርቲዎቹ ቁጥር ማነስና ለአስተዳደርም ሆነ ለምርጫ ምቹ መሆን ነው። እናም በዓላማ አንድ ነን ወይም እንመሳሰላለን፤ የምንወክለው ሕዝብ ወይም ማህበረሰብ ተመሳሳይ ነው፤ እንዲሁም የምንከተለው ወይም የምናራምደው ርዕዮተ ዓለም ወይም የፖለቲካ መስመር ያገናኘናል የሚሉ ሁሉ ሊጣመሩ ወይም ሊዋሀዱ ይገባል። ይህ ደግሞ ዘመናዊነትና ተራማጅ አካሄድ ነው።

ይሁንና ጥምረቱ ወይም ውህደቱ ስስና በቀላሉ ለችግር በሚዳርጉ ጉዳዮች ዙሪያ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ይልቁንም ዘመንና ትውልድ በሚሻገሩ አገርንና ህዝብን ለዘለቄታው አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ፤ አብዛኛውን የሀገሪቱን ሕዝብ ባማከለ መልኩ ቢሆን ተመራጭ ነው እንላለን። እንዲህ ሲሆን ዛሬ የሚታየው ከመቶ የዘለቀው የፖለቲካ ድርጅቶቸ ቁጥር በጣት ወደሚቆጠር መጠን እንደሚወርድ አያጠራጥርም።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ባነሰ ቁጥር ለአስተዳደር ይመቻል። ወጪ ይቆጥባል፤ የሚበታተነውን መራጭ ወደአንድ ያሰባስባል። ለሕዝቡም ምርጫው በ“እከሌነት” ከሚሆን ይልቅ በሀሳብና በፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ይሆንለታል። እናም አማራጭ ፖሊሲ ለማቅረብም ሆነ ከዚህ በፊት በምርጫ እጦት የተንገላታ ሕዝብ መካስ የሚቻለው ፓርቲዎቸ አሁን በጀመሩት ሁኔታ እየተጣመሩ ወይም እየተዋሀዱ በአንድ ዓላማና በአንድ ጥላ ስር ተሰልፈው ሲቀርቡ ነው እንላለን።

በዚህ ረገድ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ ሌሎች ወደ ውህደት ለመምጣት ቁርጠኝነት ያሳዩ ድርጅቶች ጅምራቸው መልካም ነውና መወደስ አለባቸው፡፡ ይህ አገርንና ህዝብን ማዕከል፤ ዓላማንና ዴሞክራሲን መሰረት ያደረገ ውህደት እስከ ዛሬ ያጣነውን የህዝብ በምርጫ አሸናፊነት ያረጋግጣል ብለን እናምናለን፡፡

እንዲህ ያለው የፖለቲካ አካሄድ ሲለመድም ለመንበረ መንግሥት የሚደረገው ፉክክር ለማስተዳደር እንጂ ለመግዛት እንዳይሆን መተማመን ይፈጥራል፡፡ እናም ሁሉም አካላት ህዝብንና አገርን አስበው በኃላፊነት ሰርተው ለፍሬ እንዲበቁ ማገዝ የሁሉም የአገር ፖለቲካ ያገባኛል ባይ ግዴታ ነው እንላለን፡፡

Page 4: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

ዓለም አቀፍየካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 7

አንተነህ ቸሬ

ሳዑዲ አረቢያ በአገሪቱ መንግሥት ላይ ትችትና ተቃውሞ የሚሰነዝሩ ግለሰቦችን በፀረ-ሽብር ሕግ ሽፋን እያፈነችና መብታቸውንም እየጣሰች ነው፣ ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቃውሞ አቅርቦባታል፡፡ የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ካውንስል (UN Hu-man Rights Council) ሰሞኑን በጄኔቫ ባካሄደው ጉባዔ የባህረ ሰላጤዋ አገር ድርጊት ሃሳብን በነፃነት ስለመግለፅ የወጡ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የሚጥስ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ፊዮኑላ አዎላይን የተባሉ የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ባለሙያ የበርካታ አገራት የፀረ-ሽብር ሕግጋት ግራ የሚያጋቡና በግልፅ ያልተቀመጡ በመሆናቸው በፀረ-ሽብር ዘመቻ ሰበብ የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብቶች ለመድፈር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል፡፡

‹‹እነዚህ ሕግጋት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፤ ምሁራንን፤ ጋዜጠኞችን፤ ደራሲያንን፤ የሃይማኖት መሪዎችንና ሌሎች በማኅበረሰቡ ዘንድ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን መብት ለማፈን በጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው›› ብለዋል፡፡

ማይክል ፎርስት የተባሉ ሌላኛው የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ባለሙያ በበኩላቸው፣ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ዜጎች ላይ ስለሚፈፅመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክትትል ሲያደርጉ እንደነበር ጠቅሰው፣ ‹‹ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደረገው ደግሞ ሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ከሁሉም የከፋ የመብት ጥሰት

የሳዑዲ አረቢያ የ‹‹ፀረ-ሽብር›› ሕግና የመንግሥታቱ ድርጅት ክስእየተፈጸመባቸው መሆኑ ነው›› ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በመንግሥት ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት ሁሉም ግለሰቦች የት እንደሚገኙ እንደማይታወቅም ገልጸዋል፡፡

በጉባዔው ላይ የተገኙ የሳዑዲ አረቢያና የሌሎች አገራት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው፣ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የመብት ተሟጋቾች እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡ የባህረ ሰላጤው የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል (Gulf Centre for Human Rights) ባልደረባ የሆኑት ዘይነብ አልካዋጃ፤ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በቁጥጥር ስር ካዋላቸው የመብት ተሟጋቾች መካከል አንዳንዶቹ በአገሪቱ ያለውን ተባዕታይ አገዛዝ የሚቃወሙና ለፆታ እኩልነት የሚታገሉ ስመጥር ግለሰቦች በመሆናቸው እርምጃው የግለሰቦቹን እንቅስቃሴ ለመግታት የታለመ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

ማዕከሉ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በግለሰቦቹ ላይ የሚፈፅማቸውን የመብት ጥሰቶች በዝርዝር የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ ማድረጉንም ዘይነብ አልካዋጃ ገልጸዋል፡፡

ኦማይማ አል-ናጃር የተባለች በስደት የምትኖር ሳዑዲ አረቢያዊት ጦማሪ፤ ሴቶች መኪና የማሽከርከር መብት እንዲኖራቸው ሲታገሉ የነበሩ ሴቶች ትግላቸው ከግብ ቢደርስም እነርሱ ግን እስካሁን ድረስ በእስራት ላይ እንደሚገኙ ጠቁማለች፡፡ ‹‹ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት ካላደረገ በስተቀር እነዚህ ሴቶች ቀሪውን ዕድሜያቸውን በእስራት እንደሚያሳልፉ ግልፅ ነው›› ብላለች፡፡

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በዜጎች ላይ እንዲህ ዓይነት እርምጃዎችን የሚወስደው ግለሰቦቹ በመንግሥት አሰራር ላይ ጥያቄ ስላነሱና ትችት ስላቀረቡ ብቻ እንደሆነ የሚናገሩት ደግሞ አርሳላን ኢፍቲቅሃር የተባሉ የሕግ ባለሙያ ናቸው፡፡ እንደባለሙያው ማብራሪያ፣ የአገሪቱ ባለስልጣናት ‹‹የፀረ-ሽብር ሕግ›› ብለው የደነገጓቸውን ሕግጋት የሚጠቀሙባቸው የመብት ተሟጋቾችን፣ የሃይማኖት መሪዎችንና ጋዜጠኞችን ለማጥቃት ነው፡፡ ‹‹ሳዑዲ አረቢያ ‹ግልፅነት ያለው የመንግሥት አሰራር እየተከተለችና በለውጥ ጎዳና እየተራመደች ነው› በሚባልበት ወቅት አገሪቱ ግን የኋልዮሽ እየተጓዘች እንደሆነ

ልዑል አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን

አንተነህ ቸሬ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በዚምባብዌ ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዝመውታል፡፡ የፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አዲሱ መንግሥት በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ላይ አደጋ

መዘንጋት የለበትም›› በማለት ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የፀረ-ሽብር ርምጃዎች አሜሪካ ከመስከረም 11 ጥቃት በኋላ የወሰደቻቸውን የፀረ-ሽብር ተግባራት ያስታውሳሉ፡፡ የአሜሪካ መንግሥት በወቅቱ የወሰዳቸው ርምጃዎች በሙስሊሞች፣ በአረቦችና በደቡብ እስያ አገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ነበሩ›› ይላሉ፡፡

እጅግ ሲበዛ አፋኝ የሕግ ስርዓት ባላት አገር ቅንጣት ታክል ገለልተኛነትና ነፃነት ይኖራቸዋል ተብለው በማይታሰቡ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡ የመንግሥትን አሰራር የሚነቅፉ የዚያች አገር ዜጎች ምን ዓይነት ፍርድ ሊገጥማቸው እንደሚችል ማሰብ እንደማይከብድም የሕግ ባለሙያው አርሳላን ኢፍቲቅሃር ይናገራሉ፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጄኔቫ ጽሕፈት ቤት የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር አብዱላዚዝ ሞ አልዋሲል፤ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የሚወስዳቸው ሁሉም ርምጃዎች ከሰብዓዊ መብት ጋር ተያያዥነት ካላቸው ዓለም አቀፍና ብሔራዊ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣሙ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ላይ አተኩረው የሚሰሩ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የመብት ተሟጋች ግለሰቦች ሳዑዲ አረቢያ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደምትፈፅም በተደጋጋሚ ሲገልፁ ይስተዋላል፡፡ ከወራት በፊት በቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የተፈፀመው የጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ግድያ የታዘዘውና

የተቀነባበረው በሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ነው የሚል ሪፖርት መውጣቱ የአገሪቱ መንግሥት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ከባድ ተቃውሞና ውግዘት እንዲገጥመው አድርጎታል፡፡ የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላና የደኅንነት ተቋም (CIA) በግድያው የአልጋ ወራሹ መሐመድ ቢን ሰልማን እጅ እንዳለበት መረጃዎቼ ይጠቁማሉ ሲል፤ የሴኔቱ አባላት የሳዑዲ መንግሥት ሌሎችም አምባገነኖች መቀጣጫ የሆነ ቅጣት መቀጣት አለበት የሚል ጠንካራ አቋም ይዘዋል፡፡ ይሁን እንጂ፤ ‹‹አልጋ ወራሹ ከደሙ ንጹህ ነው›› ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሴናተሮቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው የኻሾግጂ ግድያ አሁንም አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

ወጣቱ የሳዑዲ ንጉሳዊ መንግሥት አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን፤ ሳዑዲ አረቢያ ካለፉት ጊዜያት የተሻለ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ምኅዳር እንዲኖራት አድርጋለሁ ብለው ቃል ከገቡ በኋላ፤ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩና ከዚህ ቀደም ተከልክለው በቆዩባቸው አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲሳተፉ አድርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ሳዑዲ አረቢያ በነዳጅ ላይ ጥገኛ ከሆነ ምጣኔ ሀብት እንድትላቀቅ የሚያስችሉ ርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ፤ ወትሮም ቢሆን ከሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጋር ስሟ በበጎ የማይነሳው ሳዑዲ አረቢያ ዛሬም በመስኩ መሻሻል አላሳየችም ተብላ ክፉኛ እየተብጠለጠለች ነው፡፡

የደቀኑ ርምጃዎችን እየወሰደ በመሆኑ ማዕቀቡ መራዘሙን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ተናግረዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎች ዜምባብዌ ከገባችበት የምጣኔ ሀብት ቀውስ እንድትወጣ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት ጥሪ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፤ የአሜሪካ ምላሽ ግን ማዕቀቡን ማራዘም ሆኗል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የማዕቀቡን መራዘም አስመልክቶ በሰጡት አጭር መግለጫ፤ ‹‹የዚምባብዌ

ፖለቲከኞች ስትራቴጂዎችና ድርጊቶች በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ አደጋ መደቀናቸውን ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም የማዕቀቡ መራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል›› ብለዋል፡፡

አሜሪካ በዚምባብዌ ላይ ማዕቀብ የጣለችው የአገሪቱ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ይጥሳል በሚል መነሻ ነበር፡፡ የፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ መንግሥት በመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ላይ ገደብ የሚጥሉ ሕጎችን እስካላነሳና መንግሥትን መቃወምን እስካልፈቀደ ድረስ ማዕቀቡ

እንደሚቀጥል የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡ እንደባለስልጣናቱ ገለፃ፣ በአሁኑ ወቅት ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋንና የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን ጨምሮ 141 ግለሰቦችና ድርጅቶች ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ምናንጋግዋ የዜምባብዌ ገዢ ፓርቲ (ZANU-PF)ን ጨምሮ፤ በቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የአስተዳደር ዘመን አሜሪካ ማዕቀብ የጣለችባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ማዕቀቡ እንዲነሳላቸው ጠይቀው እንደነበር

አሜሪካ በዚምባብዌ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዝማለች

ይታወሳል፡፡ ዚምባብዌ በአሁኑ ወቅት ካለፉት አስር ዓመታት

ወዲህ የከፋ ነው በተባለ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ትገኛለች፡፡ አገሪቱ ያላት የመጠባበቂያ ገንዘብ በእጅጉ እንደተመናመነ ይነገራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፤ የነዳጅ እጥረት ደቡብ አፍሪካዊቷን አገር ከባድ ፈተና ውስጥ ዘፍቋታል፡፡ የአገሪቱ መንግሥት ባለፈው ጥር ወር ይፋ ያደረገው የ150 በመቶ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ዜጎችን ለአደባባይ ተቃውሞ ዳርጎ ከእስራትና ብጥብጥ ባለፈ የሕይወት ዋጋ አስከፍሏል፡፡

Page 5: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከኢትዮጵያ ሂሣብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ረቡዕ የሚወጣ

9

ለዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች ትግበራ ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት

ጌትነት ምህረቴ

ከአምስት ዓመት በፊት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዜጎች ብሄራዊ መታወቂያ እንዲሰጥ አዋጅ ቢያጸድቅም እስካሁን ድረስ ሥራ ላይ አልዋለም፡፡ በዚሁ ወቅትም የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በ2005 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሰነድ ላይ ለብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት 3 ሚሊዮን 773 ሺህ 271 ብር በጀት መድቦ ነበር። በአሁኑ ጊዜም ይህ ብሄራዊ መታወቂያ የመስጠት ስልጣንም አዲስ ለተቋቋመው ሰላም ሚኒስቴር ተሰጥቷል።

በአዋጁ መሰረት አዲስ ይወጣል የተባለው ብሄራዊ መታወቂያ የግለሰቦችን ማንነት በቀላሉ መለየት የሚያስችል ምስጢራዊ ቁጥር ያለው ነው፡፡ የአዋጁ መውጣት የብሄራዊ መታወ ቂያ በተለያዩ ስሞችና ማንነቶች በህገወጥ መንገድ መታወቂያዎችን የማውጣት የወንጀል ድርጊ ቶች እንዳይፈጸሙ ይከላከላል ተብሏል፡፡ ረቂቅ አዋጁ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የማውጣት ግዴታ እንዳለበት ሲያመላክት፤ ይህንን ግዴታ ውን ያላከበረም በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል። በተጨማሪም በምዝገባ ወቅት ሐሰተኛ መረጃ የሚሰጡ ሰዎች ከአንድ እስከ አምስት ዓመት እስራት ይከናነባሉ።

መታወቂያው የግለሰቦችን ሙሉ አድራሻና ማንነት የሚገልፅ መረጃ የሚይዝ ሲሆን፤ ለአሥር ዓመትም ፀንቶ እንደሚቆይ ረቂቅ አዋጁ አመልክቷል፡፡ በቀድሞው በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ፣ የራሱ ምስጢራዊ ኮድ ያለው መታወቂያ በብሔራዊ ደረጃ ማዘጋጀት ያስፈለገው ሽብርና ወንጀልን ለመከላከል፣ ለግብር አከፋፈል፣ ለፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት ጥቅም እንዲሰጥ ታስቦ ነው ይላል፡፡ሆኖም በአገሪቱ ብሄራዊ መታወቂያ ሥራ ላይ አለመዋሉም ባንኮች ለመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ብድር እንዳይሰጡ ችግር ፈጥሮባቸዋል።

የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት

አቶ አቤ ሳኖ በኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ አለመኖሩ የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መልኩ እንዳይሰጡ ማድረጉን ያረጋግጣሉ፡፡ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ከሚያስፈልጉት አንዱ የደንበኛን ታሪክ በእርግጠኝነት ማወቅ ይጠይቃል፡፡ የደንበኛን የግል ታሪክ በደንብ ማወቅ ሲቻል፤ ማለትም ምን ገቢና ወጪ እንዳለው፤ ምን ወንጀልና መልካም ነገር እንደሰራ ዝርዝር ታሪኩ ከታወቀ ወደ ባንክ ቤት ሳይመጣ ባለበት ቦታ የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት መስጠት ይቻላል። ይህ መረጃ ሊገኝ የሚችለው ደግሞ የዜግነት ቁጥር ያለው ብሄራዊ መታወቂያ (ናይሽናል አይዲ) ሲኖር ነው ፡፡

በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ብሄራዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት ቢኖር እያንዳንዱ ዜጋ ማንነቱ በአሻራና በዓይኑ ብሌን ተለይቶ ይታወቃል፡፡ የትም ቦታ ቢሄድ መቀየር የማይችል ብሄራዊ መታወቂያ ይኖረዋል። ብድር ባይመልስ፣ ግብር ባይከፍል፣ ወንጀል ቢሰራ፣ ቢያጭበረብር ሁሉም ታሪኩ በኤሌክ ትሮኒክስ መታወቂያ ሥርዓቱ ሰፍሮ ይገኛል። ይህ መረጃ ለባንኮችም ሆነ ለመሰል ተቋማት ተደራሽ ስለሚሆን የደንበኛውን ማንነት አውቆ ያለ ስጋት ማንኛውንም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የባንክ አገልግሎቶች መስጠት ይቻላል የሚል ሃሳብ አላቸው። አቶ አቤ።

ሌሎች አገሮች ብሄራዊ መታወቂያ በመኖሩ ባንኮች የተቀላጠፈ አገልግሎታቸውን በቴክ ኖሎጂ ስለሚሰጡ ደንበኞችና ባንኮቹ በአካል የማይገናኙበት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ በአንጻሩ በኢ ትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ባለመኖሩ ባንኮች ደንበኞቻቸውን የሚያገለግሉት በጣም ውድ በሆነ ዋጋ ነው፡፡ ምክንያቱም፤ በቴክኖሎጂ በቀ ላሉ የሚሰጠውን አገልግሎት በሰው ኃይል ነው እየሰጡ ያሉት፤ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አንድ ሰው መታወቂያው መቶ ሊሆን ስለሚችል ትክክለኛው ሰው በመታወቂያው አይታወቅም፡፡ ለማጭበርበርም የተጋለጠ ነው፡፡

በቂ ገንዘብ በባንኮች ውስጥ እያለ ስጋቱን በመፍራት ብቻ የብድር አገልግሎት ሥራ ላይ አይውልም፡፡ የዜጎችን ትክክለኛ መረጃ የሚገኝበት በኮምፒዩተር የታገዘ ብሄራዊ መታወቂያ ስለሌለ የሚበደር ሰው መምረጥ ድካሙና ወጪው ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ከሙያተኞቹ ጋር የጥቅም ትስስር ሊኖር ይችላል በሚል ሙሉ እምነት የለም፡፡ ለደንበኞችም በቴክኖሎጂ የታገዙ የባንክ አገልግሎቶችን

ለመስጠት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ በጥቅሉ የብሄራዊ መታወቂያ አለመኖር ባንኮች የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በጣም ውስን እንዲሆኑ አድርጓል ሲሉ አቶ አቤ ችግሩን አሳይተዋል።

የዳሸን ባንክ የማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ አለመኖር ባንኮች የተቀላጠፈና ከስጋት ነጻ የሆነ አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል የሚለውን የአቶ አቤ ሀሳብ ይጋራሉ፡፡ በተለይ ብሄራዊ መታወቂያ አለመኖር በባንኮች የብድር አቅርቦት ተደራሽነት ላይ ትልቅ ችግር ፈጥሯል ይላሉ። ባንኮች ለመካከለኛና ለዝቅተኛ ገቢ ላለው የህብረተሰብ ክፍል በስፋት ብድር ለማቅረብ አንዱ መሰረታዊ ችግር ኤሌክትሮኒክስ የሆነ ብሄራዊ መታወቂያ (ብሄራዊ አይዲንቲፊኬሽን ሲስተም) አለመኖሩ ነው።

ሰዎች በየትኛውም የአገሪቷ ጫፍ ቢኖሩ በተለየ መልኩ የሚታወቁበት መታወቂያ ስለሌለ እዚህም እዚያም ከአንድ በላይ መታወቂያ ማውጣት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች አሉ። ሰዎች በተለየ መልኩ የሚታወቁበት ስርዓት ከሌለ ደግሞ ከማስያዥያ ውጭ ብድር ማበደር ስጋት አለው። በአንጻሩ መታወቂያ ቢኖር ኖሮ ተበዳሪዎች ከየትኛው ባንክ ብድር መውሰዳቸውና የብድር አመላለስ ታሪካቸው በቀላሉ ስለሚታወቅ የብድር ተጠቃሚ ለማድ ረግ የሚፈጥረው ስጋት አይኖርም፡፡

በተቃራኒው ብሄራዊ መታወቂያ አለመኖር የባንኮችን የብድር አቅርቦት ውስን አድርጎታል። በተለይ መካከለኛና አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዳይሆኑ አድርጓል፡፡ ለምሳሌ፤ የዳሸን ባንክ የመኪና ብድር ለተወሰኑ ትልልቅ ተቋማትና ግብረሰናይ ድርጅት ሠራተኞች ይሰጣል፡፡ ተቋማቱ ኃላፊነት ወስደው፣ ማስያዥያ አስይዘው፣ ብድሩን በየወሩም ከደመወዛቸው እየቆረጡ ለባንኩ ገቢ ለማድረግ ስምምነት በማድረጋቸው ሠራተኞቻቸው ከባንኩ የመኪና መግዥ ብድር የሚያገኙበት ሁኔታ መኖሩን አቶ ሙሉጌታ ያነሳሉ።

በአገሪቱ ብሄራዊ መታወቂያ ቢኖር ግን፤ ይህ የብድር አቅርቦት በዚህ ደረጃ ሳይወሰን አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ጭምር የአቅርቦቱ ተጠቃሚ ማድረግ ይቻል ነበር። በተለይ፤ በአሁኑ ጊዜ ባንኮች በኤሌክትሮኒክስ በታገዙ የግብይት ስርዓቶች ውስጥ እየገቡ

በመሆኑ የብሄራዊ መታወቂያው አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ አይገባም፡፡ ስለዚህ፤ ለዘርፉ ዕድገትና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት አስፈላጊነቱ የጎላ በመሆኑ መንግሥት ሊያስብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ይሳቅ መንገሻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ክፍል ኃላፊ ደግሞ፤ ባንኮች ለደበኞቻቸው ሂሳብ ሲከፍቱ፣ የሀዋላና የብድር አገልግሎት ሲሰጡ ሥራቸው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ስለሆነ የእያንዳንዱን ሰው መረጃ ለማወቅና ለማረጋገጥ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ምክንያቱም አንድ ሰው ብዙ መታወቂያዎች ሊኖሩት ይችላል፡፡ በቴክኖሎጂ የታገዘ ወጥ አገራዊ መታወቂያ ካለ ግን ማንነቱ በቀላሉ ይታወቃል፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴውም ከዚህ ስርዓት ጋር የተቆራኘ ስለሚሆንና የሁሉም መረጃዎች መነሻ መታወቂያ ስለሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ መታወቂያ መኖሩ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወደፊት ሁሉም ሰው ብሄራዊ መታወቂያ እንዲኖረው ሁሉም በኮምፒዩተር ተመዝግቦና ማንነቱ ታውቆ የትም ቢሄድ በዚህ በመታወቂያ የሚለይበት ሁኔታ ቢፈጠር ለባንኮች ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ተቋማትም በጣም ጠቃሚ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

የብሄራዊ መታወቂያ አለመኖር በተጭበረበረ መልኩ ብዙ መታወቂያዎች ለማውጣት ስለሚ ያስችል የደንበኞችን ማንነት ለማወቅ ረጅም ጊዜ ይወስዳል፡፡ ስጋቱም ከፍተኛ በመሆኑ የባንኮች አገልግሎቶች በዓይነት ውስን ናቸው። ብሄራዊ መታወቂያ ቢጀመር ግን የግለሰቦች ትክክለኛ መረጃ ስለሚኖር ባንኮች ከስጋት ነጻ ሆነው የተለያዩ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈና ተደራሽ በሆነ መልኩ ለሁሉን የህብረተሰብ ክፍሎች መስጠት ያስችላቸዋል፡፡ ወጪያቸውንም ይቀን ስላቸዋል፡፡ ጊዜያቸውን ይቆጥብላቸዋል። በጥቅሉ የተቀላጠፈ ኢንቨስትመንት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

ብሄራዊ የመታወቂያ ሥርዓት በሰለጠኑ አገሮች ብቻ ሳይወሰን በአፍሪካም ተግባራዊ ተደርጎ አገሮች የፋይናንስ ሥርዓታቸውን እያቀላጠፉበት ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጋምቢያ፣ ቦትስዋና፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ ይገኙበታል። ኢትዮጵያ ግን ትልቅ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቀስ ቢሆንም የብሄራዊ መታወቂያ ሥርዓት እስካሁን ድረስ መዘርጋት ተስኗታል።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አንድ ሰው

መታወቂያው መቶ ሊሆን ስለሚችል

ትክክለኛው ሰው በመታወቂያው አይታወቅም፡፡ለማጭበርበርም የተጋለጠ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በሀገሪቱ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች ትግበራ ተፈፃሚ ለማድረግ ዋና ዋና የሚባሉ የሚመ ለከታቸው ተቆጣጣሪ እና ባለድርሻ አካላት በመለየትና የጋራ የትብብር ስምምነት በመፈራረም ሊያሰራ የሚችል የቁጥጥር ድግግሞሽን ባስቀረ እና ጥራትን በሚጨምር መልኩ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ሪፖርት አቅራቢ አካላት ለንግድ ድርጅቶቻቸው አግባብነት ያላቸው ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መተግበርን ተከትሎ ከሚከሰቱ ለውጦች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ እንደ የተሰማሩበት የሥራ ባህሪ ተፈጻሚ እየሆኑ ያሉ አስገዳጅ የሆኑ የሪፖርት አቀራረብ ቁጥጥር ሥርዓቶችን መገምገምና መከለስ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ሪፖርት አቅ ራቢ አካላቱ እና ቦርዱ በሚመሩባቸው ህጎችና አሰራሮች መካከል ያሉ ክፍተቶችን የሚያጠናና በሚያጋጥሟቸው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለመቀበል በሚያደርጉት ዝግጅት ሂደት ላይ ምክር እና ድጋፍ የሚሰጥ ተዛማጅ ከሆኑ ተቋማት የተውጣጣ የግብረ ኃይል ቡድኖች ተቋቁሟል፡፡ ከዚሁ በተጓዳኝ በየመስኩ የተዘረጋውን አስገዳጅ የቁጥጥር ስርዓት ለመከለስ የሚያስችል እቅድ በማዘጋጀት ተፈጻሚ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የሂሳብ አያያዝና የኦዲት ደረጃዎችን መተርጎምን በተመለከተ ግብረ ኃይሉ ከእነዚህ የክትትል አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ፍላጎቶችና በደረጃዎቹ መካከል ተቃርኖ እንዳይኖር በማድረግ በአገሪቱ እምነት የሚጣልበት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ሥርዓት እንዲኖር ይደረጋል፡፡ ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች የሚደረገውን ሽግግር በተመለከተ የሂሳብ መግለጫዎች አዘጋጆችና ተጠቃሚዎች፣የትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ተቆጣጣሪ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚዘጋጀው እቅድ በሚገባ የተቀናጀና ሁሉም እንዲያውቁት የተደረገ መሆን ይኖርበታል።

የድርጊት መርሐ ግብሩ እና በውስጡ የተካተቱት ዝርዝር ተግባራት በተቀመጠላቸው

የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠናቀቅ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ይህም ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች የሚደረገውን ሽግግር ሊኖረው ስለሚችለው ውጤት ግንዛቤ መፍጠርን፣ የተቀናጀ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የክትትል ስርዓት በሀገሪቱ ለማስፈን የሚቻልበትን ሁኔታ በመለየት በጋራ የመስራት አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ ያስጨብጣል። ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች በሚደረገው ሽግግር በድርጅቶች የፋይናንስ አቋም እና አፈጻጸም ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ጊዜያዊ ውጤት መረጃ መስጠትን ጭምር ያካትታል፡፡ በዚህ ረገድ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲፈጽሙ ይጠበቅባቸዋል፡፡

- በሂሳብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ረገድ የሚነሱ ጉዳዮችን ማወቅ፣ በአገሪቱ በሥራ ላይ ባለው የሂሳብ አያያዝና የሪፖርት አቀራረብ ማዕቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መካከል ያሉትን ዋና ዋና ክፍተቶች መለየት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በተመለከተ አዲስ ለሆኑ ጉዳዮች ትኩረት መስጠት ማለትም ገና በረቂቅ ደረጃ ያሉ ደረጃዎችና ቁርጥ ያለ አቋም ያልተወሰደባቸውን ... ወዘተ። በተቆጣጣሪ አካላት ወይም በህግ ሪፖርት እንዲደረግለት ለታዘዘ አካልና ለግብር ሰብሳቢ መ/ቤት በሚቀርብ ሪፖርት ላይ የሚያስከትለውን ውጤት መመርመር እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎች በየዓመቱ ጉልህ የሆነ ለውጥ ሊደረግባቸው የሚችል ስለመሆኑ መረዳት ያስፈልጋል።

እነዚህ ጉዳዮች በሚገባ ካልተስተናገዱ ሊከ ሰቱ ከሚችሉ ችግሮች መካከል በዋናው መ/ቤት የተለዩ ክፍተቶችን በስሩ በሚገኙ ድርጅቶች አለማወቅና በሽግግር እቅዳቸው ውስጥ አለ ማካተት፤ በድርጅቱ ውስጥ ወጥ የሆነ የደረጃዎች አተረጓጎም አለመኖር፤ በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መሰረት የተዘጋጁ የሂሳብ መግለጫዎች የጥራት ደረጃ ዝቅተኛ መሆን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መሰረት የሚደረጉ ማስተካከያዎች ዘገምተኛ መሆን ይጠቀሳል፡፡

- መምራት የሚቻለው መለካት ሲቻል ብቻ መሆኑን መገንዘብ ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች የሚደረገውን ሽግግር በፋይናንስና በድርጅቱ ሥራ ላይ የሚኖረውን ውጤት መረዳት፤

ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ሥራ ላይ ሲውሉ ሊኖር የሚችል የውጤት መዋዠቅን ለማለዘብ ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎችን ከወዲሁ መወሰን ፤ የሥራ አስፈፃሚዎች በአዲሶቹ የሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ የተዛቡ ትርጉሞችንና አሠራሮችን ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች በሚገባ ካልተስተናገዱ ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች መካከል ለውጡ በፋይናንስ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ እጅግ ዘግይቶ መረዳት አንዱ ነው። በዚህም የተነሳ ችግሩን ለመቀነስ የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ ወይም አማራጮችን ለማጥናት በቂ ጊዜ ያለመኖር፤ አሁን በሥራ ላይ ያለው የሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ስርዓትና ደጋፊ ቴክኖሎጂ ከአንድ በላይ ደረጃዎችን በአንድ ላይ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም የሌለው በመሆኑ ህግን ተከትሎ ያለ መስራት ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል።

- የአሰራር ስርዓቶችንና የሥራ ሂደቶች ለዓለም አቀፍ ደረጃዎች ተስማሚና በቀጣይነት ሊደግፉት የሚችሉ መሆኑን ማረጋገጥ፤ የአሰራር ሥርዓቶችና የሥራ ሂደቶች በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ የተጠቃለሉ የሂሳብ መግለጫዎች አዘገጃጀት ስርዓቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽ ዕኖ መፈተሽ፣ መረጃ ለማግኘት በሶፍትዌር ፕሮግራሞች መነሻ ኮዶች ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ለውጦችን አስቀድሞ መወሰን ያስፈልጋል። የንግዱን ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መሰረት የሂሳብ መግለጫዎችን ለማዘጋጀት የሚያስችል እና የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ የሚደግፉ አዳዲስ አሰራሮችን መተግበር ተገቢ ነው።

ስለሆነም እነዚህ ጉዳዮች በሚገባ ካልተስ ተናገዱ ሊከሰቱ ከሚችሉት ችግሮች በዓለም አቀፍ የሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች ላይ የተመሰረተውን አዲሱን ስርዓት ጥንካሬ ለማወቅ የሙከራ ፍተሻ ማድረጊያ ጊዜ አለመኖር

አንዱ ነው። አሁን ያሉት ስርዓቶች የዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለማስተናገድ የሚችል አቅም የሌላቸው መሆን፣ ዓለም አቀፍ የሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎችን ከነባሩ ስርዓት ጋር ለማስተጋበር በቂ ጊዜ ስለማይኖር ከስርዓቱ ውጪ የሚያልፉ በርካታ ሥራዎች መኖራቸው ነው፡፡

- ስርዓቱን ለመተግበር ቁልፍ ሚና ያላቸውን ሰዎች ማብቃት ማለትም በከፍተኛ ሥራ አስፈፃሚው ደረጃ ድጋፍ ማግኘት፣ የድርጅቱን ይሁንታና ድጋፍ ማግኘት፤ በቂ የስልጠና/እውቀት ሽግግር ሥራዎችን ለመስራት ማቀድ እና ጠንካራ የለውጥ ሥራ አመራር ሥራዎችን መስራት ነው፡፡

ስርዓቱን ለመተግበር ቁልፍ ሚና ያላቸውን ሰዎች ማብቃት ካልተቻለና በሚገባ ካልተስተናገዱ ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች መካከል በመስኩ የሰለጠነ ባለሙያ አለማግኘት፣ በአመራሩ ዘንድ ስለዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች እና ከባለሃብቶች ጋር የሚኖርን ግንኙነት በአግባቡ ስለመምራት በቂ ግንዛቤ አለመኖር፤ ከአ ማካሪዎች ወደ ፋይናንስ ሠራተኞች በቂ የእውቀት ሽግግር አለመኖር፤ የሥራ አመራር አባላት በፕሮጀክት አፈጻጸም ረገድ ያላቸው የሥራ ድርሻና ኃላፊነት ግልጽ አለመሆን፤ ከበጀት በላይ ማውጣት እና ሥራዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማጠናቀቅ አለመቻል ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ናቸው፡፡

ሪፖርት አቅራቢ አካላት የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳና ዓመታዊ የሽያጭ ወይንም የገቢ መጠን መሰረት ድርጅታቸውን በቦርዱ አስመዝግበው ተገቢውን ደረጃ ለመተግበር የሚያስችል አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጀመር አለባቸው፡፡

በአዋጅ ቁጥር 847/2006 መሰረት ኩባንያ ዎችን ጨምሮ ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ድርሻ ያለው፣ መስፈርቶቹን የሚያሟላ የግል፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የሚገባውን ደረጃ መተግበር «ቢያንስ» ድርጅቱን ከኪሳራና ከውድቀት ስጋት ለማዳንና «ቢበዛ» ግዴታ መሆኑን አውቆ ለፋይናንስ ስርዓቱ ጤናማነት ሁሉም ሚናውን ሊወጣ ይገባል፡፡

Page 6: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

ፖለቲካየካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 11

አጎናፍር ገዛኸኝ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራ ሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ማሻሻያዎችን እያደረገ እንደሆነ ይገለፃል። ፓርቲው አዲስ የመዋቅርና የፖለቲካ አካሄድም ለመከተል እየሰራ መሆኑ ይሰማል። ለመሆኑ ድርጅቱ እየሰራቸው ያላ ቸው ሥራዎች ምንድናቸው? በሚለው ዙሪያ ከድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገን ለአንባቢዎቻችን እንደሚከተለው አቅርበናል።

አዲስ ዘመን፡- ኢህአዴግ መኖሩን የሚጠራጠሩ አሉ። ኢህአዴግ አለ?

አቶ መለሰ፡- ጥያቄውን በሁለት መልኩ ማየት ይገባል። ድርጅታዊ ህልውናን በሚመለከት አንድ ፓርቲ ሊኖር የሚገባው ተቋማዊ አቋም አለው። ምክር ቤት፣ ጉባዔ፣ ሥራ አስፈፃሚና ሌሎች ነገሮች ሁሉ አለው። በአገሪቱም እንደ ፓርቲ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ሲታገልና ሲያታግል የቆየ፤ አሁንም በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ የሚመራ ነው። በህዝብ የተመረጠና አገር የሚያስተዳድር መሪ ፓርቲ ነው። እነዚህን ሁኔታዎች ወስዶ ድርጅቱ አለወይ? ከተባለ መልሱ አለ ነው።

ሁለተኛው ሁኔታ ኢህአዴግ በተልዕኮና በይዘት ምን ይመስላል? ከሆነ ጥያቄው ኢህአዴግ በባህሪው፣ በዓላማው እና በተልዕኮው ተራማጅ ፓርቲ ነው። ተራማጅ ፓርቲዎች በባህሪይ ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ የሚታገሉ ናቸው። ኢህአዴግም የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት በተለያዩ ስልቶች የሚታገል ነው። በዚህም የተለያዩ ለውጦችንም ሲመራ ነበር። አሁንም ከተራማጅ ባህሪው ተነስቶ በአገራችን በህዝብ ተገፋፍቶ የመጣውን ለውጥ እየመራና እያስተባበረ ነው። የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ተረድቶ የለውጡን ዓላማ ለማሳካት እየመራ ራሱንም እያስተካከለ ያለ ፓርቲ ነው። ኢህአዴግ አለ? ወይስ የለም? ለሚለው ጥያቄ ከዚህ ውጭ መልስ የለኝም።

አዲስ ዘመን፡- «ኢህአዴግ አለ። ከተራማጅ ባሕሪው ተነስቶ ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እያደረገ ነው፤» ነው የሚሉኝ?

አቶ መለሰ፡- ኢህአዴግ አለ። እንደተራማጅ ፓርቲ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ራሱን እያስተካከለ ወደፊትም ይቀጥላል።

አዲስ ዘመን፡- ቀደም ባለው ኢህአዴግና በአሁኑ ኢህአዴግ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

አቶ መለሰ፡- ከህብረተሰቡ የለውጥ ፍላጎት ተነስቶና በተራማጅ ባህሪው ምክንያት ኢህአዴግ ራሱን እየለወጠ ነው። ለውጡ የህብረተሰቡን ፍላጎት ከመምራት ጋር የሚያያዝ ነው። ድርጅቱ ከአሁን በፊት ለበርካታ ለውጦች ምላሽ እየሰጠ ነው የመጣው። አሁንም የደረስንበትን የህብረተሰብ ዕድገትና ትግሉ የሚጠይቀውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለውጡ ከህዝብ ቢመጣም ተቀብሎ እየመራ ነው። ከአሁን በፊት ለውጥ ሲታሰብ ኢህአዴግ ራሱ ቀድሞ አቅዶ ይመራው ነበር። አሁን ግን ለውጡ ኢህአዴግ አቅዶት ሳይሆን በህብረተሰብ ግፊት የመጣ ነው። መለያ ባህሪው ይህ ነው። የለውጡ ዋና ዋና ምክንያቶችም ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ የተካሄደው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገቶች የፈጠሯቸው ተጨማሪ ፍላጎቶች ናቸው።

አዲስ ዘመን፡- በለውጡ ሂደት በአራቱ ግንባር ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል?

አቶ መለሰ፡- የፓርቲዎቹ ግንኙነት የሚወሰነው በአሰራራቸውና አደረጃጀታቸው ነው። አራቱም ብሄራዊ ድርጅቶች የለውጡ መነሻ የሆነውን የጥልቅ ተሀድሶ በጋራ በመገምገም አቅጣጫ አስቀምጠዋል። በ17ቱ ቀናት የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ግምገማ አመራር መቀየር እንዳለበት ተስማምተዋል። ከአመራር ለውጥ በኋላ በተወሰዱ ርምጃዎች አገሪቱ ከነበረችበት የሰላም ችግር ወጥታ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል። በርካታ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። ለውጡ በመልካም ዕድልና በስጋት ታጅቦ ቢሄድም ተስፋው የሚያመዝን እንዲሆን አድርጎታል።

በሂደት አራቱ ድርጅቶች በአሰራሮቻቸው በጋራ በሚያስቀምጡት አቅጣጫ እና በየራሳቸው አመራር በሚሰጡባቸው ክልሎች ለውጡን ሲመሩ ቆይተዋል። ድርጅቶቹ ጉባዔ አካሂደው ተቋማዊ እንዲሆንም አድርገዋል። የፖለቲካ ማስተካከያም እየተደረገ ነው። የኢኮኖሚ ማስተካከያውም እየቀጠለ ነው። አስተዳደራዊና ህጋዊ ማሻሻያዎችም እየተሰሩ ናቸው። እነዚህም በጉባዔው የተቀመጠውን አቅጣጫ ተከትለው እየተሰሩ፤ በተቀመጠላቸው ጊዜ መሰረት እየተካሄዱ ናቸው። በምክር ቤት ደረጃ በየስድስት ወራት፤ በአስፈፃሚ ደረጃ በየሦስት ወራት በህገ ደንባቸው መሰረት ጉባኤ እየተካሄደ ነው። አራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች በተቀመጠው አቅጣጫና አሰራር መሰረት ለውጡን እየመሩት ነው። ግንኙነታቸውን በሚመለከትም በዚህ መንገድ የሚገለጽ ነው።

አዲስ ዘመን፡- በህዝብ ዘንድ ኦዴፓና አዴፓ የለውጥ ኃይሎች፤ ደኢህዴን የዳር ተመልካች፤ እንዲሁም ህወሓት ፀረ ለውጥ ሲባል ይሰማል። ለዚህ መልስዎ ምንድን ነው?

አቶ መለሰ፡- በህብረተሰቡና በማህበራዊ ሚዲያ ይህ ጉዳይ ይነሳል። ይህ በሃሳብ ደረጃ ሊነሳ ይችላል። በግንባሮቹ መካከል በተደረገው ግምገማ እንዲህ ዓይነት ነገር አለ ተብሎ አልተወሰደም። በኢህአዴግ ውስጥ በርካታ ለውጦች ተደርገዋል።

ከዛሬ 16 ዓመት በፊት ለውጥ ተደርጓል። ያኔም በለውጡ ወቅት የተለያዩ ሃሳቦች ተራምደዋል። በሂደት ግን ሃሳቦቹ እየጠሩ ሄደዋል። ለውጥ በሚካሄድበት ጊዜ እንዲህ ዓይነት እሳቤ የሚጠበቅ ነው። በድርጅቶቹ ውስጥ ግን አንዱ የለውጥ ኃይል ሌላው አደናቃፊ ተብሎ በጥቅል ሊቀመጥ አይገባም። በግለሰብ ደረጃ ግን በለውጡ ላይ ሁሉም ሰው እኩል አቋም አለው ተብሎ ሊወሰድ አይችልም።

ግለሰቦች በውስጠ ዴሞክራሲ ነፃ ሆነው ሃሳባቸውን አቅርበው ይከራከራሉ። አብዛኛው ለወሰነው ተገዥ በመሆንም የተወሰነውን ተቀብለው ይተገብራሉ። በሂደት ልዩነት ካላቸው ልዩነታቸውን እያቀረቡ በጉዳዮቹ ላይ ፍጭት እያደረጉ ጠንካራው እየቀጠለ ደከም የሚለው እየታረመ ይቀጥላል።

ፓርቲዎቹ የየራሳቸው ህልውና አላቸው። የራሳቸው ምክር ቤት፤ ጉባዔ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ፤ ሥራ አስፈፃሚ እና ጽሕፈት ቤት አላቸው። ስለዚህ በሁሉም ደረጃ ባላቸው መዋቅር ያሉት አባሎቻቸው በአንድ ጉዳይ ላይ በአንድ ጊዜ አኩል እምነትና አስተሳሰብ ሊኖራቸው አይችልም። ይህ የተለመደና ወደፊትም የሚቀጥል ነው። ይህ ማለት ግን አንድ ፓርቲ እንደፓርቲ ልዩነት አለው ማለት አይደለም።

ደኢህዴንን ብንወስድ «ለለውጡ ሚና የለውም» ይባላል። ግን ይህ ሊሆን አይችልም። ደኢህዴን በለውጡ ሚና የለውም ከተባለ 45 ድምጽ ኢህአዴግ አይኖረውም ማለት ነው። ይህ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ደኢህዴን ሚና የለውም ከተባለ፤ በጥልቅ ተሀድሶው ውስጥ ሚና የለውም ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ የግለሰብ ሳይሆን የፓርቲ ስለሆነ ፓርቲው አይወስንም ማለት ነው። በአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶችም ተመሳሳይ ነው። ሁሉም ለለውጡ አስተዋጽዖ አላቸው። ይህ ማለት እንደድርጅት የራሳቸው ጥንካሬና ጉድለቶች የሏቸውም ማለት አይደለም። ይህ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚለያይ ነው። በአንድ ጊዜ ጠንካራ የሆነው በሌላ ጊዜ ሊደክም ይችላል። ከለውጡ ጋር ተያይዞ ግን ምንም ልዩነት የለም፤ የተፋዘዘ ነው ሊባል ግን አይችልም።

አዲስ ዘመን፡- ታዲያ ይህ አስተሳሰብ እንዴት ሊፈጠር ቻለ?

አቶ መለሰ፡- ለሰዎች አስተሳሰብ ምላሽ መስጠት አልችልም። ምላሽ መስጠት ያለባቸው ይህን ያሰቡ ሰዎች ናቸው። በውስጥም በውጭም ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። በውስጥ ያሉ ሰዎች ይህ አስተሳሰብ ካላቸው ማንጸባረቅ ያለባቸው በፓርቲው ውስጥ ነው። ሃሳብ አንጸባርቀው ሃሳባቸው በብዙሃኑ ከተሸነፈ ለዚያ መገዛት ግድ ነው። ብዙሃኑም የነሱን ሃሳብ ያከብራል። ይህ ማለት ግን፤ በኢህአዴግ ውስጥ ልዩነት አለ ማለት አይደለም። በኢህአዴግ ውስጥ ልዩነት አለ የሚባለው የአቋም ልዩነት ሲኖር ነው። እያንዳንዱ ፓርቲ በሚመራው ክልል ያለው ነባራዊ ሁኔታና የሚሰጠው ምላሽ ህሊናዊ ሁኔታ ልዩነት ሊኖረው ይችላል። በዚህም ሰዎች በለውጡ ልዩነት እንዳለ እንዲገምቱ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህ ግን የፓርቲው ሊሆን አይችልም።

አዲስ ዘመን፡- በሀዋሳው ጉባዔ ኢህአዴግ ተስማምቶ መውጣቱን ገልጿል። ከጉባዔው በኋላ ብሄራዊ ድርጅቶች የሚሰጧቸው መግለጫዎች፤ መሪዎችም የሚያነሷቸው ሃሳቦች መስማማታችሁን አያሳዩም። ተስማምተናል ብላችሁ ህዝቡን ዋሽታችሁታል?

አቶ መለሰ፡- በጉባዔው መገናኛ ብዙሃን፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፤ የሲቪክ ተቋማት ተገኝተዋል። በሂደቱም ኢህአዴግ ግልጽ ውይይት በማካሄድ የውስጥ ዴሞክራሲ አሳይቷል። በርካታ ጉዳዮችም በጉባዔው ተነስተዋል። መሰረታዊ የማስተካከያ ውሳኔ የሚያሳልፈው ይህ ጉባዔ በመሆኑ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተው ክርክር ተደርጓል። በመጨረሻም፤ የጋራ የሚያደርጉን በርካታ ጉዳዮች ስለነበሩ ጉባዔው ለውጡን፣ የለውጡን መርሆዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ መግባባት ላይ ተደርሶ ጉባዔው ውሳኔ አሳልፏል።

በጉባዔው ነፃ ሆነው ሃሳብ በማንሳት የተከራከሩት ፓርቲዎቹ በማመንና በማሳመን የጋራ አድርገው በመወሰን ውሳኔውን እስከቀጣዩ ጉባዔ ድረስ ተግባራዊ ለማድረግ ወስነዋል። ይህን ውሳኔ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ ፓርቲዎቹ ወስደዋል። ይህ ደግሞ በኢህአዴግ የተለመደ ነው። በየትኞቹም ጉባዔዎች የትኛውም ጉዳይ ይነሳል፤ የጋራ መግባባት ተይዞ ይወጣል። በዚህ ጉባዔም የነበረው ይህ ነው። ከዚያ ውጭ አንዱን ለማስደሰት ሌላውን ለማስቀየም ተብሎ ኢህአዴግ ህዝብን አይዋሽም። እንዲህ አይነት ተቋማዊ እምነት የለውም። እንደዚያ ሊያደርግም አይችልም።

አዲስ ዘመን፡- ስምምነት የደረሳችሁባቸው ጉዳዮች በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ እየሆኑ ነው?

አቶ መለሰ፡- በጉባዔ የተቀመጠውን አቅጣጫ ለመፈጸም በመጀመሪያ እቅድ ነው የሚዘጋጀው፤ እቅዱ ከተዘጋጀ በኋላም የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር፤ እቅዱ ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ፤ የስምሪት፤ የዝግጅት፤ የክትትል እና የድጋፍ ሥራዎች ይሰራሉ። ከዚህ አንፃር የጉባዔውን ውሳኔ የሚመጥን እቅድ በኢህአዴግ ጽሕፈት

ቤት ተዘጋጅቶና በሥራ አስፈፃሚ ታይቶ፤ ሁሉም ብሔራዊ ድርጅቶችና የሚመለከታቸው ሁሉ ከተሳተፉበት በኋላ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ስድስት ወራት በመሆኑ ስለውጤታማነቱ ክትትል እየተደረገ ነው።

አዲስ ዘመን፡- ከአጋር ድርጅቶች ጋር ለመዋሀድ ጥናት አጥንታችኋል። ከጥናቱ የተገኘው ፍሬ ነገር ምንድን ነው?

አቶ መለሰ፡- የጥናቱ መነሻ ጥልቅ ተሀድሶውና አጠቃላይ አገራዊ ግምገማው ነው። በግምገማው የተቀመጠው አቅጣጫ አሁን በደረስንበት ነባራዊ ሁኔታ የትግል ስልታችን ከህብረተሰብ የዕድገት ፍላጎት ጋር የሚመጥን መሆን አለበት የሚል ነው። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ፓርቲዎቹ የሚታገሉበት አካሄድ ምን መሆን አለበት? የሚለው ከፓርቲዎቹ ከራሳቸው የመሳተፍ ጥያቄ ተነስቷል። እነዚህ ጉዳዮች በጥናት መመለስ አለባቸው። በአስረኛው የድርጅት ጉባዔ መታየት አለበት ተብሎ አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር። ባለፈው የድርጅት ጉባዔ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል። ይህ ብቻ አይደለም፤ ተጠንቶ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ መሳተፍ አለባቸው የሚል ውሳኔም ተላልፏል። የአጋር ድርጅቶች ሥራ አስፈጻሚዎች በኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ውሳኔዎች ላይ እየተሳተፉ ነው። ጥናቱ የተጀመረው ሂደቱን ወደ ተግባር ለመቀየር ነው።

የጥናቱ ዋና ጉዳይም ፓርቲዎቹ ሲዋሀዱ ከፕሮግራም፤ ከአመራር ስምሪት፤ ከአባላት መብትና ግዴታ፤ ከተልዕኮና ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ያሉ ጥያቄዎች እንዴት ምላሽ ማግኘት አለባቸው የሚሉትን ነው ያጠናው፤ በጥናቱም ፓርቲዎቹ ሲዋሀዱ ኢህአዴግ ምን አይነት ቅርጽ መያዝ አለበት? ከኢህአዴግ ጋር ተዋህደው የሚታገሉ ፓርቲዎች በዓላማና በትግል ስልቱ ላይ ምን ድርሻ እንደሚኖራቸው የሚያይና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች የሚመለሱበት ነው ጥናቱ፤

ጥናቱ ይህን ብቻ ሳይሆን፤ በአገሪቱ ከፖለቲካዊው ለውጥ ጋር ፓርቲውም ራሱን እየለወጠ ለመሄድም ነው። ፓርቲው ከለውጡ ጋር ራሱን እንዴት እያጣጣመ ይሄዳል? የሚለውን ጭምር የሚመልስ ነው። በውህደቱ ሂደት የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለማለፍ፤ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም የሚያስችልም ነው። ጥናቱ የሌሎችን አገራት ተሞክሮዎችና የእኛን አገር ተጨባጭ ሁኔታዎች የዳሰሰ ነው። ጥናቱ የተጠናቀቀ ሲሆን በፓርቲዎቹ ውይይት ተደርጎ የጋራ ስምምነት ሲደረስ ይፋ ይሆናል።

አዲስ ዘመን፡- የኢህአዴግ አራቱ ፓርቲዎች ግንባር ናቸው። አሁን በተደረገው ጥናት ግንባር ወይስ ውህድ ፓርቲ ነው የምትሆኑት?

አቶ መለሰ፡- አሁን ላይ ግንባር ወይም ውህድ ፓርቲ ለማለት አይቻልም። ለፓርቲዎቹ ቀርቦ ውይይት ከተደረገና ውሳኔ ሲያገኝ ነው ይህ የሚታወቀው፤ ጥናቱ እየተጠናቀቀ ነው። ኢህአዴግ የአራት ግንባርና የአጋር ፓርቲዎች ድርጅት ነበር። አሁን ግን ይህ ይቀየራል። በመጀመሪያ የሚፈጸመው የኢህአዴግና የአጋር ድርጅቶች ውህደት ነው። የተቀራረበ ርዕዮተ ዓለም ያላቸው ፓርቲዎች እንደአገር ሰብሰብ ብለን መስራት ስላለብን እየጠበብን በመጣን ቁጥር ለትግል ይመቻል። ይህን ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካ ማሻሻያ አቅጣጫ ነው የምንከተለው።

አዲስ ዘመን፡- ለሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችም እንዲቀላቀሉ ክፍት ታደርጋላችሁ?

አቶ መለሰ፡- ኢህአዴግ የህዝብ ድርጅት ነው። የተወሰኑ ግለሰቦች አይደለም። ተራማጅም ነው። ዓላማው ኋላ ቀርነትን ከማጥፋት እስከዳበረ ዴሞክራሲ አገሪቱን ማድረስ ነው። ከድህነት ወጥታ የበለጸገች አገር መገንባት ነው። ይህ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ነው። ትግሉ በኢህአዴግ ብቻ የሚያልቅ አይደለም። እንደአንድ ፓርቲ ይታገልለታል እንጂ፤ ኢህአዴግ የሚታገልለት ዓላማ የተለያዩ ፓርቲዎችን ትግል የሚጠይቅ ነው። የፓርቲዎችን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ትግል ይጠይቃል። ከዚህ አንፃር ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ካለ ኢህአዴግ የእኔ ብቻ የሚልበት ምንም ምክንያት የለውም።

ተፎካካሪዎችም ቢሆኑ ኢህአዴግ ማሻሻያ ሲያደርግ በሩን ዘግቶ አይደለም። የሚወሰነው ግን በተፎካካሪ ፓርቲዎች ፍላጎት ነው። ኢህአዴግ ከማንም ጋር አልገናኝም ብሎ በሩን የዘጋ አይደለም። ሊዘጋም አይችልም። ግን ደግሞ አብረን እንሁን ብሎ አያስገድድም።

አዲስ ዘመን፡- ከአጋሮች ጋርም ሆነ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ግንባር ብትፈጥሩ ማዋቅሩ ይፈቅድላችኋል። ምክንያቱም በእያንዳንዱ የግንባር ፓርቲ 45 የምክር ቤት አባል፣ 9 ስራ አስፈፃሚ ነው ያላችሁ፤ ይህ በፓርቲዎች ብዛት ልክ የሚጨምር ከሆነ አስቸጋሪ ይሆናል። ስለዚህ ምን ይላሉ? ውህደት ብትፈጽሙ አሁን በአገሪቱ ያለው የብሄር ፖለቲካ ያዋጣችኋል?

አቶ መለሰ፡- ለዚህ ነው ጥናትና ውይይት የሚካሄደው፤ የሚያስቸግሩ ነገሮች እንደሚኖሩ ይጠበቃል። እነዚህን እንዴት እንለፋቸው? ውህደት ሲፈጠር ምን ስጋቶችና ዕድሎች ይመጣሉ? ብሎ በመለየት፤ ዕድሎቹን እንዴት እንጠቀማለን? ስጋቶችን እንዴት እንገራቸዋለን? የሚለውን ለማስቀመጥ ነው። እንደአገር ያለንን ዓላማ ማሳካት በጥናቱ የሚመለሱ ናቸው። በመሆኑም ግንባር ወይም ውህደት የሚፈጸመው ጥናቱን መሰረት በማድረግ ነው። ዋናው ዓላማ አንድ ጠንካራ፤ ተፎካካሪና አገሪቱ አሁን በደረሰችበት ደረጃ ሊያታግል የሚችል ፓርቲ መፍጠር ነው።

አዲስ ዘመን፡- ኢህአዴግ የጽሕፈት ቤቱን መዋቅርም እያሰራ ነው። የዚህ ፋይዳው ምንድነው?

አቶ መለሰ፡- ከአገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ ማስተካከያ የሚደረግባቸው አቅጣጫዎች ተለይተዋል። አንዱ አገራዊ የፖለቲካ ሪፎርም ማድረግ ነው። የዚህ ማስተካከያ ባለፉት ወራት በተወሰዱት እርምጃዎች ይገለፃል። በሰብዓዊ መብት፤ በፓርቲዎች አያያዝ፤ በዳያስፖራ ዲፕሎማሲና በሌሎች ሁኔታዎችም ይገለፃል።

ከዚህ በመነሳትም ኢህአዴግ በህዝብ ውስጥ ያለውን የለውጥ ሚና መወጣት አለበት። የፓርቲ የውስጥም ይሁን የውጭ ዴሞክራሲ ትግሉ በደረሰበት ደረጃ መሆን አለበት። በጽሕፈት ቤት ደረጃ የሚደረገው ማሻሻያም የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማሻሻያ ለማሳለጥ እንዲረዳ ለማድረግ ነው። ይህን የሚመራበት ቁመና መያዝ አለበት። የተጀመረው ለውጥ ህጋዊና አስተዳደራዊ አመራር ያስፈልገዋል። ይህን የሚመራ ኃይል መፍጠር አለበት። በጽሕፈት ቤት ደረጃ የሚደረገው ማሻሻያና ለውጥ ውጤታማ የሚያደርግ የማዕከል ግንባታ ነው። የአደረጃጀት፤ የአሰራር፤ የሰው ኃይል አደረጃጀት ለውጡ ይህን የሚሸከም ማዕከል ለመገንባት ነው።

አዲስ ዘመን፡- መዋቅሩ ግለሰቦችን ማዕከል ያደረገ ነው የሚሉ አሉ። ስለዚህ ምን ይላሉ?

አቶ መለሰ፡- ማሻሻያ ግለሰቦችን ማዕከል ሊያደርግ አይችልም። ግለሰቦችን ማዕከል ካደረገ ሪፎርም ሊሆን አይችልም። የማሻሻያው ዓላማ ለውጡ ውጤት እንዲያመጣ ማድረግ ነው። ይህን ያሳካል አያሳካም የሚለው በሂደት የሚታይ ነው።

አዲስ ዘመን፡- ኢህአዴግ ማህበራዊ መሰረቱን እየረሳ ነው የሚሉ አሉ። መልስዎ ምንድን ነው?

አቶ መለሰ፡- የድርጅቱ ማህበራዊ መሰረቱ ከለውጡ ጋር ተያይዞ አርሶ አደሩ፤ የከተማው ነዋሪ፤ ወጣቱ፤ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው። የለውጡ መነሻም የተለያዩ የህብረተሰብ ቅሬታዎች ናቸው።

ወጣቱን ለማስተማር ከፍተኛ ወጪ ወጥቷል። አሁን ላለው ለውጥ የምትጠቀምበት ነው። ይህን ያለመጠቀም ችግር እንደነበርና አኩራፊ መሆኑ ተገምግሟል። የለውጡም አካል ነው። ወጣቱን አንዱ መሰረት አለማድረግ ወላጆችን የሚያስከፋ ነው። በዚህም የተነሳ ማህበራዊ መሰረታችን ሰፍቷል። ወጣቱ፣ ሴቶች፣ አርሶና አርብቶ አደሩ፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ ባለሃብቶችና ምሁራን የኢህአዴግ መሰረት ናቸው። ሲደመር ልማት ሁሉንም በተመጣጠነና በአቅም ልክ ማልማት ነው።

ወደዚህ ለመግባት ግን የመጀመሪያው ሥራ ሰላምን ማረጋገጥ ነው። የሰላም እጦት እየቀነሰ ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች አሉ። ይህን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያስፈልጋል። ባለፉት ወራት በስፋት የተሰራው እዚህ ላይ ነው። ሰላምን ማረጋገጥ ለሁሉም መሰረት ነው።

አዲስ ዘመን፡- አብዮታዊ ዴሞክራሲን መስመራችሁን ትታችኋል በሚል ትታማላችሁ። ለዚህ ምንድን ነው የሚሉት?

አቶ መለሰ፡- አብዮታዊ ዴሞክራሲ ማለት ልማትና ዴሞክራሲ ማለት ነው። ይህን መስመር አልለቀቅንም። በዚህ አገር መሰረታዊ ችግር የሚባለው የድህነትና የዴሞክራሲ ችግር ነው።

ድርጅታችን በነዚህ ላይ አትኩሮ የሚሰራ ነው። ከዚህ በፊትም እንደተገለጸው ልማታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራሙ መሆኑ ግልጽ ነው። ተራማጅ ከመሆኑ አንፃር በቀጣይ ማስተካከል ሲኖርበት የሚስተካከል ይሆናል። ከለውጡ ጋር ተያይዞ መደናገር እንዳለ እናውቃለን። እስካሁን የቀየርነው ፕሮግራም የለም። ለውጥን የሚመሩ፣ የሚከተሉና የሚያደናቅፉ ሁሌም በለውጥ ውስጥ አሉ። በለውጡ ወቅትም የሚደናገሩ ይኖራሉ እንጂ እኛ እስካሁን የቀየርነው የለም።

አዲስ ዘመን፡- የኢህአዴግ ባህል እየተሸረሸረ እንደሆነ የሚያነሱ አሉ። በተለይም ከአመራሮች መግነንና ክህዝባዊነት ይልቅ መሬት የመቀራመት አባዜ ተጠናውቷቸዋል ይባላል። ስለዚህስ ምን ይላሉ?

አቶ መለሰ፡- የመሬትን ሌብነት በሚመለከት ድርጅቱ ግልጽ አቋም አለው። ወሰንን በሚመለከት ከሆነም በመርህና በተቋማዊ አሰራር ይመለሳል የሚል አቋም ነው ያለን፤ ከዚያ ውጭ ፍላጎት አለ የለም የሚለው በተለያየ መልኩ ይነሳል። የወሰን ጥያቄ የህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ስለሆነ ህዝቦችን በማቀራረብ ይፈታል ብሎ ኢህአዴግ ያምናል። ከጉባዔው ውሳኔ በመነሳትም የእርቅና የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው። በግለሰብ ደረጃ የተለያየ ፍላጎት ቢንፀባረቅም የፓርቲ ሊሆን ግን አይችልም። ክልሎች ካላቸው ነባራዊ ሁኔታ ተነስተው የተለያየ ሃሳብ ሊያንጸባርቁ ይችላሉ። በኢህአዴግ ደረጃ ውይይት ሲደረግ እየተፈታ የሚሄድ ነው። ኢትዮጵያ ሁሉም ህዝቦች የሚወዷት አገር ትሆናለች። ስርዓት ባለው መንገድ ችግሮች ይፈታሉ። የተቀመጠው አቅጣጫ ችግሮቹን የሚፈታ ነው። በለውጥ ወቅት የተለያየ እሳቤ ስለሚኖርና ይህንንም የተለያዩ አካላት ለተለያየ ዓላማ ለመጠቀም ስለሚጎትቱት መደናገር ቢኖርም በይዘቱ ግን ችግር የለም፤ በተቀመጠው አቅጣጫም ይፈታል።

በህብረተሰቡ መለወጥና በነባራዊ ሁኔታዎች መቀየር የኢህአዴግ ባህልም ይለወጣል። ከአመራሩ ጎልቶ መውጣት ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ያልተማረ ሰው ይበዛ ነበር። አሁን የተማረ ሰው ቁጥሩ ጨምሯል። የነበረው አስተሳሰብ ተለውጧል። ይህ ብቻ አይደለም፤ አሁን የመረጃ ዘመን ነው። የሰው የንቃት ደረጃም ጨምሯል። ቀደም ሲል የነበረውን የኢህአዴግ የግንኙነት ስልት ዛሬ ሊጠቀምበት አይችልም። የዛሬውንም በቀጣይ ሊቀጠምበት አይችልም። ከጊዜውና ከሁኔታዎች ጋር አብሮ ይቀያየራል።

አዲስ ዘመን፡- በሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ አገርን ሊበትን የሚችል አደጋ መኖሩን፣ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ እንዳለ፤ እንዲሁም እርስ በርስ መጠራጠር እንዳለ ተማምናችኋል። ለዚህ ማንን ተጠያቂ አደረጋችሁ?

አቶ መለሰ፡- የአገሪቱን ሁኔታ በሚመለከት በለውጥ ውስጥ ናት። በዚህ ምክንያት ለውጡን የሚመራና ለውጡን ለመቀልብስ የሚፈልግ፤ እንዲሁም በነበረው ፍላጎትና አስተሳሰብ ለመቀጠል የሚፈልግ አለ። እነዚህ በማንኛውም ለውጥ ውስጥ የማይቀሩ ናቸው። ይህ የሚለየው በአቅጣጫዎችና በውሳኔዎች ላይ ተመስርቶ ነው። ለውጡ በራሱ ጥርጣሬ የሚፈጥር ነው። አንዳንድ ጊዜ የለውጡ ኃይል እንዲበዛ ማቀዝቀዝም ያስፈልግ ነበር። በሂደቱ የተለያዩ ግለሰቦች የተለያየ አቋም ይይዛሉ። እንደኢህአዴግ ለውጡን የሚመራው ባላደራ ነው። ከዚህ የተነሳ ሁልጊዜም ትግል ይፈልጋል። በለውጥ ሂደት ውስጥ ያለ ነው።

እርምጃ በመውሰድም ሂደት ፊትና ኋላ የመሆን ሁኔታ አለ። ይህ እየተገመገመ እየተስተካከለ የመጣና ወደፊት የሚሄድ ነው። በሂደቱ ግን በአመራሩ፤ በድርጅቱ ውስጥና በህብረተሰቡም ጭምር መጠራጠር ይኖራል። ይህ ግን በኢህአዴግና በውጭ የተለያየ እሳቤ ነው። ኢህአዴግ በለውጥ ሂደት ችግሮች እንደሚፈጠሩና እየተገማገሙ፤ እየተስተካከሉ እንደሚሄዱ ያውቃል። እየተስተካከለም መጥቷል። ልዩነቶች ካሉም በቀጣይ ውይይት ይደረጋል። በተግባቦት ይፈጸማል። መጠራጠር ከሌለ ግን አደገኛ ነው። በመሆኑም ችግሩ ለእከሌ ተብሎ የሚሰጥ አይደለም። የሁሉም ነው። እየተተጋገለ ችግሮችን እየፈታ ይመጣል።

አዲስ ዘመን፡- ስለሰጡኝ ማብራሪያ በአንባቢዎች ስም አመሰግናለሁ!

አቶ መለሰ፡- እኔም አመሰግናለሁ!

«ኢህአዴግ አለ!»አቶ መለሰ አለሙ

ፎቶ

:-ገባቦ

ገብ

Page 7: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

ማህበራዊ/ልዩ ልዩየካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 13

አድሀም ዱሪ

ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሕጎች መደንገግ እና የተቋማት መዘርጋት አስፈላጊነት የሚያከራክረን ነጥብ አይደለም፡፡ በእነዚህ መዋቅሮች አማካኝነት ሰብዓዊ መብቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ በመንግሥታት ላይ የተለያዩ ግዴታዎች ይጣላል፡፡ መንግሥታት የሕዝቦቻቸው መብት እንዲከበር ለማስቻል ከተጣሉባቸው ግዴታዎች መካከል፣ የማክበር ግዴታ፣ የመጠበቅ ግዴታ እና የማሟላት ግዴታ ናቸው፡፡ እነዚህን ግዴታዎች የሚመነጩት ከዓለም አቀፍ ሕጎች፣ ውሎችና ስምምነቶች፣ አህጉራዊ ስምምነቶች እና ሀገራት ከሚያወጧቸው ሕግጋት ነው፡፡

ከላይ የተመለከትናቸው ግዴታዎችና ከግዴታዎቹ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ህጎችን ለማስፈፀም የተለያዩ ድርጅቶች ማለትም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ አህጉራዊ ድርጅቶች እና ሌሎች ብሄራዊ ተቋማት ተቋቁመው ይገኛሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰብዓዊ መብቶችን አስመልክቶ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት የተቋቋሙ ልዩ ውክልና የተሰጣቸው አካላት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮን ጨምሮ ሌሎች መዋቅሮች አሉ፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግም እ.ኤ.አ በ1993 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባካሄደው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ላይ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በብሄራዊ ደረጃ እንዲቋቋም ወስኗል፡፡

ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ሀገራት ተቋሞችን በኮሚሽንና በተለያዩ ደረጃዎች አቋቁመዋል፡፡ ምክንያቱም ሰብዓዊ መብቶች፣ የህግና የፍትህ ተቋማት ከሚሰጡዋቸው ሽፋን ያለፈ ጥበቃ ስለሚያሻቸው፡፡ ሀገራችንም

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ረቡዕ የሚቀርብ

በምርመራ ወቅት የሚፈፀም ማሰቃየት

አካትቶን ውጤታማ ለማድረግ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በመባል የሚታወቀውን በዋናነት ለሰብዓዊ መብት እንዲቆም የተዋቀረ ተቋም አቋቁማለች፡፡ ተቋሙ ረብ ያለው ተግባር ያከናውን ዘንድም ተግባርና ኃላፊነቶቹ በአዋጅ ተጠቅሰው በአንቀፆች ተቀንብበው ተሰጥተውታል፡፡ ከነዚህ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዲመረምር የተሰጠው ስልጣን አንዱ ነው፡፡

ኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር ስልጣን ሲሰጠው በዚህ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ዝርዝር ነጥቦች ሊኖሩ ግድ ይሆናል፡፡ ዝርዝር ነጥቦቹም ተቋሙን በቂ የመመርመር ስልጣንን የሚያጎናፅፉ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡ በቂ የምርመራ ስልጣን መኖር መሰረታዊ ተደርጎ የሚወሰድበት ዋነኛ ምክንያት ሰብዓዊ መብቶችን የሚያስጠበቅ ዋነኛው ክንፍ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ምርመራ በተገቢው መንገድ ሊካሄድ የሚገባውና ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው፡፡ አንዳንዴ ከህጎች ባሻገር በመሄድ በተለያዩ ምክንያቶች የምርመራ ሂደቱ ውስጥ ተመርማሪ በስቃይ እንዲገደድ ይደረጋል፡፡ ለመሆኑ ይህ ማሰቃየት የሚባለው ምንድን ነው? ድርጊቱስ በህግ የተቀመጠ ትርጓሜ አለው? የሚሉትንና እና የማሰቃየት ትርጓሜ፣ ህጋዊ አተያይና ከመንግሥት አንፃር በምርመራ ጊዜ ማሰቃየት ተከስቷል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰብዓዊ መብት ጥበቃና ክትትል በአቶ አድሀም ዱሪ እንደሚከተለው ተዳሷል፡፡

በሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብት መግለጫ (UDHR) እና በዓለም አቀፉ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት (ICCPR) ላይ ማንም ሰው ስቃይ እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት እንዳለው ተደንግጓል፡፡ ኢትዮጵያ ሁለቱንም ሰነዶች እንደተቀበለችና ድንጋጌዎቹም የአስገዳጅነት ኃይል እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ፣ እነዚህ ሁለት ሰነዶች ሰዎች ከእንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች

የመጠበቅ መብት እንዳላቸው ከመግለጽ ያለፈ ስለ ማሰቃየት ተግባር ዘርዘር ያለ ጉዳይ አልያዙም፡፡

ማሰቃየትን በተመለከተ ሰፊ ተቀባይነት ያለው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ እ.ኤ.አ ታኅሳስ 10 ቀን 1984 ዓ.ም ‘ከስቃይና ከሌሎች ጭካኔ ከተሞላባቸው፣ ኢሰብዓዊ ወይም አዋራጅ አያያዝና ቅጣት ለመጠበቅ የወጣው ስምምነት’ ላይ የሰፈረው ትርጉም ነው፡፡ ኢትዮጵያም በመጋቢት 1984 ዓ.ም ላይ ይህንኑ ስምምነት ተቀብላ ያፀደቀችው ስለሆነ በዚሁ ስምምነት ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች እንጠቀማለን፡፡

በእዚህ ስምምነት ላይ በተሰጠው ትርጓሜ መሠረት አንድን ድርጊት ማሰቃየት ነው ለማለት ቢያንስ የሚከተሉትን አምስት መመዘኛዎችን ማሟላት አለባቸው፡፡ የማሰቃየት ድርጊት መኖር ድርጊቱ ለከፍተኛ ሕመምና ሰቆቃ የሚዳርግ መሆኑ፣ የስቃዩ ዓይነት ደግሞ አካላዊም አዕምሯዊም ሊሆን መቻሉ፣ ሆን ተብሎ መፈጸሙ፣ ማሰቃየቱ ዓላማ ያለው መሆኑ፣ እንዲሁም የመንግሥት ሰዎች ወይም ባለሥልጣናት ተሳትፎ ማድረጋቸው ናቸው፡፡

"ስቃይ" የሚለው ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ አሰቃዮቹ የሚያደርሱት የስቃይ ድርጊት መኖር አለበት፡፡ “ድርጊት” የሚያመለክተው አንዱ ሰው ሌላው ላይ የሚፈጽመውን ቢሆንም፣ በተለይ በወንጀል ሕግ ከመታቀብ ወይም ከመተው የሚከሰተውንም ያካትታል። ስለሆነም፣ ማሰቃየት በሚባልበት ጊዜ አሰቃዮቹ በራሳቸው የሚያደርጓቸውንም ሆነ በመተው የሚመጡትንም ያካትታል። ጥፍር መንቀል፣ የወንድ ብልት ላይ ዕቃ ማንጠልጠል፣ በኤሌክትሪክ መግረፍ ወዘተ በማድረግ ውጤት እንደሆኑት ሁሉ ምግብና መጠጥ አለመስጠት፣ ሲታመሙ ሕክምና ወደሚገኝበት ቦታ አለመውሰድ ደግሞ በመተው የሚመጡ ናቸው፡፡ በስቃይ ድርጊት መሞትም ሊኖርም ላይኖርም ይችላል፡፡

አንድ ድርጊት ማሰቃየት ለማለት መጨረሻው መለያ ደግሞ የመንግሥት ሰዎች

ወይም ባለሥልጣናት በተግባርም ይሁን

በዝምታ ተስማምተው የሚፈጽሙት፤

አለበለዚያም የማሰቃየት ድርጊቱን መንግሥት

ሳያስቆም ሲቀር፤ ማሰቃየት ተፈጽሟል

ይባላል፡፡ አሰቃዩ በመንግሥት የተቀጠረ፤

የስቃይ ድርጊቱም የሚፈጸምበት ቦታ

በመንግሥት እጅ ሥር ያለ ከሆነ የሚፈጸምበት ተቋም ኃላፊ የስቃይ ድርጊቶችን ባለማስቆሙ በማሰቃየት ወንጀል ያስጠይቃል፡፡

ማሰቃየት ከሌሎች ተቀራራቢ ድርጊቶች የሚለይባቸው መገለጫዎች አሉት፡፡ ማንኛውም ኢሰብዓዊና አዋራጅ አያያዝና ቅጣት ሁሉ ማሰቃየት አይሆንም፡፡ በእርግጥ ማሰቃየት ኢሰብዓዊም፣ ክብርን የሚነካና የሚያዋርድ ነው፡፡ ነገር ግን ማሰቃየት ከእነዚህ የከፋና የሚያሳቅቅ ድርጊት መሆኑን ከላይ የጠቀስነው ዓለም አቀፍ ስምምነት ያመለክታል፡፡

በእስረኞች ላይ የሚፈጸም የማሰቃየት ተግባር ምንጊዜም ቢሆን ሆን ተብሎ እንጂ በቸልተኝነት አይደረግም፡፡ ከአያያዝ ጉድለት፣ ጥንቃቄ ማድረግ ሲገባ ባለማድረግ ወዘተ የሚከሰቱ የስቃይ ድርጊቶች ሊኖሩ ቢችሉም እንዲህ ዓይነቶቹ በዚህ ሥር አይወድቁም፡፡ አሰቃዩ አካል የሚፈጽመውን ድርጊት አስቦበት፣ በማሰቃየቱ የሚመጣውንም ውጤት ተቀብሎት መሆን አለበት፡፡

ማሰቃየት የሚፈጸመው የሆነ ዓላማን ወይም ግብን ለማሳካት ነው፡፡ በማሰቃየት መረጃ ማግኘት፣ ስለሌሎችም ሆነ ስለራስ ለማናዘዝ ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ አገላለጽ ለማሰቃየት ምክንያቶቹ በርካታም የተለያዩም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ቅጣት፣ ብቀላ፣ ማስተማር፣ መቀጣጫ ማድረግ፣ መረጃ ለማግኘት፣ እንዲናዘዝ ለማድረግ ወይም በስቃዩም ለመደሰት ሊሆን ይችላል፡፡

አንድ ድርጊት ማሰቃየት ለማለት መጨረሻው መለያ ደግሞ የመንግሥት ሰዎች ወይም ባለሥልጣናት በተግባርም ይሁን በዝምታ ተስማምተው የሚፈጽሙት፤ አለበለዚያም የማሰቃየት ድርጊቱን መንግሥት ሳያስቆም ሲቀር፤ ማሰቃየት ተፈጽሟል ይባላል፡፡ አሰቃዩ በመንግሥት የተቀጠረ፤ የስቃይ ድርጊቱም የሚፈጸምበት ቦታ በመንግሥት እጅ ሥር ያለ ከሆነ የሚፈጸምበት ተቋም ኃላፊ የስቃይ ድርጊቶችን ባለማስቆሙ በማሰቃየት ወንጀል ያስጠይቃል፡፡

ዘላለም ግዛው

እግር ኳስ ይወዳል፡፡ ከአገር ውስጥ ይልቅ የውጭ አገር ጨዋታዎች ቢያስደስቱትም፤ የአገር ውስጡንም ችላ አይለውም፡፡ ከአገር ውስጥ የቡና እግር ኳስ ቡድንን ይደግፋል። ያደንቃልም፤ ከውጭ አገር ደግሞ የአርሴናል ቡድን ደጋፊ ነው፡፡ የስድስተኛ ክፍል ተማሪው አብነት አለነ መስማት የተሳነው ነው፡፡ እኔ እና እርሱ እንደልብ ለመግባባት አልቻልንም፡፡ በመሆኑም አብራው የምትማረው የክፍል ጓደኛው ተማሪ ጽዮን አንዱዓለም በምልክት ቋንቋ እያግባባችን መነጋገራችንን ቀጥለናል፡፡

አብነት የሞባይል ጥገና ባለሙያ ለመሆን ይፈልጋል፡፡ ገንዘብ የሚገኝበት መሆኑን ከመገንዘቡም ባሻገር፤ ለሙያው ከፍተኛ ፍቅር እንዳለው ነግሮኛል፡፡ እቤት ውስጥ የተጣሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መፈታታት እንደሚያስደስተውም ነው የገለጸለኝ፤ አንድ ወንድም ያለው ሲሆን፤ ‹‹ሲያድግ የምልክት ቋንቋ አስለምደዋለሁ›› ብሎኛል፡፡

የአካትቶ ትምህርት ዓላማው ልዩ ፍላጎትን ለይቶ ማብቃትን መሰረት ያደርጋል፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎችም በዚሁ ይስማማሉ፡፡ ልዩ ፍላጎትን በሁለት ከፍሎ መግለጽ የሚቻል ሲሆን፤ ተሰጥኦን ወይንም ልዩ ችሎታን የሚያማክለው በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች የሚረዱበት ደግሞ ሁለተኛው መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ አካሄድ አሁን ካለበት የበለጠ ተጠናክሮ ውጤት ተኮር እንዲሆን መስራት አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ እንዳለ ማየት ቢቻልም በቂ ነው ብሎ ለመደምደም ግን አዳጋች ይሆናል፡፡

በዳግማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዋ ጽዮን የ13 ዓመት ዕድሜ ያላት የ6ኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ በአካትቶ ትምህርት በመማሯ የምልክት ቋንቋ ችላለች፡፡ የምልክት ቋንቋ መልመዷ መስማት ከማይችሉት የክፍል ጓደኞቿ ጋር

ለመግባባት አስችሏታል፡፡ ከነርሱ ጋር በእረፍት ሰዓት በሚኖራት ቆይታ ተግባብታ በመነጋገሯ በጣም ደስ እንደሚላት እና መስማት ከማይችሉት ጓደኞቿ ጋርም ጥሩ ፍቅር እንዳላቸው ነው ያጫወተችኝ፤ የእረፍት ጊዜ ከሴት ጓደኞቿ ጋር የተለያዩ ጨዋታዎች በመጫወትም እንደምታሳልፍ ነግራኛለች፡፡ ከጓደኞቿ ጋር የምታሳልፈው ጊዜ ደስ እንደሚላት ፈገግታ በሞላ ፊቷ ደስታ ባዘሉ ቃላቶች ነው ያጫወተችኝ፡፡

መስማት ከተሳናቸው ጓደኞቿ ጋር በምልክት ቋንቋ እንደሚግባቡ የምትናገረው ተማሪ ጺዮን፤ ትምህርት እንደጀመረች ለመግባባት ትቸገር እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ ሁለተኛ ክፍል ከገባች በኋላ ግን በደንብ መግባባት መቻሏን ነው የነገረችኝ፤ ወደፊት የህክምና ዶክተር ለመሆን እንደምትፈልግ እና በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት አንደኛ ደረጃ እንደያዘች፣እንዲሁም ይህንን ውጤት አስጠብቃ ለመቀጠል ተግታ እያጠናች መሆኑን ትናገራለች፡፡ ሌሎች ጓደኞቿንም ታግዛቸዋለች። ስዕል እንደምትወድ፣ በትርፍ ሰዓቷም የመኖሪያ አካባቢዋን የሚያሳይ እና የተለያዩ ስዕሎችን እንደምትስልም ገልጻልኛለች፡፡

ተማሪ አብነት ዕድሜው 12 ሲሆን፤ በአካትቶ ትምህርት ከተማሪ ጺዮን ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ይማራሉ፡፡ በመጀመሪያው ሴሚስተር አምስተኛ ደረጃ ይዟል፡፡ በቀጣይ ግን ደረጃውን ማሻሻል እንደሚፈልግ ገልጾልኛል፡፡ የሞባይል ጥገና ባለሙያ መሆን እንደሚፈልግ፤ ከዚህ ባሻገርም ነጋዴ የመሆን ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ጠቁሞኛል፡፡ የሞባይል ጥገና ባለሙያ ለመሆን የፈለገው ገንዘብ ለማግኘት በማሰብ መሆኑንም ነው የነገረኝ፤

ከጓደኞቹ ጋር በክፍል ውስጥም ሆነ በጨዋታ ቦታ ለመግባባት እንደማይቸገር የሚናገረው ተማሪ አብነት፤ ከዕድሜ እኩዮቹ ጋር ተግባብቶ ይማራል፤ ይጫወታል።

ሆኖም፤ አንዳንዴ አንብቦ ለመረዳት እንደሚቸገር እና ማንበብ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ገልጾልኛል፡፡ ቤተሰቦቹ በቤት ውስጥ በማስጠናት ቢረዱት የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ

እንደሚችልም ያምናል፡፡ ቀደም ሲል አባቱ በማስጠናት ይረዳው እንደነበር በመጠቆምም፤ አባቱ ከቤት በመውጣቱ የሚረዳው ሰው ማጣቱን ነግሮኛል፡፡

በዳግማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የልዩ ፍላጎት መምህርት ሳራ መብራቱ፤ ሁሉም ሰው ልዩ ፍላጎት እንዳለው ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ፤ በትኩረት የሚታይ አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡ አንዳንድ ሰው የመናገር ብቃት ማነስ፤ ሌላው ደግሞ ሌላ አይነት ክፍተት ሊኖርበት ይችላል በማለት ይጠቁሙና፤ ተከታትሎ የመናገር ችሎታው ወይም ክፍተቱ እንዲዳብር ቢደረግ ክፍተቱ ሊሞላለት ይችላል ባይ ናቸው፡፡

እንደ መምህርት ሳራ ማብራሪያ፤ መስማት የተሳናቸው መስማት ከሚችሉ ሰዎች የሚለያቸው ነገር ቢኖር የምልክት ቋንቋ ተጠቃሚ መሆናቸው ነው፡፡ ማየት የተሳናቸውም ልዩ ፍላጎት አላቸው ስንል ብሬል ተጠቃሚ መሆናቸው ነው፡፡ የመማር ችግር አለባቸው ብለን በልዩ ፍላጎት የምንይዛቸው በሆነ ቦታ ላይ ተክተን የምንደግፍ ሲሆን ነው ይላሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት የልዩ ፍላጎት እንደሌለው ማህበረሰብ እኩል ተደራሽ ይደረጋል የሚሉት መምህርቷ፤ እነርሱም ለአገር እኩል ድጋፍ የሚያደርጉ፣ የሚንቀሳቀሱ እና የሥራ ዕድልም የሚያገኙ መሆናቸውን በበጎነት ያነሳሉ፡፡ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ማብቃት ከተፈለገ መስማት ለተሳናቸው ትክክለኛውን የምልክት ቋንቋ የሚችል፣ በምልክት ቋንቋ የተመረቀ መምህር በሁሉም ዘርፍ እንዲኖር ማድረግ ይገባል፤ ይላሉ፡፡ ባብዛኛው በልዩ ፍላጎት የተመረቁ መምህራን ሁሉንም የትምህርት ዓይነት እንዲያስተምሩ ሲደረግ፤ በመማር ማስተማሩ ሥራም ክፍተት ሊፈጥር እንደሚችል ይገልጻሉ። መስማት ለተሳናቸው ብቻ ሳይሆን በሌላውም ዘርፍ እንደየአስፈላጊነቱ ብቁ መምህራን እንዲኖሩ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት መቶ በመቶ ጥሩ ነው ባይባልም መልካም ነገር አለው የሚሉት መምህርት ሳራ፤ ልጆቹ ትምህርት ቤት መጥተው መማራቸው፣

በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት መቻላቸው፤ እንዲሁም በሥራ መሰማራታቸውን በስኬት ያነሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ፣ አሁንም መምህራን በበቂ ሁኔታ ሰልጥነው መቀላቀል ይገባቸዋል። ትክክለኛ ድጋፍ መሰጠትም አለበት ሲሉ ነው የሚገልጹት፤ አካትቶ የትምህርት አሰጣጡ አካታች ማህበረሰብ

ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ እንዲሁም ትምህርት መስማት የማይችሉት ከእኩዮቻቸው ጋር ጥሩ ተግባቦት እንዲፈጥሩም ይረዳቸዋል፡፡

የልዩ ፍላጎት መምህርቷ ራሄል ወልደ ስላሴም ሁሉም ተማሪ ልዩ ፍላጎት እንዳለው በመጠቆም፤ ተማሪዎች ያላቸውን ዕምቅ ችሎታ እንዲያወጡ መደረግ አለበት ባይ ናቸው፡፡ ውጤታማ ተማሪዎችን ማፍራት ካስፈለገ የተለየ ትምህርት አሰጣጥ አስፈላጊ መሆኑን ይስማሙበታል፡፡ መምህራን የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት ለይተው መከታተልም አለባቸው ይላሉ፡፡ በልዩ ፍላጎት ትምህርት ስር የሚጠቃለሉት አካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው፣ ማየት የተሳናቸው፣ የእጅ ወይም የእግር ጉዳት ያለባቸው፣ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት፣ የሚጥል በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ የልብ ህመም፣ ኤች አይ ቪ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ልዩ ፍላጎት የተለየ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች መደበኛ ከሆነው የተለየ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ የሚሰለጥኑበት መንገድ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ በምሳሌነት ሲያነሱም፣ መስማት የተሳናቸውን ከመደበኛው በልሳን ከሚማሩት በተለየ መስማት ከሚችሉት ጋር በኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ እንደሚሰጥ ነው የሚናገሩት፡፡

ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ለማብቃት መጀመሪያ መምህሩ መብቃት አለበት የሚሉት መምህርት ራሄል፣ መምህራንን የማብቃት ተግባር ቀዳሚ ሊሆን ይገባዋል የሚል አቋምም አላቸው፡፡ እንዴት አድርጎ ተማሪዎችን እንደሚያግዝ የተገነዘበ መምህር ተማሪዎቹን ማብቃት ይቻለዋል ይላሉ፡፡

የሰለጠነ በቂ የሰው ኃይል አለመኖር ዘርፉን እየፈተነው መሆኑን የሚናገሩት መምህርቷ፤ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በትምህርታቸው ብቁ ሊያደርጋቸው እና ሊያግዛቸው የሚያስችል የመርጃ መሳሪያ የማሟላቱ ሥራ ትኩረት የሚገባው ነው ይላሉ መምህርት ራሄል፡፡

የአካትቶ ትምህርት ዓላማው ልዩ ፍላጎትን

ለይቶ ማብቃትን መሰረት ያደርጋል።

የዘርፉ ባለሙያዎችም በዚሁ ይስማማሉ፡፡ ልዩ ፍላጎትን በሁለት ከፍሎ መግለጽ የሚቻል ሲሆን፤ ተሰጥኦን ወይንም ልዩ ችሎታን የሚያማክለው በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ያጋጠማቸው

ተማሪዎች የሚረዱበት ደግሞ ሁለተኛው መሆኑን

ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

ውጤታማ ተማሪዎችን ማፍራት ካስፈለገ የተለየ ትምህርት አሰጣጥ እንደሚያስፈልግ አያጠያይቅም፡፡ በተለይም የተለየ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች መደበኛ ከሆነው የተለየ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ በማሰልጠን ማብቃት አስፈላጊ ነው፡፡ በአካትቶ ትምህርት የሰለጠነ በቂ የሰው ኃይል አለመኖር፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በትምህርታቸው ብቁ ሊያደርጋቸው እና ሊያግዛቸው የሚያስችል የመርጃ መሳሪያ የማሟላቱ ችግሮች እንዲሁም የቤተሰብ ድጋፍ ማነስ ዘርፉን እየፈተነው መሆኑን የታዘበው የአዲስ ዘመኑ ዘላለም ግዛው በዳግማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የቃኘውን እንደሚከተለው ያጋራናል።

Page 8: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

መዝናኛየካቲት 27 ቀን 2011 ዓም አዲስ ዘመን

በቅኝ ከተገዙት በምን ተሻልን?

15

አንተነህ ቸሬ

ጋዜጠኛ፡- ‹‹የዓድዋ ጦርነት በማንና በማን መካከል የተካሄደ ጦርነት ነው?››

መላሽ፡- ‹‹በግብፅና በሐረር መካከል››…ጋዜጠኛ፡- ‹‹የውጫሌን ውል ከኢጣሊያ በኩል

ሆኖ ሲያስፈፅም የነበረው ማን ነው?››መላሽ፡- ‹‹ጋዳፊ›› …ጋዜጠኛ፡- ‹‹ስለ ዓድዋ ጦርነት ድል

የምታውቀውን ንገረኝ እስኪ?››መላሽ፡- ‹‹ ስለዓድዋ ጦርነት ምንም አላውቅም››… ጋዜጠኛ፡- ‹‹የዓድዋ ድል የሚከበረው መቼ

ነው?›› መላሽ፡- ‹‹ግንቦት 20››…ጋዜጠኛ፡- ‹‹ሚያዝያ 27 ቀን ተከብሮ የሚውለው

ብሔራዊ በዓል ምን ይባላል?››መላሽ፡- ‹‹መድኃኔዓለም››…ከላይ የተጠቀሱት ምልልሶች የተለያዩ መገናኛ

ብዙኃን ጋዜጠኞች በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ተዘዋውረው ለሕዝቡ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችና ለጥያቄዎቹ የተሰጡ ምላሾች ናቸው፡፡ መቼም ለጥያቄዎቹ የተሰጡት ምላሾች ‹‹የመድኃኔዓለም ያለህ!›› የሚያስብሉ ናቸው፡፡

እንግዲህ እኛ እንዲህ ሆነናል … ስለ የካቲት 23 ስንጠየቅ ስለ ግንቦት 20 የምናወራ፣ ስለኮንት ፒየትሮ አንቶኒሊ ስንጠየቅ ስለ ጋዳፊ የምንመልስ … ብቻ እንዲህ ያለን ሆነናል!

ምላሾቹን ከሰጡት መካከል አብዛኛዎቹ ሰዎች ወጣቶች መሆናቸው ከግምት ውስጥ ሲገባ ነገሩ በዝምታ መታለፍ የሚገባው እንዳልሆነና የሚያስጨንቅም፤ የሚያስፈራም እንደሆነ አመላካች ነው፡፡ ጥያቄው ‹‹ይህ ዓይነቱ ነገር ምን ያሳየናል? ምንስ ያስተምረናል?›› ነው፡፡ ለዚህ ‹‹ውርደት›› ብዙ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ቢችሉም ዋናው ግን ትውልዱ በቤተሰብ ክትትል ማጣትም ይሁን ተቋማዊ በሆነ ሴራና ጫና ታሪኩን እንዳያውቅ መደረጉ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ቀደምት ኢትዮጵያውያን ዓለም ያደነቀውንና ‹‹ልዩ/ብቸኛ›› ያስባለንን ዓድዋን ድል በደማቅ ቀለም ፃፉት፤ እኛ ግን ታሪኩን በጥቂቱ እንኳን ማወቅ ከበደን፡፡ ‹‹… ስለዓድዋ ጦርነት ምንም አላውቅም›› ብሎ በኩራት መናገር ምንጩ ምን ይሆን?! በሰው ልጅ ታሪክ ከተፈፀሙት አሰቃቂ ቅጣቶች መካከል ስለሚመደበው፣ ከ82 ዓመታት በፊት አዲስ አበባ ላይ ስለተፈጸመውና ስለእናት አገር ሉዓላዊነት ሲባል ኢትዮጵያውያን ስለተቀበሉት የየካቲት 12 ጭፍጨፋ አምስት ገፅ ታሪክ እንኳን ለማገላበጥና ሰው ለመጠየቅ ለምን ሰነፍን?!

ልጅ እንዲህ እስከሚሆን ድረስ ወላጅስ ምን ሥራ ይዞ ነበር?! መንግሥትስ ቢሆን ልማትና ዴሞክራሲ የሚባሉት ነገሮች ታሪኩንና ማንነቱን በማያውቅ ኅብረተሰብ ውስጥ ተንሰራፍተው ቢቀመጡ እንኳን ዘላቂነታቸው አስተማማኝ እንደማይሆን ጠፍቶት ነው?

ታሪካቸውንና ማንነታቸውን ረስተው፤ ልማትና ብልፅግና ላይ ብቻ አተኩረው ሀብታም የሆኑ አገራት ዛሬ ‹‹ከሕዝብ ታሪክና መገለጫ (ባህል) ጋር ያልተጣጣመ ልማት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል›› ብለው ጉዟቸውን እየፈተሹ እንደሆነስ አልሰማንም?

ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ፤ ጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙኃን ላይ ፕሮግራም

የሚያቀርቡ ግለሰቦች በእነዚህ በዓላት ላይ የሚያቀርቧቸው መሰናዶዎች ከላይ ከተጠቀሱት ምላሾች ብዙም ያልራቁና ያልተሻሉ መሆናቸው ነው፡፡

እስኪ ጉዳዩን በምሳሌ እንመልከተው፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በየዓመቱ የካቲት 23 ቀን ሲከበር በዕለቱና በዚያው ሰሞን ተደጋገመው ከሚደመጡ አገላለጾች መካከል ‹‹በዓድዋ ጦርነት ወቅት ሁሉም የኢጣሊያ የጦር መሪዎች በኢትዮጵያውያን ተገድለዋል … ጦርነቱ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ተጠናቅቋል … ›› የሚሉት ሃሳቦች ይገኙበታል፡፡

እግረ መንገዴን ስህተታቸውን ጠቁሜ ልለፍ፤ ለግንዛቤ ማስጨበጫም ይሆናል ብዬ እገምታለሁ።

1ኛ. ከዋናዎቹ የኢጣሊያ ጦር አዛዦች መካከል ጀኔራል ጁሴፔ አሪሞንዲ እና ጀኔራል ቪቶሪዮ ዳቦርሚዳ በጦርነቱ ላይ የሞቱ ሲሆን፤ ጠቅላይ አዛዡ ጀኔራል ኦረስቴ ባራቲዬሪ ሸሽቶ አምልጧል፡፡ የመሐል ጦር አዛዡ ጀኔራል ማቴዮ አልቤርቶኒ ደግሞ በኢትዮጵያ ጦር ተማርኳል፡፡

2ኛ. ጦርነቱ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ያለቀ ውጊያ አልነበረም፡፡ እንዲያውም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የተካሄደው የዓድዋ ጦርነት ሙሉ ቀን ሲካሄድ የዋለ የተጋጋለ ፍልሚያ እንደነበር የታሪክ ጸሐፍት መዝግበውታል፡፡

እንዲያው እኔ ለማሳያ ያህል እነዚህን ብቻ ጠቀስኩ እንጂ፤ ወጣቶቹ የሰጧቸው አስገራሚ/አስደንጋጭ ምላሾች፤ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ‹‹ባለሙያዎች›› የሚፈፅሟቸው ስህተቶች እነዚህ ብቻ አይደሉም፤ ብዙ ናቸው፡፡ የሕዝቡን (በተለይ የወጣቱን) ነገር እያየነው ነው፤ ጋዜጠኞቹ ከሕዝቡ የተሻሉ ሆነው ሕዝቡን ካላስተማሩና ስህተቱን ካላረሙ ጉዞው ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል፡፡

ሰሞኑን 73ኛ የልደት ቀናቸውን ያከበሩት ዝነኛውና አንጋፋው የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በአንድ ወቅት ‹‹… ትውልዱ ታሪኩን ቢያውቅ ኖሮ ይህን ሁሉ ስህተት አይሠራም ነበር …›› ብለው ነበር፡፡ ከዚህ ንግግር መገንዘብ የሚቻለው ታሪክ ማወቅ ‹‹ይህን ሠርቻለሁ›› እያሉ ለመኩራትና የበለጠ ስኬት ለማስመዝገብ፤ ለመነሳሳት ብቻ ሳይሆን ትናንት የተፈጸሙ ስህተቶችን ባለመድገምና ከስህተቶቹ በመማር ነገን የተሻለ ለማድረግ ዋስትና መሆኑን ነው።

እውቁ የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ማርክስ ጋርቬይም ‹‹ታሪኩን የማያውቅ ሕዝብና ስር የሌለው ዛፍ አንድ ናቸው›› በማለት ታሪክን አለማወቅ ምን ያህል ከሰውነት ተራ ዝቅ እንደሚያደርግ አስገንዝቧል፡፡

በእርግጥ ከዓመታት በፊት ጀምሮ ትውልዱ በታሪክ ላይ ያለው ግንዛቤ ሲተችና ሲነቀፍ በተደጋጋሚ እንሰማለን፡፡ ትችቱና ነቀፋው ግን የሚፈለገውን ውጤት አምጥቷል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እንዲያውም ፌስቡክ (Facebook) በስፋት መጠቀም ከተጀመረ ወዲህ የታሪክ ጉዳዮች ጥሩ የሚባል ሽፋን እያገኙ መምጣታቸውን መካድ አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ፤ ታሪክ እጅግ ተለዋዋጭና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ በሆነው የፌስቡክ መድረክ ቀርቦ የትውልዱን ግንዛቤ ችግር ለመፍታት አስተማማኝ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ማሰብ ታሪክ እንዳይታወቅና በሚገባ እንዳይመረመር ለማድረግ ሌላ ተጨማሪ አደጋ መጋበዝ ይሆናል።

ዛሬ የትናንት፤ ነገ ደግሞ የዛሬ ውጤቶች ናቸው። ታሪክ ማወቅ የሚያስፈልገው መልካም በሆነው የታሪክ ክስተት በመኩራት ለተሻለ ስኬት ለመነሳሳት ብቻ ሳይሆን፤ ከመጥፎው አጋጣሚ ትምህርት ለመውሰድና ያን መጥፎ አጋጣሚ ላለመድገምም ጭምር ነው፡፡ ትናንት በኢትዮጵያ ታሪክ የተፈፀሙትን

ክስተቶች ብንወዳቸውም ብንጠላቸውም ከታሪክ አጋጣሚነታቸው/ክስተትነታቸው ልንፍቃቸው አንችልም። በተለያዩ ጊዜያት ለገባንባቸው ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች አንዱ ምክንያት ይኸው በታሪክ ላይ ያለን ደካማ ግንዛቤ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በጎውን አጠንክሮ ማስቀጠሉ ይቅርና የትናንትናውን ስህተት ዛሬ እየደገምነው ከችግር አዙሪት መውጣት አቅቶናል፡፡ ‹‹ትናንት ይህ ስህተት እንደነበር አይተናል፤ ዛሬ መደገም የለበትም›› ያሉት ግን የትናንት ስህተታቸውን ባለመድገማቸው አቅጣጫቸው ወደፊት፤ ጉዟቸውም ወደተሻለ ደረጃ ሆኗል፡፡

ቀደምት ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያን ድንበር ለመድፈር ከሞከሩ ኃይሎች ጋር ተፋልመው፣ ዓድዋ ላይ ያን የመሰለ ትልቅና አኩሪ ድል አስመዝግበው፤ እንዲሁም ለአምስት ዓመታት ያህል በዱርና በበረሃ ታግለው ሉዓላዊነቷን ያስጠበቀች ነፃ አገር ያስረከቡን ለአገራቸውና ለክብራቸው ካላቸው የማይበገር ቀናኢነት በተጨማሪ፤ በወራሪ ኃይሎች በቅኝ ግዛት የተገዙ አገራት ሕዝቦች የተቀበሉት መከራ እንዳይገጥመንና እኛ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ እንድንቆም ነበር፡፡ ዠግን ስለ ዓድዋ ጦርነትና ድል ስንጠየቅ/ሲጠይቁን ‹‹ስለ ዓድዋ ጦርነትና ድል ምንም አላውቅም›› ብለን ምላሽ ከሰጠን በቅኝ ግዛት ከተገዙትና ታሪካቸውንና ማንነታቸውን ከተነጠቁት አገራት ህዝቦች በምን ተሻልን?!

(ማሳሰቢያ፡- በዚህ ጽሑፍ ‹‹ወጣቱ›› እያልኩ የወቀስኩበት ገለፃ በአገራቸው ታሪክ ላይ አሳሳቢ የሆነ የግንዛቤ ክፍተት ያለባቸውን በርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን የመጠቆም ሙከራ እንጂ ሁሉንም ወጣት በአንድ ቅርጫት ውስጥ የማስቀመጥ ፍረጃ እንዳልሆነ ሊታወቅልኝ ይገባል!)

የየሳ

ምንቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ፕሬዚዳንት ሳልቫር

ማርዴት በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ተገናኝተው በቀጠናው ኢኮኖሚ

ልማት፣ ሰላምና ደህንነት ዙሪያ መክረዋል።

Page 9: 78 ኢህአዴግ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርቲዎች · ማስረጃዎችን የማደራጀት፣ የጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን

26 የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም

• ለኤችአይቪይበልጥተጋላጭነን!

እንመርመርራሳችንንእንወቅ።

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

በኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን በባለቤትነት የሚመራው ስፖርታዊ ክንውን ባህላዊ ስፖርቶችን ከማጉላት በተጓዳኝ፣ በሀገር አንድነትና ሰላም ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በርካቶች ሲናገሩ ይደመጣሉ።የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የማንነታቸው መገለጫ የሆነውን ባህላዊ ስፖርት አንዱ ክልል ከሌላኛው ክልል፣ አንዱ ከተማ አስተዳደር ከሌላው ክልል እና ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት አውድ መሆኑን ይገልጻሉ። በአምቦ ከተማ ለአንድ ሳምንት የተካሄደው 16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 12 ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ይሄንኑ ያሳየ መድረክ እንደነበር ለመታዘብ ተችሏል። በመድረክ ተሳታፊ የነበሩና ከተለያዩ ክልሎች የመጡትን ተወዳዳሪዎች የባህል ስፖርት ውድድሩ ለሀገር አንድነትና ሰላም ያለው ሚና ጉልህ መሆኑን ለአዲስ ዘመን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክሎ በኩርቦ የባህል ስፖርት የተወዳደረው አብተው ይርጋ ፤የባህል ስፖርት ውድድሩና ፌስቲቫሉ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና አለው ይላል።በተለይ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን በማጠናከር የእርስ በርስ ቅርርብን ይፈጥራል። በአምቦ ከተማ በነበረው መድረክም ይሄንኑ በሚገባ መመልከቱን ምስክርነት ሰጥቷል።

በውድድሩ ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት መታየቱን የምትገልጸው ደቡብ ክልልን በመወከል

ኩርቦ የባህል ስፖርት ተወዳዳሪ የነበረችው ብርሀኔ ብሬ በበኩሏ፣በስፖርታዊ ውድድሩም ሆነ በባህል ፌስቲቫሉ ላይ አንዱ ክልል የሌላውን ባህል በሚገባ እንዲያውቅና ልምድን እንዲቀስም የማድረግ አጋጣሚን ሲፈጥር ለመመልከት መቻሏን ትናገራለች። እርሷ የመጣችበት ክልል በሌላ አካባቢ ያለውን የባህልና ሌሎች ልምዶችን በአንድነት መንፈስ እንዲለዋወጡ ያደረገ መልካም አጋጣሚ ሆኖ እንደተሰማት ገልጻለች። የባህል ስፖርት ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ተጀምሮ መጠናቀቁ ደግሞ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ከምንም ጊዜው በላይ ጥሩ ነበር ብላለች።

የአማራ ክልልን በባህል ስፖርት ወክሎ የመጣው ወርቅነህ አገኘሁ በተመሳሳይ በአምቦ ከተማ ለአንድ ሳምንት የነበረው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር መድረክ ኢትዮጵያዊነት ስሜትን በመቀስቀስ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ያስፈነጠዘ እንደነበር ይገልጻል። በደጋፊዎች በኩል ይሰሙ የነበሩ ዜማዎችም የልዩነት ነጋሪት ጉሰማውን ድምጽ የዋጠና፣ የአንድነቱን ድምጸት ያጎላም ጭምር መሆኑን ይገልጻል። በሀገራችን ያለውን የእርስ በርስ መቀራረብ ስሜት በአምቦ ከተማ በነበረው የውድድር መድረክ ላይ በሚገባ እንደተንጸባረቀ ይናገራል። ከስፖርታዊ ፉክክሩ በተለየ መልኩ ሰላምና አንድነት መንጸባረቁ ደግሞ ከውድድሩ አላማ ጋር የተጣጣመ ክንውን እንደሆነ በሙሉ ልብ መናገር ያስችላል ይላል ። ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር አልነበረም።ለዚህ ደግሞ የአምቦ ከተማ ህዝብና አስተዳደር ከፍተኛ የሆነ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን በመግለጽ ንግግሩን

ይቋጫል።የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን

ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ሰለሞን አስፋው በበኩላቸው፣ የስፖርት ውድድሩ ዓላማ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቱባ ባህሎቻቸውን ለማስተዋወቅና ልምድ ለመለዋወጥ መሆኑን ይናገራሉ።በመድረኩም ላይ ፍጹም የሆነ ስፖርታዊ ጨዋነትና የእርስ በርስ ግንኙነት የተጠናከረበት መድረክ እንደነበረም ተናግረዋል።የባህል ስፖርት ውድድሩና ፌስቲቫሉ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር አስችሏል:: በቀጣይም የውድድር አውዶች ይኸው መልካም

የአምቦ ስታዲየም ግንባታ፤ የከተማዋ የልማት ረሀብ ማስታገሻዳንኤል ዘነበ

ዳንኤል ዘነበ

የውድድር መንፈስ ይበልጥ ይንጸባረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

«የባህል ስፖርት ተሳትፏችን ለሰላምና ለአንድነታችን» በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ ከየካቲት 16 እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው 16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 12 ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ሰላምና አንድነት በጋራ ተጣመረው የታዩበት መድረክ ሆኖ ተጠናቋል። በመድረኩ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ተሳታፊ

ያደረገ ነበር። በ13 የስፖርት ዓይነቶች ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ሁኔታ ተጀምሮ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በባህል ስፖርቶች ውድድር አማራ ክልል አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ሲያጠናቅቅ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ከ2 እስከ 3 ያለውን ደረጃ ይዘው ነበር ያጠናቀቁት:: የብዙዎችን ትኩረት የሳበው 12 ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ደቡብ ክልል አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከ2 እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። አዲስ አበባ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

አምቦ ከተማ ዓለም አቀፍ ደረጃን የተላበሰና ዘመናዊ ስታዲየም ባለቤት የምትሆነው መቼ ነው? የሚል ጥያቄ እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል። በ1888 ዓ.ም መመስረቷ በታሪክ የተጻፈላት ቢሆንም ከልማት ርቃና ተገላ እንደኖረች ተደጋግሞ ይገለጻል። የአምቦ ህዝብ ከትናንት እስከ ዛሬ የኢትዮጵያ አንድነት፣ ልማትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የተሟገተ ህዝብ ባለቤት ናት።የህዝቧ ለውጥን መሻት፣ ልዩነትን መርሳት ደግሞ በሦስት መንግሥታት ከልማት እንድትርቅ መደረጓን የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። የአምቦ ከልማት ውጪ የመሆኑን እውነታ ምስክርነት «በከተማዋ ይሄነው የሚባል ዓለም አቀፍ ስታዲየም ራሱ የለም » ሲሉ ያነሳሉ።

የአምቦ ከተማ ከልማት የመገፋትን ሀቅ ከየካቲት 16 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም 16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 12ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ለመዘገብ ከሥፍራው በተገኘንበት ወቅት ይሄንኑ እውነታ ለመታዘብ ችለናል። ሀገራዊ ስፖርታዊ ክንውኑ መክፈቻው ሆነ መዝጊያውን ያስተናገደው የአምቦ ስታዲየም ለዚሁ ቋሙ ምስክር የሆነ ተናጋሪ ቅርስ ነበር። የእግር ኳስ ሜዳው ሳሩ እምጥ ይግባ ስምጥ ባይታወቅም ሙሉ ለሙሉ በአፈር ተሸፍኖ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴውን በአቧራ የታጀበ እንዲሆን አስገድዶታል። የአምቦ ስታዲየምን የሜዳላይ እንቅስቃሴውን በበጋ ወቅት አዋራ በክረምት ደግሞ የቦካ ጭቃው የሜዳላይ ቆይታን ከአዝናኝነት ወደ ዘግናኝነት እንደሚያሸጋግረው አይን አይቶ ይፈርዳል። የመሮጫው ትራክም ቢሆን አይደለም ለመሮጥ ለመራመድ ራሱ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ነው። በስሙ ብቻ የመሮጫ ትራክ ለመባል ያህል ቀይ አሸዋ የለበሰ ነው። ይህ የመሮጫ ሜዳው «ፀረ ሩጫ እንጂ የመሮጫ ሜዳ ነው» ብሎ መናገር እጅጉን አሳፋሪ ይሆናል።ይሄን የተመለከተው ዓይኔ በእርግጥም ከአምቦ አብራክ የወጡ እነ ፊጣ ባይሳ፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ ………. ሌሎች የአገር ኩራት የሆኑ አትሌቶች የፈሩባት ሆና ስለምን በስታዲየሟ አትሌቶችን የሚያፈራ የማዘውተሪያ ስፍራ እንድታጣ ተፈረደባት ? ሲል ጥያቄውን ለሚመለከተው አሻግሬ ከስታዲየሙ ገጽታ ውጣሁ።

አምቦ ከተማ ከሰው ቀድማ ነቅታ ከሰው በታች ሆና ለምትታወቅ ለከተማዋ አንድ ለእናቱ በመሆን ለዘመናት ሲያገለግል እንደኖረ የከተማዋ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተውኛል። ስታዲ የሙ በጊዜው ጥሩ የሚባልና ከጊዜው ጋር አብሮ ይራመዳል። የስፖርቱ እንቅስቃሴም ቢሆን ተመሳሳይ መልክ የተላበሰ ነበር። በከተማዋ መሰረቱን ያደረገው የሙገር ሲሚንቶ ክለብ በሀገር

አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ያሳረፈም ጭምር ነው። የክለቡ መኖር ደግሞ በከተማዋን ስፖርት ላይ የራሱ የሆነ ጉልህ ድርሻን ሲጫወት ቆይቷል። የእግር ኳሱ ቁመና ይህን መስሎ ጉዞውን ሲያደርግ ቆይቶ ሆን ተብሎ ሙገር ሲሚንቶ መቀመጫውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያሸጋገር መደረጉን ያስታውሳሉ። በዚህ ምክንያት በአምቦ የነበረው የስፖርት እንቅስቃሴ ሆነ የአምቦ ስታዲየም በነበረበት ቆሞ መቅረቱን ይናገራሉ። ስታዲየሙ ምንም አይነት እድሳት ሳይደረግለት የድሮ መልኩን በመያዝ ዛሬ ላይ መድረሱን በቁጭት የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። ከዚህ ቁጭት ጀርባ ከአብዛኛው የከተማዋ ነዋሪ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው አምቦ ዩኒቨርሲቲ ይሄንኑ ቁጭት ያበረደ ተግባር መፈጸሙን ከመናገር አያመነቱም።

የአምቦን የልማት ረሀብ የተመለከተው አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከተማዋን ወደኋላ ከቀረችበትን ልማት ፎቀቅ እንድትል ጥረቱን ማድረጉም አልቀረም። ዩኒቨርሲቲው ከያዘው የመማር ማስተማር ራዕይው እኩል ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ከዚሁ ትይዩ አስፍሮታል። በዚህ መሰረትም ዩኒቨርሲቲው

የተለያዩ የልማት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። ተግባሩን ያልዘነጋው ተቋሙ ከዓመት በፊት ያስቀመጠላቸው የመሰረት ድንጋይ ደግሞ ለዓመታት አንድ ለናቱ የነበረውን የአምቦ ስታዲየም የሚያስረሳ ስታዲየም ለመገንባት ውጥን መያዙን ይፋ ማድረጉ ነበር። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ ወጪ በመሸፈን የከተማዋን ህብረተሰብና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ስታዲየም መሆኑ ደግሞ ድርብ ደስታን የፈጠረ እንደነበር ያነጋገርኳቸው ነዋሪዎች ሳይደብቁ ስሜታቸውን አጋርተውኛል። የአምቦን የልማት ረሀብ የተመለከተው አምቦ ዩኒቨርሲቲ በአዋሮ ካምፓስ እያስገነባ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ግንባታ ሂደትን ለመመልከት ሞክረናል።

የአምቦ ከተማ የዓመታትን ቁጭት ታሪክ ያደርጋል የሚል ተስፋ የተጣለበትን የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ግንባታ በቦታ በመገኘት ጉብኝት ባደረግንበት ወቅት ያነጋገርናቸው በቲኤንቲ ኮንስትራክሽንና ንግድ ድርጅት የአምቦ ስታዲየም ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጂነር አብነት

ፊጣ፤ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የግንባታ ሂደት በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ መሆኑን በመግለጽ ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት።እንደ ኢንጂነር አብነት ገለጻ፤ የግንባታው ኮንትራት ውሉ ስምምነት በ2009 ዓ.ም ግንቦት ወር የተፈረመ ሲሆን፤ በተለያዩ ምክንያቶች ከተባለበት ጊዜ በጥ ቂት ወራት በመዘግየትም ህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም ሊጀመር መቻሉን ያስታወሳል። በዚህ መልኩ የተጀመረው የግንባታው ሂደት በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ይገኛል ያለው ኢንጂነሩ፤ በአሁኑ ወቅት የግንባታው ዋናው ተግባር የሚባለው የኮንክሪት ሥራው መጠናቀቁንና ቀሪው ሥራ የፊኒሺንግ ሥራና የኤሌክትሮ መካኒክ ሥራው እንደሚቀር ይገልጻሉ።

በግንባታ ሂደቱ ውስጥ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የተከናወነው ሥራ ከ50 በመቶ በላይ ሥራ ማከናወን መቻሉን ይገልጻሉ ።በዚህም መሰረት ቀሪውን የግንባታ 50 ከመቶ የሚይዙትን የፊኒሽንግና የኤሌክትሮ መካኒክ መሆኑን ገልጿል። ኢንጂነር አብነት የኤሌክትሮ መካኒክ ሥራ ማለትም እንደ ጄኔሬተር፣ በስታዲየሙ ውጭም ውስጥም

ክፍል የሚተከሉት ስትሬት ላይት ሥራዎች በቀጣይ የሚሰሩ መሆናቸውን ነበር ያብራሩት።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አልሰም ፊሮምሳ በተመሳሳይ፤ በ3 መቶ 19 ሚሊዮን ብር አምቦ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በጥሩ ፍጥነት እየሄደ መሆኑን በማረጋገጥ ሃሳባቸውን ይጀምራሉ። ስታዲየሙ 30 ሺህ ተመልካች እንደሚያስተናግድ ገልጸው፤ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ከስፖርታዊ ክንውኖች በተጓዳኝ ለሌሎች አገልግሎቶች የሚ ውሉ 252 ክፍሎችን ይዟል። በዚህም ሱቆች፣ ስብሰባ አዳራሽ፣ የተወዳዳሪዎች ማደሪያም ያካተተ ስታዲየም ነው። ለህብረተሰቡ የገቢ ምንጭ መፍጠሪያ የሚያስችል መሆኑን አክለው ይገልጻሉ። « ይህን መልክ የተጎናጸፈው ስታዲየም የግንባታው ሂደት ፍጥነት ደግሞ የጥራቱን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ይታወቃል ። የእኛ ተቋራጭ ይሄንኑ ጥያቄ በመለሰ መልኩ እየተጓዘ እንደሆነ እናምናለን።ለዚህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ያቆመው ኮንሰልታንት ይገኛል። የግንባታው ሂደት በምን ዓይነት ጥራት እየሄደ ይገኛል የሚለውን በሚገባ ማረጋገጫ እየሰጠ መሆኑ ለዚህ ምስክር ይሆናል»ሲሉ ይናገራሉ።

ኢንጂነር አልሰም በስተመጨረሻም፤ ስታዲ የሙ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ለከተማው ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጓዳኝ አገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው። ከዚህ አኳያ የስታዲየሙ የግንባታ ሂደት ከምንም በላይ ህብረተሰቡ በንቃት ሲከታተል ቆይቷል። በዚህ የስሜት እርካብ የተጫነው የስታዲየም ግንባታ በአሁኑ ወቅት ሀምሳ በመቶ መጠናቀቁን ገልጸው፣ ቀሪው ደግሞ በ2012 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ መታቀዱን በመግ ለጽ ሀሳባቸውን ይቋጫሉ።

በሀገሪቱ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ስታዲየሞች እየገነቡ ይገኛሉ ።በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት ሰጥተው እየሰሩበት ይገኛል።በመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ ዓለም አቀፍ ስታዲየሞች መበራከት ያላቸው ፋይዳ ሰፊ እንደሆነ ይናገራል።በከተማ የስፖርት እንቅስቃሴን ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲጓዝ ከማድረግ አኳያ፤ በሀገሪቱ በቀጣይ በዓለም አቀፍም ሆነ አህጉር አቀፍ የውድድር መድረኮችን ለማዘጋጀት ዕድሉን እንድታገኝ ያስችላል። በመሆኑም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መገንባቱ የሚሰጠው ጠቀሜታ ዘርፈ ብዙ እንደሚሆን እሙን ነው። ከዚህ ሀቅ በመነሳት የአምቦ ስታዲየም ግንባታ የአምቦ ከተማ ሀዝብ የልማት ረሀብ የሚያስታግስ ጅምር ተግባር ይሆናል። አምቦ ከተማ ከአዲስ አበባ 114 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ መሆኑ ሀገሪቱ ኢንተርናሽናል ውድድሮች በቅርብ ርቀት ለማከናወን አጋዥ ይሆናል።

ሰላምና አንድነት የተንጸባረቁበት የባህል ስፖርት

የ16ኛ የባህል ስፖርት ውድድርና 12ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በአምቦ ከተማ በድምቀትና በስፖርታዊ ጨዋነት ተካሂዷል

የስታዲየም ግንባታው በ2012 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል

ፎቶ

- ሐዱ

ሽ አብ

ርሃ