የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት...

8
የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት ሐምሌ እና ነሓሴ ፳፻፯ ዓ.ም. በመጀመሪያው እትእ አፈጻጸምና በሁለተኛው የእትእ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ የመጀመሪዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በኢንስቲትዩቱ የዕቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችም በስድስት ቡድኖች ተመድበው በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ ያደረጉ ምክንያቶች የሚሏቸውን በየቡድናቸው ተወያይተው በማቅረብ በጋራ መድረክ ላይ በመወያየት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ውይይቱ በማግስቱም የቀጠለ ሲሆን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአቶ ተስፋዬ ብርሃኑ ቀርቦ በቡድኖች ውይይት ተደርጎበታል፡፡በዚህም መሰረት በቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ አራት ፕሮግራሞች (የኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ማሳደጊያ፣የምርትና ምርታማነት ማሳደጊያና ማስፋፊያ፣የገበያ ማስፋፊያና ማሳደጊያ እና የድጋፍ አቅም ማስፋፊያና ማሳደጊያ ፕሮግራም) እና 17ቱ ፕሮጀክቶች የታቀዱ ሲሆን አተገባበራቸውን በተመለከተም ገለጻ ተደርጓል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ባደረጉት ውይይት አንድ ፕሮገራም እና አንድ ፕሮጀክት በተጨማሪነት እንዲካተት አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ ወንዱ ለገሰ የኢንስቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልእክት ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሳካ ራሳችንን በይቻላል መንፈስ አጠናክረን መነሳት ይገባናል ብለዋል፡፡ ቶ ታደሰ ኃይሌ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ፣ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ማኔጅመንትና የንኡስ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት ተግተው መስራት እንዳለባቸው አስገነዘቡ፡፡ ሚንስትር ዴኤታው ይህን መልእክት ያስተላለፉት ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከኢንስቲትዩቱ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች እንዲሁም ከንዑስ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም እና የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡ በፈጻሚው በኩልም ዕቅዱንና ስትራቴጅዎቹን ያለመገንዘብ፣ባለሀብቱን በማሳመን በኩል በትጋት ያለመስራትና የተጠያቂነት መንፈስ አለማዳበር ጉልህ ችግር መሆኑ በውይይቱ ላይ ተመልክቷል፡፡ ባለሀብቱን በተመለከተም ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት አለመላቀቅ ፣በዘመናዊ አመራር አለመመራት፣ሀገራዊ ራዕይ ሰንቆ አለመንቀሳቀስ እና በቅንጅት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር አለመስራት የሚሉት የተነሱ ችግሮች ናቸው፡፡ በተመሳሳይም ሐምሌ 27 እና 28 የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች በቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ በመጀመሪዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም እና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

Transcript of የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት...

Page 1: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት ሐምሌ እና ነሓሴ ፳፻፯ ዓ.ም.

በመጀመሪያው እትእ አፈጻጸምና በሁለተኛው የእትእ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ

የመጀመሪዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በኢንስቲትዩቱ የዕቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችም በስድስት ቡድኖች ተመድበው በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ ያደረጉ ምክንያቶች የሚሏቸውን በየቡድናቸው ተወያይተው በማቅረብ በጋራ መድረክ ላይ በመወያየት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ውይይቱ በማግስቱም የቀጠለ ሲሆን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአቶ ተስፋዬ ብርሃኑ ቀርቦ በቡድኖች ውይይት ተደርጎበታል፡፡በዚህም መሰረት በቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ አራት ፕሮግራሞች (የኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ማሳደጊያ፣የምርትና ምርታማነት ማሳደጊያና ማስፋፊያ፣የገበያ ማስፋፊያና ማሳደጊያ እና የድጋፍ አቅም ማስፋፊያና ማሳደጊያ ፕሮግራም) እና 17ቱ ፕሮጀክቶች የታቀዱ ሲሆን አተገባበራቸውን በተመለከተም ገለጻ ተደርጓል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ባደረጉት ውይይት አንድ ፕሮገራም እና አንድ ፕሮጀክት በተጨማሪነት እንዲካተት አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ወንዱ ለገሰ የኢንስቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልእክት ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሳካ ራሳችንን በይቻላል መንፈስ አጠናክረን መነሳት ይገባናል ብለዋል፡፡

አቶ ታደሰ ኃይሌ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ፣ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ማኔጅመንትና የንኡስ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት ተግተው መስራት እንዳለባቸው አስገነዘቡ፡፡

ሚንስትር ዴኤታው ይህን መልእክት ያስተላለፉት ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከኢንስቲትዩቱ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች እንዲሁም ከንዑስ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም እና የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

በፈጻሚው በኩልም ዕቅዱንና ስትራቴጅዎቹን ያለመገንዘብ፣ባለሀብቱን በማሳመን በኩል በትጋት ያለመስራትና የተጠያቂነት መንፈስ አለማዳበር ጉልህ ችግር መሆኑ በውይይቱ ላይ ተመልክቷል፡፡

ባለሀብቱን በተመለከተም ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት አለመላቀቅ ፣በዘመናዊ አመራር አለመመራት፣ሀገራዊ ራዕይ ሰንቆ አለመንቀሳቀስ እና በቅንጅት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር አለመስራት የሚሉት የተነሱ ችግሮች ናቸው፡፡

በተመሳሳይም ሐምሌ 27 እና 28 የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች በቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ በመጀመሪዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም እና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

Page 2: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሚዘጋጅ

ወርሃዊ ዜና መጽሔት

ነሐሴ ፳፻፯ ፤ ቅጽ 1 ቁጥር 3

ዋና አዘጋጅብርሃኑ ስርጃቦ

አዘጋጆችዕዝራ ኃይለማርያም

ሰብስቤ ባዩሲሳይ አስታጥቄ

የገጽ ንድፍና ቅንብርሙላቱ ዘነበፎቶ ግራፍ ሙላቱ ዘነበ

አድራሻ

ስልክ ቁጥር 251 – 11- 4391700251 – 11- 4391682

ፋክስ 251 – 11- 4392259ፖ.ሳ.ቁ 24692 Code 1000

ድረ ገጽ www.elidi.org [email protected]

በዚህ እትም የዋና ዳይሬክተሩ መልእክት የዋና አዘጋጁ መልእክት የኤክስፖርት አፈፃፀም በመጀመሪያው እትእ አፈጻጸምና በሁለተኛው

የእትእ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ ዳይሬክቶሬቶች በመጀመሪያው እትእ አፈጻጸምና

በሁለተኛው እትእ ላይ ተወያዩ የሀዘን መግለጫ ለኢንስቲትዩቱ አመራሮች የውጤት ተኮር ምዘና

ስርዓት ( ቢ ኤስ ሲ) ስልጠና ተሰጠ ለአዲስ ሠራተኞች የትውውቅ ፕሮግራም ተካሄደ

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በሐምሌና ነሐሴ ወራት በርካታ ሥራዎች ሰርቷል፡፡ በዐብይነት የሚጠቀሱትም የመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ምን ይመስል እንደ ነበር እንዲሁም የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትኩረቶችን በተመለከተ ከኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ ድክመቶችን ነቅሶ በማውጣት የሚስተካከሉበትን መንገድ በስፋት በመወያየት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ መልካም ተመክሮዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት እያንዳንዱ ሰራተኛ የተመደበበትን ስራ በብቃት በመወጣት ስኬታማ መሆን ይቻል ዘንድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት በተደረጉት ስብሰባዎችና ውይይቶች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተችሏል፡፡

ሥራዎችን በኃላፊነት ስሜት መስራት፣ ምንጊዜም ለስኬትና ለመልካም ለውጥ መትጋት፣ የራስን ጉድለት በየጊዜው በመፈተሸ ድክመትን ማስወገድና ጠንካራ ጎንን አጠናክሮ ማስቀጠል ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ተግባር መሆን አለበት፡፡ እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት ቁም ነገር ስራን ማሸነፍ፣ ለስኬትና ለመልካም ለውጥ መትጋት፣ ጉድለትን ፈትሾ ድክመትን ማስወገድና በጎነትን ማዳበር ከማንም በላይ የሚጠቅመው ራስን ነው፡፡

ይህን መሰረት በማድረግም በአዲሱ 2008 ዓመት በቆዳ ኢንዱስትሪ ስኬታማ የምንሆንበት ዘመን እንደሚሆን እናምናለን፡፡ ስኬት የሚመጣው ከብዙ ትጋትና ጥንካሬ በመሆኑ የምንተጋበት ዘመን እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ስለሆነም በተሰለፍንበት የሥራ መስክ ለኅሊናችን ብለን በመስራት ኃላፊነታችንን በብቃት ለመወጣት ቃል በመግባት ስኬታማ በመሆን ሽልማቱን ከኅሊናችን የምንቀበልበት ዘመን ይሁንልን እላለሁ፡፡

በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የስኬት፣ የጤና፣ የብልጽግናና የበረከት ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡

ብርሃኑ ሰርጃቦ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን

የዋና አዘጋጁ መልእክት

Page 3: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

የዋና ዳይሬክተሩ መልእክት

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ

አስቀድሜ ለቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች እንዲሁም ለቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ለአዲሱ 2008 ዓመት አደረሳችሁ እላለሁ፡፡

2007 ዓ.ም አገራችን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ባስመዘገበቻቸው ስኬቶች ዓለም አቀፍ እውቅናና ሞገስ ያገኘችበት ዘመን ነው፡፡ ይህ ስኬት የተገኘው መንግስት የነደፋቸውን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ለመፈጸም መላው ሕዝብ ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት እንደሆነ ይታመናል፡፡ 2007 በጀት ዓመት በቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ በርካታ ስራዎች የተሰሩበት ዘመን ነው፡፡ ሁለተኛው የቁርኝት ፕሮጀክት መጀመሩ፣ የሀገራቸንን ቆዳ ኢንዱስትሪ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምዳል ተብሎ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ-ቻይና ዶንግ ጓን ኋጂያን ዓለም አቀፍ የጫማ ፋብሪካ የኢንዱስትሪ ፓርክ መቋቋሙ፣ ጆርጅ ሹ ፕሮጄክትን ጨምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ባለ ሀብቶች በርካታ ኢንቨስትመንት እየተስፋፋ መሄዱ ፣ ኢንስቲትዩታችን ሁለት የምርምር ጽሑፎች በአገር አቀፍ ደረጃ በምርምርና ፈጠራ ከቀረቡት ፕሮፖዛሎች ውስጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ምክር ቤት ተመርጠው በአገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ መሆናቸውና የስራ ማስኬጃ ድጋፍ አግኝተው የምርምር ስራዎቹ መጀመራቸው የሚያበረታቱ ስራዎቻችን ናቸው፡፡

በሌላ በኩል፣ በዘመኑ በንኡስ ዘርፉ የታቀደውን የኤክስፖርት ገቢ ሙሉ በሙሉ ማሳካት አለመቻላችን በድክመት ያየነው እና በ2008 ዓ.ምጠንክረን በትጋት ልንሰራው የሚገባን ቁልፍ ተግባራችን ነው፡፡ መጭው አዲስ ዓመት የሁለተኛው እድገትና

ትራንስፎርሜሽን እቅድ (2008- 2012) መጀመሪያ ዓመት በመሆኑ የንኡስ ዘርፉን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ስራ የምንሰራበት ዓመት እንደ ሆነ ይታመናል፡፡

በሀገራችን የቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ መሳተፍ ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች መንግስት የተለመደውን ተገቢ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸኩ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ንኡስ ዘርፉን በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን እገልጻለሁ፡፡

በመጨረሻም አዲሱ ዓመት ድክመታቻችንን በማስወገድ እና መልካም ተመክሮዎቻችንን አጠናክረን በማስቀጠል ስኬታማ የምንሆንበት ዘመን እንደሚሆንልን ያለኝን ተስፋ እየገለጽኩ፣ ለኢንስቲትዩታችን ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች እንዲሁም ለንኡስ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ &08 (2008 ዓ.ም) የደስታ፣ የጤና፣ የበረከትና የስኬት ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡

ወንዱ ለገሰ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

ከእንስሳት አርቢ እስከ ዓለም አቀፍ ገበያ ድረስ የሚገኙ ባለ ድርሻ አካላት የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እጅ ለእጅ ተያይዘን ልንወጣ ይገባል፡፡ ለዚህም የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርና ተነሳሽነት ወሳኝ ሲሆን ከሁሉም በላይ ሁል ጊዜ ለኅሊናችን የምናቀርበው ጥያቄም “ለቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ ዕድገትና ተወዳዳሪነት ምን አበረከትኩ?” የሚል መሆን አለበት፡፡

የዋና አዘጋጁ መልእክት

Page 4: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

ለኢንስቲትዩቱ አመራሮች የውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት ( ቢ ኤስ ሲ) ስልጠና ተሰጠ

ለቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት መካከለኛ እና ዝቅተኛ አመራሮች የሁለት ቀናት የውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት( ቢ ኤስ ሲ) አተገባበር ስልጠና ተሰጠ፡፡

ነሐሴ 21 እና 22 ቀን 2007 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ የተሰጠውን ስልጠና የሰጡት ሱፐር ኮንሰልት ከተባለ ተቋም የመጡ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች ሲሆኑ 61 የኢንስቲትዩቱ መካከለኛ እና ዝቅተኛ አመራሮችም በስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በቁርጠኝነት እና በላቀ ብቃት ለመምራት እና ለመፈፀም እንዲቻል በእቅዱ የዝግጅት ምዕራፍ አመራሩን በተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች የማስፈፀም አቅሙን መገንባት በማስፈለጉ ስልጠናው መዘጋጀቱም ተጠቁሟል፡፡

ስራዎች የሚመሩት በውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት ወይንም ቢ ኤስ ሲ በመሆኑ አመራሩ ስለስርዓቱ ትክክለኛ እና የጠራ ግንዛቤ ኖሮት ወደ ስራ መግባት እንዳለበት በኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት በመታመኑ ስልጠናው መዘጋጀቱንየኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሰ በስልጠናው ወቅት ተናግረዋል፡፡

የውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት ጽንሰ ሀሳብንና ስራ ላይ ማዋልን በተመለከት በተግባር ልምምድ የታገዘ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ አመራሮችም መሰል ስልጠናዎች ስለስርዓቱ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዙ እንደሚያስችላቸው እና ለቀጣይ የሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ለአመራሩ እና ለአጠቃላይ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኛ በእቅድ ትግበራ ላይ የሚያተኩሩ መሰል ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁም ከኢንስቲትዩቱ የሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ በፊት በኢንስቲትዩቱ የውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት ሰነድ ተዘጋጅቶና እቅዶችም በዚሁ አግባብ ታቅደው ሲተገበሩ ቢቆዩም በአተገባበሩ እና በጽንሰ ሀሳቡ ላይ በቂ ሊባል የሚችል ግንዛቤ እና እውቀት ባለመኖሩ ክፍተቶች መፈጠራቸውን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ስልጠና አመራሩ በውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ እንዲይዝ ያስችለዋል ብለዋል፡፡

Page 5: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

ዳይሬክቶሬቶች በመጀመሪያው እትእ አፈጻጸምና በሁለተኛው እትእ ላይ ተወያዩ

በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የዋና ዓላማ አስፈጻሚ (Core Process) ዳይሬክቶሬቶች ባለሙያዎች፣ ነሐሴ አንድ እና ሁለት በመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

ውይይቱን ያካሄዱት የቆዳ አልበሳትና እቃዎች፣ የጫማ ቴክኖሎጂ፣ የቆዳ ቴክኖሎጂ እና የምርምርና ፍተሻ ላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬቶች ባለሙያዎች ናቸው፡፡ ዳይሬክቶሬቶቹ በሚፈጽሟቸው አብይት ፕሮግራሞችና ፕሮጄክቶች ላይ በፓወር ፖይንት የተደገፈ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለአዲስ ሠራተኞች የትውውቅ ፕሮግራም ተካሄደ

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የእንኳን ደህና መጣችሁና የትውውቅ ፕሮግራም አካሔደ፡፡

አቶ ብርሃኑ ንጉስ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እዚህ መስሪያ ቤት የመጣችሁ ባለሙያዎች ክፍት የስራ ቦታ ስላለ ብቻ ሳይሆን ተቋሙ ላቀደው ለሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት ስለምታስፈልጉ ነው ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አዲስ የተቀጠሩ ባለሙያዎች ከተቋሙ ማኔጅመነት አባላት ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን፣ ስለ መንግስት ሰራተኞች መብትና ግዴታ፣ የሥነ-ምግባር መርሆዎች፣የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ፣ የዓመት ዕረፍት ፍቃድ፣ የዲሲፒሊን እርምጃዎችና የቅሬታ አቀራረብ፣ የጡረታ መዋጮና የጡረታ መውጫ ዕድሜ፣ ስትራቴጃዊ የውጤት ተኮር ደረጃዎች ላይ በሚመለከታቸው አካላት ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡

አቶ ወንድሙ ኩመራ፣ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳሉት ሲቪል ሰርቪሱ የሕዝብ አገልጋይ በመሆኑ የተመደባችሁበትን ስራ በብቃት በመወጣት ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በየዳይሬክቶሬቶቻቸው በቡድን ተከፋፍለው በቀረቡት አብይ ፕሮግራሞችና ፕሮጄክቶች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ተወያዮቹም በመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻልና መልካም ተመክሮዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬታማ ለማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ብሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሰ ባደረጉት ንግግር ሁላችንም ታዘን ብቻ ሳይሆን በራሳችን ተነሳሽነት ፈጥረን በሙሉ ኃይላችን በመስራት የተሠጠንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

Page 6: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

በ2007 በጀት ዓመት በቆዳ ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ የተያዘውን የልማት አቅጣጫና ግብ ለማሳካት በርካታ የድጋፍ መርሐ-ግብሮች የተነደፉ ሲሆን የኤክስፖርት ገቢ የተሻለ የእሴት ጭማሪን ካረጋገጡ ምርቶች በማግኘት የንዑስ ዘርፉን የኤክስፖርት ምርት አወቃቃር መሠረታዊ በሆነ መልኩ ለመለወጥ በርካታ ጥረቶችና ተግባራቶች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በዕቅድ የተያዙ ዓመታዊ የወጪ ንግድ ገቢ ግቦችን ለማሳካት የተደረጉ ጥረቶች በአብይነት ይጠቀሳሉ፡፡

ከንዑስ ዘርፉ የተሻለ አፈፃፀምና አጠቃላይ የልማት ዕድገት ጋር በተያያዘ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የማይተካ ድርሻ ያላቸውን የልማት ኃይሎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በሙሉ በየደረጃው በማስተባበርና አጠቃላይ ንቅናቄን የመፍጠር ሥራ ተሰርቷል፡፡ በንዑስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የተሻለ የእሴት ጭማሪ አቅጣጫ አፈፃፀም አጠናክሮ በማስቀጠል በ2007 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 357.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሠረት በ2007 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ ወቅት በኢንቨስትመንት፣ በምርትና በግብይት የትኩረት መስኮች መከናወን ባለባቸው ቁልፍና አበይት ተግባራት ላይ ከንኡስ ዘርፉ ባለሀብቶች ጋር ውይይቶች ተደርገው የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በተደረሰው ስምምነት መሰረትም የኤክስፖርት ገቢ እቅድን ለማሳካት ጥረት ቢደረግም እቅዱ ሙሉ በሙሉ ሊሳካ አልቻለም፡፡

በ2007 በጀት ዓመት የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የኤክስፖርት አፈጻጸም በሚከተለው መልኩ በሠንጠረዥ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ1:- የ2007 በጀት ዓመት ያለፉት አስራ ሁለት ወራት የኤክስፖርት ዕቅድ አፈጻጸም (/በሺህ የአሜሪካን ዶላር)

የምርቱ ዓይነት

የአስራ ሁለት ወራት ዕቅድ

የአስራ ሁለት ወራት አፈጻጸም

አፈጻጸምበመቶኛ

ቆዳና የቆዳ ውጤቶች

357,746.84 132,861.49 37.14

ያለቀለት ቆዳ 231,250.00 92,102.62 39.83

ጫማ 115,476.00 34,577.57 29.94

የቆዳ ጓንት 10,018.99 5,343.33 53.33

የቆዳ አልባሳትና ዕቃዎች

1,001.85 837.97 83.64

የ2007 በጀት ዓመት የኤክስፖርት አፈጻጸም ከ2006 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ያለው ንጽጽር እንደሚከተለው በሠንጠረዥ 2 ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ2:- የ2007 እና የ2006 የአስራ ሁለት ወራት የኤክስፖርት ገቢ አፈጻጸም ንጽጽር፤ በሺህ የአሜሪካን ዶላር/

የኤክስፖርት ክትትልና ድጋፍ ሥራዎች የምርቱ ዓይነት

የ2006 በጀት ዓመት የአስራ ሁለት ወራት አፈጻጸም

የ2007 በጀት ዓመት የአስራ ሁለት ወራት አፈጻጸም

ዕድገት/ቅናሽ በመቶኛ

ቆዳና የቆዳ ውጤቶች

132,947.96 132,861.49 (0.07

ያለቀለት ቆዳ 97,692.3792,102.62

(5.72)

ጫማ 30,543.7334,577.57

13.21

የቆዳ ጓንትየቆዳ

4,315.63 5,343.33 23.81

አልባሳትና ዕቃዎች

396.23837.97

111.49

Page 7: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

ከላይ የቀረበውን መሰረታዊ ጥያቄ በኅሊናችን ፊት በትክክል መልሰን ራሳችንን ለስኬት ካዘጋጀን በ2008 በጀት ዓመት ውጤታማ እንሆናለን፡፡ ለስኬት ቆርጦ የተነሳ ያለመውን ለማሳካት የተጋ ምንጊዜም ስኬታማ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ስኬታማ ሰዎች በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ ናቸው፡፡ መንገዳቸውን ሊዘጋ ያጋጠማቸውን ደንቃራ እንደ ምቹ እድል በመቁጠር እንቅፋቱን ጠርገውና አስተካክለው በግብአትነት ይጠቀሙበታል፡፡

የቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ ለሀገራችን ኢኮኖሚ የሚያበረክተው እድገት የጎላ ነው፡፡ ከዚህም አንጻር የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በ2008 የታቀደውን የኤክስፖርት ገቢ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በይቻላል መንፈስ ቆርጠን በመነሳት ኅሊናዊና ሙያዊ አደራ አለብን፡፡ እንደ ምናሳካውም ሙሉ እምነት አለን፡፡

በበጀት ዓመቱ ከቆዳና ቆዳ ውጤቶች ንዑስ የኢንዱስትሪ ዘርፍ 357.75 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የኤክስፖርት ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 132.86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን አፈፃፀሙ የዕቅዱን 37.14 በመቶ ነው፡፡ ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ተገኝቶ ከነበረው የ132.95 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ0.09 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (0.07%) ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የተገኘው 132.86 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የኤክስፖርት ገቢ በምርት ስብጥር ሲታይ ያለቀለት ቆዳ 69.32 በመቶ፣ ጫማ 26.03 በመቶ፣ የቆዳ ጓንት 4.02 በመቶ፣ የቆዳ አልባሳትና ዕቃዎች 0.63 በመቶ ድርሻ ይዘዋል፡፡ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ከፍተኛ የእሴት ጭማሪ ያላቸው ምርቶችም (የጫማ፣ የቆዳ ጓንትና የቆዳ አልባሳትና ዕቃዎች) ከጠቅላላው ኤክስፖርት 30.68 በመቶ ድርሻን ይዘዋል፡፡

በ2007 በጀት ዓመት እቅድ አለመሳካት በርካታ ምክንያቶችን መደርደር ቢቻልም ዋናው ቁም ነገር ለኅሊናችን የምናቀርበው “ በሙያዬ መስራት የሚገባኝን በብቃት ሰርቼያለሁ ወይ? ሀገራዊና ሙያዊ ኃላፊነቴን በብቃት ተወጥቼያለሁን? ” የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡

7

Page 8: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትlidi.gov.et/images/July.pdfሪፖርት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ

የሕንድ ጫማ ዲዛይን ልማት ኢንስቲትዩት (Footwear De-sign & Development Institute) የኢትዮጵያ ፕሮጄክት አስተባባሪ የነበሩት ሚስተር ቢ ኤስ ካቲያር ነሐሴ 11 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ሚስተር ቢ ኤስ ካቲያር የቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ ቤንች ማርኪንግ ፕሮግራም ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እኤአ ከ2010 ጀምሮ እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስ የሕንድ ጫማ ዲዛይን ልማት ኢንስቲትዩት (Footwear Design & Development Institute) በመወከል የኢትዮጵያ ፕሮጄክት አስተባባሪ በመሆን በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አገልግለዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የቁርኝት ፕሮጄክት ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እኤአ ከ2011 ጀምሮ ፕሮጄክቱ ስኬታማ እንዲሆን በትጋት ሲሰሩ ነበር፡፡

ሁለተኛው ዙር የቁርኝት ፕሮጄክት ስምምነት ተፈርሞ መተግበር ከጀመረበት ከጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ በኢንስቲትዩታችን በመገኘት አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍና እገዛ በማድረግ ላይ እያሉ ነሐሴ 11 ቀን 2007 ዓ.ም በድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም አልፈዋል፡፡

በሚስተር ቢ ኤስ ካቲያር በሀገራችን በቆዩበት ዓመታት ለአገራችን የቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ በተለይም ለጫማ ኢንዱስትሪው እድገት ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የሕንድ ጫማ ዲዛይን ልማት ኢንስቲትዩት ( Footwear Design & Development Institute) ከቆዳ ኢንዱስትሪ

ለሚስተር ቢ ኤስ ካቲያር ሕልፈት የሽኝት ፕሮግራም ተካሔደ

ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተሳሰብና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ዘላቂነት ያለው መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር በማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ለስልጠና ሕንድ የሚሄዱ የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎችን ተቀብሎ በማስተናገድ፣ መረጃ በመስጠት፣ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ በማድረግ እንዲሁም የባይተዋርነት ስሜት እንዳይሰማቸው የማይረሳ አስተዋጽኦ ከማድረጋቸውም በላይ ባለፉት ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ የኅብረተሰቡን ባህልና ልምድ አክብረውና ተላምደው በፍቅር የኖሩ የሀገራችን ወዳጅ ነበሩ፡

ነሐሴ 12 ቀን 2007 ዓ.ም የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ለአስክሬኑ የሽኝት ፕሮግራም ያዘጋጁ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ ሚስተር ቢ ኤስ ካቲያር በአገራችን ቆዳ ኢንዱስትሪ በተለይም በጫማ ቴክኖሎጂ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ተወስቷል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አቶ ወንዱ ለገሰ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት ንግግር የሀገራችን ቆዳ ኢንዱስትሪ በተለይም የጫማ ኢንዱስትሪ እድገት እንዲያሳይ ከኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሙያ አጋራችን ነበሩ ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች በሙያ አጋራችን እልፈት የተሰማንን መሪር ሐዘን የምንገልጸው ለሀገራችን ቆዳ ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ እድገት ያደረጉትን ሕያው አስተዋጽኦ በታላቅ አክብሮት በመዘከር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛሉ በማለት በኢንስቲትዩቱና በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል፡፡

8