ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ...

80
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ …ዕለታዊ የመንፈሳዊ ጥናት መጽሃፍ Chris Oyakhilome

Transcript of ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ - Christ...

  • ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

    …ዕለታዊ የመንፈሳዊ ጥናት መጽሃፍ

    Chris Oyakhilome

  • www.rhapsodyofrealities.orgemail: [email protected]

    All rights reserved under International Copyright Law. Contents and/or cover may not be reproduced in whole or in part in any form without the express written permission of LoveWorld Publishing.

    NIGERIA:Christ Embassy Plot 97, Durumi District, Abuja, Nigeria.

    LoveWorld Conference CenterKudirat Abiola Way, OregunP.O. Box 13563 Ikeja, LagosTel.: +234-812-340-6547 +234-812-340-6791

    UNITED KINGDOM: Believers’ LoveWorldUnit C2, Thames View Business Centre, Barlow Way Rainham-Essex, RM13 8BT. Tel.: +44 (0)1708 556 604Fax.: +44(0)2081 816 290

    CANADA:Christ Embassy Int’l Office, 50 Weybright Court, Unit 43BToronto, ON MIS 5A8Tel.:+1 647-341-9091

    USA:Believers’ LoveWorld4237 Raleigh StreetCharlotte, NC 28213Tel: +1 980-219-5150

    USA:Christ Embassy Houston,8623 Hemlock Hill DriveHouston, Texas. 77083 Tel.: +1-281-759-5111; +1-281-759-6218

    SOUTH AFRICA:303 Pretoria AvenueCnr. Harley and Braam Fischer, Randburg, Gauteng South Africa.Tel.:+27 11 326 0971Fax.:+27 113260972

    KuKÖ S[Í“ }ÚT] KT²´:

    ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...ዕለታዊ የመንፈሳዊ ጥናት መጽሃፍISSN 1596-6984ሚያዝያ 2011 editionCopyright © 2011 by LoveWorld Publishing

    u}K¾ G

  • የ 2011 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ እርምጃና እድገት ለማሳደግ በተለየና ባማረ ሁኔታ ለተሻለ ነገር በሚያነሳሳ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመረጃና በመገለጥ ከተሞሉ ፁሁፎች በተጨማሪ የዚህ ወር ዕትም በየዕለቱ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ መገኘት ለማወቅ በምታደርገው ጉዞ እምነትህን በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንድታሳድግ በተመቻቸ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ቀርቦልኃል፡፡ በየቀኑ ባጠናኽው፣ ባሰላሰልከውና በአፍህ በተናገርከው ወይም ደግሞ ባወጅከው መጠን እየታደስክ ትሄዳለህ፡፡

    የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ በወሰድን ጊዜ የእግዚአብሔርን የክብር መገኘትና ድል ዓመቱን በሙሉ እንዲደሰቱበት ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በጣም እንወዳችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

    - ይህንን መነቃቅያ እንዴት በበለጠ መጠቀም ይቻላል -

    መግቢያ

    -ፓስተር ክሪስና ኦያኪሎሜ

    ይህን ጽሁፍ አንብብና በጥንቃቄ አሰላስል፡፡ ፀሎቶቹንና የአፍ ምስክርነት ቃሉን

    በየቀኑ ለራስህ ድምጽህን ጎላ አድርገህ መናገርህ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወትህ

    እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በአዲሱ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ

    ቅዱስ ጥናት በሚገባ አንብቡ

    የዕለታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን በጠዋትና በማታ ከፍለህ ማንበብ ትችላለህ

    መነቃቅያውን በጸሎት ተጠቀሙበትና በእያንዳንዱ ወራት ያላችሁን ግብ ጻፉና

    ከአንዱ ግብ ወደ ሌላው ግብ ያላችሁን ስኬት በሚገባ ለኩ

  • eU

    ݃^h

    eM¡

    ¾ÓM S[Í

  • ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

    www.rhapsodyofrealities.org

    ...ዕለታዊ የመንፈሳዊ ጥናት መጽሃፍ

  • amharic

    ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የኋለኛው አዳም ነው፡፡ እርሱ ህይወት ሰጪ ነው፤ በእናንተ ውስጥ ደግሞ በመንፈሱ ስለሚኖር፣ እና የእርሱን ዓይነት ህይወት ስለሰጣችሁ፣ እናንተ አሁን ህይወትን ስለሰጣችሁ እናንተ አሁን ህይወትን የምትሰጡ ናችሁ፡፡

    እኛ ለሰዎች ክርስቲያን ተራ ሰው እንዳልሆነ፣ ከጌታ ጋር በአንድ ዓይነት ተልእኮ እና ዓላማ ላይ ያለ ከእርሱ ጋር አንድ እንደሆነ እንናገራለን። በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10፡10 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ይናገራል፡- “…እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” ዓላማውን በተመለከተ፣ እርሱ ማንንም እንኳ ጥርጣሬ ላይ አልጣለም፡፡ እርሱ የመጣው በእርሱ ለሚያምኑት የዘላለምን ህይወትን ሊሰጣቸው ነው፡፡ ይህንኑ እውነት እንደዚህ በማለት በይበልጥ አረጋግጦታል፡- “በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥…” (ዮሐንስ 10፡27-28)፡፡

    በመክፈቻ ጥቅሳችን ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ተብሎ መገለጹ የሚያስገርም አይደለም፡፡ እናንተ ደግሞ አሁን ዳግም ተወልዳችኋልና ከክርስቶስ ጋር አንድ ናችሁ፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡17 “ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።” ይላል፡፡ ከጌታ ጋር አንድ መንፈስ ሆናችኋል፤ እርሱ እንዳለ እናንተ ደግሞ ናችሁ (1ኛ ዮሐንስ 4፡17)፤ ስለዚህ እናንተ ህይወትን የምትሰጡ መንፈስ ናችሁ፡፡ እናንተን ያደረጋችሁ፣ የእርሱን ህይወት ተካፋዮች ብቻ ሳይሆን፣ የዘላለም ህይወትን የምትሰጡ ወይም የምታከፋፍሉም ጭምር ነው፡፡

    የጠፉትን በወንጌል አማካኝነት ወደ ጽድቅ ህይወት ማምጣት የእናንተ

    እናንተ ህይወትን የምትሰጡ መንፈስ ናችሁ

    እንዲሁ ደግሞ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ

    መንፈስ ሆነ። (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡45)

    ሰኞ 1

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 9:1-17 & መጽሀፈ ኢያሱ ወልደነዌ 10-12

    የማቴዎስ ወንጌል 26:69-75 & ኦሪት ዘሌዋውያን 1

    2 ኛ ጢሞቴዎስ 1:9-10; የዮሐንስ ወንጌል 3:16; 1 ኛ ቆሮንጦስ 15:45-49

    የህይወት ዓላማ ነው፡፡ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡10 ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ሽሮ በወንጌል ህይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን እንዳመጣ ያሳውቀናል፡፡ በወንጌል መስበክ አማካኝነት፣ የዘላለም ህይወት ይገለጣል፡፡ የህይወት ቃል አላችሁ፡፡ እናንተ ስትናገሩ ደህንነትና የእግዚአብሄር ጽድቅ ይገለጣሉ፡፡

    ኢየሱስ በዮሐንስ 20፡21 ላይ፡- “…አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ” ብሏል፡፡ እናንተ የእግዚአብሄር ህይወትን ለአህዛብ እንድትገልጡ እርሱ መርጧችኋል፡፡ የጠፉትን ወደ እግዚአብሄር ልጆች ነጻነት ማለትም በእርሱ ወዳለው የክብር ህይወት እንድታመጡ እርሱ የወንጌሉ አቅራቢዎች እንድትሆኑ ልኳችኋል፡፡

    ኢየሱስ እንዳለ፣ እኔም ደግሞ ነኝ፤ እኔ ህይወትን የምሰጥ መንፈስ ነኝ፤ የዘላለም ህይወት እና የመንግስቱን የዘላለም እውነታዎች አቅራቢ እና አከፋፋይ ነኝ፡፡ ዛሬ እኔ ለብዙዎች ደስታን አመጣለሁ፤ ህይወታቸውን ለመለወጥ እና በክርስቶስ ወዳላቸው ርስት የሚያስፈነጥራቸውን የእግዚአብሄር ኃይል የሆነውን ወንጌል አካፍላቸዋለሁ፡፡ ሃሌሉያ!

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    የመክፈቻ ጥቅሳችን ዛሬ በቤተክርስቲያን ያሉ ሊረዱት የሚገባቸውን አንዳች አስደናቂ ነገር ይገልጣል፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ሆኖ ነገሮችን በዓለም ውስጥ እንዴት እንደሚከናወን ወይም በሌላ አደጋ ውስጥ ያሉትን ልጆቹን እንዴት እንደሚረዳ በመጨነቅ ላይ አይደለም፡፡ ይልቁንስ እርሱ በሰማይ በእረፍት ላይ ነው፡፡ እናንተ ህይወት እንዲሆንላችሁ እና በሙላት እንድትደሰቱበት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አስቀድሞ ሁሉን አከናውኖ አሁን ዘና ብሎ በእረፍት ላይ ነው፡፡

    ነገር ግን እኔ አንዳች ነገር ሲገጥመኝ በድንቅ ጣልቃ ወደሚገባው ወደ እግዚአብሄር ስጸልይ ያ ማለት እርሱ አንዳች ነገር አደረገ ማለት አይደለምን ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ አይደለም፣ እርሱ ምንም ነገር አላደረገም፡፡ እርሱ አስቀድሞ ያደረገውን ትቀበሉ ዘንድ እምነታችሁን ብቻ ነው ያንቀሳቀሳችሁት፡፡ በመቀጠልም እንዲህ ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡- “ነገር ግን ሐዋርያው ጳውሎስ እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥ (ኤፌሶን 3፡20) “ ብሏል፡፡ ይህ እግዚአብሄር ዛሬም ነገሮችን እያደረገ መሆኑን አያሳይም? ኋለኛውን የጥቅሉን ክፍል ልብ አድርጋችሁ አስተውሉ፤ እርሱ እናንተ እንዲያደርግላችሁ የምትጠይቁትን ማናቸውንም ነገር የሚያደርገው በእናንተ ውስጥ እንደሚሰራው ኃይል መጠን ነው እንጂ ከሰማይ ሆኖ በሚያንቀሳቅሰው ኃይል አይደለም፡፡ እንዲህ ያሉ ተአምራቶች ሲፈጸሙ ትሩፋቱን ለእናንተ የሚሰጠውም ለዚህ ነው፡፡ እርሱ ድውዮችን አንድንፈውስ፣ ለምጻሞችን እንድናነጻ፣ ሙታንን እንድናነሳ፣ አጋንንትን እንድናስወጣ ነግሮናል (ማቴዎስ 10፡8)፡፡ “እነዚህን ነገሮች እንዳደርግ ወደ እኔ ጸልዩልኝ” አላለም፡፡

    ዝቅተኛ በሆኑ የመንፈሳዊ መረዳት ደረጃዎች የሚፈቀዱ አንዳንድ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ለምሳሌ በመነቃቃት ጉባኤዎች “ዛሬ እግዚአብሄር ይፈውሳችኋል” ልንል እንችላለን፤ እናም ደግሞ ልዩ ልዩ የፈውስ ተአምራት ይከናወናሉ፡፡ ያ ግን፣ ዝቅተኛ እውነት ነው፡፡ በዘፍጥረት 1፡16 ላይ ስለ

    እርሱ በእርግጥ ዛሬ እየሰራ አይደለም

    ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና። (ዕብራውያን 4፡10)

    ማክሰኞ 2

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 9:18-36 & መጽሀፈ ኢያሱ ወልደነዌ 13-15

    የማቴዎስ ወንጌል 27:1-10 & ኦሪት ዘሌዋውያን 2

    1 ኛ ጴጥሮስ 2:1-2; የማቴዎስ ወንጌል 6:25-26; ኤፌሶን 1:3

    ታላቁ እና ታናሹ ብርሃን እናነባለን፡፡ ብርሃን እውነትን ይወክላል፡፡ አነስተኛ የሆኑ እና ጠቅላላ እውነቶች በክርስቶስ ላሉ ህጻናት ናቸው፤ ስለዚህ፣ “ዛሬ እግዚአብሄር ይፈውሳችኋል” ትሏቸዋላችሁ፡፡

    ነገር ግን፣ ወደ እግዚአብሄር ቃል ጠልቃችሁ ስትገቡ፣ ዛሬ ብዙዎች በሚረዱት መልኩ እግዚአብሄር በእርግጥ ለማንም ምንም እያደረገ እንዳልሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ እርሱ ሁሉን በክርስቶስ ኢየሱስ አስቀድሞ አከናውኖታል! ሊፈውሳችሁ ወይም አንዳች ነገር ሊሰጣችሁ ምንም ጥረት እያደረገ አይደለም፡፡ 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3፡- “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥…” ይላል፡፡ እርሱ አስቀድሞ ፈጽሞታል! አሁን እናንተ ማድረግ የሚያሻችሁ በቃሉ ልክ እርምጃ መውሰድና በርስታችሁ ውስጥ መመላለስ ነው፡፡ እርሱ እናንተን ያደረጋችሁን ሁሉ ሁኑ፤ እናም በክርስቶስ ለእናንተ ያደረገውን አቅራቦት ሁሉ ተደሰቱበት፡፡

    እግዚአብሄር ይባረክ! እኔ የመጠቀ የክብር ህይወት እኖራለሁ፤ በክርስቶስም ደግሞ ሁልጊዜ በሁሉም ስፍራ እና በነገር ሁሉ ድል አድራጊ ነኝ፡፡ የመለኮቱ ኃይል ለእውነትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ ሰጥቶኛል፡፡ ስለዚህም ህይወት አለኝ፤ ህይወቴንም በሙላት እየተደሰትኩበት ነው፡፡ ሃሌሉያ!

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    የምትመሰክሩባቸው ሶስት መንገዶች አሉ፤ እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ለራሱ ለእግዚአብሔር መመስከር አንዱ መንገድ ነው፡፡ በረከታችሁን በመቁጠር በግል ሕይወታችሁ ላይ በጎነቱን መስክሩ፤ ያደረገላችሁን ማለትም በእናንተ ውስጥና በእናንተ ያደረገውን ሁሌም ታስባላችሁ፡፡ ደግሞም ከፀጋው የተነሣ ያገኛችሁትን ምህረት፣ ታማኝነትና፡ ለዘላለም የሚፀና ፍቅር ትመሰክራላችሁ፡፡

    ሁለተኛው መንገድ ስጦታ በመስጠት መመስከር ነው፡፡ ይሄን መንገድ ብዙ ሰዎች አይረዱትም ደግሞም ተግባራዊ አያደርጉትም፤ የመስጠትን ኃይል፡፡ ለእግዚአብሔር ስጦታን ስታቀርቡ እርሱ አምላክ እንጂ ሰው እንዳይደለ የሚገልፅ የተቀደሰ ስራ ነው እንጂ መዋጮ አይደለም፡፡ ስጦታ ስትሰጡ በሕይወታችሁ ክብርን እየሰጣችሁትና እየመሰከራችሁ ነው፡፡

    የሀይማኖት አባቶች -- አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን -- ሁሉም እግዚአብሔርን ለማምለክ ስጦታን መስዋዕት አርገው ሰጥተዋል፡፡ ለምሳሌ ሰለሞንን ውሰዱት፡- 1 ነገሥት 3:4 እንዲህ ይላል፡- “. . .ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፡፡” በእግዚአብሔር ዘንድ በጣም ያነሰ መስዋዕት ተቀባይነት ቢኖረውም እንኳን፡ ሰለሞን የእግዚአብሔርን ታላቅነት ስላወቀና መመስከር ስለፈለገ ነው አንድ ሺህ የሚቃጠል መስዋዕት ያቀረበው እየመሰከረ ነው፡፡

    መስዋዕት እግዚአብሔርን ስለሰጣችሁ ሀብት የምታከብሩበት መንገድ ከመሆኑ ሌላ፡ ታላቅነቱን የምትመሰክሩበትና ለኃይሉ እንዲሁም ለሁሉን ቻይነቱ እውቅና የምትሰጡበት መንገድ ነው፡፡

    ሶስተኛው የምትመሰክሩበት መንገድ ጌታ በእናንተ ውስጥና በእናንተ ስላደረገላችሁ ነገሮች ለሌሎች በመመስከር ነው፡፡ የጽድቅን ፍሬዎች በማፍራትና የዕለት ኑሮዋችሁን በዕምነት በመምራት ስለበጎነቱ ለሰዎች መንገር ማለት ነው፡፡ በምንም አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ደስተኛዎች ናችሁ፡፡

    የምንመሰክርባቸው ሶስት መንገዶች

    እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን፡፡ (1 ዮሐንስ 4:14)

    ረቡዕ 3

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 9:37-62 & መጽሀፈ ኢያሱ ወልደነዌ 16-19

    የማቴዎስ ወንጌል 27:11-25 & ኦሪት ዘሌዋውያን 3

    የሉቃስ ወንጌል 17:17-19; የዮሐንስ ራዕይ 12:11

    እምነታችሁንና በጌታ ላይ ያላችሁን መተማመን ሰዎች ሲያዩ እንዲሁም በምንም ዓይነት ሁኔታና ፈተና ውስጥ ስታልፉ ደስተኛ መሆናችሁን ማየታቸው ራሱ ምስከርነት ነው፡፡ በምንም ዓይነት ውጥረት ውስጥ ብታልፉም እንደ ሁልጊዜው ሙሉ በሙሉ ራሳችሁን ለጌታ ቤት አሳልፋችሁ በመስጠታችሁ በጌታ ላይ ያላችሁን መተማመን ልብ ይላሉ፡፡ ይህ ነው ምስክርነት ማለት፡፡

    ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች በሕይወታችሁ ስላለው የእግዚአብሔር ክብር የምትመሰክሩባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ ሀሌሉያ!

    ውድ አባት ሆይ፡ ምስጋና የሚገባህ ታላቅና ክቡር አምላክ ነህ፡፡ ከፍቅርህና ከበጎነትህ የተነሣ በሕይወቴ እያጣጣምኩት ስላለው በረከትህና ተአምራትህ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሰማይና ምድር ታላቅ ስራህን፣ የማያልቀውን ጥበብህንና፡ ደግነትህን ያውጃሉ፤ ለዘላለም የክብር ንጉስ ለሆንከው ላንተ፡ ፍጥረት ሁሉ “ሀሌሉያ” እያለ ይዘምራል፡፡ አሜን፡፡

    ጸሎት

  • amharic

    ክርስትና ማለት ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ሲገለጥ ማለት ነው፤ ክርስቶስ በእናንተ ሲኖር — በእናንተ ውስጥና በኩል እየሰራ፤ በእናንተ ሕይወትን እየነካና እየቀየረ፡፡ ይህ ነው የክርስትና ፍሬ ነገር፡ ክርስቶስ መንፈሳችሁ ውስጥ ሲኖርና መኖሪያ መቅደሱ ሲያደርጋችሁ፡፡

    እግዚአብሔር በምድር ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ነገር ሁሉ በእኛ በኩል ብቻ እንደሆነ ማድረግ የሚችለው ታውቃላችሁ? እኛ የሥራው ማዕከል ነን፤ በእኛ ውስጥ በመኖር ነው ሚናገረው፣ ሚንቀሳቀሰው፣ የሚናገረውና የሚባርከን፡፡ ነብዩ እንዲህ አለ፡- “. . . ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል፡፡” (ኢሳያስ 53:10)፤ ያ ዘር እኛ ነን፡፡ ሀሌሉያ፡፡ እናንተ የእሱ ውበት፣ የዋንጫ ሽልማትና የተዘረጋ እጁ ናችሁ፡፡

    ዮሐንስ 15:5 ላይ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፡፡ . . .” ቅርንጫፎች ፍሬ የሚያፈራው የዛፍ ክፍል ናቸው፡፡ ስለዚህም የክርስቶስን ክብርና ውበት ታሳያላችሁ፡፡ ያም ክብር ያለው፡ ክርስቶስ በሚገኝበት፡ በመንፈሳችሁ ውስጥ ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልጋችሁ፡ በውስጣችሁ ክርስቶስ እንደሚኖር ማወቅና ልብ ማለት ነው፡፡ በውስጣችሁ ያለው ክርስቶስ ነው በውጪ የሚታየውን ክብር የሚፈጥረው፡፡ ወደ ውስጣችሁ ወደ መንፈሳችሁ በመመልከት ውስጣችሁ ያለውን ክብር ተመልከቱ፤ ያንንም ክብር ለዓለማችሁ ግለጡ፡፡ ይህ ነው ክርስትና፤ በውስጣችሁ ያለውን ክርስቶስ መግለጥና ማሳየት፡፡

    እውነተኛ መንፈሳዊ ዕድገት የሚወሰነው በእናንተ በኩል ክርስቶስ በተገለጠበት ልክ ነው—ማንነቱና ባህሪው በእናንተ ውስጥና በእናንተ በኩል ሲገለጥ፡፡ ለዛ ነው በደንብ አስባችሁበት ቃሉ በሙላት እንዲኖርባችሁ

    ክርስቶስን ማሳየትና መግለጥ

    የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን

    እንሰጣለንና፡፡ (2 ቆሮንቶስ 4:11)

    ሐሙስ 4

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 10:1-24 & መጽሀፈ ኢያሱ ወልደነዌ 20-22

    የማቴዎስ ወንጌል 27:26-37 & ኦሪት ዘሌዋውያን 4

    2 ኛ ቆሮንጦስ 4:10-11; ቆላስያስ 3:3-4; 1 ኛ ጴጥሮስ 2:9

    መፍቀድ ያለባችሁ፡፡ ጌታና ቃሉ አንድ ስለሆኑ ቃሉን ማጥናትና ማሰላሰል አታቋርጡ፡፡ ከሱ ጋር ህብረት በማድረግ ይበልጥ ስታውቁት፡ በእናንተ ውስጥና በእናንተ በኩል ይበልጥ እየተገለጠ ይሄዳል፡፡

    ክርስቶስ በመንፈሴ ውስጥ ይኖራል፤ የክርስቶስን ሕይወት በመኖርና ባህሪውን፣ ክብሩን፣ ፀጋውንና ፅድቁን በመግለጥ፡ መኖሪያ መቅደሱና የስራው ማዕከል ሆኛለሁ፡፡ በእኔ በኩል የጌታ ውበትና ፍፅምና፡ ውስጤ በሚሰራው መንፈስ ቅዱስ፡ ለዓለሜ መግለጡ ከቀን ወደ ቀን ለዘላለም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    ደስታ ዳግም የተፈጠረው የሰው ልጅ መንፈስ ነው፤ በውስጣችሁ ያለ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሊያሳዝናችሁ የሚሞክር ዜናም ሆነ ሁኔታ ምንም ለውጥ አያመጣም፤ ሁልጊዜም በመንፈስ ቅዱስ ድስተኛ ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሄር መንግሥት እንደዚያ ነው፡፡ ሮሜ 14፡17 እንዲህ ይላል፡- “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።”

    ኤፌሶን 5፡18-19 ሁልጊዜም በመንፈስ ቅዱስ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደምትችሉ ይገልጥልናል፤ እንዲህ ይላል፡- “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”::

    ይህ የሐዋርያው ጳውሎስ አንዱ የስኬት ምሥጢር ነበር፡፡ በመክፈቻ ጥቅሳችን ያነበብነውን የጻፈው በእሥር ቤት በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን ደግሞ “የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤ ስለ ወንጌልም በሰንሰለት መልእክተኛ የሆንሁ፥ መናገር እንደሚገባኝ ስለ እርሱ በግልጥ እናገር ዘንድ ለምኑ።” (ኤፌሶን 6፡19-20) ብሏል፡፡ የተሰመረበትን ክፍል አስተውሉ፤ ልምምዱ ስሜቱን እንዲወስን ወይም በጌታ በልቡ ውስጥ ያለውን ደስታ እንዲነካ አልፈቀደም፡፡

    በህይወታችሁ ውስጥ፣ ተግዳሮቶችን ለእድገታችሁ ዕድሎች እና የእግዚአብሄርን ክብር ለመግለጥ እንደሆኑ አድርጋችሁ እይዋቸው፤ በዚያ መንገድ ሁልጊዜም ሙሉ በሙሉ ደስተኛ ትሆናላችሁ፡፡ ያዕቆብ 1፡2-3 እንዲህ ይላል፡- “ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን

    የደስታችሁን ፍም ማርገብገብ

    ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። (ፊልጵስዮስ 4፡4)

    አርብ 5

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 10:25-42 & መጽሀፈ ኢያሱ ወልደነዌ 23-24

    የማቴዎስ ወንጌል 27:38-44 & ኦሪት ዘሌዋውያን 5

    መጽሀፈ ነህምያ 8:10; 1 ኛ ጴጥሮስ 1:8; ትንቢተ ኢሳያስ 12:3

    እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፡፡” ሮሜ 8፡28 እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”

    ሁልጊዜም የደስታችሁ ምክንያት ቃሉ ይሁን፡፡ ሁኔታዎችን በእግዚአብሄር ቃል መሰረት ስትተረጉሟቸው እና ምላሽ ስትሰጡባቸው፤ በህይወት ውስጥ ምንም መጥፎ ቀን ሊሆንባችሁ ወይም ሊጎዳችሁ እንደማይችል ትገነዘባላችሁ፤ ምክንያቱም ደስታችሁ የሚመነጨው በቃሉ አማካይነት እና በእግዚአብሄር መንፈስ ስለሆነ ነው፡፡

    ጌታ ኢየሱስ፣ በምትክ ሞቱ እና አሸናፊ በሆነው ትንሣኤው ገደብ ወደሌለው የደስታ፣ የድል፣ የመግዛት እና የጽድቅ ህይወት አምጥቶኛል፤ በዚህም የተነሣ መናገር በማይቻል ደስታ እና በክብር ተሞልቼ ለዘላለም ሐሴት አደርጋለሁ፡፡ ደስታዬ በቃሉ እና በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ በመሆኑም ለደስታ ገደም የለውም፡፡ ሃሌሉያ!

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    ቅዳሜ 6

    በብሉይ ኪዳን ካህኑ የተቃጠሉ መስዋዕቶችና ዕጣን ያቀርብ እንደነበረው፤ ዛሬ እኛ በከንፈራችን ፍሬ ማለትም ለእርሱ በምስጋና በምንናገራቸው ቃሎች፣ የምስጋና መስዋዕቶችን ለጌታ እናቀርባለን፡፡ “ማመስገን” የሚለው የግሪክ ቃል “ሆሞሎግዮ” የሚለው ሲሆን ትርጓሜውም ማወጅ ማለት ነው፤ በእርሱ ስም ማወጅ ማለት ነው፡፡

    የምስጋና መስዋዕታችን በቃሉ ነው፤ እናም “ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ” ከሚለው ያለፈ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር እውነተኛ የምስጋና መስዋዕት ይሆን ዘንድ፣ ከመንፈሳችሁ ከመጣ ነገር ጋር መዋሃድ ይገባዋል፤ እርሱን ለማመስገን የተወሰነ ምክንያት ያስፈልጋችኋል፤ ከዚያም ከመንፈሳችሁ መናገር አለባችሁ፡፡

    እርሱን የምታመሰግኑባቸው ነገሮች ሊኖሩ ይገባል፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ሆን ብላችሁ ለተወሰኑ ነገሮች በኢየሱስ ስም እያመሰገናችሁት ነው ማለት ነው፡፡ የምስጋና መስዋዕቶቻችሁ፣ ስለ እርሱ ፍቅር፣ ጸጋና ለእናንተ ስላለው መልካምነት የምታደርጓቸው የእምነት አዋጆቻችሁ፣ ንግግሮቻችሁ እና መንፈሳዊ መዙሙሮቻችሁ ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ ንግሥናውን እውቅና የምትሰጡበት እና የምትወድሱበት የአድናቆት መግለጫዎች እና ንግግሮች ናቸው፤ እርሱን ለማክበር የምንናገራቸው የእግዚአብሄር ቃል ናቸው፡፡

    እነኚህ አዋጆች የከንፈራችን ፍሬዎችና ጠቦቶች ናቸው፤ ከአፋችን የሚወጡ እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ቃሎች ናቸው፡፡ ስለዚህ፣ ቃሉን ስናውጅ ስለእግዚአብሄር የተዋቡ ነገሮችን ተናገሩ፤ ስለ አስደናቂ ስራዎቹም ምስክርነትን ስጡ፡፡ ስለራሱና ስለ እናንተ የተናገረውን አውጁ፤ “እርሱ ራሱ። … ብሎአልና፤ ስለዚህ በድፍረት። … እንላለን።” (ዕብራውያን 13፡5-6)፡፡

    እነኚህን አዋጆች በኢየሱስ ስም ስታደርጉ፤ እርሱ (ኢየሱስ) የእኛ ታላቅ

    የምስጋና መስወዋዕታችን በቃሉ ነው

    እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ

    እናቅርብለት። (ዕብራውያን 13፡15)

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 11:1-13 & መጽሀፈ መሳፍንት 1-2

    የማቴዎስ ወንጌል 27:45-54 & ኦሪት ዘሌዋውያን 6

    ትንቢተ ሆሴዕ 14:2; ዕብራውያን 13:15 AMPC

    ካህን እንደመሆኑ መጠን በአብ ፊት ያቀርባቸዋል፣ አብ ደግሞ የእናንተን ምስጋና እና አምልኮ እንደ ጣፋጭ መዓዛ ይቀበለዋል፡፡ ሃሌሉያ!

    የተባረክህ አባት ሆይ፣ አንተ እንዴት ታላቅና አስደናቂ ነህ! አንተ የሰዎች ጉዳይ ላይ የምትገዛ እና የምትነግስ ብቸኛው እውነተኛ እና ጠቢብ አምላክ ነህ፡፡ አቤቱ ጌታ ሆይ፣ ክብር ሁሉ፣ ንግስና፣ መግዛት እና ምስጋና ለአንተ ይሁን! በክብር፣ በጽድቅና በሰላም ህይወቴን የተዋበ ስላደረግኸው አመሰግንሃለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

    ጸሎት

  • amharic

    የእግዚአብሔር ጸጋ መለኮታዊ ነው! የሞገስ፣ የብልፅግና የፈውስና የልዕለ ተፈጥሮ ጭማሪን ያመጣል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ርህራሄና ሀይል መገለጫ ነው፤ ፀጋው በሰው መንፈስ ውስጥ ያለው መለኮት ውጫዊ መገለጫ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ መክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንደተናገረው ይህ መለኮታዊ ፀጋ ተሰጥቷችኋል፡፡

    ፀጋው ተቀባይነትን፣ ክብርንና ማዕረግን ያመጣል፤ ፀጋው እግዚአብሔር ለሕይወታችሁ ካለው ዓላማ ጋር የሚሄዱ ትክክለኛ ሰዎችን፣ ሁኔታዎችንና አስፈላጊ ነገሮችን ወደ እናንተ ይስባል፡፡ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ፀጋው ከምንም ዓይነት ችግር በላይ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፡፡

    ፀጋው ከዓለም ለክብርና ለልቀት ይለያችኋል፡፡ በዚህ ዓለም ያለው የትኛውም ነገር ዝናን ወይም ሀብትን ጨምሮ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ከሰጣችሁ ጋር አይወዳደርም፡፡ ለዚህ ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ 2 ቆሮንቶስ 6:1 ላይ እንዲህ ብሎ ምክርን ያቀረበው፡- “አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤” ነገር ግን “. . . በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ፡፡” (2 ጢሞቴዎስ 2:1)

    በእግዚአብሔር ጸጋ መጠንከር ማለት በጸጋው ሙላት መመላለስ ማለት ነው፡፡ የአብርሃም ዘር ስለሆናችሁ የብልጽግና ጸጋ በእናንተም ውስጥ እየሠራ ነው፡፡ ያ ጸጋ ወደ ፊት እያስኬደ ልክ እንደ ይስሐቅ ስኬታማ ያደርጋችኋል፣ በድርቅ ጊዜ ዘርቶ በዛው ዐመት መቶ እጥፍ እንዳፈራው ማለት ነው (ዘፍጥረት 26:12-13) ፡፡

    በጸጋው መመላለስ

    እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና። (ዮሐንስ 1:16)

    እሁድ 7

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 11:14-36 & መጽሀፈ መሳፍንት 3-4

    የማቴዎስ ወንጌል 27:55-66 & ኦሪት ዘሌዋውያን 7

    2 ኛ ቆሮንጦስ 13:14; ትንቢተ ዘካርያስ: 4:7; ሮሜ 5:17

    ውድ አባት ሆይ፥በእኔ ላይ ስላበዛኸው ፀጋ ሀሴት አደርጋለሁ፥ ደግሞም በፍቅርህ ስመላለስ፡ሕይወቴ የክብርህ፣ የደግነትህ፣ የልቀትህና የታላቅነትህ መገለጫ ሆኗል ብዬ አውጃለሁ፡፡ጸጋህና ሰላምህ በህይወቴ እየጨመረ በሚሄደው የቃልህ መገለጥ በዝቶልኛል፥ በኢየሱስ ስም፡፡አሜን፡፡

    ፀሎት

  • ወንጌሉን የመድረሻ ቁልፍ

    በቃሉ የመቀየ የጁሴፔ ምስክርነት!

    ጁሴፔ አንድ ኢጣልያዊ ወጣት ነው፤ የመጀመርያውን የራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ቅጂ ያገኘው፣ በመኖርያው አካባቢ ያንን መጽሀፍ በምታሰራጭ ሴትዮ አማካኝነት ነው፡፡ እንደ ተራ መጽሐፍ እንዳያነበው፤ ነገር ግን መልእክቱን እንዲያጠናና እንዲያሰላስለው ነግራው ነበር፡፡ እሱም ምክሯን ተቀብሎ እንደነገረችው አደረገ፡፡ብዙም ሳይቆይ፣ በህይወቱ ውስጥ ለውጥን ማየት ጀመረ፡፡ ህይወቱን በሙሉ የማያውቀውን፣ የመንፈስ ዓለም የበለጠ እያወቀ መጣ፡፡ የራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስን ማጥናት፣ በመንፈሱ ዓለም እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለበት እና በአሸናፊነት እንዴት መኖር እንደሚችል ለመረዳት ቻለ፡፡ “ወደ ጣሊያንኛ ቋንቋ ባይተረጉሙት ኖሮ፣ እነኚህን የተዋቡ ትምህርቶች ባላገኘሁ ነበር፡፡ እንግሊዘኛ አልናገርም፣ የምናገረው ጣሊያንኛ ብቻ ነው “ ብሏል፡፡ ይህንን የአምልኮ መጽሀፍ በጣሊያንኛ ቋንቋ ማግኘት፣ ለጁሴፔ ትልቅ ነገር ነው፤ ምክንያቱም፣ ሌላ ምንም ቋንቋ የማይናገሩ ወይም የማይረዱ ብዙ ሰዎችን ያውቃል፡፡ “በሌላ ቋንቋዎች የማላነበው እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ ስለዚህ፣ ይህ ትርጉም ወንጌሉ በእነርሱ ህይወት ውስጥ እንዲገባ፣ የመድረሻ ቁልፍ ነው፡፡” ይህን መጽሐፍ በጣሊያንኛ ቋንቋ ለሌሎች ለማዳረስ ትጉህ የሆነውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን፣ በጣሊያን ባህል በጥልቀት የተመሰረቱ፣ ሳን ጊሚኛኖ እና ሴይና የተባሉ ሁለት ጥንታዊ ከተሞችን እርሱ እና ጓደኞቹ ደርሰዋል፡፡ ወንጌሉን በእናታቸው ቋንቋ በተለያዩ የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ሰዎች በማድረስ፣ በራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ውስጥ ያለውን የተተረጎመ የደህንነት ጸሎት ተጠቅመው፣ ብዙዎችን ወደ ክርስቶስ በአስደናቂ ሁኔታ እየመሩ፣ ውጤታማ በሆነ መንገድ ዘልቀው ገብተዋል፡፡

    የራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ፣ በ 1,900 ቋንቋዎች የቀረበ ሲሆን፣ ቁጥሩ አሁንም እየጨመረ ነው፡፡ ልክ እንደ ጁሴፔ፣ ዛሬ በልባቸው ቋንቋ የእግዚአብሄርን ቃል ወደ እነርሱ በማድረስ፤ ለሌሎች በረከት ሁኑ፡፡

  • Te ¨h

    Te ¨

    h

  • amharic

    ብዙ የቤተ ክርስትያን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ስለሚደረግ የመለኮታዊ ጉዞ አገልግሎት አያውቁም፡፡ የራዕይ መፅሐፍ ላይ ስለ ዮሐንስ የተፃፈውን አንብቡ፤ ፍጥሞ የምትባል ደሴት ውስጥ ሳለ በድንገት ወደ እግዚአብሔር ህልውና ተጓዘ፡፡(ዮሐንስ ራዕይ 1:9-11) ሌላው ምሳሌ ፊሊጶስ ነው፡፡ ሐዋሪያት ሥራ 8:39 እንዲህ ይላል፡- “ከውኃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጠቀው፤ ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፥ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና፡፡”

    የጌታ መንፈስ ፊሊጶስን በአካል ሌላ ቦታ ወሰደው፡፡ (ሐዋሪያት ሥራ 8:40) አስታውሱ፥ ፊሊጶስ ዳግም ተወልዶ መንፈስ ቅዱስን ተሞቶ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ ያለውን አላማ በእኛ ውስጥ በማገልገል ነው የሚፈፅመው፡፡

    2 ቆሮንቶስ 13:14 እንዲህ ብሎ ያውጃል፡- “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኀብረጽ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡” “ኀብረት” ተብሎ የተተረጎመው ቃል “ኮይኖንያ” ከሚለው የግሪክ ቋንቋ የመጣ ሲሆን፡ ትርጓሜውም ንግግር ውስጥ ያለ መጓጓዣ ማለት ነው፡፡ ሐዋሪያው ጰውሎስ ቤተ ክርስትያን መለኮታዊ የሆነውን በመንፈስ ቅዱስ የሚደረግ ጉዞ፡ እንድትለማመድ አዘውትሮ ይጸልይ ነበር፡፡

    በሕይወታችሁ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ራሳችሁን አሳልፋችሁ ስትሰጡ፡ ከመነገር በሚያልፍ ሀይል ነው እግዚአብሔር የሚጠቀምባችሁ። ከማነቃቃትና ከመባረክ አልፎ ሩቅ ወዳሉ ምድሮች መለኮታዊ ሥራዎችን እንድታከናውኑ በመለኮቱ ሊያጓጉዛችሁ ይችላል፡፡ እዛው በግላችሁ

    በመንፈስ ቅዱስ የሚደረግ መለኮታዊ ጉዞ

    መንፈስ አንሥቶ አስወገደኝ፥ እኔም በምሪትና በመንፈሴ ሙቀት ሄድሁ፥ የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ በርትታ ነበር።

    (ሕዝቅኤል 3:14)

    ሰኞ 8

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 11:37-54 & መጽሀፈ መሳፍንት 5-6

    የማቴዎስ ወንጌል 28:1-10 & ኦሪት ዘሌዋውያን 8

    ዕብራውያን 11:5; የሐዋርያት ስራ 8:39-40; ኦሪት ዘፍጥረት 5:24

    በምትጸልዩበት ስፍራ፡ በልሳን ስትጸልዩ፡ በሺዎች ማይልስ በሚቆጠር ርቀት ላይ ያሉ ሕይወቶችን መንካትና ነገሮችን መለወጥ ትችላላችሁ! ሀሌሉያ!

    ውድ አባት ሆይ፥ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ካንተ ጋር ጥልቅ የሆነ፣ ልባዊ፣ የተነቃቃና፣ ጥብቅ ኀብረት ደስ ብሎኝ ማጣጣሜ፡ ታላቅ ዕድልና በረከት ነው! ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባለኝ ኀብረት ከፍ ወዳለ ተፅዕኖ አምጪነት፣ ክብርና በረከቶች መለኮታዊ ጉዞ አድርግያለሁ፤ ስለዚህም በወንጌል ሕይወቶችን እነካለሁ፣ ሕዝቦችን እቀይራለሁ፣ ዓለም ላይም ተፅዕኖን አመጣለሁ፥ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

    ጸሎት

  • amharic

    በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት እንደመሆናችሁ፥ ልዩ ናችሁ፤ በውስጣችሁ ብዙ መልካም ነገሮች አሉ፤ ጌታ በውስጣችሁ ለሕይወታችሁ ያስቀመጠው በጣም ብዙ ነገር አለ፡፡ እንዲያው አይደለም የፈጠራችሁ፤ በእርሱ ዘንድ ዋጋ አላችሁ፡፡

    የእግዚአብሔርን ክብር መገለጫዎች ስለሆናችሁ ራሳችሁን ልትወዱና ለራሳችሁ ዋጋን ልትሰጡ ይገባል፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር በእናንተ ነው በምድር ላይ የሚነግሰው፣ ጽድቁን የሚመሰርተውና የሚያስፋፋው፡፡ ዮሐንስ ራዕይ 5:10 ክርስቶስ ያደረገንን ይናገራል፡- “ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፡፡” 1 ቆሮንቶስ 15:25 ላይ ደግሞ እንዲህ እናነባለን፡- “ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና፡፡” ኢየሱስ ዛሬ በምድር ላይ በአካል የለም፥ ነገር ግን አሁንም በእናንተ በኩል በምድር ላይ ይነግሣል፡፡ በክርስቶስ የንጉስ ካህናት ተደርጋችኋል (ዮሐንስ ራዕይ 1:6) ክቡር የሆነው ወንጌል ለእናንተ በአደራነት ተሰጥቷችኋል፡፡

    አሁን እንግዲህ ጌታ ይሄን ያህል በእናንተ ተማምኖ በእናንተ በኩል ከነገሰና፡ ክቡሩን ወንጌል ለእናንተ አሳልፎ ከሰጠ፡ በእውነትም በእርሱ ዘንድ ዋጋ ያላችሁ ናችሁ፡፡ ስለዚህ እናንተም የዛው አይነት ዋጋን ለራሳችሁ ስጡ። አስተሳሰባችሁ፣ ንግግራችሁ፣ አረማመዳችሁና ኑሯችሁ እንደ ልዩ ሰው ይሁን፤ በእርግጥ ልዩ ሰዎች ናችሁና፡፡ የመለኮታዊ ዕውቀትና የመንግስቱ እውነታ ባላደራ ናችሁ፤ እንዴት ታላቅ ነገር ነው!

    እግዚአብሔር መልካምና ውብ የሆነውን የዕውቀቱን የመዓዛ ሽታ ወደ ሁሉም ስፍራ የሚያስፋፋው በእናንተ በኩል እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡- “ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም

    ለራሳችሁ ፍቅርንና ዋጋን ስጡ

    የእምነትህም ኀብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤

    (ፊልሞና 1:6)

    ማክሰኞ 9

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 12:1-21 & መጽሀፈ መሳፍንት 7-8

    የማቴዎስ ወንጌል 28:11-20 & ኦሪት ዘሌዋውያን 9

    1 ኛ ጴጥሮስ 2:9 AMPC; ኤፌሶን 2:10 AMPC

    በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤” (2 ቆሮንቶስ 2:14) ቃሉ በዓለም እንዲሰማ ማድረግ አገልግሎታችሁ፣ ጥሪያችሁና፡ ሀላፊነታችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታን ውደዱት፥ እርሱ የሰራውንም ውደዱ፤ ራሳችሁን!

    በሕይወታችሁ እያንዳንዱ ደቂቃ ደስ ይበላችሁ፡፡ ራሳችሁንና አካባቢያችሁ ያሉትን ሰዎች አድንቁ፡፡ አእምሮዋችሁን በትክክለኛው አቅጣጫ ለማስኬድ ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ፤ በውጤቱ ትደነቃላችሁ፡፡ ለእግዚአብሔር ምርጥ ናችሁ፡፡

    ሰዎች ስለናንተ እንደሚናገሩት አርጋችሁ ራሳችሁን አትመልከቱ፤ ዋናው ነገር እግዚአብሔር ስለናንተ የሚያስበው ሃሳብ ነው፡፡

    የተባረክ አባት ሆይ፥ የክብርህና የፀጋህ መገለጫ ስለሆንኩኝና ጽድቅህ በእኔ ውስጥና በኩል ስለተገለጠ አመሰግንሃለሁ፡፡ በክርስቶስ ያገኘሁትን የድል ሕይወት እያሰብኩኝና፡ ባገኘሁት የርስት ክብር እየተደሰትኩኝ፡ የመለኮቱን በጎነትና ፍጹምነት አሳያለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን!

    ጸሎት

  • amharic

    ዘጸአት 25:8 ላይ እግዚአብሔር በሕዝቡ መሃከል ማደር እንደሚፈልግ ግልጽ አርጓል፡፡ “በመካከላቸውም አድር ዘንድ” ልብ በሉ ለጉብኝት አይደለም “ . . .መቅደስ ይሥሩልኝ” ብሏል፡፡ “እንድጎበኛቸው” እንዳላለ ልብ በሉ፤ እንዲጎበኛቸው አይደለም፡፡ ያለው፡- “በመካከላቸው አድር ዘንድ” ነው፡፡

    ሙሴ የእግዚአብሔርን መመሪያ ታዞ፡ እግዚአብሔር በሰጠው ንድፍና ዕቅድ መሠረት፡ እስራኤላውያን ውብ የሆነ ቤተ መቅደስ ለመስራት የሚያስፈልገውን አስፈላጊ ነገር ሁሉ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ያ፡ ጌታ የሚፈልገውን ያህል መልካም አልነበረም፡፡ እግዘአብሔር አዲስ ቤተ መቅደስ ፈለገ፤ እርሱንም በራዕይ ለዳዊት አሳየው፤ የአሰራሩንም ዝርዝር ሰጠው፡፡

    ዳዊትም ደስ ብሎት ለቤተ መቅደሱ ህንፃ ማሰሪያ ብዙ ወርቅና ብር ሰጠ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር፡ ልጁ ሰለሞንን ነበር ቤተ መቅደሱን እንዲሰራ የፈለገው፤ ስለዚህም ሰለሞን ለእግዚአብሔር እፁብ ድንቅ የሆነን ቤተ መቅደስ ሰራ፡፡ አሁንም ግን እግዚአብሔር አልረካም፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ነገር ግን. . . ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም፡፡” (የሐዋሪያት ሥራ 7:48)

    ኢየሱስ ሲመጣ እንዲህ አለ፡- “. . . በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም፡፡” (ማቴ 16:18) “ቤተ ክርስትያን” ተብሎ የተተረጎመው ቃል “የተጠሩ ሰዎች ስብሰባ ወይም ጉባዔ” ማለት ነው። ግዑዝ አካልን የያዘ ሕንጻ አይደለም ማለት ነው፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር የተመረጠና የተጠራ ሕይወት ያለው ሰዋዊ ቤተ መቅደስ ነው፡፡

    ኤፌሶን 2:21-22 NIV እንዲህ ይላል፡- “እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም፡፡ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ በእርሱም ሕንጻ ሁሉ

    የሚኖረውና የሚመላለሰው በእኛ ውስጥ ነው

    ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ

    አታውቁምን? (1 ቆሮንቶስ 6:19)

    ረቡዕ 10

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 12:22-48 & መጽሀፈ መሳፍንት 9

    የማርቆስ ወንጌል 1:1-13 & ኦሪት ዘሌዋውያን 10

    ኦሪት ዘሌዋውያን 26:11-12; የሐዋርያት ስራ 7:44-49; ቆላስያስ 1:26-27

    እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤ በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ፡፡” እኛ በመንፈስ የእግዚአብሔር መኖሪያ ነን! በሰዎች መካከል ለመኖር የነበረው ራዕይ እውን ሆኗል፡፡

    2 ቆሮንቶስ 6:16 እንዲህ ይላል፡- “. . . እኛ የሕያው እግአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፡- በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፡፡” እያንዳንዳችን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ነን፡፡ በእኛ ውስጥ ይኖራል ይመላለሳልም፡፡ ምድር ሲመሰረት ጀምሮ የነበረው የእግዚአብሔር ህልም አሁን ተፈፅሟል፡፡ ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረው ሚስጥር አሁን ተገልጧል፥ ሆኗልም፡፡ ሚስጥሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው፡፡ (ቆላስይስ 1:26-27) ሀሌሉያ!

    ውድ አባት ሆይ፥ አመልክሃለሁ፡ እወድሃለሁ፥ ማደርያህ ስላደረከኝ ተመስገን፡፡ በውስጤ ለሚኖረው፣ ለሚጠብቀኝና፣ ወደ ፍፁም ፈቃድህ ለሚመራኝ መንፈስህ ዕውቅናን እሰጣለሁ፡፡ ክቡር በሆነው መገኘትህ ሕይወቴን ስላስዋብከው አመሰግንሃለሁ፥ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

    ጸሎት

  • amharic

    በእምነት ጉዞዋችን ውስጥ አንዳንዴ ዕምነታችንን የሚፈታተኑ ከባድ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጤናችሁን ወይም ገቢያችሁን በተመለከተ ሊሆን ይችላል፤ ማድረግ ይገባኛል ብላችሁ ያሰባችሁትን ሁሉ አድርጋችኋል፥ የምታውቋቸውንም መርሆዎች ሁሉ ተጠቅማችሁ ምንም ለውጥ አልመጣም። አሁን በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እያሰባችሁ ነው፡፡

    በመጀመሪያ ወንጌልንና የእግዚአብሔርን ልጆች ሊቃወም የወጣ ጠላት እንዳላችሁ መገንዘብ ይገባችኋል፡፡ 1 ጴጥሮስ 5:8-9 እንዲህ ይላል፡- “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፡፡” ከዛም በመቀጠል ኤፌሶን 6:10-11 እንዲህ ይላል፡- “በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ፡፡”

    ጠላታችሁ ሰይጣን ተሸ ንፏል፥ ምንም ጉልበት የለውም፡፡ የሚንቀሳቀሰውና ያለው ነገር ቢኖር ማታለልና ማሞኘት ነው፡፡ ቃሉ እንደሚናገረው አስቀድማችሁ አሸንፋችሁታል፡፡ “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና፡፡” (1 ዮሐንስ 4:4) ከእናንተ የሚጠበቀው ቃሉን ማድረግ ነው፤ ኤፌሶን 6:10-11 ላይ ያነበብነውን ተግባራዊ በማድረግ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ፡፡

    የጦር ዕቃውን ሁሉ ያልለበሱት በቀላሉ ይጎዳሉ፡፡ ኤፌሶን 6፡12 ለምን የጦር ዕቃውን ማድረግ እንዳለብን ያሳውቀናል፡፡ እንዲህ ይላል፡- “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ፡፡”

    ጠላታችሁ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ቃል እውነት ዞር ሊያረጋችሁ ይሞክራል፤ ራሳችሁን ጭንቀት ውስጥ እንድትቀብሩና በቃሉ ላይ ተስፋ

    የማትረበሹ ሁኑ፤ ድል ማድረጋችሁን ቀጥሉ

    የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ (2 ቆሮንቶስ 10:4)

    ሐሙስ 11

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 12:49-59 & መጽሀፈ መሳፍንት 10-11

    የማርቆስ ወንጌል 1:14-28 & ኦሪት ዘሌዋውያን 11

    2 ኛ ቆሮንጦስ 2:14; 1 የዮሐንስ ወንጌል 5:4; 1 ኛ ጴጥሮስ 5:8-9

    እንድትቆርጡ ሊያረጋችሁ ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ተስፋ መቁረጥን እምቢ በሉ፤ ይልቁንስ ቃሉ የሚላችሁን አድርጉ፤ ዲያቢሎስን ተቃወሙት፡፡ ያዕቆብ 4:7 እንዲህ ይላል፡- “. . . ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤” የዮሐንስ ራእይ ደግሞ እንዲህ ይላል፡- “እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም፡፡”

    ጠላት ምንም ዓይነት ነገር ቢወረውርባችሁ አትረበሹ፤ ድል ማድረጋችሁን ቀጥሉ፡፡ በክርስቶስ ያገኛችሁትን ማንነትና፡ መቼም በማይወድቀው ቃሉና፡ ሃይሉ ላይ ያላችሁን ታላቅ እምነት፡ ያለ ማቋረጥ አውጁ፡፡ የዛኔ ሁሌም ታሸንፋላችሁ፡፡

    ካሸናፊዎች እበልጣለሁ፤ ሰይጣንን፣ ዓለምንና ስርዓቶቹን ሁሉ አሸንፍያለሁ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፡ በመለኮታዊ ርስቴ ብርሃን ውስጥ በመመላለስ በሕይወት ላይ ነግሻለሁ፡፡ ሁሉም የኔ ነው፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ ሀሌሉያ!

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    የአንድ ቤት ባለቤት ብትሆኑና ለተወሰነ ጊዜ ለአንድ ሰው በኮንትራት ብትሰጡት፡ የእናንተው ሆኖ ይቀጥላል፤ ነገር ግን ኮንትራት በሰጣችሁበት ጊዜ ቤቱን ልታስተዳድሩት አትችሉም፡፡ የተከራየው ሰው ለዛን ጊዜ በኮንትራቱ መሠረት እንደ ባለቤት ሆኖ ያስተዳድረዋል፡፡

    ልክ እንደዛው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ነው ለጊዜው ዓለምን እንድያስተዳድሩ የሰጠው፥ እርሱ ሊያስተዳድረው አይችልም፡፡ ዓለምን የማስተዳደሩን ስልጣን ለሰው ሰጥቷል፡፡ እርሱ ይህን ዓለም የሚያስተዳድርበት ጊዜ ይመጣል፥ እስከዛ ድረስ ግን እናንተና እኔ ነን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ዓለም ለማስተዳደር መለኮታዊ ሃላፊነት የተሰጠን፤ እናም ዓለማችንን ያስተዳደርንበትን ሁኔታ በተመለከተ ተጠያቂዎች ያደርገናል፡፡

    ብዙዎች የተወሰኑ ክርስትያኖንችም ጨምሮ ድርጊቶችንና ሁኔታዎችን እየመረመሩ፡ ለምንድነው እግዚአብሔር ነገሮችን የማያስተካክለው ብለው ያስባሉ፡፡ እግዚአብሔር እንድያስተካክል ከጠበቃችሁ ተሳስታቸኋል፡፡ እናንተ ታስፈልጉታላችሁ፡፡ ዘመኑ እስኪያልቅ ድረስ ያለናንተ ምንም ነገር አያደርግም፡፡ እስከዚያን ቀን ድረስ ግን እኛ ነን ይሄንን ዓለም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መግዛት አለብን፡፡

    እንዲህ አርጋችሁ ተመልከቱት፤ እግዚአብሔር ዓለሙ ሁሉ እንዲድን ይፈልጋል፥ ለዛም ነው ኢየሱስን ለሰዎች መዳን ሕይወቱን አሳልፎ እንዲሰጥ የላከው፥ ሆኖም ግን ለጠፉት መጸለይ እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ለምንድን ነው እንድንጸልይላቸው የሚፈልገው? ለምን በቀላሉ ህጋዊ መዳናቸውን የሚለማመዱት የሕይወት መዳን አያረግላቸውም? በሰው በኩል ነው ይህንን የማድረግ መብት የሚያገኘው፥ ስለዚህም ነው እንድንጸልይ የነገረን፡፡

    ስለዚህ የተፈጠራችሁበትን ምክንያት ለመፈጸም ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሽ በመሆን ያገኛችሁትን ቦታ ያዙ፡፡ ሮሜ 8:19-21 እንዲህ በማለት

    ዓለምን የሚያስተዳድረው በእናንተ ነው

    የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት፡፡ (መዝሙረ ዳዊት 115:16)

    አርብ 12

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 13:1-21 & መጽሀፈ መሳፍንት 12-13

    የማርቆስ ወንጌል 1:29-39 & ኦሪት ዘሌዋውያን 12

    ትንቢተ ኢሳያስ 53:10; ፈልጵሱዮስ 2:13; መዝሙረ ዳዊት 115:15-16

    ግልፅ አርጎ ያስረዳል፡- “የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና፡፡ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው፡፡”

    አብ ፍጥረቱን ከሙስና ባርነት አውጥተን፡ ክቡር ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ልጆች ነጻነት እንድንወስድለት እኛን ነው የሚጠብቀው፡፡

    ውድ አባት ሆይ፡ ክርስቶስ በምድር ላይ ያለውን ጊዜ እያራዘምኩኝ ያለሁኝ የክርስቶስ ዘር ነኝ፤ በውስጤ ስለሚሰራው ሀይልህ፣ በእኔ ውስጥና፡ በእኔ በኩል እየተገለጠ ስላለው ክብርህ አመሰግንሃለሁ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሀይልና፡ በወንጌል አማካኝነት፡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን በክርስቶስ ወደሚገኘው ርስት የማምጣት ሀላፊነቴን እወጣለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

    ጸሎት

  • amharic

    ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮማዊያን ክርስቲያን ለአገልግሎት ለመሄድ ባቀደ ጊዜ የወንጌል በረከት ሙላት በእርሱ ውስጥ እናዳለ እና ከእርሱም ጋር እንደሆነ ተረድቶ ነበር:: ይህ በጣም አስደናቂ ነው:: አንዳንዶች “በምድር ላይ እስካላችሁ ድረስ የእግዚአብሔር በረከት ሙላትን ልትለማመዱ አትችሉም ይላሉ” ነገር ግን ቃሉ የሚለው ይህንን አይደለም:: ጳውሎስ በወንጌል በረከት ሙላት ውስጥ ይመላለስ ነበር:: ስለ ክርስቶስ ያላችሁ ንቃተ ህሊና ይወስነዋል:: ህይወቱ እና ኃይሉ በእናንተ ውስጥ:: ሃሌሉያ!

    የሕያው እግዚአብሔር ታላቅነት እና ገደብ የሌለው ጥበቡ እና ኃይሉ በእናንተ ውስጥ እንዳለ መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው:: ሐዋሪያው ጳውሎስ በቃሉ ላይ እንደዚህ አይነት አዎጅን ለማወጅ ደፋር እምነት ነበረው:: እርሱ በክርስቶስ የወንጌል በረከት ሙላት ይራመድ ነበር እናም በሮም ያሉትን ክርስቲያኖችን ሲጎበኝ መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንደሚያካፍላቸው ተስፋ ነበረው::

    ይህ አሁን ለእናንተ ምን ማለት ነው? በክርስቶስ የወንጌል በረከት ሙላት እንዳላችሁ እና በዛም መመላላለስ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ? ይህን መረዳታችሁ ወይም ስለዚህ ነገር ያላችሁ ግንዛቤ ህይወታችሁን ሙሉ በሙሉ ይለውጠዋል:: ጴጥሮስም ይህንን ተረድቶ በዛም ይመላለስ ነበር:: በ(2ኛ ጴጥሮስ 1: 4) ላይ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች ነን ብሎ ማወጁ የማያስገርመው ለዚህ ነው:: እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ያለን ነን እናም በዚህ ንቃተ ህሊና መኖር አለብን::

    ዮሐንስ ለቤተክርስቲያን ሲጽፍ እንዲህ አለ “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና” (1ኛ ዮሐንስ 4:4)። እነዚህ ሰዎች በክርስቶስ የወንጌል

    የእግዚአብሔር የበረከት ሙላት አላችሁ

    ወደ እናንተም ስመጣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንድመጣ አውቃለሁ። (ሮሜ 15:29)

    ቅዳሜ 13

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 13:22-35 & መጽሀፈ መሳፍንት 14-16

    የማርቆስ ወንጌል 1:40-45 & ኦሪት ዘሌዋውያን 13

    የዮሐንስ ወንጌል 1:16; ኤፌሶን 1:3; 2 ኛ ጴጥሮስ 1:3

    በረከት ሙላት ውስጥ መመላለስ ምን ማለት እንደሆነ ተረድተዋል፤ ክርስቶስ ማን እንዳደረገን ተረድተው ነበር እናም እርሱንም ይናገሩ እና ይኖሩት ነበር:: መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቶስ ሲናገር “እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን” ይላል:: ክርስቶስን ስትቀበሉ የእግዚአብሔርን የበረከት ሙላት ተቀበላችሁ ምክንያቱም ክርስቶስ ሁሉ ነገር ነው! በእናንተ ውስጥ ያለውን ክርስቶስን እወቁት::

    እኔ ከመለኮት ባህሪ ተካፋይ ስለተደረኩ የእግዚአብሔርን የበረከት ሙላት ተቀብያለሁ:: እኔ የእግዚአብሔር ወራሽ ነኝ፥ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሽ ነኝ:: ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ሁሉ ነገሬ ነው:: እኔ ከአሽናፊዎች በላይ ነኝ በህይወት ነገር ሁሉ ላይ በጽድቅ እና በጸጋ እየገዛሁ:: እግዚአብሔር ይባረክ!

    ጸሎት

  • amharic

    እንደ እግዚአብሔር ልጅ፥ ፈጽሞ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ፈጹሞ ብቻችሁን ልትራመዱ አትችሉም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ አለ:: ሁልጊዜ በእናንተ ውስጥ ከእናንተ ጋር ይኖራል:: በህይወታችሁ ውስጥ ካለው የእርሱ አገልግሎት ውስጥ አንዱ ከእናንተ ጋር ህብረት ማድረግ፥ የእግዚአብሔርን ፍቃድ እንድታደርጉ እና ጥሪያችሁን እንድትፈጽሙ በእምነት ማበርታት እና በውስጣችሁ ድፍረትን ማነሳሳት ነው::

    በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እና ስራ በውስጣችሁ ለመኖሩ እና ለዘላለማዊ መገኘቱ እውቅና እና ክብር በመስጠት አበረታቱ:: ለወንጌል ስርጭት ስትወጡ፥ ክርስቶስን ለሌሎች ስትመሰክሩ እርሱ ከእናንተ ጋር እንደ ሆነ እወቁ:: ቃሉን ስታገለግሉ እና ስታካፍሉ ምናልባት ሰውየውን ከላይ ልታናግሩት ትችላላችሁ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በዛ ሰው ልብ ውስጥ በማጽናት ከውስጥ ያገለግለዋል:: እንደ እረዳታችሁ ከእናንተ ጋር አብሮ ያገለግላል::

    ኢየሱስ እንደተናገረ ሁል ጊዜ በእናንተ ውስጥ ያለውን ለእርሱን መገኘት እና ስራ እውቅና ስጡ:: በዮሐንስ 14:10 ላይ ኢየሱስ እንዲህ አለ “. . .ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል”:: አብ መንፈስ ቅዱስን በመመሰል በእርሱ ውስጥ እንዳለ እና በእርሱ ውስጥ እና በእርሱ በኩል እንደሚሰራ እውቅና ሰጠ:: መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ማለት መሪያችሁ እና ጠባቂያችሁ አብ በእናንተ ውስጥ ማለት ነው:: በህይወታችሁ

    በእናንተ ውስጥ ላለው መገኘቱ እና አገልግሎቱ እውቅና ስጡ

    . . . እርሱ ራሱ [እግዚአብሔር] በምንም ሁኔታ አልጥልህም፥ በአንተ ተስፋ አልቋርጥም ወይም ያለ እርዳታ አልተውህም:: በምንም መልኩ ያለ እርዳታ በፍጹም ከቶ

    አልጥልህም ወይም አልተውህም።(እኔ ይዜሃለሁና ተረጋጋ) (ዕብራውያን 13:5 AMPC ትርጉም)

    እሁድ 14

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 14:1-24 & መጽሀፈ መሳፍንት 17-18

    የማርቆስ ወንጌል 2:1-12 & ኦሪት ዘሌዋውያን 14

    የማቴዎስ ወንጌል 28:19-20; የዮሐንስ ወንጌል 14:26

    እርሱን እማኑት:: እርሱ ልታገኙ ከምትችሉት በላይ የልብ ጓደኛችሁ እና እረዳታችሁ ነው::

    አሁን በህይወታችሁ ምናልባትም በገንዘባችሁ፥ በጤንነትችሁ፥ በትምህርታችሁ፥ በትዳራችሁ፥ በንግዳችሁ ወይም በስራችሁ ላይ ተግዳሮት ካለ አትደንግጡ መንፈስ ቅዱስን እመኑት:: ትኩረታችሁን እና ተስፋችሁን በእርሱ ላይ አድርጉ፥ እርሱ ፈጹሞ አይጥላችሁም:: እርሱ ለእናንተ ያለውን የመተማመኛ እና የማጽናኛ ቃል በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ በድጋሚ አንብቡ እና ሽክማችሁን አራግፉ:: “. . . እርሱ ራሱ [እግዚአብሔር] በምንም ሁኔታ አልጥልህም፥ በአንተ ተስፋ አልቋርጥም ወይም ያለ እርዳታ አልተውህም:: በምንም መልኩ ያለ እርዳታ በፍጹም ከቶ አልጥልህም ወይም አልተውህም (እኔ ይዜሃለሁና ተረጋጋ) . . .” ::

    በእኔ ውስጥ ከሚኖረው እና ከሚሰራው ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ እኔ በህይወት አሸናፊ ነኝ:: የእርሱን በህይወቴ ውስጥ መገኘት እና መስራት እውቅና ሰጣለሁ እንዲሁም ለዘላለማዊ የስኬት እና ያለገደብ የማደግና ድል የማግኘት ህይወት ዋስትናዬ እርሱ ነው ብዬ አውጃለሁ:: በኢየሱስ ስም:: አሜን::

    ጸሎት

  • Te ¨h

    Te ¨

    h

    amharic

  • Te ¨h

    Te ¨

    h

  • amharic

    መጽሐፍ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ያሳየውን ከመጠን በላይ ስለሆነው የአብ ፍቅር ይናገራል:: ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ለእኛ ሲል ሞተ ይህም በእኛ ላይ ያሳየው በጣም አስደናቂ ፍቅር ነው:: እርሱ የሞተልን በትክክል እየኖርን ስለ ነበር አይደለም፤ እርሱ የሞተልን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ነው:: ይህ አስደናቂ ፍቅር ነው እንዲሁም ዋጋችን ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል::

    ኢየሱስ ማን እንደሆነ እና ህይወቱን እናንተን ለማዳን እንደሰጠ ስታውቁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን እንደሚያስብ፥ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትረዳላችሁ:: የእርሱ የወኪልነት ሞት የእናንተን ዋጋ ይናገራል:: የእናንተ ዋጋ የእርሱን ህይወት ያህል እንደሆነ አስቦአል ስለዚህ ህይወቱን በእናንተ ቦታ አቀረበ:: ይህ የሚያሳየው እናንተ ልክ እንደ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር አስፈላጊ እንደሆናችሁ ነው:: ጌታ ኢየሱስ ወደ አብ ሲጸልይ በፍጹም ልቡ እርሱን በወደደው መጠን እኛን እንደ ወደደን አለም እንዲያውቅ የፈለገው የማያስገርመው ለዚህ ነው (ዮሐንስ 17:23)::

    እናንተ ህይወት እንዲኖራችሁ ኢየሱስ ህይወቱን እንደሰጠን ማወቅ እንዴት የሚያበረታታ ነው:: አሁን ልትኖሩበት የሚገባው ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ ሕይወት ነው፥ የእርሱን ዓላማ ኑሩ:: ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ በድፍረት “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” ብሎ አወጀ።

    ያነሰ ኑሮ አትኑሩ:: የእግዚብሔርን ዓላማ ኑሩ:: እናንተ ዋጋ እንዳላችሁ

    እውነተኛ ዋጋችሁ ተወስኖአል

    ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።

    ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። (ሮሜ 5: 8-9)

    ሰኞ 15

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 14:25-15:1-10 & መጽሀፈ መሳፍንት 19-21

    የማርቆስ ወንጌል 2:13-22 & ኦሪት ዘሌዋውያን 15

    ኤፌሶን 3:17-19; 1 የዮሐንስ ወንጌል 4:8-10

    እርሱ ያስብባል ስለዚህም እራሱን ለእናንተ ሰጠ:: 1ኛ ጴጥ 1: 18-19 እንዲህ ይላል “ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።”

    የተወደድክ አባት ሆይ፥ ስለማይወድቀው ፍቅርህ አመሰግንሃለሁ፤ ፍቅርህ እንደ ጋሻ በዙሪያዬ ይከበኛል እናም በዘላለም መደላደል እና ደስታ እኖራለሁ:: ይህ ፍቅር ወንጌልን ለጠፉት ሰዎች እንድሰብክ እናም ከኃጥያት ወደ ጽድቅ እንዲሁም ከሰይጣን ኃይል ወደ እግዚአብሔር ኃይል እንድመልሳቸው ግድ ይለኛል:: በኢየሱስ ስም:: አሜን::

    ጸሎት

  • amharic

    ጌታ ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አላቸው “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም”። ቀጥሎም እንዲህ አለ “ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል”:: ኢየሱስ ጥልቅ የሆነውን እውነት፥ ሚሥጢራት እና ስለ እግዚአብሔርና ስለ መንግስቱ የሆነ መገለጥ መንፈስ ቅዱስ እንዲያስረዳን ለእርሱ ሰጠ:: የተሰወሩ ሚስጥራትን እና የተፈጥሮ ሰው ሊረዳው የማይችለውን ሚስጥር እንዲሁም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን የሚገልጽልን መንፈስ ቅዱስ ነው::

    1ኛ ቆሮንቶስ 2:9-12 እንዲህ ይላል “ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።” መንፈስ ቅዱስን እንድንቀበል ያደረገን እግዚአብሔር ይመስገን!

    ለእኛ እግዚአብሔር በነጻ የሰጠን ነገሮች አሉ እናም መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች ይገልጽልናል እንዲሁም እንድንጠቀማቸው ይረዳናል:: ብዙዎች መንፈስ ቅዱስን ችላ በማለት በህይወት እግዚአብሔር ያዘጋጃቸውን ነገሮች ሁሉ ሳያጣጥሙ ይቀራሉ:: አንዳንዶቹም እግዚአብሔር ደስ እንዲሰኑበት ታላቅ ህይወት እንደሰጣቸው እንኳን አያውቁም:: ከእግዚአብሔር ምንም እንዳልተሰጣቸው በጨለማ፥ በችግር ህይወት ውስጥ ይመላለሳሉ::

    የእግዚአብሔርን ጥልቅ ሚስጥር ገላጭ

    ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል . . . (ዮሐንስ 16:13)

    ማክሰኞ 16

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 15:11-32 & መጽሀፈ ሩት 1-4

    የማርቆስ ወንጌል 2:23-28 & ኦሪት ዘሌዋውያን 16

    የዮሐንስ ወንጌል 14:26; 2 ኛ ጴጥሮስ 1:20-21; 1 ኛ ቆሮንጦስ 2:9-12 NIV

    መንፈስ ቅዱስ ያለው ማንም ሰው በጨለማ ወይም እርግጠኛ ባለመሆን መመላለስ የለበትም:: እርሱ የህይወት ብርሃን ነው:: በእርሱ ብርሃን እግዚአብሔር የባረካችሁን ሁሉ ትመለከታላችሁ እንዲሁም በክርስቶስ ባላችሁ ውርስ ብርሃን መመላለስ ትችላላችሁ:: ሙሉ ህይወት፥ ጽድቅ፥ መለኮታዊ ጤንነት፥ ብልጽግና፥ የኃጢያት ስርየት፥ ከአብ ጋር ያለ ህብረት ወዘተ በነጻነት እንድትደሰቱበት እግዚአብሔር ከሰጣችሁ በረከቶች አንዳንዶቹ ናቸው:: ነገር ግን እነዚህን በረከቶች ለእናንተ የመግለጥ ብቻ ሳይሆን እንዴት በእነሱ መመላለስ እንደምትችሉ የማስተማር አገልግሎት የመንፈስ ቅዱስ ነው::

    መንፈስ ቅዱስ አስተማሪዬ እና መሪዬ ነው፥ በህይወት በልቀት እንድመላለስ የመንፈሳዊ እውነታዎችን መረዳት እየሰጠኝ ልቤን በጥበብ ያጥለቀልቀዋል:: ዛሬ እኔ ከእርሱ ጋር አንድ መሆኔን በመረዳት እመላለሳለሁ እንዲሁም በክርስቶስ ስላለኝ የአዲስ ህይወት ሚስጥራትን በጥልቅ ማስተዋል እቀበላለሁ::

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    ረቡዕ 17

    በቆላስይስ 1:9 ላይ ጳውሎስ በመንፈስ ሲጽልይ “ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም።” “አእምሮን” የሚለው ቃል የተተረጎመው ከግሪኩ “ሰንሲስ” የሚል ቃል ነው፤ ትርጓሜውም የአስተሳሰብ ሁኔታ፥ ነገሮችን የምንረዳበት መንገድ ማለት ነው:: ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ ውስጥ እግዚአብሔር የተሰጠን የመረዳት ችሎታ ማለትም የመገለጥ ማስተዋልን ይናገራል::

    በመረዳት በማጥናት በእግዚአብሔር ቃል ላይ መቆም ያለብን ለዚህ ነው:: የመክፈቻ ጥቅሳችንን እንደገና አንብቡ “የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ . . .” ይላል:: ይህ በመንፈሳዊ ብልህ፥ አስተዋይ እና ጥበበኛ ያደርጋቹኃል::

    ሌላው የዚህ ውብ ነገር እግዚአብሔር እያሳደገን ያለው ለዚህ ዓለም ብቻ አይደለም፤ በውስጣችን እየሰራ እና በቃሉ እያሰተካከለን ያለው ለሚመጣም ዓለም ጭምር ነው:: አሁን በዚህ ዓለም እያላችሁ ቃሉ በውስጣችሁ ከሌለ፥ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ መረዳትን ካልሰጣችሁ፥ የመንግስቱን እውነታዎች ካለተረዳችሁ በሚመጣው ዓለም እንዴት ልትኖሩ ትችላላችሁ?

    ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን በደስታ ማጥናት በጣም ያስፈልጋል፤ ለቃሉ ታላቅ እና የማይጠግብ ፍላጎት ይኑራችሁ:: የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ነገር ነውና ለቃሉ እራሳችሁን ስጡ:: በዚህ ዓለም የምትፈልጉት ነገር ምንም ግድ አይልም ቃሉ በእናንተ ውስጥ ካለ የምትሹትን ልታገኙ ትችላላችሁ!

    ቃሉ በመንፈሳችሁ ውስጥ

    የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ። በመዝሙርና በዝማሬ

    በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። (ቆላስይስ 3:16)

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 16 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1-2

    የማርቆስ ወንጌል 3:1-7 & ኦሪት ዘሌዋውያን 17

    የሐዋርያት ስራ 20:32; ኤፌሶን 1:17-18

    የእግዚአብሔር ቃል በመንፈሳችሁ ውስጥ እና በአንደበታችሁ ስትናገሩት በዘመናት ሁሉ ጌታን በታማኝነት ታገለግሉታላችሁ እንዲሁም ክብርን ለእርሱ ታመጣላችሁ

    እኔ በጽድቅና በመግዛት እመላለሳለሁ:: የእግዚአብሔርን መንግስት ምስጥራት እና የረቀቁ ነገሮችን መረዳት አለኝ:: እኔ ከዓለም እና ከወደቀ ስርዓቷ በላይ ሆኜ እኖራለሁ:: እኔ በክርስቶስ እና በእርሱ ዓለም ስርዓት እኖራለሁ:: ሃሌሉያ!

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    እግዚአብሄር ትልቁ ምኞት ሰዎች ሁሉ የዘላለም ህይወትን ተቀብለው ወደእራሱ ህብረት እንዲመጡ ማድረግ መሆኑን ከቃሉ በግልጽ ማየት እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ አለም የመጣበት ምክንያትም ይሄው ነው፤ ሰዎችን የእግዚአብሄር ልጆች ለማድረግ፡፡ ስለሆነም በህይወት ቅድሚያ የምትሰጡት ነገር ከዚህ ጌታ ከመጣበት አላማ ጋር የሚስማማ መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ወንጌልን ከማስተዋወቅ ስራ አትቆጠቡ፡፡ ኢየሱስ የኖረው፤ የሞተው እንዲሁም በትንሳኤ የተነሳው ለዚሁ አላማ ነውና፡፡

    ነፍሳትን ቅድሚያ ስራቸው የሚያደርጉ ሰዎችን፤ የእግዚአብሄርን ህልም የራሳቸው ህልም የሚያደርጉ ሰዎችን ሰማይ እውቅናና ክብር ይሰጣቸዋል፡፡ ከወንጌልጋር ማለትም ነፍሳትን ከማዳን ጋር ያልተያያዘ ማንኛውም በዚህ ምድር ላይ የምንሰራው ስራ በሰማይ ትርጉምና ዋጋ የለውም፡፡ ሰዎችን ወደክርስቶስ ለማምጣትም ሆነ በቤቱ ጸንተው እነርሱ እራሳቸው ነፍሳትን እንዲያድኑ የማድረግ ሀላፊነት አለባችሁ፡፡

    እምነታቸውን እንድታሳድጉላቸው፤ ጸሎት እንድታስተምሯቸው፤ በክርስቶስ ያላቸውን እርስት እንዲያውቁና እንዲኖሩበት በመንገዳችሁ ላይ የሚያመጣቸው ሰዎች አሉ፡፡ ይህንን ማድረግ በክርስቶስ ወንጌል የተጣለባችሁ የሀላፊነታችሁ አንድ ክፍል ነው፡፡ የዳናችሁት ሌሎችን ለማዳን ነው፤ የታነጻችሁት ሌሎችን ለማነጽ ነው፤ የማስታረቅ አገልግሎት ተሰጥቷችኋል፡፡ “ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ

    የእርሱን ህልም ህልማችሁ አድርጉት

    ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።

    (2 ጴጥ 3፡9)

    ሐሙስ 18

  • Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

    ለተጨማሪ ጥናት:

    የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    የሉቃስ ወንጌል 17:1-19 & መጽሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 3-7

    የማርቆስ ወንጌል 3:8-19 & ኦሪት ዘሌዋውያን 18

    1 ኛ ቆሮንጦስ 9:16; ፈልጵሱዮስ 1:12-14

    ቃል አኖረ።” 2 ቆሮ 5፡19ሁላችንም ሀላፊነታችንን በሙሉ አቅማችን ብንወጣ ኖሮ ምን

    ያህል ያልዳኑ ሰዎች ይድኑ እንደነበር ልብ በሉ፡፡ ይሄንን በቁም ነገር አስተውሉት፡፡ ሌሎች ቅዱሳን የተቀደሰውን አገልግሎት እንዲያገለግሉ ከሚያበረታቱ መሀከል ሁኑ፡፡ ዘላለማዊ ዋጋ ለሌለው ጊዜያዊ አላማ አትኑሩ። በህይወታችሁ የእግዚአብሄር ስራ የመጀመሪያ ይሁን፡፡ ህልሙ ህልማችሁ ይሁን፤ ያኔ ዘላለማዊ ደሰታና እርካታ ታገኛላችሁ፡፡

    የተባረክህ አዳኛችን ሆይ፤ ህይወቴ ላንተ ክብር ነው፡፡ ለመንግስትህ መስፋትና ጽድቅህ በሰዎች ልብ ውስጥ ሁሉ እንዲተከል አጥብቄ እየፈለግሁ ለወንጌል አላማ እኖራለሁ፡፡ ሌሎች ቅዱሳን በአገልግሎታቸው ውጤታማ እንዲሆኑና የተቀደሰውን አገልግሎት እንዲያገለግሉ ከሚያበረታቱ መሀከል ነኝ፡፡ ስለሆነም ዘላለማዊ ደሰታና እርካታ እለማመዳለሁ፡፡

    የእምነት አዋጅ

  • amharic

    ምናልባት ይህን በእኛ ምትክ ኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት እንደሆነ የሚገልጸውን ውብ ዝማሬ ታውቁት ይሆናል እንዲህ ይላል፦ “የሌለበትን ዕዳ ከፈለ፥ ልከፍለው የማልችለው ዕዳ ነበረብኝ፤ አንድ ሰው ኃጢአቴን እንዲያጥብልኝ የሚያስፈልገኝ ነበርኩ: አሁን ግን አስገራሚ ጸጋ የሚልን አዲስ ዝማሬን ዘምራለሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ልከፍለው የማልችለውን ዕዳዬን ከፈለ . . .” አዎ በእርግጥም እርሱ የኃጢአታችን ቅጣት ሁሉ ከፈለ!

    አዳም እግዚአብሔርን ሳይታዘዝ ሲቀር ቅጣቱ መንፈሳዊ ሞት ነበር (ዘፍጥረት 2:17)፤ ይህም መሉ