ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

38
ማማማ ማማማማ ማማማማ ማማማ ማማማ ማማማ ማማማማማማ ማማማማማማማ

Transcript of ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

Page 1: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ማገዶ ቁጠባና የምርጥማገዶ ቆጣቢምድጃ

አመራረትና አጠቃቀም፡፡

Page 2: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ዓላማ

ዋና ዓላማ ፡ የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን ምርትና ስርጭት እንዲስፋፋ በማድረግ ማገዶ ቁጠባንና የተፈጥሮ

ሀብት እንክብካቤ ግንዛቤ ለማሳደግ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ማገዝ ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማዎች የማገዶ ፍጆታን በመቀነስ የደን መራቆትን መግታት፣ ከደን መራቆት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የአፈር መሸርሸርን

መቀነስ ፣ የሕብረተሰቡን በተለይም የሴቶችንና የህፃናትን የስራ ጫና

ለመቀነስ እንዲሁምጤናቸውን ለመጠበቅ ፣ ሕብረተሰቡ ወደ ተሻለና ዘመናዊ የኑሮ ደረጃ እንዲሸጋገር

ለማስቻል ናቸው ፣

Page 3: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

በስልጠናው የሚዳሰሱ ነጥቦች

1. የግብርና የተፈጥሮ ሀብት መንደርደርያ ሀሳቦች ፣2. ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች ፣

3. የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም ዘዴዎች ፣

4. የምርጥ ምድጃ አገጣጠምና አጠቃቀም ፣

5. አነስተኛ ማገዶን በመጠቀም ማብሰል ፣

Page 4: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

1. የግብርና የተፈጥሮ ሀብትመንደርደርያ ሀሳቦች

የተፈጥሮ ሀብት ታዳሽና አላቂ በመባል በሁለትይከፈላሉ

* ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብት

ዕፅዋት ፣ እንሰሳት ፣ አፈር ፣ ውሀ ፣ የአየርንብረት

* አላቂ የተፈጥሮ ሀብት

ማዕድናት ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፣ ነዳጅ

Page 5: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የሀገራችን የሀይል ሚዛን (Energy balance) መረጃ

* …………………ባሕላዊ የሀይል ምንጭ93%

……………የእንጨት ማገዶ ... 76% ……………………… ኩበት 8.5% ………………የእርሻ ቃርሚያ . 7.5% ………………………ከሰል ..1% * ………………… ዘመናዊ የሀይል ምንጭ

7%

Page 6: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የኢትዮጲያ ደን አጠቃላይ ገጽታበ19 ኛው ምዕተ ዓመት መግቢያ ላይ 40 %

እንደነበር ጥናቶች ያረጋግጣሉ፣በ1955 ዓ. ም በተደረገ ጥናት ወደ 16 % ቀንሶ

እንደነበር ሲታወቅ ፣በ1970 ዎቹ መጀመርያ ላይ 3.5 % ብቻ መቅረቱ

በጥናት የተደረሰበት ሲሆን ፣ በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የደን ሽፋኑ

በመጠኑ በመጨመር ከ9-11% እንደደረሰ ጥናቶችያስረዳሉ

Page 7: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የደን መመናመን መንስኤዎቹ

* የህዝብ ቁጥር በየዓመቱ መጨመር ፣ * ለእርሻ ፣ለግጦሽና ለመኖርያ ቦታ ለማግኘት ፣

* የማገዶ እንጨት ፍላጎት ለማሟላት ፣ የደን መመናመን የሚያስከትሉት ተፅዕኖዎች

* የአፈር መሸርሸርና የእርሻ መሬቶች መበላሸት ፣

* የእርሻ ምርት ማሽቆልቆል ፣

* የመሬት ድርቀትና የበረሃማነት መስፋፋት ፣

* የአካባቢ አየር መዛባትና የምድራችን ሙቀት

መጨመር ፣

Page 8: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም
Page 9: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የደንና ተዛማች ችግሮችን ለማቃለል የሚረዱ መፍትሄዎች * ያለውን የተፈጥሮ ደን ተከታታይና የማያ ቋርጥጥቅም ሊሰጥ በሚችል መልኩ እንዲተዳደር ማድረግ ፣ * አሁን ላለውም ሆነ ለሚመጣው ትውልድ በቂ የደን ውጤቶችን ሊሰጥ የሚችል ሰው ሰራሽ የደን ልማት ማስፋፋት ፣ * የማገዶ አጠቃቀም ብኩንነትን ለመቀነስ የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ፣ * የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤን አስመልክቶ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ፣ * በቤተሰብ ምጣኔ ዙርያ ህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስጨበጥ ፣

Page 10: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

2. ማገዶ ቆጣቢምድጃዎች በሀገራችን ለእንጀራ መጋገርያ ከምንጠቀምባቸው

ምድጃዎች

የተለመዱት የ 3 ጉልቻ ምድጃ ፣ ምርጥና ጎንዜ የሚጠቀሱ

ናቸው፡፡ የባህላዊ 3 ጉልቻ ምድጃ ከማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች

በተነፃፃሪ ከፍተኛ ማገዶ ይጠቀማሉ ይህም የሆነው ከሚቀጣጠለው ማገዶ የሚገኛውሙቀት ባብዛኛው

ስለሚባክን ነው፡፡

Page 11: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ከምድጃዎችሙቀት እንዴት ይባክናል? * ማገዶውሙሉ ለሙሉ አለመንደድ ፣

* የጭስ ውስጥሙቀት ብክነት ፣

* በማብሰያውና በምድጃው አካላት የሚወሰድሙቀት

* ከማብሰያው ወደ አካባቢው የሚባክን ሙቀት ፣

Page 12: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም
Page 13: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የተሻሻለ ምድጃ አጠቃለይ ባህርያት

* የማገዶ ፍጆታን የሚቀንስ ፣

* ለተለያዩ የጪስና የሙቀት አደጋዎች የማያጋልጥ ፣

* ህብረተሰቡ ለሚያዘወትረው የማገዶ ዓይነት

ተስማሚ የሆነ ፣

* በተጠቃሚው ዘንድ ተቀባይነት ያለው ፣

Page 14: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የሙቀት ሀይል ብክነትን እንዴት መቀነስ ይቻላል? * እሳቱን መከለል ፣ * ወደ እሳቱ የሚገባውን አየር መመጠን ፣

* የእሳቱን ክፍል / ፋየር ቦክስ/ የውስጥ ከፍታበትክክል

መመጠን ፣

Page 15: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን መጠቀምየሚሠጠው

ጥቅም * በተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ

- የማገዶ ፍላጎት ይቀንሳል

- የተፈጥሮ ሀብት ይጠበቃል

- የመሬት ምርታማነት ይጨምራል

* በኢኮኖሚ ዘርፍ

- ለነዳጅ የሚወጣውን የውጪምንዛሪ ይቀንሳል

- የሥራ እድል ይፈጥራል

- ድህነትን ይቀርፋል

Page 16: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

…የቀጠለ

* በጤና ዘርፍ

- የማዕድ ቤት ውስጥ አየር በጭስ መበከልይቀንሳል

- የአይንና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችይቀንሳል

- የማዕድ ቤት ንፅህና ይጨምራል

* የኑሮ ሁኔታ መሻሻል

- የምግብ ማብሰል ስራ አመቺ ይሆናል

- የማዕድ ቤት ይዞታ ይሻሻላል

- ማገዶ ይቆጥባል

Page 17: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም
Page 18: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

3. የምርጥማገዶ ቆጣቢምድጃ አመራረትና አጠቃቀም ዘዴዎች የምርጥ ምድጃ በቤተሰብ ውስጥ ተሞክሮ ከ33-57%

ማገዶ እንደሚቆጥብ የተረጋገጠና በባህላዊ ማገዶ የሚሰራ የእንጀራ ምድጃ ነው፡፡

በማገዶነት እንጨት ፣ ቅጠል ፣ ጭራሮ ፣ እንጨት ቅጠል ድብልቅ እንዲሁም ሰጋቱራና የእርሻ ተረፈ ውጤቶችንም

በመጠቀም አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የምርጥ ምድጃ ዋና ዋና ጥቅሞች

* ማገዶ ስለሚቆጥብ የማገዶን ወጪ በመቀነስየዳነውን

ወጪ ለሌሎች የቤተሰብ አገልግሎት ማዋል ይቻላል

Page 19: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

…የቀጠለ

* ከነበልባል ወይም ከእሳት ወላፈን ይከላከላል፣

* ከእንጀራ መጋገር በተጨማሪ ውሃ ማሞቅ ምግብ

መቀቀልና ወጥመሥራት ያስችላል፣

* ከሦስት ጉልቻ በተሻለ ፍጥነት ይጋግራል፣

* ሴቶችና ህፃናቶችን ማገዶ ለመሰብሰብየሚያጠፉትን

ጊዜና ጉልበት ይቀንሳል፣

Page 20: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ምርጥን ለማምረት የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

* ፑምቼ ወይም ቀይ አሸዋ ወይም የወንዝ አሸዋ ፣ * ሲሚንቶ ፣ ውኃ ምርጥን ለማምረት የሚያስፈልጉ የሥራ ዕቃዎች

* ባለ 5 ሚሊ ሜትርና ባለ 3 ሚሊ ሜትር ከሽቦና

ከእንጨት የተሰራ ወንፊት ፣

* አካፋ ፣ ባልዲ ፣ ጋሪ ፣ የግንበኛ ማንኪያ ፣

የውኃ ማጠጫ ፣ አነስተኛ ብረት ወይም እንጨት

* ምድጃውን የማምረቻና ቅርጽ ማውጫሞልድ ፣

Page 21: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

…የቀጠለ

* ስፋታቸው 40 ሴ.ሜ. በ40 ሴ.ሜ. የሆኑ በዛ ያሉ

አነስተኛ ሳንቃዎች(ጣውላዎች) * የተቃጠለ ዘይት ወይም አመድ ምርጥን ለማምረት የምንከተለው የሥራ ሂደት

* ከፑምቼ ሲሰራ

1. በመጀመሪያ ተገቢውን ፑምቼ መምረጥ ፣ ከዚያምበ3ሚ. ሜ ወንፊት ማበጠር፣ ወንፊቱ ላይ የቀረውን አሸዋ

በድጋሚ በ5ሚ. ሜ ወንፊት ማበጠር፣ የቀረውን ለይቶማስቀመጥ፡፡

Page 22: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

…የቀጠለ

2. አሁን ሁለት መጠን ያላቸው አሸዋ አለን፡፡ እነዚህንበ3 እጅ ለአንድ እጅ በሚገባ ማደባልቅ (በ3ሚ. ሜ

ወንፊት ያለውን 3 እጅ በ5ሚ. ሜ ወንፊት ያለውን1እጅ)

3. ቀጥሎም የፑምቼውን ድብልቅ ከሲሚንቶ ጋር በ5 እጅ ለአንድ እጅ በደንብ ማደባለቅ( ከድብልቁ 5 እጅ

ከሲሚንቶ 1እጅ)፡፡4. ከዚያም ውሃ በትንሽ በትንሹ በማርከፍከፍ ማርጠብናማቡካት፡፡

5. የቅርጽ ማውጫውን የውስጥ ክፍል በተቃጠለ ዘይት ወይም አመድ መቀባት፡፡

Page 23: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

…የቀጠለ

6. ሞልዱን በእንጨት ጣውላ ወይም በላስቲክ ላይ በማሳረፍ የተቦካውን ድብልቅ በግንበኛ ማንኪያ በመጠቀም ቅርፅ

ማውጫ ሞልድ ውስጥ በመጨመር በእንጨት ወይም በብረት መጠነኛ ኃይል በመጠቀምመጠቅጠቅ፡፡

7. በመጨረሻም የተሰራው ቅርፅ እንዳይፈርስ ቀስ ብሎ ሞልዱን በእንጨት መታ መታ በማድረግ የቅርፅ ማውጫው

ላይ የሚገኙትን የብረት ዘንጎች ወይም ሽቦዎች በማላቀቅ የቅርጽ ማውጫውን ከተመረተው ምድጃ ክፍል በጥንቃቄ

መለየትና ማውጣት ነው፡፡

8. የተመረተውን ምድጃ በጣውላ ላይ እንዳለ እስከሚደርቅ ድረስ ከ4-6 ቀናት በጥላ ውስጥ እንዳለ ውሃ በየጊዜው

ይጠጣል ከዚያም በፀሀይ ላይ እንዲደርቅ መተው ይቻላል፡፡

Page 24: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

* ከቀይ አሸዋ ሲሰራ ቀደም ሲል ባየነው ቅደም ተከተል በተመሳሳይ መልኩ

ተገቢውን ቀይ አሸዋ መምረጥ ፣ ከዚያም በ3ሚ. ሜ እና በ5ሚ. ሜ ወንፊት ማበጠርና መለየት፣ ቀይ አሸዋ

ስንጠቀም የሚኖረው የድብልቅ መጠን 4፡1 ነው፡፡ ይህም 4 እጅ ቀይ አሸዋ ከ1 እጅ ሲሚንቶ ጋር

በማደባለቅ ይሆናል፡፡ ቀጣይ የአመራረት ሂደት ቀደም ሲል ከተገለፀው

በተመሳሳይ መልኩ በመከተል ከቀይ አሸዋ ምድጃውን ማምረት ይቻላል

Page 25: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

* ከወንዝ አሸዋ ሲሰራ የወንዝ አሸዋ በተቻለ መጠን ከጭቃና ከሌሎች

ቆሻሻዎች ንፁህ መሆን አለበት፡፡ የወንዝ አሸዋ ስንጠቀም የሚኖረው የድብልቅ መጠን

3፡1 ማለትም 3 እጅ ከወንዝ አሸዋ 1 እጅ ከሲሚንቶነው፡፡

ቀጣይ የአመራረት ሂደት ቀደም ሲል ከተገለፀው ተመሳሳይ ነው፡፡

Page 26: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም
Page 27: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

4. የምርጥ ምድጃ አገጣጠምና አጠቃቀም

ምድጃውን ከፍ ያለ ቦታ ላይ መትከል ያስፈልጋል ይህም ፤

* በጋገራ ግዜ ቁጭ ብድግ ከማለትና አጎንብሶ ከመስራት ጋር

የተያያዘው ድካም በእጅጉ ይቀንሳል ፣

* በቀላሉ እሳቱን መቆጣጠር ያስችላል ፣

* ሌሎች ለሥራ የሚያስፈልጉ እቃዎችን በቅርብና በንፅህና

ማስቀመጥና መጠቀም ያስችላል ፣

* ህፃናትና እንሰሳት ለእሳት አደጋ እንዳይጋለጡ ያደርጋል ፣

* የተለያዩ ፍሳሾች ወደ ምድጃ ውስጥ ገብተው የእሳት መቀ

ጣጠያ ቦታውን እንዳያረጥቡትና እሳት ለማቀጣጠል አስቸ

ጋሪ እንዳያደርጉት ያግዛል፡፡

Page 28: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ሀ. ወጥመደብ

የአፈርና የድንጋይመደብ

1. ተለቅ ተለቅ ያሉ ድንጋዮችን በመደቡ ስፋት ዳር ዳሩን

ይትከሉ ፣ 2. ዙርያውን በድንጋዮቹ የታጠረው ስፋት በድንጋይ

በኮረትና

በአፈር ይሞላል፡፡በዚህ ሁኔታ እሚፈለገው ከፍታ ድረስ

ይደርሳል ፣

3. የመደቡ ወለል አፈሩን ረጠብ በማድረግ በደንብይደመደ

ማል፡፡ለእይታ እንዲያምርም የመደቡ ግንብ ዙርያ በጭቃ

ሊመረግ ይችላል ፣

Page 29: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

4. ወለሉ የውሃ ልኩን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡

ለ. ሰቀላመደብ

የአፈርና የድንጋይመደብ

1. እንደመደቡ ስፋት ከግማሽ ሜትር እስከ 80 ሴ. ሜ በሚደር

ስ ርቀትና በመጨረሻ ከላይ በአፈርና በድንጋይ የሚጨመረ

ውን ከፍታ መጠን ባገናዘበ መልኩጠንካራና ቀጥ ያሉ የተ

ፈትሮ ባላ እንጨቶች ይተከላሉ ፣ 2. ባላዎቹ ላይ ጠቅጣቃ የእንጨት እርብራብ ጠንከር ካሉ

እንጨቶች ጠበቅ ተደርጎ ይሰራል ፣

3. በእንጨት ርብራቡ ላይ ትናንሽ ድንጋዮችና ኮረት ተረብር

ቦ አፈሩ በላይ ላይ ይሞላል፡፡

Page 30: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

• ምርጥ ምድጃ በማንኛውምመደብ ላይ በምትተከልበት ጊዜ ከምድጃዋ ስር ምጣድ ወይም የምጣድ ገል

በሚገባ አጠጋግቶ መቅበር መደቡ በእሳት እንዳይበላና አመድ በሚጫርበት ጊዜም እንዳይቦረቦር ከመርዳቱም

በተጨማሪ የሙቀት ብክነትን ስለሚቀንስ በአፅንኦት የሚመከር ጉዳይ ነው፡፡

የምርጥምድጃ አገጣጠም ሂደት

1. ለመደብ መስርያና ለምድጃውመገጣጠምያ ክፍሎች

የሚሆንጭቃ ከጭድ ጋር ደባልቆ ማቡካት፣

2. ከዚያም ታችኛውን ከፈፍ ዙርያ ጭቃ ከቀባን በኋላ ውኃ

ልኩን ጠብቆ ምድጃውን ማስቀመጥ ፣

Page 31: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

3. ከዛም ላይኛውን የምድጃ ከፈፍጭቃ መቀባት ፣ 4. በምድጃው ከፈፍ ላይ ምጣዱን ማስቀመጥ እና ውሃ ልኩ

እንዲጠበቅ ማድረግ፡፡

የምርጥምድጃ አጠቃቀም• ምድጃው ሲለኮስ ከዳር ትንሽ ማገዶ በማቀጣጠል መጀመር ፣

ይህም ከምድጃው አቅም በላይ ሆኖ ለማቀጣጠል/ለማያያዝ/ እንዳያስቸግር ነው፤• እንጀራ በሚጋገርበት ጊዜ መጠኑ እየታየ ትንሽ ትንሽ ማገዶ

በመጨመር መጠቀም ይህም ማገዶ ለመቆጠብ ያስችላል፤

Page 32: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

• እንጀራ በሚጋገርበት ጊዜጭስ ማውጫው ላይ በሚገኘው ጉልቻ ላይ በድስት ውኃ መጣድ፡፡ይህም

ሙቀቱ በምጣዱ ላይ እኩል እንዲሰራጭ ከማድረጉም በላይ በጭስ ማውጫው በኩል አላግባብ የሚባክነውን ሙቀትጥቅም ላይ እንዲውል ይረዳል፡፡

• ምድጃውሥራ ላይ ከዋለ በ ኋላ ጉዳት እንዳይደርስበት በተለይ ትኩስ እያለ ውሃ ወይንም ማናቸውንም ዓይነት

ፈሳሽ ነገር ላለማስነካት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡• ከጋገራ በኋላ ምድጃው ሲበርድ አመዱን አውጥቶ

ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡

Page 33: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

• የተገጣጠመበትጭቃ በእሳት ተበልቶ ካለቀ መልሶ በጭቃ ማያያዝ/ መድፈን ያስፈልጋል፡፡

• በአጋጣሚ በሥራ ላይ እያለ የተሰበረ አካል ቢኖር ሁሉንም ከጥቅም ውጪ ከማድረግ የተሰበረውን ብቻ

ገዝቶ መተካት ይቻላል፡፡• የማገዶና አየር ማስገቢያው የምድጃ ክፍል በማግዶ

መጠቅጠቅ የለበትም፡፡• በተቻለ መጠን ደረቅ እንጨት መጠቀም ፣• በሚጋግሩበት ወቅት እሳቱ ቢጠፋ ማራገብ እንጂ

በትንፋሽ ለማቀጣጠልመሞከር አደጋ ሊያስከትልይችላል፡፡

Page 34: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ምርጥን በመጠቀም ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች

• እሳቱ አልቀጣጠል ይላል ወይምጭስ ይበዛል፣

መፍትሄ - አመድ አለመከማቸቱን ያረጋግጡ

- ምድጃው ለሀይለኛ ንፋስ አለመጋለጡንያረጋግጡ

- ማገዶው እርጥብ አለመሆኑን ያረጋግጡ• ምጣዱ ከምድጃው ስፋት ይበልጥ ይሰፋል

- ምጣድ ይቀይሩ

Page 35: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

ማገዶን የሚቆጥቡ የማብሰል ዘዴዎችንመጠቀም• ጥሩ የማገዶ እንጨት ማዘጋጀት

- ደረቅ የሆነ ፣ በቀጫጭኑ የተፈለጠ፣ በምድጃው ልክ

የተቆራረጠ ሲሆን በደንብ ከመንደዱም በላይ ከፍተኛ

ሙቀት ይሰጣል፡፡• ክዳንን በመጠቀም ማብስል

- ክዳንን በመጠቀም ማብሰልሙቀት ከድስቱ አፍ

እንዳይባክን ይረዳል የማብሰያ ውሃ መጠንንም ይቀንሳል፡፡• በማንተክተክ ማብሰል

- ማንተክተክ ማለት የሚበስለው ነገር መፍለቅለቅ ከጀመረ

በኋላ የእሳቱን መጠን በመቀነስ በጣም በትንሹ የመፍለቅለ

Page 36: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

- ቅ ጠባይ እያሳየ እስከሚበስል መቆየት ነው፡፡

- ምግብ እየተንተከተከ ሲቆይ በዚያው ፍጥነት እየበሰለ ነው

ማለት ነው፡፡• እሳቱን በምንጠቀምበት ሰዓት ብቻ ማንደድ

- እሳቱን ከማቀጣጠል በፊት የሚያስፈልጉትን ቁሳቁስ

ማዘጋጀት፡፡ - በምድጃው ውስጥ የሚገኘውን ከሰል በአመድማዳፈን፡፡

- ምድጃውና እንጨቱ እንዳይረጥቡ እሳትን በውሃ

አለማጥፋት፡፡

Page 37: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

• ጥራጥሬን መዘፍዘፍ

- በቆሎን ባቄላንና ሌሎችን የሚቀቀሉ ደረቅ ምግቦችን

መዘፍዘፍ በቶሎ እንዲበስሉ ያደርጋል፡፡• ምግቡን ቆራርጦ ማብሰል

- ምግቡን በትናንሹ መቆራረጥ በቶሎሙቀት ከውጪ ወደ

ውስጥ እንዲደርስ ያደርጋል ስለዚህ በቶሎ ይበስላልማለት

ነው፡፡

Page 38: ማገዶ ቁጠባና የምርጥ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አመራረትና አጠቃቀም

እናመሰግናለን